አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

የኢየሱስ ክርስቶስ ሰብአዊነት 

This entry is part 15 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

በትምህርት አንድ ላይ፥ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ሙሉ በሙሉና ፍጹም እግዚአብሔር መሆኑን እንደሚያስተምር ተገንዝበናል። እንደዚሁም መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ሙሉ በሙሉና ፍጹም ሰው መሆኑን ያስተምራል። ኢየሱስ በልደቱ ኃጢአት የሌለበትና ኃጢአትም ያላደረገ ንጹሕ ካመሆኑ በስተቀር ልክ እንደ እኛው ሰው ነበር። በዚህ ሳምንት በመቀጠል የክርስቶስን ስብእና በተመለከተ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ማብራሪያ የሚሰጡንን ትምህርቶች እናጠናለን።  የኢየሱስ ፍጹም ሰብአዊነት  ዛሬ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰብአዊነት የሚያስረዳንን ትምህርት ማጥናት እንጀምራለን። አዲስ ኪዳን ኢየሱስ በተፈጥሮ ኃጢአት የሌለበትና ኃጢአትም ያላደረገ ንጹሕ ከመሆኑ በስተቀር፥ ልክ እንደ እኛ ሰው እንደነበረ በግልጽ ያስተምረናል። እንግዲህ በዛሬውና በነገው ትምህርታችን ላይ ስለ ኢየሱስ ሰብአዊነት የቀረቡ ልዩ ልዩ የማረጋገጫ ትምህርቶችን እንማራለን። በዚህ ሳምንት ቆየት ብለን ደግሞ ስለ ክርስቶስ ሰብአዊነት የሚናገሩ ልዩ ምክንያቶችን የምንመለከት ሲሆን፥ እነርሱም በፈተና ወቅት ምንም ኃጢአት ስላለማድረጉና ከድንግል ስለ መወለዱ ናቸው።  1. ኢየሱስ ሰው እንዲሆን ለምን አስፈለገ?  1.1 ኢየሱስ ሰው እንዲሆን ያስፈለገበት ምክንያት የሰው ልጆች በሞት ላይ ድልን እንዲቀዳጁ ለማድረግ የዘላለም ሕይወትን  ለመስጠት ነው።  የኢየሱስ ፍጹም ሰብአዊነት አማኞች ሊያውቁት የሚገባቸው በጣም ጠቃሚ የሆነ ትምህርት ነው። ጌታ ኢየሱስ ሰው እንዲሆን ያስፈለገበት የተለያዩ ምክንያቶች ነበሩ።  ጥያቄ፡- ዕብራውያን 2፡14-15 እና 1ኛ ቆሮንቶስ ኢየሱስ ሰው እንዲሆን በምን ምክንያት አስፈለገ?  ዕብራውያን 2፡14-5 ያለው ክፍል ኢየሱስ ሰው እንዲሆን በምን ምክንያት እንዳስፈለገ ይነግረናል። ኢየሱስ ወደ እዚህ ምድር የመጣበት አንዱና ዋናው ምክንያት ሰይጣንና በሰው ልጆች ላይ የነበረውን የበላይነት ለመደምሰስ ነው። ከእነዚህ ካነበብናቸው ጥቅሶች እንደምንረዳው ሰይጣን በሰው ልጆች ላይ ከነበረው ሥልጣን የሞት ኃይል በእጁ መሆኑ አንደኛው ገጽታ ነው። ያ ማለት ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጭ ሰዎችን ለመግደል ኃይል አለው፥ ወይም ኢየሱስ የሞተው ለሰይጣን ብድራቱን ሊከፍል ነው ማለት አይደለም። ሰይጣን በሞት ላይ ያለው ሥልጣን እኛ ኃጢአት እንድንሠራ መፈተን ነው። እኛ ደግሞ ኃጢአት ስናደርግ የእግዚአብሔርን ሕግ ስለምንተላለፍ በሥጋም በመንፈስም እንድንሞት ይፈረድብናል። ስለዚህ ከኃጢአታችን የተነሣ የሞትና የሰይጣን ባሪያዎች እንሆናለን። እንግዲህ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው እንዲሆን ያስፈለገበት  ምክንያት ሰይጣን በእኛ ላይ ያለውን ሥልጣን እንዲያስወግድ ነው። ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ በሞቱ የሰይጣንን ኃይል ሽሮታል። እርሱም በሞተ ጊዜ እኛ ልንሞተው የሚገባንን ሞት ሞተልን። በዚህም ሞቱ የኃጢአታችንን ቅጣት ከፈለልን። በመሆኑም ክርስቲያኖች ስለ ኃጢአታቸው ዋጋ ስለተከፈለላቸው መፍራት የለባቸውም። ዘላለማዊ ሞት ይደርስብናል ብለው ሊሰጉ አይገባም። ኢየሱስ ሰው የሆነው ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት በሞቱ ቅጣታቸውን ሊቀበልና ሊከፍል ነው። እርሱ ለው ባይሆን ኖሮ ሊሞትና የሰው ልጆችን ኃጢአት ሊከፍል ባልቻለም ነበር።  ጥያቄ፡- ብዙ ጊዜ ሰዎች በቀብር ላይ ተስፋ በቆረጠና በሚያስፈራ ሁኔታ ሊያለቅሱ ይታያሉ። የክርስቶስ ሰው መሆንና ከሞት መነሣት ፍርሃትንና የሞትን ተስፋ የማስቀረጥ ሁኔታ እንዴት አስወገደ?  1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 5 እንደሚያስተምረን፥ ክርስቲያኖች ካሉን ታላላቅ ተስፋዎች መካከል ትንሣኤ ሙታን አንዱ ነው። ስለዚህ እያንዳንዱ አማኝ ከሞቱ በኋላ ከክርስቶስ ጋር ለዘላለም አብሮ ለመኖር በአዲስና ክብርን በተሞላ አካል ከሙታን ይነሣል። ታዲያ ክርስቲያኖች ይህን አስደናቂ የትንሣኤ ዋስትና እንዴት ተቀበሉት? በ1ኛ ቆሮንቶስ 15፡21 ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቲያኖች በትንሣኤ የሚነሡት ኢየሱስ ሰው ሆኖ በመሞቱ፥ ኋላም ከሙታን በመነሣቱ መሆኑን ያስረዳል። ስለዚህ ክርስቲያኖች በሞት ላይ ድልን እንዲቀዳጁ ክርስቶስ ራሱ መሞትና እንደ ሰው ከሙታን መነሣት ነበረበት። ማንኛውም ክርስቲያን ሞትን በፍርሃትና ተስፋ በመቁረጥ ስሜት ሊመለከተው አይገባም። ምክንያቱም ሁላችንም ስለ ትንሣኤ ሙታንና ስለ ዘላለም ሕይወት እርግጠኞች ነንና። ለክርስቲያኖች የተሰጠ ትንሣኤና ዘላለማዊ ሕይወት የተገኘው ኢየሱስ ልክ እንደ እኛው ሰው በመሆኑ ነው።  1.2 በድካማችን እንዲራራልንና በኃጢአት ስንፈተን እንዲረዳን ኢየሱስ ሰው መሆን ነበረበት።  ጥያቄ፡- ዕብራውያን 4፡5-16 ያሉትን ጥቅሶች አንብቡ። ሀ) ኢየሱስ ሰው እንዲሆን ለምን አስፈለገ? ለ) ኢየሱስ ክእኛ ከሰው ልጆች የሚለይበት አንድ መንገድ ምንድን ነው?  ጥያቄ፡- ያዕቆብ 1፡13 አንብቡ። ሊፈትን ወይም ሊፈተን የማይችል ማን ነው?  ዕብራውያን 4፡2-6 ያለው ክፍል ኢየሱስ ሰው እንዲሆን ያስፈለገበትን ሁለተኛ ምክንያት ያቀርባል። ይህ ክፍል ኢየሱስ ሰው በመሆን ራሱን በኃጢአት እንዲፈተን መፍቀዱን ይገልጻል። ይህን ክፍል ያቀረበልን ጸሐፊ ኢየሱስ ይፈተን እንጂ ምንም ዓይነት ኃጢአት ያልፈጸመ መሆኑን በጥንቃቄ ያስገነዝባል። ስለሆነም እርሱ በእርግጥ ቢፈተንም በአጋጠመው ፈተና ተሸንፎ ኃጢአት አልሠራም። በዚህ ሳምንት በሌላ ትምህርት ላይ መለስ ብለን ኢየሱስ ኃጢአትን እንዲያደርግ ስለደረሰበት ፈተና እንወያያለን። በዛሬው ትምህርታችን ላይ ማስተዋል ያለብን ኢየሱስ ሰው በመሆኑ ኃጢአትን እንዲፈጽም ስለ መፈተኑ ይሆናል። ያዕቆብ 1፡13 እንደሚያስረዳን፥ እግዚአብሔር ኃጢአትን እንዲፈጽም ሊፈተን አይችልም፡፡ ስሕተትንም የመፈጸም ባሕርይ የለውም። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር የሰው ልጆችን ፈተና ለመገንዘብና የሚፈተኑትንም ሊረዳቸው ሲል ራሱ ሰው ሆነ። ስለዚህ ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ የእኛ ፈተና እንዲሰማውና እንዲፈተንም ሰው ሆነ፡ ጌታ ኢየሱስ ራሱ የተፈተነ በመሆኑ በምንፈተንበት ጊዜ ከጎናችን ሆኖ ያበረታታል።  ጥያቄ፡- ሀ) ዘወትር የምትፈተኑባቸውን ሁለት መንገዶች ጻፉ። ኢየሱስ የእኛ ፈተና የሚሰማው መሆኑን መገንዘባችን ምን ያህል ያጽናናናል?  ሰዎች ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ካመኑ በኋላም እንኳን ቢሆን ፈተናዎች ያጋጥሟቸዋል። ነገር ግን ኢየሱስ ራሱ በተፈተነ ጊዜ ፈተናውን መቋቋሙን በመረዳት ልንጽናና እንችላለን። ኢየሱስ ፈተናዎችን መቋቋም ምን ያህል አስቸጋሪ መሆኑን ያውቃል፤ ፈተናዎች በሚያጋጥሙን ጊዜ ለእግዚአብሔር የምንታዘዝበትን ኃይል ይሰጠናል።  1.3 ኢየሱስ እግዚአብሔርን ለእኛ ለመግለጽ ሰው መሆን ነበረበት።  ጥያቄ፡- ዕብራውያን 1፡1-3 አንብቡ። የእግዚአብሔር ዋና ነጸብራቅ (ምሳሌ) ማን ነበር?  ባለፈው ሳምንት የክርስቶስ የመለኮቱ መገለጫ ማረጋገጫ የሆነውን ዕብራውያን 1፡1-3 አጥንተን ነበር። ይህ ክፍል የኢየሱስ ሰብእዊነት በምን ምክንያት እንዳስፈለገ እንድንገነዘብ ረድቶናል። ዕብራውያን 1፡1-3 እርሱ ፍጹም የእግዚአብሔር ነጸብራቅ መሆኑን ይነግረናል። እግዚአብሔር ራሱን ከሰው ልጆች ጋር ሊያስተዋውቅበት የፈለገው ዋናው መንገድ ራሱን ሰው ማድረግ ነበር። እግዚአብሔር ራሱን ሰው በማድረጉ ብቻ ሰዎች በሚገባቸው መንገድ ሊያውቁትና ሊገነዘቡት ቻሉ። ኢየሱስ እግዚአብሔርን ለሰዎች ሊገልጥ የሚችለው ራሱ ሰው በመሆን ስለነበረ የእርሱ ሰብአዊነት በጣም አስፈላጊ ነበር። እኛ እግዚአብሔርን ልናውቀው የምንችልበት ብቸኛ መንገድ የኢየሱስን ሕይወት በማጥናት ነው።  የኢየሱስ ሰብአዊነት ስለምን አስፈላጊ ሆነ? ኢየሱስ ከኃጢአታችንና የኃጢአታችን ቅጣት ከሆነው ከሞት ሊያድነን የሚችለው ሰው በመሆን ብቻ ስለነበረ ነው። ኢየሱስ ኃጢአትን እንድናደርግ በምንፈተንበት ጊዜ ከጎናችን ሆኖ ሊያበረታን የሚችለው ሰው ሲሆን ብቻ ነው። ኢየሱስ እግዚአብሔርን በሚገባ ሊገልጥልን የሚችለው ሰው በመሆን ብቻ ነው፡፡ ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

የኢየሱስ ክርስቶስ ሰብአዊነት  Read More »

የክርስቶስ አምላክነት በቆላስይስ 1፡15-20 

This entry is part 14 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

በሚመጡት ሳምንታት ስለ ኢየሱስ ሥጋ መልበስ (ተሠግዎ) እናጠናለን። በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን የሚናገሩ በርከት ያሉ ሌሎች ጥቅሶችን እንማራለን። ዛሬ ግን የኢየሱስን መለኮትነት የሚያጠናክረውንና ነገር ግን አንዳንድ የኑፋቄ ቡድኖች ለሐሰት ትምህርታቸው አላግባብ የሚጠቀሙበትን ጥቅስ ዘርዘር አድርገን እናጠናለን። ደግሞም እነዚህ አሳሳች ክፍሎች ኢየሱስን እግዚአብሔር ፈጠረው፥ እናም ኢየሱስ አምላክ አይደለም በማለት ለሐሰት ትምህርታቸው የሚጠቀሙበትን ሌላ ጥቅስ በአጭሩ እናጠናለን።  ቆላስይስ 1፡5-20  35ኛ ጥያቄ፡- ቆላስይስ 1፡15-20 አንብቡ። በምታነቡበትም ጊዜ ይህ ክፍለ ምንባብ ስለ ኢየሱስ አምላክነት የሚያስተምርባቸውን የተለያዩ መንገዶች ጻፉ። 36ኛ ጥያቄ፡- ቆላስይስ 1፡15-18 አንብቡ። ሀ) ኢየሱስ እግዚአብሔርን እንዴት አድርጎ ይገልጻል? ለ) ኢየሱስ አምላክ አይደለም ብለው ለማለት የሐሰት መምህራን ጥቅሱን እንዴት ይጠቀሙበታል? ልትለጧቸው ስለምትችሉት መልስ ማሰብ ትችላላችሁ? ሐ) ኢየሱስ ምንን ፈጠረ? እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን ይህ እንዴት ያረጋግጣል? መ) ክርስቶስ ምን ያህል ኖረ? ሠ) ክርስቶስ በአሁኑ ጊዜ ለፍጥረተ ዓለም (ዩኒቨርስ) ምን እያደረገ ነው? ረ) ኢየሱስ የፍጥረት ሁሉ በኩር ነው ሲባል ምን ማለት ይመስላችኋል?  ቆላስይስ 1፡5-20 የኢየሱስን አምላክነት አጥብቆ የሚያረጋግጥ ክፍል ነው። ነገር ግን ይህ ክፍል የእርሱን አምላክነት የሚከዱ አንዳንድ ሃይማኖቶችም የሚጠቀሙበት ነው። ቆላስይስ 1፡15-16 ክርስቶስ የእግዚአብሔር ምሳሌ ነው በማለት ይጀምራል። ምሳሌ ለሚለው የገባው የግሪኩ ቃል ልጁ እግዚአብሔርን በትክክል እንደሚገልጸው ያስገነዝባል። ምሳሌ ሲባል እውነተኛ ያልሆነ ነገር ማለት አይደለም። ይልቅስ «ለአንድ ነገር የተወከለና የዚያንም ነገር መሠረታዊ ባሕርይ የሚገልጽ ምሳሌ ማለት ነው። እንዲያውም ያንኑ ነገር ሊሆንም ይችላል።» ላለዚህ ቆላስይስ 1፡5፥ «እግዚአብሔር አይታይም፤ ግን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ራሱን ገልጾአል፤ ራሱንም ወክሏል፥ ባሕርይውንም አሳይቷል» ይላል። ይህ ሐረግ ልጁ የእግዚአብሔርን መሠረታዊ ባሕርይ እንደሚገልጽ ይናገራል። እና ይህ የሚያመለክተው እርሱ አምላክ መሆኑን ነው።  የሚቀጥለው ሐረግ ደግሞ ይበልጡኑ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ መሆኑን አጉልቶ ያመለክታል። እርሱ በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ እንደ ፈጠረ ይናገራል። ሌሎች ዙፋኖች፥ ጌቶች፥ ገዢዎችና ሥልጣናት በኢየሱስ የተፈጠሩና ለሥልጣኑ የሚገዙ ዝርዝሮች ናቸው። እዚህ ላይ ጳውሎስ የሚናገረው ስለ ሰብአዊ ሥልጣናትም ብቻ ሳይሆን ስለ መንፈሳዊ ሥልጣናት ነው። ወልድ ሁሉንም መላእክትንና በኋላ ወደ ኃጢአት ወድቀው አጋንንት የሆኑትን መናፍስትንም ጭምር ፈጥሮአል። ስለሆነም ኒየሱስ ሁሉንም በመፍጠሩ በላያቸው ላይ ሥልጣን አለው። ሊፈጥር የሚችል እግዚአብሔር ብቻ ነው። በመናፍስት ዓለምም ላይ ሥልጣን ያለው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ስለዚህ ይህ ጥቅስ በግልጽ ኢየሱስ አምላክ እንደሆነ ያስተምረናል።  እንዲሁም ልጁ «የፍጥረታት ሁሉ በኩር ነው፡፡» አንዳንድ የኑፋቄ ክፍሎች “በኩር” የሚለውን ቃል ይመለከቱና እንዲህ ማለት ልጁ መጀመሪያ አለው ማለት ነው ብለው ያስባሉ። እነዚህ መናፍቃን አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ቃል ይለውጣሉ። ኢየሱስ ሁሉን ነገር» ፈጠረ በማለት ፈንታ ጥቅሱን ለውጠው «ሌሎች» የሚል ቃል ይጨምሩበታል። እርሱ «ሌሎችን ነገሮች ሁሉ ፈጠረ» ይላሉ። ነገር ግን «ሌሎች» የሚለው ቃል በመጀመሪያ በተጻፈው ግሪክ ውስጥ የለም። ኢየሱስ የተፈጠሩትን ነገሮች ሁሉ ፈጠረ። ይህ በግልጽ እንደሚያስረዳው እርሱ ራሱ አልተፈጠረም ማለት ነው።  በተጨማሪም፥ «በኩር” የሚለው ቃል ልጁ ጅማሬ አለው ማለትም አይደለም። በኩር” የሚለው ቃል «በጊዜ ረገድ የመጀመሪያው» ማለትም አይደለም። በዚህ ፈንታ እገላለጹ አብዛኛውን ጊዜ «ዋነኛ» ማለት ነው። በአይሁድ ባሕል የበኩር ልጅ ሕጋዊ ወራሽ ነው። የበኩር መብትና ቡራከም የሚያገኘው እርሱ ነው (ዘፍጥረት 25፡24-34፤ 27፡1-4) እንዲሁም 48፡1 20 እንደ ምሳሌ ተመልከቱ።) ስለዚህ የበኩር ልጁ እጅግ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ነው፡ ነገር ግን የበኩር ልጅ መብት ለሌላ ሊተላለፍ ይችላል። በጊዜም ሁኔታ ከታየ ያዕቆብ የይስሐቅ የበኩር ልጅ አይደለም። ነገር ግን እንደ ስኩር ልጅ ታይቷል። በዘፀአት 422 ላይ እግዚአብሔር እስራኤልን የበኩር ልጄ ይለዋል። (እስራኤል የያዕቆብ ሌላው ስሙ ነው።) እንዲህ ማለት እስራኤል ልዩ በረከትና እንክብካቤ የሚያገኝ የእግዚአብሔር ሕዝብ ማለት ነው። በጊዜ ሁኔታ ከሄድን ኤፍሬም የዮሴፍ የበኩር ልጅ አይደለም። ነገር ግን እንደ በኩር ልጅ ተቀጠረ። እንዲያውም እግዚአብሔር የበኩር ልጄ ይለዋል (ኤርምያስ 31፡9)። በመዝሙር 89፡7 ላይ ምንም እንኳን ጻዊት ለቤተሰቡ የበኩር ልጅ ባይሆንም፥ እግዚአብሔር ዳዊትን «የበኩር» ንጉሥ ብሎ ይጠራዋል። ጻዊት ለቤተሰቡ የመጀመሪያ ልጅ አልነበረም። ለእስራኤልም የመጀመሪያው ንጉሥ አልነበረም፡ ቢሆንም በልዩ ሁኔታ እግዚአብሔር የመረጠው ንጉሥ ነበር። በመጨረሻም፥ በዚሁ ክፍለ ምንባብ በቆላስይስ 18 ኢየሱስ ከሞት በመነሣት ፊተኛ» ነው ይላል። ኢየሱስ ከሞት በመነሣት የመጀመሪያው ሰው አልነበረም። ኤልሳዕ የመበለቷን ልጅ ከእርሱ በፊት ከሞት አስነሥቶታል (2ኛ ነገሥት 4፡2-37)። ኢየሱስም የኢያኢሮስን ለት ልጅ (ማርቆስ 5፡41-42) እና አልዓዛርን (ዮሐ 1፡43-44) ከራሱ ትንሣኤ በፊት ከሞት አስነሥቶአቸዋል። ከሞት በመነሣት ፊተኛውና መጀሪያው ሲባል ከሞት በመነሣት እርሱ በጣም በተለየ ሁኔታ ይታያል ለማለት እንጂ፥ እርሱ ከሞት በመነሣት በታሪክ የመጀመሪያው ሰው ነው ማለት አይደለም።  በመሆኑም በኩር ወይም የመጀመሪያው ሲባል «እጅግ በጣም የታወቀና በተለየ ሁኔታ በእግዚአብሔር የተመረጠ» ማለት ነው። ኢየሱስ እግዚአብሔር የፈጠረው የመጀመሪያው ፍጡር ነው የሚልና እርሱ የፍጥረታት አካል ነው የሚል ትርጉም አይሰጥም። ይልቅስ ጥቅሱ የሚያስተምረው ኢየሱስ እጅግ በጣም የታወቀና ፍጥረታትን ሁሉ የሚገዛ መሆኑን ነው።  በቆላስይስ 1፡17 ውስጥ ጳውሎስ ትርጉሙን ፍጹም ግልጽ ያደርገዋል። ክርስቶስ የተፈጠሩትን ሁሉ የፈጠረ በመሆኑ እርሱ ከፍጥረታት በፊት ቀድሞ እንደነበረ ግልጽ ነው። እርሱ ሁልጊዜም ነበረ። ነገር ግን ፈጣሪ ብቻም አልነበረም። በአሁኑ ጊዜ ፍጥረታትን በአንድነት የያዘም እርሱ ነው። ሳይንቲስቶች የደረሱበት እንደ ስበት ኃይል (ግራቪቲ) ያሉትን የተፈጥሮ ሕይወት በግዙፉ ዓለም ውስጥ በሥርዓት ያደረገና የሚቆጣጠር ክርስቶስ ነው። አንድ የግሪክ ፈላስፋ ሲናገር ፍጥረተ ዓለምን (ዩኒቨርስን) በአንድነት ያስተሳሰረው ሰንሰለት «ቃል» ነው ብሏል። ጳውሎስም በዚህ አገላለጽ ይስማማል። ነገር ግን እርሱ ጨመር አድርጎ ያ ሰንሰለት ዮሐንስ «ቃል» ብሎ የጠራው (ዮሐንስ 1፡1) ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ይላል። በእርግጥም ፍጥረተ ዓለምን (ዩኒቨርስን) በሙሉ በአንድነት ሊይዝ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ፍጠረተ ዓለምን (ዩኒቨርስን) በአንድነት መያዝ ስለሚችል ኢየሱስ እርሱ አምላክ መሆን አለበት።  ጥያቄ፡- ቆላስይስ 1፡18 አንብቡ። ሀ) ክርስቶስ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ያለው ንኙነት ምንድን ነው? ለ) ክርስቶስ ከፍጥረት ጋር ያለው ግንኙነት ምንድን ነው?  ክርስቶስ ከሞት በመነሣት ፊተኛና መጀመሪያ መሆኑን ቁጥር 18 ላይ ተመልክተናል። ነገር ግን በዚህ ጥቅስ ውስጥ ስለ ክርስቶስ ጌትነት የሚያመለክቱ ሁለት ጠቋሚ አሳቦችም አሉ። በመጀመሪያ፥ ጳውሎስ እርሱ የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው ይላል። ቀጥሎም፥ እርሱ የመጀመሪያ እንደሆነና ከሁሉ ነገር በፊት እርሱ ነበር ብሎ ይናገራል። ይህ ቁጥር ለየት አድርጎ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው አይልም። ነገር ግን እርሱ እግዚአብሔር በመረጠው ሕዝብ እና በፍጥረታት ሁሉ ላይ ጌታ ነው ይላል። ይህ ጥቅስ ክርስቶስን ከፍጥረታት ሁሉ በላይ አድርጎ ስላሚያቀርበው የእርሱን መለኮትነት ይገልጻል።  ጥያቄ፡- ቆላስይስ 1፡19-20 አንብቡ። ሀ) ጳውሎስ በክርስቶስ ውስጥ ምን አለ ይላል? ለ) እንዲህ ማለትስ ምንድን ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?  በቆላስይስ 1፡19 ላይ ጳውሎስ፥ «የመለኮት ሙላት በልጁ ውስጥ ይኖራል» ይላል። እንዲህ ማለት ክርስቶስ የእግዚአብሔር ኃይልና ባሕርያት ሁሉ አለው ማለት ነው። እግዚአብሔር የሚሆነውን ሁሉ ክርስቶስም ነው። የክርስቶስ ሕልውናዊ ባሕርይ ልክ እንደ እግዚአብሔር ሕልውናዊ ባሕርይ ነው። በመሆኑም ለሐዋርያው ጳውሎስ የእግዚአብሔር ሙላት በእርሱ ውስጥ ይኖራል ከማለት የተሻለ የክርስቶስን አምላክነት አጥብቆ የሚገልጽበት ቃል ሊኖረው አይችልም።  ቆላስይስ 1፡15-20 ያለው ቃል ስለ ክርስቶስ መለኮታዊነት ግልጽና ጠንካራ የሆነ አገላለጽ ነው። ምንም እንኳን አንዳንድ መናፍቃን ልጁ ፍጡር ነው መጀመሪያም አለው ለማለት እንዲያመቻቸው በቁጥር 5 ላይ ወደ ተጻፈው «ሰኩር» ወደሚለው ቃል ቢያመለክቱም፥ ከጥቅሱ ጭብጥ እንደምንረዳው ከሆነ ክርስቶስ ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔር ነው። በዚህ ክፍል «በኩር» ማለት ክርስቶስ ወደር የሌለው ታላቅና ፍጥረታትን ሁሉ የሚገዛ ማለት ነው እንጂ እርሱ የእግዚአብሔር ፍጥረት አካል ነው ማለት አይደለም።  ጥያቄ፡- ሀ) ክርስቶስ ፈጣሪና የፍጥረታት ሁሉ ገዥ ከሆነ እኛ ለእርሱ ምላሽ መስጠት ያለብን እንዴት ነው? በዚህ ሳምንት ውስጥ ለክርስቶስ በመታዘዝ

የክርስቶስ አምላክነት በቆላስይስ 1፡15-20  Read More »

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ተቀብሏል 

This entry is part 13 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ጥያቄ፡- ሀ) ማቴቃለ 26፡59-66 አንብቡ። ኢየሱስ በእርሱ ላይ ለተሰነዘሩ ለእናታቱ ክሶች የሰጠው ምላሽ ዝምታ ነበር። በመጨረሻ በተናገረ ጊዜ ለየትኛው ጥያቀ ነው መልስ የሰጠው? ለ) ኢየሱስ በመለሰው መልስ ካህኑ ለምን ተቆጣ?  ኢየሱስ ተወንጅሎ በአይሁድ ሸንጎ ፊት በቀረበ ጊዜ፥ አይሁዶች ኢየሱስን የሚከሱበትን ወንጀል ይፈልጉ ነበር። ነገር ገን ምንም ዓይነት የክለ ምክንያቶችን ለማግኘት ቢጥሩም፥ ሕግ ለማፍረሱ ምንም ማስረጃ ሊያገኙ አልቻሉም። በመጨረሻም ሊቀ ካህናቱ፥ «አንተ የእግዚአብሔር ልጅ መሢሑ ክርስቶስ ነህን?» አለው። በሚቀጥለው ትምህርት ላይ መለስ ብለን «ክርስቶስ እና የእግዚአብሔር ልጅ» የሚሉትን የማዕረግ ስያሜዎች እናጠናለን። ለአሁኑ ስለ ኢየሱስ መልስና ስለ ካህናቱ ስሜት እናጥና። ኢየሱስ በአጭሩ መልስ ሲለጥ፥ «አንተ አልህ» ነበር ያለው። ይህን ሲመልስ ምን ማለቱ ነበር? ይህ አንተ የምትለው ነው፤ ነገር ግን እውነት አይደለም ማለቱ ነው? እንዲህ ማለቱ አይደለም። ኢየሱስ ያለው፥ «አዎን፥ ልክ አንተ እንዳልኸው ነው» ነበር። በሚቀጥለው ዐረፍተ ነገር ይህን ማለቱ እንደሆነ እንገነዘባለን። ኢየሱስ ወደ ፊት በእግዚአብሔር ቀኝ እንደሚቀመጥ ከዚያም በአምላካዊ ኃይልና ሥልጣን ወደ ምድር እንደሚመለስ ተናግሯል።  ኢየሱስ ራሱ የእግዚአብሔር ሥልጣንና ባሕርይ እንዳለው ገልጾአል፡ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆኑ ከካህኑ ጋር ተስማምቷል። ነገር ግን ስለ መሢሕነቱ ከካህኑ ጋር ከመስማማትም ያልፋል፡ እንደ መሢሕነቱ ኃይል፥ ሥልጣንና ከእግዚአብሔር ከራሱ ጋር የተስተካከለ ባሕርይ እንዳለው አክሎ ገልጾአል።  ኢየሱስ ይህንን ያለው በካህናቱ ምላሽ ምክንያት እንደሆነ እንገነዘባለን ካህናቱም እርሱ ያለውን እንደ ሰሙ፥ ልብሳቸውን ቀድደው ተሳደበ በማለት ከሰሱት። እርሱ አምላክ መሆኑን በማሳወቁ እግዚአብሔርን እንደ ተሳደር አድርገው ቆጠሩ።  ከእነዚህ ክፍለ ምንባቦች በግልጽ እንደሚታየው ኢየሱስ ራሱ አምላክ መሆኑን ገልጾአል። ኢየሱስ ስለ ራሱ የሚናገረውን ተቀብሎ ሳይስማማበት ማንም ሰው እርሱን አከብራለሁ፥ እንደዚሁም እከተለዋለሁ ሊል አይችልም፡ እርሱን እንደ እግዚአብሔር ልናመልከውና ልንታዘዘው ይገባል።  ጥያቄ፡- ኢየሱስን እንደ ነቢይ ወይም እንደ ታላቅ ሰው አድርጎ የሚያከብር ነገር ግን አምላክነቱን የሚክድ ሰው አጋጥሟችሁ፥ ወይም እንዲህ ስላለ ሰዉ የተጻፈ መጽሐፍ አንብባችሁ ታውቃላችሁ?  ጥያቄ፡- ኢየሱስን እንደ እግዚአብሔር መልእክተኛ እናከብራለን ስለሚሉ ግን እርሱ ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ለሚክዱ ሰዎች ምን ትመልሳላችሁ መልሳችሁን በማስታወሻ ደብተራችሁ ውስጥ ጻፉ። ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ተቀብሏል  Read More »

ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ዓይነት ባሕርይ እንዳለው ገለጸ 

This entry is part 12 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ጥያቄ፡- ዮሐንስ 8፡54-59 አንብቡ። ሀ) ኢየሱስ በቁጥር 56 ለመግለጽ { የፈለገው ምንድን ነው? ለ) በቁጥር 58 ላይ ምን መግለጽ ፈለገ? ሐ) ኢየሱስ በቁጥር 59 አይሁዶች በነበራቸው ተቃውሞ ላይ ምላሽ በለጠ ጊዜ የተገነዘቡት ምን ነበር?  ኢየሱስ በዮሐንስ 8፡54-59 ከእግዚአብሔር አብ ጋር የተለየ ግንኙነት እንዳለው አስታውቋል። ምክንያቱም አይሁዶች አብርሃምን በጣም ያከብሩ ስለነበር፥ አብርሃም እራሱ ሕይወቱንና በምድር ላይ ሊያከናውን ያለውን ተባር እንደ ተመኘ በመግለጽ ንግግሩን አጠቃሏል። ቀጥሉም እርሱና አብርሃም እንደሚተዋወቁ ጨምሮ ተናገረ። አይሁዶች ይህን ንግግር በሰሙ ጊዜ፥ እንደ ስድብ ወይም እብደት ቆጠሩት። ገና ወጣት ሆኖ እንዴት አብርሃምን አውቃለሁ ይላል? አሉ። የኢየሱስ መልስ ግን መለኮትነቱን ከሚገልጹት ልጽ ማረጋገጫዎች መካከል አንዱ ነበር። እንዲህም አለ፥ «አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ አለሁ።» ይህ አባባል በሁለት መንገዶች አምላክነቱን ያመለክታል። መጀመሪያ፥ ኢየሱስ ከአብርሃም መወለድ በፊት እንኳ እንደነበረ የሚገልጽ ነው። ይህን ሲል መኖር የጀመረው ከተወሰነበት ጊዜ አንሥቶ እንዳልሆነና እንደ ሰው ከመወለዱ በፊትም ሕያው እንደ ነበር መግለጹ ነበር። ይህ የቅድመ ሕላዌ (pre-existence) ገለጻ ከተራ ሰብአዊ ፍጡር መብለጥን የሚያመለክት ነው። ነገር ግን ኢየሱስ ስለ መለኮትነቱ ይበልጥ ፍንትው አድርጎ ሲያቀርብ ይታያል። «ክአብርሃም በፊት እኔ ነበርሁ አላለም። ይህ ከሰው መብለጡን ሲያመለክትም፥ ኢየሱስ ጅማሬ እንዳለው የሚጠቁም ይሆናል። ይህም ኢየሱስ ያልነበረበት ጊዜ ነበር ወደሚለው አሳብ ሊወስደን ይችላል። ኢየሱስ ይበልጥ ሲናገር፤ «አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ» የሚለው ዘላለማዊነቱን ሲያላይ ቅድመ አብርሃም ቀናትም ቢሆን ጅማሬ እንደሌለው ያመለክታል።  በኢየሱስ አገላለጽ እግዚአብሔር ስለመሆን ከዚህም የጠነከረ ቃል አለ። ስለሆነም በዘaአት 3፡14-5 ባለው ክፍል፥ እግዚአብሔር ስሙን ለሙሴ ሲነገረው «እኔ ነኝ» ብሏል። ኢየሱስም «አብርሃም ከመውለዱ በፊት እኔ አለሁ” ሲል፥ በነደደው ቁጥቋጦ ውስጥ በሙሴ ፊት የተገለጠው እርሱ ራሱ መሆኑን ማስረዳቱ ነው። «እኔ» የሚለው የዕብራይስጥ ቃል፥ «ያህዌ» የሚል ፍች አለው። ኢየሱስም ያህዌ መሆኑን ያረጋግጣል። ታላቁ «እኔ ነኝ» ማለቱ ነው።  ኢየሱስ በንግግሩ ውስጥ የሚሰነዝራቸውን ቃላት ፍች አይሁዳውያን በትክክል መረዳታቸው ልጽ ነው። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ተሳድቧል በሚል ቁጣቸው ገንፍሎ እርሱን ወግረው ለመግደል ድንጋይ አንሥተዋል። ኢየሱስም የሞቱ ጊዜ አለመድረሱን በመገንዘብ እንዳይገድሉት ተሰወረ። ሆኖም አይሁዳውያን ምን ያህል ተቆጥተው እንደነበረ ማየት እንችላለን። ኢየሱስ በተዘዋዋሪ መንገድ እግዚአብሔር መሆኑን መግለጹ ይገባቸው ነበር። ኢየሱስም በተሳሳተ መንገድ ተረድታችሁኛል ብሎ እንዳልተናገራቸው እንመለከታለን። «የምለው አልገባችሁም። እኔ ያህዌ ነኝ ማለቴ አይደለም።» አላላቸውም፡ በተዘዋዋሪ መንገድ እግዚአብሔር መሆኑን ሲናገር እርሱ ያለው በትክክል ገብቶአቸዋል። በዚህ ክፍለ ምንባብ ውስጥ፥ «እኔ እግዚአብሔር ነኝ። ባይልም እግዚአብሔር መሆኑን በትክክል ገልጾአል።  ጥያቄ፡- ዮሐንስ 14፡7-10 አንብቡ። በዚህ ክፍለ ምንባብ ውስጥ ኢየሱስ ከአባቱ ጋር ስላለው ግንኙነት እንዴት ይገልጻል? ጥያቄ፡- ዮሐንስ 10፡29-33 አንብቡ። ሀ) ኢየሱስ ከአባቱ ጋር ስላለው ግንኙነት እንዴት አድርጎ ይገልጻል? ለ) የኢየሱስን ንግግር አይሁዳውያን እንዴት ተረጎሙት?  ኢየሱስ ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር አባቱ መሆኑን በተለየ አኳኋን ገልጾአል። ኢየሱስ እግዚአብሔር አባቱ መሆኑን በገለጸባቸው በአንዳንድ ክፍለ ምንባቦች ላይ ከእግዚአብሔር ጋር በማዕረግ እኩል መሆኑን አበክሮ ይናገራል። በዮሐንስ 14፡7-10 ባለው ክፍል ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ለብቻ ሲነጋገር ሳለ እርሱን ካወቁ እብንም ሊያውቁ እንደሚችሉ ነግሮአቸዋል። ፊልጶስ «አብን እንዲያሳያቸው» በጠየቀው ጊዜ፥ ኢየሱስ፥ «እኔን ያየ አብን አይቷል» ብሏል። እዚህ ላይ ኢየሱስ እርሱ ራሱ እግዚአብሔር አብ መሆኑን አልተናገረም። እርሱ ያለው የእርሱ ባሕርይና ማንነት ልክ እንደ እግዚአብሔር አብ መሆኑን ነው። በዚህም አብ በእርሱ ፍጹም ሆኖ ይገለጣል። ከዚህም በበለጠ ኢየሱስ ያለው አባት ልጁን እንደሚወድ እግዚአብሔርም እርሱን እንደሚወድ ከመግለጽ የላቀ ነው። ኢየሱስ እየተናገረ ያለው ከእግዚአብሔር አብ ጋር አንድ የሆነ ባሕርይ አለኝ ነው። ይህም በተዘዋዋሪ አገላለጽ አምላክ ነኝ ማለቱ ነው።  ኢየሱስ በዮሐንስ 10 ተከታዮቹ በአባቱ ክንድ ውስጥ ስላላቸው ጥበቃ ይገልጻል። ይህንንም ሲያጠቃልልም አብ ለኢየሱስ ተከታዮች ይህን ጥበቃ የሚያድረግላቸው እርሱና አብ አንድ በመሆናቸው ምክንያት መሆኑን ያስገነዝባል። ወዲያውኑ አይሁዶች ኢየሱስን ሊገድሉት ቆረጡ። እርሱን ለመግደል በምን ምክንያት ቆረጡ? ኢየሱስ ከእግዚአብሔር አብ ጋር ስላለው የቅርብ ግንኙነት መግለጡ እርሱ ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን እንደሚያመለክት ስለተገነዘቡ ነበር። በዮሐንስ 14 ውስጥ እንዳለው ሁሉ፥ ኢየሱስ እርሱና አብ ተመሳሳይ ባሕርይ ወይም ማንነት እንዳላቸው ይናገራል። በሚከተሉት ቁጥሮች (ዮሐንስ 10፡34-42) ውስጥ ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን መግለጹን አልካደም፥ ነገር ግን ለአገልግሎት ለመረጣቸው ሰዎች እግዚአብሔር መለኮታዊ ሥልጣን እንደሚሰጣቸው ጠቅሷል። ስለሆነም ያለጥርጥር ለልጁ መለኮታዊ ሥልጣን ይሰጣል። በውይይታቸው ፍጻሜ እንኳን ቁጥር 39 ላይ ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን መግለጺን ሕዝቡ ስለተረዱ ሊይዙትና ሊቀጡት ሞክረው ነበር።  ኢየሱስ ኃጢአትን ይቅር በማለት፥ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር እኩል ሥልጣን በመቀዳጀት፥ እንደዚሁም ከእግዚአብሔር አብ ጋር አንድ ባሕርይና ማንነት እንዳለው በመናገር፥ በተዘዋዋሪ መንገድ አምላክነቱን እንደ ገለጸ ተረድተናል። ነገር ግን ኢየሱስ አምላክ መሆኑን በቀጥታ ወደ መናገሩ የተቃረበበት አንድ ወቅት ነበር። ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ዓይነት ባሕርይ እንዳለው ገለጸ  Read More »

ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሥልጣን አለው 

This entry is part 11 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ጥያቄ፡– ማርቆስ 2፡23-27 አንብቡ። ሀ) በዚህ ክፍለ ምንባብ ውስጥ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ የሃይማኖት መሪዎችን ያስቀየመ ምን ተግባር ፈጸሙ? ለ) ይህ በምን ምክንያት የሃይማኖት መሪዎችን እስከፋ? ሐ) ኢየሱስ በቁጥር 28 ላይ ስለ  ምን ሥልጣን ተናገረ?  በማርቆስ 2፡23-27 ድረስ እንደተነገረው፥ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ በመጓዝ ላይ ሳሉ እንደ አገሩ ባሕል በመንገድ ዳር ካገኙት እሸት ጥቂት ወስደው በሉ። ሆኖም ይህን ያደረጉበት ቀን ሰንበት ነበር። በኢየሱስ ዘመን የነበሩ የሃይማኖት መሪዎች ደግሞ በሰንበት ቀን እሸት ተቀጥፎ መበላት የለበትም ባይ ነበሩ። ስለዚህ ይህ እንዳይደረግ ከልክለዋል። ኢየሱስ ግን ደቀ  መዛሙርቱ ከእሸቱ ወስደው እንዲበሉ ፈቀደላቸው። በዚህ ምክንያት ፈሪሳውያን ሕግ አፍርሷል ብለው በከሰሱት ጊዜ ኢየሱስ ስለ ሰንበት የሚናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የመተርጎም ሥልጣኑን ተጠቀመ። የሰንበት ሕግ የተሰጠው በእግዚአብሔር በራሱ ነው (ዘፀአት 20፡8-10። ኢየሱስ ሕጉን ተረጎመ ማለት እርሱ ከሃይማኖት መሪዎች ባላይ ነው እንደ ማለት ነው። ስለዚህ በሰንበት ቀን ምን መሠራት እንዳለበት ሊናገር፥  መለኮታዊ ሥልጣኑን መግለጹ ነበር። እርሱ የሚናገረው ሥልጣን ምን እንደሆነ በእርግጥ ይነዘቡ ዘንድ በቁጥር 28 ላይ፥ «የሰው ልጅ ለሰንበት ጌታዋ ነው» አለ። ኢየሱስ ራሱን «የሰው ልጅ ብሎ ሲጠራ ምን ማለቱ እንደሆነ በሌላ ክፍለ ትምህርት እናጠናለን። ይህ የኢየሱስ የተለመደ መጠሪያ ነው። በዚህ አገላለጹ ስለ እራሱ እንደሚናገር ገባቸው። እዚህ ላይ ኢየሱስ፤ «የሰው ልጅ ለሰንበት ጌታዋ ነው» በማለት እግዚአብሔር ስለ መሠረታት ሰንበት ሊናገር፥ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል ስለሆነው ሥልጣኑ ማስረዳቱ ነበር።  28ኛ ጥያቄ፡- ሀ) ማቴዎስ 5፡21-22፥ 27-28፥ 31-32፥ 33-34፥ 38-39፥ 43-44 ያሉትን ክፍሎች አንብቡ፡ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ተረጋግመው የተነሡ ሐረጎች የትኞቹ ናቸው? ለ) ኢየሱስ በእነዚህ ሁለት ሐረጎች ደጋግሞ ሲጠቀም ምን ለማለት የፈለገ ይመስላችኋል?  ማቴዎስ 5-7 ያለው ክፍል ኢየሱስ በተራራ ላይ ስላሰማው ስብከት ይዘግባል። ወደዚህ ስብከት መጀመሪያ አካባቢ ኢየሱስ ሁለት ሐረጎች ስድስት ጊዜ ደጋግሞ ይጠቅሳል። የመጀመሪያው ሐረ፥ «እንደተባለ ሰምታችኋል” የሚል ነው። ኢየሱስ እነዚህን ሐረጎች በተጠቀመ ቁጥር ከብሉይ ኪዳን ሕግ ይጠቅስ ነበር። አንዳንድ ጊዜም ባሕላዊውን የሕግ ትርጉም ያክልበት ነበር። ሁለተኛው የሚደጋግመው ሐረግ ደግሞ፥ «እኔ ቀን እላችኋለሁ” የሚለው ነው። ኢየሱስ በዚህ ሐረግ በሚጠቀምበት ጊዜ፥ ለብሉይ ኪዳን ሕግ የጠለቀ ትርጉም ይጨምርበት ነበር። ለምሳሌ ያህል፥ በማቴዎስ 5፡21-22 እንዲህ ይላል፥ «አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ እኔ ገን እላችኋለሁ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል።» ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ስለ መግደል የተነገረው ማንም ሰው ሌላውን እንዳይጠላው የሚል መሆኑን በሥልጣን ያስገነዝባል። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ በተደጋጋሚ፥ ኢየሱስ፥ «እንደ ተባለ ሰምታችኋል እኔ ግን እላችኋለሁ።» ሲል የእርሱ ትምህርት ልክ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሁሉ የሚታመን መሆኑን መግለጹ ነበር። እንደዚሁም ኢየሱስ የእርሱ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቃል ጋር እኩል መሆኑን ያስረዳል። ኢየሱስ በተራራ ስብከቱ ላይ ትምህርቱን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር እኩል በማድረግ፥ በተዘዋዋሪ መንገድ እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን ይገልጻል።  ከፍ ብለን ኢየሱስ ኃጢአትን ይቅር በማለትና ቃሉ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ካለው የእግዚአብሔር ቃል ጋር እኩል እንደሆነ በማሳወቅ በተዘዋዋሪ መንገድ እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን እንደ ገለጻ ተከታትለናል። እንደዚሁም፥ እርሱ ከእግዚአብሔር አብ ጋር አለኝ ባለው ልዩ ግንኙነት በተዘዋዋሪ መንገድ ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ገልጾአል። ጌታ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር አብ ጋር ግንኙነት እንዳለው ሲናገር፥ ከእግዚአብሔር አብ ጋር አንድ ዓይነት የተፈጥሮ ባሕርይ እንዳለው ማስገንዘቡ ነው። ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሥልጣን አለው  Read More »

ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ገልጾአል ፤ ኢየሱስ ይቅርታን መስጠት ይችላል 

This entry is part 10 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ስለ ኢየሱስ መለኮታዊነት ከሚጠቀሱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መተማመኛ ነጥቦች አንዱና ዋንኛው ኢየሱስ ስለ ራሱ ሲያስብና ሲናገር የነበረውን መመልከት ነው። ኢየሱስ የኖረበት የአይሁዳውያን ሳሕል በአንዱ አምላክ ብቻ አጠንክር የሚያምን ነበር። ብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ግርማ ሞገስ ያለው ኃይለኛና ከሰዎችም ሁሉ በላይ መሆኑን አስተምሯል። ይህ እንግዲህ ሰው አምላክ ሊሆን እንደሚችል ለመገመት የሚሳነው ባህል ነበር። የሆነ ሆኖ ኢየሱስ በዚህ ባሕል ውስጥ ያደገ ቢሆንም እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን አስታውቋል። በአንድ አምላክ በሚያምን ባሕል ውስጥ ስለኖረም፥ ኢየሱስ በግልጽ «እኔ አምላክ ነኝ» አላለም። በዚህ ፈንታ እርሱ አምላክ መሆኑን በንግግሩና በሥራው አማካይነት በተዘዋዋሪ መንገድ ይገልጽ ነበር። ስለ አምላክነቱ በአካባቢው ለነበሩ ሰዎች ብዙ ማስረጃዎችን ሰጥቷል። ስለሆነም ኢየሱስ አምላክነቱን በባሕርይውና በተግባሩ ያረጋግጥ ነበር።  አንዳንድ መናፍቃንና የሃይማኖት ክፍሎች የኢየሱስን አምላክነት ሲክዱም፥ በአንጻሩ ታላቅ ሰው መሆኑን፥ ነቢይነቱንና እግዚአብሔር ከፈጠራቸው ፍጥረታት ሁሉ በላይና በኩር መሆኑን ይናገራሉ። በዛሬው ጥናታችን፥ ኢየሱስ ራሱ አምላክ መሆኑን ሲገልጽ እንመለከታለን። እንግዲህ ኢየሱስን ለማክበር የሚፈልግ ሰው፥ እርሱ ስለ ራሱ ያሳወቀውንና የገለጸውን ሐቅ መቀበል አለበት። ስለዚህ ማንም ሰው በአንድ በኩል ኢየሱስን እያከበረ፥ በሌላ በኩል አምላክነቱን ሊክድ አይችልም። ኢየሱስ ይቅርታን ሰጠ  ጥያቄ፡ በማርቆስ ወንጌል 2፡1-22 ያለውን ታሪክ አንብቡ። ሀ) በዚህ ክፍለ ምንባብ ውስጥ ኢየሱስ አምላክነቱን ያረጋገጠባቸው ብዙ መንገዶች የትኞቹ ናቸው? ቢያንስ ሦስት መንገዶችን ፈልጉ፡ ላ) በቁጥር 5 ላይ ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ያውቅ እንደነበር የሚገልጽ ምን ተናገረ? ሐ) በቁጥር 7 ላይ የሕግ መምህራን ጥያቄ | አንሥተዋል። ለዚህ ጥያቄ መልሱ ምን ይመስላችኋል?  ማርቆስ 2፡1-12 ኢየሱስ በብዙ ምክንያቶች እግዚአብሔር መሆኑን የሚያስገነዝብ ማረጋገጥ ነው። በመጀመሪያ፥ ኢየሱስ ሽባውን ሰው ሲፈውስ በታምራዊ ኃይሉ አምላክነቱን አሳይቷል። ሁለተኛ፥ ኢየሱስ የሕግ መምህራኑ ያሰቡት የነበረውን ያውቅ እንደ ነበር በአነጋገሩ አስገንዝቦአቸዋል። ኢየሱስ የሰዎችን አሳብና ሌሎችንም ነገሮች ሁሉ ያውቅ ስለ ነበረ እግዚአብሔር መሆኑን አሳይቷቸዋል። ሦስተኛው፡ ኢየሱስ አምላክነቱን የገለጸው ኃጢአትን ይቅር በማለት ነበር። ኢየሱስ ሽባውን ሰው ከመፈወሱ በፊት ገና እንዳየው «ኃጢአትህ ተሰረየችልህ» አለው። ይህ አነጋገር እዚያ የነበሩትን የሕግ መምህራን አስከፋ። ምክንያቱም ኃጢአትን ይቅር ለማለት የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ ያስቡ ስለነበር ነው። አዎን፥ ትክክል ነበሩ፥ ኃጢአትን ይቅር ለማለት የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ይህንንም ኢየሱስ ደህና አድርጎ ያውቅ ነበር። ስለዚህ፥ ለሽባው ሰው «ኃጢአትህ ተሰረየችልህ» ሲለው፥ በተዘዋዋሪ መንገድ «እኔ የእግዚአብሔር ሥልጣን አለኝ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ» ማለቱ ነበር። ከዚያም ኃጢአትን ይቅር የማለት ሥልጣን እንዳለው ሽባውን ሰው በመፈወስ አረጋገጠ። ስለዚህ ኢየሱስ ኃጢአትን ይቅር የማለት ሥልጣን እንዳለው በመግለጽ፥ እርሱ እግዚአብሔር መሆኑንም አረጋግጧል።  ጥያቄ፡- ሉቃስ 7፡36-50 አንብቡ። ይህ ታሪክ በማርቆስ 2፡1-12 ካለው ጋር በምን መንገድ ይመሳሰላል?  በሉቃስ 7፡36-50 ተመሳሳይ ታሪክ ተፈጽሟል። ኢየሱስ ስምዖን ወደ ተባለ ፈሪሳዊ ቤት እራት ተጋብዞ ነበር። እዚያም በማዕድ ላይ ሳሉ አንዲት ኃጢአተኛ ሴት ወደ ቤቱ ገብታ በኃጢአቷ እየተጸጸተች የኢየሱስን እግር በሽቶ ቀባችው። ኢየሱስም ንስሐ መግባቷንና እምነትዋን ካየ በኋላ «ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል» አላት። ልክ በማርቆስ 2 ላይ እንደተናገሩት ኢየሱስ ኃጢአትን ይቅር በማለቱ የሃይማኖት መሪዎች ተበሳጩ። ልክ በማርቆስ 2 ላይ እንደተገለጸው ኢየሱስ እግዚአብሔር ብቻ ኃጢአትን ይቅር እንደሚል ያውቅ ነበር። ነገር ግን ለሴትዮዋ ኃጢአትሽ ተሰረየልሽ በማለቱ በተዘዋዋሪ መንገድ አምላክ መሆኑን ገለጸ። ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ገልጾአል ፤ ኢየሱስ ይቅርታን መስጠት ይችላል  Read More »

ኢየሱስ ተሰግዶለታል

This entry is part 9 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ጥያቄ፡- ሀ) ራእይ 19፡10 አንብቡ። ሐዋርያው ዮሐንስ ለመልአኩ ሊሰግድ ወ መሬት በተደፋ ጊዜ፥ መልአኩ ምን አደረገ? ሊሰገድለት የሚገባው ብቸኛው ማ ነው አለ? ለ) ዕብራውያን 1፡6 እንብቡ። መላእክት ልጁን ምን እንዲያደርጉ ታዘዙ  ሐ) ፊልጵስዩስ 2፡9-11 አንብቡ። ሰመጨረሻው ላይ ሕዝቦች ሁሉ በኢየሱስ ፊት ምን ያደርጋሉ?  በራእይ 19፡10 ላይ እንደ ተገለጸው ሐዋርያው ዮሐንስ መልአኩን ስላየ በተናገረውም ቃል ስለተሸነፈ፥ ሊሰግድለት እግሮቹ ሥር ወደቀ። ነገር ግን መልአኩ ወዲያውኑ ገሠጸው። ከዚያም ልክ እንደ ሐዋርያው ዮሐንስ እርሱ ከእግዚአብሔር አገልጋዮች መካከል አንዱ መሆኑን አስረዳው። ሊሰገድለት የሚገባው እግዚአብሔር ብቻ ነው።  በዕብራውያን 1፡6 ውስጥ መላእክት ለማን መስገድ እንዳለባቸው ነa የተነገረው? መላእክቱ የተነገራቸው ለልጁ እንዲሰግዱ ነው፤ እርሱም ኢየሱ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ በፊልጵስዩስ 2፡9-11 ሰመጨረሻው ጊዜ የሰa ልጆች ሁሉ በፊቱ በጉልበታቸው ተንበርክከው ይሰግዳሉ ይላል። ቅዱሳ’ መላእክት ለኢየሱስ ሰግደውለታል። የሰው ልጆች ሁሉ ይሰግዱለታል እንግዲህ ኢየሱስ እግዚአብሔር አምላክ ለመሆኑ ይህ ግልጽ ማስረጃ ነው፡፡  ጥያቄ፡– በዚህ ሳምንት ኢየሱስን እንደ እግዚአብሔር የምታመልኩትን አንድ መንገድ በጽሑፍ ግለጹ።  ጥያቄ፡- አንድ አማኝ ካልሆነ ወዳጃችሁ ጋር ተዛማጅነት ያለው የኢየሱስ መለኮታዊ ባሕርይ የትኛው ነው? በዚህ ሳምንት ያንን ባሕርይ ለወዳጃችሁ ለማካፈል ዕቅዱን በጽሑፍ ግለጹ።  ጥያቄ፡- ከዚህ ትምህርት ውስጥ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ባሕርያት እንዳሉትና እግዚአብሔር የሚያደርገውን ሥራ እንደሚሠራ የሚገልጹ ሁለት ጥቅሶችን በቃል እጥኑ።  ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

ኢየሱስ ተሰግዶለታል Read More »

ኢየሱስ ሕይወትን ይሰጣል 

This entry is part 8 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ጥያቄ፡- ዮሐንስ 5፡21፥ 25 እንዲሁም ዮሐንስ ጥቅሶች ውስጥ ኢየሱስ ምን አደረገ?  በዮሐንስ 5፡21 ኢየሱስ ራሱን ከእግዚአብሔር አብ ጋር ያነጻጽራል፡ ለሙታን ሕይወት የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር አብ ለሙታን ሕይወትን እንደሚሰጥ ሁሉ፥ እግዚአብሔር ወልድም ለሙታን ሕይወትን ይሰጣል። ስለሆነም ኢየሱስ ሕይወትን በመስጠት ኃይሉ፥ ራሱን ከእግዚአብሔር አብ ጋር እኩል ያደርጋል። ኢየሱስ በዮሐንስ 5፡25 ላይ አካላዊ ሕይወትን መስጠት (ለአልዓዛር እንዳደረገው) ብቻ ሳይሆን  መንፈሳዊ ሕይወትንም የመስጠት ኃይልና ሥልጣን እንዳለው ይገልጻል እግዚአብሔር ብቻ ነው አካላዊና መንፈሳዊ ሕይወትን ሊሰጥ የሚችል ኢየሱስም አካላዊና መንፈሳዊ ሕይወትን ስለሚሰጥ፥ እርሱ አምላክ ነው።  ኢየሱስ በዮሐንስ 15፡26 ላይ ለደቀ መዛሙርቱ መንፈስ ቅዱስ እንደሚልክላቸው ተስፋ ሰጥቷቸዋል። በዮሐንስ 14፡16፥26 እግዚአብሔር እብ መንፈስ ቅዱስን እንደሚልክ ተናግሯል። ኢየሱስም ደግሞ መንፈ ቅዱስን ይልካል። መንፈስ ቅዱስን የመላክ ብቸኛ ሥልጣን ያለው እግዚአብሔር ራሱ ነው። ከእግዚአብሔር በታች የሆነ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ሊልክ አይችልም። ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን የመላክ ሥልጣ” ስላለው፥ እርሱ ራሱ እግዚአብሔር አምላክ መሆኑ ግልጽ ነው።  ኢየሱስ በሁሉም ስፍራ ይገኛል፤ እርሱ የመፍጠር፥ ሕይወት የመስጠትና መንፈስ ቅዱስን የመላክ ኃይልና ሥልጣን አለው። እርሱ ሁሉ ነገር ያውቃል፤ ደግሞም ፈጽሞ አይለወጥም። በነገው ትምህርት ኢየሱስ ስ  መለኮታዊነቱ በሚገለጽባቸው ሌሎቹ ሥራዎች ላይ ትኩረት እናደርጋለን ኢየሱስ በግልጽ የእግዚአብሔር ባሕርያት ስላለው እግዚአብሔ የሚያደርገውን ሁሉ ያደርጋል። ኢየሱስ ራሱ አምላክ/ እግዚአብሔር ነው።  ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

ኢየሱስ ሕይወትን ይሰጣል  Read More »

የኢየሱስ ባሕርይ አይለዋወጥም 

This entry is part 7 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ጥያቄ፡- ሀ) መዝሙር 102፡25-27 እና ሚልክያስ 3፡6 አንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ እግዚአብሔር ምንን ያስተምሩናል? ለ) ዕብራውያን 13፡8 አንብቡ። ይህ ጥቅስ ስለ ኢየሱስ ምን ያስተምረናል?  መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ከሚያስተምረን ትምህርት ውስጥ አንደኛው አስደናቂ ነገር እግዚአብሔር የማይለወጥ መሆኑ ነው። ሰዎች ልብሶቻቸውን እንደሚቀያይሩ፥ የፍጥረት አካል የሆነ ነገር ሁሉ ይለዋወጣል። ዳሩ ግን እግዚአብሔር አይለወጥም። ባሕርይውም ቢሆን የጸና ነው። ለዓለም ያለው ዕቅድና ዓላማም እንደነበረ ነው። ለሕዝቡ የሰጠው ተስፋም እንዲሁ የጸና ነው።  ዕብራውያን 13፡8 ኢየሱስ እንደማይለወጥ ያረጋግጥልናል። በሚቀጥሉት ምዕራፎች ውስጥ እንደምንመለከተው ስለ ኢየሱስ አንዳንድ ነገሮች ተለውጠዋል። ለምሳሌ ያህል፥ በአንድ ወቅት እርሱ መለኮታዊ ብቻ ነበር ነገር ግን ከድንግል ማርያም ሲወለድ፥ ሰውም አምላክም ሆነ። ታዲያ ዕብራውያን 13፡8 ኢየሱስ ክርስቶስ አይለወጥም ሲል ምን ማለቱ ነው? የዚህ ጥቅስ ዓውደ ንባብ የእግዚአብሔር ፍርሃት ያለበት ክርስቲያናዊ ባሕሪ ስለሚያሳዩ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች የሚናገር ነው። ስለዚህ ጥቅሱ በመሠረቱ ስለማይለወጠው የኢየሱስ ባሕርይ ያስተምረናል። የእግዚአብሔር ባሕርይ እንደማይለወጥ ሁሉ፥ የኢየሱስ ባሕርይም እንደዚሁ አይለወጥም። ይህም ኢየሱስ አምላክ ለመሆኑ ሌላው ማስረጃ ነው። | 19ኛ ጥያቄ፡- የማይለወጠው የኢየሱስ ባሕርይ እንዴት ነው የሚያጽናናችሁ?  የኢየሱስ የማይለወጥ ባሕርይ ስንል፥ እርሱ ለእኛ ያለው አመለካከት ይለወጣል ብለን መፍራት የለብንም። ሰዎች ብዙ ጊዜ በሌሎች ያላቸውን ስሜት ይለውጣሉ። ኢየሱስ ለእኛ ያለው ፍቅር በፍጹም አይለወጥም። ኢየሱስ ተስፋውን በፍጹም አይለወጥብንም። ሰዎች ተስፋ ይሰጣሉ፤ ነገር ግን እነዚያን ተስፋዎች አይጠብቁትም። ኢየሱስ ግን የሰጠንን ተስፋ ሁሉ ይጠብቃል። ስለዚህ እርሱ ዛሬ ፍጹም፥ ጻድቅና አፍቃሪ መድኅን እንደሆነ ሁሉ፥ ነገም እንደዚሁ ስለሚሆን በእርሱ ልንታመን እንችላለን። ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

የኢየሱስ ባሕርይ አይለዋወጥም  Read More »

ኢየሱስ በሁሉም ቦታ ይገኛል 

This entry is part 6 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ጥያቄ፡- ሀ) መዝሙር 139፡7-10 አንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች መሠረት እግዚአብሔር የት ነው? ለ) ማቴዎስ 18፡20፤ 28፡20፤ ዮሐንስ 14፡23 አንብቡ። እንደ እነዚህ ጥቅሶች እገላለጽ ኢየሱስ የት ነው?  እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ብቻ ሳይሆን በየትኛውም ስፍራ በማንኛውም ጊዜ በሙሉ ማንነቱ ይገኛል። መዝሙር 139 እኛ ሰብአዊ ፍጡራን የትም ብንሄድ፥ እግዚአብሔር ከእኛ ቀድሞ እዚያ እንደሚገኝ ይነግረናል። ወደ ሰማይ ብንወጣ፥ ወደ ጥልቁ ምድር ብንወርድ እግዚአብሔር እዚያም መኖሩን ያስታውሰናል። ወደ ምሥራቅ ወይም ወደ ምዕራብ፥ ወደ ሰሜን ወይም ወደ ደቡብ ብንሄድም እግዚአብሔር እዚያ አለ። ስለዚህ እግዚአብሔር በሁሉም ስፍራ ይገኛል።  ኢየሱስም ቢሆን በተመሳሳይ ሁኔታ በየትም ስፍራ ይገኛል። ማቴዎስ 18፡20 ሁለት ወይም ሦስት አማኞች በሚሰበሰቡበት ስፍራ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር እንደሚሆን ያስረዳል። በዓለም ውስጥ በየትም ስፍራ በሚሰበሰቡ አማኛች መካከል በአንድ ጊዜ ይገኛል። ኢየሱስ በየትኛውም ስፍራ የሚገኝ ከሆነ በአማኞቹም መካከል ይገኛል። በማቴዎስ 28፡20 ላይ አማኞች ወንጌሉን እስከ ዓለም ዳርቻ በሚወስዱበት ጊዜ እንኳን አብሮአቸው እንደሚሆን ተስፋ ሰጥቶአቸዋል። በዚህ ምድር ላይ ወዴትም ይሂዱ፥ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ይሆናል። በዮሐንስ 14፡23 ላይ እግዚአብሔር አብ በየትኛውም ስፍራ ይሁን ከሚወዳቸው ሁሉ ጋር እንደሚሆን ኢየሱስም እንዲሁ ከሚወዳቸው ሁሉ ጋር እንደሚሆን ተስፋ ሰጥቶአል። እግዚአብሔር በየትኛውም ስፍራ እንደሚገኝ ሁሉ፥ ኢየሱስም በየትኛውም ስፍራ ይገኛል።  መደምደሚያው፡- ኢየሱስ አምላክ ነው!  ጥያቄ፡- የኢየሱስ በአንድ ጊዜ በሁሉም ስፍራ መገኘቱ እንዴት ያጽናናችኋል፣ ቢያንስ ሁለት መንገዶችን ጻፉ።  ኢየሱስ በሁሉም ስፍራ ስለሚገኝ በብዙ መንገድ ልንጽናና እንችላለን፡፡ በሩቅ ስፍራ ከሚገኙ ወዳጆቻችንና ዘመዶቻችን ዘንድ ተገኝተን ልንረዳቸው በማንችልበት ሁኔታ ኢየሱስ እነርሱ ዘንድ ተገኝቶ በሚያስፈልጋቸው ያገለግላቸዋል፡፡ እንደዚሁም ወደ አንድ አዲስ ስፍራ በምንሄድበት ጊዜ ቦታውን ሊያዘጋጅልን እርሱ ከእኛ ቀድሞ እዚያ መገኘቱን ማወቅ ያጽናናናል። በእምነታችን ምክንያት ከምንወዳቸው ወዳጆቻችን ብንለይም፤ በምንሄድበት ሁሉ አብሮን እንደሚሆን መረዳታችን ኃይልንና ብርታትን ይሰጠናል።  ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

ኢየሱስ በሁሉም ቦታ ይገኛል  Read More »