የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የአምልኮ መርሖዎች (ማቴ. 6፡1-18)

ዮሐንስ የአንዲት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መጋቢ ነበር። እርሱም በጸሎቱ የታወቀ አገልጋይ ነበር። በየእሑዱ «ሃሌሉያ» እያለ ረዥም ጸሎት ያቀርባል። ዮሐንስ በረዥም ጸሎቱ መንፈሳዊነቱን ለሰዎች እንደሚያሳይ ያስብ ነበር። ብዙነሽ ክርስቲያን ነጋዴ ነበረች። አንድ ቀን ቤተ ክርስቲያኗ ለአዲስ የሕንጻ ግንባታ ገንዘብ ታሰባስብ ነበር። ብዙነሽ መሪው በምእመናኑ ፊት እያንዳንዱ ሰው የሰጠውን የገንዘብ ልክ እንደሚናገር ታውቅ ነበር። ስለሆነም ትክክለኛውን ጊዜ ጠብቃ ብዙ ስጦታ ይዛ ገባች። ለእግዚአብሔር ብዙ ገንዘብ ለመስጠት ሰዎችን ማስደነቅ መቻሏ ያስደስታታል። የውይይት ጥያቄ፡- ሀ) መንፈሳዊ ነገሮችን በራስ ወዳድነት አመለካከት ማድረግ የሚቀልለው እንዴት ነው? ለ) መንፈሳዊ የሚመስሉ ነገሮችን የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ ባለን ፍላጎት ልናደርግ የምንችልባቸውን መንገዶች ዘርዝር። ኤርምያስ በ17፡9 ላይ የሰው ልብ ክፉና ተንኮለኛ ማንም የማያውቀው እንደሆነ ይናገራል። በልባችን ራሳችንን ከምናታልልባቸው እጅግ አደገኛ መንገዶች አንዱ አምልኮ ነው። የሐሰት አምልኮ ሊመጣ የሚችለው የውሸት ጣዖት በማምለክ ወይም በኢየሱስ ክርስቶስ ባለማመን ብቻ አይደለም። ለእግዚአብሔር ሕዝብ፥ በምናከናውናቸው የአምልኮ ተግባራት ሁሉ የሐሰት አምልኮ መፈጸሙ ቀላል ነው። ስለሆነም ክርስቶስ የተሳሳተ አመለካከት በሚኖረን ጊዜ፥ ሊከሰቱ የሚችሉትን የተለመዱ የአምልኮ ተግባራት ገልጾታል። እነዚህ ምሳሌዎች ብቻ ናቸው። ለሌሎች መንፈሳዊ መስለን ለመታየት በምንፈልግበት ጊዜ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ማምለክ አቁመናል ማለት ነው። በኳየር (በሕብረ ዝማሬ) ውስጥ የምንዘምረው የኳየር ልብሳችንን ለማሳየት፥ ዓይኖቻችንን በመጨፈን ወደ ሰማይ በማየትና በመወዛወዝ መንፈሳዊነታችንን ለማሳወቅ፥ ወይም «ሃሌሉያ» እያልን በመጮኽ የሕዝቡን ስሜት ለማነሣሣት ከሆነ፥ እነዚህ ሁሉ ነገሮች የማይጠቅሙ ይሆናሉ። እውነተኛ አምልኮ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የልባችን መግለጫ ነው። ከዚህ ውጭ የምናደርገው ሁሉ የሐሰት አምልኮ ነው። በክርስቶስ ዘመን ሌሎችን ለማስገረም የሚካሄዱ የአምልኮ ተግባራት በፈሪሳውያን ሕይወት ውስጥ ይታዩ ነበር። አለባበሳቸው፥ በሕዝቡ ፊት የነበራቸው አክብሮትና ሰዎች ልብ ብለው እንዲያዩዋቸው መፈለጋቸው ሁሉ አምልኳቸው እንዲበላሽ አድርገዋል። ክርስቶስ እነዚህን አደጋዎች በመረዳት፥ ደቀ መዛሙርቱ አምልኳቸው ተቀባይነትን እንዲያገኝና ትክክለኛ አመለካከት እንዲኖራቸው «ምጽዋታችሁን በሰው ፊት እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ፊት ዋጋ የላችሁም» ሲል አስጠነቀቃቸው። ክርስቶስ «ምጽዋታችሁን» ሲል በእግዚአብሔር ፊት «ትክክለኛ ነገሮችን» እንድንሠራ ማሳሰቡ ነው። ለድሆች በመመጽወት ማምለክ (ማቴ. 6፡1-4)። ለድሆች መስጠት እግዚአብሔር ከልጆቹ ሁሉ የሚጠብቀው ተግባር ነው። የወንጌል አማኝ ክርስቲያኖች፥ ሌሎች ወገኖች የሚሰጡበትን ምክንያት በመንቀፍ የሕይወት ማዕበል ለሚያንገላታቸው ወገኖች ርኅራኄን ማሳየት አቁመዋል። ነገር ግን ከመስጠት የሚበልጠው በምንሰጥበት ጊዜ በልባችን ውስጥ ያለው አመለካከት ነው። በመስጠት ዙሪያ አራት አመለካከቶች ይንጸባረቃሉ። በመጀመሪያ፥ «ለድሃ ብሰጥ እግዚአብሔር እኔን ወደ መንግሥተ ሰማይ ያስገባኛል፤ ኃጢአቴንም ይሰርዝልኛል» የሚል አመለካከት አለ። አንድ መልካም ነገር በማድረግ ኃጢአታችንን ልናስወግድ ወይም ወደ መንግሥተ ሰማይ ልንገባ አንችልም። አንድ ሰው የኃጢአትን ይቅርታ አግኝቶ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነትን ሊያገኝ የሚችለው፥ የእግዚአብሔርን ይቅርታ በመጠየቅና በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ ነው። ሁለተኛው፥ በመስጠት እግዚአብሔር ሀብታም እንዲያደርገን ለማስገደድ እንችላለን ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ። «ለእግዚአብሔር ብዙ ገንዘብ ስጠው፤ ይህም እግዚአብሔር ከሰጠኸው የበለጠ እንዲመልስልህ ያደርገዋል። ለእግዚአብሔር 100 ብር ብትሰጠው፥ እርሱ 1000 ብር ይሰጥሃል። ብዙ ከሰጠኸው ሀብታም ትሆናለህ።» እግዚአብሔር በትክክለኛ አመለካከት ከሰጠነው ይባርከናል። ነገር ግን ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔር የሚሰጠን የበረከት ተስፋ የግድ በምድር ላይ ብዙ ገንዘብ የምናገኝበት ሳይሆን፥ በመንግሥተ ሰማይ የምንቀበለው ነው። ከእግዚአብሔር ዘንድ አንድ ነገር ለማግኘት ተብሎ የሚደረግ ስጦታ የራስ ወዳድነት ተግባር ነው። ይህ በርኅራኄ ሳይሆን አንድን ነገር በአጸፋው ለማግኘት የሚደረግ ጥረት በመሆኑ፥ እግዚአብሔር የሚያከብረው ዓይነት ስጦታ አይደለም። ሦስተኛው፥ «ሌሎች አይተው በችሮታዬ ሊያመሰግኑኝ በሚችሉበት መንገድ ለድሃ መስጠት አለብኝ» የሚሉ ሰዎች አሉ። ይህ የርኅራኄ መግለጫ ሳይሆን፥ በሌሎች ፊት ታዋቂ ለመሆን የሚደረግ ስጦታ ነው። ክርስቶስ የዚህ ዓይነቱ መስጠት የሰዎችን ምስጋና ከማስከተል ያለፈ፥ ሌላ ማዕረግ እንደማያስገኝ ተናግሯል። ይህ እግዚአብሔርን የማያስደስት በመሆኑ፥ ከእርሱ ዘንድ ምንም ምስጋና አያስገኝም። ፈሪሳውያን የሚያደርጉት ይህንኑ ነበር። በቤተ መቅደስ ገንዘብ በሚሰጡበት ጊዜ ሕዝቡ ምን ያህል እንደሰጡ እንዲያውቁላቸው ይፈልጉ ነበር። እንዲያውም አንዳንዶች ሰዎች እንዲያዩላቸው መለከት እየነፉ ይሰበስቧቸው ነበር። አራተኛው፥ ከርኅራኄና እግዚአብሔርን ከመታዘዝ የተነሣ ለተጎዱ ሰዎች የሚበረከት ስጦታም አለ። ይህ ስጦታ በሚለገስበት ጊዜ ተመልካች ስለመኖር አለመኖሩ ሳንጨነቅ የምናደርገው ነው። መንፈሳዊ ልብ ለእውቅና አይጣደፍም። ስሙ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለ መጠራት አለመጠራቱም አይጨነቅም። ክርስቶስ በመስጠት ጊዜ የሚከሰተውን አደጋ በማጤኑ፥ ቀኝ እጃችን የሚሰጠውን ግራው እንደማያውቅ ያህል በምሥጢር እንድናደርገው አዟል። እግዚአብሔርን የሚያስደስተው የዚህ ዓይነቱ ልግስና ብቻ ነው። እግዚአብሔር ትልቅ ግምት የሚሰጠው የዚህ ዓይነቱን ልግስና ብቻ ነው። አንዳንድ ጊዜ እርሱን እንድናገለግለው በምድር ብዙ ሀብት በመስጠት ቢባርከንም፥ ከሁሉም የሚበልጠው በሰማይ የሚገኘው በረከት ነው። (አሁንም ቢሆን በሰማይ ትልቅ ስጦታ ለማግኘት ስንል፥ በራስ ወዳድነት ዓላማ አለመስጠታችንን ማረጋገጥ አለብን። እግዚአብሔር ከሰው ምንም ነገር ለማግኘት ሳይሆን፥ ከፍቅሩና ከርኅራኄው የተነሣ እንደሚሰጥ፥ የእኛም ስጦታ ከርኅራኄ ልብ ሊመነጭ ይገባል።) የውይይት ጥያቄ፡- ሀ) ክርስቲያኖች በእነዚህ አራት መንገዶች ሊሰጡ ስለሚችሉባቸው መንገዶች ግለጽ። ለ) በቤተ ክርስቲያንህ ሰዎችን ወደ ተሳሳቱ አቅጣጫዎች ሊመሩ የሚችሉ አንዳንድ ልምምዶች ምንድን ናቸው? ሐ) ምእመናን እግዚአብሔርንና ሰዎችን በመውደዳቸው ምክንያት፥ ከራስ ወዳድነት በጠራ መንፈስ በልግስና እንዲሰጡ ለማገዝ፥ ሊለወጥ የሚገባው ነገር ምንድን ነው? አምልኮ በጸሎት (ማቴ. 6:5-15)። ጸሎት ከተሳሳቱ አነሣሽ ምክንያቶች ሊመነጭ ይችላል? ክርስቶስ፥ «አዎን» ብሏል። ክርስቲያኖች የአምልኮ ግብዝነታቸውን ከሚያሳዩባቸው ዐበይት መንገዶች አንዱ ጸሎት ነው። ክርስቶስ ካስተማራቸው ዐበይት የአምልኮ ተግባራት አንዱ ጸሎት ነው። ብዙ ሰባኪዎች ሰዎችን ለማስደሰት ሲሉ ረዥም በሆኑ ወይም በስሜት ጸሎቶች ይጠቀማሉ። እንዲሁም ለስብከት የጸሎት ጊዜን ይጠቀማሉ። ጸሎት ከሰዎች ጋር ሳይሆን፥ ከእግዚአብሔር ጋር የምንነጋገርበት መሣሪያ ነው። ሌሎች መሪዎች የተወሰኑ ቃላትን በመደጋገም መንፈሳዊነታቸውን ለማሳየት ይፈልጋሉ። አንዳንዶች የእግዚአብሔርን ወይም የክርስቶስን ስሞች ይደጋግማሉ። ሌሎች ደግሞ «ሃሌሉያ» የሚለውን ቃል ይደጋግማሉ። በኢየሱስ ዘመን ፈሪሳውያን መንፈሳዊነታቸውን በጸሎት ለማሳየት ይፈልጉ ነበር። ስለሆነም በአምልኮ ዕለት ወደ ምኩራብ ገብተው ከፊት በመቀመጥ ረዥም ጸሎቶችን ያቀርባሉ። ያም ባይሆን ሕዝብ ወደሚሰበሰብባቸው አካባቢዎች ሄደው ሁሉም ሰው እስኪሰማቸው ድረስ፥ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ይጸልያሉ። ክርስቶስ፥ «ይኼ ምን እርባና አለው?» ሲል ነቅፏቸዋል። ብድራታቸው የእግዚአብሔር ሳይሆን፥ የሰዎች አድናቆት ነበር። የኢየሱስ ተከታዮች የጸሎት አመለካከት ፍጹም የተለየ ሊሆን ይገባል። ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር የምናደርገው ንግግር ስለሆነ፥ የሰዎች መኖር አለመኖር ሊያሳስበን አይገባም። ክርስቶስ በሕብረት መጸለይ የለብንም አላለም። ክርስቶስም ሆነ ሐዋርያት ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበባቸው ስፍራዎች ጸልየዋል። ነገር ግን ክርስቶስ በሕዝብ ፊት በምንጸልይበት ጊዜ አመለካከታችን ትክክለኛ መሆን እንዳለበት አስገንዝቧል። ኢየሱስ ተከታዮቹ በትክክለኛ መንገድ እንዲጸልዩ የተወሰኑ መመሪያዎችን ሰጥቷቸዋል። ሀ. ክርስቶስ ጸሎትን ከተሳሳቱ አነሣሽ ምክንያቶች ለመጠበቅ፥ አብዛኛውን ጸሎታችንን እግዚአብሔር ብቻ በሚሰማባቸው ስውር ስፍራዎች እንድናደርግ አስተምሮናል። እግዚአብሔር ከመናገራችን በፊት ጸሎታችንን ስለሚያውቅ፥ ስለ ጸሎታችን መጮኹ የግድ አስፈላጊ አይደለም። ጮክ ብሎ መጸለዩ ተጨማሪ በረከት አያስገኝም። ጮክ ብለን መጸለያችን እግዚአብሔር በተሻለ ሁኔታ እንዲያደምጠን አያደርገውም። እግዚአብሔር ደንቆሮ ስላልሆነ መጮኽ አያስፈልገንም። ጮክ ብለን የምንጸልይ ከሆነ፥ አነሣሽ ምክንያታችንን መመርመር ይኖርብናል። ክርስቶስ ከእርሱ ጋር ከተነጋገርን፥ ለጸሎታችን መልስ እንደሚሰጠን ተናግሯል። ለ. ጸሎት በቃላት አማካኝነት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነው። ስለሆነም ቀጥተኛ የሆነ አነጋገር ለጸሎት ተስማሚ ነው። ክርስቶስ ቀጥተኛ ከሆነ የጸሎት ቃላት ውጪ ሳይታሰቡ የሚወረወሩ ቃላት ለጸሎት ሊያገለግሉ እንደማይገባ አስጠንቅቋል። ስሙን በመደጋገማችን ወይም «ሃሌሉያ» እያልን በመጮኻችን ብቻ እግዚአብሔር ጸሎታችንን በተሻለ ሁኔታ አያደምጥም። ይህንን የምናደርግ ከሆነ፥ «ለምንድን ነው የማደርገው?» ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን። ያለልማድ የምንጠቀምባቸው ቃላት ብዙውን ጊዜ ለሌሎች እንደምንጸልይ ወይም ሳናስብ በልማድ እንደምንጸልይ ያሳያሉ። ሐ. ረዥም ጸሎት የግድ አስፈላጊ አይደለም። ክርስቶስ ብዙ ቃላት መደጋገም እንደማያስፈልግ ገልጾታል። ብዙ በጸለይን ቁጥር ትክክለኛ ጸሎት እናደርጋለንን? አናደርግም። ጥርት ባለ ሁኔታ እግዚአብሔርን የሚያመሰግንና ለእግዚአብሔር ለመናገር የምንፈልጋቸውን ነገሮች የሚገልጽልን የሁለት ደቂቃ ጸሎት በቂ ነው። በተለይ በሌሎች ሰዎች ፊት ረጅም ጸሎት የምንጸልይ ከሆነ፥

የአምልኮ መርሖዎች (ማቴ. 6፡1-18) Read More »

ክርስቶስ የመጣው የብሉይ ኪዳንን ሕግ ለመሻር ሳይሆን ለመፈጻም ነው (ማቴ. 5፡16-48)

የውይይት ጥያቄ፡- ማቴ. 5፡16-48ን አንብብና ክርስቶስ ከብሉይ ኪዳን ሕግ ጋር ምን ዓይነት ግንኙነት እንደ ነበረው ግለጽ። የክርስቶስ ቀንደኛ ጠላቶች ፈሪሳውያን ነበሩ flip። እነዚህ ሰዎች ከክርስቶስ ጋር የሚጋጩት እርሱ የብሉይ ኪዳን ሕግን ባለመፈጸሙ ምክንያት ሳይሆን፥ እነርሱ የጨመሯቸውንና ከብሉይ ኪዳን ሕግ እኩል እንደሆኑ የሚያስተምሯቸውን ሕግጋት ለመፈጸም ባለመፈለጉ ነበር። ይህም ክርስቶስ ሕግን አያከብርም የሚል ወሬ እንዲዛመት አደረገ። ማቴዎስ ግን ክርስቶስ የብሉይ ኪዳንን ሕግ እንደማይቃወም አመልክቷል። ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ሕግ አንዲት ነቁጥ እንኳ እንደማትወድቅ አስተምሯል። ሰዎች የእርሱ ተከታዮችና የመንግሥቱ አካል ለመሆን ከፈለጉ፥ የእግዚአብሔርን ሕግ በሙሉ መጠበቅ እንዳለባቸውም አስተምሯል። ምሑራን ክርስቶስ «ልፈጽም» ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ ይከራከራሉ። ክርስቶስ የብሉይ ኪዳን የሕግ ዓይነቶች በሙሉ በሁሉም ዘመን ለሚኖሩ ክርስቲያኖች አሁንም ይሠራሉ ማለቱ ይሆን? ቤተ ክርስቲያን ዛሬ የሥነ ምግባር ሕግን (ለምሳሌ፥ «አታመንዝር»)፣ ሥርዓታዊ ሕግን (ለምሳሌ፥ ለእግዚአብሔር በመሠዊያ ላይ መሥዋዕቶችን ማቅረብ)፥ እና ማኅበራዊ ሕግን (ለምሳሌ፥ የአንድ ሰው በሬ ወደ ሌላው ግለሰብ እርሻ ዛሬ በሚገባበት ጊዜ ምን እንደሚደረግ) መጠበቅ አለበት? ይህ የዕብራውያን መጽሐፍ ከክርስቶስ መሥዋዕት የተነሣ የብሉይ ኪዳን መሥዋዕቶች እንደተሻሩ ከሚናገረው ወይም የምግብ ሥርዓቶች ከእንግዲህ እንደማይጠቅሙ ከሚያስረዳው ከሐዋርያት ሥራ 10 ጋር እንዴት ይዛመዳል? ስለሆነም ኢየሱስ ሕግን ስለመፈጸሙ ሲናገር ምን ማለቱ እንደሆነ የሚያስረዱ የተለያዩ አሳቦች አሉ። ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን ሕግን ሙሉ በሙሉ ፈጽሟል፤ ለሕጉ ታዟል። ብሉይ ኪዳን በሙሉ ወደ ክርስቶስ ያመለክታል። ዘጸአት ክርስቶስ ከባርነት እንደሚያወጣን ያሳያል። መሥዋዕቶችና ሃይማኖታዊ በዓላት ሁሉ ወደ ክርስቶስና አገልግሎቶቹ ያመለክታሉ። ነቢያት ሁሉ በክርስቶስና በተግባሩ ላይ ያተኩራሉ። ስለሆነም የብሉይ ኪዳን የተስፋ ቃሎች በሙሉ በኢየሱስ ተፈጻሚነትን አግኝተዋል። እርሱ እውነተኛ የአምልኮ መንገድ ነው። እርሱ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋርና እርስ በርሳቸው የሚዛመዱበትን መንገድ ያስተምራል። ሰዎች እንዴት በፍቅር አብረው እንደሚኖሩ ያሳያል። ክርስቶስ የኢሳይያስን ትንቢቶች እንደፈጸመ ሁሉ፥ በብሉይ ኪዳንም የእግዚአብሔርን ተምሳሌቶች ሁሉ ፈጽሟል። የብሉይ ኪዳን ሥርዓታዊ ሕግና ማኅበራዊ ሕግ መሢሑ ከመጣ በኋላ አስፈላጊዎች አልነበሩም። በኢየሱስ መምጣት፥ የብሉይ ኪዳን ሕግና የተስፋ ቃሎች፥ እግዚአብሔር ለእነርሱ የነበረው ዓላማ ከፍጻሜ ደረሰ። ኢየሱስ ብሉይ ኪዳን ከእንግዲህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንዳልሆነ አልተናገረም። ይህ ከእግዚአብሔር የመነጭ በመሆኑ፥ ሁልጊዜም የመጽሐፍ ቅዱስ አካል ነው። ነገር ግን በክርስቶስ መምጣት ብሉይ ኪዳንን የምንረዳበት መንገድ የተለወጠበት ሁኔታ አለ። አሁን እግዚአብሔር ብሉይ ኪዳንን የሰጠባቸውን ዓላማዎች ከአዲስ ኪዳንና ከክርስቶስ ትምህርቶች እንረዳለን። ከዚያ በኋላ ግን ክርስቶስ የዘላለምን ሕይወት የሚቀበሉት፥ ከፈሪሳውያንና ከሕግ መምህራን የበለጠ ጽድቅ ያላቸው ብቻ እንደሚሆኑ ገልጾታል። ይህ አባባሉ አይሁዶችን አስደነገጠ። የፈሪሳውያንን ያህል መንፈሳዊ የሚመስል ሰው አልነበረም። የሕይወታቸውን ክፍሎች የሚገዙ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕግጋትን ይከተሉ ነበር። አይሁዶች «እንዴት ከፈሪሳውያን በላይ መንፈሳዊ መሆን ይቻላል?» ብለው ማሰባቸው አልቀረም። ክርስቶስ ምክንያቱ የፈሪሳውያን በውጫዊ ነገሮች ላይ ማተኮር እንደሆነ ገለጸ። የእግዚአብሔርን ሕግጋት ከመጠበቅ ጀርባ ስለነበሩት መርሖዎች አይጨነቁም ነበር። እግዚአብሔርን የሚያሳስበው ከውጫዊ ሥርዓት ይልቅ የልባችን ነገር ነው። እግዚአብሔር ልባችን ትክክል ከሆነ ትክክለኛ ተግባር እንደምናከናውን ያውቃል። ፈሪሳውያን የተለወጠ ልብና ትክክለኛ ምኞት ስላልነበራቸው በእግዚአብሔር ፊት ከንቱዎች ነበሩ። የውይይት ጥያቄ፡- ብዙውን ጊዜ ክርስቲያኖች ከተግባሩ ባሻገር ያሉትን አነሣሽ ምክንያቶችና አመለካከቶች ሲያጤኑ በውጫዊ ተግባራት ላይ እንዴት እንደሚያተኩሩ አብራራ። ኢየሱስ ሕግን እግዚአብሔር በሚፈልገው መንገድ ከልብ መታዘዝ ከውጫዊ ተግባራት እንዴት እንደሚለይ ለማሳየት ስድስት ምሳሌዎችን ሰጥቷል። እነዚህም እግዚአብሔር ሕግን ስለመጠበቅ ያለው አመለካከት ከፈሪሳውያን የላቀ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው። (ማቴዎስ በዚህ ክፍል ውስጥ ከሚያሳያቸው ነገሮች መካከል አንዱ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ልብ ለመተርጎም እንደሚችል ነው። የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆኑ መጠን፥ ክርስቶስ የተጻፉትን የብሉይ ኪዳን ሕግጋት ብቻ ሳይሆን ከ1400 ዓመታት በፊት የሙሴን ሕግ ሲሰጥ ከሕዝቡ ምን እንደፈለገም ያውቅ ነበር። ክርስቶስ «ሙሴ ተብሏል እኔ ግን እላለሁ» ሲል ሕግን ከሰጠው እግዚአብሔር ጋር ራሱን እኩል እያደረገ ነበር።) ሀ. ስለ መግደል የተነገረ ምሳሌ (ማቴ. 5፡21-26)። ብሉይ ኪዳን ሰው መግደል የተከለከለ መሆኑን በግልጽ አስተምሯል። ፈሪሳዊ ሰው ገድሎ ስለማያውቅ፥ ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ ግንኙነት እንዳለው ያስብ ነበር። ይህ ሕግ ትዕቢቱንና ቁጣውን እንዲያስወግድ፣ ወይም የተበላሸውን ግንኙነት እንዲያስተካክል አላስገደደውም ነበር። ክርስቶስ ግን የግድያ ሁሉ ሥር በሆነው ጥላቻ ላይ አተኮረ። በእግዚአብሔር ዐይን፥ አንድን ሰው መጥላት ኃጢአት ነው። የቁጣ ውጤት በመጀመሪያ ደረጃ የግድያን ያህል አስከፊ ላይሆን ቢችልም፥ የግድያ ሁሉ ሥር ቁጣ ነው። ስለሆነም ከሕይወታችን ውስጥ ቁጣን እስካላስወገድን ድረስ እግዚአብሔር የሚፈልገውን የፍቅር ግንኙነት፥ ከሌሎች ጋር የማድረግ ሕይወት ልንመራ አንችልም። («ደንቆሮ» የሚለው አንድ ሰው በሌላው ላይ የሚሰነዝረው የንቀት ስድብ ነው። የአይሁድ ሸንጎ የግድያ ጉዳዮችን የሚመረምር የአይሁዶች የሕግ ምክር ቤት ነበራቸው።) ትዕቢተኛ፥ ሌሎችን የሚንቅ፥ በጥላቻና በክፋት የተሞላ ልብ ለእግዚአብሔር የነፍሰ ገዳይን ያህል የከፋ ነው። ሁለቱም ግለሰቡ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት እንደማያደርግና የተለወጠ ሕይወት እንደሌለው ያሳያሉ። ክርስቶስ የሕግ ዋንኛ መልእክት ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት ማድረግ መሆኑን ለማሳየት ሁለት ምሳሌዎችን ተጠቅሟል። የመጀመሪያው ምሳሌ በመሠዊያው ላይ እንስሳትን በመሠዋት እግዚአብሔርን የሚያመልከውን ሰው ይመለከታል። እየሰገደ ሳለ አንድ የተጣላው ሰው እንዳለ ትዝ አለው። ምንም እንኳ ሰጋጁ ከራሱ ልብ ጉዳዩን ያወጣው ቢሆንም፥ ግለሰቡ ግን አሁንም እንደተናደደ ያውቅ ነበር። በሰዎች መካከል ጥል እያለ እግዚአብሔርን ማምለክ አይቻልም። ስለሆነም ኢየሱስ፥ መሥዋዕትን የሚሠዋው አማኝ፥ አስቀድሞ የተቀየመውን ግለሰብ መታረቅ እንዳለበት ገልጾታል። ከዚያ በኋላ ተመልሶ መሥዋዕት በማቅረብ እግዚአብሔርን ሊያመልክ እንደሚቻል አስረድቷል። ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ መከፋፈል ይታያል። ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር እንደሚደሰትብን እያሰብን በመዘመር፥ ስብከቶችን በመስማት፥ በመጸለይና በመጾም እናመልከዋለን። ክርስቶስ ግን ግንኙነቶች ከተበላሹ ማንም ይበድል ማን ሁለቱም ወገኖች ግንኙነቱን ለማስተካከል መጣር እንዳለባቸው ገልጾታል። እግዚአብሔር በአምልኳችን ደስ የሚሰኘው በዚህ ጊዜ ብቻ ነው። የውይይት ጥያቄ፡- ሀ) በብዙ የተበላሹ ግንኙነቶች ውስጥ እግዚአብሔርን ለማምለክ ብንሞክር፥ ዛሬ ለእኛ የሚሰጠው ማስጠንቀቂያ ምንድን ነው? ለ) የተቀያየምኸው ሰው አለ? እግዚአብሔር ብርታትና ምሪት እንዲሰጥህ ጠይቅና ግንኙነቱን ለማስተካከል ትችል ዘንድ ወደ ግለሰቡ ሄደህ ተነጋገር። በክርስቶስ ዘመን ሰዎች ገንዘብ የመበደር ልማድ ነበራቸው። የተበደሩትን ገንዘብ ለመክፈል ካልቻሉ፥ እነርሱ ወይም ቤተሰቦቻቸው ለባርነት ይሸጡ ነበር። ወይም ደግሞ ገንዘቡን እስኪከፍሉ ድረስ ወኅኒ ቤት ይወርዳሉ። ክርስቶስ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ችሎት ከመድረሱ በፊት ተበዳሪው ከአበዳሪው ጋር ሆኖ መፍትሔ መፈለግ እንዳለበት ተናግሯል። ክርስቶስ ይህንን በመጠቀም አለመስማማትና ክርክሮችን እንዴት ማስተናገድ እንደሚገባ አስተምሯል። በክርክር ውስጥ አቋምህን በልበ ደንዳናነት ይዘህ በቀጠልህ ቁጥር፥ ክርክሩ እየከፋ ሄዶ በአንተና በተሟጋችህ ላይ ጉዳት ማድረሱ የማይቀር ነው። ስለሆነም ቁጣና ትዕቢት የፍትሕን በር ከመዝጋታቸው በፊት፥ ችግሩን ለመፍታት መሞከሩ መልካም ነው (ምሳሌ 25፡8-10ን አንብብ።) አለመስማማትን በጊዜ ውስጥ ለመፍታት መሞከራችን ክብደቱን ከማቃለሉም በላይ በእኛና በቤተሰባችን፥ በቤተ ክርስቲያናችንና ከሁሉም በላይ በጌታ ስም ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት በእጅጉ ይቀንሳል። ለ. ስለ ዝሙት የተነገረ ምሳሌ (ማቴ. 5፡27-30)። የሙሴ ሕግ ሰዎች ዝሙትን መፈጸም እንደሌለባቸው በግልጽ አመልክቷል። ያገባ ሰው ከሚስቱ ውጭ ወሲባዊ ግንኙነት እንዳያደርግ ተከልክሏል። ያላገባ ሰው ደግሞ ከማግባቱ በፊት ምንም ዓይነት ወሲባዊ ግንኙነት ማድረግ አይችልም ነበር። አሁንም ለክርስቲያኖች «ዝሙት አልፈጸምሁም» ብሎ መኩራራቱ ቀላል ነው። ነገር ግን ክርስቶስ ዋናው ጉዳይ ውጫዊው የወሲብ ተግባር እንዳልሆነ ገልጾታል። ዋናው ጉዳይ ከልብ ጋር ሲሆን፥ አንድ ሰው በተግባር ዝሙት ባይፈጽምም ይህንኑ ለማድረግ ሊመኝ ይችላል። የዝሙት ሥር ምኞት ስለሆነ፥ እግዚአብሔርንና ሌላውን ሰው የሚያስከብር ውስጣዊ ሕይወት ለመምራት ከምኞት መራቅ እንዳለበት ኢየሱስ አስተምሯል። ብዙ ጊዜ ኃጢአትን ቀላል አድርገን እንመለከታለን። ኃጢአት ከፈጸምን በኋላ ይቅርታ ለመጠየቅ እንደምንችል እናስባለን። «ሌላውን ሰው እስካልጎዳሁ ድረስ ምን ችግር አለው?» ብለን ራሳችንን እንጠይቃለን። ክርስቶስ የሰዎችን ትኩረት ለመሳብና እግዚአብሔር ኃጢአትን እንዴት አጥብቆ እንደሚጠላ ለማሳየት ፈለገ። ሰዎችን ለማስደንገጥ የሚያስችል የንግግር ዓይነት በመጠቀም፥ ክርስቶስ ወደ አንድ ኃጢአት የሚመራ ዝንባሌ ያለው

ክርስቶስ የመጣው የብሉይ ኪዳንን ሕግ ለመሻር ሳይሆን ለመፈጻም ነው (ማቴ. 5፡16-48) Read More »

የክርስቶስ ተከታዮች ለዓለም ብርሃንና ጨው መሆን አለባቸው (ማቴ. 5፡13-16)

ብዙ ክርስቲያኖች፥ «ዓለም ለእኛ በጣም መጥፎ ስለሆነች የመንግሥት ሥራ ትተን ወደ ክርስቲያናዊ ድርጅቶች ብንሄድ ይሻላል። ወይም ከማኅበረሰባችን ወጥተን ከሚመስሉን ሰዎች ጋር የምንሠራበትንና የምንኖርበትን ክርስቲያናዊ ማኅበረሰብ እንመሥርት» ይላሉ። ነገር ግን ይህ ክርስቶስ ያስተማረው የደቀ መዝሙርነት ዐይነት ነው ወይ? ከማኅበረሰቡ ወጥተው የራሳቸውን የቅዱሳን ማኅበረሰብ ከመሠረቱት ኢሴናውያን በተቃራኒ፥ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱ በዓለም ውስጥ እንደ ጨውና ብርሃን እንዲያገለግሉ የሚፈልግ መሆኑን ገልጾአል። ኢየሱስ በዓለም ውስጥ ደቀ መዛሙርቱ ያደረጉትን አስተዋጽኦ ከሦስት ነገሮች ጋር በማነጻጸር አብራርቷል። በመጀመሪያ፥ ከጨው ጋር አነጻጽሯቸዋል። በጥንት ዘመን ጨው በጣም ጠቃሚ ነገር ነበር። እንደ ጥንታዊት ኢትዮጵያ በመሳሰሉት አገሮች፥ የመገበያያ ገንዘብ ሆኖ አገልግሏል። ጨው ለሁለት ነገሮች ያገለግል ነበር። ሀ ለጣዕም፥ ወጥ እንዲጣፍጥ፥ በገጠር በቡና ጭምር ጨው እንደሚጨመር ሁሉ፥ በክርስቶስ ዘመን ጨው ለጣዕም መስጫ ያገለግል ነበር። 2) ለማቆያ። ሥጋ እንዳይበላሽ በጨው ቀምመው ቋንጣ ያደረጉት ነበር። በተመሳሳይ ሁኔታ በቁጥር ቢያንሱም እንኳ እግዚአብሔር በሚፈልገው መንገድ ቢኖሩ ክርስቲያኖች በማኅበረሰቡ ውስጥ እነዚህን ሁለት ተግባራት መፈጸም ይችላሉ። መንፈሳዊ ምሳሌነት ያለው ሕይወት በመምራት በክፋት ለተሞላው ማኅበረሰብ መልካም መዓዛ ይጨምራሉ። በተጨማሪም እግዚኣብሔር ክፋት እንዳይጨምርና ማኅበረሰቡ የበለጠ ክፉ እንዳይሆን ለመከላከል፥ በውስጡ ያሉትን ክርስቲያኖች ይጠቀማል። እስራኤላውያን ጨው የሚያገኙት ከኢየሩሳሌም በስተ ደቡብ ምሥራቅ ከሚገኘው ሙት ባሕር ነበር። ከመሬትም ቆፍረው ያወጡታል። ነገር ግን ይህ ንጹሕ ጨው ስላልሆነ፥ በፍጥነት ካልተጠቀሙበት ጨውነቱን እያጣ ይሄድ ነበር። ከዚያ በኋላ ሊያገለግል የሚችለው ወደ መሬት በመጣል፥ ወይም ጣሪያቸው እንዳያፈስ ከዚያው ላይ በማስቀመጥ ብቻ ይሆናል። ዛሬም እንኳ ብዙ የአይሁድ ቤቶች ውኃ የሚያስገቡ ጣሪያዎች አሏቸው። ዛሬም ድረስ ያረጀና የማይጠቅም ጨው በጣሪያቸው ላይ በማድረግ ዝናብ ይከላከላሉ።) በተመሳሳይ ሁኔታ የአንድ ክርስቲያን ባሕርይ የዓለምን ሲመስል፥ ለማኅበረሰቡ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ሊኖር አይችልም። ሁለተኛው ማብራሪያ ብርሃን ነበር። በጥንት ዘመን ኤሌክትሪክ ስላልነበረ፥ ሰዎች በወይራ ዘይት የተሞሉ ኩራዞችን ይጠቀሙ ነበር። ብርሃን አስደናቂ ነገር ነው። ትንሽ ብርሃን ብዙ ጨለማ ትገፋለች። የክርስቶስ ተከታዮች በቁጥር ቢያንሱም እንኳ፥ የክርስቶስን ባሕርያት በዓለም ውስጥ ማብራት አለባቸው። የሰዎችን ክፋት አብርተን በማሳየት፥ ሕይወታቸውንና ማኅበረሰባቸውን በሚለውጥ መንገድ እንዴት ሊኖሩ እንደሚችሉ እናሳያቸዋለን፡ ነገር ግን ሕይወታችን ዓለምን በመምሰል በኃጢአት ከጨለመ፥ ይህ በማሰሮ ውስጥ እንዳለ መብራት ይሆናል። ወይም ደግሞ ስደትን ፈርተን ብርሃናችንን ብንደብቅ፥ እግዚአብሔር ጽድቁን ለማብራት እኛን የተጠቀመበት ዓላማ ከግቡ ሳይደርስ ይቀራል፡፡ ሦስተኛው ምሳሌ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ናት። እንደተለኮሰ መብራት፥ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አትችልም። በተመሳሳይ ሁኔታ እነዚህን ክርስቶስ የጠቀሳቸውን ባሕርያት የያዙ ክርስቲያኖች ለሁሉም በግልጽ የሚለዩ ይሆናሉ። ምስክርነታችን የሚመጣው ከአፋችን ሳይሆን ከተግባራችን ነው። የውይይት ጥያቄ፡- ሀ) ለእግዚአብሔር የሚኖሩ ጥቂት ክርስቲያኖች እንደ ብርሃንና ጨው ኅብረተሰቡን ሲለውጡ ያየህበትን ሁኔታ ግለጽ። ለ) እንደ ዓለማውያን በመኖራቸው ምክንያት የብርሃንነትና የጨውነት አገልግሎታቸው የጠፋበትን ሁኔታ ግለጽ። ሐ) ሕይወትህ እንደ ብርሃንና ጨው የሆነው እንዴት ነው? ብርሃንህና ጨውህ የበለጠ እያደገ በማኅበረሰቡ ላይ የበለጠ ለውጥ ለማስከተል ትችል ዘንድ ምን ታደርጋለህ? (ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ ስለዚህ አስደናቂ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡)

የክርስቶስ ተከታዮች ለዓለም ብርሃንና ጨው መሆን አለባቸው (ማቴ. 5፡13-16) Read More »

የተራራው ስብከት [እግዚአብሔር የባረከው ሰው ባሕርይ] (ማቴ. 5፡1-12)

የውይይት ጥያቄ፡- አራት ዓምዶች ያሉት ሠንጠረዥ በወረቀት ላይ ሣል። የመጀመሪያውን ዓምድ «ባሕርይ»፥ ሁለተኛውን «ያ ባሕርይ ምን ማለት እንደሆነ»፤ ሦስተኛውን ዓምድ «ክርስቶስ ተስፋ የሰጠው በረከት»፥ እንዲሁም አራተኛውን ዓምድ «ዓለም ሰዎች እንዴት እንዲኖሩ እንደምትፈልግ» በሚሉ ርእሶች ለይ። በማቴ. 5፡3-12 የሚገኙትን የብፅዕና ዓይነቶች በሠንጠረዥ ውስጥ ሙላ። ይህ የመጀመሪያው ክፍል በክርስቶስ ተከታዮች ባሕርይ ላይ ያተኩራል። እኛ ብዙውን ጊዜ ክርስቲያን ሊያደርገው ይገባል ወይም አይገባም በምንለው ውጫዊ ተግባር ላይ ስናተኩር፥ ክርስቶስ ግን የተገቢው ተግባር መሠረቱ፥ ባሕርይ መሆኑን ያመለክታል። ክርስቶስ የባሕርያችን መለወጥ የተግባራችንን መለወጥ እንደሚያስከትል ያውቃል። ከእነዚህ ባሕርያት ውስጥ አንዱን መርጠን ሌሎችን መተው አንችልም። እነዚህ ሁሉ የክርስቶስ ተከታዮችን መለያ ባሕርያት ለመመሥረት በአንድነት የሚታዩ ናቸው። አንድ ሰው እንደተናገረው፥ እነዚህ ባሕርያት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ወደር የሌላቸው የክርስቶስ መገለጫዎች ናቸው። እነዚህ ባሕርያት ዓለም አስፈላጊዎች ናቸው ብላ ከምታስተምረው ትምህርት ጋር የሚቃረኑ ናቸው። ሀ. በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። ለአይሁዶች «ብፁዕ» የሚለው ቃል ደስተኛ ከመሆን የላቀ ፍች ነበረው። ይህ ቃል በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ማግኘትንና የበረከቱ ተቋዳሽ መሆንን ያሳያል። የመጀመሪያው በረከት የተሰጠው፥ በመንፈስ ድሆች ለሆኑት ሰዎች ነው። እዚህ ላይ ክርስቶስ የሚናገረው ስለ ሥጋዊ ድህነት ሳይሆን፥ ስለ መንፈሳዊ ድህነት ነው። ሥጋዊ ድህነት ያጠቃቸው ሰዎች ሙሉ በሙሉ በሰዎች ላይ ጥገኞች ሆነው የሚኖሩ ናቸው። የራሳቸው ሀብት ስለሌላቸው ለኑሮአቸው የሚደገፉት በሰዎችና በእግዚአብሔር ላይ ነው። በመንፈስ ድሀ መሆን ማለት፥ እግዚአብሔርን የሚያስደስትና ለእግዚአብሔር ለመኖር የሚያስችል መንፈሳዊ ሀብት እንደሌለን መገንዘብ ነው። ስለሆነም እርሱ ይረዳን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንመለከታለን። በመንፈስ ድሆች የሆኑ ሰዎች ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር ቢኖር፥ ወደ እግዚአብሔር ጸጋና ምሕረት ፊታቸውን መመለስ እንደሆነ ያውቃሉ። ወደ እርሱ ስለሚመለከቱ እግዚአብሔር ምሕረትን፥ ጸጋንና መዳንን ይሰጣቸዋል። በመንፈስ ድሆች የሆኑ ሰዎች በራሳቸው ችሎታ ሳይመኩ ማንኛውም መፍትሔ ከእግዚአብሔር እንደሚመጣ ያምናሉ። ዓለም የምታስተምረው የዚህን እውነታ ተቃራኒ ነው። የኋላ ኋላ ዓለም በሌሎች ላይ በሚደገፍ ሰው ትቀልድበታለች። ዓለም በማንነታችንና በተግባራችን እንድንኮራ ታስተምረናለች። ስለዚህ በሃይማኖታዊ ውርሳችንና በመንፈሳዊነታችን እንኩራራለን። እንዲሁም ተነሣሽነት ያላቸውን፥ ብልሆችን፥ ሀብታሞችንና ኃይለኞችን እናደንቃለን። በራሳቸው ብርታት ሊሠሩ የሚችሉ ሰዎች የሥልጣን ስፍራ ይሰጣቸዋል። የሃይማኖት ሰዎች ሳይቀሩ መንፈሳውያን ለመሆንና ደኅንነትን ለማግኘት በመቻላቸው ይኩራራሉ። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ በመንፈሳዊ ባለጸግነታቸው በመመካታቸው ክርስቶስ ሊሰጣቸው የሚፈልገውን በረከት ያጣሉ። በመንፈስ የሚታበዩ ሰዎች የክርስቶስ መንግሥት አካል አለመሆናቸውን ያሳያሉ። በመንፈስ ድሆች የሆኑ መንግሥተ ሰማይን ከእግዚአብሔር ዘንድ በስጦታ ይቀበላሉ። ክርስቶስ እንደ አማኑኤል ከእነርሱ ጋር ይኖራል። እርሱ በሕይወታቸው ላይ ይነግሣል። ስለሆነም በመንፈስ ድሆች የሆኑ ሰዎች በምድር ላይ የእርሱ መንግሥት አካል ሲሆኑ፥ መንፈሳዊ በረከቶቹን ይቀበላሉ። ከዚህም በላይ የክርስቶስ ዘላለማዊ መንግሥት አካል ለመሆናቸው እርግጠኞች ናቸው። የውይይት ጥያቄ፡- ሀ) አንድ ክርስቲያን በመንፈስ ድሀ ከመሆን ይልቅ፥ በመንፈስ ሀብታም ሊሆን የሚችልባቸውን መንገዶች ዘርዝር። ለ) በመንፈስ ድሀ የሆነው ክርስቲያን፥ በመንፈስ ትዕቢተኛ ከሆነው ክርስቲያን በአኗኗሩ እንዴት እንደሚለይ ግለጽ። ለ. የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መጽናናትን ያገኛሉና። ክርስቶስ በምን ምክንያት እንደሚያለቅሱ አልገለጸም። ዐውደ ምንባቡ ግን መንፈሳዊ ባሕርይ ያለው ነው። በኃጢአተኛነታቸውና በልባቸው ድንዳኔ የሚያዝኑ፥ እንዲሁም በቤተ ክርስቲያንና በአገራቸው ኃጢአት ምክንያት የሚያለቅሱ ወገኖች ይጽናናሉ [መዝ. (119)፡136 አንብብ]። የሚያለቅሱት የራስ ወዳድነት ፍላጎቶቻቸው ስላልተሟሉላቸው ሳይሆን፥ ዓለምና ሰዎች እግዚአብሔር በሚፈልገው መንገድ ባለመጓዛቸው ምክንያት ነው። ይህም ዓለም ከምታስተምረው አሳብ ተቃራኒ ነው። ዓለም በሕይወታችን እንድንደሰት ታስተምረናለች። ስለዚህም «ሰው እስከሆንህ ድረስ ለኃጢአት መጨነቅ የለብህም፥ የቤተ ክርስቲያንም ሆነ የአገር ኃጢአት ሊያስጨንቅህ አይገባም ልትለውጠው አትችልምና» ትለናለች። ክርስቶስ ስለ ኃጢአት የሚያለቅሱ ሰዎች እንደሚጽናኑ ተናግሯል። እነርሱም እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን ይቅርታ ስለሚያውቁ ይጽናናሉ። እግዚአብሔር በእነርሱና በጸሎታቸው አማካይነት የራሳቸውንና የሌሎችንም ሕይወት እንደሚለውጥ ስለሚያውቁ ይጽናናሉ። በኀዘናቸው ጊዜ ራሱ ክርስቶስ አብሯቸው እንደሚሆን ስለሚያውቁ፥ ይጽናናሉ። አንድ ቀን ኀዘንም ሆነ ለቅሶ የሌለበት መንግሥት ቤተሰቦች ስለሚሆኑ ይጽናናሉ (ራእይ 7፡17፤ 21፡4)። የውይይት ጥያቄ፡- ለመጨረሻ ጊዜ በሕይወትህ ውስጥ ወይም በቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ ስለተከሰተው ኃጢአት ያለቀስኸው መቼ ነበር? አልቅሰህ ከሆንህ ይህ ስለ ልብህ ሁኔታ ምንን ያሳያል? ሐ. የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና። የዋህ የሚለውን ቃል ለመተርጎም አስቸጋሪ ነው። ብዙውን ጊዜ የዋህነት ሰዎች ያሻቸውን ነገር ሲያደርጉ መልስ አለመስጠት ወይም ሞኝነት እንደሆነ እናስባለን። ይህ ግን ክርስቶስ ያስተማረው የዋህነት አይደለም። ክርስቶስ የዋህ የነበረ ቢሆንም፥ ይፋዊ ተቃውሞ ሳያሳይ ኢ-ፍትሐዊ የሆነ ነገር እንዳይደረግ ተከላክሏል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የዋህነት የተለያዩ ጽንሰ አሳቦች አሉት። በሕይወታችን ውስጥ ችግሮች በሚከሰቱበት ጊዜ ቁጡና መራር ሳይሆኑ፥ በትዕግሥት መገዛት የዋህነት ነው። ወይም የዋህነት ነገሮችን በራሳችን መንገድ ከማከናወንና የምንፈልገውን የማያደርጉትን ከመቃወም ይልቅ፥ በገር መንፈስ መመላለስ ሊሆን ይችላል። የዋህ ሰው እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር እንደሚሠራና የኋላ ኋላም ለጥቅማችን እንደሚያውለው ይገነዘባል። ስለሆነም እግዚአብሔር በሁኔታዎች ሁሉ ውስጥ ፍጹም ፈቃዱን ተግባራዊ እንደሚያደርግ ይተማመናል። የዋህነት በራስ ጥረት ሳይመኩ ሕይወትን ከእግዚአብሔር እጅ እንደተቀበሉ አድርጎ ማስተናገድ ነው። የዋህነት ራሳችንን ወይም አሳባችንን ለመከላከል አለመሞከርና ስሕተታችንን መቀበል ነው። ከዚህ በተቃራኒው ዓለም ዐመፅን፥ ተቃውሞንና የግል ፍላጎትን ታከብራለች። አንድን ነገር ከፈለግህ ተጠቀምበት። አንድ ሰው ካበሳጨህ እርሱን የሚያበግን አንድ እርምጃ ውሰድ። በሕይወት ቀዳሚ ሆነህ ለመገኘት፥ ከሌሎች ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ለማግኘት፥ የተሻለ ሥራ ለመያዝ፥ የቤተ ክርስቲያን መሪ ለመሆን፥ ጠልፈህ መጣል፥ ካስፈለገም ሰዎችን መገፍተርና ማጭበርበር ይኖርብሃል ትላለች። የዓለም ሥርዐት በሰዎች ላይ ኃይልን እንድንቀዳጅ ያበረታታል። በዚህ ሁኔታ ዓለም ሰዎች በማታለልና በማጭበርበር የቀዳሚነትን ስፍራ እንደሚይዙ ስታስተምር፥ ክርስቶስ ግን የዋሆች ምድርን እንደሚወርሱ አስተምሯል [መዝ. (37)፡9-11 አንብብ።] ይህ እንዴት ይሆናል? በመጀመሪያ፥ ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር ዓለም ከምትጠብቀው ተገላቢጦሽ የሆነውን ይሠራል። የቀዳሚነትን ስፍራ ለመያዝ የሚፍጨረጨሩ ሰዎች ምንም እንኳ ለጊዜው መጠቀም ቢችሉም፥ የኋላ ኋላ ፍሬያማ አይሆኑም። እግዚአብሔር በራሱ ጊዜና በራሱ መንገድ እንደሚባርካቸው የሚተማመኑ ግን፥ ባልተጠበቀ መንገድ የእግዚአብሔርን በረከት ይቀበላሉ። ይህም ሆኖ በረከቶቹ ይገቡናል፥ በበጎ ሥራችን አገኘናቸው የሚል ስሜት የላቸውም። ማቴዎስ ያተኮረው ግን በወደፊቱ ጉዳይ ላይ ነው። ክርስቲያኖች ምድራዊ በረከት ልንቀበል ወይም ላንቀበል ብንችልም፥ ከክርስቶስ ጋር እንደምንነግሥ ግን ጥርጥር የለውም። ይህ አጭር ምድራዊ ቆይታ፥ በዘላለማዊ መንግሥት የሚተካ ሲሆን፥ ምድራዊ የዋህነታችን መንፈሳዊ በረከትን ያስገኝልናል (ሉቃስ 22፡29-30፤ ራእይ 20፡4)። የውይይት ጥያቄ፡- በቤተ ክርስቲያንህ የየዋህነት ጉድለት ችግር ያስከተለበትን አጋጣሚ ግለጽ። መ. ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና። በዓለም ውስጥ ከሚገኙ እጅግ ጠንካራ ስሜቶች ሁለቱ ረሃብና ጥማት ናቸው። ምግብና ውኃ ሳናገኝ ብንቀር፥ አሳባችን ሁሉ እነዚህን ሁለት ነገሮች በማግኘቱ ላይ ያተኩራል። ያለእነዚህ ነገሮች ለመኖር አንችልም። ብዙውን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ጥልቅ መንፈሳዊ ፍላጎትን ከረሃብና ከጥማት ጋር ያነጻጽራል [መዝ. (42)፡1-2 አንብብ።] ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን በጊዜያዊ ነገሮች ከመወሰድ ይልቅ፥ ጽድቅን ሊራቡ እንደሚገባ አስተምሯቸዋል። ጽድቅ ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ ግንኙነት ማድረግ ወይም ሙሉ በሙሉ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መመላለስ ነው። በአሉታዊ ጎኑ፥ ከኃጢአትና እግዚአብሔርን ከማያስደስቱ ነገሮች መራቅ ነው። በአዎንታዊ ጎኑ፥ እግዚአብሔርን የሚያስደስቱትን ነገሮች ማድረግ ነው። እግዚአብሔርን በበለጠ ለማወቅና እርሱን ለማስከበር መፈለግ ነው። በተጨማሪም በቤተ ክርስቲያንም ሆነ በዓለም ሰዎች ትክክለኛና የእግዚአብሔር ፈቃድ ያለበትን ሕይወት ሲመሩ ለማየት መፈለግ ነው። ዓለም ግን የምትራበው ሌሎች ነገሮችን ነው። ትምህርትን፥ ገንዘብን፥ ኃይልና ሥልጣንን፥ ሌሎችንም ነገሮች ትራባለች። ዓለማውያን እግዚአብሔርን በሚያስደስት መንገድ የሚኖር ሰው ሞኝ እንደሆነ ያስባሉ። ኢየሱስ ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ እንደሚጠግቡ ተናግሯል። ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸው ግንኙነት እያደገ ሲሄድ ይመለከታሉ። ጽድቅን የሚሹ ሰዎች ባሕርያቸው ተለውጦ፥ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ሲስማማ ያያሉ። በእነርሱ አማካይነት በቤተ ክርስቲያናቸውና በማኅበረሰቡም መካከል ለውጦች ይከሰታሉ። ከሁሉም በላይ ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ሰዎች፥ ጽድቅ የሚገዛበት ዘላለማዊ መንግሥት ዜጎች በመሆናቸው ይጠግባሉ። 9ኛ ጥያቄ፡- ሕይወትህን መርምር። የምትራበውና የምትጠማው ለምንድን ነው? ጽድቅን የምትራብና የምትጠማ

የተራራው ስብከት [እግዚአብሔር የባረከው ሰው ባሕርይ] (ማቴ. 5፡1-12) Read More »

ክርስቶስ ለተከታዮቹ ያቀረበው ግብረገባዊ ትምህርት ማጠቃለያ (ማቴ. 5-7)

ክርስቶስ በማቴ. 5-7 ላይ ያስተማራቸው ትምህርቶች፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙ ዐበይት እውነቶች መካከል የሚመደቡ ናቸው። የውይይት ጥያቄ፡- ማቴ. 5፡1-2ን አንብብ። ሀ) ክርስቶስን ስለ መከተል የምንማራቸው ዐበይት ትምህርቶች ምንድን ናቸው? ለ) ከእነዚህ ባሕርያት መካከል ብዙውን ጊዜ ሰዎችን የሚታገሏቸው የትኞቹ ናቸው? አንዳንድ ምሳሌዎችን ጥቀስ። ተመስገን በወንጌላዊነት የሚያገለግል ወንድም ሲሆን፥ ለሌላ ጎሳ ስለ ክርስቶስ እንዲመሰክር ቤተ ክርስቲያኑ ላከችው። እርሱ የተላከባቸው ሰዎች አርብቶ አደሮች ነበሩ። ምንም እንኳ ተመስገን ለእነዚህ ሰዎች ስለ ክርስቶስ ቢመሰክርም፥ የወንጌል ትምህርቱን ያቀረበበት መንገድ ከእነርሱ አኗኗርና ባሕል የተለየ ነበር። በክርስቶስ በሚያምኑበት ጊዜ ሰውነታቸውን እንዲታጠቡ፥ ልብስ እንዲለብሱ፥ መጠጥ እንዲያቆሙ፥ ሁለተኛ ሚስቶቻቸውን እንዲፈቱ አሳሰባቸው። ጌታሁን ለቤተ ክርስቲያን ቅድስና የሚያስብ መጋቢ ነበር። ስለሆነም በሚሰብክበት ጊዜ ሰዎች ከመጠጥ፥ ከዝሙትና ከጫት እንዲታቀቡ አስጠነቀቀ። የውይይት ጥያቄ፡- ሀ) አንድ ሰባኪ ወይም ወንጌላዊ፥ ሰዎች ሊያደርጓቸው የሚገባቸውን ወይም የማይገባቸውን ነገሮች በመዘርዘር ወንጌልን ሲሰብክ የሰማኸው መቼ ነው? ለ) ከማቴ. 5፡1-12 ክርስቶስ ስለ መንግሥት ያቀረበው ስብከት፥ ብዙውን ጊዜ እኛ ወንጌሉን ከምንገልጽበትና ክርስቶስን ስለ መከተል ከምናስተምርበት መንገድ የሚለየው እንዴት ነው? ሐ) ሰዎች መንፈሳዊነትን እንዲማሩ ከመምከር ይልቅ፥ ውጫዊ ተግባራት ላይ በማተኮር ይህን አድርጉ፥ ያን አታድርጉ የሚሉ ዝርዝሮችን ሰጥቶ፥ አፈጻጸማቸውን መለካት የሚቀልለው እንዴት ነው? ማቴዎስ 5-7 ድረስ የተጻፈው ትምህርት ከየትኞቹም ወንጌላት በላይ ሰፋ ብሎ የቀረበ ሲሆን፥ ክርስቶስ ምን ትምህርት እንዳስተማረ ያብራራል። ምሑራን ይህ ትምህርት በአንድ ስብከት ስለ መጠናቀቁ ይከራከራሉ። ምናልባትም ክርስቶስ ይህን ትምህርት በሁለትና ሦስት ቀናት ውስጥ ለሕዝቡ ያስተማረው ትምህርት አጠቃላይ አሳብ ሊሆን ይችላል። ክርስቶስ ከስፍራ ወደ ስፍራ እየተዘዋወረ ስለሚያስተምር፥ ከእነዚህ እውነቶች ብዙዎቹ በሌሎችም ስፍራዎች ላይደገሙ አልቀሩም። አንዳንድ ምሑራን ማቴዎስ መጽሐፉን በሚጽፍበት ወቅት፥ ክርስቶስ፥ ደቀ መዛሙርቱ ሊኖሩት የሚገባቸውን ሕይወት በአንድ ላይ እንዳሰባሰበ ይናገራሉ። ስለሆነም ምንም እንኳ ማቴዎስ ኢየሱስ ለረዥም ጊዜ በተራራ ላይ ሆኖ ማስተማሩን ቢገልጽም፥ ክርስቶስ በሦስት ዓመት ይፋዊ አገልግሎቱ ጊዜያት ያስተማራቸውን ሌሎች እውነቶችም ጨምሯል። ኢየሱስ በገሊላ በአገለገለባቸው ጊዜያት ለደቀ መዛሙርቱ፥ የእርሱ ተከታይ መሆን፥ ፈሪሳውያን ብቁ አይሁዳዊ ስለ መሆን ከሚያስተምሩት ትምህርት የተለየ መሆኑን አሳይቷል። ምንም እንኳ ብዙ ሰዎች ትምህርቱን ቢከታተሉም፥ ማቴዎስ እንደሚነግረን፥ ክርስቶስ በተለይ ትምህርቱን ያተኮረው በደቀ መዛሙርቱ ላይ ነበር። ከማቴዎስ 5-7 ድረስ የተጠቀሱትን እውነቶች ክርስቶስ በደቀ መዛሙርቱ ሕይወት ውስጥ ሲተገበሩ ለመመልከት ፍላጎት ነበረው። በየዘመኑ ውስጥ የኖሩ ክርስቲያኖች እነዚህን እውነቶች ተግባራዊ ለማድረግ ታግለዋል። ይሁን እንጂ ሙሉ በሙሉ መፈጸም አልተቻላቸውም። አንዳንድ ክርስቲያኖች የእነዚህ ምዕራፎች ትምህርት በተራ ክርስቲያኖች የማይሞከሩ ስለሆነ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ብቻ ሊፈጽሟቸው የሚገቡ እንደሆነ አስተምረዋል። ሌሎች ደግሞ ክርስቶስ እነዚህን ትምህርቶች መፈጸም የማይቻል መሆኑን እያወቀ፥ ሰዎች ወደ ጸጋው እንዲመለሱ ለማበረታታት እንዳስተማረ አድርገው ገልጸዋል። የተቀሩት ደግሞ ክርስቶስ እነዚህን ትምህርቶች ለክርስቲያኖች እንዳልሰጠና፥ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ ለሺህ ዓመታት በሚነግሥበት ጊዜ ለሚኖሩት አይሁዶች የታቀዱ እንደሆነ አስረድተዋል። እነዚህ ሁሉ ክርስቶስ ከአስተማረው አስቸጋሪ ትምህርቶችና ደቀ መዛሙርቱ እንዲኖሩት ይፈልግ ከነበረው ሕይወት ለመሸሽ የተደረጉ ጥረቶች ነበሩ። ክርስቶስ እርሱን ለመከተል የሚፈልጉ ሁሉ ራሳቸውን ለእርሱ ሊያስገዙና በተለወጠ ሕይወት የመንግሥቱ አካል እንዲሆኑ ይሻል። ባሕርያቸው፥ ከሌሎች ጋር የሚዛመድበት መንገድና ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት አምልኮ ሁሉ መለወጥ አለበት። የክርስቶስ ተከታይ በሁሉም የሕይወት ዘርፍ ዐቢይ ለውጥ ማሳየት ይኖርበታል። ማቴዎስ 5-7 የተሰጠው ትምህርት ምናልባትም እንደ ክርስቶስ ተከታዮች እንዴት መኖር እንደሚገባን ከአዲስ ኪዳን ምንባቦች ሁሉ ጥርት ባለ ሁኔታ የሚያስተምረን ክፍል ነው። ምንም እንኳ ይህ በራሳችን ኃይል የማይቻል ቢሆንምና ማናችንም ከመቅጽበት ለመለወጥ ባንችልም፥ ክርስቶስ እንድንኖር የሚፈልገው በዚህ መንገድ ነው። (ማብራሪያው የተወሰደው በኤስ አይ ኤም ከታተመውና «የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ» ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ ስለዚህ አስደናቂ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው።)

ክርስቶስ ለተከታዮቹ ያቀረበው ግብረገባዊ ትምህርት ማጠቃለያ (ማቴ. 5-7) Read More »

የክርስቶስ የመጀመሪያ ዓመት አገልግሎት ማጠቃለያ (ማቴ. 4፡12-25)

የውይይት ጥያቄ፡- ሀ) ማቴ. 4፡12-25ን አንብብ። የክርስቶስ የመጀመሪያው አገልግሎት ዐበይት ባሕርያት ምንድን ናቸው? ለ) የክርስቶስ ትምህርት ከመጥምቁ ዮሐንስ ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው? ከማቴ. 3፡2 ጋር አነጻጽር። የክርስቶስ የመጀመሪያ ዓመት አገልግሎት እንደ ቀጣዩ ሁለት ዓመት ጥድፊያ የበዛበት አልነበረም። ማቴዎስ የመጀመሪያውን ቀዳሚ ዓመት አገልግሎቱን አልጠቀሰም። ክርስቶስ ውኃውን ወደ ወይን ጠጅ እንደለወጠ ወይም በኢየሩሳሌም ከኒቆዲሞስ ጋር እንደተገናኘ ማቴዎስ አልገለጸም። ማቴዎስ ከመጀመሪያው ዓመት ብዙ ሥራዎችን አልፎ፥ ይፋዊ አገልግሎቱን ብቻ በማጠቃለያ መልክ ይጀምራል። ይህንንም የሚያደርገው መጥምቁ ዮሐንስ ከታሰረበት ዓመት በመጀመር ነው። ምናልባትም ማቴዎስ ታሪኩን በዚህ መልክ የጻፈው፥ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የመጥምቁ ዮሐንስ «የመንገድ ጠራጊነት» ተግባር እንደተጠናቀቀ ለማሳየት ይሆናል፡፡ በዚህ ጊዜ መሢሑ መጥቷል። ማቴዎስ ስለ ክርስቶስ የመጀመሪያ አገልግሎት ሲያጠቃልል በቀረው ማጠቃለያ ላይ በአራት ነገሮች ላይ ትኩረትን አድርጓል፡ ሀ. ክርስቶስ በቀዳሚነት በገሊላ ስለ ማገልገሉ በተከታዩ የአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ፥ ክርስቶስ በአብዛኛው ከናዝሬት 25 ኪሎ ሜትር ያህል ርቃ በምትገኝ በገሊላ ባሕር ጫፍ ላይ በነበረችው በቅፍርናሆም ከተማ አገልግሏል። ከተማይቱ ጠቃሚ በሆነ የንግድ መስመር ላይ ትገኝ ስለነበር፥ በቅፍርናሆም የሚያልፉ ብዙ ሰዎች ስለ ክርስቶስ ሰምተው ሊያምኑበት ችለዋል። በተጨማሪም ቅፍርናሆም ጴጥሮስንና ማቴዎስን ጨምሮ የብዙ ደቀ መዛሙርት መኖሪያ ነበረች። ማቴዎስን ያስደነቀው ነገር ቢኖር፥ ክርስቶስ በገሊላ የሰጠው አገልግሎት የትንቢት ፍጻሜ መሆኑ ነበር (ኢሳ. 9፡1-2)። ገሊላ በብሉይ ኪዳን ዘመን በዛብሎንና በንፍታሌም ነገዶች ግዛት ውስጥ ትገኝ ነበር። እነዚህ ሁለቱም አካባቢዎች በኢየሩሳሌም በሚኖሩ አይሁዶች ዘንድ የተናቁ ነበሩ። ለዚህም ምክንያት የነበረው፥ በእነዚህ አካባቢዎች ይኖሩ የነበሩ አይሁዶች ከአሕዛብ ጋር ተጋብተው ጣዖታቸውንም ያመልኩ ስለነበር ነው። በ722 ዓ.ዓ. እስራኤል በአሦር ከተማረከችበት ጊዜ አንሥቶ፥ ይህ የፍልስጤም ክፍል በአሕዛብ ቅኝ ግዛት ሥር ውሎ ነበር። ከዚህ በኋላ አይሁዶች በመቃባውያን ዘመን በገሊላ ሰፈሩ። እነዚህ አነስተኛ የአይሁድ ቅኝ ግዛቶች እያደጉ የሄዱ ሲሆን፥ ብዙውን ጊዜ በይሁዳ ከሚኖሩ አይሁዶች በላይ ብሔራዊ ስሜት ይሰማቸው ነበር። ይህም ሆኖ፥ በይሁዳ የሚኖሩ አይሁዶች የገሊላ አይሁዶችን ይንቋቸው ነበር። እንኳን መሢሑ አብዛኛውን ጊዜውን በምድር ላይ ማሳለፉ ቀርቶ፥ ምንም መልካም የሆነ ነገር ከገሊላ ይመጣል ብሎ የጠበቀ ሰው አልነበረም (ዮሐ. 1፡45-46፤ 1፡41፥ 52 አንብብ)። ምንም እንኳን ገሊላ በብዙ ሰዎች ብትናቅም፥ እንደ ሰው የአገርና የጎሣ ኩራት በማያጠቃው አምላክ ተከበረች። ለ. ኢየሱስ፥ «መንግሥተ ሰማይ ቀርባለችና ንስሐ ግቡ» እያለ አስተማረ። ማቴዎስ፥ የክርስቶስ መሠረታዊ ትምህርት የመጥምቁ ዮሐንስ ዓይነት መሆኑን አሳይቷል። ይህም ለሰዎች መንግሥተ ሰማይ እንደቀረበችና ንስሐ መግባት እንዳለባቸው የሚያሳስብ ትእዛዝ ነበር። መሢሑ በመካከላቸው ስለነበረ፥ ሕዝቡ ሕይወታቸውን መለወጥ ነበረባቸው። ከአሮጌው ሕይወታቸው ተመልሰው ለመሢሑ መንግሥት መዘጋጀት ያስፈልጋቸው ነበር። ሐ. ኢየሱስ ሰዎች ደቀ መዝሙሩ ሆነው እንዲከተሉት ጠርቷል። በአፈ ታሪክ እንደሚነገረው፥ የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎች ስለ እግዚአብሔር ዐበይት እውነቶችን የሚያስተምሯቸው ደቀ መዛሙርት ነበሯቸው። እነዚህ ደቀ መዛሙርት መምህሮቻቸው ወደሚሄዱበት ሁሉ እየሄዱ ይረዷቸውና ትምህርት ይቀስሙ ነበር። ክርስቶስ ይህንን ትውፊት በመከተል ከመጀመሪያው ራሱን እንደ ሃይማኖት መሪ አስተዋውቋል። ክርስቶስ ሰዎች እስኪከተሉት ከመጠበቅ ይልቅ፥ ደቀ መዛሙርቱን ለመምረጥ የአስተዋይነት ምርጫ አድርጓል (ማቴ. 4:18-22)። ማቴዎስ ክርስቶስ ከመረጣቸው ደቀ መዛሙርት የመጀመሪያ አራቱን ጠቅሷል። የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ፥ ስምዖን ጴጥሮስና እንድርያስ የሚባሉ ወንድማማቾች ሲሆኑ፥ ሌሎቹ ሁለቱ ያዕቆብና ዮሐንስ የሚባሉ ወንድማማቾች ነበሩ። ክርስቶስ ከዚህ በፊት የነበራቸውን ሥራ ትተው እንዲከተሉት ጠራቸው። ዓሣ ማጥመዳቸውን እንዲተዉና የእርሱን ትምህርት ተቀብለው ሰዎችን እንዲያጠምዱ አሳሰባቸው። (ይህንን በዮሐንስ 1 ከሚገኘው ታሪክ ጋር በምናነጻጽርበት ጊዜ፥ አራቱም ደቀ መዛሙርት ለተወሰነ ጊዜ ክርስቶስን ከተከተሉ በኋላ ወደ ቀድሞ ሥራዎቻቸው በመመለሳቸው፥ ክርስቶስን ለመከተል እንደገና የተጠሩ ይመስላል።) በወንጌላት ውስጥ ብዙውን ጊዜ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ስለመሆን ያገለገለው ቃል፥ «መከተል» የሚል ነው። ክርስቶስ ይህን ቃል በመጠቀም በእርሱ የሚያምኑ ሰዎች በሕይወታቸው ላይ ላለው ሥልጣን እንዲገዙ እየጠየቃቸው ነበር። ዕቅዶቻቸውን ትተው የክርስቶስን ፈቃድ መፈጸም ያስፈልጋቸው ነበር። አኗኗሩን፥ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን ቅርበት፥ ከሰዎች ጋር የነበረውን ቅርበትና ያገለገለበትን መንገድ መከተል ነበረባቸው። ተከታዮቹ እርስ በርሳቸው ኅብረት ነበራቸው። ይህም ኅብረት ቤተ ክርስቲያን ይባላል። አካሉ በሆነችው ቤተ ክርስቲያን አማካይነት ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይሠራሉ። የውይይት ጥያቄ፡- ሀ) ለጴጥሮስ፥ እንድርያስ፥ ያዕቆብና ዮሐንስ ክርስቶስን የመከተሉ ምርጫ አስቸጋሪ ሊሆን የቻለው እንዴት ነበር? ለ) ከዚህ፣ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ስለ መሆን ምን እንማራለን? ሐ) የክርስቶስ «ተከታይ» መሆንህን እንዴት እያሳየህ እንደሆነ አብራራ። በማቴ. 28፡19-20 ላይ፥ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱ የራሱን አርአያ በመከተል ሌሎች ደቀ መዛሙርትን እንዲያፈሩ ነግሯቸዋል። በምድር ላይ ከሚገኙ ነገዶች ሁሉ ሰዎችን ደቀ መዛሙርት ማድረግ ይኖርባቸዋል። እያንዳንዱ ክርስቲያን የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ለመሆን ተጠርቷል። ይህ ምን ማለት ነው? ማቴዎስ ደቀ መዝሙር የክርስቶስን አዲስ የሕይወት ልምምድ ለመቀበል ሲል፥ አሮጌ ሕይወቱን የሚተው ሰው እንደሆነ ይነግረናል። ይህ በቀዳሚነት ስለ ኢየሱስ በመመስከር፥ ደቀ መዛሙርት ይሆኑ ዘንድ «ሰዎችን ማጥመድ»ን ጭምር የሚያካትት ነው። ክርስቶስ እርሱን ለመከተል ሥራችንን እንድንተው አይጠይቀን ይሆናል፤ ይሁንና ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ ለእርሱ እንድናስገዛ ይፈልጋል። ማቴዎስ ክርስቶስን መከተል ማለት እርሱን ለመከተል ሁሉንም ነገር መተው እንደሆነ አመልክቷል። ይህ ከፍተኛ ዋጋን የሚያስከፍለን እንጂ ቀላል ውሳኔ አይደለም። መ. ኢየሱስ ሲያስተምር፥ ሲሰብክና ሲፈውስ ዝናው እየገነነ መጣ። ማቴዎስ፥ ክርስቶስ ያደረጋቸውን ነገሮች ሁሉ ከመዘርዘር ይልቅ በማቴዎስ 5-7 ላይ በቀረበው የትምህርት አገልግሎቱ ላይ ያተኩራል። ነገር ግን የክርስቶስ ትምህርት የታላቁ አገልግሎት አካል እንደሆነ ለማሳየት ሲል፥ ማቴዎስ የክርስቶስን ተግባራትና የሕዝቡን ምላሽ ጠቅለል አድርጎ ገልጾታል። እንደተጻፈው ሁሉ ክርስቶስ በገሊላ ከተማ ውስጥ ከስፍራ ወደ ስፍራ እየተዘዋወረ ያስተምር ነበር። በምኩራብና በሜዳ ላይ ባለማቋረጥ ያስተምር፥ ይሰብክና ይፈውስ ነበር። አንድ ምሑር እንደገለጹት፥ «ማስተማር» ኢየሱስ ሰዎች እንዲያውቁ የፈለጋቸውን እውነቶች ማሳወቁን ያመለክታል። ስብከት ደግሞ ክርስቶስ ሰዎች እውነትን ተግባራዊ ለማድረግ ሕይወታቸውን እንዲለውጡ መፈለጉን ያሳያል። ፈውስ ደግሞ ክርስቶስ ለሕዝቡ የነበረውን ርኅራኄ ብቻ ሳይሆን፥ መሢሕ መሆኑንም በይፋ ያሳየበት አገልግሎት ነበር። ከፈውሱ ዓይነት አንዱ ከአጋንንት ነፃ መውጣት ሲሆን፥ ይህም የክርስቶስ መንግሥት የሰይጣንን መንግሥት እያሸነፈ መሆኑን አሳይቷል። ክርስቶስ በዚህ ባሕሪው በሰዎች ዘንድ ተወዳጅነትን እያተረፈ ሊመጣ ችሏል። ከገሊላ በስተ ሰሜን ከምትገኘው ከሶሪያ እስከ ደቡባዊቷ ኢየሩሳሌምና በስተምሥራቅ እስከሚገኙት ዐሥሩ ከተሞች ድረስ ስለ እርሱ ሥራ በሰፊው ይወራ ነበር። ማቴዎስ ክርስቶስ የፈጸመውን ተግባር ጠቅለል ባለ ይዘት ካቀረበ በኋላ፥ በተቀረው የመጽሐፉ ክፍል ሁሉ በክርስቶስ ተአምራትና ዐበይት ትምህርቶች ላይ ያተኩራል። (ማብራሪያው የተወሰደው በኤስ አይ ኤም ከታተመውና «የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ» ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ ስለዚህ አስደናቂ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው።)

የክርስቶስ የመጀመሪያ ዓመት አገልግሎት ማጠቃለያ (ማቴ. 4፡12-25) Read More »

የኢየሱስ መፈተን (ማቴ. 4፡1-11)

ተስፋዬ እግዚአብሔርን የሚወድ ክርስቲያን ነጋዴ ሲሆን፥ እግዚአብሔር ንግዱን በሚያካሄድበት ታማኝ መንገድ ሁሉ ሊከብር እንደሚፈልግ በጥልቀት ያውቃል። ነገር ግን በሕገ-ወጥ አሠራር ለለመዱት የመንግሥት ሹማምንት የተወሰነ ጉቦ ካልከፈለ በስተቀር፥ ባለሥልጣናቱ የእርሱን ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ በጊዜው እንደማያድሱለት በተግባር ይገነዘባል። በዚህ ከባድ ውጥረት ውስጥ እያለ «ለመሆኑ እኔ ንግዴን ለማስቀጠልና ቤተሰቤን ለመመገብ ስል ጉቦ ብሰጣቸው ምን አለበት? ሌላውም እኮ እየሰጠ ነው!» ሲል በልቡ አሰበ። ስለሆነም ተስፋዬ የጽድቅን መንገድ ትቶ በስውር ጉቦ በመስጠት የንግድ ፈቃዱን አሳደሰ። ነገር ግን በዙሪያው ያሉ ማኅበረሰቦችና ክርስቲያን ያልሆኑ ሰዎች ተስፋዬ ፈቃዱን ለማግኘት ጉቦ መስጠቱን ወዲያውኑ በሰሙና በተረዱ ጊዜ፥ እርሱ በመድረክ እንደሚሰብከው እውነተኛና ታማኝ የእግዚአብሔር ሰው አለመሆኑን አወቁ፤ የክርስቶስም ስም በእርሱ ምክንያት ተሰደበ። በተመሳሳይ መንገድ ጌታሁን ወደ አሜሪካ አገር ሄዶ በከፍተኛ ትምህርት ለመማርና እዚያው ለዘላለም ለመኖር የሚፈልግ እጅግ ብሩኅ አእምሮ ያለው ወጣት ተማሪ ነበር። ነገር ግን በቪዛ ቃለ-መጠይቅ ወቅት ለኤምባሲው ኃላፊዎች «እኔ እዚያው ቀርቼ በቋሚነት ለመኖር ታማኝ ምኞት አለኝ» ብሎ እውነተኛውን የልቡን ሃሳብ ቢናገር፥ የኤምባሲው ሕግ የኢሚግሬሽን ስጋት ስላለበት ቪዛውን ፈጽሞ እንደማይሰጠው አስቀድሞ በሚገባ ያውቃል። ስለሆነም ጌታሁን ቪዛውን በእጁ ለማስገኘት ሲል፥ በኤምባሲው ኃላፊዎች ፊት ቆሞ «እኔ ትምህርቴን በአሜሪካ በሚገባ ካጠናቀቅሁ በኋላ፥ ወዲያውኑ ወደ እናት አገሬ ወደ ኢትዮጵያ እመለሳለሁ» በማለት የሐሰት ቃል ኪዳን ገባላቸው። 👥 የውይይት ጥያቄ እና ተግባራዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልስ የሰይጣን ዲያብሎስ ማንነትና የፈተና ተፈጥሮ ሁላችንም እንደ አምላክ ቃል እውነት ሰይጣን እውነተኛ የሰው ልጅ ጠላትና ክፉ ፈታኝ መሆኑን በሚገባ እናውቃለን። እርሱና ረዳቶቹ የሆኑት ርኩሳን አጋንንት የእግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ በምድር ላይ ኃጢአትንና ዓመፅን እንዲፈጽም ባለማቋረጥ በየዕለቱ ይፈትናሉ። ከፈተኑንና በኃጢአት ውስጥ ጥለው ካሳቱ በኋላ ደግሞ፥ ወዲያውኑ ፊታቸውን አዙረው በቅዱሱ እግዚአብሔር ፊት ሌሊትና ቀን በከፍተኛ ቁጣ ይከሱናል (ራእይ 12:10)። በዕብራይስጥ ቋንቋ «ሰይጣን» (Satan) ማለት ቀጥተኛ ትርጉሙ «ተቃዋሚ / ጠላት» ማለት ሲሆን፥ በግሪኩ ደግሞ «ዲያብሎስ» (Diabolos) ማለት «ከሳሽ / ስም አጥፊ» ማለት ነው። ይህም ሰይጣን አማኞች ኃጢአት በሚሠሩበት ጊዜ የእግዚአብሔርን የምሕረት ጸጋ ለማስጣል በፈጣሪ ፊት እንዴት በክፉ እንደሚከሳቸው በግልጽ ያሳያል። አንድን የእግዚአብሔርን ቃል የሚጥስ የተሳሳተ ተግባር ለመፈጸም በልባችን በምንነሳበት ጊዜ ሁሉ በትክክል እንፈተናለን። ሰይጣን ፈተናውን በፊታችን ሲያቀርብ ሁልጊዜ ያ ነገር በአእምሯችን እጅግ መልካም፥ ጠቃሚ ወይም ሥጋን የሚያስደስት አምሳል አስመስሎ ነው። የምንፈልገውን አስቸጋሪ ምድራዊ ነገር በአጭር ጊዜ ውስጥ ያለምንም ድካም የምናገኝበት ብልህ «የአቋራጭ መንገድ» ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ይህ አቋራጭ መንገድ ሁልጊዜም እግዚአብሔር በቃሉ ለእኛ ካዘጋጀው ከጽድቅና ከቅድስና መንገድ ፍጹም ውጭ የሆነ የጥፋት ወጥመድ ነው (ምሳሌ 14:12)። የመጀመሪያዋ ሴት ሔዋን በእግዚአብሔር ሉዓላዊ አገዛዝ ሥር በትሕትና መኖር ትታ፥ በገዛ ራሷ መንገድ «ልክ እንደ እግዚአብሔር ለመሆን» በሥጋ ስላለች፥ እግዚአብሔር አትብሉ የተባለችውን መልካሙንና ክፉውን የምታስታውቀውን የዛፍ ፍሬ በጉጉት በላችና ውድቀትን አመጣች (ዘፍጥ. 3፡6)። ዛሬም በተመሳሳይ መንገድ ወሲባዊ እርካታንና ፍቅርን በሥጋ ስለምንሻ፥ እግዚአብሔር የደነገገው የተቀደሰው የጋብቻ ጊዜያችን በትዕግሥት ሳይደርስ፥ አሁኑኑ በኃጢአትና በዝሙት አቋራጭ መንገድ የሥጋ ፈቃዳችንን ለመፈጸም በጽኑ እንሻለን። ወይም ቁሳዊ ሀብቶችንና ስኬትን አብዝተን እንፈልግና እግዚአብሔር በራሱ መለኮታዊ የጊዜ ሰሌዳ በበረከቱ እንዲጎበኘን በትሕትና ከመጠበቅ ይልቅ፥ ያንን ምድራዊ ነገር በፍጥነት ለማግኘት ስንል ያለምንም ፍርሃት በውሸት እንናገራለን፤ ሥራችን እንዲቀናም ለምድራዊ ሹማምንት ጉቦ እንሰጣለን። ሁለተኛው አዳም — የክርስቶስ መፈተን ምስጢር ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምድራዊ የድነት (የደኅንነት) ታሪክ ከሚያስደንቁንና ከሚገርሙን ታላላቅ መለኮታዊ ምስጢራት መካከል አንዱ፦ ቅዱሱ እግዚአብሔር አብ አንድያ ልጁ በሥጋ ወደዚህ ምድር በመጣበት ወቅት፥ ልክ እንደ እኛ በሰይጣን ዲያብሎስ ፈተና ውስጥ እንዲያልፍ በሉዓላዊ ጥበቡ መፍቀዱ ነው። በዕብራውያን መልእክት 2፡17-18 እና 4፡15 ላይ ከኃጢአት በረከስ በስተቀር፥ በነገሮች ሁሉ ልክ እንደ እኛ እውነተኛ ሰብአዊ ፈተናዎችን በምድር የተቀበለና የተፈተነ ታላቅና ሩኅሩኅ ሊቀ-ካህናት እንዳለን ተገልጧል፦ «ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።» (ዕብራውያን 4:15) ለዚህ ነው እኛ አማኞች በምድር ኑሯችን የሰይጣን ከባድ ፈተናና መከራ ሲያጋጥመን፥ ያንን ፈተና በድል እንድንወጣና እንድናሸንፍ በጸጋው ዙፋን ፊት ቀርቦ የሚረዳን እውነተኛ ሊቀ-ካህናችን እርሱ ብቻ የሆነው (ዕብ. 2:18)። የእግዚአብሔር ልጅ ለይፋዊ አገልግሎቱና ለወንጌል መቀባት በሚዘጋጅበት የታሪክ ቅጽበት፥ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሆን ብሎ ልጁ በምድረ-በዳ በዲያብሎስ እንዲፈተን መራው (ማቴ. 4፡1)። ክርስቶስ በይሁዳ በረሃ ውስጥ ለ 40 ቀናትና ለ 40 ሌሊት ያለምንም ምድራዊ ምግብ በጽኑ በጾመበት ወቅት፥ በረሃብ ደክሞ በነበረበት ሰዓት ሰይጣን እርሱን በኃጢአት ወጥመድ ለማጥመድ የሚችልበት ትክክለኛ ምድራዊ አጋጣሚ የደረሰ መሰለው። ሰይጣን ሁልጊዜ እኛን አማኞችን ለመጣል የሚፈትነን በአካላችንና በሕይወታችን ውስጥ እጅግ ደካማና የተራብን በምንሆንበት የታሪክ ሰዓት ላይ ነው፤ በክርስቶስም ላይ ያደረገው በትክክል ይህንኑ ነበር። ይህ በምድረ-በዳ የተከሰተው ፈተና ክርስቶስ የእስራኤል መሢሕ እንደመሆኑ መጠን፥ ወደፊት በምድር አገልግሎቱ ከሚጋፈጣቸው ታላላቅ መለኮታዊ ተልእኮዎች ጋር በጥልቀት የሚዛመድ ነበረ። ሐዋርያው ማቴዎስ በወንጌሉ ምዕራፍ 4 ላይ ይህንን የጌታን የፈተና ታሪክ በጥንቃቄ የዘገበበት ታላቅ ዓላማ፦ ሰይጣን እያንዳንዳችንን አማኞች በምድር ላይ በምን ዓይነት ስልታዊ መንገዶች እንደሚፈትነን እንድንረዳና ያንን ፈተና በመንፈስ ቅዱስ ሰይፍ በእግዚአብሔር ቃል እንዴት በኃይል ማሸነፍና መቋቋም እንደምንችል ታላቅ መንፈሳዊ ትምህርት ሊሰጠን ስለፈለገ ነው። ክርስቶስ በምድረ-በዳ በሰይጣን የተፈተነበት ሦስት ታላላቅ የሕይወት ፈርጆች፥ ሐዋርያው ዮሐንስ በመልእክቱ ላይ ከዓለም የሚመጡ የኃጢአት መነሻዎች ብሎ ከዘረዘራቸው ከሦስቱ ዋና ዋና ክፍሎች ጋር ፍጹም አንድ ወጥ ናቸው፤ እነርሱም፦ የሥጋ ምኞት፥ የዓይን አምሮትና የሕይወት ትምክህት ናቸው (1ኛ ዮሐ. 2፡16)። ነገረ-መለኮት ሊቃውንት የዚህን ታላቅ ፈተና መለኮታዊ ውጤት በጥንቃቄ ሲተረጉሙት የሚከተሉትን 2 ታላላቅ ሚዛናዊ ምስጢሮች ያስተምራሉ፦ 👥 የውይይት ጥያቄ እና ተግባራዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልስ ፩. የመጀመሪያው ፈተና — የሥጋ ምኞት (ድንጋይን ወደ ዳቦ መለወጥ) ሰይጣን ወደ ጌታ ቀርቦ ያቀረበው የመጀመሪያው ፈተና፦ «የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ እዘዝ» የሚል ነበረ (ማቴ. 4፡3)። ክርስቶስ ለ 40 ቀናት ሙሉ በሙሉ ከጾመ በኋላ ሰብአዊ አካሉ በረሃብ እጅግ ዝሎና ደክሞ ነበር። ለመሆኑ ድንጋይን በተአምር ወደ በላ ዳቦ መለወጡ በራሱ ምን ኃጢአትና ችግር አለው? ክርስቶስ በኋላ ላይ በምድር አገልግሎቱ አምስት እንጀራና ሁለት ዓሣ አብዝቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በተአምር መግቦ የለ! (ማቴ. 14:19-20)። ታዲያ በተራበበት በዚያ ሰዓት የገዛ መለኮታዊ ኃይሉን ተጠቅሞ ያንን ድንጋይ ለምን ዳቦ አላደረገውም? የዚህ ፈተና ዋናው ስውር መሠረት፦ የተሰጠውን መለኮታዊ ሥልጣንና ኃይል ለእግዚአብሔር አብ ፈቃድና ክብር ሳይሆን፥ ለገዛ ራሱ ሥጋዊ ጥቅም ማዋል በሚለው አጀንዳ ላይ ነበር። በአባቱ በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዕቅድ የተወሰነው ፍጹም መመሪያ፦ ክርስቶስ የተሰጠውን ተአምራት የማድረግ መለኮታዊ ኃይል በሙሉ ለሌሎች ሰዎች ድነትና ለእግዚአብሔር መንግሥት ክብር ብቻ እንዲጠቀምበት እንጂ፥ ለገዛ ራሱ ሥጋዊ ምቾትና ለግል ጥቅሙ ማርኪያ ፈጽሞ እንዳይገለገልበት ነበር። ክርስቶስ በምድር ላይ መለኮታዊ ኃይሉን ይጠቀም የነበረው፥ እግዚአብሔር አብ በቃሉና በመንፈሱ ሲፈቅድለትና ሲያዘው ብቻ ነበር፤ ጌታም በወንጌሉ ላይ «አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም» በማለት ይህንን ፍጹም ታዛዥነት በክብር ገልጾታል (ዮሐ. 5:19)። ሰይጣን እዚህ ላይ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንዲጠራጠር ለማድረግ አልሞከረም፤ ምክንያቱም ሰይጣንም ሆነ ክርስቶስ የእርሱን ዘላለማዊ አምላክነት በሚገባ ያውቁ ነበር። ነገር ግን ሰይጣን የፈለገው የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ክርስቶስ፥ የሥጋ ፍላጎቱ አሸንፎት ሥልጣኑን እግዚአብሔር አብ ባልፈቀደበት በራሱ መንገድ በአቋራጭ እንዲጠቀምበት መፈተን ነበር። 👥 የውይይት ጥያቄ እና ተግባራዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልስ ታላቁ ሐዋርያው ጳውሎስ በፊልጵስዩስ መልእክት 2፡5-8 ላይ እንደገለጠው፥ የሰማይና የምድር ጌታ የሆነው ክርስቶስ ወደ ምድር በሥጋ በመጣ

የኢየሱስ መፈተን (ማቴ. 4፡1-11) Read More »

የኢየሱስ መጠመቅ (ማቴ. 3፡13-17)

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምድራዊ ሕይወት ሙሉ በሙሉ በአባቱ በእግዚአብሔር ሉዓላዊ አመራርና መለኮታዊ የጊዜ ሰሌዳ ሥር ነበር። እርሱም ይፋዊው የማዳን አገልግሎቱ የሚጀመርበት የታሪክ ሰዓት እስኪደርስ ድረስ፥ በትሕትናና በትዕግሥት በናዝሬት ከተማ ውስጥ በጸጥታ ሲጠብቅ ቆየ። በዚያን ጊዜ በይሁዳ ምድረ-በዳ የታላቁ የመጥምቁ ዮሐንስ ወንጌላዊ አገልግሎትና ስብከት በሕዝቡ ዘንድ በስፋት ታውቆ ነበር። አንድ ቀን ጌታ ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት ተነሥቶ፥ ዮሐንስ ወደሚያጠምቅበት ዮርዳኖስ ወንዝ (በይሁዳ ምድር) በቀጥታ መጣ። መጥምቁ ዮሐንስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ኢየሱስ የእግዚአብሔር እውነተኛ መሢሕ መሆኑን ወዲያውኑ አወቀ። በሕግና በልምድ ሥርዓት ብዙውን ጊዜ ታላቁና ዋናው አገልጋይ ታናሹን ስለሚያጠምቅ፥ መጀመሪያ ላይ ዮሐንስ ክርስቶስን ለማጥመቅ ፈጽሞ አልፈለገም ነበር፤ ይልቁኑ ራሱ ዝቅ ብሎ፦ «እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል፥ አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?» አለው (ማቴ. 3፡14)። አንዳንድ መጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን ዮሐንስ ይህንን ማለቱ፥ ከእርሱ የውኃ ጥምቀት እጅግ የሚበልጠውን የክርስቶስን የመንፈስ ቅዱስና የእሳት ጥምቀት በናፍቆት ፈልጎ ስለነበር ነው ይላሉ። ክርስቶስ ግን በሥልጣን ምላሽ ሰጥቶ፦ «አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲሁ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና» በማለት ዮሐንስ ሊያጠምቀው እንደሚገባ በግልጽ ገለጸ (ማቴ. 3፡15)። ክርስቶስ «ጽድቅን ሁሉ መፈጸም» ሲል፥ ይህ ጥምቀት በእግዚአብሔር አብ ዘላለማዊ ዕቅድ ውስጥ በጥንቃቄ የታቀደ መለኮታዊ ዝግጅት መሆኑንና ዮሐንስም እንደ መንገድ ጠራጊነቱ ይህንን ሊፈጽም እንደሚገባው መግለጹ ነበር። ይህ ፍጹም የታዛዥነትና የጽድቅ መንገድ ነበር። የነገረ-መለኮት ምሁራን «ክርስቶስ ራሱ ለምን በጥምቀት ውስጥ ማለፍ አስፈለገው?» በሚለው አሳብ ላይ ሰፊ ትንታኔዎችን ይሰጣሉ። ክርስቶስ ፍጹም ቅዱስና ከኃጢአት የጠራ በመሆኑ (ዮሐ. 8፡46፤ ዕብ. 4፡15)፥ የእርሱ ጥምቀት ልክ እንደ ተራው ሕዝብ ከኃጢአት ንስሐ መግባትንና በባህርይ ላይ የሕይወት ለውጥ ማድረግን የሚያመለክት ፈጽሞ አልነበረም። ምክንያቱ ግን እጅግ የላቀ ሰማያዊ ምስጢር ነበረው። ክርስቶስ የተጠመቀባቸው 4 ታላላቅ መለኮታዊ ምክንያቶች በወንጌላውያን ነገረ-መለኮት ውስጥ አዘውትረው የሚጠቀሱትና ለቤተ ክርስቲያን መሠረት የሆኑት 4ቱ ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦ ፩. የውይይት ጥያቄ፦ የቅዱስ ሥላሴ መገለጥ በዮርዳኖስ ወንዝ በአጠቃላይ በአዲስ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ፥ ሦስቱ የሥላሴ መለኮታውያን አካላት (አብ፥ ወልድና መንፈስ ቅዱስ) በአንድ የታሪክ ቅጽበት በአንድነት አብረው የሠሩበትና የተገለጡበት ከሁሉ የላቀው ታላቁና ግልጹ ምሳሌ የክርስቶስ ጥምቀት ክስተት ነው (ማቴ. 3፡16-17)። በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ላይ ፍጹም አንድ አምላክ የሆኑት ሦስቱ መለኮታውያን አካላት በሚከተለው አስደናቂ አኳኋን ተገልጠዋል፦ ፩. እግዚአብሔር ወልድ በሥጋ ተጠመቀ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ልጅ የሆነው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰብአዊ አካል ለብሶ በምድር ላይ በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ በዮሐንስ እጅ በጥምቀት ወረደ። ፪. እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወረደ ክርስቶስ ከውኃው ወዲያውኑ በወጣ ጊዜ፥ ሰማያት ተከፈቱ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም በአካል ገጽታ በርግብ አምሳል በግርማ ወርዶ በክርስቶስ ላይ በክብር አረፈ። ክርስቶስ ፍጹም አምላክ እንደመሆኑ መጠን፥ በምድር ላይ በገዛ መለኮታዊ ሥልጣኑ ብቻ ታላላቅ ተአምራትን ሊሠራና ሊያስተምር ሙሉ አቅም የነበረው ቢሆንም፥ እርሱ ግን ፍጹም ሰው ሆኖ የመጣ አማኝ እንደመሆኑ መጠን ለእኛ ታላቅ ምሳሌ ሊሆን ዘንድ ራሱን ለአዳኙ መንፈስ ቅዱስ ኃይልና አሠራር ሙሉ በሙሉ አስገዛ። መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ላይ በኃይል መውረዱ፥ በብሉይ ኪዳን ትንቢት የተነገረው መለኮታዊ የመሢሕነት አገልግሎቱን በይፋ ለመጀመር የተቀባበት ታላቅ ማረጋገጫ ምልክት ነበር (ኢሳ. 11፡2፤ 61፡1)። በርግብ አምሳል የመውረዱ ምስጢር፦ መንፈስ ቅዱስ በዮርዳኖስ ወንዝ ላይ የባሕርይ ምልክቱ ይሆን ዘንድ የርግብን አምሳል የመረጠው ለምንድን ነው? በመጀመሪያ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክ ውስጥ ርግብ ሁልጊዜ ከመለኮታዊ ተፈጥሮና ንጽሕና ጋር ተያይዛ ትጠቀሳለች፤ ገና በፍጥረት መጀመሪያ ምድር ባዶና በጨለማ ውስጥ ሳለች የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በውኃ ላይ ልክ እንደ ርግብ ሰፍፎ (በዕብራይስጥ Merachephet – ክንፎቹን ዘርግቶ) ሕይወትን ይፈልቅ እንደነበር ተመዝግቧል (ዘፍጥ. 1፡2)። በሁለተኛ ደረጃ በአይሁድ ማኅበረሰብ እይታ ዘንድ ርግብ ፍጹም የዋህነትን፥ ትሕትናንና ሰላማዊ አገልግሎትን ታመለክታለች (ማቴ. 10:16)። ምንም እንኳ በዘመኑ የነበሩት አይሁድና መጥምቁ ዮሐንስ መሢሑ ሲመጣ ወዲያውኑ ጠላቶቹን ሮማውያንን በሰይፍ እያወደመና ምድራዊ የጽድቅ መንግሥት በኃይል እየመሠረተ በቁጣ እንዲገለጥ በሥጋ ቢፈልጉም፥ ክርስቶስ ግን መጀመሪያ ወደ ምድር የመጣው በታላቅ ትሕትና፥ በየዋህነትና በሰላም መንፈስ መሆኑን ለማሳየት መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በላዩ አረፈ (ማቴ. 11፡29)። ፫. እግዚአብሔር አብ ከሰማይ በድምፅ መሰከረ በዚህ ታላቅ መለኮታዊ ሥራ ውስጥ እግዚአብሔር አብም ከሰማያት በቀጥታ በከበረ ድምፅ በመናገር ታላቅ ተሳትፎ አድርጓል። ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ እግዚአብሔር አብ ከሰማይ ታላቅ ድምፅ በማውጣት፦ «በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው» በማለት ኢየሱስ የእርሱ አንድያ መለኮታዊ ልጅ መሆኑን ለዓለም ሁሉ በይፋ መሰከረ (ማቴ. 3፡17)። ይህ ታላቁ የአብ መለኮታዊ ቃል በብሉይ ኪዳን ስለ መሢሑ ንጉሥነት የተነገሩትን መዝሙረ ዳዊት 2፡7ን እና ስለ ታማኙ አገልጋይ የተነገረውን የትንቢተ ኢሳይያስ 42፡1ን ቃል ፍጹም አድርጎ በአንድነት ያንጸባረቀ ነበረ። እግዚአብሔር አብ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ቅዱስ ባሕርይ፥ ታዛዥነትና ማዳን ተግባራት ላይ ሙሉ በሙሉ ደስ ተሰኝቶ ነበር። ክርስቶስ በምድር ላይ የሰው ልጆች ሁሉ ሊከተሉት የሚገባ ብቸኛው ፍጹም ሰው ነበረ። ይህ ክስተት እግዚአብሔር አብ በሰማይ ሆኖ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ማንነት ላይ ደስ መሰኘቱን በሰው ጆሮ በይፋ ከመሰከረባቸው ሦስት ታላላቅ የታሪክ አጋጣሚዎች መካከል መጀመሪያው ነበር (ቀሪዎቹ ሁለቱ በተራራው ላይ በተለወጠ ጊዜ – ማቴ. 17፡5 እና ከመሰቀሉ በፊት በኢየሩሳሌም – ዮሐ. 12፡28 ናቸው)። 👥 የውይይት ጥያቄ እና የሥላሴ አስተምህሮ መከላከያ ፪. የውይይት ጥያቄ፦ በእኛ በዳግም በተወለድን አማኞች በጴንጤቆስጤ (በወንጌላውያን) እምነት ሥርዓት መሠረት፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ዋነኛውና የማይናወጠው መሠረት የቅዱስ ሥላሴ (The Holy Trinity) አስተምህሮ ነው። እግዚአብሔር በአንድ መለኮታዊ ባሕርይ (ተፈጥሮ) ያለ አንድ እውነተኛ አምላክ ነው፤ ነገር ግን በዚህ በአንድ መለኮት ውስጥ እርስ በርስ ፍጹም የሚዋደዱና የማይቀላቀሉ ሦስት የተለያዩ ዘላለማውያን አካላት (አብ፥ ወልድና መንፈስ ቅዱስ) አሉ። የ«ኢየሱስ ብቻ» (Modalism / Sabellianism) ተከታዮች ግን ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ሙሉ በሙሉ በመካድ፥ «እግዚአብሔር አንድ አካል ብቻ ነው፤ ስሞቹ ግን የተለያዩ ናቸው» እያሉ ትልቅ የክህደት ትምህርት ያስተምራሉ። የማቴዎስ ወንጌል 3፡16-17 ያለው የክርስቶስ ጥምቀት ታሪክ ግን፥ ይህንን የ«ኢየሱስ ብቻ» ወገኖች የሚያስተምሩትን ስሕተት ሙሉ በሙሉ የሚያፈርስና በአንድ የታሪክ ቅጽበት ሦስቱም የሥላሴ አካላት በተለያዩ መገለጫዎችና በተለያዩ ስፍራዎች በአንድ ጊዜ በተግባር መኖራቸውን የሚያረጋግጥ ታላቅ መለኮታዊ ሰይፍ ነው፦ ስለሆነም የ«ኢየሱስ ብቻ» እምነት ተከታዮችን በወንጌል ፍቅር ቀርበን ከስሕተታቸው ለመመለስ ስንወያይ፥ ይህንን ጥቅስ መነሻ በማድረግ እንዲህ ብለን በጥበብ ልንጠይቃቸው ይገባል፦ «በዮርዳኖስ ወንዝ ጥምቀት ሰዓት በወንዙ ውስጥ የነበረው ኢየሱስ፥ ከሰማይ የወረደው መንፈስ ቅዱስና ከሰማይ የተናገረው አብ ሦስት የተለያዩ አካላት በተግባር በአንድ ጊዜ ካልሆኑ፥ ታዲያ በወንዙ ውስጥ ያለው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ራሱ ሮጦ ሄዶ ድምፅ እያወጣ ደግሞ በርግብ አምሳል እየወረደ ራሱን እያታለለ ነበርን?»። ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐቅ በጥንቃቄ ሲብራራላቸው፥ አእምሯቸው ተከፍቶ የእግዚአብሔርን ቃል እውነትና የሥላሴን ዘላለማዊ ክብር አምነው ከተሳቱበት የኑፋቄ ጨለማ ወደ ወንጌል ብርሃን እንዲመለሱ ታላቅ መንፈሳዊ መሠረት ይሆንላቸዋል። ምንጭ፦ «የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ»፣ በኤስ.አይ.ኤም (SIM) ጽሑፍ ክፍል የታተመና የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው። ለዚህ አስደናቂና ለቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ለሚሆን ታላቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር አምላክ ዘመናቸውንና አገልግሎታቸውን አብዝቶ ይባርክ።

የኢየሱስ መጠመቅ (ማቴ. 3፡13-17) Read More »

የመጥምቁ ዮሐንስ ስብከት (ማቴ. 3፡1-12)

ሐዋርያው ማቴዎስ በወንጌሉ ላይ የክርስቶስን ታሪክ የቀጠለው ከልደቱ ታሪክ በኃላ ከሰላሳ ዓመታት ጸጥታ ወዲህ ነበር። ማቴዎስ የክርስቶስን ይፋዊ መለኮታዊ አገልግሎት ከመዘገቡ በፊት፥ ከክርስቶስ ቀድሞ መጥቶ ሰዎችን ለእውነተኛ እምነትና ለንስሐ ስለሚያዘጋጀው ታላቅ ነቢይ በአጭሩ በመግለጽ ይጀምራል (ማቴ. ምዕ. 3)። ከዚያም ክርስቶስ የእግዚአብሔር አዳኝና ሊቀ-ካህናት ሆኖ አገልግሎቱን እንዲጀምር ያዘጋጁትን ሁለት ታላላቅ መለኮታዊ ክስተቶች (የጌታን ጥምቀትና የገደል ፈተናን) በሥርዓት አስፍሯል። በብሉይ ኪዳን ትንቢት ውስጥ እግዚአብሔር ከመሢሑ መምጣት አስቀድሞ ታላቅ መንገድ ጠራጊ ነቢይ ወደ እስራኤል እንደሚላክ ለአይሁድ ሕዝብ በግልጽ ነግሯቸው ነበር (ኢሳ. 40:3)። የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው የእግዚአብሔር ነቢይ የሆነው ሚልክያስ ይህንን መንገድ ጠራጊ ነቢይ «ነቢዩ ኤልያስ» ብሎ በትንቢት ጠርቶታል (ሚልክ. 4፡5)። ይህም ያ አዲስ ነቢይ ከጥንቱ ከኤልያስ ጋር ፍጹም በሚመሳሰል በታላቅ መንፈሳዊ ኃይል፥ ቅንዓትና የአኗኗር ዘይቤ እንደሚመጣ የሚያሳይ ነበር። ከነቢዩ ሚልክያስ ዕረፍት ጀምሮ እስከ መጥምቁ ዮሐንስ መነሳት ድረስ ለ 400 የዝምታ ዓመታት እግዚአብሔር በነቢያት በኩል ለሕዝቡ ምንም ዓይነት አዲስ መለኮታዊ ቃል አልተናገረም ነበር፤ በመንፈስ ቅዱስ የተመራ አንድም ነቢይ በእስራኤል ምድር አልተነሳም ነበር። ከዚህ ረጅምና አስፈሪ የዝምታ ዘመን በኋላ ግን፥ አንድ ዐይን የማይገባ (ከግመል ጠጉር የተሠራ) ግዙፍ ልብስ የለበሰና በወገቡ የቆዳ ቀበቶ የታጠቀ ድንቅ ሰው ከይሁዳ በረሃ ተነስቶ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ አቅራቢያ በመጣ ጊዜ ያ 400 ዓመታት የዝምታ መርገም ሙሉ በሙሉ አበቃ። ይህ መጥምቁ ዮሐንስ በምድረ-በዳ የነበረው የአኗኗር ባሕርይ፥ የቆዳ ልብስ መልበሱና አንበጣና የበረሃ ማር መመገቡ—የብሉይ ኪዳን ነቢያት አባትና ምሳሌ የሆነውን ነቢዩ ኤልያስን ፍጹም ለመምሰልና ትንቢቱን ለመፈጸም የተደረገ መለኮታዊ ዝግጅት ነበር (2ኛ ነገ. 1፡8)። የእርሱ ስም ዮሐንስ ሲሆን፥ ልዩ መለኮታዊ መጠሪያውም «መጥምቁ» የሚል ነበር፤ ይህም ሰዎች ኃጢአታቸውን ተናዝዘው ሕይወታቸውን ሙሉ በሙሉ እንዲለውጡና ለመሢሑ በተዘጋጀ ቅዱስ ልብ ለመኖር መወሰናቸውን በምልክት ለማሳየት ሰዎችን ሁሉ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ለጥምቀት በመጥራቱ ምክንያት የተሰጠው ስም ነበር። 1. መጽሐፍ ቅዱሳዊ የንስሐ እውነተኛ ትርጉም መጥምቁ ዮሐንስ በይሁዳ ምድረ-በዳ እያወጀ ያስተላለፈው ዋና መልእክት፦ «የሰማይ መንግሥት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ!» የሚል እጅግ ቀላልና ጥብቅ መልእክት ነበር (ማቴ. 3፡2)። በአሁኑ ዘመን በብዙዎች ዘንድ ንስሐ መግባት ማለት፥ እንዲሁ ለፈጸምነው ስሕተትና በደል በሥጋ መጸጸት ወይም ማልቀስ ብቻ ይመስለናል። ነገር ግን በአዲስ ኪዳን የተጻፈበት የግሪኩ ቃል «ሜታኖያ» (Metanoia) ትርጉም ከዚህ እጅግ የጠለቀና የሚከተሉትን 2 ታላላቅ መለኮታዊ ነጥቦችን በጥንቃቄ ያካተተ ነው፦ ሀ. ዝርዝር ኃጢአትን ለእግዚአብሔር መናዘዝ እውነተኛ ንስሐ የሚጀምረው የፈጸምናቸውን ዝርዝር ድካሞችና እግዚአብሔርን ያልታዘዝናቸውን በደሎች በሙሉ ያለምንም ማመኻኛ በጥፋተኝነት አምኖ በመቀበል ነው። አብዛኛውን ጊዜ በምድር ላይ ይቅርታ ስንጠይቅ ሰዎችን ስለመበደላችን ብቻ እናስባለን እንጂ፥ የሠራነው ኃጢአት በሉዓላዊው ፈጣሪ በእግዚአብሔር ላይ የተደረገ ታላቅ ዓመፅ መሆኑን በልባችን እምብዛም አናስተውልም። ዳዊት በበደሉ ጊዜ የጸለየው ታላቅ ጸሎት፦ «አንተን ብቻ በደልሁ፥ በፊቶችህም ክፉ ነገርን አደረግሁ» የሚል ነበር (መዝ. 51፡4)። እያንዳንዱ ኃጢአት በመሠረቱ በእግዚአብሔር ቅድስና ላይ የሚደረግ ዓመፅ መሆኑን እስካልተረዳን ድረስ፥ ኑዛዜያችን ላይ ላዩን የደረቀ ሥርዓት ብቻ ስለሚሆን በደሉን ደግመን ከመሥራት ፈጽሞ አንለወጥም። ፩. የውይይት ጥያቄ፦ ለ. ጠቅላላ የአኗኗር አቅጣጫን መለወጥ (ሜታኖያ) እውነተኛ ንስሐ የፈጸምነውን ድንገተኛ መጥፎ ድርጊት መጸጸት ብቻ ሳይሆን፥ ጠቅላላ የተሳሳተ የአኗኗር መንገዳችንን ሙሉ በሙሉ የሚቀይር ጽኑ የልብ ቁርጥ ውሳኔን በውስጡ ያጠቃልላል። የግሪኩ ቃል «ሜታኖያ» የሚያስተላልፈው እውነተኛ አሳብ፦ ወደ አንድ የተሳሳተ የዓለም አቅጣጫ ቁልቁል በፍጥነት ይሄድ የነበረ ሰው፥ የቃሉን ድምፅ ሰምቶ አእምሮውንና ሃሳቡን በመቀየር ፊቱን 180 ዲግሪ ሙሉ በሙሉ አዙሮ፥ በተቃራኒው አቅጣጫ ፊቱን ወደ እግዚአብሔር አድርጎ በቅድስና መጓዝ መጀመሩን ያሳያል። ስለዚህ በዕለታዊ ባህሪ ላይ ፍጹም የተግባርና የፍቅር ለውጥ የሌለበት ለቅሶ—በመጽሐፍ ቅዱስ ሚዛን እውነተኛ ንስሐ ተብሎ ፈጽሞ ሊጠራ አይችልም። የአይሁድ የሃይማኖት መሪዎች (ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን) የልባቸውን ክፉ ባህሪና ትዕቢት ሳይለውጡ፥ እንዲሁ በሰዎች ፊት ለመታየት ብቻ ውጫዊ የጥምቀትን ሥርዓት ለመፈጸም ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ በመጡ ጊዜ፥ መጥምቁ ዮሐንስ በታላቅ የነቢይ ቅንዓት እንዲህ ሲል በኃይል ገሠጻቸው፦ «እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቁጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ? እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ።» (ማቴ. 3፡7-8)። ዮሐንስ በግልጽ እንደነገራቸው በስም ሃይማኖተኛ መሆን፥ ወይም በሥጋ ከትክክለኛው የተቀደሰ ነገድ ወገን መሆን (የአብርሃም ልጆች ነን ማለት) ብቻውን ከቅዱሱ እግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ የኅብረት ግንኙነት እንዲኖራቸው ፈጽሞ አያደርጋቸውም፤ የልብ ለውጥና የባህርይ ፍሬ የግድ ያስፈልጋል። ፪. የውይይት ጥያቄ፦ 2. የመጥምቁ ዮሐንስ ጥምቀት እና የክርስቲያን ጥምቀት ንጽጽር ነቢዩ ዮሐንስ ከልባቸው ለተለወጡና ለመሢሑ መምጣት ራሳቸውን በቅድስና ለሚያዘጋጁት ሰዎች ሁሉ የንስሐ ጥምቀትን በውኃ ያጠምቅ ነበር። የነገረ-መለኮት ምሁራን ዮሐንስ የጥምቀትን ሥርዓት ከየት እንዳመጣው ታሪካዊ መነሻውን ሲመረምሩ፥ ጥምቀት በአይሁድ ታሪክ ቀድሞ በሁለት ታዋቂ መንገዶች የተለመደ ሥርዓት እንደነበረ ያስተምራሉ፦ በመጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎት የነበረው ጥምቀት 2 ታላላቅ ዐበይት ዓላማዎች ነበሩት፦ ፫. የውይይት ጥያቄ፦ በጥንቱ ዘመን የነበረው ያ የመጥምቁ ዮሐንስ የአይሁድ የጥምቀት ግንዛቤና ዓላማ፥ ዛሬ እኛ በአዲስ ኪዳን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከምንፈጽመው ከክርስቲያን ጥምቀት መለኮታዊ ትርጉም ጋር የሚመሳሰለው ወይም የሚለያየው በምን መንገዶች ነው? ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ከተነሳ በኋላ፥ የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን የጌታን ታላቅ ትእዛዝ መሠረት በማድረግ የክርስቲያን ጥምቀትን በታላቅ ክብር ማካሄድ ጀመረች (ማቴ. 28፡19)። በአዲስ ኪዳን የክርስቲያን ጥምቀት ከዮሐንስ ጥምቀት እጅግ የላቀ መንፈሳዊ ምስጢር አለው፦ 3. “የሰማይ መንግሥት” መለኮታዊ ፅንሰ-አሳብ መጥምቁ ዮሐንስ በበረሃ ሆኖ ታላቁ «መንግሥተ-ሰማይ» (የሰማይ መንግሥት) መቅረቧን በኃይል አውጇል። ቀደም ሲል በሰፊው እንደተመለከትነው፥ በሐዋርያው ማቴዎስ ወንጌል ውስጥ 33 ጊዜ ያህል የተጠቀሰው ይህ «የሰማይ መንግሥት» የሚለው ቁልፍ ሐረግ—ማቴዎስ ወንጌሉን መጀመሪያ ለአይሁድ ወገኖች እንደጻፈ የሚያሳይ ታላቅ መለኮታዊ ማስረጃ ነው። ምክንያቱም አይሁድ የእግዚአብሔርን (የይሖዋን) ቅዱስ ስም ያለ አግባብ በቀጥታ ለመጥራት እጅግ ስለሚፈሩ (ዘፀ. 20፡7)፥ የፈጣሪን ስም በሰማይ ተክተው «የሰማይ አምላክ» ወይም «የሰማይ መንግሥት» ማለትን ባህል አድርገውት ነበር (ነህ. 1፡4)። ስለዚህ «የሰማይ መንግሥት» እና ማርቆስና ሉቃስ ለአሕዛብ የጻፉት «የእግዚአብሔር መንግሥት» ፍጹም አንድ ዓይነት ትርጉም ያላቸው መለኮታዊ ቃላት ናቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት መሠረት፥ «መንግሥት» (በግሪክ Basileia) የሚለው ቃል መጀመሪያ የሚያመለክተው በካርታ ላይ የሚገኝን የተወሰነ ምድራዊ መልክዐ-ምድራዊ አካባቢን ወይም ድንበርን ፈጽሞ አይደለም። ይልቁኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉሙ፦ «ሉዓላዊ ኃይል፥ መለኮታዊ ሥልጣንና የአገዛዝ የበላይነትን» ብቻ ነው የሚያሳየው። 4. የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት እና የእሳት ጥምቀት ምስጢር ነቢዩ መጥምቁ ዮሐንስ እግዚአብሔር ታሪክን የሚያካሂድበትን አጠቃላይ የጊዜ ሰሌዳ (በክርስቶስ መጀመሪያ ምጽአትና በዳግም ምጽአቱ መካከል ያለውን ሰፊ የቤተ ክርስቲያን ዘመን ክፍተት) መጀመሪያ ላይ ሙሉ በሙሉ አልተረዳውም ነበር (ማቴ. 11፡2-6)። ዮሐንስ የጠበቀው መሢሑ ወዲያውኑ መጥቶ አሕዛብንና ክፉዎችን በእሳት አጥፍቶ ምድራዊውን የዳዊት መንግሥት የሚመሠርት መስሎት ነበር፤ ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መጀመሪያ የመጣው በትሕትና ሰዎችን ከኃጢአት ለማዳን የመጣ መንፈሳዊ ንጉሥ ሆኖ ነበር። መጥምቁ ዮሐንስ ራሱን ሁልጊዜ ከፍ ከፍ ከማድረግ ተቆጥቦ፥ እርሱ ከእርሱ በኋላ ለሚመጣውና ከእርሱ እጅግ ለሚበልጠው ለታላቁ መሢሕ መንገድ የሚያዘጋጅ ትሑት ባሪያ መሆኑን በሚገባ ያውቅ ነበር (ማቴ. 3:11)። ዮሐንስ ወደ መሢሑ ጌትነት በማመልከት ክርስቶስ ለዓለም የሚያበረክታቸውን 2 ታላላቅ መለኮታዊ አገልግሎቶች ለሕዝቡ እንዲህ ሲል በይፋ አበሰረ፦ 👥 የውይይት ጥያቄ እና ተግባራዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልስ ፬. የውይይት ጥያቄ፦ የመጥምቁ ዮሐንስ ሕይወት ዛሬ በ 2026 ዓ.ም. ላለንበት የወንጌል አገልግሎት 3 ታላላቅ መለኮታዊ ምሳሌዎችን ይሰጠናል፦ ምንጭ፦ «የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ»፣ በኤስ.አይ.ኤም (SIM) ጽሑፍ ክፍል የታተመና የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው። ለዚህ አስደናቂና ለቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ለሚሆን ታላቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር አምላክ ዘመናቸውንና አገልግሎታቸውን አብዝቶ ይባርክ።

የመጥምቁ ዮሐንስ ስብከት (ማቴ. 3፡1-12) Read More »

የንጉሡ የኢየሱስ ልደት (ማቴ. 1፡18-2፡23)

በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ የክርስቶስን መለኮታዊ ልደት በዝርዝር የሚገልጹት ወንጌላት ሁለት ብቻ ናቸው፤ እነርሱም የማቴዎስና የሉቃስ ወንጌል ናቸው። ከእነዚህ ከሁለቱ መካከል፥ ሐኪሙ ሉቃስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር የቅርብ ውይይት በማድረግ ስለ ክርስቶስ ልደት እጅግ ሰፊ መለኮታዊ ምርምር አካሂዷል (ሉቃስ 1፡1-4)። ይሁን እንጂ በይዘት ረገድ ትልቅ ልዩነት አላቸው፦ ታላቁ የክርስቶስ ልደት የሆነው ዮሴፍና ማርያም በሕግ ተጫጭተው (ታጭተው) በነበሩበት ወቅት ነበር። በጥንቷ እስራኤል ባህልና ሥርዓት መሠረት፥ የአይሁድ መተጫጨት ልክ እንደ ዛሬዋ አገራችን እንደ ኢትዮጵያ ባህላዊ ሥርዓት ሁሉ እጅግ ከፍተኛ ማኅበራዊና ሕጋዊ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነበር። አይሁዶች ከተጫጩ በኋላ ባልና ሚስት እንደሆኑ ተቆጥረው በአንድ ቤት አብረው መኖር ከመጀመራቸው በፊት ለአንድ ዓመት ያህል በትዕግሥት ይጠብቁ ነበር። ይህ ጽኑ የቃል ኪዳን መተጫጨት በዝሙት ምክንያት ሊፈርስ የሚችለው በሕጋዊ የፍቺ ጽሕፈት ብቻ ነበር (ዘዳግ. 22:23-24)። በትክክል በዚህ በተቀደሰው መተጫጨት ወቅት ማርያም ከዮሴፍ ጋር ሳትገናኝ በፊት፥ ሳይታሰብ «በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች» (ማቴ. 1፡18)። 👥 የውይይት ጥያቄ እና ተግባራዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልስ ፩. የውይይት ጥያቄ፦ ቅድስት ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ስለደረሰላት ታላቅ መለኮታዊ ብስራትና ስለ ፅንሰቷ ምስጢር (ሉቃስ 1:35) ለእጮኛዋ ለዮሴፍ በቅንነት በቃላት ገልጻለት ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን በማቴዎስ ጽሑፍ ውስጥ ስለዚህ ጉዳይ በቀጥታ የተጠቀሰ ነገር የለም። ይሁን እንጂ ዮሴፍ ማርያም ማርገዟን በምልክት በሆነ መንገድ ደርሶበት እንደነበረ ግልጽ ነው። ዮሴፍ የእግዚአብሔርን ሕግ የሚወድ እውነተኛ ጻድቅና የዋህ ሰው ስለነበረ፥ ማርያም ከሌላ ወንድ ጋር በበደል የወደቀች መስሎት በይፋ አውጥቶ በሕዝብ ፊት ሊወቅሳት፥ ሊያዋርዳትና በሕጉ መሠረት በድንጋይ ተወግራ እንድትሞት ፈጽሞ አልፈለገም (ዘዳግ. 22:22)። ስለሆነም ለእርሷም ሆነ ለማኅበረሰቡ ሳይናገር በስውር የፍቺ ጽሕፈት ሰጥቶ ሊተዋት በልቡ በጥንቃቄ አሰበ (ማቴ. 1፡19)። ጻድቁ ዮሴፍ በዚህ ከባድ የልብ ውሳኔና ኀዘን ውስጥ እያለ፥ እግዚአብሔር ግን ማርያም ከሌላ ሰው ጋር በዝሙት እንዳልረከሰችና በትክክልም ከመንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ኃይል በተአምር እንደፀነሰች ለዮሴፍ እውነትን ለመግለጥ በሌሊት በሕልም ቅዱስ መልአኩን ላከለት (ማቴ. 1፡20)። ምንም እንኳን ማርያም በሰፈሩ ሰዎች ዘንድ በማርገዟ ምክንያት ብትናቅና በተለያየ ስላቅ ቢቀልዱባትም፥ ዮሴፍ ግን የእግዚአብሔርን ቃል በፍርሃት ታዞ ማርያምን በክብር ወደ ቤቱ ወሰዳት። የኢየሱስ ስምና የአማኑኤል ትንቢት ፍጻሜ እግዚአብሔር በዚህ መሲሑን ወደ ምድር የመላክ ታላቅ የድነት ሂደት ውስጥ ማርያምን ብቻ ሳይሆን፥ ጻድቁን ዮሴፍንም እጅግ አክብሮታል። በአይሁድ ሥርዓት እንደ እውነተኛ ባልና የቤት ራስ ሁሉ፥ እግዚአብሔር አባት ዮሴፍ ለሚወለደው ሕፃን መለኮታዊ ስም የማውጣት ሕጋዊ መብትን በይፋ ሰጠው። ለክርስቶስ ስም በማውጣቱ አማካይነት፥ ዮሴፍ የሕፃኑን የዳዊት ወራሽነት ሕጋዊ አባትነቱን በታሪክ እያረጋገጠ ነበር። እግዚአብሔር ዮሴፍ ሕፃኑን «ኢያሱ» (በዕብራይስጥ ቋንቋ Yeshua) ወይም ወደ ግሪክ ሲተረጎም «ኢየሱስ» (Iesous) ብሎ እንዲጠራው በቅንነት ነገረው። የዚህ ታላቅ ስም ትርጉም በምስጢር፦ «ይሖዋ (እግዚአብሔር) መድኃኒት ነው» ወይም «እግዚአብሔር ድኅንነት ነው» ማለት ነው (ማቴ. 1፡21)። ይህ መለኮታዊ ስም የሚያበሥረው፦ የመሲሑ ቀዳሚና ዋና ተግባር በምድር ላይ በሰይፍ የሚዋጋ ምድራዊ ድል ነሺ ንጉሥ መሆን ሳይሆን፥ ሰዎችን ከኃጢአት ባርነት የሚያድን ሰማያዊ አዳኝ መሆኑን ነው። ክርስቶስ «ሕዝቡን ከኃጢአታቸው የሚያድን» እውነተኛ መንፈሳዊ አዳኝ እንጂ፥ አይሁድ እንደጠበቁት የሮምን ቀንበር የሚሰብር ምድራዊ ፖለቲካዊ ነፃ አውጪ እንዳልሆነ ማቴዎስ በስሙ ትርጉም በግልጽ አስምሮበታል። ማቴዎስ የድንግሊቱ በተአምር መውለድና የክርስቶስ የልደት ዝርዝር ጉዳዮች ሁሉ፥ በአጋጣሚ የተከሰቱ ሳይሆኑ በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ጥበብ በጥንቃቄ የታቀዱና በብሉይ ኪዳን በነቢዩ በኢሳይያስ የተነገሩ ታላላቅ ትንቢቶች ፍጻሜ መሆናቸውን አስረድቷል። ማርያም በሚያስደንቅ መለኮታዊ መንገድ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ በመውለዷ ምክንያት፥ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድ አካል ፍጹም ሰውና ፍጹም አምላክ ሆኖ ተገልጧል። በዚህም ምክንያት እርሱ ብቻ እውነተኛው «አማኑኤል» — ትርጉሙም «እግዚአብሔር ከእኛ ጋር» የሆነው መለኮታዊ አምላክ ነው (ኢሳ. 7፡14)። በጥንቱ በብሉይ ኪዳን ዘመን እግዚአብሔር የክብር ደመናውን (የሸኪና ክብርን) በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በሰዎች መካከል ያኖረ ሲሆን፥ አሁን በአዲስ ኪዳን ግን እግዚአብሔር ራሱ ፍጹም ሥጋ ለብሶ በሰዎች መካከል በታሪክ አድሯል (ዮሐ. 1፡14)። ክርስቶስ የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ወደ ሰማይ ከመመለሱ በፊት፥ ለቅዱሳን ደቀ-መዛሙርቱ አሁንም ሁልጊዜ አማኑኤል ሆኖ እንደሚቀጥል፥ ማለትም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከእነርሱ ጋር አብሮ እንደሚኖር በታላቅ ቃል ኪዳን አረጋግጦላቸዋል (ማቴ. 28፡20)። የአሕዛብ ሰብአ ሰገል (Magi) አምልኮ ማቴዎስ ወንጌሉን ለአይሁድ ሲጽፍ፥ እግዚአብሔር ለአይሁድ ብቻ ሳይሆን ለአሕዛብም ታላቅ የማዳን ዕቅድ እንዳለው በተግባር አመልክቷል። ለዚህም ትልቅ ማረጋገጫው በታሪክ መጀመሪያ ጊዜ ሕፃኑን ክርስቶስን በኢየሩሳሌም መጥተው ያከበሩትና በፊቱ ወድቀው ያመለኩት ከሩቅ አገር የመጡት አሕዛብ ሰብአ ሰገል መሆናቸውን በክብር ገልጿል (ማቴ. ምዕ. 2)። ማቴዎስ እነዚህ ሰብአ ሰገል ከየትኛው አገር በትክክል እንደመጡ ወይም በቁጥር ስንት እንደሆኑ በወንጌሉ ውስጥ አልጠቀሰም። በጥንታዊው የቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ሦስት ሰዎች እንደሆኑ የሚታመነው፥ ለሕፃኑ ካበረከቷቸው ከሦስቱ ታላላቅ መለኮታዊ ስጦታዎች (ከወርቅ፥ ዕጣንና ከከርቤ) በመነሳት ነው። ለእነዚህ ሰዎች በጥንቱ የግሪክ ጽሑፍ የተሰጣቸው ስም «ማጂ» (Magi) የሚል ነው። ማጂ በጥንቱ መካከለኛ ምሥራቅ የነበሩ የከዋክብት ተመራማሪዎች፥ የንጉሥ አማካሪዎችና የልዩ ምስጢራዊ ዕውቀት ሰዎች ማኅበር ሲሆን፥ ብዙ የታሪክ ምሁራን እነዚህ ወገኖች የመጡት ከታላቂቱ ከፋርስ (ከኢራን) ወይም ከሳውዲ ዓረቢያ ምድር እንደነበረ በታሪክ ይናገራሉ። እነዚህ ሰዎች ምንም እንኳ በአሕዛብ ምድር በከዋክብት ጥናት ቢታገሉም፥ በዚያ በምርኮ ዘመን በዳንኤል ትንቢት በኩል የተላለፈውን ስለ መሢሑ ንጉሥ መነሳት የሚናገረውን መለኮታዊ ግንዛቤ በሚገባ ያውቁት ነበር (ዳን. 9:24-26)። ስለሆነም በሰማይ ያዩት ያ አዲስ ድንቅ መለኮታዊ ኮከብ ለአይሁድ ሕዝብ ልዩ የዘላለም ንጉሥ እንደተወለደ የሚያመለክት መሆኑን በመንፈስ አስተዋሉ፤ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው በፊቱ የመስገዳቸውና የማምለካቸው ታላቅ ተግባር ደግሞ፥ ይህ የተወለደው ሕፃን ከተራ ምድራዊ ነገሥታት ሁሉ በላይ ፍጹም መለኮታዊ ሥልጣን ያለው አምላክ መሆኑን በልባቸው እንደተገነዘቡ ያሳያል። እነርሱም የአይሁድ ታሪካዊት መዲና ወደሆነችው ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ እስኪደርሱ ድረስ፥ ለብዙ ወራት ያንን መለኮታዊ ኮከብ በታማኝነት እየተከተሉ በበረሃ ተጓዙ። የንጉሥ ሄሮድስ ቁጣና የሃይማኖት መሪዎች ድንዛዜ ሰብአ ሰገል ወደ ኢየሩሳሌም በገቡ ጊዜ፥ «የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ በቤተ መንግሥት ውስጥ ይገኛል» ብለው ስለገመቱ፥ ቀጥታ ወደ ንጉሥ ሄሮድስ ቤተ መንግሥት በመሄድ አዲስ ስለተወለደው ንጉሥ በጥያቄ አወቁ። ቀደም ሲል የገዛ ዙፋኔን ይነጥቁኛል በሚል ክፉ የሥልጣን ፍርሃትና ጥርጣሬ ምክንያት፥ የገዛ አጎቱን፥ ሚስቱንና የገዛ ልጆቹን ጭምር በጭካኔ የፈጀው ያ አሮጌው ንጉሥ ሄሮድስ፥ ይህንን የአዲስ ንጉሥ መወለድ የምሥራች ከሰብአ ሰገል በአፉ በሰማ ጊዜ በከፍተኛ ድንጋጤና ስጋት ተናወጠ (ማቴ. 2:3)። ንጉሥ ሄሮድስ ይህንን መለኮታዊ ምስጢር ለማወቅ ሲል፥ ወዲያውኑ የአይሁድን የሃይማኖት መሪዎች፥ የሕግ መምህራንን (ጸሐፍትን) እና ከፍተኛ ካህናትን በአንድነት ሰበሰበ። እነዚህ የሃይማኖት መሪዎች መጽሐፍ ቅዱስን (ኦሪትን) ጠንቅቀው የሚያውቁ ሊቃውንት ስለነበሩ፥ በነቢዩ በሚክያስ ትንቢት መሠረት (ሚክ. 5:2) መሢሑ የሚወለደው ከኢየሩሳሌም ሰባት ኪሎ ሜትር አጭር ርቀት ላይ ወጣ ብላ በምትገኘው በትንሿ በይሁዳ ቤተልሔም ከተማ መሆኑን ጥቅሱን መዝዘው ወዲያውኑ ለንጉሡ ነገሩት። የመሪዎቹ አስገራሚ ድንዛዜ፦ እዚህ ላይ እጅግ ሊታሰብበት የሚገባው ታላቅ መንፈሳዊ ምስጢር አለ፦ እነዚህ የአይሁድ የሃይማኖት መሪዎች መሢሑ የት እንደሚወለድ ቃሉን በሚገባ ቢያውቁም፥ ከሩቅ አገር መጥተው የሕፃኑን መወለድ ከሚናገሩት ከሰብአ ሰገል ጋር አብረው ግንኙነት ለማድረግና ሕፃኑን መሢሕ በዓይናቸው ለማየትና ለመስገድ ግን ሰባ ኪሎ ሜትር እንኳ ለመጓዝ ልባቸው ፍጹም አልተንቀሳቀሰም ነበር! እነርሱ በደረቀ ቃላቸውና በሃይማኖታዊ ዕውቀታቸው ብቻ በትዕቢት ተሞልተው በቤታቸው ተቀመጡ። ንጉሥ ሄሮድስም የሕፃኑን ትክክለኛ ቦታ መለኮታዊ ትንቢት ካረጋገጠ በኋላ፥ ሰብአ ሰገል ሄደው ሕፃኑን ካገኙት በኋላ መጥተው እንዲነግሩት በምስጢር አዘዛቸው፤ ምንም እንኳ ሄሮድስ «እኔም መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ» ብሎ በውሸት ቢናገራቸውም፥ የልቡ እውነተኛ ፍላጎት ግን ያንን ሕፃን ንጉሥ ፈጥኖ መግደል ብቻ

የንጉሡ የኢየሱስ ልደት (ማቴ. 1፡18-2፡23) Read More »