ሌሎች ትምሕርቶች

የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ መተግበሪያ  (Amharic Bible Commentary App)

ከዚህ በታች ያለው የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ መተግበሪያን ማውረድ እና መጠቀም የሚችሉት የአንድሮይድ ሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች ብቻ መሆናቸውን አስቀድመን ማሳወቅ እንፈልጋለን፡፡ መተግበሪያውን በስልክዎ ላይ ለማውረድ የሚከተለውን ቅደም ተከተል ተግባራዊ ያድርጉ፡፡ በመጀመሪያ፣ ከዚሀ በታች ያለውን “የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ መተግበሪያውን ያውርዱ” የሚለውን ሊንክ ተጭነው ለአንድ ሰከንድ ይቆዩ፤ በመቀጠል ከቀረቡት አማራጮች መካከል “Download link ” የሚለውን በመምረጥ መተግበሪያውን ያውርዱ (download ያድርጉ)፤ ያወረዱትን መተግበሪያ ለመክፈት ሲሞክሩ፣ በቅድሚያ “Setting” ላይ በመሄድ ለመተግበሪያው የይለፍ ፈቃድ እንዲሰጡ ይጠየቃሉ፡፡ ይህን ለማድረግ “Setting” የሚለውን በመጫን “Allow from this source” የሚለውን ይምረጡ፡፡ ይህን ሲያደርጉ “Installing apps from this source may put your phone and data at rick.” የሚል መልእክት የሚመጣ ቢሆንም፣ ወደኋላ በመመለስ ሳይሰጉ መተገበሪያውን ይጫኑ፡፡ መተግበሪያውን ከጫኑ በኋላ ለአጠቃቀሙ ከዚህ በታች የቀረበውን ባብራሪያ ይመልከቱ፡፡ መልካም ጥናት!!! በምስሉ ራስጌ በቢጫ ቀለም የተከበበበትን ስፍራ አንዴ በመጫን የ66ቱን ቅዱሳት መጻሕፍት ዝርዝር ማግኘት ይችላሉ፡፡ በምስሉ ግርጌ በቀይ የተከበበውን አካባቢ በመጫን ደግሞ የመጽሐፉን ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡ጽሑፉን ማጋራትን ጨምሮ ሌሎች አማራጮችን ለማግኝት በሰማያዊ የተከበበውን ስፍራ አንዴ ይጫኑ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ መተግበሪያ (Amharic Bible Commentary App)

የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ መተግበሪያ  (Amharic Bible Commentary App) Read More »

ስለ ኢየሱስ ሰምተው የማያውቁ ሰዎች ምን ይሆናሉ?

ሰዎች ስለ ክርስቶስ “ሰሙም አልሰሙም” በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂዎች ይሆናሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ፣ እግዚአብሔር ራሱን በፍጥረቱ (ሮሜ 1፡20) እና በሰዎች ልብ ውስጥ (መክብብ 3፡11) እንደገለጠ ይናገራል፡፡ ችግሩ ያለው የሰው ዘር ኃጢአተኛ በመሆኑ ምክንያት ይህን መገለጥ ወደጎን በመግፋት በእግዚአብሔር ላይ ማመጹ ላይ ነው (ሮሜ 1፡21-23)፡፡ እንደ እግዚአብሔር ፀጋ ባይሆን ኖሮ፣ ሁላችን ለልባችን ክፉ ምኞት ተላልፈን በመሰጠት ያለ እሱ ሕይወት ምንኛ እርባናቢስ እና አስከፊ መሆኗን እናውቅ ነበር፡፡ ያለማቋረጥ ጀርባቸውን በሚሰጡት ሁሉ ላይ ግን እግዚአብሔር ይህን ሕይወት እንዲጋፈጡ ይፈርዳባቸዋል (ሮሜ 1፡24-32)፡፡ የችግሩ እውነታ፣ እነዚህ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር አለመስማታቸው ሳይሆን የሰሙትን እና በፍጥረት ውስጥ ተገልጦ የሚታየውን እውነታ ለመቀበል አለመፍቀዳቸው ነው፡፡ ዘዳግም 4፡29፣ “…አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትሻላችሁ፤ በልብህም ሁሉ በነፍስህም ሁሉ የፈለግኸው እንደ ሆነ ታገኘዋለህ” ይላል፡፡ ይህ ጥቅስ አንድ ጠቃሚ መርሕ ያስተምራል – እግዚአብሔርን በእውነት የሚፈልግ ሁሉ ያገኘዋል። አንድ ሰው እግዚአብሔርን በእውነት ለማወቅ ከፈለገ እግዚአብሔር ራሱን ይገልጥለታል። ችግሩ፣ እግዚአብሔር አለመገለጡ ሳይሆን “…አስተዋይ” እና “እግዚአብሔርንም የሚፈልግ” ሰው አለመኖሩ ነው (ሮሜ 3፡11)፡፡ በርካታ ሰዎች በፍጥረት እና በልባቸው ውስጥ የሚገኘውን የእግዚአብሔርን እውቀት ወደጎን በማድረግ ራሳቸው የፈጠሩትን “አምላክ” ለማምለክ መርጠዋል፡፡ በመሆኑም፣ እግዚአብሔር፣ የክርስቶስን ወንጌል ለመስማት እድሉን ባላገኘው ሰው ላይ ሳይቀር ይፈርዳል፤ በዚህ ፍርድ ፍትሐዊነት ላይ መከራከር አመክኗዊነት የለውም፡፡ ሰዎች እግዚአብሔር አስቀድሞ በገለጠላቸው ነገር አንጻር በእርሱ ፊት ተጠያቂዎች ይሆናሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ ሰዎች ለዚህ መገለጥ (እውቀት) ጀርባቸውን እንደሰጡ ይናገራል፤ ስለሆነም እግዚአብሔር በእነሱ ላይ የሚያስተላልፈው የገሃነም ፍርድ ፍትሃዊ ይሆናል፡፡ ወንጌል ባልሰሙት ሰዎች ዕጣ ፈንታ ላይ ከመከራከር ይልቅ እኛ ክርስቲያኖች እነዚህ ሰዎች ወንጌል መስማታቸውን ለማረጋገጥ የተቻለንን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ወንጌልን ወደ አሕዛብ ሁሉ ለማዳረስ ተጠርተናል (ማቴዎስ 28፡19-20፤ ሐዋ 1፡8)፡፡ ሰዎች በፍጥረት ውስጥ ለተገለጠው የእግዚአብሔር እውቀት እንቢተኞች ሊሆኑ ይችላሉ፤ ይህ ሃቅ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ብቻ የሚገኘውን የመዳንን የምሥራች እንድናበስር ሊያነሳሳን ይገባል። ሰዎች ከኃጢአታቸው የሚድኑትና ዘላለማቸውን ከእግዚአብሄር ተነጥለው ከማሳለፍ የሚተርፉት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የእግዚአብሔርን ጸጋ በመቀበል ብቻ ነው፡፡ ወንጌልን በጭራሽ ሰምተው የማያቁ ሰዎች ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሳ እንዲሁ ይድናሉ ብለን የምናስብ ከሆነ ትልቅ ችግር ውስጥ ነን፡፡ ወንጌልን በጭራሽ ያልሰሙ ሰዎች ባለመስማታቸው ምክንያት እንዲያው የሚድኑ ከሆነ፣ እንግዳውስ ሰዎች ይድኑ ዘንድ ወንጌል እንዳይሰሙ ማድረግ ይኖርብናል የሚለው እሳቤ ምክንያታዊ ይሆናል፡፡ በዚህ እሳቤ መሰረት ወንጌል ሳንነግረው እንዲያው ይድን የነበረውን ሰው ወንጌል በመንገራችን እና እርሱም ይህን ወንጌል በመቃወሙ ምክንያት በፍርድ ስር እንዲወድቅ ማድረጋችን ትልቅ ጥፋት ይሆናል ማለት ነው፡፡ እውነታው፣ ወንጌልን ያልሰሙ ሰዎች በእግዚአብሔር ፍርድ ስር መሆናቸው ነው፡፡ አለበለዚያማ ወንጌል መስበካችን ምን ፋይዳ ይኖረዋል? ወንጌልን ባለመስማታቸው ምክንያት አስቀድሞዉኑ “ድነው” የነበሩትን ሰዎች ወንጌል ሰምተው እንዲቃወሙት በር በመክፈት እንዲጠፉስ ለምን እናደርጋለን?  ምንጭ፡- https://www.gotquestions.org/ ትርጉም፡- አዳነው ዲሮ ዳባ

ስለ ኢየሱስ ሰምተው የማያውቁ ሰዎች ምን ይሆናሉ? Read More »

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የመሙላት ተግባሩ

This entry is part 19 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ህ. የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ሲብራራ  ከመንፈስ ቅዱስ የማዳን ተግባራት፥ ማለት ዳግም ከመወለድ፥ በእማኝ ውስጥ ከማደር፥ ኮማተም እና ከማጥመቅ ሥራ ጋር ሲነጻጸር፥ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ከከርስቲያን ልምምድ፥ ኃያል እና አገልግሎት ጋር ነው የሚገናኘው። ከድነት ጋር የተያያዘው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ለአንዴና ለዘላለም የሚከናወን ሲሆን፥ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ግን የሚደጋገም ልምምድ መሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጊዜ ተገልጧል።  የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ከጰንጠቆስጤ ዕለት በፊት በጣም ውሱን በሆነ ደረጃ በአንዳንድ ግለሰቦች ላይ ታይቷል (ዘፀ. 28፡3፤ 31፡3፣ 35፡31፤ ሉቃስ 1፡15፥ 41፥ 67፤ 4፡1)። የእግዚአብሔር መንፈስ ሰግለሰቦች ላይ መውረዱና የአገልግሎት ኃይል የሞላበት ሁኔታ መኖሩ የሚያጠራጥር አይደለም። በአጠቃላይ ሲታይ ግን ካጳንጠቆስጤ ዕለት በፊት በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉት ጥቂት ናቸው። የመንፈስ ቅዱስ ሥራም እግዚአብሔር በልዑል ዓላማው መሠረት በግለሰቦች አማካይነት ከሚያከናውነው አንዳንድ ልዩ ሥራዎች ጋር የተያያዘ ይመስላል። የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ከጰንጠቆስጤ ዕለት በፊት ሕይወቱን ለጌታ ለሰጠ ሰው ሁሉ ክፍት የነበረ መሆኑን የሚያመለክት ነገር የለም።  ከጰንጠቆስጤ ዕለት ወዲህ ያለው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ሁሉ የሚሠራበት እዲስ ዘመን ሆኗል። በዚህ ዘመን አማኝ ሁሉ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ካምሆኑም በላይ፥ ቅድመ ሁኔታዎችን ካሟላ ሰመንፈስ ቅዱስ ሊሞላ ይችላል። ይህን እውነት አዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉ አያሌ መግለጫዎች ያረጋግጣሉ (ሐዋ. 2፡4፤ 4፡8፥ 31፤ 6፡3፥ 5፤ 7፡55፤ 9፡17፤ 11፡24፤ 13፡9፥ 52፤ ኤፌ. 5 ፡18)።  የመንፈስ ቅዱስ ሙላት፥ መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ልብና ሕይወት ውስጥ ሊሠራ የሚፈልገውን ያለመከልከል ሲሠራ በእማኝ ሕይወት ውስጥ የሚከሰት ሁኔታ ነው ማለት ይቻላል። ድርጊቱ መንፈስ ቅዱስን ይበልጥ የመቀበል ሳይሆን፥ የእግዚአብሔር መንፈሰ ራሱ አማኙን ይሰልጥ የራሱ ማድረጉ ነው። የመንፈስ ቅዱስ ሙላት በዚህ ዘመን ከጰንጠቆስጤ ዕለት በፊት እንደነበረው በተወሰኑ ሰዎች ላይ ለልዩ ሥራ መከናወን የሚሆን ሳይሆን፥ አማኞች ሁሉ ሊያገኙት የሚቻላቸውና በእርሱ ለሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር የቀረበ የክርስቲያን ልምምድ ነው። ክርስቲያን ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ እንዲሞላ ታዟል (ኤፌ. 5፡18)፤ በመንፈስ ቅዱስ አለመሞላት ግን ከፊል አለመታዘዝ ነው።  ክርስቲያን ባሕርይና ዕለታዊ ሕይወቱ ውስጥ በግልጥ የሚታይ ልዩነት አለ። ጥቂቶች መንፈስ የሞላሳቸው ሆነው ይታወቃሉ። የዚህ ጸጋ ተጠቃሚዎች ቁጥር ጥቂት የመሆኑ ምክንያት፥ ከእግዚአብሔር ልግስና ማነስ ሳይሆን፥ ሰዎች ራሳቸውን ሳያዘጋጁና የእግዚአብሔር መንፈስ ሕይወታቸውን እንዲሞላው ሳይፈቅዱ መቅረታቸው ነው።  በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ከመንፈሳዊ እድገት ጋር ሊነጻጸር ይገባል። ድነትን ካገኘ አጭር ጊዚው የሆነ አዲስ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ሊሞላና የመንፈስ ቅዱስ ኃያልም በሕይወቱ ሊገለጥ ይችላል። በክርስትና ሕይወት መብሰል፥ በእውቀት ማደግ፥ በመንፈስ ቅዱስ የመሞላት የማያቋርጥ ልምምድ እና መንፈሳዊ ነገሮችን በመለየት ማደግ ነው። ይህ የሚገኘው፥ እስከ ሕይወት ፍጻሜ በሚያድግ መንፈሳዊ ልምምድ ይሆናል። አዲስ የተወለደ ሕፃን ሙሉ ጤናማ ሊሆን እንደሚችል፥ አዲስ ክርስቲያንም በመንፈስ ቅዱስ ይሞላ ይሆናል። ነገር ግን ልክ አዲስ እንደተወለደ ሕፃን አዲሱን ክርስቲያንም ወደ እድገት የሚያደርሰው በሕይወቱ የሚያገኘው ልምምድ ነው። ለዚህ ነው ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች ስለ መንፈሳዊ እድገት አበክረው የሚናገሩት። የስንዴ ቡቃያ እስከ መከር ያድጋል (ማቴ. 13፡30)። እግዚአብሔር መንፈሳዊ ስጦታዎች ባሏቸው ሰዎች አማካይነት ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ይሠራል። ይህን የሚያደርገው፥ ቅዱሳኑን ለአገልግሎት ብቁ ለማድረግ፥ በእምነት በእውቀትና በመንፈሳዊ ሁኔታ ለማሳደግ እንዲሁም የክርስቶስ አካል የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን ለመቀደስ ነው (ኤፌ. 4፡11-16)። ጴጥሮስ አዲስ የተወለዱ ሕፃናት ለእድገታቸው መንፈሳዊ ወተት እንደሚያሻቸው ይናገራል (1ኛ ጴጥ. 2:2)። “በጌታችንና በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ” (2ኛ ጴጥ. 3፡18) በማለትም ክርስቲያኖችን ይመክራል።  በመንፈስ ቅዱስ ሙላትና በመንፈሳዊ እድገት መካከል ግልጥ የሆነ ግንኙነት አለ። በዚሁ መሠረት በመንፈስ ቅዱስ ካልተሞላ ከርስቲያን ይልቅ የተሞላው በፍጥነት በመንፈስ ያድጋል። በመንፈስ ቅዱስ መሞላትና ውጤቱ የሆነው መንፈሳዊ እድገት፥ እግዚአብሔር ለሕይወቱ ያለውን ፈቃድ ለማግኘት፥ የእርሱንም እቅድ በመፈጸም ረገድ በክርስቲያን ሕይወት የሚከናወኑ ሁለት ዋና ዋና ነገሮች ናቸው (ኤፌ. 2፡10)።  በዚህ መሠረት የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ለማንኛውም አማኝ የሚደረግ ነው። ይህ የሚሆነው ግን አማኙ ሕይወቱን ሙሉ በሙሉ ውስጡ ለሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ሲያስገዛ ይሆናል። ይህ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ግለሰቡን ይቆጣጠረዋል፥ ኃይልም ይሰጠዋል። የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የሚገለጥባቸው ሁኔታዎችና የሚሰጠው መለኮታዊ ኃይል ደረጃም ያላያዩ ይሆናል። በመንፈስ ቅዱስ የመሞላት ማዕከላዊ አሳብ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለ ምንም መከልከል በአማኙ ውስጥና በርሱ በኩል ይሠራል የሚል ነው። እግዚአብሔር ለዚያ ሰው ያለው ፍጹም ፈቃድ እንዲህ ይከናወናል።  የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ፅንሰ አሳብ አዲስ ኪዳን ውስጥ በርከት ባሉ ጥቅሶች ተመልክቷል። እጅግ በላቀ ሁኔታ የታየው፥ ሉቃስ 4፡1 ውስጥ “መንፈስ ቅዱስ ሞልቶበት፥ በተባለው በኢየሱስ ነው። መጥምቁ ዮሐንስ እናቱ ማኅፀን ውስጥ እንዳለ በመንፈስ ቅዱስ በመሞላቱ በሌሎች ያልተላመደ ልምምድ በረው (ሉቃስ 1፡15)። እናቱ ኤልሳቤጥና አባቱ ዘካርያሰም ለጊዜው በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ነበር (ሉቃስ 1፡41፥ 67)። ይህን የመሰለው የመንፈስ ቅዱስ ሙላት፥ ለጥቂት ሰዎች ብቻ የሚደረግና ሰብሉይ ኪዳን በተደረገው አኳኋን የሚከናወን የልዑል እግዚአብሔር እሠራር ነው።  በጰንጠቆስጤ ዕለት ግን በዚያ የነበሩት ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተዋል። ሰጥንታዊቱ ቤተ ክርስቲያን፥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ የፈለጉ ሁሉ፥ በጴጥሮስ እንደሆነው (ሐዋ. 4:8) በተደጋጋሚ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተዋል። ለእግዚአብሔር ኃይልና ብርታት የጸለዩ ክርስቲያኖች (ሐዋ. 4፡31)፥ ጳውሎስም ከተለወጠ በኋላ (ሐዋ. 9፡17) እንዲሁ ተሞልቷል። አንዳንዶች፥ ማለት የመጀመሪያዎቹ ዲያቆናት፥ (ሐዋ. 6፡3)። ሰማዕቱ እስጢፋኖስ (ሐዋ. 7:55) እና በርናባስ (ሐዋ. 11፡24) በተከታታይ በመንፈስ ቅዱስ እንደተሞሉ ተናግሯል። ጳውሎስ በተደጋጋሚ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቷል (ሐዋ. 13፡9)፤ ሌሎች ደቀ መዛሙርትም እንዲሁ (ሐዋ. 13: 52)። በእያንዳንዱ ሁኔታ በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉት ራሳቸውን ለእግዚአብሔር የሰጡ ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው።  የብሉይ ኪዳን አማኞች በአንዳንድ ሁኔታዎች ተግሣጽ ቢሰጣቸውም በመንፈስ ቅዱስ እንዲሞሉ ሰፍጹም አልታዘዙም። የእግዚአብሔር ሥራ መከናወኑን አስመልክቶ ዘሩባቤል በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፡(ዘካ. 4፡6) ተብሏል። በዚህ ዘመን ክርስቲያን ሁሉ ኤፌሶን 5፡18 ውስጥ እንደተመለከተው በመንፈስ ቅዱስ እንዲሞላ ታዟል። “መንፈስ ቅዱስ ይሙላባችሁ እንጂ፥ በወይን ጠጅ አትስከሩ፥ ይህ ማባከን ነውና።” ድነት በእምነት እንጂ በሥራ እንደማይገኝ፥ በመንፈስ ቅዱስ መሞላትም በሰብአዊ ጥረት የሚሆን አይደለም። ያ የሚሆነው፥ አንድ ሰው እግዚአብሔር በሕይወቱ ይህን የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ይሠራ ዘንድ ሲፈቅድ ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንረዳው፥ አንድ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ሳይሞላ ድነትን ሊያገኝ ይችላል። በዚህ መሠረት የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የድነት አንዱ አካል አይደለም ማለት ነው። የመንፈስ ቅዱስ ሙላት አንድ አማኝ በዳነ ጊዜ ለአንዴና ለዘላለም በሕይውቱ ከተከናውነው ሥራ ጋር ሊገናዘብ ይችላል። አንድ ሰው ድነትን ሲያገኝ በመንፈስ ቅዱስ ሊሞላ ቢችል እንኳን፥ ክንውኑ ሕይወቱን ከሰጠ ክርስቲያን ውስጥ በተደጋጋሚ የሚፈጸም ነው። በመሆኑም ይህ ተደጋጋሚ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የክርስቲያኖች የዘወትር ልምምድ ሊሆን ይገባል።  በመንፈስ ቅዱስ መሞላት በተደጋጋሚ መፈጸም ያለበት መሆኑ ኤፌሶን 5፡18 ውስጥ “መንፈስ ይሙሳሳችሁ” በሚለው ቃል ተገልጧል። ቃሉ “ሁልጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ” የሚል ቀጥተኛ ፍቺ ነው ያለው። ይህ ቃል ምንባቡ ውስጥ ሰውነትንና አእምሮን ከሚጎዳ ስካር ጋር ተነጻጽሯል። ስለዚህ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት አንድ ጊዜ ለዘላለም የሚሆን ነገር አይደለም። በተደጋጋሚ የሚከናወን ነገር ሆኖ ሳለ፥ አልፎ አልፎ እንደሚሰማው ሁለተኛ የጸጋ ሥራ መባሉ ግን ተገቢ አይደለም። ለመጀመሪያ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ የመሞላት ልምምድ ያለ ጥርጥር ለክርስቲያን አስደናቂ ሁኔታ ነው። የክርስትና ልምምድንም ወደ አዲስ ከፍታ የሚያወጣ የመሠረት ድንጋይ ሊሆንም ይችላል። ያም ሆነ ይህ ክርስቲያን ለማያቋርጥ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት በእግዚአብሔር ነው የሚተማመነው፤ በትላንትናው መንፈሳዊ ኃይል የሚኖር ክርስቲያን የለም።  በመንፈስ ቅዱስ ከመሞላት ምንነት በመነሣት በክርስቲያኖች መንፈሳዊ ልምምድና በእግዚአብሔር ዓላማ እንዲሁም ፍላጎት መጣጣም መካከል ሰፊ ልዩነት የሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ከመሞላት ወይም ካለመሞላት የተነሣ ነው ብሎ ለመደምደም ይቻላል። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም የሚፈልግ አማኝ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ እንዲሆን ከእግዚአብሔር ወደተሰጠው መብት መግባትና ሕይወቱንም ለእግዚአብሔር መንፈስ ሙሉ በሙሉ ማስረከብ

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የመሙላት ተግባሩ Read More »

የሚያንገጫግጭ መንገድ

ሰዎች፣ ሕይወት አስቸጋሪ እንደሆነች ሲነግሩኝ ሁልጊዜ የምመልሰው ‹‹በእርግጥ አስቸጋሪ ናት፡፡›› በማለት ነው፡፡ ልሰጥ ከምችላቸው ምላሾች በላይ ይህ መልስ ያረካኛል፡፡ ፀሐፊ ቻርለስ ዊሊያምስ በአንድ ወቅት እንዲህ አለ፣ ‹‹አለም በሁሉም ረገድ ስቃይ አለባት፤ ይህን ስቃይ መውደድ ይኖርብናል የሚለውን ሃሳብ መስማት ደግሞ ሊሸከሙት የማይችሉት ዜና ነው፡፡›› እግዚአብሔር እኛን ይዞን የሚጓዝበት መንገድ ብዙውን ጊዜ እኛ ለራሳችን ካየነው ጥሩ መንገድ አንጻር በተቃራኒው ሊመስል ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት አንዳንዴ እየተጓዝንበት ያለንበት የእግዚአብሔር መንገድ ትክክለኛ ያልሆነ ይመስለናል፡፡ ለዚህ ነው ብዙዎቻችን፣ በትክክለኛው መንገድ ላይ ብሆን ኖሮ፣ የእግዚአብሔር መልካምነት፣ ሁል ጊዜ ከችግር ነፃ በሆነ የሕይወት ጎዳና ይመራኝ ነበር ብለን የምናስበው፡፡ይህ ሃሳብ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሃሳብ የወጣና ሊሰራ የማይችል ሕልም ነው፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር ምድራዊ ምቾት በሌለበት ጎዳና ሊመራን ይችላል፡፡ ጳውሎስ እንዲህ ይላል፣ ‹‹… ስለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም›› (ፊል. 1፡29)፡፡ ስንጓዝበት ከነበረው የመከራ ጉዟችን ስንወጣ እያንዳንዱን ሁኔታ እግዚአብሔር ለዘለቄታዊ ጥቅማችን ሲል የፈቀደው እንደነበረ ይገባናል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ የሆነው ኤፍ ቢ ሜየር እንዲህ አለ፣ ‹‹ካለፍንበት መንገድ የተሻለ ተስማሚ ወይም ደህና መንገድ የለም፤›› ‹‹አንድን መንገድ ልንመረጠው የምንችለው እግዚአብሔር እንደሚያየው፣ እኛም ማየት ስንችል ብቻ ነው፡፡›› ዴቪድ ሮፐር ይህን አስመልክቶ ሲናገር ደግሞ እንዲህ ይላል፣ «እግዚአብሔር መከራዎቻችንን የፈቀደበት ምክንያት አውቀነው ቢሆን ኖሮ የትኛውም መከራ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንድንገባ ባላደረገን ነበር፡፡›› ወንጌል በድረ ገጽ አገልግሎት፤ https://yehiwotenjera.com/Our daily Bread – (መጋቢት 21, 2005) – የሚያንገጫግጭ መንገድትርጉም፣ አዳነው ዲሮ

የሚያንገጫግጭ መንገድ Read More »

በወንጌል በድረገጽ ላይ ያሉ ጽሁፎችን በ PDF ፋይል ፎርማት ለማስቀመጥ (save) ለማድረግ

ሰላም፣ በወንጌል በድረገጽ ላይ ያሉ ጽሁፎችን በ PDF ፋይል ፎርማት በግሎ ማህደር ለማስቀረት (save) የሚሹ ከሆነ የሚከተሉትን ቅደም ተከተሎች ተግባራዊ ያድርጉ፦ የሚፈልጉትን ጽሑፍ ከዌብ ሳይቱ (https://yehiwotenjera.com/) ላይ ከከፈቱ በኋላ የጽሁፉ መጨረሻ (ግርጌ) ላይ ይሂዱ፤ በጽሁፉ መጨረሻ (ግርጌ) ላይ የሚከተሉትን አማራጮች ያገኛሉ (Press This, Twitter, Facebook, More)፣ ከእነዚህ አማራጮች መካከል (More) የሚለውን ይጫኑ (ክሊክ) ያድርጉ፤ (More) የሚለውን ሲጫኑ የሚመጣውን (Print) የሚል አይከን ይጫኑ፤ በሚከፈተው የ Print ዊንዶ ውስጥ (Destination) በሚለው ትይዩ ያለውን ድሮፕ ዳውን (የተዘቀዘቀ ቀስት የሚመስል ምልክት) በመክፈት (Save as PDF) የሚለውን ይምረጡ፤ ከዛም (Save) ያድርጉት፡፡ አበቃ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስዎን በማጥናት መንፈሳዊ ሕይወትዎን ያሳድጉ (https://yehiwotenjera.com/)

በወንጌል በድረገጽ ላይ ያሉ ጽሁፎችን በ PDF ፋይል ፎርማት ለማስቀመጥ (save) ለማድረግ Read More »

የንጉሡ የኢየሱስ ልደት (ማቴ. 1፡18-2፡23)

በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ የክርስቶስን መለኮታዊ ልደት በዝርዝር የሚገልጹት ወንጌላት ሁለት ብቻ ናቸው፤ እነርሱም የማቴዎስና የሉቃስ ወንጌል ናቸው። ከእነዚህ ከሁለቱ መካከል፥ ሐኪሙ ሉቃስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር የቅርብ ውይይት በማድረግ ስለ ክርስቶስ ልደት እጅግ ሰፊ መለኮታዊ ምርምር አካሂዷል (ሉቃስ 1፡1-4)። ይሁን እንጂ በይዘት ረገድ ትልቅ ልዩነት አላቸው፦ ታላቁ የክርስቶስ ልደት የሆነው ዮሴፍና ማርያም በሕግ ተጫጭተው (ታጭተው) በነበሩበት ወቅት ነበር። በጥንቷ እስራኤል ባህልና ሥርዓት መሠረት፥ የአይሁድ መተጫጨት ልክ እንደ ዛሬዋ አገራችን እንደ ኢትዮጵያ ባህላዊ ሥርዓት ሁሉ እጅግ ከፍተኛ ማኅበራዊና ሕጋዊ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነበር። አይሁዶች ከተጫጩ በኋላ ባልና ሚስት እንደሆኑ ተቆጥረው በአንድ ቤት አብረው መኖር ከመጀመራቸው በፊት ለአንድ ዓመት ያህል በትዕግሥት ይጠብቁ ነበር። ይህ ጽኑ የቃል ኪዳን መተጫጨት በዝሙት ምክንያት ሊፈርስ የሚችለው በሕጋዊ የፍቺ ጽሕፈት ብቻ ነበር (ዘዳግ. 22:23-24)። በትክክል በዚህ በተቀደሰው መተጫጨት ወቅት ማርያም ከዮሴፍ ጋር ሳትገናኝ በፊት፥ ሳይታሰብ «በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች» (ማቴ. 1፡18)። 👥 የውይይት ጥያቄ እና ተግባራዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልስ ፩. የውይይት ጥያቄ፦ ቅድስት ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ስለደረሰላት ታላቅ መለኮታዊ ብስራትና ስለ ፅንሰቷ ምስጢር (ሉቃስ 1:35) ለእጮኛዋ ለዮሴፍ በቅንነት በቃላት ገልጻለት ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን በማቴዎስ ጽሑፍ ውስጥ ስለዚህ ጉዳይ በቀጥታ የተጠቀሰ ነገር የለም። ይሁን እንጂ ዮሴፍ ማርያም ማርገዟን በምልክት በሆነ መንገድ ደርሶበት እንደነበረ ግልጽ ነው። ዮሴፍ የእግዚአብሔርን ሕግ የሚወድ እውነተኛ ጻድቅና የዋህ ሰው ስለነበረ፥ ማርያም ከሌላ ወንድ ጋር በበደል የወደቀች መስሎት በይፋ አውጥቶ በሕዝብ ፊት ሊወቅሳት፥ ሊያዋርዳትና በሕጉ መሠረት በድንጋይ ተወግራ እንድትሞት ፈጽሞ አልፈለገም (ዘዳግ. 22:22)። ስለሆነም ለእርሷም ሆነ ለማኅበረሰቡ ሳይናገር በስውር የፍቺ ጽሕፈት ሰጥቶ ሊተዋት በልቡ በጥንቃቄ አሰበ (ማቴ. 1፡19)። ጻድቁ ዮሴፍ በዚህ ከባድ የልብ ውሳኔና ኀዘን ውስጥ እያለ፥ እግዚአብሔር ግን ማርያም ከሌላ ሰው ጋር በዝሙት እንዳልረከሰችና በትክክልም ከመንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ኃይል በተአምር እንደፀነሰች ለዮሴፍ እውነትን ለመግለጥ በሌሊት በሕልም ቅዱስ መልአኩን ላከለት (ማቴ. 1፡20)። ምንም እንኳን ማርያም በሰፈሩ ሰዎች ዘንድ በማርገዟ ምክንያት ብትናቅና በተለያየ ስላቅ ቢቀልዱባትም፥ ዮሴፍ ግን የእግዚአብሔርን ቃል በፍርሃት ታዞ ማርያምን በክብር ወደ ቤቱ ወሰዳት። የኢየሱስ ስምና የአማኑኤል ትንቢት ፍጻሜ እግዚአብሔር በዚህ መሲሑን ወደ ምድር የመላክ ታላቅ የድነት ሂደት ውስጥ ማርያምን ብቻ ሳይሆን፥ ጻድቁን ዮሴፍንም እጅግ አክብሮታል። በአይሁድ ሥርዓት እንደ እውነተኛ ባልና የቤት ራስ ሁሉ፥ እግዚአብሔር አባት ዮሴፍ ለሚወለደው ሕፃን መለኮታዊ ስም የማውጣት ሕጋዊ መብትን በይፋ ሰጠው። ለክርስቶስ ስም በማውጣቱ አማካይነት፥ ዮሴፍ የሕፃኑን የዳዊት ወራሽነት ሕጋዊ አባትነቱን በታሪክ እያረጋገጠ ነበር። እግዚአብሔር ዮሴፍ ሕፃኑን «ኢያሱ» (በዕብራይስጥ ቋንቋ Yeshua) ወይም ወደ ግሪክ ሲተረጎም «ኢየሱስ» (Iesous) ብሎ እንዲጠራው በቅንነት ነገረው። የዚህ ታላቅ ስም ትርጉም በምስጢር፦ «ይሖዋ (እግዚአብሔር) መድኃኒት ነው» ወይም «እግዚአብሔር ድኅንነት ነው» ማለት ነው (ማቴ. 1፡21)። ይህ መለኮታዊ ስም የሚያበሥረው፦ የመሲሑ ቀዳሚና ዋና ተግባር በምድር ላይ በሰይፍ የሚዋጋ ምድራዊ ድል ነሺ ንጉሥ መሆን ሳይሆን፥ ሰዎችን ከኃጢአት ባርነት የሚያድን ሰማያዊ አዳኝ መሆኑን ነው። ክርስቶስ «ሕዝቡን ከኃጢአታቸው የሚያድን» እውነተኛ መንፈሳዊ አዳኝ እንጂ፥ አይሁድ እንደጠበቁት የሮምን ቀንበር የሚሰብር ምድራዊ ፖለቲካዊ ነፃ አውጪ እንዳልሆነ ማቴዎስ በስሙ ትርጉም በግልጽ አስምሮበታል። ማቴዎስ የድንግሊቱ በተአምር መውለድና የክርስቶስ የልደት ዝርዝር ጉዳዮች ሁሉ፥ በአጋጣሚ የተከሰቱ ሳይሆኑ በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ጥበብ በጥንቃቄ የታቀዱና በብሉይ ኪዳን በነቢዩ በኢሳይያስ የተነገሩ ታላላቅ ትንቢቶች ፍጻሜ መሆናቸውን አስረድቷል። ማርያም በሚያስደንቅ መለኮታዊ መንገድ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ በመውለዷ ምክንያት፥ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድ አካል ፍጹም ሰውና ፍጹም አምላክ ሆኖ ተገልጧል። በዚህም ምክንያት እርሱ ብቻ እውነተኛው «አማኑኤል» — ትርጉሙም «እግዚአብሔር ከእኛ ጋር» የሆነው መለኮታዊ አምላክ ነው (ኢሳ. 7፡14)። በጥንቱ በብሉይ ኪዳን ዘመን እግዚአብሔር የክብር ደመናውን (የሸኪና ክብርን) በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በሰዎች መካከል ያኖረ ሲሆን፥ አሁን በአዲስ ኪዳን ግን እግዚአብሔር ራሱ ፍጹም ሥጋ ለብሶ በሰዎች መካከል በታሪክ አድሯል (ዮሐ. 1፡14)። ክርስቶስ የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ወደ ሰማይ ከመመለሱ በፊት፥ ለቅዱሳን ደቀ-መዛሙርቱ አሁንም ሁልጊዜ አማኑኤል ሆኖ እንደሚቀጥል፥ ማለትም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከእነርሱ ጋር አብሮ እንደሚኖር በታላቅ ቃል ኪዳን አረጋግጦላቸዋል (ማቴ. 28፡20)። የአሕዛብ ሰብአ ሰገል (Magi) አምልኮ ማቴዎስ ወንጌሉን ለአይሁድ ሲጽፍ፥ እግዚአብሔር ለአይሁድ ብቻ ሳይሆን ለአሕዛብም ታላቅ የማዳን ዕቅድ እንዳለው በተግባር አመልክቷል። ለዚህም ትልቅ ማረጋገጫው በታሪክ መጀመሪያ ጊዜ ሕፃኑን ክርስቶስን በኢየሩሳሌም መጥተው ያከበሩትና በፊቱ ወድቀው ያመለኩት ከሩቅ አገር የመጡት አሕዛብ ሰብአ ሰገል መሆናቸውን በክብር ገልጿል (ማቴ. ምዕ. 2)። ማቴዎስ እነዚህ ሰብአ ሰገል ከየትኛው አገር በትክክል እንደመጡ ወይም በቁጥር ስንት እንደሆኑ በወንጌሉ ውስጥ አልጠቀሰም። በጥንታዊው የቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ሦስት ሰዎች እንደሆኑ የሚታመነው፥ ለሕፃኑ ካበረከቷቸው ከሦስቱ ታላላቅ መለኮታዊ ስጦታዎች (ከወርቅ፥ ዕጣንና ከከርቤ) በመነሳት ነው። ለእነዚህ ሰዎች በጥንቱ የግሪክ ጽሑፍ የተሰጣቸው ስም «ማጂ» (Magi) የሚል ነው። ማጂ በጥንቱ መካከለኛ ምሥራቅ የነበሩ የከዋክብት ተመራማሪዎች፥ የንጉሥ አማካሪዎችና የልዩ ምስጢራዊ ዕውቀት ሰዎች ማኅበር ሲሆን፥ ብዙ የታሪክ ምሁራን እነዚህ ወገኖች የመጡት ከታላቂቱ ከፋርስ (ከኢራን) ወይም ከሳውዲ ዓረቢያ ምድር እንደነበረ በታሪክ ይናገራሉ። እነዚህ ሰዎች ምንም እንኳ በአሕዛብ ምድር በከዋክብት ጥናት ቢታገሉም፥ በዚያ በምርኮ ዘመን በዳንኤል ትንቢት በኩል የተላለፈውን ስለ መሢሑ ንጉሥ መነሳት የሚናገረውን መለኮታዊ ግንዛቤ በሚገባ ያውቁት ነበር (ዳን. 9:24-26)። ስለሆነም በሰማይ ያዩት ያ አዲስ ድንቅ መለኮታዊ ኮከብ ለአይሁድ ሕዝብ ልዩ የዘላለም ንጉሥ እንደተወለደ የሚያመለክት መሆኑን በመንፈስ አስተዋሉ፤ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው በፊቱ የመስገዳቸውና የማምለካቸው ታላቅ ተግባር ደግሞ፥ ይህ የተወለደው ሕፃን ከተራ ምድራዊ ነገሥታት ሁሉ በላይ ፍጹም መለኮታዊ ሥልጣን ያለው አምላክ መሆኑን በልባቸው እንደተገነዘቡ ያሳያል። እነርሱም የአይሁድ ታሪካዊት መዲና ወደሆነችው ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ እስኪደርሱ ድረስ፥ ለብዙ ወራት ያንን መለኮታዊ ኮከብ በታማኝነት እየተከተሉ በበረሃ ተጓዙ። የንጉሥ ሄሮድስ ቁጣና የሃይማኖት መሪዎች ድንዛዜ ሰብአ ሰገል ወደ ኢየሩሳሌም በገቡ ጊዜ፥ «የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ በቤተ መንግሥት ውስጥ ይገኛል» ብለው ስለገመቱ፥ ቀጥታ ወደ ንጉሥ ሄሮድስ ቤተ መንግሥት በመሄድ አዲስ ስለተወለደው ንጉሥ በጥያቄ አወቁ። ቀደም ሲል የገዛ ዙፋኔን ይነጥቁኛል በሚል ክፉ የሥልጣን ፍርሃትና ጥርጣሬ ምክንያት፥ የገዛ አጎቱን፥ ሚስቱንና የገዛ ልጆቹን ጭምር በጭካኔ የፈጀው ያ አሮጌው ንጉሥ ሄሮድስ፥ ይህንን የአዲስ ንጉሥ መወለድ የምሥራች ከሰብአ ሰገል በአፉ በሰማ ጊዜ በከፍተኛ ድንጋጤና ስጋት ተናወጠ (ማቴ. 2:3)። ንጉሥ ሄሮድስ ይህንን መለኮታዊ ምስጢር ለማወቅ ሲል፥ ወዲያውኑ የአይሁድን የሃይማኖት መሪዎች፥ የሕግ መምህራንን (ጸሐፍትን) እና ከፍተኛ ካህናትን በአንድነት ሰበሰበ። እነዚህ የሃይማኖት መሪዎች መጽሐፍ ቅዱስን (ኦሪትን) ጠንቅቀው የሚያውቁ ሊቃውንት ስለነበሩ፥ በነቢዩ በሚክያስ ትንቢት መሠረት (ሚክ. 5:2) መሢሑ የሚወለደው ከኢየሩሳሌም ሰባት ኪሎ ሜትር አጭር ርቀት ላይ ወጣ ብላ በምትገኘው በትንሿ በይሁዳ ቤተልሔም ከተማ መሆኑን ጥቅሱን መዝዘው ወዲያውኑ ለንጉሡ ነገሩት። የመሪዎቹ አስገራሚ ድንዛዜ፦ እዚህ ላይ እጅግ ሊታሰብበት የሚገባው ታላቅ መንፈሳዊ ምስጢር አለ፦ እነዚህ የአይሁድ የሃይማኖት መሪዎች መሢሑ የት እንደሚወለድ ቃሉን በሚገባ ቢያውቁም፥ ከሩቅ አገር መጥተው የሕፃኑን መወለድ ከሚናገሩት ከሰብአ ሰገል ጋር አብረው ግንኙነት ለማድረግና ሕፃኑን መሢሕ በዓይናቸው ለማየትና ለመስገድ ግን ሰባ ኪሎ ሜትር እንኳ ለመጓዝ ልባቸው ፍጹም አልተንቀሳቀሰም ነበር! እነርሱ በደረቀ ቃላቸውና በሃይማኖታዊ ዕውቀታቸው ብቻ በትዕቢት ተሞልተው በቤታቸው ተቀመጡ። ንጉሥ ሄሮድስም የሕፃኑን ትክክለኛ ቦታ መለኮታዊ ትንቢት ካረጋገጠ በኋላ፥ ሰብአ ሰገል ሄደው ሕፃኑን ካገኙት በኋላ መጥተው እንዲነግሩት በምስጢር አዘዛቸው፤ ምንም እንኳ ሄሮድስ «እኔም መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ» ብሎ በውሸት ቢናገራቸውም፥ የልቡ እውነተኛ ፍላጎት ግን ያንን ሕፃን ንጉሥ ፈጥኖ መግደል ብቻ

የንጉሡ የኢየሱስ ልደት (ማቴ. 1፡18-2፡23) Read More »

የማቴዎስ ወንጌል ዐላማ

ከሉቃስና ከዮሐንስ ወንጌል በተቃራኒ፥ ሐዋርያው ማቴዎስ ወንጌሉን ለምን እንደጻፈው ግልጽ የጽሑፍ ምክንያት በመጽሐፉ መግቢያ ላይ በቀጥታ አይገልጽም (ሉቃስ 1፡1-4፤ ዮሐ. 20፡30-31)። ስለሆነም የማቴዎስን እውነተኛ መለኮታዊ ዓላማ በሙላት የምንረዳው፥ በወንጌሉ ውስጥ የተመዘገቡትን ታሪኮች፣ ትምህርቶችና አወቃቀሮች በጥንቃቄ በመገንዘብ ነው። ማቴዎስ ይህንን ቅዱስ መጽሐፍ የጻፈባቸው በርካታ ታላላቅ ምክንያቶች እንዳሉ ባይጠራጠርም፥ ዋና ዋናዎቹን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዓላማዎች እንደሚከተለው በዝርዝር አደራጅተናቸዋል፦ 1. ክርስቶስ የመለኮታዊ ዕቅድና የትንቢቶች ፍጻሜ መሆኑ ፩. የውይይት ጥያቄ፦ ማቴዎስ በሥጋ የገዛ ወገኖቹ ለሆኑት ለአይሁድ ሕዝብ ድነት በልቡ እጅግ ያስብና ይጨነቅ ነበር። አይሁድ የብሉይ ኪዳን ቃል ኪዳን ሕዝብና የእግዚአብሔር ምርጦች ነበሩ። ነገር ግን በእጃቸው የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትና የነቢያት ድርሳናት በሙላት ቢኖሯቸውም እንኳ፥ ናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በነቢያት በኩል የሰጣቸው የኪዳን ተስፋዎች ሁሉ እውነተኛ ፍጻሜ መሆኑን ለመረዳት በልባቸው ታውረው ተቸግረው ነበር። ስለሆነም ማቴዎስ አይሁድ ለዘመናት በናፍቆት ሲጠብቁት የነበረው እውነተኛው መሢሕ ኢየሱስ መሆኑን በቅዱስ ቃል ለማሳመንና ወደ እምነት ለማምጣት ወንጌሉን ጻፈ። ማቴዎስ ይህንን ታላቅ ዓላማ ያከናወነባቸው 3 መለኮታዊ መንገዶች የሚከተሉት ነበሩ፦ 2. የሰማይ መንግሥት እውነተኛ ባሕርይ ፪. የውይይት ጥያቄ፦ ማቴዎስ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም ያመጣው መንግሥት ምድራዊ ፖለቲካዊ ሳይሆን፥ ፍጹም ሰማያዊና መንፈሳዊ መንግሥት መሆኑን ለሕዝቡ ለማስረዳት ሲል፥ በወንጌሉ ውስጥ «የሰማይ መንግሥት» የሚለውን ልዩ ስያሜ በጥንቃቄ ተጠቅሟል። ማቴዎስ ይህንን ቃል ሲጠቀም፥ ክርስቶስ በአማኞች ሕይወት ውስጥ የሕያውን እግዚአብሔርን ሉዓላዊ አገዛዝ የሚገልጽ መንግሥት በምድር እንደመሠረተ ማብራራቱ ነበር። የእርሱ ሰማያዊ መንግሥት በጦር መሣሪያ ላይ ሳይሆን፥ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በመከተልና በመታዘዝ ላይ ብቻ ያተኮረ ነበር። ይህም በምድራዊ ሥልጣን ላይ ሳይሆን፥ በአንድ ሰው የተሰበረ ልብ ውስጥ በጸጋ የሚቀመጥና ጠቅላላ ሰብአዊ ባህሪውንና አመለካከቱን የሚለውጥ የውስጥ መንፈሳዊ መንግሥት ነበር (ማቴ. ምዕራፍ 5-7)። በዚህ ታሪካዊ ዘመን እግዚአብሔር ክርስቶስ ይህንን መንፈሳዊ መንግሥት በቤተ ክርስቲያን በኩል እንዲጀምር በምድር ላይ ልኮታል። ነገር ግን አንድ ቀን ክርስቶስ በታላቅ መለኮታዊ ክብሩና በግርማው ተመልሶ ሲመጣ፥ የብሉይ ኪዳን የተስፋ ቃሎች ሁሉ ሙሉ በሙሉ የሚፈጸሙበትን ያንን የከበረ ምድራዊ መንግሥት (የሺህ ዓመቱን መንግሥት) በጽዮን ይመሠርታል (ራእይ 20፡4-6)። ወደዚያች የከበረች መንግሥት በክብር የሚገቡት ግን፥ ዛሬ በምድር ላይ ለእግዚአብሔር መንፈሳዊ መንግሥትና ለቃሉ ሥልጣን ሕይወታቸውን በቅድስና ያስገዙ እውነተኛ አይሁድና አሕዛብ አማኞች ብቻ ይሆናሉ። ፫. የውይይት ጥያቄ፦ 3. አዳዲስ አማኞችን ማሠልጠንና የአሕዛብ ድነት ዕቅድ የማቴዎስ ወንጌል የሚጀምረው፥ «የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ» በማለት ነው (ማቴ. 1፡1)። ይህም ማቴዎስ ወንጌሉ የዳዊት ልጅና ትክክለኛ የእስራኤል ዘላለማዊ ንጉሥ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ብቻ እንደሚያተኩር ያሳያል። ክርስቶስ ስለ መሢሑ የተነገሩት ትንቢቶች ሁሉ ፍጹም ፍጻሜ ነው። እነዚህም የዳዊት ልጅ በእስራኤልና በዓለም ሕዝቦች ሁሉ ላይ በጽድቅ እንደሚነግሥ የሚያመለክቱ ታላላቅ ትንቢቶች ነበሩ (ኢሳ. 11፡1-10)። በተጨማሪም ማቴዎስ ክርስቶስ «የአብርሃም ልጅ» መሆኑን ገልጿል፤ ይህም ክርስቶስ ፍጹም እስራኤላዊ መሆኑን ብቻ ሳይሆን፥ ለአብርሃም የተሰጠው የታላቁ ቃል ኪዳን ብቸኛ ፍጻሜ መሆኑንም ያረጋግጣል። ፬. የውይይት ጥያቄ፦ የኦሪት ዘፍጥረት 12፡1-3 በጥንቃቄ አንብብ። በዚህ ታላቅ መለኮታዊ ቃል ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር ለአብርሃም ብዙ የተስፋ ቃሎችን ሰጥቶት ነበር። አብዛኞቹ የተስፋ ቃሎች ከእስራኤል ሕዝብ መነሳት ጋር የተያያዙ ቢሆኑም (ገላ. 3፡16)፤ ከምንም በላይ እግዚአብሔር ለአብርሃም፦ «የምድርም ነገዶች ሁሉ በአንተ ይባረካሉ» በማለት የዓለም ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ በኩል መለኮታዊ በረከትንና ድነትን እንደሚያገኙ ተናግሯል (ዘፍጥ. 12:3)። ይህ ሁለንተናዊ የተስፋ ቃል ፍጻሜውን ያገኘው፥ የአብርሃም እውነተኛ ልጅ በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ብቻ ነበር። ክርስቶስ በመስቀል ላይ ቅዱስ ደሙን በማፍሰሱና በመሞቱ፥ ለዓለም ሕዝብ ሁሉ የኃጢአት ይቅርታንና የእርቅን በር ወለል አድርጎ ከፈተ። ዛሬ በክርስቶስ ማዳን የሚያምኑ አሕዛብና ሕዝቦች ሁሉ በአንድነት የእግዚአብሔር ቤተሰብ በመሆን፥ የአብርሃም እውነተኛ መንፈሳዊ ልጆችና የበረከቱ ወራሾች ለመሆን በቅተዋል (ገላ. 3፡7-9፤ ሮሜ 11፡11-24)። ማቴዎስ አዳዲስ ክርስቲያኖችን በቅድስና ኑሮ ለማሠልጠንና ለማስተማር በማሰብ ወንጌሉን እንደጻፈ ግልጽ ነው። ብዙዎች በክርስቶስ አምነው ወደ ቤተ ክርስቲያን ቢመጡም (ሮሜ 10፡9-10)፥ ስለ ክርስቶስ ሕይወትና ትምህርት የሚያውቁት ጥልቅ ግንዛቤ አልነበራቸውም። ሐዋርያት በአካል በሌሉባቸው ሩቅ አህጉራት ሁሉ ወንጌል በከፍተኛ ፍጥነት ይስፋፋ ስለነበር፥ እያንዳንዱ አማኝ ስለ ክርስቶስ መሢሕነት በትክክል ማወቅ ነበረበት። ስለሆነም ማቴዎስ አዳዲስ ክርስቲያኖች ስለ ክርስቶስ መለኮታዊ ማንነትና በመስቀል ላይ በፈጸመው የማዳን ሥራ ላይ ፍጹም የጠራ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ፈለገ። ማቴዎስ «በክርስቶስ አምናለሁ» የሚለው አጠቃላይ አሳብ ብቻ ለአማኞች በቂ እንዳልሆነ ያውቅ ነበር፤ ይልቁንም ስለ ክርስቶስ ማንነት፥ ምን እንዳደረገ፥ ስለ ሞቱና ትንሣኤው፥ እንዲሁም «እከተልሃለሁ» ከሚሉት ሕዝቦች በየዕለቱ ምን ዓይነት የቅድስና ሕይወት እንደሚፈልግ ማወቅ ያስፈልጋቸው ነበር። ማቴዎስ ክርስቶስ እውነተኛ ተከታይ ስለመሆን ያስተማረውን ጥብቅ ትምህርቶች በወንጌሉ መዝግቧል። አንድ አማኝ ክርስቶስን ሲከተል አጠቃላይ የልብና የሕይወት ለውጥ ያስፈልገው ነበር፤ ከእንግዲህ ወዲህ በሰዎች ውጫዊ ደንቦችና በደረቁ ሕግጋት ላይ ሳይሆን፥ በመንፈስ ቅዱስ በሚቀረጽ ውስጣዊ ባሕርይና ቅዱስ አመለካከት ላይ ማተኮር ይኖርባቸዋል (ማቴ. ምዕራፍ 5-7)። አይሁዶች ከሌሎች ሕዝቦች እንደሚበልጡ በማሰብ በምድራዊ ብሔራዊ ውርሳቸውና በዘራቸው መመካት እንደሌለባቸው፥ ይልቁንም የአሕዛብና የአይሁዶች ንጉሥ የሆነውን ክርስቶስን ብቻ በትሕትና መከተል እንዳለባቸው ገልጿል። እውነትም መለኮታዊው ወንጌልና የእግዚአብሔር አባትነታዊ በረከት ለሰዎች ሁሉ በጸጋ የተሰጠ እንጂ ለአንድ የተወሰነ ጎሳ ወይም ብሔር ብቻ አልነበረም። ፭. የውይይት ጥያቄ፦ የማቴዎስ ወንጌል እግዚአብሔር ለአሕዛብ ድነት ታላቅና ልዩ ዕቅድ እንዳለው በግልጽ ያሳያል። በማቴዎስ ዘመን የነበሩት አብዛኞቹ ትዕቢተኞች አይሁድ አሕዛብን ሁሉ ስለሚንቁና ስለሚጠሉ፥ እግዚአብሔርም አሕዛብን ሁሉ እንደሚጠላና ያዘጋጃቸውም ለገሃነም ማቀጣጠያ ብቻ እንደሆነ አድርገው በስሕተት ያስተምሩ ነበር። ማቴዎስ ግን በወንጌሉ ውስጥ ለአሕዛብ ድነት ልዩ መለኮታዊ ትኩረት ይሰጣል፦ 4. የክርስቶስ መለኮታዊ ሥልጣንና ለአይሁድ ጥያቄዎች የተሰጠ ምላሽ የመጀመሪያው ወንጌል ክርስቶስ ፍጹም ታሪካዊ ሰው ብቻ ሳይሆን፥ በፍጥረትና በነገሮች ሁሉ ላይ ፍጹም ሉዓላዊ ሥልጣን ያለው እውነተኛ አምላክ መሆኑን ያሳያል። ማቴዎስ ክርስቶስ በሁሉም ዘርፍ ላይ ፍጹም ሥልጣን እንዳለው በተአምራቱ አሳይቷል፦ ክርስቶስ ፍጹም ኃያልና አምላክ በመሆኑ አማኞች በፊቱ ወድቀው በክብር ሰግደውለታል፥ አምልከውታልም (ማቴ. 8፡2፤ 14፡33)። ኢየሱስ አምላክ በመሆኑ ለሰዎች የራቀና ስለ ፍጥረቱ ምንም ግድ የማይሰጠው አምላክ አይደለም፤ ይልቁኑ ወደ ምድር መጥቶ በሰዎች መካከል በመመላለስ ለሕዝቡ ችግር ሁልጊዜ ከልቡ ይራራ ነበር (ማቴ. 9፡36፤ 14:14)። የደከሙና ሸክም የበዛባቸው ሰዎች ሁሉ የሚፈልጉትን ዘላለማዊና እውነተኛ መንፈሳዊ ዕረፍት የሚያገኙት በእርሱ ብቻ ነው (ማቴ. 11፡28-30)። ማቴዎስ አይሁድ በክርስቶስ መሢሕነትና ልደት ላይ ለሚያነሡዋቸው የተለያዩ የጥላቻ ጥያቄዎች መለኮታዊ ምላሽ ለመስጠት ወንጌሉን አዘጋጅቷል። ለምሳሌ አይሁድ ክርስቶስ የዮሴፍ ተፈጥሯዊ የሥጋ ልጅ እንዳልሆነ ያውቁ ስለነበርና እርሱን ለማዋረድ «ኢየሱስ ዲቃላ ነው» ብለው በሐሰት ያስቡ ስለነበር (ዮሐ. 8፡41)፤ ማቴዎስ ክርስቶስ በዮሴፍ የሥጋ ፈቃድ ሳይሆን ከመንፈስ ቅዱስ በተአምር የተፀነሰ ፍጹም ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን በወንጌሉ መጀመሪያ ላይ በጥንቃቄ አብራርቷል (ማቴ. 1፡18-25)። ሌሎች ደግሞ «ኢየሱስ የገሊላ ሰው ነው እንጂ በይሁዳ ቤተልሔም አልተወለደም፤ ስለሆነም መሢሕ ሊሆን አይችልም» እያሉ ይከራከሩ ነበር። ማቴዎስ ግን ኢየሱስ በትክክል በይሁዳ ቤተልሔም እንደተወለደና የነቢዩ ሚክያስን የተስፋ ቃል እንደፈጸመ (ሚክ. 5:2)፥ ቀጥሎም ከሄሮድስ ቁጣ የተነሳ በታሪክ ወደ ግብፅና ወደ ናዝሬት እንደተጓዘ በማሳየት የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች በሕይወቱ መፈጸማቸውን አረጋግጧል። ሌላው ታላቅ ምሳሌ ማቴዎስ የክርስቶስን ትንሣኤ እውነት ለማጥፋት ሲሉ የአይሁድ የሃይማኖት መሪዎች ለሮም ወታደራዊ ጠባቂዎች እጅግ ብዙ ገንዘብ (ጉቦ) በመስጠት፥ «ደቀ-መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰረቁት» ብለው ያሰራጩትን የውሸት ታሪክ በቃሉ ሙሉ በሙሉ ማፍረሱና ጠባቂዎቹ ለምን እንደዋሹ ማጋለጡ ነው (ማቴ. 28፡11-15)። በሮም ግዛት የነበሩ ሰዎች ሁሉ በተለይም አይሁድ የሚያነሱት አንድ ታላቅ ጥያቄ ነበር፦ «ክርስቶስ እውነተኛ መሢሕ ከነበረ እንዴት በውርደት በመስቀል ላይ

የማቴዎስ ወንጌል ዐላማ Read More »

ማቴዎስ ወንጌሉን የጻፈበት ጊዜና ቦታ

ብዙዎቹ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት በትክክል መቼና የት እንደተጻፉ በእርግጠኝነት ለማወቅ በታሪክ አስቸጋሪ ነው። በመሆኑም የስነ-ጽሑፍ ምሁራን በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱትን ታሪካዊ ክስተቶችና የዓለም ነገሥታት አገዛዝ በጥንቃቄ በማገናዘብ፥ የመጻሕፍቱን የመጻፊያ ዘመን ለመገመት መጽሐፉን በሰፊው ይመረምራሉ። ይህ የታሪክ አውድ ምርምር ዘዴ፦ በኮሚኒዝም (በደርግ) ጨቋኝ ዘመን የተጻፈ መጽሐፍ ይዘትና መልእክት፥ ምንም ዓይነት የመንግሥት ስደትና ከባድ ችግር በሌለበት የነጻነት ዘመን ከተጻፈ መጽሐፍ ፍጹም የተለየ አሳብና መንፈስ ከሚያስተላልፍበት ታሪካዊ ሁኔታ ጋር ሙሉ በሙሉ ይመሳሰላል። 👥 የውይይት ጥያቄ እና ተግባራዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልስ ፩. የውይይት ጥያቄ፦ በአገራችን በነበረው በኮሚኒዝም (በደርግ) ጨቋኝ የሶሻሊስት አገዛዝ ዘመን የነበሩ ወንጌላውያን አገልጋዮች የጻፏቸው መጻሕፍት፥ ትምህርቶችና የክብር መዝሙራት በዋናነት የሚያተኩሩት፦ በመከራ ውስጥ ስለመጽናት፥ ስለ ሰማዕትነት ክብር፥ ስለ ጌታ ዳግም ምጽአት ተስፋ፥ ራስን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር አሳልፎ ስለመስጠትና በምድራዊ ስደት ፊት እምነትን ስላለ መካድ በሚሉ እጅግ ጽኑና ጥልቀት ባላቸው መንፈሳዊ ጭብጦች ላይ ብቻ ነበር። ምክንያቱም በወቅቱ ቤተ ክርስቲያን በድብቅ በቤት ውስጥ (በከርሰ-ምድር) የምትጸልይና በከባድ የመንግሥት ግርፋትና እስራት ውስጥ ያለች በመሆኗ፥ ሕዝቡን ከመሸሽ የሚጠብቅና የሚያጸና ቃል እጅግ ያስፈልጋት ነበር። በአንጻሩ ግን አብያተ ክርስቲያናት ምንም ዓይነት የመንግሥት ስደት በሌለበትና ሙሉ ነጻነት አግኝተው በገሃድ በሚያመልኩበት በአሁኑ ዘመን የሚጻፉ መጻሕፍትና ስብከቶች አብዛኛውን ጊዜ የሚያተኩሩት፦ ስለ ምድራዊ ስኬት፥ ስለ በረከት፥ ስለ ማኅበራዊ ኑሮ መሻሻል፥ ስለ አመራርና ስለ ቤተ ክርስቲያን ድርጅታዊ ዕድገት ላይ ነው። ይህ ታሪካዊ ሐቅ የወንጌላትን አጻጻፍ ምስጢር በሚገባ እንድንረዳ ታላቅ ብርሃን ይሰጠናል፦ አራቱ ወንጌላውያን (ማቴዎስ፥ ማርቆስ፥ ሉቃስ፥ ዮሐንስ) ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት የጻፉት እንዲሁ ታሪኩን በባዶ ለመዘገብ ብቻ አልነበረም፤ ይልቁንም በዘመናቸው የነበሩት አማኞች የሚጋፈጡትን ታላቅ የፖለቲካና የሃይማኖት ውጥረት (የሮምን ከባድ ስደትና የአይሁድን ብሔርተኝነት ቁጣ) በሚገባ ይመለከቱ ነበር። ስለሆነም እግዚአብሔር አምላክ ያዘጋጃቸውንና በዘመኑ ለሚነሱት ከባድ ችግሮች ፍጹም መለኮታዊ መፍትሔና መጸናኛ የሚሆኑትን የተወሰኑ የኢየሱስን ታሪኮች፣ ተአምራትና ትምህርቶች ብቻ ጸሐፊዎቹ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት መርጠው በወንጌላቸው ውስጥ በጥንቃቄ እንዲያሰፍሩ አደረጋቸው (ዮሐ. 20:30-31)። ለዚህ ነው የማቴዎስ ወንጌል አማኞች በፈተናና በውጥረት ዘመን እምነታቸውን እስከ ፍጻሜው እንዲጠብቁ የሚያበረታቱትን እንደ ማቴዎስ 10፡22 ያሉትን ጽኑ የጌታን ትምህርቶች ለይቶ የዘገበው። የማቴዎስ ወንጌል የተጻፈበት ዘመንና ስፍራ ቀደም ሲል በሰፊው እንደተገለጠው ሁሉ፥ ነገረ-መለኮት ምሁራን የመጀመሪያውን የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ (የማቴዎስን ወንጌል) በትክክል ማን እንደጻፈውና መቼ እንደጻፈው በተለያዩ ታሪካዊ መረጃዎች መነሻነት ይከራከራሉ። አንዳንድ ታዋቂ ምሁራን የማቴዎስ ወንጌል በአጠቃላይ በመጀመሪያ የተጻፈ የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ነው ብለው በጽኑ ይናገራሉ። መጽሐፉ ሙሉ በሙሉ በአይሁድ ሕዝብ እምነትና በብሉይ ኪዳን ትንቢት ፍጻሜዎች ላይ አጥብቆ ስላተኮረ፥ መጽሐፉ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ሩቅ አሕዛብ አገሮች በስፋት ከመስፋፋቷና የኢየሩሳሌም ጉባኤ ከመደረጉ በፊት ሳይጻፍ እንዳልቀረ በምክንያት ያስረዳሉ፤ ስለሆነም መጽሐፉ እጅግ ቀድሞ ከ 50 እስከ 55 ዓ.ም. ባለው የታሪክ ጊዜ ውስጥ እንደተጻፈ ይገምታሉ። የማቴዎስ ወንጌል የማርቆስን ወንጌል ታሪካዊ መዋቅር ከመረጃ ምንጮቹ አንዱ አድርጎ እንደተጠቀመ የሚያስተምሩት ሌሎች ምሁራን ግን፥ መጽሐፉ ከ 55 እስከ 65 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ እንደተጻፈ በታሪክ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ ሁለቱም ወገኖች የሚስማሙበት ታላቅ ታሪካዊ ሐቅ፦ የማቴዎስ ወንጌል አይሁዶች በ 66 ዓ.ም. በሮም ጨካኝ አገዛዝ ላይ በከፍተኛ ቁጣ ከማመጻቸውና ጦርነት ከመጀመራቸው አስቀድሞ፥ በ 60 ዓ.ም. አካባቢ ተጽፎ የተጠናቀቀ መለኮታዊ መጽሐፍ መሆኑን ነው። ሐዋርያው ማቴዎስ ይህንን ታላቅ ወንጌል በሚጽፍበት የታሪክ ሰዓት በትክክል በየትኛው ከተማና ምድር ላይ ይኖር እንደነበረ ዛሬ በእርግጠኝነት ለማወቅ የሚያስችል ግልጽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ ባይኖርም፥ መጽሐፉ የተጻፈው ግን በመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ውስጥ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ይህ መጽሐፍ ከሌሎቹ ሦስቱ ወንጌላት ሁሉ ይበልጥ እጅግ የላቀና የጠነከረ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የአይሁዳዊነት ጠረንና ይዘት ስላለው፦ ምንጭ፦ «የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ»፣ በኤስ.አይ.ኤም (SIM) ጽሑፍ ክፍል የታተመና የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው። ለዚህ አስደናቂና ለቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ለሚሆን ታላቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር አምላክ ዘመናቸውንና አገልግሎታቸውን አብዝቶ ይባርክ።

ማቴዎስ ወንጌሉን የጻፈበት ጊዜና ቦታ Read More »

ማቴዎስ ወንጌሉን የጻፈው ለማን ነው?

በመጀመሪያዎቹ 100 የቤተ ክርስቲያን ዓመታት ውስጥ፥ የማቴዎስ ወንጌል በአማኞች ዘንድ እጅግ በጣም ተወዳጅና ተፈላጊ መጽሐፍ ነበር። የዓይን ምስክር በነበረ ቀጥተኛ ሐዋርያ (በቀራጩ ማቴዎስ) የተጻፈ በመሆኑ፥ በጉባኤ መካከል እጅግ ታላቅ መለኮታዊ ሥልጣንና ክብር ያለው ወንጌል እንደሆነ ይታሰብ ነበር። ስለሆነም የጥንቷ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ብዙውን ጊዜ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነትና ስላስተማረው ሰማያዊ አሳብ ለሕዝቡ በሚያብራሩበትና በጽሑፍ በሚመልሱበት ጊዜ፥ ከሁሉ በላይ ከማቴዎስ ወንጌል ገጽ ላይ በስፋት ይጠቅሱ ነበር። የማቴዎስ ወንጌል በአጠቃላይ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ከሚገኙት 27ቱ መጻሕፍት ሁሉ የላቀና የጠነከረ የአይሁዳዊነት ባሕርይ አለው። ማቴዎስ ራሱ አይሁዳዊ እንደ መሆኑ መጠን፥ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ወንጌሉን ሲጽፍ ቀዳሚና ዋነኛ አንባቢዎቹ አድርጎ የመረጠው የገዛ ወገኖቹን አይሁዳውያንን እንደነበረ የታሪክ ሐቁ ያሳያል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ የአይሁድ ዘር ሆኖ መምጣቱን መነሻ በማድረግ አንዳንድ የስነ-ጽሑፍ ምሁራን፦ የማቴዎስ ወንጌል ክርስቶስ ስለኖረበትና ስላስተማረበት እውነተኛ ማኅበራዊ ሁኔታ ከሁሉም የበለጠ ፍጹም ሚዛናዊና ትክክለኛ አመለካከት የሚያቀርብ መጽሐፍ ነው ይላሉ። ማቴዎስ ክርስቶስ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ፍጻሜ የሆነው እውነተኛው ንጉሥና መሢሕ መሆኑን፥ በክህደት ላሉትና ለማያምኑት አይሁድ ወገኖቹ በኃይል ለማካፈልና ለማረጋገጥ በጥብቅ ፈልጓል። ስለሆነም ማቴዎስ ከየትኛውም የአዲስ ኪዳን ጸሐፊ በላይ ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ትንቢቶችን በቀጥታ እየመዘዘ በስፋት በጥቅስነት ተጠቅሟል። በተጨማሪም ማቴዎስ አይሁድ ብቻ የሚረዷቸውን ልዩ ሃይማኖታዊ አገላለጾችን በወንጌሉ ውስጥ በጥንቃቄ ተጠቅሟል፤ ለምሳሌ ያህል አይሁዶች የእግዚአብሔርን ቅዱስ ስም ያለ አግባብ ላለመጥራት ከነበራቸው ጥንቃቄ የተነሳ፥ እርሱም እንደ ማርቆስና ሉቃስ አሕዛባዊ አገላለጽ «የእግዚአብሔር መንግሥት» ከማለት ይልቅ፥ እግዚአብሔር የሚለውን ስም በሰማይ ተክቶ «የሰማይ መንግሥት» (Kingdom of Heaven) የሚለውን ልዩ ቃል በተደጋጋሚ ተጠቅሟል። ዓለም አቀፋዊው የወንጌል ተልእኮ የማቴዎስ ወንጌል ለአይሁዳውያን ክርስቲያኖችም ቢሆን በምድር ላይ መከራና ውጥረት ባለበት ዘመን ክርስቶስን በታማኝነት መከተልና ደቀ-መዝሙር መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ በግልጽ ያስተማረ መለኮታዊ መመሪያ ነው። ነገር ግን ማቴዎስ በወንጌሉ ውስጥ በጥልቀት ከሚያስተምራቸው ታላላቅ መለኮታዊ እውነቶች መካከል ዋነኛው፦ እግዚአብሔር በደሙ የመሠረታት አዲሲቱ ቤተ ክርስቲያን ከአይሁድ ወገን ብቻ የተገነባች ጠባብ ማኅበር ሳትሆን፥ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ በአንድነት የሚሰበሰቡባት ሁለንተናዊ መለኮታዊ አካል መሆኗን ማብራራት ነው (ማቴ. 16:18)። ስለሆነም ምንም እንኳ ማቴዎስ ወንጌሉን መጀመሪያ ለአይሁድ ወገኖች ቢጽፈውም፥ የክርስቶስ ማዳን ታሪክ ግን አይሁዳውያን ላልሆኑት ለአሕዛብ ክርስቲያኖች ጭምር ፍጹም የሚሠራ የጸጋ ስጦታ መሆኑን በብዙ ታሪካዊ ክስተቶች አብራርቷል፦ ወንጌሉ የተጻፈበት ቋንቋ ማቴዎስ ወንጌሉን መጀመሪያ በምን ዓይነት ቋንቋ እንደጻፈው የምሁራን ክርክር ያለበት ጉዳይ ነው። ከጥንት የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች መካከል ግንባር ቀደሙ የነበረው ሊቁ ፓፒያስ (Papias) እንደመሰከረው፦ ሐዋርያው ማቴዎስ ወንጌሉን መጀመሪያ የጻፈው በዕብራውያን ወገኖች ዘንድ ይነገር በነበረው በአረማይስጥ ቋንቋ እንደነበረና ከዚያ በኋላ ግን ወደ ግሪክ ቋንቋ እንደተረጎመው ገልጿል። ነገር ግን ዛሬ ያሉ አብዛኞቹ ወንጌላውያን ምሁራን መጽሐፉ የያዘውን ከፍተኛ የግሪክ ሥነ-ጽሑፍ ጥራትና መዋቅር በመመልከት፥ በሰፊው የሮም ግዛት የነበሩት አይሁድም ሆኑ አሕዛብ ሁሉ በአንድነት በቀላሉ ያነቡት ዘንድ፥ ማቴዎስ ወንጌሉን መጀመሪያውኑ በይፋ የጻፈው በኮይኔ ግሪክ ቋንቋ እንደነበረ በጽኑ ያምናሉ። የብሔርተኝነት ፈተና እና የአይሁድ ክርስቲያኖች ታላቅ ውጥረት ማቴዎስ ወንጌሉን በሚጽፍበት በዚያ ታሪካዊ ዘመን፥ በይሁዳ ምድር የነበሩት አይሁድ በብሔርተኝነት ስሜት ተቀስቅሰው የሮምን ጨካኝ አገዛዝ በጦርነት ገርስሰው ለመጣልና እንደገና የዳዊትን ነፃ ምድራዊ መንግሥት ለመመሥረት በከፍተኛ ቁጣ ጥረት ያደርጉ ነበር። በብሉይ ኪዳን ትንቢት የተነገረላቸው እውነተኛ መሲሖች እኛ ነን እያሉ ሕዝቡን በውሸት የሚያታልሉ በርካታ የጦር አማፂያን መሪዎችም በየበረሃው በኃይል ተነስተው ነበር። በጥቂት ዓመታት ውስጥ ይህ የአማፂያኑ ጽንፈኛ ተቃውሞና በሮማውያን ላይ የነበራቸው መራራ ጥላቻ፥ ከመላው የሮም መንግሥት ጋር ወደተደረገ ታላቅ ግልጽ የትጥቅ ጦርነት መራቸው። ነገር ግን ታሪክ እንደሚያረጋግጠው ሮማውያን የአይሁዶችን ተቃውሞ በጭካኔ በመምታትና በመደምሰስ፥ በ 70 ዓ.ም. ቅድስት ከተማዋን ኢየሩሳሌምን፥ የከተማዪቱን ቅጥሮችና ታላቁን የይሖዋ ቤተ መቅደስ ሙሉ በሙሉ አፈራረሱት። በዚህ ከባድ የታሪክ ቀውስና ፍልሚያ ውስጥ፥ በይሁዳ ምድር ይኖሩ በነበሩት በአይሁድ ክርስቲያኖች መካከል እጅግ ከፍተኛ የሆነ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ውጥረት ተከስቶ ነበር፤ አማኞቹ በሕይወታቸው ሁለት ታላላቅ ውሳኔዎችን ለማድረግ በጽኑ ይገደዱ ነበር፦ ስለሆነም የአይሁድ አማኞች ከእነርሱ ጋር የሥጋ ጎሣና ብሔር የሆኑትን አይሁዶችን በዓለማዊው የጦርነት መስፈርት መደገፍ? ወይስ ለእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈሳዊ ቤተሰብ (ለቤተ ክርስቲያን) ያላቸውን ታማኝነት በማስቀደም አብዛኞቹ አይሁዶች ከሚያደርጉት የጥላቻና የዓመፅ መንገድ ሙሉ በሙሉ ተለይቶ መቆም? ለሚለው ጥያቄ ከባድ ምርጫ ማድረግ ነበረባቸው። በአሕዛብ አማኞች ላይ ጀርባቸውን ሳይሰጡና ሳይለዩ፥ እንዴት ታማኝ አይሁዳዊነታቸውን ለወገኖቻቸው ማሳየት እንደሚችሉ ማወቅ እጅግ አስቸጋሪ ሆኖባቸው ነበር። ስለሆነም አንዳንዶቹ ደካማ አማኞች ለገዛ ወገኖቻቸው «እኛም እኮ የሙሴን ሕግ የምንከተል ታማኝ አይሁድ ነን» ብለው ለማረጋገጥ ሲሉ፥ በክርስቶስ ያመኑት የአሕዛብ ክርስቲያኖች ሁሉ የግድ እንደ አይሁድ መገረዝ አለባቸው የሚል የሐሰት ሕግ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በጥበብ መጠየቅ ጀመሩ (ሐዋ. 15፡1)። ታማኙ ሐዋርያ ማቴዎስ ወንጌሉን በይፋ ጽፎ ያበረከተው፥ በትክክል ሕዝቡ በዚህ ከባድ የፖለቲካና የማኅበራዊ ፈተና ውጥረት ውስጥ በነበረበት ታሪካዊ ወቅት ነበር። ማቴዎስ ወንጌሉን የጻፈበት ዋነኛው መለኮታዊ ዓላማ፦ ማቴዎስ በአገሪቱ ባለው በዚህ ከባድ የፖለቲካ ውጥረትና የጎሳ ጥላቻ ምክንያት፥ የአይሁድ ክርስቲያኖች የወንጌል እውነታቸውንና የክርስቶስን ፍቅር ፈጽመው እንዳይጥሉ በቃሉ በጥብቅ አስጠነቀቃቸው። በምድር ላይ ምንም ዓይነት መከራና ስደት ቢመጣባቸውም እንኳ፥ ሰማያዊውን የድል አክሊል ለማግኘት እስከ ፍጻሜው ድረስ እምነታቸውን በጽናት መጠበቅ እንዳለባቸው በጌታ ቃል አበከረላቸው፦ «እስከ መጨረሻው የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።» (ማቴ. 10፡22)። ማቴዎስ በወንጌሉ በግልጽ እንዳሳየው፥ እግዚአብሔር ለአሕዛብ ድነት የወጠነው ዘላለማዊ የጸጋ ዕቅድ፥ አሕዛብን መጥላትን ወይም እነርሱ በግድ አይሁዳዊ እንዲሆኑ ማስገደድን ፈጽሞ አይጨምርም ነበር። አይሁድ ራሳቸውም ቢሆኑ በክርስቶስ እውነተኛ መሢሕነትና ጌትነት ካላመኑ በስተቀር፥ የሥጋ ትውልድ ስላላቸው ብቻ የእውነተኛው የእግዚአብሔር ሕዝብ አካል መሆን ፈጽሞ እንደማይችሉ በሥልጣን አስተማረ። 👥 የውይይት ጥያቄ እና ተግባራዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልስ ፩. የውይይት ጥያቄ፦ ዛሬ በአገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ዘመናትና ወቅቶች የጎሳ (የብሔር) ፖለቲካ ውጥረትና ማኅበራዊ ግጭቶች በኃይል በሚነሱበት አስቸጋሪ ወቅት ላይ፥ ብዙ ወንጌላውያን ክርስቲያኖች በጥንቱ ዘመን የአይሁድ ክርስቲያኖች የገጠማቸውን ዓይነት ፍጹም አስከፊና ከባድ መንፈሳዊ ውግያ በልባቸው ይጋፈጣሉ። በማኅበረሰቡ መካከል የጎሳ መከፋፈልና ቁጣ በሚገነፍልበት ጊዜ፥ አንዳንድ አማኞች ከእግዚአብሔር ቃል እውነት ወጥተው ለገዛ ሥጋዊ ብሔራቸው ጥቅም መጮኽ፥ ጥላቻን መዝራትና ወገንተኝነትን ማሳየት ይጀምራሉ፤ ይህንን ባያደርጉ ግን በሥጋ ወገኖቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ዘንድ «የጎሳችንን ጠላት የምትደግፍ ከሃዲ ነህ» ተብለው መገለልና ከባድ ስደት ይደርስባቸዋል። ነገር ግን እኛ በጴንጤቆስጤ (በወንጌላውያን) እምነታችን የምናውቀውና የምንናገረው ፍጹም የጸና የመጽሐፍ ቅዱስ መርሕ አለ፦ አንድ አማኝ በክርስቶስ ደም ዳግም ተወልዶ የእግዚአብሔር ቤተሰብ አካል በሚሆንበት ቅጽበት፥ ከምድራዊው የሥጋ ጎሳና የደም ዝምድና በላይ — በክርስቶስ ደም የተመሠረተው ሰማያዊው የመንፈስ ቅዱስ ዝምድና (ቤተ ክርስቲያን) ከምንም ነገር በላይ የእርሱ ብቸኛውና ዋናው ዘላለማዊ ቤተሰቡ ይሆናል (ማቴ. 12:48-50)። ስለሆነም በአገራችን ውስጥ የብሔር ውጥረቶች በሚከሰቱበት በማንኛውም ጊዜ አማኝ ክርስቲያን ሊያሳየው የሚገባው ታማኝነት የሚከተለው መሆን አለበት፦ የማቴዎስ ወንጌል በታሪክ እንደሚያስተምረን፥ እኛ ምድራዊ ጥቅማችንንና የሥጋ ወገኖቻችንን አስደስተን ለእግዚአብሔር መንግሥት ታማኝ መሆን ፈጽሞ አንችልም፤ የሰላሙ ንጉሥ ክርስቶስ የሞተለት እውነተኛው ፍቅር የዘርና የጎሳ ልዩነት ሳይደረግበት አማኞች ሁሉ በአንድ መንፈስ ቅዱስ የታሸጉበት ታላቁ ሰማያዊ ቤተሰብ ነው (ኤፌ. 4:3-5)። ስለዚህ እያንዳንዱ አማኝ በዚህ የፈተና ዘመን በኢትዮጵያ ውስጥ በሚነሱ የብሔር ውዝግቦች ሳቢያ እምነቱንና የክርስቶስን ፍቅር እንዳይጥል፥ እስከ ፍጻሜው ድረስ የወንጌሉን የቅድስና እውነት ብቻ አጥብቆ መያዝ ይኖርበታል። ምንጭ፦ «የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ»፣ በኤስ.አይ.ኤም (SIM) ጽሑፍ ክፍል የታተመና የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው። ለዚህ አስደናቂና ለቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ለሚሆን ታላቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር አምላክ ዘመናቸውንና አገልግሎታቸውን አብዝቶ ይባርክ።

ማቴዎስ ወንጌሉን የጻፈው ለማን ነው? Read More »

የማቴዎስ ወንጌል ጸሐፊ

ለአዲስ ኪዳን መጻሕፍት መጀመሪያ የተሰጠው ይፋዊ ስያሜ «የማቴዎስ ወንጌል» የሚል ነው። ይህ ታላቅ ስያሜ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ስለሚገኘው ስለ መጀመሪያው መጽሐፍ ሁለት ዐበይት መንፈሳዊ ቁም ነገሮችን በግልጽ ያስጨብጠናል፦ የዘመናችን ነቃፊ ምሁራን ለመጽሐፉ የተሰጠውን ይህንን ስያሜ «ማቴዎስ በገዛ እጁ ይጻፈው ወይም አይጻፈው እርግጠኞች አይደለንም፤ ስያሜው በኋላ የተጨመረ ነው» እያሉ ለመጠራጠር ይሞክራሉ። ነገር ግን «የማቴዎስ ወንጌል» የሚለው የክብር መጠሪያ፥ የመጀመሪያው ወንጌል ተጽፎ ከተጠናቀቀ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን እንደተጨመረ የሚያመለክቱ ጽኑ ታሪካዊ ማስረጃዎች አሉ። ለምሳሌ በ 125 ዓ.ም. ተባዝቶ ይገኝ የነበረው እጅግ ጥንታዊው የማቴዎስ ወንጌል የብራና ቅጂ «የማቴዎስ ወንጌል» የሚል መጠሪያ በይፋ ነበረው። ይህም የመጀመሪያው ወንጌል የክርስቶስ ቀጥተኛ ሐዋርያ በሆነው በማቴዎስ እጅ እንደተጻፈ የሚያመለክተውን የመጀመሪያዎቹን ቅዱሳን አማኞች አመለካከትና ታሪካዊ ሐቅ በጽኑ ያጠናክረዋል። ከቅርብ ዘመናት ወዲህ አንዳንድ የዓለማውያን ምሁራን መጽሐፉ በማቴዎስ መጻፉን መጠራጠር በመጀመር፥ «መጽሐፉ የዓይን ምስክር በነበረ ሰው የተጻፈ አይመስልም፤ ከሐዋርያት ሞት በኋላ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተከሰቱትን ድርጅታዊ ሁኔታዎች ይጨምራል» እያሉ በሐሰት ያስረዳሉ። ነገር ግን ይህ መጽሐፍ የጥንቷ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከመጀመሪያው ጀምሮ በጽኑ እንደምታምነውና ታሪኩም እንደሚያረጋግጠው፥ የክርስቶስ እውነተኛ ሐዋርያ በነበረው በማቴዎስ (በሌዊ) እጅ እንደተጻፈ የሚያመለክቱ እጅግ ጠንካራና የማይናወጡ የውስጥና የውጭ መረጃዎች አሉ። የቀራጩ ሌዊ (ማቴዎስ) ማኅበራዊ ሕይወት ማቴዎስ በሰውኛ ደካማ አስተሳሰብና በዓለም ሚዛን ቢታይ፥ ሐዋርያ መሆኑ ቀርቶ በአዲስ ኪዳን ውስጥ እጅግ ጠቃሚና መሠረታዊ ከሆኑት መጻሕፍት መካከል የመጀመሪያውን ታላቅ ወንጌል ለመጻፍ ፈጽሞ ብቁ የሆነ ሰው አይመስልም ነበር። ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ሉዓላዊው እግዚአብሔር በጸጋው የሚሠራው፥ እኛ ሰዎች በሥጋዊ አእምሯችን በምናስበውና በምንጠብቀው ጠባብ መንገድ አይደለም። ለዚህ ነው አስደናቂው መንፈስ ቅዱስ ቀራጩን ማቴዎስን መርጦ የመጀመሪያው ወንጌል ከበር ጸሐፊ እንዲሆን ያደረገው። ቀድሞ «ሌዊ» ይባል የነበረው ማቴዎስ በዘሩ ንጹሕ አይሁዳዊ ነበረ (ማር. 2፡14)። ነገር ግን በምድራዊ ኑሮውና በሃይማኖታዊ ሕይወቱ በሕዝቡ ዘንድ የተከበረ አጥባቂ አይሁዳዊ አልነበረም። ማቴዎስ በሮም አገዛዝ ሥር በነበረችው በገሊላ አውራጃ በቅፍርናሆም ከተማ አጠገብ፥ ዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮችንና ጎዳናዎችን አቋርጠው በሚያልፉ ነጋዴዎች ላይ የመንግሥትን የጉምሩክ ቀረጥና ግብር የሚሰበስብ ቀራጭ ነበረ። ማቴዎስ ይህንን ትልቅ የገንዘብ ጥቅም ያለበትን የሥራ መደብ ለማግኘት፥ የአሕዛብን መሪዎችና የሮማውያንን የፖለቲካ ባለሥልጣናት በቅርብ መወዳጀትና ማገልገል ነበረበት። ብዙውን ጊዜ ይህንን የቀራጭነት ሥራ ማግኘት የሚቻለው ለአሕዛብ መኳንንት ወይም ለሮም ሹማምንት እጅግ ከፍተኛ የገንዘብ ጉቦ በመስጠት ብቻ ነበር። ምንም እንኳን አይሁዶች ቀራጮችን እንደ አገር ከሃዲና እንደ ኃጢአተኞች አጥብቀው ቢጠሏቸውም፥ ማቴዎስ ግን ምድራዊ ገንዘብንና ሀብትን አብዝቶ በመውደዱ ምክንያት፥ የሮም ባለሥልጣናት ለዚህ የጥቅም ሥራ እንዲመርጡት ሲል የገዛ ይሁዳዊ ክብሩን አዋርዶ የአባቶቹን ጥብቅ የአይሁድ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ሙሉ በሙሉ ለመተው በልቡ ወስኖ ነበር። ስለሆነም ከአሕዛብ ጋር የነበረውን ስግብግብ ወዳጅነት የሚጠሉ አይሁዳውያን ወገኖቹ ሁልጊዜ በምኩራብ ፊት ሲያዩት ይተፉበት፥ ያላግጡበትና እንደ ረከሰ ሰው አጥብቀው ይንቁት ነበር። በጥንቱ ታሪክ አብዛኞቹ ቀራጮች የሮም መንግሥት ከደነገገው በላይ ከተጓዥ ነጋዴዎች ላይ በግፍ ተጨማሪ ገንዘብ ለመቀማት በስግብግብነት ይሮጡ ነበር። ለምሳሌ ሮማውያን ከአንድ ተጓዥ ነጋዴ ላይ 100 ብር ቀረጥ እንዲቀበሉ ቢያዟቸው፥ ቀራጮቹ ነጋዴው መቶውን ብር በፍጥነት ከመክፈል ነፃ የሚሆንበትን የውሸት መንገድ ለማመቻቸት ጉቦ ይቀበሉ ነበር፤ ወይም ደግሞ በተንኮል ተጨማሪ 20 ብር በላዩ ላይ በመጠየቅ፥ በጠቅላላው 120 ብር እያስገደዱ ያስከፍሉት ነበር። የሮም ባለሥልጣናት የጠየቁትን ዋናውን 100 ብር ከቀራጩ እጅ በትክክል ከተቀበሉ፥ ያ ቀራጭ ከተራው ነጋዴ ላይ በግፍ ምን ያህል ተጨማሪ ገንዘብ እንደሰበሰበና እንደበዘበዘ ምንም ዓይነት ግድ አይሰጣቸውም ነበር። ፩. የውይይት ጥያቄ፦ ዛሬ በአገራችን በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ዘንድ ብዙ ሰው በምግባራቸውና በሥራቸው ምክንያት አጥብቆ የሚጠላቸውና የሚያገላቸው ሰዎች ምን ዓይነት ምድራዊ ሕይወት ያላቸው ወገኖች ናቸው? ዛሬ ያሉ የወнጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ምእመናንና መሪዎች፥ እንደዚህ ዓይነት መጥፎ ታሪክ የነበራቸውን ሰዎች ለቤተ ክርስቲያን መሪነት ወይም ለአገልግሎት መድረክ በፍጥነት ማጨት ፈጽሞ የማይፈልጉበትና የማይመርጡበት መሠረታዊ ምክንያት ምንድን ነው? (ለምሳሌ፦ በአሁኑ ዘመን በከተማ ያለች አንዲት የታወቀች ሴተኛ አዳሪ ወደ ወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያን መጥታ በክርስቶስ መስቀል ጸጋ አምና መንፈሳዊ ሕይወት ለመጀመር ብትፈልግ፥ በውስጥ ያሉ የዳኑ ምእመናን መጀመሪያ የሚኖራቸው እውነተኛ ስሜትና ምላሽ ምን ይሆናል? በክርስቶስ ካመነች በኋላስ በጉባኤ መካከል ከእርሷ ጋር በቅንነት የሚዛመዱትና የሚቀበሏት እንዴት ነው? ከእርሷ ጋር በቤታቸው እውነተኛ መንፈሳዊ ጓደኛ ለመሆን ከልባቸው ይፈቅዳሉ?) የማቴዎስ አስደናቂ ጥሪና ዋጋ ያስከፈለው መለኮታዊ ምርጫ አንድ ቀን የሰላሙ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ማቴዎስ በተቀመጠበት በቀረጥ መቀበያ ስፍራ አጠገብ እያለፈ ሳለ፥ ቆም ብሎ በሉዓላዊ ሥልጣኑ እርሱን እንዲከተለው በግልጽ ጠየቀው (ማቴ. 9፡9)። ከዚያ የታሪክ ቅጽበት በፊት ማቴዎስ ራሱ ፈልጎ የክርስቶስ ደቀ-መዝሙር ለመሆን እንደሞከረ የሚያመላክት ምንም ዓይነት ቀዳሚ የታሪክ መረጃ የለም። ነገር ግን ማቴዎስ በቅፍርናሆም ከተማ ውስጥ ይኖር እንደነበረ ሰውነቱ፥ የኢየሱስን ታላቅ መለኮታዊ ማንነትና ተአምራት አስቀድሞ ሳይሰማና ሳያውቅ ፈጽሞ አልቀረም፤ ምክንያቱም ክርስቶስ በቅፍርናሆም ከተማ በስፋት ከማስተማሩና ከማገልገሉ በላይ፥ ሰማያዊ ትምህርቱና ድንቅ ተአምራቱ የብዙዎችን ልብ አናውጦ ነበር። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ማቴዎስ በቀጥታ በመቅረብ በተመለከተው ጊዜ፥ በማቴዎስ ልብ ውስጥ በገንዘብ ሊሞላ ያልቻለውን ታላቅ መንፈሳዊ ባዶነት፥ በምድራዊ ሀብት ውስጥ ሆኖም ሕይወቱን ከእውነተኛው አምላክ ጋር ለማስተካከልና በገዛ ወገኖቹ ዘንድ በየዕለቱ ከመናቅና ከመገለል ለመዳን በውስጡ በጥልቀት ይናፍቅ እንደነበር መለኮታዊ ዓይኑ ተመልክቶ ነበር። ክርስቶስ «ተከተለኝ» ብሎ በሥልጣን በጠራው ጊዜ፥ ማቴዎስ በሕይወቱ እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ታላቅ መለኮታዊ ምርጫ ፊት በአንድ ጊዜ ወደቀ፦ ፪. የውይይት ጥያቄ፦ ሁሉን ትቶ መከተል እና የቀድሞ ባልደረቦችን መጥራት ቀራጩ ማቴዎስ የክርስቶስ እውነተኛ ደቀ-መዝሙር ለመሆን በቆረጠ ጊዜ፥ የነበረውን ትልቅ ምድራዊ ሀብትና ወንበሩን ሁሉ በአንድ ጊዜ በትሕትና ተወ። ማቴዎስ ከዘመናት በኋላ በገዛ እጁ ወንጌሉን በጻፈበት ወቅት፥ ክርስቶስን መከተል በምድር ላይ ምን ያህል ታላቅ ሥጋዊ ዋጋና መሥዋዕትነትን እንደሚያስከፍል አማኞችን አጥብቆ ለማስተማር የፈለገው (ማቴ. 16:24)፥ ምናልባትም ራሱ በሕይወቱ ከከፈለው ከዚህ ታላቅ መለኮታዊ ተሞክሮ በመነሳት ሳይሆን አይቀርም። ምክንያቱም ክርስቶስን በታማኝነት መከተል በምድር ላይ ጊዜያዊ ሥጋዊ ድህነት ወይም መከራ ቢኖርበትም እንኳ፥ በሰማይ ግን ሊለካ የማይችል ዘላለማዊ ክብርና እውነተኛ የሕይወት ሰላምን ያስገኛል። ማቴዎስ ክርስቶስን በመከተሉ የቀድሞውን ጨካኝ የቀራጭነት ተግባሩንና የኃጢአት ኑሮውን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያቆመ ብቻ ሳይሆን፥ ይህ መለኮታዊ ጥሪ የእርሱን ጠቅላላ የሕይወት አመለካከትና መድረክ ሙሉ በሙሉ ሊለውጠው ችሏል። ማቴዎስ በልቡ ዳግም ከተለወጠ በኋላ መጀመሪያ ለማድረግ ከፈለጋቸው ታላላቅ መንፈሳዊ ነገሮች መካከል ዋናው፦ የነበሩትን የቀድሞ የኃጢአት ጓደኞቹንና ቀራጮችን በሙሉ ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ፍቅር ጋር በአንድነት ማስተዋወቅና እርሱም ከእንግዲህ ወዲህ የክርስቶስ ፍጹም ተከታይ መሆኑን በዓለም ፊት በይፋ ማወጅ ነበር። ለዚህም ታላቅ የወንጌል ዓላማ ይረዳው ዘንድ በገዛ ቤቱ ትልቅ የእራት ግብዣ በማዘጋጀት፥ የነበሩትን የሥራ ባልደረቦቹንና ቀራጮችን በሙሉ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ይዞ መጣ (ሉቃስ 5፡29)። ከዚህ ታላቅ ጥሪ ጥቂት ጊዜ በኋላ፥ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ማቴዎስን ለቤተ ክርስቲያን መሠረት ከሆኑት ከአሥራ ሁለቱ ቁልፍ ደቀ-መዛሙርት መካከል አንዱ አድርጎ በሉዓላዊ ጸጋው መረጠው (ማቴ. 10፡1-4)። እነዚህ አሥራ ሁለቱ ደቀ-መዛሙርት በኋላ ላይ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የዓለም አቀፏ ቤተ ክርስቲያን ዋና መሪዎችና የዓለም አቀፍ ወንጌል ዓምዶች ለመሆን በቅተዋል። ክርስቶስ እነዚህን መሪዎች «ሐዋርያት» (Apostles – ፍጹም ሥልጣን ያላቸው መልእክተኞች) ብሎ በመሰየም፥ በሰፊው ዓለም ውስጥ የእርሱ ሰማያዊ አምባሳደሮችና ሕጋዊ እንደራሴዎች አድርጎ በሥልጣን ሾማቸው። ማቴዎስ ከሦስት ዓመታት በላይ የክርስቶስን መለኮታዊ ትምህርት በቅርብ እየተማረና ድንቅ ተአምራቱን በዓይኑ እያየ በታማኝነት ተከትሎታል። ከሁሉ በላይ ደግሞ ከሙታን በታላቅ ክብር የተነሣውን ሕያውን ጌታ በዓይኑ የመመልከት ታላቅ ዕድል ያገኘ ሲሆን፥

የማቴዎስ ወንጌል ጸሐፊ Read More »