ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች — አዲስ ንድፍ

✦ ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

52 መሠረታዊ የክርስትና ትምሕርቶች

መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶችን በተደራጀ ቅደም ተከተል፣ አንድ ትምሕርት በአንድ ጊዜ ያጥኑ።

52 ትምሕርቶች6 ዋና ክፍሎችበራስዎ ፍጥነትበመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ
ጥናቱን ይጀምሩ →
ስለ ትምሕርቱ ያንብቡ

“ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” የሚለው መጽሐፍ  በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር ተጽፎ በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ እና በላፕስሊ ብሩክስ ፋውንዴሽን የታተመ ነው፡፡ አስቀድመን ስለ እነዚህ ቅዱሳን ትጋት እና የክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን ለማገልገል ለከፈሉት ዋጋ ምስጋናችን እናቀርባለን፡፡ በመቀጠል ጽሁፉን ኮፒ እና ፕሪንት በማድረግ ለግልም ሆነ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ማዋል የተፈቀደ ቢሆንም ያለአሳታሚው ፈቃድ ጽሁፉን መለወጥም ሆነ ለሽያጭ ማዋል ግን ፈጽሞ በሕግ የተከለከለ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ መልካም ጥናት!

ይህ መጽሐፍ የሥነ-መለኮት ሥልታዊ ትምህርትን ሙሉ በሙሉ ያሟላል በሚል አሳብ የተጻፈ አይደለም። መጠነኛና እጅግ አስፈላጊ በሆኑ መሠረታዊ የክርስትና ትምህርቶች ላይ በማተኮር፥ ጥልቅ የሆነ የሥነ-መለኮት ትምህርት የሌላቸውን አማኞች ለመርዳት የተጻፈ ነው። “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” የመገለጦች መልህቅ ነው። አስተዋይ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ በአዲስ ኪዳን ጥልቅና መሠረታዊ ትምህርት መደነቁ እርግጥ ነው (ማቴ. 7፡28፤ ዮሐ. 7፡16-17፤ ሐዋ. 2፡42፤ ሮሜ 6፡ 17፤ ኤፌ. 4፡14፤ 1ኛ ጢሞ. 1፡3፤ 4፡6፥ 16፤ 6፡1፤ 2ኛ ጢሞ. 3፡ 10፥ 16፤ 4፡2-3፤ 2ኛ ዮሐ. 9-10)። የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ የእምነት ትምህርት በሚገባ የማይረዳ አማኝ ኤፌሶን 4፡ 14 ውስጥ “እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን..” የሚለውን እውነት ይደርስበታል። ጠንካራ ናቸው የሚባሉ አማኞች በአሁኑ ጊዜ በሀሰት ትምህርት መወሰዳቸው ለዚህ ማረጋገጫ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የመለኮት ዓላማ፥ “ቃሉን ስበክ፤ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፤ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ ዝለፍና ገሥጽ፥ ምከርም፤ ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሥበት ዘመን ይመጣልና” በሚለው ቃል መሠረት የጌታ ተከታይ የሆነ ሁሉ ዝግጁ እንዲሆን ነው። በዚህ መጽሐፍ የተካተቱ ምዕራፎች በሙሉ በክብሩና በጸጋው ባለጠጋ ለሆነ ጌታ ክብር ይሆን ዘንድ በጸሎት በመታገዝ ቀርበዋል። የጌታ ልጆች የሆኑ አማኞችም “ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርትን ለመናገር ብቃት እንዲኖራቸው ያግዝ ዘንድም ይህ መጽሐፍ ተዘጋጀ። ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር

1
ትምህርት 1 ከ52

መጽሐፍ ቅዱስ፡- የእግዚአብሔር ቃል

የተለየ ትኩረት ሳይሰጥ የሚያነብ አንባቢ እንኳን መጽሐፍ ቅዱስን በሚያነብበት ጊዜ መጽሐፉ ፍጹም ልዩ መሆኑን ይገነዘባል። መጽሐፍ ቅዱስ የሰውን ልጅ የብዙ ሺህ ዓመታት ታሪክ የሚያጠቃልል ሲሆን ፥ ከአርባ በሚበልጡ በተለያዩ ዘመናትና፥ የኑሮ ሁኔታዎች ውስጥ ባለፉ ጸሐፊዎች የተጻፈ ነው። ይሁን እንጂ የማይገናኙ ልዩ ልዩ ጽሑፎች ስብስብ ሳይሆን፥ አስደናቂ ተከታታይነትና ወጥነት ያለው፥ መጽሐፍ ነው። በአማርኛችን መጽሐፍ ቅዱስ የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ድንቅ መጽሐፍ፥ በግሪክኛ “ቢብሉስ” በሚል ስያሜ ይታወቃል። እንግሊዝኛ ተናጋሪዎች “ዘ ባይብል” የሚል ስያሜ የሰጡትም ከዚህ ቃል የተነሣ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በሰዎች የተጻፈ ቢሆንም በእርግጥ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ይህ ነው ልዩ ባሕርዩ። 

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን የሚደግፉ ሁለት ማረጋገጫዎች አሉ። 1. አንዱ ውስጣዊው ማረጋገጫው ነው። ይኸውም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተመለከቱት እውነታዎች እና መጽሐፉ ራሱ ስለመለኮታዊነቱ የሚገልጠው ሲሆን፤ 2. ውጫዊው ማረጋገጫ ደግሞ፥ ልዕለ-ተፈጥሮ የሆነ ባሕርይውን የሚደግፉትና ውስጡ የተጠቀሱት እውነቶች ናቸው። 

ሀ. ውስጣዊ ማረጋገጫ 

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን በመቶ በሚቆጠሩ የንባብ ክፍሎቹ ራሱ ገልጧል (ዘዳ. 6፡6-9፥ 17-18፤ ኢያሱ 1፡8፤ 8፡32-35፤ 2ኛ ሳሙ. 22፡31፤ መዝ. 1፡2፤ 12፡6፤ 19፡7-11፤ 93፤5፤ 119፡9፥ 11፥ 18፥ 89-93፥ 97-100፥ 104-105፥ 130፤ ምሳሌ 30፡5-6፤ ኢሳ. 55፡10-11፤ ኤር. 15፡ 16፤ 23፡29፤ ዳን. 10፡21፤ ማቴ. 5፡17-19፤ 22፡29፤ ማር. 13፡31፤ ሉቃስ 16፡17፤ ዮሐ. 2፡22፤ 5፡24፤ 10፡35፤ ሐዋ. 17፡ 11፤ ሮሜ 10፡17፤ 1ኛ ቆሮ. 2፡13፤ ቆላ. 3፡ 16፤ 1ኛ ተሰ. 2፡13፤ 2ኛ ጢሞ. 2፡15፤ 3፡15-17፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡23-25፤ 2ኛ ጴጥ. 3፡15-16፤ ራእይ 1፡2፤ 22፡18)። ለማንም ግልጥ በሚሆን ሁኔታና በብዙ መንገዶች፥ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ቅዱሳት መጻሕፍት ገልጠዋል። የብሉይ ኪዳንና የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ክርስቶስም ጭምር፥ መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር ገላጭነት የተጻፈ ቃል ነው ይላሉ። ለምሳሌ መዝሙር 19፡7-11 ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑ ተገልጦ፥ ፍጹምነትንና በአንጻሩ በቃሉ አማካይነት የተለወጡ ስድስት ሰብአዊ ባሕርዮች ተመልክተዋል። ኢየሱስ ክርስቶስም ሕግ መፈጸም እንደነበረበት ገልጧል (ማቴ. 5፡17-18)። ዕብራውያን 1፡ 1-2 ውስጥም እግዚኣብሔር በብሉይ ኪዳን ለነቢያቱ፥ በአዲስ ኪዳን ደግሞ ለልጁ የተናገረ መሆኑ ተረጋግጧል። ሰው የመጽሐፍ ቅዱስን የእግዚአብሔር ቃልነት የማይቀበል የሚሆነው፥ መጽሐፉ የእግዚአብሔር ቃል ስለመሆኑ ራሱ የሚሰጠውን የተደጋገሙ መረጃዎች የማይቀበል ሲሆን ብቻ ነው። 

ለ. ውጫዊ ማረጋገጫ 

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን በራሱ የሚያስረግጥ ብቻ ሳይሆን፥ ተጠራጣሪዎችን እንኳን ለማሳመን በሚችሉ ብዙ መረጃዎች የተሞላ ነው። 

1. የመጽሐፍ ቅዱስ ተከታታይነት ወይም ወጥነት። ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ከተገለጡት እጅግ አስገራሚ እውነቶች አንዱ፥ ወደ 1600 ዓመታት በሚጠጋ ጊዜ ውስጥ በኖሩና ከአርባ በላይ በሚሆኑ የተለያዩ ሰዎች የተጻፈ መሆኑ ነው። ይሁን እንጂ መጽሐፉ የስድሳ ስድስት መጻሕፍት ስብስብ ሳይሆን፥ አንድና ወጥ ነው። ጸሐፊዎቹ ከተለያየ ማኅበራዊ መሠረት የመጡ ናቸው፤ ነገሥታት፥ ጭሰኞች፥ ፈላስፋዎች፥ ዓሣ አጥማጆች፥ ሐኪሞች፥ የመንግሥት ባለሥልጣናት፥ ምሁራን፥ ባለቅኔዎች እና ገበሬዎች ነበሩ። እነዚህ ሰዎች በተላያዩ ባሕሎችና ልምዶች መኖር ብቻ ሳይሆን፥ የተላያዩ ባሕርያትም ነበሯቸው። ቢሆንም መጽሐፍ ቅዱስ ከዘፍጥረት እስከ ራእይ በግልጥ የሚታይ ተከታታይነትና ወጥነት አለው። 

የመጽሐፉ ተከታታይነት ከአሁኑ ዓለም አፈጣጠር እስከ አዲሱ ሰማይና ምድር መፈጠር ድረስ ባለው ታሪካዊ ቅደም ተከተል ሥርዓት ሊታይ ይችላል። ብሉይ ኪዳን ስለ እግዚኣብሔር ባሕርይ፥ ስለ ኃጢአት፥ ስለ ድነት፥ እንዲሁም እግዚአብሔር ስለ መላው ዓላም፥ ስለ እስራኤልና ስለ ቤተ ክርስቲያን ያለውን ዓላማና ዕቅድ ይገልጣል። መለኮታዊ ትምህርት ከዝቅተኛው፥ ማለት ቀለል ካለ መግቢያ ተነሥቶ እስከተወሳሰበ ትምህርትነት ደረጃ በደረጃ ይቀርባል። መጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌያዊ አገላለጦችን በቀጥተኛ ትርጉማቸው፥ ትንቢቶችን ደግሞ በተወሰነ ጊዜ ክንውናቸው ያሳያል። ከመጽሐፍ ቅዱስ ዐበይት ጉዳዮች አንዱ፥ በሰማይና በምድር እጅግ ስለከበረውና ፍጹም ስለሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በቅድሚያ መተንበይ፥ የትንቢቱን እውንነት ማመልከትና ኢየሱስን ከፍ ማድረግ ነው። ይህ አስደናቂ መጽሐፍ በሰዎች ተጻፈ ብሉ ከማመን ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ገላጭነት ተጻፈ የሚለውን መቀበሉ ይቀልላል። ስለሆነም፥ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚያምኑ ሁሉ፥ የተለያዩት የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክቶች በተለያዩ ሰዎች የተጻፉ መሆናቸውን በመቀበል፥ የመልእክቶቹን አንድ ወጥነት በመንፈስ ቅዱስ ምሪትና አነሳሽነት ይረዳሉ። 

2. የመጽሐፍ ቅዱሳዊ መገለጥ ጥልቅነት። እውነትን በመግለጥ ረገድ መጽሐፍ ቅዱስ ተመርምሮ አያልቅም። ቴሌስኮፕ የሰማይን ከፍታ እንደሚያሳይ፥ መጽሐፍ ቅዱስም የእግዚአብሔርን የእጅ ሥራዎች ከመነሻ እስከ ፍጻሜ፥ ከሰማያት ከፍታ፥ እስከ ሲኦል ጥልቀት ያመለክታል። ማይክሮስኮፕ ረቂቅ ነገሮችን እንደሚያሳይ ሁሉ፥ ረቂቁ የእግዚአብሔር ሥራ፥ ዕቅድና ዓላማው እንዲሁም የፍጥረቱ ፍጹምነት በመጽሐፍ ቅዱስ ተገልጧል። ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተካተቱት ብዙ መጻሕፍት የተጻፉት፥ ጸሐፊዎቹ ስለዘመናዊው ግኝት ግምት ባልነበራቸው ጊዜና በጥንታዊው የሰው ልጅ እውቀት ደረጃ ቢሆንም፥ በቅርቡ የተገኙት የሥነ-ምድር ምርምር ጥናቶች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን እውነቶች ከመቃረን ይልቅ ይደግፋሉ። ጥንታዊዎቹ ቅዱሳት መጻሕፍት በሚያስደንቅ አኳኋን ከዘመናዊው የሥነ-ምድር ምርምር ግኝቶች ጋር ይስማማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ዘላለማዊነት ያላቸውንና በእግዚአብሔር ብቻ የሚታወቁትን እውነቶች ስለሚገልጥ፥ ከሰው ምርምርና ግኝት በላይ የሆኑ እውነቶችን ይዟል። መጽሐፍ ቅዱስ እውነትን በሙላትና በረቂቅነት የሚያሳየንን ያህል የሚያሳይ ሌላ መጽሐፍ በዓለም የለም። 

3. የመጽሐፍ ቅዱስ የመለወጥ ኃይልና ኅትመቱ። በዓለማችን የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል ለተለያዩ ሕዝቦችና ባሕሎች በተለያዩ ኣያሌ ቋንቋዎች የታተመ ሌላ መጽሐፍ የለም። የማተሚያ መኪና እንደተፈለሰፈም ለመጀመሪያ ጊዜ የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። በዓለም ታላላቅ ቋንቋዎች ሁሉ በብዙ ሚሊዮን ቅጂዎች ታትሟል። ጽሑፍ ያለው እያንዳንዱ ቋንቋ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቢያንስ ጥቂት ክፍሎች የታተመ ነገር አለው። ምንም እንኳን እንደ ፈረንሳዊው ቮልቴር ያሉ ሃይማኖት የለሾች መጽሐፍ ቅዱስ ከአንድ ትውልድ ዕድሜ በኋላ ከአገልግሎት ውጪ ይሆናል ቢሉም፥ የሀያኛው ክፍለ-ዘመን ደራሲያንም መጽሐፉ ይረሳል ወይም ፈላጊ አይኖረውም ቢሉም፥ ካለፈው ይበልጥ በብዙ ቋንቋዎች በመታተም ላይ ነው። በተከታዮች ብዛት ከክርስትና የሚበልጡ ሌሎች ሃይማኖቶች፥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ሊወዳደር የሚችልና መገለጥ ያለው ጽሑፍ ሊያቀርቡ አልቻሉም። የመጽሐፍ ቅዱስ ሕይወትን የመለወጥ ኃይል በዘመናችንም ቀጥሏል። ላልዳነ ሰው መጽሐፍ ቅዱስ “የመንፈስ ሰይፍ” ነው (ኤፌ. 6፡17)፤ ለዳነው የሚያነጻ፥ የቅድስናና ድል አድራጊነት ኃይል ነው (ዮሐ. 17፡17፤ 2ኛ ቆሮ. 3፡ 17፥ 18፤ ኤፌ. 5፡25-26)። መጽሐፍ ቅዱስ የሕግና የሥነ-ምግባር ብቸኛው መለኮታዊ መሠረት እንደሆነ ይኖራል። 

4. የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት። የመጽሐፍ ቅዱስ ከሰው እውቀት በላይ የሆነ ባሕርይ የሚታየው፥ ሊታወቅ የማይቻልን እውነት ግልጥና እንዲታወቅ አድርጎ ማቅረቡ ነው። ዘላለምን ማለት ሰው ከመፈጠሩ በፊት የነበረውን ተፈጥሮ ሳይቀር ይገልጣል። የእግዚኣብሔር ባሕርይና ሥራዎቹም ተገልጠውበታል፡፡ እግዚኣብሔር ለዓለም፥ ለእስራኤልና ቤተ ክርስቲያን ያለው አሳብና ዘላለማዊ ዕቅዱ፥ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ትንቢት ውስጥ ተጠቃሏል። በማንኛውም ጉዳይ ላይ የሚሰጠው ገለጣ የመጨረሻ፥ ትክክልና ጊዜ የማይገድበው ነው። ሁለንተናዊ ባሕርይው ኣንባቢዎቹን ከጊዜና ከዘላለም ጋር በተዛመደ ነገር ብልሆች አድርጓቸዋል። 

5. መጽሐፍ ቅዱስ ስነ-ጽሑፍነቱ። በሥነ-ጽሑፍነቱ ሲታይ፥ መጽሐፍ ቅዱስ ምጡቅ ነው። ታሪካዊ ዘገባዎችን ብቻ ሳይሆን፥ ዝርዝር ትንቢቶችን፥ ውብ የሆኑ ቅኔዎችን፥ ልዩ ውበት ያለው ተውኔትን፥ የፍቅርና የጦርነት ታሪኮችን፥ በመጽሐፍ ቅዱሳዊው እውነት ላይ የሚነሡ ፍልስፍናዎችን ያጠቃልላል። የጸሐፊዎቹ መለያየት ከያዛቸው ጉዳዮች ስብጥር ብዛት ጋር ይስማማል። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ በዘመናት የኖሩትንና በሁሉም የእውቀት ደረጃ ላይ የነበሩትን ሰዎች የማረከ ጽሑፍ የለም። 

6. የማያዳላው የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን። መጽሐፍ ቅዱስ በሰዎች መጻፉ ለሰዎች እንዲያደላ አላደረገውም። ያለማመንታት የማንንም ኃጢአት እና ደካማነት ይገልጣል። ይህ ብቻ አይደለም፥ በራሳቸው በጎ ምግባር የሚታመኑ ፍጻሜያቸው ጥፋት መሆኑንም ያስገነዝባል። በሰዎች ብዕር ቢጻፍም፥ ከሰው ወደ ሰው ሳይሆን፥ ከእግዚአብሔር ወደ ሰው የተላለፈ መልእክት ነው። ስለ ምድራዊ ነገሮችና ስለ ሰዎች ልምምድ ቢገልጥም፥ የሰማይና የምድርን፥ የሚታዩና የማይታዩ ነገሮችን፥ ስለ እግዚአብሔር የሚገልጡ እውነቶችን፥ ስለ መላእክት፥ ስለ ሰው፥ ስለ ጊዜና ዘላለም፥ ስለ ሞትና ሕይወት፥ ስለ ኃጢአትና ድነት፥ ስለ መንግሥተ ሰማያትና ሲኦልም በግልጥነትና በሥልጣን ያብራራል። እንዲህ ያላን መጽሐፍ ሰው መጻፍ ቢፈልግ እንኳን፥ ያለመለኮታዊ ምሪት ሊጽፈው አይችልም ነበር። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ፥ ሰሰው ቢጻፍም፥ እግዚአብሔር ብቻ ከሚሰጠው እርግጠኛነት፥ ዋስትና እና ሠላም ጋር ከርሱ የተላከ ነው። 

7. የመጽሐፍ ቅዱስ ሉዓላዊ ባሕርይ። መጽሐፍ ቅዱስ፥ ከሁሉም ይልቅ እግዚአብሔር በልጁ በኩል እራሱን መግለጡን ያመለከተ፥ አካልነቱንና ክብሩን ያስገነዘበ ታላቅ መጽሐፍ ነው። እንደ ኢየሱስ ያለው ሰብእና የሟች ሰው ፈጠራ ሊሆን አይችልም፤ ምክንያቱም ፍጹምነቱ ከሁሉ የላቀ እንዲሁም ቅድስናና ጥበብ ያለው በመሆኑ የዚህ ምድር ሰው የሚገነዘበው አልነበረም። የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና ባሕርይ የኢየሱስ ክርስቶስን ታላቅ ታሪክ በመግለጥ ተረጋግጧል። 

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተካተቱት ሰብአዊና ከሰብአዊነት በላይ በሆኑ ባሕርያት ኅብረት የተነሣ፥ የተጻፈ ቃል በሆነው መጽሐፍ ቅዱስና፥ ሕያው ቃል በሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ መካከል ተመሳሳይነት ይታይ ይሆናል። ሁለቱም ከመሠረታቸው መለኮታዊ ናቸው። በመሆናቸውም የመለኮትንና የሰውን ምስጢራዊና ፍጹም ግንኙነት ይገልጣሉ። ሁለቱም በሚያምኑ ሰዎች ሕይወት ውስጥ የሚሠራ የመለወጥ ኃይል ያላቸው ሲሆን፥ የማያምኑ ሰዎችን ደግሞ እንዳይቀበሷቸው በሚፈልግ ፈቃዳቸው እንዲቀጥሉ እግዚአብሔር ትቷቸዋል። በሁለቱም ውስጥ የማይበከለውና የማይሻረው መለኮታዊ ፍጹምነት አለ። የሚገልጿቸው እውነቶች የሕፃን አእምሮ በሚገነዘበው ደረጃ ቀላል ናቸው። ያንኑ ያህል፥ ፍጻሜ የሌለው የመለኮታዊው ጥበብ እንዲሁም እውቀት ሀብቶች ሲሆኑ፥ እንደፈጠራቸው እንደ እግዚአብሔር ዘላለማዊ ናቸው።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

2
ትምህርት 2 ከ52

መጽሐፍ ቅዱስ፡- እስትንፋሰ-እግዚአብሔር

መጽሐፍ ቅዱስ፥ ጸሐፊዎቹ በእግዚአብሔር እየተመሩ የጻፉት ብቸኛ መጽሐፍ ነው። ይህ በእግዚአብሔር ምሪት መጽሐፍ ቅዱስን መጻፍ፥ እስትንፋሰ-እግዚአብሔር ይባላል። የእስትንፋሰ-እግዚአብሔር ትርጉም እግዚኣብሔር ሰብአውያን ጸሐፊዎችን ተጠቅሞ ለሰው ዘር ያለውን ሙሉና ተከታታይነት ያለውን አሳቡን ማስጻፉ ነው። ይህን ሲያደርግ ጸሐፊዎቹ እነሱነታቸውን፥ የአጻጻፍ ስልታቸውን እና የግል ሁኔታቸውን ሳይተዉ እንዲጽፉ ፈቅዷል። ጽሑፉን በማዘጋጀት ረገድ እግዚአብሔር በሰዎች መገልገሉ እውነት ነው። እነዚህ ሰዎች የሚጽፉትን ሁሉ ባይረዱም፥ በእግዚአብሔር እየተመሩ መጽሐፉን መጽሐፍ ቅዱስ ያሰኙትን ስድሳ ስድስት መጻሕፍት ጽፈዋል። እነዚህ መጻሕፍት አስገራሚ አንድነት ወይም ተያያዥነት ያላቸው ከመሆናቸውም ሌላ፥ የተጻፈው ቃል ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ መጻፉ ቋሚ ማስረጃዎች አሏቸው። 

በዚህ መሠረት መጽሐፍ ቅዱስ ምንም እንኳን በሰው ብዕር ቢጻፍ፥ ሰው ለመሰሉ ሰው የጻፈው ሳይሆን፥ እግዚአብሔር ለሰው ያስተላለፈው መልእክት ነው። መጽሐፍ ቅዱስን እግዚአብሔር ቃል በቃል አጻፈውም አላጻፈው፥ የጥንት ዘገባዎች ግልባጭ ሆነም አልሆነ፥ የሰብአዊ ጻሐፊዎች የምርምር ውጤት፥ አሳብ፥ ምኞታቸው ወይም ፍርሃታቸው ሆነም አልሆነ፥ በማንኛውም መንገድ እግዚአብሔር እርሱ የሚፈልገውን ብቻ ይጽፉ ዘንድ ጸሐፊዎቹን መርቷቸዋል። ይህ በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ በትክክል የእግዚአብሔር ቃል ነው። ምንም እንኳን የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች በአቀራረባቸው ምናልባት የሚለያዩ ቢሆኑ፥ እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እስትንፋሰ-እግዚአብሔር ነው። 

የእስትንፋሰ-እግዚአብሔር አስተምህሮ፥ ልዕለ ተፈጥሮ (supernatural) በመሆኑ፥ ለሰዎች ግንዛቤ አንዳንድ ችግሮች ያስከትል ይሆናል። እንዴት ነው አንድ ሰብአዊ ጻሐፊ በራሱ አሳብና እውቀት እየጻፈ፥ እግዚአብሔር እንዲመዘግብ የሚያዘውን ብቻ በትክክል ሊጽፍ የሚችለው? ይህን ከመሳሰሉ ጥያቄዎች የተነሣ፥ ሰብአዊው ጸሐፊው ምን ያህል በመለኮት ቁጥጥር ሥር ነበር? በሚለው ጥያቄ ላይ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰንዝረዋል። እነዚህ አስተያየቶች “እስትንፋሰ-እግዚአብሔርን አስመልክቶ የቀረቡ ንድፈ-አሳቦች” ተብለዋል። ስለሆነም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ፈቺዎች ሁሉ ከነዚህ ንድፈ-አሳቦች አንዱን ወይም ከዚያ በላይ የሆኑትን ንድፈ-አሳቦች ይከተላሉ። ተቀባይነት ያለው ንድፈ-አሳብ ለመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አፈታት ሁሉ መሠረት የሆነው ነው። ስለሆነም ስለ እስትንፋሰ እግዚአብሔር ትክክለኛ የሆነውን ንድፈ-አሳብ በጥንቃቄ መለየት ይገባል። 

ሀ. የእስትንፋሰ-እግዚአብሔር ንድፈ-አሳቦች 

1. “ቃል” እና “ምሉእ” እስትንፋሰ-እግዚአብሔር። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ትክክለኛው እስትንፋሰ-እግዚአብሔር የቃልና ምሉእ እስትንፋሰ-እግዚአብሔር ተብሎ ይገለጣል። “የቃል እስትንፋሰ-እግዚአብሔር” ትርጉሙ የመጀመሪያዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ጽሑፎች በተጻፉበት ጊዜ ጸሐፊዎቹን በቃላት አመራረጥ ሳይቀር እግዚአብሔር መርቷቸዋል ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ግን የሰውን ጸሐፊነትም ያመለክታል። የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት የጸሐፊዎቹን የግል ባሕርይ ሰአጻጻፍ ስልታቸውና በቃላት አመራረጣቸው የሚገልጡ ሲሆን፥ ማንነታቸውም ብዙውን ጊዜ በአስተሳሰባቸው፥ በአመለካከታቸውና በጸሎታቸው ወይም በፍርሃታቸው ይታወቃል። ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰብኣዊነት ቢኖርም፥ እስትንፋሰ-እግዚአብሔር፣ የተመዘገቡት ቃላት ሁሉ ከእግዚአብሔር እንዲሆን ያደርጋል። ይህ “ምሉእ” በመባል የሚታወቅ ሲሆን፥ ትርጉሙም (“ምሉእ እስትንፋሰ-እግዚአብሔር” ማለት ነው። ይህ አሳብ፥ ለመጽሐፍ ቅዱስ የተሰጠው እስትንፋሰ-እግዚአብሔር ግማሽ ነው የሚለውን አመለካከት ይቃወማል። 

ትክክለኛውና መሠረታዊው የእምነት ትምህርት ምን እንደሆነ ግልጥ ለማድረግ ብዙ ጊዜ ተጨማሪ ገላጭ ቃላት ታክለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ስሕተት የለሽና ትክክል መሆኑን ለመግለጥ፥ የማይሳሳት፥ የእውነት ቃል መሆኑን ለመግለጥ ደግሞ፥ ስሕተት ኣልባ ተብሏል። ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስ ኣንዳንድ ጊዜ እውነት ያልሆኑ ገለጣዎችን፥ ከዚያም አልፎ ዘፍጥረት 3፡4 ላይ እንደተመለከተው፥ የሰይጣንን የሐሰት ትምህርት ቢያቀርብም፥ እነዚህ ሁሉ ሰዎችን ወይም ሰይጣንን የሚያመለክቱ እንደሆኑ በግልጥ ተጠቅሷል። እግዚአብሔርም የእነዚህን ገለጣዎች እውነትነት አላረጋገጠም። መጽሐፍ ቅዱስ ቃል በቃል እስትንፋሰ-እግዚአብሔር ነው ብሎ መግለጥ፥ እንዲሁም እውነትን በመግለጥ ረገድ ስሕተት አልባና ሐቅ ነው ማለት፥ መጽሐፉ እንደ መለኮታዊ ቃልነቱ ተዓማኒ ይሆን ዘንድ ለእያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ልዕለ-ተፈጥሮና ፍጹም የሆነው የእግዚአብሔር ምሪት አለው ማለት ነው። 

እስትንፋሰ-እግዚአብሔር በእርግጥ የሚመለከተው የመጀመሪያዎቹን ወይም ዋነኞቹን ጽሑፎች እንጂ፥ ቅጂዎችንና ትርጉሞችን አይደለም። የመጀመሪያው ዋና ጽሑፍ በአሁኑ ጊዜ የሌለ ከመሆኑ የተነሣ፥ ምሁራን አሁን ያለውን መጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛነት ለማረጋገጥና ለመወሰን ብዙ ጥረዋል። እውነትን ለመማማር ላለን ዓላማ ግን፥ አሁን በእጃችን የሚገኙት የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች፥ የመጀመሪያዎቹ ጽሑፎች ትክክለኛ ብዢዎች መሆናቸውን ለመገመት ይቻላል። በይዘት ሳይሆን፥ በአገባብ ጥቃቅን፥ ልዩነቶች ቢኖሩም፥ የመጽሐፍ ቅዱስን አስተምህሮን እምብዛም የሚያዛንፉ አይደሉም። የተገኙት ተጨማሪ ጽሑፎችም ከላይ ከተጠቀሰው የግንዛቤ መደምደሚያ ጋር ይስማማሉ። 

ለተግባራዊ ዓላማዎች ሲባል፥ በዕብራይስጥ የተጻፈው ብሉይ ኪዳንና በግሪክኛ የተጻፈው አዲስ ኪዳን በአንድነት፥ የእግዚአብሔር የራሱ ቃል መሆናቸውንና እርሱ ለሰው ሊያስተላልፍ የፈለጋቸው እውነቶች መሆናቸውን አምኖ ለመቀበል ይቻላል። 

2. ሜካኒካዊ ወይም የቃል በቃል ንድፈ-አሳብ። ቀደም ሲል እንደተመለከተው፤ እውነተኛው እስትንፋሰ-እግዚአብሔር ቃሉ በሚጻፍበት ጊዜ፥ በእግዚአብሔር አመራር ውስጥ የጸሐፊዎችን የመጻፍ ሰብእናና ነጻነት ይፈቅዳል የሚለው እውነተኛ አስተምህሮ ተገልጧል። የዚህ ተቃራኒ አመለካከት ግን ቅዱሳት መጻሕፍት በሚጻፉበት ጊዜ፥ ሰዎች የራሳቸውን የአጻጻፍ ዘዴ ምንም ሳይጠቀሙ እግዚአብሔር እንደ ጽሕፈት መኪና ተጠቅሞባቸዋል ይላል። እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስን ቃል በቃል አጽፎት ሲሆን ኖሮ፥ የአጻጻፉ ስልትና ቃላቱ በአጠቃላይ አንድ ዓይነት በሆኑ ነበር። የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች የግል ፍርሃታቸውን፥ ስሜታቸውን፥ የእግዚአብሔርን ማዳን እና ጸሎታቸውን በብዙ ሁኔታዎች ገልጠዋል። በመሆኑም በተዘዋዋሪ መንገዶች የራሳቸውን ማንነት በዚሁ መለኮታዊ ጽሑፍ ውስጥ አስገብተዋል። ለምሳሌ ሮሜ 9፡1-3 ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ ለእስራኤል ያደረገው ጸሎት ቃል በቃል ከእግዚአብሔር የተሰጠ ቢሆን ኖሮ ትክክለኛ ትርጉሙን ያጣ ነበር። 

በመሆኑም እስትንፋሰ-እግዚአብሔር እያንዳንዱን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሚመለከት ቢሆንም፥ ማንነትን፥ የአጻጻፍ ስልትን ወይም የግል ፍላጎትን አያስቀርም። መጽሐፍ ቅዱስ በአጻጻፍ ረገድ መለኮታዊውን ሥልጣን እንደሚቀበል ሁሉ፥ የጸሐፊውን ነጻነትም ያረጋግጣል። እግዚአብሔር ሰብአዊ ጸሐፊዎችን በመጠቀም ትክክለኛነትን አከናውኗል፤ ይህን ሲያደርግ ግን የቃል በቃል አጻጻፍን ተከትሎ አይደለም። አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እግዚአብሔር በቀጥታ እየተናገረ የተጻፉ መሆናቸው ተዘግቧል። አብዛኛዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ግን፥ ቀጥታ ቃል በቃል ለመጻፋቸው ምንም ማስረጃ ስለሌለ በሰብአዊ ጸሐፊዎች ነው የተመዘገቡት ለማለት ይቻላል። 

3. ፅንሰ-ሐሳባዊ ንድፈ-አሳብ። አንዳንዶች የመጽሐፍ ቅዱስን ፍጹም እስትንፋሰ እግዚአብሔርነት በማቃለል፥ እግዚአብሔር እስትንፋሱን የሰጠው በትክክለኛዎቹ ቃላት ሳይሆን፥ ፅንሰ-አሳብን ብቻ ነው በማለት የመጽሐፉን ደራሲነት ለሰብአዊ ጸሐፊዎቹ ለመስጠት ሞክረዋል። ይህ አመለካከት ችግሮች አሉት። ምክንያቱም ሰዎች በሚጽፉበት ጊዜ እግዚአብሔር የገለጠላቸውን የተረዱት በከፊል ብቻ ቢሆንና ያን በራሳቸው ቃላት ቢያሰፍሩት ኑሮ በቀላሉ የማይገመት ችግር ያስከትሉ ነበር። 

ለጸሐፊዎች የተሰጧቸው ንድፈ-አሳቦች ብቻ ናቸው የሚለውን አስተያየት መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ይቃወማል። የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በእግዚአብሔር መሪነት የተጻፈ መሆኑ ተደጋግሞ በአጽንኦት የተገለጠ እውነት ነው። የቃላት ጠቃሚነት በተደጋጋሚ ተጠቅሷል (ዘጸ. 20፡1፤ ዮሐ. 6፡63፤ 17፡8፤ 1ኛ ቆሮ. 2፡13)። ከብሉይ ኪዳን በመጥቀስ ቃላቱ ከእግዚአብሔር መሆናቸው በተደጋጋሚ ተረጋግጧል (ዮሐ. 10፡17፤ ገላ. 3፡16)። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑ ኤፌሶን 6፡17፤ ያዕቆብ 1፡21-23፤ 1ኛ ጴጥሮስ 2፡2 ውስጥ በተደጋጋሚ ተመልክቷል። ከእግዚኣብሔር ቃል ላይ በሚቀንስ በማንኛውም ሰው ላይም ከባድ እርግማን ተላልፎበታል (ራእይ 22፡18-19)። ስለዚህም ይህ ንድፈ-አሳባዊ ትንታኔ፥ ቅዱሳት መጻሕፍት ራሳቸው በእግዚአብሔር እስትንፋስ የተጻፉ ስለመሆናቸው የሚያውጁትን እውነት በተመለከተ ከትክክለኛነት የራቀ ነው። 

4. ከፊል እስትንፋሰ-እግዚኣብሔር። ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰኑ ክፍሎች ብቻ ናቸው በእግዚአብሔር መሪነት የተጻፉ የሚሉ የተለያዩ ንድፈ-ሐሳቦች ተከሥተው ነበር። ለምሳሌ አንዳንዶች፥ ስለ መለኮታዊ እውነት መገለጥ የሚናገሩት የቃሉ ክፍሎች ትክክለኛ ቢሆኑም፥ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን ታሪካዊ፥ መልከዓ-ምድራዊ ወይም ሳይንሳዊ አባባሎችን በዚህ መልኩ ኣንቀበላቸውም ብለዋል። ከዚህ ጋር ተጓዳኝ የሆነው አመለካከት ደግሞ፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቂት ክፍሎች ይበልጥ እስትንፋሰ እግዚአብሔር ያለባቸው ስለሆኑ፥ የእውነትና የስሕተታቸው ሁኔታ የደረጃ ጉዳይ ነው የሚለው ነው። ይህም መጽሐፍ ቅዱስ በሚጻፍበት ወቅት እግዚአብሔር ጻሐፊዎቹን በተለያዩ ደረጃዎች የረዳቸው ቢሆንም፥ ያለ ስሕተት ለመጻፍ የሚያስችላቸውን ክህሎት ግን አልሰጣቸውም የሚል ነው። በመሆኑም ከፊል እስትንፋሰ-እግዚአብሔር በሁሉም አቀራረቡ የቃሉን የመጨረሻ ዳኝነት ለእያንዳንዱ አንባቢ ይተዋል። በመሆኑም በዚህ አካሄድ የቃሉ ሥልጣን፥ የአንባቢው ግለሰብ ሥልጣን ይሆንና፥ ሁለት አንባቢዎች በትክክል እውነት የሆነውና ያልሆነው የቱ ነው በሚለው እሳብ የማይስማሙበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። 

5. አዲሱ ኦርቶዶክሲ (Neo-Orthodoxy) አስተሳሰብ ስለ እስትንፋሰ እግዚአብሔር ያለው አመለካከት። በሀያኛው ምዕተ ዓመት ካርል ሳርት በሚባል ሰው አማካይነት አዲስ መለኮታዊ መገለጥ ማለት “እዲሱ ኦርቶዶክሲ” የተሰኘ አመለካከት ተከሠተ። ይህ አመለካከት መጽሐፍ ቅዱስ በሚጻፍበት ጊዜ መለኮታዊ ድርሻ ያለበት መሆኑን ባይክድም፣ መጽሐፉ ስሕተቶች ስላሉበት እንደ ስሕተት አልባ ጽሑፍ ሊቆጠር አይገባም ይላል። ይህ አመለካከት እግዚአብሔር በቅዱሳን መጻሕፍት አማካይነት እንደሚናገርና እውነትን ወደ እኛ ለማስተላለፊያነት የሚጠቀምባቸው መሆኑንም ያምናል። 

በዚህ አመለካከት መሠረት እንግዲህ፥ መጽሐፍ ቅዱስ የመለኮታዊ መገለጥ መተላለፊያ የሚሆነው፥ የሚያምር አበባ ወይም ደስ የሚያሰኝ የፀሐይ መጥለቅ እግዚአብሔር ፈጣሪ መሆኑን የሚናገረውን ያህል ይሆናል ማለት ነው። በዚህ ንድፈ-አሳብ መሠረት መጽሐፍ ቅዱስ እውነት የሚሆነው፥ እያንዳንዱ አንባቢ በተረዳው መጠን ሲሆን፤ እውነትም የሚረጋገጠው በዚያው ልክ ነው። የዚህ አመላካከት ታሪክ እንደሚያረጋግጠው፥ ሁለት የዚህ አመለካከት ደጋፊዎች በምንም አኳኋን መጽሐፍ ቅዱስ በሚያስተምረው እውነት አይስማሙም። እንደ ከፊል እስትንፋሰ-እግዚአብሔር አመለካከት ሁሉ፥ እነርሱም መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ትክክል ወይም ስሕተት የመሆኑን ውሳኔ ለግለሰብ አንባቢዎች ይተዋሉ። 

6. ተፈጥሮአዊ እስትንፋሰ እግዚአብሔር የተሰኘው አስተሳሰብ ያለው አመለካክት። ይህ አመለካከት ከላይ ከጠቀሱት ሁሉ የባሰና ያለማመን አመለካከት ሲሆን፥ መጽሐፍ ቅዱስን እንደማንኛውም ሌላ መጽሐፍ ነው የሚቆጥረው። በዚህ መሠረት ምንም እንኳን እግዚአብሔር ፅንሰ-አሳቦችን ይገልጡ ዘንድ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ልዩ ችሎታዎችን የሰጣቸው ቢሆንም፣ መጽሐፍ ቅዱስ መለኮታዊ አመራር የሌለበት ፍጹም የሰው ሥራ ነው ይላል። ስለሆነም፥ ለዚህ አመለካከት መጽሐፍ ቅዱስ የቀደሙ ሰዎችን መንፈሳዊ ልምምድ የሚገልጥ ተራ የሃይማኖት መጽሐፍ ነው። ይህ አመለካከት የመጽሐፍ ቅዱስን ልዩ መለኮታዊ ሥልጣን የሚሽር ከመሆኑም በላይ፥ መጽሐፉ በውስጡ የያዘውን አስደናቂ እውነት ትክክለኛነት አይገልጠውም። 

እንግዲህ የመጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ የሆነ ሰው ሰለዚህ መጽሐፍ ምንነት ምርጫ ማድረግ አለበት። ያለውም ምርጫ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ እስትንፋሰ-እግዚአብሔር መሆኑን ስለሚናገር፥ ይህንኑ አምኖ መቀበልና እግዚአብሔር ራሱ ያለ ሰብአዊ ደራሲ እንደጻፈው ማመን ነው። ከዚህ ሌላ ያለው አማራጭ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያውጀውን በማስረጃ ለማስደገፍ ኣይችልም፤ የእግዚአብሔር ቃል አይደለም፥ በማለት ይህን መጽሐፍ መካድ ይኖርበታል። ስለ መጽሐፍ ቅዱስ በእስትንፋሰ-እግዚአብሔር መጻፍ አያሌ ማረጋገጫዎችን ማቅረብ ቢቻልም፥ ዋናው ማረጋገጫ ግን መጽሐፉ ስለ ራሱ የሚያቀርበው እውነት ነው። የመጽሐፉ ሕይወትን የመለወጥ ኃያል፥ እምነታቸውን በቃሉ እንዲሁም በሚሰጠው ተስፋ ላይ ባደረጉና በሚሊዮን በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ታይቷል። 

ለ. የክርስቶስ ምስክርነት 

መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፈ የእግዚአብሔር ቃል የመሆኑ እውነት በብዙ ውስጣዊ ማረጋገጫዎች ተደግፏል፤ በእግዚአብሔር ቃልነቱ የሰውን ሕይወት የመንካትና የመለወጥ ኃይሉም ተረጋግጧል። ከምስክርነቶቹ ሁሉ እጅግ ታላቁ የክርስቶስ ኢየሱስ የራሱ ምስክርነት ሲሆን፥ ያም መጽሐፍ ቅዱስ እስትንፋሰ-እግዚአብሔር መሆኑን ያረጋግጣል። ክርስቶስ ከመጻሕፍት በሚጠቅስበት ጊዜ ሁሉ ቃሉ ሥልጣን እንዳላውና የመጣውም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት መሆንን ሙሉ በሙሉ በመረዳት ነበር። በማቴዎስ 5፡18 መሠረት ከሕግ አንዲት ነጥብ ብትሆን እንኳን ሳትፈጻም እንደማትቀርም አረጋግጧል። ይህን ሲል አንዲት ነጥብ ከቃሉ ሳይፈጸም አይቀርም ማለቱ ነበር። እንግዲህ ትክክለኛነትና እስትንፋሰ-እግዚአብሔርነት እስከ አንዲት ፊደል ድረስ በዝርዝር የሚሄድ ከሆነ፥ ክርስቶስ ያረጋግጥ የነበረው የብሉይ ኪዳንን እስትንፋሰ-እግዚአብሔርነት ነበር። 

ክርስቶስ ዮሐንስ 10፡35 ውስጥ “መጽሐፉ ሊሻር አይችልምና” በማለት ያረጋግጣል። ማቴዎስ 1፡22-23 ውስጥ እንደተጠቀሰው፥ የብሉይ ኪዳንን መፈጸም አዲስ ኪዳን በተደጋጋሚና በግልጥ አረጋግጧል (ከማቴዎስ 4፡14፤ 8፡ 17፤ 12፡17፤ 15፡7-8፤ 21፡4-5፥ 42፤ 22፡29፤ 26፡31፥ 56፤ 27፡9-10፥ 35 ጋር ያነጻጽሩ)። እነዚህ የማቴዎስ ወንጌል ጥቅሶች በመላው አዲስ ኪዳን የሚገኘው ማረጋገጫ ዓይነተኛ ምሳሌዎች ናቸው። የስፍረ-ዘመን ለውጥ ወይም የሕይወት ሕግ ለውጥ በሚረጋገጥበት ጊዜ እንኳ፥ የመጀመሪያዎቹ (ዋናዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ገለጣዎች ሥልጣንና እስትንፋሰ እግዚአብሔርነት የሚያጠያይቅ አይሆንም (ማቴ. 7-12)።

ከብሉይ ኪዳን የሚጠቀሱት ክፍሎች ወደ እያንዳንዱ ጠቃሚ ክፍል የሚደርሱ ሲሆኑ፥ እነርሱም ብዙ ጊዜ ሊብራልስት የሚባሉ ወገኖች የሚሟገቱባቸውና እንደ ኦሪት ዘዳግም፥ ትንቢተ ዮናስ እና ትንቢተ ዳንኤል (ዘዳ. 6፡16ን፤ ከማቴ. 12፡40፤ ዳን. 9፡27፥ 12፡11ን፤ ከማቴ. 24፡ 15 ጋር ያነጻጽሩ) ያሉት ናቸው። ስለዚህ የክርስቶስን ባሕርይና እውነትነት ካልተጠራጠሩ፥ የብሉይ ኪዳን እስትንፋሰ-እግዚአብሔርነትን መጠራጠር ወይም አለመቀበል ከቶ ያዳግታል። ለዚህ ነው በእስትንፋሰ-እግዚአብሔር የተገኘውን ቃል መካድ፥ ሥጋ የለበሰውን የእግዚአብሔር ቃል መካድ የሚሆነው። 

ክርስቶስ የብሉይ ኪዳንን እስትንፋሰ-እግዚአብሔርነትና ስሕተት አልባነት ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን፥ የአዲስ ኪዳንን መጻፍ አስቀድሞ ተናግሯል። በዮሐንስ 16፡ 12-13 መሠረት ደቀ መዛሙርቱ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ ከመንፈስ ቅዱስ እውነትን መቀበል ነበረባቸው። ደቀ መዛሙርቱ የእውነት ምስክሮች እንደሚሆኑ ክርስቶስ ተናግሮአል (ማቴ. 28፡19፤ ሉቃስ 10፡22-23፤ ዮሐ. 15፡27፤ ሐዋ. 1፡8)። ይህ ብቻም አይደል ደቀ መዛሙርቱ እውነትን እንዲናገሩ ሥልጣን ሰጥቷቸዋል ሉቃስ 10፡16፤ ዮሐ. 13፡19፤ 17፡14-18፤ ዕብ. 2፡3-4)። 

አዲስ ኪዳን በሚጻፍበት ጊዜ ጸሐፊዎቹ በእግዚአብሔር መንፈስ መመራታቸውን ያውቁ ስለነበር፤ አዲስ ኪዳን እንደብሉይ ኪዳን እስትንፋሰ-እግዚአብሔር መሆኑን አውጀዋል። ልክ ዳዊት በመንፈስ ቅዱስ ምሪት እንደጻፈ (ማቴ. 22:43)፥ ዘማሪውም በእስትንፋሰ እግዚአብሔር እንደተቀኘ (ዕብ. 3፡7-11፤ መዝ. 95፡7-11)፥ አዲስ ኪዳንም በተመሳሳይ ሁኔታ እስትንፋሰ-እግዚአብሔር ነው። ዘዳግም 25፡4 እና ሉቃስ 10፡7 እስትንፋሰ-እግዚአብሔር መሆናቸው 1ኛ ጢሞቴዎስ 5፡18 ውስጥ ተጠቅሷል። 2ኛ ጴጥሮስ 3፡15-16 ውስጥ የጳውሎስ መልእክቶች እንደ ሌላው የመጽሐፍ ክፍል መቆጠር ያለባቸው መሆኑ ተገልጧል። አዲስ ኪዳን እንደ ብሉይ ኪዳን እስትንፋሰ-እግዚአብሔር መሆኑን ራሱ ያረጋግጣል። 

ሐ. ስለእስትንፋሰ-እግዚአብሔር ጠቃሚ ምንባቦች (ጥቅሶች) 

የመጽሐፍ ቅዱስን እስትንፋሰ-እግዚአብሔርነት ከሚናገሩት ማዕከላዊ ምንባቦች አንዱ፥ 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16 ውስጥ “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት፥ በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል” የሚለው ነው። ሐዋርያው “መጽሐፍ” ሲል የሚያመላክተው በ2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡15 የተመለከቱትን “ቅዱሳን መጻሕፍት” ሲሆን፥ ሁለቱንም ማለት ብሉይንና አዲስ ኪዳንን ያጠቃልላል። “የእግዚአብሔር-እስትንፋስ” የሚለው አገላለጥ በአዲስ ኪዳን ግሪክኛ “ቲኦኒዮስቶስ” ማለት ሲሆን፥ ትርጉሙም “እግዚኣብሔር እፍ አለ” የሚል ይሆናል። ይህ አገላለጥ መጽሐፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር የወጣ መሆኑን ያመለክታል። በዚህ እውነት መሠረት ቃሉ የእግዚአብሔር ባሕርይ የሆነውን ፍጹምነት ይይዛል። የስሕተት ጸሐፊ መሆን ለእግዚአብሔር አይቻለውም። መጽሐፍ ቅዱስ እስትንፋሰ-እግዚአብሔር መሆኑ በሰው ጸሐፊዎች ላይ ሳይሆን፥ በእግዚአብሔር ቃልነት ላይ ያተኩራል። ጸሐፊዎቹ እንደ ሰብአዊነታቸው ስሕተትና የማይታመን ነገር ለመጻፍ የተጋለጡ መሆናቸውን በማወቅ ስሕተት አልባ የሆነ ቃሉን በነርሱ በኩል አስተላላፈ፥ በመለኮታዊ ኃይሉና ምሪቱ መራቸው። በመሆኑም እነሱ የጻፉት ቃል ስሕተት አልባ የእግዚአብሔር ቃል ነው። የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ ለትምህርተ እምነት፥ ለተግሣጽ፥ ልብን ለማቅናትና፥ በጽድቅ ላለው ትምህርት ይጠቅማል። 

ብዙ ጊዜ ከሚነሱ ጠቃሚ ጥያቄዎች አንዱ፥ እንዴት ነው እግዚአብሔር በአንድ በኩል ሰብኣዊ ደራሲነትንና ግለ ባሕርይን ፈቅዶ፥ በሌላ በኩል ደግሞ እስትንፋሱ የሆነውን ቃል ስሕተት አልባ የሚያደርገው? የሚለው ነው። እግዚአብሔር ሉዓላዊ የሆነ አሠራሩን እንዴት እንደፈጸመ መመለስ ሁልጊዜ የማይቻል ቢሆንም ጥያቄውን በሚመለከት ግን 2ኛ ጴጥሮስ 1፡21 ውስጥ “ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ” ተብሎ ተገልጧል። ነቢያቱ በቃልም ተናገሩት ወይም ጻፉት፥ ማብራሪያው “በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው” ነው ይላል። “ተነድተው” ተብሎ የተተረጎመው ቃል ሸክምን ያመለክታል። በመሆኑም በዚህ አባባል መሠረት ጀልባ ተሳፋሪዎቹን ወደ አንድ መድረሻ እንደሚወስድ፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎችም እግዚኣብሔር ወዳሰበው መድረሻ ተወስደዋል። 

በጀልባ የሚጓዙ መንገደኞች (ተሳፋሪዎች) ጀልባው ውስጥ ለመመላለስ የሚያስችል ሰብአዊ ነጻነት ቢኖራቸውም፥ ወደጀልባው መድረሻ መወሰዳቸው እንደማይቀር ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር በውስጣቸው ይሠራ ነበር። እንደ ቧንቧ እንዲያስተላልፉም ቃሉን እፍ ይልባቸው ነበር። አንዳንድ የቃሉ ክፍሎች በትክክል ቃል በቃል በእግዚአብሔር እየተነገሩ የተጻፉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ይቻላል። ለምሳሌ ያህል ዘጸአት 20፡1-17 ውስጥ የሕግ መሰጠትን እናገኛለን። ብሉይ ኪዳን በመደጋገም “እግዚአብሔር አለ” በማለት ያውጃል (ዘፍ. 1፡3)። ሌላው የተደጋገመ አገላለጥ፥ “የጌታ ቃል…መጣ” የሚለውና ከነቢያት አንዱ የመጣው ነው (ኤር. 1፡2፤ ሆሴዕ 1፡1፤ ዮናስ 1፡1፤ ሚክ. 1፡1፤ ሶፎ. 1፡ 1፤ ሐጌ 1፡1፤ ዘካ. 1፡ 1)። በሌሎች ሁኔታዎች ደግሞ እግዚአብሔር በሕልም ይናገራል (ዳን. 2፡1)፤ ወይም በሕልምና በራእይ ይገለጣል (ዳን. 7፡1)። የመለኮታዊ መገለጥ ዓይነቶችና ሁኔታዎች የተለያዩ ቢሆኑም፥ በነዚህ ሁሉ እግዚአብሔር በሥልጣን፥ በትክክልና ያለ ስሕተት ይናገራል። በመሆኑም ቃሉ በእግዚአብሔር ያለውን ፍጹም የእውነት ባሕርይ ይናገራል። 

መ. ተጨማሪ ማብራሪያዎች 

መጽሐፍ ቅዱስ በአጠቃላይ እስትንፋሰ-እግዚአብሔር መሆኑን ስንናገር፥ እንዳንድ ጊዜ ውሸትን በውሸትነቱ የሚመዘግብ መሆኑን ማመን ይገባል። ይህ ዘፍጥረት 3፡4 ውስጥ የሰይጣንን ውሸት በመመዝገብ ተረጋግጧል። ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ልምምድና አስተሳሰብ ለመመዝገብ ይችላል። ይህም በመጽሐፈ ኢዮብና በመኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን የምናገኘው ማስረጃ ነው። የሰዎቹን ማሰብ ወይም መናገር አስመልክቶ መጽሐፍ ቅዱስ የሚጠቅሰው ነገር፥ እዚያው መጽሐፉ ውስጥ ሌላ ስፍራ ባለው እውነት መፈተን (መመዘን) ይኖርበታል። በዚህ አኳኋን ስናየው፥ አንዳንዶቹ የኢዮብ ጓደኞች ንግግሮች ስሕተት ሲሆኑ፥ የመኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን አንዳንድ ፍልስፍናና ምርምርም ከሰው ጥበብ ልቆ እንዳልሄደ እንረዳለን። መጽሐፍ ቅዱስ እውነትን እውነት ነው በማለት በሚመዘግብበት ጊዜ፥ ይህ ሁኔታ እውነት መሆን ያለበት በእግዚአብሔር ማንነት መገለጥ፥ በግብረገብ ደረጃዎቹ ወይም በትንቢት መርሐ ግብሩ ወይም ታሪክን፥ መልክዓ-ምድርን በማጠቃለሉ ወይም ከሳይንስ ጋር የሚዛመዱ እውነታዎችን ሲያገናዝብ ነው። የእግዚአብሔር ቃል ትክከለኛነት የሚያስደንቅ ምስክርነት አለው። ይኸውም ጥንታውያን ጸሐፊዎች ምንም እንኳ ሳይንሳዊ ግኝቶችን መገመት ሳይችሉ፥ እና ቴክኒካዊ ቋንቋ ባይጠቀሙ፥ ጽሑፋቸው የሰው ልጅ በምድር ከሚያገኘው እውነት ጋር አይቃረንም። 

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጥያቄ የሚያሥነሡ ችግሮችም አሉ። አንዳንድ ጊዜ በቂ መረጃ ካለማግኘት የተነሣ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱን የሚቃረን ሊመስል ይችላል። እንደ ምሳሌ የሚጠቀሰው፥ ኢያሪኮ ውስጥ የተፈወሱት ዓይነ ስውሮች አንድ ወይም ሁለት መሆናቸው (ማቴ. 20፡30፤ ማር. 10፡46፤ ሉቃስ 18፡35)፥ ደግሞም ድርጊቱ የተፈጸመው ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ ሲገባ (ሉቃስ 18፡ 35)፥ ወይም ከኢያሪኮ ሲወጣ (ማር. 10፡ 46፤ ሉቃስ 19፡ 1) መሆን አለመሆኑ በግልጥ ያለመለየቱ ጉዳይ ነው። እነዚህን የመሳሰሉ ችግሮች የሚወገዱት፥ መጽሐፍ ቅዱስን በትዕግሥት በማጥናት ሲሆን፥ ችግሩ የሚቃለለውም እውነቱ በትክክል ሲታወቅ ነው። ለምሳሌ ሁለት የኢያሪኮ ከተሞች፥ ኣንድ ጥንታዊ እና ሌላ ዘመናዊ ነበሩ። ክርስቶስ ከላይ የተጠቀሰውን ድርጊት በፈጸመበት ጊዜ ከአንደኛው ኢያሪኮ ወደ ሌላኛው ኢያሪኮ በመግባት ላይ ሊሆን ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ የተባሉ ብዙ ስሕተቶች በከርሠ-ምድር ቁፋሮ ግኝት አማካይነት እውነትነታቸው ተረጋግጧል። 

ማንም ቢሆን የቅዱሳት መጻሕፍት አባባሎች የሚያመለክቱት፥ የዓለምን ወይም የሰውን አፈጣጠር ወይም ከዚያም አልፎ ሌላ ዝርዝር ትረካ መሆን አለመሆኑን ለመለየትና ለመቃረን የሚያስችል በቂ እውቀት የለውም። በሚገባ ከተገነዘቡት፥ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ትክክለኛነት እና እውነት እንደሚያረጋግጥ ሐውልት ነው። እግዚአብሔር ራሱ ለአንባቢው ግለሰብ የሚናገረው ተደርጎ ሊታመንም ይገባል። ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስን ለማናናቅና ለማጥፋት በየዘመናቱ የተቻለው ሁሉ ሲሞከርም፥ መጽሐፉ የእግዚአብሔርን እውነት ለሚፈልጉ ሁሉ ብቸኛው ባለሥልጣንና የእውነተኛ መለኮታዊ መገለጥ ምንጭ እንደሆነ ይቀጥላል።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

3
ትምህርት 3 ከ52

መጽሐፍ ቅዱስ፡- መልእክቱና ዓላማው

ሀ. ኢየሱስ ክርስቶስ በመልእክትነት 

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና መልእክት ነው። ስለሆነም የክርስቶስን ማንነትና የሥራውንም ፍጹምነት በሚመለከት በብዙ መንገዶች የቀረበውን መግለጫ በትክክል ለማወቅ የሚቻለው፥ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን፡- 

1. ኢየሱስ ክርስቶስ ፈጣሪ ነው። የኦሪት ዘፍጥረት የመጀመሪያ ምዕራፎች እግዚአብሔር ዓለምን እንደፈጠረ የመዘገቡልን ሲሆን፥ ይህንንም “ኤሎሂም” በሚል የዕብራይስጥ ቃል ይገልጣሉ። ቃሉም አብን፥ ወልድን እና መንፈስ ቅዱስን ያመለክታል። አንድ ሰው ሁሉም ነገር የተፈጠረው በክርስቶስ መሆኑን የሚረዳው አዲስ ኪዳን (ዮሐ. 1፡3) ላይ ሲደርስ ነው። ቆላስይስ 1፡16-17 ውስጥ፥ “የሚታዩትና የማይታዩትም ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ፥ በእርሱ፥ ተፈጥረዋልና፤ ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል እርሱ ከሁሉም በፊት ነው ሁሉም በርሱ ተጋጥሞአል” በማለት ክርስቶስ የሁሉም ነገር ፈጣሪ መሆኑን ይመሰክራል። ይህ ማለት ደግሞ፥ እግዚአብሔር አብ እና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በፍጥረት ሥራ ውስጥ ምንም ድርሻ አልነበራቸውም ማለት አይደለም። ነገር ግን በፍጥረት ሥራ ውስጥ ለክርስቶስ የዋና አድራጊነትን ስፍራ ይሰጠዋል። በዚህ መሠረት ዓለምና በዓለም ያሉት ሁሉ የክርስቶስን የእጅ ሥራ ፍጹምነት ይገልጣሉ። 

2. ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ዓለም ልዑል ገዥ። ኢየሱስ ክርስቶስ ፈጣሪ ስለሆነ በዓለማት ሁሉ ላይ ሉዓላዊ ገዥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ልዕልና የእግዚአብሔር አብ መሆኑን ይናገራል። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ሁሉ ይገዛ ዘንድ የእግዚአብሔር አብ ፈቃድና ዓላማ ነው (መዝ. 2፡8-9)። ምላስ ሁሉ ክርስቶስ ጌታ መሆኑን እንዲመሰክር፥ ጉልበትም ሁሉ ለክርስቶስ ክብር እንዲሰግድና፥ እንዲንበረከክ የእግዚአብሔር ዓላማ ነው (ኢሳ. 45፡23፤ ሮሜ 14፡11፤ ፊሊ. 2፡9-11)። የሰው ዘር ታሪክ በእግዚአብሔር ላይ የማመፅ መዘክር ቢሆንም እንኳ (መዝ. 2፡1-2)፥ ክርስቶስ በመላው ዓለም ላይ በፍጹም ልዑልነቱ የሚገለጥበትን ጊዜም በመጠበቅ ላይ ነው (መዝ. 110፡1)። ጊዜውም ክርስቶስ ኢየሱስ በሁሉም ነገር ላይ ፍጹም ጌታ የሚሆንበት፥ በኃጢኣት ላይ የሚፈርድበት እና ገዥነቱ የሚረጋገጥበት ይሆናል (ራእይ 19፡15-16)። 

ዓላማውን በማከናወን ረገድ እግዚአብሔር የዓለም ነገሥታት በዙፋናቸው እንዲሆኑ ፈቅዷል። በየዘመናቱ ታላላቅ መንግሥታትና መሪዎቻቸው ተነሥተዋል፥ ወድቀዋል። ከእነዚህም ጥቂቶቹ ግብፅ፥ ሶርያ፥ ባቢሎን፥ ፋርስ፥ ግሪክ እና ሮም ይገኙባቸዋል። የመጨረሻው መንግሥት ግን ከሰማይ የሚመጣውና ክርስቶስ የሚገዛው ይሆናል (ዳን. 7፡13-14)። 

ክርስቶስ ኢየሱስ የሕዝቦች ገዢ መሆን ብቻ ሳይሆን፥ የዳዊት ልጅ እንደመሆኑ በዳዊት ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ የእስራኤል ንጉሥ ይሆናል (ሉቃስ 1፡31-33)። ይህ የሚረጋገጠው፥ ጌታ ዳግም ተመልሶ የሺህ ዓመት መንግሥቱን ሲመሠርትና በመላው ዓለምና በእስራኤል ላይ ሲነግሥ ነው። 

ሉዓላዊነቱም ራስ ከሆነላት ቤተ ክርስቲያን ጋር ባለው ኅብረት ይገለጣል (ኤፌ. 1፡22-23)። ክርስቶስ የዓለም፥ የእስራኤል እና የቤተ ክርስቲያንም ራስ (ኤፌ. 1፡20-21) እንደመሆኑ በሰው ሁሉ ላይ ልዑል ፈራጅ ነው (ዮሐ. 5፡27፤ ኢሳ. 9፡6-7፤ መዝ. 72፡1-2፥ 8፥ 11)። 

3. ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ የሆነ ቃል፡፡ በተለይ በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ የሆነ ቃል መሆን ተገልጧል። እግዚአብሔር በአካል የተገለጠበት እና ባሕርይው፥ እንዲሁም ማንነቱ የተገለጠበት መሆኑን ነው ይህ የሚያሳየው። የእግዚአብሔር ባሕርያት ሁሉ በክርስቶስ ተገልጠዋል፤ በተለይም ጥበቡ፥ ኃይሉ፥ ቅድስናው እና ፍቅሩ። ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ምንነት የተገለጠበት ቃል ነው (ዮሐ. 1፡ 1)። ከሌላ ከማንኛውም መለኮታዊ መገለጥ ይልቅ፥ ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔርን በትክክል ሊያውቁት ይችላሉ። ዕብራውያን 1፡3 ውስጥ እንደተገለጠው፥ “እርሱም የክብሩ መንፀባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ”። የእግዚአብሔር ዋና ዓላማ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ራሱን ለፍጥረታቱ መግለጥ ነው። 

4. ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ አዳኝ። የመጽሐፍ ቅዱስ ዋናውና ታላቁ መልእክት፥ በሰው መፈጠርና በኃጢአት መውደቅ ጀምሮ በአዲስ ሰማይና አዲስ ምድር በሚያበቃው የሰው ዘር ታሪክ ክንዋኔ ውስጥ የሚገኘው የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የአዳኝነት ሥራ ነው። ክርስቶስ ሰይጣንን ድል የሚያደርግ የተስፋ ዘር ነበር (ዘፍ. 3፡15)። የዓለምን ኃጢአት የሚሸከም የያህዌ አገልጋይ መሆኑ በብሉይ ኪዳን ተመልክቷል (ኢሳ. 53፡4-6፤ ከዮሐ. 1፡29 ጋር ያመሳከሩት)። የኃጢአት መሥዋዕት ሆኖ የዓለምን ሁሉ የኃጢአት ፍርድ በመሽከም በመስቀል ላይ መሞት ነበረበት (1ኛ ቆሮ. 15፡3-4፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡ 19-21፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡ 18-19፤ 1ኛ ዮሐ. 2፡2፤ ራእይ 1፡5)። በአዳኝነቱ የኃጢአታችን መሥዋዕት ብቻ ሳይሆን፥ ሊቀ-ካህናችንም ነው (ዕብ. 7፡25-27)። 

በቅዱሳት መጻሕፍት ተደጋግሞ እንደተረጋገጠው፥ ከእግዚአብሔር ዋና ዋና ዓላማዎች አንዱ፥ ለጠፋው የሰው ዘር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድነትን መስጠት ነው። በዚሁ መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ ከዘፍጥረት እስከ ራእይ በከፍተኛ ሁኔታ እንደብቸኛው አዳኝ ቀርቧል (ሐዋ. 4፡ 12)። 

ለ. የሰው ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ 

መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበት ዋና ዓላማ እግዚአብሔርን ለማክበር ሲሆን፥ ይህን ከመፈጸሙ አንጻር የሰውንም ታሪክ ያቀርባል። በመጀመሪያዎቹ የኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፎች የሚገኘው የፍጥረት ታሪክ በአዳምና ሔዋን መፈጠር ተደምድሟል። መጽሐፍ ቅዱስ በአጠቃላይ የሚገልጠው፥ እግዚአብሔር ለሰው ዘር ያለውን ዓላማ ነው። 

የሚቀጥሉት ምዕራፎች እንደሚገልጡት፥ እግዚአብሔር ለዓለም ሕዝቦች ያለው ሉዓላዊ ዓላማ በትውልዶች ታሪክ ውስጥ ተገልጧል። የአዳምና ሔዋን የቅርብ ትውልዶች በኖኅ ዘመን በጥፋት ውኃ ጠፉ። ዘፍጥረት 10 ውስጥ የኖኅ ትውልዶች ሦስቱን ዋና ዋና የሰው ዘር ክፍፍሎች እንደመሠረቱ ተመዝግቧል። የኖኅ ትውልዶች ከእግዚአብሔር መንገድ ተሰናከሉና በባቢሎን ግንብ ሥራ ወቅት ተቀጡ። ከዚያም እግዚአብሔር ራሱን በእስራኤል በኩል የሚገልጥበትን ዓላማ ለመፈጸም አብርሃምን መረጠ። ከኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 12 ጀምሮ ያለው የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና መልእክት የእስራኤል መንግሥት መመሥረትና የዚያ ታሪክ ነው። የብሉይ ኪዳን አብዛኛው ክፍል የሚገልጠው፥ በዙሪያዋ ከነበሩ አሕዛብ ጋር ስትነጻጸር እጅግ ትንሽ ስለነበረችው እስራኤል ነው። በእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ፥ በብሉይ ኪዳን ለአብርሃም በአንተ ዘር የሰው ዘር ሁሉ ይባረካል ተብሎ የተነገረለት ተስፋ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት ሙሉ በሙሉ እውን በመሆን በአዲስ ኪዳን ተፈጽሟል። 

ሌላ አዲስ የሰው ዘር ክፍፍል በአዲስ ኪዳን ውስጥ ይታያል። ይኸውም ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኛቸው ያመኑ አረማውያንና፥ አይሁድን የያዘችው የክርስቶስ አካል ቤተ ክርስቲያን ናት። አዲስ ኪዳን፥ በተለይም በሐዋርያት ሥራና በመልእክቶች አማካይነት እግዚኣብሔር ከቤተ ክርስቲያን ጋር ያለውን ግንኙነት ያስገነዝባል። የራእይ መጽሐፍ የዚህ ሁሉ ታላቅ ፍጻሜ ነው። በግብፅና በሶሪያ በመጀመር በባቢሎን፥ በሜዶንና ፋርስ፥ በግሪክ፥ በሮም እያሉ የቀጠሉት ታላላቅ ተከታታይ መንግሥታት ሂደት፥ በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ጊዜ ከሰማይ በሚመጣው መንግሥት ይደመደማል። በሺህ ዓመቱ መንግሥት ዘመን የሚገኙት፥ አይሁድም ሆኑ አረማውያን፥ እስራኤል በመሢሕ ንጉሥዋ ሥር በምትይዘው መሬት ላይ ሆና እና የዓለም ሕዝቦች ባጠቃላይ የሺህ ዓመቱን መንግሥት በረከት ይጋራሉ። 

መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስን ማዕከሉ የሚያደርግና የእግዚአብሔር ክብር በዓለም ታሪክ ጋር እንዴት እንደተገለጠ የሚያሳይ ሲሆን፥ በዚሁ መሠረት የእግዚአብሔር ዋና ዋና ሥራዎቹ በሕዝቦች ላይ ባለው የበላይነት፥ ለእስራኤል ባለው ታማኝነትና ለቤተ ክርስቲያን ባለው ጸጋ አማካይነት ተገልጧል። የዚህ ሁሉ መጨረሻ፥ ታሪክ በሚፈጸምበት፥ እንዲሁም ዘላለም በሚጀምርበት፥ በአዲሱ ሰማይና በአዲሱ ምድር፥ በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ይሆናል። 

ሐ. የመጽሐፍ ቅዱስ ዓላማ 

በጽሑፍ በሰፈረው የእግዚአብሔር ቃል መሠረት፥ እግዚአብሔር ያደረገው ወይም የሚያደርገው ነገር፥ ከፍጥረት መጀመሪያ እስከ ዘላለም ያለው አንድ ታላቅ ዓላማ ተገልጧል። ይህ ታላቅ ዓላማ የእግዚአብሔር ክብር መገለጥ ነው። ለዚህ ዓላማ መላእክት ተፈጠሩ፥ ቁሳዊዎቹ ዓለማት ይህን ክብር ያንጸባርቁ ዘንድ ተፈጠሩ፥ እና ሰው በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ተፈጠረ። በማይመረመረው የእግዚአብሔር ተግባራዊ ጥበብ ኃጢአት እንኳ ተፈቅዶ፥ ድነትም ተሰጥቷል። ይህ የሆነው የዚህን ታላቅ ዓላማ መፈጸም አስቀድሞ በማሰብ ነው። 

እግዚአብሔር ክብሩን ለመግለጥ መፈለጉ ትክክልና ተገቢ ነው። ሰው ራሱን ገናና ለማድረግ የሚያስችለው አንዳች ነገር የለውም። ምክንያቱም ፍጹምነት በርሱ ዘንድ አለመኖሩ ነው። እግዚአብሔር ክብሩን ገለጠ ማለት፥ ለፍጥረታት ሁሉ የማይወሰን በረከትን የሚያመጣ እውነትን ገለጠ እና አሳየ ማለት ነው። እግዚአብሔር በሕልውናው ዘላለማዊና በፍጹምነቱ ምሉእ እንደመሆኑ፥ ፍጹም ክብር ይገባዋል። ፍጥረቶቹ የሚገባውን ክብር ቢነፍጉት ግን ድርጊታቸው ሕገወጥ ነው። እግዚአብሔር ክብሩን የሚገልጠው ለራሱ ሳይሆን፥ ለፍጥረታቱ ጥቅም ነው። እግዚአብሔር ራሱን ለፍጥረታቱ መግለጡ፥ ለፍቅርና አምልኮ የሚያበቃ ነገር ሰጥቷቸዋል። እምነትና የአእምሮ ሠላም፥ እንዲሁም በጊዜና በዘላለም ውስጥ የድነትን ዋስትና አትርፎላቸዋል። ሰው የእግዚአብሔርን ክብር ይበልጥ በተረዳ ቁጥር፥ የሚያገኘው በረከት እየላቀ ይሄዳል። 

መጽሐፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር ለሰው የተሰጠ መልእክት እንደመሆኑ መጠን፥ ዓላማው የእግዚአብሔር ዓላማ፥ ማለት እግዚአብሔር ይከበር ዘንድ ነው። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ፦ 

1. “የሚታዩትና የማይታዩትም ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል” በማለት ለክብሩ ይመሰክራል (ቆላ. 1፡16)። መላእክትና ሰዎች በዓለማት ያሉት ፍጥረታት በሙሉ ለክብሩ መፈጠራቸውን ያረጋግጣል። እንዲሁም “ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል” (መዝ. 19፡ 1)። 

2. ሕዝበ እስራኤል ለእግዚአብሔር ክብር ነው(ኢሳ. 43፡7፥ 21፥ 25፤ 60፡ 1፥ 3፥ 21፤ 62፡3፤ ኤር. 13-11)። 

3. ድነት ለእግዚአብሔር ክብር ነው(ሮሜ. 9፡23)፤ ለእግዚአብሔር ጸጋ መገለጥ (ኤፌ. 2፡7)፥ አሁን ደግሞ የእግዚአብሔር ጥበብ መግለጫ ነው (ኤፌ. 3፡ 10)። 

4. አገልግሎት ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር መሆን አለበት (ማቴ. 5፡16፤ ዮሐ. 15፡8፤ 1ኛ ቆሮ.10፡31፤ 1ኛ ጴጥ. 2፡12፤ 4፡ 11፥ 14)። መጽሐፍ ቅዱስ፥ ራሱም እግዚአብሔር የራሱን ሰው ለበጎና ለመልካም ሥራ የሚያዘጋጅበት መሣሪያ ነው (2ኛ ጢሞ. 3፡ 16፥ 17)። 

5. አዲሱ የክርስቲያን ፍቅር እግዚአብሔር ይከብር ዘንድ ነው (ሮሜ. 5፡2)። 

6. የክርስቲያን ምት እንኳን እግዚአብሔርን ያከብራል (ዮሐ. 21፡19፤ ፊልጵ. 1፡20)። 

7. ድነትን ያገኘ ሰው የክርስቶስን ክብር ይካፈል ዘንድ ሥልጣን ተሰጥቶታል (ዮሐ. 17፡22፤ ቆላ. 3፡4)። 

በአጠቃላይ ሲታይ መጽሐፍ ቅዱስ በመልእክቱም ሆነ በዓላማው፥ በዓለም ከሚገኝ ከማንኛውም መጽሐፍ ፍጹም የተለየ ነው። የሰውን ሥራና የድነት ዕድል በማመልከት ረገድ ከሁሉ ይልቃል። የኢየሱስ ክርስቶስ ባሕርይና ሥራ፥ እንዲሁም ብቸኛ አዳኝነት፥ የእግዚአብሔርን ፍጹም ገናናነት በዝርዝር ይገልጣል። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ፈጣሪን ለፍጥረቱ የሚገልጥ፥ ዕውን ደግሞ ከነጉድለቱ ፍጹም ሙሉ ከሆነው አምላክ ጋር የሚታረቅበትንና ዘላለማዊ ኅብረትን የሚፈጥርበትን መንገድ የሚያመለክት የሆነ፤ ብቸኛ የሆነ መጽሐፍ ነው።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

4
ትምህርት 4 ከ52

መጽሐፍ ቅዱስ፡- እንደ መለኮታዊ መገለጥ

ሀ. የመለኮታዊ መገለጥ ዓይነቶች 

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ሕልውና፥ ሥራዎቹንና ዕቅዶቹን ለመግለጫነት ነው የተጻፈው። ፍጹም ልዑል የሆነው አምላክ ራሱን ለፍጥረታቱ መግለጡ ተገቢ ሲሆን፥ ፍጥረትን የፈጠረበት ዓላማም ይሞላ ዘንድ ይህ አስፈላጊ ነበር። አእምሮ ያላቸው ፍጡራን በሙሉ ፈጣሪያቸውን ለማወቅ መሞከራቸው ትክክል ነው። የተፈጥሮ ከፍተኛ ደረጃ ሰው ከሆነ፥ ፈጣሪውን ለመገንዘብና ከርሱ ጋር አንድነት ለመፍጠር ከቻለ፥ ፈጣሪ ዓላማና ፍቃዱን እንዲህ ላለው ፍጡር በመግለጥ እንደሚገናኘው መገንዘብ ይቻላል። እግዚአብሔር በሦስት ዋና ዋና መንገዶች ራሱን ገልጧል። 

1. የእግዚአብሔር መገለጥ በፍጥረት ውስጥ። የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ሥልጣንና ባሕርይ በፈጠራቸው ፍጥረታት አማካይነት ተገልጧል (ሮሜ. 1፡20)። ተፈጥሮአዊው ዓለም የእግዚአብሔር ሥራ እንደመሆኑ፥ እግዚአብሔር የማይወሰን ኃይልና ጥበብ ያለው መሆኑን፥ እንዲሁም ነባራዊውን ዓለም ጥበብ ለተሞላበት ዓላማ እንደፈጠረው ያረጋግጣል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር በተፈጥሮ በኩል ያሳየው መገለጥ፥ የእግዚአብሔርን ፍቅር፥ ወይም ቅድስና በተመለከተ ጥርት ያለ መግለጫ ስለማናገኝለት የራሱ ገደብ አለው። እግዚአብሔር በፍጥረት አማካይነት ያሳየው መገለጥ፥ የማያምነው ዓለም እርሱን እንደፈጣሪው ባለማምለኩ እንዲፈርድበት ቢያስችለውም፥ ይህ መገለጥ ኃጢአተኞች ቅዱስ ከሆነው እግዚአብሔር ጋር የሚታረቁበትን የድነት መንገድ አያመለክትም። 

2. በክርስቶስ የታየ የእግዚአብሔር መገለጥ። ታላቁ የእግዚአብሔር መገለጥ የተከናወነው ራሱ በወሰነው ጊዜ በተወለደው በክርስቶስ እና በክርስቶስ ሥራ ነው (ገላ. 4፡4)። የእግዚአብሔር ልጅ ሰው ሆኖ ወደ ዓለም የመጣው፥ ሰዎች ሊረዱት በሚቻላቸው አኳኋን እግዚአብሔርን ሊገልጥ ነው። ክርስቶስ ሥጋ ለብሶ በመወለዱ እጅግ ከባድ የሆነ የእግዚአብሔር እውነት፥ ውስኑ የሰው አእምሮ በሚረዳው ደረጃ ተገልጧል። ስለዚህ በክርስቶስ የተገለጠው፥ የእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ ብቻ ሳይሆን፥ በጎነቱ፥ ቅድስናው፥ ጸጋውና ፍቅሩ ጭምር ናቸው። ይህንም ክርስቶስ ራሱ ሲመሰክር፥ “እኔን ያየ አብን አይቶአል” በማለት አረጋግጧል (ዮሐ. 14፡9)። ስለሆነም ክርስቶስ ኢየሱስን ያየውና ያወቀው ሁሉ፥ እግዚአብሔር አብንም አይቶታል፥ አውቆታልም። 

3. በተጻፈ ቃል አማካይነት የተሰጠ የእግዚአብሔር መገለጥ። በጽሑፍ የሰፈረው የእግዚአብሔር ቃል፥ በክርስቶስ በራሱና በሥራው ከታየው ይልቅ ግልጥ በሆነ ቃል እግዚአብሔርን ሊገልጠው ይችላል። ቀደም ብሎ የተጻፈ እንደመሆኑ መጠን፥ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ትንቢት ዓላማ ወይም ባለቤት እና እንደ ትንቢት ፍጻሜ የሚያስተዋውቀን መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በዝርዝር ከመግለጥ አልፎም፥ እግዚአብሔር ለእስራኤል፥ ለመንግሥታትና ለቤተ ክርስቲያን ያለውን ፕሮግራም ያመለክታል። የሰው ዘር ታሪክንና የዓለማትን መታወቅ የመሳሰሉ ነገሮችንም ይመለከታል። 

መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን ዋና ጉዳዩ አድርጎ ማቅረብ ብቻ ሳይሆን፥ የእግዚአብሔርን ዓላማም ይገልጣል። በጽሑፍ የሰፈረው መገለጥ አጠቃላይ ነው። እግዚአብሔርን በተመለከተ፥ በተፈጥሮ አማካይነት የተገለጡትን እውነቶች ሁሉ ለማስገንዘብ፥ የእግዚአብሔርን በክርስቶስ መገለጥ ብቸኛ ዘገባ ያቀርባል። እግዚአብሔር አብን፥ ወልድን፥ መንፈስ ቅዱስን መላእክትን፥ አጋንንትን፥ ሰውን፥ ኃጢአትን፥ ድነትን፥ ጸጋን፥ እና ክብርን በተመለከተ ያለውን መገለጥ በጥልቀት ይዘረዝራል። በዚህ መሠረት፥ መጽሐፍ ቅዱስ፥ በተፈጥሮ በከፊል የታየውን፥ ይበልጥ በሙላት በክርስቶስ የተገለጠውን እና በጽሑፍ በሰፈረው ቃል የተጠቃለለውን መለኮታዊ መገለጥ ከፍጻሜ እንዳደረሰ ሊቆጠር ይችል ይሆናል። 

ለ. ልዩ መገለጥ 

በመላው የሰው ልጅ ታሪክ እግዚአብሔር ልዩ ራእይ ወይም መገለጥን ሰጥቶአል። በኤደን ገነት ውስጥ ከሰው ጋር ፊት ለፊት ተነጋግሯል። በተመሳሳይ ሁኔታ ከነቢያት ጋር በብሉይ ኪዳን ወይም ከሐዋርያት ጋር በአዲስ ኪዳን የተናገረባቸው ብዙ ሁኔታዎች ተመዝግበዋል። ከነዚህ ልዩ መገለጦች ጥቂቱና በእስትንፋሰ-እግዚአብሔር የተሞላ ሥልጣን ያላቸው፥ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግበዋል። 

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉ ስድሳ ስድስት መጻሕፍት ሌላ ኣዲስ መጻሕፍትን ሊያስጨምር የሚችል ልዩ መገለጥ አይኖርም። ስለዚህ አዋልድ መጻሕፍት እስትንፋሰ እግዚአብሔርነት ስለሌላቸው፥ ከስድሳ ስድስቱ መጻሕፍት እኩል የሚታዩ አይደሉም። 

ይሁን እንጂ፥ በአሁኑ ጊዜ በልዩ መገለጥ ፈንታ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ጎልቶ ይታወቃል። የእግዚአብሔር መንፈስ ለቃሉ አብርሆት ወይም ብርሃን እንደሚሰጥ፥ የአሁኑ ጊዜ መገለጥም የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮዎች ለግል ሕይወትና ሁኔታዎች ግልጥ የሚሆኑት በዚህ አኳኋን ነው። ከእስትንፋሰ-እግዚአብሔር ጋር በተጓዳኝ የምናየው ነገር፥ መንፈስ ቅዱስ ለአንድ ሰው የሚያስፈልጉት አጠቃላይ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ተግባራዊ የሚሆኑበትን መንገድ የመምራቱ ሥራ ነው። ሁለቱም፥ ማለት ምሪትና አብርሆት ትክክለኛዎቹ የእግዚአብሔር ሥራዎች ቢሆኑም፥ አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ በሙሉ ለመረዳቱ ወይም የእግዚአብሔርን ምሪት በትክክል ለመገንዘቡ ዋስትና አይሰጡም። ስለዚህ፥ አብርሆትና ምሪት የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ቢሆኑም፥ ለስሕተት በሚጋለጥ ሰብአዊ ፍጡር በኩል የሚመጡና ለእርሱ የሚያስፈልገውን ነገር ለመግለጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በተያያዘ መልክ ስለሚሰጡ፥ “በእስትንፋሰ-እግዚአብሔር” የተጻፈን የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል ስሕተት ኣልባ ሊሆኑ አይችሉም። 

1ኛ ቆሮንቶስ 2፡10 ውስጥ እንደተመለከተው፥ ቃሉን በሚገልጥልን በእግዚአብሔር መንፈስ አማካይነት ካልሆነ በስተቀር፥ እውነትን በሚገባ የምንረዳበት መንገድ የለም። የእግዚአብሔር ቃል እውነት፥ በእግዚአብሔር መንፈስ ሊገለጥልን ይገባል። መማር ያለብንም በመንፈስ ቅዱስ ነው (1ኛ ቆሮ. 2፡13)። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡14 ውስጥ እንደተጠቀሰው፦ “ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፥ በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊያውቀው አይችልም”። ስለዚህ ትክክለኛ ፍቺውን መረዳትን በተመለከተ፥ መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያን ላልሆነና ከመንፈስ ቅዱስ ለማይማር ሰው ስውር ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን የሚማር ሰው፥ መንፈስ ቅዱስ እውነቱን ይገልጥለት ዘንድ ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ግንኙነት ሊኖረው ይገባል። 

ሐ. ትርጉም ወይም ፍቺ 

አንድ በክርስቶስ አማኝ የሆነ ሰው፥ የእግዚአብሔርን ቃል መገለጥ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በሚያጠናበት ጊዜ፥ ትርጉምን ወይም ፍቺን በሚመለከት አንዳንድ ችግሮች ይገጥሙታል። በመሆኑም አንድ ሰው “የመጽሐፍ ቅዱስ አፈታት ዘዴ” (“ኸርማኒዩቲክስ” /hermeneutics) ተብሎ በሚጠራው የእግዚአብሔር ቃልን የማጥኛ ስልት ለመጠቀም ከፈለገ፥ የአተረጓጎም መሠረታዊ ደንቦችን ሊከተል ይገባል። ፍቺን ወይም መረዳትን በተመለከተ በመንፈስ ቅዱስ ላይ መደገፍ አስፈላጊነቱ ሳይዘነጋ፥ አንዳንድ መሠረታዊ የማጥኛ ስልቶች ስለሚያስፈልጉ በዝርዝር ልናያቸው ይገባል። 

1. የመጽሐፍ ቅዱስ አጠቃላይ ዓላማ። መጽሐፍ ቅዱስ በሚተረጎምበት ወይም በሚፈታበት ጊዜ ራሱን በራሱ የማይቃረን መጽሐፍ ስለሆነ፥ እያንዳንዱ ጥቅስ ከአጠቃላዩ ይዘት ጋር መዛመድ አለበት። 

2. እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ የያዘው ልዩ መልእክት። የእግዚአብሔር ቃል ፍቺ ወይም ትርጉም ሥራ ሁልጊዜ የሚተረጎመውን መጽሐፍ ዓላማ ከግንዛቤ ማስገባት አለበት። በዚህ መሠረት፥ የመጽሐፈ መክብብ ጥናት ወይም አተረጓጎም፥ ከራእይ ወይም ከመዝሙረ ዳዊት ጥናት ይለያል። ለዚህ ነው አንድ ትርጉም ከሚተረጎመው መጽሐፍ ዓላማ መራቅ የለበትም የሚባለው። 

3. ለማን ተጻፈ? መጽሐፍ ቅዱስ በእስትንፋሰ-እግዚአብሔር የተጻፈ ቢሆንም፥ ሁሉም በእኩልነት ሥራ ላይ የሚውል አይደለም። የእግዚአብሔርን ቃል በተሳሳተ አኳኋን ከመተርጎም የተነሣ ብዙ የሐሰት አስተምህሮዎች ተፈጥረዋል። ስለዚህ አንድ የንባብ ክፍል በሚጠናበት ጊዜ፥ ማን፥ ለማን፥ የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሣት ተገቢ ነው። የተጻፈውን መልእክት ስንመለከት፥ የተጻፈላቸው የመጀመሪያዎቹ ተቀባዮች ሲሆኑ፥ ከዛ በኋላ የሚያነቡት ሁለተኛ ተጠቃሚዎች ወይም ከራሳቸው ጋር አዛማጆች ይሆናሉ። የመጀመሪያው ተግባር ጽሑፉ እስከተጻፈለት ግለሰብ ወይም ቡድን የሚደርስ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ለገላትያ ሰዎች የተላከው መልእክት ወይም በዳዊት የተጻፈው መዝሙር ሊሆን ይችላል። በመጽሐፍ ቅዱሳዊው የንባብ ክፍል ውስጥ ያለ እውነት፥ በመጀመሪያ ጽሑፉ ለተጻፈላቸው ሰዎች የሚሆን ሲሆን፥ በሁለተኛ ደረጃ ሌሎችን የሚያጠቃልል እውነት ይኖረዋል። ስለዚህ፥ የብሉይ ኪዳን ሕግ ለእስራኤል የተጻፈ ቢሆንም፥ በዚህ ስፍረ-ዘመን ያሉ ክርስቲያኖች ቃሉ የእግዚአብሔር ቅድስና መግለጫ እንደሆነ ተገንዝበው ያጠኑታል። በዚህ መሠረት አንዳንድ ልዩ ነገሮች ለኛ ሁኔታ የሚውሉና የሚጠቅሙ ሊሆኑ ይችላሉ። 

4. ዐውደ-ንባቡ ወይም አገባቡ (context)። ማንኛውም ምንባብ በሚብራራበት ጊዜ ልብ ሊባሉ ከሚገባቸው ጠቃሚ ነገሮች አንዱ፥ የምንባቡን የቅርብ ዐውድ ወይም አገባብ ማጤን ነው። ይህ አሠራር ብዙ ጊዜ በገላጣው ውስጥ ሊባል ስለተፈለገው ነገር ፍንጭ ይሰጣል። ማንኛውንም ጥቅስ የሚቀድም ወይም የሚከተል ቃል እንዲሁም ዓረፍተ ነገር፥ አንባቢው ጥቅሱን እንዲገነዘብ ይረዳዋል። 

5. በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በሌላ ስፍራ የሚኖሩ ተመሳሳይ ትምህርቶች። መጽሐፍ ቅዱስ ራሱን በራሱ የሚቃረን ስላይደለ፥ ስለ አንድ ጥቅስ ትምህርተ-መለኮታዊ ገለጣ ሲሰጥ፥ በሌላ ስፍራ ካሉ ገለጣዎች ጋር መዋሐድ ወይም መጣጣም አለበት። ይህ ነው የቅንብራዊ ትምህርተ-መለኮት (Systematic Theology) ልዩ ተግባር። ይህ ቅንብራዊ ትምህርተ-መለኮት፥ መለኮታዊውን መገለጥ እንዳለ በመውሰድ፥ ከማንኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጋር በማይቃረን ሁኔታ በትምህርትነት ሊያቀናብረው ይሞክራል። የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት ብዙ ጊዜ ይደጋገፋሉ። ለምሳሌ፥ መጽሐፈ ራእይ ስለ መልእክቱ ፍቺ በዳንኤል ወይም በሌሎቹ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ላይ ይደገፋል። የእግዚአብሔር ደራሲ መንፈስ ቅዱስ ከሆነ፥ በመጽሐፉ አንድ ስፍራ የተጠቀሰ ነገር በሌላ ስፍራ የተባለውን ለመረዳት የሚያግዘን መሆን አለበት። 

6. የአንድ ጥቅስ ቃላት ትክክለኛ ትንታኔ። መጽሐፍ ቅዱስ በመጀመሪያ የተጻፈው በዕብራይስጥና በግሪክ ቋንቋዎች በመሆኑ፥ ብዙ ጊዜ በትክክለኛ ትርጉም አሰጣጥ ረገድ ችግር አለ። ስለሆነም የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበትን ቋንቋ ማወቁ፥ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ምን መልእክት እንዳለው በውል ለመረዳትና ለመወሰን በጣም ይጠቅማል። እነዚህ ቴክኒካዊ እውቀቶች የሌሏቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች፥ አንድን የተለየ ጽሑፍ ከመጽሐፍ ቅዱስ መፍቻዎችና ማብራሪያዎች ይረዳሉ። ለአብዛኛው ጉዳይ ወይም ዓላማ ጥሩ ትርጉም በቂ ቢሆንም፥ ጥንቁቅ ተማሪዎች ልዩ ለሆኑ ጥቅሶች ማብራሪያ ሊሰጡ የሚችሉ ምሁራንን ያማክራሉ። 

የአንድን ቃል ቀጥተኛ ትርጉም ከመወሰን ጋር፥ ቃሉን ፈሊጣዊ ነው ለማለት የሚያበቃ ነገር ከሌለ፥ እያንዳንዱ ቃል የራሱ ተገቢና ቀጥተኛ ትርጉም አለው። ትክክለኛው አተረጓጎም ይህን ይቀበላል። ለምሳሌ፥ ለእስራኤል ተስፋ የተገባለት ምድር መንግሥተ ሰማያትን የሚያመለክት ሆኖ ሊቆጠር አይገባም። ከዚያ ይልቅ፥ ቅድስቲቱን ምድር (አገር) የሚያመለክት መሆን አለበት። በተመሳሳይ ሁኔታ ለእስራኤል የተሰጡ ተስፋዎች በክርስቶስ ላመኑ አሕዛብም እንደሚሆኑ ለማድረግ ሲባል መንፈሳዊ ትርጉም ሊሰጣቸው አይገባም። የትርጉም ሕግ የሚለው፥ ፈሊጣዊ አነጋገር ከሌለ እና አገባቡም ይህን የሚመለከት ካልሆነ በቀር፥ ቃላት ትክክለኛ ወይም ቀጥተኛ ትርጉም ነው ሊሰጣቸው የሚገባ። 

7. ከመጥፎ አመለካከት መጠበቅ። አንድ የእግዚአብሔር ቃል ፈቺ ወይም ተርጓሚ፥ አንድን የንባብ ክፍል፥ መጽሐፍ ቅዱስን ከማጥናትና ከትምህርተ-መለኮት እምነቱ አንጻር መመልከቱ ተገቢ ሲሆን፥ አንድን ጥቅስ ቀደም ተብሎ ከተፀነሰ አሳቡ ጋር ለማዋሐድ ሲል ሊያዛባው ግን አይገባም። ከሌሎች የመጽሐፉ ክፍሎች ጋር ያለውን ተዛምዶ በተመለከተ ያልተፈታ ችግር ቢኖርም እንኳን፥ እያንዳንዱ ቃል ራሱን በራሱ መፍታት አለበት። ከሌላ ቃል ጋር ያለውን መዋሐድ በተመለከተ ችግር ቢኖርበትም፥ እያንዳንዱ ጥቅስ በራሱ ቃል በቃል የሚሰጠውን ትርጉም መያዝ ይገባዋል። 

መጽሐፍ ቅዱስ በሚፈታ ወይም በሚተረጎምበት ጊዜ፥ የእግዚአብሔር ቃል በመንፈስ ቅዱስ ለሚመሩ ሁሉ ይረዱት ዘንድ የተሰጠ መጽሐፍ መሆኑን መገንዘብ ይገባል። የመጽሐፍ ቅዱስ ዓላማ እውነትን ማስተላለፍ ነው። በትክክል ሲፈታ፥ የተዋሐደ፥ እርስ በርሱ የማይቃረንና የተትረፈረፈ የትምህርት ፍሬ አለው።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

5
ትምህርት 5 ከ52

እግዚአብሔር ሥሉስ

ሀ. በእግዚአብሔር ሕልውና ማመን 

ከሰው የሚልቅና መለኮታዊ ሕልውና ያለው አካል መኖሩን ማመን በማንኛውም ባሕልና ሥልጣኔ ያለ ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት፥ ባንድ ወገን፥ ሰው ስለ ዓለማችንና ስለ ሰብአዊ ልምምድ የሚገለጥ አንድ ነገር መኖር አለበት፥ ይህን ለመግለጥም፥ ያ ከሰው የሚልቅ አካል ይቻለዋል ብሎ ስለሚመራመር ነው። ሰው በተፈጥሮ አስተዋይነቱ እንዲሁም ሃይማኖታዊ ተፈጥሮው ከርሱ የሚልቅ ሕልውና ወዳለው አካል የመድረስ ፍላጎት አለው። ይህ ፍላጎቱ በትምህርተ መለኮት ለሁሉም የሚሆን ጸጋ በመባል ከሚታወቅ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ጋር በመያያዝ ሊገለጥ ይችላል። ይህ ከሰዎች ድነት ጋር ከተያያዘው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ የተለየ ነው። እግዚአብሔር የለም የሚሉ ብዙ ሰዎች ዘመናዊ ክሥተት የሚመነጨው፥ ከተዛባ አስተሳሰብ እና በማንኛውም አቅጣጫ በሚደረግ ምርምር ዓለምን ለመግለጥ ይቻላል ከሚል አመለካከት ነው። እግዚአብሔር የለም የሚለውን ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ሞኝ* ይለዋል(መዝ. 14፡1)።

*እዚህ ላይ የተጠቀምነው የ1980ውን ትርጉም ነው። ምክንያቱም ዩናባል ለሚለው የዕብራይስጥ ቃል የተሻለ ትርጉም ይሰጣል ብለን ስለምናምን ነው።  በተለያዩ አገባቦች “ናባል” የሚለው ቃል ብሉይ ኪዳን ውስጥ 36 ጊዜ ጥቅም ላይ ውሏል። አምስት ጊዜ የአእምሮ ችግርን ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል። ነገር ግን በአብዛኛው “ናባል” በሕብረተሰብ ያለውን ሕግ ወይም የእግዚአብሔርን ሕግ በድፍረት የሚጥስ ሰው አስተሳሰብን ይገልጣል። ለምሳሌ “ናባል” ሴኬም ዲናን አስገድዶ መድፈሩን ለመግለጥ (ዘፍጥ. 34፡7)፥ አምኖን ትዕማርን አስገድዶ መድፈሩን (2ኛ ሳሙ. 13፡12-13)፥ ከጎረቤት ሚስት ጋር ማመንዘርን (ኤር. 29፡23) ለመግለጥ ጥቅም ላይ ውሏል። አካን ከኢያሪኮ ድል በኋላ የፈጸመው የምርኮ ዕቃዎች ስርቆት “ናባል’ ነበር (ኢያሱ 7፡15)። የኢዮብ ጓደኞች “ናባል” ተብለው ተጠርተዋል። ምክንያቱም አስተሳሰባቸውና ድምዳሜያቸው ከእግዚአብሔር አልነበረምና (ኢዮ. 42፡8)። የእስራኤል መሪዎችም እርኩሰትን ሲለማመዱ፥ ዓመጽን ሲያቅዱ፥ ሰዎችን ሲያስርቡ ናባል ተብለው ይጠሩ ነበር (ኢሳ. 32፡5-7)።  ሐሰተኛ ነቢያት አክአብና ሴዴቅያስ “ናባል” ነበሩ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን እውነት አልተናገሩም (ኤር. 29፡23)። የእስራኤል ሕዝብ ናባል ነበር (ዘዳ. 32፡6፥ 15፥ ኤር. 14፡1)። ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ክብርና ታላቅነት እያወቀ ከእርሱ ይርቅ ነበር። ናባል የእግዚአብሔርን መኖር የሚክድና (መዝ. 14፡1፥ 53፡2)፥ በእግዚአብሔር በሚታመኑት ላይ የሚሳለቅ ነው (መዝ፡39፥9፥ ኢዮ. 2፡10)።  

በተለምዶ ሰዎች ስለ ራሳቸው ሕልውናም ሆነ፥ በስሜት ሕዋሶቻቸው አማካይነት ሊረዱአቸው ስለሚችሉአቸው ቁሳዊ ነገሮች ሕልውና ማረጋገጫ አይጠይቁም። እግዚአብሔር በአካለ ሥጋ ባይታይም ሕልውናው የተረጋገጠ በመሆኑ፥ በአብዛኛው ሰዎች ስለ መኖሩ ምንም ማስረጃ አይጠይቁም። የእግዚአብሔርን ሕልውና መጠራጠር የሚመጣው፥ ሰው ራሱ ትክክለኛውን መንገድ ከመሳቱና መንፈሳዊ ዓይኑ በመታወሩ፥ እንዲሁም ከሰይጣናዊ ተጽዕኖ የተነሣ ነው። የእግዚአብሔር ሕልውና በተፈጥሮ አማካይነት በሚገባ ተገልጧል። ስለ ወንጌል ያልሰማው የማያምን ዓለም የፍርድ መሠረትም ይህን በተፈጥሮ የተገለጠ የእግዚአብሔር ሕልውና አለማመኑ ነው። በመሆኑም ሮሜ 1፡19-20 ውስጥ፥ “እግዚአብሔር ስለገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና”፥ በሚለው ቃል መሠረት ይፈረድባቸዋል። 

መጽሐፍ ቅዱስ ከመጻፉ በፊት በነቢያት በኩል የተላለፈውን እና በመጽሐፉ የተላለፈውን የእግዚአብሔር መገለጥ ዛሬ በተወሰነ ደረጃ አብዛኛው ሰው ያውቀዋል። ዓለም በጠቅላላው ሲታይ በመጽሐፍ ቅዱስ ስለተላለፈው መገለጥ መሃይም ቢሆንም፥ በመጠኑም ቢሆን ስለ እግዚአብሔር እንዲያሰላስል መገለጡ የዓለምን ሁሉ አሳብ ይዞታል። ስለዚህ በአንድ ሉዓላዊ በሆነ አካል ማመን መጽሐፍ ቅዱስ በቀጥታ ባልደረሳቸው ሰዎች ዘንድ እንኳ አለ። 

ጥንታዊ የግሪክ ፈላስፋዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊውን መገለጥ ባያውቁትም፥ አንድ ሉዓላዊ አካል አለ በሚል አስተሳሰብ ላይ በመመሥረት ዓለማትን ለመግለጥ ሞክረው ነበር። በዚሁ መሠረት የተለያዩ የአስተሳሰብ ዘዴዎች ቀርበዋል። እነሱም፦ 

1. በብዙ አማልክት ማመን (Polytheism)፤ 

2. ኃይሎኮይዝም (Hylozoism) በእያንዳንዱ ተፈጥሮ ውስጥ የሚገኘው የሕይወት ሥርዓት ራሱ እግዚአብሔር ነው የሚል እምነት፤ 

3. ቁስ-አካላዊነት (Materialism)፥ ቁስ-አካል በራሱ የተፈጥሮ ሕግ መሠረት የሚሠራ ስለሆነ፥ ለማንኛውም እንቅስቃሴው ምንም አምላክ አያስፈልገውም። ይህ ትምህርት የአዝጋሚ ለውጥን (Evolution) አሳብ የሚደግፍ ነው፤ 

4. “ፖንቴይዝም” (Pantheism) የሚባለው ደግሞ እግዚአብሔር ስብእና የሌለውና ከተፈጥሮ ጋር አንድ የሆነ ነው፥ ስለዚህም እግዚአብሔር አብሮ ያለ፥ የቅርብና እኩያ እንጂ የበላይ የሆነ ወይም አእምሮን የሚያልፍ አይደለም ይላል። ስለ እግዚአብሔር ይህን የመሳሰሉ ብዙ አስተሳሰቦች አሉ። 

ስለ እግዚአብሔር መኖር ከቃሉ ከሚገኘው መገለጥ ውጪ፡ከተፈጥሮ እውነት አንጻር ብቻ ሲታይ እንኳን የሚከተሉት አራት ዋና ዋና አሳቦች ወይም ምክንያቶች ሊስተዋሉ ይችላሉ። እነርሱም፡

1. እግዚኣብሔር አለ ብሎ ሰው ሁሉ ስለሚያምን እግዚኣብሔር መኖር አለበት የሚለው አሳብ ነው። ይህ አስተሳሰብ “አንተሎጂካል ተሐስቦ” (Ontological argument) ይባላል። 

2. የዓለማት አፈጣጠር ተሐስቦ (Cosmological argument) የተሰኘው አመለካከት፥ ማንኛውም ውጤት ምክንያት ወይም መነሻ ሊኖረው ይገባል፤ ስለሆነም ውጤት የሆኑት ዓለማት መነሻ የሆን ፈጣሪ ሊኖራቸው ይገባል ይላል። በዚህም አሳብ የተካተተው ሌላ አመለካከት በአጋጣሚ ሊመጡ የማይችሉት ዓልማት ሥርዓት ውስብስብነት ነው። 

3. ማንኛውም ውጥን ወይም ዕቅድ ያለ አድራጊና ያለ ዓላማ ሊከናወን አይችልም የሚለው “ቴሌሎጂካል ተሐስቦ” (Teleological argument) አስተሳሰብ፥ ተፈጥሮ ባጠቃላይ በረቀቀ ሁኔታ የታቀደና አንዱ ከሌላው የተዛመደ እንደ መሆኑ እንድ ታላቅ ሠሪ ሊኖረው ይገባል ይላል። ነገሮች ሁሉ በአንድነትና በኅብረት የመሥራታቸው እውነት፥ እነሱን የሠራ ፈጣሪ ፍጹም ኃይልና ጥበብ ያለው መሆኑን ያመለክታል። 

4. ሥነ-ሰብአዊ (Anthropological argument) አመለካከት፥ የሰው ተፈጥሮ በአምሳያው ከፈጠረው፥ ነገር ግን ከርሱ እጅግ ከሚልቀው ከእግዚአብሔር ባሕርይ ተለይቶ ሊገለጥ አይችልም ይላል። ከዚሁ ጋር ሰው አእምሮ (የማሰብ ችሎታ)፥ ስሜት (በስሜት የመገንዘብ ችሎታን)፥ ፈቃድ (ምርጫ የማድረግ ችሎታ) አለው። እንዲህ ያሉት ልዩ ችሎታዎች ተመሳሳይ ነገር ግን የላቀ ባሕርይ ወዳለውና ሰውን ወደፈጠረ አምላክ ያመለክታሉ። 

የእግዚአብሔርን ሕልውና አስመልክቶ የተነሡ እነዚህ አስተሳሰቦች በቀላሉ የማይገመት ጠቀሜታ አላቸው። ሰውም እነዚህን አሳቦች ባለመቀበሉ የተፈረደበት መሆኑ ትክክል ቢሆንም (ሮሜ 1፡18-20)፥ ሰው በትክክል ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኝ አልረዳውም፤ ወይም ያለ መጽሐፍ ቅዱስ እርዳታ በእግዚአብሔር እውነተኛ እምነት እንዲኖረው አልረዳም። የእግዚአብሔር ሙሉ መገለጥ የተሰጠው በመጽሐፍ ቅዱስ ነው። በመሆኑም ተፈጥሮ ውስጥ ያሉትን እውነታዎች እና በርሱም ላይ ተፈጥሮ ሊገልጣቸው የማይቻለው ብዙ እውነቶች ታክለዋል። 

ለ. የሥላሴ መለኮታዊ አንድነት 

ብሉይ ኪዳን በአጠቃላይ የእግዚአብሔርን ውሑድነት ወይም አንድነት ይገልጣል (ዘፀ. 20፡3፤ ዘዳ. 6፡4፤ ኢሳ. 44 ፡6)። ይህን እውነት አዲስ ኪዳንም ያስተምራል (ዮሐ. 10፡30፤ 14፡9፤ 17፡11፤ 22፡23፤ ቆላ. 1፡15)። ብሉይ ኪዳን፥ በይበልጥም አዲስ ኪዳን፥ እግዚአብሔር በሥሉስነት ማለት፥ እግዚአብሔር አብ፥ እግዚአብሔር ወልድ፥ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሆኖ እንደሚኖር ያስገነዝባሉ። ብዙ ሰዎች የሥላሴ ትምህርት ኤሎሂም በሚለውና የእግዚአብሔርን ሥሉስነት ያመለክታል ተብሎ በሚታመነው ስም ውስጥ ይጠቃለላል ይላሉ። ይህንንም የሚሉበት ምክንያት ኤሎሂም የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር በመሆኑ ነው። 

በዘፍጥረት መጀመሪያ ክፍሎች ስለ እግዚአብሔር መንፈስ የሚገልጥና እግዚአብሔርን በብዙ ቁጥር የሚያመለክት ተውላጠ ስም ይገኛል (ዘፍጥ. 1፡26፤ 3፡22፤ 11፡7)። የአብን፥ የወልድንና የመንፈስ ቅዱስን ባሕርይ በተመለከተ፥ ብዙ ጊዜ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ልዩነቶች አሉ። ኢሳይያስ 7፡14 ላይ ወልድን አማኑኤል “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” በማለት ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ለየት አድርጎ ያቀርበዋል። ኢሳይያስ 9፡6 ላይ ደግሞ፥ ይሄው ወልድ “ኃያል አምላክ፥ የዘለአለም አባት፥ የሠላም አለቃ” ተብሏል። 

መዝሙረ ዳዊት 2፡7 ውስጥ “እኔ” ተብሎ የተጠቀሰው እግዚአብሔር አብ፥ ዓሳማው ልጁን የዓለም ልዑል ገዢ ማድረግ መሆኑ ተገልጧል። አብና ወልድ እንደተለያዩ ሁሉ፥ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን መላኩ በተገለጠበት መዝሙረ ዳዊት 104፡30 ውስጥ፥ አብ ከመንፈስ ቅዱስ የሚለይ መሆኑ ተመልክቷል። በዚህ ላይ የሚታካሉት ሌሎች ማስረጃዎች፥ የእግዚአብሔርን ልጅ መገለጥ በሚያመለክተው ብሉይ ኪዳን ውስጥ “የያህዌህ መልአክን” መታየት የሚያሳዩት ታሪኮች ናቸው። የእግዚአብሔር መንፈስ፥ መንፈስ ቅዱስ መሆኑና እርሱም ከአብና ከወልድ የተለየ መሆኑ መገለጡም ከዚሁ ጋር የሚዳመር ነው። 

ለነዚህ የብሉይ ኪዳን ማስረጃዎች እዲስ ኪዳን ተጨማሪ መገለጥ ይሰጣል። ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ የተፀነሰና የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ፥ ማለት ሥጋ የለበሰ አምላክ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ሥርዓተ ጥምቀት ጊዜ፥ እግዚእብሔር አብ ከሰማይ ሲናገር፥ መንፈስ ቅዱስ በእርግብ አምሳል ወርዶ በላዩ ሲያርፍበት እና፥ ኢየሱስ እራሱ ሲጠመቅ፥ በሥላሴ ውስጥ ያለው ልዩነት ተገልጧል (ማቴ. 3፡16-17)። ይህ የሥላሴ ልዩነት ዮሐንስ 14፡16 በመሳሰሉ ክፍሎችም ታይቷል። በነዚህ ምንባቦች አብና አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ከክርስቶስ ተለይተው ተገልጠዋል። ማቴዎስ 28፡19 ውስጥ ደቀ መዛሙርት “በአብ፥ በወልድ፥ በመንፈስ ቅዱስ ስም” እንዲያጠምቁ በታዘዙበትም ልዩነቱ ተመልክቷል። 

እግዚአብሔር በሥሉስነት የሚኖር መሆኑን በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን የሚያመለክቱት ክፍሎች፥ የሥላሴን ትምህርት በመግለጥ ረገድ ከጥንት እስከዛሬ የትክክለኛው እምነት ማዕከላዊ እውነት ናቸው። በመሆኑም ይህን አለመቀበል የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት እንዳለመቀበል ተቆጥሯል። “ሥላሴ” የሚለው ቃል መጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ ባይገኝም፥ የእግዚአብሔር ቃል መገለጥ እውነቶች ይህንኑ ብቻ የሚያሳዩ ናቸው። 

የሥላሴ ትምህርት የክርስትና እምነት ትምህርት ማዕከላዊ እውነት ሲሆን፥ ከሰብአዊ ግንዛቤ በላይና በሰው ልምምድ ውስጥ አምሳያ የሌለው ነው። እግዚአብሔር አንድ ሲሆን፥ በሦስት አካልነት ይኖራል የሚለው አገላለጥ ከሁሉ የተሻለ ነው። እነዚህ አካላት አቻ ናቸው፥ አንድ ባሕርይ አላቸው፤ እኩል ክብር፥ አምልኮና መታመን ይገባቸዋል። ያም ሆኖ ስለ እግዚአብሔር አምላክ ውሑድነት ያለው መሠረታዊ ትምህርት እነዚህ አካላት እንደተለያዩ ሰዎች ማለት፥ ጴጥሮስ፥ ያዕቆብ፥ ዮሐንስ እንደ ማለት የተለያዩ ሦስት አማልክት አለመሆናቸውን በግልጥ ያስረዳል። በመሆኑም እውነተኛው የክርስትና እምነት የሦስት አማልክት እምነት አይደለም። በሌላም በኩል ሥላሴ እግዚአብሔር እራሱን የገለጠበት ሦስት መንገዶች እንደሆነ ሊታሰብ አይገባም። ሥላሴ ማለት ስለ እግዚአብሔር ሕላዌና ማንነት የሚናገር እንጂ፥ ራሱን የገለጠበትን ሦስት መንገዶች የሚያሳይ አይደለም። ስለሆነም የሥላሴ ትምህርት ስለ እግዚአብሔር ባለ ትምህርት ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ነው። 

የሥላሴ አካላት በሕላዌ አቻ ባሕርይ ቢኖራቸውም፥ በአንዳንድ ሁኔታዎች ይለያያሉ። በዚሁ መሠረት የመጀመሪያው አካል እግዚአብሔር አብ ይባላል። ሁለተኛው በአብ የተላካውና እግዚአብሔር ወልድ ተብሎ የሚጠራው ነው። ሦስተኛው አካል ደግሞ፥ በአብና በወልድ የተላከው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው። ይህ በትምህርተ-መለኮት ገላጣ ሥርፀት የሚባል ሲሆን፥ ፈጽሞ አይዛባም፤ ማለት ወልድ በምንም ሁኔታ አብን፥ ወይም መንፈስ ቅዱስ ወልድን አይልክም። የአምላክን ልዩ ባሕርይ በተመለከተ፥ ለሰብአዊ አእምሮ የሚገባ ተምሳሌት የለም። ስለሆነም ምንም እንኳ ከሰብአዊ ግንዛቤና ቋንቋ በላይ ቢሆን፥ በእግዚአብሔር ቃል መገለጥ ላይ በመመሥረት ትምህርቱን በእምነት መቀበል ይገባል። 

ሐ. የእግዚአብሔር ስሞች 

በብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር በሦስት ዋና ዋና ስሞች ተጠርቷል። የመጀመሪያው “ያህዌህ” የሚለው ሲሆን፥ የእውነተኛው አምላክ መጠሪያ ስም ነው። ይህ ስም ዘፍጥረት 2፡4 ላይ እንደተመለከተው፥ ከፍጥረት ጋር ተያይዞ የቀረበ ሲሆን፥ የስሙም ትርጉም ዘዳግም 3፡13-14 ላይ እንደተመለከተው “ያለና የሚኖር እኔ ነኝ” ተብሎ ተገልጧል። የዚህ ፍቺው በራሱ የሚኖር ዘላለማዊ አምላክ ማለት ነው። 

በብሉይ ኪዳን የተለመደው የእግዚአብሔር ስም “ኤሎሂም” የሚለው ሲሆን፥ ለእውነተኛው አምላክና ለአሕዛብ አማልክት መጠሪያነት አገልግሏል። ስሙ መጀመሪያ የተገለጠው ዘፍጥረት 1፡1 ውስጥ ነው። የዚህ ስም ትርጉም ወይም ፍቺ አከራካሪ ሆኖ ቆይቷል። ቢሆንም “ብርቱው” ሊፈራና ሊከበር የተገባው የሚሉትን አሳቦች ያካተተ ይመስላል። የብዙ መጠሪያነትም ስላለው የሥላሴ አካላትን ያካተተ ይመስላል፤ የሥላሴን አካላት በተናጠል ለመጥራትም ያገለግላል። 

ብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚገኝ የእግዚአብሔር ሦስተኛ ስም፥ “አዶናይ” የሚለው ሲሆን፥ ትርጉሙም በተለምዶ “ጌታ” ማለት ነው። ይህ እግዚአብሔር ጌታችን መሆኑን ለማመልከት ብቻ ሳይሆን፥ በአገልጋዮቻቸው ላይ ጌታ ለሆኑ ሰዎች መጠሪያነትም ያገለግላል። ዘፍጥረት 15፡2 ውስጥ እንደተመለከተው፥ ይህ ቃል ኤሎሂም ከሚለው ስም ጋር በተደጋጋሚ ይያያዛል። እንዲያ ተያይዞ ሲጠቀስ እግዚአብሔር ጌታችን መሆኑን ያመለከታል። ብሉይ ኪዳን ውስጥ ብዙ የነዚህ ስሞች ጥምሮች አሉ። ብዙ ጊዜ የሚጠቀሰው ግን፥ ያህዌህ፥ ኤሎሂም ወይም አዶናይ ኤሎሂም የሚለው ነው። 

ከነዚህ ሦስት ዋና ዋና ስሞች ጋር ተያያዥ ወይም ተዋሐጅ የሆኑ ብዙ ቃላት ኣሉ። እነዚህም፥ ያህዌህ-ይርኤ “እግዚአብሔር ያዘጋጃል”፥ (ዘፍጥ. 22፡13-14)፥ ያህዌህ-ራፋ “እግዚአብሔር ፈዋሽ” (ዘጸ. 15፡26)፥ ያህዌህ-ንሲ “እግዚኣብሔር ዓላማዬ” (ዘጸ. 17:8-15)፥ ያህዌህ-ሻሎም “እግዚእብሔር ሰላማችን” (መሳ. 6፡24)፥ ያህዌህ-ጽድቅኒ “እግዚአብሔር ጽድቃችን” (ኤር. 23፡6)፥ ያህዌህ- ሻማ “እግዚኣብሔር እዚህ አለ” (ሕዝ. 48፡35) የሚሉ ናቸው። 

አዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉ ተጨማሪ የእግዚአብሔር ስሞች፥ የመጀመሪያው አካል “አብ”፥ ሁለተኛው አካል “ወልድ”፥ እና ሦስተኛው ኣካል “መንፈስ ቅዱስ” የሚሉ ናቸው። እነዚህ ስሞች አዲስ ኪዳን ውስጥ ይበልጥ የተለመዱ ይሁኑ እንጂ፥ ብሉይ ኪዳን ውስጥም አሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ የሚደረገው ውይይት ሦስቱን የሥላሴ አካላት ኣስመልክቶ በሚቀርቡት ምዕራፎች ውስጥ ይቀጥላል። 

መ. የእግዚአብሔር ባሕርያት 

በእግዚአብሔር ዋና ሕልውና ውስጥ እንዳንድ ተወራራሽ ወይም መሠረታዊ ባሕርያት አሉ። እነዚህ ባሕርያት፥ ለዘላለም የሥላሴ የሆኑና በሁሉም የሥላሴ አካላት ውስጥ በእኩል የሚኖሩ ናቸው። ከባሕርያቱ ውስጥ፥ እግዚአብሔር መንፈስ ነው (ዮሐ. 4፡24)፤ ሕይወት ነው (ዮሐ. 5፡26)፤ ኗሪ ነው (ዘጸ . 3፡14)፤ ገደብ የለውም (መዝ. 145፡3)፤ አይለወጥም (መዝ. 102፡27፤ ሚል. 3፡6፤ ያዕ. 1፡17)፤ እውነት ነው (ዘዳ. 32፡4፤ ዮሐ. 17፡3)፤ ፍቅር ነው (1ኛ ዮሐ. 4:8)፤ ዘለአለማዊ ነው (መዝ. 90፡2)፤ ቅዱስ ነው (1ኛ ጴጥ. 1፡16፤ 1ኛ ዮሐ. 1፡5)፤ በሁሉም ስፍራ አለ (መዝ. 139፡8፤ ኤር. 23፡23-24)፤ ሁሉን የሚያውቅ ነው (መዝ. 147፡4-5)፤ ሁሉን ቻይ ነው (ማቴ. 19፡26)፤ የሚሉት ይገኙባቸዋል። 

የእነዚህ ባሕርያት የተለያዩ ገጽታዎች፥ በእግዚአብሔር መልካምነት፥ መሐሪነትና ልዕልና ውስጥ ይታያሉ። ፍጹምነት ለዘላለም የእግዚአብሔር ሲሆን፥ ሥራዎቹና ሕልውናውም ፍጹም ናቸው። የዓለማት ዕቅድና ዝርዝር ሥራዎቹ የልዑልነቱ፥ የኃይሉና የጥበቡ ማረጋገጫዎች ናቸው። በቃሉ እንደተነገረው፥ የመገለጡ ዕቅድ፥ የፍቅሩ፥ የጽድቁ እና የጸጋው ማረጋገጫዎች ናቸው። ከርሱ ቁጥጥር ውጭ የሚሆን ተፈጥሮ የለም፤ የድንቢጥን ያህል ያነሰ ነገር እንኳን በልዑላዊ ዕቅዱ ውስጥ አይዘነጋም። 

ሠ. የእግዚአብሔር ልዕልና 

እግዚአብሔር ከሁሉ የላቀ መሆኑን ባሕርያቱ ይገልጣሉ። ለምንም ኃይል፥ ሥልጣን ወይም ከብር እንዲሁም ከርሱ ለበለጠ ፍጹም ትልቅ አካል የሚገዛ አይደለም። በሕልውናውና በማንኛውም ሁኔታ ፍጹም ነው። ድንገት ድል መሆንና ያልተረጋገጠ ነገር በርሱ ዘንድ የለም። ይሁን እንጂ ሥልጣኑን ሳይተው ወይም ፍጹም የሆነ ፍቃዱን ከማከናወን ሳይገታ፥ የተወሰነ የምርጫ ነጻነት ለሰዎች ወድዶ ሰጥቷል። በዚሁ መሠረት በምርጫው በመገልገሉ ረገድ እግዚአብሔር ሰውን ተጠያቂ ያደርገዋል። 

ሰው ከአምላክ ጸጋ በመወገዱ ሳቢያ፥ ለእግዚአብሔር ሥራ ዕውርና ስሜቱም የደነዘዘ በመሆኑ፥ እግዚኣብሔር ራሱ በመንፈሱ አማካይነት ካላነሣሣው በቀር፥ ወደ እግዚኣብሔር እንደማይመለስ ከመጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ለመረዳት ይቻላል (ዮሐንስ 6፡44፤ 16፡7-11)። ይሁን እንጂ ሰውም በበኩሉ ባለማመኑ በኃላፊነት ተጠያቂ ስለሆነ፥ ይድን ዘንድ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምን ታዟል (ሐዋ. 16፡31)። እንዲሁም እግዚአብሔር በሰዎች፥ በተለይም በክርስቲያኖች ጉዳይ ወይም ነገር አማካይነት ፍቃዱን ለመፈጸም ይሠራል (ፊሊጵ. 2፡13)። ቢሆንም በፈቃደኝነታቸው እንጂ ሰዎችን በኃይል እያስገድዳቸውም (ሮሜ 12፡1-2)። 

እግዚአብሔር ለሰው የተወሰነ ነጻነት መስጠቱ በዓለማት ውስጥ እርግጠኛነት የለም እያሰኝም። እግዚአብሔር፥ ሰው ከመለኮትና ከመሰሉ ከሰው ለሚደረግበት ተጽዕኖ የሚመልሰውን አጸፋ ሁሉ አስቀድሞ ያውቃል። ስለሆነም ልዕልናው እስከ ማንኛውም ድርጊት፥ እርሱ የሚከብርበት ከሆነ፥ ክፉ ነገርን ለጊዜው እስከ መፍቀድም ይደርሳል። 

ረ. የእግዚአብሔር ድንጋጌ 

የእግዚአብሔር ልዑላዊ ዓላማና ዕቅድ በትምህርተ-መለኮት የእግዚኣብሔር ድንጋጌ ተብሏል። ይህ ስያሜ ወደፊት የሚሆኑትን ክንውኖች ሁሉ የሚጨምረውን ጠቅላላ ዓላማና ዕቅድ ያመለክታል። የእግዚአብሔር ድንጋጌ እርሱ ራሱ የሚያደርጋቸውንና በተፈጥሮ ሕግ በኩል የሚያከናውናቸውን ይጨምራል። እነዚህን ሁሉ በፍጹም ሉዓላዊነቱ የሚቆጣጠራቸው እርሱ ነው። የሰው ድርጊቶች እንዴት በዘላለማዊ ዕቅዱና ድንጋጌው ውስጥ እንደተካተቱ ለመረዳት እጅግ ያዳግታል። 

የማይገባን ቢሆን እንኳ፥ የጥበብ አምላክ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የወደደውን እንዲያደርግ ነጻነት ሲሰጠው፥ በተሰጠው ነጻ ፍቃድ ምን እንደሚያደርግ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ፥ እርግጠኛ ያለመሆን ነገር በድንጋጌው ውስጥ የለም። በዚሁ መሠረት፥ መለኮታዊው ዕቅድ፥ አዳምና ሔዋን እንዳደረጉት ሰው ኃጢአትን እንዲያደርግ መፍቀድን ይጨምራል። ይህ ፍቃድ፥ በክርስቶስ በመስቀል ላይ መሞትና ሰዎችን ወደ ንስሐና እምነት በሚያመጣው የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች ሁሉ ውጤት የሆነው መለኮታዊ ፈውስንም ይጨምራል። 

እግዚአብሔር በሰዎች ልብ የሚያከናውነው ተግባር የማይመረመር ቢሆንም፥ ሰው በአንድ በኩል ድርጊቱ በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ድንጋጌ ውስጥ መታከሉ፥ በሌላ በኩል ደግሞ በነጻ ምርጫው የሚኖርና፥ ለዚህ ምርጫውም ተጠያቂነት ያለበት መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ያስረዳል። የእግዚአብሔር ድንጋጌ ባወጣው ያውጣው የሚል፥ ጭፍንና እንደ ግዑዝ መሣሪያ ነገራትን የሚቆጣጠር ሳይሆን፤ በማስተዋል በፍቅርና በጥበብ የተሞላ ነው። ስለሆነም ከሰው ምርጫ በመነሣት ክፉውን ይቀጣል መልካሙን ደግሞ ይሸልማል። 

የእግዚአብሔርን ድንጋጌ በንዑሳን ክፍሎች፥ ማለት የመፍጠር ድንጋጌ፥ ዓለምን የማጽናት ድንጋጌ፥ የጥበቃና ክብካቤ ድንጋጌ እና ዓለማትን የመምራት ብልህ አመራር ብሎ ለመመደብ ይቻላል። ድንጋጌው የእግዚአብሔርን ተስፋ ወይም ቃል ኪዳን፥ የዓላማውን መፈጸም እና ለሰዎች የተገለጠውን ልዑል ዓላማ ይጨምራል። እንዲህ ባለው ልዑል አምላክ ፊት ሰው ሊያደርግ የሚችለው፥ በመገዛት፥ በፍቅርና በአክብሮት መንበርከክ ነው።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

6
ትምህርት 6 ከ52

እግዚአብሔር አብ

ሀ. አብ የመጀመሪያው አካል 

አብ፥ ወልድ፥ መንፈስ ቅዱስን በሚገልጠው የሥላሴ ትምህርት፥ የመጀመሪያው አብ ይባላል። አብ፥ ወልድም ሆነ መንፈስ ቅዱስ በተናጠል ሥሉስ አይደሉም። ሥላሴ ሦስቱንም አካላት ይይዛል። ምንም እንኳ የአብ፥ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ አስተምህሮ በብሉይ ኪዳን ሲሰጥና ይህ ቃል ለሥላሴ መጠሪያነት ያገለገለ ቢሆን፥ አዲስ ኪዳን ነው ሙሉውን አስተምህሮ የሚገልጠውና የሚያብራራው። አብ እንደ መራጭ፥ አፍቃሪና ለጋስ ተገልጧል። ወልድ እንደ ሕማም ሰው ፥ ተቤዥ እና ዓለማትን እንደሚይዝ ተገልጿል። መንፈስ ቅዱስ ዳግም ልደት የሚሰጥ፥ በሰው የሚያድር፥ የሚያጠምቅ፥ ኃያል የሚሰጥ እና የሚቀድስ ሆኖ ነው የተገለጠው። የአዲስ ኪዳን መገለጥ ዋና ጉዳይ፥ ኢየሱስ ክርስቶስን መግለጥ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ እግዚአብሔር ልጅ ሲገለጥ፥ የእግዚአብሔር አብ እውነትም አብሮ ይገለጣል። አብ ልጁን የላከበትና የሾመበት፥ ወልድ ደግሞ መንፈስ ቅዱስን የላከበትና የሾመበት ቅደም ተከተል የማይዛባ ሲሆን፤ ይህ የሥነ-መለኮት ትምህርት ሊገለጥ የማይቻለውን የወልድንና የመንፈስ ቅዱስን መለኮትነት በምንም ሳያሳንስ አብን የመጀመሪያው አካል አድርጎ የሚሰይም ነው። 

የእግዚአብሔርን አባትነት በሚመለከተው መገለጥ ውስጥ አራት የተለያዩ ሁኔታዎች ይታያሉ። (1) እግዚአብሔር አብ እንደ ፍጥረት ሁሉ አባት፥ (2) እግዚአብሔር አብ በቅርብ ግንኙነት፥(3) እግዚአብሔር አብ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባት፥(4) እግዚአብሔር አብ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነትና ጌትነት ለሚያምኑ ሁሉ አባት ነው። 

ለ. ለፍጥረት ሁሉ አባትነት 

ምንም እንኳን በመፍጠር ተግባር፥ እንዲሁም ቁሳዊዎቹን ዓለማትና በውስጣቸው ያሉትን በመደገፉ ረገድ፥ ሦስቱም አካላት ቢሣተፉ፥ የመጀመሪያው አካል፥ እግዚአብሔር አብ፥ በልዩ ሁኔታ የፍጥረታት ሁሉ አባት ነው። ኤፌሶን 3፡14-15 ውስጥ ጳውሎስ “ስለዚህ ምክንያት በሰማይና በምድር ያለ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ” ብሏል። እዚህ ላይ የተገለጠው የሥነ-ምግባራዊ ምርጫ ማድረግ ከሚችሉ ፍጡራን (መላእክትና ሰው) መካከል እግዚአብሔር አባት የሆነበት ቤተሰብን የሚያመለክት ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ የመጀመሪያው አካል ዕብራውያን 12፡9 ውስጥ “የመናፍስት አባት” ተብሏል። ይህ እንደገና ሥነ-ምግባራዊ ፍጡራንን ሁሉ ማለት፥ ሰውንና መላእክትን ይጨምራል። 

ያዕቆብ 1፡17 ውስጥ በተገለጠው መሠረት የመጀመሪያው አካል፥“የብርሃናት አባት” ነው። ይህ ልዩ አገላለጥ፥ አካሉ የመንፈሳዊ ብርሃን ሁሉ ምንጭ መሆኑን የሚያመለክት ይመስላል። ኢዮብ 1፡6፤ 2፡1፤ 38፡7 ውስጥ መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች ተብለዋል። ሉቃስ 3፡38 ውስጥ አዳም በፍጥረቱ የእግዚአብሔር ልጅ ተብሏል። ነቢዩ ሚልክያስ በመጽሐፉ ምዕራፍ 2:10 ውስጥ “ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን?” በማለት ይጠይቃል። ሐዋርያው ጳውሎስም አርዮስ ፋጎስ በተባለው ስፍራ ለአቴናውያን ባደረገው ንግግሩ፥ “እንግዲህ የእግዚአብሔር ዘመዶች* ከሆንን” በማለት ጠቅሷል (ሐዋ. 17፡29)። (በዚህ ስፍራ የተጠቀሰው “ጌኖስ” የሚለው ቃል “ዘር” ወይም “ልጅ” የሚለው ትርጉም አለው። የ1980ውና የ2001 ዓ.ም. የአማርኛ ትርጉሞች ሁለቱም “ልጆች” ብለው ተርጉመውታል። ይህም “ዘመዶች” ከሚለው ትርጉም ይልቅ ትክክለኛ ነው)። 1ኛ ቆሮንቶስ 8፡6 ውስጥ “ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ፥ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን” ተብሎ ተጽፏል። 

በነዚህ ጽሑፎች መሠረት፥ የሥላሴ ቀዳሚ አካል እንደፈጣሪነቱ የፍጥረታት ሁሉ አባት መሆኑን እና አካል ያላቸው ፍጡራን ሁሉ መነሻ እርሱ መሆኑን ለማመን የሚያበቃ ማረጋገጫ አለ። በዚህ መንገድ ብቻ ነው የእግዚአብሔርን ሁለንተናዊ አባትነት ለማመልከት የሚቻለው። በዚህ ሁኔታ ፍጥረታት ሁሉ ሁለንተናዊና ተፈጥሯዊ ወንድማማችነትን (ዝምድና) ይጋራሉ። ይሁን እንጂ ይህ አባባል ለዘብተኛ ትምህርተ መለኮታውያን (liberal theologians)፥ ሁለንተናዊ ድነት ወይም እግዚአብሔር ለማንኛውም ሰው በመንፈስ አባት ይሆነዋል፥ የሚሉትን የተሳሳተ አስተምህሮ አይደግፈውም። 

ሐ. በቅርብ ግንኙነት የሚመሠረት አባትነት 

ብሉይ ኪዳን ውስጥ የአባትነትና የልጅነት ፅንሰ-አሳብ እግዚአብሔርን ከእስራኤል ጋር ለማዛመድ በብዙ አጋጣሚ ተጠቅሷል። ዘጸአት 4፡22 ውስጥ ሙሴ ፈርዖንን እንዲህ ብሎታል “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- እስራኤል የበኩር ልጄ ነው”። ይህ እግዚአብሔር ለእስራኤል ፈጣሪ ከመሆን በተጨማሪ ያለውን ግንኙነት ሲገልጥ፥ እስራኤላውያን ዳግመኛ ተወልደዋል ከማለት ደግሞ ጥቂት የሚያንስ ነው። ምክንያቱም፥ መንፈሳዊ ሕይወት የነበራቸው ሁሉም እስራኤላውያን አልነበሩም። ይህ ሁኔታ አባት ለልጁ እንደሚያደርገው፥ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያለውን መለኮታዊ ግንኙነት፥ ክብካቤና ርኅራኄ ያመለክታል። 

እግዚአብሔር ለዳዊት ቤት ያለውን ፍቅር ለራሱ ለዳዊት ሲገልጥለት፥ በርሱና በዳዊት ልጅ በሰሎሞን መካከል የሚኖረው ግንኙነት የአባትና የልጅን ያህል እንደሚሆን እንዲህ በማለት አስታውቆታል፡- “እኔም አባት እሆነዋለሁ፥ እርሱም ልጅ ይሆነኛል” (2ኛ ሳሙ. 7፡14)። በአጠቃላይ እንደ አምላካቸው ለሚተማመኑበት ሁሉ እንደ አባት እንደሚጠነቀቅላቸው እግዚአብሔር ገልጧል። ይህ አባባል መዝሙረ ዳዊት 103፡13 ውስጥ “አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል” ተብሏል። 

መ. የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት 

የእግዚአብሔርን አባትነት በተመለከተ እጅግ ጠቃሚውና ሰፊው መገለጥ፥ የመጀመሪያው አካል ከሁለተኛው አካል (አብ ከወልድ) ጋር ያለውን ግንኙነት ያጠቃልላል። የመጀመሪያው አካል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት፥ ተብሏል (ኤፌሶን 1፡3)። የአዲስ ኪዳን ትምህርተ-መለኮታዊ አጠቃላይ መገለጥ እግዚአብሔር አብ ወይም የመጀመሪያው አካል፥ የሁለተኛው አካል የኢየሱስ ክርስቶስ አባት መሆኑን የሚያመለክተው ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን በተደጋጋሚ እንደ እግዚአብሔር ልጅ መገለጡ፥ እንዲሁም የእግዚአብሔር ባሕርያትና ሥራዎች በተከታታይ ለርሱ መሰጠታቸው የኢየሱስ ክርስቶስን መለኮትነት ያረጋግጣሉ። የሥላሴ ትምህርት ባጠቃላይ፥ ክርስቶስን እንደ ሁለተኛ አካልና ከአብ ጋር ደግሞ እንደ ልጁ ባለ ግንኙነት ይገልጠዋል። 

የሥነ-መለኮት ምሁራን አብ እንዴት የሁለተኛው አካል፥ ማለት የወልድ አባት ሊሆን ይችላል? ለሚለው ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ ለማግኘት፥ ከአንደኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ የበረታ ጥረት እድርገዋል። “አብ” እና “ወልድ” የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት፥ በአብና በወልድ መካከል ያለውን ልዩ የሆነ ግንኙነትን ሲሆን፥ ይህ፥ ግንኙነቱ በሰብአዊ አባትነትና ልጅነት መካከል እንዳለው የግንኙነት ዓይነት ነው ማለት እይደለም። ይህ ሁኔታ በተለይ የሚረጋገጥበት አሳብ አብና ወልድ ሁለቱም ዘላለማዊ መሆናቸውን በሚያሳየው እውነት ነው። በአራተኛው መቶ ክፍለ-ዘመን የተነሣው መናፍቅ፥ የአርዮስ የመጀመሪያ ስሕተት፥ ወልድ የፍጥረት ሁሉ በኩር ነው የሚለው ነበር። ጥንታዊቱ ቤተ ክርስቲያን ወልድ እንደ አብ ዘላለማዊ ነው ከሚለው መሠረተ አሳብ በመነሣት ይህን አስተምህሮ በኑፋቄነት አወገዘችው። 

አንዳንድ የሥነ-መለኮት ምሁራን የወልድን ዘላለማዊነት ተቀብለው፥ ነገር ግን ሁለተኛው አካል እንደ ወልድ ተግባሩን የጀመረበትን ሁኔታ በጊዜ ውስጥ አንድ ነጥብ ላይ ማለት፥ በፍጥረት መጀመሪያ፥ ሥጋ በለበሰበት ወቅት ወይም የኋላ ኋላ ሁለተኛው አካል ልዩ ግንዛቤ ባገኘ ጊዜ፥ ማለትም በተጠመቀበት ወቅት በትንሣኤው ወይም በዕርገቱ ጊዜ ነው ለማለት ሞክረዋል። ይሁን እንጂ እነዚህ አማራጭ አመለካከቶች ሁሉ ስሕተት ናቸው። ምክንያቱም ወልድ ከዘመናት በፊት ጀምሮ ከአብ ጋር አንድነት ያለው መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ያመለክታል። በዚህ መሠረት ወልድ፥ “አንድያ ልጅ (ዮሐ. 3፡16) ሲሆን፥ ሥጋ በለበሰ ጊዜ እግዚአብሔር ለዓለም የሰጠው” ልጁ ነው። ወልድ ለዓለም የተሰጠው እንደ እግዚአብሔር ልጅነቱ እንጂ፥ ከመሰጠቱ በኋላ ልጅ ይሆን ዘንድ አይደለም። ኢሳይያስ 9፡6 ውስጥ “ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል” ተብሏል። ይህ አሳብ ቆላስያዕ 1፡15-16 ውስጥ ይበልጥ ግልጥ ተደርጓል። በዚህ ስፍራ ክርስቶስ፥ «የማይታይ አምላክ ምሳሌ፥ … ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር” እንደሆነ ተነግሯል። ክርስቶስ የፍጥረታት ሁሉ በኩር ከሆነ፥ ማለት ከማንኛውም ፍጥረት ሁሉ በፊት የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ፥ የርሱ ልጅነት ከዘላለም በፊት መሆኑ ግልጥ ነው። 

ስለዚህ የአብና የወልድ አንድነት ከዘላለማዊነት አንጻር ከቅድስት ሥላሴ ዘላለማዊ መለኮትነት ጋር የሚያያዝ ገጽታ ሲኖረው፤ በሌላ በኩል ወልድ ሥጋን ከለበሰበት ዘመን እንጻር ደግሞ የሚታይ ለየት ያለ የጊዜ ገጽታ አለው። የኒቅያው ጉባኤ (325 ዓ.ም.) በአራተኛው ክፍለ-ዘመን ለተነሣው የአርዮስ ኑፋቄያዊ አስተምህሮ በሰጠው የመልስ ድንጋጌ፥ ለወልድ፥ የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ፥ ከዓለማት መፈጠር በፊት የአብ የሆነ፥ ከእግዚአብሔር የወጣ እግዚአብሔር፥ ከብርሃን የሆነ ብርሃን፥ ከእውነተኛው አምላክ የወጣ እውነተኛ አምላክ፥ የተወለደ፥ ያልተፈጠረ፥ ከአብ ጋር አንድ የሆነ” ብሏል። በተመሳሳይ ሁኔታ አትናቴዎስ በተባለው ጳጳስ አማካይነት የተቀናበረው ድንጋጌ እንዲህ ይላል፡- “ወልድ ከአብ ብቻ የሆነ፥ የተወለደ እንጂ ያልተሠራ ወይም ያልተፈጠረ፥ ከዘላለም በፊት ከአብ የወጣ። 

“አብ” እና “ወልድ” የሚሉት ቃላት ቀዳማዩንና ደህራዩን አካል ለመግለጥ በሚያገለግሉበት ጊዜ የሕይወትን፥ የባሕርይንና የልዩ መለያን አድነት ሊያስገነዝቡ በሚቻላቸው ከፍተኛ ሁኔታ ይገልጣሉ። ምንም እንኳን የጠበቀ የአባትና ልጅነት አንድነት ቢኖር፥ አብ ልጁን የመስጠቱና የመላኩ ሁኔታ፥ የወልድን እስከ መስቀል ሞት ድረስ መታዘዝን የሚጠይቅ ነበር። በዚህም የክርስቶስ በልጅነቱ መታዘዙ በሥላሴ የሥነ-መለኮት ትምህርት እኩልነታቸውን እና አንድነታቸውን የሚያሳይን ሐቅ በማፋለስ፥ የወልድን ከአብ ማነስ የሚያመለክት አይደለም። 

በቀዳማዩና ደሀራዩ የሥላሴ አካላት መካከል ያለው አንድነት፥ በአባትና በልጅ፥ እንዲሁም በልጅና በአባት መካከል እንዳለው ነው (2ኛ ቆሮ.1፡3፤ ገላ.4፡4፤ ዕብ. 1፡2)። ይህ አንድነት ፍጹም ከሆነው አእምሮ ዕቅድ ወይም አሳብ ጋር ራሱን የሚያስማማና እጅግ አስፈላጊ የሆነው እውነት መግለጫ ነው። አብ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት የመሆኑ እውነት፥ ብሉይ ኪዳን ውስጥ አልፎ አልፎ ቢጠቀስም፥ (መዝ. 2፡7፤ ኢሳ. 7፡14፤ 9፡6-7)፥ አንዱ የአዲስ ኪዳን ዋናና አጠቃላይ አስተምህሮ ነው። 

1. የእግዚአብሔር ልጅ የአብ አንድያ ልጅ ተብሏል (መዝ. 2፡7፤ ዮሐ. 1፡14፥ 18፤ 3፡16፥18፤ 1ኛ ዮሐ. 4፡9)። 

2. አብ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልጄ ነው ብሎታል (ማቴ. 3፡17፤ 17፡5፤ ሉቃስ 9፡35)። 

3. ወልድ አብን አባቴ ብሎታል (ማቴ. 11፡27፤ 26፡63-64፤ ሉቃስ 22፡29፤ ዮሐ. 8፡16-29፥33-44፤ 17፡1)። 

4. አብ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ አባት መሆንን ሰዎች አምነዋል(ማቴ. 16፡16፤ ማር. 15:39፤ ዮሐ. 1፡34፥ 49፤ ሐዋ. 3፡13)። 

5. ወልድ በመታዘዝ የአብን አባትነት አረጋግጧል (ዮሐ. 8፡29፥ 49)* 

6. ይህን በአብና ወልድ መካከል ያለ አንድነት አጋንንት እንኳን ያረጋግጣሉ (ማቴ. 8፡29)። 

ሠ. በክርስቶስ የሚያምኑ ሁሉ አባት 

እግዚአብሔር አብ እንደ ፈጣሪነቱ ለፍጡራን ሁሉ አባት ከመሆኑ ግንዛቤ በተነጻጻሪ፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ላመኑትና የዘላለም ሕይወት ላገኙት ልዩ በሆነ መልኩ አባት ነው። እግዚአብሔር የፍጥረታት አባት መሆኑ፥ ለሰዎች ሁሉ የድነት ወይም የዘላለም ሕይወት ዋስትና አይደለም። ድነት ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኛቸው በእምነት ለተቀበሉት ብቻ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ያስገነዝባል። እግዚአብሔር የሰው ዘር ሁሉ አባት ነው፥ በሰዎች መካከልም ዓለም አቀፋዊ ወንድማማችነት አለ፥ የሚለው አሳብ ሁሉም ድነው ወደ መንግሥተ ሰማያት ይገባሉ ማለት አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረን፥ ለድነት በኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑት ብቻ በመንፈሳዊ ትርጉሙ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናቸውን ነው። ይህ የሚሆነው፥ ሰው ሆነው በመፈጠራቸውና የፈጠራቸው እግዚአብሔር በመሆኑ ሳይሆን፥ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ቤተሰብነት ከመንፈስ ዳግም በመወለዳቸው ነው ( ዮሐ. 1፡12፤ ገላ. 3፡26፤ ኤፌ. 2፡19፤ 3፡15፤ 5፡1)። 

መንፈስ ቅዱስ በሚያከናውነው ዳግም ልደት አማካይነት አማኝ የእግዚአብሔር የጸጋ ልጅ ይሆናል። አማኝ እግዚአብሔር አባቱ ስለሆነለት “አባ አባት ብሎ እንዲጠራው በመንፈስ ቅዱስ ይገፋፋል። ከእግዚአብሔር የተወለደ ነውና፥ የመለኮታዊው ባሕርይ ተካፋይ ነው። ከዚህ የልጅነት ሥልጣን የተነሣ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የእግዚአብሔር መንግሥት ወራሽ ነው (ዮሐ. 1፡12-13፤ 3፡3-6፤ ሮሜ 8፡16-17፣ ቲቶ 3፡4-7፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡4)። አማኝ በእምነት የሚጋራው መለኮታዊ ባሕርይ፥ በምንም ምክንያት ከርሱ በማይወሰድበት ሁኔታ ጸንቷል። 

የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ አሁን ካለው የሰይጣን ኃይልና ሥልጣን አኳያ ሲታይ፤ ሰዎች ሁሉ በሥጋዊ ትውልዳቸው የእግዚአብሔር ልጆች አለመሆናቸውን የሚያሳይ ተጨማሪ ማስገንዘቢያ ተሰጥቷል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ሁኔታ የኢየሱስ ክርስቶስ ቀጥተኛና ታማኝ አባባሎች ማረጋገጫዎች ናቸው። ስለማያምኑ ሰዎች ሲናገር፡- “እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ” (ዮሐ. 8፡4) ብሏል። በተመሳሳይ ሁኔታ፥ ዳግም ስላልተወለዱት ሲናገር፥ “እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው”(ማቴ. 13: 38) በማለት ገልጧል። ሐዋርያው ጳውሎስ ድነት ስላሳገኙ ሰዎች ሲጽፍ፥ “የአለመታዘዝ ልጆች” እና “የቁጣ ልጆች” (ኤፌ. 2፡2-3) ብሏቸዋል። 

ሊተኮርበት የሚገባ እውነት፥ ማንም ቢሆን ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ ሊያደርግ አለመቻሉ ነው። እግዚአብሔር ራሱ ነው ይህን ለውጥ ሊያከናውን የሚችል። ይህን የሚያደርገውም እርሱ ራሱ ባስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ፥ ማለት ክርስቶስ ሊታመንበትና እንደ አዳኝ ሊቀበሉት የሚገባ በሆነው አሠራር አማካይነት ነው (ዮሐ. 1፡12)። 

የእግዚአብሔር አባትነት፥ የአዲስ ኪዳን ዋና አስተምህሮ ነው (ዮሐ. 20፡17፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡24፤ ኤፌ. 1፡3፤ 2፡18፤ 4፡6፤ ቆላ. 1፡12-13፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡3፤ 1ኛ ዮሐ. 1፡3፤ 2፡1፥ 22፤ 3፡1)። የሰማያዊው አባታችን ፍቅርና ጥበቃ ዋስትና ያለን መሆኑ፥ ለክርስቲያኖች ታላቅ መጽናናት፥ እንዲሁም ለእምነትና ለጸሎት የሚያበረታታን ነው።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

7
ትምህርት 7 ከ52

እግዚአብሔር ወልድ፡- መለኮታዊነቱና ዘላለማዊነቱ

መጽሐፍ ቅዱስ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ፍጹም ሰውና ፍጹም መለኮት አድርጎ ያቀርበዋል። በዚህ መሠረት እንደ ማንኛውም ሰው ነው፥ አይደለም። በዮሐንስ 1፡14፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡ 16 እና ዕብራውያን 2፡14-17 መሠረት፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰው የተወለደ፥ በሰዎች መካከል የኖረ፥ የተሠቃየ እና የሞተ መሆኑ ተገልጧል። ኢየሱስ ክርስቶስ ከዘላለም በፊት የነበረ በመሆኑ፥ እንደ ሰው አለመሆኑን፥ በሰብአዊነቱ ኃጢአትን የማያውቅ መሆኑን፥ ሞቱ ለዓለም ሁሉ ኃጢአት መሥዋዕት መሆኑን፥ ከሙታን ተለይቶ በመነሣትና ወደ ሰማይ በማረግ መለኮታዊ ኃይሉን የገለጠ መሆኑን በማስገንዘብ ረገድም መጽሐፍ ቅዱስ ግልጥ ነው። 

በሰብአዊነቱ ጅማሬ ነበረው፤ ከመንፈስ ቅዱስ ተፀንሶ ከድንግል ማርያም ተወልዷል። በመለኮታዊነቱ ግን ከዘላለም በፊት የነበረ በመሆኑ ጅማሬ የለውም። ኢሳይያስ 9፡6 ውስጥ “ሕፃን ተወልዶልናል፤ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል” የሚል ትንቢት ተነግሮ ነበር። በተወለደ ሕፃንና በተሰጠ ልጅ መካከል ያለው ልዩነት ግልጥ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ ገላትያ 4፡4 ውስጥ እንዲህ ተብሏል፡- “… የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን፥ ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ”። ዘላለማዊው የእግዚአብሔር ልጅ ሥጋ በመልበስ “ ከሴት ተወሰደ። 

ክርስቶስ ከመወለዱ በፊት ነባሪ ነው፥ የሚለው ገለጣ ከመወለዱ በፊት መኖሩን በቀላሉ ያረጋግጣል። የፍጥረታት ሁሉ በኩር ሆኖ ብቻ ይኖር ነበር፥ የሚለው አስተሳሰብ (በአራተኛው ክፍለ ዘመን የነበረ አርዮሳዊ ኑፋቄን፥ የጊዜያችን ትምህርት አይደለም። ስለዚህ የቀዳሚ ነባሪነቱና የዘላለማዊነቱ ማረጋገጫዎች ጣምራ ናቸው። ክርስቶስ እግዚአብሔር ከሆን ዘላለማዊ መሆኑ፥ ዘላለማዊ ከሆነ እግዚአብሔርነቱ እርግጥ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮትነትና ዘላለማዊነት የሚደጋገፉ ናቸው። 

የኢየሱስ ዘላለማዊነትና መለኮትነት በሁለት መንገድ ተገልጧል፡- (1) ቀጥተኛ ገለጣ (2) በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጠ። 

ሀ. የእግዚአብሔርን ልጅ ዘላለማዊነትና መለኮትነት ቀጥተኛ ገለጣ 

የኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊነትና መለኮትነት እጅግ ሰፊ በሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በተመዘገበው ቃል ተረጋግጧል። ይህም ከሴሳው የሥላሴ አካል ከአብ ጋር አቻነቱን፥ ፍጹምነቱንና ዘላለማዊነቱን ያረጋግጣል። ይህ እውነት ክርስቶስ ሥጋ በመልበሱ ሳቢያ አልተዛባም። 

መጽሐፍ ቅዱስ ዮሐንስ 1፡ 1-2 ውስጥ የመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። “ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነው አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም” ይላል። በትንቢተ ሚክያስ 5፡2 ሲገለጥ ደግሞ 

“አንቺ ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ! አንቺ ከይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤል ላይ ገዢ የሚሆን ይወጣልኛል” ተብሏል። ኢሳይያስ 7፡ 14 ውስጥ ደግሞ፥ ከድንግል መወለዱን አረጋግጦ እማኑኤል የሚል ስም ይሰጠዋል፤ ትርጉሙም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” ማለት ነው። በኢሳይያስ 9፡6-7 መሠረት፥ ኢየሱስ እንደ ሕፃን ቢወለድም፥ እንደ ወንድ ልጅም የተሰጠ ነው። ይህ ብቻም አይደለም፥ “ኃያል አምላክ” ተብሏል። ክርስቶስ ራሱ ዮሐንስ 8፡58 ውስጥ ሲገልጥ፥ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ” ብሏል። 

ይህ አገላለጥ፥ መለኮታዊነትንና ዘላለማዊነትን እንደሚያመለክት አይሁድ ተገንዝበዋል (ዘጸ. 3፡ 14፤ ኢሳ. 43፡13)። ዮሐንስ 17፡5 ውስጥ እንደተጠቀሰው ደግሞ፥ ክርስቶስ በጸሎቱ፥ “አሁንም አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አክብረኝ” ብሏል (ይህን ቃል ከዮሐ. 13፡3 ጋር ያነጻጽሩት)። ፊልጵስዩስ 2፡6-7 ውስጥ ክርስቶስ ሥጋ ከመልበሱ በፊት “በእግዚአብሔር መልክ” እንደነበር ተገልጧል። 

ከሁሉም ግልጥ የሆነው ማስገንዘቢያ የሚገኘው፥ ቆላስይስ 1፡15-19 ውስጥ ነው። በዚያ ስፍራ ክርስቶስ ከፍጥረት በፊት እንደነበር፥ ራሱ ፈጣሪ እንደሆነ እናየማይታየው አምላክ ምሳሌ እንደሆነ ተገልጧል። 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡ 16 ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ “በሥጋ የተገለጠ አምላክ” ተብሏል። ዕብራውያን 1፡2-3 ውስጥም ወልድ ፈጣሪ እና የተገለጠ የእግዚአብሔር አምሳል መሆኑ እንደገና ተገልጧል። ዘላለማዊነቱም ዕብራውያን 13፡ 8 ውስጥ ተረጋግጧል (ይህን ማረጋገጫ ከኤፌሶን 1፡4፤ ራእይ 1፡8 ጋር ያነጻጽሩት)። ክርስቶስ ዘላለማዊ እና አምላክ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ አበክሮ ይገልጣል። ጥቂት ከሃዲ የአምልኮ ክፍሎች ሲቀሩ፥ መጽሐፍ ቅዱስ እጅግ ሥልጣን ያለው መሆኑን የሚቀበሉ የጊዜያችን ምሁራን ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊና መለኮታዊ መሆኑን ያረጋግጣሉ። 

ለ. የእግዚአብሔርን ልጅ ዘላለማዊነት የሚያመለክቱ ሁኔታዎች 

የእግዚአብሔር ቃል፥ የኢየሱስ ክርስቶስን ከዘላለም በፊት ኗሪነትና ዘላለማዊነት በተከታታይና ባለማቋረጥ ያመለክታል። የዚህ እውነት ግልጥ ማረጋገጫ ከሆኑት አንዳንዶቹን ለመጥቀስ ይቻላል። 

1. ተፈጥሮ በክርስቶስ እንደተከናወነ ተገልጧል(ዮሐ. 1፡ 3፤ ቆላ. 1፡16፤ ዕብ. 1፡ 10)። ስለዚህ ከፍጥረታት ሁሉ ይቀድማል። 

2. የእግዚአብሔር መልአክ መታየቱ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ተመዝግቧል፤ የያዌ መልእክ ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ሌላ ሊሆን አይቻልም። አንዳንድ ጊዜ እንደ መልአክ ከዚያም አልፎ እንደ ሰው ቢታይም፥ የማያሳስት የመለኮትነት መገለጫ አለው። ለአጋር ተገልጧል፥ (ዘፍጥ. 16፡7)፥ ለአብርሃም (ዘፍጥ. 18፡ 1፤ 22 ፡ 11-12፤ በተጨማሪ ዮሐ. 8፡58ን ልብ ይብሉ)፥ ለያዕቆብ (ዘፍጥ. 48፡ 15-16፥ እንዲሁም ዘፍጥ. 31፡11-13፤ 32፡24-32)፥ ለሙሴ፥ (ዘጸ. 3፡2፥14)፥ ለኢያሱ፥ (ኢያ. 5፡13-14)፥ እና ለማኑሄ፥ (መሳ. 13፡ 19-22)። የራሱ ለሆኑ የሚዋጋና የሚጠብቃቸው እርሱ ነው (2ኛ ነገሥት 19፡35፤ 1ኛ ዜና 21፡ 15-16፤ መዝ. 34፡7፤ ዘካ. 14፡ 1-4)። 

3. የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መጠሪያዎችና ማዕረጎች ዘላለማዊነቱን ያመለክታሉ። እርሱ በትክክል እንደ ስሙ ነው። “የእግዚአብሔር ልጅ”፥ “አንድያ ልጅ”፥ “የመጀመሪያውና የመጨረሻው ፥ “አልፋና ኦሜጋ”፥ “ጌታ”፡ (“የሁሉ ጌታ”፥ “የክብር ጌታ”፥ “ክርስቶስ”፥ “ድንቅ”፥ “መካር”፥ “ኃያል አምላክ”፥ “የዘላለም | አባት”፥ “እግዚአብሔር ከኛ ጋር”፥ “ታላቅ አምላካችን” እና “ለዘላለም የተባረከ አምላክ። 

እነዚህ መጠሪያዎች ኢየሱስን በብሉይ ኪዳን ከተገለጠው ያህዌ- አምላክ ጋር ያዛምዱታል (ማቴ. 1፡23፥ ይህን ካኢሳ. 7፡ 14 ጋር ያነጻጽሩት፥ ማቴ. 4፡7ትን ደግሞ ከዘዳ. 6፡ 16 ጋር፥ ማር. 5፡ 19ን ከመዝ. 66፡ 16 ጋር እና ማቴ. 22፡42-45ትን ከመዝ. 110፡1 ጋር ያነጻጽሩ)። 

አዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሱት የእግዚአብሔር ልጅ ስሞች ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ መጠሪያዎች ጋር ተዛምደዋል። ይህም ከአካላቱ ጋር ያለውን አቻነት ያመለክታል (ማቴ. 28፡19፤ ዮሐ. 14፡1፤ 17፡3፤ ሐዋ. 2፡ 38፤ 1ኛ ቆሮ. 1፡3፤ 2ኛ ቆሮ 13፡ 14፤ ኤፌ. 6፡23፤ ራዕ. 20፡6፤ 22፡3)። በማያሻማ ሁኔታም እግዚአብሔር ተብሏል (ዮሐ. 1፡ 1፤ ሮሜ. 9፡5፤ ቲቶ 2፡ 13፤ ዕብ. 1፡8)። 

4. የእግዚአብሔር ልጅ ከዘላለም በፊት ኗሪነቱና ዘላለማዊነቱ፥ የእግዚአብሔር ባሕርያት ያሉት መሆኑን በሚያስገነዝቡት እውነቶች ውስጥ ተመልክቷል። ሕይወት (ዮሐ. 1፡4)። ኗሪ (ዮሐ. 5፡26)፥ የማይለወጥ ወይም የማይሻር (ዕብ. 13፡8)፥ እውነት (ዮሐ. 14፡6)፥ ፍቅር (1ኛ ዮሐ. 3፡ 16)፥ ቅድስና (ዕብ. 7፡26)፥ ዘላለማዊነት (ቆላ. 1፡17፤ ዕብ. 1፡ 1 1 )፥ በሁሉም ስፍራ መገኘት (ማቴ. 28፡20)፥ ሁሉን አዋቂነት (1ኛ ቆሮ. 4 ፡ 5፤ ቆላ. 2፡3) እና ሁሉን ቻይነት(ማቴ. 28፡ 18፤ ራእይ 1፡8)። 

5. በተመሳሳይ ሁኔታ ከዘላለም በፊት ኗሪነቱና ዘላለማዊነቱ፥ እንደ እግዚአብሔር በመመሰኩ እውነት ውስጥ ተገልጧል (ዮሐ. 20፡28፤ ሐዋ. 7:59-60፤ ዕብ. 1፡6)። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር እንደመሆኑ፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ኗሪ ነው። 

የእግዚአብሔር ልጅ መለኮትነትና ዘላለማዊነት ጉዳይ፥ ከክርስቶስ ከሰብአዊ ልደት ወይም ሥጋ መልበስ ጋር በቅርብ መያያዝ አለበት። ይህ ነው የሚቀጥለው ምዕራፍ መነጋገሪያችን።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

8
ትምህርት 8 ከ52

እግዚአብሔር ወልድ፡- ተሠግዎቱ

የክርስቶስን ሥጋ መልበስ በምናጤንበት ጊዜ ሁለት ዐበይት እውነቶችን ልብ ልንል ይገባል፡- 1) ክርስቶስ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው ሆኗል፥ 2) ሥጋ ሲለብስ፥ ምንም እንኳን ክብሩን ቢተው፥ በምንም ሁኔታ መለኮትነቱን አልጣስም። ሥጋ በለበሰ ጊዜ መሠረታዊ የመስኮትነት ባሕርያቱን እንደያዞ ነው። ሙሉ መለኮትነቱና ፍጹም ሰብአዊነቱ ለመስቀል ላይ ሥራው አስፈላጊ ነበሩ። ሰው ባይሆን ኑሮ እይሞትም፥ እግዚአብሔር ባይሆን ኑሮ ደግሞ፥ ሞቱ ዘላለማዊ ዋጋ አይኖረውም ነበር። 

ሐዋርያው ዮሐንስ (ዮሐ. 1፡1) ከእግዚአብሔር ጋር አንድ የሆነውና ለዘላለም እግዚአብሔር የሆነው ክርስቶስ ሥጋ ሆኖ በእኛ ዘንድ እንዳደረ ይገልጣል (ዮሐ. 1፡14)። ጳውሎስም በእግዚአብሔር መልክ የነበረው ክርስቶስ፥ የሰውን ምሳሌ መያዙን ያስገነዝባል (ፊልጵ. 2፡6-7)። “አምላክ በሥጋ ተገለጠ’” (1ኛ ጢሞ. 3፡16)፤ የእግዚአብሔር ሙሉ ክብር መገለጥ ነጻብራቅ የሆነው ክርስቶስ፥ የባሕርዩ ምሳሌ ነው (ዕብ. 1፡3)። ሉቃስም የክርስቶስን መፀነስና መወለድ ታሪካዊ እውነት ሰፋ ባለ ዝርዝር አቅርቧል (ሉቃስ 1፡26-38፤ 2፡5-7)። 

መጽሐፍ ቅዱስ አያሌ ማነጻጸሪያዎችን አቅርቧል። ክርስቶስ ፍጹም አምላክ እና ፍጹም ሰው ሆኖ መገለጡ ግን ከሁሉ ይልቃል። ይህን የመሰሉ የማነጻጻሪያ ጎለጣዎች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ናቸው። ደክሞት ነበር (ዮሐ. 4:6)፥ ነገር ግን ደካሞችን ሊያሳርፋቸው ወደ ራሱ ጠራቸው (ማቴ. 11፡28)። ተርቦ ነበር (ማቴ. 4፡2)፥ ነገር ግን ራሱ “የሕይወት እንጀራ ነው” (ዮሐ. 6፡35)። ተጠምቷል (ዮሐ. 19፡28)፥ ነገር ግን ራሱ የሕይወት ውኃ ነው” (ዮሐ. 7፡37)። ተሠቃየ (ሉቃስ 22፡44)፥ ነገር ግን ሰዎችን ከማንኛውም በሽታ ፈወሰ፥ ማንኛውንም ሕመም አስወገደ። “አደገ፥ በመንፈስም ጠነከረ” (ሉቃስ 2፡40)፥ ነገር ግን ከዘላለም በፊት ነበር (ዮሐ. 8፡58)። ተፈትኗል (ማቴ. 4፡1)፥ ሆኖም አምላክ በመሆኑ፥ ኃጢአትን አላደረገም። በእውቀት የተወሰነ ነበር (ሉቃስ 2፡52)፥ ነገር ግን ራሱ የእግዚአብሔር ጥበብ ነበር። ለጥቂት ጊዜ ሥጋን በመልበሱ ራሱን ዝቅ በማድረጉና በማዋረዱ ከመላእክት ትንሽ ማነሱን ይናገራል (ዕብ. 2፡6-7 )፤ “አባቴ ከእኔ ይበልጣል” (ዮሐ. 14፡28) ይልና “እኔን ያየ አብን አይቷል” (ዮሐ. 14 :9) እና “እኔና አባቴ አንድ ነን” (ዮሐ. 10፡30)፥ በማለት ንጽጽሩን ራሱ ያቀርበዋል። ጸልይዋል (ሉቃስ 6፡12)፥ ነገር ግን ራሱ ለጸሎት መልስ ይሰጣል (ሐዋ. 10፡31)። በመቃብር አጠገብ አለቀሰ ( ዮሐ. 11፡35)፥ ነገር ግን ራሱ ሙታንን ከመቃብር እንዲነሡ ይጣራል (ዮሐ. 11፡43)። “የሰውን ልጅ ሰዎች ማን ይሉታል?” በማለት ጠየቀ (ማቴ. 16፡13)፥ ነገር ግን ““ስለ ሰው ማንም እንዲመሰክርለት አልፈለገም፤ በሰው ውስጥ ያለውን ያውቅ ነበርና” (ዮሐ. 2፡25)። “አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ?” አለ (ማር. 15፡34)፥ ነገር ግን እርሱ የጮኸለት አምላክ በዚያን ሰዓት “ዓለሙን ሁሉ ከራሱ ጋር የሚያስታርቅ ነበር” (2ኛ ቆሮ. 5፡19)። ሞተ፤ ዳሩ ግን የዘላለም ሕይወት ነው። እርሱ ለእግዚአብሔር ምቹ የሆነ ሰው፥ ለሰው ምቹ የሆነ አምላክ ነው። 

ከዚህ ሁሉ ለመረዳት የሚቻለው፥ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አንዳንድ ጊዜ ፍጹም ሰው ሆኖ የሚሠራ ሲሆን፥ በሌላ ጊዜ ደግሞ ፍጹም አምላክ በሆነ ሁኔታ ሲሠራ መታየቱን ነው። መለኮታዊ ሕላዌው ሰው በመሆኑ ምክንያት ከቶ ውሱን አልሆነም። መለኮታዊነቱን በምንም ዓይነት ለሰብአዊ ፍላጐቱ መገልገያነት አልተጠቀመበትም። ሰብአዊ ርሃቡን ለማርካት ድንጋዩን ወደ ዳቦነት ሊለውጠው ይችል ነበር፤ እርሱ ግን አሳደረገውም። 

ሀ. ክርስቶስ ሰው የመሆኑ እውነት 

1. ክርስቶስ ሰው የመሆን እውነት የታቀደውና የታለመው ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ነበር (ኤፌ. 1፡4-7፤ 3፡11፤ ራእይ 13፡8)። የእግዚአብሔር በግ የመባሉ ምሥጢር፥ ደም ለማፍሰስና መሥዋዕት ለመሆን አካለ ሥጋን በቅድመ ሁኔታነት የሚፈልግ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው። 

2. በብሉይ ኪዳን ስለ ክርስቶስ ሥጋ መልበስ የተነገረው ምሳሌና ትንቢት፥ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አስቀድሞ ለማሳወቅ ነበር። 

3. የክርስቶስ ሰው የመሆን እውነት የተረጋገጠው፥ እንደማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ተፀንሶ በመወለዱ ነው (ሉቃስ 1፡31-35)። 

4. ምድራዊሕይወቱሰው መሆኑን አሳይቶአል። ይኽውም፡- 

(ሀ.) በሰብአዊ ስሞቹ፥ “የሰው ልጅ”፥ “ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ”፥ “የዳዊት ልጅ” የሚሉትና የመሳሰሉት፥ በሰብአዊ ትውልዱ፤ 

(ሰ.) በሰብአዊ ውልደቱ፥“የወገብ ፍሬ”፥ “የበኩር ልጅዋ”፥ “የዚህ ሰው ዘር”፥ “የዳዊት ዘር”፥ “የአብርሃም ዘር”፥ “ከሴት የተወለደ”፥ “ከይሁዳ የወጣ መባሉ፤ 

(ሐ.) ሰብአዊ አካል፥ ነፍስና መንፈስ ያለው ስለመሆኑ (ማቴ. 26፡38, ዮሐ. 13፡21፤ 1ኛ ዮሐ.4፡2፡9) እና 

(መ.) ራሱ ወዶ በወሰደው ሰብአዊ ውሱንነት። 

5. የክርስቶስ ሰው መሆን በሞቱና በትንሣኤው ታይቷል። በመስቀል ላይ የሞተውም ሥጋ በሆነ አካሉ ሲሆን፥ መቃብርን አሸንፎ በትንሣኤው ክብር የተነሣውም በአካሉ ነበር። 

6. የክርስቶስ ሰው የመሆን እውነት ወደ ሰማይ በማረጉ ታይቷል። አሁን ደግሞ በከበረ ሰውነቱ የራሱ የሆኑትን በማገልገል ላይ ነው። 

7. ዳግም በሚመለስበት ጊዜም ያው “አንዱ ኢየሱስ” ወደ ሰማይ ባረዝት ነገር ግን በከበረ አካሉ)፥ በተሠግዎ ይመለሳል። 

ለ. የተሠግዎው ምክንያቶች 

1. የመጣው እግዚአብሔርን ለሰው ለማሳየት ነው(ማቴ. 11፡27፤ ዮሐ. 1፡18፤ 14:9፤ ሮሜ 5፡8፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡16)። ሥጋ በመልበሱ ሰው ከአእምሮው በላይ የሆነውን እግዚአብሔርን እንዲረዳ አደረገ። 

2. ሰውን ለመግለጥ መጣ። ኢየሱስ እግዚአብሔር የሚፈልገው ሰው ምሳሌ በመሆኑ፥ ለሚያምኑ ሁሉ አርአያ ነው (1ኛ ጴጥ. 2፡21)። ለማያምኑ ግን ከቶ ምሳሌ አይደለም። ምክንያቱም እግዚአብሔር በአሁኑ ዘመን የሚፈልገው ያልዳኑትን ለማሻሻል ሳይሆን፥ ስማዳን ነው። 

3. ለኃጢአት መሥዋዕት ሊሆን መጣ፤ በመሆኑም ስለ ሰብአዊ አካሉ እና ይህ አካሉም ለኃጢአት ይቅርታ የተዘጋጀ በመሆኑ፥ እግዚአብሔርን ሲያመሰግን ታይቷል (ዕብ. 10፡1-10)። 

4. የዲያብሎስን ሥራ ያፈርስ ዘንድ ሥጋ ለብሶ መጣ (ዮሐ. 12፡31፤ 16፡11፤ ቆላ. 2፡13-15፤ ዕብ. 2፡14፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡8)። 

5. ወደ ዓለም የመጣው፥ ይቅር ባይና ለእግዚአብሔር ታማኝ ሊቀ ካህን ይሆን ዘንድ ነው(ዕብ. 2፡16-17፤ 8፡1፣ 9፡11-12፥24)። 

6. ሥጋ ለብሶ የመጣው፥ እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ ነው (2ኛ ሳሙ. 7፡16፤ ሉቃስ 1፡31-33፤ ሐዋ. 2፡30-31፥36፤ ሮሜ 15፡8)። በዚሁ መሠረት በከበረ ሥጋው ይገለጣል፥ “የነገሥታት ንጉሥ፥ የጌቶችም ጌታን በመሆን ይነግሣል። በአባቱ በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል (ሉቃስ 1፡32፤ ራእይ 19፡16)። 

7. ሥጋለብሶ አዲስ የተፈጠረችው ቤተ ክርስቲያን ራስን(ኤፌ. 1፡22)። 

የእግዚአብሔር ልጅ ሥጋ ሲለብስ ሰብአዊ አካልን ብቻ ሳይሆን፥ ሰብአዊ ነፍስና መንፈስንም ወስዷል። በዚህ ሁኔታ ቁሳዊውንና መንፈሳዊውን ሰብአዊነት ተሳበሰ። ሁለንተናዊ ሰው በመሆንም በቅርብና በቋሚነት የሰብአዊው ቤተሰብ አባል ሆኖ፥ “የኋለኛው አዳም” (1ኛ ቆሮ. 15፡45) ተባለ። “ክቡር ሥጋው” ተብሏልም (ፊልጵ. 3፡21)። ይህ አሁን ሕያው እውነት ነው። 

ይህ ዘላለማዊ ልጅ፥ ያህዌ እምላክ፥ የማርያም ልጅ፥ የናዝሬት ወጣት፥ የይሁዳ መምህርና ፈዋሽ፥ የቢታንያ እንግዳ፥ የቀራንዮ በግ ነበር። አሁን የሰዎች አዳኝ፥ ወደፊት ደግሞ የክብር ንጉሥ፥ ሊቀካህን፥ የሚመጣው ሙሽራና ጌታ ይሆናል።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

9
ትምህርት 9 ከ52

እግዚአብሔር ወልድ፡- የምትክነት ሞቱ

ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተው ለዓለም ሁሉ ኃጢአት መሥዋዕትነት መሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ ተገልጧል። በዚሁ መሠረት መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን ሲያስተዋውቅ፡- የዓለምን ሁሉ ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” (ዮሐ. 1፡29) ብሏል። ኢየሱስ የሞተው ለሌሎች መሥዋዕትነትና ምትክነት ነው። “ምትክ” የሚለው ቃል በግልጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባይሆንም፥ ኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢአተኞች ምትክ የመሆኑ እውነት ግን በመጽሐፍ ቅዱስ በሚገባ ተረጋግጧል። ክርስቶስ በምትክነት ሞቱ የማይለካውን እግዚአብሔር በኃጢአተኞች ላይ ያለውን የጽድቅ ፍርድ ተሸከመ። የዚህ የምትክነት ጸጋ ውጤት ግልጥና፥ የተከናወነም ነው። አዳኝ የሆነው ክርስቶስ የእግዚአብሔርን ቁጣ ሊያበርድ በሚችል ሁኔታ በኃጢአተኞች ሳይ የነበረውን መለኮታዊ ፍርድ ተሸክሟል። ሰዎች ይህን የእግዚአብሔር ማዳን ተቀብለው የምሥራቹን እንዲያምኑ፥ ክርስቶስ ስለ ኃጢአታቸው መሞቱን እንዲገነዘቡ እና እርሱ የግል አዳኛቸው መሆኑን እንዲቀበሉ ተጠይቀዋል። 

“ምትክነት” የሚለው ቃል፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት አማካይነት የተፈጸመውን ሥራ በከፊል ብቻ ይገልጣል። በመሠረቱ ይህን ሥራ የሚገልጥ አጠቃላይ ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጥቅም ላይ አልዋለም። “ሥርየት” የሚለው ቃል ትምህርተ-መለኮት ውስጥ ብዙ ጊዜ አጠቃላይ ገላጭ ሆኖ አገልግሏል። ይሁን እንጂ በብሉይ ኪዳንም ሆነ አዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሰ ተመሳሳይ ቃል የሰውም። ብሉይ ኪዳን ውስጥ የሥርየት ጽንሰ አሳብ ያገለገሰው ኃጢአተኛ በሚያቀርበው መሥዋዕት አማካይነት ኃጢአት ለጊዜው የመሸፈኑን ተግባር ለመግለጥ ነበር። ይህ ድርጊት ለጊዜያዊ ይቅርታ መሠረት ሆኗል። “ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለመተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው” (ሮሜ 3፡25)። እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ዘመን ኃጢአትን ይቅር በማለት ፍጹም በሆነ ጽድቅ ይሠራ ነበር። ኃጢአትን ለጊዜው መሸፈን ብቻ ሳይሆን፥ ለዘላለም የሚያስወግደውንና እንደ መሥዋዕት በግ የሚሆነውን የልጁን መምጣትም አስቀድሞ አቅዷል (ዮሐ. 1፣ 29)። 

ሀ. የልጁ ሞት የሚያከናውናቸው ነገሮች 

የኢየሱስ ክርስቶስን ሞት ሙሉ ዋጋ ለማገናዘብ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በርከት ያሉ ጠቃሚ እውነቶች ተጎልጠዋል። 

1. የክርስቶስ ምታ እግዚአብሔር ለኃጢአተኞች ያለውን ፍቅር ያረጋግጣል (ዮሐ. 3፡16፤ ሮሜ 5፡8፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡16፤ 4፡9)። አማኝ በእግዚአብሔር የመወደዱ እውነት፥ አማኝን የማያምን ሰው በማይችለው ላቅ ያለ ሥነ-ምግባራዊ ኑሮ መኖር የሚጠበቅበት ያደርገዋል (2ኛ ቆሮ. 5፡15፤ 1ኛ ጴጥ. 2፡11-25)። 

2. የክርስቶስ ምታ፥ ኃጢአተኛውን ከኩነኔ ለመቤዠት የእግዚአብሔር ጻድቅ ፍርድለሚጠይቀው የቤዛነት ዋጋ የተከፈለ ነው ተብሏል። ኃጢአተኛውን ከእግዚአብሔር ጻድቅ ፍርድ ለማዳን የተከፈለ የቤዛነት ዋጋ ነው (ማቴ. 20፡28፤ ማር. 30፡45፤ 1ኛ ጢሞ. 2፡6)። የክርስቶስ ሞት ስለ ኃጢአተኛ የተከፈለ ተገቢ ቅጣት ነበር (ሮሜ 4፡25፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡21፤ ገላ. 1፡4፤ ዕብ. 9፡28)። 

ክርስቶስ ዕዳችንን በመክፈል ነጻ አወጣን። ይህን አሳብ ለመግለጥ ሦስት ጠቃሚ የግሪክ ቃላት አዲስ ኪዳን ውስጥ ተጠቅሰዋል። 

(ሀ) “አጎራዞ፥ “ከበያ መግዛት” ማለት ይሆናል። (“አጎራ ማለት “ገበያ” ነው)። ሰው በኃጢአቱ ሳቢያ ከሞት ፍርድ በታች እንደሆነ ተቆጥሯል (ዮሐ. 3፡18-19፤ ሮሜ 6፡23)፥ ማለት “ለኃጢአት የተሸጠ” ባሪያ (ሮሜ 3፡14) ሆኗል። ነገር ግን የመቤዥት ተግባር በሆነውና የኢየሱስ ክርስቶስ ደም አማካይነት ተገዝቷል (1ኛ ቆሮ. 6፡20፤ 7፡23፤ 2ኛ ጴጥ. 2፡1፤ ራዕይ 5:9፤ 14፡3-4)። 

(ለ) “ኤክሳጎራዞ”፥ “ጎዝቶ ከገበያ ማውጣት” ማለት ሲሆን፥ አሳቡ መግዛት ብቻ ሳይሆን፥ ከግብይት ማውጣትንም ያካትታል (ገላ. 3፡13፤ 4፡5፤ ኤፌ. 5፡16፤ ቆላ. 4፡5)፤ አባባሉ ነጻ የማውጣቱ ተግባር ለዘላለም መሆኑንን ያመለክታል። 

(ሐ) “ሉትሮ፥ “መፍታት” ወይም “በነጻ መልቀቅ” (ሉቃስ 24፡21 ፤ ቲቶ 2፡14፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡18) ማለት ነው። ይህ ቃል ባሪያን ነጻ ማድረግን ያመለክታል (ሉቃስ 21:28፤ ሮሜ 3፡24፤ 8፡23፤ 1ኛ ቆሮ. 1፡30፤ ኤፌ. 1፡7፥ 14፤ 4፡30፤ ቆላ. 1፡14፤ ዕብ. 9፡15፤ 11፡35)። በዚሁ መሠረት መቤዥት የሚለው አሳብ፥ መግዛትን፥ ከግብይት ማውጣትን እና የተቤዠውን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት፥ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ፍጹም ነጻ ማውጣትን ይጨምራል። 

የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ለኃጢአት የቀረበ መሥዋዕት ነው። መሥዋዕቱ በብሉይ ኪዳን ዘመን ይቀርብ እንደነበረውና ኃጢአትን ለጊዜው እንደሚሸፍነው፥ እንዲሁም የጽድቅን ፍርድ ያዘገይ እንደነበረው የእንስሳት መሥዋዕት ዓይነት አልነበረም። ክርስቶስ በመሥዋዕትነቱ ኃጢአታችንን ለዘላለም ተሸክሟል (ኢሳ. 53፡7-12፤ ዮሐ. 1፡29፤ 1ኛ ቆሮ. 5፡7፤ ኤፌ. 5 ፡2፤ ዕብ. 9፡22፥ 26፤ 10፡14)። 

3. የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት፥ ኃጢአተኞች ለተላለፉት ሕግ ጋን ለመክፈል የታዛዥነት ተግባር ነው። ይህ መታዘዝ ኃጢአተኛ በበደሉ ምክንያት ይቀበሰው የነበረውን የእግዚአብሔር ፍጹም ፍርድ ያሟላል። ሄላስቴሪዮን” የሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን፥ ማስተሥረያውን (ዕብ. 9፡5) ማለትም ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የነበረና በታቦቱ ውስጥ የነበረውን ሕግ የሸፈነ ኪዳንን የሚያመለክት ነው። ሰሥርየት ዕለት (ዘሌዋ. 16፡14) ማስተሥረያው ላይ ከመሠዊያው የተወሰደ ደም ይረጭበታል፤ ይህ ክንውን የፍርድን ዙፋን ወደ ምህረት ዙፋንነት ይቀይረዋል (ዕብ. 9፡11-15)። በተመሳሳይ ሁኔታ የእግዚአብሔር ዙፋን በኢየሱስ ክርስቶስ የማስተሥረይ ሥራ የጸጋ ዙፋን ይሆናል (ዕብ. 4፡14-16)። 

የዚህ ቃል ተመሳሳይ የሆነውና ሂላስሞስ የሚለው የግሪክ ቃል የማስተሥረይን ተግባር ይገልጣል (1ኛ ዮሐ. 2፡2፤ 4፡10)። ትርጉሙ ክርስቶስ በመስቀል ሞቱ አማካይነት እግዚአብሔር ከሰው ኃጢእት የሚጠይቀውን ዋጋ (ሞት) ፍጹም በሆነ መንገድ አርክቷል ማለት ነው። ሮሜ 3፡25-26 ውስጥ እንደተገለጠው፥ እግዚአብሔር ኃጢአትን ይቅር በማለቱ ጳድቅ ተብሏል። ይህ በመስቀሉ ፊት የሚደረግ ይቅርታ፥ በመጨረሻ ጊዜ ክርስቶስ በሞቱ የጽድቅን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ የሚያረካ የመሆኑ መሠረት ነበር። በዚህ ሁሉ እግዚአብሔር ኃጢአተኛን በመቅጣት የሚረካ ሆኖ አልታየም። ይልቁንም የፍቅር አምላክ ስለሆነ ኃጢአተኛውን ይቅር በማለት ደስ የሚሰኝ መሆኑ ተገልጧል። የሥርየትና የመቤዥት ተግባር፥ በክርስቶስ ለሚያምን ሰው ሁሉ ዕዳው ሙሉ ለሙሉ እንደተከፈለለት፥ ከኃጢአት ባርነት ነጻ መውጣቱ እና ኃጢአተኛ ይደርስበት የነበረ የእግዚአብሔር ቁጣ ሙሉ ለሙሉ የቀረለት መሆኑን ያረጋግጣል። 

4. የክርስቶስ ምት ኃጢአተኛውን የዋጀና ሥርየት ያመጣለት ብቻ ሳይሆን፥ እግዚአብሔርን ያረካና ዓለም ከእርሱ ጋር የታረቀበት መሠረትም ነው። ካታላሶ፡የሚለውና “ማስታረቅ” የሚል ትርጉም ያለው የግሪክ ቃል ሰውን ሙሉ በሙሉ መለወጥ ከእግዚአብሔር ጋር ማገናኘት የሚል አሳብ አለው። ይህ ማስታረቅ የሚል ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ ብዙ ቦታ ተጠቅሷል (ሮሜ 5፡10-11፤ 11፡15፤ 1ኛ ቆሮ. 7፡11፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡18-20፤ ኤፌ. 2፡16፤ ቆላ. 1፡20-21)። መታረቅ በሚለው ቃል ውስጥ ያለው ፅንሰ-አሳብ፥ እግዚአብሔር ይለወጣል ማለት ሳይሆን፥ በክርስቶስ ነጻ የማድረግ ሥራ አማካይነት ከሰው ጋር ያለው ግንኙነት ይቀየራል ማለት ነው። ሰው ነው ይቅር የተባለ፥ የጸደቀ እና ከእግዚአብሔር ጋር ሊታረቅ በሚችልበት ደረጃ በመንፈስ ካፍ ያስ። አሳቡ የሚገልጠው እግዚአብሔር ከኃጢአተኛ ጋር መታረቁን ማለትም ከኃጢአተኝነት ጋር መስማማቱ ሳይሆን፥ ኃጢአተኛው ከእግዚአብሔር ቅዱስ ባሕርይ ጋር እንዲስተካከል መደረጉን ነው። እግዚአብሔር ዓለምን በሞላ ነጻ እንዳደረገና ለኃጢአት ሁሉ ሥርየትን እንደሰጠ፥ እርቅም እንዲሁ የተሰጠ ነው፤ ሆኖም ዓለም ሁሉ ይህን እልተጠቀመበትም (2ኛ ቆሮ. 5፡19፤ 2ኛ ጴጥ. 2፡1፤ 1ኛ ዮሐ. 2 ፡1-2)። ይህ የእግዚአብሔር መቤዥት አስደናቂ ስጦታ ከሁሉ የላቀ ዋጋ ያለው ነው። ሥርየትና የማስታረቅ ሥራም እንዲሁ ናቸው፤ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን፥ እግዚአብሔር በዚህ ስጦታው አማካይነት ከዓለም ጋር ይታረቃል(2ኛ ቆሮ. 5፡18-19፤ ኤፌ. 2፡16)። 

5. በክርስቶስ ምት የሰውን ልጅ ከውድቀቱ የሚያመጣ የኃጢአት ዕዳ ተከፍሏል። በዚሁ መሠረት እግዚአብሔር የሥርየት ዋጋን በመከፈል ሰውን ከራሱ ጋር አስታርቋል። ከእንግዲህ ወዲህ ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኙ የሚያምን ሰው ሁሉ እግዚአብሔር እንዳይቀበለው የሚያደርግ አንዳች እንቅፋት የለበትም (ሮሜ 3፡26)። ዓለማት ተሰብስበው ከሚያከናውኑት ነገር ሁሉ ይልቅ እግዚአብሔርን ያረካ የክርስቶስ ሞት ነው። በመሆኑም ይህ እርካታ የእግዚአብሔር ቅድስና ከኃጢአተኞች የሚፈልገውን ዋጋ በመክፈል ፍቅርና ኃይሉን እንዲለግስ አድርጎታል። 

6. ክርስቶስ በሞቱ የኃጢአተኞችን ቅጣት ሰመሸከም የእነሱ ምትክ ሆኗል (ዘሌዋ. 16፡21፤ ኢሳ. 53፡6፤ ማቴ. 20፡28፤ ሉቃስ 22 ፡37፤ ዮሐ. 10፡11፤ ሮሜ 5፡6-8፤ 1ኛ ጴጥ. 3፡18)። ይህ እውነት ለድነት ወደ እግዚአብሔር ለሚቀርቡ ሁሉ የዋስትና መሠረት ነውዬ ማንኛውም ሰው ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖረው ግንኙነት ኃጢአትን አስመልክቶ ያለውን ጥያቄ ሁሉ የሚፈታ እውነትም ነው። ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ሞቷል የሚለው አጠቃላይ እምነት በቂ አይደለም። ክርስቶስ ኃጢአቴን ተሸክሟል የሚል የግል እምነት ያስፈልጋል፤ ይህም ዕረፍት ደስታና እርካታን ያስገኛል (ሮሜ 15፡13፤ ዕብ. 9፡14፤ 10፡2)። ድነት በክርስቶስ ለሚያምን ሁሉ በቅጽበት የሚሰጥ የእግዚአብሔር ኃያል ሥራ ነው። 

ለ. የወልድን ሞት አስመልክቶ ያለ የተሳሳተ ግንዛቤ 

የክርስቶስ ሞት ብዙውን ጊዜ የተሳሳተ ትርጉም ይሰጠዋል። ክርስቲያን ሁሉ እነዚህን ዛሬ እየሰፉ የመጡ ስሕተተኛ ገለጣዎችን በሚገባ መረዳት አለበት። 

1. እግዚእብሔር የበደለውን ኃጢአት በንጹሑ ሰው ላይ እያኖርም ከሚለው እሳብ በመነሣት የምትክነት ወይም የቤዛነት ሥራ ተገቢ አይደለም ተብሏል። ክርስቶስ ፈቃደኛ ያልሆነ በደል ተሸካሚ ሲሆን ኑሮ ይህ አገላለጥ ምናልባት ልክ ይሆን ይሆናል። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ የሚገልጠው፥ ክርስቶስ በሙሉ አሳብ ለአባቱ ፈቃድ የታዘዘና በዘላለም ፍቅር ያደረገው መሆኑን ነው (ዮሐ. 13፡1፤ ዕብ. 10፡7)። በተመሳሳይ ሁኔታ እግዚአብሔር አብ ራሱ ነበር በማይመረመር ጥበቡ በክርስቶስ በኩል ዓለምን ከራሱ ጋር ያስታርቅ የነበረው (2ኛ ቆሮ. 5፡19)። ጻድቅ ፈራጅ የሆነው እግዚአብሔር በፍጹም ፍቅርና መሥዋዕት አማካይነት ቅድስናው የሚጠይቀው ፍርድ ይሞላ ዘንድ ቅጣቱን በራሱ መሸከሙን ይህ ያሳያል። 

2. ክርስቶስ በሰማዕትነት ሞተ የሚሉ ክፍሎች አሉ። የሞቱንም ፋይዳ ለእምነቱ የተከፈለ የደፋርነትና የታማኝነት አርአያነት እንደሆነ ይቆጥሩታል። ለዚህ የተሳሳተ አመለካከት በቂ መልስ አለ። ይኸውም፥ ክርስቶስ ለመሥዋዕትነት ከእግዚአብሔር የተሰጠ በግ ስለሆነ፥ ማንም ሕይወቱን አልወሰደበትም (ዮሐ. 10፡18፤ ሐዋ. 2፡23)። 

3. ክርስቶስ የሞተው የመልካም ሥነ-ምግባር አርአያ ለመሆን ነው የሚሉም አሉ። እንደነሱ አባባል የክርስቶስ መስቀል የሚያመለክተው፥ መለኮታዊውን የኃጢአት ዋጋ በመሆኑ፥ ይህን የሚረዱ ሰዎች ከኃጢአተኛነት ይቆጠባሉ። ምንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌለው ይህ ፅንሰ-አሳብ፥ እግዚአብሔር በአሁኑ ጊዜ ሰውን ከነበረበት ሁኔታ ላማሻሻል እንደሚፈልግ ያምናል። እውነቱ ግን የክርስቶስ መስቀል የዳግም ልደት መሠረት መሆኑ ነው።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

10
ትምህርት 10 ከ52

እግዚአብሔር ወልድ፡- ትንሣኤው

ሀ. ትንሣኤ በብሉይ ኪዳን 

የሰዎችን ሁሉ ትንሣኤና የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚያመለክት አስተምህሮ ብሉይ ኪዳን ውስጥ አለ። አስተምህሮው ቀደም ሲል ምናልባት በአብርሃም ዘመን ይኖር እንደነበር በሚገመተው ከኢዮብ ጊዜ ጀምሮ ነበር፤ ኢዮብ ሰእምነት መግለጫው እንዲህ ብሏል። “እኔን የሚቤዠኝ ሕያው እንደሆነ፥ ሰመጨረሻም ዘመን በምድር ላይ እንዲቆም፥ ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ፥ እኔ ራሴ አየዋለሁ፥ ዓይኖቼም ይመልከቱታል፥ ከእኔም ሌላ አይደለም። ልቤ በመናፈቅ ዝሎአል” (ኢዮብ 19፡25-27)። ኢዮብ በዚህ ቃሉ የሚያረጋግጠው የራሱን ትንሣኤ ብቻ ሳይሆን፥ አዳኝ የሆነ ጌታው ሕያው እንደሆነና ሰኋላም በምድር ላይ የሚቆም መሆኑን ጭምር ነው። ሰዎች ሁሉ በዘመን ፍጻሜ የሚነሡ የመሆኑ ትምህርት ዮሐንስ 5፡28-29 እና ራእይ 20፡4-6፥ 12-13 ውስጥ ይገኛል። 

ብሉይ ኪዳን ውስጥ የተለያዩ ትንቢቶች ስለ ሰው አካል ትንሣኤ ይናገራሉ (ኢዮብ 14፡13-15፤ መዝ. 16፡9-10፤ 17፡15፤ 49፡15፤ ኢሳ. 26፡19፤ ዳን. 12፡2፤ ሆሴዕ 13፡14፤ ዕብ. 11፡17-19)። የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ መዝሙረኛው ዳዊት፥ “ስለዚህ ልቤን ደስ አለው፥ ምላሴም ሐሴት አደረገች፤ ሥጋዬ ደግሞ በተስፋ ታድራለች፤ ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም” (መዝ. 16፡9-10) ባለው ክፍል በግልጥ ተነግሯል። ዳዊት በዚህ ክፍል የሚገልጠው፥ በተስፋ ስለሚጠብቀው የግል ትንሣኤው ብቻ ሳይሆን “ቅዱስህን” ብሎ የሚጠራው ኢየሱስም 

መበስበስን እንደማያይ ያረጋግጣል። ይህ የዳዊት ቃል የክርስቶስን ትንሣኤ በሚያመለክትበት ሁኔታ ሰጴጥሮስ ስብከት ውስጥ (ሐዋ. 2፡24-31)፥ እንዲሁም በጳውሎስ ስብከት ውስጥ (ሐዋ. 13፡34-37) ተጠቅሷል። 

የክርስቶስ ትንሣኤ መዝሙረ ዳዊት 22፡22 ውስጥም ክርስቶስ ራሱ ከሞቱ በኋላ ስሙን “ለወንድሞቹ” የሚገልጥ መሆኑን ባስገነዘበበት ሥፍራም ተመልክቷል። ክርስቶስ ከፍ ከፍ ብሎ የማዕዘን ራስ እንደሚሆን መዝሙረ ዳዊት 118፡22-24 ውስጥ የተገለጠው፥ በሐዋርያት ሥራ 4፡10-11 ላይ የኢየሱስን ትንሣኤ በማጉላትና በማብራራት ተጠቅሷል። የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ብሉይ ኪዳን ውስጥ በመልከ ጼዴቅ ተምሳሌትነት የተተነበየ ይመስላል (ዘፍጥ. 14፡18፤ ዕብ. 7፡15-17፥ 23-25)። በተመሳሳይ ሁኔታ ዘሌዋውያን 14፡4-7 ውስጥ ስለ ለምጻሙ ሰው ክሚቀርቡት ሁለት ወፎች ውስጥ የሚለቀቀው ወፍ እና የመከሩ በኩራት (ዘሌ. 23፡10-11) ተምሳሌቶች ክርስቶስ የትንሣኤ በኩራት እንደሆነ ያመለክታሉ። ያቆጠቆጠችው የአሮን በትርም (ዘኁ. 17፡8) ስለ ትንሣኤ ታመለክታለች። ስለዚህ የሰው ሁሉና የክርስቶስ ትንሣኤ ብሉይ ኪዳን ውስጥ በሚገባ ተረጋግጧል። 

ለ. ክርስቶስ ስለራሱ ትንሣኤ፥ የተናገራቸው ትንቢቶች 

ክርስቶስ በወንጌሎች ውስጥ ስለ ሞቱና ትንሣኤው በተደጋጋሚ አስቀድሞ ተናግሯል (ማቴ. 16፡21፤ 17፡23፤ 20፡17-19፤ 26፡12፥ 28-29፥ 31-32፤ ማር. 9፡30-32፤ 14 ፡28፤ ሉቃስ 9፡22፤ 18፡31-34፤ ዮሐ. 2፡19-22፤ 10፡17-18)። ትንቢቶቹ በጣም የተደጋገሙ፥ ግልጥ እና ክርስቶስ የራሱን ሞት እራሱ የተነበየ ለመሆኑ በማያጠያይቅ ሁኔታ በብዙ ተዛማጅ ሁኔታዎች የተገለጡ ናቸው። የእነዚህ ትንቢቶች መፈጸምም ትክክለኛነታቸውን ያረጋግጣል። 

ሐ. የክርስቶስ ትንሣኤ ማረጋገጫዎች 

አዲስ ኪዳን የክርስቶስን ትንሣኤ እስመልክቶ እጅግ ብዙ ማረጋገጫዎችን ያቀርባል። ክርስቶስ ከትንሣኤው በኋላ ቢያንስ ለአሥራ ሰባት ጊዜ ታይቷል። እነዚህም፡(1) ለማርያም መግደላዊት (ዮሐ. 20፡11-17፤ ማር. 16፡9-11)፥ (2) ለሴቶች (ማቴ. 28፡9-10)፥ (3) ለጴጥሮስ (ሉቃስ 24፡34፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡5)፥ (4) በኤማሁስ መንገድ ላይ ለደቀ መዛሙርቱ (ማር. 16፡12-13፤ ሉቃስ 24፡13-35)፥ (5) ለአሥሩ ደቀ መዛሙርት (እዚህ ላይ “አሥራ አንዱ” ይላል፥ ግን አሥር ናቸው።) ምክንያቱም ቶማስ በወቅቱ በቦታው አልነበረም (ማር. 16፡14፤ ሉቃስ 24፡36-43፤ ዮሐ. 20፡19-24)፥ (6) ከትንሣኤው ከአንድ ሳምንት በኋላ ለአሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት (ዮሐ. 20፡26-29)፥ (7) በገሊላ ባሕር አጠገብ ለሰባቱ ደቀ መዛሙርት (ዮሐ. 21፡1-23)፥ (8) ለአምስት መቶ ሰዎች (1ኛ ቆሮ. 15፡6)፥ (9) ለያዕቆብና ለጌታ ወንድም ለዮሐንስ (1ኛ ቆሮ. 15፡7)፥ (10) በገሊላ ተራራ ላይ ለአሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት (ማቴ. 28፡16-20፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡7) ፥ (11) በደብረ ዘይት ተራራ በዕርገቱ ወቅት ለደቀ መዛሙርቱ (ሉቃስ 24፡44-53፤ ሐዋ. 1፡3-9)፥ (12) ሰማዕቱ እስጢፋኖስ ከመሰዋቱ በፊት ሰአባቱ ቀኝ ሆኖ (ሐዋ. 7፡55-56)። (13) ደማስቆ መንገድ ላይ ለጳውሎስ (ሐዋ. 9፡3-6፤ 22፡6-11፤ 26፡13-18፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡8)። (14) በዐረቢያ ምድር ለጳውሎስ (ሐዋ. 20፡24፤ 26፡17፤ ገላ. 1፡12፥ 17) 15) ቤተ መቅደስ ውስጥ ለጳውሎስ (ሐዋ. 22፡17-21፤ 9፡26-30፤ ገሳ. 1፡18)፡(16) ቂሳሪያ እስር ቤት ለጳውሎስ (ሐዋ. 23፡11)፥ (17) ለሐዋርያው ዮሐንስ (ራእይ 1፡12-20)። 

እነዚህ በብዙ የተለያዩ ሁኔታዎች የተፈጸሙ መታየቶች እና በዙሪያቸው ያሉ ማረጋገጫዎች ሁሉ ክርስቶስ ከሞት የተነሣ መሆኑን የሚመሰክሩ ብርቱ የታሪክ ማረጋገጫዎች ናቸው። 

መታየቱን አስመልክቶ ከቀረቡት ማረጋገጫዎች አያሌ ተጨማሪ ማስረጃዎች ለመጥቀስ ይቻላል። ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ መቃብሩ ባዶ ነበር (ማቴ. 28፡6፤ ማር. 16፡6፤ ሉቃስ 24፡3፥ 6፥ 12፤ ዮሐ. 20፡2፥ 5-8)። የክርስቶስ ትንሣኤ ምስክሮች ድልሎችና በቀላሉ የሚታለሉ እለመሆናቸው እርግጥ ነው። እንደውም ማረጋገጫዎችን ለመገንዘብ የዘገዩ ነበሩ (ዮሐ. 20፡9፥ 11-15፥ 25)። የትንሣኤውን እውነት ከጨበጡ በኋላ ግን፥ በክርስቶስ ላላቸው እምነት ለመሞት ዝግጁ ሆኑ። ከትንሣኤው በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ለውጥ ታይቶባቸዋል። ኀዘናቸው በደስታና በእምነት ተተክቷል። 

ከክርቶስ ትንሣኤ በኋላ በደቀ መዛሙርቱ ስለተከናወነው የመንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ኃይል፥ ስላወጁት የምሥራች ቃል ኃይል እና ያን ይደግፉ የነበሩትን የማረጋገጫ ተአምራት የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ይመሰክራል። የጰንጠቆስጤ ዕለት ሌላው ጠቃሚ ማረጋገጫ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ እውነት ባይሆን ኖሮ በዚህ ዕለት ሦስት ሺህ ሰዎችን ለማሳመን እይቻልም ነበር። ይህ የትንሣኤ ቃል አፈ ታሪክ ብቻ ቢሆን ኑሮም እነዚያ ሰዎች ማስረጃውን የመመርመርና የማረጋገጥ ዕድል ነበራቸው። 

ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን የምታከብረው የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን፥ ከምትፈጽመው ሥርዓቶች ደግሞ የጌታ እራትና ይቀርብ የነበረው መባ ሌሎቹ ታሪካዊ ማረጋገጫዎች ናቸው (ሐዋ. 20፡7፤ 1ኛ ቆሮ. 16፡2)። ክርስቶስ ከሞት ባይነሣ ኖሮ። ሐዋርያቱ የተሰደዱና የተገደሉባት ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ጸንታ የመኖሯ እውነት ያለ በቂ መግለጫ ይቀር ነበር። የክርስቶስ አካላዊ ትንሣኤ ነው አካሉ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን ለሰማያዊ ሥራዋ ብቁ የሚያደርጋት። 

መ. የክርስቶስ ትንሣኤ ምክንያቶች 

ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ ቢያንስ ሰባት ዋና ዋና ምክንያቶችን ለመጥቀስ ይቻላል። 

1. የክርስቶስ ትንሣኤ አማንነቱ የሚመነጭበመሪን(ሐዋ. 2፡24)። 

2. ለዳዊት የተሰጠን ቃል ኪዳን ለመፈጸም (2ኛ ሳሙ. 7፡12-16፤ መዝ. 89፡20-37፤ ኢሳ. 9፡6-7፤ ሉቃስ 1፡31-33፤ ሐዋ. 2፡25-31)። 

3. የትንሣኤ ሕይወትን ለመስጠት (ዮሐ. 10፡10-11፤ 11፡25-26፤ ኤፌ. 2፡6፤ ቆላ. 3፡1-4፤ 1ኛ ዮሐ. 5፡11-12)። 

4. የትንሣኤ ኃይል ምንጭ ለመሆን (ማቴ. 28፡18፤ ኤፌ. 1፡19-21፤ ፊል. 4፡13)። 

5. የቤተ ክርስቲያን ራስ ለመሆን(ኤፌ. 1፡20-23)። 

6. ጽድቃችን ስለተከናወነልን(ሮሜ 4፡25)። 

7. የትንሣኤ በኩርዕመናን(1ኛ ቆሮ. 15፡20-23) ነው። 

ሠ. የክርስቶስ ትንሣኤ ጠቃሚነት 

የክርስቶስ ትንሣኤ ከታሪካዊነቱ የተነሣ የመለኮታዊነቱ ዋና ማረጋገጫ ነው። ትንሣኤው በሞትና በኃጢአት ላይ ታላቅ ድል እንደመሆኑ፥ ኤፌሶን 1፡19-21 ላይ እንደተጠቀሰው የዘመናችን መለኮታዊ ኃይል መለኪያም ነው። ትንሣኤ እንዲህ ያለ ጠቃሚ አስተምህሮ በመሆኑ፥ በዘመናችንም የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ለኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ መታሰቢያነት ተለይቷል። ይህ ሰንበት እስራኤላውያን እንዲያከብሩት ከታዘዙበት የሰባተኛው ቀን የሰንበት ሕግ ይልቃል። ስለዚህ ትንሣኤ ለክርስትና እምነት የማዕዘን ድንጋይ ነው። ጳውሎስ 1ኛ ቆሮ. 15፡17 ውስጥ “ክርስቶስ ካልተነሣማ እምነታችን ከንቱ ነው፤ ገና በኃጢአታችሁ ናችሁ” እንዳለው ትንሣኤውን በእርግጠኛነት እንናገራለን፥ ክርስቶስ ከሞት ስለተነሣ እምነታችን እርግጠኛ፥ ድል አድራጊነቱን እውነት፥ የክርስትና እምነታችንን ደግሞ ፍጹም ያደርገዋል።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

11
ትምህርት 11 ከ52

እግዚአብሔር ወልድ፡- ዕርገቱና የክህነት አገልግሎቱ

ሀ. የክርስቶስ ዕርገት እውነትነት 

በክርስቶስ መከበር ቅደም ተከተል ትንሣኤው የመጀመሪያው ሲሆን፥ ዕርገቱ ደግሞ ቀጣይ ዋና ነገር ነው። ይህ ማርቆስ 16፡19፤ ሉቃስ 24፡50፥51፤ የሐዋርያት ሥራ 1፡9-11 ውስጥ ተመዝግቧል። 

ክርስቶስ በትክክለኛው ሁኔታ ከማረጉ በፊት ወደ ሰማይ ወጥቶ ነበር? የሚል ጥያቄ ይነሣል። ይህንም በተመለከተ ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ፥ “እኔ ወደ አባቴና ወደ እባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁም በርጋለሁ” ሲል ለመግደላዊት ማርያም የተናገረው ይጠቀሳል (ዮሐ. 20፡17)። በብሉይ ኪዳን ዘመን ካህኑ ከመሥዋዕት በኋላ ደም ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚገባበት ሁኔታ በምሳሌነት ቀርቧል (ዕብ. 9፡12፥ 23-24)። የደሙ መሥዋዕት ተግባራዊ በሆነ ሁኔታ የተከናወነው መስቀሉ ላይ ነው። መስቀሉ ላይ የተከናወነው ሥራ ጥቅሞች ለአማኞች መዋላቸው ዛሬም ይቀጥላል (ዮሐ. 1፡7 )። ምንም እንኳ ቃሉ የተለያዩ ፍቺዎች ቢሰጡትም፥ አብዛኛዎቹ የወንጌል አማኞች ዮሐንስ 20፡17 ውስጥ የተጠቀሰውንና “ዐርጋለሁ” የሚለውን ቃል የወደፊት ጊዘ ገሳጭ አድርገው ይገነዘቡታል። 

1103 ሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ አንድ ውስጥ እንደተጠቀሰው፥ የክርስቶስ ዕርገት በእርግጠኛነት መከናወኑን በተመለከተም ጥያቄ ተነሥቷል። ክርስቶስ በመፀነስና በመወለድ ወደ ምድር መምጣቱ እውነት እንደሆነ ሁሉ፥ ወደ ሰማይ የማረጉን እውነትነት ምንባቡ በሚገባ ይደግፋል። የክርስቶስን ዕርገት ለመግለጥ ሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 1 ውስጥ አራት የግሪክ ቃላት ጥቅም ላይ ውለዋል። “ከፍ ከፍ አለ” (ቁ.9)፥ “ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው፡” (ቁ.9)፥ “ሲሄድ” (ቁ. 30)፥ “ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው” (ቁ. 1)። እነዚህ አራት ገለጣዎች ጠቃሚ ናቸው፤ ምክንያቱም ቁጥር 11 ውስጥ ዳግም ምጽአቱ ልክ እንደ ዕርገቱ፥ ማለትም በዓይኖቻቸው እያዩት በአካል ደመናት እንደተቀበሉት ሁሉ፥ ሲመለስም ሁሉ እያየው በአካል እንደሚመለስ ተተንብዮአል (ሐዋ. 1:9-11)። ይህ ክፍል የሚያመለክተው ክርስቶስ የሚመጣው ቤተ ክርስቲያኑን ለመውሰድ ሳይሆን፥ መንግሥቱን ለመመሥረት መሆኑን ነው። 

ለ. ክርስቶስ ሰማይ የመግባቱ ማረጋገጫ 

ክርስቶስ ከምድር ወደ ሰማይ ማረጉ ብቻ ሳይሆን፥ እዚያ መድረሱም በተደጋጋሚ መገለጡ የዕርገቱን እውነተኛነት ያረጋግጣል። የከርስቶስን በሰማያዊ ሥፍራ መሆን አያሌ ምንባቦች ያሳያሉ (ሐዋ. 2፡33-36፤ 3፡21፤ 7፡55-56፤ 9፡3-6፤ 22፡6-8፤ 26፡13-15፤ ሮሜ 8፡34፤ ኤፌ. 1፡20-22፣ 4፡8-10፤ ፊልጵ. 2:6-11፤ 3፡20፤ 1ኛ ተሰ. 1፡10፣ 4፡16፤ 1ኛ ጢሞ. 3፡16፤ ዕብ. 1፡3፥ 13፣ 2-7፤ 4፡14፤ 6፡20፤ 7፡26፤ 8፡1፤ 9፡24፤ 10፡12-13፤ 12፡2፤ 1ኛ ዮሐ. 2፡1፤ ራእይ 1፡7፥ 13-18፤ 5፡5-12፤ 6፡9-17፤ 7:9-17፤ 14፡1-5፤ 19፡11-16)። 

ሐ. የዕርገቱ ትርጉም 

የክርስቶስ ዕርገት የምድራዊ አገልግሎቱን መጠናቀቅ ያስረዳል። ክርስቶስ ወደ ምድር በመምጣት ቤተልሔም ውስጥ እንደተወለደ ሁሉ፥ አሁን ደግሞ ወደ አባቱ ተመልሷል። ዕርገቱ በተጨማሪ የሚያስገነዝበው፥ ከትንሣኤው በኋላ ቀድሞ ወደነበረ ገናና ክብሩ መመለሱን ነው። ወደ ሰማይ ማረጉ፥ ምድራዊ ሥራውን ማጠናቀቁንና በአባቱ ቀኝ ወዳለው አዲስ ተግባር መግባቱን ያስገነዝባል። 

ክርስቶስ በሰማያትና በምድር ሁሉ ላይ ጌትነቱን እንደጨበጠ አሁን ባለበት ሰማያዊ ስፍራ ሆኖ እውን ሊሆን ያለውን የፍጻሜ ድሉንና ዳግም ምጽአቱን ይጠብቃል። በአብ ቀኝ እንደተቀመጠም በተደጋጋሚ ተገልጧል (መዝ. 110፡1፤ ማቴ. 22 :44፤ ማር. 12፡36፤ 16፡19፤ ሉቃስ 20፡42-43፤ 22፡69፤ ሮሜ 8፡34፤ ኤፌ. 1፡20፤ ቈላ. 3፡1፤ ዕብ. 1፡3-13፤ 8፡1፤ 10፡12፤ 12፡2፤ 1ኛ ጴጥ. 3፡22)። በሰማያት የተቀመጠበት ዙፋን የአብ ነው፤ ይህን ምድራዊ ከሆነው የዳዊት ዙፋን ጋር አንድ በማድረግ ልናየው አይገባም። ምድር የክርስቶስ ዙፋን ማረፊያና የእግሩም መረገጫ ለመሆን በመጠባበቅ ላይ ናት (ማቴ. 25፡31)። የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደመሆኑ አሁን ያለው ስፍራ የክብርና የሥልጣን ነው። 

መ. ክርስቶስ በአሁኑ ጊዜ በሰማይ የሚያከናውነው ተግባር 

በአብ ቀኝ ተቀምጦ ባለው ክብሩ ከቤተ ክርስቲያን ጋር የሚያገናኙትንና በተምሳሌትነት የተጠቀሱ ሰባት ተግባራትን ያከናውናል፡- 1. እንደ የመጨረሻው አዳም እና የአዲሱ ፍጥረት ራስ፥ 2. አካሉ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ራስ በመሆን፥ 3. እንደ በጎቹ (የመንጋው) መልካም እረኛ፥ 4. ለቅርንጫፎቹ እንደ እውነተኛ የወይን ግንድ5. እንደ ሕንጻ ለምትቆጠረው ቤተ ክርስቲያን በማዕዘን ድንጋይነት፥ 6. የንጉሥ ካህናት ስብስብ ለሆነች ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ካህን በመሆን፥ 7. እንደ ሙሽሪት ለምትጠብቀው (ቤተ ክርስቲያን) እንደ ሙሽራዋ። እነዚህ ሁሉ ተምሳሌቶች ክርስቶስ በአሁኑ ጊዜ የሚያከናውናቸውን ተግባራት በሚገባ ይገልጣሉ። ይሁን እንጂ ዋናው አገልግሎቱ ቤተ ክርስቲያንን በመወከል በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት እንደ ሊቀ ካህን መቅረብ ነው። 

በሊቀ ካህንነት አገልግሎቱ ውስጥ አራት ጠቃሚ እውነቶች ተገልጠዋል። 

1. ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በላይ ሳለች እውነተኛይቱ ድንኳን ሊቀ ካህን በመሆን፥ በዓለም ላሉትና የራሱ ለሆኑት እንደ ሊቀ ካህን ሆኖ ሊያገለግል ወደ ሰማይ ገብቷል (ዕብ. 8፡1-2)። ወደ ሰማይ በዕረገ ጊዜ የሰማይ አባቱ የተቀበለው መሆኑ አንድ እውነትን ያሳያል፤ ይህም ምድራዊ እገልግሎቱ በአባቱ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ መሆኑን ነው። በአብ ቀኝ መቀመጡም በዓለም የሚያከናውነው ተግባር መጠናቀቁን ያመለክታል። 

በራሱ ሳይሆን በአባቱ ዙፋን መቀመጡ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በቋሚነትና ባለማቋረጥ የሚያስገነዝበን፥ በመጀመሪያ ምጽአቱ ወቅት መንግሥቱን ምድር ላይ አለመመሥረቱን ነው። መንግሥቱን በምድር መመሥረቱ ወደፊት የሚጠበቅ” ሲሆን፥ ያኔ መለኮታዊ ፈቃዱ በሰማይ እንደሆነ በምድርም ይሆናል።ያኔ የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ከዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል” (ራእይ 11፡15) የተባለው ይፈጸማል። ንጉሥ የሆነው ልጅ ያኔ መንግሥትን ከአባቱ ይለምናል፥ አባቱም አሕዛብን ለርስቱ፥ የምድርንም ዳርቻ ስግዛቱ ይሰጠዋል (መዝ. 2፡8)። 

ይህን መንግሥቱኝ አሁን በምድር እንዳልመሠረተ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ያመለክታል (ማቴ. 25፡31-46)። ሆኖም ሰማያዊ ዜጋ የሚሆኑ ሕዝቦችን ከአይሁድና ከአሕዛብም አሁን በምድር እየጠራ ነው። ይህ ሕዝብም እካሉና ሙሽራው የሆነች ሴት ክርስቲያን ናት። የአሁኑ ጊዜ ዕቅድ ሲያበቃ፥ ወደ ምድር ይመለስና “የወደቀችውን የዳዊትን ድንኳን እንደገና እሠራታለሁ” የሚለውን ትንቢት ይፈጽማል (ሐዋ. 15፡16፥ እንዲሁም ከቁጥር 13 እስከ 18 ያለውን ይመልከቱ)። ምንም እንኳን እርሱ እንደ መልከ ጼዴቅ ንጉሥና ካህን ቢሆን (ዕብ. 5፡10፤ 7፡1)፥ በአሁኑ ጊዜ እንደ ንጉሥ ሳይሆን እንደ ካህን ነው በማገልገል ላይ ያለው። ዳግም ሊመጣና የነገሥታት ንጉሥ ሊሆን ያለው ወደ ሰማይ ዐርጓል። “ከሁሉ በላይ ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው። እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት” (ኤፌ. 1፡22-23)። 

2. ክርስቶስ ሊቀ ካዘናችን እንደመህን የመንፈሳዊ ስጦታዎች ሁሉ ለጋሽ ነው። አዲስ ኪዳን እንደሚነግረን፥ መንፈሳዊ ስጦታ ለአማኝ የሚሰጥና በመለኮታዊ ኃይል የሚታገዝ ችሎታ ሲሆን፥ የሚሰጠውም አማኙ ውስጥ በሚያድረው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ነው። ይህም መንፈስ ቅዱስ በውስጡ ያደረበትን ሰው ተጠቅሞ መለኮታዊ ሥራዎችን ለማከናወን የሚሠራው ሥራ ነው። ይህ ሙሉ በሙሉ በመንፈስ ቅዱስ የሚከናወን ስለሆነ፥ በምንም ሁኔታ በመንፈስ ቅዱስ የተረዳ የሰዎች ሥራ ሊባል አይገባም። 

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተለያዩ ስጦታዎች ቢጠቀሱም (ሮሜ 12፡3-8፤ 1ኛ ቆሮ. 12፡4-11)፡በምንም አኳኋን ሁለት ነፍሳት ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ሊኖሩ ስላማይችሉ የስጦታዎቹ መለያየት ያዚያኑ ያህል በርካታ ስጦታዎች እንዲኖሩ ያደርጋል። ይሁን እንጂ ስጦታዎቹና ኃይላቸው በግብር የሚታዩት የአማኙ ሕይወት ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ሲሰጥ ነው (ሮሜ 12፡1-2፥ 6-8)። እያንዳንዱ አማኝ መንፈሳዊ ስጦታ ተሰጥቶታል። በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ እማኝ እግዚአብሔር የሚከበርበትን ሥራ በተመለከተ እምብዛም ማደፋፈር አያሻውም፤ ማድረግንም፥ ፈቃዱንም ሰሰውዬው ውስጥ የሚያኖረው መንፈስ ቅዱስ ነው (ፊልጵ. 2፡13)። 

የዐረገው ጌታ አንዳንድ ሰዎችን እንደ ስጦታ ሰጥቷል። ኤፌሶን 4፡7-11 ውስጥ “ለሰዎችም ስጦታን ሰጠ” በማለት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የሆኑትን ይዘረዝራል። እነዚህንም በየአጥቢያው አድርጓል። ጌታ ይህን ተግባር ብቃትና እርግጠኛነት አጎደሰው የሰዎች አሠራር አልተወም (1ኛ ቆሮ. 12፡11፥ 18)። 

3. የፀረገው ክርስቶስ እንደ ዘላለማዊ ሊቀ ካህን የራሱ ለህኑት እየማለደ ይኖራል። ይህን አገልግሉቱን የጀመረው ገና በዓለም ሳለ ሲሆን (ዮሐ. 17፡1-26)። እገልግሎቱም ለዳኑት እንጂ ላልዳኑ ሰዎች አይደለም (ዮሐ. 17፡9)። ይህ ተግባር የርሱ የሆኑት በዓለም እስካሉ ድረስ በሰማይ ይቀጥላል። የመማለድ ተግባሩ በምድር ያሉ ቅዱሳንን ደካማነት፥ አጋር የለሽነትና፥ አለመብሰል ይመሰክታል። እነዚህ ነገሮች ቅዱሳኑ በምንም አኳኋን በደለኞች የሚሆኑባቸው አይደሉም። የቅዱሳኑን ድካም የሚረዳ፥ የጠላታቸውን ኃይልና ዓላማ የሚያውቅ ይህ ጌታ እረኛቸውና የነፍሳቸው ሊቀ ጳጳስ ነው። ለጴጥሮስ ያደርግለት የነበረ ጥበቃ የዚህ እውነት መገለጫ ነበር (ሉቃስ 22፡31-32)። 

የክርስቶስ ካህናዊ ምልጃ ውጤታማ ብቻ ሳይሆን፥ ዘላለማዊም ነው። የብሉይ ኪዳን ካህናት ሟች ስለሆኑ አገልግሎታቸው ተቋርጧል፤ ክርስቶስ ግን ዘላለማዊ ስለሆን የማይሻር ሊቀ ካህንነት አለው። “ስለ እነርሱም ሊማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል፤ ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል” (ዕብ. 7፡25)። ዳዊት ይህን መለኮታዊ እረኝነት እና ዘላለማዊ ጥበቃ ተረድቷል (መዝ. 23፡1)። 

4. ክርስቶስ አሁን fራሱ ኝት በአማላጅነት እግዚያብሔር ፊት ይቀርባል። ይህ የክርስቶስ የውክልና ወይም የጥብቅና ተግባርና በሞቱም አማካይነት ያመጣው ድነት ባይኖር፥ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ እማኝ ከሚሠራው ኃጢአት የተነሣ በደለኛና ከእግዚአብሔር የሚለይ ይሆን ነበር። ኃጢአት፥ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት፥ ሰላሙን፥ ደስታውን እና ኃይሉን እንዲያጣ ያደርገዋል። በሌላ በኩል ግን በደለኛው ኃጢአቱን ቢናዘዝ ይህ ሁኔታ ድንቅ በሆነው የጌታ ጸጋ አማካይነት ይቅር ይባልለታል (1ኛ ዮሐ. 1፡9)። ስለዚህ የክርስቲያንን ኃጢአት ከእግዚአብሔር ቅዱስ ባሕርይ አንጻር መገንዘቡ እጅግ ጠቃሚ ነው። 

ክርስቶስ በሰማይ ከሚያከናውነው ካህናዊ ጥብቅና የተነሣ፥ ክርስቲያን በኃጢአት ውስጥ ቢሆን እንኳን ፍጹም የድነትና የጥበቃ ዋስትና አለው። ጠበቃ በግልጥ ችሎት ላይ ሌላ ሰውን ወክሎ የሚቆም ነው። ክርስቶስም እንደ ጠበቃነቱ የራሱ ለሆኑት ኃጢአት ሲያደርጉ (1ኛ ዮሐ. 2፡1) ሁልጊዜ በሰማይ አብ ፊት በመቅረብ ይማልዳል (ዕብ. 9፡24)። ምልጃን የሚያቀርበው ለእግዚአብሔር አብ ነው። ሰይጣንም ሌሊትና ቀን ወንድሞችን በእግዚአብሔር ፊት እየከሰሰ እዚያው አለ (ራእይ 12፡10)። ለክርስቲያን ኃጢአት ቀላል ነገር ይመስለው ይሆናል። ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር ግን በቀላሉ እያልፈውም። በምድር ኃጢአት ምስጢራዊ ይሆን ይሆናል፤ በሰማይ ግን የተገለጠ ነው። ጠበቃችኝ ያለ ማንም ጠያቂነት በአስደናቂ ጸጋው ስለ በደለኛው አማኝ ይማልዳል። ይህ ጠበቃ የአማኙን ድነት በማስገኘት ረገድ ፍጹም ከሆነው የእግዚአብሔር ፍርድ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ጻድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ” ተብሏል። ጌታ ሊያነጻ ብቃት ያለውን የራሱን ደም በማቅረብ ይማልዳል። አብም ክርስቶስ በሞቱ የኃጢአት ቤዛ ከመሆኑ የተነሣ ልጆቹን ከማንኛውም የሰይጣን ክስ ደግሞም ኃጢአት ከሚያመጣው ፍርድ ያድናቸዋል (1ኛ ዮሐ. 2፡2)። 

ክርስቶስ በሰማይ የክህነት አገልግሎት መስጠቱ ክርስቲያን ኃጢአትን እንዲሠራ ያመቸዋል ማለት አይደለም። ይልቁንም በተቃራኒው ኃጢአትን እንዳንሠራ ግድ የሚለን መሆኑ ነው የተጻፈው (1ኛ ዮሐ. 2፡1)። በጠበቃው (በክርስቶስ) ላይ የሚያስከትለውን የመማለድ ጫና የሚረዳ ማንም አግኝ፥ በግዴለሽነት ኃጢአት ሊሠራ አይችልም። የክርስቶስ የክህነት አገልግሎት ለዳኑት የመማለድና በነሱ ስፍራ በመቆም ዘላለማዊ ዋስትና የሚሰጥ ነው (ሮሜ 8፡34)። 

ሠ. ክርስቶስ በአሁኑ ጊዜ በምድር የሚያከናውነው ተግባር 

ክርስቶስ በአካል በሰማይ በአባቱ ቀኝ ሆኖ፥ በምድርም በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ይሠራል። በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ ጌታ በቤተ ክርስቲያን ውስጥና ከቤተ ክርስቲያን ጋር መኖሩ ተገልጧል (ማቴ. 28፡18-20፤ ዮሐ. 14፡18፥ 20፤ ቈላ. 1፡27)። ለቤተ ክርስቲያኑ ዘላለማዊ ሕይወት የሚሰጥ እርሱ በመሆኑ በእርሷ ይኖራል (ዮሐ. 1፡4፤ 10፡10፤ 11፡25፤ 14፡6፤ ቈሳ. 3፣ 4፤ 1ኛ ዮሐ. 5፡12)። ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ካለው አገልግሎት በተጨማሪ፥ በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን አገልግሎት በአማኞች አማካይነት ያከናውን ዘንድ መንፈስ ቅዱስን ልኳል። አብም በዚህ ዘመን በአማኞች ሁሉ ይኖራል (ዮሐ. 14፡23)። 

የአሁኑ የክርስቶስ አገልግሎት፥ እግዚአብሔር የሚያከናውነውን፥ ማለት የክርስቶስን አካል (ቤተ ክርስቲያንን) ለመመሥረት ሰዎችን መጥራቱን ማረጋገጫ ቁልፍ ነው ለማለት ይቻላል። እግዚአብሔር እነዚህ እስከ ምድር ዳርቻ የክርስቶስ ምስክሮች ይሆኑ ዘንድ ኃይል ይሞላቸዋል፥ ይቀድሳቸዋል። የአሁኑ ሥራው ከዳግም ምጽአቱ ጋር ከተያያዙት ሥራዎች ቀዳሚው ነው።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

12
ትምህርት 12 ከ52

እግዚአብሔር ወልድ፡- ለቅዱሳኑ መምጣቱ

ሀ. ያልተፈጸመ ትንቢት 

በዚህ ምዕራፍ የተመረጠው አስተምህሮ እጅግ ጠቃሚ ከሆኑት ያልተፈጸመ ትንቢት ጉዳዮች አንዱ ነው። የዚህ ጽሑፍ አንባቢ ሊረዳው የሚገባ ነገር፥ ትንቢት እግዚአብሔር አስቀድሞ የተናገረውና በጽሑፍ የሰፈረ ታሪክ መሆኑን ነው። ስለዚህ እንደ ማንኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይታመናል። መጽሐፍ ቅዱስ ሲጻፍ አንድ አራተኛ የሚሆነው ከፍሉ በትንቢት መልክ ነበር። ብዙው ትንቢት ተፈጽሟል፥ እያንዳንዱ ፍጻሜ ልክ በትንቢት እንደተነገረው ነው። ከልደቱ ብዙ ዓመታት በፊት እንደተተነበየው ክርስቶስ የመጣው ከይሁዳ ነገድ፡ከአብርሃም ልጅ፥ ከዳዊት ልጅ፥ ቤተልሔም ውስጥ ከአንዲት ድንግል በመወሰድ ነበር። በተመሳሳይ ሁኔታ፥ የአሟሟቱ ዝርዝር መዝሙረ ዳዊት ውስጥ ከሺህ ዓመታት በፊት በተተነበየው መሠረት በትክክል ተፈጽሟል። 

የእግዚአብሔር ቃል በአሁኑ ጊዜ ያልተፈጸሙ ብዙ ትንቢቶች አሉት። ስለሆነም ትንቢቶቹ በአሁኑ ጊዜ እንዳሉት እንደ ሌሎቹ የእግዚአብሔር ሥራዎች ሁሉ ያለጥርጥር እንደሚፈጸሙ ማመኑ ተገቢና እግዚአብሔርንም በእምነት ማክበር ነው። 

ኢየሱስ ክርስቶስ ልክ ወደ ሰማይ በሄደበት አኳኋን፥ “ይህ…ኢየሱስ” በዕረገበት አካሉና በደመናት ታጅቦ (ሐዋ. 1፡11) የሚመለስ መሆኑ በትንቢት ቃሎች በሚገባና በስፋት ተገልጧል። በታላላቅ የክርስትና እምነት መግለጫዎች ውስጥም ታክሏል። ይህ እውን ቢሆንም፥ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት አስተምህሮ ልዩ ጥንቃቄ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። 

ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ትንቢትን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ጋር በተዛመደ አኳኋን ሲመለከቱ፥ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያኑ መምጣቱን (የአማኞች ወደ ሰማይ መነጠቅ) እና ግልጥ ከሆነው ዳግም ምጽአት (መንግሥቱን ለመመሥረት እና ለሺህ ዓመታት ለመግዛት ከቅዱሳኑ ጋር ከመምጣቱ) ይለያዩታል። በነዚህ ሁለት ክንውኖች መካከል ብዙ ዋና ዋና ክስተቶች ይታያሉ፤ የዓለም አቀፊቱ ቤተ ክርስቲያን ብቅ ማለት፥ በአምባገነን መሪ የሚተዳደር ዓለም አቀፍ መንግሥት መመሥረት፥ እና እጅግ አሠቃቂ ጦርነቶች መቀስቀሳቸው የሚጠቀሱ ናቸው። እርሱ መንግሥቱን ሊያቆም እስኪመጣ ጦርነቶቹ ይካሄዳሉ። ትንቢቶች ቃል በቃል ከተተረጎሙ የሚኖረው ቅደም ተከተል በመጀመሪያ ከርስቶስ ለቤተ ክርስቲያኑ የመምጣቱ ክንውን ነው። 

ምንም እንኳን ከቤተ ክርስቲያን መነጠቅ በኋላ የፍጻሜው ዘመን ክንውኖች በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ትንቢቶች ቢጠቀሱ፥ ክርስቶስ መጀመሪያ ለቤተ ክርስቲያኑ የመምጣቱ እውነት መጀመሪያ ብሉይ ኪዳን ውስጥ አልተገለጠም፤ የአዲስ ኪዳን ትንቢት ነው፡፡

ለ. ስለ መነጠቅ የተነገሩ ትንቢቶች 

ክርስቶስ ከፍጻሜው ዘመን ክንውኖች በፊት ለቅዱሳኑ የመምጣቱን መገለጥ፥ በመሰቀሉ ዕለት ዋዜማ በላይኛው ክፍል ውስጥ ለደቀ መዛሙርቱ ነግሯቸዋል። ዮሐንስ 14:2-3 ውስጥ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሏቸዋል፡- “በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ፤ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ”። 

ደቀ መዛሙርቱ ያን ትንቢት ለመስማት ፈጽሞ የተዘጋጁ አልነበሩም። ማቴዎስ 24፡26-31 ውስጥ ክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ዳግም በክብር ስለመምጣቱ ተነግሯቸዋል። እስከዚያች ሰዓት ድረስ ከርስቶስ መጀመሪያ ወደ ሰማይ እንደሚወስዳቸውና በመጨረሻው ዘመን ከሚፈጸሙ ክፉ ነገሮች እንደሚጠብቃቸው ደቀ መዛሙርቱ አልተገነዘቡም ነበር። ዮሐንስ 14 ውስጥ እንደተጠቀሰው ክርስቶስ ስፍራ ሊያዘጋጅላቸው የሚሄድበት የአብ መኖሪያ በሰማይ መሆኑ ግልጥ ነው። ስፍራ ካዘጋጀ በኋላ ሊወስዳቸው እንደሚመለስ ተስፋ ሰጥቷቸዋል። ዓላማው ደቀ መዛሙርቱን ከምድር ወደ አባቱ ቤት መውሰድ ነው። ይህን ተስፋ ሐዋርያው ጳውሎስ በዝርዝር ገልጿል። 

ጳውሎስ በቅዱሳን ትንሣኤና ክርስቶስ በምድር ላሉት ቅዱሳን በመምጣቱ መካከል ስላለው ጉዳይ የተሰሎንቄ ሰዎች ለነበራቸው ጥያቄ መልስ ሲጽፍ የዚህን ታላቅ ክንውን ዝርዝር ገልጧል (1ኛ ተሰ. 4፡13-18)። ከ16-17 ባሉት ቁጥሮች እንዲህ ብሏል፡- “በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፥ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን”። 

የክርስቶስ ለቅዱሳኑ መምጣት ሁኔታዎች ቅደም ተከተል የሚጀምረው ክርስቶስ ከዙፋኑ ተነሥቶ ከምድር በላይ ወዳለው አየር ሲወርድ ነው። ሲመጣ ድምፅ ይሰጣል። ያም ድምፅ የትእዛዝ ድምፅ” ነው። ይህ ሁኔታ በመላእክት አለቃ ሰሚካኤል የድል ድምፅና የእግዚአብሔር መለኮት ይታጀባል። ሙታን ክርስቲያኖች የክርስቶስን ድምፅ በመታዘዝ ( ዮሐ. 5፡28-29) ከመቃብር ይነሣሉ። ሰiኛ ተሰሎንቄ 4፡14 ላይ እንደተጠቀሰው የሙታኑ ነፍሳት ክርስቶስን ያጅቡታል። ምክንያቱም ቃሉ እንዲሁም በኢየሱስ ያንቀላፉትን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋል” ይላልና። እነዚህ ነፍሳት ጌታን አጅበው ከመጡ በኋላ መቃብር ውስጥ ከነበረውና ከሚያርገው አካላቸው ጋር ይገናኛሉ። በክርስቶስ ያንቀላፉት (የሞቱት) ከተነሣ በኋላ፥ በሕይወት ያሉት ክርስቲያኖች “ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና ይነጠቃሉ”። በዚህ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያን ከምድር ትወሰድና፥ በአብ ዘንድ በመኖር ዮሐንስ 14 ውስጥ የተጠቀሰውን ተስፋ ትፈጽማለች። 

ተጨማሪ ዝርዝር 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡51-58 ውስጥ ተሰጥቷል። ጌታ ለቤተ ክርስቲያኑ የሚመጣበት ሁኔታም “ምስጢር” ተብሏል። ይህ ማለት፥ እውነታው በብሉይ የተሸሽገና በአዲስ ኪዳን የተገለጠ ነው ለማለት ነው (ሮሜ 16፡25-26፤ ቈላ. 1፡26)። ክርስቶስ መንግሥቱን በምድር ለመመሥረት የመምጣቱ እውነት በብሉይ ኪዳን የተገለጠ ሲሆን፥ ንጥቀት ግን በአዲስ ኪዳን ብቻ ነው የተገለጠው። ጳውሎስ 1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 15 ውስጥ ክንውኑ ወዲያውኑ “ሰቅፅበተ ዓይን” እንደሚሆን ገልጧል። የሙታኑ አካል የማይበሰብስ፥ የማያረጅና የማይሞት ይሆናል (1ኛ ቆሮ. 15፡53)። 

አዲሱ አካላችን ኃጢአት አልባ እንደሚሆን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ያስረዳል (ኤፌ. 5፡27፤ ፈልጵ. 3፡20-21)። በመቃብርም ሆነ በሕይወት ያሉት አካላት ለመንግሥተ ሰማያት የሚስማሙ አይደሉም። ለዚህ ነው ጳውሎስ “እኛ ሁላችንም እንለወጣለን” (1ኛ ቆሮ. 15፡51) ያለው። ከቤተ ክርስቲያን (አማኞች) ትንሣኤና መነጠቅ ጋር ሲነጻጸር፥ ከጰንጠቆስጤ ዕለት በፊት የሞቱ፥ ወይም ከመነጠቅ ክንውን በኋላ የሚሞቱ ቅዱሳን ትንሣኤና ንጥቀት ክርስቶስ መንግሥቱን ሊመሠርት እስኪመባ ይዘገያል (ዳን. 12፡1-2፤ ራእይ 20፡4)። ኃጢአተኞች ግን እስከ ክርስቶስ የሺህ ዓመታት አገዛዝ ፍጻሜ ድረስ አይነሡም (ራእይ 20፡5-6፥ 12-13)። 

ሐ. ክርስቶስ ለቅዱሳኑ መምጣቱ እና ከቅዱሳኑ ጋር መምጣቱ ሲነጻጸሩ። 

መነጠቁ የሚከናወነው ከፍጻሜው ጊዜ ቀድሞ ነው የሚለው አስተምህሮ፥ ቅድመ ፍዳ አመለካከት ይባላል። ከዚህ ጋር የሚነጻጸረው ሌላ አመለካከት ደግሞ ድኅረ ፍዳ ዘመን የተሰኘው ሲሆን፥ የክርስቶስን ለቅዱሳኑና ከቅዱሳኑ ጋር መምጣት እንደ አንድ ክንውን የሚያይ ነው። ከነዚህ ሁለት አመለካከቶች የቱ ነው ትክክል ለሚለው ጥያቄ መልስ የሚሆነው፥ ትንቢትን በትክክል የመተርጎሙ ውጤት ይሆናል። 

በሁለቱ ክንውኖች መካከል አንዳንድ ልዩነቶች ይታያሉ። 

1, ክርስቶስ ቅዱሳኑን በሰማይ ወዳለ አባቱ ቤት ለመውሰድ የመምጣቱ ሂደት፥ ከምድር ወደ ሰማይ የሚደረግ እንቅስቃሴ ሲሆን፥ ከቅዱሳኑ ጋር የመምጣቱ ክንውን ግን ከሰማይ ወደ ምድር የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው። ይህም ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተገልጦ መንግሥቱን የሚመሠርትበት ጊዜ ይሆናል። 

2. በሕይወት ያሉ ቅዱሳን በሙሉ በመነጠቅ ጊዜ ቀሚለወጡ ሲሆን፥ ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት ጋር በተያያዘ ሁኔታ ግን ቅዱሳን አይለወጡም። 

3. በመነጠቅ ጊዜ ቅዱሳን ወደ ሰማይ የሚሄዱ ሲሆን፥ በዳግም ምጽአቱ ግን ሳይለወጡ በምድር ላይ ይኖራሉ። 

4. በመነጠቅ ጊዜ ዓለም የማይለወጥና የማይፈረድበት ሆኖ በኃጢአቱ ይቀጥላል፥ በዳግም ምጽአት ግን ይፈረድበታል፥ ጽድቅም በምድር ላይ ይመሠረታል። 

5. ቤተ ክርስቲያን የምትጠቀሙ ከሚመጣው የቁጣ ቀን ለመሳኝ ሲሆን፥ ዳግም ምጽአቱ ግን በክርስቶስ በማመን በመከራው ጊዜ ሁሉ ታግሠው የቆዩትን ለማዳን ነው። 

6. መነጠቅ ሳይታሰብና በቅፅበት ሊሆን እንደሚችል የተገለጠ ሲግ፥ ዳግም ምጽአቱ ግን ብዙ ምልክቶችና ድርጊቶችን ተከትሎ የሚፈጸም ይሆናል። 

7. መነጠቅ በአዲስ ኪዳን ብቻ የተገለጠ እውነት ሲሆን፥ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ግን በቅድሚያ ሊከናወኑ ካሉ ምልክቶችና ሁኔታዎች ጋር በብሉይም በአዲስም የተጠቀሰ እውነት ነው። 

8. መነጠቅ የዳኑትን ብቻ የሚመለከት ሲሆን፥ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ግን ሁለቱንም ማለት የዳኑትንና ያልዳኑትን ይመለከታል። 

9. በመነጠቀ ጊዜ ሰይጣን ስለማይታሰር በቀጣዮቹ ጊዜያት ከበፊቱ ይልቅ ይበረታል። በዳግም ምጽእት ግን ይታሰራል። ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርግ ይጠበቃል፥ ይከለከላል። 

10. መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ስተመሠረተችበት ወቅትና ስመነጠቋ መካከል ይህ እንዲከናወን የግድ መፈጸም ያለበት ትንቢት የለም። ንጥቀት ቅፅበታዊ ነገር ነው። ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት ቀደም ብሎ ግን መፈጸም የሚገባቸው ብዙ ምልክቶች አሉ። 

11. ክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ወደ ምድር በሚመጣበትና ከቅዱሳን መነጠቅ ጋር በተያያዘ ሁኔታ፥ የሕያዋን ቅዱሳን በዚያው ጊዜ መለውጥ በብሉይም ሆን በአዲስ ኪዳን አልተጠቀሰም። እንደውም ሕያው ቅዱሳን በሺሁ ዓመት መንግሥት ውስጥ ለማገልገል በተፈጥሮ አካላቸው መኖር ስላለባቸው ይህ ዓይነቱ አስተምህሮ የማይሆን ነገር ነው። 

12. የክርስቶስን ወደ ምድር መምሰስ በሚገልጠው ቅደም ተከተል ውስጥ ንጥቀትን የሚመስል ሌላ ክንውን የለም። በማቴዎስ 25፡31-46 መሠረት ከክርስቶስ መመለስ ቀጥሎ በመጣው የፍርድ ወቅት እማኞችና የማያምኑ ሰዎች ተደባልቀዋል። በመሆኑም ክርስቶስ ወደ ምድር በሚመለስበት ወቅት የዳኑትን ካልዳኑት የሚለይ መነጠቅ፥ ወይም ሌላ መለያ አልተከናወነም። 

13. ክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት መምጣኝ፥ እንዲሁም ከዚያ ቀድመውና ተከትለው የሚከናወኑ ነገሮችን የሚገልጠውን አስተምህሮ ማጥናት፥ ክንውኖቹ ቤተ ክርስቲያንን ሳይሆን እስራኤልንና፥ ያመኑ አሕዛብን እንዲሁም ያላመኑ አሕዛብን የሚመለከቱ መሆናቸውን በግልጥ ለመገንዘብ ይረዳል። ይህ ጉዳይ በሚቀጥለው ምዕራፍ ይገለጣል። 

የኢየሱስ ክርስቶስ ባልተጠበቀ ጊዜ ወይም ድንገት ለቤተ ክርስቲያኑ መምጣት ነቅተን እንድንኖር የሚያደርገን እውነት ነው። የተሰሎንቄ ክርስቲያኖች 1ኛ ተሰሎንቄ 1 ፡10 ውስጥ “ከሙታን ያስነሣውን ልጁን እርሱንም ኢየሱስን ከሚመጣው ቁጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ” ተብሎ ተነግሯቸዋል። ተስፋቸው በፍዳው ውስጥ ማለፋቸው ሳይሆን፥ በምድር ላይ ሊዘንብ ካለው የእግዚአብሔር ቁጣ መዳን ነው (1ኛ ተሰ. 5፡9፤ ራእይ 6፡17)። እዲስ ኪዳን ውስጥ እንደተገለጠው፥ መነጠቅ አጽናኝ ተስፋ ዮሐ. 14፡1-3፤ 1ኛ ተሰ. 4፡18)፥ የሚያነጻ ተስፋ (1ኛ ዮሐ. 3፡1 -3) እና የተሳረከ ወይም የደስታ ተስፋ (ቲቶ 2፡13) ነው። ክርስቶስ መንግሥቱን ምድር ላይ ለመመሥረት እስከሚመጣ ድረስ ዓለም አያየውም፤ ክርስቲያኖች ግን በመነጠቅ ጊዜ በክብሩ ያዩታል። ያም ጊዜ “የታላቁን አምላካችንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ” የሚመለከቱበት ይሆናል (ቲቶ 2: 13)።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

13
ትምህርት 13 ከ52

እግዚአብሔር ወልድ፡- ከቅዱሳኑ ጋር ስለ መምጣቱ

በዚህ ምዕራፍ፥ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ጋር እና ለቅዱሳኑ መምጣቱን የሚያመለክተው ትምህርት ለአንዳንዶች ግር ይላቸዋል፥ ስለዚህ ልዩነታቸውን ለማጤን ሁለቱን ክንውኖች በጣምራ ማጥናቱ ተጎቢ ይሆናል። 

ሀ. ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት የሚቀድሙ ዓበይት ሁኔታዎች 

ኋላ ከመጨረሻው ዘመን ትንቢት ጋር በተያያዘ መልኩ በምናደርገው ጥናት እንደምናገኘው፥ ቤተ ክርስቲያን መነጠቅና በክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ዳግም መምጣት መካከል ያለው ጊዜ ግልጥ በሆኑ ሦስት ወቅቶች ተከፋፍሏል። 

1. ዮዝግጅቱ ወቅት ክቅዱሳን መነጠቅ ቀጥሎ የሚመጣ ሲሆን፥ ያን ጊዜ ስምታንሠራራው ጥንታዊት የሮም መንግሥት ሥር አሥር መንግሥታት በኮንፌዴሬሽን አስተዳደር ይጠቃለላሉ። ከዚህ አስተዳደር ውስጥ መጀመሪያ ሦስቱን፥ ቍጥሉ ደግሞ አሥሩንም መንግሥታት የሚገዛ አምባገነን መሪ ይነሣል። 

2. ይህ መሪ ከእስራኤል ጋር በሚያደርገው የሰባት ዓመት ቃል ኪዳን መሠረት በሜዲትራንያን ባሕር አካባቢ የሠላም ጊዜ ይሆናል(ዳን. 9:27)። 

3. ቃል ኪዳን ከተደረገ ሦስት ዓመት ተኩል በኋላ እምባገነኑ መሪ ቃሉን ስለሚያፈርስ፥ በእስራኤልና በክርስቶስ በሚያምኑ ሁሉ ሳይ ስደት ይነሣል። ይህ መሪ የዓለም አምባገነን መሪ ይሆናል፥ ስግደት ለርሱ ብቻ እንዲሆን ከመሻቱ የተነሣ የዓለም ሃይማኖቶችን ሁሉ ያጠፋል። ከርሱ ፈቃድ በቀር መገብየት እንዳይኖርና፥ ያለርሱ ፈቃድ መሸጥ ወይም መግዛት እንዳይቻል ለማድረግ በዓለም ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ ሁሉ ይቆጣጠራል። 

ይህ የሦስት ዓመት ተኩል ጊዜ ታላቁ ፍዳ ይባላል (ዳን. 12፡1፤ ማቴ. 24፡21 ፤ ራእይ 7፡14)። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ታላቅ ፍርድ ይወርዳል (ራእይ 6፡1-18፥ 24)። ታላቁ ፍዳ ወደ ታላቅ የዓለም ጦርነት ይሸጋገራል (ራእይ 16፡14-16)። ጦርነቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በሚደርስበት ጊዜ፥ ክርስቶስ ሰማዕት ያልሆኑ ቅዱሳንን ለመታደግ፥ በምድር ላይ ሊፈርድና የጽድቅ መንግሥቱን ሊመሠርት ይመጣል። ከብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ለመረዳት እንደሚቻለው፥ ይህ ታላቅ፥ የሁከት ሁኔታ ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት ይቀድማል። እነዚህ ክንውኖች ሳይፈጸሙ የክርስቶስን ዳግም ምጽአት ይሆናል ብሎ መጠባበቅ አይቻልም። 

ለ. ከዳግም ምጽአቱ ጋር የሚዛመዱ ወሳኝ እውነታዎች 

1. ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር ቀሚመለስ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል (ዘካ. 14፡4)፤ በእካል (ማቴ. 25፡31፤ ራእይ 19፡11-16)፤ በደመና እንደሚመለስ (ማቴ. 24፡30፤ ሐዋ. 1፡11፤ ራእይ 1፡7)። ስለዚህ የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሁሉ እንደሚገልጡት ይህ ሁኔታ ዓለም ሁሉ የሚያየውና የከበረ ዕለት ነው (ራእይ 1፡7)። 

2. በኢየሱስ ክርስቶስ በራሱ እንደተገለጠውና ማቴዎስ 24፡26-29 ውስጥ እንደተመዘገበው፥ የርሱ መገለጥ የመብረቅ ብርሃን ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ ይሆናል። ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት ከዚያች ወራትም መከራ በመባል በሚታወቁት ጊዜያት፥ በሰማይ ሁከት ይሆናል፥ ፀሐይ ትጨልማለች፥ ጨረቃ ብርሃን አትሰጥም፥ ከዋክብት ከሰማያት ይወድቃሉ፥ ሰማያት ራሳቸው ይናወጣሉ። ራእይ 6፡12-17፤ 16፡1-21 ውስጥ ሁኔታው በበለጠ ዝርዝር ተብራርቷል። የክርስቶስ ዳግም ምጽአት በምድር በሚኖሩ ሁሉ የሚታይ ይሆናል (ማቴ. 24፡30፤ ራእይ 1፡7)። “የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፡” (ማቴ. 24፡30)። ምክንያቱም ብዙዎቹ ፍርድ የሚጠብቃቸው በዚህ ጌታ ያላመኑ ሕዝብ ናቸው። 

3. ክርስቶስ በዳግም ምጽአቱ ወቅት በቅዱሳንና በመላእክት በድምቀት ይታጀባል። ሁኔታው ራእይ 19፡11-16 ውስጥ በዝርዝር ተገልጧል። ዮሐንስ እንዲህ ነው የጻፈው:- “ 

ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም አምባላይ ፈረስ፥ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም። ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፤ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፤ ከእርሱ በስተቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤ በደምም የተረጨ ልብስ ተጎናጽፏል፤ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሏል። በሰማይም ያሉ ጭፍሮች ነጭና ጥሩ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ለብሰው በአምባላዮች ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር። አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሠይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም ሰብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔር የብርቱ ቁጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል። በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ የሚል ስም አለው”። 

የክርስቶስ በቅዱሳን ሁሉና በመላእክት የታጀበ መሆኑ፥ ሂደቱን ዝግ ያለና ብዙ ሰዓት የሚወስድ መሆኑን ያመለክታል። በዚህ ጊዜ ዓለም ሁሉ ክንውኑን ያይ ዘንድ መሬት ትሽከረከራለች። የዳግም ምጽአቱ ክንውን ክርስቶስ ወደ ሰማይ በዐረገበት በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ያበቃል (ዘካ. 14፡1-4፤ ሐዋ. 1፡9-12)። በዚያን ጊዜ የክርስቶስ እግሮች ደብረ ዘይት ተራራ ላይ ያርፋሉ፤ ተራራውም ሁለት ላይ ደካፈልና ከኢየሩሳሌም ወደ ምሥራቅ እስከ ዮርዳኖስ የሚዘልቅ ሸለቆ ይፈጠራል። 

4. ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ በመጀመሪያ በጦርነቱ የተሳተፈውን የዓለም ጦር ሥራት ይቀጣል (ራእይ 19፡15-21)። መንግሥቱንም እንደመሠረተ እስራኤልን ሰብስቦ ወደ ሺህ ዓመቱ መንግሥት ለመግባት ካላቸው ብቃት አንጻር ይፈርድባቸዋል (ሕዝ. 20፡34-38)። በተመሳሳይ ሁኔታ ‘አሕዛብን” ሰብስቦ ይፈርድባቸዋል (ማቴ. 25፡31-46)። ከዚህ ሁሉ በኋላ የጽድቅና የሰላም መንግሥቱን ምድር ላይ ይመሠርታል። ሰይጣን ይታሰርና ግልጥ የሆኑ ዓመፃዎች ሁሉ ፍርዳቸውን ያገኛሉ። ይህን አሳብ በሚቀጥሉት ምዕራፎች ላይ በስፋት እንመለከታለን። 

ሐ. ዳግም ምጽአቱ ከመነጠቅ ጋር ሲነጻጸር 

ባለፈው ምዕራፍ እንደታየው በክርስቶስ ለቅዱሳኑ መምጣትና፥ በቅዱሳኑ ታጅቦ መምጣት መካከል ብዙ ማነጻጸሪያዎች አሉ። ሁለቱን ክንውኖች፥ ማለት የክርስቶስን ለቅዱሳኑ መምጣትና ከቅዱሳኑ ጋር መምጣትን በዚህ አኳኋን ለመለየት ይቻል ይሆናል። ልዩነታቸውን በደንብ ለመገንዘብ የክርስቶስን ለቅዱሳኑ መምጣትና ከቅዱሳን ጋር መመለሱን በተመለከተ ከዚህ በታች ያለውን ሠንጠረዥ ይመልከቱ። 

ለቅዱሳን መምጣቱ 

(1) “በአንድነት ወደ እርሱ መሰብሰባችን”። 

(2) እንደ ንጋት ኮከብ” ይመጣል (ራእይ 2፡28፤ 22 ፡16፤ 2ኛ ጴጥ. 1፡19)፡፡

(3) “የክርስቶስ ቀን” (1ኛ ቆሮ. 1፡8፤ 2ኛ ቆሮ. 1፡14፤ ፊልጵ. 1፡6፤ 10፤ 2፡16)፡፡

(4) ያላ ምልክት እንደ ሌባ በድንገት የሚመጣ ቀን ነው። 

(5) ድንገተኛ፥ በማንኛውም ጊዜ ሊሆን የሚችል፡፡

(6) ስለ ኃጢአት አልተጠቀሰም፡፡

(7) እስራኤል አትለወጥም፡፡

(8) ቤተ ክርስቲያን ከምድር ትወሰዳለች፡፡

(9) መንግሥታት አይለወጡም

(10) ፍጥረት አይለወጥም፡፡

(11) አስቀድሞ ያልተገለጠ “ምስጢር”፡፡

(12) ተስፋ ክርስቶስ ላይ ብቻ ይሆናል “ጌታ በደጅ ነው” (ፊልጵ 4፡5)፡፡

(13) ክርስቶስ እንደሙሽራ፣ እንደጌታ እና የቤተ ክርስቲያን ራስ ይገለጣል (ኤፌ 5፡25-27፤ ቲቶ 2፡13)፡፡

(14) አመጣጡን አለም አያየውም

(15) ክርስቲያኖች ሊሸለሙ ካለው ነገር አንጻር ለብያኔ ይቀርባሉ፡፡

ከቅዱሳን ጋር መምጣቱ 

(1) “የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት” (2ኛ 1 ተሰ. 2፡1)።

(2) እንደ “ጽድቅ ፀሐይ” (ሚል. 4፡2)። 

3) “የጌታ ቀን” (2ኛ ጴጥ. 3፡10)። 

(4) መቃረቡ ይታያል (1ኛ ተሰ. 5፡4፤ ዕብ. 10፡25)። 

(5) ስለ ቀኑ የተነገረው ትንቢት አስቀድሞ ይፈጸማል (2ኛ ተሰ 22፡23)፡፡

(6) ኃጢአት ይጠፋል፥ ሰይጣን ይፈረድበታል፥ የኃጢአት ሰው ይደመሰሳል (2ኛ ተሰ. 2፡8፤ ራእይ 19፡20፤ 20፡1-4)። ሊሆን የሚችል። 

(7) ቃል ኪዳኗ ሁሉ ይፈጸማል (ኤር. 23፡5 -8፤ 30፡3-11፤ 31፡27-37)። 

(8) ከክርስቶስ ጋር ትመለሳለች (1ኛ ተሰ. 4፡17፤ ይሁዳ 14-15፤ ራእይ 19፡14)። 

(9) መንግሥታት ይፈርድባቸዋል (ማቴ. 25፡31-46)።  

(10) ፍጥረት ከክፉ እሥራት ነጻ ይወጣል (ኢሳ. 35፤ 65፡17-25)። 

(11) በብሉይና በአዲስ ኪዳን በአጠቃላይ ታይቷል (ዳን. 7፡13-14፤ ማቴ. 24፡27-30፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡51-52)። 

12) መንግሥቱ ትመጣለች (ማቴ. 6፡10)። 

(13) ክርስቶስ እንደ ንጉሥ፥ መሢሕ እና የእስራኤል መድኅን ይገለጣል (ኢሳ. 7፡14፤ 9፡6-7፤ 11፡1-2)፡፡

(14) በታላቅ ሥልጣንና ክብር ይመጣል (ማቴ. 24፡27፥ 30፤ ራእይ 1፡7)። 

(15) ነገሥታት ለርሱ ከሰጡት ምላሽ አንጻር ይበየንባቸዋል (2ኛ ቆሮ. 5፡10-11፤ ማቴ. 25፡31-46)። 

ጠቃሚ ጥቅሶች 

ዮሐ. 14፡1-3፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡51-52፤ 1ኛ ተሰ. 4፡13-18፤ ፊሊጵ 3፡20-21፤ 2ቆሮ 5፡10፤ 

ዘዳ. 30፡1-10፤ መዝ. 72፤ የነቢያትን ትንቢቶች በሙሉ ያስተውሉ (ማቴ. 25፡1-46፤ ሐዋ. 1፡11፤ 115፡13-18፤ 2ኛ ተሰ 22፡112፤ 2ኛ ጴጥ. 2፡1-3፡8፤ ራእይ. 19፡11-20፡6)።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

14
ትምህርት 14 ከ52

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- አካልነቱ

ሀ. የአካልነቱ አስፈላጊነት 

መንፈስ ቅዱስን በተመለከተ ሰሚሰጥ ትምህርት ውስጥ እበይት ከሆኑት እውነቶች መካከል በማንነቱ ሳይ ልዩ ትኩረት ሊደረግ ይገባል። ይህ የሚያስፈልግበት ምክንያት በአሁኑ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ የሚሰማውን እንጂ (ዮሐ. 16፡13፤ ሐዋ. 13፡2) ከራሱ ወይም ስለ ራሱ የማይናገር መሆኑና ወደ ዓለም የመጣውም ክርስቶስን ሊያከብር በመሆኑ ነው (ዮሐ. 16፡14)። ከዚህ ጋር ሲነጻጸር አብም ሆነ ወልድ ከራሳቸው እንደሚናገሩ አድርጎ ነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚያቀርበው። ይህ ሲሆን አብና ወልድን የሚያቀርባቸው በልዑላዊ ሥልጣንና እኔ በሚለው ተውላጠ ስም ብቻ ሳይሆን፥ እርስ በርሳቸው ቀጥተኛ መስተጋብር፥ ኅብረትና መስማማት እንዳላቸው በማረጋገጥ ነው። ከራሱና ስለ ራሱ አለመናገሩ ስለ መንፈስ ቅዱስ ማንነት ያላን መረዳት ውሱን ያደርገዋል። በዚሁ መሠረት በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የመንፈስ ቅዱስ አካልነት ለብዙ መቶ ዓመታት እንደቀላል ነገር የታየ ጉዳይ ነበር። በ325 ዓ.ም. በኒቅያ የእምነት መግለጫ አብና ወልድ በዝርዝር በተገለጡ ጊዜ ነው መንፈስ ቅዱስም እንደ አካል እውቅና ያገኘው። 

በትክክለኛው አስተምህሮ በኋላ እንደተገለጠው፥ መጽሐፍ ቅዱሳዊው እውነት እግዚእብሔር በሦስት አካል ይገለጣል የሚል ነው። ይሄውም አብ፥ ወልድ፥ መንፈስ ቅዱስ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ተቀባይነት አግኝቷል። መንፈስ ቅዱስ እንደ አብና እንደወልድ አካል መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ያስተምራል። ከዚህ የሥላሴ አስተምህሮ ጥናት የምንረዳው፥ ሦስቱ አካላት አንድ አምላክ እንጂ ሦስት አማልክት አለመሆናቸውን ነው። 

ለ. ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የተገለጠው የመንፈስ ቅዱስ አካልነት 

1. መንፈስ ቅዱስ አካል ያለው ብቻ ሊሠራ የሚችለውን እንደሚሠራ ተገልጿል። 

(ሀ) ዓለምን ይወቅሳል፡- “እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት፥ ስለ ጽድቅም፥ ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል” (ዮሐ. 16፡8)። 

(ለ) ያስተምራል፡- “እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል” (ዮሐ. 14፡26፤ ህ. 9፡20፤ ዮሐ. 16፡13-15፤ 1ኛ ዮሐ. 2፡27)። 

(ሐ) ይናገራል፡- “ልጆችም ስለሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሉ የሚጮህ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ” (ገላ. 4፡6)። 

(መ) ይማልዳል፡- “ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል” (ሮሜ 8፣ 26)። 

(ሠ) ይመራል፡- “በመንፈስ ብትመሩ” (ገላ. 5፡18፤ ሐዋ. 8፡29፤ 10፡19፤ 13፡2፤ 16፡6-7፤ 20፡23፤ ሮሜ 8፡14)። 

(ረ) ምዕመናንን ለአገልግሎት ይሾማል፡- “መንፈስ ቅዱስ በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ” (ሐዋ. 13፡2፤ 20፡28)። 

(ሰ) መንፈስ ቅዱስ ራሱ ለአገልግሎት ይላካል፡(ዮሐ. 15፡26)። 

ሸ መንፈስ ቅዱስ ያገለግላል፥ ዳግም ልደትንም ይሰጣል፡- (ዮሐ. 3፡6)፤ ያትማል (ኤፌ. 4፡30)፤ ያጠምቃል (1ኛ ቆሮ. 12፡13)፤ ይሞላል (ኤፌ. 5 ፡18)። 

2. እካል እንደመሆኑ መጠን በሌሉች ተጽዕኖ ይነካል። 

(ሀ) አብ ወደ ዓለም ይልከዋል (ዮሐ. 14፡16፥ 26)። ወልድም ይልከዋል (ዮሐ. 16፡7)። 

(ለ) ሰዎች ያስቆጡታል (ኢሳ. 63፡10)፥ ያሳዝኑታል (ኤፌ. 4፡30)፥ ያጠፉታል (ማዳፈን)፥ (1ኛ ተሰ. 5፡19)፥ ይሰድቡታል (ማቴ. 12፡31)፥ ይዋሹታል (ሐዋ. 5፡3)፥ ያክፋፉታል (ዕብ. 10፡29)፥ ቃል ይናገሩበታል (ማቴ. 12፡32)። 

3. መንፈስ ቅዱስን በተመለከተ መጽሐፉ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ አባባሎች ሁሉ አካልነቱን ያመለክታሉ። 

(ሀ) “ሌላው አጽናኝ” ተብሏል። ይህም የክርስቶስን ያህል አካልነት ያለው መሆኑን ያመለክታል (ዮሐ. 14፡16-17፥ 26፤ 16፡7፤ 1ኛ ዮሐ. 2፡1-2)። 

(ለ) እግዚአብሔር መንፈስ እንደተባለ፥ መንፈስ ቅዱስም እንደአካል በዚሁ ስም ተጠርቷል (ዮሐ. 4፡24)። 

(ሐ) ለመንፈስ ቅዱስ መጠሪያነት ያገለገሉ ተውላጠ ስሞች አካልነቱን ያመለክታሉ። በግሪክ “መንፈስ” የሚለው ቃል ጾታ የማይለይ ስም ሲሆን፥ በጾታ ለማይለይ አካል መጥሪያነት ያገለግላል። ይህ ጾታ የማይለይ ተውላጠ ስም በአንዳንድ ሁኔታዎች ተጠቅሷል (ሮሜ 8፡16፥ 26)። ብዙ ጊዜ ግን የተባዕታይ ጾታ ተውላጠ ስም የመንፈስ ቅዱስን አካልነት በሚገልጥ መልኩ አገልግሏል (ዮሐ. 14፡16-17፤ 16፡7-15)። 

ሐ. መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር አካል እንደመሆኑ ከአብና ከወልድ ጋር እኩል ነው 

1 እግዚአብሔር ተብሎ ይጠራል። ኢሳይያስ 6፡8-9 ውስጥ ያለውን ክፍል ከሐዋርያት ሥራ 28፡25-26፥ ኤርምያስ 31፡31-34ን ከዕብራውያን 10፡15-17 ጋር በማነጻጸር ይህን እውነት ለመረዳት ይቻላል። (2ኛ ቆሮ. 3፡18 እና ሐዋ. 5፡3-4 ውስጥ ይህን ቃል ልብ ይበሉ፡- “መንፈስ ቅዱስን ታታልልና ከመሬቱም ሽያጭ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን በልብህ ሰለምን ሞላ? እግዚአብሔር እንጂ ሰውን አልዋሸህም።” ምንም እንኳን መንፈስ ቅዱስን ባታልሉት ላይ እግዚአብሔር ጠበቅ ያለ ፍርዱን ቢያወርድባቸውም (ሐዋ. 5፡3)፥ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዳይምሉ ቢከለከሉና መንፈስ ቅዱስ በመባል ቢጠራም፥ ከአብና ከወልድ ይበልጥ ቅዱስ ነው ማለት አይደለም። ፍጹም ቅድስና የሥላሴ ዋና ባሕርይ ነው። 

2. መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ባሕርያት አሉት(ዘፍጥ. 1፡2፤ ኢዮብ 26፡13፤ 1ኛ ቆሮ. 2፡9-11፤ ዕብ. 9፡14)። 

3. የእግዚአብሔርን ሥራዎች ያከናውናል(ኢዮ. 33፡4፤ መዝ. 104:30፤ ሉቃስ 12፡11-12፤ ሐዋ. 1፡5፤ 20፡28፤ 1ኛ ቆሮ. 6፡11፤ 2፡8-11፤ 2ኛ ጴጥ. 1፡21)። 

4. ከላይ እንደተጠቀሰው መንፈስ ቅዱስን ለማመልከት ያገለገሉት ሰብዓዊ ተውላጠ ስምች ማንነቱን ያረጋግጣሉ። 

5. መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተጠቀሰው፥ መንፈስ ቅዱስ ሊታመንበት የሚገባ አካል ሆኖ ቀርቧል (መዝ. 51፡11፤ ማቴ. 28፡19፤ ሐዋ. 10፡19-21)። የሚታመንበት አካል እንደመሆኑ፥ ሊታዘዙትም የሚገባው ነው። በክርስቶስ ያመነ ሰው፥ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በሕብረት ስለሚጓዝ፥ ኃይሉን፥ መሪነቱን፥ ትምህርቱን፥ እና ሙሳቱን (ብቃቱን) በመለማመድ፥ የመንፈስ ቅዱስን አካልነት በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ታላቅ የአስተምህሮ እውነት ይረዳል። 

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

15
ትምህርት 15 ከ52

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- መውረዱ

የመንፈስ ቅዱስ በጳንጠቆስጤ ዕለት ወደ ዓለም መምጣት መታየት ያለበት ከዚያ ሰፊት በነበሩት ሥፍረዘመናት ከነበረው ሥራ ጋር በተያያዘ መልኩ ነው። መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ዘመን በሁሉም ስፍራ የሚገኝ አምላካዊ ባሕርይ ሆኖ በዓለም ነበር። ቢሆንም ሰጰንጠቆስጤ ዕለት ወደ ዓለም የሚመጣ መሆኑ ተነግሯል። በዘመናችንም በዓለም ይኖራል። አንድ ቀን ግን ልክ እንደ ጰንጠቆስጤ ዕለት አመጣጡ ከዓለም ይለያል። ይህ የሚሆነው በቤተ ክርስቲያን መነጠቅ ጊዜ ነው። ይህን ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚነገር እውነት ለመረዳት ይቻል ዘንድ፥ መንፈስ ቅዱስ ከዓለም ጋር ያለው ግንኙነት የተለያዩ ሁኔታዎች ሊታዩ ይገባል። 

ሀ, መንፈስ ቅዱስ ሰብሉይ ኪዳን 

ከክርስቶስ ልደት በፊት በነበረው ረጅም ዘመን መንፈስ ቅዱስ በሁሉም ስፍራ መገኘት በሆነው ሳሕርዩ በዓለም ነበር። በመለኮታዊ ፈቃዱ መሠረትም በእግዚአብሔር ሰዎች ውስጥና አማካይነት ሠርቷል (ዘፍጥ. 41፡38፤ ዘጸ. 31፡3፤ 35፡31፤ ዘኁል. 27፡18፤ ኢዮብ 33፡4፤ መዝ. 139፡7፤ ሐጌ 2፡4-5፤ ዘካ. 4፡6)። በብሉይ ኪዳን ዓለም ሲፈጠር የእግዚአብሔር መንፈስ አብሮ ፈጥሯል። ለቅዱሳንና ለነቢያት የመለኮታዊውን እውነት የመግለጥ ድርሻ ነበረው። ለተጻፉ የእግዚአብሔር ቃላት ምሪትን ሰጥቷል፥ ኃጢአትን ከዓለም በመከልከል አገልግሏል፥ አማኞች ለአገልግሎትና ታአምራትን ለመሥራት አስችሏቸዋል። እነዚህ ሁሉ ክንውኖች የሚያመላክቱት መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ዘመን በጣም ይሠራ የነበረ መሆኑን ነው። ይሁን እንጂ በዚያ ዘመን በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ስለማደሩ ምንም ማስረጃ የለም። የዮሐንስ ወንጌል 14፡17 የሚያመለክተው፥ “ከእነርሱ” በማለት ከሰዎች ጋር እንደነበር እንጂ፥ በ“ውስጣቸው” እንደነበር አይደለም። ካጰንጠቆስጤ ዕለት በፊት የመንፈስ ቅዱስ የማተም ወይም የማጥመቅ ሥራ አልተጠቀሰም። ካለፉት ዘመናት፥ ከጰንጠቆስጤ ዕለት በኋላ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ የሳቀ ነው። 

ለ. መንፈስ ቅዱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ዘመን 

ሥጋ የለበሰና የሚሠራ፥ የሥላሴ ሁለተኛ አካል በዓለም መገኘቱ፥ የመንፈስ ቅዱስን ሥራ ለየት የሚያደርገው መሆኑን መገመት ተገቢ ነው። እውነት ሆኖም እናገኘዋለን። 

1. ከክርስቶስ በተገናኘ ሁኔታ ሲታይ፥ እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ለድንግሊቱ ማኅፀን ውስጥ የተፀነሰበትን ኃይል ያመነጨው መንፈስ ቅዱስ ነበር። ክርስቶስ በሚጠመቅበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በእርግብ አምሳል ሲወርድበት ታይቷል። ክርስቶስ ራሱን ለእግዚአብሔር የሰጠው በዘላለማዊ መንፈስ ብቻ መሆኑም ተገልጧል (ዕብ. 9፡14)። 

2. ክርስቶስ ምድራዊ አገልግሎት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከሰው ጋር የነበረው ግንኙነት እየሰፋ የሚመጣ ነበር። ክርስቶስ፥ ቢጠይቁ መንፈስ ቅዱስን ሊቀበሉ እንደሚችሉ ለደቀ መዛሙርቱ መጀመሪያ አረጋገጠላቸው (ሉቃስ 11፡13)። ምንም እንኳን ቀደም ሲል መንፈስ ቅዱስ እንደ ልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ በሰዎች ላይ ቢወርድም፥ በሰዎች ልብ የመኖሩ ነገር ግን በሰዎች ጥያቄ የሚከናወን አልነበረም። የእግዚአብሔር ቃል እንደሚያስረዳውም ይህን መብት ጌታ ከመናገሩ በፊት ማንም አልተጠቀመበትም። ክርስቶስ በአገልግሎቱ መጨረሻና በሞቱ ዋዜማ እንዲህ ብሏል “እኔም አብን እለምናለሁ፥ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፥ እርሱም የእውነት መንፈስ ነው” (ዮሐ. 14፡16-17)። በተመሳሳይ ሁኔታ ከትንሣኤው በኋላ ተነፈሰባቸውና “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ” አላቸው (ዮሐ. 20፡22)። ይሁን እንጂ ለጊዜው መንፈስ ቅዱስን ቢቀበሉም፥ ከላይ በሚወርድ ኃይል እስኪሞሉ ድረስ ኢየሩሳሌም ውስጥ መቆየት ነበረባቸው (ሉቃስ 24፡49፤ ሐዋ. 1፡4)። 

ሐ. በጰንጠቆስጤ ዕለት የመንፈስ ቅዱስ መውረድ 

በአብ (ዮሐ. 14፡16-17፥ 26) እና በወልድ (ዮሐ. 16፡7) በተሰጠው ተስፋ መሠረት፥ በሁሉም ሥፍራ በመገኘት ባሕርይው ሁልጊዜ በዓለም የነበረው መንፈስ ቅዱስ በጳንጠቆስጤ ዕለት ወደ ዓለም መጣ። የዚህ የተደጋጋመ የሚመስል አሳብ ኃይል ገሀድ የሆነው፥ መንፈስ ቅዱስ በጰንጠቆስጤ ዕለት የመጣው በሰው ልብ ለማደር መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ነው። እግዚአብሔር አብ፥ ምንም እንኳን በሁሉም ሥፍራ ያለ (ኤፌ. 4፡6) ቢሆን፥ በሰማያት የምትኖር አባታችን” በሚለው መሠረት መኖሪያው በሰማያት ነው (ማቴ. 6፡9)። በተመሳሳይ እግዚአብሔር ወልድ፥ በሁሉም ሥፍራ የሚገኝ ቢሆን (ማቴ. 18፡20፤ ቈላ. 1፡27)፥ አሁን መኖሪያው በእግዚአብሔር ቀኝ ነው (ዕብ. 1፡3፤ 10፡12)። መንፈስ ቅዱስም እንዲሁ ምንም እንኳን በሁሉም ሥፍራ የሚገኝ ቢሆን፥ ማደሪያው በምድር ነው። ማደሪያው በምድር ነው የሚባለው ስጳንጠቆስጤ ዕላት አመጣጡ መሠረት ነው። መኖሪያውን ከሰማይ ወደ ምድር ለውጧል። ደቀ መዛሙርቱ እንዲጠባበቁ የተነገራቸው ይህን የመንፈስ ቅዱስ መምጣት ነበር። መንፈስ ቅዱስ ባይመጣ ኑሮ የዚህ አዲስ የጸጋ ዘመን አገልግሎት ሊጀመር አይችልም ነበር። 

የአሁኑ ዘመን የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በሚቀጥሉት ምዕራፎች ይቀርባል። ዮሐንስ 16፡7-11 ውስጥ እንደተገለጠው፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ከሁሉ በፊት ዓለምን የማገልገል ተልዕኮ አለው። የመጣው ዓለምን ስለ ኃጢአት፥ ስለ ጽድቅ፥ ስለ ፍርድ ለመውቀስ ነው። አንድን ሰው ክርስቶስን እንዲቀበል በአእምሮ የማዘጋጀት ልዩ ሥራ የመንፈስ ቅዱስ ነው። ሰይጣን የዘጋውን የማያምኑ ሰዎች አእምሮ የማብራት የጸጋ ሥራ በሦስት ታላላቅ አስተምህሮዎች መሠረት ይከናወናል። 

1. ያላመነ ሰው፥ በርሱና በድኀነት መካከል የሚገኝኃጢአት ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኙ አድርጎ አለማመን መሆኑን እንዲገነዘብ ይደረጋል። ጥያቄው የርሱ ብቁ ሆኖ መገኘት፥ ስሜቱ ወይም ሌላ ሁኔታ አይደለም። ያለማመን ኃጢአት ድኅነትን እንዳያገኝ ያደርገዋል (ዮሐ. 3፡18)። 

2. ላላመነ ሰው ስለ እግዚአብሔር ጻድቅነት ይነገረዋል። ክርስቶስ በምድር በተመላለሰ ጊዜ የእግዚአብሔር ጽድቅ መግለጫ ነበር፤ እርሱ ሲሄድ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ጽድቅ ለዓለም ይገልጥ ዘንድ ተላከ። እግዚአብሔር ጻድቅ እንደመሆኑ፥ ማንኛውም ሰው ሊያደርገው ከሚችለው በላይ የሆነን የጽድቅን ሥራ ይጠይቃል። ይህ ሁኔታ ምንም ዓይነት የሰው ሥራ ለሰው ልጅ ድኅነት መሠረት የመሆኑን ነገር ውድቅ ያደርገዋል። ከሁሉም ይልቅ በክርስቶስ በማመን የሚገኝ ጽድቅ መኖሩን መንፈስ ቅዱስ ይገልጣል። አንድ ሰው በክርስቶስ በማመኑ፥ በእግዚአብሔር ከኃጢአት ፍርድ ነጻ እና ጻድቅ ይባላል። ይህ የሚሆነው፥ ጻድቅ በሆነው ክርስቶስና በመስቀል ላይ በፈጸመው ሥራ ብቻ በመታመኑ ነው (ሮሜ 1፡16-17፤ 3፡22፤ 4፡5)። 

3. የዚህ ዓለም ገዢ ሰይጣን በመስቀል ላይ የተፈረደሰትና የለም ቅጣት የተጣለበት የመሆን እውነት ተገልጧል። ይህ የሚያስገነዝበው፥ የመስቀል ላይ ሥራ የተፈጸመ፥ ፍርድ የተሰጠ፥ ሰይጣን ድል የሆነ እና፥ በክርስቶስ ለሚያምኑ ሁሉ ድኅነት የተዘጋጀላቸው መሆኑን ነው። አንድ ሰው ድኅነት እንዲያገኝ እነዚህን ሁሉ ሙሉ በሙሉ ይረዳ ዘንድ አስፈላጊ አይደለም። መንፈስ ቅዱስ ነው እውነቱን በሙላት ገልጦ በአእምሮ ዝግጅት ክርስቶስን በአካልነቱና በሥራው እንዲቀበል የሚያደርገው። 

ባለፉት ዘመናትም፥ በብሉይ ኪዳን እንኳን ሰው ያለመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ሊያምንና ሊድን አለመቻሉን የሚያመለክቱ የተወሰኑ ሁኔታዎች አሉ። በአሁኑ ዘመን ግን፥ ከክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ በኋላ እውነቶቹ ይበልጥ ግልጥ ሆነዋል። መንፈስ ቅዱስ ወደ ዓለም የመምጣቱና የመኖሩ አንዱ ዋና ምክንያት እነዚህን ሁኔታዎች ለማያምኑ ሰዎች ለመግለጥ ነው። 

መንፈስ ቅዱስ በጰንጠቆስጤ ዕለት ወደ ዓለም በመምጣት ተልዕኮው በብዙ አዳዲስ መንገዶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዲከናወን እደረገ። ይህ በሚቀጥሉት ምዕራፎች የምንመለከተው ጉዳይ ይሆናል። መንፈስ ቅዱስ ለሚያምን ሰው ሁሉ አዲስ ልደት የሚሰጥ መሆኑ ተገልጧል (ዮሐ . 3፡3-7፥ 36)። በእያንዳንዱ አማኝ ውስጥ ይኖራል (ዮሐ. 7፡37-39፤ ሐዋ. 11፡15-17፤ ሮሜ 5፡5፤ 8፡9-11፤ 1ኛ ቆሮ. 6፡19-20)። መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ውስጥ እንደመኖሩ መጠን ለመዳን ቀን ያትናል (ኤፌ. 4፡30)። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጅ ወደ ክርስቶስ አካልነት የተጠመቀው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ነው (1ኛ ቆሮ. 12፡13)። እነዚህ ሁሉ አገልግሎቶች በዚህ ዘመን ላሉ እውነተኛ አማኞች ሁሉ ይሰጣሉ። ከነዚህ ከአማኙ ድኅነት ጋር የተያየዙት ሥራዎች በተጨማሪ፥ የመንፈስ ቅዱስ ሙላትና በርሱም ምሪት መሥራት ይኖራል። እነዚህ ታላላቅ የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች በዚህ ዘመን ላለ አማኝ የአገልግሎቶች ሁሉ በር የሚከፍቱለት ለድኅነት ብቻ ሳይሆን፥ አጥጋቢ የክርስትና ሕይወት ለመኖር ቁልፍ በመሆንም ጭምር ነው። 

እግዚአብሔር ለዚህ ዘመን ያለው ዓላማ በቤተ ክርስቲያን መነጠቅ ሲያበቃ፥ መንፈስ ቅዱስም ወደ ዓለም የመጣበትን ልዩ ተልዕኮ ያበቃና በጳንጠቆስጤ ዕላት በመጣበት አኳኋን ከዓለም ይወሰዳል። ኢየሱስ ክርስቶስ ሥራውን ለማከናወን ወደ ምድር እንደመጣና ከዚያም ሥራውን አጠናቆ ወደ አባቱ እንደሄደ፡መንፈስ ቅዱስም ለዚህ ዘመን ያለውን ሥራ ይሠራ ዘንድ ከላይ ወረደ። አሁን ሥራውን በማከናወን ላይ ነው፤ በንጥቀት ጊዜ ደግሞ ሥራውን አጠናቆ ይመለሳል። ይሁን እንጂ ልክ እንደ ክርስቶስ፥ መንፈስ ቅዱስም በሁሉም ሥፍራ በመገኘት ሳሕርይው መሠረት፥ ከቤተ ክርስቲያን መነጠቅ በኋላም ከጴንጠቆስጤ በፊት በነበረው አኳኋን ሥራውን ይቀጥላል። 

በዚህ መሠረት እንግዲህ ይህ ዘመን በብዙ መልኩ የመንፈስ ቅዱስ ዘመን ነው፤ ማለትም የእግዚአብሔር መንፈስ የክርሰቶሰን አካል (ቤተ ክርስቲያንን ለመመሥረት ከአይሁድና ከአሕዛብ በልዩ አኳኋን ሰዎችን የሚጠራበት ነው። መንፈስ ቅዱስ ከንጥቀት በኋላ መሥራቱን ይቀጥላል፤ በሚመጣው የክርስቶስ መንግሥት ዘመንም ይሠራል። ይህ ሥራ ሰመንፈስ ከማጥመቁ ተግባር በስተቀር፥ ምናልባት በአሁኑ ዘመን ያለውን የመንፈስ ቅዱስ ሥራ የሚጨምርና ለየት ያለ ሁኔታ ያላውም ይሆናል። የመንፈስ ቅዱስ መምጣት በአሁኑ ዘመን ላለ የእግዚአብሔር ሥራ አስፈላጊነቱ ልክ እግዚአብሔር ለዓለም ሁሉና፥ በተለይ ለሚያምኑ ድኅነት ለመስጠት ለነበረው ታላቅ ዓላማ፥ የኢየሱስ መምጣት አስፈላጊ የነበረውን ያህል ታላቅ ምዕራፍ ነው።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

16
ትምህርት 16 ከ52

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የዳግም ልደት ሥራ

የክርስትና እምነት ሕይወት ከዳግም ልደት የሚጀምር ስለሆነ፥ ከድኅነት ጋር በተዛመደ መልኩ ሲታይ ዳግም ልደት መሠረታዊ ከሆኑት አስተምህሮዎች አንዱ ነው። ስለዚህ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሥራ ተገቢ መረዳትና ከአጠቃላዩ የክርስትና ሕይወት ጋር ያለውን ድንቅ ግንኙነት መገንዘቡ፥ ውጤት ላለው የወንጌል ሥራና ለመንፈሳዊ ብስለት ጠቃሚ ነው። 

ሀ. የዳግም ልደት ትርጉም 

“ዳግም ልደት” የሚለው ቃል ጽንሰ አሳብ አዲስ ሕይወት፥ አዲስ ልደት፥ መንፈሳዊ ትንሣኤ፥ አዲስ ፍጡር፥ ባጠቃላይ አማኞች እንደ እግዚአብሔር ልጅነታቸው የሚያገኙትን ከሁሉ የላቀ ወይም ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ሕይወትን ለመግለጫነት በሥነ-መለኮት ሰዎች የተመረጠ ነው። ይህ ቃል በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ብዙ ጊዜ ትክክለኛ ትርጉሙን አላገኘም። ትክክለኛ ግንዛቤ ቢያገኝ ግን ትርጉሙ እንድ ሰው በክርስቶስ ባመነ ጊዜ ወደ ዘላለም ሕይወት፥ ማለት በቅጽበት ከመንፈሳዊ ሞት ወደ መንፈሳዊ ሕይወት ተሸጋገረ ማለት ነው። 

ለ. በመንፈስ ቅዱስ ዳግም መወለድ 

ዳግም ልደት ከመሠረቱ የእግዚአብሔር ሥራ የመሆኑ እውነት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ቦታ ላይ ተጠቅሷል (ዮሐ. 1፡13፤ 3፡3-7፤ 5፡21፤ ሮሜ 6፡13፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡17፤ ኤፌ. 2፡5፥ 10፤ 4፡24፤ ቲቶ 3፡5፤ ያዕ. 1፡18፤ 1ኛ ጴጥ. 2፡9)። በዮሐንስ 1፡13 መሠረት ዳግም ልደት ያገኘ ሰው፥ ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።”። ዳግም ልደት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ቦታ ላይ ከመንፈሳዊ ትንሣኤ ጋር ተነጻጽሯል (ዮሐ. 5፡21፤ ሮሜ 6፡13፤ ኤፌ. 2፡5)። የእግዚአብሔር የመፍጠር ሥራም ስለሆነ ከተፈጥሮ ጋር ተነጻጽሯል (2ኛ ቆሮ. 5፡17፤ ኤፌ. 2፡10፤ 4፡24)። 

ለአማኝ ዳግም ልደትን በመስጠቱ ተግባር ሦስቱም የሥላሴ አካላት ይሳተፋሉ። ያዕቆብ 1፡17-18 ውስጥ አብ ከዳግም ልደት ተግባር ጋር ተዛምዷል። ኢየሱስም በዚህ ተግባር መሣተፉ በተደጋጋሚ ተገልጧል (ዮሐ. 5፡21፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡18፤ 1ኛ ዮሐ. 5፡12)። ይሁን እንጂ ሦስቱም አካላት የተሣተፉባቸው ሌሎች የእግዚአብሔር ሥራዎች ቢኖሩም፥ በዮሐንስ 3፡3-7 እና ቲቶ 3፡5 ውስጥ መንፈስ ቅዱስ እንደ ዳግም ልደት ሰጭ ሆኖ ተገልጧል። መንፈስ ቅዱስ በዳግም ልደት ውስጥ ባለው ተግባር መሠረት በክርስቶስ መጸነስ ሁኔታ ተሳትፏል። በክርስቶስ ልደት እግዚአብሔር አብ የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ሲሆን፥ የወልድ ሕይወት በክርስቶስ ሆኖ በመንፈስ ቅዱስ ተፀነሠ። 

ሐ. በዳግም ልደት የተገኘ የዘላለም ሕይወት 

የዳግም ልደት ዋና አሳብ፥ በመንፈስ ሞቶ የነበረ አማኝ አሁን የዘላለም ሕይወት ማግኘቱ ነው። ይህን አሳብ ለማገናዘብ ሦስት መግለጫዎች ተጠቅሰዋል። አንዱ ዳግም የመወለድ አሳብ ነው። ክርስቶስ ከኒቆዲሞስ ጋር በሚነጋገርበት ጊዜ “ዳግም ልትወለድ ይገባል” ወይም አንዳንዴ እንደሚተረጎመው “ከላይ ልትወሰድ ይገባል” ብሎታል። ዮሐንስ 1፡13 ውስጥ እንደተጠቀሰው ዳግም ልደት ከሰብዓዊ ልደት ጋር በመነጻጸር ተገልጧል። ሁለተኛውና መንፈሳዊ ትንሣኤን የሚመለከተው እሳብ፥ በክርስቶስ ያመነ ሰው ከሙታን ተለይቶ በሕይወት እንደሚኖር…” (ሮሜ 6፡13) ያስረዳል። ኤፌሶን 2፡5 ውስጥ በበደላችን ሙታን እንኳን በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን” ይላል። ቀጥታ አባባሉ “ከክርስቶስ ጋር ሕያው አደረገን” ማለት ነው። ሦስተኛው አሳብ አዲስ ፍጥረትን የሚያመለክት ሲሆን፥ አማኞች “ለእውነትም በሚሆን ጽድቅና ቅድስና በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ” (ኤፌ. 4፡24) ተብለዋል። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17 ውስጥ አሳቡ ይበልጥ ግልጥ ተደርጓል። “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፥ አሮጌው ነገር አልፎአል፥ እነሆ ሁሉም አዲስ ሆኖአል”። ከላይ የተጠቀሱት ሦስት ምሳሌዎች በክርስቶስ በማመን ስለሚገኘው አዲስ ሕይወት ነው የሚናገሩት። 

ከአዲስ ልደት፥ ከመንፈሳዊ ትንሣኤና መፈጠር ሁኔታ በግልጥ የምንረዳው ነገር፥ ዳግም መወሰድ በማንኛውም ሰው መልካም ሥራ የማይገኝ መሆኑን ነው። የሰው በጎ ፈቃድ ሥራ ወይም የማንኛውም የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት አይደለም። ማለትም እንደ ጥምቀት የመሳሰሉ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶች ውጤትም አይደለም። ሙሉ ለሙሉ እግዚአብሔር ለሰው እምነት የሚመልሰው ፍጹም መለኮታዊ አጸፋ ነው። 

በመሆኑም ዳግም ልደት ቀጥሎ ካሉት ልምምዶች ሊለይ ይገባል። ዳግም ልደት ቅጽበታዊ ክንውንና ከድኅነት የማይለይ ነው። በትክክለኛው መንገድ ድኅነትን ያገኘ ሰው ተከታታይ መንፈሳዊ ልምምድ ይኖረዋል። ይህ ልምምድ ግን የዳግም ልደት ማረጋገጫ እንጂ ራሱ ዳግም ልደት አይደለም። ለነገሩ አዲሱን ልደት በመለማመድ ላይ ነን በማለት ለመናገር እንችላለን፤ የዚህ አባባላችን ትክክለኛ ትርጉም ግን የአዲስ ልደትን ውጤቶች በመለማመድ ላይ መሆናችንን ነው የሚያመላክተው። 

መ. የዳግም ልደት ውጤት 

ዳግም ልደት በብዙ ሁኔታው ድኅነታችን የተገነባበት መሠረት ነው። በክርስቶስ የሆነ አዲስ ሕይወት ካልተገኘ፥ መንፈስ ቅዱስን፥ ጽድቅን ወይም ሌሎች ተከታታይ ውጤቶችን የማግኛ መንገድ የለም። በዳግም ልደት ወዲያውኑ እውን የሚሆኑ አንዳንድ ነገሮች ግን አሉ። 

አንድ እማኝ ክርስቶስን በእምነት ሲቀበል፥ አዲስ ልደትን ያገኛል፤ በዚያም አማካይነት አዲስ ፍጡር ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ “እዲሱ ሰው” (ኤፌ. 4:24) የሚለው ይህን ነው። አዲሱ ሰው፥ ለአዲሱ እኛነታችን ይጠቅመን ዘንድ “እንድንለብሰው> የተነገረን ነው። በክርስቶስ የሚያምን እንድ እማኝ ከሚኖረው አዲስ ባሕርይ የተነሣ ድንቅ የሆነ ለውጥ በሕይወቱ ይሆናል። ይህን ለውጥ ያገኘ አማኝ ስለ እግዚአብሔር ያለው እመለካካትና፥ ኃጢአትን ላለማድረግ ያለው ጽናት ከቀድሞው የተለየና የበረታ ነው። ዳግም የተወለደ ሰው አዲስ ተፈጥሮ በእግዚአብሔር ባሕርይ አምሳል የተለወጠ ሲሆን፥ ይህ ተፈጥሮ አዳም ከመውደቁ በፊት ከነበረው ተፈጥሮ ለየት ያለ ነው። አዲሱ ተፈጥሮ መለኮታዊ ባሕርይ ዕላላው የእግዚአብሔር የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ይሻል። ያለመንፈስ ቅዱስ እርዳታ የራሱን ፍላጎት ለመፈጸም ኃይል ባይኖረውም፥ ለሕይወት እዲስ አቅጣጫን፥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም ደግሞ አዲስ ምኞትን ይሰጣል። 

ዳግም ልደት የሂደት ልምምድ ሳይሆን ቅጽበታዊ ነው። ቢሆንም ዳግም የተወለደ ሰው የሚቀበለው አዲስ ሕይወት አንዳንድ ልምምድን ለመለማመድ የሚረዳ ብርታትን ይሰጠዋል። አዲሱ አማኝ ቀድሞ ዐይነ ሥውር ነበር። አሁን ግን ያያል። ቀድሞ ሙት ነበር፥ አሁን ግን ለመንፈሳዊ ነገሮች ሕያው ነው። ቀድሞ ከእግዚአብሔር የተለየና አንድነት የሌለው ነበር። አሁን ግን የአንድነት መሠረት ስላለው የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ያገኛል። አማኝ ራሱን ለጌታ በሰጠ መጠን የጌታን ድንቅ ስጦታዎች ይላማመዳል። ይህ ልምምድ ጌታ በአንድ ራሱን የሰጠ ሰው ሕይወት የሚያደርገው ድንቅና ሉዓላዊ ሥራ መግለጫ ነው። 

የዘላለም ሕይወት የማግኘቱ ሌላ ጠቃሚ ነገር፥ የዘላለም ዋስትና መሠረትነቱ ነው። አንዳንዶች፥ ሰው ከእምነቱ ቢያፈነግጥ ድኅነቱንና የዘላለም ሕይወትን ያጣል ብለው ቢያስተምሩም፥ የዘላለም ሕይወትና የአዲስ ልደት ባሕርይ ራሱ ይህን የእግዚአብሔርን ሥራ የመሻር ሁኔታ ይከለክላል። ድኅነት በመጀመሪያ የሰው ሳይሆን የእግዚአብሔር ሥራ ነው፤ በሰው ሥራ ብቁዕነት የሚገኝም አይደለም። እምነት አስፈላጊ ቢሆንም ድኅነት የሚያስገኝ መልካም ሥራ ሆኖ ሊቆጠር አይገባም። እምነት እግዚአብሔር በአማኙ ሕይወት እንዲሠራ በር ይከፍታል። ተፈጥሯዊ ልደት ወደነበረበት እንደማይመለስ፥ መንፈሳዊ ልደትም እንዲሁ ነው። አንዴ ከተከናወነ እግዚአብሔር ሁልጊዜ ሰማያዊ አባቱ እንደሆነ ለአማኙ ያረጋግጥለታል። 

የትንሣኤ ክንውን ወደነበረበት አይመለስም። በተመሳሳይ ሁኔታም በእግዚአብሔር አሠራር ወደ አዲስ ሕይወት ስለተሸጋገርን ይህን ሕይወት መቀየር አይቻልም። አዲስ ልደት ልክ እንደ ፍጥረት አሠራር አንዴ ከተከናወነ ለዘላለም የሚቀጥል መሆኑ ሌላው ማረጋገጫ ነው። ሰው ከተፈጠረ በኋላ ራሱን ወዳልተፈጠረበት ሁኔታ መመለስ እይችልም። እንዲሁም የዘላለም ዋስትና አስተምህሮ በሚከተሉት ትምህርት ጥያቄዎች ላይ የተመሠረተ ነው፡- ድኅነት የእግዚአብሔር ወይስ የሰው ሥራ፥ ሙሉ በሙሉ በጸጋ ላይ ወይስ በሰው ሥራ ላይ የተመሠረተ ነው? ምንም እንኳን በክርስቶስ አዲስ የሆነ ሰው እንደ እግዚአብሔር ልጅነቱ መሆን እንደሚገባው ሊሆን ባይችል፥ ልክ በሰብዓዊ ቤተሰብ የአንድ ሰው ልጅ ባደረገው ጥፋት ልጅነቱ እንደማይሻር፥ እማኝም ያገኘውን የዘላለም ሕይወት አያጣም። አሁን ያለን የዘላለም ሕይወት በመንፈሳዊ ልምምድ የተገለጠው በከፊል ብቻ መሆኑም እውነት ነው። የዘላለም ሕይወት ደስታ ፍጹም የሚሆነው፥ እግዚአብሔር ባለበት በሰማይ ነው።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

17
ትምህርት 17 ከ52

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- በሰው ውስጥ ማደሩና ማተሙ

ሀ. የአሁኑ ዘመን አዲስ ገጽታው 

በብሉይ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ ከሰዎች ጋር የኖረና የአዲስ ሕይወታቸው ምንጭ፥ የመንፈሳዊ ድላቸው መገኛ የነበረ ቢሆንም፥ የዚያን ጊዜ አማኞች ሁሉ መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው ያደረ መሆኑን የሚገልጥ ማረጋገጫ የለም። ይህን አስተምህሮ በተመለከተ ብሉይ ኪዳን የሚጠቅሰው ነገር የለም። ኢየሱስ ክርስቶስም በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረውን ሁኔታ ሰአሁኑ ዘመን ካለው ጋር በማነጻጸር የተለያ ትምህርቱን ሲጠቅስ “ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውስጣችሁም ስለሚሆን” ብሏል (ዮሐ. 14፡17)። መንፈስ ቅዱስ በእያንዳንዱ አማኝ ውስጥ የማደሩ ጉዳይ የዚህ ዘመን ልዩ ገጽታ ሲሆን፥ በሺህ ዓመት መንግሥት ዘመንም የሚሆን ነው። በሌላ በማንኛውም ጊዜ አይገኝም። 

ለ. የመንፈስ ቅዱስ በአማኞች ሁሉ ውስጥ ማደር 

ክርስቲያኖች በመንፈሳዊ ኃይልና የመንፈስን ፍሬ በማፍራት ረገድ በጣም የሚለያዩ ቢሆንም፥ እያንዳንዱ ክርስቲያን ከጰንጠቆስጤ ዕለት ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ እንደሚያድርሰት መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። መንፈስ ቅዱስ በሰው ውስጥ ሳያድር የመዘግየቱ ሁኔታ ምሳሌ ሐዋርያት ሥራ ውስጥ ታይቷል (8፡14-17፤ 19፡1-6)። እነዚህ ሁኔታዎች ችካካል ከሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የሽግግር ባሕርይ የተነሣ የተፈጠሩ ናቸው። መንፈስ ቅዱስ ሰዎች ውስጥ የማደሩ እውነት፥ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን የሚቀበል ሰው ጥያቄ በማይሆንበት ሁኔታ በብዙ ስፍራ ተጠቅሷል (ዮሐ. 7፡37-39፤ ሐዋ. 11፡17፤ ሮሜ 5፡5፤ 8፡9፥ 11፤ 1ኛ ቆሮ. 2፡12፤ 6፡19-20፤ 12፡13፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡5፤ ገላ. 3፡2፤ 4፡6፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡24፤ 4፡13)። እነዚህ ጥቅሶች ከጳንጤቆስጤ ዕለት በፊት፥ ማለት በብሉይ ኪዳን አሠራር፥ መንፈስ ቅዱስ በጥቂት ሰዎች ብቻ ያድር የነበረ መሆኑን በግልጥ ያስረዳሉ። ከጰንጠቆስጤ ዕለት በኋላ ግን ትክክለኛው የመንፈስ ቅዱስ አሠራር በአማኝ ውስጥ ማደር ነው። 

መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያኖች ሁሉ የሚያድር መሆኑ ሮሜ 8፡9 ውስጥ የከርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለምን” ሰሚለው ቃል ተደግፏል። በተመሳሳይ ሁኔታ ይሁዳ 19 ውስጥ እንደተገለጠው፥ የማያምኑ ሰዎች (“መንፈስ የሌላቸው” ተብለዋል። ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጭ የሚኖሩና በቁጣው ሥር ያሉ (የሚቀጡ) ክርስቲያኖች እንኳ አካላቸው የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 6፡19 ውስጥ እንደተጠቀሰው፥ ሥጋዊ የሆኑ የቆሮንቶስ ሰዎች አካላቸው የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ስለሆነ፥ እግዚአብሔርን የሚያሳዝን ኃጢአት እንዳይፈጽሙ አስጠንቅቋቸዋል። 

መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ስጦታ እንደሆነም በተደጋጋሚ ተገልጿል። የስጦታ መሠረታዊ እውነት ከተቀባዩ ምንም አጻፋ አለመፈለጉ ነው (ዮሐ. 7፡37-39፤ ሐዋ, 11፡17፤ ሮሜ 5፡5፤ 1ኛ ቆሮ. 2፡12፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡5)። በተመሳሳይ ሁኔታ ከጌታ ጋር ለመጓዝ የሚሹ ክርስቲያኖች ለሚጠበቅባቸው የሕይወት ከፍተኛው ደረጃ፥ አስፈላጊውን መለኮታዊ ችሉታ ይሰጣቸው ዘንድ መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው ማደሩ ተገቢ ነው። ካህናትና ነገሥታት ተቀብተው ለተቀደሰ ሥራ እንደሚለዩ፥ ክርስቲያንም ድነቱን በሚቀበል ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ይቀባና በውስጡ በሚኖረው መንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወደ ፊት ከክርስቶስ ጋር ለሚኖረው አዲስ ሕይወት ይለያል (2ኛ ቆሮ. 1፡21፤ 1ኛ ዮሐ. 2፡20፥ 27)። መቀባት ድነትን በመቀበያ ጊዜ የሚከናወንና ለሁሉም አማኝ የሚሰጥ ሲሆን፥ መንፈስ ቅዱስ በአማኙ ውስጥ የማደሩ እውነት ከሚያሳየው አስተምህሮም ጋር ይመሳሰላል። አንድ አማኝ ከዳነ በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ይቀባል፥ ይህም የጸጋ ሁለተኛ ክፍል ነው፥ ወይም ከመንፈስ ቅዱስ ሙላት በኋላ ብቻ የሚከናወን ነው የሚለው ትምህርት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። 

ሐ. መንፈስ ቅዱስ በአማኙ ውስጥ ስለ ማደሩ በሚሰጠው አስተምህሮ ውስጥ የሚታዩ ችግሮች 

መንፈስ ቅዱስ በእያንዳንዱ አማኝ ውስጥ የማደሩ እውነት፥ ከአንዳንድ አከራካሪ ጥቅሶች የተነሣ አጠያያቂ ይሆናል። በብሉይ ኪዳንና በወንጌል ውስጥ ባሉ ሦስት ጥቅሶች (1ኛ ሳሙ. 16፡14፤ መዝ. 51፡11፤ ሉቃስ 11፡13) መሠረትነት አንዳንድ ሰዎች መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ሰው በአንዳንድ ሁኔታዎች የእግዚአብሔርን መንፈስ ያጣል ብለው አምነዋል። ዳዊት በሳዖል እንደተደረገበት ሁሉ (1ኛ ሳሙ. 16፡14) ከእርሱም የእግዚአብሔር መንፈስ እንዳይወሰድበት የጸለየው ጸሎት (መዝ. 51፡11)፥ በብሉይ ኪዳን እሠራር ላይ የተመሠረተ ነው። በዚያ ወቅት መንፈስ ቅዱስ በሁሉም ውስጥ ማደሩ የተለመደ አልነበረም። በመሆኑም በጌታ ሉዓላዊነት የተሰጠ መንፈስ በዚሁ ሉዓላዊነት ሊወሰድ ይችል ነበር። 

ሐዋርያት ሥራ ውስጥ ያሉ ሦስት ጥቅሶችም መንፈስ ቅዱስ በሁሉም ሰው ማደሩን አስመልክቶ የሚከሰትን አንድ ችግር የሚጠቁሙ ይመስላሉ። (1) ሐዋርያት ሥራ 5፡32 ውስጥ መንፈስ ቅዱስ “እግዚአብሔር ለሚታዘዙት የሰጠው” ተብሏል። እዚህ ላይ መታዘዝ የተባለው ለወንጌል መታዘዝ ነው፥ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚመለከተው በከፊል በማይታዘዙት እንኳን መንፈስ ቅዱስ ያድርባቸዋል። (2) ሰማርያ ውስጥ ፊሊጶስ ወንጌል የሰበከላቸው ሰዎች መንፈስ ቅዱስ ሳይቀበሉ የመዘግየታቸው ምክንያት፥ ይህን አዲስ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ኢየሩሳሌም ከነበሩ ሐዋርያት ተግባር ጋር ለማያያዝ ታስቦ ነበር። ለዚህ ነበር ሐዋርያቱ መጥተው እጃቸውን እስኪጭኑባቸው ድረስ ሰዎቹ በመንፈስ ቅዱስ ያልተሞሉት (ሐዋ. 8፡17)። ይህ ከቆርነሌዎስ መዳን ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር በተለመደው መንገድ የሆነ አልነበረም። እርሱ መንፈስ ቅዱስን የተቀበለው እጅ ሳይጫንበት ነው። (3) ሐዋርያት ሥራ 19፡1-6 ውስጥ የተወቀሰው ሁኔታ በመጥምቁ ዮሐንስ ስብከት እንጂ፥ ፈጽሞ በኢየሱስ ያሳመኑትን ሰዎች የሚመለከት ነው የሚመስለው። ሰዎቹ ጳውሎስ እጅ በጫነባቸው ጊዜ ነው መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት። 

ይህ ሁኔታም ያልተለመደና ከዚያ ወዲህ ያልተደገመ ነው። 1ኛ ዮሐንስ 2:20 ውስጥ ቅዱሱ ቅባት” የተባለውና 1ኛ ዮሐንስ 2፡27 ውስጥ የተጠቀሰው ቃል በትክክል ከተተረጎመ። መንፈስ ቅዱስ አማኙ ውስጥ መጀመሪያ ከማደሩ ጋር እንጂ፥ በኋላ ከሚሆን የመንፈስ ቅዱስ አሠራርጋር የሚዛመድ አይደለም። 

አዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሰው ማንኛውም የመንፈስ ቅዱስ መቀባት፥ ከጰንጠቆስጤ ዕለት በኋላም ሆነ በፊት፥ ሰው በጌታ እንዳመነ የሚሆን የመጀመሪያ ጊዜ ክንውን ነው (ሉቃስ 4፡18፤ ሐዋ. 4፡27፤ 10፡38፤ 2ኛ ቆሮ. 1፡21፤ 1ኛ ዮሐ. 2፡20፡27)። ስለዚህ ይህን አስተምህሮ የተመለከቱ ችግሮች የሚወገዱት። ችግሮቹ የሚነሡባቸውን ጥቅሶች በጥንቃቄ በማጥናት ነው። 

መ. የመንፈስ ቅዱስ ሰሰው ውስጥ ማደር ከሌሎች አገልግሎቶች ጋር ሲነጻጸር 

አንድ አማኝ አዲስ ልደት በሚያገኝበት ወቅት አንዳንድ የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች ወዲያውኑ በሕይወቱ ስለሚከናወኑ፥ እነዚህን የተለያዩ ክንውኖች በጥንቃቄ መለየት ይገባል። ሁለቱም በአንድ ጊዜ የሚከናወኑ ቢሆኑም፥ የመንፈስ ቅዱስ በአማኙ ውስጥ ማደርና በመንፈስ ቅዱስ ዳግም መወለድ አንድ አይደሉም። በተመሳሳይ ሁኔታ ዳግም ልደትና የመንፈስ ቅዱስ በአማኙ ውስጥ ማደር በመንፈስ ቅዱስ ከመጠመቅ ጋር አንድ አይደሉም። በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቁ ጉዳይ ወደፊት የምንገልጠው ይሆናል። የመንፈስ ቅዱስ በሰው ውስጥ ማደር በመንፈስ ቅዱስ ከመሞላት ይለያል። ይህም ልዩነት ክርስቲያኖች ሁሉ መንፈስ ቅዱስ ሊያድርባቸው ሲችል፥ በመንፈስ ቅዱስ የሚሞሉት ሁሉም አለመሆናቸው ነው። የመንፈስ ቅዱስ በአንድ ሰው ውስጥ ማደር ለአንዴና ለዘላለም የሚከናወን ሲሆን፥ በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ግን ብዙ ጊዜ በክርስቲያን ልምምድ የሚፈጸም ነው። የመንፈስ ቅዱስ በአንድ ሰው ማደር ግን፥ በመንፈስ ቅዱስ ከመቀባትና ከመታተም ጋር ተመሳሳይ ነው። 

የመንፈስ ቅዱስ በሰው ውስጥ ማደር ወይም መቀባት የዚህ ዘመን ክንውን ነው (ዮሐ. 14፡17፤ ሮሜ 7፡6፤ 8፡9፤ 1ኛ ቆሮ. 6፡19-20፤ 2ኛ ቆሮ. 1፡21፤ 3፡6፤ 1ኛ ዮሐ. 2፡20፥27)። መንፈስ ቅዱስ በውስጡ ከማደሩ የተነሣ አማኝ ይቀደሳል፥ ወይም ለእግዚአብሔር ይለያል። በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረው የቅባት ዘይት በአሁኑ ዘመን ያለው በመንፈስ ቅዱስ የመቀባት ምሳሌ ነው። ዘይት ከሰባቱ የመንፈስ ምሳሌዎች አንዱ ነው። 

1. በዘይት የተቀባ ነገር ሁሉ ወዲያውኑ የተቀደሰ ይሆናል (ዘፀ. 40፡9-15)። በተመሳሳይ ሁኔታ በዚህ ዘመንም መንፈስ ቅዱስ ሰውን ይቀድሳል (ሮሜ 15፡16፤ 1ኛ ቆሮ. 6፡11፤ 2ኛ ተሰ. 2:13፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡2)። 

2. ነቢዩ በዘይት ተቀድሶ ነበር (1ኛ ነገ, 9፡16)። እንዲሁም ክርስቶስ በመንፈስ ነቢይ ነው (ኢሳ. 61፡1፤ ሉቃስ 4፡18)። አማኝም በመንፈስ ምስክር ነው(ሐዋ. 1፡8)። 

3. ካህን በዘይት ይቀደስ ነበር(ዘፀ. 40፡15)፤ ክርስቶስም እንዲሁ በመሥዋዕቱ በመንፈስ ተቀድሷል (ዕብ. 9፡14)። እማኝም በመንፈስ ይቀደሳል (ሮሜ 8፡26፤ 12፡1፤ ኤፌ. 5፡18-20)። 

4. ንጉሡ ዘይት ተቀድሷል (1ኛ ሳሙ. 16፡12-13)። ክርስቶስም እንዲሁ በመንፈስ (መዝ. 45፡7) እና አማኝም በመንፈስ ይነግሣል። 

5. በዘይት መቀባት ለፈውስ ነበር (ሉቃስ 10፡34)፤ ይህም በመንፈስ ቅዱስ በሚገኝ ድነት አማካይነት የነፍስ ፈውስ የሚገኝ መሆኑን ያመለክታል። 

6. ዘይቱ ፊት እንዲያበራ ያደርጋል፤ እንደ ደስታ ዘይት ነው (መዝ. 45፡7)፤ ለዚህም ንጹሕ ዘይት አስፈልጓል (መዝ. 92 ፡10)። የመንፈስ ፍሬ ደስታ ነው (ገላ. 5፡22)። 

7. ሰማደሪያው ድንኳን የሚያስፈልጉ ነገሮች ሲዘረዘሩ ለመቅረዙ ዘይት የሚያስፈልግ መሆኑ በግልጥ ተጠቅሷል (ዘፀ. 25፡6)። ዘይት መንፈስ ቅዱስን፥ የዘይት ክር ደግሞ አማኝን በማስተላለፈያነት ሲገልጡ፥ ከዘይት የሚገኝ ብርሃን ደግሞ የክርስቶስን ብሩህነት ያመለክታል። በሚገባ ይሰራ ዘንድ ክሩ ዘይቱ ውስጥ መግባት ይኖርበታል፤ አማኝም በመንፈስ መመላለስ አለበት (ገላ. 5፡16)። ክሩ ወደ ዘይቱ ዘልቆ እንዳይገባ ከሚያሰናክለው ከማንኛውም ዓይነት ነገር ነጻ መሆን እንዳለበት ሁሉ አማኝም መንፈስ ቅዱስን መቃወም የለበትም (1ኛ ተሰ. 5፡19)። ክሩ መስተካከል እንዳለበት ሁሉ አማኝም ከኃጢአት ራሱን በንሰሐ ማንጻት አለበት (1ኛ ዮሐ. 1፡19)። 

የተቀደሰው የቅባት ዘይት (ዘፀ. 30፡22-25) ራሱ የሚቀመመው ከአራት የተለያዩ መሠረታዊ ቅመሞች ነበር። እነሱም በክርስቶስ ብቻ የሚገኙትን ባሕርያት ያመለክታሉ። የቅመሞቹ ውህደት የሚያመለክተው፥ መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስን እውነተኛ ሕይወትና ባሕርይ ወስዶ በአማኝ ሕይወት የሚያውለው መሆኑ ነው። 

ሰማደሪያው ድንኳን ውስጥ የሚቀመጥ ዕቃ ሁሉ መቀባትና ለእግዚአብሔር መታየት ነበረበት። ይህ የሚያመለክተው የአንድ አማኝ ለእግዚአብሔር መሰጠት ፍጹም መሆን ያለበት መሆኑን ነው (ሮሜ 12፡1-2)። 

ሠ. በመንፈስ ቅዱስ መታተም 

የመንፈስ ቅዱስ በአማኝ ውስጥ ማደር፥ በአዲስ ኪዳን ሦስት ክፍሎች ውስጥ እንደ እግዚአብሔር ማኅተም ተመስሏል (2ኛ ቆሮ. 1፡22፤ ኤፌ. 1፡13፤ 4፡30)። በምንም ዓይነት መንገድ ብናየው በመንፈስ ቅዱስ የማተሙ ተግባር የእግዚአብሔር ሥራ ነው። ማንኛውም ክርስቲያን የታተመ ስለሆነ፥ በመንፈስ ቅዱስ መታተምን እንዲሻ ሊነገረው አያሻም። ስለዚህ የመንፈስ ቅዱስ የማተም ሥራ በድነት ጊዜ የሚከናወን ሲሆን፥ መንፈስ ቅዱስ በእማኝ ሁሉ ውስጥ እንደሚያድር በመንፈስ መታተምም በሁሉም ዘንድ የሚከናወን ነው። 

የኤፌሶን ክርስቲያኖች “ለቤዛ ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝኑ” (ኤፌ. 4፡30) ተብለዋል። ኃጢአት ቢሠሩና መንፈስ ቅዱስን ቢያሳዝኑ እንኳን፥ እስከ ቤዛ ቀን ማለት እስከ ትንሣኤው ወይም እስከ መገለጥ ድረስ የታተሙ ናቸው። ያኔ አዲስ አካል ስለሚሰጣቸው ፈጽሞ ኃጢአት አይሠሩም። 

ልክ መንፈስ ቅዱስ በአማኙ እንደሚያድር ሁሉ፥ መታተምም በእምነት ከእግዚአብሔር የሚገኝ እንጂ፥ ልምምድ አይደለም። በመንፈስ ቅዱስ መታተም አስደናቂ የክርስቲያን ድነት ዋነኛ ክፍል ነው። በመሆኑም አማኙ ድነትና ዋስትና ያለው፥ እንዲሁም የእግዚአብሔር መሆኑን ያመለክታል። ይህም ሙሉ ለሙሉ ለጌታ እንዲሆን የሚያስፈልገው ዋጋ ሁሉ መካፈሉን ያመለክታል። ስለሆነም ክርስቲያን እካሉ በክብር እስከሚለወጥበትና እስከ ቤዛ ቀን ድረስ ታትሟል። ጠቅለል አድርገን ስንመለከተው መንፈስ ቅዱስ እንደ ማኅተማችን ሆኖ በውስጣችን ማደሩ፥ ይህን ታላቅ እውነት ለሚረዳ ክርስቲያን ልብ ዋስትኖን እና መጽናናትን ያመጣል።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

18
ትምህርት 18 ከ52

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- የማጥመቅ ተግባሩ

ሀ. የመንፈስ ቅዱስ ማጥመቅ ትርጉም 

የመንፈስ ቅዱስ ማጥመቅ አስተምህሮ ከሌሎቹ አስተምህሮዎች ይልቅ ግራ የሚያጋባ ይመስላል። ይህ ችግር በአብዛኛው የሚከሰተው፥ የመንፈስ ቅዱስ የማጥመቅ ተግባር የሚጀምረው ከሌሎቹ ታሳሳቅ የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች፥ ማለት ከዳግም ልደት፥ መንፈስ ቅዱስ በአማኙ ውስጥ ከማደሩ እና ከማተሙ ተግባር ጋር በአንድ ላይ በመሆኑ ነው። በአንዳንድ ሁኔታዎችም የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና መሞላት ተግባር በአንድ ጊዜ ሆኖ ያውቃል። ይህ ሁኔታ አንዳንድ ተንታኞች ሁለቱም ክንውኖች ተመሳሳይ ናቸው እንዲሉ አድርጓቸዋል። ይሁን እንጂ አንድ ሰው ከመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ጋር የተዛመዱ የመጽሐፍ ክፍሎችን በጥንቃቄ ሲመረምር፥ በአተረጓጎም የሚፈጠረው አለመግባባት ይፈታል። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን በሚመለከት አዲስ ኪዳን ውስጥ በአጠቃላይ አሥራ አንድ ግልጥ ጥቅሶች አሉ (ማቴ. 3፡11፤ ማር. 1፡8፤ ሉቃስ 3፡16፤ ዮሐ. 1፡33፤ ሐዋ. 1፡5፤ 11፡16፤ ሮሜ 6፡3-4፤ 1ኛ ቆሮ. 12፡13፤ ገላ. 3፡27፤ ኤፌ. 4፡5፤ ቆላ. 2፡12)። 

ለ. የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ከጰንጠቆስጤ ዕለት በፊት 

አራቱ ወንጌላትና በሐዋርያት ሥራ 1፡5 ውስጥ ያሉት ጥቅሶች ሲመረመሩ፥ በእያንዳንዱ ሁኔታ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ከዚያ በቀደሙ ጊዜያት ያልሆነና የወደፊት ከንውን መሆኑ ግልጥ ይሆናል። ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ብሉይ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሰ ነገር የለም። አራቱ ወንጌላት ናቸው ከሐዋርያት ሥራ 1፡5 ጋር በአንድ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ጎና ሊሆን የሚገባው ነገር እንደነበር የገለጡት። ወንጌላት ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ በኩል የሚያከናውነው ተግባር ሆኖ ነው የቀረበው። ለምሳሌ ማቴዎስ 3፡11 ውስጥ መጥምቁ ዮሐንስ “እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል” በማለት ስለ ክርስቶስ ተንብዮአል። በእሳት የማጥመቁ ጉዳይ በኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ወቅት ስለሚኖረው ፍርድ የሚያመለክት ይመስላል። ይህ ጉዳይ ሉቃስ 3፡16 ውስጥ እንጂ ማርቆስ 1፡8 ወይም ዮሐንስ 1፡33 ውስጥ አልተጠቀሰም። አንዳንድ ተንታኞች ይህን ሁኔታ በሐዋርያት ሥራና በመልእክቶች ከተጠቀሰው የመንፈስ ጥምቀት የተለየ አድርገው ነው የተገነዘቡት። የተሻለው አመለካከት ግን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በመላው አዲስ ኪዳን ተመሣሣይ መሆኑን መገንዘቡ ነው። በየትኛውም ሁኔታ ይሁን ጥምቀቱ የሚከናወነው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ነው። ይህም ክርስቶስ ራሱ የርሱን በዮሐንስ እጅ መጠመቅ ከአማኞች ወደፊት በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ ጋር ባነጻጸረበት ሥፍራ ተገልጧል። ይህም ከእርገቱ በኋላ የሚፈጸም ነበር። ክርስቶስ እንዲህ ብሏል፡- ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፤ እናንተ ግን ከጥቂት ቀናት በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ” (ሐዋ. 1፡5)። 

ሐ. በዚህ ዘመን ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀዋል 

የመንፈስ ቅዱስን የማጥመቅ ሁኔታና ጊዜ በተመለከተ ከሚፈጠረው ግራ መጋበት የተነሣ ማንኛውም ክርስቲያን ድነትን ባገኘ ወቅት በመንፈስ ቅዱስ መጠመቁን ብዙዎች አይገነዘቡትም። ይህ እውነት በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቅ ጉዳይ ማዕከላዊ ጥቅስ በሆነው በ1ኛ ቆሮንቶስ 12፡13 ውስጥ “አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን፥ ባሪያዎችም ብንሆን፥ እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናል። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል” ተብሏል። ጥቅሱ የሚያመለክተው በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካይነት ከዚሁ መንፈስ ጋር ወደ እዲስ ግንኙነት የመግባታችንን እውነት ነው። 

“እኛ ሁላችን” የሚለው አገላሰጥ የሚያመለክተው ሁሉንም ሰዎች ሳይሆን፥ ክርስቲያኖችን መሆኑን በሚገባ መገንዘብ አስፈላጊ ነው። ይህም ክርስቲያኖች ለሆኑ ሁሉ የሚሆን እንጂ ከመካከላቸው ለተወሰኑ ቡድኖች ብቻ አለመሆኑ መታወቅ አለበት። እውነቱ ክርስቲያን ሁሉ ከዳነበት ቅጽበት ጀምሮ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወደ ክርስቶስ አካል መጠመቁ ነው። በዚሁ መሠረት ኤፌሶን 4፡5 ላይ “አንድ ጌታ፥ አንድ ሃይማኖት፥ አንዲት ጥምቀት” ይላል። የውኃ ጥምቀት ሥርዓት የተለያየ ቢሆንም፥ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አንድ ብቻ ነው። የዚህ አገልግሎት ሁለንተናዊነት እንደሚያመለክተው ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ለመጠመቅ ጥረት እንዲያደርግ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ጊዜ አልተጠየቀም፤ ከመንፈስ ቅዱስ እንዲሞላ ነው የተመከረው (ኤፌ. 5፡18)። 

መ. በመንፈስ ቅዱስ በመጠመቅ ወደ ክርስቶስ አካል መጨመር 

በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካይነት ሁለት ዋና ዋና ውጤቶች ይገኛሉ። የመጀመሪያው አማኙ መጠመቁ ወይም ወደ ክርስቶስ አካል መጨመሩ ሲሆን፥ ከዚሁ ጋር የተያያዘውና ሁለተኛው ደግሞ አማኙ ወደ ክርስቶስ ውስጥ መጠመቁ ነው። እነዚህ በአንድ ላይ የሚፈጸሙ ሁለት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀቶች እጅግ ዋናዎቹ ናቸው። 

በዚህ ዘመን አንድ አማኝ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የእውነተኛ እማኞች ሕያው ሕብረት ወደሆነው የክርስቶስ አካል ይጨመራል። በዚህ ደረጃ የጥምቀት መሠረታዊ ትርጉም መጨመር፥ መገናኘት፥ እንዲሁም አዲስና ዘላለማዊ ግንኙነት መስጠት የሚለውን ይይዛል። በዚህ መሠረት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በተለያዩ ዘመናት ከተለያዩ ሕዝቦች የመጡ አማኞችኝ ሁሉ ወደ አንድ የክርስቶስ አካል እንዲጨመሩና አዲስና ዘላለማዊ ኅብረትን የሚካፈሉ ያደርጋቸዋል። 

በዚህ ሁኔታ በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካይነት የሚፈጠረውና አዳዲስ አባላት በተጨመሩ ቁጥር የሚያድገው የእማኞች አካል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል (ሐዋ. 2፡47፤ 1ኛ ቆሮ. 6፡15፤ 12፡12-14፤ ኤፌ. 2፡16፤ 4:4-5፥ 16፤ 5፡30-32፤ ቆላ. 1፡24፤ 2፡19)። የዚህ አካል ራስና ክንውኖቹን ሁሉ የሚመራ ክርስቶስ ነው (1ኛ ቆሮ. 11፡3፤ ኤፌ. 1፡22-23፤ 5፡23-24፤ ቆላ. 1፡18)። በዚህ ሁኔታ በክርስቶስ የተፈጠረውንና የሚመራውን አካል ክርስቶስ ራሱ ያሳድገዋል፥ ይጠነቀቅለታል (ኤፌ. 5፡29፤ ፊልጵ. 4፡13፤ ቆላ. 2፡19)። ከከርስቶስ ተግባራት አንዱ ይህን አካል በክብር ለመገለጡ ዕለት ለማቅረብ መቀደስ ነው (ኤፌ. 5፡25-27)። 

እማኝም እንደ ክርስቶስ አካል አባልነቱ በዚህ አካል ውስጥ የሚያከናውናቸው ልዩ ልዩ ስጦታዎች ወይም ሥራዎች አሉ (ሮሜ 12፡3-8፤ 1ኛ ቆሮ. 12፡27-28፤ ኤፌ. 4፡7-16)። በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወደ ክርስቶስ አካል መጨመር፥ ዘር፥ ባሕል ወይም ማንነት የሌለበትን አካል ሕብረት ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን፥ አማኙ የራሱ የተለየ ሥራና ሥፍራ ያለው የመሆን ዋስትና ይሰጠዋል። በአቅሙና በስጦታው መሠረት በአካሉ ውስጥ እግዚአብሔርን እንዲያገለግልም ዕድል ያስገኝለታል። አካሉ በአጠቃላይ “የተጋጠመና የተያያዘ” (ኤፌ. 4፡16) ነው። እባላቱ የተለያዩ ቢሆኑም፥ እካሉ ግን በሚገባ የተያያዘና የተደራጀ ነው። 

ሠ. መንፈስ ቅዱስ ወደ ክርስቶስ ውስጥ ማጥመቁ 

በመንፈስ የተጠመቀ አማኝ፡የክርስቶስ አካል ከሆኑት አማኞች ጋር ካለው አንድነት ተጨማሪ፥ በክርስቶስ ያለ በመባሉ አዲስ ሥፍራ አለው። ይህ ሁኔታ ዮሐንስ 14፡20 ውስጥ ክርስቶስ በመሰቀሉ ዋዜማ ምሽት “እኔ በአባቴ እንዳለሁ፥ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ፥ እኔም በእናንተ እንዳለሁ፥ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ” በማላት በተናገረው ቃል ተተንብዮ ነበር። “እናንተም በእኔ” የሚለው አነጋገር ሊመጣ ያለውን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነበር የተነበየው። 

አማኝ በክርስቶስ ውስጥ በመሆኑ ክርስቶስ በሞቱ፥ በትንሣኤውና በክብሩ ከፈጸመው ክንውን ጋር ይዛመዳል። ይህ ሮሜ 6፡1-4 ውስጥ አማኝ ወደ ክርስቶስ እካልነትና ወደ ሞቱ የተጠመቀ መሆኑን በሚያስገነዝበው ቃል ተረጋግጧል። በሞቱ ከተዛመደ ከክርስቶስ ጋር ተቀብሮ አብሮት ተነሥቷል። ብዙ ጊዜ ይህ ድርጊት የውኃ ጥምቀት ሥርዓትን የሚወክል ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ ነገር በማንኛውም እኳኋን የመንፈስ ቅዱስን ሥራ የሚጨምር መሆኑና ያለ እርሱ የጥምቀቱ ሥርዓት ትርጉም የለሽ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ቆላስይስ 2፡12 ውስጥ ተመሣሣይ ምንባብ አለ። በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካይነት ከክርስቶስ ጋር መመሳሰላችን፥ እግዚአብሔር ሰጊዜ ውስጥና ሰዘላለም ለአማኙ ለሚያደርገው ሁሉ ዋና መሠረት ነው። 

አንድ እማኝ ክርስቶስ ውስጥ ከመሆኑ የተነሣ፥ አካል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ራሷ ከሆነው ክርስቶስ የምትጋራው ሕይወት ተካፋይ ነው። ክርስቶስ ራሷ ከሆነው ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለው ግንኙነት፥ ልክ ሰብአዊ አእምሮ አካልን እንደሚመራ፥ እርሱም ልዑላዊ በሆነ መንገድ መምራቱ ነው። 

ረ. የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ከመንፈሳዊ ልምምድ ጋር ሲዛመድ 

ማንኛውም ክርስቲያን ድነትን ባገኘ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቋል ከሚለው እውነት የምንረዳው ነገር፥ ጥምቀት በእምነት ልንቀበለው የሚገሳ የእግዚአብሔር ሥራ መሆኑን ነው። ምንም እንኳን የኋላ መንፈሳዊ ልምምድ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን የሚያረጋግጥ ቢሆን፥ ጥምቀት በራሱ ልምምድ አይደለም። ጥምቀት ለሁሉም አማኝ የሚሆንና በክርስቶስ ካለን ሥፍራ ጋር የሚዛመድ ስለሆነ፥ በቅጽበት የሚከናወን የእግዚአብሔር ሥራ እንጂ፥ ከዳግም ልደት በኋላ ይመጣል ተብሎ የሚጠበቅ አይደለም። 

ብዙ ስሕተት የሚፈጠረው፥ ክርስቲያኖች በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የልሳን በመናገር የተገለጠውን ዓይነት የመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ ሊፈልጉ ይገባል ከሚለው አመለካከት ነው። ሐዋርያት ሥራ ውስጥ በሦስት ሁኔታዎች (ምዕራፎች 2፥ 10 እና 19) ክርስቲያኖች በመንፈስ ቅዱስ ሲጠመቁ በልሣን መናገራቸው ተገልጧል። ቢሆንም ያ ሁኔታ ያልተላመደና ከሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ሽግግራዊ መሆን ጋር የተያያዘ መሆኑ ግልጥ ነው። የድነት ሥራ በተከናወነባቸው ሌሎች ሁኔታዎች፥ በመንፈስ ቅዱስ በመጠመቅ ጊዜ በልሣን የመናገር አጋጣሚ አልተጠቀሰም። 

የጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ክርስቲያኖች ሁሉ በመንፈስ መጠመቃቸው ግልጥ ቢሆንም፥ ሁሉም በልሳን ተናግረዋል ማለት ግን አይደለም። ስለዚህ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ልዩ ለሆነ የእግዚአብሔር አሠራር ምክንያት አስፈላጊ አድርጎ መውሰድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የለውም። የመንፈስ ቅዱስ ሙላትን በልሳን ከመናገር ጋር በማያያዝ እንደ ብቸኛ ምልክት ከመውሰድ ይልቅ፥ ገላትያ 5፡22-23 ውስጥ እንደተጠቀሰው፥ በመንፈስ ፍሬ ነው የአንድን ሰው በመንፈስ ቅዱስ መሞላት መመዘን የሚቻለው። የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በመንፈስ ቅዱስ ሳይሞሉ በልሳን ተናግረዋል። 

ሁላት ዓይነት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አለ የሚል ሌላ ስሕተተም እንዳንዴ ይነገራል። አንደኛው በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2፥ ሌላው በ1ኛ ቆሮንቶስ 12፡13 ላይ የተመሠረተ ነው። ሐዋርያት ሥራ 10-11 ውስጥ ያለውን የቆርነሌዎስ መለወጥ፥ ከሐዋርያት ሥራ 2 ጋር በማነጻጸር እሕዛብ በሆነው ቆርነሌዎስ ላይ የተፈጸመው ሁኔታ በጰንጠቆስጤ ዕለት ሰሐዋርያት ሳይ ከደረሰው ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ለመረዳት ይቻላል። ሐዋርያት ሥራ 11፡15-17 ውሰጥ ጴጥሮስ “ለመናገርም በጀመርኩ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ፥ ለእኔ ደግሞ በመጀመሪያ እንደወረደ፥ ለእነርሱ ወረደላቸው። ዮሐንስ በውኃ አጠመቀ እናንተ ግን በመንፈስ ትጠመቃላችሁ ያለውም የጌታ ቃል ትዝ አለኝ። እንግዲህ እግዚአብሔር በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ላመንነው ለእኛ ደግሞ እንደሰጠን፥ ያን ሰጦታ ለእነርሱ ካሰጠ፥ እግዚአብሔርን ለመከልከል እኔ ማን ነበርሁ?” ብሏል። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አንድን አማኝ ወደ ክርስቶስ አካል የሚጨምረው እንደመሆኑ፥ ከሐዋርያት ሥራ 

ምዕራፍ ሁለት ጀምሮ እስከዚህ ዘመን ድረስ ያለው አሠራር ተመሳሳይ ነው። 

ስለዚህ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ከክርስቶስ እና ከእማኞች ጋር በአዲስ ሕብረት የሚያገናኝ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ስለሆነ ታላቅ ነገር ነው። በክርስቶስ እዲስ ሥፍራ ያስገኛል፥ ከክርስቶስ አካል ጋርም በቅርብ ያስተሣሥራል። አማኙን ፍጹም አድርጎ በመጨረሻ በክብር የሚያቀርብ የጽድቅና የእግዚአብሔር ሥራ ሁሉ መሠረት ነው። 

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

19
ትምህርት 19 ከ52

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- የመሙላት ተግባሩ

ህ. የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ሲብራራ 

ከመንፈስ ቅዱስ የማዳን ተግባራት፥ ማለት ዳግም ከመወለድ፥ በእማኝ ውስጥ ከማደር፥ ኮማተም እና ከማጥመቅ ሥራ ጋር ሲነጻጸር፥ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ከከርስቲያን ልምምድ፥ ኃያል እና አገልግሎት ጋር ነው የሚገናኘው። ከድነት ጋር የተያያዘው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ለአንዴና ለዘላለም የሚከናወን ሲሆን፥ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ግን የሚደጋገም ልምምድ መሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጊዜ ተገልጧል። 

የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ከጰንጠቆስጤ ዕለት በፊት በጣም ውሱን በሆነ ደረጃ በአንዳንድ ግለሰቦች ላይ ታይቷል (ዘፀ. 28፡3፤ 31፡3፣ 35፡31፤ ሉቃስ 1፡15፥ 41፥ 67፤ 4፡1)። የእግዚአብሔር መንፈስ ሰግለሰቦች ላይ መውረዱና የአገልግሎት ኃይል የሞላበት ሁኔታ መኖሩ የሚያጠራጥር አይደለም። በአጠቃላይ ሲታይ ግን ካጳንጠቆስጤ ዕለት በፊት በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉት ጥቂት ናቸው። የመንፈስ ቅዱስ ሥራም እግዚአብሔር በልዑል ዓላማው መሠረት በግለሰቦች አማካይነት ከሚያከናውነው አንዳንድ ልዩ ሥራዎች ጋር የተያያዘ ይመስላል። የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ከጰንጠቆስጤ ዕለት በፊት ሕይወቱን ለጌታ ለሰጠ ሰው ሁሉ ክፍት የነበረ መሆኑን የሚያመለክት ነገር የለም። 

ከጰንጠቆስጤ ዕለት ወዲህ ያለው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ሁሉ የሚሠራበት እዲስ ዘመን ሆኗል። በዚህ ዘመን አማኝ ሁሉ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ካምሆኑም በላይ፥ ቅድመ ሁኔታዎችን ካሟላ ሰመንፈስ ቅዱስ ሊሞላ ይችላል። ይህን እውነት አዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉ አያሌ መግለጫዎች ያረጋግጣሉ (ሐዋ. 2፡4፤ 4፡8፥ 31፤ 6፡3፥ 5፤ 7፡55፤ 9፡17፤ 11፡24፤ 13፡9፥ 52፤ ኤፌ. 5 ፡18)። 

የመንፈስ ቅዱስ ሙላት፥ መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ልብና ሕይወት ውስጥ ሊሠራ የሚፈልገውን ያለመከልከል ሲሠራ በእማኝ ሕይወት ውስጥ የሚከሰት ሁኔታ ነው ማለት ይቻላል። ድርጊቱ መንፈስ ቅዱስን ይበልጥ የመቀበል ሳይሆን፥ የእግዚአብሔር መንፈሰ ራሱ አማኙን ይሰልጥ የራሱ ማድረጉ ነው። የመንፈስ ቅዱስ ሙላት በዚህ ዘመን ከጰንጠቆስጤ ዕለት በፊት እንደነበረው በተወሰኑ ሰዎች ላይ ለልዩ ሥራ መከናወን የሚሆን ሳይሆን፥ አማኞች ሁሉ ሊያገኙት የሚቻላቸውና በእርሱ ለሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር የቀረበ የክርስቲያን ልምምድ ነው። ክርስቲያን ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ እንዲሞላ ታዟል (ኤፌ. 5፡18)፤ በመንፈስ ቅዱስ አለመሞላት ግን ከፊል አለመታዘዝ ነው። 

ክርስቲያን ባሕርይና ዕለታዊ ሕይወቱ ውስጥ በግልጥ የሚታይ ልዩነት አለ። ጥቂቶች መንፈስ የሞላሳቸው ሆነው ይታወቃሉ። የዚህ ጸጋ ተጠቃሚዎች ቁጥር ጥቂት የመሆኑ ምክንያት፥ ከእግዚአብሔር ልግስና ማነስ ሳይሆን፥ ሰዎች ራሳቸውን ሳያዘጋጁና የእግዚአብሔር መንፈስ ሕይወታቸውን እንዲሞላው ሳይፈቅዱ መቅረታቸው ነው። 

በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ከመንፈሳዊ እድገት ጋር ሊነጻጸር ይገባል። ድነትን ካገኘ አጭር ጊዚው የሆነ አዲስ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ሊሞላና የመንፈስ ቅዱስ ኃያልም በሕይወቱ ሊገለጥ ይችላል። በክርስትና ሕይወት መብሰል፥ በእውቀት ማደግ፥ በመንፈስ ቅዱስ የመሞላት የማያቋርጥ ልምምድ እና መንፈሳዊ ነገሮችን በመለየት ማደግ ነው። ይህ የሚገኘው፥ እስከ ሕይወት ፍጻሜ በሚያድግ መንፈሳዊ ልምምድ ይሆናል። አዲስ የተወለደ ሕፃን ሙሉ ጤናማ ሊሆን እንደሚችል፥ አዲስ ክርስቲያንም በመንፈስ ቅዱስ ይሞላ ይሆናል። ነገር ግን ልክ አዲስ እንደተወለደ ሕፃን አዲሱን ክርስቲያንም ወደ እድገት የሚያደርሰው በሕይወቱ የሚያገኘው ልምምድ ነው። ለዚህ ነው ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች ስለ መንፈሳዊ እድገት አበክረው የሚናገሩት። የስንዴ ቡቃያ እስከ መከር ያድጋል (ማቴ. 13፡30)። እግዚአብሔር መንፈሳዊ ስጦታዎች ባሏቸው ሰዎች አማካይነት ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ይሠራል። ይህን የሚያደርገው፥ ቅዱሳኑን ለአገልግሎት ብቁ ለማድረግ፥ በእምነት በእውቀትና በመንፈሳዊ ሁኔታ ለማሳደግ እንዲሁም የክርስቶስ አካል የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን ለመቀደስ ነው (ኤፌ. 4፡11-16)። ጴጥሮስ አዲስ የተወለዱ ሕፃናት ለእድገታቸው መንፈሳዊ ወተት እንደሚያሻቸው ይናገራል (1ኛ ጴጥ. 2:2)። “በጌታችንና በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ” (2ኛ ጴጥ. 3፡18) በማለትም ክርስቲያኖችን ይመክራል። 

በመንፈስ ቅዱስ ሙላትና በመንፈሳዊ እድገት መካከል ግልጥ የሆነ ግንኙነት አለ። በዚሁ መሠረት በመንፈስ ቅዱስ ካልተሞላ ከርስቲያን ይልቅ የተሞላው በፍጥነት በመንፈስ ያድጋል። በመንፈስ ቅዱስ መሞላትና ውጤቱ የሆነው መንፈሳዊ እድገት፥ እግዚአብሔር ለሕይወቱ ያለውን ፈቃድ ለማግኘት፥ የእርሱንም እቅድ በመፈጸም ረገድ በክርስቲያን ሕይወት የሚከናወኑ ሁለት ዋና ዋና ነገሮች ናቸው (ኤፌ. 2፡10)። 

በዚህ መሠረት የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ለማንኛውም አማኝ የሚደረግ ነው። ይህ የሚሆነው ግን አማኙ ሕይወቱን ሙሉ በሙሉ ውስጡ ለሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ሲያስገዛ ይሆናል። ይህ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ግለሰቡን ይቆጣጠረዋል፥ ኃይልም ይሰጠዋል። የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የሚገለጥባቸው ሁኔታዎችና የሚሰጠው መለኮታዊ ኃይል ደረጃም ያላያዩ ይሆናል። በመንፈስ ቅዱስ የመሞላት ማዕከላዊ አሳብ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለ ምንም መከልከል በአማኙ ውስጥና በርሱ በኩል ይሠራል የሚል ነው። እግዚአብሔር ለዚያ ሰው ያለው ፍጹም ፈቃድ እንዲህ ይከናወናል። 

የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ፅንሰ አሳብ አዲስ ኪዳን ውስጥ በርከት ባሉ ጥቅሶች ተመልክቷል። እጅግ በላቀ ሁኔታ የታየው፥ ሉቃስ 4፡1 ውስጥ “መንፈስ ቅዱስ ሞልቶበት፥ በተባለው በኢየሱስ ነው። መጥምቁ ዮሐንስ እናቱ ማኅፀን ውስጥ እንዳለ በመንፈስ ቅዱስ በመሞላቱ በሌሎች ያልተላመደ ልምምድ በረው (ሉቃስ 1፡15)። እናቱ ኤልሳቤጥና አባቱ ዘካርያሰም ለጊዜው በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ነበር (ሉቃስ 1፡41፥ 67)። ይህን የመሰለው የመንፈስ ቅዱስ ሙላት፥ ለጥቂት ሰዎች ብቻ የሚደረግና ሰብሉይ ኪዳን በተደረገው አኳኋን የሚከናወን የልዑል እግዚአብሔር እሠራር ነው። 

በጰንጠቆስጤ ዕለት ግን በዚያ የነበሩት ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተዋል። ሰጥንታዊቱ ቤተ ክርስቲያን፥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ የፈለጉ ሁሉ፥ በጴጥሮስ እንደሆነው (ሐዋ. 4:8) በተደጋጋሚ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተዋል። ለእግዚአብሔር ኃይልና ብርታት የጸለዩ ክርስቲያኖች (ሐዋ. 4፡31)፥ ጳውሎስም ከተለወጠ በኋላ (ሐዋ. 9፡17) እንዲሁ ተሞልቷል። አንዳንዶች፥ ማለት የመጀመሪያዎቹ ዲያቆናት፥ (ሐዋ. 6፡3)። ሰማዕቱ እስጢፋኖስ (ሐዋ. 7:55) እና በርናባስ (ሐዋ. 11፡24) በተከታታይ በመንፈስ ቅዱስ እንደተሞሉ ተናግሯል። ጳውሎስ በተደጋጋሚ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቷል (ሐዋ. 13፡9)፤ ሌሎች ደቀ መዛሙርትም እንዲሁ (ሐዋ. 13: 52)። በእያንዳንዱ ሁኔታ በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉት ራሳቸውን ለእግዚአብሔር የሰጡ ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው። 

የብሉይ ኪዳን አማኞች በአንዳንድ ሁኔታዎች ተግሣጽ ቢሰጣቸውም በመንፈስ ቅዱስ እንዲሞሉ ሰፍጹም አልታዘዙም። የእግዚአብሔር ሥራ መከናወኑን አስመልክቶ ዘሩባቤል በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፡(ዘካ. 4፡6) ተብሏል። በዚህ ዘመን ክርስቲያን ሁሉ ኤፌሶን 5፡18 ውስጥ እንደተመለከተው በመንፈስ ቅዱስ እንዲሞላ ታዟል። “መንፈስ ቅዱስ ይሙላባችሁ እንጂ፥ በወይን ጠጅ አትስከሩ፥ ይህ ማባከን ነውና።” ድነት በእምነት እንጂ በሥራ እንደማይገኝ፥ በመንፈስ ቅዱስ መሞላትም በሰብአዊ ጥረት የሚሆን አይደለም። ያ የሚሆነው፥ አንድ ሰው እግዚአብሔር በሕይወቱ ይህን የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ይሠራ ዘንድ ሲፈቅድ ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንረዳው፥ አንድ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ሳይሞላ ድነትን ሊያገኝ ይችላል። በዚህ መሠረት የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የድነት አንዱ አካል አይደለም ማለት ነው። የመንፈስ ቅዱስ ሙላት አንድ አማኝ በዳነ ጊዜ ለአንዴና ለዘላለም በሕይውቱ ከተከናውነው ሥራ ጋር ሊገናዘብ ይችላል። አንድ ሰው ድነትን ሲያገኝ በመንፈስ ቅዱስ ሊሞላ ቢችል እንኳን፥ ክንውኑ ሕይወቱን ከሰጠ ክርስቲያን ውስጥ በተደጋጋሚ የሚፈጸም ነው። በመሆኑም ይህ ተደጋጋሚ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የክርስቲያኖች የዘወትር ልምምድ ሊሆን ይገባል። 

በመንፈስ ቅዱስ መሞላት በተደጋጋሚ መፈጸም ያለበት መሆኑ ኤፌሶን 5፡18 ውስጥ “መንፈስ ይሙሳሳችሁ” በሚለው ቃል ተገልጧል። ቃሉ “ሁልጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ” የሚል ቀጥተኛ ፍቺ ነው ያለው። ይህ ቃል ምንባቡ ውስጥ ሰውነትንና አእምሮን ከሚጎዳ ስካር ጋር ተነጻጽሯል። ስለዚህ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት አንድ ጊዜ ለዘላለም የሚሆን ነገር አይደለም። በተደጋጋሚ የሚከናወን ነገር ሆኖ ሳለ፥ አልፎ አልፎ እንደሚሰማው ሁለተኛ የጸጋ ሥራ መባሉ ግን ተገቢ አይደለም። ለመጀመሪያ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ የመሞላት ልምምድ ያለ ጥርጥር ለክርስቲያን አስደናቂ ሁኔታ ነው። የክርስትና ልምምድንም ወደ አዲስ ከፍታ የሚያወጣ የመሠረት ድንጋይ ሊሆንም ይችላል። ያም ሆነ ይህ ክርስቲያን ለማያቋርጥ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት በእግዚአብሔር ነው የሚተማመነው፤ በትላንትናው መንፈሳዊ ኃይል የሚኖር ክርስቲያን የለም። 

በመንፈስ ቅዱስ ከመሞላት ምንነት በመነሣት በክርስቲያኖች መንፈሳዊ ልምምድና በእግዚአብሔር ዓላማ እንዲሁም ፍላጎት መጣጣም መካከል ሰፊ ልዩነት የሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ከመሞላት ወይም ካለመሞላት የተነሣ ነው ብሎ ለመደምደም ይቻላል። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም የሚፈልግ አማኝ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ እንዲሆን ከእግዚአብሔር ወደተሰጠው መብት መግባትና ሕይወቱንም ለእግዚአብሔር መንፈስ ሙሉ በሙሉ ማስረከብ ይኖርበታል። 

ለ. ለመንፈስ ቅዱስ ሙላት የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች 

በመንፈስ ቅዱስ መሞላት የሚያስፈልጉ ሦስት ቀላል ትእዛዛት ተጠቅሰዋል። እነርሱም የሚከተሉት ናቸው። 

የመጀመሪያዎቹ ሁለት ክፍሎች አሉታዊ ትእዛዞች ሲሆኑ፥ ሦስተኛው አዎንታዊ ነው። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡19 ውስጥ “መንፈስን አታጥፉ” የሚል ትእዛዝ ተሰጥቷል። ኤፌሶን 4፡30 ውስጥ ደግሞ ክርስቲያኖች “ለቤዛ ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ” ተብለዋል። ሦስተኛው ትእዛዝ ጎላትያ 5፡16 ውስጥ የተጠቀሰው ሲሆን “ነገር ግን እላለሁ ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ” ይላል። ስለ መንፈስ ቅዱስ ሙላት የሚያስረዱ ሌሎች ክፍሎች ቢኖሩም፥ እነዚህ ሦስቱ ዋና ዋናዎችን ያጠቃልላሉ። 

1. መንፈስን አታጥፉ” ተብሎ 1ኛተስሎንቄ 5፡19 ውስጥ fተሰጠው ትእዛዝ፥ እገሰቡ በደንብ የተለጠ ሳይሆንም፥ መንፈስ ቅዱስን ስእሳት ምሳሌነት ዮሚያሳይ መሆን ግለጥ ነው። “ማጥፋት” ማለት መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ውስጥ ፈቃዱን እንዳይፈጽም ማፈን ወይም ነጻነትና ፈቃድ መከልከል ማለት ነው። በቀላሉ ሲገለጥ መንፈስ የራሱን ፈቃድ እንዳያደርግ (“እምቢ” ማለት ወይም ፈቃደኛ አለመሆን ሊሆን ይችላል። 

በእግዚአብሔር ላይ ማመፅ የሰይጣን የመጀመሪያ ኃጢአት ነበር (ኢሳ. 14፡14)፤ እናም አንድ ክርስቲያን ክርስቶስ በጌቴሴማኒ እንዳደረገው “የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ” ( ሉቃስ 22: 42) በማለት ፈንታ የእኔ ፈቃድ ይሆናል”፥ በሚልበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ማጥፋቱ ነው። 

አንድ አማኝ የመንፈስ ቅዱስ ሙላትን ለመለማመድ ይችል ዘንድ በመጀመሪያ ሕይወቱን ለጌታ ማስረከብ አለበት። አንድ ሰው ሁለት ጌቶችን ሊያገላግል እንደማይችል ክርስቶስ ገልጧል (ማቴ. 6፡24)። ክርስቲያኖችም ራሳቸውን ስእግዚአብሔር እንዲሰጡ በተከታታይ ተመክረዋል። የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቲያን ሕይወት የሚከናወንበትን ጠቅላላ ሁኔታ ጳውሎስ ሮሜ 6፡13 ውስጥ ሲያስተዋውቅ፥ “ብልቶቻችሁን የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፤ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ። ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ” ብሏል። ምርጫው በእያንዳንዱ ክርስቲያን ፈት ተቀምጧል። ራሱን ለእግዚአብሔር ወይም ኃጢአት ሊሰጥ ይችላል። 

ሮሜ 12:1-2 ውስጥም ተመሳሳይ ምንባብ አለ። ጳውሎስ በእንድ ክርስቲያን ሕይወት ድነትና ቅድስና የሚያድግበትን ሁኔታ ለሮሜ ሰዎች ሲገልጥ፥ “እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው። የእግዚአብሔር ፈቃድ፥ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ፥ ይህን ዓለም እትምሰሉ” እያለ ያሳስባል። ሮሜ 6፡13 እና 12፡1 ውስጥ “ራሳችንን ለእግዚአብሔር ማቅረብ የሚለው የግሪኩ አባባል ያለው ስሜት “ለአንዴና ለዘላለም ራስን ለእግዚአብሔር መስጠት” የሚል ነው። በመሆኑም በመንፈስ ቅዱስ ለመሞላት የሚቻለው፥ ክርስቲያን መላ ሕይወቱን ሕያው መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር የማስረከቡን ቀዳሚ እርምጃ የወሰደ እንደሆን ብቻ ነው። ክርስቲያን ለዚህ ዕድል የሚዘጋጀው፥ መሥዋዕቱን ቅዱስና በእግዚአብሔር ዘንድ ብቁ በሚያደርገው ድነቱ አማካይነት ነው። ለዚህ ድነትን ለሚቀበል ሰው ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተለት ስለሆነ፥ እግዚአብሔር ከዚያ ሰው ይህን ሁኔታ መጠበቁ ተገቢ ነው። 

ክርስቲያን ራሱን ለእግዚአብሔር በሚያቀርብበት ጊዜ፥ የውስጥ ሰውነቱ በመንፈስ ቅዱስ የሚለወጥበትና፥ ክዚህ የተነሣ የእእምሮ መታደስን በማግኘቱ የመንፈሳዊ እውነቶችን ክቡርነት የሚገነዘብበት ሂደት ነው። ራሱን ለጌታ በማቅረቡ ይህን ዓለም የማይመስልን ሕይወት ይኖራል። የእግዚአብሔር ፈቃድ ያልሆነውን ከ እግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር” ሮሜ 12፡2 ለመለየት ይችላል። 

ራስን መስጠት የሚያመለክተው አንድን የተለየ ጉዳይ ሳይሆን፥ በማንኛውም ረገድ እግዚአብሔር ለሕይወቱ ያለውን ፈቃድ ያ ሰው መውሰዱ ነው። ስለዚህ ራስን መስጠት ማለት፥ እግዚአብሔር አማኙ እንዲያደርግ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆን ማለት ነው። የእግዚአብሔርን ፈቃድ በሕይወቱ መፈጸም እና እርሱ ሲመራ ማንኛውንም ነገር መቼም የትም እና እንደ ምንም ለማድረግ ፈቃደኛ ሆኖ መገኘት ነው። “መንፈስን አታጥፋ” የሚለው ትእዛዝ የሚያመለክተው፥ ይህ ሁኔታ ራስን በመስጠት የሚጀምርና የሚቀጥል ልምምድ መሆኑን ነው። 

ባለማቋረጥ ራሱን ለእግዚአብሔር ለመስጠት የሚመኝ ክርስቲያን፥ ድርጊቱ ከብዙ ሁኔታዎች ጋር የሚዛመድ ሆኖ ያገኘዋል። ራስን መስጠት ከሁሉ በፊት ለእግዚአብሔር ቃል ትምህርትና እውነት መገዛት ነው። ታላቁ መምህር መንፈስ ቅዱስ ሲሆን፥ አንድ አማኝ እውነትን በተረዳ ቁጥር ላወቀው እውነት መግዛት አለበት። ለእግዚአብሔር ቃል አለመገዛት የመንፈስ ቅዱስ ሙላትን ይከላከላል። 

ራስን መስጠት ካምሪት ጋርም ይያያዛል። በብዙ ሁኔታዎች የእግዚአብሔር ቃል ክርስቲያን ሊወስነው የሚጎባውን ነገር በግልጥ አያስረዳም። ስለዚህ አንድ አማኝ በእግዚአብሔር ቃል መመራት አለበት፥ የእግዚአብሔር መንፈስም ቃሉ በሚገልጠው ላይ በመመሥረት ምሪት ይሰጣል። በመሆኑም በመንፈስ ቅዱስ ለመሞላት ለመንፈስ ቅዱስ ምሪት መታዝ ያሻል (ሮሜ 8፡14)። አንዳንድ ጊዜ ክርስቲያን አንድ ነገር ያደርግ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ያዘው፥ በሌላ ሁኔታ ደግሞ ይከለክለው ይሆናል። አንዱ ምሳሌ በአገልግሎቱ መጀመሪያ ወቅት እስያና ቢታኒያ ውስጥ እንዳይሰብክ የተከለከለው ጳውሎስ ነው። በኋላ ግን ወደነዚሁ ስፍራዎች እንዲሄድና እንዲሰብክ ታዟል (ሐዋ. 16፡6-7፤ 19፡10)። የመንፈስ ቅዱስ ሙላትና ጌታ መመራት የማይነጣጠሉ ናቸው። 

አንድ ክርስቲያን የማይፈልገው ሁኔታና ልምምድ ውስጥ የሚከተው ቢሆን እንኳን ለእግዚአብሔር ምሪት መገዛት አለበት። ስለዚህ ጉዞው ሥቃይ ያለበትና ደስ የሚያሰኝ ቢሆንም እንኳ፥ ለእግዚአብሔር ፈቃድ መገዛት ማለት ምን ማለት መሆኑን አማኝ መገንዘብ እለበት። 

በመንፈስ ቅዱስ የመሞላትና ለእግዚአብሔር የመሰጠት ታላቅ ምሳሌ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ነው። ፊልጵስዩስ 2፡5-11 ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር በመምጣቱና ለዓለም ኃጢአት በመሞቱ፥ እግዚአብሔር ወደመረጠው መሄድንና እብ የመረጠውን ሥራ መፈጸምን ያሳያል። በመንፈስ ቅዱስ ለመሞላት የሚመኝ አማኝ ይህን የመሰለ መሰጠትና ታዛዥነት ሊኖረው ይገባል። 

2. በመንፈስ ቅዱስ ከመምላት ጋር በተያያዘ ሁኔታ፥ እማኝ “መንፈስ ቅዱስን እንዳያሳዝን” (ኤፌ. 4፡30 ተመክሯል። ይህ ከፍል ኃጢአት ወደ ከርስቲያኑ ሕይወት መግባቱንና ራሱንም ለጌታ እለመስጠቱን ያመለክታል። በመሆኑም ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ሕይወት እንዲኖረው፥ መንፈስ ቅዱስን የሚያሳዝን ኃጢአት እንዳይሠራ ታዟል። አማኝ ውስጥ ያለ የእግዚአብሔር መንፈስ ሲያዝን፥ ከአማኙ ጋር ያለው አንድነት፥ ምሪት፥ ትምህርቱ እና የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይታገዳል። ምንም እንኳን መንፈስ ቅዱስ በአማኙ ውስጥ ሲኖር፥ ሥራውን ለማከናወን ነጻ አይደለም። 

የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ልምምድ በአማኙ አካላዊ ሁኔታ ሳቢያም ይታጎል ይሆናል። የደከመ፥ የራበው ወይም ሕመምተኛ ክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ የሆኑት ትከክለኛ ደስታና ሰላም በሕይወቱ እይታዩ ይሆናል። በመንፈስ ቅዱስ ስላ መሞላት የሚናገረው ሐዋርያ ራሱ 2ኛ ቆሮንቶስ 1፡8.9 ውስጥ “ስለ ሕይወታችን እንኳ ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከአቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶብን ነበር ብሏል። ስለዚህ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ክርስቲያንም ውስጣዊ መሽበር ይገጥመው ይሆናል። ይሁን እንጂ የአማኙ ችግር የከፋ ሰሆን መጠን፥ በመንፈስ ቅዱስ የመሞላቱና ለእግዚአብሔር ፈቃድ የመገዛቱ አስፈላጊነት የጎላ ይሆናል፤ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በግለሰቡ ሕይወት ይገለጥ ዘንድ ነው። 

አንድ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስን ያሳዘነ መሆኑ ሲሰማው፥ መፍትሔው ኤፌሶን 4፡30 ውስጥ እንደተጻፈው መንፈሱን የሚያሳዝነውን ድርጊት ማቆም ነው። ይህ ሊፈጸም የሚችለው 1ኛ ዮሐንስ 1፡9 ውስጥ የተጠቀሰውን በመታዘዝና አንድ የእግዚአብሔር ልጅ ያደርገው ዘንድ የተገባን ነገር በማድረግ ነው፡– “በኃጢአታችን ብንናዘዝ፥ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያድነን የታመነና ጻድቅ ነው። ይህ ጥቅስ የሚመለከተው በሰማይ አባቱ ዘንድ ኃጢአት የፈጸመን የእግዚአብሔር ልጅ ነው። የክርስቶስ ሞት ለኃጢአት ሁሉ ሥርየት በቂ ሰመሆኑ፥ የመመለሻው ወይም ይቅርታ የማግኛው መንገድ ክፍት ነው (1ኛ ዮሐ. 2፡1-2)። 

ስለዚህ አንድ አማኝ ከእግዚአብሔር ጋር ወዳለው አንድነት የመመለሻው መንገድ፥ የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት የይቅርታ መሠረት መሆኑን በመገንዘብ ነው። ይህ ብቻም አይደል፥ ከእግዚአብሔር አብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋ እንደገና የቀረበ ግንኙነት ለመጀመር መፈለግ ወይም መወሰንም ያስፈልጋል። ይህ ሁኔታ በፍርድ ቤት የሚታይ የፍትሕ ጉዳይ ሳይሆን፥ በአባትና ልጅ መካከል ጠፍቶ የነበረውን ግንኙነት እንደገና መቀጠል ነው። እግዚአብሔር ኃጢአትን ይቅር የሚል ቅን ፈራጅና ታማኝ መሆኑን ጥቅሱ ያረጋግጣል። አንድ ክርስቲያን እግዚአብሔርን እንደበደለ አምኖ በቅንነት ንስሐ ሲገባ ሰግንኙነቱ መካከል እንደ ግድግዳ የቆመው በደል ይገዳል። የኃጢአት ንስሐ በአንዳንድ ሁኔታዎች በደል ወደተሠራባቸው ሰዎች መሄድንና ችግሩን ማስተካከልን የሚጠይቅ ቢሆንም፥ ዋናው ጉዳይ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረትን በመመሥረት ተከናውኗል። 

አንድ ክርስቲያን ሲናኝ ሰመለኮት በኩል ያለው ነገር ወዲያውኑ እንደሚስተካከልለት ዋስትና አለው። ክርስቶስ የእማኙ አማሳጅ ወይም አስታራቂና በመስቀል ላይ የሞተለት እንደመሆኑ፥ በሰማይ ያለውን አስፈላጊ ማስተካከያ ሁሉ አስቀድሞ እከናውኗል። ዕለዚህ ወደ አንድነቱ የመመለሱ ጉዳይ በሰብአዊው በኩል የሚከናወን ንስሐና ራስን የመስጠት ተግባር ነው። 

መጽሐፍ ቅዱስ አማኝ መንፈስ ቅዱስን በተከታታይ በማሳዞን ሳቢያ የመጣበት ክፉ ሁኔታ መኖሩንም ያስጠነቅቃል። ዕብራውያን 12፡5-6 ውስጥ እንደተመለከተው ይህ ምናልባት እማኙን ለማስተካከል ሲባል ከእግዚአብሔር የሚመጣ ቅጣት ሊሆን ይችላል። ክርስቲያን ራሱን ባያስተካክል እግዚአብሔር በመለኮታዊ ማስተካከያው ጣልቃ እንደሚገባ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል (1ኛ ቆሮ. 11፡31-32)። ክርስቲያን በማንኛውም ሁኔታ ከእግዚአብሔር ጋር ካለው እንድነት ሲርቅ ወዲያውኑ የሚያጣው ነገር አለ። ልክ ታማኝ አባት ባጠፋ ልጁ ላይ እንደሚያደርገው ሁሉ ተከታታይና ከባድ ቅጣት የማስከተል አደጋም ይኖራል። 

3. በመንፈስ ቅዱስ መመላለስ፥ ከላይ ከተመለከትናቸው ትእዛዛት ጋር ሲነጻጸር እዎንታዊ ሳይሆን አሉታዊ ነው። በመንፈስ ቅዱስ መመላለስ ማለት (ገላ. 5፡16) ከመንፈስ ቅዱስ የሚገኘውን ኃይልና በረከት እንድንቀበል የሚያስገነዝብ ትእዛዝ ነው። ክርስቲያን ሁልጊዚ በመንፈስ ምሪት እንዲጓዝ ታዟል። 

የክርስቲያን መንፈሳዊ ሕይወት ደረጃ በጣም ከፍተኛ ነው፤ ያለ እግዚአብሔር ኃይል የአምላክን ፈቃድ ሊፈጽም አይችልም። በመሆኑም በውስጡ ያለው መንፈስ ቅዱስ በሚገባ እንዲመላለስ ይመራዋል። 

በመንፈስ ቅዱስ መመላለስ እምነትን ያካተተ ነው። በመሆኑም መንፈስ ቅዱስ የሚያደርገውን ብቻ ለማድረግ በርሱ ላይ መታመን ያሻል። ክርስቶስ እንደወደደን እንድንዋደድ (ዮሐ. 13፡34፤ 15፡12) እና አእምሮ ሁሉ ለክርስቶስ እንዲገዛ የታዘዘበት (2ኛ ቆሮ. 10፡5)፥ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው የዚህ ዘመን ትእዛዛት ያለ መንፈስ ቅዱስ እርዳታ አይቻሉም። በተመሳሳይ ሁኔታ፥ ሌሎች የመንፈሳዊ ሕይወት መገለጫዎች ማለት እንደ መንፈስ ፍሬዎች (ገላ. 3፡22-23)፥ “ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፥ ሳታቋርጡ ጸልዩ” (1ኛ ተሰ. 5፡16-17) እና “ሰሁሉ አመስግኑ፥ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና” (1ኛ ተሰ. 5፡18)የሚሉት እሳሶች ሰው በመንፈስ ካልተመላለሰ በቀር ለማድረግ የማይቻሉት ናቸው። 

ክርስቲያን ኃጢአት በሞላበት ዓለምና የማያቋርጥ ክፉ ተጽዕኖ ባለበት ሁኔታ ውስጥ ስለሚኖር፥ በመንፈሳዊ ሕይወት ክፍተኛ ደረጃ ላይ ለመድረስ በጣም ያስቸግረቸዋል (ዮሐ. 17፡15፤ ሮሜ 12፡2፤ 2ኛ ቆሮ. 6፡14፤ ገላ. 6፡14፤ 1ኛ ዮሐ. 2፡15)። በተመሳሳይ ሁኔታ ክርስቲያን በሰይጣን ተቃውሞ ይደርስበታል። ከዚህ የእግዚአብሔር ጠላት ጋርም በማያቋርጥ ውጊያ ውስጥ ነው (2ኛ ቆሮ. 4፡4፤ 11፡14፤ ኤፌ. 6፡12)። 

ክርስቲያን ከዓለምና ከሰይጣን ከሚመጣበት ተቃውሞ በተጨማሪ፥ በውስጡም ጠላት አለበት። ያም አሮጌውን ሰው ወደ አለመታዘዝ ሕይወት ሊመልሰው የሚሻ ኃጢአታዊ ተፈጥሮ ነው (ሮሜ 5፡21፤ 6፡6፤ 1ኛ ቆሮ. 5፡5፤ 2ኛ ቆሮ. 7፡1፤ 10፡2-3፤ ጎሳ. 5፡16-24፤ 6፡8፤ ኤፌ. 2፡3)። ኃጢአታዊው ተፈጥሮ ክርስቲያን ውስጥ ካለው አዲስ ተፈጥሮ ጋር የማያቋርጥ ውጊያ ሰለሚያደርግ፥ እርሱን ድል ለማድረግ የሚቻለው፥ ሁል ጊዜ በእግዚአብሔር መንፈስ ላይ በመታተዝ ብቻ ነው። ለዚህ ነው ምንም እንኳን አንዳንዶች ክርስቲያን ወደ ኃጢአት የዕሽ ፍጹምነት ይደርሳል ብለው በተሳሳተ ሁኔታ ሲገልጡ፥ ይህ ኃይል ሰሕይወት ውስጥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ያከናውን ዘንድ የአማኙ ባለማቋረጥ በመንፈስ ቅዱስ መመላለስ አስፈላጊ የሚሆነው። በአካልና በመንፈስ ፍጹም የመሆኑ ነገር በሰማይ ነው አማኙን የሚጠብቀው፤ ስለሆነም እስከሞት ወይም እስከመነጠቅ ድረስ መንፈሳዊ ውጊያው ይቀጥላል። 

እነዚህ እስካሁን የተመለከትናቸው እውነቶች አንድ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስ ሕይወቱን እንዲቆጣጠርና እንዲመራው በመፍቀድ በርሱ ኃይልና ምሪት መመላለስ ያለበት መሆኑን የሚያመለክቱ ናቸው። 

ሐ. በመንፈስ የመሞላት ውጤቶች 

አንድ ሰው ራሱን ለእግዚአብሔር አሰረክቦ በመንፈሰ ቅዱሰ በሚሞላበት ጊዜ የሚከተሉት እጅግ አስደናቂ ውጤቶች በሕይወቱ ይታያሉ። 

1. በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚመላለስ ክርስቲያን የሚያድግ እና የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች የሚታዩበት የሕይወት ቅድስና ይታይበታል (ገላ. 5፡22-23)። ይህ ሕይወት የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በአማኝ ላይ የመሥራቱ ምሳሌያዊ መገለጫ ነው። የመንፈስ ቅዱስ ኃይል መገለጫ ብቻ ሳይሆን፥ አማኝ ወደፊት በሰማይ ክርሰቶስን በመምሰል ለሚገለጥበት ወቅት ምድራዊ ዝግጅት ነው። 

2. ከመንፈስ ቅዱስ ዋና ዋና አገልግሎቶች አንዱ፥ ለአማኙ መንፈሳዊ እውነትን ማስተማር ነው። አማኝ የእግዚአብሔርን ቃል ፍፁም እውነት ሊረዳ የሚችለው፥ በመንፈስ ቅዱስ ምሪትና አብርሆት ብቻ ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ ለአንድ ሰው የድነትን እውነት ለመግለጥ አስፈላጊ የመሆኑን ያህል (ዮሐ. 16፡7-11)፥ ክርስቲያኑንም ወደ እውነት ሁሉ ይመራዋል (ዮሐ. 16፡12-14)። የእግዚአብሔር ጥልቅ ነገሮች እና በመንፈስ ቅዱስ የተማረ ሰው ብቻ የሚረዳው እውነት፡በመንፈሰ ለሚመላለስ ሰው ብቻ ነው የሚስጠው (1ኛ ቆሮ. 2፡9-3፡2)። 

3. መንፈስ ቅዱስ እንድኝ ክርስቲያን ሊመራና የእግዚአብሔርን ቃል አጠቃላይ እውነት ክርስቲያኑ ላለበት ልዩ ሁኔታ ሊያውለው ይችላል። ሮሜ 12፡2 ውስጥ “የእግዚአብሔር ፍቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ” ሲል ይህንኑ ማለቱ ነበር። ብሉይ ኪዳን ውስጥ እንደነበረው የአብርሃም አገልጋይ ክርስቲያንም “እኔ በመንገድ ሳለሁ እግዚአብሔር መራኝ” (ዘፍጥ. 24፡27) ማለትን ሊለማመድ ይችላል። ይህ ዓይነቱ አመራር ከእግዚአብሔር መንፈስ ጋር ተገቢው አንድነት ባላቸው ክርስቲያኖች የታወቀ ልምምድ ነው (ሮሜ 8፡14፤ ገላ. 5፡18)። 

4. የድነት ሦስትና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ከሚኖር አንድነት ሦሚገኝ ሌላ ጠቃሚ ውጤት ነው። በሮሜ 8፡16 መሠረት የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል” (ይህን አባባል ከገላ. 4፡6፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡24፤ 4፡13 ጋር ያነጻጽሩት)። ክርስቲያን ስለ ደኅንነቱ እርግጠኛነት ሊኖረው የሚገባ መረዳት ልክ አንድ ሰው በአካል ስለመኖሩ እርግጠኛ የመሆኑን ያህል ነው። 

5. አንድ ሰው እግዚአብሔርን ለማፍቀርናለርሱ ለመስገድ የሚችለው፥ በመንፈስ ቅዱስ ሲመላለስ ነው። ኤፌሶን 5፡18 ውስጥ ከተጠቀሰው ምክር ቀጥሎ ያሉት ምንባቦች የሚገልጡት፥ ትከከለኛውን አምልኮና ከእግዚአብሔር ጋር ሊኖር የሚገባን አንድነት ነው። ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት የሌለው ሰው ባማረ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቢያመልክና ሥርዓቶችን ሲፈጽም፥ እግዚአብሔርን በእውነት እመለከ ማለት እይደለም። እምልኮ ክርክስቶስ ላሳምራዊቱ ሴት “እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል” (ዮሐ. 4፡24) እንዳለው ከልብ የሚሆን ነገር ነው። 

6. በእንድ አማኝ ሕይወት እጅግ ጠቃሚ ከሆኑ ነገሮች እንጂ ከጌታ ጋር በጸሎት አማካይነት ያለው ንድነት ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ ጸሎትን ሲያግዝና ሲመራ፥ ጸሎት ሥርዓት ያለውና ትክክለኛ ይሆናል። ጸሎቱ በእግዚአብሔር ቃል መሠረት እንዲሆን ከተፈለገም ቃሉ ሊጠና ይገባል። መንፈስ ቅዱስ ካልረዳ በቀር እውነተኛ ምስጋናና አምልኮ አይቻልም። አማኝ ከሚያቀርበው ጻሉት በተጨማሪ መንፈስ ቅዱስም እንደሚማልድለት ሮሜ 8፡26 ይገልጣል። ብርቱ የጸሎት ሕይወት የሚገኘው በመንፈስ ቅዱስ ከመመላለስ ነው። 

7. እስካሁን ከተጠቀሱት መንፈሳዊ ብቃቶች በተጨማሪ፥ የአማኙ የአገልግሎት ሕይወት፥ የተፈጥሮና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎቹ ልምምዶች በአጠቃላይ ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚገኙ ናቸው። ክርስቶስ ይህን በተመለከተ ዮሐንስ 7፡38-39 ውስጥ ሲጠቅስ፥ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ከሰው ልብ የሚወጣና እንደሕያው ውኃ ምንጭ የሚፈስ መሆኑን አስገንዝቧል። ስለዚህ አንድ ክርስቲያን ታላላቅ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ሊኖሩት፥ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የማይመላለሰ በመሆኑ ሊጠቀምባቸው የማይቻለው ይሆን ይሆናል። በአንጻሩ ደግሞ ጥቂት መንፈሳዊ ስጦታዎች ያሏቸው ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በመመላለሳቸው እግዚአብሔር በጣም የሚጠቀምባቸው ሊሆኑ ይችላሉ። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሙላት የሚያስተምረውን ክርስቲያን በሚገባ ሊረዳ፥ በተግባር ሊተረጉመው፥ ሊጠቀምበት የሚገባ በጣም አስፈላጊ የሆነ እንዱ እውነት ነው።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

20
ትምህርት 20 ከ52

ሥፍረ-ዘመናት

ሀ. የሥፍሩ-ዘመናት ትርጉም 

መጽሐፍ ቅዱስ በሚጠናበት ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል መገለጥ ሥርዓትን በተከተስ መንገድ በተጎለጡ ወቅቶች መመደቡን መረዳት ይገባል። እነዚህ ጊዜያት የተለዩ በመሆናቸው በየምድባቸው ለይቶ ማወቁ የመለኮታዊ ዓላማ አሠራርን ሰመረዳትና ትክክለኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ለማወቅ ወሳኝ ነው። እነዚህ የእግዚአብሔር የመለኮታዊ ዓላማና አሠራር ጊዜያት “ሥፍረዘመናት” ተብለው ይታወቃሉ። በመሆኑም በእግዚኦብሔር አሠራር ውስጥ ዘመናት የተለያየ ስፍራ ስላላቸውና፥ የሚስኩትም በእርሱ የሥራ ዘመን በመሆኑ ተከታታይ ሥፍረ-ዘመናት ተለይተው ይታያሉ። 

ሥፍረዘመን ማለት ለየት ባሉ ዘመናት እግዚአብሔር ሰዎችን የመራበትና የሕይወት መመሪያ የሰጠባቸው የጊዚ ክልል ማለት ነው። በእያንዳንዱ ዘመን ውስጥ ሰዎች የእግዚአብሔር መመሪያን መከተል ተስኗቸው ወድቀዋል። ስለዚህ ከውድቀታቸው የተነሣ እያንዳንዱ ሥፍረ-ዘመን በእግዚአብሔር ፍርድ መገለጥ ያጠቃለሳል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ሥፍረ- ዘመን” እና “ዘመን አንድ አይደሉም። ነገር ግን እያንዳንዱ ዘመን የራሱ የሆነ ሥፍረ-ዘመን ኦለው። ዘመናት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሰዋል (ኤፌ. 2፡7፤ 3፡5፡9፤ ዕብ. 1፡2)። ዘመናት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተለይተዋል (ዮሐ. 1፡17ን፤ ከማቴ. 5፡21-22፤ 2ኛ ቆሮ. 3፡11፤ እና ከዕብ. 7፡11-12 ጋር አስተያዩ)። 

ከሌላ ከማንኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናን ዘዴ ይበልጥ የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክቶች ለመረዳት የሚጠቅመውና ሰሚገባም የሚገልጠው፥ የእግዚአብሔርን አሠራር ሥፍረ-ዘመናት ማወቅና መረዳት ነው። (* አውግስጢኖስ (354-430 ዓ.ም.) እንዲህ አለ፡- “በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሱ ዘመናትን በትክክል መለየት ከቻልኝ፥ የመጽሐፍ ቅዱስን የተያየዘና ወጥ መሆንን በደንብ እንረዳለን።”) የእግዚአብሔርን ሥፍረዘመናትና፥ ከእነርሱም ውስጥ የተገለጡትን መለኮታዊ ዓላማዎች ውጤቶች በቅድሚያ መረዳት ራሱ የመጽሐፍ ቅዱስን ጠቃሚ እውቀት የመረዳት መጀመሪያ ከመሆኑም ባሻገር፥ ለመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ያለንን ፍላጎት ይቀሰቅሳል። የሰውና የእግዚአብሔር ግንኙነት በየዘመናቱ ሁሉ አንድ ዓይነት አይደለም። በኃጢአት የተበከለውን ሰው በመለኮታዊ ሚዛን ውስጥ አስገብቶ መፈተን አስፈላጊ ነው። ይህ ደግሞ በከፊል በየዘመናቱ የሚታይ የእግዚአብሔር ዓላማ ነው። የፈተናውም ውጤት የሚያሳየው፥ ሰው በማያጠያይቅ ደረጃ ፍጹም በሆነ የውድቀትና የኃጢአተኛነት ሕይወት ውስጥ መሆኑን ያረጋግጣል። በመጨረሻም ሰው ሁሉ የልቡ ምኞትና አሳብ ስንፍናና ቅድስና እንደጎደለው በየዘመናቱ የተረጋገጠ መሆኑ የሚያስደንቅ እውነት ነው። 

እያንዳንዱ ሥፍራ-ዘመን የሚጀምረው ሰው አዲስ መብትና ኃላፊነት ውስጥ በመግባቱ ነው። ሥፍራ- ዘመኑ የሚያበቃው ደግሞ፥ ሰው የተሰጠውን ልዩ መብትና ኃላፊነት መወጣት ተስኖት በእግዚአብሔር ጻድቅ ፍርድ ሥር ሲሆን ነው። በየዘመናቱ ሁሉ ለሰው ዘር የሚሰጡ የተለያዩ አመራሮችና ኃላፊነቶች እንደየዘመናቱ ቢለያዩም፥ ዘላለማዊው የእግዚአብሔር የቅድስና ባሕርይ ግን እይላውጥም። 

ከዚህ ጋር በተያያዘ ሁኔታ፥ ማንኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ፥ የእግዚአብሔር ቃል መጀመሪያም ሆነ በሁለተኛ ደረጃ የተነገረው ለማን መሆኑን መረዳት ይኖርበታል። 

የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው ሁሉ ሰቀጥታ ላለበት ዘመን የሚመለከተውን ብቻ መጠቀምና መከተል ይገባዋል። እነዚህን የቃሉን መመሪያዎች ሙሉ በሙሉ እንዲፈጽም ይጠበቅበታል። በሁለተኛ ደረጃ መታየት ያለበት ደግሞ፥ ማንኛውም ክርስቲያን በሌሉች ዘመናት የተሰጡትን ሕጎችና መመሪያዎችን እንደ መንፈሳዊ ትምህርት ሊወስዳቸው ይችላል። በሌሎች ዘመናት ሰዎች እንዲመሩበት ጌታ የሚፈልገው ዓይነት ኑሮን ይኖር ዘንድ እግዚአብሔር አልመረጠውም። መገንዘብ ያለብን መጽሐፍ ቅዱስ የሁሉም ዘመናት ስለሆነ፥ ለሁሉም ዘመን የሚሆን መንፈሳዊ ትምህርት ያለው መሆኑን ነው። ለምሳሌ በዚህ ዘመን ያለ አማኝ፥ አዳም ወይም አብርሃም ወይም እስራኤላውያን በሕግ ይመሩ እንደነበረ የእግዚአብሔር ፈቃድና አሠራር በነበረበት ዘመን ሁኔታ ውስጥ አይደለም፤ ወይም ንጉሡ (ኢየሱስ) መጥቶ መንግሥቱን ምድር ላይ በሚመሠርትበት ወቅት የሚኖሩ ሰዎች ሊኖራቸው የሚገባን ልዩ ሕይወት እንዲኖርም አልተፈጠረም። 

የእግዚአብሔር ልጅ ለዕለታዊ ሕይወቱ አጠቃላይ መመሪያ ለማግኘት የሚችለው ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። ነገር ግን የተለያዩ ዘመናት መመሪያዎችና ሕጎች በጣም የተለያዩና አንዳንዴም የሚቃረኑ ይሆናሉ። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር የጸጋ ልጅ በቀጥታ እርሱን የሚመለከቱ የቃል ክፍሎች ለይቶ ቢያውቅ፥ የእግዚአብሔር ፈቃድና የእግዚአብሔር ክብር ምን እንደሆነ ተረድቶ በዚያው ለመመላለስ ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን አጠቃላይ ምዕክርነት በምናይበት ጊዜ፥ አንድ አማኝ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ተረድቶ እርሱንም ለመፈጸም ይችል ዘንድ ሰቀጥታ የማይመለከተውን ክፍል ማወቁ የሚመለከተውን የማወቅ ያህል አስፈላጊና ጠቃሚ ነው። ስለዚህ አንድ አማኝ የሥፍረ ዘመናትን በቂ እውቀት ሳያገኝ በአሁኑ ዘመን የእግዚአብሔር ዓላማና ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ተረድቶና አስተውሎ ራሱን ከሁኔታዎች ጋር ለማገናዘብ እይችልም። ይህ እውቀት ብቻ ነው በሕግ ይሆን የነበረውን ያለፈ ዘመንና፥ ገና ምንም ማድረግ የማይቻለውን መጪ ዘመን በማሰብ ልባችን እንዳይዝል የሚያደርገው። 

መጽሐፍ ቅዱስ ወደተለያዩ ቋንቋዎች በሚተረጎምበት ጊዜ፥ የዘመናት ትክክለኛ መግለጫ የሆኑ እንዳንድ ቃላት እገባብ ትክክል ያለመሆኑ ችግር አለ። ለምሳሌ በግሪክ ቋንቋ “አዮን” የሚለው ቃል በአማርኛ “ዓለም” ተብሎ ተተርጉሟል። የቃሉ ትክክለኛ ትርጉም ግን “ዘመን” ወይም “ሥፍረ-ዘመን” ማለት ነው። ማቴዎስ ወንጌል 13፡49 ውስጥ የተጠቀሰው “በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው፥ የቁሳዊውን ዓለም መጨረሻ (ኢሳ. 66 ፡22፤ 2ኛ ጴጥ. 3፡7፤ ራእይ 20፡11) ሳይሆን፥ ያለንበትን ዘመን መጨረሻ ነው። በመቃረብ ላይ ያለው የዓለም መጨረሻ ሳይሆን፥ የዘመኑ መጨረሻ ነው። በመጽሐፍ ቅዱሳችን መሠረት ሰባት ታላላቅ ሥፍረ-ዘመናት ያሉ ሲሆን፥ እኛ አሁን ያለንበት፥ የስድስተኛው ሥፍረ-ዘመን መዳረሻ ነው። የሺህ ዓመቱ መንግሥት ዘመን ገና ሊመጣ ነው (ራእይ 20፡4፥ 6)። 

በመሠረቱ አንድ ሥፍረ-ዘመን ከሌላው የሚለየው፥ በአዲስ መለኮታዊ አሠራርና በምሪት መጀመሩና በእነዚህም ላይ በሚሰጠው መለኮታዊ ፍርድ በመጠናቀቁ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙዎች የሚረዷቸው ሰባት ሥፍረ-ዘመናት፡-(1). የንጽሕና ሥፍረ ዘመን፥ (2) የሕሊና ሥፍረ-ዘመን (3) የሰብአዊ መንግሥት ሥፍረ-ዘመን፥ (4) የተስፋ ሥፍረ-ዘመን፥ (5) የሕግ ሥፍረ-ዘመን፥ (6) የጸጋ ሥፍረ-ዘመን፥ (7) የሺህ ዓመት መንግሥት ሥፍረ-ዘመን ናቸው። 

ዕባቱ ሥፍራ-ዘመናት ሰሚጠኑበት ጊዜ ትምህርቱን ለመረዳት የሚያግዙ አንዳንድ መመሪያዎች ያስፈልጋሉ። አንደኛው፥ የሥፍረ-ዘመናት ትምህርት የሚባለው ሲሆን፥ ይህ ትምህርት መጽሐፍ ቅዱስን የሚገነዘበው፥ ቃል በቃል በሆነ አተረጓጎም ላይ በመመሥረት ነው። ዘመናትንና በውስጣቸው የሚገኙትን ሥፍረ-ዘመናት በደንብ ለይተው ሳያውቁና ሳይረዱ፥ መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል ለመረዳትና ለመተርጎም እይቻልም። ሁለተኛው መመሪያ፥ ተከታታይ መገለጥን የሚያሳይ ነው። ይህ በሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ዘንድ በተጨባጭ ታይቷል። መገለጥ በየደረጃው የሚሰጥ መሆኑን የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችም ተረድተዋል። ሦስተኛው መመሪያ፥ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያብራሩ ሰዎች ሁሉ፥ ተከታዩ መገለጥ ቀዳሚውን ራእይ በመጠኑም ቢሆን የሚተካው መሆኑን ማወቅ ያጎባቸዋል የሚለው ነው። ምክንያቱም የመጀመሪያው መገለጥ በተሰጠበት ወቅት የነበረው ሁኔታ ሊለወጥ፥ ሊቀር ወይም ሌላ የሕይወት መመሪያና ደንብ ሊሰጥ ስለሚችል ነው። ለምሳሌ፥ በሰንበት ቀን እንጨት ሲለቅም በመገኘቱ ወደ ሙሴ ሰፍርድ የመጣው እስራኤላዊ በድንጋይ ተወግሮ እንዲገደል እግዚአብሔር ሙሴን እዞታል (ዘኁል. 15፡32-36)። ዛሬ ይህን ሕግ አንጠቀምበትም። ማድረግም አይገባም። ምክንያቱም በቃሉ መሠረት እኛ የምንኖረው፥ ፍጹም ልዩ በሆነ ሌላ ሥፍረ-ዘመን ውስጥ ነው። 

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተለይተው የተመለከቱት ሰባት ሥፍረ-ዘመናት ቢሆኑም፥ ሦስቱ ግን ከሌሎቹ ይበልጥ ጠቃሚ ሆነው እናገኛቸዋለን። እነርሱም የሕግ ዘመን (ከሙሴ ጊዜ ጀምሮ እስራኤላውያን በብሉይ ኪዳን ዘመን የተመሩበት)፤ የጸጋ ዘመን (የአሁኑ ዘመን)፤ ወደፊት የሚመጣው እና የሺህ ዓመቱ መንግሥት ዘመን ናቸው። 

ለ, የንጽሕና ሥፍረ-ዘመን፡- የነጻነት ዘመን 

ይህ ዘመን ከሰው መፈጠር (ዘፍጥ. 1፡26፥ 27) ጀምሮ እስከ ዘፍጥረት ምዕራፍ 3 ቁጥር 6 ድረስ ይሄዳል። በዚህ ዘመን ስው ፍሬያማ እንዲሆን፥ ምድርን በሙሉ እንዲገዛ፥ በእንስሳት ላይ እንዲሠለጥን፥ አትክልትና ፍሬ እንዲመገብና የዔደን ገነትን የአትክልት ስፍራ እንዲጠብቅ ኃላፊነት ተሰጥቶት ነበር (ዘፍጥ. 1፡28-29፤ 2፥ 15)። 

ሰው የተከለከው አንድ ነገር፥ ይኸውም መልካምና ክፉን ለመለየት እውቀት ከምትሰጥ የዛፍ ፍሬ እንዳይበላ ነበር (ዘፍጥ. 2፡17)። ምንም እንኳ ሰው የከበረ ስፍራ፥ ፍጹም አካል፥ አእምሮና ባሕርይ፥ እንዲሁም ሕይወትን የሚያረኩ ነገሮች ተስተካክለው ቢሰጡት፥ ሔዋን ተፈትና ተሸነፈችና ከተከለከለው ዛፍ ፍሬ በላች፤ አዳምም አብሮአት ሰመብላት ያለመታዘዝዋ ተባባሪ ሆነ (ዘፍጥ. 3፡1-6)። ከዚህም የተነሣ ውጤቱ ሰማያዊ ፍርድ፥ መንፈሳዊ ሞት፥ የኃጢአት እውቀት፥ እግዚአብሔርን መፍራትና የኅብረት መበላሸት ሆነ። 

በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳ እግዚአብሔር የጸጋውን መመሪያ፥ የአዳኝን ተስፋ (ዘፍጥ. 3፡15) ሰመስጠት መዳንን የሚያሳይ የቁርበት ልብስ አለበሳቸው (ዘፍጥ. 3፡21)። ከገነት ተባረሩ፤ የግል ሕይወታቸውን ከዚያ ውጪ እንዲመሩ ተፈረደባቸው (ዘፍጥ. 3፡23-24)። በእነርሱ ላይ በተሰጠው ሰዚህ የእግዚአብሔር ፍርድ የመጀመሪያው ሥፍረዘመን አበቃና እዲሱ ሥፍረ-ዘመን ተጀመረ። በዚህ የንጽሕና ሥፍረ-ዘመን እግዚአብሔር የሰውን ውድቀት እሳየ፥ የሚመጣውን አዳኝ ተስፋ ሰጠ፥ በፍጥረቱ ላይ በመፍረዱ ደግሞ ሉዓላዊነቱን (ታላቅነቱን) አስመሰከረ፥ የጻጋውንም መመሪያ ጀመረ። 

ሐ. የሕሊና ሥፍረ-ዘመን፡የሰው የመምረጥና የመወሰኝ ዘመን 

ይህ ሥፍረዘመን የሚያመለክተው፥ እግዚአብሔር ከአዳምና ከሔዋን ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ሲሆን፥ ከኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 3 ቁጥር 7 ጀምሮ እስከ ምዕራፍ 8 ቁጥር 19 ይደርሳል። በዚህ ጊዜ ሰው ፍጹም አዲስ የሆነ ኃላፊነት ተሰጠው። ሰይጣን ተረጎመ (ዘፍጥ. 3፡14-15)፥ በአዳምና በሔዋን ላይም እርግማን ወደቀባቸው (ዘፍጥ. 3፡16-19)። እርግጥ በዚህ ጊዜ ሰው በዝርዝር የተገለጡ ሕጎች ባይሰጡትም፥ ከርሱ የሚፈለገው በተሰጠው የሕሊና ነጻነት መሠረት፥ እግዚአብሔር በገለጠለት እውቀት መጠን መኖር ብቻ ነበር። 

በዚህ ሰሕሊና ዘመንም ቢሆን ሰው ከዚያ በፊት እንደለመደው በመተላለፍ ኃጢአት መውደቁን ቀጠለ። ሕሊና ይወቅሳል እንጂ ለድል አያበቃም (ዮሐ. 8፡9፤ ሮሜ 2፡15፤ 1ኛ ቆሮ. 8፡7፤ 1ኛ ጢሞ. 4 ፡2)። የአዳም ልጆች ከአባታቸው የወረሱት የኃጢአተኛነት ባሕርይ ቃየን የደም መሥዋዕት ባለማቅረቡ (ዘፍጥ. 4፡7) የተገለጠ ሲሆን፥ ውጤቱም አቤልን በመግደሉ ተረጋገጠ (ዘፍጥ. 4፡8)። ከዚህ የተነሣ የቃየን ሥልጣኔ ውጤት ኃጢአተኛነት ነበር (ዘፍጥ. 4፡16-24)፤ አካላዊ ሞትም የተለመደ ሆነ (ዘፍጥ. 5፡5-31)። የሰው ልብ ጠማማነት ይህን ያህል ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ እንደገና ፍርድ አስፈለጎ (ዘፍጥ. 6፡5፥ 11-13)። ፍርዱም በቃየን ላይ ተገለጠ (ዘፍጥ. 4፡10-15)፥ በአጠቃላይም በሰው ዘር ላይ ሞት ሆነ (ዘፍጥ. 5)። በመጨረሻም እግዚአብሔር በምድር ላይ ታላቁን የጥፋት ውኃ ማምጣት ነበረበት (ዘፍጥ. 7፡21-24)። 

በዚህ ዘመን ሳይቀር የእግዚአብሔር መለኮታዊ ጸጋ ሄኖክን በማዳኑና (ዘፍጥ. 5:24)፥ የኖኅን ቤተሰቦች መርከብ ውስጥ ሰውሮ ማዳኑ ተገልጧል (ዘፍጥ. 6፡8-10፤ ዕብ. 11፡7)። ሁላችንም እንደምናውቀው ይህ ሥፍረ-ዘመን በጥፋት ውኃ አማካይነት በተገለጠው ፍርድ ሲጠናቀቅ፥ ኖኅና ቤተሰቦቹ ብቻ ድነዋል። 

በዚህ ዘመን የእግዚአብሔር ዓላማ፥ የሰውን ውድቀት በሕሊናው በሚመራበት ሰአዲሱ ሁኔታ ውስጥ ላማሳየት ነበር። ቢሆንም እግዚአብሔር በዚህ ዘመን ሊመጣ ያለውን እዳኝ የትውልድ ሐረግ ይጠብቃል። ዓለሙን በሙሉ በጥፋት ውኃ ሰመቅጣት የራሱን ታላቅነት እሳየ፥ ለኖኅና ለቤተሰቡም ጸጋውን ገለጠ። 

መ. የሰው መንግሥት ሥፍረ-ዘመን፡- ከኖኅ ጋር የተደረገ ቃል ኪዳን 

ይህ ሥፍረ-ዘመን ከዘፍጥረት ምዕራፍ 8 ቁጥር 20 ጀምሮ እስከ ዘፍጥረት ምዕራፍ 11 ቁጥር 9 ድረስ ያለውን ጊዜ ያጠቃልላል። እግዚአብሔር፥ ለኖኅ የማይፈርስ ቃል ኪዳን (ዘፍጥ. 8፡20-9፡17) የገባለት ሲሆን፥ ከእንግዲህ ወዲያ ምድርን በጎርፍ እንደማያጠፋ እረጋገጠለት (ዘፍጥ. 8፡21፤ 9፡1)። ወራት በተፈጥሮ ሕግ መሠረት ጊዜያቸውን ጠብቀው እንደሚፈራረቁ ሁሉ (ዘፍጥ. 8፡22)፥ ሰውም እንዲባዛ እግዚአብሔር የታደሰ ሕግ ሰጠ (ዘፍጥ. 9፡1)። እንዲሁም ሰው በእንስሳት ላይ ያለውን ሥልጣን እንዲቀጥል (ዘፍጥ. 9፡2) አደረገና ሥጋ መብላትን ፈቀደለት፤ ደም ከመብላት ግን ተከልክሏል (ዘፍጥ. 9፡4)። ከሁሉም ይበልጥ የሚጠቅመው፥ በዚህ ዘመን ነፍሰ ገዳዮች የሚቀጡበት የሰው መንግሥት ሕልውና አግኝቶ የመመሥረቱ ጉዳይ ነው (ዘፍጥ. 9፡5-6)። 

ሰሌሎች እንደታየው ሁሉ ለዚህ ዘመንም የሰው ውድቀት በግልጥ ተከስቷል። የኖኅ መስከርና (ዘፍጥ. 9፡21) የልጁ የካም አባቱን (ኖኅን አለማከበር ማስረጃዎች ናቸው (ዘፍጥ. 9፡22)። ዘመኑ ሥነ-ምግባር የጎደለበትና እግዚአብሔርን ማምለክ የቀነሰበት ሆነ (ዘፍጥ. 11፡1-4)። እንደ ሕሊና ሁሉ የሰው መንግሥት የሰውን ኃጢአት ተቆጣጥሮ ሊገታው አልቻለም፤ ውጤቱም የሳሲሉን ግንብ ሆነ (ዘፍጥ. 11፡4)። የእግዚአብሔር ፍርድ ቋንቋቸውን መደበላለቅና (ዘፍጥ. 11፡5-7) ሥልጣኔአቸውን ገትቶ እነርሱን በምድር ሁሉ ላይ መበታተን ነበር (ዘፍጥ. 11፡8-9)። 

ይሁን እንጂ በዚህ ዘመን ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረባቸው ሰዎች ከጥፋት በመጠበቃቸውና አብርሃምም በመመረጡ ጻጋ መኖሩ ግልጥ ነበር (ዘፍጥ. 11፡10-12፡3)። የሴቲቱ ዘር ተርፎአል፥ የእግዚአብሔር ታላቅነትና የሁሉ የበላይነትም ተገልጧል። ሥፍረ-ዘመኑ የሚያበቃው በባቢሎን ግንብ ምክንያት በደረሰው ፍርድ ነው። 

የሕሊናና የሰው መንግሥት ሁኔታ በሚቀጥሉት ሥፍረ-ዘመናትም ያላበቁ መሆናቸውን ማስተዋል ይገባል። የተስፋ ሥፍረ-ዘመን ውስጥ የሚገኙት አብርሃምና ዘሩ ብቻ ናቸው። በአጠቃላይ ይህ የሰው መንግሥት ሥፍረ-ዘመን፥ ከዚህ አዲስ የሕይወት ድንጋጌ በታች ያለውን የሰውን ውድቀት አሳየ። የእግዚአብሔርን ለይቶ የመፍረድ ሁኔታም ገለጠ። መለኮታዊ ጸጋን ማሳየቱንም ቀጠለ። 

ሠ. የተስፋ ሥፍረ-ዘመን፡- ከአብርሃም ጋር የተደረገ ቃል ኪዳን 

ይህ ቃል ኪዳን ከዘፍጥረት 11፡10 ጀምሮ እስከ ዘፀአት 19፡2 ይደርሳል። በዚህ ዘመን ለሰው የተሰጠው ኃላፊነት፥ እግዚአብሔር ለአብርሃም የገለጠውን ተስፋ ማመን ነው። †መለኮታዊው መገለጥ ይዘት ለአብርሃም የተስጠውኝ ተስፋ ይጨምራል (ዘፍጥ. 12፡1-2፤ 13፡16፤ 15፡5፤ 17፡6)። ለእስራኤል (የአብርሃም ዘር የተሰጠው ተስፋ ታላቅ መንግሥት እንደሚሆኑ፥ እግዚአብሔርም የቃል ኪዳኑን ተስፋ እንደሚፈጸምባቸው (ዘፍጥ. 12፡2-3፤ 13፡16፤ 15:5፥ 18-21፤ 17፡7-8፤ 28፡13-14፤ ኢያሱ 1፡2-4)፥ እንዲሁም ዓለሙን በሙሉ በአብርሃም በኩል እንደሚባርክ ነበር (ዘፍጥ. 12፡3)። መመሪያውም በግልጥ የተመሰከተ ሲሆን፥ አብርሃምን የሚባርኩትን እንደሚባርክና፥ የአብርሃምን ዘር የሚረግሙትን ደግሞ እንደሚረግም አረጋገጠ። 

ከአብርሃም ጋር የነበረው ቃል ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉት ጠቃሚ ቃል ኪዳኖች አንዱ ሲሆን፥ እርሱም፡- እስራኤል ዘላለማዊ መንግሥት የምትመሠርትበት፥ ምድሩንም ለዘላለም የግሷ የምታደርግሰት፥ በመንፈሳዊ ነገሮች የምትባረክበት፥ በመለኮታዊ ጥበቃ ሥር ለዘላለም የምትሆንበት እና ለዚህም ምቹ ሆና ለመገኘት ልዩ የሆነ የመገረዝ ሥርዓት እንደሚያስፈልጋት አጠቃሎ ይገልጣል (ዘፍጥ. 17፡13-14)። ቃል ኪዳኑም በእግዚአብሔር እንጂ በሰው ታማኝነት ላይ የተመሠረተ ስላልሆነ የጸጋ መመሪያ ነበር። የቃል ኪዳኑ ተስፋዎች አብርሃም በሕይወት እያለ በከፊል የተፈጸሙ ቢሆንም፥ እግዚእብሔር ለአብርሃም የገባላት ተስፋና በእርሱም አማካይነት የሚገኙት በረከቶች እስከ ዓለምና የሰው ልጅ ታሪክ ማብቂያ ድረስ መፈጸማቸውን ይቀጥላሉ። እርግጥ ከበረከቶቹ አንዳንዶቹ የዕውን መታዘዝ የሚሹ መሆናቸው በየትውልዱ ተገልጧል፤ የቃል ኪዳኑ ተስፋ ግን ለዘላለም መሆኑ ነው የታወጀው (ዘፍጥ. 17፡7፤ 13፡19፤ 1ኛ ዜና 16፡16-17፤ መዝ. 105፡10)። የሥፍሩ-ዘመን ኃላፊነትን በሚመለከት ከአብርሃም ጋር የነበረው ቃል ኪዳን በቀጥታ አስቀድሞ የሚያመለክተው፥ አብርሃምንና የአብርሃም ዘሮችን ኃላፊነት ነው። ዓለም አጠቃላይ ሰሰው መንግሥትና በሕሊና የሚመራ መሆኑ ቀዳሚ ኃላፊነቱ ስለሆነ በዚሁ ቀጠለ። 

ከአብርሃም ጋር በነበረው ቃል ኪዳን ውስጥ ተደጋጋሚ የሆነ ውድቀት የሚታይ ሲሆን፥ ይህም ወደ ተስፋ ምድሩ ከመሄድ መዘግየት (ዘፍጥ. 11፡31)፥ እስማኤልን በመውለድና (ዘፍጥ. 16፡1-16)፥ ወደ ግብፅ ሰመውረድ (ዘፍጥ. 12 ፡10-13፡1) ተገልጧል። ነገር ግን አብርሃም እየቆየ ሲሄድ በእምነትና በጸጋ በማደጉ የተነሣ፥ ልጁን ይስሐቅን እስከ መስዋት ደረጃ ድረስ ስእግዚአብሔር ያለውን ታዛዥነት እስመስክሯል (ዘፍጥ. 22)። 

ከአብርሃም በኋላ ይስሐቅ ከግብፅ ጋር በጣም ተቀራርቦ በመኖሩ ወደቀ (ዘፍጥ. 26፡1-16)፤ ያዕቆብም ደግሞ ሲወለድ ለእናቱ እግዚአብሔር የገባላትን የቃል ኪዳን ተስፋ ባለማመኑ ወደቀ (ዘፍጥ. 25፡23፤ 28፡13-15፥ 20)፤ እንዲሁም ያዕቆብ ውሽታም፥ አታላይና ነገረኛ ነበር (ዘፍጥ. 27፡1-29)። በመጨረሻም ከአገሩ ወጥቶ ረሃቡ እሰኪያልፍ ድረስ ወደ ግብፅ ወረደ (ዘፍጥ. 46፡1-4)። 

እስራኤላውያን ደግሞ ገና በግብፅ እያሉ እግዚአብሔር በተአምራቱ ጠብቆ ወደ አገራቸው ሊመልሳቸው ተስፋ ከሰጣቸው በኋላ እምነት አጥተው በማጉረምረም ወደቁ (ዘጸ. 2፡23፣ 4፡1-10፤ 5፡21፤ 14 ፡10-12፤ 15፡24)፤ ከግብፅ ከወጡም በኋሳ ወደዚያው ለመመሰስ በመመኘት (ዘፀ. 14፡11-12)፥ እንዲሁም በተከታታይ በማጉረምረማቸው እግዚአብሔርን በደሉ (ዘፀ. 15፡24፤ 16፡2፤ ዘኁል. 14፡2፤ 16፡11፥ 41፤ ኢያሱ 9፡18)። የእግዚአብሔርን ሕግ ሲቀበሉና፥ በቃዴስ የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ሲሰጥ ባለማመናቸው ውድቀታቸው በግልፅ ታየ (ዘኁል. 14) በዘመኑ የአብርሃም የተስፋው ቃል የእነሱ ኃላፊነት መሆኑን ካለማመናቸው የተነሣ የተስፋይቱን ምድር ለጊዜው ሳይወርሱ ቀሩ፤ በግብፅ በባርነት ተቀመጡ። እንዲሁም ወደ ተስፋው ምድር እንደገና ከመግባታቸው በፊት በምድረበዳ ብዙ ተንከራተቱ። ይህ ሁሉ ውድቀታቸው ለሙሴ ሕግ መሰጠት መድረክን አመቻቸ። 

በተስፋ ሥፍረ-ዘመን ብዙ መለኮታዊ ጸጋ ከእግዚአብሔር ይሰዛላቸው፥ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ሕዝቡን ይጠብቃቸው ነበር። ከግብፅ አዳናቸው፥ እንዲሁም የፋሲካን ሥርዓት ሰጣቸው። ይህ የተስፋ ሥፍረ-ዘመን ሕግ ለሙሴ ሕግ በተሰጠበት ወቅት (ዘፀ. 19) ያበቃ ቢመስልም፥ እስከ ታሪክ ፍጻሜ ድረስ የሚቀጥል ነው። ለአብርሃም የተገባው ተስፋ በአሁኑ ዘመን ላሰው የጸጋ ሥፍረ-ዘመንና ለወደፊቱ መንግሥት ሥፍረ-ዘመን መሠረት ነው። እንዲያውም ከተስፋው ከፊሉ የማያልቁና በዘላለማዊው መንግሥት ወቅት የሚፈጸሙ ናቸው። 

የተስፋ ሥፍረ-ዘመን የመለኮታዊ ሉዓላዊነትን በግልጥ አጸና። ለእስራኤል ልዩ የሆነ የመለኮታዊ መገለጥ መንገድን አዘጋጀለት፥ መለኮታዊ ድነትና በረከትም እንዲቀጥል አደረገ። የእግዚአብሔር ጸጋ የተገለጠበት ከመሆኑም ሌላ ይህን ሁሉ ለዓለም የሚናገር ምስክር እንደሚመጣ የተረጋገጠበት ነው። እንደ ሌሎቹ ሥፍረዘመናት ሁሉ ይህም ሥፍረ-ዘመን ያላቀው፥ እግዚአብሔርን ለመምሰልና ፈቃዱን ለመከተል ካለመቻል የተነሣ በመጣ ውድቀት ነው። ይህም ውድቀት ነው፥ ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያደርስ ሞግዚቱ ሆኖ ለሰው እንዲሰጠው መሠረት የጣለ (ገላ. 3፡24)። 

ረ. የሕግ ሥፍረ-ዘመን 

ሕግ በሌላ በኩል በመስቀል ላይ የተፈጸመ መሆኑ ቢታወቅም፥ የሕግ ሥፍረ-ዘመን ከዘፀአት ምዕራፍ 19 ቁ.3 ጀምሮ እስከ የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 ዕለተ-ጰንጠቆስጤ ድረስ ያለውን ዘመን በሙሉ ያጠቃልላል። የአሁኑ የጸጋ ዘመን፥ ከወንጌል ክፍሎች እንደ ዮሐንስ ወንጌል ባሉትና በሌሎችም ወንጌሉች በተወሰኑ ሥፍራዎች ተገልጧል። 

የሙሴ ሕግ የተሰጠው በቀጥታ ለእስራኤል ብቻ ስለነበር፥ አሕዛብ በዚህ ሕግ መሠረት አልተፈረደባቸውም። ሕጉም በዝርዝር በተመለከቱት ሦስት የሥራ ስልቶችና ክፍሎች ተመድቧል። እነርሱም ትእዛዛት (የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚገልጡ፥ ዘጻ. 20፡1-26)፥ ፍርዶች (የእስራኤላውያን ማኅበራዊና ሕዝባዊ መመሪያዎች፥ ዘጸ. 21፡1 24፡11)፥ እንዲሁም ሥርዓቶች (የእስራኤላውያን ሃይማኖታዊ ሕይወት፥ ዘጸ. 24 ፡12 31 ፡18) ናቸው። የመሥዋዕትና የክህነት ሥርዓት በዚህ ውስጥ የተጠቃለለ ሲሆን፥ ጸጋዊና ሕጋዊም ነበር። የዚህ ሥፍረ-ዘመን መንግሥት እግዚአብሔር ራሱ ይጎዛው ዮነበረ ሲሆን ለአገዛዙ ቢሆንም ይጠቀምባቸው የነበሩት ነቢያት፥ ካህናትና በኋላም ነገሥታት ነበሩ። የሙሴ ቃል ኪዳንም እንደተለመደው ሁሉ ጊዜአዊ ነበር፤ ምክንያቱም ቃል ኪዳኑ በሥራ ላይ የዋለው፥ መሢሑ እስኪመጣ ድረስ ብቻ ነበርና (ገላ. 3፡24-25)። የሥፍረ-ዘመኑ ባሕርይ ደግሞ ሁኔታዊና ምክንያታዊ ነበር። ማለትም መታዘዝ በረከትን የማግኛ ቅድመ 

ሁኔታ ነበር። 

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሶ የሚገኘው የዚህ ዘመን ሕግ፥ በሰው ዘር ታሪክ ውስጥም የመጀመሪያው ነው፡፡ከዚህ የተነሣ መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ሕግ አማካይነት ዝርዝርና አጠቃላይ የሆነ ሃይማኖታዊ ሥርዓትን ከመግለጡም በላይ፥ ለይቅርታና ለመንጻት ሁኔታ ያመቻቸ፥ ለአምልኮ፥ ለጸሎትና ለምስጋና ደንብ የሰጠና ለወደፊቱ ተስፋን ያስጨበጠ ነበር። 

በሕጉም ወቅት ተከታታይ ውድቀት ነበር። ይህ በተለይ የተረጋገጠው፥ በመሳፍንት አመራር ወቅት ሲሆን፥ ከሰሎሞን ሞትና እንዲሁም የእስራኤል መንግሥት ሁለት ላይ ከተከፈለ በኋላም ውድቀቱ ቀጠለ። ሕጉ ሙሉ በሙሉ ተረስቶ፥ የጣዖት አምልኮ ያየለባቸው ጊዚያትም ነበሩ። አዲስ ኪዳን ይህን የውድቀት ታሪክ መዝግቦታል። ውድቀቱ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰው፥ በተስፋ ቃል ኪዳኑ መሠረት ሰውን ሊቤዥና ሊታደግ የመጣውንና ሕግን በመጠበቅ ፍጹም የሆነውን ኢየሱስን በመጥላትና በመስቀል ነው። 

በዚህ የሕግ ሥፍረ-ዘመን ወቅት በእስራኤላውያን ላይ ብዙ የእርግማንና የቅጣት ፍርድ እንደተበየነባቸው ዘዳግም 28፡1-30፡20 ውስጥ ተመልክቷል። ከፍርዶቹ ሁሉ ከፍተኛ የሆኑት ለእሥሪያና ለባቢሎን ምርኮ እልፎ መሰጠት ሲሆኑ፥ የእስራኤል ልጆች ጊዜያቸውን ጠብቀው ከምርኮው ተመልሰዋል። በሥፍረ-ዘመኑ መጨረሻ አካባቢም ሌላ ፍርድ መጥቶባቸው ነበር። ይኽውም በ70 ዓ,ም. የተፈጻመው የኢየሩሳሌም መፍረስና የእስራኤላውያን በዓለም ሁሉ መበታተን ነበር። ሌላው “የያዕቆብ መከራ” በመባል የሚታወቀው ታላቁ መከራ ገና ወደፊት ሊመጣ ያለው ነው (ኤር. 30፡1-11፤ ዳን. 12፡1፤ ማቴ. 24፡22)። 

በሕግ ደግሞ ኃጢአተኛዋን እሰራኤል ለመታደግ ሲባል መለኮታዊ ጸጋ በመሥዋዕቱ ሥርዓት አማካይነት ይፈጸም ነበር። ይህ ታላቁ የእግዚአብሔር ትዕግሥት ኃጢአተኛዋን እስራኤል ለመመለስ ነቢያትን፥ መሳፍንትንና ነገሥታትን ሰማዘጋጀቱና ዓላማውን እንዲሁም ፍቃዱን በእርስዋ በኩል በመፈጸሙ ይህ ተገልጧል። እውነተኛው የእስራኤል ንስሐ ብዙ ጊዜ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘ ሲሆን፥ ብሉይ ኪዳን የተጻፈውም በዚሁ ጊዜ ነበር። ታላቁን በረከት ማለት የክርስቶስን መሢሕ ሆኖ መምጣት የእስራኤል ሕዝብ በአጠቃላይ አልተቀበለውም። 

በአንድ በኩል የሕግ ሥፍረ-ዘመን በመስቀሉ ላይ አብቅቷል (ሮሜ 10፡4፤ 2ኛ ቆሮ. 3፡11-14፤ ገላ. 3፡19፥ 25)። በሌላ በኩል ግን አዲሱ የጸጋ ዘመን የጀመረበት የጰንጠቆስጤ ዕለት እስኪደርስ ድረስ የሕግ ሥፍረዘመን አልተጠናቀቀም። ሕጉ ግልጥ የሕይወት መመሪያነቱ ቢያበቃም የእግዚአብሔር የቅድስና መግለጫ እንደሆነ የሚቀጥል ስለሆነ፥ ክርስቲያኖች በደንብ ቢረዱት፥ የእግዚአብሔርን ጳድቅ ባሕርይ ሕጉ ውስጥ የተካተቱት የሥነ-ሥርዓት መመሪያዎች እንዳሉ ይቀጥላሉ። እግዚአብሔር የማይለወጥ በመሆኑ እርሱም አይልም። የዚህ ሥፍረ-ዘመን ሕግ የተሰጠው በቀጥታ ለእስራኤል እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ስላልሆነና፥ ሥፍረ-ዘመኑም የተለወጠ በመሆኑ፥ የአሁኑ ዘመን አማኞች ሕጉን በዝርዝር እንዲያከብሩት አይገደዱም። ሕጉን በተለያዩ መንገዶች በሥራ ላይ ለማዋል ቢቻልም፥ ጥብቅ የሆነው አተረጓጎም የሚያስገነዝበው የሙሴ ሕግ ለእስራኤል ብቻ መሆኑን ነው። 

ሕግ የተሰጠው ኃጢአትን ወደ ፍርድ ለማምጣትና ለሕይወት የጽድቅ መመሪያ ለመስጠት ነበር። የሥነ-ምግባር፥ የመንግሥትና የሃይማኖት ሕግ እንደማያድንና እንደማይቀድስ በሕግ ሥር የነበሩት የእስራኤላውያን አኗኗር አሳይቷል። ሕግ የተሰጠው ለሰው ድነትን ለማስገኘት አልነበረም። ሕግ ሰራሱ ደካማ ስለነበር፥ ሊያጸድቅ አልቻለም (ሮሜ 3፡20፤ ገላ. 2፡16)፤ ሰውን ሊቀድስ ወይም ፍጹም ሊያደርግም አልቻለም (ዕብ. 7: 18-19)። የሕግ ኃይልና ቆይታ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ነበር (ገላ. 3፡19)፥ ሕግ ሕያው ሊያደርግ አልቻለም (ገላ. 3፡21-22)፥ ተግባሩ ኃጢአትን በይፋ ማውጣት ብቻ ነበር (ሮሜ 7፡5-9፤ 8፡3፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡56)። ሰው ሁሉ ጥፋተኛ ወይም ኃጢአተኛ መሆኑን ለማሳየትና የክርስቶስን አስፈላጊነት ጉልህ አድርጎ ለማቅረብ ቻለ (ሮሜ 3፡19፤ 7፡7-25፤ ገላ. 3፡21-27)። 

ሰ. የጸጋ ሥፍረ-ዘመን 

የጸጋ ሥፍረ-ዘመን በትክክል ከሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 ጀምሮ በአዲስ ኪዳን በሙሉ ይቀጥልና በቤተ ክርስቲያን መነጠቅ ይጠናቀቃል። ስለዚህ የጸጋ ሥፍረ-ዘመን ከዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 13 እስከ ምዕራፍ 17 ባለው ክፍል አንዳንድ ትምህርቶች ተስጥተው ነበር። ይህ ዘመን የሚያጠቃልላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፥ ከሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 1 እስከ ዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ 3 ያሉት ናቸው። 

ይህ የጸጋ ሥፍረ-ዘመን የተሰጠው ሰቀጥታ ለቤተ ክርስቲያን ብቻ በመሆኑ፥ መላው ዓለም በሕሊናና በሰው መንግሥት ውስጥ እንዳለ ይቀጥላል። ሰውስጡም ድነት የሚገኘው በእምነት ብቻ መሆኑ የተገለጠ ሲሆን፥ ይህ እውነት ሁልጊዜ ያለና አሁን ደግሞ ይበልጥ ግልጥ የሆነ ነው (ሮሜ 1፡16፤ 3፡22-28፣ 4፡16፤ 5፡15-19)። በዚህ ሥፍረ-ዘመን ያለው የጸጋ መመሪያ ሥፍረ-ዘመኑን ከቀደምት ሥፍረ-ዘመናት ሁሉ ልዩና ታላቅ ያደርገዋል (ዮሐ. 13፡34-35፤ ሮሜ 12፡1-2፤ ፊልጵ. 2፡5፤ ቈላ. 1፡10-14፤ 3፡1፤ 1ኛ ተሰ. 5፡23)። 

በጸጋ ሥፍረ-ዘመንም በውድቀት ታይቷል። ምክኝያቱም ጸጋ ቢኖርም ዓለም ሁሉ ክርስቶስን ስላልተቀበለውና ፍጹም የሆነች ቤተ ክርስቲያን ስለማትታይ ነው። ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መንፈሳዊነት ከመጉደሉ የተነሣ፥ ሰዎች በሐሰት ተመርዘው ስሕተትን የሚያስፋፉበት ዘመን እንደሚመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል (1ኛ ጢሞ. 4፡1-3፤ 2ኛ ጢሞ. 3፡1-13፤ 2ኛ ጴጥ, 2-3፤ የይሁዳ መልእክት በሙሉ)። እግዚአብሔር ሕዝቡን ከአይሁድና ከአሕዛብ መካከል እየጠራ ዓላማውን በመፈጸም ላይ ነው። ይሁኝ እንጂ፥ አሁን ባለችው ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ፥ ግን ያልዳኑ ሰዎች፥ ቤተ ክርስቲያን ስትነጠቅ እዚሁ ይቀሩና ክርስቶስ መንግሥቱን ሊመሠርት በሚመጣበትና በቤተ ክርስቲያን መነጠቅ መካከል ባለው ጊዜ ፍርዳቸውን ይቀበላሉ (ማቴ. 24፡1-26፤ ራእይ 6፡19)። እውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን ግን በመንግሥተ ሰማያት በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት ፍርዷ ይታያል (2ኛ ቆሮ. 5፡10-11)። 

በዚህ ዘመን መለኮታዊ ጸጋ ተገልጧል፡- በተለይም በክርስቶስ መምጣት አማካይነት (ዮሐ. 1፡17)፥ በአማኝ ድነትና በእግዚአብሔር ፊት በመቆማችን (ሮሜ 3፡24፤ 5፡1-2፥ 15-21፤ ገላ. 1፡1-2፣ 21፤ ኤፌ. 2፡4-10)፥ እና ጸጋ ራሱ የሕይወት መመሪያ ሕግ በመሆኑ (ገላ. 3፡1-5፡26)። 

የጸጋ ሥፍረ-ዘመን የሚያበቃው፥ በእውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን መነጠቅ ሲሆን፥ ከዚያ የሚቀጥለው አሰተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚሰጠው ፍርድ ይሆናል (ራእይ 17፡16)። ይህ የአሁኑ የጸጋ ዘመን ልዩ ሥፍረ-ዘመን የሚሆንበት ዋና ምክንያት ቤተ ክርስቲያን ልለምታጠቃልላቸው ከአይሁድና ከአሕዛብ የሆኑትን አማኞች ሁሉ ነው። በተቃራኒው ግን የእስራኤል ሕግ ለእስራኤል ብቻ፥ ሰብዓዊ መንግሥት ለመላው ዓለም፥ እንዲሁም ሕሊና ለሁሉም የሰው ልጅ ሆነው እናገኛቸዋለን። በጸጋ ሥፍረ-ዘምን የሙሴ ሕግ ሙሉ በሙሉ ተሰርዟል። ይሁን እንጂ የእግዚአብሔርን ቅድስና እየመሰከረ፥ የሰውንም ደካማነት እያሳየ፥ በጸጋ ሰመመራት ቢጠቀሙበት ትርፍ ላለበት መንፈሳዊ ትምህርትነት ያለውን ዋጋ እንደያዘ ይቀጥላል። ሁሉም ሥፍረ-ዘመናት በአጠቃላይ የእግዚአብሔር ጸጋ አላቸው። የጸጋ ሥፍረ-ዘመን ግን በሚገኝበት ጸጋ ሙሉነትና በሕይወት መመሪያነቱ ከሁሉም የላቀ መገለጥ ነው። 

ሸ. የእግዚአብሔር መንግሥት ሥፍረ-ዘመን 

የዚህ መንግሥት ሥፍረ-ዘመን የሚጀምረው በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ሲሆን (ማቴ. 24፤ ራእይ 19)፥ በሽግግር ወቅትነት የሚያገለግለውን የመከራ ጊዜ ያስቀድማል። ማስረጃውም ስለሚመጣው መንግሥት በሚናገሩት የብሉይና የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት በሙሉ ይገኛል፡- (በተለይም መዝ. 72፤ ኢሳ. 2፡1-5፤ 9፡6-7፥ 11፤ ኤር. 33፡14-17፤ ዳን. 2፡44-45፤ 7፡9-14፥ 18፥ 27፤ ሆሴዕ 3፡4-5፤ ዘካ. 14፡9፤ ሉቃስ 1፡31-33፤ ራእይ 19-20)። ሰመንግሥቱ ውስጥ የሰው ኃላፊነት፥ በብረት በትር ለሚገዛው ንጉሥ መታዘዝ ብቻ ይሆናል (ኢሳ. 11፡3-5፤ ራእይ 19፡15)። መንግሥቱም እግዚአብሔር ራሱ የሚነግሥሰት ሲሆን፥ አዲስ የመሥዋዕት ሥርዓትና ክህነት ይኖረዋል (ኢሳ. 66፡21-23፤ ሕዝ. 40-48)። የዚህ ዘመን ልዩ ባሕርይ ሰይጣን መታሰሩና አጋንንትም ሥልጣን ተወስዶባቸው ምንም ሊያደርጉ አስመቻላቸው ነው (ራእይ 20፡1-3፥ 7)። ከምንግሥቱ ውስጥ ውድቀትም ይኖራል (ኢሳ. 65፡20፤ ዘካ. 14፡16-19)፤ ሰማብቂያውም አለመታዘዝና ዓመፅ ይኖራል(ራእይ 20፡7-9)። 

ቀጥሎ የሚመጣው መለኮታዊ ፍርድ፥ የዓመፀኞች በእሳት መጥፋትና (ራእይ 20፡9)፥ የአሮጌው ሰማይና ምድር በተመሳሳይ ሁኔታ መጥፋትን ያጠቃልላል (2ኛ ጴጥ. 3፡7፥ 10-12)። 

በዚህ የሺህ ዓመት መንግሥት ውስጥም መለኮታዊ ጻጋው አዲሱን ቃል ኪዳን በመፈጸም (ኤር. 31፡31-34)፥ በድነት (ኢሳ. 12)፥ በቁሳዊ ብልጽግና (ኢሳ. 35)፥ ራእይ አትረፍርፎ በመስጠት (ኤር. 31፡33-34)ይቅርታ በማብዛት (ኤር. 31፡34)፥ እንዲሁም በእስራኤል እንደገና መስብስብ ይገለጣል (ኢሳ. 11፡11-12፤ ኤር. 30፡1-11፤ ሕዝ. 39፡25-29)። ይህ የሺህ ዓመት መንግሥት ሰአሮጌው ሰማይና ምድር መጥፋት የሚጠናቀቅ ሲሆን፥ ቀጥሎ የዘላለም መንግሥት ይከተላል(ራእይ 21-22)። 

የሺህ ዓመቱ መንግሥት ሥፍረ-ዘመን ከቀደሙት ሥፍረ-ዘመናት በሙሉ የሚለየው፥ የሰው ሥነ-ምግባር የሚፈተንበት የመጨረሻ ቅርጽ በመሆኑ ነው። ይህ ሥፍረ-ዘመን ከሁሉ የሚሻልባቸው መንገዶች ፍጹም የሆነ መንግሥት፥ የክርስቶስ በክብርና በግርማ መገኘት፥ አጠቃላይ በሆነ የእግዚአብሔር እውቀት መሞላት፥ ድነትን መረዳትና የሰይጣን ኃይል መወሰድ ናቸው። የዚህ መንግሥት ዘመን በብዙ ረገድ የመጨረሻው ከመሆኑም በላይ፥ እግዚአብሔር ከሰው ጋር ያለው ጉዳይ የሚጠናቀቅበት ነው። 

በየዘመናቱ እግዚአብሔር ከሰው ጋር ያለውን ጉዳይ በተለያዩ ስልቶችና መንገዶች አሳይቷል። በዘመናት ሁሉ ሰው ይወድቃል፥ የእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ነበር ብቁ። በሥፍረ-ዘመናቱ በተፈጥሯዊው ዓለምና ስሰው ታሪክ አማካይነት የእግዚአብሔር ክብር ተገልጧል። እግዚአብሔር ሰው ወደ ድነት የሚደርስበትን ወይም በራሱ ችሎታና ብቃት ለቅድስና የሚበቃበትን ሌላ ዕድል ሊሰጥ ይችል ነበር ወይ? ብሎ ማንም ጥያቄ ለማንሣት እይችልም። ስለዚህ የእግዚአብሔርን የተለያዩ ሥፍረ-ዘመናት መረዳቱ 1ኛ. በታሪክ ውስጥ የእግዚአብሔርን ዓላማ፥ 2ኛ. እግዚአብሔር ከሰው ጋር ያለውን ግንኙነት፥ 3ኛ. ሲል ራሱ የሰጠውን መለኮታዊ መገለጥ እና 4ኛ. በዘመናቱ ሁሉ ሰው የነበረበትን ድካምና የጌታን ታላቅ ፍቅር ላመገንዘብ ይረዳል። 

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

21
ትምህርት 21 ከ52

ቃል ኪዳኖች

የሰው ልጅ ታሪክ ዘላለማዊው የእግዚአብሔር ዓላማ አፈጻጸም ታሪክ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጣል። የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዕቅድ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጠ ሲሆን፥ እርሱም ክቡር የሆኑ ቃል ኪዳኖቹን መሠረት ያደረገ ነው። ቢያንስ ስምንት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ኪዳኖች በቃሉ ተመዝግበው ይገኛሉ። እነርሱም እግዚአብሔር ስለ ዓለም ካለው ዕቅድና ዓላማ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ዓበይት እውነታዎች ያካትታሉ። ከእነዚህ ቃል ኪዳኖች ብዙዎቹ መፈጸማቸው በማይቀርና በአዋጅ መልካ የቀረቡ መለኮታዊ ዓላማዎች ናቸው። የሥነ-መለኮት ጠበብት ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ኪዳኖች በተጨማሪ ከሰው ድነት ጋር የሚገናኙ ሦስት ሥነ-መለኮታዊ ቃል ኪዳኖችን አቅርበዋል። 

ሀ. ሥነ-መለኮታዊዎቹ ቃል ኪዳኖች 

የሥነ-መለኮት ሊቃውንት የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ ዓላማ በሚገልጡበት ጊዜ፥ ዘላለማዊ ዓላማው የመረጣቸውን ማለት፥ ከዘላለም በፊት ለድነት የወሰናቸውን ማዳን ነው የሚል ፅንሰ አሳብ አቅርበዋል። ይህን ትምህርታቸውን ሲያስፋፉ መሠረታዊ የሆኑ ሦስት ሥነ-መለኮታዊ ቃል ኪዳኖችን ያብራራሉ። 

1. ከአዳም ጋር የተደረገው የሥራ ቃል ኪዳን። አዳም በቃል ኪዳኑ መሠረት እግዚአብሔርን ቢታዘዝ፥ ሰሙንፈሳዊ ሁኔታው የሚጠበቅ ከመሆኑም ባሻገር፥ ዘላለማዊ ሕይወትም ያገኝ ነበር። ቃል ኪዳኑ መልካምና ክፉ እውቀት ስለምትሰጠው ዛፍ በተነገረውና “ከእርሱ በላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና” (ዘፍጥ. 2:17) ተብሎ በተሰጠ ማስጠንቀቂያ የተደገፈ ነበር። ከዛፉ ባይበላ ኖሮ ባልሞተም ነበር፤ ደግሞም እንደ ቅዱሳን መላእክት ለእርሱም ተሰጥቶ የነበረው ሰፍራ ይጸናለት ነበር ተብሎ ይገመታል። ይህ ቃል ኪዳን ሙሉ በሙሉ የተመሠረተው በግምት ላይ በመሆኑና መጽሐፍ ቅዱስ በቃል ኪዳንነት ያልተጠቀሰ በመሆኝ፥ እንዲሁም በቂ መሠረት እንደሌለው ስለታወቀ ሰብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ዘንድ ተቀባይነት የለውም። 

2. ሌላው ቃል ኪዳን ማመቤዠት ቃል ኪዳን” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፥ እርሱም የሰውን ድነት የሚመለከት ሆኖ በእግዚአብሔር እብና በእግዚአብሔር ወልድ መካክል አላለም ጀምሮ ያተደረገ ቃል ኪዳን ነው ተብሏል። ይህ ቃል ኪዳን የእግዚአብሔር ልጅ ለሚያምኑበት የድነት ቤዛ እንደሚሆንና እግዚአብሔር አብም መሥዋዕቱን እንደሚቀበልለት ተስፋ የተሰጠበት ነው። 

ቃል ኪዳኑ ቀደም ሲል ከተጠቀሰው የሥራ ቃል ኪዳን ይበልጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ድጋፍ አለው። ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ እንደሚያውጀው፥ የእግዚአብሔር የማዳን ዕቅድ ዘላለማዊ ነው። በዚህ ዕቅድ መሠረትም ክርስቶስ የኃጢአት መሥዋዕት ሆኖ እንደሚሞትና እግዚአብሔርም በክርስቶስ የሚያምኑትን ለማዳን መሥዋዕቱን በቂ አድርጎ እንደሚቀበል በመታወቁ ነው። ይህም የዓለም ሳይፈጠር በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን” (ኤፌ. 1፡4) ተብሎ በተጻፈው ቃል ተረጋግጧል። በክርስቶስ ያለንን ቦታ በማስመልከት ደግሞ፥ “እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን (ኤፌ. 4፡11) ተብሏል። 

ከእነዚህና ከሌሎችም ጥቅሶች በግልጥ የምንረዳው፥ በማዳን ረገድ የእግዚአብሔር ዓላማ ዘላለማዊ መሆኑን ነው። በእግዚአብሔር አብና እግዚአብሔር ወልድ መካከል የተደረገው ግልጥ ቃል ኪዳን የሚያመለክተው የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዓላማ ሰዎችን ማዳን መሆኑን ነው። 

3. ሌላው አቀራረብ የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ የማዳን ዓላማ እንደ የጸጋቃል ኪዳን” መመልከት ይገባል የሚለው ነው። በዚህ አመለካከት መሠረት ክርስቶስ የቃል ኪዳኑ መካከለኛና እምነታቸውን በእርሱ ለሚያደርጉ ሁሉ ወኪሳቸው እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል። ሰዎች ለዚህ ቃል ኪዳን ብቁ የሚሆኑት፥ ክርስቶስን አዳኛቸው አድርገው እምነታቸውን በእርሱ ላይ ሲያደርጉ ነው። ይህ ቃል ኪዳን ከዘላለማዊ የድነት ዕቅድ በተወሰደ ግምት ላይ የተመሠረተ ሲሆንዎ፥ የእግዚአብሔርን የማዳን ባለጠግነት ያጎላዋል። በመሆኑም የመቤዥት ቃል ኪዳንና የጸጋ ቃል ኪዳን የተወሰነ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት አላቸው። የሥራ ቃል ኪዳን የመጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ድጋፍ የሌለው ከመሆኑ የተነሣ፥ ሰብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም። 

ነገር ግን ከፍተኛ ችግር የተነሣበት ሁኔታ አለ። ይኸውም የሥነ-መለኮታዊ ቃል ኪዳኖች ደጋፊ የሆኑ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ የእግዚአብሔርን የማዳን ዕቅድ እርሱ ለሰው ታሪክ ያለው የመጀመሪያ ዓላማ ያደርጉታል። ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ለእስራኤል፥ ለቤተ ክርስቲያንና ለአሕዛብ ያለውን ዕቅድ ልዩ ሁኔታዎች ቸል ወደ ማለት ያዘነብላሉ። የእግዚአብሔር የማዳን ዕቅድ የዘላለማዊ ዓላማው ዋና ክፍል ቢሆንም አጠቃላይ ዕቅዱ ግን አይደለም። የተሻለው አመለካከት እግዚአብሔር በታሪክ ያለው ዕቅድ ክብሩን መግለጥ ነው የሚለው ይሆናል። ይህን የሚያደርገው ሰዎችን በማዳን ብቻ ሳይሆን፥ ዓላማውን በማከናወንና ከእስራኤል፥ ከቤተ ክርስቲያንና ካሕዝቦች ጋር በሚያደርገው ግንኙነት ራሱን በመግለጥ ጭምር ነው። በመሆኑም ታሪክን እግዚአብሔር በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ያለውን ዋና ዋና ዓላማዎች በሚገልጡትና የማዳን ዕቅዱን ባካተቱት ስምንት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ኪዳኖች በኩል መመልከቱ ይመረጣል። በሥነ-መለኮታዊ ቃል ኪዳኖች ላይ የሚያተኩሩ ወገኖች “የቃል ኪዳን ሥነ-መለኮታውያን” ተብለው ሲጠሩ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ኪዳኖች የሚደግፉ ግን “ሥፍረ-ዘመናውያን” ይባላሉ፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ኪዳኖች በየሥፍረ-ዘመናቱ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በየደረጃው የታዩትን ልዩነቶች ስለሚገልጡ ነው። 

ለ. መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ኪዳኖች 

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቃለሉት የእግዚአብሔር ቃል ኪዳኖች በሁለት የሚመደቡ ሲሆን፥ እነርሱም ቅድመ ሁኔታዊና ከቅድመ ሁኔታ ነጻ የሆኑ ናቸው። ቅድመ ሁኔታዊ ቃል ኪዳን፥ ቃል ኪዳኑ ከሚመለከታቸው ሰዎች በኩል ለሚወሰድ እርምጃ እግዚአብሔር የሚሰጠው አጸፋ ነው። ቅድመ ሁኔታዊ ቃል ኪዳን፥ ሰዎች የሚጠበቅባቸውን ካደረጉ፥ እግዚአብሔር የራሱን ድርሻ እንደሚያደርግ ፍጹም እርግጠኛነት ዋስትና ይሰጣል። ሰው የሚጠበቅበትን ባያደርግ ግን፥ እግዚአብሔር ቃል ኪዳኑን ደፈጽም ዘንድ አይገደድም። 

ከቅድመ ሁኔታ ነጻ የሆነው ቃል ኪዳን ምናልባት አንዳንድ ከሰው የሚፈልጉ ሁኔታዎችን ጨምሮ የተወሰኑ የእግዚአብሔር ዓላማዎች አዋጅ ሲሆን፥ የዚህ ቃል ኪዳን ተስፋዎች ያለ ጥርጥር በእግዚአብሔር ጊዜና አሠራር ይፈጸማሉ። ከስምንቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ኪዳኖች፥ ኤደን ገነት ውስጥ የተደረገውና የሙሴ ቃል ኪዳኖች ነበሩ ቅድመ ሁኔታ የነበራቸው። ይሁን እንጂ ቅድመ ሁኔታዊ ሳልሆኑ ቃል ኪዳኖችም ሲሆን የተወሰኑ ግለሰቦችን ሰሚመለከት ቅድመ ሁኔታዊ ነገር አለ። ከቅድመ ሁኔታ ነፃ የሆነ ቃል ኪዳን ከቅድመ ሁኔታዊ ቃል ኪዳን የሚለየው፥ የመጨረሻ አፈጻጸሙ በእግዚአብሔር ተስፋ የተሰጠበት፥ እንዲሁም በርሱ ኃይልና ሉዓላዊነት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ነው። 

1. ቅኤደን ቃል ኪዳን” እግዚአብሔር ከሰው ጋር የገባው የመጀመሪያ ቃል ኪዳን ነበር (ዘፍጥ. 1፡26-31፤ 2፡16-17)። ያም ቅድመ ሁኔታዊ ሆኖ በአዳም ታማኝ መሆን ወይም አለመሆን ምክንያት ሕይወትና በረከት ወይም ሞትና እርግማን የሚመጡ መሆናቸውን የሚገልጥ ነበር። የኤደን ቃል ኪዳን የሚያጠቃልለው፥ አዳም የሰው ዘር ሁሉ አባት የመሆኑን ኃላፊነት፥ ምድርን የመግዛት፥ እንስሳትን የማዘዝ፥ የአትክልቱን ስፍራ የመጠበቅና መልካሙንና ክፉውን ከምታስታውቀው ዛፍ ፍሬ አለመብላትን ነበር። አዳምና ሔዋን ከተከለከለው ዛፍ ፍሬ በመብላታቸው፥ ያለመታዘዝ ቅጣት የሆነው ሞት ተፈረደባቸው። ወዲያውኑ መንፈሳዊ ሞት ሞቱ፥ ከዚያ ለመዳን ዳግም ልደት አስፈለጋቸው። ቆይተውም አካላዊ ሞት ሞቱ። የእነርሱ ኃጢአት የሰውን ዘር ሁሉ ተመሳሳይ በሆነ ኃጢአትና ሞት ውስጥ ጣለው። 

2. ኅዳማዊው ቃል ኪዳን” ከውድቀት በኋላ ከሰው ጋር የተደረገ ነበር(ዘፍጥ. 3፡16-19)። ይህ ቃል ኪዳን ከቅድመ ሁኔታዎች ነጻ የሆነና ከኃጢአቱ የተነሣ የሰው ዕጣ በሕይወቱ ዘመን ምን መምሰል እንዳለበት እግዚአብሔር ያወጀበት ነው። ምንም ዓይነት ይግባኝ ወይም የሰው ኃላፊነት አልነበረበትም። 

ቃል ኪዳኑ በአጠቃላይ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሰውን ሕይወት የሚለውጡ ጠቃሚ ሁኔታዎችን የሚያዘጋጅ ነበር። በዚህ ቃል ኪዳን የምንመለከተው ነገር፥ በእባብ የተመሰለው ሰይጣን መረገሙ (ዘፍጥ. 3፡14፤ ሮሜ 16፡20፤ 2ኛ ቆሮ. 11፡3፥ 14፤ ራእይ 12፡9)፤ እና አዳኝ የሚመጣ የመሆኑ ተስፋ (ዘፍጥ. 3፡15) ሲሆን፥ ተስፋው በመጨረሻ በክርስቶስ ተፈጽሟል። በዚያ ጊዜ ሴት በወሊድ ወቅት በብዙ ምጥና ጣር እንድትሠቃይ የተፈረደባት ከመሆኑም ባሻገር፥ ወንድ ራስ መሆኑን አውቃ እንድትገዛለት ተወስኖባታል (ዘፍጥ. 1፡26-27፤ 1ኛ ቆሮ. 11፡7-9፤ ኤፌ. 5፡22-25፤ 1ኛ ጢሞ. 2:11-14)። ከዚያ ወዲህ ሰው ሰፊቱ ወዝ እንጀራ እንዲበላ (ዘፍጥ. 2፡15፤ 3፡17-19)፥ በድካም እንዲኖርና በመጨረሻም እንዲሞት ተፈረደበት (ዘፍጥ. 3፡19፤ ኤፌ. 2፡5)። ከዚህ ጊዜ በኋላ ሰውም በአጠቃላይ በአዳማዊ ቃል ኪዳን ሥር መተዳደሩን ቀጠለ። 

3. ኖኀዊው ቃል ኪዳንስኖጎና ከልጆቹ ጋር ተደረገ(ዘፍጥ. 9፡1-18)። ይህ ቃል ኪዳን ከአዳማዊው ቃል ኪዳን የተወሰኑ ሁኔታዎችን የሚደግም ቢሆንም፥ ኃጢአትን ለመግታት ይቻል ዘንድ አዲስ የሰብአዊ መንግሥት ሥርዓትን አምጥቷል። እንደ አዳማዊው ቃል ኪዳን ከቅድመ ሁኔታዎች ነጻ ስለሆነም ከኖኅ ቀጥሎ ላለው የሰው ዘር የእግዚአብሔርን ዓላማ ገልጧል። 

የቃል ኪዳኑ ደንቦች ሰው የገደለ ይሙት የሚል ሕግ ያለውን ሰብአዊ መንግሥት አካተዋል። የተፈጥሮ ትክክለኛ ሥርዓትም ጸንቷል (ዘፍጥ. 8፡22፤ 9፡2)፥ ከጥፋት ውኃ በፊት አትክልት ብቻ ይመገብ የነበረው ሰው፥ የእንስሳት ሥጋም እንዲበላ ተፈቀደለት (ዘፍጥ. 9፡3-4)። 

የኖኅ ቃል ኪዳን ስለ ሦስቱ ልጆቹ ትውልድ የተነገረውን ትንቢት ያካትታል (ዘፍጥ. 9፡25-27)፤ ሴምም መሢሕ የሚመጣበት የትውልድ መስመር እንዲሆን ተሰይሟል። አሕዛብ በዓለም ታሪክ የበላይነት የሚኖራቸው መሆኑ ስለ ያፌት በተነገረው ትንቢት ተገልጧል። የሕሊና ሥፍረ-ዘመን በአዳም ቃል ኪዳን እንደተጀመረ ሁሉ፥ በኖኅ ቃል ኪዳንም የሰብአዊ መንግሥት ሥፍረ ዘመን ተጀመረ። 

4 . ብርሃማዊው ቃል ኪዳን” (ዘፍጥ. 12፡1-4፤ 13፡14-17፤ 15፡1-7፤ 17፡1-8)፥ የወደፊቱን ታሪክ በተመለከተ የቀረበና ከታላላቅ የእግዚአብሔር መገለጦች አንዱ ሲሆን፥ በውስጡም ስምስት አቅጣጫ ያተኮሩ ጥልቅ ተስፋዎች ተሰጥተዋል። ከሁሉም አስቀድሞ ለአብርሃም ዘሩ እጅግ እንደሚበዛ፥ (ዘፍጥ. 17፡16)፥ እንደሚባረከ (ዘፍጥ. 13፡14-15፥ 17፤ 15፡6፥ 18፤ 24፡34-35፤ ዮሐ.8፡56)፤ ስሙ ታላቅ እንደሚሆንና (ዘፍጥ. 12፡2)፥ ራሱም በረከት እንደሚሆን ተስፋ ተሰጥቶታል። 

ሁለተኛ፥ በአብርሃም በኩል ታላቅ ሕዝብ እንደሚመጣ ተስፋ ነበረ (ዘፍጥ 12፡2)። በእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ ይህ በዋናነት የሚመለከተው፥ እስራኤልንና አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች የመሠረቱትን የያዕቆብ ትውልድ ነው። ለዚህ ሕዝብ ምድርን የመውረስ ተስፋ ተሰጥቶት ነበር (ዘፍጥ. 12፡7፤ 13፡15፤ 15፡18-21፤ 17፡7-8)። 

ሦስተኛው ታሳቅ የአብርሃም ቃል ኪዳን ክፍል በአብርሃም አማካይነት መላው ዓለም እንደሚባረክ የተሰጠው ተስፋ ነው (ዘፍጥ, 12፡3)። ይህም እስራኤል የእግዚአብሔር ልዩ መለኮታዊ መገለጥ መተላለፊያ፥ እግዚአብሔርን የሚገልጡ ነቢያት ምንጭና የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎችን አመንጭ በመሆኗ የሚከናወን ነበር። ከሁሉም የሚልቀው ተስፋ ለአሕዛብ የሚሆነው በረከት የሚመጣው፥ ከአብርሃም ዘር በሚወስደው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መሆኑ ነበር። እስራኤል ከእግዚአብሔር ጋር ባላት ልዩ ግንኙነት ምክንያት የሚረግሙአትን እርሱ እንደሚረግምና የሚባርኩትንም እንደሚባርካቸው ልዩና የማይሻር ቃል ኪዳን አደረገ (ዘፍጥ. 12፡3)። 

እንደ እዳማዊና ኖኀዊ ቃል ኪዳኖች ሁሉ የአብርሃማዊው ቃል ኪዳንም ከቅድመ ሁኔታ ነጻ ነው። የማንኛውም የእስራኤል ትውልድ አባላት ለእግዚአብሔር ቢታዘዙ የተዘጋጀላቸውን ሁሉ እንደሚያገኙና ባይታዘዙ ግን ለምርኮ አልፈው እንደሚሰጡ የታወቀ ነበር። እግዚአብሔር ለእስራኤል የነበረው የመጨረሻ ዓላማ መባረከ፥ ራሱን በእስራኤል በኩል መግለጥ፥ ቤዛነትን በርሷ በኩል ማዘጋጀትና እሰራኤልን ወደ ተስፋይቱ ምድር ማስገባት ነበር። ጉዳዩ በትክክል በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ኃይልና ፈቃድ እንጂ በሰው ኃይልና ፈቃድ ላይ የተመሠረተ ስላልነበረ መከናወኑ ፍጹም እርግጥ ነበር። በብሉይ ኪዳን እስራኤላውያን ቢወድቁም፥ እግዚአብሔር በብዙ ሁኔታዎች ራሱን ገልጦላቸዋል፥ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲጻፍ አድርጓል። እንዲሁም በመጨረሻ ክርስቶስ ተወለደ፥ ኖረ፥ ሞተ፤ የእግዚአብሔር ቃል እንደተናገረውም በትክክል ከሙታን ተነሣ። የሰው ውድቀት ያለ ቢሆንም የእግዚአብሔር ዓላማ መፈጸሙም የተረጋገጠ ነው። 

5, ሙሌያዊው ቃል ኪዳንለእስራኤል ልጆች በሙሴ አማካይነት የተተቸው፥ ከግብፅ ወጥተው ወደ ተስፋይቱ ምድር በሚጓዙበት ጊዜ ነበር (ዘጸ. 20፡1-31፡18)። በዘጸአት መጽሐፍ እንደተካተተውና በሌሎችም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንደተብራራው፥ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር የሚኖረውን የግንኙነት ሕግ ለሙሴ ሰጠው። እነዚህ ወደ ሰድሰት መቶ ይደርሳሉ ተብሎ የሚገመቱ ግልጥ ትእዛዞች በሦስት ዐበይት ክፍሎች ይመደባሉ። ሀ. ትእዛዛት፡- የእግዚአብሔርን የተለየ ፈቃድ የሚያጠቃልሉ (ዘፍጥ. 20፡1-26)፤ ለ. ፍርዶች፡- ከእስራኤል ማኅበራዊ ሕይወት ጋር የተዛመዱ (ዘጸ. 21፡1-24፡11) እና ሐ. ሥርዓቶች ናቸው (ዘጸ. 24 ፡12-31፡18)። 

የሙሴ ሕግ በቅድመ ሁኔታዎች ላይ የተመሠረተ በመሆኑ፥ እስራኤል ሲታዘዝ እግዚአብሔር የሚባርከው መሆኑን፥ ባይታዘዝ ግን የሚረግመውና የሚቀባው መሆኑን የሚናገረ ሥርዓት በውስጡ እካቷል። ይህ በተለይ ዘዳግም 28 ውስጥ በግልጥ ይታያል። እስራኤል እንደማይታዘዝ የተነገረ ቢሆንም፥ እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደማይተው ተስፋ ሰጥቷል (ኤር. 30፡1)። ሙሴያዊው ቃል ኪዳን ጊዜያዊና በክርስቶስ መሰቀል የሚያበቃ ነበር። ጸጋን የሚመዕከቱ ነጥቦች ቢኖሩትም፥ በመሠረቱ ግን የሥራ ቃል ኪዳን ነው። 

6. ስለ ከነዓን ምድር የተሰጠው ቃል ኪዳን (ዘዳ. 30፡1-10) ከቅድመ ሁኔታ ነጻ የኝ ቃል ኪዳን ሲሆን፥ እስራኤል በመጨረሻ ምድሩን የምትይዝ መሆንን ያስገነዝባል። ይህ ቃል ኪዳን የሚያስገነዝበን በመሠረቱ እንድ ከቅድመ ሁኔታዎች ነጻ የሆነ ቃል ኪዳን በርግጥ የሚፈጻም መሆኑን ነው። ሆኖም ይብዛም ይነስ ለማንኛውም የተለየ ትውልድ ቅድመ ሁኔታዊ ይዘት ይኖረዋል። ዘፍጥረት 12፡7 ላይ እና፥ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ለአብርሃም እንደገና የተረጋገጠሰት ተስፋ፥ ዘሩ ምድሪቱን የሚወርስ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነበር። ይሁን እንጂ፥ ካለመታዘዝ ሳቢያ ያዕቆብና ትውልዱ ከስደት በፊት በመቶዎቹ ለሚቆጠሩ ዓመታት ግብፅ ውስጥ ኖሩ። ያም ሆኖ ከእግዚአብሔር ዓላማ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ተመልሰው ቢያንስ የምድሪቱን ከፈል ያህል ወርሰዋል። በኋላ ደግሞ ካለመታዘዝና የእግዚአብሔርን ሕግ ካለማክበር የተነሣ ለአሶርና ለባቢሎን ምርኮ ተዳረጉ። በባቢሎን ምርኮ ሰባ ዓመት ከቆዩ በኋላ በእግዚአብሔር ጸጋ እንደገና ተመልሰው፥ በ70 ዓ.ም. ኢየሩሳሌም እስከተደመሰሰች ድረስ ምድሪቱን ይዘው ነበር። ይሁን እንጂ፥ እስራኤል ዓመፀኛም ብትሆን በመጨረሻ ወደ ምድሯ እንደምትመለስ፥ በሠላምና በበረከት እንደምትኖር እንደገናም እንደማትበትን ተስፋ ተሰጥቷታል (ሕዝ. 39፡25-29፤ አሞፅ 9፡14-15)። 

ስለዚህ የአሁኑ የእስራኤል ወደ ምድሯ መመለስ ታላቅ ጉዳይ ነው። ምክንያቱም ለፍጻሜው ዘመን እስፈላጊ የሆነውን መድረክ ይህ የእስራኤል መመለስ ያከናውነዋል። 

የእስራኤል ወደ ምድሯ የመመለስ ዕቅድ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ መንግሥቱን ከመሠረተ በኋላ አንድ እስራኤላዊ እንኳ እስከማይቀር ድረስ ይጠናቀቃል (ሕዝ. 39፡25-29)። ማንኛውም ትውልድ ባለመታዘዙ ሳቢያ ከምድሩ እንዲሰደድ ሲደረግም፥ እግዚእብሔር ሕዝቡን ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመመለስ ያለው የመጨረሻ ዓላማ፥ ቅድመ ሁኔታ የሌለውና በእርግጥ የሚፈጸም ነው። 

በመሆኑም ስለ ከነዓን ምድር የተሰጠው ቃል ኪዳን የእስራኤልን ባሰማመኗና ባለመታዘዟ መበታተንን (ዘፍጥ. 15፡13፤ ዘዳ. 28፡63-68)፥ የንስሐና የመታደስ ጊዜያትን (ዘዳ. 30፡2)፥ የእስራኤልን እንደገና መሰብሰብ (ዘዳ. 30፡3፤ ኤር. 23፡8፤ 30፡3፤ 31፡8፤ ሕዝ. 39፡25-29፤ አሞጽ 9፡9-15፤ ሐዋ. 15፡14-17)፥ የእስራኤልን በምድርዋ እንደገና መመሥረት (ኢሳ. 11፡11-12፤ ኤር. 23፡3-8፤ ሕዝ. 37:21-25፤ አሞጽ 9፡9-15)፥ የእስራኤል መንፈሳዊ መለወጥና ብሔራዊ መጠናከርን (ሆሴ. 2፡14-16፤ ሮሜ 11፡26-27)፥ በመንግሥትነት የመጨረሻውን ሠላምና ብልጥግና ማግኘቷን (አሞጽ 9፡11-15)፥ የጠላቶቿን ሰመለኮታዊ ፍርድ መቀጣት ያጠቃልላል (ኢሳ. 14፡1-2፤ ኢዩ. 3፡1-8፤ ማቴ. 25፡31-46)። 

1. “ዳዊታዊው ቃል ኪዳን” (2ኛ ሳሙ. 7፡4-16፤ 1ኛ ዜና. 17፡3-15)። ከቅድመ ሁኔታዎች ነጻ የሆነና እግዚአብሔር ፍጻሜ የሌለውን ንጉሣዊ ሐረግ፥ ዙፋንና መንግሥት ለዳዊት እንደሚሰጠው ተስፋ የገባበት ሲሆን፥ ተስፋዎቹ ሁሉ ዘላለማዊ ናቸው። ይህ ቃል ኪዳን ያህዌህ የዳዊትን ትውልድ ዘመነ መንግሥት አስፈላጊ ከሆነ በቅጣት ሊያቋርጥባቸው መብት እንዳለው የሚያረጋግጥ ቢሆንም (2ኛ ሳሙ. 7፡14-15፤ 

መዝ. 89፡20-37)፥ ቃል ኪዳኑ ግን የሚፈርስ ወይም የሚቀየር አይደለም። 

አብርሃማዊው ቃል ኪዳን ለእስራኤላውያን በሕዝብነታቸው የዘላለም ዋስትናን እንዳረጋገጠና (ኤር. 31፡36)፥ ምድሪቱንም ለዘላለም እንዳስጨበጣቸው ሁሉ (ዘፍጥ. 13፡15፤ 1ኛ ዜና. 16፡15-18፤ መዝ. 105 ፡9-11)፥ የዳዊት ቃል ኪዳንም እንዲሁ የዘላለም ዙፋንን (2ኛ ሳሙ. 7: 16፤ መዝ. 89፡36)፥ የዘላለም ንጉሥ (ኤር. 33፡21)፥ እና የዘላለም መንግሥትን ያረጋግጥላቸዋል (ዳን. 7፡14)። ይህ ቃል ኪዳን ከተደረገና በእግዚአብሔር መሐላ ከጸደቀበት ዕለት ጀምሮ (ሐዋ. 2፡30)፥ እስከ ክርስቶስ ልደት ድረስ ዳዊት በዙፋኑ የሚቀመጥሰትን ልጅ አላጣም (ኤር. 33፡21)። የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ልጅና የዳዊትም ልጅ የሆነው ክርስቶስ የዙፋኑ ባለመብት፥ ሰራሽና ገና በዙፋኑ ላይ የሚቀመጥ እንደመሆኑ (ሉቃስ 1፡31-33)፥ ከልጆቹ አንዱ ለዘላለም ይነግሣል የሚለውን ተስፋ ከፍጻሜ ያደርሰዋል። 

ዳዊታዊው ቃል ኪዳን ከሁሉም የሚልቀው፥ ክርስቶስ በምድር ላይ የሚነሥበትን የሺህ ዓመት መንግሥት በማረጋገጡ ነው። ከሙታን የሚነሣው ዳዊት፥ በንጉሡ ክርስቶስ ሥር ሆኖ በእስራኤል ላይ ይገዛል (ኤር. 23፡5-6፤ ሕዝ. 34፡23-24፤ 37፡24)። ዳዊታዊው ቃል ኪዳን ከርስቶስ በሰማይ ዙፋኑ በነገሠ ጊዜ የተፈጸመ አይደለም። ዳዊት መቼም ሰአብ ዙፋን ላይ አልተቀመጠም፤ ወደፊትም አይቀመጥም። የሚነግሠው በምድራዊው ዙፋን ነው (ማቴ. 25፡31)። ስለዚህ ዳዊታዊው ቃል ኪዳን ወደፊት ለሚፈጸመው የእግዚአብሔር ትንቢታዊ ዕቅድ ቁልፍ ነው። 

8. ብሉይ ኪዳን ውስጥ የተተነበየውና የመጀመሪያ ፍጻሜው በሺህ ዓመቱ መንግሥት የሚሆነው እዲስ ቃል ኪዳንከቅድመ ሁኔታ ነጻ ነው(ኤር. 31፡31-33)። እርሱም በኤርምያስ እንደተገለጠው እግዚአብሔር ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር” የሚገባው አዲስ ቃል ኪዳን ነው (ቁ. 31 )። ይህ ቃል ኪዳን በእስራኤል ከተጣሰው ሙሴያዊ ቃል ኪዳን ጋር ሲነጻጸር፥ አዲስ ቃል ኪዳን ነው (ቁ.32)። 

በቃል ኪዳኑም እግዚአብሔር “ከእነዚያ ወራት በኋላ …ሕጌን በልቦናቸው እኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፥ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፥ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል” በማለት ተስፋ ይሰጣል (ቁ. 33)። እግዚአብሔር ራሱን በግል በመግለጡና ፈቃዱንም ለሕዝቡ በማሳወቁ እንዲህ ተብሏል፡- “እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፥ እያንዳንዱም ወንድሙን፥ እግዚአብሔርን እወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፥ ይላል እግዚአብሔር። ሰደሳቸውን እምራቸዋለሁና፥ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስብምና” እያለ ያረጋግጣል (ኤር. 31፡34)። 

ይህ ምንባብ ክርስቶስ ስለሚነግሥበት የሺህ ዓመት መንግሥት ሁኔታዎችና ሰው ሁሉ ስለ ክርስቶስ የሚያውቅ ስለመሆኑ ይናገራል። በመሆኑም አንድም ሰው ባልንጀራውን ስለ ክርስቶስ ወንጌል ማስተማር እያስፈልገውም። ምክንያቱም ጌታን የሚመለከቱትን እውነታዎች ሁሉ መላው ዓለም ያውቃቸዋል። ደግሞም ዘመኑ እግዚአብሔር የእስራኤላውያንን ኃጢአት ይቅር የሚልበትና እጅግ የሚባረኩበት ዘመን ይሆናል። በኤርምያስ በኩል ከተሰጠው ከዚህ ቃል ኪዳን ግልጥ መሆን ያለበት ነገር፥ ቃል ኪዳኑ ዛሬ በመፈጸም ላይ አለመሆኑ ነው። ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያንም እውነትን ላልተረዳው ዓለም ወንጌሉን የማዳረሷ ትእዛዝ ገና በመከናወን ላይ ነው። 

አዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያንን ከአዲሱ ቃል ኪዳን ጋር ስለሚያገናኛት፥ አንዳንዶች ለእስራኤል የተሰጠውን ቃል ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ትፈጽመዋለች በማለት አስተምረዋል። በዚህ መሠረት የሺህ ዓመቱ መንግሥትና በእስራኤል መታደስ የማያምኑ ክፍሎች ይህ አዲስ ቃል ኪዳን ቤተ ክርስቲያን እንደሚፈጸም ያስተምራሉ። ይህን የሚያስተምሩበት ምክንያት በቃል ኪዳኑ የተገለጡ ተስፋዎችን ቃል በቃል ሳይሆን መንፈሳዊ ትርጉም በመስጠትና እስራኤልንና ቤተ ክርስቲያንን አንድና የማይለያዩ በማድረግ ነው። የእስራኤልን የወደፊት መታደሰና የሺህ ዓመቱን መንግሥት የሚቀበሉ ሌሎች ክፍሎች ደግሞ አዲስ ኪዳን አዲሱን ቃል ኪዳን ይመለከታል ይሳሉ። 

ይኸውም እስራኤል ካቤተ ክርስቲያን ጋር የሚኖራትን የወደፊት ቃል ኪዳን ወይም ሁለት እዲስ ቃል ኪዳኖችን ለመለየት (አንዱ በኤርምያስ የተገለጠውና ለእስራኤል የተሰጠው ሲሆን፥ ሌላው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት በአሁኑ የጸጋ ዘመን የተሰጠውና ለቤተ ክርስቲያን ድነት የሆነው አዲስ ቃል ኪዳን ነው) ነው በማለት ያስገነዝባሉ። እርግጥ አዲሱ ቃል ኪዳን የተሰጠው ለእስራኤልም ይሁን ለቤተ ክርስቲያን የሚገኘው በክርስቶስ ሞትና በፈሰሰው ደሙ ነው። 

እዲሱ ቃል ኪዳን እግዚአብሔር ከልጁ ደም የተነሣ ለሰዎች ሊያደርግ ያቀዳቸውን ነገሮች ሁሉ ያረጋግጣል። ይህም በሚከተሉት ሁለት መንገዶች ሊታይ ይችላል። 

(ሀ) በክርስቶስ የሚያምኑትን ሁሉ ያድናቸዋል፥ ይጠብቃቸዋል። ልጁን መስለው በመንግሥተ ሰማያት እንዲኖሩ ያስችላቸዋል። ለመዳን በኢየሱስ ክርስቶስ የማመኑ አስፈላጊነት እውነታ በዚህ ቃል ኪዳን ውስጥ እንደ ቅድመ ሁኔታ የተጠቃለለ ጉዳይ አይደለም። ማመን የቃል ኪዳኑ ክፍል ሳይሆን፥ ከዚያ ወደሚገኘው ዘላለማዊ በረከት ለመድረስ የሚያስችል መሠረት ነው። ቃል ኪዳኑም በቀጥታ የሚገናኘው ካልዳኑት ጋር ሳይሆን ከዳኑት ጋር ሆኖ ስለ እነርሱ የእግዚአብሔርን ታማኝነት ተስፋ ይሰጣል። ይህም፥ 

“በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ተረድቼአለሁና” ተብሎ በተጻፈው ቃል ተረጋግጧል (ፊልጵ. 1፡6)። የእግዚአብሔርን የማዳንና የመጠበቅ ኃይል የሚገልጠው ሌላ ተስፋ ሁሉ በጸጋ የዚሁ ቃል ኪዳን አካል ነው። 

በአሁኑ ዘመን በምድር ለሰው ፍጹም ጥበቃን የማያረጋግጥና በመጨረሻም የዳነውን በክብር የማያቀርብ ድነት ከቶ የለም። በአብና ክርስቲያን በሆነ ልጁ መካከል የየዕለት ሕይወትን የሚመለከት ጉዳይ ሊኖር ይችላል። ዳዊት ኃጢአት በሠራ ጊዜ እንደሆነው ሁሉ፥ የክርስቲያንም ኃጢአት ከእግዚአብሔር ቅጣትን ያስከትል ይሆናል። ነገር ግን በአማኝ ዕለታዊ ሕይወት ውስጥ የሚነሡ ጥያቄዎች እግዚአብሔር በጸጋ በተቀበላቸው ሰዎች የዘላለም ድነት ተስፋ ላይ ከቶ ምንም የቅድመ ሁኔታ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ አይችሉም። 

በሰው ፈቃድ፥ ኃይልና አስፈላጊነት ላይ ትኩረት የሚሰጡ ወገኖች አሉ። በዚህ አመለካከታቸው መሠረት የድነትና ሰላም መጠበቅ በሰው ፈቃድ ትብብር ቅድመ ሁኔታ መከናወን አለበት ይላሉ። አባባሳቸው በሰው አእምሮ ሲገመገም ትክክል ቢመስልም፥ መጽሐፍ ቅዱስ በሚሰጠው መገለጥ ላይ የተመሠረተ አይደለም። 

በማንኛውም ሁኔታ እምነታቸውን ሰርሱ ለሚያደርጉ ሁሉ እግዚአብሔር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሚያደርግላቸውን አውጇል (ዮሐ. 5፡24፤ 6፡37፤ 10፡28)። ይህ የእያንዳዱኝ ሰው እሳብና ልብ ሙሉ በሙሉ ሊገዛ ይገባል። እግዚአብሔር ለኖኅ፥ ዘሩ የሰጠውን ትዕዛዛት በሙሉ እንደሚከተሉ ወይም ደግሞ ለአብርሃም ታላቅ ሕዝብ እንደሚያደርገው እና ከዘሩ ክርስቶስ እንደሚወለድ ያወጀውን እንዳለ አምኖ የመቀበልን ያህል ለሕሊና አስቸጋሪ አይሆንምና። 

በማንኛውም ረገድ ሲሆን ይህ ጉዳይ የሉዓላዊ ኃይልና ሥልጣን መግለጫ ነው። እግዚአብሔር ለሰው ፈቃድ ነጻነትን መስጠቱ ይታወቃል። እርሱ የሰዎችን ፈቃድ ይመለከታል። የዳኑ ሰዎችም ድነትና አገልግሎታቸው በምርጫቸው እንደሆነ እርግጠኞች ናቸው። እግዚአብሔር የሰዎችን ፈቃድ የሚቆጣጠር መሆኑ ተነግሮናል (ዮሐ. 6፡44፤ ፊል. 2፡13)። እንዲሁም የሰውን ፈቃድ የሚፈልግና በረከቱንም በዚያ ላይ እንደሚመሠረት እንረዳለን (ዮሐ. 5፡40፤ 7፡17፤ ሮሜ 12፡1፤ 1ኛ ዮሐ. 1፡9)። 

መጽሐፍ ቅዱስ ለእግዚአብሔር ሉዓላዊነት የማያወላውል ትኩረትን ይሰጣል። መሆን ያለበትን ነገር ሁሉ እግዚአብሔር በትክክል ወስኗል፤ ያም መፈጸም አለበት። እርሱ ሰሚሆኑት ነገሮች ለመጸጸት ወይም ለመደነቅ አይችልም። እንዲሁም የእግዚአብሔር የማይለወጥ ታላቅነት ሁለት አቅጣጫዎች፥ ማለት ዘላለማዊ ዓላማና ትክክለኛ ተፈጻሚነቱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እኩል ትኩረት ተሰጥቷቸዋል። ለሰብዓዊ ፈቃድ አንዳንድ ክንዋኔዎች በቂ ነጻነትን ቢሰጥም ዓላማው በምንም ሁኔታ አይሰናከልም። የዚህን እውነት አንድ ገጽታዎች ከሌሳው ለይቶ መመልከት፥ በአንድ በኩል ወደ ጸሎት ልምምድ ወደማያደርስ፥ የእግዚአብሔርን ፍቅር ለመግጠን ወደማይቻልበት፥ ለፍርድ የሚሆን መሠረት ወደሌለበት፥ ለወንጌል ሥራ አሳብን የሚስብ ፍሬ ወደማያፈራበትና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ፍቺም ትርጉም ወደማይሰጥበት ያደርሳል። በሌላ አባባል እግዚአብሔርን ከዙፋኑ ወደማውረድ አዝማሚያ ያመራል። የሰው ፈቃድ በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ሊሆን እንደሚችል ማመኑ ተገቢ ነው። የእግዚአብሔር ሉዓላዊነት ከሰው ፈቃድ ጋር የተያያዘ ነው ብሎ ማመን ግን መሠረት የለሽ አሳብ ነው። ያመኑ ሁሉ የዳኑና ለዘላለም የማይጠፉ ናቸው፤ ምክንያቱም ድነታቸው ቅድመ ሁኔታ በሌለው የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ላይ ተመሥርቷል። 

(ለ) የእስራኤል የወደፊት ድነት ከቅድመ ሁኔታ ነጻ በሆነ አዲስ ኪዳን የተሰጠ ተስፋ ነው (ኢሳ. 27:9፤ ሕዝ. 37 ፡23፤ ሮሜ 11፡26-27 )። ድነቱ የሚፈጸመው በፈሰሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ብቻ ነው። ከክርስቶስ መሥዋዕትነት የተነሣ እግዚአብሔር ግለሰብን ለማዳን ፈቃዱ እንደሆነ ሁሉ፥ ሕዝብንም ለማዳን ይፈቅዳል። በክርስቶስ ትምህርት መሠረት እስራኤል በእርሻ ውስጥ የተሰወረች መዝገብን ትመሰላለች። እርሻው ዓሰም ነው። ያንን መዝገብ ለመግዛትና የራሱ ላማድረግ ያለውን ሁሉ የሸጠው ክርስቶስ እንደሆነ እናምናለን (ማቴ. 13፡44)። 

ስምንቱ ቃል ኪዳኖች በሚመረመሩበት ጊዜ፥ ከቅድመ ሁኔታ ነፃ የሆኑ ቃል ኪዳኖችን በተመለከተ በእግዚአብሔር ታላቅነት ላይ ብቻ ብዙ ማተኮር ይገባል። ይህ የሚሆነው፥ በቅድመ ሁኔታ ላይ ተመሠረቱና ሰውም ከቶ ከማይቻለው ቃል ኪዳኖች መፈጸም ጋር ሲነጻጸር ነው። እግዚአብሔር ከቅድመ ሁኔታ ነጻ አድርጎ የሚፈጽመው ማንኛውም ነገር የሚከናወነው፥ ከእርሱ ፍጹምነት የተነሣ ነው።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

22
ትምህርት 22 ከ52

መላእክት

ሀ. የመላእክት አፈጣጠር 

መጽሐፍ እንደሚናገረው፥ እግዚአብሔር ሰውን ከመፍጠሩ አስቀድሞ ለቁጥር የሚያዳግቱ ሠራዊተ መላእክት ፈጥሯል። መላእክት ልክ እንደ ሰው ሕልውና ያላቸው ከመሆናቸውም በላይ፥ ታላቅ እውቀትና የግብረ ገብ ኃላፊነት ችሎታ አላቸው። “መልአክ” ማለት ልዩ በሆነ አገባሱና አገላለጡ መልእክተኛ ማለት ነው። ቃሉ አንዳንዴ ለሌሎች መልእክተኞች ማለት በራእይ 2-3 የተጠቀሱትን የሰባት የእስያ አብያተ ክርስቲያን መልእክተኞች ላመሳሰሉት መጠሪያ ሊሆንም ይችላል (ራእይ 1፣ 20፤ 2፡1፥ 8፥ 12፥ 18፤ 3፡1፥ 7፥ 14)። አንዳንዴም ለሰብአዊ መልእክተኞች መጠሪያነት አገልግሏል (ሉቃስ 7፡24፤ ያዕ. 2፡25)። የሞቱ ሰዎችን መንፈስ ላመጥቀሻም ውሏል (ማቴ. 18፡10፤ ሐዋ. 12፡15)። እዚህ ላይ ከፍተኛ ግንዛቤኝ የሚሻው ዐቢይ ጉዳይ፥ ሰዎች ሲሞቱ ወደ መላእክትነት ይለወጣሉ ወይም ከሰዎች የተለየ መንፈስ ይሆናሉ ማለት አለመሆኑ ነው። “መልእክተኛ” የሚለው ቃል በጣም ሰፊ አሳብ ይዟል። በዚህ ሁኔታ “መላእክትን የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን መልአክ ለማመልከትም፥ ማለት ክርስቶስ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ሰመላእክት መልክ ከእግዚአብሔር ወደ ሰው የተላከ መሆኑን ለመግለጫነት አገልግሷል (ዘፍጥ. 16፡1-13፤ 21፡17-19፤ 22፡11-16)። 

ቃሉ ሰውን ወይም እግዚአብሔርን በግልጥ ለማመልከቻነት በማይውልበት ጊዜ፥ ግብረ ገባዊ ኃላፊነት ላሰባቸውና፥ በዚህም አኳያ እግዚአብሔርን ለሚያገለግሉ ማለት ልዩ ሁኔታ ላላቸው ሰዎች መጠሪያነት ያገለግላል። መላእክት እንደ ሰው ሁሉ ለዘላለም የሚኖሩና ከሌሎች ፍጡራን የሚሰዩ ናቸው። እግዚአብሔር በዘመናት ባለው ዕቅድ ውስጥ ጎላ ያለ ስፍራ የሚይዙ ሲሆኑ፥ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ከመቶ ጊዜ በላይ፥ አዲስ ኪዳን ውስጥ ደግሞ ይበልጥ በተደጋጋሚ ተጠቅሰዋል። 

መላእክት እጅግ ከቁጥር በላይ ሆነው በአንድ ጊዜ የተፈጠሩ ናቸው (ዕብ. 2፡22፤ ራእይ 5፡11)። ጥበብ፥ ፈቃድና ስሜት ያለው አንድ ፍጡር የሚኖሩት ባሕርያት ሁሉ አሏቸው። ከዚህም የተነሣ ለእግዚአብሔር አምልኮ የማቅረብ ችሎታ አላቸው (መዝ. 148 ፡2)። ስላ አገልግሎታቸውና ሥነ- ምግባራዊ ምርጫቸውም ኃላፊነት አለባቸው። 

2204 በመንፈሳዊ ሥርዓት የተፈጠሩ እንጂ፥ ሰብአዊ አካል ያላቸው አይደሉም (1ኛ ቆሮ. 15፡44)። አንዳንዴ ግን በአካል ሊገለጡና እንደ ሰው ሊታዩ ይችላሉ (ማቴ. 28፡3፤ ራእይ 15፡6፤ 18፡1)። በመዋለድ አይባዙም፥ አካላዊ ሞትም አይሞቱም። ከሰው ጋር የሚመሳሰሉበት ነገር ቢኖርም፥ ዓበይት በሆኑ ነገሮች የተለዩ ናቸው። 

ለ. ያልወደቁት መላእክት 

በአጠቃላይ መላእክት፥(1) ያልወደቁ መላእክት፥ (2) የወደቁ መላእክት ተብለው በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ይመደባሉ። ያልወደቁት መላእክት በዘመናቸው ሁሉ የተቀደሱ ስለሆኑ ቅዱሳን መላእክት” ተብለው ይጠራሉ (ማቴ. 25፡31)። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በአጠቃላይ ስለ መላእክት ሲጠቀስ በዓይነ ሕሊና የሚታዩት ያልወደቁ መላእክት ናቸው። የወደቁ መላእክት የሚባሉት ደግሞ ቅድስናቸውን ያልጠበቁት ናቸው። 

ያልወደቁ መላእክት በሚከተለው አኳኋን በልዩ ክፍል የሚመደቡ ሲሆን፥ ከእነርሱም አንዳንዶቹ በስም ተጠቅሰዋል። 

1. የቅዱሳን መላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሲሆን፥ የስሙም ትርጉም ንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው” ማለት ነው (ዳን. 10፡21፤ 12፡1፤ 1ኛ ተሰ. 4፡16፤ ይሁዳ 9፤ ራእይ 12፡7-10)። 

2. ከዋና ዋናዎቹ የእግዚአብሔር መልእክተኞች አንዱ ቅዱስ ገብርኤል ሲሆን፥ የስም ትርጉም ተግዚአብሔር ጀግና” ቀሚል አው። ለዳንኤል የተላኩ ታላላቅ መልእክትን (ዳን. 8፡16፤ 9፡21)፥ ለዘካርያስ (ሉቃስ 1፡18-19)፤ እና ለቅድስት ድንግል ማርያም (ሉቃስ 1፡26-38) የተላለፉትን ጭምር በታማኝነት አድርሷል። 

3. ተስዙዎቹ መላእክት የየራሳቸው ስም ባይሰጣቸውም፥ የተመረጡ ተብለው ይጠራሉ (1ኛ ጢሞ. 5፡21)። ይህ አሳብ የሚገርም ነጥብ አለው። ይህም መላእክት በመለኮታዊ አጠራር የተመረጡ መባላቸው፥ ዳግም ተወልደው የዳኑ ሰዎችም የተመረጡ ተብለው ከተጠሩበት አጠራር ጋር መመሳሰሉ አስደናቂ ነው። 

4 . “ኃይላትና ሥልጣናት” የሚለው መጠሪያ የወደቁትንም ሆኝ ያልወደቁን መላእክት ለመጥሪያነት የሚያገለግል ይመስላል (ሉቃስ 21፡26፤ ሮሜ 8፡38፤ ኤፌ. 1፡21፤ 3፡10፤ ቈላ. 1፡16፤ 2፡10፥ 15፤ 1ኛ ጴጥ. 3፡22)። ይህም በመሆኑ ሰዎችን ለመቆጣጠር ወይም ለመያዝ በቅዱሳኑና በወደቁት መላእክት መካከል የማያቋርጥ ጦርነት ይካሄዳል። 

5 . አንዳንድ መላእክት ኪሩቤል በመባል የሚታወቁ ሊሆኝ፥እነርሱም የእግዚአብሔርን ቅድስና ከማንኛውም ዓይነት የኃጢአት ርኩሰት የሚከላከሉ ሕያው ፍጡራን ናቸው(ዘፍጥ. 3፡24፤ ዘጸ. 25፡18፥ 20፤ ሕዝ. 1፡1-18)። የወደቁት መላእክት አለቃ ሰይጣንም በመጀመሪያ ቅዱስ ሆኖ ለዚህ ዓላማ ነበር የተፈጠረው (ሕዝ. 28፡14)። በብሉይ ኪዳን፥ መገናኛው ድንኳን እንዲሁም ቤተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የታቦቱን የሥርየት መክደኛ የሚጠብቁት የኪሩቤል ምስሎች ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ። 

6. ሱራፌል በመባል የሚጠሩት መላእክት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት አንዴ ብቻ፥ ኢሳይያስ 6፡2-7 ውስጥ ነው። እነርሱም ስድስት ክንፎች ያሏቸው፥ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑ፥ በእግዚአብሔር ወደ ምድር የሚላኩና በተለይ የእርሱን ክብር የሚጠብቁ ናቸው። 

7. “የእግዚአብሔር መልአክ” የሚለው ቃል የክርስቶስን በመልከ መልክ መለጥ ለማመልከት ብሉይ ኪዳን ውስጥ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል። ስሙም የሚገባው ለእግዚአብሔር ብቻ ሲሆን፥ ያገለገለውም ከመለኮት ስምድር መገለጥ ጋር ነው። በመሆኑም በምንም ሁኔታ የሠራዊተ መላእክት መጠሪያ ሊሆን አይገባም (ዘፍጥ. 18፡1-19፡29፤ 22፡11፥ 12፤ 31፡11-13፤ 32፡24-32፤ 48፡15፥ 16፤ ኢያሱ 5፡13-15፤ መሳ. 13፡19-22፤ 2ኛ ነገሥት 19፡35፤ 1ኛ ዜና 21፡12-30፤ መዝ. 34፡7)። የእግዚአብሔር መልአክ በሆነው ክርስቶስና በሌሉች መላእክት መካከል ያለው እጅግ ከፍተኛ ልዩነት፥ ጳውሎስ ወደ ዕብራውያን ባስተላለፈው መልእክት ውስጥ ተገልጧል(ዕብ. 1፡4-14)። 

ሐ. የወደቁ መላእክት 

ያልወደቁ መላእክት እንዳሉ ሁሉ፥ ስፍር ቁጥር የሌላቸውና የመጀመሪያ ክብራቸውን ትተው የወደቁ መላእክት መኖራቸውም ተገልጧል። ሲፈጠር ቅዱስ በነበረውና በኋላ ግን በትዕቢቱ ከከፍታ ቦታ በወደቀው መልአክ፥ በሰይጣን የተመሩት እነዚህ ለቁጥር የሚያዳግቱ መላእክት ከዳተኞች፥ በእግዚአብሔር ላይ ያመፁ፥ እንዲሁም በተፈጥሯቸውም ሆነ በስፍራቸው ኃጢአተኞች ሆኑ። 

የወደቁ መላእክት በሁለት ይመደባሉ። እነርሱም፦ (1) ነጻ የሆኑና (2) በእስራት ያሉ ናቸው። ከወደቁት መላእክት ሰይጣን ብቻ ነው በተለይ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚጠቀሰው። ሰይጣን በወደቀ ጊዜ ብዙ ከእርሱ ያነሱ ታናናሽ መላእክትን አስከትሎ እንደነበር ለመገመት ይቻላል (ዮሐ. 8፡44)። ከእነርሱም አንዳንዶቻቸው እስከ ታላቁ የፍርድ ቀን ድረስ ታስረው ለፍርድ ተጠብቀዋል (1ኛ ቆሮ. 6፡3፤ 2ኛ ጴጥ. 2:4፤ ይሁዳ 6)። ሌሎቹ ደግሞ ለጊዘው ነጻ የሆኑና አጋንንት ወይም መናፍስት እየተባሉ በአዲስ ኪዳን በተደጋጋሚ የሚጠቀሱት ናቸው (ማር. 5፡9 15፤ ሉቃስ 8፡30፤ 1ኛ ጢሞ. 4፡1)። በድርጊቱ ሁሉ ተሳታፊ ሆነው ሰይጣንን ስለሚያገለግሉት፥ የመጨረሻ ዕጣውም ተሳታፊዎች ይሆናሉ (ማቴ. 25፡41፤ ራእይ 20፡10)። 

መ. የቅዱሳን መላእክት አገልግሎት 

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ መላእክት በሰፊው የተጠቀሰው አገልግሎታቸው ነው። ቀዳሚው አገልግሎታቸው እግዚአብሔርን ማምለክ ሲሆን፥ ራእይ 4፡8 ውስጥ የአንዳንዶቹ አገልግሎት፥ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም” ተብሏል። ይህ በሌላም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ተጠቅሷል (መዝ. 103፡20፤ ኢሳ. 6፡3)። በአጠቃላይ ቅዱሳን መላእክት በተለያዩ ብዙ መንገዶች እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ መሆናቸው ቀጥሎ ባሉት ተግባራታቸው በመጠኑ ተገልጧል። 

1. በፍጥረት መጀመሪያ(ኢዮብ. 38፡7)፥ ሕግ በሚሰጥበት ጊዜ(ሐዋ. 7፡53፤ ገላ. 3፡19፤ ዕብ. 2፡2፤ ራእይ 22፡16)፥ ክርስቶስ ሲወለድ (ሉቃስ 2፡13)፥ ሲፈተን (ማቴ. 4፡11)፥ በአትክልቱ ስፍራ(ሉቃስ 22:43)፥ በትንሣኤ (ማቴ. 28፡2)፥ በዕርገት ጊዜ(ሐዋ. 1፡10) የነበሩ ሲሆን፥ በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ጊዜም አብረውት ይገለጣሉ (ማቴ. 24፡31፤ 25፡31፤ 2ኛ ተሰ. 1፡7)። 

2. ቅዱሳን መላእክት የድነት ወራሾች የሆኑትን የሚያገለግሉ መናፍስት ናቸው (ዕብ. 1፡14፤ መዝ. 34፡7፤ 91፡11)። ከመላእክት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ወይም ኅብረት እንዲኖረን ባይነገረንም፥ የሁልጊዜ በጎ አገልግሎታቸውን ልንረዳ ይገባል። 

3. መላእክት በምድር ላይ ያሉ ነገሮችን የሚመለከቱና ምስክሮች ናቸው (መዝ. 103፡20፤ ሉቃስ 12፡8፥ 9፤ 15፡10፤ 1ኛ ቆሮ. 11፡10፤ 1ኛ ጢሞ. 3፡16፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡12፤ ራእይ 14፡10)። 

4. አልዓዛር ሲምት ወደ አብርሃም እቅፍ የተወሰደው በመላእክት ነበር(ሉቃስ 16፡22)። 

5. መልእክት በታሪክ አተረዘሩት እገልግሎቶቻቸው በተጨማሪ፥ ጌታችን ወደ ምድር ሲመለስ አብረውት ይመጣሉ፥ በአዲሲቷ ኢየሩሳሌምም ለዘለም ይታያሉ(ዕብ. 12፡22-24፤ ራእይ 19፡14፤ 21፡12)። ቅዱሳን መላእክት በሺህ ዓመቱ መንግሥት መጨረሻ፥ ማለት በአዲሱ ዘላለማዊ መንግሥት መጀመሪያ፥ ፍርድና ሽልማት ሳይጠብቃቸው አይቀርም። የወደቁት መላእክት ደግሞ በዚሁ ጊዜ ከመሪያቸው ጋር በአንድነት ይፈረድባቸውና ወደ እሳት ባሕር ይጣላሉ። 

6. በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጠው የቅዱሳን መላእክት አገልግሎት ትምህርት እጅግ ጠቃሚ ነው። በታሪክ የተገለጠውንና እግዚአብሔር ለፍጡራኑ ያለውን ሰጎ ፈቃድና ልዑላዊ ምሪትን ለመረዳትም በዋናነት ያገለግላል።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

23
ትምህርት 23 ከ52

ሰይጣን፡- ማንነቱና ኃይሉ

ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፍጥረታት ሁሉ ብልጫ ያለው ሆኖ ቢፈጠርም፥ በርሱና በሕያው፥ ዘላለማዊ እና ባልተፈጠረው አምላክ መካከል ሰው ሊረዳ ከሚችለው በላይ የሆነ ልዩነት አለ። በሚቀጥለው ምዕራፍ እንደሚቀርበው ሰይጣን ቀድሞ ቅዱስ መልአክ የነበረ ቢሆንም፥ ካሰበት ቅድስና በመውደቅ የእግዚአብሔር ተፃራሪና የወደቁ መላእክት መሪ ሆነ ። 

ሀ. የሰይጣን ማንነት 

ልክ እንደ እግዚአብሔር እና እንደ ሌሎቹ መላእክት ሁሉ ሰይጣንም በአካለ ሥጋ እይታይም። ማንነቱን ለማወቅ የሚቻለው በቅዱሳት መጻሕፍት በሚቀርበው ማስረጃ መሠረት ነው። ማስረጃዎቹም በሚቀጥለው አኳኋን ቀርበዋል። 

1. ሰይጣን አካል ሆኖ ነው የተፈጠረው። በሰማይና በምድር ያሉ ፍጥረታት ሁሉ “የሚታዩትና የማይታዩት፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት” በክርስቶስ ለክርስቶስ እንደተፈጠሩ በቁሳስይስ 1፡16 ውስጥ ተገልጧል። የሠራዊተ መላእክት አፈጣጠር ምናልባት ከሌሎች ቁሳዊ ፍጥረታት ይቀድም ይሆናል። ነገር ግን ዮሐንስ 1፡1-2 ውስጥ እንደተገለጠው፥ ሕልውናው ዘላለማዊ የሆነው መለኮት ግን ከሁሉ በፊት ነበር። 

ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ የሰይጣን አፈጣጠር ነው በተለይ የተጠቀሰው። ይህ እውነት ከማይታዩ ሌሎች የእግዚአብሔር ፍጥረታት ሁሉ ጋር ሲነጻጸር ሰይጣን ታላቅ የክብር ስፍራ የነበረው መሆኑን ያመለክታል። 

ሕዝቅኤል 28፡11-19 ውስጥ “ለጢሮስ ንጉሥ” የሙሾ መልእክት እንደመጣለት እንመለከታለን። የመልእክቱ ሙሾ በቀጥታ፥ ለጢሮስ ንጉሥ የተነገረ ነው። ነገሩን ወለቅና ሰፋ አድርገን በመንፈሳዊ ዓይን ስንመረምረው፥ ከእግዚአብሔር ፍጥረታት ሁሉ ቁንጮና ታላቅ የሆነውን ፍጡር፥ ማለት ሰይጣንን እንመለከታለን። ይህ ፍጡር “ጥበብ የተሞላ፥ የውበትም መጨረሻ” ተብሏል።“በእግዚአብሔር ገነት በኤደን የነበርህ ተብሎም ተነግሮለታል። (ቁጥር 13 ላይ የተጠቀሰው ስፍራ ምናልባት ዘፍጥረት 3 ውስጥ የተገለጠው ሳይሆን፥ የመጀመሪያው የእግዚአብሔር ፍጥረት ወይም ቀዳሚው ኤደን ሊሆን ይችላል።) ሰይጣን በመለኮታዊ ዕቅድ የእግዚአብሔርን ቅዱስ ተራራ እንዲሸፍን የተፈጠረና የተቀባ ኪሩብም ነበር (ቁጥር 14)። የእግዚአብሔር ተራራ በቅዱሳት መጻሕፍት አገላለጥ የሚያመለክተው፥ ዙፋንን ወይም የእግዚአብሔን የአጎዛዝ ኃይል ማዕከልን ነው። እዚህ ላይ የተገለጠውን ያህል ብቃት ያለው የጢሮስ ንጉሥ ኖሮ አያውቅም። ይህ አገላላጥ የሚያመለክተው ሌላ ማንንም ሳይሆን ከውድቀቱ በፊት የነበረውን የሰይጣንን ሁኔታ ብቻ ነው። 

2. ሕልው የሆነ አካል የሚፈጽማቸውን ድርጊቶች ሁሉ ሰይጣን ይፈጽማል። የሰይጣንን ማንነት ከሚገልጡ አያሌ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች መካከል ለአብነት ያህል የሚከተሉትን መመልከት ይቻላል። 

(ሀ) ኢሳይያስ 14፡12-17። ነቢዩ በዚህ ስፍራ ሰይጣን ዘመኑ እንዳሰፈበትና በዘመኑም መጨረሻ እንደተፈረደበት፥ እንዲሁም ከታላቅ ቦታውና ክብሩ እንደወደቀ አስተውሎ ከተመለከተና ከተረዳ በኋላ በመለኮታዊ አጠራር የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ” በማለት ይጠራዋል። “መንገሥታትን ያናወጠው። እርሱ ቁጥር 12) በአምስት ሁኔታዎች በእግዚአብሔር ፈቃድ ላይ ዓምፆአል። ሕዝቅኤል 28፡15 ውስጥ እንደተገለጠው ሁሉ በዚህም ክፍል በልቡ የተሰወረውን ኃጢአት እግዚአብሔር አውቆ እንዳጋለጠው እንማራለን (1ኛ ጢሞ. 3፡6ን ይመልከቱ)። 

(ለ) ዘፍጥረት 3፡1-15። በዚህ ስፍራ በተመዘገቡት ድርጊቶቹ ሳቢያ ሰይጣን “እባብ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። ምክንያቱም ለአዳምና ለሔዋን የተገለጠው በእባብ ተመስሎ ነበር። በዚያ የንባብ ክፍል የተጻፈው እያንዳንዱ ቃልና የተገለጠው የሰይጣን ዕቅድ ሁሉ ስለ እርሱ ማንነት ግልጥ ማስረጃ ነው (2ኛ ቆሮ. 11፡3፥ 13-15፤ ራእይ 12፡9! 20፡2)። 

(ሐ) ኢዮብ 1፡6-12፤ 2፡1-13። በእነዚህ ስፍራዎች የተገለጠው ልዩ ሁኔታ የሚያስረዳን፥ ሰይጣን እግዚአብሔር ዘንድ (ሉቃስ 22፡31፤ ራእይ 12፡10)፥ እንዲሁም ወደ ሰው (ኤፌ. 6፡10-12፤ 1ኛ ጴጥ. 5፡8) መቅረብ እንደሚችልና የማናቸውንም እውነተኛ አካል ባሕርይ የሚያሳይ መሆኑን ነው። 

(መ) ሉቃስ 4፡1-13። በዚህም ስፍራ እንደተገለጠው ሰይጣን የመጨረሻው አዳም የሆነውን የእግዚአብሔር ልጅ በምድረ በዳ በፈተነው ጊዜ ማንነቱ ተገልጧል። በልዑል እመሰላለሁ ብሎ ያሰበው (ኢሳ. 14፡14)፥ ይህን አሳቡንም ለመጀመሪያው ሰውና ለመጀመሪያይቱ ሴት ያስተላለፈው (ዘፍጥ. 3፡5)። አሁን ደግሞ ክርስቶስ ወድቆ ቢሰግድላት በምድር ያለ ሀብትና ንብረት እንደሚሰጠው ቃል ሲገባ ይታያል። ይህ ክርስቶስ አሻፈረኝ ያለው የሰይጣን ስጦታ የሆነ ሥልጣንና ኃይል ወደፊት በሚነሣው የጥፋት ልጅ ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቶ ይከናወናል (2ኛ ተሰ. 2፡8-10፤ 1ኛ ዮሐ. 4፡3)። 

(ሠ) ኤፌሶን 6፡10-12። በዚህ ስፍራ የተመለከቱትና ሰይጣን የእግዚአብሔርን ልጆች የሚዋጋቸው እንዲሁም የሚቃወምባቸው መንገዶች ማንነቱን በሚገባ ያስረዳሉ። መጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ በየትኛውም ስፍራ ሰይጣን የራሱ የሆኑትን፥ ማለት ያልዳኑና ዳግም በመንፈስ በመወለድ የእግዚአብሔር ልጆች ያልሆኑትን እንደሚዋጋቸውና እንደሚቃወማቸው ተጽፎ አናገኝም። እንዲያ ያሉ ሰዎች የራሱ ስለሆኑ በሥልጣኑ ሥር ናቸው (ዮሐ. 8፡44፤ ኤፌ. 2፡2፤ 1ኛ ዮሐ. 5፡19)። 

ለ. የሰይጣን ኃይል 

ሰይጣን የወደቀና በክርስቶስ የመስቀል ሥራ ላይ የተፈረደበት ቢሆንም (ዮሐ. 12፡31፤ 16፡11፤ ቈላ. 2፡15)፥ በዓለም ያለው ሥፍራ አልተወሰደበትም፥ ከኃይሉ ያጣውም ጥቂቱን ብቻ ነው። አካላዊና ሥልጣናዊ ብርታቱ በሁለት መንገዶች ይገለጣል። 

1. ጥንካሬው ፈገመት አይቻልም። ሰይጣን ራሱ እንደገለጠው እና ክርስቶስም እንዳልካደው፥ በዚህ ዓለም ማለት ተሰጥተውኛል በሚላቸው መንግሥታት ላይ ሙሉ ሥልጣን አለው። ይህን ሥልጣን ለሚፈቅደው ሊሰጥ ይችላል (ሉቃስ 4፡6)። በሞት ላይ ሥልጣን የነበረው መሆኑ ተነግሮለታል (ዕብ. 2፡14)። ይሁን እንጂ ይህ ሥልጣኑ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተሽሮአል (ራእይ 1፡18)። ሰይጣን ኢዮብን በተመለከተ በሕመም ላይ ሥልጣን ነበረው (ኢዮብ 2፡7)፤ ሐዋርያው ጴጥሮስን እንደ ስንዴ ሊያበጥረው ይችል ነበር (ሉቃስ 22፡31፤ 1ኛ ቆሮ. 5፡5)። በተመሳሳይ ሁኔታ ሰይጣን “ምድርን ያንቀጠቀጠ፥ መንግሥታትን ያናወጠ፥ ዓለሙን ባድማ ያደረገ፥ ከተሞችን ያፈራረሰ፥ ምርኮኞቹንም ወደቤታቸው ያልሰደደ” (ኢሳ. 14፡12-17) መሆኑ ተገልጧል። በሰይጣን ሥልጣን ላይ የመላእክት አለቃ ሚካኤል እንኳ የስድብ ቃል ሊናገር አልደፈረም (ይሁዳ 9)። ይህ ሁሉ ቢሆንም የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና በክርስቶስ ደም አማካይነት በሰይጣን ሳይ ድል አለው (ኤፌ. 6፡10-12፤ 1ኛ ዮሐ. 4: 4፤ ራእይ 12፡11)። ሰይጣን ኃይሉንና ሥልጣኑን ለመጠቀም የሚችለው፥ ከእግዚአብሔር በተፈቀደለት መጠን ብቻ ነው። 

2. ሰይጣን በአጋንንት ይታገዛል። የሰይጣን ኃይል የሚበረታው ፈቃዱን በሚፈጽሙና በሚያገለግሉት አጋንንት አማካይነት ነው። እንደ እግዚአብሔር በሁሉም ቦታ የሚገኝ፥ ሁሉን የሚችል ወይም ሁሉንም የሚያውቅ ባይሆንም፥ በሚያገለግሉት ርኩሳን መናፍስት አማካይነት መላውን ዓለም ያዳርሳል። 

ሰይጣን ዓለምን ለመቆጣጠር በሚያደርገው ማናቸውም እንቅስቃሴ አጋንንት እጅግ ጠቃሚ ሚና ይጫወታሉ (ማር. 5፡9)። በሰዎችና በእንስሳት ውስጥ የማደርና እነርሱንም የመቆጣጠር ችሎታ እሳቸው (ማር. 5፡2-5፤ 11-13)። አካል ባለው ነገር ሁሉ ውስጥ የማደር ፍላጎት አላቸው (ማቴ. 12፡43-44፤ ማር. 5፡10-12)። 

እንዳንዴ በሰዎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። በሌላ ሁኔታ ደግሞ በሰዎች በማደር አካላቸውንና ንግግራቸውን ይቆጣጠራሉ (ማቴ. 4፡24፤ 8፡16፥ 28፥ 33፤ 9፡32፤ 12፡22፤ ማር. 1፡32፤ 5 ፡15-16፥ 18፤ ሉቃስ 8፡36፤ ሐዋ. 8፡7፤ 16፡16)። አጋንንት እንደ ሰይጣን ሁሉ ርኩሳንና ተንኮለኞች ናቸው። በመሆኑም የያዟቸውን ሰዎች ይጎዷቸዋል (ማቴ. 8፡28፤ 10፡1፤ ማር. 1፡23፤ 5፡3-5፤ 9፡17-26፤ ሉቃስ 6፡18፤ 9፡39-42)። ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር መሆኑን እንደሚያውቁ በብዙ ሁኔታዎች ያረጋግጣሉ (ማቴ. 8፡28-32፤ ማር. 1፡23-24፤ ሐዋ. 19፡15፤ ያዕ. 2፡19)። 

እንደ ሰይጣን ሁሉ አጋንንትም ለዘላለም ቅጣት የተወሰኑ መሆናቸውን ያውቃሉ (ማቴ. 8፡29፤ ሉቃስ 8፡31)። አጋንንት የአካላት መናወጥ (ማቴ. 12፡22፤ 17፡15-18፤ ሉቃስ 13፡16) እና የአእምሮ መታወክን ሊያስከትሉ ይችላሉ (ማር. 5፡2-13)። የአእምሮ መታወክ በአካላዊ ችግሮች ሊከሰት ቢችልም፥ አንዳንድ የአእምሮ መታወክ ዓይነቶች ያለ ጥርጥር ከአጋንንት ናቸው። የአጋንንት ተጽዕኖ ወደተሳሳተ ሃይማኖት፥ ከሰው ተለይቶ ወደመኖርና ወደአለማመን ሊመራ ይችላል (1ኛ ጢሞ. 4፡1-3)። 

እጋንንት በክርስቲያን ላይ የሚያደርጉት ተጽዕኖ ግልጥ ነው (ኤፌ. 6፡12፤ 1ኛ ጢሞ. 4፡1-3)። የሥልጣናቸው ተጽዕኖ መጠንም ዳግም በተወለዱትና ባልዳኑት ነፍሳት ላይ ተመሳሳይ አይደለም። ምክንያቱም ክርስቲያን ከዳነበት (ዳግም ከተወለደበት ጀምሮ የሚያድርበት የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ አለ። እጋንንት ያልዳኑትን ሊይዙና ሊያድሩባቸው ሲችሉ፥ በዳኑት ላይ ግን ተጽእኖ ብቻ ሊያደርጉ ነው የችሉት። በዳኑት ላይ የሚያሳድሩት የተጽዕኖ ጊዜም ውስን ነው። ቁጥራቸው እጅግ የበዛ እነዚህ አጋንንት፥ የሰይጣንን ፈቃድ ባያከናውኑ፥ ትእዛዙንም ባያፈጽሙለት ኖሮ ሥራው ባልተከናወነለት ነበር። አጋንንት ስለሚያግዙት የማያቋርጥና በዓይን የማይታይ ጦርነት ከቅዱሳን መላእክት ጋር ሁሌ ያካሂዳል።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

24
ትምህርት 24 ከ52

ሰይጣን፡- ሥራውና የመጨረሻው ዕጣው

ሀ. ሰይጣንን በሚመለከት የሚቀርቡ ስሕተተኛ ፅንሰ-አሳቦች 

የሰይጣንን ማንነት በሚመለከት በአሁኑ ጊዜ ሁለት ታላላቅ ስሕተቶች አሉ። የስሕተቶቹ ተጠቃሚ ራሱ ሰይጣን መሆኑን መረዳቱ ተገቢ ነው። 

1. ብዙዎች ዕይጣን የለም፥ ሰይጣን የሚባለው በሰዎችና ስዓለማችን ያለው ክፉ አሠራር ወይም ተጽዕኖ ነው ብለው ያምናሉ። ይህ አስተሳሰብ ስሕተት ነው። ምክንያቱም የክርስቶስን መኖር የሚያረጋግጡ አያሌ ማስረጃዎች የመኖራቸውን ያህል፥ የሰይጣንንም መኖር የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች አሉ። ይህን ጉዳይ አስተማማኝ በሆነ መንገድ የመግለጥና የማረጋገጥ ሥልጣን ያለው መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። በመሆኑም ስለ ክርስቶስ መኖር መጽሐፍ ቅዱስ የሚያቀርበው ምስክርነት ከታመነ፥ ስለ ሰይጣን ሕልውና የሚገልጠውም መታመን አለበት። 

2. ሰይጣን የማንኛውም ሰው ኃጢአት መነሻ ነው የሚለውን ስሕተት የሚያምኑም አሉ። ይህ ግንዛቤ እውነት አይደለም ምክንያቱም፡- (ሀ) ሰይጣን ኃጢአትን በዓለም የማስፋፋት ዕቅድ የለውም። የርሱ ዓላማ “በልዑል እመሰላለሁ” (ኢሳ. 14፡14) ማለት ነበር። በዓለም ብዙ ጥፋት ለማድረስ አይፈልግም፤ ምክንያቱም ዓላማው በዓለም ላይ ሠልጥኖ መኖር ስለሆነ፥ ከዚህ ዓላማው አኳያ የዓለምን ሥርዓት ከነባሕሉ፥ ሃይማኖትና እውቀቱ ጋር ማቀናጀትና መያዝ ነው (2ኛ ቆሮ. 11፡13-15)። ስለዚህ ሰይጣን የኃጢእት ቀጥተኛ ምክንያት ነው የሚለው እምነት ስሕተት ነው። (ላ) የሰው ኃጢአት በቀጥታ የሚመጣው በኃጢአት ከወደቀው የሰው ልብ ነው (ዘፍጥ. 6፡5፤ ማር. 7፡18-23፤ ያዕ. 1፡13-16)። 

ለ. የሰይጣን ሥራ 

ስለ ሰይጣን ሥራ የሚያስተምሩን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ብዙ ሲሆኑ፥ ኢሳይያስ 14፡12-17 ውስጥ የተጠቀሰው አንዱ ነው። ይህ ክፍል የሰይጣንን ቀዳሚና ዋና ዓላማ ይገልጣል። ሰይጣን ወደ ሰማያት ከፍ የማለት፥ ዙፋኑን ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ የማድረግ፥ በልዑልም የመመሰል ዕቅድ ነበረው። ይህን ዓላማውን ለማሳካት ከመጠን በላይ የሆነ ሥልጣንና ጥበቡን ይጠቀማል። መንግሥታትን ያዳክማል፤ ምድርን ያንቀጠቅጣል፤ ዓለምን ምድረ በዳ ያደርጋል፤ ከተሞችን ያፈርሳል፤ ምርኮኞቹንም አይለቅም። የዚህ ክፍል እያንዳንዱ ሐረግ እስደንጋጭ ቢሆንም፥ በተለይ ሁለት ነጥቦችን በዋናነት መጥቀስና እነርሱንም መረዳት ይገባናል። 

1. ብልዑልም እመሰላለሁ” የሚለው አነጋገር(ቁ. 14)፥ ከውድቀቱ በኋላ ለሚያከናውናቸው ነገሮች በዋና ዓላማነት የሚቆም መህኑን ያመለክታል። ዘፍጥረት 3፡5 ውስጥ ለአዳምና ለሔዋን በቁም ነገር ያቀረበሳቸው ይህን ዓላማውን ነበር። እነርሱም የሰይጣንን ዓላማ በመቀበል ራስ ወዳዶች፥ በራሳቸው የሚታመኑና የእግዚአብሔር እርዳታ የማያሻቸው ሰዎች ሆኑ። ዓላማው ተዋሐዳቸውና ትውልዳቸው “የቁጣ ልጆች” (ኤፈ. 2፡3፤ 5፡6፤ ሮሜ 1፡18) እስኪባል ድረስ ለልጅ ልጆቻቸው ተላለፈ። በመሆኑም የአዳም ልጆች (የሰው ዘር ሁሉ) ዳግም ሊወለዱ (ዮሐ. 3:3)፥ እና ከዳኑ በኋላም ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ፈቃድ ለማስገዛት ሊጥሩ ይገባል። በልዑል እመሰላለሁ” የሚለው የሰይጣን ዓላማ ክርስቶስ እንዲሰግድለት ባሳየው ፍላጎትም ታይቷል (ሉቃስ 4:5-7)። የዓመፅ ሰው ወደተቀደሰው ስፍራ ገብቶ እንደ እግዚአብሔር ሲሰገድለት (2ኛ ተሰ. 2፡3-4፤ ዳን. 9፡27፤ ማቴ. 24 ፡15፤ ራዕይ 13፡4-8)፥ የሰይጣን ዋና ዓላማ ለአጭር ጊዜ ይከናወንለታል። እንዲያ የሚሆነው ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። 

2. ምርኮኞችን ልሰደዳቸውም” (ኢሳ. 14፡17) የሚለው ለሳ፥ ሰይጣን በአሁኑ ጊዜ ባልዳኑ ሰዎች ላይ ያለውን ኃይልና፥ ከሚጠብቃቸው ዘላለማዊ ፍርድ ሊያድናቸው አለመቻሉን የሚያመለክት ይመስላል። ይህ ጥቅስ የተወሰደበት የትንቢት ክፍል ሁሉ ሰይጣን ወደ መጨረሻ ፍርዱ በደረሰ ጊዜ የሚከናወኑ ነገሮችን ያመለከታል። ብዙው ክንውን ወደፊት የሚሆን መሆኑ አያጠራጥርም። ይሁን እንጂ ያልዳኑ ሰዎች ከጭለማ ኃይል ነጻ እንዳይወጡና ወደ እግዚአብሔር ውድ ልጅ መንግሥት (ቈላ. 1፡13) እንዳይገቡ ሰይጣን ባለ ኃይሉ እንደሚሠራ እናውቃለን። በማይታዘዙ ልጆች የሚሠራው ሰይጣን ነው (ኤፌ. 2፡2)፤ የወንጌል ብርሃን እንዳይበራላቸው ያልዳኑ ሰዎችን አእምሮ ያሳውራል (2ኛ ቆሮ. 4፡3-4)፤ ማስተዋል የጎደለውን ዓለምም ይዟል (1ኛ ዮሐ. 5፡19)። 

ሰይጣን በሚያደርገው ውጊያ የእግዚአብሔርን ነገር በራሱ መንገድ በማስመሰል ያቀርባል። ይህ “በልዑል እመሰላለሁ ሰሚለው ዓላማው መሠረት የሚያደርገው ነው። የተለያዩ የሐሰት ሃይማኖቶችን ያስፋፋል (1ኛ ጢሞ. 4፡1-3፤ 2ኛ ቆሮ. 11፡13-15)። ይህን ሰሚያደርግበት ጊዜ፥ በተመረጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ላይ የተመሠረቱና ክርስቶስን እንደመሪ የሚመለከቱ፥ እንዲሁም ማንኛውንም የክርስትና ደረጃ የሚጠብቁ የሚመስሉ ሃይማኖቶችን ሊፈጥር እንደሚችል መረዳት ያስፈልጋል። እነዚህ ሃይማኖቶች ግን ድነት፥ በፈሰሰው የክርስቶስ ደም በጸጋ ብቻ የሚገኝ መሆኑን የሚገልጡ አይደሉም። እንዲህ ያሉ የሰይጣን ማሳሳቻዎች በዓለም ተስፋፍተዋል፥ አያሌ ሰዎችንም በማሳሳት ላይ ናቸው። እንዲህ ያሉ ትምህርቶች የሚመዘኑት፥ በክርስቶስ ደም የማዳን ኃይል አማካይነት ስለሚገኘው የእግዚአብሔር ማዳን በሚኖራቸው አመለካከት ነው (ራእይ 12፡11)። 

በመሠረቱ የሰይጣን ጠላትነት በእግዚአብሔር ላይ ብቻ ነው። ካልዳኑት ሰዎች ጋርማ ምንም ጠላትነት የለውም። በእግዚአብሔር ልጆች ላይ የእሳት ፍላጻውን የሚወረውረውና የሚዋጋቸው፥ መለኮታዊ ባሕርይ ስለአደረባቸው፥ በእግዚአብሔር ስለሚታመኑ እና የጸጋ ስጦታን (በኢየሱስ በማመን የሚገኘውን የዘላለም ሕይወት) ተቀብለው የጌታ ልጆች በመሆናቸው ነው። 

በዚህ መሠረት ሰይጣን ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር የሚያደርገው ይህ ጦርነት “በደምና በሥጋ” የሚካሄድ ሳይሆን፥ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ባላቸው ሰማያዊ ኅብረት ላይ የሚያተኩር መንፈሳዊ ነው። ይህ ማለት አማኝ እንደማያምን ሰው በሥጋ ምኞት ተጠላልፎ አይወድቅ ይሆናል፥ ነገር ግን በጸሎት ሕይወቱ፥ በምስክርነትና በአጠቃላይ መንፈሳዊ ሕይወቱ የሚደክምበት ሁኔታ ይኖራል። ይህ የአማኝ ድካም በእግዚአብሔር ፊት እንደ ማንኛውም የዓለም ኃጢአት ውጤት መሸነፍና ውርደት የሚቆጠር ስለሆነ በቀላሉ የሚታይ አለመሆኑን መረዳት ይገባል። 

ሐ. የሰይጣን ፍጻሜ 

የእግዚአብሔር ቃል ስለ ሰይጣን አፈጣጠር ግልጥ እንደመሆኑ ሁሉ፥ ስላ ተግባሩና ፍጻሜውም ግልጥ ነው። በዚሁ መሠረት ሰይጣን ቀጥሎ የተመለከቱት አምስት ተከታታይ ፍርዶች ይጠብቁታል። 

1. መቼ መሆን በትክክል ባይገለጥም፥ ሰይጣን በትዕቢቱ ከእግዚአብሔር የተለየ መሆኑ በግልጥ ተጠቅሷል (ሕዝ. 28፡15፤ 1ኛ ጢሞ. 3፡6)። ቢሆንም በሰማያት ያለው ሥፍራና ብዙው ኃይሉ አልተወሰደበትም። ወደ እግዚአብሔር የመቅረቢያ መንገዱም እልተዘጋበትም። 

2. በክርስቶስ የመስቀል ላይ ሥራአማካይነት ሰይጣን ተገቢው ፍርድ የተበየነበት ቢሆንም (ዮሐ. 12፡31፤ 16፡11፤ ቈላ. 2፡14-15)፥ ፍርዱ ተግባራዊ የሚሆንው ገና ወደፊት ነው። ፍርዱና አፈጻጸሙ በኤደን የአትክልት ሥፍራ ነው የተተነበየው (ዘፍጥ. 3፡15)። 

3. ሰይጣን ከሰማይ ይጣላል። በሚመጣው የፍዳ ዘመን ወቅት በሰማይ በሚነሣው ጦርነት ምክንያት ሰይጣን ከሰማይ ተጥሎ በምድር ብቻ ተወስኖ እንዲኖር ይደረጋል። ያኔ፥ ገና ጥቂት ጊዜ እንደቀረው በመረዳት በታላቅ ቁጣ ይሠራል (ራእይ 12፡7-12፤ ኢሳ. 14፡12፤ ሉቃስ 10፡18)። 

4. ሰይጣን ወደ ጥልቁ ይጣላል። በሺህ ዓመቱ የክርስቶስ መንግሥት ጊዜ ሰይጣን በጥልቁ ይታሠራል። ከእስራቱ ግን “ለጥቂት ጊዜ” ይፈታል (ራእይ 20፡1-3፥ 7)። ታስሮ ወደ ጥልቁ የሚጣልበት ዋና ዓላማ፥ በምድር ላይ በነጻነት እየተመላለሰ መንግሥታትን እንዳያስት ለማገድ ነው። 

5. ሰይጣን የመጨረሻ ፍርድ የሚሰጠው፥ በሺህ ዓመቱ መንግሥት ማብቂያ ላይ ነው። ተፈትቶ በነበረበት “ጥቂት ጊዜ” በእግዚአብሔር ላይ የተቻለውን አመፅ ሁሉ ከአካሄደ በኋላ፥ ተይዞ ሌትና ቀን ለዘላለም ይሰቃይ ዘንድ እሣት ባሕር ውስጥ ይጣሳል (ራእይ 20፡10)።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

25
ትምህርት 25 ከ52

ሰው፡- አፈጣጠሩ

ሀ. የሰው ፍጡርነት 

ሰው በዚህ አስደናቂ በሆነ ፍጥረተ ዓለም መካከል በመሆን፥ የዚሁ ፍጥረተ ዓለም ቁንጮ ሆኖ ሲኖር፥ የራሱንና የሌሎቹን ፍጥረታት አጀማመር ለመረዳት ጥረት ያደርጋል። ተፈጥሮ የሰውን አፈጣጠር ስለማይገልጥና በቃል እየተወራረደ የመጣ ትምህርትም የሚያስተማምን መረዳት ስለማያስገኝ፥ እግዚአብሔር ራሱ ስለ ሰው አፈጣጠር በመጽሐፍ ቅዱስ አማካይነት የገለጠውን መመልከቱ አስተማማኝ ማረጋገጫ ይሆናል። በዘፍጥረት መጽሐፍ የመጀመሪያ ምዕራፎች በሌሎችም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የሰው አፈጣጠር በማያሻማ አኳኋን ተገልጧል። 

የሰውን አመጣጥ ማወቅ ለሰው ዘር ሁሉ ሰብእዊ ጥያቄና መላምታዊ ጉዳይ ከመሆኑ የተነሣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ለጥያቄው መልስ ለመሻት የሞከሩ ሁሉ፥ የሰውን አፈጣጠር ለመግለጥ ብዙ ጥረዋል። እነዚህ እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ሰብአዊ የሙከራ ውጤቶች የሚያመለክቱት፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ከተገለጠው ውጭ ሰው ስለ ራሱ አፈጣጠር የሚያገኘው ማረጋገጫ የሌላ መሆኑን ነው። ትክክለኛውና የማያወላውለው ማረጋገጫ የሚገኘው ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። 

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሰው አፈጣጠር ትክክለኛና ብቸኛ ምስክር መሆኑን ከሚጻረሩ አመለካከቶች አንዱ፥ የአዝጋሚ ለውጥ ወይም ኢቮሉሽን (evolution) ፅንሰ-አሳብ ነው። በዚህ ንድፈ-አሳብ መሠረት የመጀመሪያው ሕያው ሕዋስ በአንድ ሁኔታ መጣና በተፈጥሮ ምርጫ ሂደት ከዚያ ሕዋስ ሰው ተገኘ። ይህ ፅንሰ-አሳብ በዓለም ያለውን የሕይወት ውስብስብ አፈጣጠር በዚህ የተፈጥሮ ሂደት መሠረትነት ለመግለጥ ይሞክራል። 

በዚህ ንድፈ-አሳብ መሠረት ዕፅዋት፥ እንስሳትና ሰው ራሱ የተገኙት በድንገተኛ ተፈጥሯዊ ለውጥ ነው። ገላጣው ሌሎች ዝርያዎችንም ይመለከታል። ይሁን እንጂ፥ ድንገተኛ ለውጦች ከጥቅም ይልቅ ጉዳት አላቸው። ድንገተኛ ለውጥ ሲጠቅም፥ ወይም አዲስ ዝርያ ሲያመጣ አልታየም። በሕያዋን ፍጥረታት ዝርያዎች መካከል ልዩነት መኖሩን መጽሐፍ ቅዱስ ሲመዘግብ፥ እግዚአብሔር እንስሳትን “እንደየወገናቸው” የፈጠራቸው መሆኑንም አረጋግጧል (ዘፍጥ. 1፡21፥ 24-25)። 

ከእንስሳት ጋር ሲነጻጸር ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሔር አምሳል ነው (ዘፍጥ. 1፡26-27)። ንድፈ-አሳብና ቅሪተ-አካላት (fossis) ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ያሉትን ሕልው ነገሮች ለመግለጥ እንደማይችሉ የአዝጋሚ ለውጥ ንድፈ-አሳብ አራማጆች ይረዳሉ። የአዝጋሚ ለውጥ ንድፈ-አሳብ ከመጽሐፍ ቅዱስ በተቃራኒነት ሰው ሊረዳው የሚቻለው ብቸኛ ገለጣ ከመሆኑም በላይ፥ ስለ ሰው አመጣጥ አሳሳዊ ባልሆነና በተፈጥሯዊነት ፅንሰ-ሃሳብ ላይ ተመሥርቶ የቀረበ ነው ይላሉ። 

በተመሳሳይ ሁኔታ፥ “መለኮታዊ አዝጋሚ ለውጥን” (theistic evolution) የተሰኘው፥ እግዚአብሔር አዝጋሚ ለውጥን ተጠቅሞበታል የሚለው ንድፈ-አሳብ፥ አስተምህሮውን የሚመሠርተው መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፍጥረት የሚገልጠውን ቀጥተኛ ትርጉም በመካድ ላይ ነው። 

የሰው አፈጣጠር መሠረታዊ ትምህርት በቅዱሳት መጻሕፍት በግልጥ ተመልክቷል (ዘፍጥ. 1፡1-2፡25፤ ዮሐ. 1፡3፤ ቆላ. 1፡16፤ ዕብ. 11፡3)። እግዚአብሔር የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ መሆኑ በዘፍጥረት መጽሐፍ መጀመሪያ ምዕራፍ ብቻ አሥራ ሰባት ጊዜ ሲገልጥ፥ በሌሎቹ ክፍሎች ደግሞ ከአምሳ ጊዜ በላይ ተጠቅሷል። አንዳንዶቹ ተፈጥሮን በቀጥታ የሚያስተምሩ ሲሆኑ፥ ሌሎቹ ደግሞ እግዚአብሔር የአዳምና የሔዋን ፈጣሪ መሆኑን ያመለክታሉ (ዘፀ . 20፡11፤ መዝ. 8፡3-6፤ ማቴ. 19፡4-5፤ ማር. 10፡6-7፤ ሉቃስ 3፡38፤ ሮሜ 5፡12-21፤ 1ኛ ቆሮ. 11፡9፤ 15፡22፥ 45፤ 1ኛ ጢሞ. 2፡13-14)። የፍጥረት መሠረታዊ ፅንሰ-አሳብ፥ ከዘፍጥረት 1፡1 በፊት ስለነበረው ሁኔታ ሳይጠቀስ፥ እግዚአብሔር ዓለምን ከምንም ፈጠረ ይላል። 

የዘፍጥረት መጽሐፍ በግልጥ እንደሚያስረዳው፥ ሰው የእግዚአብሔር ፍጡራን ሁሉ መደምደሚያ ሲሆን፥ እግዚአብሔር የመፍጠር ሥራውን ያጠናቀቀውም በስድስት ቀናት ነው። መጽሐፍ ቅዱስን በእግዚአብሔር ቃልነት በሚቀበሉ ሰዎች ስለ ፍጥረት ቀናት የተለያዩ አመለካከቶች ተሠንዝረዋል። መጽሐፍ ቅዱስ እስትንፋሰ-እግዚአብሔር መሆኑን ከሚያምኑ ሰዎች አንዳንዶች ደግሞ ዘፍጥረት 1 ላይ ያለው ገለጣ፥ ቀደም ሲል ከሰይጣንና ከወደቁት መላእክቱ ጋር በተያያዘ ሁኔታ የጠፋው ዓለም እንደገና መፈጠር ታሪክ ነው ይላሉ። በዘፍጥረት መጽሐፍ ምዕራፍ 1-2 ከተገለጠው የስድስት ቀን የፍጥረት ሥራ በፊት ሕይወት አልባ የሆነ ዓለም ነበር ለሚለው አመለካከት ይህ እንደማስረጃ የሚቀርብ ነው። 

አንዳንዶች የስድስቱ ቀናት የፍጥረት ጊዜ ዕለታዊ ስሌት፥ ከሀያ አራት ሰዓት ሊበልጥ ወይም ሊያንስ ይችላል። ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ቀን” የሚለው ፅንሰ-አሳብ አንዳንዴ ረዘም ያለ ጊዜን፥ ለምሳሌ “የጌታ ቀን” የሚለውን ዓይነት ያመለክታል ይላሉ። ሌሎቹ ደግሞ በአንደኛው ቀን በሁለተኛው ቀን በሦስተኛው ቀን … በማለት፥ “ቀን” ከሚለው ቃል ጋር የተወሰነ ጊዜን ለማመልከት ቁጥር ስለተጨመረበት፥ 

“ቀን” ማለት ሀያ አራት ሰዓት ነው በማለት አጥብቀው ይከራከራሉ። ስለዚህ በዚህ አመለካከት እግዚአብሔር ሰውንና እንስሳትን ሲፈጥራቸው፥ የተወሰነ ዘመን ያህል የኖሩ በሚመስል መልክ እንደፈጠረ ዓለምንም በዚሁ ሁኔታ የፈጠረ መሆኑ ታምኖበታል። 

ሌሎች ደግሞ የፍጥረት ጊዜ በዘፍጥረት 1፡11 ላይ ከተጠቀሰው ቃል፥ ማለት ፍሬ የሚሰጠው ዛፍ በምድር በቅሎ ከማደጉ አኳያ ሲታይ፥ ከሀያ አራት ሰዓት በላይ ወስዷል ይሳሉ። እግዚአብሔር ያደገ ዛፍ መፍጠር የማይሳነው መሆኑ ቢታወቅም፥ በቀለ የሚለው ቃል የሚያመለክተው፥ የፍጥረቱ ጊዜ ከሀያ አራት ሰዓት በላይ የወሰደ መሆኑን ነው። 

የፍጥረትን ትክክለኛ ሂደት አስመልክቶ የወንጌል አማኞች እንኳ የተለያየ አመለካከት አላቸው። የመጽሐፍ ቅዱስን እስትንፋሰ-እግዚአብሔርነትና ስሕተት አልባነት የሚያምኑ የቃሉ ፈቺዎች ወይም ተርጓሚዎች፥ ሰውና እንስሳት ወዲያውኑ አሁን ባሉበት ሁኔታ እግዚአብሔር የፈጠራቸው መሆኑን ያረጋግጣሉ። ፍጡራን በተፈጥሮና በአዝጋሚ ሕግ መለወጣቸውን የሚገልጥ ምንም ማስረጃ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። 

ለ. የሰው አፈጣጠር 

ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚመሰክሩት፥ ሰው በአሁኑ ሰብአዊ ቅርፁ የፍጥረታት ሁሉ መደምደሚያና ማሳረጊያ ሆኖ በእግዚአብሔር ተፈጥሯል። አፈጣጠሩም በእግዚአብሔር መልክ፥ እንዲሁም ምሳሌ እንደሆነ (ዘፍጥ. 1፡26) እና እግዚአብሔር የሕይወት እስትንፋስ እፍ እንዳለበት (ዘፍጥ. 2፡7) ተገልጧል። እነዚህ መለያዎች ሰውን በምድር ካሉ ፍጥረታት ሁሉ በላይ ያደርጉታል፤ ሰው እእምሮ። ስሜትና ፈቃድ ያለው ፍጡር መሆኑንም ያመለክታሉ። 

በጠቅላሳው አነጋገር፥ የሰው አፈጣጠር ቁሳዊ የምድር አፈር” እና መንፈሳዊ “የሕይወት እስትንፋስ” ነው። ይህ ጥምር መለያ “ውጫዊ ሰው) እና “ውስጣዊ ሰው” (2ኛ ቆሮ. 4፡16) ወይም “ምድራዊ ሸክላ” እና “መዝገብ” (2ኛ ቆሮ. 4፡7) ተብሏል። የሰው ነፍስና መንፈስ ለዘላለም የሚኖሩ መሆናቸው ሲገለጥ፥ ሥጋ ቀድሞ ወደመጣበት አፈር ይመለሳል (መክ. 12፡7)። በመሆኑም ሰው ሥጋን እንጂ ነፍስን መግደል አይቻለውም (ማቴ. 10፡28)። 

መጽሐፍ ቅዱስ ሥጋዊ ስላልሆነው የሰው አካል ሲገልጥ የተለያዩ ቃላትን በማቀያየር ይጠቀማል (ዘፍጥረት 41፡8ን ከመዝሙር 42፡6 ጋር፥ ማቴዎስ 20፡28ን ከ27፡50 ጋር፥ ዮሐንስ 12፡27ን ከ13፡21 ጋር፥ እንዲሁም ዕብራይስጥ 12፡23ን ከራእይ 6፡9 ጋር ያነጻጽሩ)። እግዚአብሔርን ለማመልከቻም እነዚህን ቃላት ይጠቀምባቸዋል (ኢሳ. 42 ፡1፤ ኤር. 9፡9፤ ዕብ. 10፡38)። ለእንስሳት እንዲሁ (መክ. 3፡21፤ ራእይ 16፡3)። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የሰውን ነፍስና መንፈስ ለይቶ ያስቀምጣል (1ኛ ተሰ. 5፡23፤ ዕብ. 4፡12)። 

ቁስ ያልሆነው ሰብአዊ አካል ከፍተኛ ተግባር አንዳንዴ የመንፈስ፥ ሌላ ጊዜ ደግሞ የነፍስ እንደሆነ ተደርጎ ቢገለጥም (ማር. 8፡36-37፤ 12፡30፤ ሉቃስ 1፡46፤ ዕብ. 6፡18-19፤ ያዕ. 1፡21)። መንፈስ ብዙ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰው፥ ስለ እግዚአብሔር የሚያሰላስል የሰው እንድ ክፍል ሆኖ ነው። ነፍስ ደግሞ ከሰው አእምሮ፥ ከስሜትና ፈቃድ ጋር የተዛመደ ነው። 

የሰውን ቁሳዊ ያልሆነ ተፈጥሮ ለመግለጥ ሌሎች ቃላት ማለት ልብ (ዘዳ. 7፡23፤ መዝ. 37፡4፤ ሮሜ 9፡2፤ 10፡9-10፤ ኤፌ. 3፡17፤ ዕብ. 4፡7) እንደሚለው ያሉት አገልግለዋል። ሌላው ቃል ስለ ሰው አእምሮ የተጠቀሰው ሲሆን፥ የነፍስ ድነት ስላላገኘ ሰው (ሮሜ 1፡28፤ 2ኛ ቆሮ. 4፡4፤ ኤፌ. 4፡17-18፣ ቲቶ 1፡15) ወይም የታደሰውን የክርስቲያን አእምሮ (ማቴ. 22፡37፤ ሮሜ 12፡2፤ 1ኛ ቆሮ. 14፡15፤ ኤፌ. 5፡17) የሚመለከት ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ “ሕሊና” እና “ፈቃድ” የሚሉት ቃላት የሰውን ኢቁሳዊ ክፍል ለማመልከት አገልግለዋል። 

አንዳንድ ጊዜ በተመሳሳይነት፥ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እርስ በርሳቸው በመነጻጸር የሚገለጡ ልዩ ልዩ ቃላት ከመኖራቸው የተነሣ፥ ብዙ ሰዎች የሰውን በቁስነትና ኢቁስነት መከፈል እንደ መሠረታዊ ክፍፍል ወስደውታል። ነገር ግን “ነፍስ” እና “መንፈስ” የሚሉት ቃላት እንኳን አንዳንድ ጊዜ አካሉን ጨምሮ የሰውን ጠቅላላ እሱነት መግለጫነት አገልግለዋል። 

አንዳንድ አረማዊ ሃይማኖቶች ቁሳዊ ያልሆነው የሰው ክፍል ወይም ነፍስ ከአካሉ መፈጠር በፊት ለዘላለም የነበረና፥ ሰው መኖር ሲጀምር ሥጋ የለበሰ መሆኑን ያምናሉ። ይህ እምነት በመጽሐፍ ቅዱስ የተነገረ አይደለም። በአንዳንድ ወንጌሳውያን የሥነ-መለኮት ሰዎች የቀረበው ሌላ አመለካከት፥ እያንዳንዱ ሰው ሕልውናውን በጀመረበት ወቅት ነፍስ ትፈጠርለታለች የሚል ነው። የሰውን ኃጢአተኛነት በሚመለከት ይህ አመለካከት ችግር አለበት። ከሁሉ የተሻለው አመለካከት ምናልባት የመራባት ጽንሰ አሳብ አራማጆች የሚያቀነቅኑት የኃጢአት ውርስ (traducian theory) የተሰኘው ነው። በዚህ አመለካከት መሠረት ነፍስና መንፈስ በተፈጥሮ ትውልዳዊ ሥርዓት ይገኛሉ። በዚህም መሠረት ሰው ኃጢአተኞች ከሆኑ ወሳጆቹ ኃጢአተኛ ነፍስና መንፈስ ይወርሳል። 

ሰብዓዊ አካል ሰው እስኪሞት ድረስ የነፍስና የመንፈስ ማደሪያ ነው። ከሞት በኋላ የሚበሰብስ ቢሆንም፥ በትንሣኤ ጊዜ ይነሣል። ምንም እንኳን ትንሣኤዎቹ ቢለያዩ ይህ ክንውን ለዳኑትም ሆነ ላልዳኑት የማይቀር እውነት ነው። አንዳንድ ጊዜ አካል “ሥጋ” ተብሏል (ቆላ. 2፡1፥ 5)። የክርስቶስን አካል ለመጥሪያነትም አገልግሏል (1ኛ ጢሞ. 3፡16፤ 1ኛ ጴጥ. 3፡18)። በሌላ ጊዜ ደግሞ ኃጢአተኛ ነፍስንና መንፈስን የሚያጠቃልለውን ኃጢአተኛ ተፈጥሮ ይገልጣል። ይህም ሐዋርያው ጳውሎስ “ሥጋን ስቀሉ” (ገላ. 5፡24) በማለት ያመለከተው ነው። በዚህ መሠረት ሥጋ በሁሉም ምንባቦች ከአካል ጋር አንድ ሆኖ ሊወሰድ አይገባም። ምክንያቱም ቃሉ ድነት ያላገኘ ሰውንም ያመለክት ይሆናል። 

የዳኑ ሰዎች አካል “ቤተ መቅደስ” (ዮሐ. 2:21፤ 1ኛ ቆሮ. 6፡19፥ ፊልጵ. 1፡20)፥ “የሸክላ ዕቃ” (2ኛ ቆሮ. 4፡7)፥ “የተዋረደ ሥጋ”፥ (ፊልጵ. 3፡21)፥ “ሊገደል የሚገባው” (ሮሜ 8፡13፤ ቆላ. 3፡5)፥ እና መጎሰም ያለባቸው ሥጋዎች (1ኛ ቆሮ. 9፡27) ተብሏል። ዳግም የተወለዱ አማኞች አካል ይለወጣል፥ ይቀደሳል፥ ይድናል፥ በኋላ ይጻድቃል። በመጨረሻም ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያኑ በሚመጣበት ጊዜ ለዘላለም ይከብራል (ሮሜ 8፡11፥ 17፥ 18፥ 23፤ 1ኛ ቆሮ. 6፡13-20፤ ፊልጵ. 3፡20-21)። ኢየሱስ ክርስቶስ ከመሞቱ በፊት ፍጹም ሰብአዊ አካል ነበረው። ከትንሣኤው በኋላ ደግሞ አማኞች በትንሣኤ ጊዜ የሚኖራቸው ዓይነት ሥጋና አጥንት የሆነ አካል ነበረው። (“አካል” የሚለው ቃል ክርስቶስ የሞተላትንና እካሉ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን በምሳሌ ለመግለጫነት አገልግሏል።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

26
ትምህርት 26 ከ52

ሰው፡- ውድቀቱ

ኃጢአት ወደ ዓለም እንዴት ገባ የሚለው ጥያቄ ማንኛውም የአስተሳሰብ ሥርዓት የሚያነሣው ሲሆንም፥ ለእነዚህና ለመሳሰሉት ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ያለው ግን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። ባለፉት ምዕራፎች ስለ መላእክት በተደረገው ጥናት እንደተመለከተው ሁሉ፥ ኃጢአት ወደ ዓለም የገባው፥ ሰው ከመፈጠሩ በፊትና በመጀመሪያ ቅዱሳን ሆነው በተፈጠሩ፥ በኋላ ግን ከሰይጣን ዓመፅ ጋር በተባበሩ መላእክት አማካይነት መሆኑን ለማስረዳት ተሞክሯል። የዘፍጥረት መጽሐፍ የመጀመሪያ ምዕራፎች አዳምና ሔዋን በኃጢአት መውደቃቸውን ያስረዳሉ። በእነዚህ ምዕራፎች ላይ ሰዎች የተለያዩ ትርጉሞችን ይሰጣሉ። ከእነዚህም መካከል የሰውን ዘር ኃጢአተኛ ድርጊት በቀጥታ የሚገልጥ ነው ብለው የሚረዱ ወይም እውነትነት የሌለው ተረት ነው በማለት የሚረዱ ይገኙባቸዋል። ትክክለኛው ትርጉም ግን፥ ድርጊቱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተገለጠው ተከናውኗል የሚል ነው። 

የሰውን በኃጢአት መውደቅ ከሦስት አቅጣጫ ለማየት ይቻላል፡- (1) አዳም ከውድቀት በፊት፥ (2) አዳም ከውድቀት በኋላ፥ (3) የአዳም ውድቀት በሰው ዘር ላይ ያስከተለው ውጤት። 

ሀ. አዳም ከውድቀት በፊት 

አዳም የመጀመሪያው ሰው ሲሆን፥ ሔዋን ደግሞ እግዚአብሔር ለአዳም ረዳቱ እንድትሆንለት የፈጠራት ሴት መሆኗን መጽሐፍ ቅዱስ ድንቅና ግልጥ በሆኑ ቃላት ያስገነዝባል። ሁለቱ በኅብረት የሰው ዘር ሁሉ መሠረት በመሆን ከመውደቃቸው በፊት ከኃጢአት ነጻ ሆነው ይኖሩ ነበር። የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመተላለፍ በበደሉ ጊዜ ግን፥ ኃጢአት ወደ ሰው ዘር ገባ። ይህ በመጽሐፍ ቅዱስ ገለጣ የሰው ዘር ውድቀት ተብሏል። 

አዳምና ሔዋን በኃጢአት ሳይወድቁ ለምን ያህል ጊዜ እንደቆዩ መጽሐፍ ቅዱስ ባይነግረንም፥ ከነበሩበት ቦታና ሁኔታ ጋር በመላመድ፥ ለእንስሳት ሁሉ ስም በማውጣት ሁም ከእግዚአብሔር ጋር በነበራቸው የአንድነት በረከት ውስጥ ለረጅም ጊዜ ኖረዋል። አዳምና ሔዋን ሲፈጠሩ እንደ ሌሎቹ የእግዚአብሔር ሥራዎች ሁሉ “መልካም” ነበሩ (ዘፍጥ. 1፡31)። ይህም ማለት ፈጣሪያቸውን ደስ የሚያሰኙ ነበሩ። መንፈሳዊ ሁኔታቸው ኃጢአት አያውቅም። ባሕርያቸው ግን ኃጢአት መሥራት ከማይቻለው እግዚአብሔር ባሕርይ ጋር ሲነጻጻር ከኃጢአት ነፃ ቢሆንም ኃጢአት ሊሠራ የሚችል ባሕርይ ነበር። 

ሰው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ በመሆኑ፥ መልካምና ክፉውን የመለየት ችሎታ፥ እንዲሁም ሙሉ ሰብዕና ነበረው። ኃጢአት ማድረግ ከማይቻለው እግዚአብሔር ጋር ሲነጻጻሩ፥ ሰውም ሆነ መላእክት ኃጢአትን ሊሠሩ የሚያስችላቸው ፈቃድ አላቸው። ባለፈው ክፍል ስለ መላእክት እንዳጠናነው፥ ሰይጣን ኃጢአት ሠርቷል (ኢሳ. 14 ፡12-14፤ ሕዝ. 28፡15)። በሰይጣን ተግባር የተሳተፉ መላእክት ደግሞ “መኖሪያቸውን የተዉ” (ይሁዳ 6) ተብለዋል። ሰይጣንና የወደቁ መላእክት የመጀመሪያዎቹ ኃጢአተኞች በመሆናቸው፥ ሰው የኃጢአት ምንጭ ወይም መነሻ አይደለም፤ ኃጢአተኛ የሆነው በሰይጣን ተጽዕኖ ሳቢያ ነው (ዘፍጥ. 3፡4-7)። 

አዳምና ሔዋን እንዴት ኃጢአት እንደሠሩ ዘፍጥረት 3፡1-6 ውስጥ ተገልጧል። በዚህ ስፍራ እንደተገለጠው ሰይጣን የመጣው ያኔ እጅግ ውብና ማራኪ በነበረው እሳብ ተመስሎ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስረዳው፥ እግዚአብሔር አዳምና ሔዋንን የከለከላቸው አንድ ነገር፥ መልካሙንና ክፉውን ከምታስታውቀው የሕይወት ዛፍ ፍሬ እንዳይበሉ ነበር። ዘፍጥረት 2፡17 ውስጥ እንደተጠቀሰው “እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ ነገር ግን መልካሙንና ክፉን ከምታስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህ” ብሎ አስጠነቀቃቸው። ይህ ቀላል ትእዛዝ የተሰጠው አዳም ወይም ሔዋን እግዚአብሔርን ይታዘዙት እንደሆን ለመፈተኛ ነበር። 

ሰይጣን ከሔዋን ጋር ስለ እግዚአብሔር ትእዛዝ ሲነጋገር፥ “በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዟልን?” (ዘፍጥ. 3፡1) በማለት የተከለከለውን ነገር አሳሰባት። የጥያቄው አዝማሚያ እግዚአብሔር አንድን መልካም ነገር እንደደበቃቸውና ክልከላውንም ጭካኔ በማስመሰል ነበር። ሔዋንም ለእባቡ ጥያቄ ስትመልስ “በገነት ካለው ከዛፍ ፍሬ እንበላለን፥ ነገር ግን ሰገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ፥ እግዚአብሔር አለ፥ እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ፥ አትንኩም” (ዘፍጥ. 3፡2-3) ብሏል አለች። 

ሔዋን በዚህ መልዕዋ ሰይጣን ውጥመድ ውስጥ ገባች። ከዚያን ወዲህ የሰው ዘር ሰሙሉ የእግዚአብሔርን መልካምነት የማቃለልና ጨካኝነቱን የማጋነን ዝንባሌ አደረበት። ሔዋን በንግግርዋ ጌታ የሰጠውን ታላቅ የማስጠንቀቂያ ትእዛዝ ለወጥ እንዳደረገች ሰይጣን ወዲያውኑ ተረዳና፥ “ሞትን አትሞቱም፥ ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ፥ እንደ እግዚአብሔርም መልካሙንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ” (ዘፍጥ. 3፡4-5) አላት። 

ሰይጣን ከሴቲቱ (ሔዋን) ጋር ባደረገው ውይይት ዋና አታላይነቱ ተገልጧል። እግዚአብሔር ትእዛዙን ከጣሱ ስለሚደርስባቸው ቅጣት የተናገረውን አቃሎ በመናገር፥ እግዚአብሔር ለአዳምና ሔዋን የሰጠውን ቃል ውሸት አስመስሎ አቀረበ። አዳምና ሔዋን የተከለከለውን ፍሬ በመብሳት ዓይኖቻቸው መከፈቱ፥ እንዲሁም መልካምና ክፉውን መለየታቸው እውነት ነው። መልካምና ክፉ የመለየቱን ኃይል የሚያገኙት መልካም የማድረግ ኃይል ሳይኖራቸው መሆኑን ግን ሰይጣን አልገለጠላቸውም። 

ዘፍጥረት 3፡6 ውስጥ የአዳምና የሔዋን ኃጢአት መውደቅ እንደሚከተለው ተመዝግቦ እናገኛለን፡- “ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፤ ለጥበብም መልካም እንደሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ”። ሔዋን ራሷ ወደ መረዳት ትድረስ ወይም ሰይጣን ያመልክታት መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ነገር የለም። 

ይህንኑ የሚመስሉትና 1ኛ ዮሐንስ 2፡16 ውስጥ በግልጥ የተጠቀሱት ሦስት የፈተና ሁኔታዎች እንደዚህ ተመልክተዋል። የፍሬው ለመብልነት መልካም መሆን የሚያመለክተው “የሥጋ ምኞትን”፥ የፍሬው ዓይን የሚስብ መሆን ደግሞ “የዓይን አምሮትን ሲያመለክቱ የፍሬው ጥበብን የመስጠት ኃይል ደግሞ “በሥጋ መመካትን” ይገልጣል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰተፈተነ ጊዜ፤ ሰይጣን ያቀረበላት ተመሳሳይ ፈተና ነበር (ማቴ. 4፡1-11፤ ማር. 1፡12-13፤ ሉቃስ 4፡1-13)። ሔዋን ፍሬውን በመብላትዋ ተታለለች፤ አዳም ደግሞ ምንም እንኳ በቀጥታ ባይታለል የእርስዋን አርአያነት ተከትሏል (1ኛ ጢሞ. 2፡14)። 

ለ. አዳም ከወደቀ በኋላ 

አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ የተባረከ ሥፍራቸውን አጡ፥ ለተለያዩ ችግሮችም ተገዢ ሆኑ። 

1. ለሥጋዊና መንፈሳዊ ሞት ተዳረጉ። እግዚአብሔር ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትምታለሁ”(ዘፍጥ. 2፡17)፤ ብለው መሠረት መለኮታዊ ፍርዱ ተከናወነ። ወዲያውኑ መንፈሳዊ ሞት ሞቱ፤ ማለት ከእግዚአብሔር ተለዩ። ኃጢአታቸው ሥጋቸው እንዲያረጅና በኋላም ነፍሳቸው ከሥጋቸው እንዲለይ አደረገ። 

2. የእግዚአብሔር ፍርድ በሰይጣንም ላይ ነበር፤ እሳብም በምድር እንዲሳብ ተረገመ (ዘፍጥ. 3፡14)። በእግዚአብሔርና በሰይጣን መካከል የሚካሄደው ጦርነት ከሰው ዘር ጋር በተገናኘ ሁኔታ ዘፍጥረት 3፡15 ውስጥ እንዲህ ተገልጧል፡- “በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል፥ ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱም ራስህን ይቀጠቅጣል አንተም ሰኮናውን ትነክሳለህ”። ይህ የሚያመለክተው፥ በክርስቶስና በሰይጣን መካካል ይነሣ የነበረውን ውጊያ ሲሆን፥ ክርስቶስ በመስቀል ላይ መሞቱን፥ ነገር ግን “ሰኮናውን ትቀጠቅጣለህ” በተባለው መሠረት ሞት የማይዘው መሆኑን ነበር። የሰይጣን የመጨረሻ መሸነፍ የተጠቆመው፥ “የሴቲቱ ዘር ጭንቅላትህን ይቀጠቅጣል” በተባለ፥ ማለት በዘላለማዊ ሞት የሚቀጣው መሆኑ በተገለጠበት ክፍል ነው። ይህ የሴቲቱ ዘር የሚለው ቃል የሚያመለክተው፥ ሞትና ትንሣኤው ሰይጣንን ድል ያደረገውን ኢየሱስን 

ነው። 

3. በሔዋን ላይ ልዩ ፍርድ፥ ማለት ልጅ በምትወልድበት ጊዜ በከባድ ምጥና ሥቃይ እንዲሆን፥ እንዲሁም የሰሏ ተገዥ እንድትሆን ተፈረዶባታል (ዘፍጥ. 3፡16)። የሞት መኖር የሰውን ዘር መዋለድና መባዛት አስፈላጊ አድርጎታል። 

4 . በአዳም ላይ የተፈረደበት ልዩ ፍርድ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ እሾህና ኩርንችት በምታበቅለው ምድር ላይ ሠርቶ ከፊቱ ዝና ከድካሙ ፍሬ እንዲበላ ነበር። ተፈጥሮ እራሷ በሰው ኃጢአት ሳቢያ ተለውጣለች (ሮሜ 8፡22)። መጽሐፍ ቅዱስ በኋላ እንደገለጠው፥ ሰውን በተመለከተ በክርስቶስ የድነት ሥራ አማካይነት የኃጢአት ኃይል በከፊል የሚቃለል መሆኑና እርግማኑም በሚመጣው የሺህ ዘመን እንዲሁ በከፊል የሚሻር መሆኑ ታውቋል። አዳምና ሄዋን ከገነት ተባረው፥ ከዚያ ወዲህ የሰው ዘር ሁሉ ዕጣ የሆነውን ሐዘንና ትግል የሞላበትን ሕይውት ይኖሩ ጀመር። 

ሐ. የአዳም ኃጢአት በሰው ዘር ላይ ያመጣው ውጤት 

ኃጢአት በእዳምና በሔዋን ላይ ያስከተለው ውጤት መንፈሳዊ ሞትና ለዚያ ዓይነት ሞት ተገዢ መሆን ነበር። የቀድሞ ተፈጥሯቸው ተገፏል፤ በመሆኑም ከዚያ ወዲህ የሰው ዘር ሁሉ በኃጢአት ባርነት ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ ከሰው ዕድልና ከአካባቢው መለወጥ በተጨማሪ፥ እግዚአብሔር አዳምን በኃጢአት ተጠያቂ ያደረገበትንና ትውልዱ የሆነውን የሰው ዘር እንዲሁ የኃጢአት ባለ ዕዳ ያደረገበትንም ጥልቅ ትምህርት ያቀርባል። 

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሦስት የመተላለፍ ዓይነቶች ተገልጠዋል፡- (1) የአዳም ኃጢአት ለዘሮቹ ተላልፏል (ሮሜ 5፡12-14)፥ (2) የሰው ሁሉ ኃጢአት ወደ ክርስቶስ ተላልፏል (2ኛ ቆሮ. 5፡21)። (3) የእግዚአብሔር ጽድቅ ወደሚያምኑበት ሁሉ ተላልፏል (ዘፍጥ. 15፡6፤ መዝ. 32:2፤ ሮሜ 3፡22፤ 4፡3፥ 8፥ 21-25፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡21፤ ፊሊሞና 17፥ 18)። 

የሰው ኃጢአት፥ ወደ ክርስቶስ መተላለፉ ግልጥ ነው። እግዚአብሔር አምላክ የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ (ኢሳ. 53፡5፤ ዮሐ. 1፡29፤ 1ኛ ጴጥ. 2፡24፤ 3: 18)። በተመሳሳይ መንገድ የእግዚአብሔር ጽድቅ በርሱ ወደሚያምኑ ሁሉ በፍርድ ይተላለፋል (2ኛ ቆሮ. 5፡21)። ከዚህ ሌላ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን የሚያስገኝ ወይም ለጽድቅ የሚያበቃ መንገድ የለም። ይህ የጽድቅ መተላለፍ እዲሱ ፍጥረት ውስጥ ባለ ግንኙነት ይገኛል። በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካይነት ከጌታ ጋር በመገናኘት (1ኛ ቆሮ. 6፡17፤ 12፡13፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡17፤ ገላ. 3፡27)፥ ደግሞ እንደ አካሉ አባልነት ከክርስቶስ ጋር ይገናኛል (ኤፌ. 5፡30)። በዚህም የክርስቶስ የሆነ ጸጋ፥ አካሉ ወደሆኑ ሁሉ ይተላለፋል። አማኝ “ክርስቶስ ውስጥ” ስለሆነ የክርስቶስ የሆነውን ሁሉ ይጋራል። 

ማንኛውም ሰው ሲወለድ አዳማዊ ባሕርይ በውስጡ አለ። ስለዚህም በአዳም የነበረው አሮጌ ተፈጥሮ ወደ እርሱ ይተላለፋል። እንዲህ ያሉ ሰዎች አዳማዊውን ተፈጥሮ ስለሚወርሱ የአዳም ኃጢአት አለባቸው ይባላሉ። ይህ የሚያመለክተው፥ የአዳም ኃጢአት ለዘሩ ሁሉ የሚተላለፈው በመለኮታዊ ፍርድ እውነትነት መሠረት መሆኑን ነው። የእግዚአብሔርም ጽድቅ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ላቅድስና ላሰው ሁሉ ይተላለፋል። ሰዎች እንደ አዳም በደሉም እልበደሉ ከእዳም የተላለፈ ኃጢአት ስላለባቸው ከመለኮታዊው ፍርድ በታች ናቸው። 

ምንም እንኳን ሰዎች እንደ ልማዳቸው አዳም ለሠራው ኃጢአት ተጠያቂ አይደለንም ቢሉ፥ መለኮታዊው መገለጥ የሚያመለክተው ግን፥ የሰው ዘር ሁሉ መጀመሪያ የሆነው አዳም ስለሆነና ሰው ሁሉ በቀጥታ ከእርሱ ስለተገኘ እግዚአብሔርም በእርሱ (በአዳም) መተሳሰፍ የተነሣ ዘሩን በሙሉ በኃላፊነት የሚጠይቅ መሆኑን ነው። የአዳም ኃጢአት ያለምንም ልዩነት በሰው ሁሉ ላይ በቀጥታ ሞት አስፈርዶበታል (ሮሜ 5፡12-14)። በዚህ ሁኔታ የአዳም ውድቀት፥ ማለት የመጀመሪያው ኃጢአቱ በኃጢአታዊ ተፈጥሮነት ለትውልድ ሁሉ ከአባት ወደ ልጅ ይተላለፋል። የውድቀቱ ውጤት ሁለንተናዊ ነው፥ መለኮታዊ ጸጋም እንዲሁ። 

ሰዎች አሁን የወደቁት፥ መጀመሪያ በሠሩት ኃጢአት ምክንያት ሳይሆን፥ በኃጢአት ከወደቀው እዳም በመወለዳቸው ነው። ኃጢአት በመሥራታቸው ኃጢአተኞች አይሆኑም፤ ነገር ግን በተፈጥሯቸው ኃጢአተኞች ስለሆኑ ኃጢአት ይሠራሉ። ማንኛውም ሕጻን መልካም እንዲሆን እንጂ፥ ኃጢአት የመሥራት ትምህርት አያስፈልገውም። 

በአዳም ኃጢአት ምክንያት የሰው ዘር ሁሉ ተጠያቂ ቢሆንም፥ ሕጻናትንና በኃላፊነት ለመጠየቅ ብቁ ላልሆኑት ሰዎች ግን የእግዚአብሔር መለኮታዊ ጸጋ እንደተዘጋጀላቸው ሊታወቅ ይገባል። የእግዚአብሔር ቅዱስ ፍርድ የሚያርፈው ከክርስቶስ ውጭ በሆኑት ሁሉ ላይ ነው። ይህ የሚሆነው፡- (1) ከአዳም ከተላለፈባቸው ኃጢአት የተነሣ፥ (2) ከወረሱት ኃጢአታዊ ተፈጥሮ የተነሣ፥ (3) ከኃጢአት በታች በመሆናቸው፥ 4. ራሳቸውም ከሚሠሩት ኃጢአት የተነሣ ነው። 

ይህ የእግዚአብሔር ቅዱስ ፍርድ ቢኖርም፥ ኃጢአተኛው በክርስቶስ በኩል ሊድን ይችላል። ይህ ነው የወንጌል የምሥራች። 

በአሮጌው ሰው ላይ የሚያርፉት ቅጣቶች፡- (1) አካላዊ ሞት፥ ማለት የነፍስ ከሥጋ መለየት፥ (2) መንፈሳዊ ሞት፥ ልክ እንደ አዳም ሁሉ በአሁኑ ጊዜ ያልዳነ ሕዝብ ነፍስ ከእግዚአብሔር የተሰየችና የጠፋች ናት (ኤፌ. 2፡1፤ 4፡18፥ 19)፥ (3) ሁለተኛው ሞት፥ ማለት የነፍስ ለዘላለም ከእግዚአብሔር መለየትና ለዘላለም መወገድ (ራእይ 2፡11፤ 20፡6፥ 14፤ 21፡8)።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

27
ትምህርት 27 ከ52

ኃጢአት፡- ባሕርዩና ሁሉን አቀፍነቱ

ሀ. ሰው ስለ ኃጢአት ያለው አስተሳሰብ። 

ኃጢአት በሰው ሕይወት ውስጥ ዋና እውነታና የመጽሐፍ ቅዱስ ታላቅ ጉዳይ በመሆኑ፥ የማያቋርጥ የውይይት ርዕስ ሆኖ ቆይቷል። መንፈሳዊ መገለጥን የማይቀበሉ ክፍሎች ስለ ኃጢአት በቂ ያልሆን ፅንሰ-አሳቦችን በመደጋገም ሰንዝረዋል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነውና የተለመደው አመለካከት፥ ኃጢአት በዓለም መልካምና ክፉ አለ በሚል የተሳሳተ ግንዛቤ ላይ በመመሥረት የሚመጣ የተሳሳተ እምነት ነው ብለውታል። ይህ ፅንሰ-አሳብ የሕይወትን እውነታና፥ የኃጢአትን ክፉነት መመልከት ይሳነዋል። የመልካም ሥነ ምግባር አምላክና ሕግጋት መኖራቸውንም አይቀበልም። 

ኃጢአትን በተመለከተ ሌላውና ጥንታዊው አመለካከት፥ ኃጢአትን ከእግዚአብሔር ተጻራሪና ከቁሳዊው ዓለም ጋር የሚዛመድ አድርጎ የሚያየው ነው። ይህ በምሥራቃውያን ፍልስፍናና በግሪክ ኖስቲካዊነት ውስጥ የሚገኝ አመለካከት ነው። ይህ አመሰካካት በመናኝነት ትምህርት (Atheism/ኤቲይዝም) ራስን የመካድና ለሥጋ ፈቃድ እምቢ የማለት አስተሳሰብ መሠረትነው። ከዚያም ሌላ የትምህርቱ ታላቅ ትኩረት፥ ሥጋን ማስደሰት ነው ለሚሰው ሌላ አስተምህሮ (Epicurianism/ኤፒኪዩሪየኒዝም) መሠረት ሆኗል። ያም ሆነ ይህ የአመለካከቶቹ መሠረታዊ አሳብ ሰው ኃጢአተኛ መሆኑንና ለሚሠራውም ኃጢአት በእግዚአብሔር ተጠያቂ መሆኑን መካድ ነው። ኃጢእት ራስ ወዳድነት ነው የሚል፥ የተለመደ ግን በቂ ያልሆነ አመለካከትም አለ። ኃጢአት ራስ ወዳድነት መሆን እርግጥ ሲሆንም፥ ይህ አመለካከት ሌሎችንም ሁኔታዎች የሚያጠቃልል አይደለም። 

ምክንያቱም ሰው አንዳንዴ በራሱም ላይ ኃጢአት ይሠራል። 

እነዚህ ሁሉ ፅንሰ-አሳቦች የኃጢአትን ምንነትና ሁለንተናዊነት አስመልክቶ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን መገለጥ የማይቀበሉ እንዲሁም ደረጃቸውን ያልጠበቁ ናቸው። 

ለ. ስለ ኃጢአት መጽሐፍ ቅዱሳዊው አስተምህሮ 

በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ መሠረት ኃጢአት በድርጊት፥ በሁኔታና በዝንባሌ ከእግዚአብሔር ባሕርይ ጋር የማይመሳሰል አኗኗርን ነው የሚያመለክተው። በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተለያዩ ኃጢአቶች ተገልጠዋል። ለምሳሌ ለእስራኤል በተሰጡት በአሥርቱ ትእዛዛት ተገልጧል (ዘፀ. 20፡3-17)። ኃጢአት ምንጊዜም ከእግዚአብሔር ማንነትና ከዘላለማዊ ቅድስና የተለየ ነገር ነው። ምንም እንኳን በሰዎች ላይ የሚፈጸም ቢሆን፥ ኃጢአት ምን ጊዜም የእግዚአብሔር ተፃራሪ ነው (መዝ. 51፡4፤ ሉቃስ 15፡18)። ስለዚህ ኃጢአትን የሚሠራ ሰው በድርጊቱ እንደ እግዚአብሔር አይደለም፤ ስለሆነም ከጌታ ፍርድ አያመልጥም። ስለ ኃጢአት የሚሰጠው አስተምህሮ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በእራት መንገዶች ቀርቧል። 

1. የግል ኃጢአት (ሮሜ 3፡23)፥ በዕለታዊ ሕይወት የሚደረግ፥ ከእግዚአብሔር ፈቃድና ከእግዚአብሔር ባሕርይ ጋር የማይስማማን ማንኛውንም ድርጊት ያጠቃልላል። 

ሰዎች ብዙ ጊዜ የግል ኃጢአታቸውን ያውቃሉ። የግል ኃጢአቶች ደግሞ በዓይነታቸው የተለዩ ናቸው። በአጠቃላይ ሲታይ የግል ኃጢአት በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተሰጠን የተለየ ትእዛዝ ካለማክበር ጋር ይዛመዳል። የዓመፅን ወይም ያለመታዘዝን ፅንሰ- አሳብ የሚያካትትም ነው። ምንም እንኳን ብሉይ ኪዳን ውስጥ ስለ ኃጢአት የተጠቀሱት ስምንት ያህል ቃላት፥ አዲስ ኪዳን ውስጥ ደግሞ አሥራ ሁለት ያህል ቢሆኑ፥ መሠረታዊው ነገር በማድረግ ወይም ባለማድረግ ከእግዚአብሔር ባሕርይና ፈቃድ ያላመስማማት ጉዳይ ነው። የኃጢአት መሠረታዊ አሳብ፥ ሰው ከእግዚአብሔር ቅዱስ ባሕርይ አንጻር ሲታይ የተወሰነለትን ግብ አለመምታት፥ የተከለለለትን መሥመር መጣስ እና ከጌታ ቅድስና መጉደል ነው። 

2. ኃጢአታዊ ተፈጥሮ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰው እንደ ኃጢአት ነው (ሮሜ 5፡19፤ ኤፌ. 2፡3)። የአዳም ኃጢአት ለውድቀት አብቅቶታል። በዚህም ሳቢያ ሰው ከእግዚአብሔር የተለየ፥ ጸጋው የተገፈፈና ኃጢአትን ለትውልዱ የሚያወርስ ሆነ። በመሆኑም ከአዳም የተወለዱ ሁሉ በአዳማዊ ተፈጥሮ ነው የተወሰዱት። የኃጢአት ዝንባሌ አላቸው። ምንም እንኳ ይህ ተፈጥሮ በክርስቶስ አማካይነት መስቀል ላይ የተፈረደበት ሲሆን (ሮሜ 6፡10)በማንኛውም ክርስቲያን ሕይወት የሚሠራ ኃይል ነው። ኃጢአት በአሁኑ ጊዜ ፍጹም ይወገዳል ወይም ይጠፋል አልተባለም። ክርስቲያን ግን ውስጡ በሚኖር መንፈስ ቅዱስ አማካይነት ኃጢአትን የማሸነፍ ኃይል አሰው (ሮሜ 8፡4፤ ገላ. 5፡16-17)። 

ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ይህን ጠቃሚ ጉዳይ ያነሡታል። ኤፌሶን 2፡3 ውስጥ ሰዎች፥ ጥፍጥረታቸው የቁጣ ልጆች” ተብለዋል። የሰው አጠቃላይ ተፈጥሮም ተበላሽቷል። አጠቃላይ መበላሸት ወይም መበከል የሚለው ፅንሰ-እሳብ ሰው ፍጹም ክፉ ነው ማለት ሳይሆን፥ በተፈጥሮው በኃጢአት ተበክሏል (ሮሜ 1፡8-3፡20) ማለት ነው። በመሆኑም የሰው ፈቃዱ (ሮሜ 1፡28)፥ ሕሊናው (1ኛ ጢሞ. 4፡2) እና አእምሮው (ሮሜ 1፡28፤ 2ኛ ቆሮ. 4:4)። ተበክሏል፤ ልቦናው ታውሯል (ኤፌ. 4፡18)። 

ባለፈው ጥናታችን እንደተመለከትነው፥ ሰዎች ኃጢአታዊ ተፈጥሮ የኖራቸው ከወላጆቻቸው ስለወረሱት ነው። በዓለም ከተወለዱት ሕፃናት ማንም ቢሆን ልዩ ከሆነው የኢየሱስ ማዳን ካልሆነ በቀር ከዚህ ኃጢአታዊ ተፈጥሮ ነጻ አይደለም። ሰዎች ኃጢአተኛ የሚሆኑት ኃጢአት በመሥራታቸው አይደለም፤ በኃጢአታዊ ተፈጥሯቸው ሳቢያ ኃጢአት ይሠራሉ እንጂ። ለዚህና ለግል ኃጢአት ፈውሱ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የተሰጠው ድነት ነው። 

3. መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተገለጠው ኃጢአት በተፈጥሯችን የሚተላለፍ ነው (ሮሜ 5፡12-18)። ከሰው በኃጢአት መውደቅ ጋር ተያይዞ ባለው ምዕራፍ እንደተገለጠው፥ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ሰው በራሱ ኃይል የማያገኛቸው ግን የሚተላላፉ ሦስት ነገሮች አሉ፡- (ሀ) ኃጢአትን የተመለከተው አስተምህሮ የተመሠረተበትና ከአዳም ወደ ትውልዶቹ በውርስ የተላለፈው፥ (ላ) የሰው ኃጢአት ወደ ክርስቶስ የተላለፈበትና የድነት ትምህርት የተመሠረተበት (ሐ) የእግዚአብሔር ጸጋ በክርስቶስ ወደአመኑት የተላለፈበትና የጽድቅ ትምህርት የተመሠረተበት። 

ይህ ከአንዱ ወደ ሌላው የሚተላለፈው ሀ. በውርስ ወይም ለ. በሕግ ሊሆን ይችላል። የውርስ የሚሆነው፥ አንድ ሰው ከቀደሙት አባቶቹ የሚተላለፍለት መሆኑን ሲገነዘብ ነው። ሆኖም ከክርስቶስ የማስታረቅ ሥራ የተነሣ እግዚአብሔር አሁን ሰውን የውርስ ኃጢአት ባለ ዕዳ አያደርገውም (2ኛ ቆሮ. 5፡19)። 

ሕግን ካለመፈጸም የሚመጣ የኃጢአት መተላለፍ በውርስ ከሚመጣው ይለያል (ፊሊሞና 18)። ከአዳም ለዘሮቹ የተሳለፈው ኃጢአት የውርስ ነው ወይስ የሕግ መተላለፍ ለሚለው ጥያቄ በሚሰጠው መልስ አለመግባባት ቢኖርም፥ ሮሜ 5፡12 ውስጥ የተጠቀሰው ቃል በግልጥ እንደሚያስረዳው የተላለፈው በውርስ ነው። የሁሉ አባት የሆነው አዳም ኃጢአት በሠራ ጊዜ፥ ትውልዱ ሁሉ ኃጢአት ሠርተዋል። 

ቀጥሎ ያሉት ሁለት ጥቅሶች (ሮሜ 5፡13-14) የተጻፉት፥ ይህ ዓይነቱ ኃጢአት የግል አለመሆኑን ለማመልከት ነበር (ዕብ. 7፡9-10ን ይመልከቱ))። ይሁን እንጂ ሮሜ 5፡17-18 እንደሚያመለክተው፥ ማለት በአንድ ሰው ኃጢአት ፍርድ በሰዎች ሁሉ ላይ መጣ፥ ስለሚል የውርስ ኃጢአት የሕግ መተላለፍም ነው። አጠያያቂ የሚሆነው፥ የመጀመሪያው የአዳም ኃጢአት ብቻ ነው። ለአዳምም ሆነ በቀጥታ ለሚተላለፍላቸው ዘሮቹ ውጤቱ ሞት ነው። ለተላሳፊ ወይም ለውርስ ኃጢአት የተለገሰ የእግዚአብሔር መለኮታዊ ስጦታ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ የዘላለም ሕይወት ነው። 

4. የኃጢአት መተላለፍ በሰው ዘር ሁሉ ላይ ያመጣው ሁኔታ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተገልጧል። ዓለም ሁሉ፥ አይሁድና ሌሎች ሕዝቦችንም ጨምሮ፥ በእግዚአብሔር ፊት “ከኃጢአት በታች” ናቸው (ሮሜ 3፡9፤ 11፡32፤ ገላ. 3፡22)። “ከኃጢአት በታች” መሆን ማላት፥ በመለኮት እይታ ከድነት ጸጋ ውጭ መሆን ማለት ነው። ድነት በጸጋ ብቻ የሚገኝ እና በሰዎች መልካም ሥራ የማይደገፍ መሆኑን ስለሚገልጥ፥ እግዚአብሔር ሁሉንም (“ከኃጢአት በታች ወይም ጸጋ የጎደላቸው ብሏቸዋል። ይህ ከኃጢአት በታች የመሆን ፍርድ ፈውስ የሚያገኘው፥ ሰው በክርስቶስ ኢየሱስ ሥራ አማካይነት በምሕረቱ ባለ ጸጋ በሆነው እግዚአብሔር ፊት ሲቆም ነው። 

በአጠቃላይ ሲታይ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያመለክተው፥ ኃጢአት በሰው ላይ የሚያመጣውን እሠቃቂ ውጤትና፥ ሰው የራሱን የኃጢአት ችግር ለማስወገድ ተስፋ የሌለው መሆኑን ነው። በመሆኑም የኃጢአትን ትክክለኛ ትምህርት መረዳቱ እግዚአብሔር ለኃጢአት የሰጠውን መፍትሔ ለመረዳት መሠረታዊ ነገር ነው።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

28
ትምህርት 28 ከ52

ከኃጢአት ቅጣት መዳን

ሀ. የድነት ትርጉም 

ድነትን የሚመለከተው መለኮታዊ መገለጥ፥ በእምነት የእግዚአብሔር ልጅ በሆነ ሰው ሁሉ በሚገባ መታወቅ አለበት። ምክንያቱም፡- (1) የግል ድነት የሚመሠረተው በርሱ ላይ ስለሆነ፥ (2) አማኝ ለዓለሙ ሁሉ እንዲያውጀው እግዚአብሔር የሰጠው ዋነኛ መልእክት ስለሆነና፥ (3) የእግዚአብሔርን ፍቅር በሙላት የሚገልጠው መለኪያ ይኸው ብቻ ስለሆነ ነው። 

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተገለጠው ሰፊ ትርጉም መሠረት፥ “ድነት” የሚለው ቃል እግዚአብሔር ሰውን ከዘላለም የኃጢአት ጥፋትና ፍርድ ያዳነበትን አጠቃላይ ሥራ ያመለክታል። የጸጋውን ባለጠግነት፥ ዘላለማዊ ሕይወትና ዘላለማዊ ክብርን በሰማይ ለኃጢአተኛው የተሰጠ መሆኑንም ያስገነዝባል። “ድነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው” (ዮናስ 2፡9)። ስለዚህ ድነት በሁሉም መልኩ በሰው ፈንታ እግዚአብሔር የሠራው እንጂ፥ በምንም ሁኔታ ሰው በእግዚአብሔር ፈንታ የሠራው አይደለም። 

የዚህ መለኮታዊ ሥራ አንዳንድ ዝርዝር ሁኔታዎች ከዘመን ዘመን የተለያዩ ናቸው። ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ በነበረው ዘመን እምነታቸውን በእግዚአብሔር ላይ የጣሉ ሰዎች በመንፈስ እንደገና ተወልደው የሰማያዊ ክብር ወራሾች መሆናቸው ተረጋግጦላቸዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ የእስራኤል መንግሥት ጌታ በሚመለስበት ጊዜ በአንድ ቀን በመንፈስ ትወለዳለች (ኢሳ. 66፡8)። 

ደግሞም በሚመጣው መንግሥት የሚኖሩ ከአይሁድና ከአሕዛብ ወገን የሆኑ ሁሉ ከትንሹ እስከ ትልቁ ጌታን ያውቁታል ተብሏል (ኤር. 31፡34)። ይሁን እንጂ፥ በአሁኑ ዘመን ለሰዎች የተሰጠው ድነት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዝርዝር መስፈሩ ብቻ ሳይሆን፥ በሚሠራቸው አስደናቂ ነገሮች ከሌሎች የእግዚአብሔር የማዳን ሥራዎች ሁሉ ይልቃል። የድነት ትምህርት፥ የመንፈስ ቅዱስን በአማኞች ውስጥ ማደር፥ ማተምና የመንፈስ ጥምቀት የመሳሰሉትን የእግዚአብሔር የጸጋ ሥራዎች ይጨምራል። 

ለ. ድነት፥ ለኃጢአት እግዚአብሔር ያዘጋጀው መፍትሔ 

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኃጢአት በሚያቀርባቸው ትምህርቶች አንዳንድ ልዩነቶች ቢኖሩም፥ የሚከተሉት ሁለት አጠቃላይ እውነታዎች በቅድሚያ መታወቅ ይኖርባቸዋል። 

1. ኃጢአት ባልሰለጠነ ወይም በሰለጠነ ሰው፥ ዳግም በተወለደ (በክርስቲያን) ወይም ባላመነ ሰው ሲሠራ፥ ሁሉንም እኩል ነው ኃጢአተኛ የሚያደርጋቸው። በፍርድ ወቅት ኃጢአተኛ ለበደሉ ብዙ ወይም መለስተኛ ቅጣት የሚቀበል መሆኑ ግልጥ ነው (ሉቃስ 12፡47-48)። ይሁን እንጂ፥ ኃጢአት ሁሉ ቅዱስ በሆነው በእግዚአብሔር ፊት ልዩነት የለውም። ምክንያቱም፥ ኃጢአት ከጌታ ቅዱስ ባሕርይ ጋር በፍጹም የሚሄድ አይደለም። 

ኃጢአት ሊፈወስ የሚችለው በፈሰሰው የእግዚአብሔር ልጅ ደም ብቻ ነው። ይህ ፈውስ የእንስሳት መሥዋዕት በማቅረብ በትንቢታቸው የክርስቶስን ሞት ለተነበዩም ሆነ ያን የክርስቶስ ሞት ወደኋላ በእምነት ለሚመለከቱ ሁሉ ይሠራል። የኃጢአትን ቅጣት በተመለከተ፥ መለኮታዊው ይቅርታ ቅጣትን የማሳሳት ድርጊት አይደለም። ኃጢአት ይቅር የተባለው በኃጢአተኛው ፈንታ ቅጣትን የሚቀበል ምትክ ስለቀረበ ነው። በአሮጌው ሥርዓት ኃጢአተኛው ይቅርታ የሚያገኘው፥ ሕጉ እንደሚያዘው የኃጢአት ማስተሥረያ የሆነውን የደም መሥዋዕት ካህኑ ካቀረበ በኋላ ነው። ይህ ሁኔታ ኃጢአተኞች ይቅርታ ያገኙበትን የክርስቶስ ሞት አስቀድሞ የሚያመለክት ነበር (ዘሌ. 4፡20፥ 26፥ 31፥ 35፤ 5፡10፥ 13፥ 16፥ 18፤ 6፡7፥ 19፡20፤ ዘኁ. 15፡25፥ 26፥ 28)። ከክርስቶስ ሞት በኋላ በቃሉ፥ “በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን፥ እርሱም የበደላችን ሥርየት” (ኤፌ. 1፡7፤ ቆላ. 1፡14) ተብሎ እንደተጻፈ ይሄው እውነት ተፈጽሟል። 

ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ ያከናወነው የምትክነት ሥራ ፍጹም ብቃትና ሙላት ያለው ነው። ስለሆነም በክርስቶስ የሚያምን ኃጢአተኛ ሁሉ ይቅርታ የሚያገኝ ብቻ ሳይሆን፥ ለዘላለም የሚጸድቅ ነው (ሮሜ 3፡24)። እግዚአብሔር ምንጊዜም ቢሆን ኃጢአትን በዋዛ እልፎ አያውቅም። የኃጢአት ይቅርታ በኃጢአተኛ ላይ ምንም ዓይነት ሸክም እይጭንበትም። ምክንያቱም ከባዱ መለኮታዊው የኃጢአት ቅጣት ክርስቶስ ላይ ስላረፈ ይቅርታ አግኝቷል፥ ጸድቋልም (1ኛ ጴጥ. 2፡24፤ 3፡18)። 

ሐ. ድነት፥ ከመሰቀሉ በፊትና በኋላ 

1. ከክርስቶስ የመስቀል ሞት በፊት የኃጢአት ይቅርታ የሚያስገኘው መለኮታዊ አሠራር የማስተሥረያ መሥዋዕት ነበር። ማስተሥረይ የሚለው ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ትርጉሙ “መሸፈን” ማለት ነው። የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን ሊያስወግድ አልቻለም፥ አይችልምም (ዕብ. 10፡4)። የደም መሥዋዕት በኃጢአተኛው በኩል የሚያመለክተው፥ የእግዚእብሔርን ጻድቅ ፍርድ ወይም ቅጣት መቀበልን ነው (ዘሌዋ. 1፡4)። በእግዚአብሔር በኩል ደግሞ መሥዋዕቱ ያመለክት የነበረው፥ ሊመጣ ያለውንና አጥጋቢ ወይም ብቁ የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ነበር። በመሥዋዕትነት ይቀርብ የነበረው የማስተሥረያ ደም፥ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ምሳሌ በመሆን ኃጢአትን ይሸፍን ነበር። ይህ ይሆን የነበረው ክርስቶስ የዓለምን ኃጢአት ለዘላለም እስከሚያስወግድበት ዕለት ነበር። “ማስተሥረይ” ወይም “መሽፈን” የሚለው የብሉይ ኪዳን ቃል፥ ማሳለፍ የሚል አሳብን ይዟል። 

1. ለምሳሌ ሮሜ 3፡25 ውስጥ “ማስተሥረይ” የሚለው ቃል “ማሳለፍ” የሚል ትርጉም አለው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ክርስቶስ በሞተ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ከመስቀሉ በፊት የተሠሩ ኃጢአቶችን በማሳለፍ ጻድቅነቱን አሳይቷል። እነዚያ ኃጢአቶች ለማስተሥረያ የደም መሥዋዕት የቀረበባቸው ነበሩ። እግዚአብሔር ብቁ የመሥዋዕት በግ እንደሚሰጥ እና፥ በብርቱ ተስፋው መሠረትም ኃጢአትን ይቅር እንደሚል ተናግሮ ነበር። በመሆኑም በክርስቶስ ሞት አማካይነት በሰጣቸው ተስፋዎቹ ሁሉ ጻድቅ መሆኑን እረጋገጠ። 

2. ኢየሱስ በመስቀሉ ላይ ከሞተ ወዲህ እግዚአብሔር ኃጢአትን የሚመለከትበት ሁኔታ ሮሜ 3:26 ውስጥ ተገልጧል። ክርስቶስ ሞቷል። ይህ መሥዋዕትነት ከእንግዲህ ገና እንደሚፈጸም ተስፋና በእንስሳት ደም ተምሳሌትነት የሚታይ አይደለም። አሁን ማንኛውም ሰው፥ የቱንም ያህል ኃጢአተኛ ቢሆን፥ እንዲያደርግ የሚጠየቀው፥ ፍጹም በሆነ ጸጋ እማካይነት ለርሱ በተከናወነው ማዳን እንዲያምን ነው። እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ኃጢአተኛ ላይ ያለውን መለኮታዊ ፍርድ ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ ከፍሏል። ይህን በማድረግም ጽድቁን፥ ወይም ቅድስናውን የማይፃረር መሆኑንና በአንጻሩም ከቅጣቱ ባሻገር በኢየሱስ የሚያምን ኃጢአተኛን የሚያጸድቅ መሆኑን አረጋግጧል። 

“ሥርየት” የሚለውና በብሉይ ኪዳን ብቻ በሚገባ ይከናወን የነበረው ቃል ኃጢአትን ለጊዜው ማሳለፍን”፥ “ይቅር ማለትን” እና “መሸፈንን” ያመለክት ነበር። ክርስቶስ መስቀሉ ላይ ኃጢአትን በቀላሉ አላሳለፈም፥ ወይም አልሸፈነም። ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ ተሸከመው። ለሁሉ ስለሚበቃው መሥዋዕትነቱም፥ “እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” ተብሎ ተመስክሮለታል (ዮሐ. 1፡29፤ ቆላ. 2፡14፤ ዕብ. 10፡4፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡5)። ደግሞም “እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ” (1ኛ ጴጥ. 2፡24) ተብሏል። መስቀሉ ላይ ኃጢአትን ለጊዜው ወይም በከፊል የማየት ጉዳይ አልነበረም። ይህ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለ ታላቅ ጉዳይ የእግዚአብሔርን ፍጹም ቅድስና በሚያረካ ሁኔታ ተከናውኗል። ቀሪው ጥያቄ በዚህ እግዚአብሔርን ባረካ መሥዋዕት ሰውስ ረክቷል ወይ? የሚለው ነው። ለኛ የክርስቶስን ሥራ መቀበል ማለት፥ ነፍስን በሚያድነው አዳኝ ማመን ማለት ነው። 

መ. የድነት ሦስቱ ጊዜያት 

1. በሰዋስዋዊ አገላለጥ የድነት ኃላፊ ጊዜ በአንዳንድ የቅዱሳት መጻሕፉት ክፍል ተመልክቷል። እነዚህ የመጻሕፍት ክፍሎች ስለ ድነት በሚናገሩበት ጊዜ፥ ለአማኙ ሙሉ በሙሉ ያለፉ ወይም የተፈጸሙ የሚሆኑ ናቸው (ሉቃስ 7፡50፤ 1ኛ ቆሮ. 1፡18፤ 2ኛ ቆሮ. 2፡15፤ ኤፌ. 2፡5፡8)። ይህ መለኮታዊ ሥራ ፍጹም ስለሆነ፥ አማኝ የዘላለም ድነት ዋስትና አለው (ዮሐ. 5፡24፤ 10፡28፥ 29፤ ሮሜ 8፡1)። 

2. ድነት የአሁን ጊዜ መሆኑን የሚያመለክተውና፥ በሚቀጥለው ምዕራፍ የሚብራራው ጉዳይ፥ በዚህ ዘመን በዓለም ነግሦ ከሚገኘው የኃጢአት ኃይል መዳንን ያስገነዝባል (ሮሜ 6፡14፤ 8፡2፤ 2ኛ ቆሮ. 3፡18፤ ገላ. 2፡19-20፤ ፊሊ. 1፡19፤ 2፡12-13፤ 2ኛ ተሰ. 2፡13)። 

3. ድነት የወደፊት ጊዜ ሆኖ በቀረበበት ክፍል የሚገልጠው ደግሞ አማኝ በእምነት ሙሉ በሙሉ ክርስቶስን እስከ መምሰል ድረስ የሚድን በመሆኑ ላይ ያተኩራል (ሮሜ 8፡29፤ 13፡11፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡5፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡2)። የድነት አንዳንድ ሁኔታዎች ለአማኙ የሚፈጸሙለት ወደፊት ነው የሚለው አባባል እውነትነት፥ ስለ መጨረሻው ፍጻሜ ጥርጥር አለ ማለት አይደለም። ምክንያቱም የድነት የወደፊት ሁኔታ በአማኙ ታማኝነት ላይ ይመሠረታል፥ የሚል ትምህርት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። እግዚአብሔር ታማኝ ነው፥ የጀመረውን መልካም ሥራ እስከ ኢየሱስ ቀን ድረስ ይፈጽመዋል (ፊልጵ. 1፡6)። 

ሠ. ድነት፥ በክርስቶስ የተፈጸመ ሥራ 

እግዚአብሔር ለጠፉ ሰዎች ያከናወነው ሥራ በሚታሰብበት ጊዜ፥ ክርስቶስ ለሁሉ ባከናወነው ፍጹም ሥራና፥ አማኝ በክርስቶስ በሚያምንበት ጊዜ እግዚአብሔር በሚፈጽመው የድነት ሥራ መካከል ያለውን ልዩነት መገንዘቡ ጠቃሚ ነው። 

ኢየሱስ ነፍሱን ከመስጠቱ በፊት “ተፈጸመ” የሚል የመጨረሻ ቃል እንደተናገረ ተጽፏል (ዮሐ. 19፡30)። ይህን በተናገረ ጊዜ ያመለከተው ስለ ራሱ ሕይወት፥ ስለ አገልግሎቱ ወይም ስለ ሥቃዩ ሳይሆን፥ አብ የሰጠው ልዩ ሥራ መፈጸሙን ለማመልከት ነበር። ይህ ሥራ ኢየሱስ እስከተሰቀለበት ጊዜ ድረስ አልተፈጸመም ነበር። ፍጻሜ ያገኘውም በመስቀል ላይ በሞተ ጊዜ ነው። ለዓለም ሁሉ የተከናወነ ሥራ ነበር (ዮሐ. 3፡16፤ ዕብ. 2፡9)። ሥራው የቤዛነት (1ኛ ጢሞ. 2፡6)፥ የማስታረቅ (2ኛ ቆሮ. 5፡19)። እንዲሁም ለእያንዳንዱ ሰው የኃጢአት ማስተሥረያ (1ኛ ዮሐ. 2፡2) ነው። 

እግዚአብሔር ከቅድስናው ጋር በሚስማማ ሁኔታ ከኃጢአተኞች ክፉውን እንኳን ያድን ዘንድ መሠረት ይሆናል እንጂ፥ ክርስቶስ በመስቀል ላይ መሞቱ ብቻውን ሰዎችን አያድንም። ይህ ነው ክርስቲያን ለዓለም ሁሉ ያውጅ ዘንድ የተሾመበት የምሥራች። የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ ደም በጌታ ፊት እጅግ ክቡር ቢሆንም፥ ኃጢአተኞችን ለመዋጀት ተከፍሏል። ኃጢአት ኃጢአተኛውን ከእግዚአብሔር ለይቶት ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ራሱ ያን ኃጢአት ለዘላለም ለማስወገድ የመሥዋዕቱን በግ ሰጠ።

ይህ ሁሉ አስቀድሞ የተፈጸመ በመሆኑ ኃጢአተኛው መልእክቱን እንደ እግዚእብሔር ምስክርነት በእምነት እንዲቀበለው ይጠየቃል። ሰው ይህን መልእክት ሰምቶ ለኃጢአቱ ይቅርታ እንዳገኘና፥ የኃጢአት ችግር ተወግዶለት እፎይ ማለቱን ተገንዝቦ፥ እግዚአብሔርን ስለ ታላቅ በረከቱ ካላመሰገነ አምኗል ለማለት ያስቸግራል። 

ረ. ድነት፥ የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ 

በአንድ ሰው መዳን ጊዜ የሚከናወነው የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ የተለያዩ የጸጋ ሥራ ደረጃዎችን ያጠቃልላል። እነርሱም ከኃጢአት ነፃነት፥ እርቅ፥ ማስተሰረይ፥ ይቅርታ፥ ዳግም ልደት፥ ውርስ፥ ጽድቅ፥ ቅድስና፥ ፍጹምነት፥ ክብር ናቸው። በዚህ የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ አማካይነት ከቅዱሳን ጋር ወራሾች ለመሆን በቅተናል (ቆላ. 1፡12)፥ በውድ ልጁ ተቀባይነትን አግኝተናል (ኤፌ. 1፡6)፥ የእግዚአብሔር ጽድቅ ሆነናል (2ኛ ቆሮ. 5፡21)፥ ወደ እግዚአብሔር ቀርበናል (ኤፌ. 2፡13)፥ የእግዚአብሔር ልጆች ሆነናል (ዮሐ. 1፡12)፥ የሰማዩ መንግሥት ዜጎች ሆነናል (ፊሊ. 3፡20)፥ አዲስ ፍጥረት ሆነናል (2ኛ ቆሮ. 5፡17)፥ የእግዚአብሔር ቤተሰብ ሆነናል (ኤፌ. 2፡19፤ 3፡15)፥ እና በክርስቶስ ፍጹም ሆነናል (ቆላ. 2፡10)። ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጅነትን ያገኘ ሰው፥ ከጨለማው ሥልጣን ድኖ ወደ ልጁ የዘላለም መንግሥት ተሸጋግሯል (ቆላ. 1፡13)። ከዚህም የተነሣ አሁን መንፈሳዊ በረከትን ሁሉ እግኝቷል (ኤፌ. 1፡3)። 

ከላይ ከተጠቀሱት አስደናቂ የእግዚአብሔር ሥራዎች ለመረዳት እንደሚቻለው፥ በክርስቶስ አምኖ የዳነ ሰው፥ ለበደሉ ይቅርታ አግኝቶ ለዘላለም ጸድቋል ስለተባለ የኃጢአት በደለኛነትና ቅጣት ተወግዶለታል። እግዚአብሔር ከክርስቶስ መስቀል ውጪ ማንንም ይቅር አይልም። ከክርስቶስ ሞት ወዲህ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሚመጡትን ሁሉ ሊያድናቸው ይችላል። 

ሰ. ድነት፥ የዳነ ሰው ከኃጢአት ጋር ያለው ግንኙነት 

1. አንድ ሰው በክርስቶስ በሚያምንበት ጊዜ፥ ወዲያውኑ የድነቱ እንድ ክፍል የሆነውን የኃጢአት ይቅርታ ያገኛል። ለድነት የሚያበቁ ብዙ ነገሮችም በእግዚአብሔር ይሠሩለታል። በጸጋ አጠቃላይ ሥራ ከሚገኝ ድነትና በክርስቶስ አዳኝነት ከማመን ውጪ ግን ይቅርታ አይገኝም። 

2. ክርስቲያን በሚሠራው ኃጢአት ላይ የሚመጣውን መለኮታዊ ቅጣት በተመለከተ፥ የሚታየው ኃጢአቱ ብቻ ነው። በዚህ መሠረት የክርስቲያኑ ኃጢአት ይቅር የሚባለው፥ ለድነት በማመን ሳይሆን፥ ለሠራው ኃጢአቱ ንስሐ በመግባቱ ነው (1ኛ ዮሐ. 1፡9)። 

ኃጢአት በአማኝ ላይ የሚያስከትለው፥ ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ ከአብና ከወልድ ጋር ያለውን አንድነት ማጣት፥ እንዲሁም በራሱ ውስጥ ያለውን መንፈስ ቅዱስ ማሳዘን ነው። ያም ሆኖ ኃጢአት የሠራ ክርስቲያን ኃጢአቱን ሲናዘዝ አንድነቱ፥ ደስታው፥ በረከቱና ኃይሉ ይመለስለታል። 

ኃጢአት በአማኝ ላይ የሚያስከትለው ነገር በረከትን ማጣት ቢሆንም በንስሐ ይታደሳል። አማኝ የሚሠራው ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት የከፋ ውጤት አለው። የፈሰሰው የክርስቶስ ደምና እርሱ በሰማያት የሚያከናውነው ጥብቅና (ሮሜ 8፡34፤ ዕብ. 9፡24፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡1-2) ባይኖር ኑሮ፥ ኃጢአት ክርስቲያንን ከእግዚአብሔር ለዘላለም ይለየው ነበር። ሆኖም ደሙ የሚያስተሰረይ (1ኛ ዮሐ. 2፡2) እና የጥበቃውም ዓላማ ጽድቅ በመሆኑ (1ኛ ዮሐ. 2፡1) ዋስትና አለን። ኃጢአት የሚያደርግ ክርስቲያን በአብ ዘንድ ጠበቃ ስላለው፥ ኃጢአት ቢያደርግ እንኳን ከኃጢአቱ የተነሣ ድነቱን አያጣም። ሆኖም ይህ እውነት ክርስቲያን ኃጢያትን ይሠራ ዘንድ ነፃነት የሚሰጠው አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ኃጢአትን አታድርጉ” የሚለው ይህ እውነት (1ኛ ዮሐ. 2፡1) በግልጥ ተጽፏል። አዳኛችን ስለ እኛ በሰማይ ጠበቃ መሆኑን መረዳቱ፥ ለማንኛውም ኃጢአት በቀላሉ እንዳንጋለጥ ሊያደርገን ይገባል እንጂ ኃጢአትን ለመሥራት አያበረታታንም። 

ሽ. በእምነት ብቻ የሚገኝ ድነት 

አዲስ ኪዳን ውስጥ 150 በሚሆኑ ስፍራዎች፥ ኃጢአተኛ ድነት የሚያገኘው በእምነት ብቻ መሆኑ ተገልጧል። አንድ ሰው ሲያምን በፈቃደኝነት በክርስቶስ ለመደገፍ ውሳኔን ያደርጋል። እምነት በሁለንተና የሚገለጥ እንጂ፥ የአእምሮ ወይም የስሜት ሥራ ብቻ አይደለም። የአእምሮ መስማማትና፥ የስሜት መነሣሣት ስላለ ብቻውን እውነተኛ እምነት አለ እያሰኝም። እምነት ግለሰብ ክርስቶስን ለመቀበል በፈቃዱ የሚፈጽመው ግልጥ እርምጃ ነው። 

መጽሐፍ ቅዱስ ከነዚህ ዋና ዋና እውነቶች ጋር ይስማማል። ነፍስን ማዳን የሚቻለው እግዚአብሔር ብቻ ሲሆን፥ ይህን የሚያደርገውም በልጁ መሥዋዕትነት በኩል ነው። ሰው ሌላ መዳኛ ሊኖረው እንደማይችል ተገንዝቦ፥ ለድነቱ ከራሱ ሥራ ይልቅ እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል ባከናወነው ሥራና በመልእክቱ ማመን አለበት። እምነት ሥራ ሳይሆን ጌታ በሠራው ላይ መደገፍ ነው። ስለዚህ ድነት ከእምነት በቀር በሌላ ነገር ላይ ከተመሠረተ፥ የድነት ትምህርት ባጠቃላይ ይዛባል። መለኮታዊው መልእክት “እመንና ጸልይ”፥ “እመንና ኃጢአትህን ተናዘዝ”፥ “እመንና የኢየሱስን ጌትነት መስክር”፥ “እመንና ተጠመቅ”፥ “እመንና ተለወጥ”፥ “እመንና ካሣ ክፈል” የሚል አይደለም። እነዚህ ስድስት ነገሮች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሰዋል። ቢሆንም ለድነታችን መሠረት ሆነው አይደለም። የድነት መሠረት እምነት ብቻ ነው። እነዚህ ነገሮች የማመንን ያህል ለድነት አስፈላጊ ቢሆኑ ኑሮ፥ የመዳን መንገድ በተጠቀሰባቸው ጥቅሶች ሁሉ ውስጥ በተገኙ ነበር (ዮሐ. 1፡12፤ 3፡16፥ 36፤ 5፡24፤ 6፡29፤ 20፡31፤ ሐዋ. 16፡31፤ ሮሜ 1፡16፤ 3፡22፤ 4፡5፥ 24፤ 5፡1፤ 10፡4፤ ገላ. 3፡22)። ድነት የሚገኘው በክርስቶስ ብቻ ነው፤ ሰዎች የሚድኑት እርሱን የግል አዳኛቸው እድርገው የተቀበሉት እንደሆነ ብቻ ይሆናል።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

29
ትምህርት 29 ከ52

ከኃጢአት ኃይል ነጻ መወጣት

ሀ. ከኃጢአት ነጻ መሆን ለክርስቲያኖች ብቻ 

ከኃጢአት ኃይል ነጻነት፥ እግዚአብሔር ከኃጢአት በደልና ቅጣት ላዳናቸው ሰዎች የተሰጠ ምሕረት እንደመሆኑ፥ ይህ ትምህርት ክርስቲያኖችን ብቻ የሚመለከት ይሆናል። ክርስቲያኖች በክርስቶስ የዳኑና ዋስትና ያገኙ ቢሆኑም፥ ኃጢአታዊ ባሕርይ ስላላቸው፥ ኃጢአት ይሠራሉ። ይህን እውነት በተመለከተ የእግዚአብሔር ቃልም ሆነ ሰብአዊ ልምድ አያሌ ማረጋገጫ ይሰጣሉ። ክርስቲያኖች ኃጢአት ይሠራሉ በሚለው እውነት ላይ በመመሥረት፥ ከዚህ የኃጢአት ድርጊት ነጻ ለመሆን ይቻል ዘንድ ከመለኮት የተሰጠውን መንገድ አዲስ ኪዳን ይገልጣል። 

ክርስቲያን ኃጢአት አይሠራም ወይም ለኃጢአት አይጋለጥም ከሚለው ስሕተት የተነሣ ብዙ አዲስ አማኞች ግራ ይጋባሉ፥ ይጨነቃሉም። ኃጢአት በሕይወታቸው የሚኖረውን ኃይል ሲገነዘቡም ድነታቸውን እስከመጠራጠር ይደርሳሉ። ኃጢአት የእግዚአብሔርን ቅድስና የሚያስቆጣ ስለሆነ፥ ስለ ኃጢአት መጨነቃቸው መልካም ነው። ታዲያ ድነትን ከመጠራጠር ወይም ለኃጢአት እጅን ከመስጠት ይልቅ፥ ነጻ የመሆኛ መንገድ የሆነውን የእግዚአብሔር የምሕረት ስጦታ መማር አለባቸው። 

ከድነት መንገድ ቀጥሎ ሰብአዊ አእምሮ ሊገነዘበው የሚገባ ጭብጥ፥ መለኮታዊ ዕቅድ ክርስቲያን ለእግዚአብሔር ክብር እንዲኖር ነው። ይህን ከመገንዘብ የሚበልጥ ጠቃሚ ነገር የለም። አለማወቅና ስሕተት እሳዛኝ መንፈሳዊ ውድቀትን ያስከትል ይሆናል። ወንጌል በሚሰበክበት ጊዜ ከኃጢአት ኃይል ነጻ መውጣትን አስመልክቶ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ትክክለኛ ገለጣ መስጠቱ እጅግ ያስፈልጋል። 

ለ. የኃጢአት ችግር በክርስቲያን ሕይወት 

ማንኛውም በእምነት የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው መለኮታዊ ተፈጥሮን የተቀበለ ቢሆንም (2ኛ ጴጥ. 1፡4)፥ አሮጌው ተፈጥሮም አብሮት ስላለ ሁለት ተፈጥሮዎች አሉት ለማለት ይቻላል። አንደኛው ኃጢአት ለመሥራት የማይችል፥ ሌላው ቅዱስ ሊሆን የማይችል ናቸው። አሮጌው ተፈጥሮ አንዳንድ ጊዜ “ኃጢአት” ይሚባለው (የኃጢአት ምንጭ ለማለት ነው) እና “አሮጌው ሰው”ን የሥጋ አንዱ አካል ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱሳዊው አገላለጥ “ሥጋ” የሚለው ቃል ሥነ-ምግባራዊ ሁኔታን ለመግለጥ ሲውል፥ መንፈስንና ነፍስን እንዲሁም እካልን ያመለክታል። ይህ በተለይ የሚያገለግለው፥ ዳግም ያልተወለደን ሰው በሚመለከት ነው። ለዚህ ነው ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ የሚለው፡- 

በእኔ ማለት በሥጋዬ በጎ ነገር እንዳይኖር አውቃለሁና” (ሮሜ 7፡18)። በሌላ በኩል ሐዋርያው ዮሐንስ ስላገኘነው መለኮታዊ ተፈጥሮ ሲናገር፥ “ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፥ ከእግዚአብሔር ተወልደልና” (1ኛ ዮሐ. 3፡9) ይላል። ይህ ምንባብ የሚያስተምረው፥ ማንኛውም ክርስቲያን ከእግዚአብሔር የተወለደ እንደመሆኑ፥ ኃጢእት የማያደርግ ወይም በኃጢአት ድርጊቱ የማይቀጥል መሆኑን ነው። “አያደርግም” በሚል ቃል የተተረጎመው ግሪክኛ ቃል ግሥ የአሁን ጊዜንና የሚቀጥልን አሳብ ያዘለ ነው። ይሁን እንጂ፥ ይሄው የዮሐንስ መልእክት ማንኛውም የእግዚአብሔር ልጅ የሆን ክርስቲያን ኃጢአታዊ ተፈጥሮ የለኝም እንዳይል (1፡8)፥ ወይም ኃጢአት አልሠራሁም እንዳይል (1፡10) ያስጠነቅቃል። 

በአማኙ ውስጥ ያሉ እነዚህ ሁለት የድርጊት ምንጮች ገላትያ 5፡17 ውስጥም ተጠቅሰዋል። እዚያ እንደተጠቀሰው መንፈስ ቅዱስና ሥጋ ሁልጊዜ ይቃረናሉ። “ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህ እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ።” ሐዋርያው የሚጽፈው በጣም መንፈሳዊ ስለሆነው እንጂ ስለ ሥጋዊ ክርስቲያን አይደለም፤ ይልቁንም የሥጋን ምኞት ለማይፈጽመው (5 ፡16) ነው። እንዲህ ባለው ክርስቲያን ውስጥ እነዚህ የሥጋና የመንፈስ ተቃርኖዎች አሉ። እንዲህ ያለው ሰው ከሥጋ ምኞት ነጻ ቢሆን እንኳ፥ እንዲያ ሊሆን የቻለው በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ስለሚመላለስ ነው። 

ሐ. ሕግ እንደ ሕይወት መመሪያነት 

ከኃጢአት ነጻ ማድረጊያ የሆነውን የእግዚአብሔር ፕሮግራም ከመረዳት ጋር፥ እንደ ሕይወት መመሪያነታቸው በሕግና በጸጋ መካከል ያለውን ልዩነት መገንዘቡ ተገቢ ነው። “ሕግ” የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተለያየ ግንዛቤ ጥቅም ላይ ውሏል። አንዳንዴ እንደ ሕይወት መመሪያ ሆኖ አገልግሏል። በዚህ ሁኔታ በሚያገለግልበት ጊዜ የተለያዩ ትርጉሞች አሉት። 

1. በድንጋይ ጽላት ላይ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፉት አሠርቱ ትእዛዛት (ዘጸ . 31፡18)። 

2. በምድሪቱ ውስጥ የነበረ የእስራኤል መንግሥት ጠቅላላ እሠራር፤ ትእዛዛቱን ጨምሮ (ዘዳ. 20፡1-26)፥ ፍርዶቹ (ዘዳ. 21፡1-24፡11)፥ እና ሥርዓት (ዘዳ. 24 ፡12-31 ፡18)። 

3. የሕግና የነቢያት ፍጻሜ የተባሉትና ወደፊት በምድር የሚመሠረተው የመሢሑ መንግሥት መተዳደሪያ መርሆች(ማቴ. 5፡1-7፡29፤ በተለይ 5፡17-18፤ 7፡12)። 

4. ማናቸውም ለሰው የተገለጡ የእግዚአብሔር ፈቃዶች (ሮሜ 7፡22፥ 25፤ 8፡4)። 

5. ሰዎች ለመንግሥታቸው አስተዳደር ያወጧቸው ሕግጋት (ማቴ. 20፡15፤ ሉቃስ 20፡22፤ 2ኛ ጢሞ. 2፡5)። “ሕግ” የሚለው ቃል ለጥቂት ጊዜ በሥራ ሳይ የሚውል ኃይል ሆኖም አገልግሏል (ሮሜ 7፡21፤ 8፡2)። 

6. “ሕግ” ሱብሉይ ኪዳን ውስጥ በተለይ በድርጊት እንደሚገለጥ ኪዳን ተደርጎ ቀርቧል። በዚህ ግንዛቤ መሠረት የሕግ ከልሉ በሥነ ጽሑፍ ከሰፈረው የሙሴ ሥርዓትና ከመንግሥቱ ሕግ የሰፋ ሆኗል። ይህ ብቻም ሳይሆን፥ ከእግዚአብሔር መልካም አጸፋን ለማግኘት ሲባል የሚደረገውን ማንኛውንም ሰብእዊ ሙከራ (በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ሆነም አልሆነ ይጨምራል። የሕግ መመሪያ “መልካም ብታደርግ እባርክሃለሁ” ይላል። ስለዚህ አንድ ሰው ሕግን የሚፈጽመው መልካም ነገርን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ያገኘ መሆኑን በመገንዘብ መሆኑ ቀርቶ፥ በራሱ መልካም ሥራ የእግዚአብሔር ሰው ለመሆን ከሆነ፥ ድርጊቱ ሙሉ በሙሉ በሕግ ለመዳን የሚደረግ ጥረት ይሆናል። 

1. ሕግ በሥጋ የመደገፍ መመሪያ ሆኖም ቀርቧል። ሕግ አክባሪዎቹ የሰጣቸው ምንም ጉልበት የለም። ተፈጥሯዊው ሰው በአካባቢው ካለው ይበልጥ እንዲሰጥ አልተጠየቀም፥ አልሰጠምም። በመሆኑም በሥጋ ኃይል የሚከናወን ነገር ሁሉ በባሕርይው ሕግ የመፈጻም ተግባር ነው። ምንም ሆነ ምን፥ የተገለጠ የእግዚአብሔር ፈቃድ፥ በሕግ የተጻፉ ትእዛዛት ሁሉ፥ የጸጋ ማነሣሣት ወይም ማንኛውም መንፈሳዊ ድርጊት ቢሆንም በሥጋ ኃይል እስከተሠራ ድረስ የሕግ ሥራ ነው የሚሆነው። 

መ. ጸጋ እንደ ሕይወት መመሪያ 

በጸጋ ሥር ለሆነ ክርስቲያን ማንኛውም የሕግ ጫና ተውግዶለታል (ዮሐ. 1፡16፥ 17፤ ሮሜ 6፡14፤ 7፡1-6፤ 2ኛ ቆሮ.3፡1-18፤ ገላ.3፡19-25፤ ኤፌ.2፡15፤ ቆላ. 2፡14)። 

1. የሙሴ ሥርዓት ክፍል የነበሩት የሕግ ትእዛዛትና የመንግሥቱ መተዳደሪያ የን ሕግጋት፥ አሁን የክርስቲያን መማሪያዎች እይደሉም። በአዲስ ጸጋ በተሟሉና ባሕርይን በሚቀርፁ መመሪያዎች ተተክተዋል። ይህ የጸጋ ሕግ በቀደመው ሕግ ውስጥ ያሉ ዋና ዋና ነገሮችን የራሱ በሆነ ልዩ ሥርዓትና ሁኔታ ሥር ያስቀምጣቸዋል። 

2. በጸጋ ሥር የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ክርስቲያን የሥራ ኪዳን ሕግ ስም ተወግዶለታል። አሁን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት እይጥርም። በክርስቶስ በኩል ተቀባይነትን እንዳገኘ ሰው ለመኖር ነጻ ነው (ኤፌ. 1፡6)። 

3. ክርስቲያን በሥጋው ብርታት እንዲኖር አይደለም የተጠራው። በውስጡ ሰሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይኖር ዘንድ እንዲህ ካለው የሕግ አሠራር ነጻ ወጥቷል። የሙሴ ሕግ የመጣው ለእስራኤል በመሆኑ፥ በክርስቶስ ሞት ከሕግ ትእዛዛት ነጻ የምትሆነውም እርሷ (እስራኤል) ብቻ ነበረች። ይሁን እንጂ፥ አይሁዳውያንም ሆኑ ሌሎች ሕዝቦች ተስፋ ቢስ ከሆነው ሰብአዊ የሥራ ሕግና ጥቅም የለሽ የሥጋ ጥረት በኢየሱስ ሞት አማካይነት ነጻ ወጥተዋል። 

4. ከሕግ ተቃራኒ፥ ጸጋ” የሚለው ቃል አንድ ሰው የማይገባውን ሞገስ ማግኘቱን ያመለክታል። ይህም ከአዳም ጀምሮ እግዚአብሔር ከሰው ልጆች ጋር ያካሂድ የነበረውን መለኮታዊ አሠራር ይወክላል። በጸጋ አሠራር እግዚአብሔር ሰዎችን የሚያስተናግዳቸው እንደየበደላቸው አይደለም። ዳሩ ግን መልካምነታቸውን ሳይመለከት ገደብ በሌለው ጸጋና ምሕረት ይቀርባቸዋል። እግዚአብሔር በኃጢአተኞች ላይ ቅድስናው የሚጠይቀውን ትክክለኛ ቅጣት ለመፈጸም ነጻ ነው። ነገር ግን ልጁ (ኢየሱስ ክርስቶስ) የኃጢአተኞችን ቅጣት ተሸክሞላቸዋል። 

የእስራኤል ሕዝቦች የእግዚአብሔርን ጸጋ በብዙ መንገዶች ቢለማመዱም፥ እንደ ሕይወት ሕግ ግን ከጻጋ ግንኙነት ወደ ሕግ ግንኙነት ተሸጋግረዋል። በዘጸአት 19፡3-25 እንደተገለጠው የእግዚአብሔርን ሕግ ሲቀበሉ፥ ጸጋ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት የማግኛ ብቸኛ መሠረት መሆኑን ባለማወቃቸው የእግዚአብሔርን ሕግ ለመጠበቅ እንደሚችሉ በሞኝነት ገምተው ነበር። እስራኤል በሕግ አሠራር ሥር ያሳለፈችው ገጠመኝ፥ በሕግ መመሪያነት ከኃጢአት ኃይል ለመላቀቅ የማይቻል መሆኑን ለሰዎች ሁሉ ያስገነዝባል። 

5. ከሕግ ሲነጻጸር፥ ጻጋ በሦስት የተለያዩ ገጽታዎች ይገለጣል። እነርሱም፡- (ሀ) በጸጋ መዳን፥ (ለ) በጸጋ መጠበቅና (ሐ) ከድነት በኋላ ጸጋን ለሕይወት መመሪያነት መጠቀም ናቸው። 

(ሀ) እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን በጸጋ ያድናል፤ ከዚህ ውጭ ለሰው ልጆች የተሰጠ የድነት መንገድ የለም (ሐዋ. 4፡12)። የድነት ጸጋ ወሰን የለውም። በክርስቶስ አማካይነት የሚያድነው ጸጋ በርሱ የመሥዋዕትነት ሞት የተገኘውን ጽድቅ ትክክለኛና የማይለወጡ ትእዛዛት በአግባቡ ለሚቀበሉ ኃጢአተኞች የሚሠራ የማይታቀብ የእግዚአብሔር ፍቅር ነው። ጸጋ ከፍቅር በላይ ነው፤ ይህም ፍቅር እግዚአብሔር በኃጢአተኛው ላይ የሚበይነውን የጽድቅ ፍርድ ወይም ቅጣት ድል ይነሣል። 

እግዚአብሔር አንድን ኃጢአተኛ ሰጻጋው በሚያድንበት ወቅት፥ ኃጢአትን ቸል በማለት ሳይሆን በመቅጣት ነው። ይህ ካልሆነ፥ ኃጢአቶቹ ፍርድን ስለሚያስከትሉ ለጸጋው እንቅፋት መሆናቸው አይቀሬ ነው። በመሆኑም በልጁ ሞት ለኃጢአት ሁሉ መፍትሔ ሰጥቷል። ከዚህም በላይ፥ ለድነት የሚጠየቅ ማንኛውም ግዴታ መወገዱ ግድ አስፈላጊ ነበር። በዚህም መሠረት ድነት ፍጹም የእግዚአብሔር ስጦታ ሆኖ ለሰው ልጆች ቀርቧል (ዮሐ. 10፡28፤ ሮሜ 6፡23፤ ኤፌ. 2፡8)። በተመሳሳይ ሁኔታ፥ ማንኛውም ለድነት የሚደረግ ሰብአዊ ጥረት መተው አለበት። ምክንያቱም እግዚአብሔር የሚያከናውነው ተግባር በምንም ዓይነት በሰዎች ሰናይ ምግባር ላይ ሊመሠረት የማይገባ እና መሠረቱ ሉዓላዊ ጸጋው ብቻ መሆኑ እንዲረጋገጥ ነው (ሮሜ 3፡9፤ 11፡32፤ ገላ. 3፡22)። ማንኛውም ሰብአዊ ነገር ከግንዛቤ የማይገባ ሲሆን፥ የጸጋ ወንጌል ግን ለሚያምኑ ሁሉ ዘላለማዊ ሕይወትና ዘላለማዊ ክብር የሚሰጥ፥ ታላቅ፥ ነጻ አውጪና የሚለውጥ የእግዚአብሔር ጸጋ አዋጅ ነው። 

(ለ) በጸጋ አማካኝነት የመጠበቁ መለኮታዊ ዕቅድ የሚያመለክተው፥ እግዚአብሔር የዳኑትን ሰዎች በጻጋ ብቻ የሚጠብቃቸው መሆኑን ነው። እግዚአብሔር ጽድቁ ከኃጢአት ከሚፈልጋቸው ነገሮች ነጻ ሆኖ የሚሠራበትን መንገድ ካቀረበ፥ ከሰው ልጆች የሚጠበቀውን ዋጋ ካስወገደና እያንዳንዱን ሰብአዊ ምግባር ለዘላለሙ ካራቀ በኋላ የሚያከናውነው ነገር፥ የዳነው ሰው ጸጋን እየተለማመደ ለዘላለሙ ተጠብቆና ዋስትናን ተጎናጽፎ እንዲኖር ማድረግ ነው። እግዚአብሔር ይህን ሲያደርግ፥ አማኝ በጸጋ ይቆማል (ሮሜ 5፡2፤ 1ኛ ጴጥ. 5፡12)። 

(ሐ) ይህ ብቻም አይደል፥ እግዚአብሔር በጸጋ መርህ ላይ በመመሥረት ላዳኑ ሰዎች የሕይወትን መመሪያ ይሰጣል። የዳኑና የተጠበቁ ሰዎች እንዴት በጸጋ ሊኖሩ እንደሚገባና በዘላለማዊ ክብሩ እንዴት ሊመላለሱ እንደሚገባ ያስተምራቸዋል። ሕግ ለእስራኤላውያን ሙሉ የሥነ-ምግባር መመሪያ ሆኖ እንደሰጣቸው ሁሉ፥ እግዚአብሔርም ለክርስቲያኑ ሙሉ የሥነ-ምግባር መመሪያ ሰጥቷል። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የቀረሱት የጸጋና የሕግ መመሪያዎች በራሳቸው ምሉአን ስለሆኑ አንዱን ከሌላው ማጣመሩ አስፈላጊ አይደለም። ስለሆነም፥ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው ከሕይወት መመሪያነት አንጻር ከሕግ በታች ሳይሆን፥ ከጻጋ መመሪያ ሥር ነው። ከጸጋ ሥር ሆኖ የሚሠራው ነገር፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ በጎ ነገርን እንዲያገኝ ሳይሆን፥ አፍቃሪው እግዚአብሔር ቀደም ብሎ ስለተቀበለው ብቻ የሚያደርገው ነው። ይህም በሥጋ ጉልበት የሚካሄድ ሳይሆን አማኙ ውስጥ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ኃይል መገለጫና ተግባራዊ አኗኗር ነው። የዚህ ዓይነቱ ሕይወት “ጻድቅ በእምነቱ በሕይወት ይኖራል” በሚለው የእምነት መርሕ ላይ የተመረኮዘ ነው። እነዚህ መመሪያዎች በወንጌላትና በመልእክቶች ውስጥ ተገልጠው ይገኛሉ። 

ሠ. ብቸኛው የድል መንገድ 

ክርስቲያን ከኃጢአት ኃይል ነጻ የሚወጣበትን መንገድ ለማሳየት የሚጥሩ ብዙ ትምህርቶች ቀርበዋል። 

1. ክርስቲያን በቂ ደንቦችን ከጠበቀ ለእግዚአብሔር ክብር ለመኖር ይገደዳል ተብሏል። ይህ የሕግ መመሪያ ሊላቀቁት በሚገባ ኃጢአተኛ ሥጋ ላይ የሚታመን በመሆኑ፥ ለውድቀት የተዳረገ ነው (ሮሜ 6፡14)። 

2. ክርስቲያን የአሮጌውን ባሕርይ ጨርሶ ለማጥፋት በመምከር ለዘለቄታው ከኃጢአት ኃይል ሊሳቀቅ ይችላል የሚል ትምህርት አለ። ይህን ንድፈ-አሳብ የሚቃወሙ ወገኖች ሲኖሩ ምክንያታቸውን እንደሚከተለው ያቀርባሉ። 

(ሀ) አሮጌውን ባሕርይ ጭራሽ የማጥፋት ንድፈ-አሳብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የለውም። 

(ለ) አሮጌው ባሕርይ የሥጋ አንድ አካል በመሆኑ፥ ሥጋ ከክርስቲያን ኃያላን ጠላቶች አንዱ ነው። ክርስቲያንን ዓለም፥ ሥጋና ሰይጣን ይፈታተኑታል። እግዚአብሔር ደግሞ ክርስቲያን በነርሱ ላይ ድል እንዲያገኝ መንፈሱን ይሰጠዋል እንጂ፥ ዓለምን፥ ሥጋን ወይም ሰይጣንን አያጠፋቸውም (ገላ. 5፡16፤ 1ኛ ዮሐ. 4፡4፤ 5፡4)። በአሮጌው ተፈጥሮ ላይ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ድልን ይሰጣል (ሮሜ 6፡14፤ 8፡2)። 

(ሐ) የአሮጌው ባሕርይ መጥፋት ንድፈ-አሳብ በእውነተኛ የሰው ልጅ ገጠመኝ አይደገፍም። ይህ ንድፈ-አሳብ እውነት ሲሆን ኑሮ፥ ይህን ዓይነቱን ሕይወት የኖሩ ወላጆች በኃጢአት ያልወደቁ ልጆች በወለዱ ነበር። 

(መ) በተመሳሳይ ሁኔታ፥ ይህን ንድፈ-አሳብ ከተቀበልን፥ ውስጣችን የሚኖረው መንፈስ ቅዱስም ሆነ የሚሰጠን አገልግሎት ትርጉም ያጣል። ይሁንና፥ እጅግ መንፈሳዊ የሆኑ ክርስቲያኖች እንኳ በመንፈስ በመመላለሱ፥ በእምነት፥ በመሰጠት፥ ኃጢአት እንዳያነግሥ በመከላከሉ፥ በማስወገዱ፥ በጭምትነትና በጽናት በመኖሩ አስፈላጊነት ላይ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። 

3. አንዳንድ ክርስቲያኖች በመዳናቸው ብቻ ከመንፈስ ቅዱስ ርዳታ ውጭ ከእግዚአብሔር ክብር ሊኖሩ እንደሚችሉ ያስባሉ። ሮሜ 7፡15-8፡4 ውስጥ ሐዋርያው ከዚህ ንድፈ-አሳብ ጋር የነበረውን ገጠመኝ ይገልጣል። መልካም የሆነውን እንደሚያውቅና ዳሩ ግን የሚያውቀውን እንዴት እንደሚፈጽም አለማወቁን ይናገራል (7 ፡18)። ስለሆነም ከሚከተለው መደምደሚያ ላይ ደርሷል፤ (ሀ) ሰብልቶች ውስጥ ለአፍታም የማይለየው የኃጢአት ሕግ በመኖሩ ምክንያት፥ ከሁሉም የላቀ ጥረት ቢያደርግም እንኳን ሁልጊዜ ይሸነፋል (7፡23)፤ (ለ) እንዲህ ባለ ሁኔታ ላይ መገኘት ጎስቋላነት ነው (7፡24)፤ (ሐ) ድነትን ቢያገኝም፥ ነጻ ያወጣው የራሱ ሥራ ሳይሆን፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ነበር (8፡2)፣ (መ) የእግዚአብሔር ሙሉ ፈቃድ በአማኙ እማካኝነት ሳይሆን፥ በአማኙ ውስጥ ተፈጽሟል (8፡4)። 

ከኃጢአት ኃይል ነጻ መውጣት የሚቻለው በኢየሱስ በኩል ነው። ከኃጢአት ነጻ መሆን ከእግዚአብሔር ጽድቅ ጋር የተያያዘ ስለሆነ፥ ነጻነት ሊመጣ የሚችለው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ነው። መንፈስ ቅዱስ እማኝ ባልሆነ ሰው ሕይወት ያላን በኃጢአት የወደቀ ባሕርይ ሊቆጣጠር አይችልም። ዳሩ ግን የክርስቲያኑ በኃጢአት የወደቀ ባሕርይ ከክርስቶስ ጋር በመሰቀሉ፥ በመሞቱና በመቀበሩ የተፈረደበት መሆኑ ሮሜ 6፡1-10 ውስጥ ተገልጧል። ይህም በአማኙ ውስጥ የሚያድረው መንፈስ ቅዱስ የመኖሪያ ስፍራ ሰማግኘት ሥን ምግባራዊ ድልን እንዲሰጠው ያደርጋል። የእነዚህ ሁኔታዎች መሟላት፥ አማኙ በአዲሱ የሕይወት መመሪያ እንዲመላለስ ይረዳዋል። ይኸውም ራሱን ለኃጢአት እንደሞተ ቆጥሮ (6፡4፥ 11)፥ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ብቻ በሚደገፍ መመሪያ መመላለስ መቻሉ ነው። ስለሆነም፥ ከኃጢአት ኃይል ነጻ መውጣት የሚቻለው፥ በክርስቶስ በኩል ነው። 

ረ. ድል በመንፈስ ቅዱስ 

ቀደም ሲል በመንፈስ ቅዱስ አስተምህሮ ጥናቶች ውስጥ እንደተመለከተው፥ አንድ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ከኃጢአት ኃይል ነጻ ሊወጣ ይችላል። በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ” (ገላ. 5፡16)። ከኃጢአት ኃይል መዳን፥ ከእግዚአብሔር ሲሆን፤ ከሰው የሚጠበቀው የእምነት ቁርጠኛ አቋም ነው። እንዲሁም ከኃጢአት ቅጣት ድነትን ማግኘት ከእግዚአብሔር ሲሆን፥ የሰውን የእምነት እርምጃ ያመለክታል። ጻድቅ በእምነት ይኖራል። ይህ እምነት በእግዚአብሔር ኃይል ላይ የሚደገፍ ነው። ጻድቅ በምድራዊ ሕይወቱ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ሙሉ ለሙሉ ከመደገፍ የሚቆጠብበት ጊዜ ከቶውንም አይኖርም። 

አማኝ መንፈስ ቅዱስ ላይ መደገፍ የሚኖርበት ሦስት ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው። 

1. አማኝ በጸጋ ትምህርቶች ሥር ሆኖ፥ ከማይሞከሩ ሰማያዊ የሕይወት መመዘኛዎች ጋር ይጋፈጣል። ሰማያዊ ዜጋ (ፊልጵ. 3፡20)። የክርስቶስ አካል ብልት (ኤፌ. 5፡30)፥ እና የእግዚአብሔር ቤተሰብ በመሆኑ (ኤፌ. 2፡19፣ 3፡15)፥ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው ከተሰጠው ሰማያዊ ስፍራው አንጻር እንዲመላለስ ተጠርቷል። ይህ ከሰብአዊነት የላቀ አኗኗር በመሆኑ (ዮሐ. 13፡34፤ 2ኛ ቆሮ. 10፡5፤ ኤፌ.4፡1-3፥ 30፤ 5፡20፤ 1ኛ ተሰ. 5፡16-17፤ 1ኛ ጴጥ.2፡9) ክርስቲያን በውስጡ ሳደረው መንፈስ ቅዱስ ላይ መደገፍ የግድ ይሆንበታል (ሮሜ 8፡4)። 

2. ክርስቲያን ዓለምን ከሚገዛው ጠላት፥ ከሰይጣን ጋር ይጋፈጣል። ስለሆነም፥ በጌታ የበረታ ሊሆን ይገባዋል (ኤፌ. 6፡10-12፤ 1ኛ ዮሐ. 4፡4፤ ይሁዳ 9)። 

3. ክርስቲያን ሊቆጣጠረው የማይቻለው አሮጌ ባሕርይ እውስጡ ይዟል። 

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚገልጠው፥ እግዚአብሔር ከኃጢአት በደል ብቻ ሳይሆን፥ ከኃጢአት ኃያልም ያድናል። በመጨረሻም ክርስቲያን ምሉእ ሆኖ በመንግሥተ ሰማይ ሲቆም ኃጢአት ክርሱ ይለያል።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

30
ትምህርት 30 ከ52

የጽድቅ አራት ገጽታዎች

መጽሐፍ ቅዱስ አጽንኦት ሰጥቶ እንደሚያመለክተው፥ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል የሚገኘው ዋነኛ ልዩነት እግዚእብሔር ጻድቅ ሲሆን (1ኛ ዮሐ. 1፡5)፥ ሰው ግን ሮሜ 3፡10 ውስጥ “ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ” የሚል መሠረታዊ ክስ የቀረበበት ነው። ከመለኮታዊ ጸጋ ክብሮች አንዱ በሆነውና እንከን በሌለው የሠርግ ልብስ የተመሰለው ፍጹም መለኮታዊ ጸጋ መሰጠቱና ለሚያምኑ ሁሉ በነጻ መታደሱም ተገልጧል (ሮሜ 3፡22)። 

መጽሐፍ ቅዱስ አራት የጽድቅ ገጽታዎችን ያቀርባል። 

ሀ. እግዚአብሔር ጻድቅ ነው 

ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ የማይለወጥና ሊለወጥ የማይችል ነው (ሮሜ 3፡25 26)። እግዚአብሔር በእርሱነቱና በአደራረጉ ሁሉ የማይወሰንና ፍጹም ጻድቅ ነው። 

እግዚአብሔር ሰኑባሬው ጻድቅ ነው። በእርሱ ዘንድ “በመዞር እንደተደረገ ጥላ” (ያዕ. 1፡1 ፥ ከገዛ ጽድቁ የማፈንገጥ ሁኔታ አይከሰትም። በምንም ሁኔታ ኃጢአትን አያናንቅም። ስለሆነም፥ ሰዎች በተፈጥሮም ሆነ በድርጊት ኃጢአተኞች በመሆናቸው፥ መለኮታዊ ፍርድ በሰዎች ሁሉ ላይ ወርዷል። የወንጌሉን መለኮታዊ ጸጋ በትክክል ለመገንዘብ ይህን እውነት መቀበሉ ወሳኝ ነው። 

እግዚአብሔር በሚያደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ጻድቅ ነው። ኃጢአትን የማሣነስ ወይም በግድ የለሽነት የማለፍ ችሎታ እንደሌለው መረዳትም ያስፈልጋል። ወንጌሉ ድል የሚነሣው እግዚአብሔር ኃጢአትን ስለሚያሳንስ አይደለም፤ ይልቁንም፥ በማይወሰን ጽድቁ በኃጢአተኛው ላይ የሚያስከትላቸውን ፍርዶች ሁሉ እርሱ ያዘጋጀው በግ በምትክነት ስለተሸከመ ነው። ይህም እግዚአብሔር በራሱ የጽድቅ መመዘኛ መሠረትነት ያቀደውና ለሚያምኑ ሁሉ የሚበቃ ነው። በዚህ ዕቅድ መሠረት እግዚአብሔር ሊለውጥ የማይችል ጽድቁን ሳይሽር፥ ኃጢአተኛውን ሰማዳን ፍቅሩን ሊያረካ ይችላል። ምንም ተስፋ የሌለው ኃጢአተኛም ከኩነኔ ሁሉ ይድናል (ዮሐ. 3፡18፤ 5፡24፤ ሮሜ 8፡1፤ 1ኛ ቆሮ. 11፡32)። 

ሰዎች እግዚአብሔርን እንደ ጻድቅ መገንዘባቸው እንግዳ ነገር አይደለም። ኃጢአተኛውን ለማዳን በሚወስደው እርምጃ የእግዚአብሔር ጽድቅ እንደማይጠፋና ሊጠፋም እንደማይችል መረዳቱ ግን ይሳናቸዋል። 

ለ. የሰው ጽድቅ 

የእግዚአብሔርን ፍጹም ጻድቅነት ከሚያሳየው መገለጥ ጋር አብሮ የሚሄድ ሌላ መገለጥም አለ። ይኸውም በእግዚአብሔር ፊት የሰው ጽድቅ (ሮሜ 10፡3) እንደ “መርገም ጨርቅ” መሆኑ ነው (ኢሳ. 64፡6)። የሰው ኃጢአተኛነት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባለማቋረጥ የታወጀ ቢሆንም፡ሮሜ 3፡9-18 ውስጥ የተባለውን ያህል የተሟላና ማጠቃለያ ጎላጣ ሰየትኛውም ክፍል አይገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተመዘገቡት ሌሎች የኃጢአት እይታዎች ሁሉ፥ ይህም ከእግዚአብሔር እይታ አንጻር የቀረበ የኃጢአት ገለጣ መሆኑን መገንዘቡ ተገቢ ነው። ሰዎች ለቤተሰብ፥ ለማኅበረሰብና ለመንግሥት ሕጋዊ መመዘኛዎችን ፈጥረዋል። ዳሩ ግን እነዚህ መመዘኛዎች ሰው የሚመራባቸውና በእግዚአብሔር ፊት ፍርድ የሚቀበልሳቸው መሠረቶች አይደሉም። ከእግዚአብሔር ጋር ያለ ግንኙነትን በተመለከተ ራስን ከሌላ ጋር አወዳድሮ የተሻልኩ ነኝ ብሎ ማሰብ ተገቢ አይደለም (2ኛ ቆሮ. 10፡12)። ሰዎች ድነትን በማጣት የሚጠፉት በማኅበረሰቡ ስለተኮነኑ ሳይሆን፥ በማይሻረው የእግዚአብሔር ጽድቅ በመኮነናቸው ነው (ሮሜ 3፡23)። ስለሆነም፥ ከእግዚአብሔር የጸጋ ልግስና ውጭ የትኛውም ግለሰብ ተስፋ የለውም። ስለዚህ እግዚአብሔር ክርስቶስን እንደተቀበለ የማይቀበለው ማንም ሰው ወደ መንግሥተ ሰማያት ክብር ሊገባ አይችልም። ለዚህ የሰው ጉድለት እግዚአብሔር የተትረፈረፈ ስጦታ አዘጋጅቷል። 

ሐ. የተላለፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ 

ቀደም ሲል ምዕራፍ 26 እና 27 ውዕዋ ስለ “መተሳለፍ” ባጠናነው አስተምህሮ እንደተገለጠው፥ እግዚአብሔር ኃጢአተኛውን የሚኮንንባቸውንና አማኙን የሚያድን ባቸውን መርሆዎች ለመረዳት፥ እርሱ ለሰዎች የሚቆጥረውን በውርስ የሚገኝ ጽድቅ ጠቃሚ መገለጥ መገንዘቡ ወሳኝ ነው (ሮሜ 3፡22)። ምንም እንኳ አስተምህሮውን መረዳቱ አስቸጋሪ ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር መገለጥ አቢይ ገጽታነቱን መረዳት ጠቃሚ ነው። 

1. የመተላለፉ” እውነታ የተከስተው፥ የአዳም ኃጢአት ለሰው ዘር ሁሉ በውርስ ስመተላለፉ ነው። በውጤቱም ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ኃጢአተኞች ተቆጥረዋል (ሮሜ 5፡12-21)። ይህ እውነት ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ የኃጢአት መሥዋዕት በሆነ ጊዜ የሰው ኃጢአት ወደ እርሱ እንደተላለፈ ያመለክታል (2ኛ ቆሮ. 5፡14፥ 21፤ ዕብ. 2፡9፤ 1ኛ ዮሐ. 2፡2)። እንደዚሁም፥ የሚያምኑ ሁሉ በክርስቶስ ፍጹምነት በእግዚአብሔር ፊት ይቆሙ ዘንድ የርሱ ጽድቅ ተላልፎላቸዋል። በዚህ መለኮታዊ ልግስና የዳኑ ሰዎች የእግዚአብሔር ጽድቅ ይሆንላቸው፥ ይኸውም በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ፍጹምነት ለመቆም ይችሉ ዘንድ ነው። በዚህ መለኮታዊ ችሮታ የዳኑ ሰዎች የእግዚአብሔር ጽድቅ እንደ ተደረጉቃ ተገልጧል (1ኛ ቆሮ. 1፡30፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡21)። ጽድቅ የእግዚአብሔር እንጂ የሰው ባለመሆኑና ከማንኛውም የራስ ሥራ፥ ወይም ሕግን የመጠበቅ ተግባር ውጭ እንደሆነ መገለጡ (ሮሜ 3፡21)፥ ለሰዎች የሚቆጠረው ጽድቅ በእነርሱ ያልተፈጸመ መሆኑን ግልጥ ያደርገዋል። የእግዚአብሔር ጽድቅ ስለሆነ በተሰጠው ስው ጥሩነት አይጨምርም፤ ወይም ከመጥፎነቱ አይቀንስም። 

2. የመተሳሰፉ” ውጤቶች የሚታዩት ታማኙ በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካኝነት ክርስቶስ ውስጥ እንዳለ በመቆጠሩ ነው። በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ከክርስቶስ ጋር በሚደረግ ዋነኛ ጥምረት፥ አማኙ የክርስቶስ አካል አንድ ክፍል እና በወይን ግንድ እንዳለ ቅርንጫፍም ይሆናል (1ኛ ቆሮ. 12፡13 ዮሐ. 15፡1፥ 5)። ክዚህ የጥምረት እውነት የተነሣ፥ እግዚአብሔር አማኙን እንደ ልጁ ሕያው አካል ይመለከተዋል። ልጁን እንደሚወደውም ይወደዋል (ዮሐ. 17፡23)፤ ልጁኝ እንደሚቀበል ይቀበለዋል (ኤፌ. 1፡6፤ 1ኛ ጴጥ. 2፡5)፤ እንደ ልጁም በመቁጠር እንደ እግዚአብሔር ጽድቅ ያየዋል (ሮሜ 3፡22፤ 1ኛ ቆሮ. 1፡30፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡21)። ክርስቶስ የእግዚአብሔር ጽድቅ እንደመሆኑ፥ የዳኑ ሰዎች በእርሱ ውስጥ በመሆን የእግዚአብሔር ጽድቅ ተደርገዋል (2ኛ ቆሮ. 5፡21)። በእርሱ ሙሉ ናቸው (ቆላ. 2፡10)፤ ለዘላለምም ፍጹም ተደርገዋል (ዕብ. 10፡10፥ 14)። 

3. መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “መተላለፍን” የሚመለከቱ ብዙ ማብራሪያዎች አሉ። እግዚአብሔር ደም በማፍሰስ በመለኮታዊ ልግስናው ለአዳምና ሔዋን የቁርበት ልብስ አልብሷቸዋል (ዘፍጥ. 3፡21)። እብርሃም እግዚአብሔርን በማመኑ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት (ዘፍጥ. 15፡6፤ ሮሜ 4፡9-22፤ ያዕ. 2፡23)። የብሉይ ኪዳን ካህናት ጽድቅ እንደተላበሱ ሁሉ (መዝ. 132፡9)። አማኝም የእግዚአብሔርን ጽድቅ ተጎናጽፏል፤ በክብር የሚገለጠውም ይህንኑ መጎናጸፊያ ደርቦ ነው(ራእይ 19፡8)። 

ሐዋርያው ጳውሎስ ላፌልሞና የነበረው አመለካከት በውርስ የተገኘን መልካም ሥራ እና በውርስ የተገኘን መልካም ያልሆነ ሥራን የሚያመለክት ነበር። ሐዋርያው ባሪያ ስለነበረው አናሲሞስ ሲናገር፥ “እንግዲህ እንደ ባልንጀራ ብትቆጥረኝ፥ እንደ እኔ አድርገህ ተቀበለው [መልካም ሥራን መቁጠር]። በአንዳች ነገር የበደለህ ቢኖር ግን ወይም ብድር ያለበት እንደሆነ፥ ይህን በእኔ ላይ ቁጠር የመልካም ያልሆነ ሥራን መቁጠር” (ፊል. 17-18፤ በተጨማሪም ኢዮብ 29፡14፤ ኢሳ. 11፡5፤ 59፡17፤ 61፡1ዕ ይመልከቱ)። 

4. የጽድቅ መተላለፍ” የፅግዚአብሔር ልጅ ያደርገናል እንጂ፥ ሰዕለት ኦሮችን ኃጢያትን ከመሥራት ነጻ መውጣታችንን አያሳይም። ከሰብአዊ ሥራዎች ሁሉ ሳሻገር፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሚቆጠር የእግዚአብሔር ጽድቅ አለ። ያም በሚያምኑት ሁሉና ለነርሱ የሚሆን ነው (ሮሜ 3፡22)። ያመኑ ሰዎች በዕለታዊ ሕይወታቸው ወይም ሁኔታቸው ገና ከፍጹምነት ደረጃ አልደረሱም። ስለሆነም፥ በዚሁ ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት “በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት ማደግ” ይኖርባቸዋል (2ኛ ጴጥ. 3፡18)። 

3, ብመተላለፍየሚገኝ የእግዚአብሔር ጽድቅ ኃጢአተኛን ለሚያጸድቅ ፍርድ መሠረት ነው። እግዚአብሔር በክርስቶስ ውስጥ የሚያየውን ሰው ለዘላለም የጻደቀ መሆኑን ያውጃል። ስለዚህ የአንድ ሰው ጻድቅ መሆን በእግዚአብሔር አሳብ የጸናና ግልጥ ነው። የእግዚአብሔር ጽድቅ ወደ ሰው እንደሚተላለፍ፥ ጽድቅም በእምነት (ሮሜ 5፡1) እና በጸጋ አማካኝነት (ቲቶ 3፡4-7) በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ በኩል የሚገኝ ነው (ሮሜ 3፡24፤ 4፡25)። በዘላለማዊው የእግዚአብሔር ልጅ ምግባር ላይ ስለተመሠረተ የማይለወጥና ዘላለማዊ ነው። 

መጽደቅ ከይቅርታ ይበልጣል። ይቅርታ የኃጢአት መሰረዝ ሲሆን፥ መጽደቅ ግን ቅድስናን ከጌታ መቀበል ነው። ይቅርታ (የኩነኔን መወገድ የሚያመለክት) አሉታዊ ፅንሰ-ሃሳብ ሲሆን፥ ጽድቅ (የክርስቶስን ምግባርና ደረጃ የሚያሳይ) አዎንታዊ አሳብ ነው። 

ያዕቆብ በሥራ ዕላ መጽደቅ የጻፈው (2፡14-26) የአማኙን ደረጃ ከሰዎች አንጻር እየተመለከተ ሲሆን፥ ጳውሎስ በእምነት ስለመጽደቅ የጻፈው (ሮሜ 5፡1) ግን የአማኙን ደረጃ ከእግዚአብሔር አንጻር በመመልከት ነበር። 

እብርሃም እምነቱን በሥራ ስላረጋገጠ በሰዎች ፊት ጸድቋል (ያዕ. 2፡2 1 )። በተመሳሳይ ሁኔታ በተቆጠረለት ጽድቅ አማካይነት በእግዚአብሔር ፊት በእምነት ጸድቋል (ያዕ. 2፡23)። 

መ. በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የተሰጠ ጽድቅ 

የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው በመንፈስ ቅዱስ በሚሞላበት ጊዜ “የመንፈስ ፍሬ”ን (ገላ. 5፡22-23) ሰጽድቅ ሥራዎች (ሮሜ 8፡4) ያከናውናል። በመንፈስ ቅዱስ አማካይነትም የአገልግሎት ስጦታዎች ይታዩበታል (1ኛ ቆሮ. 12፡7)። እነዚህ ውጤቶች የሚገኙት መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ውስጥና በአማኙ አማካይነት ከሚፈጽማቸው ቅፅበታዊ ክንውኖች መሆኑ ተገልጧል። እንድ አማኝ ሰላለው ሕይወት ስንነጋገር ጌታ መንፈስ ቅዱስ በሕይወቱ ውስጥ የሚሠራውን ሥራ ማመልከታችን ነው። “በሥጋ ሳይሆን በመንፈስ ሰሚመላለሱ፥ የጽድቅ ሕግ በነሱ ይፈጸማል። 

በነርሱ ብቻ ከቶውንም ተፈጻሚነትን ሊያገኝ የሚችል አልነበረም። በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በሕይወታቸው ተፈጻሚነትን ሲያገኝ ግን፥ ወደነርሱ የተላለፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ሕይወት እንጂ ሌላ ሊሆን እንደማይችል ቃልጥ ነው።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

31
ትምህርት 31 ከ52

ቅድስና

ሀ. የትክክለኛ አተረጓጎም አስፈላጊነት 

ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ አስፈላጊ ጭብጥ ላይ ጥልቅ መገለጥ ቢያቀርብም፥ ሰዎች የቅድስናን አስተምህሮ በተሳሳተ መንገድ ይረዱታል። ከዚህ የአስተምህሮ ታሪክ አንጻር፥ ሦስት የአተረጓጎም ሕጎችን ልብ ማለቱ ተገቢ ነው። 

የመቀደስን አስተምህሮ በትክክል ለመረዳት፥ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህን በተመለከተ የተወቀሱ ክፍሎችን ሁሉ መመልከት ያሻል። 

2. የቅድስና አስተምህሮ ስልምድ ሊለጥ እይችልም። ከቅድስና አስተምህሮ ሦስት የቅድስና ገጽታዎች ትምህርት አንዱ ብቻ ነው ከሰው ዕለታዊ ሕይወት ጋር የሚዛመደው። ስለሆነም የአንድ ዓይነት የግል ልምምድ ትንታኔ የእግዚአብሔር ቃል የሚሰጠውን ትምህርት ሊተካ አይገባም። መቀደስ በሰብአዊ ልምምድ መስክ የተወሰነ ቢሆንም፥ ፍጹም ምሳሌው መሆኑን ሊያረጋግጥ የሚችል አገልግሎት አይኖርም። ወይም ስለዚያ ልምምድ የሚሰጥ ሰብአዊ ገለጣ መለኮታዊ እውነትን በሙላት ሊገልጥ አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስ ልምምድኝ ይተረጉመዋል እንጂ ልምምድ መጽሐፍ ቅዱስን አይተረጉመውም። የትኛውም ከእግዚአብሔር የሆነ ልምምድ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይስማማል። 

3. የቅድሰና አስተምህሮ ከሁሉም የመጽሐፉ ቅዱሰ አሰተምህሮ ጋር በትክክል መዛመድ አለበት። በየትኛውም አንድ አስተምህሮ ላይ ከመጠን ያለፈ ትኩረት ማድረግ፥ ወይም እውነትን ሁሉ በአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት መስመር የመመልከት ልማድ፥ ወደ ክፋ ስሕተት ይመራል። እንደ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮዎች ሁሉ፥ የቅድስና ትምህርት የሚወከለውና የሚያብራራው በእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ የተወሰነውን ትክክለኛ ሰፍራ ነው። 

ለ. የቅድስና ትርጉም 

1. የመቀደስ” ማለት “መለየት” ወይም የተለዩ መሆን ማለት ነው። በስፍራና በግንኙነት ክፍፍል ማድረግን ነው ቃሉ የሚያመላከተው። የክፍፍሉ መሠረት የተለየው ሰው ወይም ነገር ቅድስና ከሌላቸው ነገሮች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በስፍራና በግንኙነት የሚለይ መሆኑ ነው። ይህ ነው የቃሉ አጠቃሳይ ትርጉም። 

2. ቅዱስ” የሚለው ቃል: ቅዱስ ካልን ነገር መራቅን፥ ወይም መለየትን ያመለክታል። ክርስቶስ፥ “ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ…” (ዕብ. 7፡26) ቅዱስ ነበር። “ቅዱስ” እና “መቀደስ” የሚሉና በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አጠቃቀማቸው ይህን ትርጉም የማያመለክቱ ነገሮችም አሉ። 

(ሀ) መጽሐፍ ቅዱስ “ቅድስት አገር”፥ “ቅዱሳን ካህናት”፥ “ቅዱሳን ነቢያት”፥ “ቅዱሳን ሐዋርያት”፥ “ቅዱሳን ወንዶች”፥ cቅዱሳን ሴቶች”፥ “ቅዱሳን ተራሮች” እና የ“ቅዱስ ቤተ መቅደስ” እያለ ስለሚገልጥ፥ ኃጢአት አልባ ቅዱስነት አንድምታ አልተሰጠውም። ከነዚህ የትኛውም ቢሆን በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት እልሳ አይደለም። ሰዎች ወይም ነገሮች ቅዱሳን ተብለው የሚጠሩት ከሌሎች ለመለየታቸው መሠረት ከጣሉላቸው አንዳንድ መመዘኛዎች ወይም ጉዳዮች አንጻር ነው። እጅግ በከፋ ጥፋት ውስጥ የነበሩ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችም ቅዱሳን ተብለዋል። ከኃጢአት ጋር ሊዛመዱ የማይችሉ አያሌ ግዑዛን ነገሮች እንኳን ተቀድሰዋል። 

(ለ) ቃሉ የግድ የፍጻሜን እንድምታ አያሳይም። ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ሰዎች ሁሉ ከፍተኛ ለሆነ የቅድስና ደረጃ ተጠርተው ነበር። በተደጋጋሚ ተለያተዋል። ሰዎች ወይም ነገሮች ለእንድ የተቀደሰ ዓሳማ ሲለዩ ቅዱሳን ይሆናሉ፤ ደግሞም ይቀደሳሉ። 

3. ቅዱስ” የሚለው ቃል ሰዎችን በተመለከተ እግዚአብሔር ለነሱ ካለው አመለካከት የተነሣ የሚያግኙት ስፍራ ነው። ቃሉ በምንም ዓይነት ከራሳቸው ዕለታዊ የሕይወት ጥረት ጋር የተያያዘ አይደለም። ቅዱሳን የሆኑት በተወሰነ ሁኔታ ስለተመደቡና በእግዚአብሔር ዕቅድና ዓላማ ስለተለዩ ነው። ማለትም፥ ስለተቀደሱ ቅዱሳን ናቸው። 

አማኞች ሮሜ 1፡7 እና 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡2 ውስጥ “ቅዱሳን ልትሆኑ” ወይም “ቅዱሳን” በግሪኩ አጠቃቀም “ቅዱስ” ተብላችሁ ተጠራችሁ ተብለዋል። ስለዚህ ክርስቲያኖች አሁን በእግዚአብሔር ሰለተጠሩ ቅዱሳን ናቸው። ወደፊት ቅዱሳን የሚያ ኑበትን ጊዜ አይደላም ቃሉ የሚያመለክተው። ቀደም ሲል ተቀድሰዋል፥ ተለይተዋል፥ ተመድበዋል፥ ስለሆነም፥ «፡ቅዱሳን ወንድሞች” ናቸው። 

ቅዱስነት በዕድገት የሚመጣ ነገር አይደለም። ማንኛውም ዳግም የተወለደ ሰው ድነትን ከተቀበለበት ቅፅበት ጀምሮ፥ በዚህ ዘመንም ሆነ በዘላለም ሕይወት ሊሆን የሚችለውን ያህል ቅዱስ ነው። የክርስቶስ አካል የሆነችው ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን ተጠርተው የመጡና የተለዩ ሕዝቦች የሚገኙባት ነች። እነዚህ ሕዝቦች የዚህ ሥፍራ-ዘመን ቅዱሳን ናቸው። ብዙ ክርስቲያኖች በክርስቶስ ያላቸውን ስፍራ ስለማያውቁ፥ ቅዱሳን መሆናቸውን አያምኑም። መንፈስ ቅዱስ ለአማኞች “ቅዱሳን” የሚለውን ማዕረግ በርከት ባለ ስፍራ ለአማኞች ሲሰጥ፥ በተጨማሪም በብዙ ስፍራ “ወንድሞች”፥ ሰጥቂት ስፍራ ደግሞ ክርስቲያኖች ተብለዋል። 

ሐ. የቅድስና መንገድ 

1. ለዘላለም ጻድቅ ከመሆኑ የተነሣ እግዚአብሔር አብ፥ ወልድ፥ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ የተቀደሰ)፥ ከኃጢአት የራቀና የተለየ ነው። ስለሆነም፥ እግዚአብሔር ቅዱስ፥ መንፈስ ቅዱስ ስሙ እኝደሚያመለክተው ቅዱስ ነው (ዘሌ . 21፡8፤ ዮሐ. 17፡18)። 

2. እብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ፥ አንድ አምላክ፥ ሰዎችን እንደሚቀድስ ተገልጧል። 

(ሀ) አብ ይቀድሳል (1ኛ ተሰ. 5፡23)። 

(ለ) ወልድ ይቀድሳል (ኤፌ. 5፡26፤ ዕብ. 2፡11፤ 9፡12፥ 14፤ 13፡12)። 

(ሐ) መንፈስ ቅዱስ ይቀድሳል (ሮሜ 15፡16፤ 2ኛ ተሰ. 2፡13)። 

(መ) እግዚአብሔር አብ ወልድን ቀድሶታል (ዮሐ. 10፡36)። 

(ሠ) እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብና ካህናትን ቀድሷል (ዘዳ. 29፡44፤ 31 ፡13)። 

(ረ) መቀደሳችን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው (1ኛ ተሰ. 4፡3)። 

(ሰ) እግዚእብሔር የቀደሰን፥ ከክርስቶስ ጋር ባለን ጥምረት (1ኛ ቆሮ. 1፡2፥ 30)፥ በእግዚአብሔር ቃል (ዮሐ. 17፡17ን ከ1ኛ ጢሞ. 4፡5 ጋር ያነጻጽሩ)፥ በክርስቶስ ደም (ዕብ. 9፡13፤ 13፡12)፥ በክርስቶስ አካል (ዕብ. 10፡10)፥ ወመንፈስ ቅዱስ (1ኛ ጴጥ. 1፡2)፥ በራሳችን ምርጫ (ዕብ. 12፡14፤ 2ኛ ጢሞ. 2፡21፥ 22)፥ በእምነት (ሐዋ. 26፡18) ነው። 

3. እግዚአብሔር ቀናትን፥ ቦታዎችንና ነገሮችን ቀድሷል (ዘፍጥ. 2፡3፣ ዘጸ. 29፡43)። 

4, ሰው እግዚአብሔርን ሊቀድስ ይችላል። ይህን የሚያደርገው፥ እግዚአብሔርን በአሳቡ እንደ ቅዱስ ሰይቶ በመመልከት ነው። “ስምህ ይቀደስ” (ማቴ. 6፡9)። “ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት” (1ኛ ጴጥ. 3፡15)። 

5. ሰው ራሱን ሊቀድስ ይችላል። ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር እስራኤላውያን ራሳቸውን እንዲቀድሱ አዟቸዋል። እኛንም፥ “እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ” ሲል ይመክረናል። “እንግዲህ ማንም ራሱን ከነዚህ (ከውርደት ዕቃዎችና ከበደል) ቢያነጻ፥ ለክብር የሚሆን፥ የተቀደሰ ለጌታውም የሚጠቅም ለበጉም ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ዕቃ ያየናል” (2ኛ ጢሞ. 2፡21)። የራስ ቅድሰና ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው፥ በመለኮታዊ የቅድስና መንገዶች አማካይነት ብቻ ነው። ክርስቲያኖች ሰውነታቸውን ሕያው መሥዋዕት፥ ቅዱስና ለእግዚአብሔር እንደሚገባ አድርገው እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል (ሮሜ 12፡1 )። 

“ከመካከላቸው ከአሕዛብ ወጥተው” መለየት አለባቸው (2ኛ ቆሮ. 6፡17)። እነዚህን የተስፋ ቃላት ይዘው “በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን፥ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ” (2ኛ ቆሮ. 7፡1) በሚለው ቃል መሠረት እንዲኖሩ ይጠበቅባቸዋል። “ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ” (ገላ. 5 ፡16)። 

6. ሰው ሰዎችንና ነገሮችን ሊቀድስ ይችላል። “ያላመነ ባል በሚስቱ ተቀ ድሶአልና፥ ያላመነችም ሚስት በባልዋ ተቀድሳለች፤ አለዚያ ልጆቻችሁ ርኩሳን ናቸው፤ አሁን ግን የተቀደሱ ናቸው (1ኛ ቆሮ. 7፡14)። ሙሴ ሕዝቡን ቀድሷል (ዘዳ. 19፡14)። 

“የእግዚአብሔርንም ቤት… ቀደሱ” (2ኛ ዜና 29፡17)። 

7. አንድ ነጎር ሌላውን ሊቀድሰው ይችላል። “ማናቸው ይበልጣል? ወርቁ ነውን? ወይስ ወርቁን የቀደሰው ቤተ መቅደስ? …ማናቸው ይበልጣል? መባው ነውን? ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው?” (ማቴ. 23፡17፥ 19)። 

ስላ መቀደስና ቅድስና መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተመለከትነው ከዚህ ውሱን ጥናት የምንረዳው፥ የቃሉ መሠረታዊ ፍቺ ለአንድ የተቀደሰ ዓሳማ መለየት መሆኑን ነው። የሚለየው ነገር አንዳንድ ጊዜ ሲነጻ፥ በሌላ ጊዜ ግን አይነጻም። አንዳንዴ ቅዱስ ሲሆን እንዳንድ ጊዜ ልክ እንደ ግዑዝ ነገር በራሱ ቅዱስ የሚባል ላይሆን ይችላል። ይሁንና፥ በራሱ ቅዱስ የመሆንም ሆነ ያለመሆን ብቃት የሌለው ነገር ለእግዚእብሔር በሚለይበት ጊዜ የተቀደሰ ይሆናል።አንድ ሰው ሲለይ መንጻትና መጽዳት እንዳንዴ ያስፈልጉት እንደነበር ደግሞ ማስተዋል ያስፈልጋል። ይህ ግን ሁልጊዜም የሚሆን አይደለም (1ኛ ቆሮ. 7፡14)። 

መ. ሦስት ዓበይት የቅድስና ገጽታዎች 

ብሉይ ኪዳን ስለ ቅድስና፥ በተለይም ከሙሴ ሕግና ከእስራኤል ጋር በተያያዘ ሰፊ መገለጥ አስተምህሮ ቢኖረውም፥ ስለ ዓበይት የቅድስና ገጽታዎች ይበልጥ ጥርት ያለ ሥዕል የሚሰወን ግን አዲሰ ኪዳን ነው። የአዲስ ኪዳን አስተምህሮ በሦስት ክፍሎች ይካተታል፥ (1) ስፍራዊ ቅድስና፥ (2) የልምምድ ቅድስና፥ (3) የመጨረሻው ቅድስና ናቸው። 

1. ስፍራ ቅድስና ስእ ግዚእብሔር አሠራር በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም አማካይነት የተፈጸመ መቀደስ፥ ቅድስናና ቅዱስነት ነው። አማኞች በከበረው የክርስቶስ ደም ተገዝተውና ነጽተው ለበደላቸው ሁሉ ይቅርታን አግኝተዋል። በርሱ ካገኙት አዲስ ሥፍራ የተነሣ ጸድቀዋል፥ ነጽተዋል። የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው። ይህ ሁሉ የሚያመለክተው፥ በኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ፀጋ አማካይነት የተፈጸመውን ጥልቅና ዘላለማዊ መለየት ነው። ይህም እማኝ በክርስቶስ ስሚኖረው ስፍራ ላይ የሚመሠረት ሲሆን፥ ለሁሉም ክርስቲያን የሚሆን ነው። ስለሆነም፥ ማንኛውም ከርስቲያን የስፍራን ቅድስና አግኝቷል፤ በእግዚአብሔር ፊት ቅዱስ ነው። ይህ ስፍራ እማኝን ለተቀደሰ ሕይወት የሚገፋፋው ሲሆን፥ በዕለታዊ ኑሮው ይህን ሕይወት የማይኖርበት ወቅት ቢኖር፥ የተሰጠውን ሥፍራ የሚያስጥለው ስላልሆነ ሰዕለታዊ ሕይወቱ ሁኔታ ላይ የሚደገፍ እይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረው፥ ክርስቲያን በክርስቶስ ያገኘው ስፍራ ከሁሉም በላይ ለሕይወት ቅድስና ማነቃቂያ ነው። 

በአዲስ ኪዳን ያሉ መልእክቶች ይህንኑ ቅደም ተከተል ይጠብቃሉ። መጀመሪያ ስለሚያድነው ጸጋ አስደናቂነት ይገልውና ሰዎች በመለኮታዊ አሠራር ካገኙት ስፍራ ጋር የሚስማማ ሕይወት እንዲመሩ ይጠይቃሉ (ሮሜ 12፡1፤ ኤፌ. 4፡1፤ ቆላ. 3፡1)። ተቀባይነት ያገኘነው ሰራሳችን ጥረት ሳይሆን በወደደን በእርሱ ነው። በራሳችን ጻድቃን አይደለንም፤ እርሱ ነው ጽድቃችን የሆነልን። የተቤዥነውም በጥረታችን አይደለም። እርሱ ተቤዥቶናል። በራሳችን ዕለታዊ ጎዞ የቅድስናን ስፍራ አላገኘንም፤ እርሱ ቅድስና የኖልናል። እርሱ ፍጹም ቅዱስ እንደሆነ፥ የስፍራ ቅድስናም ፍጹም ነው። እርሱ የሆነውን ያህል በርሱ ውስጥ ያለን እኛም ተቀድሰናል። 

የስፍራ ቅድስና ሙሉነት እጅግ ለደከመው ክርስቲያንም ሆነ እጅግ ለበረታው ክርስቲያን እኩል ነው። የሚወሰነው አንድ ክርስቲያን በክርስቶስ ባገኘው ስፍራና ጥምረት ብቻ ነው። እማኞች ሁሉ “ቅዱሳን” የሚል ምድብ ተሰጥቷቸዋል። የተቀደሱ” ተብለዋል (ሐዋ. 20፡32፤ 1ኛ ቆሮ. 1፡2፣ 6፡11፤ ዕብ. 10፡10፥ 14፤ ይሁዳ 1)። ፍጹማን ያልሆኑ አማኞች፥ የስፍራን ቅድስና ያገኙ መሆናቸውንና ከዚህም የተነሣ ቅዱሳን መሆናቸውን የሚያረጋግጥልን መረጃ 1ቆሮንቶስ ውስጥ ይገኛል። ምንም እንኳን የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በሕይወታቸው ቅዱሳን ባይሆኑ (1ኛ ቆሮ. 5፡1-2፣ 6፡1-8)፥ ሁለት ጊዜ ቅዱሳን ተብለዋል (1ኛ ቆሮ. 1፡2፣ 6፡11)። 

ስለሆነም፥ ክርስቲያኖች ከስፍራቸው አንጻር “ቅዱሳን” እና “ቅዱሳን ወንድሞች” መባላቸው ትክክል ነው። የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል” (ዕብ. 10፡16)። “በጽድቅና በቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ” (ኤፌ. 4፡24) የተፈጠሩ “አዲስ ሰዎች” ናቸው። 

ክርሰቲያን በክርስቶስ ውስጥ ሲሆን፥ በእግዚአብሔር ፊት ለዘላለም ተቀባይነት ያገኘና ጻድቅ ነው። ይሁን እንጂ፥ ማንም ቢሆን በክርስቶስ ውስጥ በመሆኑ ያገኘውን ስፍራ መሠረት በማድረግ በዕላታዊ ኑሮው ጻድቅ ወይም ቅዱስ ነኝ በማለት እንዳሻኝ እሆናለሁ ከሚል ድምዳሜ ላይ ሊደርስ አይገባም። ክርስቲያኖች በክርስቶስ ባገኙት ስፍራ የተቀደሱ ቢሆኑም፥ የዕለታዊ ሕይወት ቅድስና ጉዳይ “ከስፍራዊ ቅድስና” የተለየ ነገር ነው። ይህ ቅድስና የልምምድ ቅድስና ተብሎ የሚጠራው ነው። 

2. ልምምዳዊ ቅድስና አዲስ ኪዳን ውስጥ ሁለተኛው የቅድስና አስተምህሮ ሲሆን፥ ቅድስናን ከእማኙ ልምምድ ጋር ያዛምደዋል። የስፍራ ቅድስና ከዕለታዊ ሕይወት ጋር ሙሉ ለሙሉ እንደማይገናኝ ሁሉ፥ የልምምድ ቅድስናም በክርስቶስ ካሰን ሰፍራ ጋር አይገናኝም። የልምምድ ቅድስና በሚከተሉት ነገሮች ላይ ባላን ደረጃ መጠን ሊደገፍ ይችላል፡- (ሀ) ለእግዚአብሔር ባለን መሰወት (ሰ) ከኃጢአት በመለየት እና (ሐ) አማኙ ሳለው የክርስትና ሕይወት ዕድገት። 

(ሀ) ልምምዳዊ ቅድስና ለእግዚአብሔር የመሰጠት ውጤት ነው። ራሳችንን ለእግዚአብሔር ሙሉ ለሙሉ መስጠታችን የሚያመለክተው ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችንን ነው። “ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መስዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ” (ሮሜ 12፡1)። ይህን በማድረግ ከርሰቲያን በራሱ ፈቃድ ለእግዚአብሔር የተላየና የተመደበ ይሆናል። ይህ ራስን በገዛ ውሳኔ ለእግዚአብሔር መለየት፥ የልምምድ ቅድስና አስፈላጊ ገጽታ ነው። “አሁን ግን ከኃጢአት አርነት ወጥታችሁ ለእግዚአብሔርም ተገዝታችሁ፥ ልትቀደሱ ፍሬ አላችሁ” (ሮሜ 6፡22)። 

ቅድስና የጽድቅ ወይም የይቅርታ እንጂ፥ የስሜት ልምምድ ሊሆን አይችልም። አንድ ሰው ለእግዚአብሔር የተለየ መሆኑን ስለሚያምን ሰላምና ደስታ ይኖረው ይሆናል። ራሱን ለእግዚአብሔር በመስጠቱም አዲስ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት በሕይወቱ ሊከሰትና ከዚህ በፊት ያላወቀው በረከት ሊያስገኝለት ይችላል። ሂደቱም ቅጽበታዊ ወይም ዘገምተኛ ይሆን ይሆናል። ያም ሆነ ይህ ሰውዬው የሚሰማመደው ቅድስናን ሳይሆን፥ በቅድስና አማካይነት ተግባራዊ ሊሆን የቻለውን የመንፈስ ቅዱስ በረከት ወይም ለእግዚአብሔር ይበልጥ መለየትን ነው። 

(ለ) የልምምድ ቅድስና ከኃጢአት ነጻ የመውጣት ውጤት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያኖች ኃጢአትን ሊሠሩ እንደሚችሉ ያመለክታል። የሚድኑት ወይም ድነው የሚቀሩት ኃጢአት የሌለባቸው ሰዎች ብቻ ናቸው ብሎ አያስተምርም። ይልቁንም፥ ቅዱሳን በኃጢአታቸው ላይ ሊወስዷቸው ስለሚገቡ የተለያዩ፥ የታመኑ፥ ደግሞም ሙሉ የሆኑ ምከሮችን ያሰጣል። እነዚህ አማኙን ከኃጢአት የሚጠብቁትና የይቅርታ መቀበያ መንገዶች ናቸው። 

ክርስቲያንኝ ከኃጢአት ለመከላከል ሦስት መለኮታዊ መንገዶች ተዘጋጅተዋል። እነሱም፥ (1) ግልጥ ትእዛዛት ያሉት የእግዚአብሔር ቃል (መዝ. 119፡11)፥ (2) በአሁኑ ጊዜ ክርስቶስ በሰማይ ሆኖ የሚያከናውነው የእረኛነትና የአማላጅነት አገልግሎት (ዕብ. 7፡25፤ ሮሜ 8፡34፤ ሉቃስ 22፡31-32፤ ዮሐ. 17 ፡1-26)፥ እና (3) ክርስቲያኑ ውስጥ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ የማስቻል ኃይል ናቸው (ገላ. 5፡16፤ ሮሜ 8፡4)፡፡ከክርስቲያን በኃጢአት ቢወድቅም እንኳን መለኮታዊ መፍትሑ ተዘጋጅቶለታል። ያም ሰአሁኑ ጊዜ ክርስቶስ በሰማይ ሆኖ የራሱን ብቁና የመሥዋዕትነት ሞት በማቅረብ የሚያከናወነው የጠበቃነት (አማሳጅነት) ተግባር ነው። ፍጹማን ያልሆኑ እማኞች ተጠብቀው ሊኖሩ የሚችሉት ፅዚህ መንገድ ብቻ ነው። 

ለእያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጅ ኃጢአትን የሚቋቋምበት መለኮታዊ እገዛ ያስፈልገዋል። ምክንያቱም ክርስቲያን አሁን ባለበት አካል እስካለ ድረስ ባለማቋረጥ ወደ ኃጢአት የሚያዘነብልና የወደቀ ተፈጥሮ ስላለው ነው (ሮሜ 7፡21፤ 2ኛ ቆሮ. 4፡7፤ 1ኛ ዮሐ. 1፡8)። መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ተፈጥሮ ለማስወገድ ይገባዎ፥ አማኝ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ድል የሚቀዳጅ መሆኑ ያረጋግጣል (ገላ. 5፡16-23)። ይህ ድል የሚገኘው፥ እምነት ጥቅም ላይ ሲውልና በመንፈስ ቅዱስ ለተሞላ ሕይወት የተሰጡ ቅድመ-ሁኔታዎች ከተሟሉ ብቻ ነው። 

ኃጢአታዊው ተፈጥሮ ሞቷል የተባለበት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የለም። ይህ ኃጢአታዊ ተፈጥሮ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅሏል፥ ሞቷል፤ ተቀብሯል። ይሁንና፥ ይህ የሚያመለክተው ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ክርስቶስ “ለኃጢአት በሞተ” ጊዜ በኃጢአታዊ ተፈጥሮ ላይ የተሰጠውን መለኮታዊ ፍርድ ነው። አንዳንድ ክርስቲያኖች ለኃጢአት እንደሞቱና ሌሎች ግን እንዳልሞቱ የሚገልጥ የመጽሐፍ ቅዱስ እስተምህሮ የላም። ምንባቦቹ የዳኑትን ሰዎች በሙሉ ያካትታሉ (ገላ. 5፡24፤ ቆላ, 3፡3)። ክርስቲያኖች በክርስቶስ ሞት አማካይነት ለኃጢአት ሞተዋል። ከዚያ ሞት የተነሣ በተሰጣቸው ነገር ሁሉ ሙሉ ለሙሉ የተጠቀሙሰት ግን ሁሉም አይደሉም። ለኃጢአት እንደሞትን እንድንቆጥር” እንጂ፥ የመከራ ሞት እንድንሞት ወይም የርሱን ሞት እስመሰለን ተውኔት እንድንሠራ አልተጠየቅንም። የሰው ልጅ ኃላፊነት ራሱን ለኃጢአት እንደሞተ መቁጠር ነው (ሮሜ 6፡1-14)። 

እያንዳንዱ በኃጢአት ላይ የሚገኝ ድል የአማኝን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ (መለየት) ወይም መቀደስን ያመለክታል። እማኝ የራሱን ምስኪንነትና የመለኮታዊውን ኃይል እስደናቂነት እየተገነዘበ ሲሄድ፥ የዚህ ዓይነቱ ድል እየጨመረ ይሄዳል። 

(ሐ) የልምምድ ቅድስና ከክርስትና ሕይወት ዕድገት ጋር የተያያዘ ነው። ክርስቲያኖች በጥበብ፥ በእውቀት፥ ሰልምድና በጻጋ የበሰሉ እይደሉም። በነዚህ ነገሮች ሁሉ የማደግ ዕድል ግን ተሰጥቷቸዋል። በመሆኑም እድገታቸው ፍሬ አፍርቶ ሊታይ ይገባል። ለዚህ ነው “በጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ” (2ኛ ጴጥ. 3፡18) የሚል ምክር የተሰጣቸው። “መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን” (2ኛ ቆሮ. 3፡18)። ይህ መለወጥ ክርስቲያኖችን ይበልጥ እየተለዩ እንዲሄዱ ሰማድረግ ይበልጥ እንዲቀደሱ ያደረጋቸዋል። 

ክርስቲያን (ነቀፋ” እንደሌለበት ለመናገር ቢቻልም፥ “ስሕትት” የሌለበት መሆኑን ማረጋገጡ ግን ያዳግታል። አንድ ልጅ የመጀመሪያ ሆሄውን ደብተሩ ላይ ለመገልበጥ በሚያደርገው ጥረት በስራው ነቀፋ አይደርስበት ይሆናል፤ ላይኖርበት ይችላል። ሥራው ግን እንከን የለሽ አይደለም። እኛም ዛሬ በተረዳነው መጠን በመመላለስ ላይ ብንሆንም፥ የአሁኑ አኗኗራችን ነገ የኛ በሚሆነው ተጨማሪ ብርሃንና ልምምድ የተሞላ እንዳልሆነ እናውቃለን። ፍጹምነት በጎደለው ነገር ውስጥ ፍጹምነት እንዳለ እንረዳለን። ፍጹም ያልሆን፥ ያልበሰልንና ለኃጢአት የተሰጠን እኛም “በርሱ እንኖራለኝ”። 

3. የመጨረሻ ቅድስና ከመጨረሻው ፍጹምነት ጋር የተያያዘና ወደ ክብር በምንለወጥበት ወቅት የምናገኘው ነው። ያኔ ጌታ በጸጋውና በሚለውጥ ኃይሉ መንፈሳችንን፥ ነፍሳችንንና ሥጋችንን ይለውጣል። የርሱን መልክ እንድንመስል እንለወጣለን። በዚህ አኳኋን “እንከን የለሽ” አድርጎ በክብሩ ፊት ያቀርበናል። ሙሽራይቱ ከየትኛውም “ጉድፍና እድፍ” ትጠራለች። ስለሆነም፥ “ከማንኛውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ። የሰላምም አምላክ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ” (1ኛ ተሰ. 5፡22-23) በሚለው ቃል መሠረት ልንኖር ይገባል።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

32
ትምህርት 32 ከ52

የድነት ማረጋገጫ

ህ. የፅንሰ-አሳቡ አስፈላጊነት 

በክርስትና ሕይወት ልምምድ ሰው በክርስቶስ በማመን የድነት ማረጋገጫ ማግኘቱ፥ በጸጋና ክርስቶስን በማወቅ ለማደጉ አጠቃላይ ሂደት መሠረት ነው። የድነት ማረጋገጫ፥ የልምምድ ጉዳይ በመሆኑ፥ ከእሁኑ ድነት እርግጠኛነት ጋር ይዛመዳል። ይህ ሰሚቀጥለው ምዕራፍ ከምንነጋገርበት ዘላለማዊ የድነት ዋስትና ጋር ሊደነጋጎር እያገባም። ዘላለማዊ ዋስትና የእውነታ ጥያቄ ሲሆን፥ የድነት ማረጋገጫ ግን አንድ ሰው በአንድ ጊዜ ስለ ራሱ ድነት የሚያምነው ነው። 

የድነት ማረጋገጫ ሰሦስት ዓበይት የልምምድ ሁኔታዎች ላይ ይመሠረታል። እነርሱም (1) በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የተገኘውን ድነት ሙሉነት መረዳት፥ (2) ይህንኑ የሚያረጋግጠው ክርስቲያናዊ ልምምድ ምስክርነት፥ (3) መጽሐፍ ቅዱስን የድነት የተስፋ ቃላት በእምነት መቀበል ናቸው። 

ለ. የድነትን ምንነት መረዳት 

ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በሞተ ጊዜ የተከናወነውን ነገር በግልጥ መረዳቱ፥ ለየትኛውም እውነተኛ የድነት ማረጋገጫ መሠረት ነው። ድነት እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሠራው እንጂ፥ ሰው ለእግዚአብሔር የሠራው ነገር አይደለም። በመሆኑም፥ የሰውን ምግባር ከግንዛቤ ሳያስገባ ሙሉ በሙሉ በመለኮታዊ ጸጋ ላይ ይመሠረታል። አንድ ሰው፥ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሞተላትና ለማንኛውም ለሚያምን ሰው የሚሰጠውን ሙሉ ድነት እንደተጎናጸፈ ከተረዳ፥ እንዲሁም ክርስቶስን እንደ ግል አዳኙ አድርጎ በማመን ቅድመ ሁኔታውን ካሟሳ፥ ወዲያውኑ ለድነቱ ማረጋገጫ ሊኖረው ይችላል። ብዙ ጊዚ የድነት ማረጋገጫ የሚታጣው፥ ስለ ድነት የተሟላ ግንዛቤ ካለማግኘት የተነሣ ነው። ድነት በስጦታ እንጂ በሥራ እንደማይገኝ፥ በሰብአዊ ጥረት እንደማይመጣ፥ ለኔ ይገባኛል ተብሎ የማይጠየቅ እንደሆነ፥ በእምነት ለሚቀበሉ ሁሉ ግን እንደ ስጦታ የሚገኝ መሆኑን ለሚገነዘቡ ተገቢው የድነት ማረጋገጫ መሠረት ተጥሏል። ሰውዬው ሰእውነት በክርስቶስ እምኗል? የሚለው ጥያቄ መልስ ሲያገኝ ነው ጉዳዩ የሚቋጨው። የዚህ ጥያቄ መልስ የሚገኘው ድነትን በተቀበለው ሰው ክርስቲያናዊ ልምምድ ውስጥ ከሚታዩ ማረጋገጫዎች ነው። 

ለነፍስ ድነትን ከሚያስገኙ የተለያዩ መለኮታዊ ተግባራት መካከል፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለሚመጣው አዲስ ሕይወት መጽሐፍ ቅዱስ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶታል። ከሰማንያ አምስት የሚልቁ የአዲስ ኪዳን ምንባቦች ይህንኑ የማዳን ጸጋ ይገልጣሉ። እነዚህን ምንባቦች መመርመሩ፥ ይህ ወደ ሰዎች የሚመጣ ሕይወት በክርስቶስ ለሚያምኑ ሁሉ እግዚአብሔር የሚሰጣቸው መሆኑን ለመገንዘብ ይረዳል (ዮሐ. 10፡28፤ ሮሜ 6፡23)። ይህ ሕይወት ከክርስቶስ የሚገኝ ነው (ዮሐ. 14፡6)፤ የዘላለም ሕይወት ከርሱ በማይታይበት ሁኔታ ክርስቶስ ሰአማኙ ውስጥ ይኖራል (ቆላ. 1፡27፤ 1ኛ ዮሐ. 5፡11-12)። ስለሆነም፥ ክርስቶስ ዘላለማዊ እንደሆነ የአማኙም ድነት ዘላለማዊ ነው። 

ሐ. የክርስቲያናዊ ልምምድ ምስክርነት 

አማኝ ክርስቶስ ሰርሱ በመኖሩ እውነት ላይ በመመሥረት፥ በእምነት መሆን አለመሆኑን ራሱ እንዲፈርድ ተወስኗል (2ኛ ቆሮ. 13፡5)። ክርስቶስ የሚያድርበት ልብ፥ ድንቅ የሆነው ክርስቶስ ሰርሱ ውስጥ መኖሩን ሊረዳ ይገባል። ይህ የሚሆነው ግን ክርስቲያኑ በውስጡ ያደረው ክርስቶስ የሚገለጥበትን ትክክለኛ ሁኔታ ለመረዳት መጽሐፍ ቅዱስ ምስጥ በተሰጠው እንጂ ተሳሳቱ ስሜቶቹና ሰአሳቡ ላይ መደገፍ የለበትም። መገለጥ ለእግዚአብሔር ቃል ለሚገዛ ክርስቲያን ሁለት ዓላማዎች አሉት። በመጀመሪያ ሥጋዊ ስሜት ከእግዚአብሔር ነው ከሚለው ግምት ይጠብቀዋል። ሁለተኛ ይህ መግለጥ የመንፈሳዊነት እውነት መመዘኛ መሠረት ሲሆን፥ የዳኑ ሰዎች ሁሉ ይህንኑ መመዘኛ ለማሟላት ባለማቋረጥ መጣር ይኖርባቸዋል። 

አንድ ያልዳነ ሰው ምንም ያህል የሃይማኖት ሥርዓቶችን ሲጠብቅ፥ በክርስቶስ ያለን ሕይወት ለማሳየት አይችልም። በተመሳሳይ ሁኔታ፥ ሥጋዊ ክርስቲያን ድነቱን በክርስቲያናዊ አኗኗር በትክክል ለማረጋገጥ በሚያስችል መልክ መመላለስ የተሳነው ሰው ነው። ምንም እንኳ ዘላለማዊ ሕይወት በራሱ ያልተገደበ ቢሆን፥ የተለመደው ክርስቲያናዊ ልምምድ ሁሉ በሥጋዊነት የተገደበ ነው (1ኛ ቆሮ. 3፡1-4)። 

ሥጋዊ ክርስቲያን የመንፈሳዊውን ክርስቲያን ያህል ፍጹም ድነት አግኝቷል። ይህ የሆነው የትኛውም ልምምድ፥ ስናይ ምግባር፡ወይም እገልግሎት የድነት መሠረት የማደኖረው በመሆኑ ነው። በመንፈሳዊ ሕይወቱ ገና ሕፃን ቢሆንም ከርስቶስ ውስጥ ነው (1ኛ ቆሮ. 3፡1)። ከዚህ ሰው የሚጠበቅበት የሚያድን እምነት እንዲኖረው ሳይሆን፥ ከእግዚአብሔር አሳብና ፈቃድ ጋር ራሱን ማስተካከል ነው። ተገቢውን ክርስቲያናዊ ልምምድ የሚገነዘቡት በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ አማኞች ብቻ መሆናቸውን መረዳቱ እጅግ ያስፈልጋል። 

በእምነት ከመዳን የሚመጣውና በክርስቶስ የሆነው አዲስ ሕይወት አንዳንድ ዓበይት ውጤቶችን ያስከትላል። 

1. በክርስቶስ ያመነ ሰው ከሚያጎኛው ክቡር ገጠመኞች አንዱ፥ እግዚአብሔር ሰማያዊ አባታችን መሆኑን መረዳቱ ነው። ማቴዎስ 11፡27 ውስጥ ከወልድና ወልድ ራሱን ከሚገልጥሰት በቀር ማንም አብን እንደማያይ ተጠቅሷል። አማኝ ያልሆነ ሰውም ስላ እግዚአብሔር እውቀት ሰመጠኑ ሊኖረው የሚችል ሲሆን፥ እግዚአብሔርን ማወቁ ግን ፍጹም ሌላ ጉዳይ ነው፡፡እግዚእብሔርን ማወቅ የሚቻለው፥ ወልድ በገለጠው መንገድ ብቻ ነው። “እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን፥ የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። (ዮሐ. 17፡3)። ከአብና ከወልድ ጋር ኅብረት ማድረግን የሚያውቁ በብርሃን የሚመላለሱት” ብቻ ናቸው (1ኛ ዮሐ. 1፡7)። ስለሆነም፥ ትክክለኛው ክርስቲያናዊ ልምምድ የእግዚአብሔርን አባትነት በግል መቀበልን ያካትታል። 

2. ኤሳው የድነት ማረጋገጫ ልምምድ ለየት ያለ የጸሎት ሕይወት ነው። ጸሎት በመንፈሳዊው ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ትልቅ ስፍራ አለው። ውስጡ ባለው መንፈስ ቅዱስ አማካይነት ምስጋናና ውዳሴ ያቀርባል (ኤፌ. 5፡18-19)፤ በመንፈስ ቅዱስ እማካይነት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የመጸለይ ችሎታ ይኖረዋል (ሮሜ 8፡26-27፤ ይሁዳ 20)። በምድርም ሆነ ሰሰማይ የክርስቶስ አገልግሎት ጸሎት ያለበት እንደ መሆኑ፥ ክርስቶስ በውስጡ ያለበት አማኝም ለጸሎት የሚነሣማና የሚጓጓ ነው። 

3. ከድነት ጋር የተያያዘው ሌላው ድንቅ ልምምድ፥ መጽሐፍ ቅዱስን የመረዳት አዲስ ችሎታ ነው። ክርስቶስ በሰጠው ተስፋ መሠረት፥ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ስለ ክርስቶስ፥ ስለ እግዚአብሔርና ስለሚመጡት ነገሮች ይረዳል (ዮሐ. 16፡12-15)። ክርስቶስ በኤማሁስ መንገድ (ሉቃስ 24፡32)፥ የአድማጮቹን ልብ ለመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ከፍቷል (ሉቃስ 24፡45)። ይህን የመሰለው ድንቅ ገጠመኝ፥ ለተወዳጅ ከርስቲያኖች ብቻ የተዘጋጀ አይደለም። በአማኙ ውስጥ በሚኖረው ክርስቶስ የሚታይ መገለጥ እንደመሆኑ፥ ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ ግንኙነት ላላቸው ሁሉ የተገባ ልምምድ ነው (1ኛ ዮሐ. 2፡27)። 

4. ኃጢአትን እንደ ኃጢአት የመገንዘብ አዲሶ ኽኝባሌ የክርስቲያን ልምምድ ነው። ውኃ ንጽሕና የጎደለውን ነገር እንደሚያጸዳ ሁሉ (ሕዝ. 36፡25፤ ዮሐ. 3፡5፤ ቲቶ 3፡5-6፤ 1ኛ ጴጥ. 3፡21፤ 1ኛ ዮሐ. 5፡6-8)፥ የእግዚአብሔር ቃልም ሰብአዊ አስተሳሰቦችን ለማስወገድ በእግዚአብሔር አሳብ ይተካል (መዝ. 119፡11)። እንዲሁም ዕመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በሚሆን የእግዚአብሔር ቃል አሠራር፥ መለኮታዊው የኃጢአት ግንዛቤ ስብእዊውን ግንዛቤ ይተካዋል። ኃጢአት የማያውቀው፥ የኃጢአት መሥዋዕት የሆነውና እንደ ደም ሳብ ያላበው ክርስቶስ በአማኝ ውስጥ ራሱን ለመግለጥ ነጻ ከሆነ፥ እማኝ ስለ ኃጢአት አስከፊ ገጽታ በቂ የሆነ ግንዛቤ እንዲኖረው ያደርጋል። 

5. ላልዳኑ ሰዎች አዲስ ፍቅር አለ። ክርስቶስ ላሰዎች ሁሉ መሞቱ (2ኛ ቆሮ. 5፡14-15፥ 19)ሐዋርያው ጳውሎስን “ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሥጋ እንደሚሆን አናውቅም” (2ኛ ቆሮ. 5፡16) እንዲል አድርጎታል። በመንፈሳዊ ዓይኖቹ ሰዎች ሁሉ ከምድራዊ ልዩነቶቻቸው ሁሉ በላይ፥ ክርስቶስ የሞተላቸው ነፍሳት ሆነው ታዩት። ሰመሆኑም፥ ከድነት ርቀው ለጠፉት ወገኖች ከመጸለይ (ሮሜ 10፡1) እና ከመጣር (ሮሜ 15፡20) አልቦዘነም። ስለነርሱ “ከክርስቶስ ተለይቶ ለመረገም፡” ፈቃደኛ ነበር (ሮሜ 9፡1-3)። እያንዳንዱ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ አማኝ በልቡ ከሚኖረው ከዚህ መለኮታዊ ሕልውና የተነሣ፥ ይህን መለኮታዊ ርኅራኄ ሊለማመደው ይገባዋል (ሮሜ 5፡5፤ ገላ. 5፡22)። 

6. ለዳኑትም አዲስ ፍቅር ይኖረዋል። 1ኛ ዮሐንስ 3፡14 ውስጥ ወንድሞችን መውደድ ለግላዊ ድነት ፍጹም መለኪያ ሆኖ ተጠቅሷል። በመንፈስ ቅዱስ ዳግም የመወለድ ሥራ አማካይነት አማኙ ወደ እግዚአብሔር ቤተሰብነት ስለተቀላቀለ፥ ይህ ትክክለኛ መመዘኛ ነው። እውነተኛው የእግዚአብሔር አባትነትና የሰዎች ወንድማማችነት የሚገኘው፥ በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ ብቻ ነው። አንድ ዓይነት መለኮታዊ መገኘት ሰሁለት ግለሰቦች ውስጥ የመኖሩ እውነት፥ በከፍተኛ ደረጃ ያዛምዳቸውና፥ አንዱን ከአንዱ ጋር የሚያስተሳስር መሰጠትን ይፈጥራል። ስለሆነም አንድ ክርስቲያን ለሌላው የሚኖረው ፍቅር፥ የእውነተኛ ደቀ መዝሙርነት ምልክት ተደርጓል (ዮሐ. 13፡34-35)። ይህ ፍቅር ሰመንፈስ ከእግዚአብሔር የተወለዱ ሰዎች ሁሉ ያላቸው የተለመደ ባሕርይ ነው። 

1. ከሁሉም የሚልቀው የድኝት መሠረት፥ የክርስቶስ ባሕርይ በአማኙ ውስጥ መገለጡ ነው። እማኙ ልብ ውስጥ ከሚኖረው መለኮታዊ ሕልውና የተሣ፥ ልቡ ውስጥ የሚከሰቱ ግላዊ ልምምዶች በዘጠኝ ቃላት ተመልክተዋል፡- “ፍቅር ፥ ደስታ ፥ ሰላም፥ ትዕግስት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት ፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት” (ገላ. 5፡22-23)። እያንዳንዱ ቃል አማኝ ውስጥ የሚኖረውንና ሉዓላዊ የሆነውን የእግዚአብሔርን ባሕርይ ያሳያል። 

ክርስቶስ የኖረው ይህንኑ ሕይወት ነበር (ዮሐ. 13፡34፤ 14፡27፤ 15፡11)። ክርስቶስን የሚመስል ሕይወት ይህ ነው (ፊልጵ. 2፡5-7)፤ ይህ ሕይወት ክርስቶስ ነው (ፊል. 1፡21)። እነዚህ ጸጋዎች በሁሉም አማኝ ውስጥ በሚያድረው መንፈስ ቅዱስ አማካይነት የሚከናወኑ በመሆናቸው፥ ልምምዶቹ ለሁሉም የተሰጡ ናቸው። 

8. የክርስትና ሕይወት ልምምዶች በክርስቶስ በማመን የሚገኘውን ድነት ያስገነዝባሉ። ሐዋርያው ጳውሎስ ከራሱ ጋር በማዛመድ፥ “ያመንሁትን አውቃለሁ”ብሏል (2ኛ ጢሞ. 1፡12)። እዛኝ በሆነው ክርስቶስ ላይ የሚኖር የግል መተማመን የፈቃድና የአእምሮ ዝንባሌ በመሆኑ፥ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚታለል ስው እይኖርም። ይሁንና፥ ተገቢውን ሕይወት የሚመራ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ማግኘቱን በልቡ እንዲያረጋግጥ የእግዚአብሔር ዓላማ ነው። መንፈሳዊ ለሆነ ክርስቲያን፥ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን መንፈስ ቅዱስ ይመሰክርለታል (ሮሜ 8፡16)። እንደዚሁም፥ በክርስቶስ ካመነ ወዲያ በኃጢአት ምክንያት የሚመጣ የፍርድ የሕሊና ወቀሳ አይኖርበትም ( ዮሐ. 3፡18፤ 5፡24፤ ሮሜ 8፡1፤ ዕብ. 10፡2)። ይህ ማለት ግን ክርስቲያን በክርስቶስ አማካይነት ለዘላለም በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አይኖረኝም የሚል ስጋት አይኖርበትም ለማለት እንጂ፥ የሚሠራውን ኃጢአት ልብ አይለውም ለማለት እይደለም (ኤፌ. 1፡6፤ ቆላ. 2፡13)። ይህ የሚያምኑ ሁሉ ዕድል-ፈንታ ነው። 

የዋና ዋናዎቹን ክርስቲያናዊ ልምምዶች ዝርዝር ስናጠቃልል፥ ሥጋዊ ስሜታዊነት ከዚህ ውስጥ እንደማይካተትና፥ የአማኙ ልምምድ ትክክለኛ የሚሆነው “በብርሃን ሲመላለስ” (1ኛ ዮሐ. 1፡7 ) ብቻ መሆኑን መረዳቱ ተገቢ ነው። 

መ. የመጽሐፍ ቅዱስን የተስፋ ቃላት እውነተኛነት መቀበል 

1. የመጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛነትና ስለ ድነት የሚሰጣቸው የተስፋ ቃላትም ትክክል እንደሚፈጸሙ መተማመን ለድነት ማረጋገጫ ነው። አማኝ ደኅንነቱን በተመለክተ ሰማይለወጠው የእግዚአብሔር ቃል እውነት ላይ ሊደፍ ያነባል። ቃሉ የግል ልምምድ ሲያስጨብጠው ከሚችለው በሳይ የታመነ ነው። ሐዋርያው ዮሐንስ ለአማኞች ሲጽፍ፥ የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ” ብሏል (1ኛ ዮሐ. 5፡13)። ለዚህ ምንባብ መሠረት ማንኛውም ክርስቲያን የድነት ማረጋገጫ ተሰጥቷል። ሥጋዊውም ሆነ መንፈሳዊው ክርስቲያን የዘላለም ሕይወት እንዳላቸው ሊያውቁ ይገባል። ይህ ማረጋገጫ ያለው ሚለዋወጥ ልምምድ ሳይሆን፥ በማይለዋወጥ የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ነው (መዝ. 119፡89፥ 160፤ ማቴ. 5፡18፤ 24፡35፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡23፥25)። 

በጽሑፍ ሰፍረው የምናገኛቸው የእግዚአብሔር የተስፋ ቃላት እንደ ውርስ ሰነዶች ( ዮሐ. 3፡16፥ 36፤ 5፡24፤ 6፡37፤ ሐዋ. 16፡31፤ ሮሜ 1፡16፤ 3፡22 ፥ 26፤ 10፡13)፥ የማይሻሩ ናቸው። እነዚህ የጅነት የተስፋ ቃላት በቅድመ ሁኔታ ሳይ ሳልተደገፈ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ጸጋ ሥር ስለሚገኙ ስለሆኑ ለእርግጠኝነታቸው ማንኛውንም ሰብዓዊ ልምምድ አይፈልጉም። እነዚህ ታላላቅ እውነቶች ከእግዚአብሔር እውነተኛነት በቀር በምንም ሌላ ሁኔታ እንዳልተፈጻሙ ሊታወቅ ይገባል። 

2. አንድ ሰው በክርስቶስ ማመኑንና ለእግዚአብሔር የተስፋ ቃላት በእርግጥ ራሱን መስጠቱን የሚጠራጠር ከፊን፥ የክርስትና እምነቱ ደካማ ነው። እጅግ ብዙ ሰዎች ደኅንነታቸውን አስመልክቶ ከክርስቶስ ጋር ኅብረት ስለማድረጋቸው እርግጠኞች አይደሉም። አንድ ሰው ሕይወቱን ለክርስቶስ ለመስጠት የወሰነበትን ቀንና ሰዓት የግድ ማወቅ ሳይኖርበትም፥ አሁን ክርስቶስን በማመን ላይ መገኘቱን መረ4ቱ ወሳኝ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ እራሱ እግዚአብሔር የሰጠውን (“አደራውን ሊጠብቅ እንደሚችል መረዳቱን ይገልጣል (2ኛ ጢሞ. 1፡12)። 

አንድ ሰው በክርስቶስ ለማመኑ እርግጠኛ ካልሆነ፥ መፍትሔው የትኛውም ቦጎነት ወይም ሃይማኖታዊ ተግባር ዋጋ እንደሌለው ተረድቶ አሁኑኑ በክርስቶስ ማመን እንደሚሆን ሊረዳ ይገባል። ሊያድን የሚችለው ክርስቶስ ብቻ ነው። እግዚአብሔር ብቻ ሊሰጥ የሚችለውን ዋስትና ለማግኘት ራሱን በእምነት ለእግዚአብሔር መስጠቱን የሚጠራጠር ማንኛውም ሰው፥ ሁነኛ የእምነት እርምጃ በመውሰድ ጉድለቱን ሊያስተካክል ይገባል። ይህ ምንም እንኳን በስሜት ሊፈጽም የሚችልና ስለ ድነት አስተምህሮ የተወሰነ ግንዛቤ የሚጠይቅ ሲሆን፥ በመሠረቱ ግን የፈቃደኛነት ተግባር ነው። ብዙዎቹ የሚከተለውን አጭር ጸሎት መጸለያቸው የድነት ውሳኔያቸውን እርግጠኝነት ለመጨበጥ ረድቷቸዋል። «ጌታ ሆይ፥ ከዚህ በፊት እምነቴን በአንተ ላይ አልጣልኩም እንደሆነ አሁን አደርገዋለሁ”። አንድ ሰው ክርስቶስን በትክክል እንደ አዳኙ በእምነት ካልተቀበለ፥ እውነተኛ የድነት ዋስትና ሊያገኝ አይችልም። 

3. የእግዚአብሔርን ታማኝነት መጠራጠር እውነተኛ የድነት ማረጋገጫን ያሳጣል። አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሔር እንደተቀበሳቸውና እንዳዳናቸው እርግጠኞች ስለማያሇኑ፥ ደኅንነታቸውን ይጠራጠራሉ። ብዙውን ጊዜ ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብ የሚመነጨው፥ ሰዎች የክርስቶስን ታማኝነት ከመመልከት ይልቅ፥ የነበራቸውን የስሜት ለውጥ ስለሚከታተሉ ነው። ስሜቶችና ልምምዶች የራሳቸው ስፍራ አላቸው። ይሁንና፥ ቀደም ሲል እንደተገለጠው፥ የአንድ ሰው ደኅንንት ማረጋገጫ፥ የማይለወጠው የእግዚአብሔር እውነተኛነት ነው እንጂ፥ የሰው ስሜት አይደለም። እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉ ያደርጋል፤ ስለሆነም በክርስቶስ ላይ እምነቱን በሚገባ የጣለ ሰው፥ ሰደኅኝነቱ ላይ ጥርጥር ሊኖረው አይገባም። 

4. በዚህ መሠረት የድነት ማረጋገጫ እግዚአብሔር በክርስቶስ ለሚያምኑ ሰዎች የሚሰጠውን ሙሉ ድነት መረዳቱ ነው። በክርስቲያናዊ ልምምድ ውስጥም የተወሰነ ማረጋገጫ ሊኖር ይችላል። ክርስቶስን እንደ አዳኙ ባመነ ሰው ሕይወት የተወሰነ ለውጥ ይኖራል። ከሁሉም በላይ የአንድ ግለሰብ ደኅንንት ማረጋገጫ ሁለት ነገሮች ናቸው፡- አንደኛ በእግዚአብሔር የተስፋ ቃላት እርግጠኛነት ላይ መደገፍ፤ ሁለተኛ በእርግጠኛነት ራሱን በእምነት ለኢየሱስ ክርስቶስ መስጠቱ። ራሱን ለክርስቶስ የሰጠ ሰው ሁለት ነገሮች ላይ ይደገፋል። እነሱም የተስፋ ቃሉን ይፈጽም ዘንድ ታማኝ በሆነው ጌታና፥ ሊያድነው በሚችል የጌታ መሰኮታዊ ኃይል (ጸጋ) ናቸው። 

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

33
ትምህርት 33 ከ52

የድነት ዋስትና

በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምኑ ብዙ ሰዎች የድነት ዋስትና ያላቸው ስለመሆኑ እርግጠኞች ናቸው። ብዙ ጊዜ የሚነሣው ጥያቄ ግን፥ “አንድ ጊዜ የዳነ ሰው ድነቱን ሊያጣ ይችላልኝ?” የሚል ነው። ድነትን የማጣቱ ፍርኃት የአንድን አማኝ የአእምሮ ሠላም በከፍተኛ ደረጃ ስለሚጎዳና ለወደፊት ተስፋውም ወሳኝ ጉዳይ ስለሆ፥ ጥያቄው የድነት አስተምህሮ እጅግ ጠቃሚ ክፍል ነው። 

አንድ ጊዜ የዳነ ሰው ድነቱን ሊያጣ ይችላል የሚለው አሳብ የተመሠረተው፥ የድነት ዋስትናን አጠያያቂ በሚያስመስሉ የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች ላይ ነው። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ፥ ሁለት ተቃራኒ የአተረጓጎም ዘዴዎች ተከስተዋል። እነዚህም የዘላለማዊ የድነት ዋስትና አስተሳሰብን የሚደግፉ የካልቪን ትምህርት ተከታዮችና፥ ይህን ፅንሰ-አሳብ የሚቃወሙ የአርሜኒዮስ ትምህርት ተከታዮች የሚያስተምሯቸው አስተምህሮዎች ናቸው። 

ሀ. የአርሚኒያውያን የድነት ዋስትና አመለካከት 

የአርሜኒያውያንን አመለካከት የሚከተሉ ሰዎች በቅድመ ሁኔታዎች ላይ የተመሠረተ የዋስትና አስተምህሮን ያረጋግጣሉ ብለው ያመኑባቸውን ሰማኒያ አምስት ያህል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ዘርዝረዋል። ከነዚህም መካከል ይበልጥ ጠቃሚዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡- ማቴዎስ 5፡13፤ 6፡23፤ 7፡16-19፤ 13፡1-8፤ 18፡23-35፤ 24፡4-5፥ 11-13፥ 23-26፤ 25፡1-13፤ ሉቃስ 8፡11-15፤ 11፡24-28፤ 12፡42-46፤ ዮሐ. 6፡66-11፤ 8፡31-32፥5 1፤ 13፡8፤ 15፡1-6፤ ሐዋ. 5፡32፤ 11፡21-23፤ 13፡43፤ 14፡21-22፤ ሮሜ 6፡11-23፤ 8፡12-17፤ 11፡20-22፤ 14፡15-23፤ 1ኛ ቆሮ. 9፡23-27፤ 10፡1-21፤ 11 ፡29-32፤ 15፡1-2፤ 2ኛ ቆሮ. 1፡24፤ 11፡2-4፤ 12፡21-13፡5፤ ገላ. 2፡12-16፤ 3፡4-4፡1፤ 5፡1-4፤ 6፡7-9፤ ቈላ. 1፡21-23፤ 2፡4-8፥ 18-19፤ 1ኛ ተሰ. 3፡5፤ 1ኛ ጢሞ. 1፡3-7፥ 18-20፤ 2፡11-15፤ 4፡1-16፤ 5፡5-15፤ 6፡9-12፥ 17-21፤ 2ኛ ጢሞ. 2፡11-18+ 22-26፤ 3፡13-15፤ ዕብ. 2፡1-3፤ 3፡6-19፤ 4፡1-16፤ 5፡8-9፤ 6፡4-20፤ 10፡19-39፤ 11፡13-16፤ 12፡1-17፥25-29፤ 13፡7-17፤ ያዕቆ. 1፡12-26፤ 2፡14-26፤ 4፡4-10፤ 5፡19-20፤ 1ኛ ጴጥ. 5፡9፥ 13፤ 2ኛ ጴጥ. 1፡5-11፤ 2፡1-22፤ 3፡16-17፤ 1ኛ ዮሐ. 1፡5-3፡11፤ 5፡4-16፤ 2ኛ ዮሐ. 6-9፤ ይሁዳ 5-12፥ 20-21፤ ራእይ 2፡7፥ 10-11 

17-26፤ 3፡4-5፥ 8-22፤ 12፡11፤ 17፡14፤ 21፡7-8፤ 22፡18-19። 

እነዚህን ምንባቦች ማጥናቱ አያሌ ጠቃሚ ጥያቄዎችን ያስነሣል። 

1. ይህን ጉዳይ አስመልክቶ መጽሐፍ ቅዱስን ዮሚተረጉምን ሰው የሚገጥመው ጠቃሚ ጥያቄ ምናልባት እውነተኛው አማኝ ማነው? ቀሚለው ይሆናል። ብዙ ሰዎች የዘላለማዊ ዋስትና አስተምህሮን የሚቃወሙት አንድ ሰው ድነትን ሳያገኝ የአእምሮ እምነት ሊኖረው ይችላል በማለት ነው። 

የዘላለማዊ ዋስትናን እሳብ የሚደግፉት ደግሞ አንድ ሰው በሕይወቱ ውጫዊ ለውጥ ሊታይ እንደሚችል ይስማማሉ። ሰውዬው የቤተ ክርስቲያን አባል በመሆን ወይም በመጠመቅ ክርስቶስን የመቀበል ውጫዊ እንቅስቃሴ ሊያሳይ፥ ከዚህም አልፎ በአኗኗሩ ላይ የተወሰነ ለውጥ ያሳይ ይሆናል፤ ዳሩ ግን በክርስቶስ እውነተኛ ድነት ላይኖረው ይችላል። 

የዳነውን ካልዳነው ለመለየት የሚያስችል ደንብ መዘርዘር ባይቻልም፥ በእግዚአብሔር አእምሮ ምንም ዓይነት አጠያያቂ ነገር እንደማይኖር ግልጥ ነው። አማኙ ከሁሉም በፊት ክርስቶስን እንደ አዳኙ የተቀበለ ለመሆኑ እርግጠኛ መሆን አለበት። በዚህ ረገድ ክርስቶስን መቀበል ስለ ድነት መንገድ የተወሰነ እውቀት ሊያካትት የሚችል የፈቃደኝነት ተግባር እንደሆነና፥ በተወሰነ ደረጃም በስሜት ሊገለጥ እንደሚችል መረዳቱ ጠቃሚ ነው። መሠረታዊው ጥያቄ ግን፥ “እውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኜ አድርጌ ተቀብያለሁን?” የሚለው ነው። ይህ ጥያቄ ታማኝ መልስ ካላገኘ፥ ለዘላለማዊ የድነት ዋስትናም ሆነ፥ ለድነት ማረጋገጫ ምንም ዓይነት መሠረት ሊኖር አይችልም። የዘላለማዊ ዋስትናን ፅንሰ- እሳብ የሚቃወሙ ሰዎች ለይስሙላ የሆነ እምነት ለማዳን አይችልም ይላሉ። የዘላለማዊ ዋስትና ደጋፊዎችም ይህን እሳብ ይደግፋሉ። እዚህ ላይ በአግባቡ የሚሰነዘረው ጥያቄ፥ በትክክል የዳነና የዘላለም ሕይወት ያገኘ ሰው ድነቱን ያጣል ወይ? የሚለው ነው። 

2. ዘላለማዊ ዋስትናን የሚቃወሙ ወገኖች የሚጠቅሷቸው ምንባቦች፥ ስለ ሰብአዊ ተግባራት ወይም ስለ ድነት መረጃ የሚናገሩ ናቸው። እውነተኛ ድነት ያገኘ ሰው በክርስቶስ ያገኘውን አዲስ ሕይወት በባሕርዩና በሥራ መግለጥ አለበት። ይሁንና፥ አንድን ሰው በሥራው መፍረድ ሊያታልል ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ክርስቲያኖች ያልሆኑ ሰዎች በአንጻራዊነት ከክርስትና ሕይወት ሥነ-ምግባር ጋር የሚነጻጸር ተግባር ሊያከናውኑ ይችላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ እውነተኛ ክርስቲያኖች የሆኑ አንዳንድ ሰዎች በሥጋዊነትና በኃጢአት ተጠምደው ድነትን ካላገኙ ሰዎች በማይለዩበት ሁኔታ ኃጢአት አዘቅት ውስጥ ይሰጥሙ ይሆናል። ሉቃስ 11፡24-26 ውስጥ የተጠቀሰው ዓይነት ሰዶ የግብረ ገባዊነት ተሐድሶ እውነተኛ ድነት እንዳልሆነና፥ ወደ ቀድሞው ሕይወት መመለስም ድነትን ማጣት እንዳልሆነ ሁሉም ይስማማሉ። 

ክርስቲያናዊ የእምነት ምስክርነት በፍሬው መረጋገጥ እንዳለበት አያሌ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች ያስገነዝባሉ። ከእግዚአብሔር የሆነ ድነት ሰተራ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን በፍሬው ምንነቱን ያስመሰክራል (ዮሐ. 8፡31፤ 15፡6፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡1-2፤ ዕብ. 3፡6-14፤ ያዕ. 2፡14-26፤ 2ኛ ጴጥ. 1፡10፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡10)። ይህም ሆኖ፥ ሁሉም ክርስቲያኖች፥ ሁልጊዜ የድነትን ፍሬዎች አያሳዩ ይሆናል። በመሆኑም፥ ድነት በሥራ መረጋገጥ እንዳለበት የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የአማኙን ዋስትና አስተምህሮ የሚቃረኑ እይደሉም። ዋናው ጥያቄ እግዚአብሔር ሰውዬውን እንደዳነ ይቆጥረዋል ወይ? የሚለው ነው። 

3. የአማኙን ዋስትና እልባነት ለማሳየት የተጠቀሱ ብዙ ምንባቦች፥ በክርስቶስ ዮማመኑ ጉዳይ ተራ ወይም የይምሰል እንዳይሆን ያስጠነቅቃሉ። አይሁዳውያን መሥዋዕቶችን የማቅረቡ ዘመን ስላለፈ ወደ ክርስቶስ እንዲመለሱ፥ ካልሆነ ግን እንደሚጠፉ አዲስ ኪዳን ውስጥ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል (ዕብ. 10፡26)። እንደዚሁም፥ ያልዳኑ አይሁዶችና አሕዛብ አብርሆትን ከሚሰጣቸውና ከሚለውጠው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ “እንዳይወድቁ” ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል (ዕብ. 6፡4-9)። መንፈሳዊ ያልሆኑ አይሁዶች በሚመጣው መንግሥት ተቀባይነት እንደማይኖራቸው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል (ማቴ. 25፡1-13)። ከእስራኤላውያን ቡድን አንጻር የአሕዛብ ቡድንም፥ ባለማመን ምክንያት በአሁኑ ዘመን ያሳቸውን የበረከት ስፍራ እንዳያጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል (ሮሜ 11፡21)። 

4. እንዳንድ ምንባቦች የሚያነሡት ክድነት ጥያቄ ይልቅ የሽልማትን ጉዳይ ነው። በክርስቶስ አምኖ የዳነ ሰው ሽልማቱን ያጣ ይሆናል (1ኛ ቆሮ. 3፡15፤ ቈሳ. 1፡21-23)። ለክርስቶስ የሰጠው አገልግሎትም ዋጋ አይኖረውም (1ኛ ቆሮ. 9፡27)። 

5. እውነተኛ ክርስቲያን በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ኅብረት ያጣ ይሆናል (2ኛ ዮሐ. 1፡6)። እንዲሁም ከድነቱ የተነሣ በዚህ ሕይወቱ ሊያገኛቸው የሚገባውን የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ማፍራትን (ገላ. 5፡22-23) እና ለክርስቶስ ውጤታማ አገልግሎት አበርክቶ እንደመርካት ያሉ መልካም ነገሮችን ይነፈጋል። 

6. እውነተኛ ታማኝ ለኮብላይነቱ፥ ልጅ በአባቱ እንደሚቀባ ሁሉ፥ ይቀጣ ይሆናል (ዮሐ. 15፡2፤ 1ኛ ቆሮ. 11፡29-32፤ 1ኛ ዮሐ. 5፡16)። ቅጣቱም እስከ ሥጋዊ ሞት ሊደርስ ይችላል። ይሁንና፥ ይህ ቅጣት የድነት ማጣት ምልክት ሳይሆን፥ አማኙ የሰማይ አባቱ የሚቀጣው የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን የሚያመለክት ነው። 

7. መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው፥ አንድ አማኝ ክጸጋ ይወድቅ ይሆናል (ገላ. 5 ፡1-4)። ይህ በአግባቡ ከተተረጎመ አማኝ ድነቱን የሚያጣ መሆኑን ሳይሆን፥ በአኗኗሩ ከጸጋ መመዘኛ እንደሚወርድና ወደ ሕግ ባርነት ሰመመለስ በክርስቶስ ያገኘውን እውነተኛ ነጻነት የሚያጣ መሆኑን ነው። ስለሆነም፥ አማኝ የሚወድቀው ከድነት ተግባር ሳይሆን፥ ከአኗኗር መመዘኛ ነው። 

8. ብዙ ችግር የሚመጣው፥ ያለአገባባቸው የሚጠቀሱ ምንባቦች በተለይም ከሌላ ሥፍራዘመን ጋር የሚዛመዱ ምንባቦችን ከመጥቀስ የተነሣ ነው። በአዲስ ኪዳን ትምህርት ላይ ተመሥርቶ እውነተኛ ዳግም ልደት ያገኘ የብሉይ ኪዳን ቅዱስ፥ የአሁኑን ዘመን ያህል ዋስትና እንዳሰው ለመገመት ቢቻልም፥ ብሉይ ኪዳን ስለ ዘላለማዊ ዋስትና ግልጥ አመለካከት አያስጨብጥም። ቢሆንም፥ ካለፈው ወይም ከሚመጣው ሥፍረ-ዘመን ጋር የሚዛመዱና እንደ ሕዝቅኤል 33፡7-8 ያሉ ምንባቦች በአገባባቸው መሠረት ሊተረጎሙ ይገባል። እስራኤላውያን ሕግን ሰመታዘዝ ስለሚያገኙት በረከትና፥ ባለመታዘዝ ስለሚደርስባቸው መርገም የሚናገረውን ዘዳግም 28ን የመሰሉ ዋና ዋና ምንባቦችም ጥንቃቄ ሊደረግላቸው ይገባል። ሌሎቹ ምንባቦች የሚያመለክቱት በመጨረሻው ዘመን የሚነሡትን ሐሰተኛና ዳግም ልደት ያላገኙ አሰተማሪዎችን ነው (1ኛ ጢሞ. 4፡1-2፤ 2ኛ ጴጥ. 2፡1-22፤ ይሁዳ 17-19)። እንዲህ ያሉ ሰዎች የስም ክርስቲያኖች ሲሆኑም፥ ዳግም የተወለዱ አይደሉም። 

9. የዋስትናን አለመኖር ለማገናዝብ ሲባል በስሕተት የተተረጎሙና ማቴዎስ 24፡13 ውስጥ ብስከ መጨረሻው የሚጸና እርሱ ግን ይድናል” የሚለውን የመሰሉ ብዙ ጥቅሶች ቀርበኞል። ይህ የሚያመለክተው፥ ከበደል ወይም ከኃጢአት መዳንን ሳይሆን፥ ከጠላቶችና ከስደት ነጻ መሆንን ነው። ከላይ የተመለከተው ጥቅስ የሚያመለክተው፥ ከታላቁ መከራ ተርፈው በኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት የሚድኑትን አማኞች ነው። ብዙ እውነተኛ ክርስቲያኖች ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት በፊት በሰማዕታትነት እንደሚሞቱና እርሱ እስኪመለስ ድረስ በሕይወት እንደማይቆዩ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ያስተምራል (ራእይ 7፡14)። ጥቅሶች ለዋስትናም ሆን ዋስትና አልባነትን ለመግለጥ እንዴት በተሳሳተ መንገድ ሊያገለግሉ እንደሚችሉ ከዚህ ምንባብ ለመረዳት ይቻላል። 

10. አማኝ ዋስትና ያለው ወይም የሌለው መሆን የሚወሰነው፥ የድነቱን ሥራ የሚሠራው ማነው? ለሚለው ጥያቄ ስሚሰጠው የመጨረሻ መልስ ላይ ነው። አንድ ጊዜ እውነተኛ ድነት ያገኘ አማኝ ለዘላለም ድኗል፥ የሚለው ፅንሰ-አሳብ ድነት በየትኛውም የአማኙ መልካም ሥራ ላይ ያልተደገፈና በርሱ ጥረት የማይቀጥል የእግዚብሔር ሥራ እንደሆነ ከሚያስረዳ መርሕ ላይ ይመሠረታል። የሚያከናውነው ሰው ከሆነ፥ ድነቱ ዋስትና የለውም። እግዚአብሔር የሚሠራው ከሆነ ዋስትና አለው። 

አንድ ጊዜ የዳነ ሰው ድነቱ ለዘላለም አብሮት እንደሚኖር የሚያሰረዳው ፅንሰ-አሳብ፥ ቢያንስ አሥራ ሁለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድጋፎች አሉት። ከነዚህም መካከል አራቱ ከአብ፥ አራቱ ከወልድና አራቱ ከመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች ጋር ይገናኛሉ። 

ለ. አብ በድነት ያለው ሥራ 

መጽሐፍ ቅዱስ ዕቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተውንና በክርስቶስ ለሚያምን ሁሉ የዘላለም ድነት ተስፋ ዮሚሰጠውን የእግዚአብሔርሉዓላዊ ቃል ይገልጣል (ዮሐ. 3፡16፤ 5፡24፤ 6፡37)። በግልጥ እንደሚታወቀው፥ እግዚአብሔር የገባውን ተስፋ ለመፈጸም ይችላል፤ የማይለወጥ ፈቃዱም ሮሜ 8፡29-30 ውስጥ ተገልጧል። 

2. የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ኃይል ሰዎችን ለማዳንና ለዘላለምም ለመጠበቅ ይችላል (ዮሐ. 10፡29፤ ሮሜ 4፡21፤ 8፡31 ፥ 38-39፤ 14፡4፤ ኤፌ. 1፡19-21፤ 3፡20፤ ፊልጵ, 3፡21፤ 2ኛ ጢሞ. 1፡12፤ ዕብ. 7፡25፤ ይሁዳ 24)። እግዚአብሔር የተስፋ ቃሉኝ የመፈጸም ታማኝነት ብቻ ሳይሆን፥ የፈቀደውን ሁሉ የሚፈጽምበት ኃይልም አለው። በክርሰቶስ የሚያምኑትን ማዳን የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑንም መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። 

3. ወሰን የለሹ የእግዚአብሔር ፍቅር የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ ዓላማ የሚመለከት ብቻ ሳይሆን፥ ዓላማው እንደሚፈጸም የሚያረጋግጥም ነው (ዮሐ. 3፡16፤ ሮሜ 5፡7-10፤ ኤፌ. 1፡4)። እግዚአብሔር ለዳኑት ያለው ፍቅር ላልዳኑት ካለው እንደሚልቅ ሮሜ 5፡8-11 ውስጥ የተገለጠ ሲሆን፥ ዘላለማዊ ዋስትናቸውንም ያረጋግጥላቸዋል። አሳቡ ግልጥና ቀጥተኛ ነው። እግዚአብሔር ገና ኃጢአተኞችን እና “ጠላቶቹ” እያሉ ሰዎችን ለማዳን ልጁን ከሰጣቸው፥ በሚቤዥ ጸጋው በፊቱ ከጻደቁና ከታረቁት በኋላማ “ይበልጥ” ይወዳቸዋል። 

እግዚአብሔር ሊተመን የማይቻል ዋጋ የገዛቸውን ሰዎች በፍጹም ፍቅር ወዷቸዋል። በመሆኑም በሉዓላዊነቱ ያለው ኃይል እስኪሟጠጥ ድረስ እንኳ እነዚህን ሰዎች ከእጁ የማያመጣቸው፥ ወይም የማይጥሳቸው ለመሆኑ ይህ ፍቅሩ ዋስትና ነው (ዮሐ. 10፡28-29)። ለንጽጽር ያህል ይህ ተባለ እንጂ፥ ጎናናው የእግዚአብሔር ኃይል ፍጻሜ የለውም። የአብ የተስፋ ቃል፥ ሰማይወሰነው ኃይሉና ፍጹም ፍቅሩ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ራሱን ለእግዚአብሔር የሰጠ ሰው፥ እግዚአብሔር ወደ ሕይወቱ ያመጣውን ድነት እንዳያጣ ያደርጉታል። 

4. የእግዚአብሔር ጽድቅ በክርስቶስ ያመኑ ሰዎችን ዘላለማዊ ዋስትና ያረጋግጣል። ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት በመሞቱ፥ የእግዚአብሔር ጽድቅ የሚጠይቀው ነገር ሁሉ ሙሉ ለሙሉ ተፈጽሟል (1ኛ ዮሐ. 2፡2)። እግዚአብሔር ኃጢአትን ይቅር የሚለውና የዘላለም ድነት ተስፋ የሚሰጠው፥ በፍጹም ጽድቅ ላይ በመመሥረት ነው። ኃጢአተኛውን ይቅር የሚለውም እንዲያው በግዴለሽነት አይደለም። ለኃጢአት ይቅርታ የሚሰጠውም ፍጹም ጻድቅ በመሆኑ ነው። ይህም ከክርስቶስ መስቀል በፊት በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበሩትን ብቻ ሳይሆን፥ ከክርስቶስ መሰቀል በኋላ የኖሩትንም ሁሉ ያካትታል (ሮሜ 3፡25-26)። የእግዚአብሔር ጽድቅ አጠያያቂ ካልሆነ በቀር፥ የአማኝ ዘላለማዊ ዋስትና አያጠያይቅም። በመሆኑም፥ እግዚእብሔር ለተሰፋው ታማኝ መሆኑ፥ ፍጹም ኃይሉ፥ ፍቅሩና ጽድቁ ተዳምረው ለአማኙ ድነት ፍጹም ዋስትና ናቸው። 

ሐ. የወልድ ሥራ 

1. ኢየሱስ ክርስቶስ በኃጢአተኞች ምትክ በመስቀል ላይ መሞቱ ለአማኝ ፍጹም ዋስትና ነው። የክርስቶስ ሞት ኮናኝ ለሆነው የኃጢአት ኃይል በቂ መልስ ነው (ሮሜ 8፡34)። ሰው ከእግዚአብሔር ያገኘውን ድነት ያጣል የሚለው አባባል የሚመሠረተው፥ እማኝ ይሠራዋል በሚለው ኃጢአት ላይ ነው። እንዲህ ያለው አስፈላጊ ነው የሚባል ነገር ግምት የሚመነጨው፥ ክርስቶስ አማኙ ወደፊት የሚፈጽማቸውን ኃጢአቶች ሁሉ ከመስቀሉ ላይ እንዳልተሸከመና እግዚአብሔርም ነፍስን ካዳነ በኋላ ያልተጠበቀ ተከታታይ ኃጢአት ከእማኙ ሕይወት ውስጥ አቆጥቁጦ ቢያይ እንደሚያዝንና እንደሚገረም ካሰብ ነው። በአንጻሩ ግን የእግዚአብሔር ሁሉን አዋቂነት ፍጹም ስለሆነ እማኝ የሆነ ልጁን ኃጢአት ወይም ሕይወቱን የሚያጨልመውን ምስጢር አስቀድሞ ያውቃል። ለእነዚህም ኃጢአቶች በቂ የሆነው የክርስቶስ የመሥዋዕትነት ደም የፈሰሰ ሲሆን፥ እግዚአብሔርም በዚያ ደም ስርየትን አድርጓል (1ኛ ዮሐ. 2፡2)። 

ላዳነም ሆነ ላልዳነ ሰው ኃጢአት ብቁ ሆኖ ከሚገኘው የክርስቶስ ደም የተነሣ፥ እግዚአብሔር የድነት ተስፋ የሌላቸውን ፍጹም የማዳኑኝ ያህል፥ ጸጋውንም እንዳለ ለመቀጠል ነጻ ነው። ለዘላለም ይጠብቃቸዋል። ይህን የሚያደርገው፥ ለነርሱ በማሰብ ብቻ ሳይሆን፥ የራሱን ፍቅር ለማርካትና ጸጋውን ለመግለጥ ጭምር ነው (ሮሜ 5፡8፤ ኤፌ. 2፡7-10)። ኵነኔ ሁሉ ለዘላለም የተወገደው፥ ድነትና ድኖ መኖር በእግዚአብሔር ልጅ መሥዋዕትነትና ምግባር ላይ ብቻ የሚደገፉ በመሆናቸው ነው (ዮሐ. 3፡18፤ 5፡24፤ ሮሜ 8፡1፤ 1ኛ ቆሮ. 11፡31-32)። 

2. የክርስቶስ ትንሣኤ ፥ ሰሞቱ ላይ Pተደረገ የእግዚአብሔር ማኅተም እንደመሆ ኑ፥ ለአማኛች የትንሣኤንና የሕይወትን ዋስትና ይሰጣል (ዮሐ. 3፡16፤ 10፡28፤ ኤፌ.2፡6)። ከክርስቶስ ትንሣኤ ጋር የተያያዙት ሁለት ዋነኛ እውነቶች የአማኙን ዘላለማዊ ዋስትና ያረጋግጣሉ። የእግዚአብሔር ስጦታ ዘላለማዊ ሕይወት ሲሆን (ሮሜ 6፡23)፥ ያም የክርስቶስ የትንሣኤ ሕይወት ነው (ቈላ. 2 ፡12፤ 3፡1)። ይህ ሕይወት ክርስቶስ ዘላለማዊ እንደሆነ ሁሉ ዘላለማዊ ነው። ክርስቶስ ሊያከትም ወይም ሊጠፋ እንደማይችል ሁሉ፥ ይህ ሕይወት ሊያከትም ወያም ሊጠፋ አይችልም። የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው በክርስቶስ ትንሣኤ፥ በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና የዘላለምን ሕይወትን በማግኘት አማካይነት የአዲሱ ፍጥረት አካል ሆኗል። ፍጡር የእግዚአብሔር ክቡር የፈጠራ ሥራ እንደመሆኑ የተፈጥሮን ሂደት ሊቀይር አይችልም። በኋለኛው አዳም በተመሰለው ክርስቶስ ውስጥ ሰመሆኑም፥ ሊቀየር አይችልም፥ ክርስቶስ ሊወድቅ አይችልምና ኦይወድቅምም። ምንም እንኳ በክርስትና ሕይወትና ልምምድ ውስጥ መውደቅ ያለ ሲሆን፥ ሁኔታዎቹ አማኝ በክርስቶስ ያለውን ስፍራ እያቀይሩትም። የእማኝ ስፍራ ከእግዚአብሔር ጸጋ፥ እንዲሁም ከክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ የተነሣ የተቀደሰ ነው። 

3. ክርስቶስ ጠበቃችን በመሆን በሰማያት የሚያከናውነው ተግባርም ዘላለማዊ ዋስትናችንን ያረጋግጣል (ሮሜ 8፡34፤ ዕብ. 9፡24፤ 1ኛ ዮሐ. 2፡1)። ክርስቶስ የእማኝ ጠበቃ ወይም ሕጋዊ ወኪል ነው። ስለዚህ የጌታ የመስቀል ላይ ሥራ ለሥርየትና እግዚአብሔር ከኃጢአተኛው ለሚጠይቃቸው ነገሮች መሟላት ብቁ ነው። ስለሆነም በክርስቶስ አማካይነት ለኃጢአተኛው ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ በቂ ዋጋ እንደተካፈለ ሰመቁጠር ይማልዳል። የክርስቶስ ሥራ ፍጹም ስለሆነ፥ ማንኛውም እውነተኛ አማኝ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይ እንደ አማኙ ተወካይ ሳቀረበው ሥራ ፍጹምነት ዋስትና ሥር ሊያርፍ ይችላል። 

4. የክርስቶስ የአማላጅነት ሥራ ሰጠቃነቱ ተግባር ተጨማሪ ማረጋጋጫ ይሆናል (ዮሐ. 17፡1-26፤ ሮሜ 8፡34፤ ዕብ. 7፡23-25)። በአሁኑ ጊዜ ክርስቶስ በሰማያት በክብሩ የሚያበረክተው አገልግሎት በምድር ከሚገኙ እማኞች ጋር የተያያዘ ነው። ክርስቶስ እንደ ጠበቃችን የመማለድና የማገልገል ተግባራትን ያከናውናል። እንደ አማላጅነቱ የአማኙን ድካም፥ አለማወቅና አለመብሰል ያያል። እነዚህ ከአማኙ በደለኛነት ጋር የማይዛመዱ ናቸው። ክርስቶስ በዚህ አገልግሎቱ በዓለም ለሚገኙ ወገኖቹ መሻት መጸለይ ብቻ ሳይሆን {ሉቃስ 22 ፣ 31-32፤ ዮሐ. 17፡9፥ 15፥ 20፤ ሮሜ 8፡34)፥ ዘላለማዊ የድነት ዋስትና ይሰጣቸዋል (ዮሐ. 14፡19፤ ሮሜ 5፡10፤ ዕብ. 7፡25)። ይህም ሰርሱ ብቃት ላይ በተመሠረተው የማይለወጥ ክህነት አማካይነት የሚከናውን ነው። 

ክርስቶስ በሞቱ፥ በትንሣኤው፥ በጠበቃነቱና በአማላጅነቱ ያከናወነው ተግባር በእንድነት ሲወሰድ፥ በመስቀልና በሰማይ ለወከለው አማኝ ፍጹም ዋስትናን ይሰጣል። ድነት ሰው ለእግዚአብሔር የሚሠራው ሳይሆን፥ እግዚአብሔር ለሰው የሚሠራው ከሆነ፥ ውጤቱ የተረጋገጠ እውነት ነው። አማኝ “ወደ ኩነኔ እንደማይመጣ” የሚናገረው የዮሐንስ 5:24 የተስፋ ቃልም ያለ ጥርጥር ይፈጸማል። 

መ. የመንፈስ ቅዱስ ሥራ 

1. እማኝ የመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋይ የሚሆንበት የዳግም ልደት ወይም የአዲስ ልደት ክንውን የማይለወጥ ሂደት ያለው የእግዚአብሔር ሥራ ነው (ዮሐ. 1፡13፤ 3፡3-6፤ ቲቶ 3፡4-6፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡23፤ 2ኛ ጴጥ. 1፡4፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡9)። የተፈጠረኝ ፍጡር እንዳልተፈጠረ ማድረግ እንደማይቻል ሁሉ፥ አዲስ ልደት ያገኘንም እንዳልተወለደ እድርጎ መመለስ አይቻልም። ተግባሩ የሚከናወነው በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር ከሆነና፥ ሙሉ ለሙሉ በጻጋ ላይ ከተመሠረተ፥ ለዘላለም የማይቀጥልበት ምክንያት እይኖርም። 

2. ስአሁኑ ዘመን በውስጡ የሚያድረው መንፈስ ቅዱስ የእግኙ ዘቂ ሀብት ነው ( ዮሐ. 7፡37-39፤ ሮሜ 5፡5፤ 8፡9፤ 1ኛ ቆሮ. 2፡12፤ 6፡19፤ 1ኛ ዮሐ. 2፡27)። ከበዓለ ኀምሳ ቀን በፊት እውነተኛ አማኞች ሁሉ የድነት ዋስትና ቢኖራቸውም፥ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ አልሆንም ነበር። በአሁኑ ዘመን ግን፥ ምንም እንኳ ኃጢአተኛና የተበላሸ ሲሆን፥ የአማኙ ሰውነት የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሆኑ፥ እግዚአብሔር አማኙን ማዳን የጀመረውን ዓላማ ከግቡ የሚያደርስ ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው። መንፈስ ቅዱስ ንስሐ ባልተገባበት ኃጢአት የሚያዝን (ኤፌ. 4፡30) እና የሚጠፋ ወይም የሚዳፈን ቢሆንም {1ኛ ተሰ. 5፡19)፥ እነዚህ ሁኔታዎች አማኝ ድነቱን እንዲያጣ የሚያደርጉ መሆናቸውን በፍጹም አያሳይም። ይልቁንም የአማኙ ድነት አለመቋረጥና ልቡ ውስጥ የሚሠራው የመንፈስ ቅዱስ እውነት ከእግዚአብሔር ጋር ወደሚስማማ ኅብረት እንዲመለስ የሚያነሣሣ መሠረት ሆኖ ቀርሷል። 

3. አማኝ ከክርስቶስና ከክርስቶስ አካል ጋር ለዘላለሙ የተጣመረበት ቀመንፈስ ቅዱስ የጥምቀትራ ሌላው ያዋስትና ማረጋገጫ ነው። አማኝ በመንፈስ ቅዱስ የማጥመቅ ሥራ፥ ክርስቶስ ራስ ወደሆነበት አካል ይጨመራል (1ኛ ቆሮ. 6፡17፤ 12፡13፤ ገላ. 3፡27)። ስለዚህም አማኝ በክርስቶስ አካል ውስጥ ነው ይባላል። ክርስቶስ ውስጥ መሆኑ ዋንኛና ቀጣይነት ያለውን ኅብረት ያመለክታል። በዚህ ኅብረት አማካይነት በስፍራና በግንኙነት የኩነኔ መሠረት የሚሆኑ አሮጌ ነገሮች ይወገዱና ሁሉም ስፍራዎችና ግንኙነቶች አዲስና ከእግዚአብሔር የተገኙ ሆነው ይለወጣሉ (2ኛ ቆሮ. 5፡17፥ 18)። የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው “በተወደደው” ጌታ አማካይነት ለዘላለም ተቀባይነትን ስላገኘ በተቀበለው ጌታ ውሰጥ ለዘላለም የመሆኑ እውነት የጸና ነው። ያስገኘለት ስፍራ የውስጡ ያለውንና የቆመበትን ስፍራ ያህል ዋስትና አለው። 

4. የመንፈስ ቅዱስ በአማኙ ውጥ መኖር እስከመቤት፥ እስክ አማኙ መለወጥ ወይም ትንሣኤ ድረስ የእግዚአብሔር ማኅተም እንደሆን ተጎልሟል (2ኛ ቆሮ. 1፡22፤ ኤፌ. 1፡13-14፤ 4፡30)። ይህ የመንፈስ ቅዱስ ማኅተም የእግዚአብሔር ሥራ ነው። ስለሆነም፥ እግዚአብሔር አማኙን በመንግሥተ ሰማይ እንከን የሌስው አድርጎ እስከሚያቀርብበት ጊዜ ድረስ የአማኙ ዋስትና የታተመ መሆኑን ያመለክታል። ይህ አንድ ጊዜ የዳነ አማኝ ድነቱን የማያጣ መሆኑን እርግጠኛ እንድንሆን ያደርጋል። 

በአጠቃላይ የአማኝ ዘላለማዊ ዋስትና በድነቱ ሁኔታ ላይ የሚመሠረትና የሰው ሳይሆን የእግዚአብሔር ሥራ ነው። የሰው ብርታት ወይም ታማኝነት ላይ ሳይሆን፥ በእግዚአብሔር ኃይልና ታማኝነት ላይ ይመሠረታል። ድነት በሥራ የሚገኝ ወያም ሥራ እንደ ሰናይ ምግባር ታይቶ ለእምነት ሽልማት የሚሰጥ ቢሆን ኖሮ፥ የሰው ዋስትና ምን ያህል አጠያያቂ ይሆን እንደነበር ለመገመት ይቻላል። ከዚህ ይልቅ በጻጋ፥ ብሎም በእግዚአብሔር የተስፋ ቃላትና ሥራ ላይ የሚመሠረት በመሆኑ፥ እማኝ ስለ ዋስትናው እርግጠኛ ሊሆንና ከጳውሎስ ጋር “በእናንተ መልካሙን ሥራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን ተረድቼአለሁ” (ፊልጵ. 1፡6) ሊል ይችላል። 

ከዚህ ታላቅ እውነት በመነሣት እግዚአብሔር የራሱ የሆኑትን ለመጠበቅ ያለው ዓላማ ከቶውንም አይታጠፍም ብሎ ለማጠቃለል ይቻላል። ለዚህ ፍጻሜ መገኘት እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮችን ሁሉ እግዚአብሔር ራሱ አስወግዷቸዋል። አማኙን ከእግዚአብሔር ይለይ የነበረው ኃጢአትም ተወግዷል። ኃጢአታችንን የተሸከመልን ጌታም እማኝ በድነቱ ይዘልቅ ዘንድ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት የሞቱን ብቃት እያሳየ በመማለድ ላይ ነው። የአማኙ ፈቃድ (ፊልጵ. 2፡13)፥ በመለኮታዊ ቁጥጥር የተያዘ ሲሆን፥ በእግዚአብሔር ጸጋና ጥበብ የሚቻል ወይም የቀላለ ይሆናል (1ኛ ቆሮ. 10፡13)። 

በዚህ ምዕራፍ ጅነትንና በድነት መጠበቅን እንደተለያዩ መለኮታዊ ተግባራት ሲገለጡም፥ እንዲህ ያሉ ልዩነቶች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሉም። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አገላለጥ፥ በጸጋ ሥር የሚታቀድ፥ የሚሰጥ ወይም ተግባራዊ የሚሆን ድነት ሁሉ ሙሉ ለሙሉ ፍጹምና ዘላለማዊ ነው። 

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

34
ትምህርት 34 ከ52

መለኮታዊ ምርጫ

ሀ. የምርጫ ውሳኔ 

መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን የሚገልጠው፥ በራሱ ምርጫ ዓለማትን እንደፈጠረና አስቀድሞ ባቀደው መሠረት ታሪክን የሚመራ ፍጹም ሉዓላዊ አምላክ መሆኑን ነው። እግዚአብሔር ሉዓላዊና ደስ ያሰኘውን የማድረግ ብቃት ያለው መሆኑ የሚታመነው፥ ሁሉን ቻይና የማይደረስበት አምላክ ከመሆኑ አሳብ ጋር ተያይዞ ነው። ይሁንና ስለዚህ ዓይነቱ የእግዚአብሔር አሠራር የሰው ልጆች የሚኖራቸው የግንዛቤ አቅም ማነስ እጅግ ብዙ ችግሮችን ያስከትላል። በተለይም በእግዚአብሔር አሠራር በተፈጠረው ዓለም ሰው የቱን ያህል ሰነጻነትና በተጠያቂነት መሥራት የሚኖርበት መሆኑን መረዳቱ የዋዛ አልሆነም። 

ሰብአዊ የአስተሳሰብ ዘዴዎች የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ዓላማ በፍጹማዊነት ወደሚስተናገድበት ወይም ደግሞ የእግዚአብሔር ቁጥጥር እስኪነጋ ድረስ የሰው ነጻነት ወደሚጋነንበት እክራሪ የአስተሳሰብ ዘዬዎች ሲያጋድሉ ኖረዋል። እንዲህ ዓይነቱን አስቸጋሪ ጉዳይ ለማቃለል ብቸኛው መፍትሔ፥ መለኮታዊውን መገለጥ መጠየቅና ሰብእዊውን ልምምድ መጽሐፍ ቅዱስ በሚያስተምረው መሠረት ለመፍታት መሞከር ነው። 

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተገለጠው፥ የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ዓላማ ግለሰቦችንም ሆነ አገሮችን ይመለከታል። እስራኤል በእግዚአብሔር የተመረጠ ሕዝብ መሆኑ ተገልጧል (ኢሳ. 45፡4፤ 65 : 9፥ 22)። “ምርጥ” የሚለው ቃል ለድነት ለተመረጡ ሰዎች መጠሪያነት በተደጋጋሚ አገልግሷል (ማቴ. 24፡22፥ 24፥ 31፤ ማር. 13፡20፥ 22፥ 27፤ ሉቃስ 18፡7፤ ሮሜ 8፡33፤ ቆላ. 3፡12፤ 1ኛ ጢሞ. 5፡21፤ 2ኛ ጢሞ. 2፡10፤ ቲቶ 1፡1፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡2፤ 5፡13፤ 2ኛ ዮሐ. 1 እና 13)። ስለ ክርስቶስም ይኸው አገላለጥ አገልግሏል (ኢሳ. 42፡1፤ 1ኛ ጴጥ. 2፡6)። “ምርጥ” ከሚለው ቃል በተጨማሪ የምርጫ እውነታም ተጠቅሷል (ሮሜ 9፡11፤ 11፡5፥ 7፥ 28፤ 1ኛ ተሰ. 1፡4፤ 2ኛ ጴጥ. 1፡10)። ምርጫ ውስጥ የሚገኘው ፅንሰ አሳብ የሚያመለክተው፥ የተጠቀሰው ግለሰብ ወይም ቡድን ላአንድ መለኮታዊ ዓላማ መመረጡን ሲሆን፥ ብዙውን ጊዜ ከድነት ጋር ይዛመዳል። 

“ምርጥ” የሚለው ቃል ለእስራኤል (ኢሳ. 44፡1)፥ ለቤተ ክርስቲያን (ኤፌ. 1:4፤ 2ኛ ተሰ. 2: 13፤ 1ኛ ጴጥ.2፡9)፥ ለሐዋርያት መጠሪያነት (ዮሐ. 6፡70፤ 13፡18፤ ሐዋ. 1፡2) አገልግሏል። 

ምርጫን በተመለከተ የተለያዩ ገለጣዎች አሉ፤ ለምሳሌ አስቀድሞ ማወቅን (ሮሜ 8፡29-30፤ ኤፌ. 1፡5፥ 11፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡20)፥ የመሳሰሉ በሐዋርያት ሥራ 4፡28 እንደተመለከተው ቅድመ ውሳኔን፥ ወይም ይሁዳ 4 እና ኤፌሶን 2፡10 ውስጥ እንደተጠቀሰው ቅድመ ስያሜን ያመለክታል። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደ 2ኛ ዜና 25፡16፥ ኢሳይያስ 19፡17፤ ሉቃስ 22፡22፥ የሐዋርያት ሥራ 17፡26 በመሳሰሉ ስፍራዎችም ይኸው “ውሳኔ” የሚለው ፅንሰ-አሳብ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል። በዚህ ሁሉ ቃላት ሊተላለፍ የተፈለገው መልእክት፥ የእግዚአብሔር ምርጫ ተግባርን የሚቀድምና በራሱ ሉዓላዊ ፈቃድ የሚወሰን መሆኑን ነው። 

ምርጫ፥ ቅድመ ስያሜና ቅድመ ውሳኔ እንደ እግዚአብሔር መለኮታዊ ዓላማ የሚከናወኑ ሲሆኑ (ኤፌ. 1፡9፤ 3፡11)፡መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከእግዚአብሔር ቅድመ ግንዛቤ ጋር የተያያዙ ናቸው (ሐዋ. 2፡23፤ ሮሜ 8፡29፤ 11፡2፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡2)። “ጥሪ” የሚለው ቃልም ሮሜ 8፡30 እና ሌሎችም በርካታ ምንባቦች ውስጥ ተጠቅሷል (1ኛ ቆሮ. 1፡9፤ 1፡18፥ 20-21፥ 22፥ 24፤ 15፡9፤ ገላ. 5፡13፤ ኤፌ. 4፡1፥ 4፤ ቆላ. 3፡15፤ 1ኛ ጢሞ. 6፡12፤ ዕብ. 5፡4፤ 9፡15፤ 1ኛ ጴጥ. 2፡21፤ 3፡9፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡1)። “ጥሪ” ስዎችን ወደ እግዚአብሔር መሳብ መሆኑን ጌታችን ዮሐ፡12፡32 ውስጥ አመልክቷል (ከዮሐንስ 6፡44 ጋር ያነጻጽሩት)። እነዚህ ሁሉ ምንባቦች የሚያስገነዝቡን ሉዓላዊው አምላክ ዓላማውን በማሳካት ላይ መሆኑን ነው። የተወሰኑ ግለሰቦች በዚሁ ዓላማው መሠረት ለድነት የተመረጡ ሲሆን፥ የተወሰኑ ሕዝቦችም መለኮታዊውን ልዩ ዓላማ ለማሳካት እንዲሁ ተመርጠዋል። በተለይ እስራኤላውያን የተለየ መለኮታዊ ዓላማ ለማገልገል ተመርጠዋል። 

ለ. የመለኮታዊ ምርጫ እውነትነት 

ምንም እንኳ የምርጫ እስተምህሮ ከስብእዊ ግንዛቤ ሰላይ ሲሆን፥ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ መሆኑ ግን አያጠያይቅም። እግዚአብሔር በመለኮታዊ ምርጫው የተወሰኑ ግለሰቦችን ለድነት በመምረጥ፥ የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስን ባሕርይ ይመስሉ ዘንድ ወስኗል (ሮሜ 16፡13፤ ኤፌ. 1፡4-5፤ 2ኛ ተሰ. 2፡13፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡2)። ምርጫ ከእግዚአብሔር መሆኑና የዘላለማዊ ዕቅዱ እካል መሆኑ ግልጥ ነው። 

መለኮታዊ ምርጫ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዓላማ አካል እንጂ፥ ሰው ከተፈጠረ በኋላ የተወሰነ አይደለም። ይህም “ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን” በሚለው ኤፌሶን 1፡4 እና ሌሎች ብዙ ምንባቦች ውስጥ ተገልጧል። 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡9 እንደሚለው ደግሞ፥ መመረጣችን “እንደራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው። ይህም ጳጋ ከዘላለም በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን።” የእግዚአብሔር ዕቅድ ዘላለማዊ በመሆኑ፥ ምርጫም በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዕቅድ ውስጥ ሆኖ ዘላለማዊ ነው። 

ሰምርጫ አስተምህሮ ውስጥ ከሚገኙ ውስብስብ ችግሮች እንዱ ምርጫ ከቅድመ ግንዛቤ ጋር ግንኙነት ያለው መሆኑ ነው። የምርጫን ፅንሰ-አሳብ አለሳልሶ የሚያቀርሰው አንድ የአተረጓጎም ስልት፥ እግዚአብሔር በክርስቶስ የሚያምኑትን ቀደም ብሎ ያውቅ ስለነበር፥ በዚሁ እውቀት ላይ ተመሥርቶ ለድነት መርጧቸዋል በሚለው አሳብ ዙሪያ ትንታኔውን ያቀርባል። ይሁንና፥ ይህ አሳብ እግዚአብሔርን ራሱ ሉዓላዊ ላልሆነበት ዕቅድ ተገዥ አድርጎ የሚያቀርበው ስለሚመስል ችግሮች አሉበት። ምንም እንኳ ምርጫና ቅድመ ግንዛቤ ተያያዥነት ቢኖራቸው፥ ቅድመ ግንዛቤ በራሱ ወሳኝ አይሆንም። 

ምንም እንኳ የሥነ-መለኮት ምሁራን ከነዚህ ችግሮች ጋር ታግለው ከአርኪ ድምዳሜዎች ላይ ለመድረስ ባይችሉ፥ መፍትሔ ሊሆን የሚችለው አንድ ነገር የእግዚእብሔርን ሁሉን አዋቂነት ማለት፥ ለዓለማት የሚያሻቸውን ዕቅድ ሁሉ እንደሚያውቅ ከመገንዘብ መጀመሩ ነው። ስፍር ካሌሳቸው ዕቅዶች ውስጥ እግዚአብሔር አንዱን መረጠ። አንድን ዕቅድ በመምረጥና የዕቅዱን ዝርዝር በማወቅ፥ እግዚአብሔር የሚድኑትንና የሚመረጡትን እስቀድሞ ሊያውቅ፥ ከድነታቸው ጋር የሚዛመዱ እውነታዎችንም ሊገነዘብ ይችላል። 

ይህን የእግዚአብሔር ቃል ለመተርጎም የሚሞክር ሰው የሚገጥመው ችግር የሰው ልጅ ነጻነት ጉዳይ ነው። ከልምድም ሆኝ ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደሚታየው፥ ሰው ምርጫዎች አሉት። ይሁን እንጂ፥ ሁሉም ነገር አስቀድሞ የተወሰነበት ከሆነ፥ ሰው በራሱ ጤናማና ነጻ የሆነ ሥነ-ምግባራዊ ምርጫ ለማድረግ እንዴት ይቻላል? ይህ ከሆነስ ሰብአዊ ተጠያቂነት እንዴት ትዕከል ይሆናል? በዚህ አስቸጋሪ አስተምህሮ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚ የሚያጋጥሙት ችግሮች እነዚህ ናቸው። 

የሥነ-መለኮት ምሁራን መለኮታዊ ምርጫ ከሰብአዊ ምርጫዎችና ሥነ-ምግባራዊ ተጠያቂነት ጋር በተዛመደ መልኩ ያለበትን ችግር እስከዛሬ ሙሉ በሙሉ ለማቃለል አልቻሉም። ይሁንና፥ ችግሩ እልባት የሚያገኘው፥ እግዚአብሔር የመረጠውን ዕቅድ በዘፈቀደ ሳይሆን፥ ሙሉ ለሙሉ በመምረጥ ይመስላል። ሰዕቅዱ ማን እንደሚድንና ማን እንደማይድን ዕቅዱን ከመምረጡ በፊት አውቋል። እግዚአብሔር ከሁሉም የተሻለውን ዕቅድ እንደመረጠ በእምነት መቀበል እለብን። ከዚህ የተሻለ ዕቅድ ቢኖር ኖሮ እግዚአብሔር ያን ይመርጥ ነበር። ዕቅዱ በአብዛኛው እግዚአብሔር ራሱ የሚሠራቸውን ነገሮች አካቷል። እነዚህም እንደ ፍጥረትና የተፈጥሮ ሕግ መደንገግን የመሳሰሉ ናቸው። ዕቅዱ እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ ራሱ የሚፈጽማቸውን ነገሮች፥ ማለትም በነቢያት አማካይነት ራሱን በመግለጥ ሰዎች ምንም እንኳ ስለምርጫቸው ተጠያቂ ቢሆኑ፥ መልካም ምርጫ እንዲኖራቸው ጫና ማድረግን የሚያካትት ነበር። 

በሌላ አባባል፥ ዕቅዱ ሰው ስምርጫው በኃላፊነት የሚጠየቅበትን የተወሰነ ነጻነት አካቷል ማለት ነው፡እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ዕቅዱ ሰው ምን እንደሚያደርግ ማወቁ፥ እያንዳንዱ ሰው የማይፈልገውን እንዲያደርግ የሚያስገድደውና ለድርጊቱም የሚቀጣው መሆኑን አያመለክትም። 

የእግዚአብሔር ዕቅድ ሁሉ በተካተተበት የክርስቶስ መስቀል ወቅት፥ ጲላጦስ በነጻነቱ ተጠቅሞ ክርስቶስን ለመስቀል መርጧል፤ ለዚህም ምርጫው ተጠያቂ ሆኗል። የአስቆሮቱ ይሁዳም ክርስቶስን አሳልፎ ለመስጠት ነጻ ውሳኔ አድርጓል። ነጻ ውሳኔውም በኃላፊነት እንዲጠየቅ አድርጎታል። ይሁንና፥ የይሁዳም ሆነ የጲላጦስ ምርጫዎች የእግዚአብሔር ፕሮግራም አካላት በመሆናቸው፥ ሰዎቹ ሳይፈጽሟቸው ሰፊት ይታወቁ ነበር። 

ስለሆነም፥ ከሰብአዊ ግንዛቤ ረገድ ችግሮች ቢኖሩም፥ ከሁሉም የሚሻለው መፍትሔ ቢገባንም ሳይገባን መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን እውነት መቀሰሉ ነው። 

ምርጫና ከዚሁ ጋር የሚመሳሰሉ ቃላት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጥ ቀርበዋል ብሎ ለመደምደም ይቻላል። ይህም አንዳንዶች ድነት እንደተመረጡና ሌሎች ግን ሳይመረጡ መታለፋቸውን የሚያመለከት ነው። ምርጫ ዘላለማዊ የእግዚእብሔር ተግባር ነው። ምርጫ ከእግዚአብሔር ሁሉን አዋቂነት ጋር ይያያዛል። ይህንን አስተምህሮ፥ ሙሉ ስሙሉ መረዳት ባይቻልም እንኳ፥ ስመለኮታዊው መገለጥ መገዛቱ ተገቢ ነው። 

ሐ. የምርጫ አስተምህሮ መረጃ 

ምንም እንኳን አንዳንድ የሥነ-መለኮት ምሁራን መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ክደው የምርጫን አስተምህሮ ሰማግለል ችግሩን ለመፍታት ቢጥሩ፥ መለኮታዊ ምርጫን በመቃወም የሚሰነዘሩ የመሟገቻ ነጥቦች ባብዛኛው አሳቡን ባለመረዳት ላይ የተመሠረቱ ናቸው። ብዙ ጊዜ ምርጫ እግዚአብሔር ያለ ምንም በቂ ምክንያት እንደሚሠራው ተደርጎ ይነገራል። ይህ አባባል የሚመነጨው ካለማመን ነው። እግዚአብሔር ሉዓላዊ ሲሆን፥ ሉዓላዊነቱ ሁልጊዜ ጥበብ፥ ቅድስና፥ በጎነትና ፍቅር የተሞላ ነው። 

ብዙ ጊዜ የሚሰነዘረው ሌላ ተቃውሞ ደግሞ፥ አንዳንዶች በእግዚአብሔር የድነት ዓላማ ውስጥ አለመካተታቸው፥ እግዚአብሔርን ፍትሕ አልባ እንደሆነ ተደርጎ የሚገለጠው ነው። እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ነገር፥ እግዚአብሔር ማንንም የማዳን ግዴታ እንደሌለበትና የሚያድናቸው ሰዎች ደግሞ የሚያምኑ መሆናቸው ነው። አንድ ሰው በክርስቶስ አምኖ የሚድንበት ሁኔታ የእግዚአብሔር አሠራር ምሥጢር ሲሆንም፥ መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች እንዲያምኑ በግልጥ ያዛቸዋል (ሐዋ. 16፡31)። ማንም ከፈቃዱ ውጭ አይድንም። ማንም ያለ ፈቃዱ አላምንም የሚል የለም። በሁለቱም ውስጥ የሰው ፈቃድ አለው። 

ይህን አስተምህሮ አስመልክቶ ዘወትር የሚሰነዘረው ተቃውሞ፥ ከድነት ስራቁ ሰዎች ወንጌል የማድረሱን አገልግሎት እንደሚያዳክምና፥ ለመዳን የሚፈልጉትንም ተስፋ የሚያስቆርጥ መሆኑ ነው። የዚህ መልሱ እግዚአብሔር ለፍጥረት ሁሉ ወንጌል እንዲሰበክ በዕቅዱ ውስጥ ማካተቱና፥ የሰውን ሁሉ መዳን የሚሻ መሆኑን መገንዘቡ ነው (2ኛ ጴጥ. 3፡9)። ይሁን እንጂ፥ ሰዎች ለማመንም ሆነ ላሰማመን የሚመርጡበት ሁለንተናዊ ሕሊና የተሰጣቸው እስከሆነ ድረስ አንዳንድ ሰዎች አለመዳናቸው አይቀሬ እውነት ነው። 

ሌላው ተቃውሞ፥ አንዳንዶች ለድነት ከተመረጡና ሌሎች ግን ላላመዳን ከተመረጡ፥ ያልተመረጡት ተስፋ የሌላቸውና የጠፉ ናቸው የሚል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው፥ ድነትን የሚፈልጉ ሰዎች ድነትን የሚያጡት ሊያገኙት ባለመቻላቸው ሳይሆን፥ ለመዳን በመምረጣቸው መሆኑ ነው። ሮሜ 9፡21-22 እና 2ኛ ጴጥሮስ 3፡9 ውስጥ እንደተመለከተው፥ የእግዚአብሔር ምሕረት ትዕግሥቱ ውስጥ ታይቷል። ማንም ቢሆን በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ፥ “እኔ ልጅን ፈልጌ ነበር፤ ዳሩ ግን ስላልተመረጥሁ ይህን ላደርግ አልቻልሁም” የሚልበት ወቅት ከቶ አይኖርም። 

ታላላቅ የሚባሉ የሥነ-መለኮት ምሁራንና ማናቸውም የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ከዚህ አስቸጋሪ አስተምህሮ ጋር መታጎላቸውን ይቀጥላሉ። የመለኮታዊ ምርጫ እውነት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጥ ቀርቧል። የዳኑ ሰዎች ምንም እንኳ በዳኑበት ወቅት አስተምህሮውን ሳያውቁትም፥ ከዘላለም በፊት በእግዚአብሔር ዕቅድ ውስጥ የነበሩ መሆናቸውን ያድርጊቱ ያስገነዝባል። ይህ ድነታቸው የእግዚአብሔርን ጸጋ ታላቅነት ያሳያል። ልዑልና ዘላለማዊ የሆነ አምላክ በማንኛውም ሁኔታ ሲታሰብ የታቀደ ፕሮግራም ይኖረዋል። በመጽሐፍ ቅዱሳዊው መገለጥ መሠረት፥ አንድ አማኝ የእግዚእብሔር ዕቅድ ቅዱስ፥ በጥበብ የተሞላና መልካም መሆኑን ከማመን በቀር የሚለው አይኖርም። ይህ ብቻ አይደለም፤ እግዚአብሔር ታጋሽና ክርስቶስ የሞተበትን ድነት አሻፈረኝ ብለው ለጠፉት የሚገደው አምላክ እንደሆነም ይረዳል።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

35
ትምህርት 35 ከ52

ቤተ ክርስቲያን፡- ምእመኖቿ

ሀ. ቤተ ክርስቲያን- የዚህ ዘመን የእግዚአብሔር ዓላማ 

ቤተ ክርስቲያን የዚህ ዘመን የእግዚእብሔር ማዕከላዊ ዓላማ መሆኗ እዲስ ኪዳን ውስጥ ተገልጧል። እግዚአብሔር ለብሉይ ኪዳን ግለሰቦችና አገሮች ከነበሩት ዓላማዎችና ለእስራኤልም ከነበረው ሰፋ ያለ ዓላማ ጋር ሲነጻጸር፥ ቤተ ክርስቲያን ከሌሎች ሕዝቦችና ከአይሁዶች የተዋቀረች የአማኞች አንድነት ሆና ተገልጣለች። እነዚህም ከዓለም ተጠርተው በመውጣት በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካይነት ሕያው አንድነት የተሳሰሩ ናቸው። 

በአጠቃላይ፥ የቤተ ክርስቲያን ፅንሰ-አሳብ በሁለት ዓበይት ምድቦች ይከፈላል። አዲስ ኪዳን ውስጥ የምንመለከተው የመጀመሪያ ፅንሰ-አሳብ፥ ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ውስጥ የሚገኙ እውነተኛ አማኞች ሁሉ ሕያው ጥምረት መሆኗን ነው። ይህም መንፈስ ቅዱስ ከወረደበት ዕለተ ጰንጠቆስጤ አንሥቶ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያኑ ዳግም በመመለሱ የሚደመደም ልዩ እውነት ነው። ጌታ በሚመለስበት ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ከዓለም መነጠቅ ወደ ሰማይ ትወሰዳለች። 

ሌላው ፅንሰ-አሳብ፥ ስለ አጥቢያ ወይም ስለ ተደራጀች ቤተ ክርስቲያን የተገለጠው ነው። ይህ በአንድ አጥቢያ የሚገኙ አማኞች ወይም ይህን የመሰሉ ጉባኤዎች የአማኞች ስብሰብ ነው (1ኛ ቆሮ. 1፡2፤ ገላ. 1፡2፤ ፊልጵ. 1፡1)። 

ቤተ ክርስቲያን” የሚለው ቃል “ኤክሌዢያ” ከሚለው ግሪክኛ የተተረጎመ ሲሆን፥ ቃሉ ለየትኛውም ዓይነት የሕዝቦች ስብሰባ ወይም ጉባኤ በተደጋጋሚ አገልግሏል። የተሰብሳቢዎቹ ዓላማ ሃያማኖታዊ ወይም ፖለቲካዊ ሊሆን ይችላል። የቃሉ ፍች ደተጠርተው የወጡ” ማለት ነው። በጥንታዊቱ ግሪክ፥ ብዙዎቹ ከተሞች የሚተዳደሩት ነጻ በሆን ዲሞክራሲ ነበር። በመሆኑም፥ እያንዳንዱ ዜጋ በጋራ ጉዳዮች ላይ ተግባራዊ እርምጃ ሰመውሰድ ይሰበሰባል። ከወትሮው ተግባራቸው ድምፅ ወደሚሰጡበት ስብሰባ ተጠርተው ሲመጡ፥ ቃሉ፥ ተጠርቶ የመውጣት ውጤት ወይም የተሰበሰቡ ሰዎች የሚል ፍች ሊሰጠው በቃ። 

ይህ ቃል የብሉይ ኪዳን የተለያዩ ጉባኤዎችን ለማመልከት የብሉይ ኪዳን የግሪክ ትርጓሜ በሆነው ሰፕቱዋጄንት ውስጥ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል። እንደ የሐዋርያት ሥራ 7፡38 እና 19፡32 በመሳሰሉ ምንባቦች ውስጥ የሰዎችን ስብስብ በሚገልጥ መልኩ ተጠቅሶ እናገኛለን። ይሁንና ቃሉ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ክርስቶስ አካል ለማመልከት በሚያገለግልበት ጊዜ ከዓለም ተጠርተው በክርስቶስ ሕያው ኅብረት የፈጠሩ ሰዎችን ለማመልከት ያገለግላል። ምንም እንኳ እስራኤላውያን አንዳንድ ጊዜ ለሃይማኖታዊ ዓላማዎች መሰባሰባቸው ቢታወቅ፥ ይሄ ፅንሰ-አሳብ ብሉይ ኪዳን ውስጥ አይገኝም። ቃሉ የዳኑትን በሚያመለክትበት ጊዜ ደግሞ የሚያመለክተው፥ በአሁኑ ዘመን በምድርም ሆነ ሰሰማይ ድነት ያገኙት ሰዎች ኅብረት ነው። 

ለ. ቤተ ክርስቲያን- የአዲስ ኪዳን መገለጥ 

ዘላሰማዊ ሕይወት በማግኘት የተባበሩ አይሁዳውያንና አሕዛብ ያሉበትን ቤተ ክርስቲያን ፅንሰ-አሳብ ከብሉይ ኪዳን ውስጥ አናገኝም፤ አዲስ ኪዳን ብቻ ነው የዚህን ዋና ጉዳይ መለኮታዊ መገለጥ የሚያስጨብጠን። በእግዚአብሔር ዕቅድ ውስጥ መጀመሪያ የክርስቶስ መምጣት፥ በመስቀል ላይ መሞት፥ ከሞት መነሣትና ወደ ሰማይ ማረግ የግድ አስፈላጊ ክንውን ነበር። የመንፈስ ቅዱስ በበዓለ ኀምሳ ዕለት መምጣት ግን፥ እግዚአብሔር በአሕዛብና በእስራኤል መካከል ልዩነት ሳያደርግ ልዩ የአማኞች ኅብረት ለመፍጠር ያለውን ዓላማ እውን አደረገበት። በዚህም መሠረት በእስራኤልና በአሕዛብ መካከል ልዩነት ሳይደረግ ሁለቱም በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዓላማ ውስጥ ስፍራ አግኝተዋል። 

በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ሁለት ውስጥ እንደተመለከተውና በዚሁ መጽሐፍ ምዕራፍ አሥር ቆርኔሌዎስ ገጠመኝ እንደተረጋገጠው፥ በክርስቶስ የሚያምኑ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀው (1ኛ ቆሮ. 12፡13) አንዳቸው የሌላው አባል ሆነዋል። ይህም በመንፈስ ቅዱስ መምጣት የተከናወነ ተግባር ነው። ከዕለተ በዓለ ኀምሳ በመለስ፥ እያንዳንዱ አማኝ ድነትን ሲያገኝ ቀደም ሲል በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ውስጥ እንደተገለጠው የክርስቶስ አካል ክፍል ይሆናል። ቤተ ክርስቲያን ዘመኗ ተፈጽሞ ወደ ሰማይ በምትነጠቅበት ጊዜ፥ መለኮታዊው ዓላማ በአይሁዶችና ሰአሕዛብ መካከል ወዳለው የተለመደ ልዩነት ይመለሳል። ይህ ከመነጠቅ በኋላ በሚኖረው የመከራ ወቅትና በሺህ ዓመቱ መንግሥት ውስጥ የሚያምኑትን አይሁዶችና አሕዛብ የሚመለከት ነው። 

ሐ. አይሁድ፥ አሕዛብና ቤተ ክርስቲያን 

በአሁኑ ዘመን፥ ሦስት ዓበይት ሰብአዊ ክፍፍሎች እንዳሉ መጽሐፍ ቅዱስ ይዘረዝራል። እነዚህም አይሁዶች፥ አሕዛብና ቤተ ክርስቲያን ናቸው (1ኛ ቆሮ. 10፡32)። እግዚአብሔር ለዚህ ዘመን ያለውን ዓላማ ለመረዳት እነዚህን ልዩነቶች ማጤኑ እጅግ 

እስፈላጊ ነው። 

1. አይሁዶች ወይም እስራኤላውያን ከአብርሃም አብራክ ወጥተው ለይስሐቅና በያዕቆብ የዘር ሐረግ የተዋለዱ ሲሆኑ፥ ከመለኮታዊ ዓላማና የተስፋ ቃል የተነሣ የተመረጡ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ናቸው። የአይሁድ ሕዝብ እስካሁን በተአምራዊ መንገድ ተጠብቆ የቆየ ሲሆን፥ በሚመጣው የእግዚአብሔር መንግሥት ዘመን በምድር ላይ ኃያልና የተከበረ ሕዝብ እንደሚሆን ትንቢቶች ያስረዳሉ (ኢሳ, 62፡1-12)። 

ያህዌ ለነዚህ ሕዝቦች የገባላቸው ዘላለማዊ የተስፋ ቃላት ሊለወጡ አይችሉም። የተስፋ ቃላቱ ከሚያካትቷቸው ነገሮች መካክል ብሔራዊ ነጻነት (ኤር. 31፡36)፥ መሬት (ዘፍጥ. 13፡15)፥ ዙፋን (2ኛ ሳሙ. 7፡13) ፥ ንጉሥ (ኤር. 33፡20-21) እና መንግሥት (2ኛ ሳሙ. 1፡16) ይገኙባቸዋል። እነዚህ ምድራዊ ባሕርይ ያላቸው የተስፋ ቃላት በእግዚአብሔር ታማኝነት እስካዛሬ በመፈጸም ላይ ናቸው። ተስፋዎቹ ዘላለማዊ በመሆ ናቸው ለዘላለም እንዲሁ ይፈጸማሉ። በነዚህ ሕዝቦች የሚፈጸመውን የመለኮታዊ ዓላማ አሠራር የሚከተሉት አራት ቃላት ይገልጧቸዋል፡- “የተመረጡ”፥ “ተበተኑ”፥ “የተሰበሰቡ” እና “የተባረኩ”። አይሁዶች በእግዚአብሔር መመረጣቸውና አሁን በምድር ሕዝቦች ሁሉ መካከል መበታተናቸው ግልጥ ነው። መሰባሰባቸውና መባረካቸው ግን አይቀሬ ነው። የዚህ ሕዝብ ልዩ እገልግሎት ሮሜ 9፡4-5 ውስጥ ተገልጧል (ከዘፍጥረት 12፡3 ጋር ያነጻጽሩት)። 

አሕዛብ እስራኤላውያንን ሳይጨምሩ ከአዳም ዘመን እሰከ ዛሬ የኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ሲሆንተቆጥረው እስከማይለቁ ድረስ እጅግ ብዙ ናቸው። ከተወሰኑ ግለሰቦች በስተቀር፥ ከአዳም እስከ ክርስቶስ ዘመን በነበረው የጊዜ ገደብ እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ምን ዓይነት ልዩ ግንኙነት እንዳደረገ ወይም ምን ዓይነት የቅርብ የተስፋ ቃላት እንዳደረገ የሚያመለክት ዘገባ አናገኝም። ወደፊት በምድር ላይ በሚመሠረተው መንግሥት ውስጥ ግን፥ አሕዛብ ታላቅ ምድራዊ በረከቶችን እንደሚያገኙ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ያመለክታሉ። በአሁኑ ዘመንም አሕዛብ ከእይሁዳውያን ጋር የወንጌሉ ዕድል ተካፋዮች ናቸው። 

3. ቤተ ክርስቲያን ሚያመለክተው፥ የተደራጀችን አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እባልነት ሳይሆን፥ በአሁኑ ዘመን ያሚድኑትን ሰዎች አጠቃላይ ኅብረት ነው። እነዚህ ሰዎች የሚከተሉት ነጥቦች ምክንያት የተለዩ ናቸው። 

ሀ) በዚያ ኅብረት ውስጥ የሚገኙ ግለሰቦች ሁሉ ዳግም የተወሰዱ በመሆናቸው፥ ወዷ እግዚአብሔር መንግሥት ይገባሉ (ዮሐ. 3፡5)። ክርስቶሰን ይመስሉ ዘንድም ከቀድሞው የተወሰኑ ናቸው (ሮሜ 8፡29)። 

(ለ) ከእንግዲህ አዳምን ተከትለው የእሮጌውን ተፈጥሮ ውድቀት የሚካፈሉ አይሆኑም (2ኛ ቆሮ. 5፡17)። ይልቁንም ክርስቶስን ተከትለው እርሱ በትንሣኤው ሕይወትና ክብር የሆነውን ሁሉ የሚሆኑ እና የአዲሱ ተፈጥሮ ተካፋዮች ናቸው (ኤፌ. 1፡3፤ ቆላ. 2፡10)። 

(ሐ) በእግዚአብሔር እይታ ዜግነታቸው ተለውጧል፤ ምክንያቱም ሰዎች አይሁዳዊ ወይም እሕዛብ ተብለው ወደማይለዩበትና ክርስቶስ ሁሉ በሁሉም ወደሆነበት አዲሰ ሕይወት መጥተዋልና(ቆላ. 3፡11)። 

(መ) አሁን የሰማይ ዜጎች ስለሆኑ (ፊልጵ. 3፡20፤ ቆላ. 3፡3)፥ የተስፋ ቃላቶቻቸው፥ ሀብቶቻቸውና ሰፍራቸው ሰማያዊ ነው (2ኛ ቆሮ. 5፡17-18)። እነዚህ ሰማያዊ ዚጎች ከምድራውያኑ በብዙ አኳኋን ይለያሉ። 

መ. ከአይሁድና ከአሕዛብ የተመሠረተች ቤተ ክርስቲያን 

የአይሁዶችና የአሕዛብ ምድራዊ ስፍራ ቀደም ብሎ ተገልጧል። በተጨማሪም እግዚአብሔር በአሁኑ ዘመን ለጸጋው ዓላማዎች አሕዛብንም ሆነ አይሁዶችን በእንድ ዓይነት መሠረት ላይ ያስቀመጣቸው መሆኑን መገንዘቡ ተገቢ ነው (ሮሜ 3:9)። ሁሉም “ከኃጢአት በታች” መሆናቸውና መዳን የሚችሉት ሰጸጋ ብቻ መሆኑ ተገልጿል። 

መለኮታዊው ፕሮግራም በክርስቶስ ሞት ተለውጧል። ይሄውም ከእንድ የተመረጠ ሕዝብ ይልቅ፥ አይሁድ ወይም አሕዛብ ሳይል ግለሰቦችን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መቀበሉ ነው። ይህ መለኮታዊ አሠራር አይሁዶች ሊገነዘቡ ያልቻሉት ነገር ነበር። ቃል ኪዳኖቹ ለጊዜው ወደ ጎን የተደረጉ እንጂ ያልተሻሩ መሆናችውን አልተረዱም። በሐዋርያት ሥራ ውስጥ እይሁዶች ይህን አለመረዳታቸውን የሚያሳይ አሳብ እናነባለን። 

አይሁዶች ካላቸው የተሳሳተ መረዳት የተነሣ በዚህ ዘመን ያለውን የእግዚአብሔር ፕሮግራም እይቀበሉትም። ቤተ ክርስቲያን እስክትነጠቅ ድረስ አይሁዶች በዚህ አስተሳሰባቸው እንደሚቆዩም ትንቢት ተነግሯል (ሮሜ 11፡25)። ከዚያ በኋላ ነጻ አውጪው ከፅዮን ስመምጣት፥ አለማመንን ከያዕቆብ ቤት ያስወግዳል። እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን እንደሚያስወግድ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን የገባበት ጉዳይ መሆኑን ይህ ያመለክታል (ሮሜ 11፡26-27)። ያም ሆነ ይህ፥ አይሁዶችም ሆኑ አሕዛብ በወንጌል ስብከት በመዳን ላይ ናቸው። ቤተ ክርስቲያንም በዚህ በመሟላት ላይ ነች። ሐዋርያው ወንጌሉ መጀመሪያ ለአይሁዶች እንዲሰበክ ያስታወቀ ሲሆን (ሮሜ 1፡16)፥ የርሱም አገልግሎት ከዚሁ ፕሮግራም አኳያ የተዋቀረ ነው (ሐዋ. 17፡1-3)። 

ቀደም ሲል እንደተገለጠው፥ ለሐዋርያው ጳውሎስ ሁሰት መገለጦች ተሰጥተውት ነበር። የመጀመሪያው የእግዚአብሔር የጸጋ ወንጌል ነው። ይህን መገለጥ የተቀበለው ምናልባት በአገልግሎቱ መጀመሪያ አካባቢ ዓረቢያ ውስጥ እያለ ሳይሆን እይቀርም (ገላ. 1፡11 -12)። ሌላው የክርስቶስ አካል ስለሆነችው ቤተ ክርስቲያን የተሰጠው መገለጥ ሲሆን፥ የተቀበለው በወኅኒ ቤት እያለ ሳይሆን አይቀርም (ኤፌ. 3፡3-6)። የሁለተኛው ምሥጢር ዋንኛ ጕዳይ እግዚአብሔር ከሁላት ምንጮች፥ ማለትም ከአይሁድና ከአሕዛብ አንድ ፡አካል በመሥራት ላይ መሆኑን የሚያመለክት ነው (ኤፌ. 2፡15)። ይህ ተሰውሮ የኖረ መለኮታዊ ምሥጢር ነው። እግዚአብሔር ለእስራኤል ወይም ላአሕዛብ ዓላማዎች እንዳሉት የብሉይ ኪዳን ትንቢት በግልጥ ያመለክታል። ይህም ከአይሁዶችና አሕዛብ እዲስ ሰማያዊ ፍጥረትን የመሥራት ምሥጢር ነው። 

ሠ. የቤተ ክርቲያን አባልነት 

“አንድ ሰው ከዳነ በኋላ የቤተ ክርስቲያን አባል ላይሆን ይችላልን?” የሚለው ጥያቄ መልስ፥ “ቤተ ክርስቲያን” ለተባለው ቃል በሚሰጠው ፍች ላይ ይደገፋል። አንድ ሰው ድነት ካገኘ በኋላ በአጥቢያ ደረጃ የተዋቀረች ቤተ ክርስቲያን አባል ላይሆን እንደሚችል እውነት ነው። ሰዎች ሁሉ የቤተ ክርስቲያን አባል ከመሆናቸው በፊት በክርስቶስ አምነው መዳን አለባቸው። ከዳኑ ደግሞ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ኅብረት ማድረግን በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ መሻታቸው ተፈጥሮአዊ ነው። 

በሌላ በኩል፥ ድነትን አግኝቶ የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን አባል አለመሆን የማይቻል ነገር ነው። ምክንያቱም በድነት ውስጥ መለኮታዊው የሥራ ድርሻ የዳነውን ሰው በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የክርስቶስ አካል ማድረግ በመሆኑ ነው (1ኛ ቆሮ. 12፡13)። ከመንፈስ ቅዱስ አሠራር ጋር በተገናኘ መልኩ እንዳገለገለው፥ ያረማጥመቅ የሚለው ቃል ከውጫዊው የውኃ ጥምቀት ሥርዓት አልፎ፥ መንፈስ ቅዱስ ለአማኝ የሚሰጠውን አገልግሎት የሚወክል ሰፋ ያለ ትርጉም አለው። ይህም የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ሰድነት ውስጥ ከሚከናወኑ ሌሎች መለኮታዊ ተግባራት ሁሉ የላቀ ውጤት ያስገኛል። ሰይጣን የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀትና፥ ጥምቀቱ የሚወክለውን መለኮታዊ አገልግሎት ግልጥ ትርጉም ማዛባቱ አስገራሚ አይሆንም። ምክንያቱም የመለኮታዊውን ጸጋ ባለጠግነት ለመረዳት ወይም ወደ ሰማያዊ ደስታ ለመግባት የምንችለው፥ በዚህ አገልግሎት ላይ በመመሥረት ብቻ በመሆኑና ከነዚህ ጸጋዎች ወደሚገኘው የተቀደሰ ሕይወት የሚገፋፋን በመሆኑ ነው። 

በምድር ላይ ቤተ ክርስቲያን ወደ ቅድስት አገር የምትጓዝ የምስክርነት ቡድን ሆና ነው የምትታየው። ክርስቶስ ከዚህ ዓለም እንዳልሆነ ሁሉ፥ ክርስቲያኖችም ከዚህ ዓለም አይደሉም (ዮሐ. 17፡16)። አብ ወልድን ወደ ዓለም እንደ ላከው፥ ወልድም እነዚህን ምስክሮች ወደ ዓለም ልኳቸዋል። በጸጋው ባለጠግነት የሚኖራቸው እውነተኛ ማንነት ገና አልታወቀም (ቆላ. 3፡4፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡2)። ቤተ ክርስቲያን፥ ማለት ቅዱሳን በሰማያዊ ስፍራ እንደ በጉ ሙሽራ፥ ከንጉሡ ጋር አብራ የምትገዛና ከዘላለማዊው የእግዚአብሔር ልጅ ክብር ዘላለማዊ ተካፋይ ሆና ትገለጣለች።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

36
ትምህርት 36 ከ52

ቤተ ክርስቲያን፡- ዓላማና ተልዕኮዋ

በአሁኑ ዘመን እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን አማካይነት ጥበቡንና ጸጋውን ለሰማያዊ ሠራዊት በመግለጥ ላይ ነው (ኤፌ. 3፡10)። ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ጸጋ ምን ሊሠራ እንደሚችል ለመግለጥ ምስክር ሆና ትቀርባለች (ኤፌ. 2፡7)። በዚህ ጠለቅ ባለ አገላለጥ መሠረት የቤተ ክርስቲያን መለኮታዊ ተልእኮ ከአጠቃላዩ አካል ይልቅ ለእያንዳንዱ አማኝ የተሰጠ ነው። እንደ ቤተ ክርስቲያን ራስነቱ ክርስቶስ እያንዳንዱን አማኝ በጌታ ፈቃድ መንገዶች የመምራት ብቃት አለው። ይህ የሚሆነው ከግል ስጦታዎቹና እግዚእብሔር ለግሰሰቡ ሕይወት ካለው ዓላማ ጋር በተስማማ መልኩ ነው። ይህ ሁሉ ታዲያ እግዚእብሔር በአሁኑ ዘመን ለቤተ ክርስቲያን ካለው እጠቃላይ ዓሳማ ጋር በመስማማት ይካሄዳል። ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአጠቃላይ እግዚአብሔር የአሁኝ መለኮታዊ ዓላማውን ሰመፈጸም ላይ ሲሆን፥ ይህም ልክ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈው በመከናወን ላይ ነው፡፡ 

ሀ. ዓለም ውስጥ የአሁኑ መለኮታዊ ዓላማ 

የዚህ ዘመን መለኮታዊ ዓላማ ዓለምን መለወጥ አይደለም። ይልቁንም በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው የክርስቶስን አካል፥ ማለትም ቤተ ክርስቲያንን የሚመሠርቱ ሰዎች መጥራት ነው። ዓለም የምትለወጥና በምድር ላይ የጽድቅ መንግሥት የሚመሠረት መሆኑ እውነት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ይህ እውነት በክርስቲያን አገልግሎት የሚመጣ አይደለም። ይህ የሚፈጸመው ክርስቶስ ሲመላስና የእርሱ በአካል መገኘትና የዓለምን ሥርዓት በመለወጥ ኃይሉ በግልጥ በሚሠራበት ወቅት ነው። 

የሰማይ አምላክ በምድር ላይ ዘላለማዊ መንግሥት የሚመሠርተው (በዳን. 2፡44-45)፥ የክርስቶስ ተምሳሌት ያለው ድንጋይ መፈንቀል የሚያመለክተው አሳብ ፍጻሜ ካገኘ በኋሳ ነው። ጌታ ተመልሶ ከክብር ዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ በኋላ ሰቀኙ የሚቆሙ በጎቹን ወደተዘጋጀላቸው ምድራዊ መንግሥት ይመራቸዋል (ማቴ. 25፡31-34)። በተመሳሳይ ሁኔታ፥ ክርስቶስ በምድር ላይ ለሺህ ዓመታት የሚነግሠው ከሰማይ ሲመጣ በግልጥ ከታየ ሰኋላ ነው (ራእይ 19፡11-20፡9ን ከሐዋ. 15 ፡13-19፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡20-25 ጋር ያነጻጽሩት)። 

የዚህን ዘመን ልዩ ገጽታዎች አስመልክቶ (ማቴ. 13፡1-50) ጌታችን ሦስት ዓበይት ሁኔታዎችን ገልጧል፡- (1) እስራኤል በዓለም ያላት ስፍራ ለእርሻ ውስጥ እንደተሸሽገ መዝገብ ይሆናል (ማቴ. 13፡44)፤ (2) ክፋት እስከ ዘመኑ ፍጻሜ ይቀጥላል (ማቴ. 13፡4፥ 25፥ 33+ 48)፤ (3) በስንዴ፥ የከበረ ዋጋ ባላት ዕንቁና በመልካም ዓሣ የተመሰሉት የመንግሥት ልጆች ይሰበሰባሉ (ማቴ. 13፡30፥ 45፥ 46፥ 48)። 

– ከነዚህ ሦስት የዘመኑ ባሕርያት የመጨረሻው ወይም የመንግሥት ልጆች መሰባሰብ በአሁኑ ዘመን የእግዚአብሔር ዋነኛ ዓላማ መሆኑ ተገልጿል። በዚሁ መሠረት ሮሜ 11፡25 ውስጥ እንደተገለጠው፥ የአሁኑ ዘመን የእስራኤል ዕውርነት የሚቆየው፥ እስከ ቤተ ክርስቲያን ዘመን ፍጻሜ (ኤፌሶን 1፡22-23ን ተመልከት)፥ ማለትም እግዚአብሔር አሕዛብን እየጠራበት ያለው ልዩ የበረከት ዘመን እስከሚያበቃ ብቻ ነው። 

እንደዚሁም “የዓመፅ ምሥጢር” ወይም በአሁኑ ዘመን የሚታየው ክፋት የእግዚአብሔር መንፈስ ስፍራ እስኪሰቅለት ድረስ ማዕቀብ ያሰበት ቢሆንም፥ የሚቀጥል መሆኑ ተገልጧል (2ኛ ተሰ. 2፡7)። መንፈስ ቅዱስ የሚሄደው የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ ከፈጸመ በኋላ ብቻ እንደመሆኑ፥ የእግዚአብሔር ቀጣይ ዓላማ በዓለም ክፋትን ማሻሻል ሳይሆን፥ የሚያምኑትን ሁሉ መለየት ነው። የእስራኤል ቃል ኪዳኖች ገና ይፈጸማሉ (ሮሜ 11፡27 ፥ ክፋት ከምድር ይወገዳል (ራእይ 21፡1)። የአሁኑ የእግዚአብሔር ዓላማ ቤት ክርስቲያንን ወደ ሙላቱ ማድረስ ነው። 

ሐዋርያት ሥራ 15፡13-19 ውስጥ እንደተገለጠው፥ የያዕቆብ ንግግር ፍሬ አሳብ ኢየሩሳሌም ውስጥ በተካሄደው የመጀመሪያ ጉባኤ ፍጻሜ ላይ ተብራርቷል። ጉባኤው የተጠራው ከአሁኑ የእግዚአብሔር ዓሳማ ጋር በሚመሳሰለው ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ነበር። በመጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በብዛት የሚገኙት አይሁዶች በመሆናቸው፥ ይህ አዲስ ወንጌል ወደ አሕዛብ መድረሱን እየተመለከቱ አይሁድነታቸው ምን የተለየ ነገር እንዳለው ግራ አጋብቷቸው ነበር። ያዕቆብ የጴጥሮስን ልምምድ በመመርኮዝ ጴጥሮስ አሕዛብ በነበረው ቆርኔሌዎስ ቤት በመገኘት ያከናወነው ነገር የሚያመለክተው፥ እግዚአብሔር ሕዝብን ለራሱ ይሰበስብ ዘንድ መጀመሪያ አሕዛብን በመጎብኘት ላይ እንዳለ የሚያሳይ ነው ብሏል። ያዕቆብ ከዚያ በኋላ፥ ጌታ እንደሚመለስና ለእስራኤልም ሆነ ለአሕዛብ ዓላማዎቹን ሁሉ እንደሚያሟላ በመግለጥ ንግግሩን ቀጥሏል። 

ይህ ሁሉ ጥናት ለዚህ ጉዳይ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ቢኖር፥ በአሁኑ ዘመን ግለሰብ አማኝ ዓለምን ለማሻሻል በእግዚአብሔር ያልተሾመ መሆኑን ነው። የአማኝ መጠራት ለክርስቶስና ለሚያድን ጸጋው በዓለም ሁሉ ምስክር ይሆን ዘንድ ነው። በዚህ የወንጌል ስብከት አገልግሎት አማካይነት ነው የእግዚአብሔር መንፈስ የዘመኑን ድንቅ ዓላማ ከግቡ የሚያደርሰው። 

ለ. የቤተ ክርስቲያን አመሠራረት 

ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያኑን እንደሚመሠርት ተንብዮ ነበር (ማቴ. 16፡18)። ሐዋርያው ጳውሎስም ቤተ ክርስቲያንን “ሕንጻ ሁሉ እየተጋጠመ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስታ ወደ መሆን ከሚያድግበት ሕያው ድንጋይ ጋር አነጻጽሯታል። “በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ ቅዱስ አብራችሁ ትሠራላችሁ” (ኤፌ. 2፡21-22)። የአማኙ የነፍሳት ምርኮኛ የክርስቶስን አካል የማነጹ አገልግሎትም የሚቀጥል ይሆናል። ይህ ለዘላለም ሳይሆን “ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ ነው (ኤፌ. 4፡13)። የክርስቶስ የሙላቱ ልክ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው፥ ሰዎች ክርስቶስን ወደ መምሰል ማደጋቸውን ሳይሆን፥ የክርስቶስ እካል ወደ ፍጻሜው ማደጉን ነው (ኤፌ. 1፡22-23)። ኤፌሶን 4፡16 ውስጥም የአካሉ ክፍሎች ልክ እንደ ሰብአዊ አካል ሕያው ሕዋሳት፥ የማያቋርጥ የነፍሳት ምርኮ ተግባር እንደሚፈጽሙና በዚህም አካሉን የሚያሳድጉ የመሆኑ እውነት ተገልጧል። 

ሐ. የአማኙ ተልእኮ 

ክርስቶስ የዚህ ዘመን መግለጫ በሆነው ዙር የመዝራት ምሳሌ፥ ከእራቱ እጅ እንዱ “ስንዴን እንደሚያስገኝ ተንብዮአል (ማቴ. 13፡1-23)። ምንም እንኳ የወንጌሉ ስብከት ከሕይወትም ሆነ ከሞት ጋር የሚዛመድ ቢሆን (2ኛ ቆሮ. 2፡16)፥ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ እማኝ የጠፉትን ለመመለስ በጊዜውም አለጊዜውም እንዲተጋ ተልኳል። እምነት ከመስማት፥ መስማትም ከእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ በመገንዘብ (ሮሜ 10፡17)፥ ወደ ዓለም ሁሉ እኝዲሄድና ለፍጥረት ሁሉ ወንጌልን እንዲሰብክ ተሹሟል (ማር. 16፡15)። በተጨማሪም፥ ሰከርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ዮነበረው እግዚአብሔር የማስታረቅን ቃል የሰጠን መሆኑ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡19 ውስጥ ተገልጧል። እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልእክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን” (2ኛ ቆሮ. 5፡20)። 

ይህ አገልግሎት አማኞች ሁሉ ሊፈጽሙት የሚገባና፥ በብዙ መንገዶች ተግባር ላይ የሚውል ነው። 

1. ወጎጌልን ለዚሁ ዓላማ ስምንሰጠው ገንዘብ አማካይነት ላልዳነ ሰው ማሰራጨት ይላል። ነፍሳትን ለክርስቶስ ለመማረክ የሚሹ ትጉህ አማኞች መኖራቸው የተረጋገጠ ቢሆንም፥ ለዚህ ዓላማ ከፍጻሜ መድረስ የሚፈለግባቸውን የገንዘብ ስጦታ ለማቅረብ ደግሞ ቸል የሚሉ መኖራቸውም እውን ነው። መልእክተኛው እስካልተላከ ድረስ አያሄድም። የሚልከውም በመሄድ ከሚያገለግል ጋር ዘላለማዊ ብድራትን ይካፈላል። 

2. ወንጌል ላልዳነ ሰው የጸሎት መልዕ ህኖ ሊቀርብ ይችላል። “ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ” (ዮሐ. 14፡14) ያለው ጌታ ለጸሎት መልስ በመስጠት ሠራተኞችን ወደ መከሩ እንደሚልክ የሚያረጋግጥ ነው። የእግዚአብሔር ልጅ ለሆነ አንድ አማኝ ከጸሎት የላቀ ፍሬያማ እገልግሎት እንደሌለ በቀላሉ ተረጋግጧል። በዚህ አገልግሎት ነፍሳት እንደሚድኑ የሚገነዘቡ ግን በጣም ጥቂት ብቻ ናቸው። 

3. ወኝጌል ላልዳነ ሰው በቃል ሊቀርብለት ይችላል። ሁሉም ለዚህ ተግባር የተላኩ እንደመሆናቸው፥ የሚከተሉትን ነገሮች በሚገባ ማስተዋል ወሳኝ ነው። (ሀ) መልእክተኛው መንፈስ ቅዱስ በሚያኖረው ስፍራ ሁሉ ለመሆን መፍቀድ አለበት፤ (ላ) እንዲያውጅ የተሾሙባቸውን የጸጋ ወንጌል እውነቶች መማር አለበት! (ሐ) በመንፈስ ቅዱስ መሞላት አለበት። ይህ ካልሆነ ለሚጠፉ ነፍሳት ምርኮ አገልግሎት ያለ ፍርሃትና ያለ ድካም እንዲነሣሣ የሚገፋፋ ፍቅር ሊኖረው አይችልም። ክርስቶስ፥ “መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ … ምስክሮቼ ትሆናላችሁ” (ሐዋ. 1፡8) ብሏል። ይህ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ከሌለ፥ ወንጌሉን የመመስከር አደራ አይኖርም። በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ አማኝ ግን መለኮታዊ ርኅራኄ ከውስጡ እየፈሰሰ ዝም ሊል አይችልም (ሐዋ. 4 ፡20)። 

4. በተጨማሪም ወንጌል እንደ ሥነ-ጽሑፍ፥ ሬድዮ፥ ቴሌቪዥንና መንፈሳዊ መዝሙሮች በመሳሰሉት መንገዶች ሊቀርብ ይችላል። ዘዴው ምንም ይሁን ምን፥ እውነቱ መንፈስ ቅዱስ በሚገለገልበት መንገድ ሁሉ ሊቀርብ ይገባል። 

5. እግዚአብሔር ወንጌልን ለማሰራጨት በሌሎች ብዙ መንገዶች እንደሚጠቀም ጥርጥር የለውም። ምንም እንኳ እያንዳንዱ ክርስቲያን ወንጌልን በቀጥታ በመስበክ እኩል ስኬታማ ባይሆንም፥ ወንጌል ለሰው ሁሉ መሰበኩን በማረጋገጡ ረገድ የሚጋራው ኃላፊነት አለ፡፡

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

37
ትምህርት 37 ከ52

ቤተ ክርስቲያን አገልግሎቷና አደራዋ

ሀ. አገልግሎቷ ለእግዚአብሔር 

ለሌላው ይጠቅም ዘንድ የሚከናወን ማንኛውም ተግባር አገልግሎት ይባላል። ይህን ጉዳይ ከመጽሐፍ ቅዱስ በምናጠናበት ጊዜ፥ በብሉይና በአዲስ ኪዳን መካከል አያሌ ተመሳሳይና ተነጻጻሪ ሁኔታዎች እንመለከታለን። የአዲስ ኪዳን አብዛኛው አስተምህሮ ብሉይ ኪዳን ውስጥ የተተነበየ ስላሆነ፥ በአዲሱ እስኪፈጸም ድረስ የብሉይ ኪዳን እስተምህሮ ጎደሎ ነው። የአገልግሎትንም ጉዳይ ስንወስድ ከዚህ የተለየ አይደለም። ስለ አገልግሎት ስናጠና በአብዛኛው የብሉይ ኪዳኑ አባባሎች እንደ ጥላ የነበራቸው ትርጉሞች በአዲስ ኪዳን ፍጻሜ ሲያገኙ እናያለን። 

በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ሥርዓት ከእግዚአብሔር የሆነ አገልግሎት ከህነት ግንኙነት የሚጠቀላል ነው። በብሉይ ኪዳን ሥርዓት ከህነት በተዋረድ የሚካሄድ ሲሆን፥ ካህናቱ በሊቀ ካህኑ ሥልጣን ሥር ያገለግሉ ነበር። በአዲስ ኪዳን ሥርዓት ግን እያንዳንዱ አማኝ ለእግዚአብሔር ካህን ነው (1ኛ ጴጥ. 2፡5-9፤ ራእይ 1፡6)። የአዲስ ኪዳን ክህነት ጠቅላላ የአጎልግሎት እውነተኛ ሊቀ ካህን በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ሥልጣን ሥር የሚካሄድ ነው። ሌሎች ሊቀ ካህናት እውነተኛ ሊቀ ካህን ወደሆነው ክርስቶስ የሚያመለክቱ ጥላዎች ብቻ ነበሩ። ስለሆነም በአዲስ ኪዳን ሥርዓት መሠረት፥ አማኞች ከእግዚአብሔር ጋር ባላቸው የክህነት ግንኙነት ላይ በመመሥረት በተመሳሳይ ደረጃ ያገለግላሉ። በክህነት አገልግሎታቸው፥ እንደ ብሉይ ኪዳን ክህነት ሁሉ የአዲስ ኪዳን ካህናትም እግዚአብሔርንና ሰውን እንዲያገለግሉ ተሹመዋል። 

በብሉይ ኪዳን ዘመን ለአሕዛብ የሚሰበክ ወንጌል ሰላልነበረ፥ አገልግሎቱ የሚያካትተው ከእግዚአብሔር የተሰጡትን ሥርዓቶች በመገናኛው ድንኳን ወይም ቤተ መቅደስ ውስጥ ማከናወንን ብቻ ነበር። ከዚህ ጋር ሲነጻጸር፥ የአዲስ ኪዳን የክህነት አገልግሎት በደረጃው የላቀና ሰፊ ነው። ይኸውም እግዚአብሔርንና ሌሎች አማኞችን ብቻ ሳይሆን፥ በሁሉም ስፍራ የሚገኙ ሰዎችን ሁሉ የሚያጠቃልል መሆኑ ነው። 

1. የመሥዋዕት አገልግሎት በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ተመሳሳይ ነበር። አንድ የብሉይ ኪዳን ካህን የሚቀደሰው ወይም የሚለየው፥ በሌዊ የካህንነት ቤተሰብ ውስጥ በመወለድና በተገቢው ሥርዓት ለክህነት አገልግሎት በመሾም ነበር። ሹመቱም ተሿሚው በሕይወት እስካለ ድረስ የጸና ነው። ካህኑ በአገልግሎቱ መጀመሪያ ላይ አንድ ጊዜ ለዘላለም በመታጠብ እንዲነጻ ይደረጋል (ዘጸ. 29፡4)። 

የብሉይ ኪዳኑ ካህናት አገልግሎታቸውን በመንጻት እንደሚጀምሩ፥ በአማናዊነት የሚፈጽም የአዲስ ኪዳን አማኝ ካህን” ድነትን ሲያገኝ ለአንዴና ለዘላለም በመንጻት ነው እገልግሉቱን የሚጀምረው (ቆላ. 2፡13፤ ቲቶ 3፡5)። ከድነቱም የተነሣ ለእግዚአብሔር ተለይቷል። እንደዚሁም በአዲስ ልደት አማካይነት እግዚእብሔር ቤተሰብ ሆኗል። ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ፥ የአዲስ ኪዳን ካህን በፈቃደኝነት ራሱን ለእግዚአብሔር መስጠቱ የተለየ መመዘኛ ሆኖ የሚታይ ነው። 

ራስን ስለ መስጠት፥ “እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ” (ሮሜ 12፡1) የሚል ቃል እናነባለን። በእግዚአብሔር ርኅራኄ” የሚለው ሐረግ ሮሜ መጽሐፍ ውስጥ ቀደም ብሎ የተጠቀሱትን ታላላቅ የድነት እውነታዎች ያመለክታል። እያንዳንዱ እማኝ ድነት በሚያገኝበት ቅፅበት ይህንኑ ምሕረት ያገኛል። ሰውነትን እንደ ሕያው መሥዋዕት ማቅረብ የሚለው ቃል፥ አማኝ ራሱንና ያለውን ሁሉ ሰውዴታው ለእግዚአብሔር ፈቃድ መስጠቱን ያመለክታል። እግዚአብሔርም አማኙ የሚሰጠውን ሁሉ ተቀብሎ በፈቀደበት ስፍራ ላአገልግሎት ያስቀምጠዋል (ኤፌ. 2፡10)። 

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አገላለጥ፥ ይህ የመቀበልና ስፍራ የመስጠት ተግባር መቀደስ ነው። ስለሆነም፥ አማኝ-ካህን ራሱን ለእግዚአብሔር የመስጠት እንጂ፥ ራሱን ለእግዚአብሔር የመቀደስ ብቃት የለውም። የሚቀድስ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ከመለኮታዊ የመቀደስ ተግባር ጋር በተያያዘ፥ በአሁኑ ዘመን ኢየሱስ ክርስቶስ የአማኞችን አገልግሎት እንደ ሊቀ ካህን በመቀበል የተቀደሰ ያደርገዋል፥ ይህ በመምራትና ሰማዕተዳደር የሚያከናውነው ተግባር፥ የብሉይ ኪዳን ካህን የሌዊን ልጆች ሰሚቀድስበት አገልግሎት ውስጥ በጥላነት የተመለከተ መሆኑ ሊጤን ይገባል። 

አማኝ-ካህን ራሱን ለእግዚአብሔር በመስጠትና ወደፊት ይህን ዓለም ሳለመምሰል፥ በውስጡ ሰሚያድረው መንፈስ ቅዱስ አማካይነት የተለወጠ ሕይወት ይኖረዋል። በዚያውም ኃይል አማካይነት “የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደሆነ” ፈጥኖ ሊያውቅ ይችላል (ሮሜ 12፡2)። 

ሰእዲስ ኪዳን ሥርዓት፥ ሰመሥዋዕትነት ለእግዚአብሔር የሚቀርበው የክህነት አገልግሎት አራት ገጽታዎች አሉት፡- (ሀ) “ሰአእምሮ የሚመች አገልግሎት” (ሮሜ 12፡1) ወይም ደግሞ ይበልጥ በቀጥተኛ ትርጉም “መንፈሳዊ አምልኮ” የተባለው ራስን የመስጠት ተግባር። ራሱ ክርስቶስ መሥዋዕት አቅራቢና መሥዋዕት እንደነበረ ሁሉ፥ አማኙም ሰውነቱን በሙሉ ለእግዚአብሔር እንደ ሕያው መሥዋዕት በማቅረብ ሊያስከብረው ይችላል፤ (ለ) የከንፈር መሥዋዕት ማለትም የምሥጋና ድምፅ ባለማቋረጥ ሊቀርብ ይገባል (ዕብ. 13፡15)፣ (ሐ) የቁሳዊ ነገር መሥዋዕት (ፊልጵ. 4፡18)፣ (መ) የሰናይ ምግባራት መሥዋዕት (ዕብ. 13፡16)። 

የካህናትን መንጻት አስመልክቶ፥ የብሉይ ኪዳን ካህን ወደ ቅዱስ አገልግሎቱ በሚገባበት ጊዜ ጠቅላሳ ሰውነቱን በመታጠብ አንድ ጊዜ ለዘላለም ይነጻ እንደነበር በድጋሚ መገንዘቡ አስፈላጊ ነው። ይህም የመታጠብ ተግባር በራሱ በካህኑ ሳይሆን በሌላ ሰው ይከናወን ነበር (ዘዳ. 29፡4)። ከዚያ በኋላ፥ ምንም እንኳን ሰውነቱን ሁሉ የታጠበ ቢሆን፥ በተደጋጋሚ ከፊል የመታጠብ ተግባሩን ሐስ ሳህን ላይ እንዲያከናውን ይጠየቃል። ይህም የትኛውንም የክህነት አገልግሎት ከማበርከት አስቀድሞ ይከናወናል። የዚህን ምሳሌያዊ ጠቀሜታ ለመፈጸም፥ የአዲስ ኪዳን ካህን ምንም እንኳ ድነትን ባገኘ ጊዜ የነጻና ይቅርታ የተደረገለት ቢሆን፥ ሁልጊዜ ልቡ የሚያውቃቸውን ኃጢአቶች መናዘዝ ይኖርበታል። ይህ የሚሆንበት ምክንያቱ ለመንጻትና ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት የማድረግ ብቃት ይኖረው ዘንድ ነው (1ኛ ዮሐ. 1፡9)። የብሉይ ኪዳን ካህን ሹመት ለዘላለም እንደሆነ ሁሉ፥ የአዲስ ኪዳን ካህንም ለዘላላም የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው። 

2. የአምልኮ አገልግሎት በቀጣዩ ምዕራፉ ውስጥ በስፋት ይቀርባል)፥ በአሁኑ ዘመን የእያንዳንዱ አማኝካህን የአገልግሎት ሕይወት ክፍል እንደን መመልከት ይቻላል። በብሉይ ኪዳን የሁሉም ካህን አገልግሎት እንደነበረው ማለት ነው። የተቀደሰው ስፍራ አሠራሮች በብሉይ ኪዳን ሥርዓት የካህኑን እምልኮ ሰተምሳሌትነት እንደሚያመለክቱና፥ የስፍራው ገጽታና አሠራር ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደሚናገር፥ የእማኝም አምልኮ በክርስቶስ አማካይነት ብቻ የሚሆን ነው። አሁንም በአገልግሎት መልክ ለእግዚአብሔር የሚቀርሰው የአማኝ አምልኮ፥ ራስን ለእግዚአብሔር ማቅረብ (ሮሜ 12 ፡1)፥ ከልብ የመነጨ ምስጋናና ውዳሴ ለእግዚአብሔር መሠዋት (ዕብ. 13፡15)፥ ወይም የመሥዋዕትነት ስጦታዎችን ለርሱ ማቅረብ ሊሆን ይችላል። 

ከብሉይ ኪዳን ካህናት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ሁኔታ ሁለት የተከለከሉ ነገሮች ተመዝግበዋል። እነዚህም ተምሳሌታዊ ፍች አላቸው። “እንግዳ” ወይም ሌላ ዕጣን ማቅረብ አይቻልም (ዘዳ. 30፡9)። ይህም ለእግዚአብሔር በሚቀርብ አገልግሎት ውስጥ ልባዊ ያልሆነ ሥርዓትን ያመለክታል። “እንግዳ” ወይም ሌላ እሳት ማቅረብም አይቻልም (ዘሌዋ. 10፡1)። ይህ ደግሞ ለክርስቶስ በመንፈስ አማካይነት እውነተኛ መሰጠት ሊኖረን ሲገባ፥ ሥጋዊ ስሜቶችን መተካትን ወይም ለክርስቶስ ልንሰጠው የሚገባንን ፍቅር በተራ ነገሮች መሸፈንን በተምሳሌትነት የሚያሳይ ነው (1ኛ ቆሮ. 1፡11-13፤ ቆላ. 2፡8፥16-19)። 

3. በቀጣዩ ምዕራፍ ውስጥ የምንመለከተው የምልጃ አገልግሎትም ካህን የተሳለው እማኝእስፈላጊ ተግባር ነው። ነቢይ ለሕዝቡ የእግዚአብሔር ወኪል እንደሆነ ሁሉ፥ ካህን ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ የሕዝብ ወኪል ነው። ክህነት መለኮታዊ ሹመት እንደመሆኑ፥ ሁልጊዜም ወደ እግዚአብሔር የመቅረቢያው መንገድ ነበር። ቢሆንም በብሉይ ኪዳን ዘመን ካሊቀ ካህናቱ በቀር የትኛውም ካህን ወደ ቅድስተ ቅዱሳን እንዲገባ አይፈቀድለትም ነበር። እርሱም ቢሆን በዓመት አንድ ጊዜ የመሠዊያ ደም ይዞ ነበር የሚገባው (ዕብ. 9፡7)። 

በዚህ ሥፍረ-ዘመን ክርስቶስ እንደ ሊቀ ካህን በራሱ ደም ወደ ሰማያዊቷ መቅደስ ገብቷል (ዕብ. 4፡14-16፤ 9፡24፤ 10፡19-22)። ስለሆነም የርሱ ለሆኑትና በዓለም ለሚገኙት በመማለድ ላይ ነው (ሮሜ 8፡34፤ ዕብ. 7፡25)። ክርስቶስ በሞተበት ቅፅበት የቤተ ክርስቲያን መጋረጃ ለሁላት ተቀዷል። ይህም ለዓለም ሳይሆን በፈሰሰው የክርስቶስ ደም በኩል ወደ እግዚአብሔር ለሚመጡ ሁሉ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚወስደው መንገድ እንደተካፈተ ያመለክታል (ዕብ. 10፡19-22)። 

የአዲስ ኪዳን ካህን ከክርስቶስ ደም የተነሣ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ስለሚችል፥ በምልጃ የማገልገል ዕድል አለው (ሮሜ 8፡26-27፤ ዕብ. 10፡19-22፤ 1ኛ ጢሞ. 2፡1፤ ቆላ. 4 ፡12)። 

ለ. የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ለሰው 

ሮሜ 12፡1-8 ውስጥ የተጠቀሰው እውነት በመለኮት የተደረገ የቅደም ተከተል እቀማመጥ አለው። በሌሎችም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንደተመለከተውና፥ በዚህ ክፍልም እንደተጠቀሰው፥ የመሰጠትና የቅድስና ሕይወት እስካልታዩ ድረስ ክርስቲያናዊ አገልግሎት የተባለ ነገር አይኖርም። እነዚህን መሠረታዊ ነገሮች ተከትሎ መለኮታዊ ጸጋ ስጦታዎች ለአገልግሎት ተሰጡ። ከዚሁ ጋር በተገናዘበ ሁኔታ መጽሐፍ ቅዱስ “ስጦታ” የሚለውን ቃል በሚጠቀምበት መንገድና በተለመደው አገላለጥ መካከል ያለውን ሰፈ ልዩነት መገንዘቡ መልካም ነው። ስጦታ በትውልድ ወይም በዘር የሚተላለፍ እና የተለየ ነገር ለማድረግ የሚያስችል ነገር አድርጎ የመቁጠር ግንዛቤ አለ። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አጠቃቀም “ስጦታ፡፡አማኝ ውስጥ የሚያድረው የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ነው። 

መንፈስ ቅዱስ አማኙን በመሣሪያነት በመጠቀም አገልግሎት ይሰጣል። የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ በማንኛውም መልኩ በአማኙ ጥረት፥ ወይም የርሱ ጥረት ታክሎበት የሚመጣ ነገር አይደለም። ክርስቲያናዊ ባሕርይ የመንፈስ ፍሬ” እንደሆነ ሁሉ (ገላ. 5፡22-23)፥ ክርስቲያናዊ አገልግሎትም <<መንፈስ ቅዱስን መግለጥ” ወይም የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ እንደሆነ ተመልክቷል (1ኛ ቆሮ. 12፡7)። 

እያንዳንዱ አማኝ አንዳንድ መለኮታዊ ስጦታዎች ቢኖሩትም (1ኛ ቆሮ. 12፡7፤ ኤፌ. 4፡7)፥ የስጦታዎቹ ዓይነት የተለያየ ነው (ሮሜ 12፡6፤ 1ኛ ቆሮ. 12፡4-11፤ ኤፌ. 4፡11)። ክርስቲያኖች ሁሉ ተመሳሳይ ሥራ እንዲያከናውኑ አይመረጡም። በዚህ ረገድ አማኞች ሁሉ ከሚሠዉበት፥ ከሚያመልኩበትና ከሚያማልዱበት የክህነት አገልግሎት ጋር “ስጦታ” ልዩ መሆኑን መገንዘቡ ተገቢ ነው። እነዚህን የሚያደርጉት ስጦታ ስላላቸው ሳይሆን ካህናት ስለሆኑ ነው። ምንም እንኳ አጠቃላይ የሆኑ የጸጋ ስጦታዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቢዘረዘሩ (ሮሜ 12፡6-8፤ 1ኛ ቆሮ. 12፡8-11፤ ኤፌ. 4፡11)፥ እና ከነዚህም መካከል አንዳንዶቹ መሥራት ቢያቆሙ (1ኛ ቆሮ. 13፡8)፥ በአማኞች አማካይነት የሚከናወነው የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎትና አማኞቹ እንዲያገለግሉ የተጠሩባቸው ሁኔታዎች እንዳሉባቸው ስፍራዎች ይለያያሉ። 

ስጦታዎች የሚሰጡት የእግዚአብሔር አገልጋይ “ጠቃሚ” ይሆን ዘንድ ነው (1ኛ ቆሮ. 12፡7)። በሥጋ ጉልበት የሚሠራ አገልግሎት ጠቃሚ ያለመሆኑን ይህ ያመለክታል። በስጦታው ልምምድ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ እንደ የሕይወት ውኃ ወንዝ” (ዮሐ . 7፡37-39) መፍሰስ እና “እግዚአብሔር እናደርገው ዘንድ አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ” (ኤፌ. 2፡10) ማከናወን ነው። 

በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ አማኞች ማንም ሳይገፋፋቸው ስጦታዎቻቸውን ባለማቋረጥ ከሥራ ላይ ያውላሉ። ሥጋዊ እማኞች ስጦታው ቢኖራቸውም፥ በትጋት የማገልገልም ሆነ ሰዎች ስጦታቸውን እንዲጠቀሙ ሲያበረታቷቸው የመንቃት ዝንባሌ አይታይባቸውም። ይሁንና ኃጢአታቸውን በመናዘዝ፥ ሕይወታቸውን በመስጠትና በውስጣቸው በሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ላይ በመደገፍ ከእግዚአብሔር ጋር በሚስማሙ ጊዜ፥ ወዲያውኑ በመንፈስ ቅዱስ ይሞሉና የእግዚአብሔርን ፈቃድ የመፈጸም መሻት ያድርባቸዋል። ሰመሆኑም፥ በውስጣቸው በሚሠራው የእግዚአብሔር ኃይል አማካይነት ቀደም ሲል እግዚአብሔር ለሰጣቸው አገልግሎት ጠቃሚ መሣሪያዎች ይሆናሉ። ክርስቲያኖች በመንፈስ ቅዱስ የሚሞሉት ትጉህ አገልጋዮች በመሆናቸው አይደለም። ይልቁንም፥ በመንፈስ ቅዱስ በመሞላታቸው ትጉህ አገልጋዮች ይሆናሉ። አንዳንድ ጊዜ የዛለ አገልጋይ እንቅስቃሴውን ሁሉ በግቆም እንዲያርፍ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ “ብቻችሁን…ሁኑ እረፉ” ያላቸው ወቅት ነበር። 

ሐ. የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ አወቃቀሟ 

የክርስቲያን የገንዘብ አስተዳደር ወይም አያያዝ በሦስት ተከፍሎ ሊታይ ይችላል፡- (1) ገንዘብን ማግኘት፥ (2) ገንዘብን በንብረትነት መያዝ፥ (3) ገንዘብን መስጠት። ገንዘብን ማግኘት በማንም ሰው ዕለታዊ ሕይወት ያለ ቢሆንም፥ የእግዚአብሔር ልጆች ስለሚያገኙት ገንዘብ አጠቃቀም በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት በሚቀርቡበት ጊዜ መልስ ይሰጥበታል (ሮሜ 14፡16-12)። ክርስቲያኖች ብዙውን ጊዜ ገንዘብ ያገኛሉ፥ ይይዛሉ፥ ያጠፋሉ፤ ከእግዚአብሔር ጋር ሊኖራቸው የሚገባ ግንኙነት ግን አያጤኑትም። 

1. ክርስቲያን ገንዘብ የማግኘቱ ተግባር ከእግዚአብሔር ጋር ካለው ግንኙነት ጋር ሰሚስማማ መልኩ ሊሆን ይገባል። ይህም “የምታደርጉትን ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት” (1ኛ ቆሮ. 10፡31) ከሚለው ትእዛዝ አንጻር ተግባራዊ መሆን አለበት። ሁሉም በወዙ እንዲያድር መለኮታዊ ዕቅድ ነው (ዘፍጥ. 3፡19፤ 2ኛ ተሰ. 3፡10)፤ ክርስቲያንም ከዚህ የተለየ አይደለም። መንፈሳዊ ለሆነና ለሚያስተውል አማኝ ግን፥ ሥራ የኑሮ ማሸነፊያ መንገድ ብቻ ሳይሆን፥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማድረግም ነው። የቱንም ያህል አድካሚ ቢሆን፥ ማንኛውም ሥራ ከእግዚአብሔር እንደተሰጠ ተደርጎ ለርሱ ክብር ሊከናወን ይገባል። ይህ ካልሆነ ባይሠራ ይሻላል። 

እግዚአብሔር በዕለታዊ ሥራ አማካይነት ለልጆቹ ምግብና ልብስ በመስጠት ደስ መሰኘቱ፥ በፍጹም ፍቅሩ ለልጆቹ የሚያስብላቸው የመሆኑን የላቀ እውነት ሊያደበዝዘው እይገባም (ፊልጵ. 4፡19፤ ዕብ. 13፡5)። “እግዚአብሔር የሚሰጠው ለራሳቸው ምንም ለማድረግ ለማይችሉ ብቻ ነው” የሚለው አባባል እውነት አይደለም። የእርሱ ለሆኑት ሁልጊዜ ይጠነቀቅላቸዋል፤ ያላቸው ነገር ሁሉ ከርሱ ነውና(1ኛ ሳሙ. 2፡7)። 

“ለሠራተኛ ደመወዙ ስለሚገባው” (ሉቃስ 10፡7)፥ በሰዎች መካከል በሚኖሩ ግንኙነቶች ውስጥ ስምምነቶችና ደመወዞች ተለይተው ይታወቃሉ። ክርስቲያን ግን አባቱ ከሆነው እግዚአብሔር ያለው ግንኙነት ምንም ሲያደርግ ለአባቱ ፈቃድና ለርሱ ሲል የሚያከናውነው ነው። የሚያከናውነው ሥራም ራሱን ለእግዚአብሔር መስጠቱን የሚገልጥበት ይሆናል። በተመሳሳይ ሁኔታ ክርስቲያን የሚያገኘው ነገር ሁሉ ከሥራው የሚገኝ ሳይሆን፥ የአባቱ የፍቅር መግለጫ ነው። የዚህ ዓይነቱ አመለካከት ስሜታዊ ወይም ከተግባራዊነት የራቀ አይደለም። ይልቁንም፥ እማኝ ድካሙን ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር በማዋል የሚቀድስበት ወይም በሕይወት ጫና ውስጥ እንኳ ቢኖር ለዘላለሙ የሚደሰትበት (1ኛ ተሰ. 5፡16) ብቸኛ መሠረት ነው። 

2. ለማንኛውም ታማኝ ክርስቲያን የገንዘብ እያያን ከፍተኛ ኃላፊነት ነው። ከየአቅጣጫው ከሚመጣው የእርዳታ ጥያቄና ገንዘብ ከሚያከናውነው ብዙ በጎ ተግባር አንጻር፥ እያንዳንዱ መንፈሳዊ ክርስቲያን ያለውን ገንዘብ “ልስጥ ወይ አልስጥ” የሚል ጥያቄ ይገጥመዋል። ንብረትን ባለማባከን መያዝ የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑ እያጠራጥርም። ራሱን ለጌታ የሰጠ አማኝ ንብረቱን ልስጥ አልዕጥ ሰማላት ሊጠይቅ ይገባል። እውነተኛ ክርስቲያን ንብረቱን እግዚአብሔር እንደመራው የማድረግ ኃላፊነት አለበት። ተቆጣጣሪውም እግዚአብሔር ነው። ሀብታሞችንም ሆነ ድሆችን የሚያነሣሡ ውስጣዊ ዓላማዎች፥ ማለትም የሳለጠግነት መሻት (1ኛ ጢሞ. 6፡8-9፥ 17-18፤ ያዕ. 1፡11፤ ዕብ. 13፡5፤ ፊልጵ. 4፡1)፥ ለነገ በመጨነቅ የማስቀመጥ ፍላጎት (ማቴ. 6፡25-34) እና ለሌሎች የመስጠት ፍላጎቶች ተገቢ የሚሆኑት፥ በእያንዳንዱ ግለሰብ ሕይወት የተገለጠውን የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚፈጽሙ ሲሆኑ ብቻ ነው። 

3 ክርስቲያን ሥርቶ ካገኘው ገንዘብ የመስጠቱ ጉዳይ ለእግዚአብሔር የሚያስ ረክተው ፆናና አስፈላጊ አገልግሎት ነው። እኔነትና ገንዘብ የክፋት ሥሮች ናቸው። በመሆኑም ገንዘብን በማግኘቱና በመጠቀሙ ረገድ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ጋር ባለው የጸጋ ግንኙነት ላይ መቆም ይጠበቅበታል። ይህም ግንኙነት አማኝ በቅድሚያ ራሱን ለእግዚአብሔር ሙሉ ለሙሉ የሰጠ መሆኑን ያመለክታል (2ኛ ቆሮ. 8፡5)። አንድ ሰው በእውነት ራሱን ለእግዚአብሔር ከሰጠ ራሱም ሆነ ያለው ንብረት ሁሉ (1ኛ ቆሮ. 6፡20፤ 7፡23፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡18-19)፥ ማለትም ሕይወቱ፥ ጊዜው፥ ብርታቱ፥ ችሎታው፥ ዓላማና ንብረቱ የእግዚአብሔር ይሆናሉ። 

ከገንዘብ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ፥ የጸጋ መርሆ የሚያካትተው፥ ክርስቲያን ባለው ነገርና በራሱም ማንነት ላይ የእግዚአብሔርን ሉዓላዊ ሥልጣን የሚገነዘብ መሆኑን ነው። ይህ ሕጉ እስከተወገደበት ጊዜ ድረስ የሕጉ አካል ሆኖ ይሠራበት ከነበረው የብሉይ ኪዳን የአሥራት አወጣጥ መንገድ ይለያል (ዮሐ. 1፡16-17፤ ሮሜ 6፡14፤ 7፡1-6፤ 2ኛ ቆሮ. 3፡1-18፤ ገላ. 3፡19-25፤ 5፡18፤ ኤፌ. 2፡15፤ ቆላ. 2፡14)። ምንም እንኳን አንዳንድ የሕግ መመሪያዎች በጸጋ ሥር እንደገና ቢገሰጡ፥ ሰንበትን እንደማከበር ሁሉ አሥራትም በዚህ ሥፍረ-ዘመን በአማኙ ላይ የተጣሉ አይደሉም። የጌታ ቀን ሕጋዊውን የሰንበት አከባበር ስለተካና ከጸጋ መመሪያዎች ጋር እንደተስማማ፥ አሥራትም በሌላ የመስጠት ዘዴ ተተክቷል። ይህም ከጻጋ ትምህርት ጋር የሚስማማ የእሰጣጥ መንገድ ነው። 

በቆሮንቶስ ቅዱሳኝ ልምምድ እንደተብራራው፥ ክርስቲያናዊ ስጦታ በጸጋ ዘመን 2ኛ ቆሮንቶስ 8፡1-9፡15 ውስጥ ተጠቃሎ ቀርቧል። በዚህ ክፍል የሚከተሉትን ነጥቦች እንመለከታለን፡- 

(ሀ) ክርስቶስ ለቆሮንቶስ ቅዱሳን ምሳሌያቸው ነበር። በጻጋ ዘመን ለሁሉም ዓይነት መስጠት ምሳሌ የሚሆነው፥ ክርስቶስ ራሱን መስጠቱ ነው (2ኛ ቆሮ. 8፡9)። እርሱ የሰጠው አሥር ከመቶውን ብቻ ሳይሆን፥ ሁሉንም ነው። 

(ለ) የሰጡት ከከፍተኛ ድህነታቸው ነበር። የቆሮንቶስ አማኞች በመስጠት አገልግሎታቸው የጎጠማቸው ነገር በአስገራሚ ቃላት ነው የተገለጠው (2ኛ ቆሮ 8፡2)፡“በብዙ መከራ ተፈትነው ሳሉ፥” “የደስታቸው ብዛት፥” (“የድህነታቸው ጥልቅነት፥” “የልግስናቸው ባለጠግነት”። በተመሳሳይ ሁኔታ በትልቅ ድህነት ውስጥ በልግስና መስጠትን በተመለከተ የጌታችንን ምስጋና ያተረፈው የመበለቲቱ ሣንቲም (ሉቃስ 21፡1-4)፥ “የነበራት ሁሉ” እንጂ ከነበራት ተከፍሎ የተሰጠ አለመሆኑን መገነዘቡ አስፈላጊ ነው። 

(ሐ) ገንዘባቸውን የሰጡት በትእዛዝ ወይም በግዴታ አልነበረም። በሕግ ዘመን አይሁዶች ከገቢያቸው አሥር እጅ እንዲከፍሉ የታዘዙ ሲሆን፥ ያም የግድ መከፈል ነበረበት። በጸጋ ዘመን ግን እግዚአብሔር የሚፈልገው ስጦታውን ሳይሆን፥ የሰጪውን ፍቅርና ታማኝነት ነው። በጸጋ ዘመን የሕግ ጫና የለም። ሊሰጥ የሚገባው መጠንም አልተጠቀሰም። እግዚአብሔር በጎ ፈቃዱን ለመቀበልና ደስ የሚያሰኘው ለማድረግ የተሰጠ ልብ የሚሠራ መሆኑ እውነት ቢሆንም (ፊልጵ. 2፡13)፥ ይበልጥ ደስ የሚሰኘው ግን፥ በልግስና በሚቀርብለት ስጦታ ነው (2ኛ ቆሮ. 9፡7)። 

ሰው ሊለግስ የሚገባውን የስጦታ መጠን የሚደነግግ ሕግ ቢኖር ኑሮ፥ ከበጎ ፈቃዳቸው ውጭ ቢሆንም እንኳ ትእዛዛትን የሚፈጽሙ ሰዎች መኖራቸው አያጠራጥርም። ይህም ቢሆን ስጦታቸው “በቅሬታ” ወይም “ሰግዴታ” የተሰጠ ይሆን ነበር። የወንጌሉን ሥራ ለመደገፍ በልግስናም ይሁን ያለ ልግስና የተሰጠ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ የምንናገር ከሆነ፥ የሚፈለገውን ውጤት የሚያስገኘው በስጦታ የተገኘው የገንዘብ ቁጥር ሳይሆን፥ በስጦታው ላይ የሚያርፈው መለኮታዊ በረከት መሆኑን ልንረዳ ይገባል። 

ክርስቶስ በአምስት እንጀራና በሁለት ዓሣ አምስት ሺህ ሰዎችን መግቧል። የእግዚአብሔር ልጆች ሰጸጋ የመስጠት ዕድላቸውን ተግባራዊ በሚያደርጉበት ስፍራ ሁሉ በረከት ይክተሳቸዋል። “እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል” (2ኛ ቆሮ. 9፡8) የሚለው ቃል እውነት ለመሆኑ ማረጋገጫ አለ። 

(መ) የመጀመሪያው ምእተ ዓመት ክርስቲያኖች ከሁሉም በፊት ራሳቸውን ነበር የሰጡት። ትክክለኛ የሆነ ስጦታ የሚቀድመው ራስን በመስጠት ነው (2ኛ ቆሮ. 8፡5)። ይህ የሚያመለክተው፥ የጸጋ ዘመን መስጠት፥ እንደ ሕግ ዘመን፥ ሰው ሁሉ የሚያደርገው ሳይሆን፥ በተወሰኑ ስዎች የሚከናወን መሆኑን ነው። አሥራትን እንዲከፍሉ እግዚአብሔር የጠየቃቸው እስራኤላውያንን እንጂ ሌሉች ሕዝቦችን አልነበረም። ስለሆነም፥ ክርስቲያናዊ መስጠት ለክርስቲያኖች ብቻ የተወሰነ ሲሆን፥ ይበልጥ ተቀባይነት የሚኖረው ሕይወታቸውን ለእግዚአብሔር ከሰጡት አማኞች የሚመጣው ነው። 

(ሠ) የቀድሞይቱ ቤተ ክርስቲያን አማኞች የአሰጣጥ ሥርዓት ነበር። እንደ አሥራት ሁሉ፥ በጸጋ ዘመንም የሚከናወን መደበኛ የአሰጣጥ ሥርዓት እንዳለ እንመለከታለን። “እያንዳንዱ በየሳምንቱ በፊተኛው ቀን እንደ ቀናው መጠን እያስቀረ በቤቱ ያስቀምጥ” (1ኛ ቆሮ. 16፡2)። ይህ ትእዛዝ “ለእያንዳንዱ” ክርስቲያን በመሆኑና የሚሰጠውም “ከተቀማጩ” በመሆኑ ማመኻኛ ማቅረብ አይቻልም። 

(ረ) የሚሰጥን አማኝ እግዚአብሔር ይደግፈዋል። በጸጋ መስጠትንም ወሰን በሌላቸው ጊዜያዊ ሀብቶች ይደግፋል (2ኛ ቆሮ. 9፡8-10፤ ሉቃስ 6፡38)። በዚህ መሠረት አሥር በመቶ ያህል የሚሰጡ ሰዎች ብዙውን ጊዜ በጊዜያዊ ነገሮች የሚበለጥጉ መሆናቸውን ለመመልከት ይቻል ይሆናል። ይሁንና፥ እማኝ ካሕግ ጋር ግንኙነት ስለሌለው (ገላ. 5፡1)። ይህ የብልጥግና ተስፋ የጻጋ እንጂ የሕግ የተስፋ ቃል ፍጻሜ አይደለም። ስለሆነም፥ በአሥራት መጠን ላይ የሚደገፍ በረከት አይኖርም። 

በረከቶቹ የሚገኙት፥ በስጦታ አማካይነት ልክ ራሱን ስለገለጠ ነው። እግዚእብሔር በቸርነቱ የማይቀበለው ከልብ ሆኖ የቀረበ ስጦታ አይኖርም። እዚህ ላይ በመስጠት የመበልጠግ ዕቅድ ሊነደፍ አይችልም። ስጦታው ከልብ የመነጨ ሊሆን ይገባል። እግዚአብሔርም ልጁ ለሆነ አማኝ የሚሰጠው መልስ፥ ካለው ፍጹም ፈቃድ አኳያ የሚፈጸም ነው። እርሱ እንደመረጠ መንፈሳዊ ወይም ምድራዊ በረከት ሊሰጥ ይችላል። 

(ሰ) እውነተኛ ብልጥግና የሚመጣው ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ብልጥግና ተሰጥቷቸው ነበር። በዚህ ዓለም ነገሮች በልጥጎ በእግዚአብሔር ፈት መደህየትም አለ (ሉቃስ 12፡21)። እንዲህ ባለ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ በእሳት የነጠረውን ወርቅ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዲገዙ ተጋብዘዋል (ራእይ 3፡18)። በክርስቶስ ሞት አማካይነት ሰዎች ሁሉ ሊበለጥጉ የሚችሉበት በር ተከፍቷል (2ኛ ቆሮ. 8፡9)። በእምነት (ያዕ. 2፡5) እና በሰናይ ምግባራት (1ኛ ጢሞ. 6፡18) መበልጠግም ይቻላል። አማኝ በኢየሱስ ክርስቶስ የጌታን “የጸጋውን ባለጠግነት” (ኤፌ. 1፡7) እና “የክብሩን ባለጠግነት” (ኤፌ. 3፡16) ይቀበላል።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

38
ትምህርት 38 ከ52

ቤተ ክርስቲያን፡- አምልኮዋ በጸሎትና በምስጋና

ሮሜ 12፡1-2 እና ዕብራውያን 13፡15-16 ውስጥ እንደተገለጠው፥ ክርስቲያን እንደ አማኝ ካህን አራት መሥዋዕቶችን ያቀርባል። እነዚህም፡- (1) የሰውነቱን መሥዋዕት (ሮሜ 12፡1-2)፥ (2) የምሥጋና መሥዋዕት (ዕብ. 13፡15)፥ (3) የሰናይ ምግባራት መሥዋዕት (ዕብ. 13፡16) እና (4) የገንዘብ አስተዳደር ወይም ዕብራውያን 13፡16 ውስጥ እንደተመለከተው ማካፈልን አትርሱ” ተብሎ ተጻፈው መሠረት የማካፈል መሥዋዕት ናቸው። ሰናይ ምግባራትንና ቁሳዊ ሀብት የማካፈል መሥዋዕቶችን ቀደም ብለን የተመለከትኝ መሆኑ፥ እንደ ካህን የተቆጠረው አማኝ በጸሎቱና ለእግዚአብሔር በሚያቀርበው ምስጋና የሚያከናውነውን ተግባር ቀጥለን እንመለከታለን። 

በዚህ ዘመን፥ አምልኮ የሥርዓት ጉዳይ አይደለም። ክርስቶስ ለሰማርያይቱ ሴት እንደተገለጠሳት፥ እግዚአብሔር መንፈስ ስለሆነ የሚያመልኩት ሁሉ በእውነትና በመንፈስ ሊያመልኩት ይገባል (ዮሐ. 4፡24)። በመሆኑም፥ አምልኮ በታላሳቅ አብያተ ከርስቲያናት ውስጥ በሚፈጸሙ ቅዱስ አገልግሎቶች የተወሰነ አይደለም። ክርስቲያን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለሰማያዊ አባቱ ምስጋናና ምልጃ ከልቡ የሚያቀርብበት ውዳሴ ነው። ጸሎትና ምስጋና የአምልኮ ዋነኛ ገጽታዎች ሲሆኑ፥ ሰዎች በቀጥታ ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙባቸው ተግባራት ናቸው። ብሉይና አዲስ ኪዳናት ውስጥ የጸሎትና የምስጋናን አስተምህሮ በምናጠናበት ጊዜ፥ እያደገ የሚሄደውን መገለጥና እየጨመረ የሚሄደውን ልምምድና ከእግዚአብሔር ጋር ያላ የቀረበ ግኑኝነትን እንመለከታለን። 

ሀ. ጸሎት ከክርስቶስ መምጣት በፊት 

በዘመናት ሁሉ ጸሎት እግዚአብሔርን በሚፈልጉ ግለሰቦች ሲቀርብ ቢቆይም። የቤተሰቡ ኃላፊ በሚያስተዳድራቸው ሰዎች ምትክ (ኢዮብ 1፡5)፥ ካህናትና ገዢዎች ደግሞ በሕዝባቸው ምትክ ይጸልዩ እንደነበር ይታወቃል። ይህ ሁኔታ በተለይ በሙሴና በክርስቶስ መምጣት መካከል በነበረው ጊዜ ይሠራበት ነበር። በነዚህ ምዕተ ዓመታት የጸሎት መሠረቶች የያህዌ ቃል ኪዳን (1ኛ ነገሥት 822-26፤ ነህ. 9፡32፤ ዳን. 9፡4) እና ቅዱስ ባሕርዩ ነበሩ (ዘፍ. 18፡25፤ ዘዳ. 32፡11-14)። ይህም የመሥዋዕትን ደም ተከትሉ የሚመጣ ነስር (ዕብ. 9፡7)። 

ለ. የመንግሥትህ ትምጣ ጸሎት 

የእስራኤል ሕዝብ የክርስቶስን መሢሕነትና በርሱም በኩል የሚመጣውን መንግሥት ላመቀበል አልፈለገም። ክርስቶስ ግን በመጀመሪያዎቹ ዓመታት ባቀረባቸው ስብከቶችና መንግሥትን ለእስራኤል ስለሚሰጥበት ወቅት፥ ደቀ መዛሙርቱ የእግዚአብሔር መንግሥት በምድር ላይ እንድትመሠረት ይጸልዩ ዘንድ አስተማራቸው። 

ማቴዎስ 6፡9-13 ውስጥ የተመለከተውና የታወቀው የጌታ ጸሎት “መንግሥትህ ትምጣ” የሚል ልመና ታክሎበታል (ማቴ. 6፡10)። ይህ ጻሎት በዋናነት በሺህ ዓመቱ ዘመን ክርስቶስ በሉዓላዊነት ምድርን የሚገዛ መሆኑን ያሳያል። 

ጸሎቱ ማቴዎስ 6፡13 ውስጥ “መንግሥት ያንተ ናትና፥ ኃይልም፥ ክብርም፥ ለዘላለሙ አሜን” በማለት ይደመድማል። ይህ የጸሎት ክፍል በብዙዎቹ የማቴዎስ ወንጌል ጥንታዊ ሰነዶች ውስጥ የማይገኝ ከመሆኑም በላይ፥ ሉቃስ 11፡2-4 ውስጥ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ምንባብም አልተጻፈም። ከዚህም የተነሣ፥ ብዙ ሰዎች ይህ ክፍል መጽሐፍ ቅዱስን የገለበጡ ሰዎች ድምዳሜውን ለማሳመር የጨመሩት እንደሆነ አድርገው ያስባሉ። ዳሩ ግን ክፍሉ በመጀመሪያው የማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ኖረም አልኖረ፥ ስለ ወደፊቱ የእግዚአብሔር መንግሥት ትክክለኛ አስተምህሮ አለው። 

የጌታ ጸሎት ለሁሉም ዘመናትና ሁኔታዎች የሚስማሙ ነጥቦችን ስለሚያካትት፥ ብዙ ጊዜ እንደ ሞዴል ጸሎት ሲጠቀስ ኖሯል። በጸሎቱ ውስጥ ለአብ የቀረበ ውዳሴ፥ የዕለት እንጀራ ልመና፥ ከፈተና የመዳን ተማጽኖና ሌሎችም ነጥቦች በሞዴልነት አገልግለዋል። ዮሐንስ 17 ውስጥ ሰፋ ያለ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸሎት ይገኛል። ጌታችን በዚያ ጸሎቱ እግዚአብሔር በዚህ ዘመን ለቤተ ክርስቲያን ያለውን ዓላማ ሙሉ ለሙሉ በመገንዘብ ለቤተ ክርስቲያኑ ማልዷል። 

አንዳንዶች ማቴዎስ ወንጌል ውስጥ የሚገኘው የጌታ ጸሎት በአሁኑ ዘመን አላግባብ ግልጋሎት ላይ የሚውል መሆኑን ይናገራሉ። ይሁን እንጂ፥ ብዙ በጊዜ የማይወሰኑ ሁኔታዎቹና ቀለል ብሎ የመቅረቡ ነገር በብዙ አማኞች ዘንድ ተወዳጅ አድርጎታል። በተጨማሪም፥ ለዛሬዎቹ አማኞች የሺህ ዓመቱን መንግሥት መምጣት በጸሎት መጠባበቁ አግባብ ያልሆነ ነገር አይደለም። ይህ የእግዚአብሔር መንግሥት ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት በፊት በሰዎች ጥረት እንደሚመጣ እድርገው የሚረዱ አሉ። ትክክለኛው አሳብ ግን ክርስቶስ ሰኃይሉና በሥልጣኑ በምድር ላይ መንግሥቱን የሚመሠርትበት ጊዜ እንደሚመጣ ነው። 

ሐ. የክርስቶስ ጻሉት 

ዮሐንስ ምዕራፍ 17 ውስጥ የቀረበው እውነተኛ “የጌታ ጸሎት”፥ በእብና በወልድ መካከል ያለውን የላቀ ሙግባባትና ነጻነት ይገልጣል። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ክርስቶስ የሊቀ ካህናቱን ተግባር ሲያከናውን እንመለከታለን። የጸሎቱ ጭብጥ ከዕለተ በዓለ ኀምሳ በኋላ በሚኖረው ዘመን አማኞች በምድር ላይ በሚያስፈልጓቸው ነገሮች ላይ ያተኮረ ነበር። 

ከርስቶስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ፥ ከመሞቱ ቀደም ብሎ ለረዥም ጊዜ ይጸልይ ነበር (ማቴ. 14፡23)። ሌሊቱን ሁሉ ሳይቀር (ሉቃስ 6፡12)፥ ጸሎቱ ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 17 ውስጥ እንደተጠቀሰው፥ ከአብ ጋር በጥሩ ኅብረት የተከናወነ መሆኑ እውን ነው። የክርስቶስ ጸሎት በተስፋ ቃሎች ወይም በቃል ኪዳኖች ላይ ሳይሆን፥ ሰማንነቱና በካህናዊ የመሥዋዕትነት ሥራው ላይ ነው። የክርስቶስ ጸሉት በተለይም ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 17 ውስጥ የሚገኘው በአብ ቀኝ ሆኖ የሚያከናውነው የምልጃ ተግባር መገለጥ ነው። ይህ የምልጃ ተግባር በአሁኑም ሥፍረዘመን ይቀጥላል። 

መ. ጸሎት በጸጋ ግንኙነት ሥር 

ጸሎት በዘመናት ሁሉ አንድ ዓይነት ገጽታ የለውም። እንደ ሌሎች ሰብአዊ ኃላፊነቶች ሁሉ፥ ከተለያዩ ሥፍረ-ዘመናት ጋር የሚዛመድ ነው። ጸሎት በአዲስ ኪዳን በተሰጠው ሰፊ መገለጥ አዲስ ደረጃ አግኝቷል። ይኸውም በመስቀል ላይ በተፈጸመው መሥዋዕት በተገኘው ሙሉ መገለጥና በክርስቶስ ስም የሚካሄድ መሆኑ ነው። 

በጸጋ ዘመን ባለ አማኝ ሕይወት ውስጥ ከሚገኙ ሰባት ታላላቅ ነገሮች መካከል ጻሉት አንደኛው ነው። እነዚህም ሰባት ነገሮች ክርስቶስ በሰገነት ላይና በጌቴሴማኒ የጠቀሳቸው ናቸው (ዮሐ. 13፡1-17፡26)። ክርስቶስ በዚህ እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ላይ ያቀረበው ትምህርት በሦስት ምንባቦች ውስጥ ተመልክቷል (ዮሐ. 14፡12-14፤ 15 ፡7፤ 16፡23-24)። ከዚህ የክርስቶስ ቃል እንደምንረዳው፥ በአሁኑ የጸጋ ዘመን ጸሎት ከምድራዊ ውሱንነቶች በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ከመሆን የተነሣ ወደማይወሰኑ ልዩ ግንኙነቶች ተሸጋግሯል። የዚህ ዓይነቱ ጸሎት በአራት መልኩ ሊታይ ይችላል። 

1. በጸሎት አገልግሎት ውስጥ የሚካተተው ምስጋና ብቻ ሳይሆን፥ እማኝ የራሱን ችግሮች ለኔታ የሚያቀርብበትና ለሌሎችም ያሚማልድበት ነው። የራሽናሊዝም አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች፥ ሁሉን አዋቂ የሆነው አምላክ ስለ አንድ ነገር ከሚጸልይ ሰው ይበልጥ የሚያስፈልገውን ነገር ስለሚረዳ መጸለይ አስፈላጊ አይደለም ይላሉ። ይሁንና፥ እግዚእብሔር ፈቃዱን ለመፈጸም ጸሎትን እንደ መሣሪያ አድርጎ በሉዓላዊነቱ የደነገገ ከመሆኑም በላይ፥ በርሱ የሚያምኑ ሰዎች ልመናዎቻቸውን እንዲያቀርቡ አስተምሯል። የጸሎት አስፈላጊነት ዮሐንስ 14፡13-14 ውስጥ የተጠቀሰ ሲሆን፥ ክርስቶስም በስሙ የሚጠየቀውን ሁሉ እንደሚሰጥ የተስፋ ቃል ገብቷል። ስለሆነም፥ እግዚአብሔር የራሱን ድርጊት ሰአማኑ ጸሎት እንዲፈጻም እስከማድረግ ድረስ ለጸሎት ከፍተኛ ስፍራ ሰጥቷል። 

እግዚአብሔርን የመጠየቅ ኃላፊነት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለ ኅብረት ጉዳይ ነው። በመሆኑም፥ ትርጉም ይሰጣል ወይም አይሰጥም የሚል ሁኔታ ሳይሆን፥ ራስን ከተሰጠው ትእዛዝ ጋር የማስማማት ጉዳይ ነው። ጸሉት ውስጥ የተካተተውን ሁሉ ልቅም አድርገን ልናውቅ ባንችልም፥ የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑ ሁሉ በጸሎት አገልግሎት አማካይነት ወደ ላቀ የተግባር ተካፋይነት እንደሚመጡ እናውቃለን። ይህ ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ የመሥራት ዕድል፥ ያለ ጸሎት ሊከናወን አይችልም። ክርስቲያን የመጭው ክብር ተካፋይ እንደመሆኑ፥ በሥራ የመካፈል ዕድልም ተሰጥቶታል። ይህ የተሳትፎ ጉዳይ ለአማኞች እንደተሰጠ ልዩ ፈቃድ የሚቆጠር ሳይሆን፥ የመሥዋዕትነት ደም ለፈሰሰላቸው (ዕብ. 10፡19-20) እና አዲስ ፍጥረት ከክርስቶስ ጋር ለተባበሩ ሁሉ የተሰጠ አገልግሎት ነው። ስለሆነም፥ የክርስቶስ ሕያው አካል የሆነ እማኝ የአገልግሉቱም ሆነ የክብሩ ተካፋይ የመሆኑ እግባብነት ግልጥ ነው (ኤፌ. 5፡30)። 

ክርስቶስ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል” (ዮሐ. 14፡12) ያለው ከዚሁ አዲስ የጸሎት ሥልጣን ተካፋይነት አዋጅ ጋር በተዛመደ መልኩ መሆኑ ሊጤን ይገባል። ክርስቶስም ለዚህ የጸሎት አገልግሎት መልስ የሚሰጠው እርሱ ብቻ መሆኑን ወዲያውኑ በተናገረው የዋስትና ቃል ገልጧል። በጸሎትና የጸሎት ውጤትን በሚያመጣው መለኮታዊ ኃይል መካከል ያለው አንድነት ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው በመሆኑ ነው አማኝ “ከዚህም የሚበልጥን ተግባር ሊያከናውን የሚችል መሆኑን ክርስቶስ የተናገረው። 

2. በጸጋ ዘመን ለእያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጅ የተሰጠው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የመጸለይ ሥልጣን፥ ከዚህ በፊት ከነበሩ ጸሎቶች ሁሉ የላቀ ጸሎትን እንዲጸልይ ያደርገዋል። ስለሆነም የአማኙን ጸሎት ከክርስቶስ መክበር በፊት ከነበሩ የጸሎት ዓይነቶች ሁሉ የላቀ የሚያደርገው፥ ከስሙ ጋር ያለ በአንድነት የመሥራት ኅብረት ነው። ክርስቶስ፥ “እስካ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም” ሲል (ዮሐ. 16፡24)። ከዚያ በፊት የነበረውን ማንኛውንም የጸሎት መሠረት መለወጡ ነበር። 

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም የአብን ልብ እንደሚስብና ያ ስም በሚጠራበት ጊዜ አብ መስማት ብቻ ሳይሆን፥ ለውድ ልጁ ሲል የተጠየቀውን ነገር እንደሚፈጽም እርግጠኞች ልንሆን እንችላለን። የክርስቶስ ስም ከማንነቱ ጋር ይያያዛል፤ ስሙ ለአማኞች የተሰጠው እንደ አንድ አስማታዊ ነገር ለመጠቀም አይደለም። በክርስቶስ ስም መጸለይ ማለት ራስን በክርስቶስ ውስጥ እንዳለ አዲስ ፍጡር መቁጠር ነው። በመሆኑም፥ የጸሎት ጉዳዮችን ከክርስቶስ ዓላማዎችና ክብር ጋር ያዛምዳቸዋል። በሌላ አባባል፥ በክርስቶስ ስም መጸለይ ማለት ክርስቶስ የሚጸልየውን መጸለይ ማለት ነው። በክርስቶስ ስም መጸለይ ለልመናችን በስሙ እንደመፈረም ስለሚቆጠር፤ በስሙ የሚቀርብ ጸሎት እርሱ እንደሚስማማበት ሆኖ ሊቀርብ ይገባል። 

ይህን ከተመለከትን ዘንዳ ያዕቆብ ስለ መንፈሳዊ ድህነት የሚናገረውን ማስተዋሉ ተገቢ ነው። “አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤ ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም?” (ያዕ. 4፡2-3)። ጸሎት ለራስ ወይም ለክርስቶስ ነገሮች ልመና ማቅረብ ነው። አማኝ ከእኔነት ስለዳነና በዋናነት ከክርስቶስ ጋር ስለተባበረ (2ኛ ቆሮ. 5፡17-18፤ ቆላ . 3፡3)፥ ስለ ራሱ ብዙም አይጨነቅም። ይህ ማለት ግን የእማኙ ዋና ፍላጎቶች ይወገዳሉ ማለት አይደለም። አማኝ እነዚህን ፍላጎቶች የሚመለከታቸው “ከርስቶስ ሁሉ በሁሉም” በሆነበት ሁኔታ ነው። ክርስቶስ ውስጥ ሆነን በስሙ መጸለያችን ተገቢ ቢሆንም፥ ከርሱ ክብር ላራቁ የራስ መሻቶች ብቻ መጸለዩ ግን ትክከል አይደለም። 

ጸሎት ሊቀርብ የሚችለው፥ በፈሰሰው የክርስቶስ ደምና አማኝ ከክርስቶስ ጋር ሳለው ግንኙነት ላይ በመመሥረት ብቻ በመሆኑ ድነት ያላገኘ ሰው ጸሎት ተቀባይነት የለውም። 

3. በጸጋ ሥር ለሚመላለስ ሰው ዮሐንስ 14፡13-14 ውስጥ እንደምናነበው “ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምን የሚለው የጸሎት አሳብ የራሱ ውሱንነቶች አሉት። ይህ በክርስቶስ ስም የሚቀርብ ጸሎት፥ ከጌታ ከክብሩና ዓላማዎቹ ጋር መገናዘብ አለበት። እውነተኛ ጸሎት ከመቅረቡ በፊት፥ ልብ ከክርስቶስ አሳብ ጋር መስማማት አለበት። “በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል” (ዮሐ. 15፡7) የተባለው እውነት ነው። የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑ አማኞች በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ልባቸውን ሲያስተካክሉ፥ ጸሎታቸው የሚያተኩረው በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ በሚገኙ ነገሮች ላይ ይሆናል። 

በጸጋ ሥር ለሚኖር፥ የእግዚአብሔርን በጎ ፈቃድ ለማድረግም ሆነ ላመሻት ለሚመርጥ ሰው ፍጹም የተግባር ነጻነት ተሰጥቶታል (ፊልጵ. 2፡13)። በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ሆኖ ለሚጸልይ ሰውም ያልተገደበ የጸሎት ነጻነት አለው። በመንፈስ ቅዱስ ለተሞላ እማኝ የሚከተለው ተብሎለታል፡- “እንዲሁም መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል” (ሮሜ 8፡26-27)። በጸጋ ዘመን፥ የጸሎት ክልል ጠባብ አይደለም። በስሙ የመጻላይ ስፋቱ የጌታችንን ዘላለማዊ መሻቶች ያህል ሰፊና ጥልቅ ነው። 

4. እውነተኛ አማኝ ጸሎቱን ሲያቀርብ ጥንቃቄ የተሞላበት ትኩረት ሲያደርግ ይገባል። አማኞች መደበኛ የጸሎት ሰዓት ቢኖራቸው መልካም ነው። ለጸሎት አክብሮት የሌለው ተግባር ከመፈጸም ወይም እንደ አረማዊው ዓለም ቃላትን በከንቱ ከመደጋገም መታቀብ ይገባል። በጸጋ ዘመን ለጸሎት የተሰጠውን መለኮታዊ ቅደም ተከተል መከተል ያሻል። ይህም በሚከተሉት ቃላት ተገልጧል፡- “በዚያን ቀንም ከእኔ እንዳች አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል” (ዮሐ. 16፡23)። ጸሎት በመንፈስ ቅዱስ” መደረግ አለበት (ይሁዳ 20)። 

ጸሎታችንን በክርስቶስ በኩል ከመጸለይ ይልቅ በቀጥታ ወደ ክርስቶስ ማድረግ የጌታን ድንቅ የአማላጅነት ሥራ መተው ይመስላል። በጸጋ ካገኘነው ታላቅ እውነት፥ ማለትም በልጁ ስም (ዮሐ. 16፡23) ወደ አብ የመቅረብን አሳብ ስፍራ ያሳጣዋል። 

እንደሁም ወደ መንፈስ ቅዱስ ስንጸልይ፥ ወደ አብ እንድንቀርብ የሚያበረታታንን የመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚያስቀርብን ይመስላል (ይሁዳ 20)። ስለዚህ በጸጋ ዘመን ጸሎት በወልድ ስምና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለአብ፥ ሊቀርብ ይገባል ለማለት ይቻላል። 

ሠ. የምስጋና ጸሎት 

እውነተኛ ምስጋና አንድ አማኝ ላገኘው በረከት ከልብ የመነጨ አክብሮት በፈቃዱ የሚገልጥበት ነው። የምስጋናችን ጥልቀት እንዳገኘነው በረከት መጠን ነው (2ኛ ቆሮ. 9፡1)። ቢሆንም የምስጋናችን ቅንነትና ከልብ መሆን ነው በጌታ ዘንድ ተቀባይነት ያለው። የምስጋናችን ፍሬም ያን ያህል ይሆናል። ምስጋና ግለሰብ በተለየ መንገድ የሚያከናውነው ነው። ሌላ ሰው ሊያከናውንልን የሚችላቸው ግዴታዎች ሲኖሩም፥ የኛን የምስጋና ቃል ሊያቀርብልን የሚችል ግን የለም (ዘሌ. 22፡29)። 

ምስጋና፥ በረከት ተቀባዩ የለጋሹን ባለ ውለታነት የሚገልጥበት እንጂ ለተገኘ ጥቅም ክፍያ አይደለም። ለማይለካና ለማይቆጠር በረከቱ ለእግዚአብሔር የሚከፈል ነገር ስለሌለ፥ ምስጋና የማቅረቡ ግዴታ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተገልጧል። ምስጋና ሁሉ ከአምልኮና ከውዳሴ ጋር የተያያዘ ነው። 

በብሉይ ኪዳን ሥርዓት፥ ከእግዚአብሔር ጋር የሚደረጉ መንፈሳዊ ግንኙነቶች የሚገለጡት በቁሳዊ መንገዶች ነበር። ከነዚህም መካከል የምስጋና መሥዋዕት ማቅረብ እንዱ ነበር (ዘሌ. 7፡12፥ 13፥ 15፤ መዝ. 107፡22፤ 116፡17)። በዚህም ዘመን ቢሆን ለእግዚአብሔር የምስጋና መሥዋዕት ማቅረብ አማኝ ሊጠቀምበት የሚገባ ዕድል ነው ። ይሁንና አማኝ የምሥጋና መሥዋዕት ስጦታ በሚያቀርብበት ጊዜ ከእግዚአብሔር ለተቀበለው በረከት አጸፋ እንደሰጠ የሚያስብ ከሆነ፥ የምስጋና ወሳኝ እሴት መና መቅረቱ ነው። 

የጸሎት ጉዳይ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ሰመዝሙረ ዳዊት በተደጋጋሚ ተጠቅሷል። በብሉይ ኪዳን ስለ ምስጋና መሥዋዕቶች ግልጥ መመሪያ የተሰጠ ሲሆን (ዘሌ. 7፡12-15)፥ ህምያ ሰመራው መነቃቃት (revival/ሪቫይቫል) ወቅት ምስጋናና ውዳሴ ልዩ አጽንኦት ተሰጥቶታል (ነህ. 12 ፡24-40)። ምስጋና በሚመጣው መንግሥት የአምልኮ አስፈላጊ ጉዳይ መሆኑን የብሉይ ኪዳን ትንቢታዊ መልእክቶችም አመልክተዋል (ኢሳ. 51፡3፤ ኤር. 30፡19)። በሰማይም የማያቋርጥ ምስጋና ይቀርባል(ራእይ 4፡9፤ 7፡12፤ 11፡7)። 

ካበረከቱ ባሻገር እግዚአብሔርን ስለ ማንነቱ ማመስገን በብሉይ ኪዳን ተቀዳሚ ተግባር እንደነበር እንመለከታለን (መዝ. 30፡4፤ 95 ፡2፤ 97፡12፤ 100፡1-5፤ 119፡62)። ምንም ችላ የተባለ ቢሆን፥ የምስጋና ጉዳይ እጅግ አስፈላጊና ተገቢ ነው። “እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው” (መዝ. 92፡1)። በአዲስ ኪዳን የምስጋና ጉዳይ አርባ አምስት ጊዜ ያህል ተጠቅሷል። ይህን መሰሉ ምስጋና ለመንፈሳዊም ሆነ ለሥጋዊ በረከቶች ይቀርባል። ክርስቶዕ አዘውትሮ ስለ ምግብ ምስጋና ማቅረቡ ለአማኞች ሁሉ ምሳሌ ሊሆን ይገባል (ማቴ. 15፡36፤ 26፡27፤ ማር. 8፡6፤ 14፡23፤ ሉቃስ 22፡17፥ 19፤ ዮሐ. 6፡23፤ 1ኛ ቆሮ. 11 ፡24)። በዚህ ረገድ፥ ሐዋርያው ጳውሎስም ታማኝ ነበር (ሐዋ. 27፡35፤ ሮሜ 14፡6፤ 1ኛ ጢሞ. 4፡3-4)። 

የሐዋርያው ጳውሎስን ምስጋና አሰጣጥ በሚገባ ልናጤነው ይገባል። ክርስቶስ “የማይነገር ስጦታ” ስለመሆኑ (2ኛ ቆሮ. 9፡15)፥ በትንሣኤው አማካይነት በሞት ላይ ስለተገኘው ድል (1ኛ ቆሮ. 15፡57)፥ ብሎም በአሁኑ ዘመን ክርስቶስ ስላስገኘልን ድል (2ኛ ቆሮ. 2፡14)፥ “ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን” ሲል ይናገራል። ስለ አማኞች ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው ምስጋና (1ኛ ተሰ. 1፡2፤ 3፡9)፥ በተለይ ደግሞ ስለ ቲቶ (2ኛ ቆሮ. 8፡16) እና ስለ ሰዎች ሁሉ ምስጋና እንዲቀርብ መምከሩ (1ኛ ጢሞ. 2፡1)፥ የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ልብ ሊሉት ይገባል። 

በአዲስ ኪዳን አገላለጥ፥ ሁለት አስፈላጊ የምስጋና ሁኔታዎች መጤን አለባቸው። 

1. ምስጋና የማያቋርጥ ጸሎት ሊሆን ይገሰል። የተወዳሹ የእግዚአብሔር ማንነት ስለማይለውጥና በረከቱም ስሰማያበቃ፥ እንዲሁም በብዙዎች ምስጋና አማካይነት የተትረፈረፈው የእግዚአብሔር ጸጋ ለክብሩ ስለሚበዛ (2ኛ ቆሮ. 4፡15)፥ ባለማቋረጥ እርሱን ማመስገን ተገቢ ነው። ይህን ስለመሰሰው ምስጋና የሚከተለውን አሳብ እናገኛለን። 

“እንግዲህ ለእግዚአብሔር የምስጋና መሥዋዕት፥ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ በእርሱ እናቅርብለት” (ዕብ. 13፡15ን ካኤፌ. 1፡16፤ 5፡20፤ ቆላ. 1፡3፤ 4፡2 ጋር ያነጻጽሩ)። ይሄው የምስጋና ጉዳይ በብሉይ ኪዳንም አጽንኦት ተሰጥቶታል (መዝ. 30፡12፤ 79፡13፤ 107፡22፤ 116፡17)። 

2. ኤፌሶን 5፡20 ውስጥ እንደተመለከተው፥ ስለ ማንኛውም ነገር ምስጋና ማቅረብ ተገቢ ነው። “ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ።” 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡18 ውስጥም ተመሳሳይ አሳብ ይገኛል፡- “በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና” (ከፊልጵ. 4፡6፤ ቆላ. 2፡7፤ 3፡17 ጋር ያገናዝቡ)። 

ሁልጊዜ ለሁሉ ነገር እግዚአብሔርን ማመስገን፥ አንዳንድ ጊዜ ላአንዳንድ ነገሮች ከማመስገን የላቀ ነው። ይሁንና፥ እግዚአብሔርን ለሚወዱት ነገር ሁሉ ለበጎ እንደሚደረግ የሚናገረውን እውነት በመቀበል፥ ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔርን ማመስገኑ ትክክለኛ ድምጻሜ ነው። እንዲህ ዓይነቱ እግዚአብሔርን የሚያከብር ምስጋና ሊቀርብ የሚችለው በጻኑና በመንፈስ ቅዱስ ሰተሞሉ ሰዎች ብቻ ነው (ኤፌ. 5፡18-20)። ዳንኤል ሞት ተፈርዶበት እያለ እግዚአብሔርን አመስግኗል (ዳን. 6፡10)፤ ዮናስም ዓሣ ነባሪ ሆድና ጥልቅ ባሕር ውስጥ ሆኖ እግዚአብሔርን አመስግኗል (ዮናስ 2፡9)። 

እግዚአብሔርን ያለማመስገን ኃጢአት በክርስቶስ አገልግሎት ውስጥ ከተመ ዘገቡት ክስተቶች በአንደኛው ተብራርቷል። አሥር ለምጻሞች ከለምጻቸው ተፈውሰው ሳለ ምስጋና ለማቅረብ የተመለሰው አንድ ሳምራዊ ብቻ ነበር (ሉቃስ 17፡11-19)። እዚህ ላይ ያለ ማመስገን “በመጨረሻ ዘመን” ከሚፈጸሙ ኃጢአቶች አንዱ ሆኖ እንደተጠቀሰ ልብ ማለቱ ተገቢ ነው (2ኛ ጢሞ. 3፡2)። ስለሆነም፥ ያለማመስገን ኃጢአት ነው። 

ድነትን ያላገኙ ብዙ ሰዎች ለተቀበሷቸው ሥጋዊ ጥቅሞች እውነተኛና ታማኝነት የሚታይበት ምስጋና ለማቅረብ ይጥራሉ። ይሁንና፥ ለኃጢአታቸው ይቅርታ እግዚአብሔር የሰጣቸውን አንድያ ልጁን ባለመቀበላቸው ምስጋናቸው እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ መልኩ አይቀርብም። ምክንያቱም ዋነኛ የሆነውን ስጦታ ስላልያዙ ነው።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

39
ትምህርት 39 ከ52

ቤተ ክርስቲያን፡- አደረጃጀትና ሥርዓቷ

ሀ. የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር 

ቤተ ክርስቲያን እንደ ክርስቶስ አካልነቷ፥ በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካይነት የአካሉ ራስ ከሆነው ክርስቶስ ጋር የተባበረውን ማንኛውንም ክርስቲያን ታካትታለች። አካል እንደ መሆኗ፥ የዕውን የአካል ክፍል በሚመስል አኳኋን ተዋቅራለች። እያንዳንዱ የሰውነት ክፍል ከሌላው ጋር ይገናኝና፥ ጠቅላላውን አካል ከሚመራው ራስ ጋር ይዛመዳል። የክርስቶስ አካል የሆነችው እውነተኛ ቤተ ክርስቲያን ግንኙነት መንፈሳዊና መለኮታዊ እንደ መሆኑ፥ ድርጅታዊነትን እንደ ዋና ነገር አድርገን መውሰድ እንችልም። 

ይህም ሆኖ፥ በቀደመው ዘመንም ሆነ ዛሬ፥ ለአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የተወሰነ አደረጃጀት አስፈላጊ ይመስላል። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ሦስት የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዓይነቶች ይገኛሉ። እነዚህ የአስተዳደር ዓይነቶች ከሐዋርያት ዘመን ጋር የተያያዙ ናቸው። 

1. በኤጵስቆጶሳዊ” የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ለጵጵስና ወይም ሌላ ዓይነት የማዕረግ ስያሜ ለአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መሪ ይሰጣል (1ኛጢሞ. 3፡1)። ይህ ዓይነቱ የቤተ ክርስቲያን ተሰያሚ በሚሰጠው ሥልጣን መሠረት ቤተ ክርስቲያኒቱን ይመራል። እንዲህ ያለው አደረጃጀት ወደ ከፍተኛ ድርጅታዊነት በማደጉ፥ ጳጳሳት በተወሰኑ እካባቢዎች የአብያተ ክርስቲያንን እንቅስቃሴዎች በበላይነት ለመቆጣጠር ይሾማሉ። እንዲህ ዓይነቱ አሠራር በሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፥ በእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያንና በሜተዲስት ቤተ ክርስቲያን የተላመደ ነው። 

2. ቀተወካዮች” የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በአግባቡ የሚወከሉ ግለሰቦችን ሥልጣን ይቀበላል። እነዚህ ተወካዮች በአብዛኛው በመልክዓ-ምድራዊ ክልል የሚወሰኑ ሲሆን፥ በፕሬስቢቲሪያንና ሪፎርምድ አብያተ ክርስቲያን ውስጥ የተለመዱ ናቸው። ብዙውን ጊዜ አንድ አካባቢ ያለ የአብያተ ክርስቲያን የተወካዮች ቡድን ከርሱ በበለጠ አካል ወይም ሲኖዶስ ሥር የሚንቀሳቀስ ይሆናል። ሲኖዶሱም በበኩሉ ከርሱ ስላቀ አጠቃላይ ጉባኤ ይገዛል። ምንም እንኳ ደንቦችና የሥልጣን ደረጃዎች ቢለያዩ፥ ዋናው አሳብ በተገቢው መንገድ የተመረጡ ተወካዮች የቤተ ክርስቲያንን ሥልጣን የሚይዙ መሆናቸው ነው። 

3. በጉባኤያዊ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዓይነት ሥልጣኑን የሚይዘው የእግቢያ ጉባኤ ነው። በዚህ የአስተዳደር ዓይነት ለዋነኞቹ ጉዳዮች ውሳኔ የሚሰጠው፥ የሌሎቹን አብያተ ክርስቲያን ወይም ባለሥልጣናት ሥልጣን ከግንዛቤ ሳያስገባ ጉባኤው ብቻ ነው። ይህን ዓይነቱ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር እንደ ባፕቲስት አብያተ ክርስቲያን በመሳሰሉት ይዘወተራል። ምንም እንኳ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ለበላይ አካላት፥ ኮሚቴዎች ወይም ኃላፊዎች በተወሰነ ደረጃ ሊገዙ የተገባ ቢሆንም፥ የዚህ ዓይነቱ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዋነኛ አሳብ፥ ጉባኤዎች የራሳቸውን ጉዳዮች የሚወስኑ አገልጋዮች የሚሾሙና የራሳቸውን መዋዕለ ንዋይ አጠቃቀም የሚመሩ መሆኑን ነው። 

በመጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን ሦስቱም የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ቅርፆች በተወሰነ ደረጃ አገልግለዋል። ሐዋርያት ቀዳሚ ሥልጣን የነበራቸው መሆኑን ብዙዎቹ የቀድሞ አብያተ ክርስቲያን ተገንዝበዋል። ይሁንና፥ ይህ ከመጀመሪያው ክርስቲያን ትውልድ ጋር ያለፈ ይመስላል። ሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 15 ውስጥ እንደተገለጠው፥ ሐዋርያትና በኢየሩሳሌም የሚገኙ ሽማግሌዎች፥ አብያተ ክርስቲያን ላነሱዋቸው የአስተምህሮ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጡ ተወካዮች ነበሩ። ይህን ካለንበት ዘመን የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር አሠራር አንጻር ስናየው ግን፥ እነዚህ ሰዎች ተመራጮች ወይም የቤተ ክርስቲያን ተወካዮች አልነበሩም። አብያተ ክርስቲያን እየበሰሉ መጥተው የሐዋ ርያትን ተቆጣጣሪነት ከማይፈልጉበት ደረጃ ላይ በደረሱ ጊዜ፥ የአብያተ ክርስቲያን አስተዳደር ለአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የተላለፈ ይመስላል። ራእይ 2-3 ውስጥ የተጠቀሱትን ሰባት የእስያ አብያተ ክርስቲያን በተመለከተ እውን የነበረ ይመስላል። እነዚህ አብያተ ክርስቲያን ከራሱ ከክርስቶስ በቀር ለማንኛውም ሰብአዊ ሥልጣን አይገዙም ነበር። ከዚህ አንጻር ሲታይ፥ በአሁኑ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚታየው የረቀቀና የተወሳሰበ አስተዳደር በመጽሐፍ ቅዱስ የሚደገፍ መሆኑ አጠራጣሪ ስለሆነ፥ ወደ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ግንዛቤ መመለሱ ተገቢ ነው። 

ለ. የቤተ ክርስቲያን መሪዎች 

በመጀመሪያው ዓመተ ምህረት የነበሩ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች እንደ “ኤጲስ ቆጶስ” ወይም “ሽማግሌዎች ተሰይመው እጥቢያይቱን የሚመሩት ሰዎችን ያካትታል። ምንም እንኳ ስሞቻቸው በመጠኑ ቢለያይ፥“ኤጵስ ቆጶሳትን እና “ሽማግሌዎች” አንድ ዓይነት ሰዎች ሳይሆኑ አይቀሩም። 

ምናልባትም የአዲስ ኪዳን የሽማግሌዎች ፅንሰ-አሳብ የተወሰደው፥ በእስራኤል ላይ ሥልጣን ከነበራቸው ሽማግሌዎች አሠራር ሆኖ (ማቴ. 16፡21፤ 26፡47÷ 57፤ ሐዋ. 4:5፥ 23)፥ በአስተሳሰቡ የበሰለና ሥልጣን ሊይዝ የሚገባውን ሰው ያመለክት ነበር። ስለሆነም፥ ሽማግሌ ለመሪነት የሚያበቁትን መመዘኛዎች የሚያሟላ ሰው እንደነበረ እንረዳለን። “ኤጲስ ቆጶስ” የሚለው ቃል የሰውን ሥልጣን ወይም አገልግሎት የሚገልጥ ነው። ኤጲስ ቆጶስ ሁልጊዜ ሽማግሌ ሲሆን፥ ሽማግሌ ግን በተወሰኑ ሁኔታዎች ምክንያት ኤጲስ ቆጶስ ሊሆን አይችል ይሆናል። ማለት ሥልጣ ሳይኖረው ብቃቱ ሲኖረው ይችላል። በቀድሞይቱ ቤተ ክርስቲያን ሁለቱም ቃላት በተመሳሳይነት ያገለገሉ ይመስላል (ቲቶ 1፡5፥ 7)። 

ኤጲስ ቆጶስና ሽማግሌዎች ቤተ ክርስቲያንን የማስተዳደር (1ኛ ጢሞ. 3፡4-5፤ 5፡17)፥ ቤተ ክርስቲያንን ከግብረ ገባዊ ወይም ሥነ-መለኮታዊ ስሕተት የመጠበቅ (ቲቶ 1፡9) እና እረኛ መንጋውን እንደሚንከባካብ ቤተ ክርስቲያንን የመንከባከብ ወይም የመቆጣጠር የመሳሰሉ ኃላፊነቶችን መወጣት ነበረባቸው (ዮሐ. 21፡16፤ ሐዋ. 20፡28፤ ዕብ. 13፡17፤ 1ኛ ጴጥ. 5፡2)። የመጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች በሐዋርያት የተሾሙ ቢመስልም፥ አብያተ ክርስቲያኑ እየበሰሉ ሲመጡ የመሾሙን ተግባር ራሳቸው ሳያካሂዱት አልቀሩም። ሹመቱ የሰዎቹን የመሪነትና መንፈሳዊ ብቃት ያገናዘበ ነበር (ሐዋ. 14፡23፤ 20፡28፤ ቲቶ 1፡5፤ 1ኛ ጴጥ. 5፡2)። 

ከሽማግሌዎችና ኤጲስ ቆጶሳት ባሻገር ሌሎች አገልጋዮች ዲያቆናት ተብለው ይሾሙ ነበር። ዲያቆናት በቀድሞይቱ ቤተ ክርስቲያን ምንም እንኳ መንፈሳዊ ስጦታዎች ሊኖራቸው ቢችል፥ ቀዳሚ ትኩረት የሚሰጡት ግን ችግረተኞችን በመርዳቱና ቁሳዊ አገልግሎት በማበርከቱ ተግባር ላይ ነበር (ሐዋ. 6፡1-6፤ 1ኛ ጢሞ. 3፡8-13)። እንደ ሽማግሌዎቹ ሁሉ ዲያቆናት በቀድሞይቱ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያት (ሐዋ. 6፡6፤ 13፡3፤ 1ኛ ጢሞ. 1፡6) ወይም በሽማግሌዎች ሳያሾሙ አይቀሩም (1ኛ ጢሞ. 4፡14)። በኤጲስ ቆጶስና ሽማግሌዎች አገልግሎት እንደሚደረገው፥ በድቁና ሹመትና ዲያቆኑ በሚያበ ረክተው አገልግሎት መካካል ልዩነት ሊደረግ ይገባል። ፊልጶስ በመንፈሳዊ ስጦታው ወንጌላዊ ቢሆንም፥ የድቁና ሥልጣን ነበረው (ሐዋ. 6፡5፤ 21፡8)። 

ዛሬ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያን መጋቢውን እንደ አንድ ብቸኛ ሽማግሌ፥ እድርገው ይመለከቱታል። በመንፈሳዊ ጉዳዮች የሚረዱትን ሌሎች ሰዎች ደግሞ እንደ ዲያቆናት ይመለከቷቸዋል። ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልምምድ አይመስልም። 

ሐ. የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶች 

አብዛኛዎቹ የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያን ሁለት ሥርዓቶችን፥ ማለት ጥምቀትንና የጌታ እራትን ብቻ ነው እንደ ሥርዓት የሚቀበሉት። ከነዚህ አብያተ ክርስቲያን አንዳንዶቹ ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጠበበትን ምሳሌ (ዮሐ. 13)፥ እንደ ሥርዓት አድርገው በመውሰድ በተግባር ይፈጽሙታል። የሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በነዚህ ላይ ሌሎች ጥቂት ሥርዓቶችን ይጨምራሉ። ከሞላ ጎደል በሁሉም የተለመዱ ሥርዓቶች ጥምቀትና ቅዱስ ቁርባን ብቻ ናቸው። 

1. በቤተ ክርስቲያን ታሪክ፥ የውኃ ጥምቀት ሥርዓት ከፍተኛ ውዝግብ ያስከተለ ሲሆን፥ ለቤተ ክርስቲያን ክፍፍልም እስተዋጽኦ አድርጓል። በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የሚነሡ ክርክሮች በአጠቃላይ ሁለት ዓበይት ችግሮችን ያካትታሉ፤ () የውኃ ጥምቀት ሥርዓት ብቻ ነው? ወይስ ለተጠማቂው የሚያበረክተው መለኮታዊ ጥቅም አለ? (2) አፈጻጻምን በተመለከተ፥ የውኃ ጥምቀት የሚከናወነው በመጥለቅ ብቻ፥ ወይስ በተጠማቂው ላይ ውኃ በማፍሰስና በመረጨትም ሊሆን ይችላል? 

የውኃ ጥምቀት፥ ሥርዓት ብቻ መሆኑን የሚያምኑ ሰዎች ድርጊቱ መንፈሳዊ እውነትን እንደሚያካትት፥ ነገር ግን ለተጠማቂው የሚያስተላልፈው ምንም ዓይነት ጸጋ ወይም ሕይወት እንደሌለ ያስረዳሉ። የውኃ ጥምቀት ሥርዓት ብቻ መሆኑን የሚያመለክተው ገለጣ የተሻለ አተረጓጎም ነው። የውኃ ጥምቀት አንዳች ልዩ ጸጋ እንደሚያስገኝ የሚያምኑ ሰዎች ድርጊቱ ለተጠማቂው የሚያስገኘውን የበረከት መጠን በተመለከተ በእጅጉ ይለያያሉ። አንዳንዶች ጥምቀትን ከዳግም ልደት ጋር በማነጻጸር፥ በአንድ ሰው ዳግም ልደት ውስጥ ድርሻ እንዳለው ይናገራሉ። ሌሎች ደግሞ እንዲሁ ጸጋን እንደሚያስገኝ ወይም ወደ እምነትና ለወንጌሉ ወደ መታዘዝ እንደሚመራ ያምናሉ። ጥምቀት ሥርዓት ብቻ የመሆኑን አሳብ የሚቃወሙ ወገኖች የውኃ ጥምቀት፥ ከመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ከአማኙ ዳግም ልደት ጋር በማይነጣጠል መልኩ የተጣመረ መሆኑን ይገልጣሉ። 

ባፕቶ” የሚለው የግሪኩ ቃል “አንድን ነገር ፈሳሽ ውስጥ መንከር” የሚል ትርጉም አለው። ይህ ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ ሦስት ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን በአማርኛ “ነከረ” (ሉቃስ 16:24)። “አወቀሰ” (ዮሐ. 13:26)፥ “ተረጨ” (ራዕይ 19፡13) በሚል ተተርጉሟል። 

“ባፕቲዞ የሚለው የግሪኩ ቃል ባፕቶ” ከሚለው የመጣ ሲሆን በአዲስ ኪዳን የተለያየ ትርጉም አለው። “ማጥመቅ” የሚለው የግሪክ ቃል ባፕቲዞ” ሲሆን፤ ይህ ቃል በአዲስ ኪዳን የተለያየ ትርጉም ይዞ እናገኘዋለን።* [* በግሪኩ ጥምቀት መጠመቅ የሚል ቀጥተኛ አባባል (ማቴ. 20፡22-23፤ ሉቃስ 12፡50፤ 1ኛ ቆሮ. 10፡2) ተጠቅሷል። ውኃ የሚል ቃል በነዚህ ክፍሎች ስለሌለ አንዳንዶች ለጥምቀት ውኃ አያስፈልግም የሚል ትምህርት ያስተምራሉ። ይህ የአባባል ጕዳይ መሆኑን ልንገነዘብ ይጎዳል። አሳሳሉ የሚሰጠው ትርጉም በአስቸጋሪ ልምምድ ወይም መከራ ውስጥ” መግባትን ነው። ስለዚህ ውኃንም ሆነ ምንም ዓይነት የሃይማኖት ሥርዓተ ትምህርትን የሚያመለክት አይደለም።] (1) የመንፃትን ሥርዓት አስመልክቶ አጥባቂ አይሁዳውያን የሚያደርጉትን የመታጠብ ሥርዓትን ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል (ማር 7፡4፤ ሉቃስ 11፡38)። (2) ቃሉ የአንድ ሰውን ወደ እንድ የሃይማኖት ቡድን መግባቱን በጉባዔ ማስታወቅን በማመልከት ረገድ ጥቅም ላይ ውሏል።* [*የጥምቀት ሥርዓት በተለያየ መልኩ በብዙ የሃይማኖት ክፍሎች ይከናወናል። ለምሳሌ ወደ አይሁዳዊነት የተለወጡ አሕዛብ በመጀመሪያ መገረዛቸው፥ ከዚያም ሁለት ካህናት ከሕግ መጻሕፍት እያነበቡላቸው መጠመቂያ ገንዳ መታጠባቸው የተለመደ ነበር።] ለምሳሌ መጥምቁ ዮሐንስ የንስሀን ጥምቀት” ሰብኳል። በዚህ ስብከቱም ብዙዎች ንስሀ በመግባት የንስሀቸውን ፍሬ ያሳዩ ዘንድ በውኃ ተጠመቁ(ማር. 1፡4)። 

ጴጥሮስም በጰንጠቆስጤ ቀን በሰበከው ስብከት ያመኑትን ይጠመቁ ዘንድ አሳስቧቸዋል (ሐዋ. 2፡38)። በጥምቀታቸው የኢየሱስ ክርስቶስን መሢሕነት በመመስክር ከክርስቲያኖች ጋር አንድነታቸውን የሚመሰከሩበት ሥርዓት ነበር። 

ክርስቶስ የሞት ሥቃዩን እንደ ጥምቀት የጠቀሰ ሲሆን፥ በቀይ ባሕር ውስጥ ውኃ ሳይነካቸው (ማቴ. 20፡22-23) ያለፉ እስራኤላውያንም በደመናና በባሕር እንደተጠመቁ ተገልጧል (1ኛ ቆሮ. 10፡2)። ስለሆነም፥ ውኃ ውስጥ በአካል መግባቱ ለመጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥምቀት አስፈላጊ አይደለም የሚል ክርክር አለ። 

በቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደታየው፥ ለሚጠመቀው ሰው ላይ ውኃ የማፍሰስ ተግባር ይከናወን ነበር። ድርጊቱ ያገለግል የነበረው፥ በጅነት ጊዜ የመንፈስ ቅዱስን መውረድ በተምሳሌትነት ለማመልከት ሲሆን፥ መጠነኛ ውኃ “በመርጨት” ብቻም ጥምቀቱ ይከናወን ነበር። በጥምቀት አስተምህሮ ዙሪያ የተነሡ ውዝግቦች መቋጫ አልነበራቸውም። በአንዳንድ አጋጣሚዎች፥ ለምሳሌ የክርስቶስን ጥምቀት ዕንመለከት፥ ሥርዓቱ ተግባራዊ የሆነው በመንከር የነበረ ይመስላል። የፈልጵስዩስን የወኅኒ ቤት ጠባቂ ዓይነቶቹን ሌሎች አጋጣሚዎች ስንመለከት ግን (ሐዋ. 16፡33)፥ ጠባቂውና ቤተሰቦቹ በዚያ ጽልመታም ጠዋት ውኃ ውስጥ ተነክረዋል ማለቱ እዳጋች ስለሚሆን፥ ጥምቀቱ ሊካሄድ የሚችለው ቤት ውስጥ በተጠማቂዎቹ ላይ ውኃ በማፍሰስ እንደሆነ ይገመታል። 

በመንከር ማጥመቁ ሥርዓታዊ ተደርጎ ስለሚወሰድ፥ የብዙዎቹ ወንጌል አማኝ አብያተ ክርስቲያን ዝንባሌ፥ መርጨት ተገቢ የጥምቀት አፈጻጸም በመሆኑ ጉዳይ ላይ ከመከራከር ይልቅ የመንከሩን ሥርዓት መከተልን፥ ይመርጣሉ። ይበልጥ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነገር ግለሰቡ ዳግም ተወልዶ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወደ ክርስቶስ አካል የመጣበቁ ጉዳይ ነው። በመሆኑም ለውኃ ጥምቀት አፈጻጸም ክርክር መፍጠር ተገቢ አይደለም። 

በዚህ ትምህርት ዙሪያ የሚነሣው ሌላ ውዝግብ ሕፃናትን የማጥመቁ ጉዳይ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ሕፃናት ጥምቀት የሚገኘው መረጃ አነስተኛ ነው። ሕፃናትን የሚያጠምቁ ወጎኖች እንደ እስራኤላውያኑ የግርዘት ሥርዓት ልጆችን ለእግዚአብሔር የሚለዩበት የዚህ ዘመን አሠራር እንደሆነ ያስባሉ። ሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 16 ውስጥ እንደተጠቀሰው፥ ምንም እንኳ የቤተሰቡ አባላት ሲጠመቁ ሕፃናትም ቢኖሩበት፥ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሌላ ስፍራ ስለ ሕፃናት ጥምቀት በግልጥ የተጠቀሰ ነገር የለም። ከዚህም የተነሣ፥ አብዛኛዎቹ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያን፥ የውኃ ጥምቀትን በክርስቶስ ላይ ለተጣለ እውነተኛ እምነት ውሳኔ ለመስጠት ከሚያስችል ዕድሜ ላይ ለደረሱት ብቻ በማቆየት፥ ልጆችን ለእግዚአብሔር አሳልፎ የመስጠትን ሥርዓት መከተሉን ይመርጣሉ። 

ልጆችን ማጥመቅ ወላጆች የኋላ ኋላ ልጃቸው እንደሚድን ያላቸውን እምነትና ተስፋ የሚገልጡበት ሥርዓት ከመሆን አያልፍም። የአዋቂዎች ጥምቀት በማንኛውም መልኩ በክርስቶስ ላይ የሚጣለውን እውነተኛ እምነት ተከትሎ ሊፈጸም ይገባዋል። ምንም እንኳን የጥምቀት አፈጻጸም ከሕፃናት ጥምቀት ጋር የግድ ባይተሳሰር፥ በአጠቃላይ አነጋገር ልጆች የሚጠመቁት ከመንከር ይልቅ በመርጨት ነው። ጥምቀት በመንከር ብቻ መፈጸም እንዳለበት የሚያምኑ ወገኖች በአጠቃላይ፥ ከልጆች ይልቅ አዋቂዎች ወይም አማኞች ብቻ መጠመቅ እንዳለባቸው ይገነዘባሉ። 

የጥምቀት አፈጻጸም ሥርዓት እንዴትም ይሁን እንዴት፥ ዋነኛ ትርጉሙ፥ አማኝ ያለ ክርስቶስ ከነበረበት ሕይወት ተለይቶ አሁን የክርስቶስ ሞትና ሕይወት በረከቶች ተጠቃሚ መሆኑ ነው። የቀድሞይቱ ቤተ ክርስቲያን የጥምቀትን ሥርዓት ባለማቋረጥ ታከናውን ነበር፤ ዛሬም ሁሉም የቤተ ክርስቲያን ክፍሎች በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የውኃ ጥምቀትን ይፈጽማሉ። 

2. የቅዱስ ቁርባን ሥርዓት የተጀመረው በክርስቶስ ምት ዜማ ምሽት ሲሆን፥ እማኝ በርሱ ምት አማካይነት የሚካፈላቸው በረከቶች ተምሳሌት ሆኖ ነው የቀረበው። ሥርዓቱ አይሁዶች ከግብፅ ከወጡበት ጊዜ አንሥቶ የሚያከብሩትን የፋሲካ በዓል ተክቷል። 

1ኛ ቆሮንቶስ 11፡23-29 ውስጥ እንደተተነተነው፥ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱ እንጀራውን እንዲቆርሱ ሲያስተምራቸው፥ እንጀራው ለነርሱ የሚሠዋ ሥጋውን እንደሚወክል ነግሯቸዋል። ይህንንም ሥርዓት እርሱ ከተለያቸው በኋላ ለመታሰቢያ ሊያደርጉት ይገባ ነበር። የወይን ጠጁን ደግሞ የአዲስ ኪዳን ደሙ እንደሆነ ክርስቶስ ገልጧል። ከጽዋው ሲጠጡ የክርስቶስን ሞት ያስታውሱ ነበር። ስለሆነም ተመልሶ እስኪመጣ ድረስ ይህንኑ ሥርዓት ማክበር ነበረባቸው። 

በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በቅዱስ ቁርባን የተለያዩ አመለካከቶች ላይ ማክተሚያ የሌላቸው ውዝግቦች ሲከሰቱ ኖረዋል። በዚህ አሳብ ዙሪያ በአጠቃላይ ሦስት ዋና ዋና ነጥቦች ነበሩ የተነሡት። የሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፥ እንጀራውና 8ይኑ ወደ ክርስቶስ ሥጋነትና ደምነት እንደሚለወጡ ታስተምራለች። ይህ ትምህርቷ “ትራንሰብስታንሺዬሽን/transubstantiation” በመባል ይታወቃል። በአስተምህሮው መሠረት እንግዲህ ምንም እንኳ የስሜት ሕዋሳቶቹ ተራ እንጀራና ወይን እንደሚወስድ ቢነግሩትም፥ ቅዱስ ቁርባኑን የሚወስደው ሰው በቀጥታ የክርስቶስን ሥጋና ደም እንደሚቋደስ ይታመናል። ሁለተኛው የሉተራን ቤተ ክርስቲያን እመለካከት ነው። ይህ ትምህርቷ ካንሰብስታንዬሽን/consubstantiation” በመባል ይታወቃል። በዚህ አመለካከት መሠረት እንጀራው በእንጀራነቱ፥ ወይኑም ሰወይንነቱ፥ የሚቆይ ሲሆንም፡የክርስቶስ ሕላዊ እንጀራውም ሆነ ወይኑ ውስጥ ስለሚገኝ፥ ቅዱስ ቁርባንን የሚወስድ ሰው የክርስቶስ አካል ተካፋይ ይሆናል። 

ሦስተኛው አመለካከት ዝዊንግሊ የተባለው የሥነ-መለኮት ምሁር ያቀረበው ሲሆን፥ እንጀራውና ወይኑ መለኮታዊ ለውጥ ሳይካሄድባቸው ድርጊቱ ለመታሰቢያነት ነው የሚያገለግለው ይላል። ጆን ካልቪን የተባለ ሌላ ሰው ደግሞ፥ ይህን አመለካከት በመጠኑ ለወጥ በማድረግ፥ በቅዱስ ቁርባኑ ሥርዓት ጊዜ ክርስቶስ በመንፈስ በእንጀራውና በወይኑ ውስጥ ይገኛል በማለት አስተምሯል። 

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ቅዱዕ ቁርባን የሚያስተምረው ዝዊንግሊ ያለውን የመታሰቢያነት አሳብ በሚደግፍ መልክ ይመስላል። እንጀራውና ወይኑ የክርስቶስን መገኘት የሚያመለክቱ ወይም የሚወክሉ ሳይሆን፥ የርሱን አለመኖር የሚያሳዩ ይመስላል። ለዚህ ነው የጌታ እራት እርሱ “እስኪመጣ ድረስ” መካሄድ የሚኖርበት። 

ተገቢው የቅዱስ ቁርባን አከባበር 1ኛ ቆሮንቶስ 11፡27-29 ውስጥ በጥንቃቄ የቀረበውን የሐዋርያው ጳውሎስን ትምህርት ያገናዘበ ሊሆን ይገባል። ቅዱስ ቁርባን በሚወሰድበት ጊዜ እግዚአብሔርን የሚያከብር ፍርሃትና መንቀጥቀጥ ደግሞም ራስን መመርመር አስፈላጊ ነው። የጌታን እራት ይወስድ ዘንድ የማይገባው ወይም በግድየለሽነት የጌታን እራት የሚወስድ ሰው በራሱ ላይ ፍርድ ያመጣል። ሐዋርያው ጳውሎስ፥ “ሰው ግን ራሱን ይፈትን፥ እንዲሁም ከእንጀራው ይብላ ከጽዋውም ይጠጣ” (1ኛ ቆሮ. 11፡28) ብሏል። 

ቅዱስ ቁርባን፥ በብዙ ክርስቲያኖች ዘንድ የክርስቶስን ሞት የሚያስቡበት የተቀደሰ ጊዜ እና ለእያንዳንዱ አማኝ ልዩ የሆነ ትርጉም የሚሰጥ ተደርጎ ይወሰዳል። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳስተማረው፥ ቅዱስ ቁርባን ልባችንን የምንፈትንበት፥ ኃጢአታችንን የምንናዘዝበትና የምንታደስበት ጊዜ ሊሆን ይገባል። እያንዳንዱ ክርስቲያን በክርስቶስ ሞት አማካይነት ያገኛቸውን ድንቅ በረከቶች የሚያስብበትም ጊዜ ነው። 

ቅዱስ ቁርባን ወደ ኋላ መለስ ብሎ ታሪካዊውን የክርስቶስ የመጀመሪያ ምጽአትና የመስቀል ላይ ሞትን እንደሚያመለክት ሁሉ፥ የቅዱስ ቁርባን ሥርዓት የሚያበቃበትን የክርስቶስ ዳግም ምጽአትም ይጠቁማል። ቅዱስ ቁርባን የሚወሰድበትን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጥ ባይቀመጥም፥ የቀድሞዎቹ ክርስቲያኖች በተደጋጋሚ ሲያከናውኑት የቆዩ ይመስላል። ይህም በሳምንቱ የመጀመሪያ ዕለት የክርስቶስን ትንሣኤ ለማክበር ሲሰባሰቡ የቅዱስ ቁርባኑን ሥርዓትም ያካሂዱ የነበረ ይመስላል። ያም ሆነ ይህ፥ የቅዱስ ቁርባን ሥርዓት መደበኛ ሆኖ ሊቀጥልና፥ ዳግም እስኪመጣ ድረስ ለመታሰቢያው እንድናደርገው ክርስቶስ እንዳዘዘን፥ ሰአግባቡና አክብሮት ባልተለየው ታዛዥነት ሲካሄድ ይገባል።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

40
ትምህርት 40 ከ52

ቤተ ክርስቲያን፡- የክርስቶስ አካልና ሙሽራ፥ የሚጠብቃት ሽልማቷ

ሀ. ሰባቱ የክርስቶስና የቤተ ክርስቲያኑ ተምሳሌቶች 

በክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን መካከል ያለውን ግንኙነት ለመግለጥ፥ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰባት ተምሳሌቶች ተጠቅሰዋል። 

1. መዝሙር 23 ውስጥ የተመለከተው የእረኛና የበግ ተምሳሌት ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ውስጥ ክርስቶስ እረኛ፥ በርሱ የሚያምኑ ደግም በጎች ህንኩ ስተለኩሰት ክፍል ተጠቅሷል። ከዚህ ምንባብ እንደምንመለከተው፡- (ሀ ክርስቶስ የመጣው በበሩ፥ ማለትም በተወሰነው በዳዊት የዘር ሐረግ አማካይነት ነበር፥ (ለ) እርሱ በጎች የሚከተሉት እውነተኛ እረኛ ነው፥ (ሐ) ክርስቶስ የበጎች በር፥ ማለትም ወደ ድነትም ሆነ ወደ ዋስትና የሚገባበት በር ነው (ዮሐ. 10፡28-29)፣ (መ) ምግብና ሕይወት ለበጎቹ በእረኛው አማካይነት ይቀርባል፥ (ሠ) ከእውነተኛው እረኛ ጋር ሲነጻጻሩ፥ ሌሎቹ እረኞች ለበጎች ሕይወታቸውን የማይሰጡ ቅጥረኞች ናቸው፥ (ረ) በእረኛውና በበጎቹ መካከል ኅብረት አለ። አባት ልጁን እንደሚያውቀውና ልጅም አባቱን እንደሚያውቀው፥ ሰጎቹ እረኛቸውን ያውቁታል፥ (ሰ) ምንም እንኳ በብሉይ ኪዳን ዘመን እስራኤል ሌላ መንጋ የነበረች ብትሆን፥ በአሁኑ ዘመን ያለው መንጋና እረኛ ግን አንድ ብቻ ነው። ይህ ነው እይሁዳውያንም ሆኑ አሕዛብ ድነትን የሚያገኙበት አንድ መንገድ (ዮሐ. 10፡16)፥ (ሸ) ክርስቶስ በእረኛነቱ ነፍሱን ሰጎች አሳልፎ መስጠት ብቻ ሳይሆን፥ ይማልድላቸውና መንፈሳዊ ሕይወት ብሎም የሚያስፈልጋቸውን ምግብ ይሰጣቸው ዘንድ ዘላለም በሕይወት ይኖራል (ዕብ. 1፡25)። መዝሙር 23፡1 ውስጥ፥ “እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም” ይለዋል። 

2. ክርስቶስ እውነተኛው የወይን ግንድ ሲሆን፥ እማኞች ደግም ቅርንጫፎች ናቸው። ምንም እንኳ ብሉይ ኪዳን ውስጥ እስራኤል በወይን ምሳሌነት ከእግዚአብሔር ጋር የተዛመደች ብትሆን፥ ዮሐንስ ምዕራፍ 15 ውስጥ እንደተገለጠው፥ ክርስቶስ እውነተኛው የወይን ግንድ፥ አማኞች ደግሞ የወይኑ ቅርንጫፎች ናቸው። ምሳሌው ከክርስቶስ ጋር የሚደረገውን ኅብረትና አንድነት ያመለክታል። ከክርስቶስ ጋር በዚህ የማይቋረጥ ግንኙነት እንዲኖሩ ተመከረዋል (15፡10)። በርሱ የመኖር ውጤቶች ደግሞ መንጻት ወይም መገረዝ (ቁ.2)፥ ፍሬያማ ጻሎት (ቁ.7)፥ ዘላቂ ደስታ (ቁ, 11) እና ዘላለማዊ እውነት ናቸው (ቁ, 16)። የወይኑ ግንድና የቅርንጫፎቹ ማዕከላዊ እውነት፥ አንድ እማኝ እውነተኛ የወይን ግንድ ከሆነው ክርስቶስ ጋር ሕያው ግንኙነት ካልኖረው በክርስትና ሕይወት ደስ የማይሰኝ ወይም በአገልግሎቱ ፍሬያማ የማይሆን መሆኑ ነው። 

3. ክርስቶስ የማዕዘን ድንጋይ ሲሆን፥ ቤተ ክርስቲያን በሕንጻው ያሉ ድንጋዮችን ይዛለች። እስራኤል ቤተ መቅደስ ውስጥ ታመልክ ከነበረበት የብሉይ ኪዳን ዘመን ጋር ሲነጻጸር (ዘፀ. 25፡8)፥ ቤተ ክርስቲያን ራሷ ቤት መቅደስ ነች (ኤፌ. 2፡21)። በዚህ ምሳሌ ክርስቶስ የማዕዘኑ ራስ ድንጋይ ሲሆን፥ እማኞች ደግሞ የሕንጻው ድንጋዮች ሆነው ተጎልጠዋል (ኤፌ. 2፡19-22)። የአሁኑ ዘመን የእግዚአብሔር ዓሳማ፥ ቤተ ክርስቲያንን ማነጽ ነው (ማቴ. 16፡18)። ቤተ ክርስቲያንን እንደ ሕንጻ በመገንባቱ ሂደት ውስት፥ እያንዳንዱ ድንጋይ የመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋይ በመሆኑ ሕያው ድንጋይ ነው (1ኛ ጴጥ. 2፡5)። ክርስቶስ የማዕዘኑ ራስና መሠረት ሲሆን (1ኛ ቆሮ. 3፡11፤ ኤፌ. 2፡20-22፤ 1ኛ ጴጥ. 2፡6)፥ ሕንጻው በጠቅላላው “ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ” ይሠራል (ኤፌ. 2፡22)። በሕንጻው ምሳሌ መሠረት፥ እያንዳንዱ አማኝ የማዕዙ ራስና መሠረት በሆነው ክርስቶስ ላይ መደገፉ ግልጥ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ፥ የሕንጻው ድንጋዮች እማኞች ሲሆኑ፥ በነርሱ መደጋገፍና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የእግዚአብሔር መቅደስ የሆነው ሕንጻ የሚሠራ መሆኑ ተገልጧል። 

4. በአዲስ ኪዳን ክርስቶስ ሊቀ ካህን፥ አማኞች ደግም ኋማኝካህናት” ሆነው ተገልጠዋል። ቀደም ሲል በዚህ መጽሐፍ ጥናታችን ውስጥ እንደተገለጠው፥ እማኝ ካህን” አራት መሥዋዕቶችን ያቀርባል፤ (ሀ) ራሱን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለእግዚአብሔር በማቅረብ፥ የመሥዋዕትነትን አገልግሎት ይሰጣል (ሮሜ 12፡1-2)። (ለ) ለእግዚአብሔር ምስጋናና ውዳሴ በማቅረብ፥ የአምልኮን አገልግሎት ይሰጣል (ዕብ. 13፡15)። ይህም የምልጃንና ለራሱ ችግሮች መጻለያን ያካትታል (ሮሜ 8፡26-27፤ ቆላ . 4፡12፤ 1ኛ ጢሞ. 2፡1፤ ዕብ. 10፡19-22)። ክርስቶስ ጎልጎታ ላይ የፈሰሰ ደሙን ይዞ እንደ ሊቀ ካህናችን ወደ ሰማይ ገብቷል (ዕብ. 4፡14-16፤ 9፡24፤ 10፡19-22)። አሁን ስለ እኛ በመማለድ ላይ ነው (ሮሜ 8፡34፤ ዕብ. 7፡25)። 

አማኞች እንደ ንጉሣዊ የክህነት አባላት፥ (ሐ) የሰናይ ምግባራትና (መ) የቁሳዊ ነገሮች መሥዋዕት ከማቅረብ ባሻገር፥ ሰውነታቸውን እንደ ሕያውና ቅዱስ መሥዋዕት አድርገው ማቅረብ ያስባቸው መሆኑን መገንዘቡ መልካም ነው (ዕብ. 13፡16)። 

5. ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን ራስ ቤተ ክርስቲያን ደግም እንደ አካል ተደርገው የተገለጡት ምሳሌ በአሁኑ ዘመን የሚሠራውን የእግዚአብሔርን ዓላማ ያሳያል። ይህ ምሳሌ ሰፋ ብሎ ለብቻው በዚሁ ምዕራፍ ወደኋላ ይቀርባል። 

6. ክርስቶስ እንደ መጨረሻው አዳም፥ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ አዲስ ፍጥረት ሆና በተለጠችበት ምሳሌ፥ ክርስቶስ ከሞት በመነሣቱ የአሮጌው ሥርዓት ራስ የነበረውን አዳምን ይተካዋል፤ አዲስ ፍጥረት ለሆኑትም ራስ ይሆናል። ምሳሌው በክርስቶስ ትንሣኤ እርግጠኛነትና በትንሣኤው ባዋቀረው አዲስ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ ነው። በአዳም ውስጥ ከመሆን ጋር ሲነጻጸር፥ አማኝ በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካይነት ክርስቶስ ውስጥ መሆኑ ተገልጧል። ባገኘው አዲስ ስፍራ አማካይነትም ክርስቶስ በርሱ ምትክ ጽድቅና አዲስ ሕይወት ለመስጠት ባከናወነው ነገር ሁሉ ተካፋይ ይሆናል። ክርስቶስ የአዲሱ ፍጥረት ራስ ስለሆነ፥ አዲስ የመታሰቢያ ዕለት ማለት በአሮጌው ሥርዓት ይከበር የነበረው የሰንበት ዕለት ተነጻጻሪ የሆነ መታሰቢያ የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን አስፈላጊ ሆኗል። 

7. ክርስቶስ እንደ ሙሽራ፥ ቤተ ክርስቲያን ደግም እንደ ሙሽሪት መገለጣቸው ለአሁኑም ሆን ወደፊት በክርስቶስና በቤተ ክርስቲያኑ መካከል ለሚኖረው ግንኙነት ትንቢታዊ ምሳሌ ነው። ብሉይ ኪዳን ውስጥ ታማኝነትን እንዳጎደሰች ሚስት ከተገለጠችው እስራኤል በተነጻጻሪነት፥ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ ኪዳን የሙሽራዋን መምጣት እንደምትጠባበቅ ሙሽሪት ተገልጣለች። ይህ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ በስፋት የምንመለከተው እሳብ ይሆናል። ቤተ ክርስቲያን እንደ ክርስቶስ አካል የተገለጠችበት ምሳሌ የአሁኑን ዘመን የእግዚአብሔር ዓላማ የሚገልጥ ሲሆን፥ የክርስቶስ ሙሽራ የመሆኗ አሳብ ደግሞ ወደፊት ቤተ ክርስቲያን ከክርስቶስ ጋር የሚኖራትን ግንኙነት የሚያመለክት ነው። 

ለ. ቤተ ክርስቲያን እንደ ክርስቶስ አካል 

ቀደም ሲል የተመለከትነው የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት፥ የአዲስ ኪዳንን የቤተ ክርስቲያን መገለጥ በማጣመር የክርስቶስን አካል መሥርቷል። ይህም 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡13 ውስጥ እንደተገለጠው፥ በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካይነት የተከናወነ ነው፤ “አይሁድ ብንሆን፥ የግሪክ ሰዎችም ብንሆን፥ ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን፥ እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናል። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።” በዚህ ገለጣ ሦስት ዓበይት እውነቶች ቀርበዋል፤ (1) ቤተ ክርስቲያን ራሷን የምታንጽ አካል ናት፥ (2) የአካሉ ክፍሎች ልዩ ልዩ ስጦታዎች የተሰጧቸውና፥ ለልዩ አገልግሎት የተሾሙ ናቸው፤ (3) አካሉ ሕያው አንድነት ነው። 

1. ቤተ ክርስቲያን ራሷን የምታንጽ አካል እንደመሆኗ መጠን፥ ኤፌሶን 4፡11-16 ውስጥ እንደተገለጠው መንፈሳዊ ስጦታዎች ያሏቸውን ግለሰቦች ታካትታለች። በዚሁ መሠረት አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሉች ነቢያት፥ ወንጌላውያን፥ ወይም መጋቢያንና አስተማሪዎች ናቸው። ማዕከላዊው እውነት አማኞች በተለያዩ ችሎታዎች እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ መሰረታታቸው ብቻ ሳይሆን፥ እግዚአብሔር የሰጣቸውን እንድ ሁነኛ ተግባር ያከናውኑ ዘንድ ብቃት የተሰጣቸው መሆኑ ነው። አንድ አማኝ ተገቢውን አገልግሎት የሚፈጽመው፥ በክርስቶስ አካል ውስጥ የተወሰነለትን ተግባር ሲወጣና የክርስቶስን እካል ፍጹም በማድረጉ ክንውን ተካፋይ ሆኖ ሲገኝ ነው (ኤፌ. 4፡13)። 

2. የክርስቶስ አካላት እንደየስጦታቸው የተወሰነ እገልግሎት እላቸው። በሰው ሰውነት ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የእካል ክፍሎች ልዩ ልዩ ተግባራትን እንደሚያከናውኑ ሁሉ፥ የክርስቶስ አካል ክፍሎችም እንዲሁ ናቸው። እያንዳንዱ አማኝ እግዚአብሔር የትኛውን ስጦታ እንደሰጠው ለማወቅ ራሱን በጥንቃቄ ሊመረምርና ስጦታውን ለእግዚአብሔር ከብር ሊያውለው ይፃባል። ዋና ዋናዎቹ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ሮሜ 12፡3-8 እና 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡28 ውስጥ ተገልጠዋል። አማኞች ሁሉ መንፈሳዊ ስጦታዎች ያሏቸው ሲሆን፥ ከአንድ በላይ ስጦታዎች ያሏቸውም አሉ። አንዳንዴ የሚዛመዱበት ሁኔታ ቢኖርም፥ መንፈሳዊ ስጦታዎች ከተፈጥሮ ችሉታ ጋር መደናገር አይኖርባቸውም። ለምሳሌ አንድ ሰው በተፈጥሮው የማስተማር ብቃት ሊኖረው ይችላል። መንፈሳዊ ነገሮችን የማስተማር ስጦታ የሚሰጠው ግን ከእግዚአብሔር ብቻ ነው። 

መንፈሳዊ ስጦታዎችን ፈልጎ ማግኘት አይቻልም። ዳሩ ግን “መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻ እያካፈለ ያደርጋል” (1ኛ ቆሮ. 12፡11)። በሐዋርያት በተመሠረተች ቤተ ክርስቲያን ጀምረው እስካሁን ድረስ የቀጠሉ አንዳንድ ስጦታዎች አሉ። ሌሎች የምልክት ስጦታዎች ግን ከመጀመሪያው የክርስቲያኖች ትውልድ በኋላ ያበቁ ይመስላል። ያም ሆነ ይህ፥ እያንዳንዱ ስጦታ ለእግዚአብሔር ቃል ደንብ ሊገዛ ይገባል። ስጦታ እያንዳንዱ አማኝ የሚጠቀምበትና ኃላፊነት ያለበት ነገር እንጂ፡የትዕቢት መሠረት የሚሆን አገልግሉት አይደለም። 

እጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሰፋፊ አደረጃጀቶችን ቢያዋቅሩም፥ አካል እንደመሆኗ ሥራዋ የሚከናወነው በእያንዳንዱ አባል ችሎታ ላይ በመመሥረት እራሷ በሆነው ክርስቶስ አመራር ነው። አንድ አማኝ በተለይ ስጦታው ባልሆነ ተግባር ላይ እንዲሠማራ መጠየቁ ያለ ቢሆንም፥ ከፍተኛ ተግባሩ ግን በክርስቶስ አካል ውስጥ የተሰጠውን ሥራ ማከናወን ነው። ሕያው መሥዋዕት አድርጎ ራሱን ለጌታ ከሰጠ፥ የእግዚአብሔርን ፍጹም ፈቃድ ሊያውቅ ይችላል (ሮሜ 12 ፡1-2)። 

3. ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ላንድ የጎችና የተመረጠች ሕያው አካል ናት። አይሁዶችን፥ እንዲሁም አሕዛብንና ከተለያየ ዘርና ባሕል የተሰበሰቡ ሰዎችን ያካተተ የቤተ ክርስቲያን አንድነት ኤፌሶን 1፡23፤ 2፡15-16፤ 3፡6፤ 4፡12-16፤ 5፡30 ውስጥ ተመልክቷል። ቤተ ክርስቲያን እንደ ክርስቶስ አካልነቷ ግሩም አንድነት ስላላት፥ በአይሁዶችና በአሕዛብ መካከል የሚኖረው ልዩነት ከግንዛቤ አይገባም፤ አይሁዶችም ሆኑ አሕዛብ እኩል ዕድልና ጸጋ ያገኛሉ። የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ከእስራኤልና ከአሕዛብ ጋር ከነለረው ግንኙነት ጋር ስትነጻጸር የተለየች ናት። ይህ ለአሁኑ ዘመን ብቻ የተወሰነ ልዩ ሁኔታ ነው። ኤፌሶን ምዕራፍ 3 እንደሚያስተምረን፥ የአካሉ ክፍሎች ከብሉይ ኪዳን ነቢያት ተሰውሮ የኖረውንና ለአዲስ ኪዳን አማኞች የተገለጠውን ድንቅ እውነት ይካፈላሉ። በዚህ መሠረት አሕዛብ በወንጌሉ አማካይነት በክርስቶስ በማመን እንደ አይሁዶች ሁሉ የአንድ አካል ክፍሎች ይሆናሉ (ኤፌ. 3፡6)። ኤፌሶን 4፡4-3 ውስጥ አጽንኦት የተሰጠው የአካል እንድነት ዘላለማዊነት አለው። በአሁኑ ዘመን ለክርስቲያናዊ ኅብረትና አገልግሎት፥ በሚመጣውም ዘመን ለዘላለማዊ ኅብረት መሠረቱ ይሄው አንድነት ነው። 

ሐ. ክርስቶስ እንደ ሙሽራ ቤተ ክርስቲያን እንደ ሙሽሪት 

ከሰባቱ የክርስቶስና የቤተ ክርስቲያን ተምሳሌቶች ትንቢታዊ ጠቀሜታ ያለው፥ የሙሽራውና የሙሽራይቱ ብቻ ነው። ታማኝነቷን ካጎደለችው የያህዌ ሚስት እስራኤል በተነጻጻሪነት ቤተ ክርስቲያን የሙሽራዋን መምጣት እንደምትጠባበቅ ድንግል ሙሽራ ሆና አዲስ ኪዳን ውስጥ ተጠቅሳለች (2ኛ ቆሮ. 11፡2)። የክርስቶስ ሙሽራነት ዮሐንስ 3፡29 ውስጥ በመጥምቁ ዮሐንስ ተገልጦአል። 

የዚህ ጉዳይ ዋና መገለጥ የተሰጠው ግን በክርስቶስ ያመኑ ባሎችና ሚስቶችን ተገቢ ግንኙነት በሚብራራበት ኤፌሶን 5፡25-33 ውስጥ ነው። በዚህ ስፍራ የክርስቶስ ሦስት ተግባራት ተገልጠዋል። ( ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን በመውደድ ነፍሱን ላርስዋ አሳልፎ ሰጥቷል (ቁ.25)። (ለ) በአሁኑ ጊዜ ክርስቶስ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ” በመቀደስ ተግባሩ ላይ ነው (ቁ.26)። (ሐ) “እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ” (ቁ.27)። ክርስቶስ በመስቀል ላይ በመሞት ሙሽራ ለሙሽሪት የሚያቀርበውን የጥሎሽ ተምሳሌት ፈጽሟል። በእሁኑ ዘመን፥ የእግዚአብሔርን ቃል ከምእመናን ሕይወት ጋር በማዋሀድና በመቀደስ፥ ሙሽሪትን ለወደፊት ግንኙነቱ እያዘጋጃት ነው። ቤተ ክርስቲያን በምትነጠቅበት የመጨረሻ ዘመን፥ ሙሽራው ወደ ምድር መጥቶ ሙሽራይቱን ወደ ሰማይ ይወስዳታል፤ የራሱን ከብር እንድታንጸባርቅ ቤተ ክርስቲያንን ፍጹም፥ እድፍ ወይም ንድፍ የሌለባት፥ ለቅዱስ ሙሽራ የምትስማማ ቅድስት ሙሽሪት አድርጎ ያቀርባታል። ከዚያ የሚከተለው ቅዱሳን ሁሉ የሚያከብሩት የከርስቶስና የቤተ ክርስቲያን የጋብቻ በዓል ነው። በዓሉ የሚፈጸመው ምናልባት በሺህ ዓመቱ መንግሥት መንፈሳዊ ኅብረት ይሆናል። ይህ የጋብቻ በዓል ክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ወደ ምድር በሚመለስበት ዋዜማ እንደሚሆን ራእይ 19፡7-8 ውስጥ ተጎልጿል። 

በዚህ ተምሳሌት አማካይነት የተገለጠውና ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያኑ ያለው ፍቅር የእግዚአብሔርን ከፍተኛ ፍቅር ያመለክታል። ከዚህ ተምሳሌት የመለኮታዊ ፍቅርን አምስት ሁኔታዎች ለመጥቀስ ይቻላል። 

1. የጸግዚአብሔር ፍቅር ዘላለማዊነት ቀሚመነጨው ናግዚአብሔር ፍቅር ነው ከሚለው እውነተኛ ትምህርት ነው (1ኛ ዮሐ. 4፡8)። እግዚአብሔር ለማፍቀር የቻለው በራሱ ጥረት ወይም ልምምድ አይደለም። ፍቅር የሚጎድለውም አይደለም። ይልቁንም ፍቅር የሕላዌው፥ የኑባሬው ወይም የርሱነቱ ዋነኛ ነገር ነው። ፍቅሩ መኖር የጀመረው እግዚአብሔር መኖር ሲጀምር ነው። ፍቅሩ የሚያበቃ ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ማንነት ዋነኛ አካል ያበቃ ነበር። የእርሱ ማንነት የሚታወቀው ከታላቅ ፍቅሩ የተነሣ ነው። 

የእግዚአብሔር ፍቅር አይለወጥም። እስራኤላውያንን፥ በዘላለማዊ ፍቅር ወድጃችኋለሁ” ያላቸው ሲሆን (ኤር. 31 ፡3)፥ ስለ ክርስቶስም፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው” ተብሎ ተጽፏል (ዮሐ. 13፡1፤ 15፡9)። እግዚአብሔር ለአንድ ሰው ያለው ፍቅር ከፍ ዝቅ የሚል ወይም የሚቋረጥ አይደለም። 

2. የእግዚአብሔር ፉቅር ለማያቋርጥ ተግባሩ ማነሳሻ ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በውድ ልጁ መሥዋዕትነት አማካይነት የተገለጠ ቢሆንም (ሮሜ 5፡8፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡16)። ይህ መሥዋዕት የሚገለጠው እግዚአብሔር ለሰዎች ያለውን ዘላለማዊ እሳብ ነው። ቁሳዊው ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የእግዚአብሔርን ልብ ለማየት ችለን ቢሆን ኖሮ፥ ለዓለም ኃጢአት ለታረደው በጉ ያኔ የተደረጉ ልግስናዎችን ሁሉ ልንመለከት እንችል ነበር (ራእይ 3:6)። አሁንም የእግዚአብሔርን ልብ ለማየት ብንችል፥ ከድነት ርቀው ለጠፉት በልጁ ሞት አማካይነት የገለጠውን ርኅራኄ እንመለከታለን። የክርስቶስ ጊዚያዊ ሞት የመለኮታዊ ፍቅር መግለጫ ትርታ ሳይሆን፥ እግዚአብሔር ከድነት ርቆ ለጠፋው የሰው ልጅ አላለማዊና የማይለወጥ ፍቅሩን ያወጀበት ድርጊት ነበር። 

3. የእግዚአብሔር ፍቅር ግልዎና ንጹሕ ነው። ይህን የእግዚአብሔር ፍቅር ለመግለጥ የሚያስችሉ ሰብአዊ ቃላት አልተገኙም። በመለኮታዊ ፍቅር ውስጥ ከቶውንም ራስ ወዳድነት ስለሌለ፥ እግዚአብሔር በፍጹም ጥቅምን ለራሱ አይሻም። ምንም አይቀበልም፥ ሁሉን ይሰጣል። ሐዋርያው ጴጥሮስ አማኞች እርስ በርሳቸው ከልባቸው አጥብቀው እንዲዋደዱ መክሯቸዋል (1ኛ ጴጥ. 1፡22)። ይሁንና፥ ከበረከቶቹ ባሻገር እግዚአብሔርን ስለማንነቱ ብቻ የሚወዱት ስንቶች ናቸው? የእግዚአብሔር ፍቅር ከዚህ ምንኛ ልዩ ነው? እግዚአብሔር ገንዘባችንን፥ አገልግሎታችንን ወይም ተጽዕኖአችንን እንደሚፈልግ አድርገን በእርግጠኝነት እናስባለን። እግዚአብሔር እኛን እንጂ ከእኛ የሚፈልገው ነገር የለም። ፍጹም ፍቅሩም እኛን ካላገኘ አይረካም። “የተወደዱ” የሚለው ቃል አማኞችን አስመልክቶ ሲነገር ከፍተኛ የገላጭነት ኃይል አለው። ምክንያቱም አማኞች ከእግዚአብሔር ጋር ባላቸው ግንኙነት ዋናው ተግባራቸው መወደድ ነው። 

የእግዚአብሔር ፍቅር ለግልቀቱ ወስን የለውም። በእጽናፈ ዓለማችን እጅግ ውድ የሆነው ነገር የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ ደም ነው። እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለምን በጣም ወደደ። ሰዎች “ኃጢአተኞች” እና የእግዚአብሔር “ጠላቶች” ሳሉ ልጁ ለእነርሱ መሠዋቱ ከገደብ ያለፈ ቢመስልም፥ ከዚህም የሚበልጥ” ፍቅር እንዳለ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። ይህም በክርስቶስ ሞት ዕርቅን ሳገኙና ለጻደቁ ሁሉ እግዚአብሔር የሚያሳየው ፍቅር ነው (ሮሜ 5፡8-10)። በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካለ የእግዚአብሔር ፍቅር የሚለየን ነገር የለም (ሮሜ 8፡29)። 

5. የግዚአብሔር ፍቅር የማያከትም በጎ ነገር አለው። እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ሳይቀር እንደሚወድ ከሚያሳየው ድንቅ እውነት ሌላ ይህች ዓለም ምንም ተስፋ የላትም። የእግዚአብሔር ፍቅር የስሜት ጉዳይ ሳይሆን በገቢር የሚገለጥ ነው። እግዚአብሔር ካታላቅ ፍቅሩ የተነሣ ለዘላለም ይጠፉ ዘንድ የሚገባቸው ኃጢአተኞችን ለመታደግ ድንቅ እርምጃን ወሰደ። ከፍጹምነቱ የተነሣ ጻድቅ ሰሆነ ፍርዱ የኃጢአተኞችን ኩነኔ ችላ ብሎ ሊያልፍ ባይችልም፥ ፍርዱ ፍጹም እንዲሆን የኃጢአተኞችን መርገም ሰራሱ መሸከም ነበረበት። (“ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት … የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም” (ዮሐ. 15፡13)። ይህን ያደረጎው የራሱን ቅድስና ሳይጎዳ ኃጢአተኞችን ለማዳን ይችል ዘንድ ነው (ሮሜ 3:26)። እግዚአብሔር በክርስቶስ የምትክነት ሞት አማካይነት ኃጢአተኞችን የሚያድንበት ነጻነት ስላሰው አሁን ያለ ምንም ውሱንነት ሰሰው ልጅ ሕይወት ይሠራል። ይህን የሚያደርገው፥ ፍጹም የሆነ ፍትህን በማሟላት ኃጢአተኞችን ታላቅ ወደሆነና ክርስቶስን ወደ መምሰል ደረጃ እስኪያደርሳቸው ነው። 

የሚያድን ጸጋ ከፍቅርም የሚልቅ ሲሆን፥ ነጻና ብርቱ የሆነ እግዚአብሔር በኃጢአተኛው ላይ የነበረውን የጽድቅ ብያኔ እንዲያልፍ የሚያደርግ መለኮታዊ ፍቅር ነው። “ጸጋው በእምነት አድኖአችኋል” (ኤፌ. 2፡8ን ከ2፡4 እና ከቲቶ 3፡4-5 ጋር ያነጻጽሩ)። 

እግዚአብሔር ለኃጢአት ከፍተኛ ጥላቻ ያለው አምላክ ነው። ይህም እንደ ፍቅሩ ሁሉ ኃጢአተኛውን ከወደቀበት አዘቅት እንዲያወጣ ይገፋፋዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ፥ ይህ ኃጢአትን የመብላት ባሕርዩ ከፍቅሩ ጋር ተቀላቅሎ እግዚአብሔርን ልጁን የሚቀጣ አባት ያደርገዋል። “እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ እቀጣቸውማለሁ” (ራእይ 3፡19)። “ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና” (ዕብ. 12፡6)። 

ከክርስቶስ ጋር ካለው ሕያው ጥምረት የተነሣ (1ኛ ቆሮ. 6፡17)፥ ክርስቶስ የተወደደውን ያህል አማኝ በአብ ተወዷል (ዮሐ. 17፡23)። ፍጹም ፍቅር በቅጣት ወይም በመከራ ጊዜ አይቀንስም። 

ከነዚህ ቀጥተኛ የእግዚአብሔር ፍቅር መገለጫዎች በተጨማሪ ብዙ ተዘዋዋሪ መገለጫዎችን ለመጥቀስ ይቻላል። አዲስ ኪዳን ውስጥ ስለ ሰብአዊ ፍቅር የተጻፈው በጣም ጥቂት ነው። መጽሐፉ የሚያተኩረው ከዚህ ይልቅ መንፈስ ቅዱስ የተሞላ አማኝ ብቻ ሰሚቀበለው መለኮታዊ የፍቅር ተካፋይነት ላይ ነው። ሮሜ 5፡5 የሚያስተላልፍልኝ መልእክት፥ በተሰጠን በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን የፈሰሰ መሆኑን ነው። መላኮታዊ ፍቅሩ የመንፈስ ፍሬ” ሰለሆነ (ገላ. 5፡22)፥ ምንጩ እርሱ ነው። በመሆኑም፥ መለኮታዊ ፍቅር በአማኙ ልብ ውስጥ በተለያየ መንገድ ይገለጣል። የአንደኛ ዮሐንስ መልእክት የሚያመለክተው ከእግዚአብሔር ከተወለድን፥ እግዚአብሔር እንደሚወድ የምንወድ መሆናችንን ነው። አንደኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 13 ደግሞ ይህ ፍቅር ከሰብአዊነት የላቀ መሆኑን ይገልጣል። የማይገደበውን የእግዚአብሔር ፍቅር ያህል በዚህ ሕይወት የሚያስደስት ምንም ነገር የለም። 

እግዚአብሔርን ስለ ማፍቀር ጉዳይ ሳይሆን፥ ከእግዚአብሔር ስለሆነ ፍቅር ነው የምንመለከተው። ይህን ፍቅር አስመልክቶ እኝዳንድ ነገሮችን መመልከቱ ተገቢ ያሆናል። 

የእግዚአብሔር ፍቅር ክርስቶስ ካቀረበው ጸሎት የተነሣ የምንለማመደው ነው (ዮሐ. 17፡26)። እግዚአብሔር የጠፋውን ዓለም ይወዳል (ዮሐ. 3፡16፤ ኤፌ. 2፡4)። ክፉ የሆነውን የዓለም አሠራር ግን ይጠሳል (1ኛ ዮሐ. 2፡15-17)። እግዚአብሔር ያዳናቸውን ሰዎች ይወዳል (ዮሐ. 13፡34-35፤ 15፡12-14፤ ሮሜ 5፡8፤ ኤፌ. 5፡25፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡16፤ 4 ፣ 12)። እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ይወዳል (ኤር. 31፡3)። ክርሱ የኮበለሉትንም ይወዳል (ሉቃስ 15፡4፥ 20)። ፍቅሩ ዘላለማዊ ነው (ዮሐ. 13፡1)። የእግዚአብሔር ፍቅር ልጁን እስኪሰጥ ድረስ መሥዋዕትን ጠይቆታል (1ኛ ዮሐ. 3፡16፤ 2ኛ ቆሮ. 8፡9፤ ኤፌ. 5፡2)። ከመለኮት በወጣ ምሥጢራዊ ርኅራኄ ሳቢያ፥ ሐዋርያው ጳውሎስ ለወንድሞቹ ማለትም በሥጋ ዘመዶቹ ለሆኑት፥ ከክርስቶስ ተለይቶ ለመረገም ፈቃደኛ ነበር (ሮሜ 9፡1-3)። 

በጸጋ ዘመን የመጀመሪያው የከርስቶስ ትእዛዝ በመላኮታዊ ፍቅር መመላለስ ነው (ዮሐ. 13፣ 34-35፤ 15፡12-14)። ይህም የእያንዳንዱ ክርስቲያን ከፍተኛ መለያ ሊሆን ይገባል (ገላ. 5፡13፤ ኤፌ. 4፡2፥ 15፤ 5፡2፤ ቆላ. 2፡2፤ 1ኛ ተሰ. 3፡12፤ 4፡9)። ከእግዚአብሔር የተቀበልነው መለኮታዊ ፍቅር በሥጋ ሊዳብርም ሆነ ሊገኝ አይችልም። ይህ ቀላሎቹን ቅድመ ሁኔታዎች አሟልተው በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ ክርስቲያኖች የታወቀ ልምምድ ነው (ገላ. 5፡22)። 

መ. ሙሽራይቱ አጊጣና ተሸልማ 

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱት ብዙ ዓበይት ፍርዶች መካከል ቤተ ክርስቲያን ፍርድ የምትቀበልበትና የምትሸለምበት የክርስቶስ የፍርድ ወንበር አንዱ ነው። ኃጢአትን በተመለከተ ከጸጋ ሥር ያለ የእግዚአብሔር ልጅ ለፍርድ እንደማይቀርብ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል (ዮሐ. 3፡18፤ 5፡24፤ 6፡37፤ ሮሜ 5፡1፤ 8፡1፤ 1ኛ ቆሮ. 11፡32)። ክርስቶስ ለኃጢአት ሁሉ፥ ማለትም ላለፈው፥ ለአሁኑ ወደፊት ለሚሠራ (ቆላ. 2፡13) ፍጹም ተተኪ ሆኖ ስለተሠዋ፥ በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆም ከመሆኑ የተነማ አማኝ ከኩነኔ ነጻ ሆኗል። በክርስቶስ በመሆኑም በርሱ ፍጹምነት የተነሣ ተቀባይነት ሳማግኘት (1ኛ ቆሮ. 1፡30፤ ኤፌ. 1፡6፤ ቆላ. 2፡10፤ ዕብ. 10፡14) እና እንደ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ለመወደድ በቅቷል (ዮሐ. 17፡23)። ሆኖም ዕለታዊ ሕይወቱንና ለእግዚአብሔር የሚያቀርበውን አገልግሎት በተመለከተ፥ አማኝ በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት መልስ ይሰጣል (ሮሜ 14 ፡16፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡10፤ ኤፌ.6፡8)። ይህ ክርስቶስ የርሱ የሆኑትን ለመቀበል በሚመጣበት ጊዜ የሚካሄድ ፍርድ ነው (1ኛ ቆሮ. 4፡5፤ 2ኛ ጢሞ. 4፡8፤ ራእይ 22፡12፤ ማቴ. 16፡27፤ ሉቃስ 14፡14)። 

ያላመኑ ሰዎች የመጨረሻ ፍርድ ለመቀበል በታላቁ ነጭ ዙፋን ፍርድ ፊት በሚቆሙበት ወቅት፥ “እንደየሥራቸው›› ብያኔ ይሰጣቸዋል (ራእይ 20፡11-15)። የዚህ ፍርድ ዓላማ እነዚያ ከነጩ ዙፋን ፊት የቆሙ ሰዎች መዳን አለመዳናቸውን መወሰን አይደለም። ይልቁንም ከድነት ርቀው የጠፉት ሰዎች ለጥፋታቸው ሊቀበሉት የሚገባን የፍርድ መጠን መወሰኝ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ፥ የዳኑትም ሰዎች በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት በሚቀርቡበት ጊዜ እንደየሥራቸው ይፈረድባቸዋል። ይህ ፍርድ መዳን አለመዳናቸውን የሚወስን ሳይሆን፥ እያንዳንዱ አማኝ ላበረከተው አገልግሎት የሚቀበለውን ወይም የሚያጣውን ሽልማት የሚያጸድቅ ነው። በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት የሚቆሙት አማኞች መዳንና በሠላም መጠበቅ ብቻ ሳይሆን፥ ፀደ መንግሥተ ሰማያት የተወሰዱ ናቸው። ይህ የሚሆነው በነርሱ ሰናይ ምግባር ላይ በመመሥረት ሳይሆን፥ በክርስቶስ የአዳኝነት ሥራ በተገኘው መለኮታዊ ጸጋ ነው። ሰጸጋ ሥር እስከሆነ ድረስ የአማኝ ሕይወትም ሆነ አገልግሎት ሁኔታ በምንም ዓይነት ዘላለማዊ ሕይወቱን አያሳውም፤ ሊያሳጣውም አይችልም። ስለሆነም፥ የርሱ የሆንንለትና የምናገለግለው ክርስቶስ በአማኙ ሕይወትና አገልግሎት ላይ መፍረዱ ከድነት የተለየ ነው። 

“በክብሩ ዙፋን ፊት” ለእስራኤልና ለሕዝቦቿ ለተደረገው በጎ ነገር ሽልማት ይሰጣል። ይህ ግን ከግላዊ የድነት ጉዳይ የራቀ ነው (ማቴ. 25፡31ን ከማቴ. 6፡2-6፤ 24:45-46፤ 25፡1-46 ጋር ያነጻጽሩ)። 

የአማኝ ሽልማቶች በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት ምን እንደሚመስሉ ላመግለጥ ሦስት ዓበይት ምሳሌዎች ተጠቅሰዋል። 

1. ሮሜ 14፡10-12 ውስጥ የተጠያቂነት ጉዳይ ተጠቅሷል። በዚህ ስፍራ ከሌሎች አማኞች ፍርድ ጋር በተያያዘ የሚከተለው ምክር ተለግሷል፡- “አንተም በወንድምህ ላይ ስል ምን ትፈርዳለህ? ወይስ አንተ ደግሞ ወንድምህን ስለ ምን ትንቃለህ? ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና። እኔ ሕያው ነኝ፥ ይላል ጌታ፥ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል መላስም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል ተብሎ ተጽፎአልና። 

እንግዲያስ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለእግዚአብሔር መልስ እንሰጣለን”። 

በዚህ ምንባብ የሌላውን ክርስቲያን የሥራ ጥራት ለመገምገም እንዳንጥር ታዘናል። ይህ ግን ኃጢአትን መገሠጽና መፍረድ የለብንም ማለት ሳይሆን፥ አሳቡ የሚያመለክተው የአማኙን ሥራ እሴት ወይም የሕይወቱን ጥራት ነው። ብዙውን ጊዜ ክርስቲያኖች በራሳቸው ግንዛቤ የራሳቸው ሕይወት የተሻለ መስሎ ይታይ ዘንድ ሌሎችን እጥብቀው ይተቻሉ። በሌላ አነጋገር፥ ራሳቸውን ከፍ ለማድረግ ሲሉ ሌላውን ይንቃሉ። 

በዚህ ምንባብ የተገለጠው እውነት፥ እያንዳንዱ አማኝ ለእግዚአብሔር መልስ የሚሰጥ መሆኑ ነው። ምሳሌው መጋቢን ወይም የማስተዳደር አደራ የተጣለበትን ሰው ይመሰክታል። አንድ ክርስቲያን በሕይወቱ ያገኘው ነገር ሁሉ ከእግዚአብሔር በስጦታ የተቀበለው ነው። ይህም ምሁራዊ ችሎታ፥ ተፈጥሮአዊ ስጦታ፥ አካላዊ ጤንነት፥ መንፈሳዊ ጸጋ፡ወይም ሀብት ሊሆን ይችላል። በዚህ ረገድ፥ ብዙ ከተሰጠው ብዙ ይጠበቅበታል። 1ኛ ቆሮንቶስ 6፡19-20 ውስጥ እንደተመለከተው፥ አማኞች “በዋጋ ተገዝታችኋልና የራሳችሁ አይደላችሁም” ተብለዋል። እግዚአብሔር ለሰጠን ነገር ሁሉ መጋቢዎች እንደመሆናችን፥ በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት ለግላችን ስለተሰጠን አደራ መልስ እንሰጣለን እንጂ ለሌሎች በተሰጣቸው ላይ አይደለም የሚፈረድብን። በፍርዱ ወቅት ዋናው ነገር ስኬት ወይም ዝና ሳይሆን፥ እግዚአብሔር ለሰጠን ነገር ታማኞች ሆነን መገኘታችን ነው። 

2. 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡9-15 ውስጥ የእማኙ ሕይወት በክርስቶስ መሠረትነት ላይ እንደተገነባ ሕንጻ ተቆጥሯል። ይህን መልእክት በመረዳቱ ረገድ፥ የሚከተሉትን ነጥቦች ልብ ማለቱ ተገቢ ነው። 

(ሀ) ክፍሉ የሚያካትተው የዳኑትን ሰዎች ብቻ ነው። “እኛ” እና “እናንተ” የሚሉት ተውላጠ ስሞች የዳኑትን ሲያካትቱ ያልዳኑትን ያገላሉ። እንደዚሁም፥ «ማንም›› የሚለው ቃል ደግሞ የሚያመለክተው፥ በዓለቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ሕንጻውን የሚሠሩትን ብቻ ነው። 

(ለ) ሐዋርያው ጳውሎስ የቆሮንቶስ ሰዎች የዳኑበትን ወንጌልና የዳኑት የሚቆሙበትን ዓለት ካገለጠላቸው በኋላ፥ ራሱን መሠረት ከሚጥል ጠቢብ አናጺ ጋር ያነጻጽራል። ጠበቅ አድርጎ በማነጻጸርም እያንዳንዱ እማኝ ከእግዚአብሔር እንፏተሰጠው ጻጋ በመሠረቱ ላይ ላዕላይ መዋቅሩን በመሥራት ላይ መሆኑን ገልጧል። እያንዳንዱ አማኝ በዚያው መሠረት ላይ እንዴት እንደሚገነባ እንዲጠነቀቅ ነው ማስገንዘቢያው። አማኝ በእሳት የሚፈተን የአገልግሎት ወይም የሥራ ሕንጻ የሚገነባ መሆኑ ነው የተመለከተው። እሳቱ ያ አገልጋይ በጌታ ፊት ሲቀርብ የሚያርፉበት የጌታ ዓይኖች ሳይሆኑ አይቀሩም (ራእይ 1፡14)። 

(ሐ) አማኝ መሠረት በሆነው ክርስቶስ ላይ የሚገነባው ሥራ እሳት የሚበላው የእንጨት፥ የሣር ወይም የአገዳ ሊሆን ይችላል። ወይ ደግሞ እሳት የማይደፍረው የወርቅ፥ የብርና ከከበሩ ማዕድናት የተሠራ ሊሆን ይችላል። ወርቅና ብርን በተመለከተ እሳት ያጠራቸዋል እንጂ አይጎዳቸውም። 

(መ) በክርስቶስ ላይ ያነጸው “ሥራ” የሚጸናለት አማኝ ሽልማት ያገኛል። “ሥራው” የሚቃጠልበት ግን ምንም አያገኝም። የሚያጣው ሽልማቱን እንጂ በተፈጸመው የክርስቶስ ሥራ ያገኘውን ድነት አይደለም። ምንም እንኳን ሥራው በእሳት ውስጥ አልፎለት ባይሸለም እሱ ይድናል። 

3. 1ኛቆሮንቶስ 9፡16-27 ውስጥ በተለይም ከቁጥር 24-27 የክርስትናሕይወትንና አገልግሎትን ጥራት ለመግለት የውድድርና የሽልማት ምሳሌ ተሰጥቷል። ሐዋርያው የራሱን የወንጌል ሰባኪነት አገልግሎት በመጥቀስ፥ “እንግዲህ፥ ሽልማቴ ምንድነው?” ሲል ይጠይቃል። የዚህ ጥያቄ እውነተኛ መልስ የሚገኘው ለእግዚአብሔር ከሰው እገልግሎት ጥራት ነው። በመሆኑም፥ ሐዋርያው ጳውሎስ በሥራዎቹ የተገለጠውን ታማኝነት ይዘረዝራል (ቁ. 18-23)። የዚህን ዘገባ እውነተኛነት የሚክድ አይኖርም። ከዚያም ክርስቲያናዊ አገልግሎትን አማኞች ሁሉ ከሚካፈሉት የሩጫ ውድድር ጋር ያነጻጽረዋል፤ በውድድሩም ሽልማቱን የሚያገኘው ከፍተኛ ጥረት ያደረገው አንድ ሰው ብቻ ነው። 

በክርስቲያናዊ አገልግሉትም እንደዚሁ እማኙ ሙሉ ሽልማቱን ያገኝ ዘንድ ባሰው ጉልበት ሊጠቀም ይገባል፤ ሁሉንም መቅደም እንደሚገባው ቆጥሮ ሊሮጥ ይገባል። ሯጭ የሚጠፋን አክሊል ለማግኘት ሰአግባቡ መሮጥ እንዳለበት ሁሉ፥ ክርስቲያኑም የማይጠፋውን አክሊል ለማግኘት መትጋት አለበት። ሐዋርያው በማያገባና በተከፈለ አሳብ ሳቢያ የተጣላ እንዳይሆን ሥጋውን ሲገዛ የኖረ መሆኑ ተገልጿል። በዚህ ስፍራ የተጣልሁ እንዳልሆን” ተብሎ የተተረጎመው ቃል በግሪክኛ “ዶኪሞስ” የሚል እሉታዊ ፍች አለው። የዶኪሞስ” አዎንታዊ ፍች ተቀባይነት ማግኘት” ተብሎ ተተርጉሟል (ሮሜ 14፡18፤ 16፡10፤ 1ኛ ቆሮ. 11፡19፣ 2ኛ ቆሮ. 10፡18፤ 2ኛ ጢሞ. 2፡15)። የተጣልሁ እንዳልሆን” የሚለው “ተቀባይነትን እንዳላጣ” ተብሎ ሊተረጎም ይገባል። የሐዋርያው ድነት በምንም ዓይነት አጠያያቂ ስላልሆነ፥ ለዘላለም ከእግዚአብሔር እስያለሁ የሚል ሥጋት አልነበረበትም። እጎልግሎቱ ተቀባይነት እንዳያጣበት ነበር ፍርሃቱ። 

ለክርስቲያኑ የሚሰጠው ሽልማት እንዳንድ ጊዜ “ዋጋ” (ሽልማት) ሲባል (1ኛ ቆሮ. 9፡24)። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ “አክሊል” ተብሏል (1ኛ ቆሮ. 9፡25፤ ፊልጵ. 4፡1፤ 1ኛ ተሰ. 2፡19፤ 2ኛ ጢሞ. 4፡8፤ ያዕ. 1፡12፤ 1ኛ ጴጥ. 5፡4፤ ራእይ 2፡10፤ 3፡11)። እነዚህ አክሊሎች አምስት የተለያዩ ክርስቲያናዊ አገልግሎቶችንና መከራን በመወከል በአምስት ሊከፈሉ ይችላሉ። የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ክርስቲያን ሽልማቱን እንዳያጣ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል (ቆሳ. 2፡18፤ 2ኛ ዮሐ. 8፤ ራእይ 3፡11)። 

የሽልማቶች ትምህርት በጸጋ የሚገኘው ድነት አስፈላጊ አካል ነው። እግዚአብሔር የአማኙን ሰናይ ምግባር ለድነቱ ስለማይቆጥርለትና ሊቆጥርለትም ስለማይችል፥ የአማኙ መልካም ሥራዎች መለኮታዊ እውቅና ማግኘታቸው ተገቢ ነው። ድነትን ያገኘ ሰው በስጦታ ለተበረከተለት ሕይወት ለእግዚአብሔር የሚከፍለው የሰውም። ይሁንና ፍጹም በሆነ መሰጠት ለእግዚአብሔር የመኖር ዕዳ አለበት። ለዚህ ፍጹም መሰጠቱ ተስፋ የተገባለት ሽልማት ሰሰማይ ይጠብቀዋል። 

ለአማኙ የሚሰጡ ሽልማቶች በአክሊሎች ተምሳሌትነት ሊገለጡም ራእይ 4፡10 እንደሚለው፥ እክሊሎቹ በሰማይ አዳኝ በሆነው ክርስቶስ እግር ሥር ይጣሳሉ። እንግዲህ፥ በታማኝነት አገልግሎቱን ለተውጣ አማኝ የሚሰጠው ሽልማት ምን ይሆን? 

በምድር ላይ በታማኝነት ማገልገል በሰማይ መልካም የአገልግሎት ስፍራ የማግኘት ሽልማት ያለው ይመስላል። ራእይ 22፡3 እንደሚለው፥ ባሪያዎቹ ያገለግሉታል።* አማኞች የወደዳቸውንና ለነርሱ ራሱን የሰጠ ዳኛቸውን በፍቅር በማገልገል የላቀ እርካታ ያገኛሉ። ማቴዎስ 25፡14-3ዕ ውስጥ ክርስቶስ ስለ መክሊት ባቀረበው ማብራሪያ፥ እምስትና ሁለት መክሊቶችን የተቀበሉት ሰዎች (ጌታቸው የሰጣቸውን እጥፍ ያደረጉ)፥ የሚከተለውን ምስጋና አግኝተዋል፤ “መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” (ማቴ. 25፡21፥ 23)። ይህ ፍርድ በቀጥታ ከቤተ ክርስቲያን ጋር የሚዛመድ ሳይመስልም። መመሪያው ዘላለማዊ ሽልማት ለሚያገኙ ለሁሉም ዘመን አማኞች ሊሠራ ይችላል። በዚህ ምድር ጌታን በታማኝነት ማገልገል በዘላሰሙ መንግሥት የተሻለ አገልግሎት እንድንሰጥ ያደርገናል። 

የክርስቶስን የፍርድ ወንበር ዋነኛ መልእክት የሚያስተላልፈው 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡10-14፥ ከክርሰቶስ የፍርድ ወንበር ፊት ክፉ ሥራዎች ከደግ ሥራዎች እንደሚለዩ ይገልጣል። አማኙም በመልካም ሥራው ይሸለማል። ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው፥ ፍርድ የሚሰጠው በኃጢአት ላይ አይደለም አማኙ ቀደም ብሎ ጸድቋልና። በአሁኑ ጊዜ ንስሐ ባልገቡ አማኞች ላይ ከሚሰጠው ቅጣት ጋር የተያያዘ ጉዳይም አይደለም (1ኛ ቆሮ. 11፡31-32፤ 1ኛ ዮሐ. 1፡9)፤ ምክንያቱም እማኝ በዚህ ወቅት በእግዚአብሔር ፊት ፍጹም ስለሆነ ነው። 

ስለዚህ፥ ቀሪው ብቸኛ ጉዳይ እግዚአብሔር የሚመዝነው የእማኙ የሕይወትና የአገልግሎት ጥራት ነው። አንድ ቀን እያንዳንዱ አማኝ ስለ ሕይወቱ መልስ ለመስጠት በእግዚአብሔር ፊት የመቆሙ እውነት ለአሁኑ ዘመን ታማኝነትን፥ ተገቢውን ግምገማና ከዘላለም እኳያ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ነገሮች ቅድሚያ የመስጠቱ ጉዳይ ሊበረታታ ይገባል።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

41
ትምህርት 41 ከ52

ሰንበትና የጌታ ቀን

ሀ. ሰንበት በብሉይ ኪዳን 

[በአማርኛ “ሰንበት” የሚለው ቃል እሁድ እንደሆነ ቢታሰብም በመጽሐፍ ቅዱስ ለአይሁድ ሰባተኛ ቀን የሆነውን ቅዳሜ የሚያመለክት ነው (ዘፀ. 16፡23-29፤ 20፡10፤ ዘሌዋ. 23፡3፤ ዘዳግ. 5፡14)። ይህን የእረፍት ቀን” (ሰንበት) በመጠበቅ አይሁዶች ለእግዚአብሔር የተለዩ ሕዝቦች መሆናቸውን የሚያሳዩበት መለያቸው ነበር (ዘፀ. 31፡13)። በሙሴ ሕግ (የሚያርሱበትን” ምድር ሰሰባተኛው ዓመት የሚያሳርፉበት “የዓመት እረፍት የሚባል ሥርዓት ደግሞ ነበራቸው (ዘሌዋ. 25፡2-8፤ 26፡34-35፥ 43፤ 2ኛ ዜና . 36፡21)። በዚህ መጽሐፍ “ዕንበት” የሚለው ቃል ቅዳሜን ማለትም “እረፍት ቀን” በመሳል ለአይሁድ የተሰጠውን ቀኝ እና ሊጠብቁት የሚጎባውን ዕለት የሚያመለክት ነው።]

እግዚአብሔር ከራሱ የፍጥረት ሥራ በመጀመር፥ የሁሉንም ጊዜ አንድ ሰባተኛ እጅ ለመቀደስ ወይም ለመለየት መርጧል። ለእስራኤላውያን ሰባተኛው ቀን የእረፍት ቀን እንዲሆን ወሰነ። በሰባተኛው ዓመት ምድሪቱ እንድታርፍ ተደርጓል (ዘዳ. 23፡10-11፤ ዘሌ. 25፡2-7)። ለሰባተኛው ዓመት ለሰባተኛ ጊዜ ለማሰብም ኀምሳኛው ዓመት እንደ ኢዮቤልዩ ይከበር ነበር። በተላያዩ ዝርዝር ጉዳዮች የሰንበትና የኢዮቤልዩ ዓመታት ለእግዚአብሔር መንግሥት ትንቢታዊ ናቸው። ይህ የእግዚአብሔር መንግሥት ሰባተኛና የመጨረሻ የአገዛዝ ሥፍረ-ዘመን ሲሆን፥ የሚታወቀውም ለፍጥረት ሁሉ የሚፈጸም የሰንበት እረፍት ሰመሆን ነው። በአሁኑ ዘመን የሚከበረው ዕለት ከአዲሱ ፍጥረት ጅማሬ ሳቢያ ሰመለኮታዊ አሠራር ከሰባተኛው ወደ አንደኛው ቀን ቢለወጥም፥ በጊዚ አከፋፈል አሁንም ለእረፍት የሚውለው ተመሳሳይ መጠን፥ ማለትም ከሰባቱ ቀናት አንዱ ሆኗል። 

“ሰንበት” የሚለው ቃል መተውን ወይም ከሥራ ሙሉ በሙሉ ማረፍን ያመለክታል። ክማያቋርጡት የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችና በዓላት ባሻገር፥ ዕለቱ በምንም መልኩ የአምልኮ ወይም የአገልግሎት ጊዜ አይደለም። 

ሰንበትን አስመልክቶ የሚታየውን ግራ መጋባት ለማቃለል፥ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ትክክለኛ መልእክት በጥንቃቄ ማጥናቱ አስፈላጊ ነው። 

ሰንበትን ከተለያዩ የዘመን ክፍሎች ጋር ስናገናዝብ፥ በተወሰነ ደረጃ ግልጥ ማስረጃ ለማግኘት ይቻላል። 

ከአዳም እስከ ሙሴ በነበረው ጊዜ እግዚአብሔር የስድስት ቀናት ሥራውን ጨርሶ እንዳረፈ ሲገለጥ (ዘፍጥ. 2፡2-3፤ ዘዳ. 20፡10-11፤ ዕብ.4፡4)፥ ሰውን በተመለከተ ስለ ሰንበት በዚህ ወቅት የተጠቀሰ ነገርን አናነብም። እስራኤላውያን ከግብፅ እስከወጡበት ጊዜ ድረስ፥ ሰው የሰንበትን ቀን እንዳከሰረ የሚያመለክት አሳብ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ አልተጠቀሰም። 

መጽሐፈ ኢዮብ የእምነት አባቶችን ሃይማኖታዊ ሕይወትና ልምምድ ይገልጣል። ምንም እንኳ እነዚህ አባቶች ለእግዚአብሔር የነበራቸው የተለያዩ ኃላፊነቶች ቢገለጡ፥ ስለ ሰንበት ዕለት ግዴታ የሚናገር አሳብ ግን አልተጠቀሰም። በሌላ በኩል ግን የሰንበት በሙሴ እጅ ለእስራኤላውያን መሰጠት፥ ሰንበት በሰው ልጆች ዘንድ መከበር የጀመረበት ጊዜ መሆኑን በግልጥ ያመለክታል (ዘጸ. 16፡29፤ ህ . 9፡14፤ ሕዝ. 20፡12)። 

በተመሳሳይ ሁኔታ፥ መጀመሪያ ከተደነገገው ሰንበት አንድ ሳምንት ወይም ሰባት ቀናት ቀደም ብሎ፥ የእስራኤል ልጆች የሰንበትን ሕግ በማፍረስ ረዥም መንገድ ተጉዘው ከኤሊም ወደ ሲና ምድረ በዳ እንደመጡ ከመጀመሪያዎቹ የሰንበት ድንጋጌ ዘገባዎች ለመረዳት ይቻላል (ዘጸ. 16፡1-35)። በዚያ ምድረ በዳ ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ በማጉረምረሙ፥ በዕለቱ ከሰማይ ምግብ ይወርድላቸው ጀመር። ምግቡ ለስድስት ቀናት እንጂ፥ በሰባተኛው ቀን መሰብሰብ አልነበረበትም። ስለዚህ በሰንበት ዕለት ጉዞ ማድረጋቸው የሚያስረዳው፥ ዕለቱን እንደ ሰንበት ያላከበሩት መሆኑን ነው። 

ከሙሴ እስከ ክርስቶስ በነበረው ዘመን፥ የሰንበት ሕግ ሥራ ላይ ውሏል። ሰንበት የማከበሩ ጉዳይ ሕግ ውስጥ የተካተተ ሲሆን (ዘጸ. 20፡10-11)፥ የሰንበትን ሕግ ለተላለፈ ሰው ይደረግ የነበረው መለኮታዊ መፍትሔም በመሥዋዕቶች ሕግ ውስጥ ተካቷል። እዚህ ላይ የሰንበት ሕግ ለአሕዛብ እንዳልተሰጠና በያህዌና በእስራኤል መካከል የሚከናወን ልዩ ምልክት እንደነበር መገንዘቡ ተገቢ ነው (ዘጸ. 31፡12-17)። ከእስራኤል ኃጢአቶች መካከል ሰንበትን ለማክበርና ለምድሪቱም እረፍት እለመስጠታቸው የተለየ አጽንኦት የተደረገባቸው ናቸው። 

በዚህ የሕግ አማካይ ክፍለ ጊዜ፥ ሆሴዕ በእስራኤል ላይ ከሚደርሱት ፍርዶች አንዱ የሰንበታቶቿ ማክተም መሆኑን ተንብዮአል (ሆሴዕ 2፡11 )። ይህ ትንቢት ከእግዚአብሔር አፍ የወጣ ነውና አንድ ቀን መፈጸሙ የግድ ነበር። 

ከሞቱ ቀደም ሲል በነበረው ጊዜ የክርስቶስ ምድራዊ ሕይወትና አገልግሎት ክሕግ በታች ነበር። በዚህም ምክንያት ክርስቶስ ሕግን እንደሚጠብቅ፥ እንደሚተነትንና በሥራ ላይ እንደሚያውል ታይቷል። በመሆኑም ክርስቶስ የሰንበት ሕግ በሰዎች ትውፊትና ትምህርቶች እንደተዛባ በመገንዘብ በዘመኑ ካሉ አስተማሪዎች የተለየ ትምህርት አስተምሯል። ስለዚህ ሰንበት ለሰው ልጅ ጥቅም እንደተሰጠና ሰው ከሰንበት ወጎች የተነሣ ቀኑ ሸክም ይሆንበት ዘንድ እንደማይገባ እስተምሯል (ማር. 2፡27)። ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ሰንበትን ላካተተው የሙሴ ሕግ ሁሉ በታማኝነት ይታዘዝ ነበር። ይህ የሆነው ጌታ በነበረበት ዘመን ሕግ በሥራ ላይ ስለነበረ ነው። ይሁን እንጂ፥ ይህ ሁኔታ በጸጋ ዘመንና በሌላ ሥፍረ-ዘመን የሚኖረው ክርስቲያን የክርስቶስን የሰንበት አክባሪነት ምሳሌ ሊከተል ይገባል ለሚል ትምህርት አባባል መሠረት ሊሆን የማይችል መሆኑን ይህ ግልጥ እውነት ያስገነዝባል። 

ለ. ሰንበት ሰአሁኑ የቤተ ክርስቲያን ዘመን 

ከክርስቶስ ትንሣኤ በኋላ፥ በአዲስ ኪዳን በስሕተት እንኳ ሰንበትን ያከበረ አማኝ አልተጠቀሰም። ከይሁዲነት ወደ ክርስትና የተመለሱ እያሌ እማኞች ሰንበትን ማከበራቸው ግልጥ ቢሆንም፥ እንዲህ ዓይነቱ አከባበር በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ አልተጠቀሰም። እንደዚሁም፥ ከክርስቶስ ትንሣኤ በኋላ ለአይሁዶች፥ ለአሕዛብ ወይም ለክርስቲያኖች ሰንበትን ያከብሩ ዘንድ የተሰጠ ትእዛዝ አናገኝም፡፡በሰንበት ቀን መሥራትም እንደ ኃጢአት የተቆጠረበት ሁኔታ አልተመለከተም። 

በተቃራኒው ግን በጸጋ ዘመን የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑ አማኞች የሰንበትን ሕግ እንዳይጠብቁ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። 

ገላትያ 4፡9-10 ቀናትን፥ ወራትን፥ ወቅቶችንና ዓመታትን የማክበሩ ተግባር የማያስፈልግ መሆኑን የሚያሳይ አሳብ አለ። እነዚህ ነገሮች የሚከበሩት በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ያስገኛሉ ከሚል አስተሳሰብ ሲሆን፥ አክባሪዎቹም በአንድ ወቅት እግዚአብሔርን የሚያስቡና በሌላ ጊዜ ግን በግዴለሽነት የሚኖሩ ሰዎች ናቸው። 

ዕብራውያን 4፡1-13 ሰንበት እግዚአብሔር ከሥራው ያረፈበትና አማኝም በሚድንበት ጊዜ የሚገባበት የእረፍት ስፍራ መሆኑን ያስረዳል። 

ቆላስይስ 2፡16-17 ውስጥ የሰፈረው ቃል የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው ከሰንበት እከባበር ጋር በተያያዘ ሊፈረድበት የማይገባ መሆኑን በግልጥ ያስረዳል። አሁን አዲስ ፍጥረት ለሆነው አማኝ ክርስቶስ ከሆነለት ሁኔታ አንጻር፥ በሰንበት ላይ የዚህ ዓይነት እመለካከት መያዙ ትክክል ነው (ቆላ. 2፡9-17)። በዚህ ምንባብ ውስጥ የተጠቀሱት የሥርዓታዊ ሕግ አካላት የሆኑት ልዩ ወይም ተጨማሪ ሰንበታት ሳይሆኑ፥ ሳምንታዊዎቹ ሰንበታት ይሆኑ ይሆናል፥ ለምሳሌ (ዘሌዋ. 16፡31)። እንድ እማኝ በራሱ አእምሮ ሲረዳ ቀናትን ሁሉ በእኩልነት ሊመለከት እንደሚችል ሮሜ 14፡5 ውስጥ ተጎልጧል። ይህ ሁኔታ በታማኝነት ማምለክን ገለል የሚያደርግ ሳይሆን፥ እንዲህ ላለው ሰው ቀናት ሁሉ ለእግዚአብሔር በመገዛት የተሞሉ መሆናቸውን ያስረዳል። 

አዲስ ኪዳን ውስጥ ሰንበትን በመጠበቅ ረገድ የክርስቲያንን ሕይወትና አገልግሎትን አስመልክቶ እንደ ሕግ የተሰጠ ነገር የለም። ስለዚህ በሙሴ በተሰጠው የሰንበት ሕግ ፈንታ፥ ሰአዲሱ ፍጥረት የጌታ ቀን ሰሚለው የተተካ መሆኑን መገንዘቡ ጠቃሚ ነው። ይህ የጌታ ቀን በክብሩ፥ በከፈተው መብትና በረከቶቹ ከሰንበት እጅግ የሚልቅ ነው። 

ሐ. ሰንበት በሚመጣው ዘመን 

ከአዲስ ኪዳን ትምህርት ጋር ሙሉ ለሙሉ በተዛመደ መልኩ፥ አዲሱ የጌታ ቀን የሚሠራው ለቤተ ክርስቲያን ብቻ ነው። የሰንበት ሕግ እንደገና በሥራ ላይ እንደሚውል ተተንብዮአል። የቤተ ክርስቲያን መጠራት ከተፈጸመና ከዓለም ከተነጠቀች በኋላ፥ የሰንበት ሕግ የጌታን ቀን በመተካት የሚሠራ መሆኑ ነው የተገለጠው። በዚህ ዘመን ፍጻሜና በእግዚአብሔር መንግሥት መካከል ጣልቃ በሚገባው የታላቁ መከራ አጭር ወቅት እንኳ የሰንበት አሳብ ይንጸባረቃል (ማቴ. 24 ፡20)። ሰንበት የሚመጣው መንግሥት ዘመን ዋነኛ ጉዳይ እንደሚሆንም በትንቢት ተመልከቷል (ኢሳ. 66፡23፤ ሕዝ. 46፡1)። 

መ. የክርስቶስ ትንሣኤና የሳምንቱ መጀመሪያ ዕለት 

ከክርስቶስ ትንሣኤ እንሥቶ እስከዛሬ ድረስ የሳምንቱ የመጀመሪያ ዕለት በቤተ ክርስቲያን በመከበር ላይ ነው። ይህ እውነት በአዲስ ኪዳን ዘገባዎች፥ በቀደምት አባቶች ጽሑፎችና በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የተረጋገጠ ነው። ከሞላ ጎደል በሁሉም ክፍለ ዘመናት፥ እግዚአብሔር ሰአዲሱ ፍጥረት ሊሠራ ያቅደውን የእሁን ዓላማ ሳይገነዘቡ ሰባተኛውን የሰንበት ዕለት ለማክበር የተነሡ ሰዎች ነበሩ። ሰባተኛውን ቀን ማክበር ያስፈልጋል በማለት የሚያስተምሩት፥ ትምህርታቸው ከቃሉ ውጭ በሆኑ ነጥቦች የተደገፈና ሌላ እምነት ያላቸው ናቸው። በሰንበት ጉዳይ ውዝግብ የሚነሣው የአማኞች አምልኮ በሙሴ የሰንበት ሕግ እንደሚመራ ተደርጎ ሲወሰድ ነው። ይህ ሲሆን አዲስ ኪዳን የሚያስተምረው የአዲስ ፍጥረት” እውነት ይዘነጋል። 

ሠ. አዲሱ ፍጥረት 

የዚህ ሥፍረዘመን የእግዚአብሔር ዓላማ ቤተ ክርስቲያንን እንደተለየ ሕዝብ የሚጠራት መሆኑን አዲስ ኪዳን ያስተምራል (ሐዋ. 15፡13-18)። በዚህ የእግዚአብሔር ጥሪ የዳኑ ሰዎችም ሰማያዊ ዜጎች የሆኑ አዲስ ፍጥረታት ናቸው። እነዚህ ሰዎች በአጠቃላይ አስደናቂ ክብርና ፍጹምነት የሚሰጣቸው መሆኑ ሲገለጥ (ኤፌ. 5፡25-27)፥ በግለሰብ ደረጃም እጅግ የላቀ መለኮታዊ ተግባርና ለውጥ የሚካሄድባቸው ናቸው። እንዲሁም ጠቅላላው አካል በመሠረቱ ከክርቶስ ጋር እንደተገናኘ ሁሉ (1ኛ ቆሮ. 12፡12)፥ ግለሰብ አማኝም በዋናነት ከጌታ ጋር ተዛምዷል (1ኛ ቆሮ. 6፡17፤ ሮሜ 6፡5፤ 1ኛ ቆሮ. 12፡13)። 

ግለሰብ አማኝን አስመልክቶ መጽሐፍ ቅዱስ የሚከተለውን ያስተምራል፡- (1) ኃጢአትን በተመለከተ፥ በዚህ አካል ውስጥ የሚገኝ እያንዳንዱ አማኝ ከኃጢአቱ ነጽቶና ይቅርታን አግኝቶ ጸድቋል። (2) ስጦታን በተመለከተ፥ ለእያንዳንዱ አማኝ ውስጡ የሚኖር መንፈስ ቅዱስና የእግዚአብሔር ስጦታ የሆነው ዘላለማዊ ሕይወት ተበርክቶለታል። ከክርስቶስ ጋርም የእግዚአብሔር ሕጋዊ ወራሽ ነው። (3) ሰፍራውን በተመለከተ፥ እያንዳንዱ አማኝ የእግዚአብሔር ጽድቅ ሆኖ ሰውድ ልጁ አማካይነት ለዘላለም ተቀባይነትን አግኝቷል (2ኛ ቆሮ. 5፡21፤ ኤፌ. 1፡6)። ይህ ብቻም አይደለ ከተሰጠው ጽድቅ የተነሣ የክርስቶስ ስውር አካል ክፍል፥ የከበረችው ሙሽራ አካልና ክርስቶስ ራሱ የሆነው የሚያስተዳድረው እዲስ ፍጥረት ሕያው ተካፋይ ለመሆን በቅቷል። “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። ነገር ግን፥ የሆነው ሁሉ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው” (2ኛ ቆሮ. 5፡17-18 ገላ. 6፡15፤ ኤፌ. 2፡10፤ 4፡24)። 

ሐዋርያው ጴጥሮስ ስለ አማኞች ሲጽፍ፥ “እናንተ የተመረጣችሁ ትውልድ ናችሁ” (1ኛ ጴጥ. 2:9) ብሏል። ይህም በቀጥታ በእግዚአብሔር ኃይል የተፈጠረና ከሰማይ የተወለደ ልዩ ዘር ወይም ብሔር ማለት ነው። የመጀመሪያው አዳም የራሱ ሰብአዊ ሕይወትና ፍጹማዊነት የጎደለው ሕይወት ተካፋይ የሆነውን የሰው ዘር እንደወለደ ሁሉ፥ የመጨረሻው አዳም ክርስቶስ ደግሞ ዘላለማዊ ሕይወቱንና ፍጹምነቱን የሚካፈል አዲስ ዘር በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በመፍጠር ላይ ነው። “ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ” (1ኛ ቆሮ. 15፡45)። አማኝ በክርስቶስ በመሆኑ የትንሣኤው ተካፋይ የሚያደርገውን ሕይወት ያገኘ መሆኑ ተገልጧል (ሮሜ 6፡4፤ ቆላ. 2፡12-13፤ 3፡1-4)። ይሁን እንጂ፥ አካሉን በተመለከተ አማኙ ገና የክርስቶስን የትንሣኤ እካል የሚመስል የከበረ አካል ሊላብስ ይገባል (ፊልጵ. 3፡20-21)። ክርስቶስ ከሞት እንደተነሣ “እንደበኩራት በሰማይ መታየቱ የሚከተሉት ሁሉ የከበረ አካል ለብሰው እንደርሱ የሚነሡ መሆናቸውን ያመለክታል (1ኛ ዮሐ. 3፡2)። 

እዲሱ ፍጥረት በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ፥ በሁሉም ስፍራ ከአሮጌው ጋር ተነጻጽሮ ቀርቧል። ይህ አዲስ ፍጥረት የጀመረው በክርስቶስ ትንሣኤ ሲሆን፥ ዳግም የተወለዱትንና በርሱ የሆኑትን ሰማያዊ ዜጎች ያካትታል። አማኝ የዳነውና ነጻ የወጣው ከዚያ አሮጌና የተበላሸ ፍጥረት መሆኑ ግልጥ ነው። 

ሰንበት አሮጌውን ፍጥረት ለመዘከር እንደተፈጠረ ሁሉ (ዘጸ. 20፡10-11፤ 31፡12-17፤ ዕብ. 4፡4)፥ የጌታ ቀንም እዲሱን ፍጥረት ይዘከረዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ፥ ሰንበት እንደ ምድራዊ የእግዚአብሔር ሕዝቦች በእስራኤላውያን ብቻ ይከበር እንደነበር ሁሉ፥ የጌታ ቀንም የዕማያዊው የእግዚአብሔር ሕዝብ አካል በሆነችው ቤተ ክርስቲያን የተወሰነ ነው። 

ረ. የጌታ ቀን (እሁድ) 

በጸጋ ሥር ባሉ የእግዚአብሔር ልጆች ላይ የሰንበት (ቅዳሜ) ሕግ ተፈጻሚ የሚሆንበት ድንጋጌ በየትኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አይታይም። በአንጻሩ ግን ክርስቲያኖች የሳምንቱን የመጀመሪያ ቀን (እሁድ) የሚያከብሩባቸው ምክንያቶች አሏቸው። 

1. ፀጸጋ ዘመን ስለ አዲስ ቀን ተተንብይዋል፥ ተወስኗልም። መዝሙር 118፡22-24 እና የሐዋርያት ሥራ 4፡10-11 እንደሚነግሩን፥ ክርስቶስ በስቅላቱ ግንበኞች” በተባሉት እስራኤላውያን የተናቅ ድንጋይ ሆኗል። ከሞት በመነሣቱ ግን የማዕዘን ራስ ድንጋይ ሆነ። ይህ አስደናቂ ነገር የተፈጸመው በእግዚአብሔር ሲሆን፥ የአፈጻጸሙ ዕለትም የደስታና የትፍስሕት ዕለት ይሆን ዘንድ በመለኮታዊ ሥልጣን ተወስኗል። በመሆኑም፥ ክርስቶስ በትንሣኤው ማለጻ ያቀረበው ሠላምታ “ደስ ይበላችሁ የሚል (ማቴ. 28፡9) ነበር። አሳቡ በቀጥታ ሲፈታ (“ታላቅ ደስታ!” ማለት ነው። “እግዚአብሔር የሠራት ቀን” እንደመሆኗ “የጌታ ቀን” መባሏ ትክክል ነው። 

2. የመጀመሪያው ዕለት አከባበር በተለያዩ ሁኔታዎች ተመልክቷል።(ህ) ክርስቶስ ከሞት በተነሣበት ዕለት (ማቴ. 28፡1)። (ለ) በዚያን ዕለት ደቀ መዛሙርቱን በአዲስ ኅብረት አገኛቸው (ዮሐ. 20፡19)። (ሐ) በዚያው ዕለት ትእዛዛትን ሰጣቸው (ሉቃስ 24፡13-45)። (መ) በዚያው ዕለት እንደ “በኩራት” ወይም እንደ በኩራት ነዶ ወደ ሰማይ ዐረገ (ዘሌ . 23፡10-12፤ ዮሐ. 20፡17፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡20፥ 23)። (ሠ) እስትንፋሱን እፍ ያለባቸው በዚያን ዕለት ነው (ዮሐ. 20፡22)። (ረ) በዚያን ዕለት መንፈስ ቅዱስ ከሰማይ ወረደ። (ሰ) ሐዋርያው ጳውሎስ በጢሮአዳ የሰበከው ያን ዕለት ነው (ሐዋ. 20፡6-7)። (ሸ አማኞች የጌታን እራት ሊወስዱ የተሰበሰቡበት ዕለትም ነው (ሐዋ. 20፡6-7)። (ቀ) እግዚአብሔር እንዳበለጠጋቸው መጠን ገንዘብ ያዋጡትም በዚያን ዕለት ነው (1ኛ ቆሮ. 16፡2)። (በ) ጌታ ለዮሐንስ በፍጥሞ ደሴት በዚያን ዕለት ተገለጠ (ራእይ 1፡10)። 

3. ስምንተኛው ቀን የግርዘት ቀን ነበር። በዚህ ዕለት የሚፈጸም ግርዘት፥ አማኝ በክርስቶስ ሞት አማካይነት ከሥጋና ከአሮጌው ሥርዓት መለየቱን በምሳሌነት ያሳያል (ቆላ. 2፡11}። ከሳምንቱ ፍጻሜ ቀጥሉ በመጀመሪያው ዕለት የሚውል ስምንተኛ ቀን እንደ መሆኑ የአዲስ ጅማሬ ተምሳሌት ነው። 

4. አዲሱ ዕለት የጸጋ ነው። በሕግ ሥራ አማካይነት ከእግዚአብሔር ጋር ለሚዛመዱ ሰዎች፥ ክሳምንቱ አድካሚ ሥራ በኋላ የእረፍት ቀን ያሰጣቸው ነበር። ሥራዎቻቸው በክርስቶስ ለተጠናቀቀላቸው የጸጋ ዘመን ሰዎች ግን ይህ ቀን እንደ እረፍት ብቻ ሳይሆን፥ የአምልኮ ዕለት ተብሎ ነው የተሰጣቸው። ይህም የሳምንቱ መጀመሪያ ዕለት እንደመሆኑ፥ የሥራ ቀናትን ሁሉ ይቀድማል። አማኝ በመጀመሪያው ዕለት ከሚያገኘው ባርኮት፥ ቀጣዮቹን ስድስት ቀናት ጌታውን ያገለግልበታል። የእረፍት ቀን የሚያስፈልገው፥ ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸው ግንኙነት በሥራዎቻቸው ላይ የተመሠረተ ለሆኑ ነው። የማያቋርጥ አምልኮና አጎልግሎት የሚካሄድበት ዕለት ደግሞ፥ ክርስቶስ በፈጸመው ሥራ አማካይነት ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ላሳቸው ሰዎች ነው። ሰባተኛው ዕለት በማይላቀቁት ሕግ ሲታወቅ፥ የመጀመሪያው ዕለት በጸጋ ምርጫና ነጻነት ይሰያል። ሰባተኛው ቀን ምናልባት አንድ ቀን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን አገኝ ይሆናል በሚል ቀቢጸ-ተስፋ ይከበር የነበር ሲሆን፥ የመጀመሪያው ቀን ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ማግኘቱን ባረጋገብ ሰው ይከበራል። ሰባተኛው ቀን የሚፈጸመው በሥጋ ኃይል ሲሆን፥ የመጀመሪያው ቀን ግን በአማኙ ልብ ውስጥ በሚያድረው መንፈስ ቅዱስ አማካይነት ይከናወናል። 

5 . አዲሱ ዕለት በእግዚአብሔር ተባርኳል። በዚህ ዘመን፥ መንፈስ ቅዱስ ሙላት ያደረባቸውና የእግዚአብሔር ፈቃድ በግልጥ የታየባቸው እውነተኛ አማኞች የጌታን ቀን ሲጠብቁ ሰባተኛውን ቀን ግን የመጠበቅ ግዴታ እንዳለባቸው አድርጎው አይረዱትም። እነዚህ ወገኖች የሰንበትን ሕግ በመጣስ በደለኞች ቢሆኑ ኑሮ ስለ ኃጢአታቸው ያቀጡ ነበር ብሎ ማሰብ ተገቢ ነው። 

6. አዲሱ ዕለት የተሰጠው ለእማኝ ግለሰብ ብቻ ነው። ላልዳነ ሰው አልተሰጠውም። ያልዳኑ ሰዎች ማንኛውንም ቀን ቢያከብሩ እግዚአብሔር ዘንድ የበለጠ ተቀባይነት እንደሚያገኙ የሚያስገነዝብ መሠረት መጣሉ እጅግ አደናጋሪ ነው። ምክንያቱም በክርስቶዕ ከሚገኘው ድነት ውጭ ሰዎች ሁሉ የጠፉ ናቸው። የእረፍት ቀን ለሰው ሁሉ ማኅበራዊ ወይም አካላዊ ጠቀሜታ ሊኖረው ቢችልም፥ እንዲህ ዓይነቱ የቀን አከባበር በእግዚአብሔር ፊት ምንም እንደማያስገኝላቸው ያልዳኑ ሰዎች ሊገነዘቡ ይገባል። 

ይህን ዕለት (እሁድ) ትጠብቅ ዘንድ ለቤተ ክርስቲያን እንደ ትእዛዝ አልተሰጣትም። ስለሆነም፥ የመጀመሪያው ዕለት አከባበር ለግለሰብ አማኝ እንጂ፥ ለቤተ ክርስቲያን አለመሰጠቱ ግንዛቤ ሊያገኝ ይገባል። አማኝ ይህን ዕለት የሚያከብርበት ሁኔታ ክርስቶስ ከሞት በተነሣበት ጠዋት ሰተናገራቸው ሁለት አባባሎች ውስጥም ተመልክቷል፤ 

“ደስ ይበላችሁ!” እና “ሄዳችሁ ተናገሩ”። ይህ ጥሪ በማንኛውም አምልኮና አገልግሎት ውስጥ የማያቋርጥ እንቅስቃሴ ማድረግን የሚጠይቅ ሲሆን፥ ከሰባተኛው ቀን እረፍት ጋር ይጻረራል። 

7. የመጀመሪያው ቀን ሰይድ እንዲከበር የተሰጠ ትእዛዝ የለም። የጸጋ ተግባር በመሆኑ፥ ዕለቱን ስለማክበር የተጻፈ ግዴታ የለም። አከባበሩ ሊከናወን የሚገባበት ሁኔታም በዝርዝር አልተመለከተም። ይህ ጥበብ የተሞላበት ልግስና እንደሚያስረዳው፥ ማንም የጌታን ቀን እንደ ግዴታ እንዲቆጥረው የተጠቀሰበት ሁኔታ የለም። ከልብ በመነጨ ፍላጎት ሊከናወን ይገባል። እስራኤል በእግዚአብሔር ፊት ሞግዚቶችና አስተዳዳሪዎች እንደሚያሻቸው ለጋ ሕፃናት ስለነበረች፤ ከሕፃን እንደሚሰጥ ዓይነት ሕግ አስፈለጋት (ገላ. 4፡1-11)። ቤተ ክርስቲያን ግን በእግዚአብሔር ፊት እንደ እዋቂ ልጆች ትታያለች። የአማኙ ሕይወት በጸጋ ዘመን ምን መምሰል እንዳለበት በሚገባ ተገልጧል። እግዚአብሔር ከእማኙ የሚፈልጋቸው ነገሮች በፈቃደኝነት መሆን ያለባቸው መሆኑን በማሰብ ያቀረበው በልመና ነው (ሮሜ 12፡1-2፤ ኤፌ. 4፡1-3)። በሚገባ ቃሉን የተረዳና በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ክርስቲያን የክርስቶስ ትንሣኤና የአዲስ ፍጥረት ዕላት በሚከበርበት ጊዜ በሌላ ሥራ ይጠመዳል ብሎ ለመገመት አይችልም። የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው ለእግዚአብሔር የማይገዛ ከሆነ፥ ያለፈቃደኛነት ቀንን ማክበር ሥጋዊ ልቡን አያስተካክለውም። እንዲህ ዓይነቱ አከባበርም እግዚአብሔርን አያስደስተውም። ስለሆነም፥ በእግዚአብሔርና በሥጋዊ ክርስቲያን መካከል ያለው ጉዳይ ውጫዊ ተግባር ሳይሆን፥ የተሰጠ ሕይወት ነው። 

የጌታ ቀን የሚከበርበት ሁኔታ ወደ ቀናት ሁሉ ሊዛመት ይችላል። ክርስቶስ ለአብ የሚገዛው እንደኛው ዕለት ከሌላው ባነሰ ሁኔታ አልነበረም። የሰንበት እረፍት ለሁሉም ቀናት በዚያው መልኩ ሊቀጥል አይችልም። ዳሩ ግን አማኝ በሳምንቱ መጀመሪያ ዕለት የበለጠ ጊዜና ነጻነት ሊኖረው ቢችልም፥ የጌታ ዕለት አከባበር መለያ የሆኑት እምልኮ፥ ደስታና እገልግሎት በተቻለ መጠን የዕለት ተዕለት ልምምዶቹ ሊሆኑ ይገባል (ሮሜ 14፡5)።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

42
ትምህርት 42 ከ52

አሕዛብ በታሪክና በትንቢት

ሀ. አሕዛብ በእግዚአብሔር ዕቅድ 

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በታሪክና በትንቢት መሠረት ሦስት ዓበይት የሰው ልጆች ከፍሉችን ለማጤን ይቻላል። 1ኛ ቆሮንቶስ 10፡32 ውስጥ በተመለከተው መሠረት የእግዚአብሔር ዓላማ ከአይሁዶች፥ ከአሕዛብና ከቤተ ክርስቲያን ጋር የሚገናኝ መሆኑ ተመልክቷል። ከዚህ ጋር የሰብአዊ ታሪክ ወይም ትንቢት ዓቢይ እካል ሆኖ የማይቆጠረው ለመላእክትና በነሱ በኩል የሚደረገው የእግዚአብሔር አገልግሎት ሊታከል ይችላል። 

እግዚአብሔር እስራኤልን የመለኮት መገለጫ፥ የክርስቶስ መምጫ ልዩ መንገድ ከማድረጉና የጸጋው መግለጫ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን ካለው ዓላማ ጋር ሲነጻጸር፥ ለአሕዛብ ያለው ዓላማ ክብሩንና ሁሉን ቻይነቱን ካመግለጥ ጋር የተዛመደ ነው። 

ለ. አሕዛብን የሚመለከቱ ቀደምት ትንቢቶች 

በአንድ በኩል፥ ለአሕዛብ ትንቢት የተጀመረው ኤደን ገነት ውስጥ ነው። የዚህ ምክንያቱ በተወሰነ ደረጃ አሕዛብ የእግዚአብሔር የድነት ዓላማ ተካፋዮች በመሆናቸው ነው። በዘፍጥረት መጽሐፍ መጀመሪያ ላይ በኖኅ ዘመን ከርሱና ከቤተሰቡ በስተቀር የሰውን ዘር ጠራርጎ ስላጠፋው የጥፋት ውኃ ትንቢት ተነግሯል። በተመሳሳይ ሁኔታ፥ ሰባቢሎን ግንብ ጊዜ እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ያወረደው ፍርድ ታሪክም ተመዝግቧል (ዘፍጥ. 11፡1-9)። ከዘፍጥረት ምዕራፍ 12 ጀምሮ ግን የሰው ዘር በሁለት ምድቦች ተከፍሏል። ይኽውም ከአብርሃም፥ ከይስሐቅና ከያዕቆብ የሚመጣውን የተስፋ ቃል ዘር እግዚአብሔር መግለጥ መጀመሩ ነው። ሌሎቹ ሁሉ በአሕዛብነታቸው ቀጠሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ያደረጋቸው መሠረታዊ ነገሮች ሁሉ ከእስራኤል ጋር በተያያዘ መልኩ ነው። 

የመጀመሪያዋ ታላቅ የአሕዛብ መንግሥት ሆና የምትታወቀው ግብፅ ናት። በመጀመሪያዎቹ አምስት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ እንደተመዘገበው፥ እስራኤላውያን ከትንሽ ቤተሰብነት ወደ ትልቅ ሕዝብነት ያደጉት ግብፅ ውስጥ ነበር። በዳዊትና ሰለሞን ዘመን እስራኤላውያን ታላቅ ሕዝብ ለመሆን ቢበቁም፥ በ721 ዓ.ዓ. አሥሩ ነገዶች ሁለተኛይቱ ኃያል የአሕዛብ መንግሥት በነበረችው በአሦር ተማርከዋል። በአሦራውያን አማካይነት በእስራኤል ላይ የደረሰው የእግዚእብሔር ፍርድ ቀደም ብሎ የተተነበየ ሲሆን፥ እንደተሳለው በትክክል ተፈጽሟል። 

ይህም ሆኖ፥ ከእስራኤል ጋር በተያያዘ ሁኔታ የአሕዛብ ዓቢይ ሚና የተጀመረው በባቢሎን መንግሥት ነበር። ባቢሎን ሦስተኛዋ ኃያል የአሕዛብ መንግሥት ስትሆን፥ በዳንኤል ትንቢቶች ውስጥ ከሚገኙት አራት መንግሥታት ግን የመጀመሪያዋ ናት። 

ሐ. የአሕዛብ ዘመናት 

ከሦስቱ የእግዚእብሔር ዕቅዶች ሁለቱ ለነብዩ ዳንኤል ተገልጠውለታል። እነሱም እግዚአብሔር ለእስራኤልና ለአሕዛብ ያሉት ዕቅዶች ናቸው። ዳንኤል ምዕራፍ 2 ውስጥ እንደተገለጠው ናቡከደነፆር በተመለከተው ሕልም ተጀምሮ ለዳንኤል በታዩት ራእዮች በቀጠለው ተከታታይ መልኮታዊ መገለጥ፥ ከባቢሎን ጀምሮ እራት ኃያላን የአሕዛብ መንግሥታት እስራኤልን እንደሚገዙ እግዚአብሔር ገልጧል። ይህም ዳንኤል ምዕራፍ ሁለት ውስጥ በታየው ታላቅ ምስል ውስጥ ተገልጧል፤ የወርቁ ራስ ባቢሎንን፥ ከላይ ብር የሆነው ሜዶንና ፋርስን፥ የታችኛው የነሐስ ገጽታ ግሪከን፥ እና ብረት የሆኑት እግሮች ሮምን ያመስክቱ ነበር። ይህ እውነት ዳንኤል ምዕራፍ 7 ውስጥ ተጠናክሯል። በዚህ ምዕራፍ አራቱ አራዊት አራቱን መንግሥታት አመልክተዋል። 

ዳንኤል በትንቢት መጽሐፉ አምስተኛ ምዕራፍ እንደተጠቀሰው፥ ሁለተኛው መንግሥት (ሜዶንና ፋርስ) በ539 ዓ.ዓ. ባቢሎንን ሲያሸንፍ በሕይወት ኖሮ ለመታዘብ በቅቷል። ከሁለት መቶ ዓመታት በኋላ የግሪክ መንግሥት በታላቁ እስክንድር እየተመራ የፋርስና ሜዶንን መንግሥት ቅሬታዎች አሸነፈ። ከክርስቶስ ልደት በፊት በሁለት መቶ ዓመት ደግሞ የሮም መንግሥት ወደ ኃያልነቱ እየተሸጋገረ መጥቶ ከሁሉም ዘመን መንግሥታት ወደላቀ ደረጃ ደረሰ። 

ከባቢሎን ጀምሮ የነበሩት የአራት መንግሥታት ዘመን በክርስቶስ (የአሕዛብ ዘመን” ተብሎ የተጠራ ሲሆን (ሉቃስ 21፡24)፥ መለያ ባሕርዩም የኢየሩሳሌም በአሕዛብ አገዛዝ ሥር መውደቅ ነው። ምንም እንኳ በኢየሩሳሌም ላይ የነበረው የአሕዛብ አገዛዝ ለአጭር ጊዜ የተነሣ ቢሆን፥ ክርስቶስ ዳግም እስኪመለስ ድረስ የኢየሩሳሌም ከአሕዛብ መንግሥታት አገዛዝ መሳቀቅ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ የሚሆን ጉዳይ አይደለም። 

በባቢሎን፥ ሜዶን-ፋርስ፥ ግሪክና ሮም መነሣትና መውደቅ እንደታየው፥ አብዛኛው የአሕዛብ ዘመን ቀደም ብሎ ተፈጽሟል። ዳንኤል ምዕራፍ ሁለት ውስጥ እንደተመለከተው በምስሉ እግርና በዳንኤል 7 እሥር ቀንዶች ባሉት አውሬ የተመሰለው የመጨረሻው ደረጃ የሮም መንግሥት ግን በቀጥተኛ ትርጉሙ አልተከናወነም። እንደ 

መጽሐፍ ቅዱስ አገላለጥ፥ እራተኛው አውሬ ከሰማይ በሚመጣው የሰው ልጅ (ክርስቶስ) ይደመሰሳል። ይህም ዳንኤል ምዕራፍ ሰባት ውስጥ እንደተመለከተው ወይም ምዕራፍ ሁለት የናቡከደናፆርን ምስል እንደሚያወድም በተጠቀሰው ድንጋይ ተመስሏል። 

በነዚህ ትንቢቶች ላይ በመመሥረት፥ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች የሮም መንግሥት ወደፊት ዳግም እንደሚነሣ ያምናሉ። መንግሥቱ ቤተ ክርስቲያን ወደ ሰማይ ክተነጠቀች በኋላና ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ዳግም ከመመለሱ በፊት እንደሚነሣ ያስረዳሉ። ይህ ክስተት መጽሐፍ ቅዱስ የፍጻሜው ዘመን (ዳን. 11፡35) እያለ በሚጠራው ጊዜ የሚከናወን ሲሆን፥ ወደ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ከሚያመራው ጊዜ ጋር ስለሚዛመድ፥ በዓለም ታሪከና ትንቢት ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ ይኖረዋል። 

ክርስቶስ ዳግም ወደ ምድር ሲመለስ፥ የአሕዛብ ዘመን ፍጻሜ ይሆናል። በዚህም ጊዜ የዳኑና በሺህ ዓመቱ ዘመን በምድር ላይ የሚገኙ እሕዛብ ከእግዚአብሔር ዘንድ ልዩ በረከትን ይቀበላሉ። ይህን ጉዳይ ወደ ኋላ ስለ ሺህ ዓመቱ መንግሥት በምንነጋገርበት ክፍል እንደገና እናየዋለን። 

በአጠቃሳይ መልኩ፥ አሕዛብን አስመልክቶ የቀረሰው መጽሐፍ ቅዱሳዊ የትንቢት አስተዋጽኦ የዓለም ታሪክ አስተዋጽኦ ነው። ይህም የቀደሙትን አያሌ ክሥተቶች የሚያብራራና በወደፊቱም ላይ ጥላውን የሚጥል ነው። አሁን በዓለም ላይ የሚታዩት ሁኔታዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ጋር የሚስማሙ ሲሆኑ፥ የመጨረሻውን ዘመን ፈጣን ፍጻሜ የሚጠቁሙ ይመስላሉ። ከመጨረሻው ዘመን መከሠት ቀደም ብሎ ቤተ ክርስቲያን ትነጠቃለች። በማጠቃለያው ከዘመኑ ጋር የሚዛመዱ ነገሮች ሁሉ ተግባራዊ ከመሆናቸውም በላይ፥ ክርስቶስ የሺህ ዓመት መንግሥቱን ለመመሥረት ይመጣል። 

አሁን ያለንበት ዘመን ስለ አሕዛብ የተነገረው ወይም በብሉይ ኪዳን የተመለከተው ዕቅድና ትንቢት መፈጸሙን አያመለክትም። ትንቢቱ በበዓለ ኀምሳ የተቋረጠና ከመነጠቅ በኋላ የሚቀጥል ይመስላል። በአሁኑ ጊዜ በዓለም እድገት ውስጥ የሚገኙ ነገሮችም የዘመኑን ፍጻሜ የሚጠቁሙ ይመስላሉ። በዚሁ መሠረት የዘመኑን ወደ ፍጻሜው መቃረብና ስስ አሕዛብ የተነገረው ትንቢት ክንውን እንደገና መጀመር ምልክት ይታያል። ስለሆነም፥ ስለ አሕዛብ የተነገረውን ትንቢት ማጥናቱ፥ የጠቅላሳው ትንቢታዊ ዕቅድ አስፈላጊ ገጽታ ሲሆን፥ እግዚአብሔር ዛሬ ምን በማድረግ ላይ እንዳለና ወደፊትም ምን ለማድረግ እንደሚፈልግ ለመረዳትም ያስችላል።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

43
ትምህርት 43 ከ52

እስራኤል በታሪክና በትንቢት

ሀ. እስራኤል ከሥፍሩ-ዘመናት ጋር ያላት ግንኙነት 

የእስራኤል ታሪክ በዘፍጥረት ምዕራፍ 12 ለአብርሃም በቀረበለት ጥሪ የሚጀምር ሲሆን፥ የብሉይ ኪዳን ዓቢይ አሳብ ነው። አዲስ ኪዳን ወንጌሳትና የሐዋርያት ሥራ ውስጥ፥ ከመጀመሪያው ክፍለ-ዘመን ስለ እስራኤል ተጨማሪ ግንዛቤ ተሰጥቷል። በሌሎች የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥም ስለ እስራኤል የተጠቀሱ ታሪካዊና ትንቢታዊ ነገሮች አሉ። 

ከተስፋ ቃሉ ሥፍረ-ዘመን (ምዕራፍ 20ን ይመልከቱ) ጀምሮ፥ እስራኤል የሁሉም ሥፍረ-ዘመናት ተካፋይ ናት። በተስፋ ሥፍረ-ዘመን ከአብርሃም ጋር የተደረገው ቃል ኪዳን እግዚአብሔር በቀጣይ ትውልዶች ከእስራኤል ጋር ላከናወናቸው ተግባራት ሰፊ መሠረት ጥሏል። የሕግ ሥፍረ-ዘመን በዘፍጥረት ምዕራፍ 19 የሚጀምር ዋነኛ የእስራኤል ሕይወት ነው። ይህ ዘመን የብሉይ ኪዳን ዋና ሥፍረ-ዘመን እንደመሆኑ፥ የእስራኤልን ታሪክ እስከ ጌታ ስቅለት ድረስ የሚወስን በመሆን ኖሯል። ከተመዘገበው የእስራኤል ታሪከ አብዛኛው ከሕግ ሥፍረ-ዘመን ጋር ይዛመዳል። 

በጸጋ ሥፍረዘመን፥ እስራኤል የጸጋን ዕድሎች ማለት ድነትንና የሕይወትን መመሪያ ከአሕዛብ ጋር ትጋራለች። እስራኤል በወደፊቱ ሥፍረ-ዘመን ተስፋ የተገባላትን ምድር በመያዝና ለኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሥነት በመገዛት ዓቢይ ሚና ትጫወታለች። ምንም እንኳ ከአሕዛብ ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ቢሆን፥ እስራኤል ከእብርሃም ጀምሮ እስከ መጨረሻው ባለው የዓለም ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ሚና ትጫወታለች (ለተጨማሪ ማብራሪያ ስፍረ-ዘመናት የሚልውን ርዕስ ይመልከቱ)። 

ለ. እስራኤል ከቃል ኪዳኖች አንጻር 

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ኪዳኖች ከተለያዩ ሥፍረ-ዘመናት ጋር በቅርብ የተያያዙ ናቸው። ዘፍጥረት ምዕራፍ 12 ውስጥ ከሚገኘው የአብርሃም ቃል ኪዳን ጀምሮ በእያንዳንዱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ኪዳኖች ውስጥ እስራኤል ዋነኛ ሚና አላት። (ምዕራፍ 21 ውስጥ ፡፡ቃል ኪዳኖቹ” የሚለውን ይመልከቱ።) 

በእስራኤል ታሪክና በትንቢት ውስጥ አምስቱ ቃል ኪዳኖች ወሳኝ ናቸው። አስቀድሞ እንደተገለጠው፥ አብርሃማዊው ቃል ኪዳን ለእስራኤል ፕሮግራም መሠረት ነው። በሕግ ሥፍረ-ዘመን የሙሴ ሕግ የእስራኤልን ሕይወት እቅድመ ሁኔታነት የሚወሰን ሲሆን፥ ከዘጸአት 19 ጀምሮ ከጠቅላላው ብሉይ ኪዳን ጋር ይዛመዳል። ከነዓንን ይወርሱ ዘንድ የተሰጠው ቃል ኪዳን ከእስራኤል የመሬት ይዞታ ጋር ይገናኛል። የመሬት ይዞታው ተለዋዋጭ ገጽታ ሲኖረውም፥ የኋላ ኋላ በሺህ ዓመቱ መንግሥት ጊዜ የከነዓን ምድር ለዘለቄታው በእስራኤል ቁጥጥር ሥር ይውሳል። ለዳዊት የተገባለት ቃል ኪዳን እስራኤል ከዳዊት ዙፋን ጋር ያላትን ግንኙነት የሚወሰን ሲሆን፥ ወደፊት በሺህ ዓመቱ ዘመን ክርስቶስ በምድር ላይ እንደሚነግሥና፥ ዳዊትም ከሞት ተነሥቶ በልዑልነት የሚገዛ መሆኑን ያመለክታል። ብሉይ ኪዳን ውስጥ የተተነበየው አዲስ ኪዳን እስራኤል በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ከምታገኘው በረከት ጋር የሚገናኝ ሲሆን፥ በሙሴ በኩል ከተሰጠው ቃል ኪዳን ጋር የሚነጻጸርና የሚተካውም ነው። ቃል ኪዳኖች ከእስራኤል ጋር ያላቸው ዝርዝር ግንኙነት ምዕራፍ 21 ውስጥ ተዘርዝሯል። 

ሐ. የእስራኤል ታሪክ በብሉይ ኪዳን 

ምንም እንኳ ትክክለኛው የእስራኤል ታሪክ የሚጀምረው እስራኤል ከተባለው ያዕቆብ ሲሆን፥ በአብዛኛው የአብርሃምንና የይስሐቅን ሕይወት ያካትታል። አብርሃምና ይስሐቅ የያዕቆብ አባትና አያት ናቸው። መጀመሪያ በከለዳውያን ዑር ይኖር የነበረው አብርሃም በሰሜን ምዕራብ ወደምትገኘው ካራኝ ሁለት ሺህ ኪሎ ሜትር ያህል ከእሳቱ ጋር ተጉዞ በመሄድ ሀብታም ከብት አርቢ ሊሆን በቅቷል። አባቱ ከሞተ በኋላ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ፥ ከሚስቱ ሣራና ከወንድሙ ልጅ ሎጥ ጋር ወደ ተስፋይቱ ምድር ተጓዘ። ያም ከካራን ወደ ሰሜን ምዕራብ ተጨማሪ የሁለት ሺህ ኪሎ ሜትር መንገድ ነበር። ከዚያም እግዚአብሔር ሰተስፋይቱ ምድር ከአብርሃም ጋር ይሠራ ጀመር። 

ታላቅ በሆነው አብርሃማዊ ቃል ኪዳን አማካይነት ታላቅ ሰውና የታላቅ ሕዝብ አባት እንደሚያደርገው፥ እንዲሁም በዘሩ በኩል ዓለሙን ሁሉ እንደሚባርክ እግዚአብሔር ለአብርሃም ቃል ገብቶለታል። ቀደም ሲል አብርሃማዊው ቃል ኪዳን ውስጥ እንደተመለከተው (ምዕራፍ 21)፥ እነዚህ የተስፋ ቃሎች በትክክል ተፈጽመዋል። አብርሃምና ሣራ እጅግ ካረጁና የመውለጃ ዕድሜያቸው ካለፈ በኋላ፥ በተአምራዊ መንገድ ይሰሐቅ ተወለደ። ከዚያም በተወሰነው ጊዜ፥ ይስሐቅና ርብቃ ያዕቆብንና ዔሳውን ወለዱ። ከመንትያ ወንድማማቾች መካከል ታናሹ ያዕቆብ የእስራኤል ሕዝብ መሪ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር መረጠው። 

የአብርሃም፥ የይስሐቅና የያዕቆብ ታሪክ ከዘፍጥረት 12-50 የተዘረዘረ ሲሆን፥ ከዚህ የምንረዳው እግዚአብሔር በዚህ ታሪክ ላይ የሰጠውን ትኩረት ታላቅነት ነው። በተለይም ጠቅላሳው የፍጥረት ታሪክ በሁለት ምዕራፎች (ዘፍጥ. 1-2)፥ ፀኃጢአት የመውደቅ ሁኔታም በአንድ ምዕራፍ (ዘፍጥ. 3) ብቻ ተጠቃሎ እንደቀረበ ስንመለከት፥ የነአብርሃም ታሪክ ዋነኛነት በግልጥ ይታያል። ከመለኮታዊ ዕይታ አንጻር፥ የእስራኤል ታሪክ ለጠቅላላው ታሪክ ቁልፍ ነው። 

ዘፍጥረት 15፡13-14 ውስጥ ለአብርሃም ከተሰጠው ትንቢት ጋር በሚስማማ መልኩ፥ በረሃብ ወቅት እስራኤላውያን ወደ ግብፅ ወረዱ። ወደዚያ የሚሄዱበት መንገድ የተጠረገላቸው የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣን በነበረው ዮሴፍ አማካይነት ነበር። ግብፅ አብርሃምንና ቤተሰቡን በመልካም ሁኔታ ተቀብላ ዮሴፍ በሕይወት በኖረባቸው ጊዜያት ሁሉ ስትንከባከባቸው ቆየች። ይሁን እንጂ፥ የተደረገው የአገዛዝ ለውጥ የድሉት ማዕረጋቸውን ነጥቆ፥ ባሪያዎች ስላደረጋቸው፥ እስራኤሳውያን ላአያሌ መቶ ዓመታት የሥቃይ ሕይወት ኖሩ። በባርነታቸው ወደ ጌታ በጮኹ ጊዜ፥ ጌታ ሕዝቡን ወደ ተስፋይቱ ምድር ይመራቸው ዘንድ ሙሴንና ኢያሱን አስነሣቸው። ምንም እንኳ እስራኤላውያን በቃዴስ በርኔ እግዚአብሔርን ባይታዘዙት (ዘኁ. 14)፥ እና ከዚህም የተነሣ ለአርባ ዓመታት በምድረ በዳ ሲቅበዘበዙ፥ በመጨረሻ ግን እግዚአብሔር ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ምድሪቱን እንዲይዙና ከሙሴ ሞት በኋሳ ዮርዳኖስን ተሻግረው አብዛኛውን ክፍል እንዲቆጣጠሩ አስችሏቸዋል። 

እስራኤላውያን ሰኢያሱ ዘመን ወደ ተስፋይቱ ምድር ተመልሰው እንደ አንድ አገር ቢበለጥጉም፥ መጽሐፈ መሳፍንት ውስጥ እንደተመለከተው በሥነ-ምግባራዊ ሕይወታቸው ከእግዚአብሔር ተለይተው ተዋረዱ። 

በዚህም ጊዜ እግዚአብሔር ነቢዩ ሳሙኤልን አስነሣ። እርሱም በአብዛኛው የእስራኤልን መንፈሳዊ ሕይወት ዳግም በመገንባት፥ ሰሳኦል፥ በጻዊትና በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት ለነበረው ክብር መሠረት ጥሏል። የመጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ የነበረው ሳኦል ባይሳካለትም፥ እርሱን የተካው ዳዊት ታላቅ የጦር ሰው በመሆኑ የተስፋይቱ ምድር አካል የሆኑትን ሰፊ ግዛቶች ላመያዝ ችሏል። 

የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ለአብርሃም የተነገሩትን አብዛኛዎቹን አካባቢዎች ማለት፥ ከግብፅ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ እስኪቆጣጠር ድረስ ድንበሩን አሰፋ። ሚስቶችን እንዳያበዛና ሰፈረሶች ብርታት እንዳይደገፍ እግዚአብሔር የሰጠውን ትእዛዝ አለመስማቱ (ዘዳግ. 17፡16-17)፥ መንግሥቱ እንዲከፋፈልና ከርሱ በኋላ የእስራኤል ኃይል በፍጥነት እንዲንኮታኮት ምክንያት ሆኗል። የሰሎሞን ልጆች ያደጉት ለእግዚአብሔር ሕግ ግድ ባልነበራቸው አረማውያን ሚስቶቹ ነበር። ከርሱ ሞት በኋላ ብዙም ሳይቆይ፥ እሥሩ የስሜን ነገዶች (እስራኤል) ለብቻቸው ተገንጥሰው በክፉ ነገሥታት ሲመሩ ኖረዋል። እነዚህ ወገኖች በ721 ዓ.ዓ. በአሦራውያን እንዲማረኩ እግዚአብሔር ፈርዶባቸዋል። ሁለቱ የደቡብ መንግሥት ነገዶች (ይሁዳ)፡ምንም እንኳን አንዳንድ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረባቸው ነገሥታት የተነሡላቸው ቢሆንም፥ እንደ እስራኤል ሁሉ በኃጢአት ወጥመድ መያዛቸው አልቀረም። ከዚህም የተነሣ፥ በ605 ዓ.ዓ. በባቢሎናውያን ምርኮ ተወሰዱ። 

ኤርምያስ 29፡10 ውስጥ በተሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት፥ ከሰባ ዓመቱ የባቢሎናውያን ምርኮ ፍጻሜ በኋሳ እስራኤል ወደ ምድሯ ተመለሰች። መጽሐፈ ዕዝራ የሕዝቡን መመለስና ቤተ መቅደሱን ለመገንባት ለሀያ ዓመታት ያደረጉትን ጥረት ይገልጣል። ነህምያ ደግሞ ከአንድ መቶ ዓመታት ያህል ጊዜ በኋላ የኢየሩሳሌምን ቅጥሮችና የከተማይቱን ዳግም መታነጽ በመግለጥ ታሪኳን ይቋጫል። ይሁንና፥ እስራኤላውያን ወደ ምድራቸው ቢመለሱም፥ እግዚአብሔርን ባለመከተላቸው ሳቢያ ለ200 ዓመታት ሰሜዶንና በፋርስ አገዛዝ ሥር ቆይተዋል። ታላቁ እስክንድር በ323 ዓ.ዓ. ከሞተ በኋላ ደግሞ ከሦሪያና ከግብፅ ጋር ይዋጉ ጀመር። 

በ242 ዓ.ዓ. ኃያሉ የሮማውያን አገዛዝ ሲሲሊን በመውረር የመስፋፋት ዘመቻውን ተያያዘው። ኢየሩሳሌም ራሷ በ63 ዓ.ዓ. ታምፒዬስ በተባለው የሮም ጄኔራል በቅኝ ተያዘችና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አይሁዶችን በባርነት ያጋዙ ሮማውያን ጭካኔ 

ማነጣጠሪያ ሆነች። በኋላ በሮማውያን ባለሥልጣናት ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቀለ። በመጨረሻም (በ70 ዓ.ም.) የኢየሩሳሌም ከተማ ተደመሰሰች፥ እስራኤላውያንም አገራቸውን ጥለው በዓለም ሁሉ እንዲበተኑ ተደረገ። እስከ ሀያኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ እሰራኤላውያን ወደ አገራቸው ለደመሰሰና ምድራቸውን እንደ አገር ለማደራጀት አልቻሉም ነበር። በ1948 ዓ.ም. ነው እንደ አንድ ፖለቲካዊ መንግሥት እውቅና ያገኙት። 

መ. የእስራኤል ታሪክና የተፈጸመ ትንቢት 

የብሉይ ኪዳን ታሪክ በአብዛኛው የታላላቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንቢቶች ፍጻሜ ነው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ትንቢቶች ቃል በቃል ተፈጽመዋል። ለአብርሃም በተሰጡት ትንቢቶች መሠረት፥ እስራኤል ታላቅ እገር ሆነች። ብሉይ ኪዳን እስራኤላውያን ከምድራቸው እንደሚወጡ የሚናገሩ ሦስት ትንቢቶችን ያስተላለፈ ሲሆን፥ እነዚህም በሚከተለው መንገድ ተፈጻሚነትን አግኝተዋል፡- (1) ወደ ግብፅ መሄዳቸው፥ ለባርነት መዳረጋቸውና ተለቀው መመለሳቸው፥ (2) በባቢሎናውያኝና አሦራውያን ምርኮ ተወስደው ከሰባ ዓመት በኋላ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፥ (3) በ70 ዓ.ም. ኢየሩሳሌም በተደመሰሰች ጊዜ ከምድራቸው ተበትነዋል። የእስራኤላውያን ምድራቸውን መያዝና እንደገና የመነጠቅ ሰፊ እንቅስቃሴ ለጠቅላላው ታሪካቸው ጠቃሚ መነሻ ፈጥሯል (ዘፍጥ. 15: 13-16፤ ዘዳ. 28፡62-67፤ ኤር. 25 ፡11-12፤ በተጨማሪም ዘሌ. 26፡3-46፤ ዘዳ. 30፡1-3፤ ህ . 1፡8፤ መዝ. 106፡1-48፤ ኤር. 9፡16፤ 18፡15-17፤ ሕዝ. 2 ፡14-15፤ 20፡23፤ 22፡15፤ ያዕ. 1፡1)። 

ስለ ያዕቆብ ልጆች ባሕርይና ፍጻሜ የተሰጡት ትንቢቶች ለእስራኤል ታሪክ በጣም አስፈላጊዎች ናቸው (ዘፍጥ. 49፡1-28)። እግዚአብሔር ከአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት ብሉይ ኪዳን ውስጥ ብዙ ትንቢቶች ተሰጥተዋል። 

ሌላው የትንቢትና ፍጻሜው ዋና ጉዳይ ከዳዊት መንግሥት ጋር ይዛመዳል። ለዳዊት ከተገባለት ቃል ኪዳን ጋር በተያያዘ ለርሱና ለዘሩ በተገባለት ቃል ኪዳን መሠረት የመንግሥት ዙፋን ለዘላለም ከቤቱ እንደማይጠፋ ተስፋ ተሰጥቶታል (2ኛ ሳሙ. 1፡16፤ መዝ. 89፡35-36፤ ኤር. 33፡21፤ ዳን. 7፡14)። እግዚአብሔር ከሳኦል፥ ዳዊትና ሰሎሞን፥ እንዲሁም ከቀጣዮቹ የእስራኤልና የይሁዳ መንግሥታት ጋር የገባቸው የበረከትና የመርገም ቃል ኪዳኖች በቀጥታ ተፈጽመዋል። 

ሠ. ስለ እስራኤል 490 ዓመታት የተነገረ ትንቢት 

[* “ሻቡአ” የሚለው የዕብራይስጥ ቃል በብሉይ ኪዳን የጭሰሳት ስብስብ” የሚል አሳብ አለው። ይህ ቃል በብሉይ ኪዳን ውስጥ 20 ጊዜ ተጠቅሷል። ከእነዚህ ሦስት ጊዜ “ሰባት ስብስብ” የሚል ትርጉምን “ቀን” ከሚል ቃል ጋራ በመያያዝ ተሰጥቶታል (ሕዝ. 45፡21፤ ዳን. 10፡2፥3)። ስድስት ጊዜ ደግሞ “በሳምንት ያሉን ሰባት ቀናትን” በማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል (#ፍጥ. 29፡27 ፥ 28፤ ዘሌዋ. 12፡5፤ ዘዳ. 16፡9፤ ኤር. 5፡24)። አምስት ጊዜ ደግሞ የሰባቱ ሱባኤ ሰዓል* የሚገልጥ ሆኖ እናገኛለን (ዘፀ. 34፡22፤ ዘኁ. 28፡26፤ ዘዳ. 16፡10፥ 16 2ኛ ዜና 8፡13)። 

ምንንም ሳያመለክት የሰባት ስብስብ” የሚል ትርጉምን ሰባት ጊዜ ተጠቅሷል (ዳን. 9:24-27)። ከእነዚህ ክፍሎች የቃሉን ትርጉም የዐውደ ምንባቡ ይዞት ነው የሚወስነው** 

ሰአጠቃላይ የሻሱአ” የሚለው ቃል ሱባኤ ማለት ሲሆን ጥሬ ቃሉ ያዘለው አሳብ ግን የሰባት ስብስብ” ሆኖ፥ ትክክለኛው ትርጉም ግን በዐውደ ምንባቡ የሚወሰን ነው። ዳንኤል 9፡24-27 ውሰጥ ይህ ቃል አሎሳኤ” ተብሎ የተተረጎመ ሲሆን፥ ፅንሰ-አሳቡ ግን ሰባት የዓመታት ስብስብን ያመለክታል። በዚህ ክፍል ነቢዩ የሚናገረው ስለተለያዩ ሰባት ዓመታት ነው (ማለትም 490 ዓመታት)። በ1980 ዓ.ም. ሰአማርኛ የታተመው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም እንደዚህ ነው የሚተረጎመው። ለዚህ አተረጓጎም ምክንያቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡–1, ዳንኤል 9፡24-27 ውስጥ ያለውን አሳብ ከማንሣቱ በፊት ሰ9፡2 ስለ ናዓምታት” ተናግሯል። ይህም ኤርምያስ 25፡11 እና 29፡10)፡፡ ውስጥ የተጠቀሰውን የምርኮ ወቅት የሚያመለክት ነው። ይህ ምርኮ እስራኤል የጌታን ሕግ፥ ሰትለይም የስድስት ዓመቱ ምድሩን የማሳረፍን ሕግ ሳልመጠበቋ የደረሰባት ቅጣት ነው (ዘሌዋ. 25፡24 4፥ 8፣ 26፡34፥ 43)። እስራኤል ይህን ሕግ ሰባ ጊዜ መተላለፏን ስናሰላ 490 ዓመት ያህል ይሆናል። ስለዚህ ቅጣታቸው ለሰሳ ዓመት ያህል ነበር። 

2. ዳንኤል 9፡24-27 ውስጥ የተጠቀሰው ሁኔታ 490 ቀናትኝ የሚያመለክት ጊዜ ሊሆን አይችልም። 3. በዳንኤል 9፡27 ውዕጥ ክሲዩ ኪዳኑ “ሰሰባኛው ቡአ አጋማሽ” እንደሚፈርስ ይተነብያል። ይህ (4ዓመታትን” እንደሚያመለክት ተደርጎ ከተወሰደ ዳንኤል 7፡25 እና 12፡7 ውስጥ እንዲሁ ከራእይ 12፡14 ውስጥ ካለው አሳብ ጋር የሚስማማ ይሆናል። 

በማጠቃለል ሳቡአ በዳንኤል 9 መሠረት በአመዛኙ የሚያመለክተው የሰባት ዓመታት ስብስብ” ነው። ከዚህ ሌላ ምንም ዓይነት ትርጓሜ ክፍሉ ጋር የሚሄድ አይሆንም፤ ይህ ቢሆንም የአማርኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ አጠቃቅም ለመከተል ሰባት ሰብስብ” የሚለው አሳብ በተቀረው በዚህ ምዕራፍ ክፍል ሰባት” ከማለት 

“ሱባዔ” በሚለው ቃል ተተክቷል። ** ይህ “እር”” ከሚለው ቃል ትርጓሜ ጋር ይመሳሰላል። “አሦር” የሚለው የዕብራይስጥ ቃል በአብዛኛው “አሥር ቀን” የሚል ትርጓሜ ይሰጠዋል። ይህ ቃል ብሉይ ኪዳን ውስጥ ከተጠቀሰባቸው 16 ስፍራዎች 13 ያህሉ ያሉበት ዕውደ ምንሳብ እንዲህ ያለ ትርጓሜ እንዲሰጠው ያደርጉታል። ሆኖም ሦስት ጊዜ የሙዚቃ መሣሪያን አስመልክቶ “አምሮ፡ይባል አሥር አውታር” የሚል ትርጉምን ይዟል (መዝ. 33፡2፣ 9፡3፤ 144፡9)። “አሦር፡፡ልክ እንደ ወላቡአ” ስብስብን የሚያመለክት ቃል ነው። ስለዚህ የአሥር ስብስብ” የሚል አሳብ አለው። በመሆኑም እንደ ዐውደ ምንባሱ ትርጉሙም ይለያያል።] 

በዳንኤል በኩል ከተሰጡት ዓበይት ትንቢቶች አንዱ፥ ዳንኤል 9፡24-27 ውስጥ የሚገኘው ነው። በዚህ ስፍራ መልአኩ ገብርኤል ለዳንኤል በገለጠው መሠረት የእስራኤል የወደፊት ታሪክ “ሰባ ሱባዔ”* ወይም ሰባ ሰባቶችን (490 ዓመታት) የሚያካትት ይሆናል። “ዓመፃን ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሥርይ፥ የዘላለምን ጽድቅ ያገባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ሳይ ሰባ ሱባኤ ተቆጥሮአል” (ዳን. 9፡24)።

ትንቢቱ የሚጀምረው ኢየሩሳሌምን ለማደስና ለመገንባት ትእዛዝ በሚወጣበት ጊዜ ሲሆን (ዳን. 9:25)፥ መሢሕ የሆነው ልዑል ከመምጣቱ በፊት ከጠቅላላዎቹ 490 ዓመታት 483ቹ ይፈጸማሉ። የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን ይህን ምንባብ በተለያየ መንገድ ቢፈቱትም፥ ከሁሉም የሚሻለው፥ ይህንኑ የ490 ዓመታት ክፍለ ጊዜ ህምያ ኢየሩሳሌምን ዳግም ከገነባበት 445ዓ.ዓ. መጀመሩ ይመስላል። ይህ የሚፈጸመው ክርስቶስ በመስቀል ላይ በሚሠዋበት በ32 ዓ.ም. ገደማ ነበር። በቅርቡ የተደረገው ምሁራዊ ትንታኔ ክርስቶስ የሞተበትን ጊዜ 33 ዓ.ም. ቢያደርገውም፥ ብዙዎቹ ተንታኞች ግን 30 ዓ.ም. ነው ብለዋል። 

በዳንኤል ትንቢት መሠረት ከ483 ዓመታት በኋላ መሞት ነበረበት። ይህም የሰባው ዓመት ሱባዔን በተመለከተ ያልተፈጸመ ሰባት ዓመት እንዳለ ያሳያል (ዳን. 9፡26)። የኢየሩሳሌም መፍረስ እንደተተነበየው በ70 ዓ,ም ኢየሩሳሌም በፈረሰችበት ወቅት ተፈጽሟል። 

በ483ቱ ዓመታት ወይም 69ኙ “ሳምንታት” ሱባዔ እና በመጨረሻዎቹ ሰባት ዓመታት ጅማሬ ወይም በሰባተኛው “ሳምንት” መካከል ረጅም ጊዜ መኖሩ ዳንኤል ትንቢት ውስጥ ተመልክቷል። የመጨረሻው ሳምንት ከተማይቱን ካጠፉት ሕዝቦች የወደፊት ልዑል ጋር የተደረገ ቃል ኪዳንን የሚያመለክት ይመስላል። የኢየሩሳሌምን ከተማ የደመሰሷት ሮማውያን በመሆናቸው፥ የሚመጣው አለቃ” (ዳን. 9፡26) የሚታደሰው የሮም መንግሥት ገዥ ሳይሆን አይቀርም። ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን ይህ የሚፈጸመው፥ ወደፊት ቤተ ክርስቲያን ከተነጠቀች በኋላ ነው ይላሉ። 

ዳንኤል 9፡27 ውስጥ እንደተመለከተው፥ ይህ አለቃ ከእስራኤል ጋር ለሰባት ዓመታት የሚቆይ ቃል ኪዳን ያደርጋል። ቃል ኪዳኑ በሱባዔው መካከል ስለሚፈርስ፥ የመጨረሻዎቹ ሦስት ተኩል ዓመታት ለእስራኤል የመከራና የስደት ጊዜ ይሆናሉ። ይህ ክፍለ-ጊዜ ራእይ 6-18 ውስጥ የተመሰከተው ትንቢት ርእሰ ጉዳይ ሲሆን፥ ራእይ 19 ውሰጥ በተገለጠው የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ይጠናቀቃል። የሚመጣው ገዥ መሥዋዕትና ቁርባን አስቀርቶ ቤተ መቅደሱን እንደሚያስረክስ መተንበዩ ልብ ሊባል የሚገባ ነገር ነው። ይህ የሚያመለክተው፥ ወደፊት ኢየሩሳሌም ከተማ ውስጥ ቤተ መቅደስ እንደሚሠራና መሠረታውያን አይሁዶች ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት በፊት የሙሴ የመሥዋዕት ሥርዓትን የሚጀምሩ መሆኑን ነው። 

የመጀመሪያዎቹ 483 ዓመታት እንደተተነበዩ በቃል መፈጸማቸው ጠቃሚ ጉዳይ ነው፡ዳንኤል 9፡25 ውስጥ እንደተመለከተው፥ ኢየሩሳሌም ሰመጀመሪያዎቹ 49 ዓመታት ውስጥ እንደገና ተገንብታለች። ከ483 ዓመታት በኋላ መሢሑ ተገድሏል። የመጨረሻው ሱባዔ ክስተቶች ገና ወደፈት የሚፈጸሙና ወደ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት የሚያመራውን 

የጊዜ ቅደም ተከተል የሚያሰናዱ ናቸው። 

ረ. ስለ መሢሑ ምጽአት የተነገረ ትንቢት 

የብሉይ ኪዳን ነቢያት የመሢሑን ሁለት ምጽአቶች ሊለዩ እንዳልቻሉ ከ1ኛ ጴጥሮስ 1፡10-11 እንረዳለን። በእግዚአብሔር ምክር ውስጥ የአሁኑ ዘመን ፍጹም ስውር ስለነበር፥ በክርስቶስ የመጀመሪያ ምጽአት የተፈጻሙትና ገና በዳግም ምጽአቱ የሚፈጸሙ ሁነቶች የአፈጻጻም ጊዜ ለብሉይ ኪዳን ነቢያት ግልጥ ሆኖ አልታያቸውም። 

ኢሳይያስ 61፡1-2 ይህን ሁኔታ ያብራራዋል። ክርስቶስ ይህን ምንባብ ቅፍርናሆም ምኩራብ ውስጥ ስለ መጀመሪያ ምጽአቱ የተጠቀሱትን ነገሮች (ሉቃስ 4፡18-21) ካነበበ በኋላ፥ በዳግም ምጽአቱ የሚፈጸሙትን በዝምታ አልፏቸዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ፥ መልአኩ ገብርኤል ስለ ክርስቶስ አገልግሎት ሲናገር፥ የመጀመሪያውንና ሁለተኛውን ምጽአቶች ተግባራት አንድ ላይ አጣምሮ ገልጧቸዋል (ሉቃስ 1፡31-33)። 

ክርስቶስ ብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ውስጥ ዝም እንደሚል የመሥዋዕት በግ (ኢሳ. 53፡1-12) እና ድል እንደሚነሣ ገናና የይሁዳ ነገድ እንበሳ (ኢሳ. 11፡1-12፤ ኤር. 23፡5-6) ተገልጧል። የብሉይ ኪዳን ነቢያት እነዚህን ሁለት የተራራቁ የትንቢት መሥመሮች በመመልከት፥ ይህ ሁሉ መች ይፈጸም ይሆን? ብለው ማሰባቸው አያስገርምም (1ኛ ጴጥ. 1፡10-11)። 

በትንቢት እንደተነገረው፥ መሢሑ ከይሁዳ ነገድ (ዘፍጥ. 49፡10)፥ ከዳዊት ቤት (ኢሳ. 11፡1፤ ኤር. 33፡23)፥ ከድንግል የመወለድ (ኢሳ. 7፡14)፥ በይሁዳ ቤተልሔም የሚወለድ (ሚክ. 5፡2)፥ የመሥዋዕትነት ሞት የሚሞት (ኢሳ. 53፡1-12)፥ የሚሰቀል (መዝ. 22፡1-21)፥ ከሞት የሚነሣ (መዝ. 16፡8-11) እና በሰማይ ደመና (ዳን. 7፡13) ዳግም ወደ ምድር የሚመለስ መሆኑ ተገልጧል (ዘዳ. 30፡3)። የናዝሬቱ ኢየሱስ ማንም ሊፈጽም በማይቻለው መልኩ ስለ መሢሑ የተነገሩትን ትንቢቶች ሁሉ ፈጽሟል። የቀሩትንም ወደፊት በዳግም ምጽአቱ ይፈጽማቸዋል። 

ሰ. ስለ እስራኤል በመጨረሻ መበተንና መሰብሰብ የተነገረ ትንቢት 

እስራኤልን አስመልክቶ ብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚገኙት እጅግ ጠቃሚ ትንቢቶች በመጨረሻ መበተኗንና መሰብሰቧን የሚመለከቱ ናቸው። እስራኤላውያን ሁሉ ስለ ኃጢአታቸው በተተነበየባቸው ብሔራዊ ቅጣት መሠረት የሰሜኑ መንግሥት በአሦር፥ የደቡቡ በባቢሎን ምርኮ በመወሰድ ወደተለያዩ የዓለም ክፍሎች ተበትነዋል። ይህ የብዙ ትንቢቶች ፍጻሜ ነበር (ዘሌ. 26፡32-39፤ ዘዳ. 28፡63-68፤ ነህ. 1፡8፤ መዝ. 44፡11፤ ኤር. 9፡16፤ 18፡15-17፤ ሕዝ. 12፡14-15፤ 20፡23፤ 22፡15፤ ያዕ . 1፡1)። 

ለብዙ መቶ ዓመታት ብትበተንም እንኳ የእስራኤል ብሔራዊ ማንነት አልጠፋም (ኤር. 31፡36፤ ማቴ. 24፡34)። መሢሑ በመጀመሪያው ምጽአቱ ለመሰብሰባቸውና ለመንግሥታቸው ክብር ያቀረበላቸውን መለኮታዊ ችሮታ አልተቀበሉም (ማቴ. 23፡37 39)። በረሃ ለበረሃ መቅበዝበዛቸው ባበቃበት ቃዴስ በርኔ ላይ (ዘኍ. 14፡1-45)፥ ቅጣታቸው እንደገና ተራዘመ። ጌታ ዳግም እስኪመጣ ድረስም የሚቀጥል ይሆናል። ያኔ ያሕዌ ሕዝቡን ወደራሳቸው ምድር በመሰብሰብ፥ የገባላቸውን ቃል ኪዳናት ባርኮትና ክብር ሁሉ ያቀዳጃቸዋል (ዘዳ. 30፡1-10፤ ኢሳ. 11፡11-12፤ ኤር. 23፡3-8፤ ሕዝ. 37፡21-25፤ ማቴ. 24፡31)። 

ሽ. ስለ መጨረሻው ዘመን የተነገረ ትንቢት 

በዳንኤል 9፡27 ላይ በተመሠረተ አጭር ጥናት እንደተገለጠው፥ እስከ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ድረስ በሚዘልቁት የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች ውስጥ እስራኤል አስደናቂ ሚና ትጫወታለች። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን፥ የእስራኤልን የወደፊት ሁኔታ በተመለከተ በዘመኑ መጨረሻ አራት ዓበይት እንቅስቃሴዎች ይኖራሉ። 

1. እስራኤል እንደ ፖለቲካዊ መንግሥት ዳግም እንደምትቋቋም ተገልጧል። “ከሚመጣው አለቃ” ጋር ቃል ኪዳን ለማድረግ ይቻላት ዘንድ፥ እንደ ፖለቲካዊ መንግሥት እንደገና መቋቋም ያስፈልጋታል። ይህም በሚያስደንቅ ሁኔታ እንደ አገር እውቅናና ተስፋ ከተገባለት ምድር የተወሰነ ክፍል ባገኘችበት ሚያዝያ 1948 ዓ.ም. (እ.አ.አ.) ተፈጽሟል። ከዚያ በኋላ በነበሩት ዓመታት፥ ዳርቻዋ እየሰፋ ከመሄዱም በላይ ኃይሏም እየተጠናከረ መጥቷል። ምንም እንኳ ዛሬ እስራኤል አነስተኛ አገር ብትሆን፥ በዓለም ጉዳዮች ላይ ዋና ስፍራ ለመያዝ በቅታለች። ይህ ወደፊት ለሚፈጸሙት ሌሎች ትንቢቶች መግቢያ ነው። 

2. ዳንኤል 9፡27 ውስጥ እንደተገለጠው፥ እስራኤል ከሜድትራኒያን የሮም እሕዛብ እለቃ ጋር ለሰባት ዓመታት ቃል ኪዳን ታደርጋለች። በዚህም ሠላምና ዋስትና ወደምታገኝበት የቃል ኪዳን ክፍለ-ጊዜ ትዘልቃለች። በዚህ ጊዜ ሌሎችም አይሁዶች ወደ ተስፋይቱ ምድር እንደሚመለሱና፥ አገሪቱ መዋለንዋያዊም ሆነ ፓለቲካዊ የብልጥግና እርከን ላይ እንደምትወጣ አይጠረጠርም። 

3. ይሁን እንጂ፥ የተገባው ቃል ኪዳን ከስት ዓመት ተኩል በኋላ ይፈርስና እስራኤል ከምገስ ይልቅ ስደት ይገጥማታል። ይህ “የያዕቆብ የመከራ ቀን” (ኤር. 30፡7)፥ የተባለው ታላቅ መከራ ነው (ዳን. 12፡1፤ ማቴ. 24፡21፤ ራእይ 7፡14)። በሚቀጥሉት ሁለት ምዕራፎች በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ እሳብ ይቀርባል። 

4. በሺህ ዓመቱ መንግሥት የእስራኤል ስከብር መመለስ የክርስቶስን ዳግም ምጽአት ተከትሎ የሚከናወን ሲሆን፥ ክርስቶስ በምድር ላይ በሚገዛበት የሺህ ዓመት ጊዜ ሁሉ ይቀጥላል። 

የእስራኤልን መመለስ አራት ደረጃዎች የመረዳቱ አስፈላጊነት። የመጀመሪያው ደረጃ ከዚህ ቀደም ከመፈጸሙና ሁለተኛው ደረጃ ምናልባትም ቤተ ክርስቲያን እስከምትነጠቅበት ጊዜ ድረስ የሚዘገይ ከመሆኑ እውነት አንጻር ሊታይ ይችላል። ለማንኛውም እስራኤል ከፍተኛ ሚና ለምትጫወትበት የመጨረሻ ዘመን ክስተቶች ሁኔታዎች በመመቻቸት ላይ ናቸው። 

ቀ. ስለ መሢሐዊው መንግሥትና የእግዚአብሔር ቀን የተነገረ ትንቢት 

ይህን እሳብ በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሰፈሩት ጥቅሶች መሐዊውን መንግሥት የሚመለከተውን ያህል ብሉይ ኪዳን ትንቢት ውስጥ የተተኮረሰት ጉዳይ የለም። እስራኤል ላይ እንደሚደርሱ ከተተነበዩት ቅጣቶች ሁሉ ባሻገር፥ ሕዝቦቿ ዳግም ወደ አገራቸው ሲሰበሰቡ የምትጎናጸፈው ክብር ይገኛል። ይህም በመሢሑ ንጉሣቸው የከበረ ዘመን የሚሆንና ከቁጥር ሁሉ ከላቀ በረከት ጋር የሚመጣ ሲሆን፥ ራእዩ ለነቢያት ሁሉ ተሰጥቷል። ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ እስራኤላውያን ከምድራቸው ተበትነው ለብዙ ምዕት ዓመታት እንደተሠቃዩ ሁሉ፥ በተቤዠችውና በከበረችው ምድር አስደናቂ በረከቶችን ወደ መቀበሉ ተሐድሶ የሚደርሱትም ሰተምሳሌታዊ ሳይሆን በቀጥተኛ መልኩ ነው (ኢሳ. 11-12፤ 24፡22-27፡13፤ 35፡1-10፤ 52፡12፥ 54-55፤ 59፡20-66፡24፤ ኤር. 23፡3-8፤ 31፡1-40፤ 32፡37-41፤ 33፡1-26፤ ሕዝ. 34፡11-31፤ 36፡32-37፡28፤ 40፡1-48፡35፤ ዳን. 2፡44-45፣ 7፡14፤ ሆሴ. 3፡4-5፤ 13፡9-14 :9፤ ኢዩ. 2፡28-3፡21፤ አሞጽ 9፡11-15፤ ሰፎ. 3፡14-20፤ ዘካ. 8፡1-22፤ 14፡9-21)። 

የእግዚአብሔርን መንግሥት በተመለከተ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ብዙውን ጊዜ የንጉሡ መመለስ ትንቢቶች አካል ናቸው። እነዚህ ሁለት ጉዳዮች በአንድ ላይ ሲዋሐዱ “የእግዚአብሔር ቀን” የሚል አሳብ ይሰጡናል። ይህ ከቤተ ክርስቲያን መነጠቅና ያን ተከትሎ በምድር ላይ ከሚፈጸሙ ፍርዶች በመጀመር እስከ የሺህ ዓመቱ ፍጻሜ የሚዘልቅ ረዥም ክፍለ ጊዜ ነው (ኢሳ. 2፡10-22፤ ዘካ. 14)። 

የእግዚአብሔር ቀን የቤተ ክርስቲያን መነጠቅን ተከትሉ ወዲያው የሚመጣ መሆንን የሚያመለክቱ ጥቆማዎች አሉ። ስለሆነም፥ የእግዚአብሔር ቀን ዓበይት ክስተቶች፥ ታላቁን መከራና ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት በፊት፥ ብሎም በዳግም ምጽአቱ ወቅት የሚሰጡትን ፍርዶችና ጠቅላላውን የሺህ ዓመት መንግሥት የሚያካትት ይመስላል። 

ብሉይ ኪዳን በተጠናቀቀበት ወቅት ብዙዎቹ ታላላቅ ትንቢቶች እስካልተፈጸሙ፥ የብሉይ ኪዳንን አያሌ ትንቢቶች ፍጻሜና ገና የሚፈጸሙትንም ትንቢቶች የተሟላ ዘገባ ለማቅረብ የአዲስ ኪዳን ተጨማሪ መገለጥ ወሳኝ ነው። የእስራኤል ታሪክ በአብዛኛው በትንቢትም ሆነ በታሪክ ተፈጽሟል። ገና ወደፊት የሚፈጸሙ ታላላቅ ክስተቶችም እሱ። እስራኤል የራሷ ወደሆነው እንደገና የምትመጣበት ጊዜ እንደቀረበ የሚያመለክቱ መረጃዎች ብዙ ናቸው። ይህን በተመለከተ፥ በሚቀጥሉት ምዕራፎች ዝርዝር አሳቦች ቀርበዋል።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

44
ትምህርት 44 ከ52

ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት ቀደም ብለው የሚከናወኑ ሁኔታዎች

ሀ. የአሁኑ ዘመን ዓበይት ሁኔታዎች 

ባለንበት የጸጋ ዘመን ብዙ ትንቢቶች በመፈጸም ላይ ናቸው። የዘመኑ አጠቃላይ ሁኔታም ማቴዎስ ምዕራፍ 13 ውስጥ በሚገኙ ሰባት ምሳሌዎች ተብራርቷል። እንደ መግቢያ በተቆጠረው የዘሪው ሰው ምሳሌ፥ ሰዎች የእግዚአብሔርን እውነት የሚቀበሉባቸው የተለያዩ ሁኔታዎች ተገልጠዋል። እውነት አንዳንድ ጊዜ ጠጣር መንገድ ዳር ይወድቅና የወፎች ቀለብ ይሆናል። ሌላው እውነት ደግሞ ብዙ አፈር በሌለው ጭንጫ መሬት ላይ ይወድቅና ገና በመብቀል ላይ ሳለ ሥሩን ለመስደድ ባለመቻሉ ይደርቃል። የቀረው በጥሩ መሬት ላይ ሲዘራም፥ በእሾህ ይታነቅና ፍሬ አልባ ይሆናል። ከዘሩ የተወሰነው ክፍል ብቻ መልካም መሬት ላይ ወድቆ መቶ፥ ስድሳ ወይም ሠላሳ ፍሬ ይሰጣል (ማቴ. 13፡1-9፥ 18-23)። 

በስንዴ መካከል የተዘራው እንክርዳድ ምሳሌ፥ እስከ መከር ጊዜ ድረስ ሳይፈረድበት የሚቆየውን አደገኛ የውሸት እምነት ያመለክታል (ቁ. 24-30፥ 36-43)። የሰናፍጭ ቅንጣት ምሳሌ በበኩሉ የክርስቲያኑ ማኅበረሰብ በፍጥነት ከትንሽ ወደ ላቀ እንቅስቃሴ የሚደርስ መሆኑን ነው የሚገልጠው (ቁ. 31-32)። የእርሾው ምሳሌ ከመልካሙ ምግብ ጋር ተቀይጦ ሁሉንም ስለሚያበላሸው ክፋት ይናገራል (ቁ. 33-35)። ማቴዎስ 13፡44 ውስጥ የተጠቀሰው የተሰወረው መዝገብ፥ ምናልባት ሰአሁኑ ዘመን በዓለም ዙሪያ የተበተኑትን እስራኤላውያን የሚያመለክትና ሕዝቡ በከርስቶስ ሞት ዳግም የተገኘ መሆኑን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል። እጅግ የተወደደው ዕንቁ (ቁ. 45፥ 46) ምሳሌ ደግሞ፥ ክርስቶስ ስለሞተላት ቤተ ክርስቲያን ያመለክታል። እርሷም በግልጥ የምትታይ ስትሆን፥ እስራኤል ግን እንደ ብሔርነቷ ከዚህ ሁኔታ ስውር ሆና ያለች ትመስላለች። ከሁሉም ዓይነት የሰበሰበችውን መረብ የሚያመለክተው ምሳሌ (ቁ. 47-51)፥ በዘመኑ መጨረሻ የዳኑት ካልዳኑት እንደሚለዩ ያስረዳል። 

ሰአጠቃላይ ማቴዎስ ምዕራፍ 13 የሚናገረው፥ በክርስቶስ የመጀመሪያና ሁለተኛ ምጽአቶች መካከል ስለሚገኘው ጊዜ ሲሆን፥ ስለ ንጥቀት ወይም ስለ ቤተ ክርስቲያን ሁኔታዎች አይጠቅስም። ይህ ክፍል የእምነት መግለጫ መጠንንና ተደባልቆ የሚገኘውን መልካምና ክፉ ምስል ይገልጣል። 

በፍርድና መለየት እልባት የሚያገኘው የመልካምና ክፉ አብሮ አደግነት፥ የአሁኑ ክፍለ-ጊዜ መለያ ነው። የእግዚአብሔር መንግሥት በወንጌል ስብከትና በሰዎች ጥረት የኋላ ኋላ እንደሚያሸንፍ የሚያስረዳው የድህረ ሺህ ዓመት አመለካከት ከዚህ አሳብ ጋር አይሄድም። በሌላም በኩል እግዚአብሔር እራሱ ዓላማውን ስለሚያከናውን ለተስፋ መቁረጥ ምክንያት የሚሆን መሠረት አይኖርም። አንዳንድ ዘር ከመልካም መሬት ላይ ወድቆ ፍሬ ይሰጣል። እንክርዳዱ ውስጥ ስንዴ፥ በተበላሸ ዓሣ መካከል ደህና ዓሣ ይኖራል። ከበዓለ ኀምሳ ዕለት ጀምሮ የነበሩት ዓመታት ያህንኑ ማቴዎስ 13 ውስጥ የተጠቀሰ ታላቅ ትንቢት ትክክለኛነት አረጋግጠዋል። 

ማቴዎስ ምዕራፍ 24 ውስጥም በመጨረሻው ዘመን ላይ በማተኮር ስለ አሁኑ ዘመን የቀረበ ተመሳሳይ ምስል አለ። ከ4-14 በሚገኙት ቁጥሮች ውስጥ የመጨረሻው ዘመን ዘጠኝ ምልክቶች ተሰጥተዋል፡- (1) ሐሰተኛ ክርስቶሶች (ቁ.5)፥ (2) ጦርነቶችና የጦርነት ወሬዎች (ቁ.6)፡(3) ረሃብ (ቁ.7)፥ (4) ቸነፈር(ቁ.7)፥ (5) የምድር መናወጥ (ቁ.7)፥ (6) ሰማዕትነት (ቁ.9-10)፥ (7) ሐሰተኛ ነቢያት (ቁ.11)፥ (8) የዓመፃ ብዛትና ለክርስቶስ ያለ ፍቅር መቀዝቀዝ (ቁ. 12)፥ (9) የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ መሰበክ (ቁ. 14)። 

የዚህ ዘመን ሌላ ገጽታ ያልዳኑ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን ውዕጥ ሆነው ከእውነተኛ እምነት ውጭ መመላለሳቸው ነው። 2ኛ ጴጥሮስ ምዕራፍ 2 እና 3 የነዚህን ሰዎች ሁኔታ በአራት ይመድባል፡- (1) የክርስቶስን አካልነትና መለኮትነት መካድ (2፡1)፥ (2) ክርስቶስ በመስቀል ላይ በመሞት ያስገኘልንን ሥራ መካድ (2፡1)፥ (3) ከሥነ-ምግባራዊነት የወረደና የዘቀጠ ምግባረ ብልሹነት (2፡2-22)፥ (4) ስለ ክርስቶስ ዳግም ምጽአትና ከርሱ ጋር ከተያያዙ ትምህርቶች መራቅ ናቸው (3፡1-13)። የአዲስ ኪዳን ሌሎች ምንባቦችም ስለ ክህደት የሚሉት አላቸው (1ኛ ጢሞ. 4፡1-3፤ 2ኛ ጢሞ. 3፡1-9፤ ይሁዳ 3-19)። ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቀስ በቀስ ስለሚፈጸመው ክህደት የሚናገሩት እነዚህ ሁሉ ትንቢቶች ከመጀመሪያው ምዕተ ዓመት ጀምሮ እስከአሁን በመፈጸም ላይ ናቸው። ዋነኛው ክህደት የሚካሄደው፥ ቤተ ክርስቲያን ስትነጠቅና ያልዳኑ አማኞች ነን ባዮች ብቻ ሲቀሩ ነው። 

እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያኑን ከጠራበት ዓላማ አንጻር፥ የአሁኑ ዘመን የሚያበቃው፥ ድንገት በሚከናወነው መነጠቅ ነው። በየትኛውም የብሉይ ኪዳን ትንቢት ያልተጠቀሰው ይህ ክስተት፥ ቤተ ክርስቲያን በሚያስደንቅ ሁኔታ ከምድር እንደምትነጠቅ ያመለክታል። በክርስቶስ የሞቱት በዚህ ጊዜ የሚው ሲሆን፥ በሕይወት የሚኖሩ ክርስቲያኖች ደግሞ ሞትን ሳይቀምሱ ወደ ሰማይ ይነጠቃሉ (1ኛ ቆሮ. 15፡51-58፤ 1ኛ ተሰ. 4፡13-18)። እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን እንደ ልዩ የቅዱሳን ስብስብ በማድረግ የወጠነውን ዕቅድ ይህ ክንውን ከፍጳሜ ያደርሰዋል። የቤተ ክርስቲያን ከዓለም መወሰድ፥ ክርስቶስ ወደ ምድር ተመልሶ የሺህ ዓመት መንግሥቱን ወደሚመሠርትበት ዘመን የሚያመሩትን ዓበይት ክንውኖች ያስከትላል። በመነጠቅና በዳግም ምጽአቱ መካከል የሚኖሩ ሦስት ዓበይት ክፍለ ጊዜያትን ለማጤን ይቻላል። እነርሱም (1) የዝግጅት፥ (2) የሠላምና (3) የስደት ጊዜያት ናቸው። 

ለ. ከመነጠቅ በኋላ የሚኖረው የዝግጅት ጊዜ 

የዳኑትን ሁሉ ከምድር የሚያስወጣው የመነጠቅ ክንውን፥ በሰብአዊ ታሪክ ውስጥ እስደናቂ የእግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት ይሆናል። ይህ ወደ ዳግም ምጽአቱ ታላቅ ፍጻሜ በፍጥነት የሚገሰግሱትን ተከታታይ ሁኔታዎች የሚጀምር ምልክት ነው። የክርስቲያኖች ሁሉ ከምድር መነጠቅ በዓለም ታሪክ ላይ አጠቃላይ ተጽዕኖ የሚያስከትል መሆኑ ግልጥ ነው። በዚህ ጊዜ በዓለም ላይ ክፋት በከፍተኛ ደረጃ የሚነግሥ ከመሆኑም ባሻገር፥ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የሰይጣን ዓላማ ይከናወናል። 

ከመነጠቅ በኋላ የሚመጣው ጊዜ ለሚቀጥሉት ዓበይት ክንውኖች ዝግጅት የሚደረግበት ይሆናል። እነሱም ከሦስት ዓበይት የትንቢት ጉዳዮች፥ ማለትም ከቤተ ክርስቲያን፥ ከእስራኤልና ከአሕዛብ ጋር የሚዛመዱ ናቸው። 

1. እምነቷ የይስሙላ የሃና እውነተኛ ያልሆንችው ቤተ ክርስቲያን፥ በመነጠቅ ጊዜ በምድር ላይ ትቀራለች። እውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን በታላቁ መከራ ውስጥ የማለፍ አለማለፍዋ ጉዳይ በማከራከር ላይ ያለ ነገር ቢሆንም፥ እንደ ክርስቶስ አካልነቷ በመነጠቅ ጊዜ የምትወሰድ ለመሆኑ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኞች ይስማማሉ። በምድር የምትቀረው ያልዳኑ ሰዎች የተከማቹባትና እውነተኛ ያልሆነችው ቤተ ክርስቲያን ስትሆን፥ ክንውኑም ከክርስቲያኑ ኅብረተሰብ ጋር የሚዛመደውን ትንቢት የሚፈጽም ይሆናል። 

እውነተኛ ያልሆነችው ቤተ ክርስቲያን ከመነጠቅ በኋላ ራእይ 7 ውስጥ እንደተጠቀሰው በጋለሞታ ተመስላለች። ይህች ጋለሞታ የጊዜው ፖለቲካ መገለጫ በሆነው ቀይ አውሬ ላይ ተቀምጣ ትታያለች። ይህም በብዙ ውኃዎች በተመሰለው የዓለም ሕዝብ ሁሉ ላይ የሚኖራትን የፖለቲካ ሥልጣን ያመለክታል (ራእይ 17፡1፥ 15)። ክዚህ ገልጣ የምንረዳው፥ እውነተኛ ያልሆነችው ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ አማኞች ከተወሰዱ በኋላ ሙሉ በሙሉ በክህደቷ የምትጋለጥ መሆኑን ነው። ከመነጠቅ በኋላ የሚኖረው ክፍለ-ጊዜ በሃይማኖት ረገድ ወደ ዓለም ቤተ ክርስቲያንና እውነተኛ አስተምህሮ ወደራቀው የዓለም ሃይማኖት ግስጋሴ የሚደረግበት ይሆናል። 

2. የዝግጅቱ ጊዜ ለእስራኤል የተሐድሶ ወቅት ነው። ሮሜ 11፡25 ውስጥ እንደተገለጠው፥ የኦሁኑ የእስራኤል ድንዛዜ ይወገድና ኢየሱስ ክርስቶስ እውነትም መሢሐቸውና አዳኛቸው መሆኑን ብዙዎች ይረዳሉ። ከመነጠቅ በኋላ በሚኖሩት ቀናት፥ በሺህ የሚቆጠሩ አይሁዶች ክርስቲያኖች ሲነጠቁ የተዉአቸውን መጽሐፍ ቅዱሶችና የክርስቲያናዊ አስተምህሮ መጻሕፍት በማንበብ ወደ ክርስቶስ ሊመለሱ ይችላሉ። መጽሐፍ ቅዱስን ከመሢሑ የመምጣት ተስፋ ጋር የሚያዛምዱትን የራሳቸውን መጻሕፍት ሰመጠቀምም በክርስቶስ ያምናሉ። ድንገት የሚሰወሩት ክርስቲያኖች የት እንደደረሱ ለማወቅ ከፍተኛ ጉጉት እንደሚኖራቸውም አይጠረጠርም። በዚህ ምርምራቸው ሳቢያ ብዙዎች በክርስቶስ ያምናሉ። በመጀመሪያው መቶ ክፍለ-ዘመን እንደነበረችው ቤተ ክርስቲያን፥ አይሁዶች የራሳቸውን ሕዝቦችና አሕዛብን ለክርስቶስ በመማረክ የወንጌሱ አምባሳደሮች ይሆናሉ። የታደሰው የወንጌል ስርጭት በዚህ አኳኋን በዓለም ሁሉ ይሰራጫል። አይሁዶች ቀደም ሲል በዓለም ሁሉ ተበትነው ብዙ ቋንቋዎች ማወቃቸው፥ የተሳካ የወንጌል ስርጭት በማካሄድ ብዙዎችን ወደ ክርስቶስ ለመመለስ እንደሚረዳ አይጠረጠርም። ይሁን እንጂ፥ በመጀመሪያው ምዕተ ዓመት እንደታየው ሁሉም አይሁዶች ወደ ክርስቶስ ስለማይመለሱ ድነትን የሚያገኙት የሚያምኑ ብቻ ናቸው። 

3. የአሕዛብን ፖለቲካ በተመለከተ፥ የዝግጅት ጊዜ ጥንታዊው የሮም አገዛዝ ሥርዓት እንዲያንሰራራ ያደርጋል። ቀደም ሲል እንደተገለጠው፥ ዳንኤል ምዕራፍ ሁለት የተገለጡት እግሮችና፥ ዳንኤል 7:7 ውስጥ የተገለጡት የአራተኛው እውሬ የአሥር ቀንዶች ደረጃዎች ገና ከፍጻሜ አልደረሱም። ይህ ትንቢት ራእይ ምዕራፍ 13 ውስጥ ከተጠቀሰው ተጨማሪ አሳብ ጋር እንደሚያሳየው፥ የሮም መንግሥት አሥር አገሮችን የሚያሰባስብ ኮንፌዴሬሽን ፈጥሮ እንደገና የሚያንሰራራ ይመስላል። የእውሮፓ የጋራ ገበያ ምናልባትም ለዚህ እርምጃ ግንባር ቀደም ይሆናል። የፖለቲካዊ ኃይሉ ማዕከል የሚያርፈው ግኝ ከአውሮፓ ይልቅ ሜድትራኒያን አካባሲ ሆኖ፥ የሰሜን አፍሪካን፥ የምዕራብ እስያንና የደቡብ አውሮፓን ዓበይት እሮች የሚያካትት ይመስላል። 

ሜድትራኒያን እንደገና (የሮም ሐይቅ› ይሆናል። እነዚህ አሥር አገሮች በአንድ ላይ ሲተባበሩ፥ ዳንኤል 3:8 ውስጥ ትንሽ ቀንድ የተባለው መሪ ይነሣል። ይህ መሪ መጀመሪያ በሦስት አገሮች ላይ አምባገነንነቱን ያሰፍንና የኋላ ኋላ አሥሩንም የሚገዛ ይመስላል። የመካከለኛው ምሥራቅ ጠንካራ የፖለቲካ ሰው ከመሆኑም በሳይ፥ የዓለም ኃያል ለመሆን ይቻለው ዘንድ ከዓለም ቤተ ክርስቲያን ጋር ይተባበራል። በጽኑ መሠረት ላይ ከተደላደለ በኋላ፥ ቀጣዩ ዓቢይ ክፍለ-ጊዜ ይቀጥላል። ይህም የቃል ኪዳን ክፍለ-ጊዜ 

ሐ. የሠላም ጊዜ 

የመካከለኛው ምሥራቅ አምባገነን መሪ ማለትም “የሚመጣው አለቃ” (ዳን. 9፡26) ሥልጣን እርከን ላይ ሲወጣ፥ ከእስራኤል ጋር የሰባት ዓመታት ቃል ኪዳን ያደርጋል (ዳን. 9፡27)። የቃል ኪዳኑ ዝርዝር ጉዳዮች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባይገለጡም፥ የጥበቃ ቃል ኪዳን ሊሆን እንደሚችል ግን ተመልክቷል። አምባገነኑ መሪ በእስራኤልና በዙሪያዋ በሚገኙ አገሮች መካከል ያለውን ውዝግብ ለማርገብ የሚፈልግ ይመስላል። እስራኤል ግዛቷን እንድትይዝ በማድረግም ሰመካከለኛው ምሥራቅ ሠላምና መረጋጋትን ይፈጥራል። ወቅቱ ሙሉ ሠላም የሚሰፍንበት መሆኑ ባይገለጥም፥ በአንጻራዊ ሁኔታ እስራኤል አስተማማኝ ሁኔታ ላይ እንድትደርስ ያደርጋታል። ከዚህም በላይ እገሪቱ በ3948 ዓ.ም. ከተመሠረተች ጀምሮ ባልተለመደ ሁኔታ ሠላሟ የተረጋጋና በንግድም ጉዳይ የምትታገዝ ትሆናለች። ይህ የሁኔታዎች ለውጥ ያለ ጥርጥር ሌሎች ብዙ አይሁዶች ወደ ጥንታዊቱ ምድራቸው እንዲመለሱ በማድረግ፥ እንድትበለጥግ ያደርጋታል። 

በዚህ ጊዜ የዓለም ቤተ ከርስቲያን ዓለም አቀፋዊ የሃይማኖት አገዛዝን ለመቀዳጀት ስትል ከሜድትራንያኑ አለቃ ጋር በመተሳሰር ወደ ከፍተኛ ደረጃ ማደጓን ትቀጥላለች። በተመሳሳይ ሁኔታ፥ እስራኤል ውስጥ የሚደረገው የወንጌል ስርጭት ብዙዎችን ወደ ክርስቶስ ይመልሳል። በሌላም በኩል ብዙዎች ወደ መሠረታዊው የአይሁድ እምነት ይመለሳሉ። ቤተ መቅደሱም ኢየሩሳሌም ውስጥ እንደገና ተሠርቶ መሠረታውያን አይሁዶች የሙሴን የመሥዋዕት ሥርዓት የሚያድሱ ይመስላል። ቤተ መቅደሱ በ70 ዓ,ም. ከተደመሰሰ አንሥቶ የመሥዋዕቱ ሥርዓት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል። ይህ ጉዳይ የመሥዋዕቱ አቅርቦት በኋላ እንደሚታቀብ በሚያመለክተው ዳንኤል 9፡27 እና ዕለታዊ መሥዋዕት እንደሚቆም ሰሚናገረው ዳንኤል 12፡11 ውስጥ ድጋፍ አግኝቷል። በግልጥ እንደሚታወቀው፥ መሥዋዕቶችን እንደገና ለማቅረብ የግድ ቤተ መቅደሱ ኢየሩሳሌም ውስጥ መታነጽ አለበት። ቤተ መቅደሱ የሚታነጽበትን ትክክለኛ ጊዜ የሚያውቅ ባይኖርም፥ በሠላሙ ጊዜ የሚሠራ ይመስላል። 

ይሁንና፥ ሕዝቅኤል 38-39 ውስጥ እንደተገለጠው የመካከለኛው ምሥራቅ መረጋጋት በድንገት ይናጋል። ይህም ሩሲያና ተባባሪዎቿ በእስራኤል ላይ በሚሰነዝሩት ጥቃት ሳቢያ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች በዚህ ጉዳይ ላይ በሚያቀርቧቸው ምርምሮችና ሰክስተቱ በሚሰጡት ቅደም ተከተል በአሳብ ይለያያሉ። ሕዝቅኤል 38 እንደሚያስተምረን፥ ጦርነቱ የሚመጣው እስራኤል በሠላምና በእረፍት ሳይ ሳለች ነው። ይህም ከሮማው አለቃ ጋር ከሚደረግ ቃል ኪዳን በኋላ ከሚመጣው ጊዜ ጋር ይስማማል። ጦርነቱ እስራኤል ከሜድትራኒያኑ መሪ ጋር ያደረገችውን ቃል ኪዳን ሁሉ የሚፈታተን በመሆኑ፥ በእስራኤል ላይ የሚሰነዘር ጥቃት ብቻ ሳይሆን ሩሲያ የመካከለኛው ምሥራቅን ፖለቲካዊና መዋዕለ ንዋያዊ ሁኔታ ለመቆጣጠር የምታደርገው ፉክክር ውጤትም ነው። ጥቃቱ ድንገተኛ በመሆኑ፥ ወራሪዎችን ለመከላከል ሠራዊት ሰለመሰብሰቡ ግን የተገለጠ ነገር የለም። እግዚአብሔር ግን ሕዝቡን ለማዳን በሉዓሳዊ ጣልቃ ገብነት ሕዝቅኤል 38፡18-23 ውስጥ በተዘረዘሩት ተከታታይ እደጋዎች የጠላትን ወታደሮች ይደመስሳል። ይህ ጦርነት የሠላሙን ጊዜ ሰማወክ ለአራተኛውና ለመጨረሻው ክፍሰ-ጊዜ ጥርጊያ መንገድ የሚያዘጋጅ ነው። 

መ. የስደት ጊዜ 

የሮም ሠራዊት መውደም ከዚያ በፊት የነበረው ሰላም እንዲያበቃ ማድረግ ብቻ ሳይሆን፥ የዓለምን ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ይለውጠዋል። በዚያን ወቅት በሚከተሉት ወገኖች መካከል የኃይል ሚዛን የሚስተዋል ይመስላል (1) በመካከለኛው ምሥራቅ አለቃና ከርሱ ጋር ከተሳሰሩት አገሮች፥ (2) ሩሲያና ግብረ አበሮቿ። የሩሲያ ሠራዊት ለጊዜው በሚሽነፍበት ወቅት የመካከለኛው ምሥራቅ አለቃ አጋጣሚውን በመጠቀም ራሱን የዓለም አምባገነን መሪ ያደርጋል። በዓለም ላይ በአንድ ጀንበር ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሃይማኖታዊ ሥልጣንን ይጨብጣል። በሁሉም ነገድ፥ ወገንና ቋንቋ ላይ ራሱን በአለቅነት ይሾማል (ራእይ 13፡7)። ዳንኤል፥ “ምድሪቱንም ሁሉ ይበላል፥ ይረግጣታል፥ ያደቅቃትማል” (ዳን. 7፡23) በማለት በትንቢቱ ጎልጦታል። የጠቅላላውን ዓለም ኢኮኖሚ ስለሚቆጣጠርም፥ ያለ እርሱ ፈቃድ ሊገዛ ወይም ሊሸጥ የሚችል አይኖርም (ራእይ 13፡16-17)። 

አለቃው በአንድ ጀንበር ቃል ኪዳኑን አፍርሶ እስራኤልን ሊያሳድዳት መነሣቱ ለአገሪቱ ቅፅበታዊ ተገላቢጦሽ ይሆንባታል። ይህም ኤርምያስ 30፡7 ውስጥ የያዕቆብ መከራ ወቅት ተብሎ የገለጠውን አሳብ ያመለክታል። ይኸው ዘመን ሌላ ስፍራ ታላቅ መከራ ተብሎ ተጠቅሷል (ዳን. 12፡1፤ ማቴ. 24፡21፤ ራእይ 1፡14)። የእስራኤል መከራ የሚጀምረው መሥዋዕት የማቅረብ ሥርዓታቸው ሰቅፅበት እንዲቆም በሚደረግበት ወቅት ነው (ዳን. 9:27፤ 12፡11፤ ማቴ. 24፡15)። ለዚህ ነው፥ እስራኤል በፍጥነት ወደ ተራሮች እንድትሸሽ ክርስቶስ የመከራት (ማቴ. 24፡16-20)። ለእስራኤል ጊዚው እጅግ የከፋ ይሆንባትና በሺህ የሚቆጠሩ አይሁዶች ይጨፈጨፋሉ (ዘካ. 13፡8)። የዓለም ገዢው ጣኦት ቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚቀመጥ ከመሆኑም በላይ (ራእይ 13፡15)፥ አንዳንድ ጊዜም ይመሰክ ዘንድ ገዢው ራሱ በአካል እዚያ ይገኛል (2ኛ ተሰ. 2፡4)። ይህ ከመሥዋዕቶች 

መከልከል ጋር ተያይዞ የተገለጠ የጥፋት ርኩሰት ነው። በተጨማሪም፥ የዓለም ገዢው ራሱን እንደ አምላክ በመቁጠር፥ ሰዎች ሁሉ እንዲሰግዱለት ያስገድዳቸዋል፥ እምቢ የሚሉትን ይፈጃቸዋል (ራእይ 13፡8፥ 15)። 

ይህ የመጨረሻ ክፍለ-ጊዜ የሚጀምረው ለቃል ኪዳን በተወጠነው የሰባት ዓመት አጋማሽ ሲሆን፥ ለአርባ ሁለት ወራት ይቆያል (ራእይ 11፡2፤ 13፡5፤ ዳን. 7፡25፤ 9፡27፤ 12፡11-12)። 

ከዚህ እጅግ ከከፋ ተሳዳቢነቱና በአይሁዶችም ሆነ በክርስቲያኖች ላይ በሚያደርሰው ስደት የተነሣ የሜድትራኒያኑ የዓለም ገዢ፥ የሚያስፈራ መለኮታዊ ፍርድ ይወርድበታል። ይህ ገዢ ብዙውን ጊዜ ሐሳዊ መሢሕ እየተባለ የሚጠራ ሲሆን፥ ዳንኤል 9፡26 ውስጥ “የሚመጣው አለቃ” ተብሏል። ይህ ሁሉ በሐሳዊው መሢሕ ላይ የሚደርስ ፍርድ ራእይ ምዕራፍ 6-19 ውስጥ ተገልጧል። የነዚህ ሁኔታዎች ዝርዝሮች በሰባቱ ማኅተሞች መፈታት (ራእይ 6፡1-8፡1)፥ በሰባቱ መለከቶች መነፋት (ራእይ 8፡2-21፤ 11፡15-19) እና በሰባቱ የእግዚአብሔር የቁጣ ጽዋዎች መፍሰስ ውስጥ ተመዝግቧል (ራእይ 16)። 

በምድር ላይ ከፍተኛ የሆኑ ፍርዶች ይወርዳሉ። ክርስቶስ ማቴዎስ 24፡21-22 ውስጥ እንደገለጠው፥ ጊዜው እጅግ ክፉ ከመሆኑ የተነሣ በዳግም ምጽአቱ እንዲያጥር ባይደረግ ኑሮ የሰው ዘር ባልተረፈም ነበር። ጦርነት፥ ቸነፈር፥ ረሃብ፥ የከዋክብት ከሰማይ መውደቅ፥ የመሬት መንቀጥቀጥ፥ የአጋንንት ጥቃትና በዓለም ላይ የሚደርሱ ከፍተኛ የተፈጥሮ አደጋዎች፥ ከዓለም ሕዝቦች አብዛኛውን ቁጥር የሚያጠፉ ይመስላል። 

በነዚህ አደጋዎች ሳቢያ የሚከሰተው ሁከት በመካከለኛው ምሥራቁ የዓለም ገዢ ላይ ተቃውሞ ያመጣበታል፤ ቃል የገባላቸውን ሠላምና ብልጥግና ለሕዝቡ ሊያመጣ እይችልም። በዚህ ሳቢያ ዓለም አቀፍ ዐመፅ ከመቀስቀሱም በላይ፥ ሥልጣኑን ለማስወገድ ዓበይት የዓለም ክፍሎች ያምፁሰታል። ይህም ዳንኤል 11፡40-45 እና ራእይ 9፡13-21፤ 16፡13-21 ውስጥ በተገለጠው አሠቃቂ ጦርነት አማካይነት ይጠናቀቃል። የዓለም ሕዝቦች በዚህ አኳኋን በትግል የሚጠመዱ ሲሆን፥ ቅድስቲቱን አገር ለመውጋት ጦርነቱ ከሰሜን፥ ከደቡብና ከምሥራቅ በሚወጣ እጅግ ብዙ ሠራዊት መፋጠጥ ብልጭ ድርግም ሲል ይቆያል። ግጭቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በሚደርስበት ጊዜ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ትግል ላይ በተሰለፉት ኃጢአተኞች ሳይ ለመፍረድና የሺህ ዓመት መንግሥቱን ለመመሥረት በኃይልና በክብር ወደ ምድር ይመለሳል። 

በአጠቃላይ ወደ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት የሚመሩ ሁኔታዎች በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን በሚገባ ተዘርዝረዋል። ጊዜው ከየትኛውም ሌሳ የታሪክ ወይም የትንቢት ክፍል የተለየና የአስደናቂ ሁኔታዎች ቅደም ተከተላዊ አፈጻጸም መከሠቻ ነው። ዓለም ወደዚህ ፍጻሜ በመገስገስ ላይ መሆኗን የሚያሳዩ ብዙ ምልክቶች፥ መጽሐፍ ቅዱስ ጌታ ቅዱሳኑን ለመውሰድ በቅርቡ እንደሚመጣ የሚያስተምረውን አሳብ ይበልጥ ያጠናክሩታል።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

45
ትምህርት 45 ከ52

ታላቁ መከራ

ሀ. ታላቁ መከራ ከአጠቃላይ መከራ ጋር ሲነጻጸር 

የታላቁን መከራ አስተምህሮ በተመለከተ የተለያዩ ግራ መጋባቶች ታይተዋል። የዚህ ምክንያቱ የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚያልፍበትን የተለያዩ መከራዎችና ፈተናዎች በታወቀ ጊዜ እንደሚመጡ ብሉይና አዲስ ኪዳናት ውስጥ ከተገለጠው ታላቅ መከራ ለመለየት አለመቻል ነው። መከራ የሚለው አሳብ የሚያመለክተው ጫናን፥ ጉስቁልናን፥ የልብ ስብራትንና ችግር የምንላቸውን ነገሮች ሁሉ ነው። መከራ ስንል በአጠቃላይ ለሰው ዘር እውን ስለሆኑ ችግሮች መናገራችን ነው። ይህ ዓይነት መከራ ከሰው ልጅ ኃጢአትና በእግዚአብሔር ላይ ማመፅ ሳቢያ ይመጣል። በእግዚአብሔርና በሰይጣን መካከል በምድር ከሚከናወን የዓላማ ልዩነት የተነሣ የሚፈጠር ችግርም ነው። 

ኢዮብ 5፡7 ውስጥ “የአሞራ ግልገሎች ግን ወደ ላይ እየበረሩ ክፍ እንዲሉ ሰው እንዲሁ ለመከራ ተወልዶአል” ይላል። ክርስቶስም ይህንኑ ዮሐንስ 16፡33 ውስጥ ሰደቀ መዛሙርቱ ሲያረጋግጥ፥ “በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ” ብሏል። ብሉይ ኪዳን ውስጥ ኢዮብ የደረሰበት መከራና አዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሰው የጳውሎስ ሥጋ መውጊያ ችግር በሰው ልጆች ላይ ያለማቋረጥ ለሚደርሰው መከራና ጉስቁልና እንደ ምሳሌ የሚወሰዱ ናቸው። ከአዳም ጀምሮ ይህ የሰው ልጆች መታወቂያ ሆኗል። በሺህ ዓመቱ መንግሥት ጊዜ በአያሌው የሚቃለል ቢሆንም፥ የሰው ልጅ ታሪክ እስኪያበቃ ድረስ ይቀጥላል። 

መከራና ሥቃይ በጣምራነት ባጠቃላይ የሰው ዘር ላይ ከሚያደርሱት ጉዳት አንጻር፥ በዘመኑ መጨረሻም ችግር የሚኖርበት የተለየ ጊዜ መኖሩን መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል። ይህ የሚሆነው፥ በተለይ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት መዳረሻ በሆነው የአርባ ሁለት ወራት ጊዜ ሰሚኖረው ታላቅ መከራ ነው። 

ለ. ስለ ታላቁ መከራ የብሉይ ኪዳን አስተምህሮ 

እስራኤል በኋለኛው ዘመኗ መከራ በሚደርስባት ጊዜ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ያለባት ስለመሆኑ ማስጠንቀቂያ የተነገራት ገና መጀመሪያ ዘዳግም 4፡29-30 ውስጥ ነበር። ይህ የተለየ ጊዜ የተነገረው ሰነቢዩ በኤርምያስ ነው። የመከራው ጊዜ የሚጀምረው እስራኤላውያን በከፊል ወደ ምድራቸው ከተመለሱ በኋላ እንደሚሆን ነቢዩ ምዕራፍ 30፡1-10 ውስጥ እንዲህ በማለት ተንብዮአል፡- “እነሆ የሕዝቤኝ የእስራኤልንና የይሁዳን ምርኮ የምመልስበት ዘመን ይመጣልና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ለአባቶቻቸውም ወደሰጠኋት ምድር እመልሳቸዋለሁ፥ እነሱም ይገዟታል” (ቁ.3)። 

ወዲያውኑ በመቀጠል ከቁጥር 4-7 ባለው ክፍል እስራኤላውያን ወደ ምድራቸው ከተመለሱ በኋላ በሚኖረው ጊዜ ስለሚደርስባቸው መከራ ተጎልጧል። ያኔ እስራኤል ልጅ እንደምትወልድ ሴት ምጥ ይይዛታል። የመከራው ጊዜ በተለይ ኤርምያስ 30፡7 ውስጥ እንዲህ ተገልጧል፡“ወዮ! ያ ቀን ታላቅ ነውና፥ እርሱንም የሚመስል የለምና፤ ያ የያዕቆብ መከራ ዘመን ነው፥ ነገር ግን ከእርሱ ይድናል” 

እስራኤል ምንም እንኳን በዚህ ታላቅ መከራ ውስጥ ብታልፍ፥ እግዚአብሔር በመጨረሻ የባርነት ቀንበሯን እንደሚሰብርና አሕዛብን ከማገልገል ነጻ እንደሚያወጣት ተስፋ ሰጥቷታል። ቁጥር 9 ውስጥ እንደተገለጠው፥ “ለአምላካቸው ለእግዚአብሔርም፥ ለማስነሣላቸው ለንጉሣቸው ለዳዊትም ይገዛሉ እንጂ ሌሉች አሕዛብ እንደገና አይገዟቸውም”። ይህ ትንቢት ዳዊት ከሞት ተነሥቶ በሺህ ዓመቱ መንግሥት ጊዜ ከክርስቶስ ጋር በእስራኤል ላይ የሚነግሥ መሆኑን ያመለክታል። ለዚህ ነው እስራኤል ተስፋ እንዳትቆርጥ “ያዕቆብም ይመለሳል፥ ያርፍማል፥ ተዘልሎም ይቀመጣል፥ ማንም አያስፈራውም” (ቁ.10) የሚል ዋስትና የተሰጣት። 

የያዕቆብ መከራ ጊዜ ወይም ታላቁ ፍዳ፥ ዳንኤል 9፡27 ውስጥ የተጠቀሰው ቃል ኪዳን ከፈረሰ በኋላ እንደሚሆን በዚሁ ክፍል ተመልክቷል። ጊዜው የሰባቱ ዓመት አጋማሽ ወይም ሦስት ዓመት ተኩል እንደሚሆን በማያሻማ ሁኔታ ተገልጧል፥ “የሚመጣውም አለቃ” (ዳን. 9፡26)፥ “ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ** (9፡27)፥ ማለት ለሰባት ዓመት ያደርጋል። ይሁን እንጂ ቃል ኪዳኑን በሱባዔው እጋማሽ፥ ማለት ከሦስት ዓመት ተኩል በኋላ ያፈርስና “መሥዋዕቱንና ቁርባኑን ያስቀራል”፥ ቤተ መቅደሱንም ያረክሳል። 

ዳንኤል 12:11 ውስጥ እንዲህ ተብሎ ሁኔታው ተብራርቷል፡- “የዘወትሩም መሥዋዕት ከቀረ ጀምሮ፥ የጥፋትም ርኩሰት ከቆመ ጀምሮ ሺህ ሁለት መቶ ዘጠነኛ ቀን ይሆናል”። ይህ ጥቂት ቀናት ተጨምሮበት ሦስት ዓመት ተኩል ይሆናል። ጊዜው የክርስቶስን ዳግም ምጽአትና ከዚያ የሚከተሉትን የመጀመሪያ ፍርዶች የሚያጠቃልል ሳይሆን አይቀርም። ዳንኤል 12፡12 ውስጥ የተገለጠውና ከ1335 ቀናት በኋላ የሚመጣው በረከት ታላቁን የመከራ ጊዜ፥ የክርስቶስን ዳግም ምጽአትና ፍርዶቹን ብቻ ሳይሆን፥ የተባረከውን የክርስቶስ ሺህ ዓመት መንግሥት በምድር መመሥረትን ይጨምራል። በዚሁ መሠረት የታላቁ መከራ ጊዜ አርባ ሁለት ወራት ወይም ሦስት ዓመት ተኩል መሆኑ ታውቋል። 

ታላቁ የፍዳ ጊዜ በኢየሱስ ክርስቶስ ምጽአት ወቅት የሚያበቃ መሆኑ በግልጥ ይታወቃል። ዳንኤል 7፡13-14 ውስጥ በተጠቀሰው ትንቢት መሠረት ጊዜው የሰው ልጅ (ክርስቶስ) ከሰማይ የመምጣቱንና መንግሥታትን በሥልጣኑ ሥር የማድረጉን ክንዋኔ ያጠቃልላል። በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ዋዜማ ላይ የሚኖረው ክፉ መንግሥትና ንጉሥ ይደመሰሳሉ (ዳን. 7፡26)። ከዚያም መጀመሪያ የሺህ ዓመቱ የክርስቶስ አገዛዝ፥ ለጥቆም በአዲስ ሰማይና አዲስ ምድር የሚመሠረተው ዘላለማዊ የእግዚአብሔር መንግሥት ይመጣሉ። የብሉይ ኪዳን አስተምህሮ በአንጻራዊ መልኩ ያብቃ ቢሆንም፥ ይህን ክንዋኔ በተመለከተ ግን አዲስ ኪዳናዊው ራእይ ሊታከልበት ይችላል። 

ዳንኤል 11፡36-39 ውስጥ በተመለከተው ትንቢት መሠረት፥ በመጨረሻው ዘመን የሚኖረው ሃይማኖት የዓለም መሪ ወይም ገዢ ሰሚሆነው ሰውዬ የሚመራና በእግዚአብሔር ሳይሆን፥ በሌሎች አማልክት ላይ የሚመሠረት ይሆናል። እነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እንደተመለከተው፥ ይህ መሪ ቀድሞ የነበሩትን አማልክት ሁሉ የማያከብርና እራሱን ከእግዚአብሔር በላይ ከፍ ከፍ የሚያደርግ ነው። የሚያከብረው የአምባዎችን አምላክ ማለት የጦርነት አምላክን ብቻ ይሆናል። ቁሳዊነት እንጂ፥ fእምልኮ መንፈስ ያለበት ሰው አይሆንም። የዚህ ሰው መንግሥት የሚያከትመው፥ ከቁጥር 40-45 ባለው ክፍል እንደተመለከተው፥ እጅግ ታላቅ በሆነ ጦርነት ነው። ከደሱብ፥ ከሰሜንና ከምሥራቅ ሠራዊቶች ይመጡበታል። የሚመጣበትን ሠራዊት ለተወሰነ ጊዜ የሚመክት ቢመስልም፥ ታላቁ ፍዳ እንዲያከትም የሚያደርገው የክርስቶስ ዳግም ምጽአት እስኪሆን ድረስ ጦርነቱ የከፋ ይሆናል። 

ሐ. የፍዳው ዘመን በአዲስ ኪዳን አስተምህሮ 

ዳግም ምጽአቱና የዓለም ፍጻሜ መቼ እንደሚሆን ክርስቶስ በደቀ መዛሙርቱ በተጠየቀ ጊዜ፥ ለእኛ የሚሆኑ የዘመኑን ምልክቶች ነው አስቀድሞ የነገራቸው። ከነዚህ ብዙዎቹ በክርስቶስ ቀዳሚና ዳግም ምጽአቶች መካከል ባለው ጊዜ መከናወን ያለባቸው እንደመሆናቸው ተፈጽመዋል (ማቴ. 24፡3-14)። 

ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱ ስለሚመጡት ምልክቶች በጠየቁት ጊዜ ማቴዎስ 24፡15-29 ውስጥ ሲመልስ የገለጠላቸው ታላቁን መከራ ነው። መከራው የሚጀምረው “በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ” (ቁ.15) ሰዎች ሲመለከቱ፥ እንዲሁም የቤተ መቅደሱን መርከስና ሰሜድትራንያን አካባቢ የሚነሣው መሪ ራሱን በእግዚአብሔር ስፍራ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ሲያኖር መሆኑን ከማስጠንቀቅ ጋር ገለጠሳቸው። አንድ ቀን ራሱን የቻለ ክንውን ሆኖ የሚገለጠው ይህ ዕለት በሚከሠትበት ጊዜ፥ ሕይወታቸውን ለማዳን ወደ ተራራዎች እንዲሸሹም የእስራኤልን ልጆች አስጠነቀቃቸው። 

ክርስቶስ ይህንኑ ዕለት ማቴዎስ 24፡21-22 ውስጥ ሲገልጠው እንዲህ ብሏል፡- “በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ያልሆነ፥ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናል። እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ። ክርስቶስ ታላቁን የመከራ ጊዜ ከሌሎቹ የመከራ ጊዜያት ሁሉ ጋር በማነጻጸር ነው የሚገልጠው። መከራው፥ ዓለም ከዚያ በፊት የተለማመደቻቸውን ነገሮች ሁሉ እስኪሸፍን ድረስ የገዘፈ ነው። 

ይህ መከራ ሳያጥር (ቶሉ ባያበቃ) ኖሮ የሰው ዘር ምድር ላይ ባልተረፈ ነበር። አንዳንድ ሰዎች “ባያጥር” የሚለውን ቃል እንደተገነዘቡት፥ ወቅቱ ከአርባ ሁለት ወራት ያነሰ ጊዜ መሆኑን ይህ አያመለክትም። ቃሉ የሚያስረዳው፥ የመከራው ጊዜ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ምክንያት ሳያጥር ኑሮ፥ ታላቁ መከራ የሰውን ዘር ሁሉ ያጠፋ የነበረ መሆኑን ነው። “ስለተመረጡት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው፥ የዳኑ እስራኤላውያንን ወይም የዳኑ አሕዛብን ወይም ሁለቱንም ነው። የክርስቶስ መመለስ ዓላማ በዓለም ለመፍረድ ሲሆን፥ በስሙ ያመኑትን ግን ከክፉ ሁሉ ይሰውራቸዋል። 

ጌታችን ስለ መከራው ጊዜ አንዳንድ ባሕርያት ቀጥሎ ባሉት ቁጥሮች ገልጧል። ያኔ ሐሰተኛ ነቢያትና ሐሰተኛ ክርስቶሶች ይነሣሉ (ማቴ. 24፡23-24)። ክርስቶስ በምሥጢር መጥቷል የሚል ሐሰተኛ ወሬም ይኖራል (ቁ. 26)። ለዚህ ነው ያን ጊዜ ማንም እንዳይታለል ደቀ መዛሙርቱን ያስጠነቀቃቸው። ምክንያቱም የክርስቶስ ዳግም ምጽአት፥ መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ ግልጥ ክንውን ይሆናል (ቁ. 27)። የፍዳው ጊዜ ሁኔታም “ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥ የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ” ተብሎ ቁጥር 29 ውስጥ ተገልጧል። ከዚህ በመቀጠል ነው የክርስቶስ ምጽአት የሚሆነው። 

ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱ ስለ ታላቁ መከራ ላቀረቡለት ጥያቄ የሰጠው ገለጣ፥ ራእይ ምዕራፍ 6-18 ውስጥ በሰጠው ተጨማሪ መግለጫ ተረጋግጧል። ራእይ 5፡1 ውስጥ የተጠቀሰውና በሰባት ማኅተም የተዘጋው መጽሐፍ ምዕራፍ 6 ውስጥ ተገልጧል። 

እያንዳንዱ ማኅተም ሲፈታ፥ ታላቅ መቅሠፍት በምድር ላይ መውረድ ይጀምራል። የሚጀምረውም የዓለምን መንግሥት በሚገልጠው የመጀመሪያ ማኅተም ነው (ራእይ 6፡1-2)። ከዚያ ቀጥሎ ጦርነት (ቁ.3-4)፥ ረሃብ (ቁ.5-6)፥ የምድር አራተኛዋ እጅ ሕዝብ መሞት (ቁ.7-8) ይሆናሉ። አምስተኛው ማኅተም ያን ጊዜ የሚሞቱትን ሰማዕታት ይወክላል (ቁ.9-11)። የሚለጥቀው፥ በሰማያት ታላቅ ነውጥ መሆኑ፥ የፀሐይ መጥቆር፥ እንዲሁም የጨረቃ ደም መምሰል ነው (ቁ. 12-14)። ይህን የመሰለው አስደናቂ መለኮታዊ ኃይል በምድር መገለጡ፥ በክርስቶስ ባሳመኑ ሰዎች ላይ ፍርሃትን ይለቅባቸዋል። በመሆኑም ሰዎቹ ተራራዎችን በላያችን ውደቁ፥ “ሰውሩን፤ ታላቁ የቁጣ ቀን መጥቷልና”(ቁ. 15-17) ይላሉ።

ሰባተኛው ማኅተም ሲፈታ (8፡1)፥ ሰባት ተከታታይ ሁኔታዎች መለከት ከያዙ ሰባት መላእክት ጋር ይቀጥላል {8፡2-9፡21፤ 11፡15-19)። ከእነዚህ ታላላቅ ፍርዶች አብዛኛዎቹ ብዙ ሕይወት የሚጠፉባቸውና በተፈጥሯዊው ዓለም ላይ የሚወርዱ ናቸው። ፍርዶቹ የምድር አንድ ሦስተኛው ሰእሳት የሚጠፉበት፥ የውቅያኖሶች አንድ ሦስተኛ ወደ ደምነት የሚለወጥበትና ውስጡ ያሉ ፍጡራንም የሚያልቁሰት፥ እንዲሁም በዚሁ የባሕር ክፍል ላይ ከዋክብት ከሰማይ የሚወድቁባቸው ናቸው (8፡7-11)። አራተኛው መለከት ከዋክብትን ይመለከታል። የፀሐይ፥ የጨረቃና የከዋክብት አንድ ሦስተኛ ክፍል ይጨልማሉ። ከዚያ ቀጥሉ በተከታታይ በሚነፉት መለከቶች አማካይነት ስለሚደርሰው አሠቃቂ እልቂቶችም ትንቢት ተነግሯል። 

አምስተኛው መለከት (9፡1-12)፥ የሚያመለክተው በክርስቶስ ያላመኑ ሰዎች ለአምስት ወራት በዲያብሎስ መሠቃየታቸውንና ሰዎቹ የገዛ ሕይወታቸውን እንኳ ሊያጠፉ አለመቻላቸውን ነው። ስድስተኛው መሰከት (9፡13-21)፥ የሚገልጠው የኤፍራጥስን ወንዝ አቋርጦ ከወደምሥራቅ ስለሚመጣው ታላቅ ሠራዊት ነው። በመከራው ዘመን ማብቂያ ላይ በሚደረገው ታላቅ ጦርነት ለመሳተፍ ነው ይህ ሠራዊት የሚመጣው። ሰባተኛው መለከት (11፡15)፥ በመከራው ዘመን ማብቂያ አካባቢ የሚነፋ ሲሆን፥ የክርስቶስን መምጣትና የመንግሥቱን በምድር ላይ መመሥረት ይጠቁማል። 

ሰባተኛው መለከት በተከታታይና በፍጥነት የሚወርዱ ሌሎች ሰባት ፍርዶችንም ያመለክታል። እነዚህ ፍርዶች ራእይ 16 ውስጥ የእግዚአብሔር ቁጣ ጽዋዎች ተብለዋል። እነዚህ ከመለካት ፍርዶች ይልቅ እውዳሚዎች ሲሆኑ፥ ምድር ላይ የሚወርደውን የመጨረሻ የእግዚአብሔር ፍርድ ያካትታሉ። ለክርስቶስ ዳግም ምጽአት ቅድመ ዝግጅትም ናቸው። 

ስድስተኛው ጽዋ አርማጌዶን ሰተባለው ስፍራ ከሚደረገው የእግዚአብሔር ጦርነት ቅድመ ዝግጅት ጋር ይዛመዳል። በራእይ 16፡14 መሠረት የምድር ነገሥታትና ሠራዊታቸው ለውጊያ በስፍራው ይከማቻሉ። እነዚህን እርማጌዶን ላይ የሚከማቹ ሠራዊቶች የሚሰበስባቸውም ሰይጣን ይሆናል። ሠራዊቶቹ የሚዋጉት ለዓለም ሥልጣን ይመስላቸዋል፤ እውነቱ ግን ክርስቶስ ወደ ምድር በሚመለስበት ጊዜ የሚያጅበውን ሠራዊት ይቃወሙ ዘንድ በሰይጣን በራሱ የሚመሩ መሆናቸው ነው (ራእይ 19፡14)። 

ራእይ 16፡17.21 ውስጥ ባለው ክፍል የተጠቀሰው የመጨረሻ ጽዋ፥ የዓለምን ታላላቅ ከተማዎች እንዳልነበሩ የሚያደርገውን፥ ባቢሎንን ለፍርድ የሚያበቃትን እንዲሁም ደሴቶችንና ተራራዎችን የሚያጠፋቸውን ታላቅ የምድር መናወጥ ያካትታል። በፍጻሜው፥ ክብደቱ እያንዳንዱ 51 ኪሎ ግራም የሚመዝን በረዶ ከሰማይ ሰመውረድ ምድር ላይ የቀረውን ሁሉ ያጠፋል። በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ወቅት ዓለም ነውጥ፥ ጥፋትና ጦርነት በአንድ ላይ ይረባረቡባታል። 

ቀስ በቀስ በእግዚአብሔር ቃል ተሸንፈው ለክርስቶስ ታዛዦች ከመሆናቸው በፊት፥ ዓለም ከጊዜ ወደ ጊዜ በመሻሻል ላይ ናት ብለው ያስቡ የነበሩ የሥነ-መለኮት ምሁራን ሕልማቸው ምንኛ የተሳሳተ ነበር! መጽሐፍ ቅዱስ ዓለምን የሚጎልማት ኢ አማኒ በሆነ ገዥ እየተመራች አሰከፊ በሆነ ኃጢአትና በእግዚአብሔር ላይ በማመፅ በደል ወደ ፍጻሜዋ የምታመራ መሆኗን ነው። የመጨረሻ መሪዋ እግዚአብሔርን የሚነቅፍና በእግዚአብሔር የሚያምኑትን ሁሉ የሚያሳድድ ይሆናል። 

በጽድቅ የተሞላው የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ ምድር የሚመጣው በሰብአዊ ጥረት ሳይሆን ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት ጋር ነው። ያኔ በዓለም ያሉ ኃጢአተኞች እጅግ ታሳቅ ፍርድ ይሰጣቸዋል፤ በነዚያ አሠቃቂ ጊዜያት እምነታቸውን በክርስቶስ ያደረጉ ደግሞ አስደናቂ ነጻነት ይሆንላቸዋል። 

ይህ የፍዳ ጊዚ ለእግዚአብሔር ልጆች ሳይሆን፥ ለነቃፊዎችና ለማያምኑ የተዘጋጀ እስከፊ ወቅት ነው። ከዚህ የተነሣ ቤተ ክርስቲያን አሠቃቂው ጊዜ ከመጀመሩ በፊት ትነጠቃለች በማለት ብዙዎች ያምናሉ፤ ያስተምራሉም። ቤተ ክርስቲያን ከታላቁ መከራ ጋር በተያያዘና በጎላ ሁኔታ አልተወቀሰችም። ምንም እንኳን ጻድቃን ወይም ቅዱሳን ተብለው የተጠቀሱ ሰዎች ወደ ክርስቶስ የሚቀርቡ መሆኑ ቢገለጥ፥ እነዚህን ሰዎች ከቤተ ክርስቲያን ጋር የሚያዛምዳቸው በግልጥ የተጠቀሰ ነገር የለም። ስለ ሰዎቹ የሚታወቀው ነገር፥ በክርስቶስ የሚያምኑ አይሁዳውያንና አሕዛብ መሆናቸው ነው። ከነዚህ ብዙዎቹ ሰማዕታት ይሆናሉ፤ ከፍዳው ጊዚ የሚተርፉት ጥቂት ናቸው። 

በአጠቃላይ እንግዲህ፥ የፍዳው ጊዜ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ዋዜማ ሲሆን፥ በኃጢአተኞች ላይ ለመፍረድና ቅዱሳንንም ለመቤዠት መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት አስፈላጊ እንደነበር ያስገነዝባል። በፍዳው ጊዜ የሚኖረውን ጭለማም ቀጥሎ ከሚመጣው የእግዚአብሔር መንግሥት ክብር ጋር ያነጻጽራል።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

46
ትምህርት 46 ከ52

የክርስቶስ ዳግም ምጽአት

ሀ. የዳግም ምጽአቱ ጠቀሜታ 

ቀደም ሲል ባሉት የዳግም ምጽእት አስተምህሮ ጥናቶች ንጥቀትን አስመልክቶ ዋና ዋና ነጥቦችን፥ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ለቅዱሳኑ፥ በምዕራፍ 12 እና ከቅዱሳኑ ጋር፥ መምጣቱን በምዕራፍ 13 ውስጥ በግልጥ ተመልክተናል። አሁን ደግሞ ክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ከቅዱሳኑ ጋር ዳግም ስለመምጣቱና ይህም ሁኔታ ጎና የሚፈጸም ዋና ትንቢት መሆኑን እንመለከታለን። በመቀጠልም ከዚህ ምዕራፍ ጋር የተያያዙት ምዕራፎች፥ ስለ ትንሣኤ፥ ስለ እግዚአብሔር ፍርድ እና ሰለ ሺህ ዓመቱ አገዛዝ ያስተምራሉ። እነዚህ ታላላቅ ጉዳዮች በአንድ ላይ በመጣመር መጽሐፍ ቅዱስ ስለታሪክ ዓሳማና መጨረሻ የሚያስተምረውን ይገልጣሉ። ይህም ደግሞ ከታሪክ አንጻር መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት መፍታት (መረዳት) እንዳለብን ያስተምረናል። 

ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥቱን በምድር ላይ ለመመሥረት የሚመጣ የመሆኑ ጠቀሜታ ብሉይና አዲስ ኪዳን ውስጥ ብዙ ስፍራ ተገልጿል። በተገለጠው መሠረት ትምህርቱ የሰው ዘር ታሪክ ማብቂያ ብቻ ሳይሆን፥ ይልቁንም የእግዚአብሔር ፕሮግራም ከፍተኛ ክንውን ነው። ይሁን እንጂ፥ የክርስቶስን ዳግም ምጽአት ትምህርት፥ እንዲሁም ክርስቶስ በምድር ላይ ስለሚመሠርተው መንግሥት የሚገልጠውን ሰፊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የማይቀበሉ ወይም የሚያቃልሉ አስተምህሮዎች አሉ። እንዲህ ያሉ አስተምህሮዎች የትንቢቶችን ትርጉምና መጽሐፍ ቅዱሳዊውን መገለጥ ይክዳሉ። 

የክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ዳግም መምጣት፥ የእግዚአብሔር ቃል ፍጻሜና የብሉይ ኪዳን ትንቢት ዋና ጉዳይ ነው። እግዚአብሔር ከአብርሃም፥ ከእስራኤል፥ ከዳዊት ጋርና እንዲሁም ለአዲስ ኪዳን የገባቸው ቃል ኪዳናት ከርሱ ፕሮግራም ጋር የተያያዙና ከሁሉ የላቁ ናቸው። መዝሙረ ዳዊት ውስጥ ካሉት መገለሶች ብዙዎቹ፥ እንዲሁም የታላላቆቹና የአናሳዎቹ ነቢያት ትንቢቶች፥ በዚህ ታላቅ ጉዳይ ዙሪያ የተካተቱ ናቸው። እንደ ዳንኤል፥ ዘካርያስ እና ራእይ ያሉ ታላላቅ የትንቢት መጻሕፍት የሚያተኩሩት በክርስቶስ ዳግም ምጽአት፥ እንዲሁም ታሪክና የመንግሥቱን ፍጻሜ በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ነው። በመሆኑም የክርስቶስ ዳግም ምጽእት አስተምህሮ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚ የሆነን ሰው አጠቃላይ ሥነ-መለኮታዊ አቋም በብዙ መልኩ ይወስነዋል። ገና የሚፈጸሙ ትንቢታዊ ሁኔታዎችን ቅደም ተከተል እንደ እግዚአብሔር ቃል መገለጥ በዝርዝርና በታማኝነት ለማቅረብ የሚደረገውን ሙከራም የሚያረጋግጥ ይሆናል። 

ለ. ስለ ዳግም ምጽአት የተነገሩ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች 

የቤተ ክርስቲያን መነጠቅ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ፈጽሞ ያልተጠቀሰና የአዲስ ኪዳን አስተምህሮ ቢሆንም (ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን በዚህ ሁኔታዋ በብሉይ ኪዳን ያልተገለጠች ምሥጢር ነበረች)፥ የዳግም ምጽአት ጉዳይ ግን ብዙዎቹ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ የዳበረ ነበር። 

የክርስቶስን ዳግም ምጽአት አስመልክቶ ከተነገሩት ግልጥ ትንቢቶች የመጀመሪያው ዘዳግም 30፡1-3 ውስጥ የተጠቀሰው ሳይሆን አይቀርም። የእስራኤልን ወደ ምድሯ መሰባሰብ አስመልክቶ በተነገረው በዚህ ትንቢት፥ ሕዝቦቿ በመንፈሳዊ ሁኔታቸው ወደ እግዚአብሔር እንደሚመለሱ ተገልጦ፥ “አምላክህ እግዚአብሔርም ምርኮህን ይመልሳል፥ ይራራልህማል፤ አምላክህም እግዚአብሔር አንተን ከበተነበት ከአሕዛብ ሁሉ መካከል መልሶ ይሰበስብሃል” (ቁ.3) ተብሏል። “መልሶ ይሰበስብሃል” የሚለው ገለጣ የሚያመለክተው፥ እግዚአብሔር በሁኔታዎች ጣልቃ የሚገባ መሆኑንና በኋሳ ከተመለከተው ጥቅስ አንጻር ደግሞ ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት ጋር በግልጥ ተገናኝቷል። 

ምንም እንኳን መዝሙራት የብሉይ ኪዳንን የአምልኮ መጻሕፍት የሚያካትቱ ቢሆኑ፥ በተደጋጋሚ የሚገልጡት ግን ስለ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ነው። መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 2 ውስጥ እግዚእብሔር ከሕዝቦች ጋር ያደረገውን ክርክር ይገልጣል። የዓለም ገዢዎች እግዚአብሔርንና ሥልጣኑን ያለመቀበል ፍላጎት ቢኖራቸውም፥ የዳዊት ዓላማ ግን ““እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ፥ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ” (መዝ. 2፡6) የሚል ነው። ይህ እግዚአብሔር የሚሾመው ንጉሥ ኃጢአተኞችን የሚያጠፋ መሆኑን ይሄው መጽሐፍ እንዲህ በማለት ይተነብያል፡- “ዕብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ትቀጠቅጣቸዋለህ” (ቁ.9)። 

መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 22፥ 23 እና 24 ውስጥ ክርስቶስ ነፍሱን ስለ በጎቹ እንደሚሰጥ መልካም እረኛ ዮሐ. 10፡11)፥ የራሱ ለሆኑት ሁሌ ለመማለድ እንደሚኖር ታላቅ እረኛ (ዕብ, 13፡20)፥ እና ለታማኞቹ እረኞች ዋጋቸውን ለመስጠት እንደ ክብር ንጉሥ እንደሚመጣ የእረኞች አለቃ (1ኛ ጴጥ. 5፡4) ተጎልጧል። ምዕራፍ 24 የሺህ ዓመቱን መንግሥት ሁኔታ ሲገልጥ፥ “ምድርና ሞላዋ የእግዚአብሔር ናት” (ቁ.1) ይላል። የኢየሩሳሌም በሮች የክብር ንጉሥን ይቀበሉ ዘንድ ይከፈቱ ተብሏል (24፡7-10)። 

መዝሙር 50፡2 ውስጥ ክርስቶስ ጽዮን ላይ ሆኖ ዓለምን የሚገዛ መሆኑ ተገልጧል። ስለ ሺህ ዓመቱ መንግሥት በምናጠናበት ጊዜ በኋላ እንደምንመለከተው፥ መንግሥታትን ሁሉ ለመግዛት ወደ ምድር የሚመጣ መሆኑ መዝሙር 72 ውስጥ ተጎልጧል። መዝሙር 89፡36 ደግሞ በዳዊታዊው ቃል ኪዳን መሠረት ከዳግም ምጽአቱ በኋላ የክርስቶስ ዙፋን የሚመሠረት መሆኑን ይገልጣል። መዝሙር 96 የእግዚአብሔርን ሞገስና ክብር ካመለከተ በኋላ፥ ምድርና ሰማይ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይላቸዋል፤ ይመጣልና፤ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፤ እርሱም ዓለምን በጽድቅ እሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል” (ቁ. 13) ይላል። 

ክርስቶስ በአሁኑ ጊዜ በአብ ቀኝ መሆኑ መዝሙር 110 ውስጥ ተገልጧል፤ ጠላቶቹን እንደሚገዛና ኃይልና ሥልጣኑም ከጽዮን እንደሚወጣ ተመልክቷል (ቁ. 2 እና 6)። ዳግም የመምጣቱና ምድርን የመግዛቱ እውነት በነዚህ ትንቢቶች ግልጥ ነው። ይህ እውነት የብሉይ ኪዳን ዋና መገለጥ ወይም ራእይ ነው። 

ጉዳዩ የዋና ዋናዎቹና አነስተኞቹ ነቢያት መልእክት ዋና ፍሬ እሳብ መሆኑ ተረጋግጧል። በኢሳይያስ 9፡6-7 ታላቅ ትንቢታዊ ገለሳ፥ ክርስቶስ እንደተወለደ ሕፃንና ““ኃያል አምላክ” ተገልጧል። ዳዊት ዙፋን ላይ የሚመሠረተው መንግሥቱ ፍጻሜ የለውም። ኢሳይያስ ምዕራፍ 11-12 ውስጥ ባለው ክፍል ደግሞ ክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ዳግም የመምጣቱ ውጤት ጉልህ ምስል ተስሏል። ይህ ጉዳይ ስለ ሺህ ዓመቱ መንግሥት በምናጠናበት ክፍል ይብራራል። የመንግሥቱ አገዛዝ መቅደም ግን ስለ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት በትክክል በተገለጠውና በኃጢአተኞች ላይ በሚገለጠው መለኮታዊ ኃይል ትምህርት ላይ የሚመሠረት ይሆናል። ክርስቶስ ዳግም ምጽአቱ በምድር ላይ የሚፈርድበት ትክክለኛ ትዕይንትም ኢሳይያስ 3፡1-6 ውስጥ ተገልጧል። 

የአሕዛብ ዘመንና እግዚአብሔር ለእስራኤል ያለው ፕሮግራም በተገለጠበት የዳንኤል ትንቢት፥ የሁለቱም ክንውኖች ፍጻሜ ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት ጋር ተዛምዷል (ዳን. 1፡13-14)። ይህ ከፍል የክርስቶስን ዳግም ምጽአት እንዲህ በማለት ይገልጠዋል፡- በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እሆም የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ፥ በዘመናት ወደሸመገለውም ደረሰ፤ ወደፊቱም አቀረቡት። ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ከብር መንግሥትም ተሰጠው፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው”። ዳንኤል የናቡከደናፆርን ሕልም በፈታበት ዳንኤል 2:44 ውስጥም “ዘላለም የማይፈርስ መንግሥት” በማለት ይህንኑ እውነት ተንብዮ ነበር። 

ብዙዎቹ አነስተኛ ነቢያትም በተለይ ዘካርያስ፥ ይህን ፍሬ አሳብ በተመሳሳይ ሁኔታ ይጠቅሱታል። ዘካርያስ 2: 10-11 ውስጥ ባለው ክፍል እንዲህ ተብሏል፡- የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እነሆ መጥቼ በመካከልሽ እኖራለሁና ዘምሪ፥ ደስም ይበልሽ ይላል እግዚአብሔር። በዚያን ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፥ ሕዝብም ይሆኑኛል፤ በመካከልም እኖራለሁ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወደ አንቺ እንደ ላከኝ ታውቂያለሽ”። ይህ በትክክል የሚያመለክተው ክርስቶስ በዳግም ምጽአቱ ምድርን ለሺህ ዓመት የሚገዛት መሆኑን ነው። ይህ ጉዳይ ዘካርያስ 8፡3-8 ውስጥ በበለጠ ግልጥነት እንዲህ ተመልክቷል፡- “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ወደ ጽዮን ተመልሻለሁ፤ በኢየሩሳሌምም መካከል እኖራለሁ፤ ኢየሩሳሌምም የእውነት ከተማ ትባላሳች፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ተራራ፥ የተቀደሰ ተራራ ይባላል” (ቁ.3)። ከቁጥር 4-8 ባለው ክፍል ዳግም የእስራኤል ልጆች ከዓለም ሁሉ ተመልሰው ኢየሩሳሌም ውስጥ እንደሚኖሩና፥ ልጆቻቸውም በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ እንደሚቦርቁ ይገልጣል። 

ዘካርያስ 14:1.4 ውስጥ የተጠቀሰው ቃል የክርስቶስን ዳግም መካከለኛው ምሥራቅንና ኢየሩሳሌምን የሚያጥለቀልቃት የዓለም ጦርነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ እንደሚሆን ያስገነዝባል። ይህንን ዘካርያስ፥ በዚያን ቀን እግሮቹ በኢየሩሳሌም ትይዩ፥ በምሥራቅ በኩል ባለው ሰደብረዘይት ላይ ይቆማሉ፤ ደብረዘይትም በመካከል ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ይሰነጠቃል፥ እጅግም ታላቅ ሽለቆ ይሆናል፤ የተራራውም እኩሌታ ወደ ሰሜን፥ እኩሌታውም ወደ ደቡብ ይርቃል” (ቁ.4) በማለት ይገልጠዋል። 

በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ጊዜ የደብረዘይት ተራራ ሁለት ላይ የመሰንጠቁ ጉልህ ገለጣ የሚያመለክተው ከዚያ ቀደም ከተከናወኑ ነገሮች ሁሉ የከርስቶስን ዳግም ምጽአት የሚተካከል አለመኖሩን ነው። የክርስቶስ ዳግም ምጽአት በጰንጠቆስጤ ዕለት፥ ወይም ኢየሩሳሌም ሰፈረሰችበት 70 ዓ.ም. ተከናውኗል የሚለው ትምህርት ከሌሎች መሰል ትንቢቶች ጋር የሚቃረን ነው። የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ወደፊት የሚከናወን መሆኑን የሚያመለክቱ ትንቢቶች (ለምሳሌ ራእይ) ይህን አተረጓጎም ይቃረኑታል፤ በዚህ ምንባብ እንደተመለከተው፥ የደብረዘይት ተራራ ሳይለወጥ መኖሩም አሳቡን ውድቅ ያደርገዋል። 

ልክ ሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 1 ውስጥ እንደተጠቀሰውና ክርስቶስ በዕረገ ጊዜ እንደሆነው ሁሉ እግሮቹ ደብረዘይት ተራራ ላይ ሲያርፉ፥ ኢየሩሳሌም ዙሪያ ያለው መልክዓ-ምድር ለውጥ ይታይበታል። ይህም ወዲያው ለሚመሠረተው መንግሥት ዝግጅት ነው። ስለዚህ፥ ስለ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት የሚያመለክተው ትንቢት እንዳለፈ ሁኔታ ሊቆጠር አይገባም። የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ቅዱሳን ሲሞቱ ወደ እነሱ መጥቶ እንደሚቀበሳቸው ተደርጎም ሆነ፥ ሌላ ዓይነት መንፈሳዊ መልክ ያለው ተደርጎ ሊወሰድ አይገባም። ስለ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ብሉይ ኪዳን ውስጥ የተገለጠው ትንቢት የሚያስረዳው፥ የዓለምን ታሪክ ፍጻሜ ነው። ይህም የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ክርስቶስ የሞተላትን ዓለም የሚረከብበት፥ እንዲሁም ለእርሱ አልገዛም ባለው ዓለም ላይ ኃይልና ሥልጣኑን የሚያሳርፍበት ጊዜ ይሆናል። 

ሐ. የክርስቶስ ዳግም ምጽአት በአዲስ ኪዳን ገለጣ መሠረት 

የክርስቶስን ዳግም ምጽአት በተመለከተ፥ ከቤተ ክርስቲያን መነጠቅ ጋር በተገናኘ ሁኔታ አዲስ ኪዳን ውስጥ ልዩ ነገር ተገልጧል። የክርስቶስን ቀዳሚና ዳግም ምጽአት አስመልክቶ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ያለው ትንቢት ብዙ ጊዜ ይደበላለቃል። በዚህም ሳቢያ ምናልባት ሁለቱን ክንውኖች መለየቱ ችግር የነበረው ሳይሆን አይቀርም። ቀዳሚው የክርስቶስ ምጽአት የተከናወነ እንደመሆኑ፥ ከሥቃዩና ከክብሩ ጋር የሚዛመዱ ትንቢቶችን በማነጻጸር ረገድ ችግር አይኖርም። 

ይሁን እንጂ፥ በአዲስ ኪዳን ክርስቶስ ለቅዱሳኑ መምጣቱንና፥ ከቅዱሳኑ ጋር መምጣቱን የሚያሳዩት አባባሎች ተመሳሳይ በመሆናቸው፥ ስለየትኛው መምጣቱ እንደሚናገሩ ለመለየት ብዙ ጊዜ ግልጥ ስለማይሆን፥ የእያንዳንዱ ገለጣ ትክክለኛነት የሚለየው በቃሉ አገባብ መሆን አለበት። ያም ቢሆን የክርስቶስ ወደፊት መምጣት ጉዳይ የአዲስ ኪዳን ዋና ፍሬ እሳብ ነው። የጌታኝ ምጽአት ክሚናገሩት ሀያ አምስት ጥቅሶች አንዱ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ይህንኑ አሳብ የሚያመለክት መሆኑ ይገመታል። ለአዲስ ኪዳን ዋና ዋና መገለጦች አስተዋጽኦ ያላቸው ቢያንስ ሀያ አንኳር ምንባቦችን ለመምረጥ ይቻላል (ማቴ. 19፡28፤ 23፡39፤ 24፡3-25፡46፤ ማር.13፡24-37፤ ሉቃስ 12፡35-48፤ 17፡22 37፤ 18፡8፤ 21፡25-28፤ ሐዋ. 1፡10-11፤ 15፡16-18፤ ሮሜ 11፡25-27፤ 1ኛ ቆሮ. 11፡26፤ 2ኛ ተሰ. 1፡7-10፤ 2ኛ ጴጥ. 3፡3-4፤ ይሁዳ 14 ፥ 15፤ ራዕይ 1፡7-8፤ 2፡25-28፤ 16፡15፤ 19፡11-21፤ 22፡2ዕን። 

ቀደም ሲል ማቴዎስ 13ትን ስናጠና ካገላጥናቸው እውነቶች በተጨማሪ፥ ትኩረት የሚሹ ዋና ዋና ነጥቦችንም መጎንዘቡ ተገቢ ነው። 

1. የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ከመከራው ወቅት በኋላና ከሺህ ዓመቱ እገዛን በፊት የሚከናወን ነው። ዳግም ምጽአቱን አስመልክቶ የተነገሩት ትንቢቶች ቃል በቃል ትርጉም፥ ክርስቶስ ለሺህ ዓመታት በምድር ላይ ለመግዛት የመምጣቱ መክፈቻ መሆኑን ያመለክታል። ክርስቶስ ለቅዱሳኑ መምጣቱን፥ ማለት የቤተ ክርስቲያን መነጠቅን ከዚህ ስመለየትም ያገለግላል። 

ወደፊት በምድር ከሚመሠረተው የጌታ መንግሥት ጋር በተዛመደ ሁኔታ ላተነገረ ትንቢት መንፈሳዊ ይዘት የሚሰጡ ወገኖች አሉ። በዚህም አመለካከታቸው ስለመነጠቅና ስለ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት የተነገሩ ትንቢቶችን እንደ ክንውን አድርጎ የማቅረብ ዝንባሌም ይታይባቸዋል። በዚህ ትንታኔያቸው መሠረት ነው መነጠቅን ከመከራው ጊዜያት በኋላ የሚከናወን ነው የሚሉት። 

የክርስቶስ ዳግም ምጽእትን የሚያሳይ ትንቢትን ቃል በቃል የሚረዱ ወገኖች ደግሞ የሺህ ዓመቱ መንግሥት ምድር ላይ ከመመሥረቱ በፊት ይከናወናል በማለት ያምናሉ። ከቤተ ክርስቲያን መነጠቅ የተለየ አድርገውም ይረዱታል። ክንውኖቹም በዓላማ፥ በባሕርይና በይዘት ይለያያሉ። 

የዚህ መጽሐፍ አንዱ ደራሲ የሆኑት ጆን ኤፍ ዋልቮርድ “የንጥቀት ጥያቄዎች”፥ በሚለው መጽሐፋቸው፥ መነጠቅ ክመክራው ጊዜ በፊት እንደሚሆንና ክርስቶስ መንግሥቱን በምድር ለመመሥረት ዳግም መምጣቱ ደግሞ ከመከራው ዘመን በኋሳ መሆኑን ለማረጋገጫነት፥ ኀምሳ ምክንያቶችን አቅርበዋል። እኚሁ ሰው “የሺህ ዓመቱ መንግሥት? በሚለው ጽሑፋቸው ባቀረቡት መከራከሪያ፥ በምድር ስለሚመሠረተው መንግሥት ከታሪካዊና ሥነ-መለኮታዊ ይዘቱ አንጻር ማስገንዘቢያ አቅርበዋል። ምንም እንኳን የሥነ-መለኮት ምሁራን ሰነዚህ ነጥቦች ያለመስማማታቸው ነገር የሚኖር ቢሆን፥ ጉዳዩ በአብዛኛው የሚወሰነው ግን ቃሉን ለመፍታት በምንገለገልበት መመሪያ ይሆናል። ትንቢትን ቃል በቃል የሚተረጉሙና ዝርዝር ጉዳዮቹን ካግንዛቤ የሚያስገቡ ክፍሎች፥ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ከመከራው ጊዜ በኋላ እና ከሺህ ዓመቱ መንግሥት በፊት ነው የሚለውን ማጠቃለያ አሳብ ሊደግፉ ይችላሉ። 

2. ስለ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት የሚገልጡት ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሁሉ ምጽአቱ እንደ ዕርንቱ መህንን ያስገነዝባሉ። ይህ ሁኔታ ሐዋርያት ሥራ 1፡11 ውስጥ እንደተገለጠው፥ የክርስቶስን ዕርገት በማየት ሽቅብ ይመለከቱ ለነበሩት ደቀ መዛሙርት በተናገሯቸው መላእክት ቃል እንዲህ ተረጋግጧል፡- “ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል”። ይህ የሚያመለክተው መነጠቅን ሳይሆን የክርስቶስን ዳግም ምጽአት ነው። ወደ ሰማይ እንደሄደ፥ እንዲሁ ወደ ምድር ይመለሳል። ይህ ጉዳይ ማቴዎስ 24፡27-31 እና ራእይ 19፡11-16 ውስጥ የተጠቀሱትን በመሳሰሉ ዋና ዋና ምንባሶችም የተደገፈ ነው። 

ዳግም ምጽአቱን የሚያመለክቱ ምንባቦች አመጣጡ እንደ ዕርገቱ መሆኑን በግልጥ ያስረጳሉ። ክርስቶስ ከመለኮታዊነቱ የተነሣ በሁሉም ስፍራ የመገኘት ባሕርይ ቢኖረውና በአንድ ጊዜ በሰማይም ሆነ በምድር መገኘት ሲችልም፥ አካሉ በሰፍራ የሚኖር ነው፤ አሁንም በአብ ቀኝ አለ። በዳግም ምጽአቱ ወደ ሰማይ እንዳረገ፥ እንዲሁ በአካል ይመለሳል። አባባሉ ዘካርያስ 14፡4 ውስጥ የተደገፈ ነው፡- “በዚያን ቀን እግሮቹ በኢየሩሳሌም ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረዘይት ላይ ያቆማሉ። ይህ እውነት ሐዋርያት ሥራ 1 ውስጥ ወደ ሰማይ እንደሄደ እንዲሁ የሚመለስ መሆኑ በተገለጠው መሠረት የሚከናወን ነው። 

መላው ዓለም የክርስቶስን ክብር የሚያይ ስለመሆኑ ምንም ማረጋገጫ ካልተነገረለት መነጠቅ ኃር ሲነጻጸር፥ ዳግም ምጽአቱ በግልጥ የሚታይና በክብር የተሞላ ይሆናል። አመጣጡ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ የሚበራ መብረቅ እንደሚመስል ክርስቶስ ራሱ ገልጧል (ማቴ. 24፡27)። ሐዋርያት ሥራ 1፡11 ውስጥ እንደተመለከተው፥ ዕርገቱ የሚታይ እንደነበር ሁሉ ዳግም ምጽአቱም ግልጥና የሚታይ ይሆናል። “ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል” ተብሎ ነው ስለ ክርስቶስ የተነገረው። 

ክርስቶስ ማቴዎስ 24፡30 ውስጥ እንዲህ ብሏል፡- “የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር፥ በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል።” የራእይ መጽሐፍ ዋና ገለጣ የሚያመላክተው፥ ክርስቶስ በዳግም ምጽአቱና በሚቀጥለው የመንግሥቱ አገዛዝ ወቅት ለዓለም የሚታይ መሆኑን ነው። ራእይ 1፡7 ውስጥ የተጠቀሰው ቃል ሲገልጥ፥ “እነሆ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ” ይላል። ክርስቶስን የሚያዩት በሞትና በሥቃይ እንደነበረ ተራ ናዝራዊ፥ ወይም በአንዳንድ ሁኔታ ክብሩ ተሸፍኖ በዐረገበት ምድራዊ አካሉ አይደለም። 

የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ቀደም ሲል ራእይ 1፡12-18 ውስጥ ለዮሐንስ እንደተገለጠው፥ የእግዚአብሔር ልጅ ክብር በሙላት የሚገለጥበት ይሆናል። ይህ ጉዳይ ራእይ 19፡11-16 ውስጥም በዝርዝር ተገልጧል። በዚህ መሠረት እንግዲህ፥ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት በዘመናት ሁሉ ከታዩት ይልቅ አስደናቂ ይሆናል። አዳም ኤደን ገነት ውስጥ ኃጢአት በሠራና የገዢነት ሥልጣኑን ባጣ ጊዜ፥ የተጀመረው የእግዚአብሔር አጠቃላይ ፕሮግራም ፍጻሜም ይሆናል። 

3. የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ወደ ምድር የመምጣቱንና የመግዛቱን ተዛምዶ ስለሚያመለከት፥ ከምድር ጋር የተያያዘ እንጂ እንደመነጠቅ በአየር ላይ የመገናኘት ጉዳይ እይደለም። ክርስቶስ ጽዮን ላይ ሆኖ ስለመግዛቱ፥ ወደ ጽዮን ስለመምጣቱ ወይም ከጽዮን ሰለመሄዱ ብዙ ምንባቦች ይናገራሉ፤ ሁሉም የኢየሩሳሌም ከተማን ነው የሚያመለክቱት (መዝ. 14፡7፤ 20፡2፤ 53፡6፤ 110፡2፤ 128፡5፤ 134፡3፤ 135፡21፤ ኢሳ. 2፡3፤ ኢዩ. 3፡16፤ አሞጽ 1፡2፤ ዘካ. 14፡1-4፤ ሮሜ 11፡26)። በመጽሐፍ ቅዱስ ገለጣ መሠረት፥ የክርስቶስ ምጽአት እግሮቹ ደብረዘይት ተራራ ላይ ማረፋቸው ብቻ ሳይሆን፥ ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት በመሞከር ላይ ያሉትን ሠራዊቶች የመደምሰስ ተልእኮም አለው (ዘካ. 14፡1-3)። 

የክርስቶስ ዳግም ምጽአት፥ ቅዱሰን መላእክትና በዘመናት ሁሉ በሰማይ የተከማቹ ቅዱሳን የሚያጅቡት ይሆናል። ይህ ክንውን ክርስቶስ ለቅዱሳኑ የሚመጣበት ሳይሆን፥ ከቅዱሳኑ ጋር ወደ ምድር የሚመስዕበት ነው። የዳግም ምጽአቱ አንድ ዋና ዓሳማ ገና በምድር ያሉትንና የሚሠቃዩትን ቅዱሳን ማዳን ቢሆንም፥ ማቴዎስ 25፡31 ውስጥ የተጠቀሰው ቃል እንደሚገልጠው መላእክት ሁሉ ከእርሱ ጋር ይመጣሉ። የሰማይ ሠራዊት ሁሉ ከእርሱ ጋር እንደሚሆኑ የሚያስረዳውና ራእይ 19፡11-21 ውስጥ ያለው ቃል ይህን እሳብ ያበልጥ ይገልጠዋል። የዚህ ሠራዊት አባላት ቅዱሳን መላእክትና በሰማይ ያሉ ቅዱሳን እንደሚሆኑ አይጠረጠርም። የክርስቶስ ዳግም ምጽአት የምርጦች ማለት፥ ትንሣኤ ያገኙት፥ የታጠቁና በምድር ላይ በተፈጥሯዊ አካላቸው ያሉትም መሰብሰቢያ ጊዜ ይሆናል። ሁሉም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሰዚህ አስደናቂ ዳግም ምጽአት ይሳተፋሉ። 

4. የዳግም ምጽአቱ ዓላማ በምድር ላይ ለመፍረድ ነው (መዝ. 6፡13)። የዚህ ጉዳይ ዝርዝር ትምህርት፥ በእስራኤል፥ በመንግሥት፥ በሰይጣንና በወደቁ መላእክት ላይ ሊሶጥ ያለውን ፍርድ በምናጠናበት ጊዜ በተከታታይ ይቀርባል። እነሱም ከእርሱ ጋር በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ላይ እንደሚፈርዱ ማቴዎስ 19፡28 ውስጥ ክርስቶስ ለአስራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ነግሯቸዋል። ማቴዎስ 25፡31-46 ውስጥ ደግሞ፥ በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ወቅት አሕዛብ የሚፈረድባቸው መሆኑ ተገልጧል። ሕዝቅኤል 20፡35-38 ውስጥም በዚሁ ወቅት በእስራኤል ላይ ፍርድ እንደሚኖር ተነግሯል። ከዳግም ምጽአቱ ቀደም ሲል በሚኖረው የስደት ጊዜ የሚሞቱት ከሙታን ተነሥተው የሚፈረድባቸው መሆኑ ራእይ 20፡4 ውስጥ ተመልክቷል። 

ይህ ጉዳይ የመጨረሻውን ጊዜ አስመልክቶ ወንጌላት ውስጥ በተነገሩ ልዩ ልዩ ምሳሌዎች ውስጥ ከመገለጡም በላይ፥ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥም በተደጋጋሚ ተጠቅሷል (ሉቃስ 12፡37፥ 45-47፤ 17፡29-30፤ 2ኛ ተሰ. 1፡7-9፤ 2፡8፤ ይሁዳ 15፤ ራእይ 2፡27፤ 19፡15-21)። በአሁኑ ጊዜ ኃጢአተኝነቷን እንዲሁም አለማመኗን እንድትገልጥ የተተወችውና እግዚአብሔር እንደሌለ በመቁጠር የምትኖረው ምድር፥ በእግዚአብሔር ጳድቅ ፍርድ ሥር ትወድቃለች። 

ፍርዱ እጅግ ሰፊ ሲሆንም፥ ምድርን ሙሉ በሙሉ አያጠፋትም። 2ኛ ጴጥሮስ 3፡10 ውስጥ የተጠቀሰው በእሳት የመቅጣት ፍርድ፥ የአሁኒቱ ምድርና የአሁኑ ሰማይ በፍጹም ጠፍተው በምትካቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እስከሚፈጠርበት እሰከ ሺህ ዓመቱ መንግሥት ፍጻሜ ድረስ አይከናወንም። 

በመነጠቅ ወቅት የሚጀመረው፥ እንዲሁም በዋዜማውና በዳግም ምጽአቱ ማግሥት የሚከናወኑ ፍርዶችን የሚያካትተው የእግዚአብሔር ቀን የሚጠቃለለው፥ ስሺህ ዓመቱ መንግሥት ፍጻሜና በአሁኗ ምድርና ሰማይ መጥፋት ነው። በአሁኒቱ ዓለማችን ላይ ኃጢእት የሚኖረው ድል ጊዚያዊ ሲሆን፥ የጽድቅ ድል ግን ዘላለማዊ ነው። 

5. የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ሦና ዓላማ፥ በመከራው ወቅት ከእስራኤልም ህን ከአሕዛብ ከሰማዕትነት የተረፉትን ነጻ ማውጣት ነው። ማቴዎስ 24፡22 ውስጥ እንደተጠቀሰው፥ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ሳልተወሰነ ጊዜ የሚዘገይ ቢሆን ኑሮ፥ ወደ ምድር የሚፈሱት አሠቃቂ ፍርዶች የሰውን ዘር በሙሉ ያጠፉት ነበር። ይህ የመከራ ወቅት የተመረጡትን ከሥቃዩ ለመታደግ ሲባል በሚከናወነው የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ሳቢያ ያጥራል። ሮሜ 11፡26-27 ውስጥ እስራኤል የዳነች ወይም ነጻ የወጣች ተብላለች። ይህ አሳብ ሉቃስ 21፡28 ውስጥ “ቤዛችሁ” በሚለው ቃል ተደግፏል። ዘካርያስ 14:4 ውስጥ እንደተጠቀሰው ያሉ የብሉይ ኪዳን ምንባቦችም ይህን ቤዛነት ገልጠውታል። 

ይሁን እንጂ፥ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት በኃጢአተኞች ላይ ፍርድ የሚያመጣና ጻድቃንን የሚያድን ብቻ ሳይሆን፥ አዲስ መንፈሳዊ ሁኔታንም ያሰፍናል። ይህን አሳብ ስለ ሺህ ዓመቱ መንግሥት በምናጠናበት ጊዜ እንደገና እንመለከተዋለን። በኃጢአተኞች ላይ ፍርድ የሚያመጣው ይህ ሁኔታ፥ በክርስቶስ ላመኑት መንፈሳዊ መነቃቃትን ይሰጣቸዋል። ይህ አሳብ ሮሜ 11፡26-27 ውስጥ ባለው ቃል የተደገፈና ኤርምያስ 31፡31-34 ውስጥ በሰፈረው አዲስ ቃል ኪዳን የተጠቃለለ ነው። 

6. የክርስቶስ ዳግም ምጽአት የዳዊትን ዙፋን እንደገና ፆመመሥረት ዓላማም አለው። ሐዋርያት ሥራ 15 ውስጥ እንደተመለከተው፥ በቤተ ክርስቲያንና በእሕዛብ መካከል ሊኖር ስለሚገባው ግንኙነት ኢየሩሳሌም ውስጥ በነበረው ጉባኤ ውይይት ተደርጎ ነበር። በጉባኤው እንደተገለጠው እንዲሁም አሞጽ 9፡11-15 ውስጥ የተጠቀሰው ቃል እንደሚያስረዳው፥ መጀመሪያ ለአሕዛብ ሰረከት የሚመጣ፥ ለጥቆ ደግሞ የዳዊት ድንኳን ትንሣኤ የሚሆን መሆኑ ተረጋግጧል። ይህ ከእስራኤሳውያን መሰባሰብና ፈጽሞ ዳግም ላለመበተን ምድራቸው ላይ ከሚሰፍሩበት ክንውን ጋር በአንድ ላይ የሚሆን ነው (አሞፅ 9: 14-15፤ ሕዝ. 39፡25-29)። የእስራኤላውያን መሰባሰብ፥ የዳዊት ዙፋን እንደገና መመሥረትና በእስራኤል ቤት ሳይ የእግዚአብሔር መንፈስ መፍሰሱ (ሕዝ. 39፡29)፥ እስራኤልንና በሌላው የዓለም ክፍል ያለውን ሕዝብ ለሚመጣው የእግዚአብሔር መንግሥት ክብር በአንድ ላይ ያዘጋጃቸዋል። ሕዝቅኤል 37፡24 ውስጥ በተጠቀሰው ቃል እንደተረጋገጠው፥ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳንም የዚህ መንግሥት ተሳታፊዎች ይሆናሉ። ዳዊትም ከክርስቶስ በታች የእስራኤል ልዑል ይሆን ዘንድ በዚህ ወቅት ይነሣል። ሉቃስ 1፡31-33 ውስጥ ለማርያም እንደተገለጠው፥ ክርስቶስ በእስራኤል ቤት ላይ ለዘላለም ይነግሥ ዘንድ ዳግም መምጣቱ የእግዚአብሔር ዓላማ ነው። 

ሲጠቃለል፥ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት፥ በታላቁ መከራ ፍጻሜና በሺህ ዓመቱ መንግሥት መጀመሪያ ላይ የሚከናወን ታላቅ ድርጊት ነው። ክርስቶስ በአካል የሚመለስበትና ዓለም ሁሉ በግልጥ እንዲያየው የሚደረግበት የእግዚአብሔር ክብር መገለጫም ነው። ከሰማይ ሳይሆን ከምድር ጋር፥ በተለይም ከኢየሩሳሌም ማለት ከደብረዘይት ተራራ ጋር የተያያዘ ክንውን ይሆናል። 

ከርስቶዕ በዳግም ምጽአቱ በቅዱሳንና በመላእክት ይታጀባል። የዳግም ምጽአቱ ዓላማም በዓለም ላይ ለመፍረድ፥ ከአይሁድም ሆነ ከአሕዛብ በእርሱ የሚያምኑትን ለማዳን፥ ለእስራኤላውያንና ለሌላው ሕዝብ መንፈሳዊ ትንሣኤን ለማምጣት፥ የዳዊትን ዙፋኝ እንደገና ለመመሥረትና የመጨረሻው ሥፍረ-ዘመን ክንውን የሆነውን የሺህ ዓመት መንግሥቱን ለመመሥረት ነው። ከዳግም ምጽአቱ ጋር የተያያዘው የትንሣኤና የፍርድ ትምህርት በዚህ ክንውን መሠረትነት ሊታይ ይችላል።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

47
ትምህርት 47 ከ52

ትንሣኤዎች

ሰዎች ሁሉ በአንድ ጊዚ ይነግሉ ከሚሰው ድጋፍ-አልባ ንድፈ-አሳብ ሳቢያ በትንቢት አተረጓጎም ዙሪያ እያሌ ውዝግብ ሲፈጠር ቆይቷል። ይህ ንድፈ-አሳብ መጽሐፍ ቅዱዕ ሰለተለያዩ ትንሣኤዎች ያስቀመጣቸውን ዝርዝር ጉዳዮች ጎለል ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ የሚያቀርብልን ወደ ሰባት የሚደርሱ ትንሣኤዎችን ነው። ከእነዚህም አንዳንዶቹ ከዚህ በፊት የተከናወኑ ሲሆኑ፥ ሌሎቹ ደግሞ በረዥም ክፍለ-ጊዚያት የተራራቁ ናቸው። እነዚህም ከክርስቶስ የሺህ ዓመታት አገዛዝ ቀድመው ወይም ተከትለው የሚፈጸሙ ትንሣኤዎች ናቸው። ሁሉም በየራሳቸው ጊዜና ቦታ እንደሚሠ እና የሰው ዘር ሕልውና ግን ለዘላለም እንደሚቀጥል መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። የትንሣኤው ትምህርት ጥናት እንደሚያመለክተው፥ ይህን የክርስትና እምነትና ተስፋ ማዕከላዊ እውነት በተመለከተ ትንቢታዊው ፕሮግራም ውስጥ ጠቃሚ መግለጫ አለ። 

ሀ. የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ 

በትንሣኤዎች ቅደም ተከተል መሠረት፥ ቀዳሚውን ስፍራ የያዘው የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው። ያም በብሉይ ኪዳን ትንቢት (እንደ መዝሙር 16፡9-10)፥ ሰአራቱ ወንጌላትና በሥነ-መለኮታዊ ረገድ ደግሞ ከሐዋርያት ሥራ ጀምሮ አዲስ ኪዳን ውስጥ የተብራራ ጉዳይ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ 1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 15 ውስጥ በስፋት እንደሚሟገተው፥ የክርስቶስ ትንሣኤ የክርስቲያን እምነትና ተስፋ ሁሉ የሚያርፍበት ማዕከላዊ ትምህርት ነው። ከአንድ የሚበልጡ ትንሣኤዎች እንዳሉ የሚያረጋግጡትን ሐቆች በምንመለከትበት ጊዜ፥ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ቀደም ሲል የተፈጻመ ልዩ ክሥተት መሆኑን ሁሉም ሊቀበሉት ይገባል። 

ለ. የኢየሩሳሌሙ የቅዱሳን ትንሣኤ 

ማቴዎስ 27፡52-53 ውስጥ ያለው ቃል እንደሚያስረዳን፥ ክርስቶስ ከሞት በተነሣ ጊዜ የቅዱሳንም ምሳሌነት ትንሣኤ ተካሂዷል። በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ወቅት የሚከተለው ክሥተት እንደተፈጸሙ ምንባቡ እንዲህ ይጎልጣል፡- “መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ። ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።” 

ይህን እንግዳ ክሥተት በተመለከተ የቀረበ ማብራሪያ የትም አይገኝ። መቃብሮች በክርስቶስ ሞት ጊዜ ቢከፈቱም፥ ክርስቶስ እስከተነሣበት ጊዜ ድረስ ቅዱሳኑ ከሞት ያልተነሡ ይመስላል። ለዚህም ምክንያቱ፥ በኩራት የሆነው ክርስቶስ ለዘላለም በማይጠፋ የትንሣኤ አካል ከሞት በመነሣት የቀዳሚነቱን ስፍራ እንደያዘ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ መናገሩ ነው። በአንጻሩም እንደ አልዓዛር ከሞት የተነሡ ሰዎች እንደገና ሞተው ተቀብረዋል። ክርስቶስ ግን ዳግም ወደ መቃብር ላይመለስ ነው የተነሣ። 

በክርስቶስ ትንሣኤ ተነሡትና በአንጻራዊነት አነስተኛ ቁጥር ለነበራቸው ቅዱሳን ትንሣኤ ተስማሚ ፍች ሊሆን የሚችል እሳብ ባለፈው በተፈጸመው የሌዋውያን መሥዋዕት ክንውን ውስጥ የሚገኝ ይመስላል። ሦስተኛው የመከር በኩራት በዓል (ዘሌ. 23፡9-14) ከሚያካትታቸው ነገሮች አንዱ፥ በመከሩ መጀመሪያ እስራኤላውያን የበኩራቱን ነዶ በእግዚአብሔር ፊት የሚወዘውዙበትና፥ ቀጣዩን መከር በመጠበቅ ተስማሚ መሥዋዕት የሚያቀርቡበት ሥርዓት ይገኝበታል። በክርስቶስ ትንሣኤ ወቅት የሆነው የነዚያ ቅዱሳን ትንሣኤ በኩርነት በመወከል፥ ክርስቶስ በትንሣኤው ብቻውን እንዳልሆነና ለሚመጣው ታላቅ መከር የፈር ቀዳጅነቱን ተግባር እንደሚወጣ ያሳያል። እነዚህ ቅዱሳንም የትንሣኤ ምሳሌዎች ነበሩ። 

ምንም እንኳን አንዳንድ ሰዎች ማቴዎስ ወንጌል ውስጥ የሚገኙትን ማጣቀሻዎች እንደ አልዓዛር ትንሣኤ ወደ ሕይወት መመለስ ብቻ እድርገው ቢተረጉሟቸው፥ በክርስቶስ ትንሣኤ ወቅት መፈጸሙ ዘላቂ ትንሣኤን የሚያመለክት ነው። ስለሆነም፥ እነዚህ ቅዱሳን ተልእኳቸውን ከፈጸሙ በኋላ ወደ ሰማይ ያረጉ መሆናቸው አያጠራጥርም። ያም ሆነ ይህ+ የእነዚህ ቅዱሳን ትንሣኤ፥ ትንሣኤዎች ሁሉ በአንድ ታላቅ የወደፊት ትንሣኤ እንደማይጠቃለሱ የሚያረጋግጥ ታሪካዊ ክሥተት ነው። 

ሐ. የቤተ ክርስቲያን ትንሣኤ 

ቀደም ሲል ክርስቶስ ለቅዱሳኑ ሰሰሚመጣበት ሁኔታና ስለመነጠቅ በተነሣው ትምህርት ውስጥ እንደተገለጠው፥ ክርስቶስ የራሱ ለሆኑት ሲመጣ በርሱ የሞቱት ይነሣሉ። ከዚያም በሕይወት ከነበሩትና ከሚለወጡት ክርስቲያኖች ጋር፥ ጌታን በአየር ይቀበሉና ወደ ሰማይ ያርጋሉ። 1ኛ ተሰሎንቄ 4:13-18 እና 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡51-58 እንደሚያዕተምሩት፥ ከሞት የተነሡትና በሕይወት የነበሩት ክርስቲያኖች የክርስቶስን የሚመስል ትንሣኤ አካል ይቀበሳሉ (1ኛ ዮሐ. 3፡2)። የቤተ ክርስቲያን ትንሣኤ የመጀመሪያው ብዝሃ ትንሣኤ ሲሆን፥ ለተከታታይ ትንሣኤዎች ግንባር ቀደሙ ነው። 

መ. የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትንሣኤ 

ኢዮብ 19፡25-26 ውስጥ እንደተገለጠው፥ ምንም እንኳኝ ብሉይ ኪዳን በተደጋጋሚ ስለ ትንሣኤ ትምህርት ቢያመለክትም፥ ትንቢት ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ አልተሰጠውም። ይሁንና፥ ተጠቅሰው የምናገኛቸው አሳቦች የሚያመለክቱት የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትንሣኤ የሚፈጸመው፥ በንጥቀት ወቅት ሳይሆን፥ ወደ ምድር በሚመለስበት ዳግም ምጽአቱ ጊዜ መሆኑን ነው። 

ዳንኤል፥ ምዕራፍ 12 ቁጥር 1 ውስጥ ታላቁን መከራ ከገለጠ በኋላ፥ ቁጥር 2 ውስጥ ደግሞ ትንሣኤን ያብራራል። ከዚህ ክፍል እንደምንመለከተው፥ ትንሣኤ ከታላቁ መከራ የሚቀጥልና የመጨረሻ ክፍል ሆኖ ቀርቧል። ስለሆነም፥ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን የሚነሡት፥ በመነጠቅ ጊዜ ሳይሆን፥ በመንግሥት ምሥረታ ወቅት ነው። ከመጽሐፈ ኢዮብ ተመሳሳይ አሳብ ለመረዳት እንደሚቻለው፥ ትንሣኤ ክርስቶስ እግሮቹን በምድር ላይ ከሚያሳርፍበት መን ጋር ተያይዟል። 

በተመሳሳይ ሁኔታ፥ ሙታን ከመቃብር የሚነቁበት የትንሣኤ ትምህርት ክርስቶስ በዓለም ላይ ሊፈርድ ከሚመጣበት ዘመን ጋር ተዛምዷል (ኢሳ. 26፡19-21)። በተጨማሪም፥ “በክርስቶስ የሞቱት” የሚለው ሐረግ ሰመነጠቅ ጊዚ የሚነሡትን ለመግለጥ እንዳገለገለ መረዳቱ ተገቢ ነው (1ኛ ተሰ. 4፡16)። “በክርስቶስ” የሚለው እገላለጥ ከመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የተነሣ አማኙ አሁን ያለውን ስፍራ ያመለክታል። 

ይህ ገለጣ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው፥ ሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 ውስጥ ሲሆን፥ ስለ ብሉይ ኪዳን ቅዱሳን አልጎለጠም። ምንም እንኳ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች አሳብ ሲለያዩና አንዳንዶቹ መነጠቅ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳንን ይጨምራል ቢሉ፥ አብዛኛው መረጃ የሚያመለክተው ግን፥ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን የሚነሡት በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ወቅት መሆኑን ነው። ያም ሆነ ይህ፥ የብሉይም ሆነ የእዲስ ኪዳን ቅዱሳን ከሺህ ዓመቱ መንግሥት በፊት ይነሣሉ። 

ሠ. የታላቁ መከራ ወቅት ቅዱሳኝ ትንሣኤ 

በታላቁ መከራ ወቅት በሰማዕትነት ስለሞቱ ሰዎች ክርስቶስ መንግሥቱን በምድር ላይ ለመመሥረት ከሚመጣበት ሁኔታ ጋር በተያያዘ መንገድ ልዩ ስሳ ተሰጥቷል። ራእይ 20፡4 ውስጥ ዮሐንስ ስለእነዚህ ወገኖች የሚከተላውን ገልጧል፡- “ስለ ኢየሱስም ምስክርና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቆረጡባቸውን ሰዎች ለአውሬውና ለምስሉም ያልሰገዱትን፥ ምልክቱንም በግንባሮቻቸው በእጆቻቸውም ላይ ያልተቀበሉትን አየሁ፤ ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመቱኝ ኖሩና ነገሡ”። 

በታላቁ መከራ ዘመን በሰማዕትነት የሚሞቱ ቅዱሳን ክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ሰሚመለስበት ጊዜ የሚነሡ ስለመሆናቸው ከላይ የቀረበው ዓረፍተ ነገር ግልጥ መረጃ ነው። ራእይ 20፡5 ውስጥ የተጠቀሰው ቃል፥ “የቀሩቱ ሙታን ግን ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በሕይወት አልኖሩም። ይህ የፊተኛው ትንሣኤ ነው” ሲል ያውጃል። ከእርሱ በፊት የክርስቶስ፥ የቤተ ክርስቲያንና የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትንሣኤዎች ተካሂደው ሳለ፥ ይህ እንዴት የፊተኛው ትንሣኤ ይሆናል? የሚል ተገቢ ጥያቄ ይነሣል። 

ለዚህ መልሱ “የፊተኛው ትንሣኤ” የሚለው ሐረግ ምንም እንኳ በጊዜ ርዝመት ቢለያዩ፥ የጻድቃንን ትንሣኤዎች ሁሉ ያመለክታል የሚል ነው። ሁሉም ከኃጢአተኞች የመጨረሻ ትንሣኤ በፊት የሚከናወኑና “ፊተኛ” ናቸው። ስለሆነም፥ «{የፊተኛው ትንሣኤ” የሚለው ሐረግ የክርስቶስን ትንሣኤ ጨምሮ፥ የሁሉንም የቅዱሳን ትንሣኤዎች የሚመለከት ነው። 

ረ. የሺህ ዓመቱ ቅዱሳን ትንሣኤ 

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በየትኛውም ስፍራ ስለ ሺህ ዓመቱ ቅዱሳን ትንሣኤ በግልጥ የተቀመጠ እሳብ ባለመኖሩ፥ አንዳንዶች ወደ ሺህ ዓመቱ መንግሥት የሚገቡ ቅዱሳን ከቶውንም እንደማይሞቱ ይናገራሉ። በሺህ ዓመቱ መንግሥት መጨረሻ ላይ ሕይወት የሚኖሩ ሰዎች ስለመነጠቃቸውም መጽሐፍ ቅዱስ የሚገልጠው ነገር የለም። እነዚህ ሁለቱም ትንቢታዊ ነገሮች ዛሬ በሕይወት ለሚኖሩ ቅዱሳን አንገብጋቢ ጉዳዮች አይደሉም። ከዚህ ጋር የሚዛመደው እውነት ክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ከተመለሰ በኋላ ሊገለጥ ይችላል። 

ይሁን እንጂ፥ የመከራውን ዘመን የሚያልፉ ቅዱሳኝ ዕድሜያቸው የሚገፋ ከመሆኑም ሌላ፥ በሺህ ዓመቱ አገዛዝ ዘመን ሁሉ በሕይወት የመኖራቸው ነገር አጠራጣሪ ነው። አዳምና ቀደምት ክርስቲያኖች እንኳ ለሺ ዓመት በሕይወት አልኖሩም። ስለሆነም ምንም እንኳ ዕድሜያቸው ሊረዝም ቢችል፥ ሺሁን ዓመት በሙሉ እንደማይኖሩና መሞታቸው እንደማይቀር ይታመናል። 

ኢሳይያስ 65፡20 ውስጥ፥ ከዚያ ወዲህ ጥቂት ዘመን ብቻ የሚኖር ሕፃን፥ ወይም ዕድሜውን ያልፈጸመ ሽማግሌ አይገኝም፥ ጎልማሳው መቶ ዓመት ሆኖት ይሞታልና፥ ኃጢአተኛውም የመቶ ዓመት ሆኖት የተረገመ ይሆናልና” የሚል ቃል አለ። በሌላ በኩል፥ ይህ ዓረፍተ ነገር ዕድሜ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጨምርና እንድ ሰው መቶ ዓመት ሆኖት ገና ሕፃን እንደሚሆን ያመለክታል። ሰሺህ ዓመቱ መንግሥት ዘመን፥ ሰዎች ዕድሜ እስኪጠግቡ ይኖራሉ። ይህ ግን ላለመሞታቸው ዋስትና አይሰጥም። በተቃራኒው በመቶ ዓመት ዕድሜው የሚሞት ሰው የሚሞተው በኃጢአቱ ምክንያት ስለሚሆን ሞት የሚመጣው እንደ ፍርድ ነው። 

ሰሺህ ዓመቱ መንግሥት ሞተው፥ በዚያው ዘመን መጨረሻ የሚነሥ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ የሚያሳይ መረጃ አለ። ይሁንና፥ ይህ ትምህርት ግልጥ በሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ላይ የተመሠረተ አይደለም። ቢሆንም ከዚህ የተሻለ ማብራሪያ ለማቅረብ አይቻልም። የሺህ ዓመቱ ቅዱሳን ከሞት እንደሚነሡ ሁሉ፥ በሕይወት የሚኖሩ የሺህ ዓመቱ ቅዱሳን ይነጠቃሉ ወይም እንደ ቤተ ክርስቲያን ሞትን ሳይቀምሱ ይወሰዳሉ። ይህም አሁን ያላቸውን ምድርና ሰማያትን ለመጠቅለል የሚደረግ ዝግጅት ነው። 

ሰ. የኃጢአተኞች ትንሣኤ 

የመጨረሻው ትንሣኤ ኃጢአተኞችን ብቻ የሚመለከት ይመስላል። ስለ ታላቁ የነጭ ዙፋን ፍርድ ራእይ 20፡11-15 ውስጥ የተጻፈው ቃል እንደሚያስረዳው፥ ቀደም ሲል ያልተነ ሙታን ሁሉ ከሞት ተነሥተው በእግዚአብሔር ፊት ለፍርድ ይቆማሉ። ከአዲስ ሰማያትና ምድር መፈጠር በፊት ይህ የመጨረሻው ትንሣኤ ነው። የዚህ ፍርድ ዝርዝር ነጥቦች በቀጣዩ ምዕራፍ ውስጥ ይቀርባሉ። 

በአጠቃላይ፥ ሰዎች ሁሉ ከሞት እንዲነሡ የተወሰነ ስለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ይናገራል። ዳንኤል ጠቅለል አድርጎ እንዲህ ይገልጠዋል። “በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉት ብዙዎች ይነቃሉ፤ እኩሌቶቹ ወደ ዘላለም ሕይወት፥ እኩሌቶቹም ወደ እፍረትና ወደ ዘላለም ተስቁልና ፣ (12፡2)። ሰዎች ቢሞቱም ይነሣሉ። ነገር ግን ትንሣኤዎች አንድ ዓይነት አይሆኑም። የሕይወት ትንሣኤ፥ የአማኞች አካል የክርስቶስን የትንሣኤ አካል የሚመስልበት የከበረ ትንሣኤ ነው። 

የኩነኔ ትንሣኤ ግን እጅግ የከፋ ትእይንት ይሆናል። የዚህ ትንሣኤ ተቋዳሾች ለዘላለም የሚኖር አካል ቢሰጣቸውም፥ ኃጢአተኛና ለሥቃይ የተጋለጠ አካል ይሆናል። እንደ ዲያብሎስና እጋንንቱ ለዘላለም በእሳት ባሕር ውስጥ ይኖራሉ። ይህ አስገዳጅ እውነት ነው ሰዎች ወንጌልን እስከ ዓለም ዳርቻ ይዘው እንዲሄዱ ያደረጋቸው። ጥረቱ በተቻለ መጠን ብዙዎችን ከእሳት ነጥቆ ለማውጣትና በኃጢአተኞች ላይ ሊመጣ ከተቆረጠው የእግዚአብሔር ቁጣ ለማዳን ነው (ይሁዳ 23)። ለጻድቃን ግን የትንሣኤው ትምህርት የተስፋ መሠረት ነው። ምንም እንኳን የመጨረሻው የቤተ ክርስቲያን ትውልድ ሞትን ሳይቀምስ የሚነጠቅ ቢሆን፥ ለአብዛኛው ዓለም ግን ከመቃብር ትንሣኤ ለምድር የተዘጋጀውን አካል እግዚአብሔር ለከበረ ሕልውናው ተስማሚ አድርጎ የሚለውጥሰት እሠራር ነው።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

48
ትምህርት 48 ከ52

የእስራኤልና የአሕዛብ ፍርድ

ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ፥ በምድር ላይ መንግሥቱን በሚመሠርቱት ታላላቅ ክንውኖች ውስጥ በእስራኤልና በአሕዛብ ላይ የሚተላለፉ ፍርዶች ይካተታሉ። ፍርዶቹ የሚጀምሩት ትንሣኤ ባገኙ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን (እስራኤልና አሕዛብ እና በታላቁ መከራ ዘመን እንዲሁ ትንሣኤ ባገኙ ቅዱሳን (እስራኤልና አሕዛብ) ይመስላል። በምድር ላይ ሰሕይወት በሚኖሩ አይሁዶችና አሕዛብም ላይ ፍርድ ይሰጣል። የኋለኞቹ ፍርዶች ለእግዚአብሔር መንግሥት በተገቡትና ከመንግሥቱ የሚገለሉትን ሰዎች የመለየት ተግባራት ናቸው። 

ሀ. ከምት የተነሡ እስራኤላውያንና አሕዛብ ፍርድ 

ባለፈው ምዕራፍ እንደተመለከተው፥ የትንሣኤ ትምህርት ብሉይ ኪዳን ውስጥ የታወቀ እውነት ነው። በቤተ ክርስቲያን መነጠቅ ወቅት ከሚካሄደው ትንሣኤ በተጨማሪ፥ ክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ወደ ምድር ከሚመጣበት ሁኔታ ጋር በተያያዘ መንገድ የሞቱ ቅዱሳን ከሞት ይነሣሉ። እስቀድሞ እንደተገለጠው፥ ይህን እውነት ዳንኤል 12፡2፥ ኢሳይያስ 26፡19 እና ኢዮብ 19፡25-26 ውስጥ እንመለከታለን። የእስራኤል ትንሣኤ በዳግም ምጽአቱ ወቅት ከሚፈጸመው የሕዝቦቹ መታደስ ጋር በተያያዘ ሁኔታም ተመልክቷል። ሕዝቅኤል 37 ውስጥ በቀረበው ራእይ የደረቁ እጥንቶች ወደ ሕያው አካልነት መቀየር የእስራኤል ሕዝብ መታደስ ተምሳሌት ሲሆን፥ እስራኤላውያን ከመቃብራቸው የሚወጡበት ጊዜ መሆኑንም እንረዳለን (37፡12-14)። እዚህ ላይ ተምሳሌታዊውና ቀጥተኛው ትንቢት የተዋሐደ ይመስላል። ዳዊት ከሞት ተነሥቶ በክርስቶስ ሥር በመሆን እንደሚገዛ በዚሁ ምዕራፍ ተገልጧል። በአጠቃላይ ስለ ሙታኝ ትንሣኤ ለሚያምኑ ሁሉ ብሉይ ኪዳን የጸና እምነት ያስጨብጣል። 

በታላቁ መከራ ወቅት በሰማዕታትነት የሚሞቱ ሰዎች ትንሣኤ በክርስቶስ ዳግም ምጽአት የሚፈጸም መሆኑ ራእይ 20 ውስጥ ተገልጧል። ይህ ምናልባትም ከብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትንሣኤ ጋር በአንድነት የሚፈጸም ይሆናል። የተነሡትም ሺህ ዓመት ከክርስቶስ ጋር እንደሚኖሩና እንደሚነግሡ ተገልጧል (ራእይ 20፡4)። ሽልማታቸውንም ቤት ክርስቲያን በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት በምትሸለምበት አኳኋን የሚቀበሉ ይመስላል። እገልግሎታቸውና እስከ ሞት ድረስ ለእግዚአብሔር በታማኝነት መጽናታቸው፥ በምድር ላይ ከክርስቶስ ጋር ሰመንገሣቸው እውቅናን ያገኛል። 

ቤተ ክርስቲያን ክክርሰቶስ ጋር መግዛቷ የተጠቀሰ ክመህኑ እውነት እንጻር እንዳንድ ግራ መጋባቶች ተፈጥረዋል። ከሺህ ዓመቱ መንግሥት ሰፊት ከሞት የሚነሡ ቅዱሳን ሁሉ በተመሳሳይ መንገድ የሺህ ዓመቱ ንግሥና ተካፋይ እንደሚሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ይጠቁማል። እያንዳንዱ በራሱ ተራና በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ዓላማ መሠረት ተግባራዊ ይሆናል። ቤተ ክርስቲያን እንደ ክርስቶስ ሙሽራ ትነግሣለች። ከሞት የሚነሡ ቅዱሳንም በተወሰነላቸው ብቃት መሠረት ድነትን እንዳገኙ እስራኤላውያን ወይም አሕዛብ ያነግሣሉ። ይህን ሁኔታ አስቴር እንደ ንግሥት፥ መርዶክዮስ ደግሞ እንደ የንጉሡ ጠቅላይ ሚኒስቴር ከሆኑበት የመጽሐፈ አስቴር ምሳሌ ለመረዳት ይቻላል። አስቴርና መርዶክዮስ የንግሥናው ተካፋዮች ናቸው፤ የንግሥናቸው መንገድና ብቃት ግን የተለያየ ነበር። በሺህ ዓመቱ መንግሥትም የሚሆነው ይኸው ነው። 

ስለሆነም፥ በክርስቶስ ዳግም ምጽእት ወቅት ከእስራኤልም ሆነ ከአሕዛብ የሞቱት ቅዱሳን እንደሚነሡ በመግለጥ መደምደም ይቻላል። ይህ ትንሣኤ የቤተ ክርስቲያን ንጥቀትና መለወጥ ተካፋዮች ያልሆኑትን ሁሉ ያጠቃልላል። 

ለ. በሕይወት የሚቆዩ እስራኤላውያን ፍርድ 

ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ፥ ሕዝቡ የሆኑትን እስራኤላውያን ከአሳዳጆቻቸው ይታደጋል። እስከ ዳግም ምጽአቱ ድረስ ብዙዎች ይገደላሉ (ዘካ. 13፡8)፣ እስከ ምጽአቱ የሚቆዩት ግን በክርስቶስ ነጻ አውጪነት ይድናሉ (ሮሜ 11፡26)። ያም ሆኖ፥ ከጠላቶቻቸው ጥቃት የሚተርፉት እስራኤላውያን ሰሙሉ ወደ መንግሥቱ የመግባት ብቃት እይኖራቸውም። የዚህ ምክንያቱ አንዳንዶቹ በጌታ ያልዳኑ መሆናቸው ነው። በእርሱ ፊት ቀርሰው ይፈረድባቸዋል (ሕዝ. 20፡33-38)። መጀመሪያ እስራኤላውያን ሁሉ ከምድር ዳርቻ ይሰበሰባሉ (ሕዝ. 39:28)። ሕዝቅኤል 20፡35-38 ውስጥ ጌታ የሚከተለውን ተናግሯል፡- “ወደ አሕዛብም ምድረ በዳ አመጣችኋለሁ፤ ከዚያም ፊት ለፊት ከእናንተ ጋር እፋረዳለሁ። የግብፅ ምድረ በዳ ክአሳቶቻችሁ ጋር እንደተፋረድሁ እንዲሁ ከእናንተ ጋር እፋረዳለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። ከበትርም በታች እሳልፋችኋለሁ፥ ወደ ቃል ኪዳንም እሥራት አገባችኋለሁ፤ ከእናንተም ዘንድ ዓመፀኞችንና የበደሉኝን እለያለሁ፤ ካኖሩባትም ምድር አወጣቸዋለሁ፥ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፤ እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።” 

በዚህ ምንባብ መሠረት፥ ዳግም የሚሰበሰቡት እስራኤላውያን ሁለት ላይ ይከፈላሉ፤ እነዚህም ኢየሱስ ክርስቶስን እንደመሢሐቸውና እዳኛቸው በመቀበል ወደ መንግሥቱ የሚገሱና በዓመፀኛነታቸውና በአለማመናቸው በመቀጠል ከእግዚአብሔር መንግሥት የሚገለሉ ናቸው። ምንም እንኳ እስራኤል በአገር ደረጃ ሞጎስ ቢደረግላትና እግዚአብሔርም ልዩ በረከቶችን ሲያሳያት፥ ግላዊ ድነት የሚመሠረተው ግለሰቡ ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖረው ግንኙነትና እምነት ላይ ነው። 

ከዚህ ቀደም ለሽመናት እንደሆነው፥ በአሁኑ ጊዜም እንደ “እውነተኛ እስራኤል” የተቆጠሩ (የዳኑ) እና ባለመዳናቸው ምክንያት በስም ብቻ እስራኤሳውያን የሆኑ ቡድኖች አሱ። ጳውሎስ ሮሜ 9፡6 ውስጥ እንደገለጠው፥ “ከእስራኤል የሚወለዱ ሁሉ እስራኤል አይደሉም።” ያልዳኑት የሥጋ ልጆች” እንጂ የእግዚአብሔር ልጆች እንዳልሆኑ ገልጧል (ሮሜ. 9፡8)። ዓመፀኞቹ ሲወገዱ፥ እውነተኛ ድነት ያገኙት እስራኤላውያን ብቻ ወደ ምድሪቱ ገብተው ይወርሷታል። ያልዳኑት ግን ወደ ምድሪቱ አይገቡም (ሕዝ. 20፡38)። 

ሐ. በሕይወት የሚኖሩ አሕዛብ ፍርድ 

በአሕዛብ ላይ የሚደርሰው ፍርድ በእስራኤል ላይ ከሚፈጸመው በተለየ መንገድ ይስተናገዳል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማቴዎስ 25፡31-46 ውስጥ ይህ ፍርድ ዳግም ምጽአቱን ተከትሎ ወዲያውኑ እንደሚፈጸም ገልጧል። የሚከናወንበትን ሁኔታ ቁጥር 31 ውስጥ ሲገልጥ፥ ምጽአቱ “የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል” ብሏል። 

በቀጣዩ ጎብጣ፥ አሕዛብ እንደ በጎችና ፍየሎች በእረኛ ፊት የሚቀርቡ መሆኑ ተመልክቷል። በዓይነታቸው እንደመለያየታቸው፥ ለሁለት ይክፈሉና በጎቹ ንጉሡ በስተቀኝ፥ ፍየሎቹ ደግሞ በስተግራ ይቆማሉ። ከዚያም በጎች ወደ መንግሥቱ እንዲገቡ ንጉሡ ይጋብዛቸዋል። እንዲህም ይላቸዋል፡- “እናንተ የአባቴ ብሩካን፥ ኑ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታሥሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና። ጻድቃንም መልሰው ይሉታል፡- ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?” (ቁ. 34-37)። 

በጎቹ እነዚህን የጽድቅ ተግባራት መቼ እንዳከናወኑ ሲጠይቁት፥ ማቴዎስ 25፡40 ውስጥ ንጉሡ እንዲህ ይመልስላቸዋል፥ “እውነት እላችኋለሁ ከሁሉ ከሚያንሡ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።” 

ከዚያም፥ ንጉሡ በስተግራው ወዳሉት ዞር በማለት እንዲህ ይላቸዋል፡- “እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ” (ቁ. 4 )። በጎቹ የሠሯቸውን ዓይነት በጎ ተግባራት እንዳላከናወኑም ይነግራቸዋል። ፍየሎቹም፥ “ጌታ ሆይ፥ ተርበህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታሥረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም? ይሉታል” (ቁ. 44)። ንጉሡም፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሡ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል” (ቁ. 45)። ከዚያ በኋላ፥ ፍየሉቹ ወደ ዘላለም ቅጣት ሲጣሉ፥ በጎቹ ደግሞ ወደ ዘላለም የሕይወት በረከት ይወሰዳሉ። 

ይህ ምንባብ ለበጎ ሥራ አጽንኦት በመስጠቱ አንዳንድ አለመግባባቶች ፈጥሯል። ላይ ላዩን ብቻ ከተመለከትነው በጎቹ፥ በሰናይ ምግባራቸው የዳኑና ፍየሎቹ ግን ሰናይ ምግባር ባለማሳየታቸው ለጥፋት የተዳረጉ ሊመስለን ይችላል። ይሁንና፥ በየትኛውም ሥፍረ-ዘመን ቢሆን ድነት በሰናይ ምግባር እንደማይገኝ መጽሐፍ ቅዱስ ግልጥ አድርጓል። በሰናይ ምግባራት ላይ ከፍተኛ እጽንኦት የሚስጠው የሙሴ ሕግ እንኳ ድነት በሰዎች ሥራ የሚገኝ መሆኑን አይናገርም። ይልቁንም፥ ድነት በሁሉም ሥፍረ-ዘመናት አንድ መሆኑ በሚከተለው አኳኋን ተገልጧል፡- “ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም” (ኤፌ. 2፡8-9)። 

ሰው ከኃጢአት ተፈጥሮ ጋር በመወለዱና በእግዚአብሔር ላይ ባመፀው የመጀመሪያ አባቱ ሳቢያ ከያዘው ስፍራ የተነሣ፥ የውርስ ኃጢአት ከድነት እርቆታል። ከዚህም የተነሣ ሰዎች ሁሉ ከሞት ዕዳ ጋር ስለተወለዱ፥ በራሳቸው ምንም ተስፋ የላቸውም። ስለሆነም፥ በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ሰዎች ሊድኑ የሚችሉት በክርስቶስ መሥዋዕት ብቻ ነው (ሮሜ 3፡25-26)። የሥራ ሕግ የሚያደርሰው ወደ ኩነኔ ሲሆን፥ የእምነት ሕግ ደግሞ ወደ ድነት ያደርሳል (ሮሜ 3፡27-28)። ይህ ሰሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም በሚገባ የተመሠረተ ከሆነ፥ የበጎችና የፍየሎች ፍርድ የሚብራራው እንዴት ነው? 

በዚህ ፍርድ ውስጥ የምንመለከተው መርህ ሥራ የድነት መሠረት ሳይሆን፥ ሥራ የመዳናችን ማረጋገጫ መሆኑን ነው። ድነት የሚገኘው በእምነት ብቻ ቢሆንም፥ እምነት ያለ ሥራ የሞተና እውነትነት የሌለው ነው (ያዕ. 2፡26)። 

በታላቁ መከራ ዘመን በበጎች የሚከናወኑ መልካም ሥራዎች በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ከሚያልፉ ሰዎች አንጻር እጅግ አስፈላጊና ጠቃሚ ነው። በዚህ ወቅት ዓለም አቀፋዊ ፀረ-ሴማዊነት ሰለሚሰፋፋ፥ ብዙ አይሁዶች ይገደላሉ። በነዚያ ሁኔታዎች፥ ከአይሁዶች ጋር ወዳጅነት መመሥረቱ ለአሕዛብ ትልቅ ነገር ይሆናል፤ “ከሁሉ ከሚያንሡ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንድ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት” (ማቴ. 25፡40)፥ በሚለው መሠረት ማለት ነው። 

አይሁዶች ለሞት የሚታደኑበት ወቅት ከእነሱ ጋር ወደጅነት መመሥረቱ፥ ለአሕዛሱ ሕይወቱንና ነጻነቱን አደጋ ላይ መጣል መሆኑ እርግጥ ነው። እንዲህ ባለው ከፍተኛ ዕይጣናዊ ማታለልና የአይሁድ ጥላቻ በነገሠበት ሁኔታ ውስጥ በጎ ምግባር ሊኖር የሚችለው፥ አሕዛቡ በክርስቶስና በመጽሐፍ ቅዱስ የሚያምን ከሆነ፥ እንዲሁም እስራኤላውያን በእግዚአብሔር የተመረዙና ልዩ ስፍራ ያላቸው መሆኑን የተገነዘበ ከሆነ ብቻ ነው። 

በመሆኑም፥ በሠላም ሁኔታ ውስጥ ላአንድ አይሁዳዊ በጎ ነገር ማድረጉ የተለየ ጠቀሜታ ላይኖረው ቢችልም፥ ዓለም አቀፋዊ ሥቃይ በሚደርስባቸው ወቅት ለአንድ አይሁዳዊ መልካምነትን ማሳየት ግን በክርስቶስ የሚገኝ ድነት እውነተኛ ምልክት ይሆናል። ስለሆነም፥ ምንም እንኳ ሰጎቹ በሥራቸው ባይድኑ፥ መዳናቸውን ሥራቸው ያመለክታል። ይህ ነው ሰው በፍሬው የሚታወቅበት መርህ። 

በዚህ ፍርድ መሠረት ጳድቃኝ አሕዛብ ወደ መንግሥቱ እንዲገቡ ተፈቅዶላቸዋል። የእስራኤላውያን ብቻ በሆነችው የተስፋ አገር ውስጥ ሳይኖሩም፥ ለእስራኤልም ሆነ ለአሕዛብ የተትረፈረፈ በረከት በሚኖርባት የሺህ ዓመቷ ምድር ውስጥ ይኖራሉ። 

ፍየሎቹ ግን ወደ ዘላለማዊ እሳት ይጣላሉ። ይህ አባባል ወደ ሲኦል እንደተጣሉና በኋላ ከሞት ተነሥተው ወደ እሳት ባሕር እንደሚጣሉ የሚያመለክት መሆን አለመሆኑ ግልጥ አይደለም። ምንም ይሁን ምን ወደ ዘላለማዊ ቅጣት መሄዳቸውና የሺህ ዓመቱን መንግሥት ዜግነት ማጣታቸው ግልጥ ነው። 

እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ የሚያወርደው ፍርድ እርሱ ሥራችንን ስለሚያጤን ሥራችን እምነታችንን ማሳየት ያለበት መሆኑን ያስታውሰናል። ሌላው ቀርቶ ለተጠማ ሰው ውኃ መስጠቱና የተራበን ግብሳቱ እንኳ ሕዝቡን የሚያፈቅረው እምላክ ይመዘግባል። ይህ ምንባብ፥ በዙሪያችን ያሉ ሰዎችን ሰብአዊ ፍላጎቶች መረዳትና ለሰዎች መልካም ፍቃድን ማሳየት የሚወጡት፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ከተሰወጠ ልብ መሆኑን ነው። አንዲት ድንቢጥ ከፈቃዱ ውጭ እንድትወድቅ የማይፈቅድ አምላክ ለፍጥረቱ ጥቃቅን ችግሮችም ይገደዋል። የክርስቶስ ልብ ያለው ሰው፥ ለእግዚአብሔር ሕዝብም ልብ ይኖረዋል። 

በአጠቃላይ፥ በከርስቶስ ዳግም ምጽአት ወቅት የሺህ ዓመቱ መንግሥት ሙሉ ለሙሉ ከመጀመሩ በፊት ጻድቃን ሁሉ ከሞት ተነሥተው ፍርጻቸውን የሚቀበሉ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ያስረዳል። በሺህ ዓመቱ መጨረሻ ላይ የሚካሄደውን የታላቁን ነጭ ዙፋን ፍርድ በመጠባበቅ ስመቃብር የሚቆዩት ያልዳኑት ብቻ ይሆናሉ።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

49
ትምህርት 49 ከ52

የሺህ ዓመቱ መንግሥት

ህ. የእግዚአብሔር መንግሥት ፅንሰ-ሃሳብ 

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሔር መንግሥት ሲባል በአጠቃላይ እግዚአብሔር ዓለማትን የሚገዛ መሆኑን ያመለክታል። እግዚአብሔር ሁልጊዚ ሉዓሳዊና ሁሉን ቻይ ሆኖ ስለሚኖር መንግሥቱም ዘላለማዊ መሆኑ ይታመናል። ሰእግዚአብሔር ብርታት ዝቅ የተደረገው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ለዚህ አባባል እንዲህ በማለት ምስክርነቱን ይሰጣል፡- «ዘመኑም ከተፈጸመ በኋላ እኔ ናቡከደናዖር ዓይኔን ወደ ሰማይ አሣሁ፥ አእምሮዬም ተመለሰልኝ፤ ልዑሉንም ባረክሁ፥ ስቶሳሰም የሚኖረውን አመሰገንሁ አከበርሁትም፤ ግዛቱ የዘላለም ግዛት ነውና። ምድርም የምኖሩ ሁሉ እንደ ምናምን ይቆጠራሉ፤ በሰማይም ሠራዊት በምድርም ላይ ሰሚኖሩ መካከል እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፤ እጁንም የሚከለክላት ወይም ምን ታደርጋለህ የሚለው የለም” (ዳን. 4፡34-35)። 

ከዘመናት በፊት ሰይጣንና እርሱን የደገፉ የመላእክት ጭፍሮች የእግዚአብሔርን የዓለማት ገዢነት ተቃውመው ነበር። እግዚአብሔር ዓመፀኞቹን በመቅጣት ሉዓላዊነቱን አሳይቷል። የኃጢአት ወደ ዓለም መቀባትም በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነት እስገንዝቧል። ይህ የሚያመለክተው፥ የመለኮታዊ መንግሥትን ፅንሰ-አሳብን ነው። በሌላ አባባል እግዚአብሔር ምንም እንኳን ዛሬ በፍጥረታቱ አማካይነት ቢሠራ፥ ብቸኛና ታላቅ ገዢ ግን እርሱ ነው። 

አዳም ሲፈጠር ምድርን እንዲገዛ ተፈቅዶለት ነበር (ዘፍጥ. 1፡26፥ 28)። ይሁንና፥ አዳምና ሔዋን ለእግዚአብሔር ባለመታዘዝ የተከለከለውን የዛፍ ፍሬ በሉ። አዳም በኃጢአት በመው፪ቁ የመግዛት መብቱን አጣ። ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ መርጦ የአገዛዝ ኃላፊነት ሰጣቸው። በዚሁ መሠረት አንዳንድ ሰዎች ገዥነት የተፈቀደላቸው መሆኑን ከታሪክ እንረዳለን። ለምሳሌ፥ ዳንኤል እግዚአብሔር ናቡከደነፆርን የቀጣው መሆኑን ሲገልጥ፥ “ልዑል አምላክም በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ የሚወደውንም እንደሚሾምበት እስኪያውቅ ድረስ” ብሏል (ዳን. 5፡21)። 

በብሉይ ኪዳን፥ መለኮታዊ አገዛዝ ያለበት መንግሥት በዓቢይነት የታየው በሳኦል፥ በዳዊትና በሰሎሞን በተጀመረው የእስራኤል መንግሥት ጊዜ ነበር። የአሕዛብ መሪዎችም በሉዓላዊው የእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ የፖለቲካ አገዛዝ ክልል እንዲይዙ ተፈቅዶላቸው ነበር። የዚህ በእግዚአብሔር ፈቃድ የሚካሄድና የሚመራ አጠቃላይ የመንግሥት ፅንሰ-አሳብ ሮሜ 13፡1 ውስጥ በሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ተገልጧል፡- ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።›› 

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ሉዓላዊነት በፖለቲካዊ መንግሥታትና በአዛዛቸው ላይ የሚገለጥ መሆኑን ከማስገንዘቡም ሌላ፥ እግዚአብሔር በሰዎች ልብ አማካይነት ስለሚዛው መንፈሳዊ መንግሥትም ምስክርነቱን ይሰጣል። ይህ ከሰው ዘር ጅማሬ አንሥቶ ሲከናወን የቆየ ነው። መንፈሳዊው መንግሥት በገዛ ፈቃዳቸው ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ያስገዙ ሰዎችንም ሆነ መላእክትን ያካትታል። ጳውሎስ ሮሜ 14፡17 ውስጥ ሰለዚሁ መንፈሳዊ መንግሥት የሚከተሰውን በመግለጥ ጽፏል፡- “የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሠላም ሰመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ፥ መብልና መጠጥ እይደለችምና።” 

ማቴዎስ ወንጌል ውስጥ፥ የሰማይ መንግሥት» እና «“የእግዚአብሔር መንግሥት”፥ የሚሉ ሐረጎችን በመጠቀም ረገድ ተጨማሪ ልዩነት ተ፪ርጓል። ሌሎቹ ወንጌላት “የእግዚአብሔር መንግሥት” የሚሏቸውን ማቴዎስ በተደጋጋሚ የሰማይ መንግሥት” ስለሚል፥ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች ሁለቱም የሚያስተላልፉት ተመሳሳይ መልእክት ነው ብለው ያስባሉ። ሐረጎቹ በጣም የሚመሳሰሉ ቢሆኑም፥ ያጠቃቀማቸው ሁኔታ ሲታይ የሰማይ መንግሥት ከእግዚአብሔር መንግሥት የሚሰፋ ይመስላል። ይሄውም በስንዴና በእንክርዳዱ ምሳሌ ውስጥ መንግሥተ ሰማይ እንክርዳድን፥ የመረቡ ምሳሌ ደግሞ መንግሥተ ሰማይ መልካምና ክፉ ዓሣዎችን ያካተተ ይመስላል (ማቴ. 13፡24-30፥ 36-43፥ 47-50)። 

በሌላ በኩል፥ የእግዚአብሔር መንግሥት ዳግም በመወለድ የሚገቡባት እንጂ በተለምዶ የጌታ ነኝ የሚሉ ሰዎች ስብስብ አይደለችም። ይህም ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ በተናገረው እሳብ እንዲህ ተብራርቷል፡- “እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም” ዮሐ. 3፡5)። ይሁን እንጂ፥ አብዛኛዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኞች በሁለቱ መንግሥታት መካከል ምንም መሠረታዊ ልዩነት የለም የሚለውን አመለካከት ይመርጣሉ። 

ሆኖም በአሁኑና በሺህ ዓመቱ መንግሥት መካከል ንጽጽር ሲደረግ የጎሳ ልዩነት አለ። የአሁኑ መንግሥት “ምሥጢራት” የተሰኙ ዓበይት ገጽታዎች አሉት፤ “ምስጢራቱ” ሰብሉይ ኪዳን ዘመን ያልተሰጡ መንስጦች ናቸው (ማቴ. 13)። ዳሩ ግን ምሥጢራዊ ያልሆነ መንግሥት ከከርስቶስ ዳግም ምጽአት በኋላ ይመሠረታል። 

በማይታይና በሚታየው መንግሥት መካከል ልዩነትም አለ። የማይታየው መንግሥት በአሁኑ ዘመን እግዚአብሔር በአማኞች ልብ ውስጥ የሚያካሂደው አገዛዝ ሲሆን፥ የሚታየው መንግሥት ከዳግም ምጽአት በኋላ ሰዎች ሁሉ በምድር ላይ የሚመለከቱት የከበረ መንግሥት ነው። የአሁኑን ዘመን መለኮታዊ አገዛዝ ክልል በሺህ ዓመቱ መንግሥት ጊዜ ከሚሆነው ጋር ለማነጻጸር፥ ይህ ልዩነት በጣም አስፈላጊና ወሳኝ ነው። 

የመንግሥትን ፅንሰ-ሃሳብ ከሺህ ዓመቱ መንግሥት ጋር ለማዛመድ በተደረገው ጥረት ሦስት ዓይነት አመለካከቶች ቀርበዋል። የቅድመ ሺህ ዓመታውያን (premillenialism/ ፕሪሚሊኒያሊዝም) አመለካከት፥ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው፥ መጀመሪያ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት እንደሚፈጸምና በኋሳ የሺህ ዓመቱ መንግሥት በምድር ላይ የሚመሠረት መሆኑን ነው፤ ከሺህ ዓመቱ መንግሥት በኋላ ዘላለማዊው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ይለጥቃል ይላል። ይህ አመለካከት ቅድመ ሺህ ዓመታዊ የተባለው የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ከሺህ ዓመቱ መንግሥት የሚቀድም መሆኑን ስለሚያስተምር ነው። 

ሁለተኛው አመለካከት፥ በምድር ላይ የሺህ ዓመት መንግሥት አይመሠረትም የሚለውና እልሶሺህ ዓመታዊ (amillenialism/ኢሚሊኒያሊዝምን የተሰኘው ነው። ይህ አመለካከት ክርስቶስ ዳግም ሲመለስ ያለ ምንም የሺህ ዓመት መንግሥት ጣልቃ ገብነት አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር የሚመሠረት መሆኑን ያስተምራል። አመለካከቱ ብሉይም ሆነ አዲስ ኪዳን ስለ ሺህ ዓመቱ መንግሥት የሚናገሩትን ምንባቦች ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ በመተርጎም የዚህ መንግሥት ዘመን በቤተ ክርስቲያን አማካይነት በአሁኑ ጊዜ በምድር ወይም በሰማይ በመከናወን ላይ ነው ይላል። 

ሦስተኛው የድህረ-ሺህ ዓመታዊነት (postmillenialism/ፖስትሚሊኒያሊዝም) አመለካከት ነው። ይህ አመለካከት በአሁኑ ጊዜ ወንጌል ዓለምን ሁሉ አሽንፎ ወርቃማ ዘመን የሚያመጣ መሆኑንና ለሺህ ዓመቱ መንግሥት የተተነበየው ሠላምና ጽድቅ በተወሰነ ደረጃ ተፈጻሚ እንደሚሆን ያምናል። አመለካከቱ ይህ ስያሜ የተሰጠው፥ የክርስቶስን ዳግም ምጽአት የወርቃማው ዘመን ጫፍ ወይም የሺህ ዓመቱ መንግሥት ፍጻሜ አድርጎ ስለሚመለከት ነው። አክራሪ የሆኑ የድህረ-ሺህ ዓመታዊ መንግሥት አመለካከት ተከታዮች ክርስቶስ ለሺህ ዓመታት በሰዎች ልብ ውስጥ የሚገዛ መሆኑን ያስተምራሉ። ወደ ለዘብተኛነት የሚያዘመው ድህረ-ሺህ ዓመታዊ አመለካከት ደግሞ፥ ከዘገምተኛ ለውጥ ሂደት አመለካከት ጋር የሚመሳሰል ሲሆን፥ ዓለም ቀስ በቀስ እየተሻሻለች እንደምትሄድና በመጨረሻ ወደ ወርቃማው ዘመን ለመድረስ እንደሚቻል ያምናል። የህያኛው ክፍለ-ዘመን ታሪክ አካሄድ የእግዚአብሔር ዓላማ በሰዎች አማካይነት ውብ እየሆነ በዓለም ያከናወናል የሚለው እምነት ከሚሰጠው መረጃ ደካማነት የተነሣ ተቀባይነት የሌለው ሆኗል። በመሆኑም በአሁኑ ዘመን እብዛኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኞች አንድም የሺህ ዓመታት ዘመን እንደሌለ ወይም ክርስቶስ ከሺህ ዓመት በፊት እንደሚመጣ የሚያምኑ ብቻ ናቸው። 

የሺህ ዓመቱ መንግሥት በትክክል በምድር ላይ የሚመሠረት መሆኑን በመደገፍና በመቃወም የሚነሡ በርካታ ሙግቶች ቢኖሩም፥ መፍትሔው የሚገኘው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንቢቶች በቀጥታ በሚፈቱበት መንገድ ነው። በዚህ ውይይታችን፥ ትንቢት እንደማንኛውም መለኮታዊ መገለጥ በቀጥታ መተርጎም የሚኖርበት መሆኑን እንመለከታለን። በመሆኑም፥ ብዙ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶችና አዲስ ኪዳን ውስጥ የራእይ ምዕራፍ ሀያ ዋነኛ እሳብ በቀጥታ የሚናገሩትን መልእክት እንዲያስተላልፉ ሆነው ተተርጉመዋል። በዚሁ መሠረት ከክርስቶስ ጳግም ምጽአት በኋላና፥ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከመፈጠራቸው በፊት የክርስቶስ የሺህ ዓመት መንግሥት ምድር ላይ የሚመሠረት መሆኑን ትንቢቶቹ ያስረዳሉ። 

ለ. የሺህ ዓመቱ መንግሥት፥ የእግዚአብሔር አገዛዝ ሰምድር ላይ 

የእግዚአብሔር መንግሥት በቀዳሚነት በሰዎች ልብ ውስጥ የሚፈጸም መንፈሳዊ አገዛዝ መሆኑን ከሚናገረው እልቦ.ሺህ ዓመታውያን አመለካከት ባሻገር፥ በምድር ላይ ክርስቶስ የሚገዛበት መንግሥት እንደሚመሠረት የሚያመለክተውን ድምዳሜ የሚደግፉ አያሌ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች አሉ። ክርስቶስ በዚሁ ምድራዊ መንግሥት ላይ ዋነኛው ፖለቲካዊና መንፈሳዊ መሪ ከመሆኑም በላይ፥ አምልኮ የሚቀርብለት ንጉሥም ነው። ይህ ፅንሰ-አሳብ በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በሚገባ ዳብሮ ቀርቧል። 

ሕዝቦች በእግዚአብሔር ላይ ማመፃቸው በተመዘገበበት መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ሁለት ውስጥ፥ ለእግዚአብሔር ልጅ፥ “ለምነኝ አሕዛብን ላርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ” የሚል ቃል ተገብቶለታል (ቁ. 8)። ይህ መንፈሳዊ አገዛዝ ሳይሆን፥ ፖለቲካዊ መሆኑ በቀጣዩ ቁጥር ውስጥ እንዲህ ተመልክቷል፡- “በብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ፥ እንደ ሸከላ ሠሪ ዕቃም ትቀጠቅጣቸዋለህ” (ቁ. 9)። ይህ የሚያመለክተው፥ ቤተ ከርስቲያንን ወይም በሰማይ የሚሆነውን መንፈሳዊ አገዛዝ ሳይሆን ኃጢአተኞችን ወደ ታች ዝቅ አድርጎ የሚገዛ ፍጹማዊ ንጉሥን ነው። 

የመንግሥቱን ምድራዊ ባሕርይ የሚያጎላው ሌላ ምንባብ ኢሳይያስ ምዕራፍ 11 ውስጥ ያለው ነው። በዚህ ስፍራ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ዳዊት ዘር በምድር ላይ በጽድቅ እንደሚፈርድና ክፉዎችን እንደሚቀጣ ተገልጧል። ኢሳይያስ 11፡4፥ ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፥ በምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል፤ በአፉም በትር ምድርን ይመታል፥ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል” ይላል። እንደ ኢሳይያስ 11፡9 በመሳሰሉት ምንባቦች “ምድር” የሚለው ቃል በተደጋጋሚ ከመጠቀሱም በላይ፣ እግዚአብሔር እስራኤልን ከምድር ሁሉ ለመሰብሰብ በአገሮች ላይ የሚያከናውናቸው ተግባራትም ተገልጠዋል። 

በርከት ያሉ ሌሎች ምንባቦችም መንግሥቱ በምድር ላይ እንደሚሆን ይገልጣሉ ወይም ይጠቁማሉ (ኢሳ. 42፡4፤ ኤር. 23፡3-6፤ ዳን. 2፡35-45፤ ዘካ. 14፡1-9)። በሺህ ዓመቱ ዘመን ክርስቶስ በምድር ላይ እንደሚነግሥ በነዚህ ምንባቦች መገለጡ፥ የአሁኑን ዘመን ወይም መንግሥተ ሰማይን አያመለክትም። ስለሆነም የትኛውም ተገቢ አፈጻጸም የክርስቶስን ዳግም ምጽእት ተከትሎ በምድር ላይ ክርስቶስ የሚገዛበትን ምድራዊ መንግሥት መመሥረትን ይጠይቃል። 

ሐ. በሺህ ዓመቱ መንግሥት ክርስቶስ እንደ ንጉሠ ነገሥት 

ብዙ የብሉይና አዲስ ኪዳን ምንባቦች ክርስቶስ በምድር ላይ የበላይ ገዥ እንደሚሆን ይመሰክራሉ። ክርስቶስ እንደ ዳዊት ልጅነቱ በዳዊት ዙፋን ላይ ይቀመጣል (2ኛ ሳሙ. 7፡16፤ መዝ. 89፡20-37፤ ኢሳ, 11፤ ኤር. 33፡19-21)። ክርስቶስ ሲወለድ መልአኩ ገብርኤል ለማርያም እንደነገራት እንደ ንጉሥ ነበር የመጣው (ሉቃስ 1፡32-33)። እንደ ንጉሥ ተቀባይነትን አጥቷል (ማር. 15፡12-13፤ ሉቃስ 19፡14)። በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ (የአይሁድ ንጉሥ” ተብሉ ነበር የሞተው (ማቴ. 27፡37)። በዳግም ምጽአቱ እንደ “ነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ” እንደሚሆን ተገልጧል (ራእይ 19፡16)። ብሉይ ኪዳን ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጥቅሶች ክርስቶስ በምድር ላይ እንደሚነግሥ ይገልጣሉ ወይም ይጠቁማሉ። ከነዚህም መካከል አንዳንዶቹ ዋነኛ ጥቅሶች በጣም ግልጥ ናቸው (ኢሳ. 2፡1-4፤ 9፡6-7፤ 11፡1-10፤ 16፡5፤ 24 ፡23፤ 32፡1፤ 40፡1-11፤ 42፡1-4፤ 52፡7-15፤ 55፡4፤ ዳኝ. 2፡44፤ 1፡27፤ ሚክ. 4፡1-8፤ 5፡2-5፤ ዘካ. 9፡9፤ 14፡16-17)። 

ከሺህ ዓመቱ መንግሥት ገጽታዎች አንዱ፥ ዳዊት ከሞት ተነሥቶ በክርስቶስ ሥር እኝደ መስፍን የሚሠራ መሆኑ ነው (ኤር. 30፡9፣ 33፡15-17፤ ሕዝ. 34፡23-24፤ 37፡24-25፤ ሆሴዕ 3፡5)። ይህ ሁኔታ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሌለ በመሆኑ፥ ትንቢቱ ከመፈጸሙ በፊት የክርስቶስን ዳግም ምጽአትና የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትንሣኤን ይጠይቃል። 

መ. የሺህ ዓመቱ መንግሥት ዓበይት ገጽታዎች 

በምድር ላይ ስለሚሆነው የክርስቶስ የሺህ ዓመት መንግሥት ምድራዊ አገዛዝ መጽሐፍ ቅዱስ ቢያንስ ሦስት ጠቃሚ ገጽታዎችን ያቀርባል። 

1. የክርስቶስ አገዛዝ ምድርን ሁሉ እንደሚያካትት ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ይመሰክራሉ። ይህም ከማንኛውም ቀደምት ምድራዊ መንግሥት ወይም ከራሱ ከዳዊት የግዛት ወሰን የላቀ ነው። ይህን ዓለም አቀፍ መንግሥት በመመሥረት ነው፥ እግዚአብሔር ሰው ምድርን እንዲገዛት የወጠነውን ዓላማ ከግቡ የሚያደርሰው። ምንም እንኳ አዳም ይህን ዓላማ ለማሳካት ባይችል፥ መዝሙረ ዳዊት 2፡6-9 ውስጥ እንደተመለከተው ሁለተኛው አዳም የሆነው ክርስቶዕ ብቁ ሆኖ ተገኝቷል። ዳንኤል 7: 14 ውስጥ ያለው ቃል እንደሚለው ልጁ፥ “ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።” ዳንኤል 2፡44፤ 4፡34፤ 7፡27 ውስጥ ተመሳሳይ አሳብ ተጠቅሷል። የክርስቶስ እገዛዝ ዓለም አቀፋዊነት መዝሙር 72፡8፤ ሚክያስ 4፡1-2፤ ዘካርያስ 9፡10 ውስጥ ተገልጧል። 

2. የክርስቶስ መንግሥት ፍጹም ሥልጣንና ኃይል ያለው ይለናል። ክርስቶስ በብረት በትር ይገዛል (መዝ. 2፡9፤ ራእይ 19፡15)። የሚቃወሙት ሁሉ ይጠፋሉ (መዝ. 2፡9፤ 72፡9-11፤ ኢሳ. 11፡4)። እንዲህ ዓይነቱ ፍጹማዊ አገዛዝ አሁን ክርስቶስ በቤተ ክርስቲያንም ሆነ በዓለም ላይ ያለውን ሥልጣን አያመለክትም። ተፈጻሚነት የሚኖረው ከዳግም ምጽአቱ በኋላ በምድር ላይ ከነገሠ ብቻ ነው። 

3. በሺህ ዓመቱ መንግሥት ወቅት የክርስቶስ አገዝ የጽድቅና የሠላም ይሆናል። እንደ ኢሳይያስ ምዕራፍ 11 እና መዝሙር 72 በመሳሰሉት እስፈላጊ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮፍሎች ውስጥ ይህ ተመልክቷል። 

እነዚህ ያልተለመዱ የመንግሥት ባሕርያት ሊከሠቱ የሚችሉት በእስራኤልና በአሕዛብ ላይ ፍርድ በመውረዱ (ባለፈው ምዕራፍ እንደተነጋገርነው)፥ እና ሰይጣን ተግባሩን እንዳያከናውን ሰመታሰሩ ነው። የሚቀረው ብቸኛ የክፋት ምንጭ በሰዎች ልብ የሚገኘው ኃጢአታዊ ተፈጥሮ ብቻ ያያናል። ስንዴው ከእንክርዳዱ (ማቴ. 13፡24-30)፥ ጥሩዎቹ ዓሣዎች ከመጥፎዎቹ መለየታቸው (ማቴ. 13፡47-50ን፥ የክርስቶስ መንግሥት ጅማሬ ዝግጅቶች ናቸው። የሺህ ዓመቱ መንግሥት በሚጀመርበት ጊዜ፥ ጎልማሶች ሁሉ እውነተኛ አማኞች ይሆናሉ። በሺህ ዓመቱ ጊዜ የሚወለዱ ልጆች ለክርስቶስ የጽድቅ መንግሥት የሚገዙ ሲሆን፥ በንጉሡ ላይ ቢያምፁ ግን እስከሞት ድረስ ይቀጣሉ (ኢሳ. 65፡17-20፤ ዘካ. 14፡16-19)። ግልጥ ኃጢአት የሚቀጣ ሲሆን፥ በሺህ ዓመቱ አገዛዝ ውሰጥ ማንም ኃጢእት እንዲሠራ እይፈቀድላትም። 

ሠ. በሺህ ዓመቱ መንግሥት የእስራኤል ልዩ ስፍራ 

በሺህ ዓመቱ መንግሥት ወቅት፥ እስራኤል መልካም ዕድልና ልዩ የበረከት ጊዜ ያጋጥማታል። አይሁዶችና እሕዛብ በተመሳሳይ ስፍራ ሆነው ተመሳሳይ ዕድል ከሚጋሩበት ከእሁኑ የቤተ ክርስቲያን ዘመን ባሻገር፥ ሰሺህ ዓመቱ መንግሥት ወቅት የእስራኤል ሕዝቦች የተስፋይቱን አገር በመውረስ የእግዚአብሔር ልዩ በረከት ተጠቃሚዎች ይሆናሉ። የሺህ ዓመቱ መንግሥት የእስራኤል ሕዝብ ዳግም የሚሰባሰብበት፥ እንደ አገር የሚታነጽበትና የዳዊትን መንግሥት የሚያድስበት ወቅት ነው። በመጨረሻም እስራኤል ምድሪቱን ሙሉ በሙሉ ትወርሳለች። 

በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች ስለዚሁ ጉዳይ ይናገራሉ። በሺህ ዓመቱ ጊዜ እስራኤላውያን ወደ ቀድሞ ምድራቸው ዳግም የመሰባሰብና የመታደስ ዕድል ይኖራቸዋል (ኤር. 30፡3፤ 31፡8-9፤ ሕዝ. 39፡25-29፤ አሞፅ 9፡11-15)። እስራኤላውያን ዳግም ወደ ምድራቸው በመመለስ፥ የታደሰውን የዳዊትን መንግሥት ይመሠርታሉ (ኢሳ. 9፡6-7፣ 33፡17፥ 22፤ 44፡6፤ ኤር. 23፡5፤ ዳኝ. 4፡3፤ 7፡14፥ 22፥ 27፤ ሚክ. 4፡2-3፥7)። የተከፈለው የእስራኤልና የይሁዳ መንግሥት እንደገና ይዋሐዳል (ኤር. 3፡18፤ 33፡143 ሕዝ. 20፡40፤ 37፡15-22፤ 39:25፤ ሆሴዕ 1፡11)። እስራኤል እንደ ያህዌ ሚስት (ኢሳ. 54፤ 62፡2-5፤ ሆሴዕ 2፡14-23) ከአሕዛብ አማኞች በላቀ የበረከት ስፍራ ትቀመጣለች (ኢሳ. 14 ፡1-2፤ 49፡22-23፤ 60፡14-17፤ 61፡6-7)። እስራኤል መንፈሳዊ ተሐድሶ እንደምታገኝም ብዙ ምንባቦች ይናገራሉ (ኢሳ. 2፡3፤ 44፡22-24፤ 45፡17፤ ኤር. 23፡3-6፤ 50፡20፤ ሕዝ. 36፡25-26፤ ዘካ. 13፡9፤ ሚልክ. 3፡2-3)። ስለተባረከው የእስራኤል ሁኔታ፥ ስለ መንፈሳዊ ተሐድሷቸውና ከአምላካቸው ጋር ስለሚኖራቸው አስደሳች ኅብረት የሚናገሩ ሌሎች ብዙ ምንባሶች አሉ። 

ምንም እንኳ ለአሕዛብ እንደ እስራኤል የተሰፋይቱ አገር ቃል ኪዳን የተገባላቸው ባይሆኑም፥ ብዙ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት እንደሚናገሩት የተትረፈረፈ በረከት ይጠብቃቸዋል (ኢሳ. 2፡2-4፤ 19፡24 25፤ 49፡6፥ 22፤ 60፡1-3፤ 62፡2፤ 66፡18. ኤር. 3፡17፤ 16፡19)። የመንግሥቱ ክብር ለእስራኤልም ሆነ ለአሕዛብ ዓለም ከዚህ ቀደም ከታየው ሁሉ እጅግ የላቀ ይሆናል። 

ረ. የሺህ ዓመቱ መንግሥት መንፈሳዊ በረከቶች 

ምንም እንኳ የሺህ ዓመቱ መንግሥት ክርስቶስ በምድር ላይ የሚገዛበት ፖለቲካዊ መንግሥት መሆኑ ቢገለጥም፥ የመንግሥቱ ባሕርይ ቀደም ባሉት ሥፍረዘመናት ታይቶ ለማይታወቅ የተትረፈረፈ መንፈሳዊ ሕይወት ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል። ይህም ሰይጣን ከመታሰሩ፥ ግልጥ ኃጢአት ፍርድን ከማስከተሉና ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን ከማወቋ ጋር የተያያዘ ነው። ኢሳይያስ 11፡9 ውስጥ እንደተጠቀሰው፥ “ውሃ ባሕርን እንደሚከድን ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና።” 

በትንቢተ ኤርምያስ እንደተገለጠው ኪዳን፥ ብዙ የመንፈሳዊ በረከት ተስፋ ቃላት ተሰጥተዋል። ኤርምያስ 31፡33-34 ውስጥ እንዲህ ተጎልጧል፡“ከእነዚያ ወራት በኋሳ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል። እያንዳንዱም ሰው ባልንጀራውን፥ እያንዳንዱም ሰው ወንድሙን፡እግዚአብሔርን እወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፥ ይላል እግዚአብሔር። በደሳቸውን እምራቸዋሳሁና፥ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አሳሰብምና።” ይህ ዘመን የጽድቅና(መዝ. 72፡7፤ ኢሳ. 11፡3-5) ዓለም አቀፋዊ የሠላም ጊዜ ይሆናል (መዝ. 72፡7፤ ኢሳ. 2፡4)። መንፈሳዊ ሁኔታዎችም ለእግዚአብሔር ሕዝቦች ልዩ የሆነ ደስታና በረከትን ያስገኛሉ (ኢሳ. 12፡3-4፤ 61፡3፥ 7)። ዛሬ በቤተ ክርስቲያን እንደሚሆነው፥ መንፈስ ቅዱስ ያኔ አማኞችን ወደ መንፈሳዊ አካል የሚያጠምቃቸው መሆኑን የሚያመለክት መረጃ ባይኖርም፥ በሺህ ዓመቱ ዘመን በአማኞች ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚኖር መሆኑ ግልጥ ነው (ኢሳ. 32፡15፤ 44 ፡3፤ ሕዝ. 39፡29፤ ኢዩ. 2፡28-29)። ልዩ ከሆነው ሁኔታ የተነሣ፥ ከማናቸውም ቀደምት ጊዜያት ሁሉ በላቀ በሺህ ዓመቱ መንግሥት ዘመን በዓለም በአጠቃላይ ከፍተኛ መንፈሳዊ በረከት ይኖራል። 

ሕዝቅኤል 40-46 ውስጥ የሺሀ ዓመቱ መንግሥት ቤተ መቅደስ እንደ አምልኮ ማዕከል ሆኖ ተጠቅሷል። ቤተ መቅደሱ ውስጥ ከሙሴ መሥዋዕት ለየት ያሉ መሥዋዕቶች ይቀርባሉ። የነዚህ መሥዋዕቶች መልእክት በቀጥታ ይወሰድ ወይስ ተምሳሌታዊ ትርጉም ይፈለግላቸው በሚለው አሳብ ዙሪያ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች በአመለካከት ይላያያሉ። ይሁንና፥ የመቅደሱንም ሆነ የመሥዋዕት ሥርዓቱን ትንቢት እንዳለ ለመቀበል የማይቻልበት ተጨባጭ ምክንያት የለም። 

ምንም እንኳ የክርስቶስ ሞት የሙሴን ሕግና የመሥዋዕት ሥርዓቶቹን ከፍጻሜ ቢያደርሰው፥ በሕዝቅኤል የተጠቀሰው መሥዋዕት የክርስቶስን መስቀል መታሰቢያ ወደ ኋላ አሻግሮ የሚመለከት ይመስላል። የብሉይ ኪዳን መሥዋዕቶች የክርስቶስን መስቀል ወደ ፊት አሻግረው ይመለከቱ እንደነበረው ማለት ነው። የሺህ ዓመቱ መንግሥት ልዩ የሆነ መንፈሳዊ በረከት ስለሚኖረው፥ የኃጢአትን አስከፊነትና የክርስቶስን መሥዋዕት አሰፈላጊነት መረዳቱ ከማንኛውም ቀደምት ጊዜ በላይ አዳጋች ሳይሆን አይቀርም። ስለሆነም፥ የመሥዋዕት ሥርዓቱ ያስፈለገው ብቻውን ኃጢአት ለማስወገድ የሚችለውን የክርስቶስ መሥዋዕትን አስፈላጊነት ለማስታወስ ይሆናል። የብሉይ ኪዳን መሥዋዕቶች የክርስቶስን ሞት በትክክል ካመለከቱ፥ ሰሺህ ዓመቱ መንግሥትም በተመሳሳይ መንገድ ለመታሰቢያነት ለመጠቀም ይቻላል። 

ምንም ይሁን ምን፥ የሺህ ዓመቱ መንግሥት ግሩም የሆነ መንፈሳዊ በረከት የሚታይበትና ጽድቅ፥ ደስታና ይሳም የምድር መለያዎች የሚሆኑበት ዘመን እንደሚሆን ግልጥ ማረጋገጫ አለ። 

የመንፈሳዊ በረከቶች መትረፍረፍ በበኩሉ ከየትኛውም ቀደምት ዘመናት የተሻለ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ያስከትላል። ሁሉም ፍትሕ የማግኘቱና ትሑቶች ከአደጋ የሚጠበቁበት ዘመን የመሆኑ እውነት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እኩልነትን ያስከትላል። ምናልባትም አብዛኛው ሰው ጌታን የሚያውቅ ይሆናል። ከምድርም ላይ ምርትን ያለመስጠት መርገም ይነሣና (ኢሳ. 35፡1-2)፥ ከፍተኛ ዝናብ ስርጭት ይኖራል (ኢሳ. 30፡23፤ 35፡7)። በአጠቃላይ፥ ዓለም ከዚህ በፊት አይታ የማታውቀው ዓይነት ብልጥግና፥ ጤንነት፥ መንፈሳዊና ቁሳዊ በረከት ይኖራታል። 

በተጨማሪም፥ በሺህ ዓመቱ መንግሥት ወቅት በምድር ላይ አስፈላጊ ለውጦች ይኖራሉ። አንዳንዶቹ በታላቁ መከራ ምክንያት የሚከሠቱ ሲሆኑ፥ ሌሎቹ ደግሞ ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት ጋር የተያያዙ ናቸው። ያን ጊዜ የፅዮን ተራራ ካለበት ተነሥቶ ወደ ምሥራቅ ኢየሩሳሌም የሚያመራ ትልቅ ሸለቆ ይፈጠራል (ዘካ. 14፡4)። ሌላው አዲስ ነገር ኢየሩሳሌም ሰአካባቢዋ ከሚገኙት ግዛቶች የላቀች ትሆናለች (ዘካ. 14፡10)። ባጠቃላይ የተስፋይቱ ምድር እንደገና የዓለም ምድራዊ ገነት፥ የእግዚአብሔር መንግሥት ማዕከልና ያልተለመደ በረከት የሚታፈስባት ስፍራ ትሆናለች። በብዙ ገጽታዎች የሺህ ዓመቱ መንግሥት፥ ወርቃማው ዘመን፥ የምድር ታሪክ መጨረሻ፥ እግዚአብሔር ልጁን የዓለማት ጠቅላይ ገዥ አድርጎ የሚሾምበት ነው።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

50
ትምህርት 50 ከ52

በሰይጣንና በወደቁ መላእክት ላይ የሚሰጠው ፍርድ

ሀ. በክርስቶስ መስቀል አማካይነት በሰይጣን ላይ የተሰጠ ፍርድ 

በሰይጣንና በእግዚአብሔር መካከል ግጭት የተፈጠረው፥ አዳምና ሔዋን ከመፈጠራቸው ረዥም ጊዜ በፊት ሰይጣን መጀመሪያ ከነበረበት ቅዱስ ስፍራ በወደቀ ጊዜ ነበር (የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 22 ይመልከቱ)። በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ፥ በሰይጣን ላይ የተለያዩ ፍርዶች ተሰጥተዋል። ከነዚህም አንዱ በኤደን ገነት ውስጥ በእባቢቱ ላይ የተሰጠው ፍርድ ሲሆን፥ የሚያመላክተው በሰይጣን ላይ የሚደርሰውን (የሚመጣውን) የመጨረሻ ውድቀት ነው (ዘፍጥ. 3፡15)። በዚያ ስፍራ የሴቲቱ ዘር የሰይጣንን ራስ እንደሚቀጠቅጥና ሰይጣንም የርሱን ተረከዝ እንደሚቀጠቅጥ ተገልጧል። ይህም የክርስቶስን መስቀል ያስከተለውንና በእግዚአብሔርና በሰይጣን መካከል የነበረውን ግጭት ያመለክታል። ክርስቶስ በመስቀል ላይ ቢሞትም ከሞት ተነሥቷል። ይህም “ዕኮናውን ትቀጠቅጣለህ” የሚለውን ቃል ያመለክታል። በአንጻሩ ግን ሰይጣን ፍጹም መሸነፉን የሚያመለክት ከፍተኛ ቁስል ደርሶበታል። ያም “ራስህን ይቀጠቅጣል” የተባለው ነው። ክርስቶስ በሞቱ በሰይጣን ላይ ዘላቂ ድል ተቀዳጅቷል። 

ይህ እውነት ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስ በመጣ ጊዜ፡- “ስለ ፍርድም የዚህ ዓለም ገዢ ስለተፈረደበት ነው” ባለበት ዮሐንስ 16፡11 ውስጥ ተመልክቷል። ሰይጣን በእግዚአብሔር ላይ በማመፁ በመስቀል ላይ ተፈርዶበታል። በሞት ፍርድ ሥር የነበረውን የሰው ዘር ለማዳን ሲባልም የክርስቶስ ሞት አስፈላጊ ሆነ። 

ቀደም ሲል በክርስቶስ ሕይወት የታየ ሌላ ክሥተትም ክርስቶስ ሰይጣንን ያሸነፈው መሆኑን አመልክቷል። ወንጌሉን ለመስበክና ተአምራት ላማድረግ የተላኩት ሰባ ሰዎች ተመልሰው፥ “ጌታ ሆይ፥ አጋንንት እንኳ በስምህ ተገዝተውልናል” አሉ (ሉቃስ 10፡17)። ክርስቶስም ሲመልስሳቸው “ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ። ብሏል (ቁ. 18)። ይህ የሰይጣንን የመጨረሻ ውድቀት የሚያመላክት ትንቢታዊ ገላጣ ነበር። 

ለ. የሰይጣን ከሰማይ መጣል 

ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት አርባ ሁለት ወራት ቀደም ብሎ በሺህ ዓመቱ መንግሥት መጀመሪያ አካባቢ፥ የቅዱሳን መላእክት አለቃ በሆነው ሚካኤልና ሰይጣን (“ዘንዶው” ተብሎ የተገለጠው) መካከል በሰማይ ጦርነት ይካሄዳል (ራእይ 12፡7-9)። ሰይጣን በሚዋጋበት ጊዚ “መላእክቱ” ማለትም የወደቁት መላእክት ከጎኑ ይቆማሉ። ሰይጣንና የወደቁት መላእክት በውጊያው ይሸነፋሉ፤ “ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ” (ራእይ 12፡9)። 

ራእይ 12፡10 ውስጥ እንደተገለጠው፥ ዕይጣን ባለማቋረጥ ወንድሞችን በመክሰስ በአምላካችን ፊት ቀንና ሌሊት ያሳጣቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰኢዮብ የተጠቀሰው የሰይጣን የክስ ተግባር፥ በመጨረሻ በራሱ በሰይጣን ላይ የሚደርሰውን የኋላ ኋላ ፍርድ በማመልከት ይጠቃለላል። ከዚህ ነጥብ ጀምሮ፥ ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት ሰግምት እርባ ሁለት ወራት በፊት (ራእይ 12፡6 ይመልከቱ) ትንቢታዊ ፕሮግራም መሠረት ሰይጣንና ክፉ መላእክት ላረዥም ጊዜ ከሰማይ ይወገዳሉ። ክርስቶስን ለመፈተን ባልቻለ ወቅት መታየት የጀመረው የሰይጣን ሽንፈት ክርስቶስና ተከታዮቹ አጋንንትን ባስወጡበት ክንውን ገሃድ ለመሆን ችሏል። ክርስቶስ የመስቀል ላይ ሞት የተረጋገጠው የሰይጣን ድል መሆን በፍጥነት ወደ ፍጻሜው በመገስገስ ላይ ነው። ቀደም ሲል ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘውና ፍርድ የተሰጠው ሰይጣን አሁን ፍርዱ ተፈጻሚ ይሆንበታል። 

ሐ. የሰይጣን ታሥሮ ወደ ጥልቁ መጣል 

በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ወቅት ፍርድ የሚሰጠው በተሳዳቢዋ ዓለምና በአለቆቿ ሳይ ብቻ ሳይሆን፥ በሰይጣንና በወደቁት መላእክት ላያም ነው። በራእይ 20፡1-3 ውስጥ ዮሐንስ የሚከተለውን ጽፏል፡- “የጥልቁንም መክፈቻና ታላቁን ሰንሰለት በእጁ የያዘ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። የቀደመውንም እባብ ዘንዶውን እርሱም ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን ያዘው፥ ሺህ ዓመትም አሠረው፥ ወደ ጥልቅም ጣለው፥ አሕዛብንም ወደፊት እንዳያስት ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በእርሱ ላይ ዘግቶ ማኅተም አደረገሰት፤ ከዚያም በኋላ ለጥቂት ጊዜ ይፈታ ዘንድ ይገባዋል።” 

በዚህ ራእይ፥ ስለ ሰይጣን ፍርድ ተጨማሪ ነገር ተገልጧል። የሰይጣን መታሠር ወደ ጥልቁ መጣልና የተዘጋበት መሆኑ ብቻ ሳይሆን፥ ይህ ፍርድ የተሰጠበት ምክንያትም ለዮሐንስ ተነግሮታል። የዚህ ፍርድ ዓላማ የሺህ ዓመቱ መንግሥት አገዛዝ እስኪፈጸም ሰይጣን ሕዝቦችን እንዳያስት ነው። እውነቱ ለዮሐንስ በራእይ የተገለጠ ስለሆነ የዚህ ራእይ ፍች ግልጥ ነው። ሰይጣን አዳምና ሔዋን ከተፈጠሩበት ጊዜ አንሥቶ ያደርግ እንደነበረው ዓለምን ሊያታልል አይችልም። 

በክርስቶስ ምድራዊ የሺህ ዓመት አገዛዝ ወቅት የሰይጣን መታሠር ግልጥ እውነትነት፥ የሺህ ዓመቱ መንግሥት ገና የሚሆን እንጂ አሁን ያለ የእግዚአብሔር አገዛዝ ላለመሆኑ ሌላው ጠቃሚ ማረጋገጫ ነው። ቀደም ሲል እንደተመለከትነው (ምዕራፍ 23)። ሰይጣን አሁን ያልታሠረ መሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ግልጥ ሆኗል። ራእይ 19-20 ውስጥ ያለው ቃል በቀጥታ መፈጻም ካለበት፥ መጀመሪያ የክርስቶስ ምጽአት፥ ከዚያ ቀጥሉ ወዲያው የሰይጣን መታሠር ተግባራዊ ሊሆን የግድ ነው። ራእይ ምዕራፍ ሀያ ውስጥ ከርሱ ቀደም ብለውና በኋላ ከሚፈጸሙት ክሥተቶች ጋር የሺህ ዓመቱ መንግሥት ስድስት ጊዜ ተጠቅሷል። በግልጥ እንደሚታየው፥ ሰይጣን የሚታሠረው የሺህ ዓመቱ መንግሥት ጊዜ ከመጀመሩ በፊት ነው። 

ስለወደቁት መላእክት እዚህ ምንም ሳይጠቀስ፥ ከሰይጣን ጋር ከአርባ ሁለት ወራት በፊት ከሰማይ እንደተጣሉ ሁሉ አብረውት እንደሚታሠሩ ለመገመት ይቻላል። መጨረሻው ላይ ለአጭር ጊዜ ሲፈታ ከሚሆነው በቀር፥ በሺህ ዓመቱ መንግሥት ውስጥ ሰይጣን ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ሲያደርግ የሚያሳይ መረጃ የለም። 

መ. የሰይጣን የመጨረሻ ፍርድ 

በራእይ 20፡7 ውስጥ “ሺሁም ዓመት ሲፈጸም ሰይጣን ከእሥራቱ ይፈታል” ይሳል። ቀጠል አድርገን ስናነብ ደግሞ የሚከተለውን አሳብ እናገኛለን፡- “በአራቱም በምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ፥ ሰግንና ማጎግን እንዲያስታቸው ለሰልፍም እንዲያሰከትታቸው ይወጣል፤ ቁጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ የሚያህል ነው። በውጫዊ ጎጽታቸው ብቻ ክርስቶስን እንከተላለን ይሉ የነበሩ ሰዎች በሰይጣን እየተመሩ አሁን እውነተኛውን ማንነታቸውን ያሳያሉ። እነዚህ በሺህ ዓመቱ መንግሥት ዘመን የተወለዱ ልጆች ናቸው፤ ምንም እንኳ በሁኔታዎች አስገዳጅነት በክርስቶስ አምነናል ቢሉ፥ አሁን ግን በግልጥ ዓመፅ የቅዱሳንን ሰፈር እና የተወደደችውን ከተማ ማለትም ኢየሩሳሌምን ይወራሉ። ዕድል-ፈንታቸው ቅፅበታዊ ፍርድ ሲሆን፥ ራእይ 20፡9 ውስጥ እንደሚለው፥ “እሳት ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወርዳ በሳቻቸው።” 

ከዚያም ወዲያውኑ «ያሳታቸውም ዲያብሎስ፥ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣል፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሣቀያሉ” (ቁ. 10)። እግዚአብሔር ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ያዘጋጃቸው የመጨረሻ 

መቅጫ የእሳት ባሕር እንደመሆኑ፥ የሰይጣን መጨረሻ በዚሁ ይደመደማል (ማቴ. 25፡4 )። 

የወደቁ መላእክትም ሰይጣን መጀመሪያ በእግዚአብሔር ላይ የወጠነው ዓመፅ ተካፋዮች ስለነበሩ ፍርድ ተሰጥቷቸዋል (ኢሳ. 14፡12-17፤ ሕዝ. 28፡12-19)። 2ኛ ጴጥሮስ 2፡4፥ “እግዚአብሔር ኃጢአትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ” እንደሰጣቸው ይናገራል። “ገሃነም” የሚለው ቃል የሚያመለክተው፥ ኃጢአተኛ ወደ ዘላለማዊ የቅጣት ስፍራ ከመሄዱ በፊት ለጊዜው የሚቆይበትን ስፍራ ማለትም “ሲኦልን” ሳይሆን፥ ዘላለማዊውን የቅጣት ስፍራ ነው (ራእይ 20፡13-14)። 

– የመላእክትም ፍርድ ይሁዳ መጽሐፍ ቁጥር 6 ውስጥ እንዲህ ተመልክቷል። “መኖሪያቸውን የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘሳሰም እሥራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ፍርድ ቀን ድረስ ጠብቋቸዋል።” ይህ አሳብ ስለ ሰይጣንና መላእክቱ ውድቀትና ፍርድ ከሚናገሩት ሴሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች ጋር ሲያያዝ፥ የሚያስተላልፈው ግልጥ መልእክት አለ። ይሄውም ምንም እንኳ ሰይጣንና አንዳንድ ክፉ መላእክት የተወሰነ ነጻነት ቢሰጣቸው፥ በቅዱሳን መላእክትና በእግዚአብሔር ሰዎች ላይ የማያቋርጥ ጦርነት ቢከፍቱም፥ የታሠሩና ነጻነት የተነፈጋቸው ሌሎች መላእክት የሚኖሩ መሆናቸውን ነው። ይሁን እንጂ፥ ክፉዎቹ መላእክት ሁሉ “ለታላቁ ፍርድ ቀን” የተወሰኑ ናቸው። ይህ “የታላቁ ፍርድ ቀን” በሺህ ዓመቱ መንግሥት ፍጻሜ ሰንሰይጣንና በወደቁት መላእክት ሁሉ ላይ የሚሰጥ ነው። 

ምንም እንኳ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሰይጣንና የወደቁ መላእክት በዓለም ላይ ከፍተኛ ኃይልና ተጽዕኖ ሲያሳድሩና ባለማቋረጥ እግዚአብሔርን ሲቃወሙ፥ የኋላ ኋላ ሽንፈታቸውና ዘላለማዊ ፍርዳቸው አይቀሬ ነው። እንደ ኢዮብ የሰይጣን ጥቃት የደረሰባቸው ክርስቲያኖች የኋላ ኋላ ድላቸው የተረጋገጠ እንደሚሆንና፥ እግዚአብሔር በራሱ ጊዜ በጠላቶቹ ላይ የሚፈርድባቸው መሆኑን በመረዳት ሊያርፉ ይችላሉ። በሰይጣንና በመላእክቱ ላይ የሚሰጠው ፍርድ ዘላለማዊ የመሆኑ ግንዛቤ የመጣው፥ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ሰሺህ ዓመቱ መንግሥት መጀመሪያ እሳት ባሕር ውስጥ ተጥለው እስከ መንግሥቱ ፍጻሜ እዚያው ከመሆናቸው የተነሣ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ እንደሚናገረው፥ ሁለት ዓበይት ፍርዶች ብቻ አሉ። እነዚህም ማለቂያ የሌለው ሰማያዊ በረከት መቀበልና ዘላለማዊ የሆነው የእሳት ባሕር ሥቃይ ናቸው።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

51
ትምህርት 51 ከ52

ታላቁ የነጭ ዙፋን ፍርድ

ሀ. የታላቁ ነጭ ዙፋን የመጨረሻ ፍርድ 

እንደ ሰብአዊ ታሪከ ድምዳሜነቱ በሺህ ዓመቱ መንግሥት መጨረሻ ላይ የታላቁ ነጭ ዙፋን ፍርድ የሚኖር መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል (ራእይ 20፡11-15)። ቀደም ሲል ለጻድቃን ከተደረጉትና በዓለም በሚኖሩ እስራኤላውያን እንዲሁም እሕዛብ ላይ ከተበየኑት የተለያዩ ፍርዶች ጋር ሲነጻጸር ይህ የመጨረሻው ፍርድ ነው። ከዐውደ-ንባቡ አኳያ ስንመለከተው ይህ ፍርድ ኃጢአተኞችን ብቻ ይመለከታል። 

ለ. የሰማይና የምድር ውድመት 

ታላቁ የነጭ ዙፋን ፍርድ ከመካሄዱ በፊት የሚከተለው ነገር እንደሚሆን ራእይ 20፡11 ውስጥ ተጽፏል፤ “ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም እልተገኘላቸውም።” ሰብአዊ ታሪከ ዘመኑን ስሰፈጀ፥ ራእይ 21፡1 ውስጥ እንደተገለጠው አሮጌው ፍጥረት ይደመሰሳል። “ፊተኛው ሰማይና ፈተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፥ ባሕርም ወደፊት የለም።” 2ኛ ጴጥሮስ 3፡10-12 ይህንኑ ክሥተት በማመልከት ታላቁን አወዳደቅ በሚከተሉት ቃላት ይገልጣል፡- “በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኩሳት ይቀልጣል፥ ምድርም በእርሷ ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል” (ቁ. 10)። ቀጣዩ ቁጥርም ይህንኑ ያረጋግጣል፤ “ስለዚያ ቀን ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኩሳት ይፈታል”፤ ቁጥር 11 እና 12 ውስጥ ደግሞ አሳቦቹ ተዋሕደው፥ “ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኩሳት ይፈታል” ተብሏል። 

ሐ. ድነት ያላገኙ ሙታን ትንሣኤ 

ራእይ 20፡12 ውስጥ እንደተጠቀሰው፥ “ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው ዮሐንስ ተመልክቷል። ራእይ 20፡13 ውስጥ ደግሞ፥ “ሳሕር በእርሱ ውስጥ ያሉትን ሙታን ሰጠ፤ ሞትና ሲኦልም በነርሱ ውስጥ ያሉትን ሙታን ሰጡ” በማለት ያክላል። ድነት ያላገኙ ሙታን ሁሉ ከሞት ተነሥተው ፍርዳቸውን ለመቀበል በእግዚአብሔር ፊት ቆመዋል። ከዮሐንስ 5፡27 እንደምንረዳው፥ ፈራጁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በዚያ ክፍል እግዚአብሔር አብ ለወልድ “የሰው ልጅም ስለሆነ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው”ይላል። 

መ. የሰዎችን ሥራዎች የሚገልጡ መጻሕፍት ተከፈቱ 

ራእይ 20፡12 ውስጥ “መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ፤ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ” ይላል። ቀጣዩ ቁጥር ይህንኑ የፍርድ እውነታ እንዲህ ይደግመዋል፡- 

“እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን ተከፈለ።” ጳጋን ያለመቀበል ውጤት እዚህ ላይ በግልጥ ይታያል። ከክርስቶስ ውጭ ይቅርታ ስለሌለ (ሐዋ. 4፡12)፥ ጸጋውን ያልተቀበሉ ሁሉ ስለ ኃጢአታቸው ተገቢውን ቅጣት ይቀበላሉ። 

የሰዎች ሥራ ብቻ ሳይሆን ስማቸውም በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ መኖሩ ይጣራል። ስማቸው ከመጽሐፉ ውስጥ ከሌለ፥ የዘላለም ሕይወት የላቸውም ማለት ነው። 

ይህ ጥፋታቸውን ገሃድ ያደርገውና፥ ራእይ 20፡14-15 ውስጥ እንደተጠቀሰው፥ “ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ። ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው። በሕይወትም መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ” የተባለው ይፈጸማል። 

ምንም እንኳ ፍርድ ከተሰጣቸው መካከል በአንጻራዊነት አንዳንዶቹ ከሌሎቹ የተሻለ መልካምነት ሊኖራቸው ቢችል፥ የዘላለም ሕይወት ማጣት እጅግ የከፋ ነው። የዘላለም ሕይወት የሌላቸው ሰዎች ሁሉ ከሥራዎቻቸውና በክርስቶስ ካለማመናቸው አኳያ ተፈርዶባቸው፥ ወደ እሳት ባሕር ይጣሳሉ። የሚያሳዝነው፥ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ክርስቶስ ለዳኑት እንደሞተ ሁሉ ለእነርሱም የሞተ መሆኑ ነው። 

2ኛ ቆሮንቶስ 5፡19 ውስጥ፥ “እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውንም አይቆጥርባቸውም ነበር” ይላል። 1ኛ ዮሐንስ 2፡2 ውስጥ ደግሞ ክርስቶስ፥ “የኃጢአታችን ማስተሥረያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ” የሚል ቃል እናነሳለን። እነዚህ ወደ ዘላለማዊ ቅጣት የሚጣሉ ሰዎች በክርስቶስ ቢያምኑ ኖሮ ይድኑ ነበር። የሚጠፉት እግዚአብሔር ስላልወደዳቸው ወይም ጻጋው ስላልበቃቸው ሳይሆን፥ ለማመን ባለመፈለጋቸው ነው። ወንጌሉን የመስማት ዕድል ያልነበራቸው ሰዎች ደግሞ እግዚአብሔር በተፈጥሯዊ ዓለም የሰጣቸውን ምስክርነት ባለመቀበላቸው ይጠፋሉ (ሮሜ 1፡18-20)። እነዚህ የበራሳቸውን ብርሃን ያልተቀበሉና ተገቢ ቅጣታቸውን ያገኙ ናቸው። የነጩ ዙፋን ፍርድ ክርስቶስን እንደ አዳኛቸውና ጌታቸው አድርገው ባልተቀበሉ ሰዎች ሁሉ ላይ የሚደርስ እጅግ አሳዛኝ ፍጻሜ ነው።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

52
ትምህርት 52 ከ52

አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር

ሀ. አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር 

ከታላቁ የነጭ ዙፋን ፍርድ እንዲሁም ከመጀመሪያው ሰማይና ምድር ውድመት በኋላ የሚሆነውን ነገር አስመልክቶ ዮሐንስ የሚከተለውን ጽፏል፡- “አዲስ ሰማይና አዲስ ምድርን አየሁ፥ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛዪቱ ምድር አልፈዋልና” (ራእይ 21፡1)። ስለ አዲሱ ሰማይ የተገለጠ ነገር የለም። ስለ አዲሲቱ ምድር የተገለጠ ነገር ቢኖር “ባሕርም ወደ ፊት የለም” የሚለው ነው (ራእይ 21፡1)። ስለ አዲሲቱ ሰማይና ምድር መጽሐፍ ቅዱስ ዝም የማለቱ ምክንያት በየትኛውም ስፍራ ማብራሪያ አልተሰጠውም። ይልቁንም ትኩረታችንን ወደ አዲሲቱ የኢየሩሳሌም ቅድስት ከተማ ይወስደዋል። 

ለ. የአዲሲቱ ኢየሩሳሌም አጠቃላይ ገለጣ 

ዮሐንስ የተመለከተውን ነገር እንዲህ ሲል ያወጋናል፡- “ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥ ለባልዋ እንደተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ” (ራእይ 21፡2)። የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎችን ሁሉ የሚገጥማቸው ቅፅበታዊ ችግር ዮሐንስ የተመለከተው ነገር ፍች ነው። ቀጥተኛ እሳቡን ከወሰድን፥ ዮሐንስ የተመለከተው፥ ከምድር ጋር አብራ ከጠፋችው አሮጌዪቱ ኢየሩሳሌም በተቃራኒ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ተብላ የተጠቀሰች ቅድስት ከተማን መሆኑን እንረዳለን። ከተማዪቱ “ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደወረደች” ተገልጧል። እንደተፈጠረች ግን እልተገለጠም። ከሺህ ዓመት መንግሥት በፊት ከአሁኗ ምድር በላይ የነበረች ከተማም ትመስላላች። ከሞት ለተነሡትና ወደ ቅድስናቸው ለገቡት አማኞች በሺህ ዓመቱ መንግሥት ጊዜ በዚህ ሁኔታዋ በመኖሪያነት ሳታገለግል አትቀርም። ስለ ሺህ ዓመቱ ዘመን ምድር ከቀረበው ገለጣ ለመረዳት እንደሚቻለው፥ በምድር ላይ እንደ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ያለ ከተማ አልነበረም። እንዳንዶች ጌታችን ዮሐንስ 14፡3 ውስጥ ሜጄ ስፍራ አዘጋጅላችኋለሁ”፥ ሲል ስለ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም መናገሩ ነበር ብለው ያምናሉ። በራእይ መጽሐፍ መሠረት አዲሲቱ ከተማ ካሰማይ በመምጣት በአዲሲቱ ምድር ላይ እንድትቀመጥ የተወሰነ ይመስላል። 

ዮሐንስ በተጨማሪም ከተማይቱን “ለባሏ እንደተሸለመች ሙሽራ” ብሉ ይገልጣታል። አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ለባሏ እንደተሸለመች ሙሽራ ውብ ናት። ስለሆነም፥ ከተማዪቱ አካላዊ ሕልውናና የሙሽራ ውበት ያላት መሆኑ ግልጥ ነው። 

ምንም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ አዲሱ ሰማይና አዲሲቱ ምድር የሚናገሩ ክፍሎች ብዙዎች ባይሆኑ፥ አሳቡ ራእይ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሰው ለመጀመሪያ ጊዜ አለመሆኑ ግልጥ ነው። ኢሳይያስ 65፡17 ውስጥ እግዚአብሔር እንዲህ ብሏል፡- “እሆ፥ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እፈጥራለሁና፤ የቀደሙትም አይታሰቡም፥ ወደ ልብም አይገቡም።” ይህ ጥቅስ የሚገኘው ካሺህ ዓመቱ መንግሥት ጋር በተዛመደ ሁኔታ በመሆኑ፥ አንዳንዶች በሺህ ዓመቱ ዘመን ስለምትታደሰው ኢየሩሳሌም የሚናገር ነው ይላሉ። ይሁንና፥ ይህ ክፍል አዲሲቱ ምድር ላይ የምትሆነውን አዲሲቱን ኢየሩሳሌም የሚያመለክት መሆኑን መረዳቱ የተሻለ አማራጭ ይሆናል። 

ሌላው ጥቅስ ኢሳይያስ 66፡22 ውስጥ ያለው ሲሆን፥ የሚከተለውን እሳብ ያስተላልፋል፡- “እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፥ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።” ምድራዊቷ ኢየሩሳሌም በሺህ ዓመቱ ፍጻሜ ላይ የምትደመሰስ ስትሆን፥ አዲሲቷ ኢየሩሳሌም ግን እንደ እስራኤል ዘር ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች። 

2ኛ ጴጥሮስ 3፡13 ውስጥ ስለ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር የተነገረው ሌላ ትንቢት፥ “ጽድቅ የሚኖርባት” እንደምትሆን ያስረዳል። ስለሆነም፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት ቃላት ሁሉ የሚያስረዱት፥ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር የታሪክ የመጨረሻ ግብና የቅዱሳን የማረፊያ ስፍራ መሆናቸውን ነው ብሎ ለመደምደም ይቻላል። 

ዮሐንስ አዲስ ሰማይን፥ አዲስ ምድርንና አዲሲቱን ኢየሩሳሌም ካስተዋወቀ በኋሳ፥ ራእይ 21:3-8 ውስጥ ዋነኛ ባሕርያቸውን ይገልጣል። በዚያ ስፍራ እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር ይኖራል፤ “አምላካቸውም ይሆናል”። ኀዘን፥ ሞትና ሥቃይ ከእንግዲህ አይኖርም፤ “የቀደመው ሥርዓት እልፎአልና” (ቁ.4)። ይሄው እሳብ ቁጥር 5 ውስጥ ““እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ” በሚለው ዓረፍተ ነገር ተረጋግጧል። 

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ አልፋና ኦሜጋነቱ በአዲሲቱ፥ ኢየሩሳሌም “ለተጠማ የሕይወትን ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ። ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል፤ አምላክም እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል” (ቁ. 6-7) በማለት ተስፋ ይሰጣል። በአንጻሩ፥ በክፉ ሥራዎቻቸውና በእምነት እልባነታቸው የተገለጡት ያልዳኑ ሰዎች፥ “ዕድላቸው በዲንና በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይሄውም ሁለተኛ ሞት ነው” (ቁ. 8)። አካላዊና መንፈሳዊ ከሆነው የመጀመሪያው ሞት ጋር ሲነጻጸር፥ ሁለተኛው ሞት ለዘላለም ከእግዚአብሔር መለየት ነው። 

ሐ. የአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ራእይ 

ዮሐንስ “የበጉ ሚስት የሆነችውን ሙሽራ፥ እንዲመለከት ተጋብዞ ነበርና፥ “በመንፈስ ወደ ታላቅና ረጅም ተራራ” ተወሰደ (ራእይ 21፡9-10)። እዚያ ሆኖ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ ይመለከታል። 

እንደ ቀጣዩ ራእይ 21 ገላጣ፥ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም “የእግዚአብሔር ክብር” አለባት፤ “ብርሃንዋም እጅግ እንደከበረ ድንጋይ እንደ ኢያሰጲድ ድንጋይ ሆኖ እንደ ብርሌ የጠራ ነበር” (ቁ. 11)። ምንም እንኳ ኢያሰጲድ የተለያየ ቀለም ያላቸውን ድንጋዮች የሚያመለክት ቢሆንና እብዛኞቹ የዘመናችን የኢያሰጲድ ድንጋዮች የጠሩ ባይሆኑ፥ እዚያ የተጠቀሰው ድንጋይ ግን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቅ መሆኑ ተመልክቷል። ዮሐንስ ሊጎልጥ የፈለገው እጅግ የላቀውን ውበት ነው። 

ቀጣዮቹ ቁጥሮች እንደሚያስረዱት የከተማይቱ ቅጥር አንድ መቶ አርባ አራት ክንድ ሲሆን፥ በአሥራ ሁለት መላእክት የሚጠበቁ አሥራ ሁለት ደጆች አሏት (ራእይ 21 ፡12)። ደጆቿ ላይ የአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ስሞች ተጽፈውባቸዋል። ከተማዪቱ በቅርፅ አራት ማዕዘን ስትሆን፥ ወደ ሰሜን፥ ደቡብ፥ ምሥራቅና ምዕራብ ትመለከታለች። ይህ ምናልባትም እንደአሁኗ ምድር በአዲሲቱም ምድር የተለያዩ አቅጣጫዎች የሚኖሩ መሆኑን ያመለክታል። ቅጥርዋ ያረፈው እሥራ ሁለት መሠረቶች ላይ ሲሆን፥ እንደ ቁጥር 14 አገላለጥ መሠረቶቹ ላይ የአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈውባቸዋል። 

ከተማዪቱ ተለክታ የተገኘው ውጤት አሥራ ሁለት ሺህ ምዕራፍ ወይም ወደ ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ኪሎ ሜትር ያህል ርዝመት ነው። ቁመቷም ከወርዷ ጋር እኩል ነበር። ይህ ከተማዪቱ ሰቅርፅ ኩብ ናት ወይስ ፒራሚዳዊ? የሚል ጥያቄ አስነሥቷል። 

ምናልባትም ፒራሚዳዊ ቅርፅ እንዳላት መገመቱ ሳይሻል አይቀርም። ራእይ 22: 1-2 ውስጥ እንደተመለከተው፥ በከተማዪቱ መካከል ውኃ እንዴት እንደሚፈስ ለማብራራት ይህ ይረዳል። 

በከተማዪቱ ውስጥ የሚገኙት ነገሮች በአጠቃላይ ብርሃን አስተላላፊዎች ናቸው። ወርቁ እንኳን እንደ ብርጭቆ የጠራ ነው (21፡18)። የከተማዪቱ ግድግዳ መሠረቶች ቤተ ክርስቲያንን የሚወክሉ አሥራ ሁለት ደቀ መዛሙርት ስሞች የተጻፉባቸውና በአሥራ ሁለት ውብ ድንጋዮች የተጌጡ ሲሆኑ፥ በቀስተ ደመናና በከተማዪቱ ድንቅ ብርሃን ውስጥ የሚገኙ ቀለማትን ያንጸባርቃሉ። ይህ ሁሉ ተዋሕዶ ሲታይ ልብን ይመስጣል (ቁ. 19-20)። 

የካተማዪቱ ደጆች ሰፋፈ፥ እያንዳንዳቸው ከዕንቁ የተሠሩና አደባባይዋ ጥሩ ብርጭቆ የሚመስል ወርቅ እንደሆነ ተገልጧል (ቁ. 21)። እግዚአብሔር በውስጧ ስለሚኖር፥ ለከተማይቱ መቅደስ አያስፈልጋትም (ቁ. 22)፤ የእግዚአብሔርና የበጉ ክብር ስለሚያበራላትም የፀሐይ፥ የጨረቃ ወይም የከዋክብት ብርሃን አያስፈልጋትም (ቁ. 23)። ከአሕዛብም የዳኑት በከተማይቱ ብርሃን እየተመላለሱ በነጻነት ወደ ሰሮቿ ይገባሉ። በዚያም ሌሊት ስለሌለ” ደጆቿ ከቶ አይዘጉም (ቁ. 25)። 

በዚህ ገለጣ መሠረት፥ የከተማይቱ ነዋሪዎች የሁሉም ዘመናት ቅዱሳን ናቸው። የተጠቀሱት እስራኤልና አሕዛብ ብቻ ሳይሆኑ፥ ቤተ ክርስቲያንን የሚወክሉ አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ጭምር ናቸው። ይህ በዕብራውያን መልእክት ምዕራፍ 12፡22-24 ውስጥ ከተገለጠው አሳብ ጋር ይስማማል። ምንባቡ እንደሚያስረዳው፥ በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም የሚገኙ ቅዱሳን፥ “አእላፋት መላእክትን፥ በሰማይ የተጻፉትን የበኩራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ የሚሆነውን እግዚአብሔርን፥ ፍጹማን የሆኑትን ጻድቃን መንፈሶችና የአዲስ ኪዳን መካከለኛ የሆነው ኢየሱስን” ያጠቃልላሉ። ከዚህ በመነሣት፥ ቤተ ክርስቲያን፥ “ፍጹማን የሆኑት የጻድቃን መንፈሶች፥ መግለትም በቤተ ክርስቲያን ያልተካተቱት አይሁዶችና እሕዛብ፥ መላእክትና የአዲሱ ኪዳን መካከለኛ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ይገኛሉ በማለት ለመደምደም ይቻላል። 

ዮሐንስ ስለ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ባቀረበው ተጨማሪ ማብራሪያ፥ በአደባባይዋ መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውኃ ወንዝ”” እንደተመለከተ ይገልጣል (ራእይ 22:1)። በከተማይቱ አደባባዮች መካከልና ከወንዙ ወዲያና ወዲህ አሥራ ሁለት ዓይነት ፍሬዎችን የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ እንደሚገኝና ለሕዝብ ፈውስን ወይም ጤናን እንደሚሰጥ ገልጧል (ራእይ 22፡2)። 

“ይህ የዘላለም መንግሥት ገለጣ ከሆነ፥ ፈውስ ያስፈለገው ለምንድነው?” የሚል ጥያቄ ሲነሣ ቆይቷል። “ለሕዝብ ጤና” የሚለው አተረጓጎም ከተወሰደ ችግሩ በቀላሉ ይወገዳል። ከሕይወት ውኃ በተጨማሪ የዛፍ ፍሬ መኖሩ ቅዱሳን ለዘላለም የሚኖራቸውን አካላዊ ሕልውና የሚገልጥ ሊሆን ይችላል። 

ዮሐንስ በተጨማሪም፡- “ከእንግዲህ ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔር የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል” ይላል (ቁ. 3)። በዚህ የበረከት ወቅት ቅዱሳን እግዚአብሔርን ፊት ለፊት የሚመለከቱት ሲሆን፥ ስሙም በግንባራቸው ላይ ይሆናል (ቁ. 4)። ዮሐንስ አዲሲቱ ከተማ እጅግ ብሩህ እንደምትሆንና ሌላ ብርሃን እንደማያስፈልጋት በድጋሚ በመግለጥ፥ ከእግዚአብሔር የሰማውን ቃል እንዲህ ይፈጽማል፡- “እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ። የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብፁዕ ነው” (ቁ. 7)። 

አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር የቅዱሳን ዘላለማዊ መኖሪያዎች መሆናቸው ሲታሰብ፥ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለዚህ እሳብ የተገለጠው ብዙ አይደለም። እርግጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ቀዳሚ ዓላማ ለአሁኑ የሕይወት ጉዟችን ብርሃን ይሆነን ዘንድ ነው። በእምነት ጉዟችን እኛን ለማበረታታት ሲባል ስለሚመጣው ክብርም በቂ ፍንጭ ተሰጥቶናል። የማያጠራጥረው ሐቅ ግን በራእይ መጽሐፍ የፍጻሜ ምዕራፎች ውስጥ ከተመሰከትነው ፍንጭ የሳቀ ክብር የሚጠብቀን መሆኑ ነው። 

ምንም እንኳ እግዚአብሔር “ዓይን ያላየችው፥ ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበ” ነገር (1ኛ ቆሮ. 2፡9) ጨልፎ ለሕዝቡ ያሳየ ቢሆንም፥ ገና ብዙ የሚያሳየን ነገር በዘላለማዊ መንግሥቱ ውስጥ አለ። ካለው ግማሹ እንኳ ያልተገለጠ ሲሆን፥ ታላቁ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኛቸውና መድኃኒታቸው አድርገው ላመኑ ሰዎች ፍቅሩንና ጸጋውን ለመግለጥ የማይነገር ዘላለማዊ ደስታ ይሰማዋል። 

የመንግሥተ ሰማይን ድንቅ ነገሮች የሚገልጥልን የእግዚአብሔር ቃል መጽሐፍ ቅዱስ፥ በኃጢአት የወደቀው የሰው ዘር ወደዚያ የሚገባበትን ቅድመ ሁኔታም ያስረዳል። እግዚአብሔር ሰዎችን ለማዳን ስለከፈተው ብቸኛ መንገድ የሚሰጠውን ማብራሪያ ችላ ብለው ወደ መንግሥተ ሰማይ እንደሚገቡ እርግጠኞች በመሆን የሚኖሩ ብዙ ሰዎች አሉ። ነገር ግን መንግሥተ ሰማይ ሁሉም የሚገባባት አይደለችም፤ ያ ሁሉ ክብርና በረከት ለዳኑት ብቻ ይሆናል። ድነትም የሚገኘው አዳኙን በፍጹም ልብ በመቀበል ነው። ይህ ለመቀበል እጅግ የቀለለ፥ ዋነኛና የተረጋገጠ እውነት ስለሆነ፥ በክርስቶስ ያመነ ሰው፥ ለድነቱ ከሁሉ በላይ በርሱ ላይ እንዲደገፍ ዋስትና ይሆነዋል።

ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

52ቱን ትምሕርቶች አጠናቀዋል

የተማሩትን በሕይወትዎ ይተግብሩ፣ መጽሐፍ ቅዱስንም በትጋት ማጥናትዎን ይቀጥሉ።