አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ሞናርካዊነት ወይም ስባልዮሳዊነት 

This entry is part 25 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

በጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ኢቢዮናዊነት ከተወገዘ በኋላ የእግዚአብሔርን እንድነት የሚያስጠብቅ የመሰለ የሐሰት ትምህርት ተነሣ። እነዚህ ቡድኖች «ሞናርካዊነት» በተባለ አስተምህሮ ያምኑ ነበር። እነርሱም እግዚአብሔር አንድ በመሆኑ ላይ አጥብቀው አጽንኦት ይሰጡ ነበር። ነገር ግን እነዚህ ቡድኖች የሚያታግል ጥያቄ ነበራቸው፡ ጥያቄያቸው እግዚአብሔር አንድ ከሆነ ኢየሱስ በምን አኳኋን እግዚኣብሔር ሊሆን ይችላል? የሚል ነበር። ከእነዚህ አንዱ የሞናርካዊነት ቡድን ደግሞ ከኢቢዮናውያን ጋር የሚመሳሰል ትምህርት ያስተምሩ ነበር። እነርሱም ኢየሱስ ሰው ነበር፥ ነገር ግን ጻድቅ የሆነ ሰው ነበር። ስለሆነም እግዚአብሔር ይህን ጻድቅ ሰው (ኢየሱስን) በጥምቀቱ ጊዜ ወስዶ በተለየ መንገድ ተገለገለበት ይላሉ። ቤተ ክርስቲያን ኢቢዮናውያንን በተቃወመችበት መንገድ መልስዋን በመስጠት ትምህርታቸው ሐሰተኛ መሆኑን አጋልጣለች። ነገር ግን ሁለተኛ ዓይነት ሞናርካዊነትም ነበር። ይህ ቡድንም በእግዚአብሔር አንድነት ላይ አጽንኦት ነበረው። እነዚህም አንድ እግዚአብሔር ብቻ አለ፥ ይህም እግዚአብሔር በተለያዩ አካላት አማካይነት ራሱን ገልጧል ይላሉ። እነርሱም አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ራሱን እንደ አብ፥ በሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ወልድ፥ በሌላ ጊዜ ደግሞ ራሱን እንደ መንፈስ ቅዱስ ገለጠ ብለው ያስተምራሉ። ስለዚህ እነዚህ ቡድኖች ኢየሱስ እግዚአብሔር በመሆኑ ላይ ቢስማሙበትም፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር አብ ጋር አንድ አካል ነው ይሉ ነበር። የዚህ ሐሰት ትምህርት ዋናው መምህር ሳባልዮስ የተባለ ሰው ነበር። ከዚህ የተነሣ አንዳንድ ጊዜ ትምህርቱ ሳባልዮሳዊነት ተብሎ ይጠራል።  ጥያቄ፡- ሀ) ሞናርካውያን ዋና ትኩረት ይሰጡዋቸው የነበረው ምንን ነበር? ለ) ሰባልዮስ ስለ አብ፥ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ያስተማረው ምን ነበር? 46ኛ ጥያቄ፡- ማቴዎስ 3፡13-17 28፡19-20፥ እንዲሁም 2ኛ ቆሮንቶስ 3፡14 አንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የሳባሊዮስ ትምህርቶች ሐሰት መሆናቸውን የሚያጋልጥ ምን አላቦች ታያላችሁ?  ሞናርካውያን ሁሉ በእግዚአብሔር ኣንድነት ላይ አጽንኦታቸውን ያደርጋሉ። ማለትም እግዚአብሔር አንድ ብቻ ነው ይላሉ። ብዙዎቹ የሳባሊዮስን አስተምህሮ በመከተል፥ እግዚአብሔር አንድ ሲሆን፥ ራሱን ግን በተለያዩ አካላት ወይም አምሳል ገልጧል በማለት ያምናሉ። ይህን ሲሉ አንዱ እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ እንደ ኣብ፥ በሌላ ጊዜ እንደ ወልድ፥ እንዲሁም በሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ መንፈስ ቅዱስ ራሱን ገልጧል ማለታቸው ነው። ሳባሊዮስ ያስተማረው ራሱን በተለያዩ ሦስት መንገዶች የገለጠ አንድ እግዚአብሔር ብቻ አለ ብሎ ነበር። በአዲስ ኪዳን ውስጥ የሚገኙ አያሌ ጥቅሶች የሳባሊዮላ አስተምህሮ ሐሰት መሆኑን ያረጋግጣሉ። ኢየሱስ – በጥምቀቱ ጊዜ ውኃው ውስጥ ቆሞ ሳለ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ ሲያርፍበት፥ ከሰማይ ደግሞ የእግዚአብሔር ድምፅ ሲመጣ ተሰምቶአል። ከዚህ ጥቅስ እንደምንረዳው እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ በአብ፥ ሌላ ጊዜ በወልድ እንዲሁም ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ በተለያየ ሁኔታ የሚገለጥ እንዳይደለ ግልጽ ነው። ሁሉም የሥላሴ አካላት በአንድ ጊዜ በተለያዩ ሁኔታዎች ይገለጣሉ። በሁለቱም በማቴዎስ 28፡19-20 እና በ2ኛ ቆሮንቶስ 13፡14፤ አብ፥ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ሁሉም አንድ አምላክ የሆኑ ራሳቸውን የቻሉ አካላት መሆናቸው ተገልጾአል። ስለዚህ የሳሳሊዮስ አስተምህሮ መጽሓፍ ቅዱሳዊ ባለመሆኑ በጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ዘንድ ተወግዟል።  ጥያቄ፡- ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ የሳባሊዮስን አስተምህሮ የተከተለ ምን የሐሰት ትምህርት ታውቃላችሁ?  ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ የሳባሊዮስን የሐሰት ትምህርት የሚከተሉ ቡድኖች «የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን» አማኒያን የሚባሉ አሉ። «የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን» ሳባሊዮስ እግዚአብሔር አንድ ብቻ ነው፤ እርሱም አንዳንድ ጊዜ እንደ አብ፥ በሌላ ጊዜ እንደ ወልድ፥ እንዲሁም ደግሞ እንደ መንፈስ ቅዱስ ራሱን ይገልጣል ብሎ ያለውን የስሕተት ትምህርት በቀጥታ ይከተላሉ። ከእነዚህ ቡድኖች መካከል አንዳንዶቹ ስሜታዊ የሆኑ ዝማሬዎችን ስለሚያሰሙና እምነታቸውንም በዚሁ ስሜት ስለሚያስፋፉ በጣም ተቀባይነት አግኝተዋል። ስለዚህ ብዙ ሰዎች እነዚህ ቡድኖች ትክክለኛች ናቸው፤ ምክንያቱም የሚታይባቸው ደስታና የመንፈስ ግለት ይህን ይመሰክራል ይላሉ። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንደሚያስተምረን እግዚአብሔር አብ፥ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሦስት አካላት እንጂ የአንድ አምላክ ልዩ ልዩ መገለጫዎች አይደሉም። የሳባሊዮስ አስተምህሮት ሐሰት መሆኑ ቢታወቅም ቤተ ክርስቲያን የሥላሴን አስተምህሮ በተመለከተ በማያሻማ ሁኔታ ጥርት ያለ ግንዛቤና አቋም እንዲኖራት በማድረግ በኩል ረድቷታል። በዚህ መሠረት የሥላሴ ኣስተምህሮ እግዚአብሔር አንድም ሦስትም ነው የሚል ጽኑ አቋም ያዘ። ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ሞናርካዊነት ወይም ስባልዮሳዊነት  Read More »

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ኖስቲካዊነት

This entry is part 24 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ኢቢዮናውያን ተነሥተው ኢየሱስ ሰው ብቻ ነበር ብለው ባስተማሩበት በዚያው ጊዜ ከኢቢዮናውያን ለየት ያለ ትምህርት ይዘው የተነሡት ደግሞ ኖስቲካውያን ነበሩ። እነዚህ ኖስቲካውያን በትምህርታቸው ውስጥ በተፈጥሮ የተገኘውና ማንኛውም አካላዊ ነገር ሁሉ ክፉ ነው ብለው። ያምኑ ነበር። ማንኛውም ተፈጥሮአዊ ነገር ወይም ቁስ አካል ክፉ በመሆኑ ምክንያት ኢየሱስ ሰው መሆኑ እውነት ሊሆን አይችልም ብለው ያስተምሩ ነበር። መንፈስ ብቻ መልካም ነው ብለው ያምኑ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ እውነተኛ የሰው አካል ያለው እውነተኛ ሰው ሳይሆን እውነተኛ የሰው አካል ያለው መስሎ የተገለጠ ነው ይሉ ነበር። በእርግጥ ኢየሱስን ድንግል ማርያም አላረገዘችውም፥ ነገር ግን በውስጧ ብቻ አለፈ ብለው ያምኑ ነበር። እንደዚሁም ኖስቲካውያን ወደ ደኅንነት ሊደረስ የሚቻለው በእውቀት ነው ብለው የሚያምኑ ነበሩ። ሰው የበለጠ መንፈሳዊ ምሥጢራትን ባወቀ መጠን ክፉ ከሆነው ከቁስ አካላዊ ዓለም ይርቅና መልካም ወደሆነው መንፈሳዊ ዓለም ይቀርባል ባይ ናቸው። የጥንት ቤተ ክርስቲያን መሪዎች በእነዚህ በኖስቲካውያን ትምህርት ውስጥ ብዙ ጉድለቶችን ሊመለከቱ ችለዋል። – በመጀመሪያ፥ ኢየሱስ በድንግል ማርያም ተፀንሶ የተወለደ፥ እውነተኛ ሰው መሆኑን ይክዳሉ። ሁለተኛ፥ ቁስ አካላዊው ዓለም በራሱና ከራሱ ክፉ ነው ይላሉ። በመጨረሻም፥ ደኅንነት በመሠረቱ የሚገኘው ጥልቅ በሆነ መንፈሳዊ እውቀት ነው ይሉ ነበር። ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ኖስቲካውያንን በዚህ ሐሳዊ ትምህርታቸው የተነሣ አውግዛቸዋለች፤ ነገር ግን ትምህርታቸው ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን የበለጠ መርምራ ወደ ትክክለኛው ግንዛቤ እንድትደርስ በማድረግ ረገድ ረድቷታል። በመጀመሪያ፥ ኢየሱስ በሰው ተመስሎ ብቻ አልታየም፤ ኃጢአት አላደረገም እንጂ በማንኛውም ሁኔታ እርግጠኛ ሰው ነበር። ሁለተኛ፥ ቁስ አካላዊው ዓለም በራሱ ክፉ ኣይደለም። እግዚአብሔር መልካም አድርጎ ፈጥሮታል። ቁስ አካላዊውም ሆነ መንፈሳዊው ዓለም ከኃጢኣት የተነሣ ክፉዎች ናቸው። ሰዎች ኃጢአትን ወደ ቁስ አካላዊው ዓለም ሲያመጡ ብቻ ክፉ ይሆናል። በመጨረሻም፥ ደኅንነት መንፈሳዊ ምሥጢርን ከመገንዘብ በላይ ነው። ስለሆነም ደኅንነት ማለት በክርስቶስ አምኖ በልብ መለወጥ ነው። ደኅንነት ክርስቶስ በመስቀል ላይ በፈጸመልን ተግባር ላይና ፈቃዳችንን ለእግዚአብሔር አሳልፈን በመስጠታችን ላይ የተመሠረተ ነው።  ጥያቄ፡- ሀ) ኖስቲካውያን ስለ ኢየሱስ ማንነት የሚያምኑት ምን ነበር? ለ) ኖስቲካውያን ስለዚህ ስለተፈጠረው ቁሳዊ ዓለም ምን ያምኑ ነበር? ሐ) ኖስቲካውያን ሰው በምን መንገድ ደኅንነትን ያገኛል ይላሉ? መ) ኖስቲካውያን ከአቢዮናውያን እንዴት ይለያሉ? ሠ) ከእነርሱ የሐሰት ትምህርት የተነሣ ስለ ኢየሱስ ምን ግንዛቤ እየጠራ ግልጽ እየሆነ ሄደ?  ጥያቄ፡- ሀ) ከኃጢአት በስተቀር፥ ኢየሱስ ሙሉ በሙሉ ሰው ነው የሚለውን እውነታ በመቀበል ረገድ ችግር ያለባቸው የምታውቃቸው ሰዎች ኣሉ? ለ) ስለ እነርሱ የምታውቁትን ጻፉ። ሐህ ክርስቶስ በእውነት ሰው መሆኑን የሚያስተምሩ የትኞቹን ክፍለ ምንባቦች አቅርባችሁ አብራችኋቸው ትወያያላችሁ?  ጥያቄ፡- ሀ) በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ውስጥ ከሁሉ የበለጠው ነገር መንፈሳዊ ምሥጢራትን መገንዘብ ነው ብለው የሚያምኑ፥ የምታውቁዋቸው ሰዎች አሉ? ለ) ስለ እነዚህ ሰዎች የምታውቁትን ጻፉ። ሐ) በዓለም ያለው ቁስ አካል ሁሉ ክፉ ነው ብለው የሚያምኑ የምታውቋቸው ሰዎች አሉ? ስለ እነዚህ ስዎች ያላችሁን ተሞክሮ ጻፉ።  ኖስቲካውያን ይህ ቁሳዊ ዓለም ክፉ በመሆኑ ኢየሱስ እውነተኛ ሰው ሊሆን አይችልም ብለው አመኑ። እንደዚሁም ወደ ደኅንነት የሚያደርሰው መንገድ በመንፈሳዊ ምሥጢራት ግንዛቤ ነው አሉ። ዛሬም በኅብረተሰቦቻችን ውስጥ የዚህ ዓይነት ተመሳሳይ እምነት ያላቸው ሰዎች ኣሉ። እንዳንድ ክርስቲያኖች መሆናቸውን እየተናገሩ ኢየሱስ እውነተኛ ስብእና እንዳለው አያምኑም። እነዚህ ወገኖች ኢየሱስ ሥጋ የለበሰ ኣምላክ ነወ ቢሉም፥ እንደ እኛ ሰው እንደ ነበረና ሰብአዊ ነፍስና ሰብአዊ መንፈስ እንደ ነበረው ይክዳሉ። ነገር ግን በዮሐንስ ምዕራፍ 1፥ በፊልጵስዩስ ምዕራፍ 2፥ እንደዚሁም በዕብራውያን ምዕራፍ 2 እና በሌሎችም ክፍለ ምንባቦች ላይ እንደተነዘብነው ኢየሱስ ከኃጢአት በስተቀር እንደ እኛው ሰው መሆኑን ተምረናል። እኛን ለማዳን ሲል ሰው መሆን እንዳስፈለገውም ተመልክተናል። ራሳቸውን ክርስቲያኖች ብለው የሚበሩ በኅብረተሰቦቻችን መካከል የሚገኙ አንዳንድ ሰዎች ጥልቅ የመንፈሳዊ ምሥጢራት ግንዛቤ ካላቸውና መንፈሳዊ ቃላትንም ካወቁ መንፈሳዊ ኃይልና ደኅንነትን የሚያገኙ ይመስላቸዋል። ነገር ግን በሚቀጥለው ትምህርታችን ላይ ደኅንነት በዕውቀት ወይም በልዩ ግንዛቤ የሚገኝ አለመሆኑን እንማራለን። ደኅንነት ፈቃድንና ልብን በመለወጥ ይመጣል። ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ኖስቲካዊነት Read More »

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ኢቢዮናውያን 

This entry is part 23 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ዛሬ ስለ ኢየሱስ ተሠገዎ ማጥናታችንን እንቀጥላለን፥ ነገር ግን ሆኖም ጥናታችን ከሌላ አቅጣጫ ይሆናል። የዛሬው ጥናታችንም የሚጀምረው የተሠዎ አስተምህሮ በጥንታዊትዋ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዴት እንደ ተስፋፋ ነው። በሚመጣው ሳምንትም የተሠገዎ አስተምህር በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዴት እንደ ተስፋፋ የምናጠና ሲሆን፥ ይህ ኣስተምህሮ በኢትዮጵያም ውስጥ እንዴት እንደ ተስፋፋ እንማራለን።  የእምነት አስተምህሮን ታሪክ መማራችን ለምን ይጠቅመናል? ከክርስቶስ ጊዜ ጀምሮ ለሁለት ሺህ ዓመታት ብዙ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ወንዶችና ለቶች መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት በታማኝነት ሊነዘቡትና ሊታዘዙትም ሞክረዋል። በእነዚህ ጥንታውያን ክርስቲያኖች ትምህርት ሁለት ከመሥመር የወጡ ወይም ጽንፍ ዘለል አመለካከቶች እንዳንይዝ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል። በአንድ በኩል ትምህርታቸው ዋጋ የለውም ብለን ጨርሰን ልናጣጥለው አይገባም። ተሞክሮአቸውንና የአሳቦቻቸውን መደምደሚያ በማጥናት፥ መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት መገንዘብ እንዳለብን ከትምህርቶቻቸው ላይ ብዙ ልንማር እንችላለን። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ አስቸጋሪ ሁኔታ በተፈጠረ ጊዜ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በመፍትሔነት በአዘጋጁት የእምነት አቋም ልዩ ትኩረት መስጠት አለብን። ነገር ግን በሌላ በኩል የእነርሱን የትምህርት ድምዳሜ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እኩል አድርገን ማስቀመጥ የለብንም። የእነዚህ የጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ኣባቶች የእምነት አንቀጾችና ትምህርቶቻቸው በጊዜው ለአጋጠሟቸው ጉዳዮችና ችግሮች በመፍትሔነት የተጠቀሙባቸው ናቸው። እነዚህ ንጥረ ድምዳሜዎች ጠቃሚዎች ናቸው፥ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ከተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ጋር በእኩልነት ደረጃ ሊታዩ አይገባም። ስለሆነም ድምጻሜዎቻቸውን በማጥናት ልንማርባቸው እንችላለን። ይሁን እንጂ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ በመመለስ ላለንበት ባሕል፥ ለቋንቋችንና ለትውልዳችን ምን ዓይነት ትምህርት እንደሚሰጡ ማብራራት አለብን። ዛሬ ክርስቲያኖች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተመሥርተው የእምነት አንቀጾቻቸውንና የአስተምህሮ መሠረታቸውን ሊጽፉ ያስፈልጋል። እነዚህ የእምነት አንቀጾች ከጥንቶቹ ጋር የማይቃረኑ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን ያንኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት በአዲስና ወቅታዊ ኣገላለጽ ሊያሰፍሩ ይችላሉ።  ለሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት የእምነት አስተምህሮን ታሪክ የምናጠና ስለሆነ የተለመደውን መንገድ በመከተል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችን በመመለስ በመልሶቻቸው ላይ አንወያይም። በዚህ ፈንታ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለሆነው ነገር በማጥናት በአጠናነው ትምህርት ላይ ለተመሠረቱት ጥያቄዎች መልስ እንሰጣለን። የጥንቷን ቤተ ክርስቲያን ታሪክን በተመለከተ በምንጭነት ብዙ መጻሕፍትን እጠቀማለሁ። ነገር ግን በተለይ «The Word Became Flesh» (ቃል ሥጋ ሆነ) ከሚለው የሚላርድ ኤሪክስን መጽሐፍ ውስጥ ለዚህ ትምህርት የሚጠቅመውን ልወስድ እወዳለሁ።  ጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን በዓመታት መካከል ስለ ኢየሱስ ማንነት ትክክለኛ ጥርት ያለ ግንዛቤን አዳብራ ቆይታለች። ታዲያ ይህ ግንዛቤ በአመዛኙ ሊዳብር የበቃው በክርስቶስ ማንነት ላይ የተነሡትን የሐሰት ትምህርቶች ለመቋቋም በተወሰደ ምላሽ ነው። የሆኑ ቡድኖች ብድግ ብለው ስለ ክርስቶስ የተሰማቸውን ማስተማር ይጀምሩ ነበር። የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ደግሞ እነዚህን ትምህርቶች አጥንተው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ያስተያዩ ነበር። ከዚያም መጽሐፍ ቅዱስ በትክክል የሚያስተምረውን በመግለጽ መልስ ይሰጡ ነበር። ከዚህ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል አዲስ ትምህርት ስሕተቱና ትክክለኝነቱ ምኑ ላይ እንደሆነ ለይተው በደንብ ያብራሩ  ነበር።  ኢቢዮናውያን  የጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን መልስ መስጠት የነበረባት በጊዜው ከተነሡት ቡድኖች መካከል አንደኛ ለሆነው ለኢቢዮናውያን ቡድን ነበር። ኢቢዮናውያን ከብዙዎቹ የቀድሞ የአይሁድ ክርስቲያኖች ሲወርድ ሲዋረድ የመጡ ናቸው። እነዚህ ሰዎች አይሁዳውያን ሲሆኑ፥ ኢየሱስንም እንደ አይሁድ መሢሕ አድርገው ይቀበሉት ነበር። እነርሱም አንድ አምላክ እንደነበርና እርሱም አይሁዶች እንደ መመሪያ አድርገው ለምን ጊዜውም የሚታዘዙበትን ሕግ እንደ ሰጣቸው አጥብቀው ያምኑ ነበር። ስለዚህ ኢስዮናውያን ሰዎች ሊድኑ ከፈለጉ ለሕጉ ተገዢ መሆን እንዳለባቸው ያምኑ ነበር። አቢዮናውያን ኢየሱስን የአይሁዶች መሢሕ አድርገው ይቀበሉት እንጂ እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን አያምኑም ነበር። አንድ አምላክ ብቻ አለ፥ ታዲያ በምን አኳኋን ሰው የሆነው ኢየሱስ እግዚአብሔር ሊሆን ይችላል የሚል ክርክር ነበራቸው። በምትኩ ኢየሱስ በተጠመቀ ጊዜ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ ወርዶ በተለየ ሁኔታ እንደ ማደጎ ልጁ አድርጎ ተቀበለው ብለው ያምናሉ። እግዚአብሔር በእርሱ ውስጥ አድሮ የመሢህን ተልዕኮ ለማሟላት ሠራ ይላሉ። ያ የተባለው ሥራ ምንድን ነበር? ኢቢዮናውያን እንደሚሉት፥ የኢየሱስ ዋነኛ ሥራ፥ ሰዎች ሕገ እግዚአብሔርን እንዲታዘዙ ማስተማር ነው ብለው ያምኑ ነበር። እኛ ከእግዚአብሔር ጋር ስምምነት ያለው ሕይወት እንድንመራ ልንከተለው የሚገባ ምሳሌያችን ሆኖ ኖረ ይላሉ። የጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን መሪዎች በዚህ በኢቢዮናውያን አስተምህሮ ላይ ሁለት ችግሮች ታይተዋቸው ነበር። በመጀመሪያ፥ ኢየሱስ ራሱ አምላክ መሆኑን መካዳቸው ሲሆን፤ ሁለተኛ፥ ሰዎች ለመዳን የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ይገባቸዋል የሚሉት ናቸው። የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ኢሲዮናውያንን በአስተማሩት በዚህ ትምህርት አውግዛቸዋለች። ነገር ግን ይህ የተሳሳተ ትምህርታቸው ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስቶስ ማንነት ያልተበረዘና ጥርት ያለ ትyህርታዊ ግንዛቤን እንድታዳብር ረድቷታል። አባቶች መጽሐፍ ቅዱስን በመመርመር፥ ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት እንኳን አምላክ እንደነበረ አረጋገጡ፥ እንደዚሁም እርሱ ለእኛ ምሳሌ ሲሆን፥ ዋና ተግባሩ ግን ስለ ኃጢአታችን መሞት መሆኑን በጥልቅ ተመለከቱ።  ጥያቄ፡- ሀ) ኢቢዮናውያን ኢየሱስ ማን መሆኑን አመኑ? ላ) ኢቢዮናውያን እግዚአብሔር በኢየሱስ ውስጥ አደረ ብለው የሚያምኑት መቼ ነው? ሐ) ኢቢዮናውያን የኢየሱስ ዋነኛ ሥራ ምን ነበር ብለው ኣመኑ? መ) ኢቢዮናውያን ያስተማሩትን ትምህርት ብንከተል ኖሮ ዛሬ እምነታችን ምንኛ ይለወጥ ነበር? 40ኛ ጥያቄ፡- ኢየሱስ እግዚአብሔር የተጠቀመበት መልካም ሰው ነበር እንጂ አምላክ አልነበረም ብለው የሚያምኑ የምታውቋቸው ሰዎች ይኖሩ ይሆን? ከእነርሱ ያገኛችሁትን የምታውቁትን ጻፉ። ለ) ቀደም ሲል ከኣጠናችኋቸውና ስለ ክርስቶስ ማንነት ከሚናገሩ ጥቅሶች የትኞቹን አብራችኋቸው ትካፈላላችሁ? 41ኛ ጥያቄ፡- የኢየሱስ ዋና ተግባር ለእግዚአብሔር ታማኝ የመሆን ምሳሌነት ነው ብለው የሚያምኑ የምታውቋቸው ሰዎች አሉ? ስለ እነዚህ ሰዎች ያላችሁን ተሞክሮ ጻፉት።  ከዚህ ቀደም እንደተመለከትነው ሁሉ፥ ዮሐንስ ምዕራፍ 1 እና ፊልጵስዩስ ምዕራፍ 2 ክርስቶስ ወደዚህ ምድር ሰው ሆኖ ከመምጣቱ በፊትም እንኳ ፍጹም አምላክ እንደነበረ በግልጽ ያስረዳሉ። አንዳንድ የሐሰት ትምህርቶች እንዲሁም ክርስቲያኖች ነን ብለው ራሳቸውን የሚጠሩ ሰዎች ሳይቀሩ ኢየሱስ እግዚአብሔር በውስጡ ያደረበትና የተገለገለበት ቅን ሰው ነበር ብለው ዛሬም ያስተምራሉ። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ጥርት ባለ ሁኔታ ኢየሱስ ሰው ሆኖ ከመወለዱ በፊትም ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ይመሰክራል። ሌላው አንዳንድ ክርስቲያኖች ደግሞ ኢየሱስ ለእኛ ምሳሌ ሊሆን የኖረውን ሕይወት ትኩረት በማድረግ የመጀመሪያውን ስፍራ ይሰጡታል። ምንም እንኳን ኢየሱስ ምሳሌያችን ቢሆንም፥ ቆየት ብለን በሚቀጥለው ትምህርታችን ውስጥ እንደምናየው እርሱ ለእኛ የኃጢአትን ይቅርታ ለመስጠት ሲል የሞተው ሞት ከሁሉም የላቀ ተግባር ነው። ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ኢቢዮናውያን  Read More »

ስለ ተሠገዎ በዕብራውያን ምዕራፍ 2 

This entry is part 22 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ዛሬ በዕብራውያን 2፡5-18 ያለውን ስለ ተሠገዎ የሚያስተምረውን ሦስተኛውን ቁልፍ ክፍለ ምንባብ እንመለከታለን። ይህ ክፍል ኢየሱስ እግዚአብሔር ሆኖ እያለ በምን ምክንያት ፍጹም ሰው ለመሆን እንዳስፈለገው እንድንገነዘብ ይረዳናል።  1. እኛ ፍጥረታትን እንድንገዛ፥ ኢየሱስ ሰው ሆነ  ጥያቄ፡- ዕብራውያን 2፡5-8 እንብቡ። ሀ) እግዚአብሔር የሚመጣውን ዓለም ለማን ነው የማይሰጠው? ለ) የሚመጣውን ዓለም ለማን ይሰጣል? ሐ) እኛስ ገና | ያላየነው ምንድን ነው?  ጥያቄ፡- ዕብራውያን 2፡9 ኣንብቡ። ምንን እናያለን?  ጥያቄ፡- ይህን ክፍል ከአነበባችሁ በኋላ ኢየሱስ ሰው እንዲሆን ያስፈለገበትን ምክንያት ለማሰላሰል ጊዜ እንዲኖራችሁ አድርጉ። ከዚያም ስታሰላስሉ የቆያችሁትን አሳብ በማስታወሻ ደብተር ጻፉ።  ዕብራውያን 2፡5-18 ለሰው ልጆች በተሰጠ አስደናቂ የተስፋ ቃል ይጀምራል። ጸሐፊው በዕብራውያን 2፡1-4 ውስጥ አንባቢዎቹ ለወደፊቱ ስላሚጠብቃቸው የደኅንነት ፍስሐ በማብሰር ይናገራል። ይህ ደኅንነት የሚመጣውን አስደናቂ ዓለም ይጨምራል ይላል። ነገር ግን ይህ መጪው ዓለም ለመላእክት አይደለም። ታዲያ የእግዚአብሔር ዓላማ መጪውን ዓለም ለማን ለመስጠት ነው? ደራሲው ለዚህ መልስ ለመስጠት መዝሙር 8፡4-6 ይጠቅሳል። ምንም እንኳን የሰው ልጆች ከመላእክት ጥቂት ቢያንሱም፥ በመጪው ዓለም ግን የክብርና የምስጋና ዘውድን ይቀዳጃሉ። ሰዎች በመጪው ዓለም የእግዚአብሔርን ፍጥረተ ዓለም ሁሉ (ዩኒቨርስን) ይገዛሉ። እኛ አማኞች ከሚኖሩን ታላቅ የደኅንነት በረከቶች አንድ ቀን እግዚአብሔር በፈጠረው ሁሉ ላይ ገዥዎች የመሆናችን እውነታ ነው።  ነገር ግን ይህን አስደናቂ በረከት ገና አልተቀበልንም። አሁን ባለንበት ሕይወት ሰብአዊ ፍጡር በፍጥረታት ላይ ያለውን የአገዛዝ ሥልጣን ገና አላየነውም። እነዚህን በረከቶች አንድ ቀን እንደምንቀበል እንዴት ልናውቅ እንችላለን? ይህን የወደፊት በረከት የሚያረጋግጡልን አንዳንድ ነገሮችን እናያለን። በአንድ ወቅት ሰው በመሆን ዝቅ ብሎ የውርደትንና የትሕትናን ሕይወት የኖረው ኢየሱስ ከፍ ከፍ ሲል አይተናል። ኢየሱስ ልክ እንደ እኛው ሰው ሆነ። ለእኛ ሊሞት ብሎ ሥጋን ለበሰ። ይህ ከእኛ እንደ አንዱ ሆኖ የኖረው ኢየሱስ አሁን በሰማይ ከፍ ከፍ ብሎ ይገኛል። መላ ፍጥረተ ዓለምን (ዩኒቨርስን) የመግዛት ክብር፥ ሞገስና ገናናነት ያለው ኢየሱስ ብቻ ነው። ነገር ግን ኢየሱስም ሰው ስለነበረና በዚህ ባሕርይ ስለምንዛመደው እኛም የዚህ አገዛዝ ተካፋዮች የመሆን ባለ መብት ነን።  አንድ ሰው የአገሩ ፕሬዚዳንት ሆኖ በሚመረጥበት ጊዜ፥ እርሱ ብቻውን የሥልጣንና የማንኛውም ክብር ባለቤት ሆኖ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ አይኖርም። ባለቤቱና ልጆቹ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ አብረውት በመሆን ክብር የተመላበትን ሕይወት ይጋራሉ። በዚሁ መሠረት እኛም ከኢየሱስ ጋር ባለን ተዛምዶ ከእርሱ ጋር ሆነን በኣዲሱ ዓለም ክብርና ደስታ የተሞላበትን ሕይወት እንኖራለን። ጌታ ኢየሱስ ሰው ሆኖ ተሠቃይቶ ከሞተልን በኋላ በሰማይ ከፍ ብሎ ስላለ፥ የደኅንነት በረከቶቻችንን እንደምናገኝ እርግጠኞች ነን። ምክንያቱም እግዚአብሔር ሰውም-ኣምላክም የሆነውን ኢየሱስን ከሁሉም በላይ ከፍ ከፍ ስላደረገው፥ ተስፋውን ጠብቆ ልጆቹ ፍጥረታትን እንዲገዙ ከፍ ከፍ እንደሚያደርጋቸው እናውቃለን።  ከኢየሱስ ጋር እንዴት ልንዛመድ ቻልን? ምክንያቱም እርሱ ፍጹም ሰው ሆኖ እስከ ሞት ድረስ ሥቃይን ስለተቀበለ ዝምድና ልንመሠርት ችለናል። ኢየሱስ የሰው ልጆች እውነተኛ አለኝታ ሆኖ ክብር የተሞላበትን ደኅንነት ለሰዎች ለመስጠት የእርሱ ሰብአዊነትና ሰብአዊ ሥቃይ አስፈላጊዎች ነበሩ። ደግሞም የኢየሱስ ሰብአዊነት ለመጪው ደኅንነታችን እውነተኛ ዋስትናችን ነው። የወደፊቱን የክብር ወራሽነት እንድናገኝ ኢየሱስ ፍጹም ሰው መሆን ነበረበት። 2. ኢየሱስ ከእኛ ጋር አንድ ቤተሰብ ሆኖ ደኅንነትን ለመስጠት ሰው ሆኖአል።  ጥያቄ፡- ዕብራውያን 2፡10 አንብቡ። እግዚአብሔር (ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ለማምጣት ብሉ) በደኅንነት ራስ (ኢየሱስ) ላይ ምን አደረገ?  ጥያቄ፡- ዕብራውያን 2፡11-13 አንብቡ። ሀ) ሌሎችን ሊቀድስ የሚችል እርሱ ማን ነው? ለ) የተቀደሱት እነማን ናቸው? ሐ) የሚቀድሰውና የሚቀደሱት ሁሉ ከአንድ ናቸውና ይላል። «ከአንድ ናቸውና» ሲል ምን ማለቱ ነው?  ጥያቄ፡- በቁጥር 11-13 ላይ ኢየሱስ የሰው ልጆችን ምን ብሎ ይጠራቸዋል? ቢያንስ ሁለት መልሶችን ፈልግ።  እነዚህ ጥቅሶች ስለ ኢየሱስ ሰብአዊነት ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ይሰጡናል። በመጀመሪያ ደረጃ ኢየሱስን የደኅንነታችን «ራስ» ሲሉ ይገልጹታል። «ራስ» ተብሎ ከግሪክኛው የተተረጎመው ቃል፥ ከሁሉ ቀድሞ ወደ አዲስ አገር ደርሶ ሌሎች እንዲከተሉት መንገድ የሚከፍት ማለት ነው። ከኃጢአት በስተቀር ኢየሱስ በሁሉም ረገድ እንደ እኛው ሆኖ ብዙ ልጆች በክብር ደኅንነቱ ደስ እንዲላቸው መንገዱን ከፈተላቸው። ነገር ግን ይህን ለማድረግ የሞትን ሥቃይ ተቀብሎ ፍጹም መሆን ነበረበት። ስለዚህ ኢየሱስ ተሠቃይቶ ባይሞት ኖሮ ፍጹም ሰው ሊሆን ባልቻለ ነበር። እንደዚሁም ሥቃይን ተቀብሎ ባይሞት ኖሮ ፍጹም መድኅን ባልሆነም ነበር። ኢየሱስ በሥቃዩና በሞቱ ጊዜ እንኳን ፍጹም ሰው ነበር። ምክንያቱም እርሱ በሥቃዩና በሞቱ ፍጹም ሰው ስለነበረ፥ የእግዚአብሔርን ልጆች ክብር ወጻለው ደኅንነት ለማምጣት የሚችል መድኅን ነበር።  ለመሆኑ ኢየሱስ ሙሉ በሙሉ ሰው ነው? ጸሐፊው ኢየሱስ ሰብኣዊ ከሆነ ቤተሰብ የተገኘ ፍጹም ሰው መሆኑን ለማስረዳት ከብሉይ ኪዳን ጥቅሶችን ያቀርባል። የሚቀድሰው ኢየሱስ ራሱ ነው። የሚቀደሱት ደግሞ ሁሉም አማኞች ናቸው። «ከአንድ ናቸውና» ወይም «ከአንድ አባት ናቸውና» ይህን ሊል ከአንድ ቤተሰብ ናቸው ማለቱ ነው። ኢየሱስና የሰው ልጆች አንድ ቤተሰብ ናቸው። ይህን ለማረጋገጥ መሢሑ የተቀሩትን የሰው ልጆች «ወንድሞቼ» ሲል የተናገረውን መዝሙር 22፡22 በመጀመሪያ ይጠቅሳል። ሰዎች የኢየሱስ ወንድሞችና እኅቶች ከሆኑ፥ እርሱ ራሱ ሰው ነው ማለት ነው። በምድር መሢሑ፥ ሌሎች እግዚአብሔርን ሲቃወሙ እግዚአብሔርን ከሚያምኑ የእግዚአብሔር ሰዎች ጋር ራሱን ያመሳሰለበትን በሁለተኛነት ኢሳይያስ 8፡17 ይጠቅሳል። ልክ ሌሎች ሰዎች በእግዚአብሔር እንደሚተማመኑ ሁሉ፥ እርሱም በእግዚአብሔር ይተማመን ነበር። በምድር በነበረበት ጊዜ ፍላጎቱን እግዚአብሔር እንዲያሟላለት በፍጹም ሰብአዊነቱ በእግዚአብሔር ይተማመን ነበር። በመጨረሻውም ላይ፥ መሢሑ ሕዝቡን «ልጆቼ» ብሎ የተናገረበትን ኢሳይያስ 8፡18 ይጠቅሳል። ምክንያቱም መሢሑ ሰዎች የሆኑ ተከታዮቹን ወንድሞቼና ልጆቼ ብሎ ስለሚጠራቸው እርሱ ሰው መሆኑን በዚህም እንረዳለን። በእርግጥም ኢየሱስ ብዙ ልጆችን ክብርን ወደ ተጎናጸፈ ደኅንነት ለማምጣት ፍጹም ሰው ሆኖአል።  3. ኢየሱስ በሞቱ ሰይጣንን ለማሸነፍ ሰው ሆኖአል።  ጥያቄ፡- ዕብራውያን 2፡14-15 አንብቡ። ሀ) ቀደም ሲል በሞት ላይ ሥልጣን የነበረው ማን ነው? ለ) ይህ ምን ማለት ነው? ሐ) ኢየሱስ ስለዚህ ምን አደረገ? መ) ኢየሱስ በሞት ፍርሃት ባርነት ውስጥ ላሉት ምን አደረገ? ሀ) ኢየሱስ ሥጋና ደምን ለምን ተዋሃደ?  ጥያቄ፡- ዕብራውያን 2፡18 ኢየሱስ የሚረዳው ማንን ነው?  ኢየሱስ ሙሉ በሙሉ ሰው የሆነበትን ምክንያት ደራሲው በሰፊው መግለጹን አሁንም ይቀጥልበታል። ኢየሱስ፥ ሰይጣን በሰዎች ላይ ያለውን የሞት ሥልጣን ለመሻርና እርሱን ለማሸነፍ ኢየሱስ ፍጹም ሰው መሆን ነበረበት። ደራሲው ሰይጣን የሞት ሥልጣን በሰዎች ላይ አለው ሲል፥ ምን ማለቱ ነው? ይህን ሲል፥ ሰይጣን ሰዎችን የመግደል ሥልጣን አለው፥ ወይም ኢየሱስ በተሰቀለ ጊዜ ለሰይጣን የሞት ካሳ ከፈለው ማለት አይደለም። ሰይጣን ሰሞት ላይ ያለው ሥልጣን፥ ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ መፈተን ነው። ሰዎች ኃጢኣትን በሚያደርጉበት ጊዜ፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለሚጥሱ በሥጋም በመንፈስም እንዲሞቱ ይፈረድባቸዋል። ስለዚህ ፍጥረተ ዓለማትን (ዩኒቨርስን) ለመግዛት የተመረጥን የሰው ልጆች ከኃጢአታችን የተነሣ የሞትና የሰይጣን ባሪያዎች እንሆናለን።  ጥያቄ፡- ሞትን በመፍራታቸው ስለምታውቋቸው ሰዎች እስቲ አስቡ። ስማስታወሻ ደበተራችሁ ውስጥ ከሁለት እስከ ሦስት ሰዎች ጻፉ። እነዚህ ሰዎች በምን ምክንያት ሞትን ይፈራሉ?  ሰዎች በሞት ፍርሃት ምክንያት በባርነት ውስጥ መኖራቸውን በቀላሉ ልንገነዘብ እንችላለን። እስቲ በቅርቡ ስለተገኛችሁበት በክርስቶስ የማያምኑ ሰዎች ልቅሶ አስቡ። የሞቱ ወላጆቻቸውና ወዳጆቻቸው ከሞት በኋላ ምን እንደሚሆኑ እርግጠኞች ባለመሆናቸው ተስፋ በቆረጠ ስሜት ያለቅሳሉ። ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች መሆናቸውን በልባቸው ያውቃሉ። እንደዚሁም በኃጢአታቸው ምክንያት ቅጣት እንደሚገባቸውም ያውቃሉ። ስለዚህ ሰዎች ራሳቸውም ሆኑ ወዳጆቻቸው በሚሞቱበት ጊዜ ቅጣታቸውን የሚቀበሉ መሆናቸውን ስለሚረዱ ሞትን በጣም ይፈሩታል። ሰይጣን ኃጢአትን እንድንሠራ ስለሚያደርገንና ኃጢአታችንም ለቅጣት አሳልፎ ስለሚሰጠን፥ ሰዎች የሞት ፍርሃት ባሪያዎች እንሆ ለልን።  ነገር ግን ኢየሱስ በሞተ ጊዜ ሰይጣን በሞት ላይ የነበረውን ኃይል ደምስሶ ሰዎችን ከሞት ፍርሃት ውስጥ ነፃ አውጥቶአቸዋል። ጥያቄ፡- ቆላስይስ 2፡13-5 አንብቡ። ሀ) ኢየሱስ በሞተ ጊዜ ይኮንኑን ስለነበሩት ሕጎች ወይም የዕዳ ጽሑፎች ምን ኣደረገ? ለ) ይህ አለቅነትንና ሥልጣናትን ምን አደረጋቸው?  ቆላስይስ 2፡13-15 ኢየሱስ በሞተ ጊዜ

ስለ ተሠገዎ በዕብራውያን ምዕራፍ 2  Read More »

ስለ ተሠገዎ በፊልጵስዩስ ምዕራፍ 2 

This entry is part 21 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ትናንትና ስለ ኢየሱስ ተሠገዎ የሚያስተምር በጣም ጠቃሚ ከሆኑ ጥቅሶች መካከል አንዱ የሆነውን ዮሐንስ ምዕራፍ አንድን አብረን አጥንተናል። ዛሬ ደግሞ ሌላ በጣም ጠቃሚ የሆነና ስለ ተሠገዎ ምሥጢር የሚያስረዳውን ከፊልጵስዩስ 2፡5-ህ ያለውን ክፍል እንማራለን። ጥያቄ፡- ፊልጵስዩስ 25 አንብቡ። ክርስቲያኖች ሊኖራቸው ይገባል?  ፊልጵስዩስ 2፡6-11 የቀድሞ ክርስቲያኖች ስለ ኢየሱስ የዘመሩትን መዝሙር ይመስላል? ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ አመራርና ግፊት ዘላለማዊው የእግዚአብሔር ልጅ ሰው በሆነ ጊዜ ምን እንደ ተደረገ ሊያመለክተን ይህን መዝሙር ጽፎታል። ነገር ግን ሐዋርያው ይህን የጻፈበት ዋነኛው ምክንያት ክርስቲያኖች ልክ ኢየሱስ የነበረውን ዓይነት የትሕትናና ራስን ዝቅ የማድረግ ልብ እንዲኖራቸው ለማበረታታት ነው። ይህ መዝሙር ኢየሱስ አምላክ ሆኖ ሳለ እንዴት በፈቃዱ ሰው ሆኖ ለእኛ ሲል ሊሞት ወደዚህ ዓለም መምጣቱን ይገልጽልናል። ኢየሱስ ለትሕትና እጅግ በጣም ጥሩ ምሳሌያችን ነው። ላለዚህ ክርስቲያኖች የክርስቶስን ትሕትና የሕይወታቸው ምሳሌ አድርገው ሊወስዱት ይገባል።  1. ኢየሱስ ወደ ዓለም ከመምጣቱ በፊት ምን ይመስል ነበር?  ጥያቄ፡- ፊልጵስዩስ 2፡6 አንብቡ። ሀ) ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት ምን ይመስል ነበር? ለ) ኢየሱስ ወደዚህ ምድር ሰው ሆኖ ከመምጣቱ በፊት፥ ስለ መለኮታዊ ተፈጥሮ የነበረው አመለካከት ምን ነበር?  ስለ ኢየሱስ ትሕትና ለመገንዘብ በመጀመሪያ ወደዚህ ምድር ከመምጣቱ በፊት የነበረውን የክብር ስፍራ ልናስተውል ይገባል። ጳውሎስ ኢየሱስ ከመወለዱ በፊትም እንደነበረ የምናውቅ እድርጎ ይገምታል። ታዲያ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት ምን ይመስል ነበር። (የቀድሞው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም «በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ» ይላል። በእንግሊዝኛው «ቅርጽ» የሚለውን ቃል በግሪኩ ትርጉም ሲታይ ውጪአዊውን መልክ ብቻ የሚመለከት አይደለም። በአንጻሩ ቃሉ ውጪአዊውን መልክና ውስጣዊውንም ተፈጥሮ ሁለቱንም ይመለከታል። ቃሉ በጥቅም ላይ ሲውል፥ የውጫውን መልክና ከበስተኋላው ያለውንም ባሕርይ ይገልጻል። እንዲህ ማለት ታዲያ ኢየሱስ ውጫዊ የእግዚአብሔር መልክና ውስጣዊ የእግዚአብሔር ባሕርይም አለው ማለት ነው፤ እርሱ እግዚአብሔር ነው እናም የእግዚአብሔር ክብር፥ ሞገስና ኃይል አለው። አዲሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም፥ «የመለኮት ባሕርይ አለው» ሲል ይህንኑ ያመለክታል። ለምሳሌ፥ ከልጆቼ ጋር በመንገድ ላይ ሳለሁ ብታገኙኝና ልጆቼን ስንከባከብ ብታዩ፥ «እስጢፋኖስ፥ ዛሬ በእርግጥ እባት ትመስላለህ?» ትሉኝ ይሆናል። እኔ አባት መምሰሌን መግለጻችሁ ብቻ ሳይሆን አባት አለመሆኔንም ነው። በዚህ ፈንታ እስጢፋኖስ፥ «አባት ነህ፥ በእውነት አባት ትመስላለህ?» ልትሉ ትችላላችሁ። ጳውሎስ ኢየሱስ ከተሠገዎ በፊትም እውነተኛ አምላክ እንደሆነ ስለ እርሱ የሆነው ሁሉ የእርሱን አምላክነት እንደሚገልጽ ይናገራል። እርሱ የእግዚአብሔር ኃይል ነበረው። ይህ ኃይል በተናገረው ቃል ፍጥረተ ዓለምን (ዩኒቨርስን) የመሠረተ ነበር። የእግዚአብሔር ጥበብ ነበረው። በኃላፊ ጊዜያት ስለተከናወኑት፥ ኣሁንና ወደፊትም ስለሚከናወኑት ሁሉ ፍጹም እውቀት አለው። እርሱ የእግዚአብሔር ክብርና ሞገስ ነበረው። ይህም በእልፍ አእላፋት መላእክት ውዳሴ የተከበበ አንጸባራቂ የሰማይ ፀዳል፥ ፍጹም ብርሃንና ክብር ነበር። እርሱ የእግዚአብሔር ፍጹም ባሕርያት የሆኑ፥ ቅድስና፥ መልካምነትና ንጽሕና ነበረው። ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን በሰማይ የነበረው ክብሩ ገልጾታል።  ጥያቄ፡- ሀ) ኢየሱስ እግዚአብሔር ለመሆኑ የሚያመለክቱ ሌሎች ባሕርያቱ የትኞቹ ናቸው? ለህ እናንተ ከእርሱ ጋር ላላችሁ ግንኙነት እነዚህ እያንዳንዳቸው ለምን ጠቃሚዎች ሆኑ?  ኢየሱስ እግዚአብሔር የመሆን ክብሩን በመብትነት መያዝን አልፈለገም። በዚህ ፈንታ በገዛ ፈቃዱ የእግዚአብሔርነትን ክብርና ግርማ አሳልፎ ለመስጠት ወደደ። በግሪኩ ቋንቋ፥ «ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቆጠረውም» የሚለው አገላለጽ፥ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን እንደ ራሱ መልካም ዕድል አድርጎ ሊጠቀምበት አልፈለገም የሚል ነው። ምንም እንኳን ክርስቶስ እግዚአብሔር ቢሆንም፥ የመለኮቱን ኃይልና ክብር ለጥቅሙ ሊያውል አልፈለገም። እግዚአብሔር የመሆኑን ክብር ለራሱ ጥቅም ሊያውለው አልፈቀደም። በዚህ ፈንታ ኢየሱስ መለኮትነቱን እንዴት ተጠቀመበት?  2. ኢየሱስ ወደ ዓለም በመጣ ጊዜ ምን ይመስል ነበር?  ጥያቄ፡- ፊልጵስዩስ 2፡7-8 ኣንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ኢየሱስ ስለ አከናወናቸው አምስት ነገሮች ምን ይላሉ?  ኢየሱስ መለኮትነቱን ለግል ጥቅሙ በማዋል ፈንታ፥ አራት ነገሮችን አድርጓል።  1) በቀድሞው የአማርኛ ትርጉም «ራሱን ባዶ አደረገ» የሚለው ሐረግ፥ የጥቅሱ የመጀመሪያው ሐረግ ባይሆንም በግሪኩ የጥቅሱ የመጀመሪያው ሐረግ ነው። በአዲሱ የአማርኛ ትርጉም ላይም የመጀመሪያው ሐረግ ሆኖ ተጽፎአል። «ራሱን ባዶ አደረገ» የሚለው የአማርኛው የቀድሞ ትርጉም፥ የግሪኩን ሐረግ ቃል በቃል ተርጉሞታል። እንዲህ ማለት ምን ማለት ነው? እንዲህ ማለት ኢየሱስ ወደ ምድር ሲመጣ የመለኮትነቱን ባሕርይ ትቶ ገዶውን መጣ ማለት ነው? ደግሞስ ወደ ምድር ሲመጣ አምላክነቱ አበቃ ማለት ነው? አይደለም። ይህ ሐረግ ኢየሱስ የፈጸመውን ተግባር ጠቅለል ኣድርጎ ያቀረበበት የጳውሎስ ልማዳዊ አገላለጽ ነው። የሚቀጥሉት ሦስት ሐረጎች ምን ማለቱ እንደሆነ ዘርዘር አድርገው ይገልጻሉ። ሐረጉ ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን ትቷል አይልም። ሐረጉ የሚለው ኢየሱስ ግዚአብሔር መሆኑ እንዳለ ሆኖ፥ ሌላ ነገር ሆነ ነው። በነበረው መለኮታዊ ሕርይ ላይ ሌላ ባሕርይ ጨመረ።  2) ጌታ ኢየሱስ የባሪያን መልክ ወሰደ። በድሮው የአማርኛው የመጽሐፍ ዱስ ትርጉም «መልክ» የሚለው ቃል በቁጥር ስድስት ከሚገኘው ጋር ንድ ነው። የባሪያን መልክ ወሰደ ማለት ኢየሱስ ሁለቱንም፥ የባሪያን ውነተኛ ውስጣዊ ባሕሪና ውጪኣዊ መልክ ያዘ ማለት ነው። እርሱም ባሪያ ነ፥ በእውነትም የባሪያን መልክ ወሰደ። ከተሠገዎ በፊት ኢየሱስ እግዚአብሔር ነበር። በእግዚአብሔርነትም ተገልጦአል። ከተሠገዎ በኋላ ባሪያ ሆነ፥ እንደ ባሪያም ተገለጠ። የጥንት ዓለም ሰዎች ስለ ባርነት ደህና አድርገው ያውቁ ነበሩ። ባሪያዎችን በየቀኑ ይመለከቱ ነበር። ባሪያዎች ጨርሶ መብት ያልነበራቸው ሰዎች ነበሩ። ታዲያ ኢየሱስ እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ በገዛ ፈቃዱ ክብሩንና ታላቅነቱን በመተው በሰዎች ዘንድ ባሪያ መስሎ ተገኘ።  (3) ኢየሱስ የሰውን መልክና ምሳሌ ወሰደ። የግሪኩ ቃል «መምሰል» የሚለው በትክክል እንደ አንድ ነገር መሆን ሊሆን ይችላል። እርሱ እንደሚለው ክርስቶስ ሙሉ በሙሉ ከሰው ዘር ጋር ተመሳስሏል። ኢየሱስ ወደ ምድር መጥቶ ራሱን ባዶ በማድረግ የተቀሩት የሰው ልጆች እንደሚኖሩት ኖረ። «መልክ» የሚለውን የግሪኩ ቃል «በስሜት ሕዋሳት የሚታወቅ አቀራረብ፥ ቅርጽ ወይም አበጃጀት» ይለዋል። እንዲህ ማለት ኢየሱስ እውነተኛ ሰው አይደለም ማለትም አይደለም። በአንጻሩ ይህ አገላለጽ ሁሉም ሰው እርሱ ሰው መሆኑን ያውቅ ነበር ማለት ነው። እርሱ እንደ ሰው ተገለጠ፤ በአካባቢው የነበሩ ሰዎችም ግንዛቤ እርሱ ሰው እንደሆነ ነበር። ይህ በአጽንኦት የሚያመለክተው ምንም እንኳን ኢየሱስ የአምላክነቱን ባሕርይ እንደ ያዘ ቢሆንም፥ የተገለጠው በሰው መልክ መሆኑን ነው። ኢየሱስ እንደ ማንኛውም ሰው ከሰዎች ጋር በመኖር ራሱን ባዶ አድርጓል። አብሮአቸው የኖረው ሰዎች የተመለከቱት እንደ እግዚአብሔር አድርገው ሳይሆን ልክ እንደ እነርሱ ሰው አድርገው ነበር። እነዚህ ቃላት በአንድነት የሚገልጹት ኢየሱስ በሰዎች መካከል ሰው ሆኖ በመኖር ራሱን ባዶ እንዳደረገ ነው። እርሱ እውነተኛ ሰው ሆኖ ኖሯል።  ጥያቄ፡– ሀ) ዘዳግም 21፡23 ኣንብቡ። በአይሁዶች እስተሳሰብ በተለይ የተረገመ ማን ነበር? ለ) ገላትያ 3፡13 አንብቡ። ኢየሱስ ለእኛ ምን ሆነ?  4) ኢየሱስ ጭካኔና ሥቃይ ስሞላበት ሁኔታ ተሰቅሎ ሞተ። ኢየሱስ በመጨረሻው ላይ ራሱን ባዶ ያደረገውና የነበረውን ክብር አሳልፎ የሰጠው ለሞት ራሱን ባስገዛ ጊዜ ነበር። ኢየሱስ ሰው ለመሆን መፍቀዱ ብቻ ሳይሆን፥ ራሱን ለሞት አሳልፎ በመስጠት ራሱን ትሑት አድርጎአል። የኢየሱስ ሕይወት ሙሉ በሙሉ የአባቱን ፈቃድ በመታዘዝ ላይ የተመሠረተ ነበር (ዮሐንስ 5፡30፤ 6፡38)። ነገር ግን በተለይ ራሱን ለስቅላት አሳልፎ በሰጠ ጊዜ ለአባቱ ፈቃድ ታዛዥነቱን አሳይቷል። ለቅላት በጥንቱ ዓለም ከባድ ጭካኔ ያለበት የውርደት ሞት ነበር። ሥቃይና መከራ ያለበት የአሟሟት ዘዴ ስለነበረ ቅጣቱ በሮም መንግሥት ላይ ላመፁ ክፉ ወንጀለኛች የተመደበ ነበር። በተለይም ስቅላት ለአንድ አይሁድ በጣም የከፋ ዮርጊት ነበር። በኦሪት ዘዳግም 21፡23 ላይ፥ «በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነው» ይላል። እንዲህ ማለት በዚህ ሁኔታ የሚሞቱ ሰዎች ከእግዚአብሔር የበረከት ኪዳን ውጭ ስለሚሆኑ፥ የመዳን ተስፋ የላቸውም ማለት ነው። በእውነቱ ኢየሱስ ለእኛ ይገባ የነበረውን የኃጢአት መርገም ተሸከመ (ገላትያ 3፡13)። ራሱንም አሳልፎ እስከ መስቀል ሞት በመስጠት የነበረውን መብትና ክብር በፈቃዱ ተወ። ሙሉ ለሙሉ ራሱን ባዶ አደረገ።  ፊልጵስዩስ 2፡6-8 ስለ

ስለ ተሠገዎ በፊልጵስዩስ ምዕራፍ 2  Read More »

ተሠገዎ በዮሐንስ 1 

This entry is part 20 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ዛሬ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ተገዎ የሚናገር፥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጠቃሚ ክፍለ ምንባቦች መካከል አንዱ የሆነውን ዮሐንስ 1፡1–14 ያለውን ጥቅስ በጥንቃቄ እናጠናለን። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ዮሐንስ ደጋግሞ ስለ «ቃል» ይናገራል። ይህን ክፍለ ምንባብ ከማጥናታችን በፊት አስቀድመን መጠየቅ ያለብን፥ «ዮሐንስ ስለ ቃል ሲናገር ምን ማለቱ ነው?» «ቃል» ማለት በግሪኩ ሎጎስ ማለት ነው። በዓለማዊው የግሪክ ፍልስፍና እሳቤ «ሎጎስ» ከዚህ ከሚታየው ፍጥረት በስተኋላ ያለና ሁሉም ነገር በእርሱ ህልውናን የሚያገኝበት መለኮታዊ መንሥዔ ማለት ነው። እንደዚሁም የሰው ነፍስ መሠረት «መነሻ» ወይም «ውስጣዊ እሳቤ» ማለትም ነው። ነገር ግን ለግሪኮች ሉጎስ ግላዊ ወይም ተሠገዎ አልነበረም።  ጥያቄ፡- ዘፍጥረት 1፡3፥ 6፥ 9፥ 14፥ 20፥ 24፤ መዝሙር 33፡6-9፤ 107፡20፤ ዘዳግም 32፡46-47፤ ኢሳይያስ 55፡11 አንብቡ። በእነዚህ ምንባቦች መሠረት የእግዚአብሔር ቃል ምን ያደርጋል?  ዕብራውያን ብሉይ ኪዳንን ወደ ግሪክ በተረጎሙ ጊዜ «ሎጎስ» የተባለውን ቃል ተጠቅመውበት ነበር። የእግዚአብሔር ሎጎስ ይፈጥራል (ዘፍጥረት 1፤ መዝሙር 3፡6)፥ ሕይወትን ይሰጣል (ዘዳግም 32፡46-47)፣ ይፈውሳል (መዝሙር 107፡20)፤ የእግዚአብሔርን ድኅነት ይፈጽማል (ኢሳይያስ 55፡ነ0፥ የእግዚአብሔር ቃል እርሱ ኃያልነቱን በፍጥረት ውስጥ የሚያሳይበት ግልጸተ መለኮትና አርነት ነው።  በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ አንድ ውስጥ ዮሐንስም ይህን ጥንታዊ የግሪክና የዕብራውያንን አሳብ በመውሰድና በማዳበር ስለ ኢየሱስ አዲስ ነገር ግንሊያስተምር ችሎአል።  1. «ቃሉ» ማን ነበር?  ጥያቄ፡- ዮሐንስ 1፡1-5 አንብቡ። ስለ «ቃል» በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እውነት የሆኑትን ሁሉ ጻፉ። ስድስት ልዩ ልዩ ነገርችን ለማግኘት ሞክሩ። 3ኛ ጥያቄ፡- ዮሐንስ 11 አንብቡ። ዮሐንስ ቃል ከእግዚአብሔር ጋር ስላለው ግንኙነት የተናገረውን ዘርዝሩና እስረዱ።  በመጀመሪያዎቹ አምስት ቁጥሮች ላይ ዮሐንስ «ስለ ቃል» ስድስት ልዩ ልዩ ነገሮችን ያስረዳል።  1. በመጀመሪያ ቃል ነበረ። ዮሐንስ፡ «በመጀመሪያ ቃል ነበረ» ሲል ቃል ያልነበረበት ጊዜ በፍጹም አልነበረም ማለቱ ነው። ማንኛውም ነገር ከመጀመሩ በፊት ቃል ነበረ። ቃል ባለፉት እልፍ ዘመናት ለዘላለም ነበር። ለዘላለም የነበረው እግዚአብሔር ብቻ ስለሆነ እንግዲህ ይህ በሌላ ኣባባል ቃል እግዚአብሔር ነው ማለት ነው።  2. ቃልም ከእግዚአብሔር ዘንድ ነበር። ቃል ከእግዚአብሔር ተለይቶ የሚታወቅና ከእግዚአብሔርም ጋር ግንኙነት ወይም አንድነት ያለው ነው።  3. ቃልም እግዚአብሔር ነው። ሆኖም ቃል ከእግዚአብሔር ጋር ነበር ማለት ብቻ አይበቃም። ቃልም እግዚኣብሔር ነበር። በመጀመሪያው ትምህርታችን ላይ እንደተመለከትነው፥ ኢየሱስ እግዚአብሔር ለመሆኑ ይህ ከግልጽ ማረጋገጫዎች መካከል አንዱ ነው። ዮሐንስ ቃል በእግዚአብሔር ወይም በመለኮት የሚመሰል ነው አላለም። እርሱ የሚለው ቃል ራሱ እግዚአብሔር እንደሆነ ነው። ዮሐንስ ቃል ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ይህ ቃልም እግዚኣብሔር ነበረ ሊል እንዴት ቻለ? እንደ ሰው አስተሳሰብ ክሆነ ይህ ስሜት የሚሰጥ አይደለም። ነገር ግን ዮሐንስ የፈለገው ከሰዎች አስተሳሰብ የተለየ ገለጻ ለማቅረብ ነበር። በአንድ መንገድ ቃል እግዚአብሔርም ነው፥ ከእግዚአብሔር የተለየም ነው። ዮሐንስ እንድንገነዘብ የፈለገው የኢየሱስ ቃላትና ተግባራት የእግዚአብሔር የራሱ ቃላትና ተግባራት መሆናቸውን ነው።  ጥያቄ፡- ዮሐንስ 1፡3 ኣንብቡ። እንደዚህ ጥቅስ ከሆነ፥ ዓለምን የፈጠረው ማን ነው?  4 ቃል ዓለምን ፈጠረ። የእግዚአብሔር ዓለምን መፍጠር በቃሉ ሆነ (ዘፍጥረት 1-2)። እግዚአብሔር ብቻ ሊፈጥር ስለሚችል፤ ቃል እግዚአብሔር ለመሆኑ ይህ ሌላ ማረጋገጫ ነው። እንደዚሁም ጊዜና ፍጥረት ሲጀመር ቃል ነበር የሚለውንም እንደገና ያጠናክራል። 5ኛ ጥያቄ፡- ዮሐንስ 1፡4-5 ኣንብቡ። ሀ) የሕይወት ምንጭ ማን ነው? ለ) ዮሐንስ፥ «ብርሃን» ሲል ምን ማለቱ ይመስላል? ሐ) ብርሃን ምን አደረገ?  5. ቃሉ ለሰዎች መንፈሳዊ ብርሃንን የሚሰጥ የሕይወት ምንጭ ነው። በራሱ ሕይወት ያለው እግዚአብሔር ብቻ ነው። እግዚአብሔር ሕይወትን ስለሚሰጣቸው፥ ዕጽዋት፥ እንስሳትና ሰዎች ሕይወት አላቸው። ነገር ግን ይህ ጥቅስ ቃሉ በራሱ ሕይወት አለው ይላል። ማንም ለእርሱ ሕይወትን አልሰጠውም፤ እንዲያውም እርሱ ለሌሎች የሕይወት ምንጭ ነው። ስለሆነም ኢየሱስ እግዚአብሔር ለመሆኑ ይህ ጥቅስ ተጨማሪ ምስክር ነው። ቃሉ የሕይወት ምንጭ እንደ መሆኑ፥ ለሌሎች መንፈሳዊ ብርሃንን ይሰጣል። ዮሐንስ ቃል የሰዎች ብርሃን ነው ሲል ቃሉ ሰዎች እግዚአብሔርን እንዲያስተውሉት፥ እንዲያዩትና እንዲያውቁት ያደርጋል ማለቱ ነው። ዮሐንስ፥ ኢየሱስ መለኮትና ሰው መሆኑን ማመልከቱን ይጀምራል። ቃል እግዚአብሔር ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔርም ደግሞ ራሱን ለሰዎች የገለጠበት መንገድ ነበር።  6. የቃሉም ብርሃን በመንፈሳዊ ጨለማ ውስጥ በራ፥ ነገር ግን በጨለማ የሚኖሩት ሕዝቦች ሊገነዘቡት አልቻሉም ወይም ጨለማው እላሸነፈውም። ቃሉ ከእርሱ በተለዩ እርሱንም ባላወቁ ሰዎች መካከል እግዚኣብሔርን ገለጠ። ነገር ግን ምንም እንኳን ቃሉ እግዚአብሔርን ቢገልጥላቸውም፤ እነርሱ ግን ሙሉ በሙሉ አልተገነዘቡትም፥ ኣላወቁትም። «አላሸነፈውም» የሚለው ቃል በኦሪጅናል ግሪክ ውስጥ ሁለት ትርጉሞች አለው። «አላሸነፈውም» ወይም «አልተገነዘበውም» ማለት ነው። ምናልባት ዮሐንስ ሁለቱንም ትርጉሞች እንድናጤን ፈልጎ ይሆናል። በኢየሱስ ዙሪያ የነበረው መንፈሳዊ ጨለማ አላሸነፈውም፤ ነገር ግን እርሱ ስለ እግዚአብሔር ስለሚገለጠው ነገርም አልተነበበም።  እነዚህ ጥቅሶች ስለ ተሠገዎ ምሥጢር ጥቂት ጠቃሚ ማብራሪያዎችን ይሰጡናል። ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ይነግሩናል። እርሱ ለዘላለም የነበረ፥ ፈጣሪና የሕይወት ምንጭ መሆኑን ይገልጡልናል። ይሁን እንጂ ኢየሱስ እግዚአብሔር ቢሆንም ይህ ለሰው ግንዛቤ አስቸጋሪ ነው። እንደዚሁም እርሱ ከእግዚአብሔር የተለየ ነው። ቃሉ ሰው ሆኖ ለመኖር በምን ምክንያት ወደ ምድር መጣ? ቃሉ ለማያውቁት ሁሉ መንፈሳዊ ብርሃን ሊሰጥና እግዚአብሔርንም ሊገልጥላቸው ወደዚህ ምድር መጣ። ምንም እንኳን ቃልን የተገናኙ ኣብዛኛዎቹ እርሱ ስለ እግዚአብሔር ምንን እንደሚገልጥ ባይገባጵውም፥ እግዚአብሔርን ለዓለም ለመግለጥ የነበረውን ዓላማ ሊሽሩት አልቻሉም።  ጥያቄ፡- በግላችሁ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እንዴት ገለጠላችሁ?  ሓዋርያው ዮሐንስ ከቁጥር 6-8 ላይ የመጥምቁ ዮሐንስን ሥራ በአጭሩ ይገልጻል። ሥራው ሰዎችን ወደ ኢየሱስ ማመላከት ነበር። ከዚያም ስለ ኢየሱስ መናገሩን ይቀጥላል።  2. በቃልና በዓለም መካከል የነበረው ግንኙነት ምን ነበር?  በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 1፡9-13 ባለው ክፍል በቃልና በዓለም መካከል ስላለው ግንኙነት ይገልጻል። ስለዚህ ግንኙነትም ሦስት ነገሮችን ያስረዳል።  ጥያቄ፡ ዮሐንስ 1፡9-13 አንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ ቃልና ዓለም ‘ የሚናገሩትን ጻፉ። ቢያንስ ሦስት ልዩ ልዩ ነጥቦችን ለማግኘት ሞክሩ።  ጥያቄ፡- ዮሐንስ 1፡9፤ 3፡19-21፤ 8፡12፣ 9፡39-41 አንብቡ። ብርሃኑ ምን ያደርጋል?  1. ዮሐንስ በምዕራፍ 1፡9 ውስጥ የኢየሱስ መምጣት ለሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን የሚገልጥ ብርሃን እንደሆነ ይናገራል። በተቀረውም የወንጌሉ ክፍል ኢየሱስ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ሲገልጥ እንመለከታለን። ይሁን እንጂ ሰዎች ልባቸውን ከፍተው ኢየሱስ እግዚአብሔርን መግለጡን ሁልጊዜ አይቀበሉም። አንዳንድ ጊዜ ብርሃኑን ችላ ይሉታል። ነገር ግን እርሱ ብርሃን በመሆኑ፥ እግዚአብሔርን እየገለጠ፥ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ውሳኔ እንዲኖራቸው ያደርጋል። ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር ለማገናኘት ዓይነተኛው መንገድ ከክርስቶስ ጋር ማገናኘት ነው።  ጥያቄ፡- ኢየሱስን እንድታምኑ ያደረጋችሁ ምንነቱ ነው? ሌሎች ሰዎች ክርስቶስን እንዲያምኑ፥ የግል ልምምዳችሁን እንዴት ትጠቀሙበታላችሁ? 10ኛ ጥያቄ፡- ዮሐንስ ፡10-11 ኣንብቡ። አብዛኛው የዓለም ሕዝብ ኢየሱስን እንዴት ተቀበሉት?  2. ምንም እንኳን ኢየሱስ እግዚአብሔርን ለዓለም ያሳየ ብርሃን ይዞ ቢመጣም፥ የዓለም ሕዝብ ግን እርሱነቱን አላወቁትም ወይም አልተቀበሉትም። የኢየሱስ የራሱ ወገን የነበሩ አይሁዳውያን እንኳን ከእግዚአብሔር እንደ ተላከና፥ እግዚአብሔርንም ለእነርሱ የሚገልጥ መሆኑን አላወቁትም ወይም አልተቀበሉትም። ምንም እንኳን ኢየሱስ እግዚኣብሔርን የሚያንጸባርቅ ብርሃን ቢሆንም፥ ኣብዛኛዎቹ ሰዎች ይገልጥላቸው የነበረውን ሊቀበሉ ፈቃደኞች አልሆኑም።  ጥያቄ፡- ለምንድን ነው ዛሬ ሰዎች ኢየሱስን ለማወቅም ሆነ ለመቀበል አሻፈረን የሚሉት? ሰዎች እግዚአብሔር ስለ ኢየሱስ ሊገልጥላቸው ለመቀበል እምቢ የሚሉባቸውን እንዳንድ ሁኔታ ጻፉ። 12ኛ ጥያቄ፡- ዮሐንስ 1፡12-13 አንብቡ። ሀ) አንዳንድ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ምን ያስባሉ? ለ) ታዲያ የዚህ ዓይነት ስሜት ያላቸው ምን ሆኑ? 3. ምንም እንኳን አብዛኛዎቹ የዓለም ሕዝቦች ኢየሱስን መቀበል ችላ ቢሉም፥ የተወሰኑ ተቀብለውታል። የተቀበሉትም እግዚኣብሔርን ለእነርሱ በእውነት መግለጡን አምነዋል። እግዚአብሔር በእርሱ አማካይነት የተገለጠላቸው መሆኑን አምነው የተቀበሉት የእግዚአብሔር ልጆች ሆኑ። የእግዚአብሔር ልጅ መሆን፥ ነገር ግን እንደ ሰብኣዊ ሕፃን ሆኖ መወለድ አይደለም። ይህ የሥጋና የደም ልደት አይደለም፥ ወይም አንድ ባል ልጅ ለማግኘት ፈልጎ እንደሚወለድለት ያለ ልጅነትም አይደለም። የእግዚአብሔር ልጆች የሚሆኑት ኃይልን በተሞላ የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ተግባር ነው።  ዮሐንስ 1፡9-13 ውስጥ ወንጌላዊው የተሠገዎ

ተሠገዎ በዮሐንስ 1  Read More »

የኢየሱስ ከድንግል መወለድ 

This entry is part 19 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

በዚህ ሳምንት በተከታተልነው ትምህርት ላይ ኢየሱስ ሙሉ በሙሉና ፍጹም ሰው ስለመሆኑ ተረድተናል። እርሱም ሰብዓዊ አካል፥ ነፍስና መንፈስ ነበረው። ሰብአዊ ስሜትም ነበረው። እንደ ሰዎች ሁሉ ፈተና አጋጥሞታል። ሆኖም በፈተና አልተሸነፈም። ዛሬ ደግሞ በመቀጠል ስለ ኢየሱስ ሰብአዊነትና ልደት በሌላ አቅጣጫ ቀረብ ብለን እንመለከታለን። ኢየሱስ ሌሎች ሰዎች ወደ ዓለም በመጡበት ሁኔታ ተወለደ። ነገር ግን የኢየሱስ ልደት ከማንኛውም ይልቅ የተለየ ነበር።  2. መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ድንግል መውለድ ምን ይላል?  ጥያቄ፡- ማቴዎስ ፡18-25 አንብቡ። ሀ) እንደ ቁጥር 18 አገላለጽ ማርያም ፀንሳ የተገኘው መቼ ነበር? ለ) በምን ኃይል ፀንሳ ተገኘች? ሐ) ዮሴፍ ማርያም መፅነሷን ባወቀ ጊዜ ምን ለማድረግ እሰበ? መ) መልአኩ ለዮሴፍ በታየው ጊዜ፥ ስለ ማርያም መፀነስ እንዴት ብሎ ገለጸለት? ሠ) መልአኩ ዮሴፍ ምን እንዲያደርግ ነገረው? ረ) ስለ ድንግል መፀነስ ማቴዎስ ተፈጸመ የሚለው የትኛውን ትንቢት ነው? ለ) በቁጥር 24 ላይ እንደ ተነገረው ዮሴፍ ምን አደረገ? ሸ) ኢየሱስ እስኪወለድ ድረስ ዮሴፍና ማርያም በምን አኳኋን አብረው ኖሩ?  በአዲስ ኪዳን ውስጥ ድንግል ማርያም ኢየሱስን ስለ መፀነስዋ ሁለት ማስረጃ ዎች አሉ። አንደኛው በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፥ ታሪኩ የተነገረው ከዮሴፍ አኳያ ነው። ማቴዎስ «ሳይገናኙ በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች» ሲል ይነግረናል። ነገር ግን ዮሴፍ ማርያም ፀንሳ ባየ ጊዜ በመጀመሪያ ከሌላ ሰው ያረገዘች መስሎት ጠርጥሯት ነበር። እርሱ ስላልተገናኛት የተረገዘው ሕፃን የእርሱ አለመሆኑ ይገባው ነበር። ቢሆንም በሰዎች ፊት ሊያጋልጣት አልፈለገም። ስለሆነም ምሥጢራዊ በሆነ መንገድ የእጮኛነቱን ውል እንዴት እንደሚያፈርስ አሰበ። እንግዲህ ይህን ሲያስብ ሳለ ነው ሕልም ያየው። በዚህ ሕልም ውስጥ መልአኩ ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መፀነስዋን አበሰረው። ከዚያም ማርያምን በሚስትነት ለመውሰድ እንዳይሰጋ ለዮሴፍ ነገረው። ስለዚህ ዮሴፍ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ማርያምን በሚስትነት አገባት። ነገር ግን ኢየሱስን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም ነበር። እዚህ ላይ ማቴዎስ በኢሳይያስ 7፡14 ላይ የተጻፈው ትንቢት መፈጸሙን ይናገራል። እርሱም ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች» የሚለው ነው።  ኢየሱስ ያለሰብአዊ አሳት በማርያም ማኅፀን ስለ መፀነሱ ማቴዎስ በሦስት መንገድ አጽንኦት ሰጥቶ ይናገራል። በመጀመሪያ፥ ማርያም የፀነሰችው እርስዋና ዮሴፍ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከማድረጋቸው በፊት መሆኑን ያስረዳል። ሁለተኛ፥ ማርያም ከሰው ጋር ግብረ ሥጋ ግንኙነት በማድረግ ሳይሆን፥ በመንፈስ ቅዱስ ኃይለ መፀነስዋን ሁለት ጊዜ ደጋግሞ ይነግረናል። በመጨረሻም፥ ድንግል ትፀንሳለች» ተብሎ በትንቢት የተነገረው ቃል መፈጸሙን ይገልጽልናል። ማቴዎስ «ድንግል» ለሚለው ቃል የተጠቀመበት የግሪክ ቃል ግልጽና የማያሻማ ቃል ነው። ቃሉ ኮረዳና ያላገባች «ልጃ ገረድ» ማለት ብቻም አይደለም። በማያሻማ መንገድ በፍጹም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ያላደረገች ሴት ማለት ነው። ድንግል ማርያም ወንድ ሳታውቅ ኢየሱስን መፀነስዋን ማቴዎስ በግልጽ ይነግረናል። 43ኛ ጥያቄ፡- ሉቃስ 1፡26-38 አንብቡ። ሀ) በቁጥር 27 ላይ ማርያም እንዴት ተገለጸች? ለ) ከቁጥር 30=33 ድረስ መልአኩ ለማርያም ያበሠረላትን መልእክት ጠቅለል ባለ ይዘት አቅርቡት። ሐህ የቁጥር 34 መልእክት በማርያም አእምሮ ውስጥ ምን ጥያቄ ቀሰቀለ? መ) በቁጥር 35 ላይ መልአኩ ለማርያም ጥያቄ እንዴት ያለ መልስ ሰጠ?  ሁለተኛ ስለ ኢየሱስ የቀረበው ማስረጃ ከማርያም አቅጣጫ ሲሆን፥ የሚገኘውም በሉቃስ ወንጌል ላይ ነው። ማቴዎስ እንደ ጻፈው ሁሉ ሉቃስም በጥንቃቄ ማርያም ገና ድንግል ሳለች መፀነሰዋን ይገልጻል። በመጀመሪያ፡ መልአኩ ወደ ማርያም በመጣ ጊዜ ድንግል እንደ ነበረች ሁለት ጊዜ ደጋግሞ ይነግረናል (ቁጥር 27)። ሁለተኛ፥ ማርያምም መልሳ ክዚህ ጊዜ በፊት ወንድ እንደማታውቅ ትናገራለች (ቁጥር 34)። ሦስተኛ፥ እርስዋ ድንግል ስለሆነች እንዴት ልትፀንስ እንደምትችል ስትጠይቀው የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መሆኑን መልአኩ መልሶ ይነግራታል። ማቴዎስ እንደ ጻፈው ሁሉ ሉቃስም ማርያም ኢየሱስን የፀነሰችው ያለምንም ግብረ ሥጋ ግንኙነት መሆኑን ትኩረት ሰጥቶ ያስረዳል።  1. ስለ ድንግል መውለድ ልናስወግዳቸው የሚገቡን ተቃውሞዎች ምንድን ናቸው?  በእነዚህ ጥቅሶች ላይ የሚሰነዘሩና ልናስወግዳቸው የሚገቡን ሁለት ተቃውሞዎች አሉ። የመጀመሪያው ተቃውሞ ኢየሱስ ከግብረ ሥጋ ግንኙነት ውጭ መወለዱን የሚጠራጠር የዘመናዊ ሰው አመለካከት ነው። እንዲህ ዓይነቶቹ ሰዎች የድንግል መውለድ ሁኔታ ከሥነ ተፈጥሮ ሳይንስ እሳቤ የራቀ ነውና ሊሆን አይችልም ይላሉ። እነዚህ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ የድንግልን መውለድ በተመለከተ ተጽፎ የሚገኘው በማቴዎስና በሉቃስ ወንጌል ውስጥ ብቻ ነው ይላሉ። ታዲያ የድንግልዋ መውለድ እርግጠኛ ቢሆን ኖሮ፥ ለምን በማርቆስና በዮሐንስ ወንጌሎች ውስጥ አልተጠቀሰም? ይላሉ። ሐዋርያው ጳውሎስ ለምን አልጠቀሰውም ባይ ናቸው። ከዚህ አልፈው ይህ ታሪክ በጥንት ዘመን አማልክት በገሃዱ ዓለም ካሉ ሴቶች ጋር ግብረ ሥጋ በመፈጸም ልጆች ይወልዳሉ ከሚባለው አፈ-ታሪክ ጋር ይመሳሰላል ይላሉ። ስለዚህ የጥንት አረማውያን አፈ-ታሪክ ነው በማለት ያናንቁታል።  እንዲህ ላሉት ተቃውሞዎችም ቢሆን በቂ የሆኑና መልስ ሊሰጡ የሚችሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ዎች አሉ። ይህን ተቃውሞ የሚያቀርቡ ሰዎች ችግር፥ የመጽሐፍ ቅዱስን ግልጽ የሆነ ማስረጃ ና ትምህርት አለመቀበል ነው። እንደዚሁም ከሰዎች ግንዛቤ በላይ በሆነ በመለኮት ሥራዎች ማመን አይፈልጉም። ማቴዎስና ሉቃስ ማርያም ኢየሱስ ተረግዞ በሚወለድበት ጊዜም ድንግል እንደነበረች በግልጽ ያስተምራሉ። ይህ ሁኔታ ከሥነ ሕይወት ጋር አይስማማ ይሆናል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር በእግዚአብሔርነቱ ከፈለገ የሥነ ሕይወትን ሂደት የሚያፋልስ ድርጊት ሊፈጽም ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው ብለን ካመንን የድንግል መፀነስ የሥነ ሕይወት እሳቤን የሚቃረን ሊሆን ይችላል። ሆኖም እግዚአብሔር እግዚአብሔር ከሆነ እግዚአብሔር በተአምር ማርያም ድንግል ሳለች፥ ኢየሱስን እንድትፀንስ ማድረጉን አምነን መቀበል ይኖርብናል። ማርቆስና ዮሐንስ የድንግልን መውለድ አክለው ያልጻፉበት ምክንያት፥ ስለ ኢየሱስ በጻፉት ወንጌላቸው ውስጥ በልጅነት ታሪኩ ላይ ትኩረት ካለመስጠታቸው የተነሣ ነው። እንደዚሁም ስለ ኢየሱስ የልጅነት ታሪክ ያልጻፉት፥ ከተነሡበት የወንጌል ዓላማ ጋር እምብዛም ስለማይገጥም ነው። ሐዋርያው ጳውሎስም ቢሆን ስለ ድንግል መውለድ ያላነበት ምክንያት መልእክቶቹ ያተኮሩት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሉ ወቅታዊ ችግሮች ላይ ስለነበረ ነው። ከዚህም በስተቀር ስለ ድንግል መውለድ በቤተ ክርስቲያኖቹ ውስጥ የተነሣ አፍራሽ ክርክር ስላልነበረ ጳውሎስ በዚህ ጉዳይ ላይ አልጻፈም። በመጨረሻም የድንግል (መፀነስ) ሁኔታ፥ ከአረማውያን አፈ ታሪክ የተለየ ነው። የድንግል መውለድ ታሪክ ሐሰተኛ አማልክት በገሃዱ ዓለም ካሉ ሴቶች ጋር ግብረ ሥጋ አድርገው ልጆች ይወልዳሉ ከሚለው አባባልም ጋር የሚመሳሰል አይደለም። ማቴዎስና ሉቃስ በግልጽ እንደ ተናገሩት ማርያም ከወንድ ጋር ግብረ ሥጋ ሳትፈጽም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መፀነስዋን ያስረዳሉ። ስለዚህ ኢየሱስ በቅዱስና ኃይል በተሞላበት የእግዚአብሔር ሥራ በማርያም ማኅፀን ሊያድር ቻለ እንጂ፥ ስግብረ ሥጋ ግንኙነት አልተፀነሰም (ሉቃስ 185)።  መጽሐፍ ቅዱስን የሚያምኑ ክርስቲያኖች የድንግል መውለድ ሊሆን አይችልም የሚሉ መናፍቃንን ማራቅ አለባቸው። እንደዚሁ ክርስቲያኖች ሊያስወግዱት የሚገባ ሁለተኛ ተቃውሞ አለ። ብዙ ክርስቲያኖች ስለ ድንግል መውለድ እነዚህ ጥቅሶች ከሚያስተምሩት መንገድ በመውጣት የራሳቸውን ሃሳብ ይጨምሩበታል። ለምሳሌ ያህል፥ ብዙ የካቶሊክና የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ማርያም ኢየሱስን ከወለደችም በኋላ በድንግልናዋ ቀርታለች ብለው ያምናሉ። ማቴዎስም ሆነ ሉቃስ ማንኛቸውም ማርያም ድንግል ሆና ቀረች ብለው አልጻፉም። በማቴዎስ 1፡25 ላይ በተጻፈው ሁኔታ ከሆነ ኢየሱስ ከተወለደ በኋላ ማርያምና ዮሴፍ ባልና ሚስት በመሆን እንደ ማንኛውም ባለትዳር የግብረ ሥጋ ግንኙነት እየፈጸሙ አብረው መኖራቸው ይገመታል። እንደዚሁም አንዳንድ የካቶሊክና የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ተአምራዊ በሆነ ድርጊት ኢየሱስ ስለተወለደ የማርያም ድንግልናዋ አልተነካም ይላሉ። እግዚአብሔር እንዲህ ያለውን ተአምር ሊፈጽም ቢችልም፥ እነርሱ በሚሉት ሁኔታ ኢየሱስ ተወለደ የሚል ማስረጃ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። በሉቃስ 2፡1-7 ተጽፎ የሚገኘው እርግጠኛው የኢየሱስ መወለድ እንደ ማንኛውም ሰው የመወለድ ሁኔታ መሆኑን ይናገራል። መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስ መፀነስ ተአምራዊ መሆኑን በግልጽ ይናገራል። ይህም እሱ ከወንድና ሴት ግብረ ሥጋ ግንኙነት ውጭ መፀነሱ ነው። እንደዚሁም ማርያም ኢየሱስን እስከወለደችበት ጊዜ ድረስ ድንግል ሆና መቆየቷን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል። ነገር ግን ማርያም ኢየሱስን ከወለደች በኋላ ድንግል ሆና ቀረች ብሎ አያስተምርም።  አንዳንድ ሰዎች ማርያም ኢየሱስን ከወለደች በኋላም ድንግል ሆና ኖራለች እያሉ ለምን ይከራከራሉ? ይህ

የኢየሱስ ከድንግል መወለድ  Read More »

ኃጢአት አልባው የኢየሱስ ሰብአዊነት 

This entry is part 18 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

በዚህ ክፍል በሙሉ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስብእና እናጠናለን። እርሱ እንደ እኛ ሰው ስለመሆኑ አይተናል። ነገር ግን ሳምንቱን በተማርነው ትምህርት ከኃጢአት ነፃ ነው ስንል ቆይተናል። ዛሬ ኢየሱስ ኃጢአት ያላደረገ ስለመሆኑ፥ ሰፋ አድርገን እናጠናለን። እንደዚሁም የሚከተለውን ጥያቄ ልናነሣ እንችላለን፡ «ኢየሱስ ፈጽሞ ኃጢአት ባይሠራም፥ ኃጢአትን ሊፈጽም ይችል ነበር?»  ኢየሱስ በፍጹም ኃጢአትን ላደረገም  ጥያቄ፡- ዕብራውያን 4፡5 አንብቡ። ሀ) ስለ ኢየሱስ መፈተን ይህ ጥቅስ ምን ይላል? ለህ እንደዚሁም ይህ ጥቅስ ኢየሱስ ኃጢአት ስለ መሥራቱና ስለ አለመሥራቱ ምን ይላል?  ጥያቄ፡- ሀ) ዮሐንስ 8፡46 አንብቡ። ኢየሱስ ለጠየቀው ጥያቄ መልሱ ምንድን ነው? ለ) ማቴዎስ 26፡59-60 አንብቡ። ኢየሱስ በሸንጎው ፊት በቀረበ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ወይም በወንጀል የከሰሰው ሰው ነበር?  ጥያቄ፡- 1ኛ ጴጥሮስ 2፡22 አንብቡ። እዚህ ላይ ጴጥሮስ ስለ መሢሑ ከኢሳይያስ መጽሐፍ ይጠቅሳል። ስለ ክርስቶስ ምን ይላል?  ጥያቄ፡- 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21 አንብቡ። ይህ ጥቅስ ስለ ክርስቶስ ምን ይላል?  ጥያቄ፡- 1ኛ ዮሐንስ 3፡5 አንብብ። ክርስቶስ ለምን ኃጢአታችንን ሊያስወግድልን ቻለ?  ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ፥ ምንም ዓይነት ኃጢአት አለማድረጉን አዲስ ኪዳን በግልጽ ያቀርበዋል። እርሱም በምድር ላይ በነበረ ጊዜ በአንዳች ኃጢአት የሚከሰው ካለ እንዲያቀርብ ይቃወሙት ለነበሩ ይነግራቸው ነበር። እንደዚሁም በሚያነጋግራቸው ጊዜ አንዳችም ኃጢአት ያላዩበት ከመሆናቸውም በላይ ከሰሰው በሸንጎ ፊት ባቀረቡትም ጊዜ አንዳች ኃጢአት አላገኙበትም። ምንም እንኳን ወንጀል የሚፈልጉበት ቢሆኑም፥ የሐሰት ምስክሮችም ቀርበው የሐሰት ክስ ሊያቀርቡበት ቢፈልጉም፥ በምንም ኃጢአት ሊወነጅሉት አልቻሉም። ስለ ኢየሱስ ምድራዊ ሕይወት ያለው ምስክርነት ግልጽ ነው፡ እርሱ ኃጢአት አልሠራም።  በአዲስ ኪዳን ውስጥ የሚገኙ መልእክቶች ኢየሱስ ኃጢአት አለመፈጸሙን በተመሳሳይ ሁኔታ ግልጽ አድርገውታል። በ1ኛ ጴጥሮስ 2፡22 ውስጥ ጴጥሮስ ከኢሳይያስ 53፡9 ላይ ጠቅሶ፥ ክርስቶስ ምንም ኃጢአት አለማድረጉን ያስረዳል። ኢየሱስ ኃጢአት አለመፈጸሙ ብቻ ሳይሆን፥ ኃጢአታዊ ባሕርይ አልነበረውም። የኃጢአት ቅድመ- ዝንባሌም አልነበረውም። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21፥ «ኃጢአት ያላወቀውን» ሲል ስለ ኢየሱስ ይመሰክራል። እርሱ በአድራጎትም ሆነ በባሕርይ ኃጢአት አልነበረበትም። 1ኛ ዮሐንስ 3፡5፥ «በእርሱም ኃጢአት የለም» ይላል። በእነዚህ በሁለቱም ጥቅሶች የተነገረው ኢየሱስ ኃጢአትን እንዳላደረገና ኃጢአትንም የመፈጸም ዝንባሌ እንዳልነበረው ነው። ስለሆነም በምንም ዓይነት መልኩ ኢየሱስ ኃጢአትን አያውቀውም። ከዚህም በስተቀር የኃጢአት ባሕርይ አልነበረውም። ኢየሱስ ከግል ኃጢአት ነፃ ሲሆን፥ የሰው ልጆች ሁሉ የወረሱትን የኃጢአት ባሕርይ እርሱ አልወረሰም።  ኢየሱስ ኃጢአትን እንዲያደርግ በእውነት ተፈትኖአል  ምንም እንኳን ኢየሱስ ኃጢአት ባያደርግም፥ ኃጢአት እንዲሠራ መፈተኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል። ዕብራውያን 4፡15 በሰብአዊ አእምሮአችን ውስጥ ሁለት ተቃራኒ አሳቦችን የሚጨምር ጠቃሚ ጥቅስ ነው። አንድ ሰው በሚፈተንበት ሁኔታ ኢየሱስም ተፈትኖአል። ይህ ማለት ሰዎችን ያጋጠማቸው የፈተና ዓይነት ሁሉ እርሱንም አጋጥሞታል ማለት ነው። በሥጋ ፍላጎት ተፈትኖአል። በዓይን አምሮትም ተፈትኖአል። እንደዚሁም በኑሮ ትምክህትም ተፈትኖአል (1ኛ ዮሐንስ 2፡16)። ኃጢአትን ለመሥራት መፈተን ማለት በፈተና መሸነፍ ማለት አይደለም። መፈተን ራሱ ኃጢአት አይደለም። ስፈተና መሸነፍ ግን ኃጢአት ነው። ምንም እንኳን ኢየሱስ ኃጢአትን እንዲያደርግ ቢፈተንም፥ በፈተና አልተሸነፈም። ኃጢአትም አላደረገም።  አንዳንድ ጊዜ እኛ አማኞችም ፈተና ያጋጥመናል፥ ነገር ግን ግን በዚህ ፈተና እንወድቃለን ማለት አይደለም። በቁጣ፥ አንዳችን ነገር በመስረቅ፥ በመመኘት፥ ወይም በውሸት እንፈተን ይሆናል። በዚህ ፈተና እንሸነፋለን ማለት አይደለም። ነገር ግን ሰይጣን ይመጣና ስለተፈተንን ብቻ ጸጸት ውስጥ እንድንገባ ያደርጋል። ስለሆነም በመፈተን ብቻ የሚመጣ ጸጸት የሰይጣን የሆነ ሐሰተኛ ጸጸት ነው። ኢየሱስም ቢሆን ተፈትኖአል። መፈተን ደግሞ ክፋት የለውም። ችግሩ ወደ ፈተና ገብቶ ኃጢአትን መሥራቱ ላይ ነው።  ኢየሱስ በሕይወቱ ሙሉ ፈተና ሊደርስበት፥ ያንን ፈተና እንዴት እንደ ተወጣው ሁሉንም አናውቅም። ነገር ግን ኢየሱስ በምድረ በዳ ያጋጠመውን ፈተና እንዴት እንደ ተጋፈጠው መጽሐፍ ቅዱስ ዝርዝር ሁኔታውን ያስረዳናል። ይህን ማስረጃ በማጥናት ኢየሱስ እንደ ሰው ያጋጠመውን ፈተና ሁሉ እንዴት ባለ መንገድ እንደ ተወጣው በብዙ ልንማር እንችላለን።  ጥያቄ፡- ሀ) ዘፍጥረት 3፡6 አንብቡ። ሔዋን በየትኞቹ ሦስት መንገዶች ተፈተነች? ለ) 1ኛ ዮሐንስ 2፡16 እንብቡ። እኛስ በየትኛቹ ሦስት መንገዶች ነው የምንፈተነው?  ጥያቄ፡- ሉቃስ 4፡1-13 እና ማቴዎስ 4፡1-1 አንብቡ። ሀ) ኢየሱስን ስላጋጠሙት ሦስት ፈተናዎች ጻፉ። ለ) ኢየሱስ ድንጋዩን ወደ ዳቦ ለውጦት ቢሆን ኖሮ ስሕተቱ ምን ላይ ይመስላችኋል? ሐ) ኢየሱስ ከቤተ መቅደስ ጫፍ ላይ ቢዘል [ ኖሮ ስሕተት ይሆን የነበረው ለምን ይመስላችኋል? መ) ኢየሱስ እንዴት እነዚህን ፈተናዎች ተቃወመ? ሠ) የኢየሱስ ፈተናዎች ከአዳምና ከሔዋን ፈተናዎች የሚመሳሰለው እንዴት ነው? ልዩነታቸውስ ምኑ ላይ ነበር?  ሉቃስ የኢየሱስን የፈተና ታሪክ በጻፈ ጊዜ ኢየሱስን ከአዳምና ከሔዋን ጋር እንድናነጻጽር የፈለገ ይመስላል። ኢየሱስ ባጋጠመው ፈተና ላይ ድልን የተቀዳጀ ሲሆን፥ በአንጻሩ አዳምና ሔዋንን በፈተናው መሸነፋቸውን ልብ እንድንል የፈለገ ይመስላል። ሉቃስ ስለ ኢየሱስ ፈተና ታሪክ ከመናገሩ በፊት ስለ ዘር ሐረጉ ይዘረዝርና ከአዳም ዘር ሲወርድ ሲዋረድ ስለመምጣቱ ያወሳል። ይህ እንግዲህ አእምሮአችንን አዳምና ሔዋን ወደነበሩበት ወደ ኤድን ገነት መልሶ ይወስደዋል። ከዚያም አዳምና ሔዋንን የሥጋ ምኞት፥ የዓይን አምሮትና የኑሮ ትምክህት ፈተና (ዘፍጥ. 3፡6) እንዳጋጠማቸው ሁሉ፥ ኢየሱስንም የሥጋ ፈተና፥ ድንጋዩን ወደ ዳቦ የመለወጥ እንዲሁም የዓይን አምሮት ፈተና፥ የዓለምን መንግሥታት በሙሉ የማግኘት እና የሕይወት ትምክህት ፈተና (በሕዝቡ ዘንድ ለመታወቅ ራስን ከቤተ መቅደሱ ወደ ታች የመወርወር) ፈተና እንዳጋጠመው ይገልጽልናል። ነገር ግን በኢየሱስ፥ በአዳምና በሔዋን መካከል፥ አንዳንድ ልዩነቶች ነበሩ። ኢየሱስ በምድረ በዳ ውስጥ ተፈተነ። አዳምና ሔዋን ግን በኤድን ገነት ውስጥ ተፈተኑ። ኢየሱስ በረሃብ በደከመ ጊዜ ተፈተነ፥ አዳምና ሔዋን ግን በምግብ ተከብበው ተፈተኑ። አዳምና ሔዋን ፈተናውን መቋቋም አቅቷቸው ወደቁ፥ ኢየሱስ ግን እነርሱ የወደቁበትን ፈተና አሸነፈ።  ሰይጣንን የማምለክ ፈተና ኃጢአት መሆኑን መገንዘብ ቀላል ነው። ምን ጊዜም ቢሆን በእግዚአብሔር ፈንታ ለማንም ለምንም መስገድ ኃጢአት ነው። ነገር ግን የተቀሩት የሰይጣን ፈተናዎች ኃጢአት ስለመሆናቸው መገንዘብ ያዳግታል። ለምሳሌ ያህል፥ ኢየሱስ ድንጋዩን ወደ ዳቦ መለወጡ ኃጢአት ይሆንበት ነበር? ኢየሱስ ኋላ ላይ ውኃውን ወደ ወይን ለውጦአል። ጥቂቱን ዳቦና ጥቂቱን ዓሣ አብዝቶአል። በዚህን ጊዜ ምግብን ማዘጋጀት ኃጢአት የሚሆነው ለምንድን ነው? መልሱ ኢየሱስ መለኮታዊ ኃይሉን ለሥጋዊ ፍላጎቶቹ ማዋሉ የአብ ፈቃድ ስላልነበረ ነው። ምንም እንኳን ኢየሱስ ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔር ቢሆንም እንደ ሰብዓዊ ፍጡር እንዲኖር የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር። ኢየሱስ መለኮታዊ ኃይሉን ያሳይ የነበረው አብ እንዲያሳይ ፈቃዱ ሲሆን ብቻ ነበር። ኢየሱስ ከዘዳግም 8፡3 ጠቅሶ ለሰይጣን ሲመልስ፥ «ሰው በእግዚአብሔር ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም» አለው። ይህ ጥቅስ ሙሴ በምድረ ባዳ ለእስራኤል ልጆች ከተናገረው ቃል የተገኘ ነው። የዕለታዊ ምግባቸውንም እንኳ የሚሰጣቸው እርሱ መሆኑን የእስራኤል ልጆች እንዲያምኑ ሙሴ እግዚአብሔር መና እንደ ላከላቸው ነገራቸው። በኦሪት ዘዳግም እንደተጻፈው ለእስራኤል ልጆች እግዚአብሔር የዕለት ምግባቸውን እንደሚሰጣቶው ማመን እንዳለባቸው ሁሉ፥ ኢየሱስም ለዕለት ምግቡ እንዲተማመን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር። ኢየሱስ ለዕለት ምግቡ እግዚአብሔርን በማመን ፈንታ በራሱ ታምኖ ቢሆን ኖሮ ኃጢአት በሆነ ነበር።  ጥያቄ፡- ሀ) በራሳችሁ እንድትታመኑ የሚጋብዙአችሁ አንዳንድ ቀላል ነገሮች ምንድን ናቸው? ለ) ለእነዚያ ነገሮች እግዚአብሔር እንድትታመኑበት የሚፈልግባችሁ እንዴት ነው?  አንዳንድ ጊዜ ቀላል ለሆኑ ነገሮች በራሳችን የመታመን ፈተ ያጋጥመናል። በቂ ምግብ በቤታችን ውስጥ በሚኖረን ጊዜ ለዕለት ምግባች በእግዚአብሔር መተማመን እንዳለብን ረስተን፥ በራሳችን መታመ’ እንጀምራለን። ሥራ አግኝተን ደመወዛችን ከፍ ያለ ሆኖ የምንፈልገው ሁሉ ስንገዛ ይህንን በሰጠን አምላክ መተማመን ትተን በራሳችን መታመ እንጀምራለን። የሚወዱን ወዳጆችና ቤተሰብ ሲኖሩን እግዚአብሔር ማመስገን ትተን በራሳችን መታመን እንቀጥላለን፥ እንደዚሁም ጤናማዎች ጠንካሮች በምንሆንበት ጊዜ ይህን በአደረገልን አምላክ መተማመን ትተን ክብሩን ለራሳችን እንሰጣለን። እግዚአብሔር ግን ይህን ሁሉ የለገሰን እርሰ መሆኑን እንድናስታውስ ይፈልጋል፥ እናም እነዚያን ጥቃቅን የሆነ ፍላጎቶቻችንን ለወደፊቱም ቢሆን እንዲያሟላልን በእርሱ መታመ’ አለብን።  ኢየሱስ ከቤተ መቅደስ ጫፍ ራሱን ወደ

ኃጢአት አልባው የኢየሱስ ሰብአዊነት  Read More »

የኢየሱስ ሰብአዊ ስሜቶች 

This entry is part 17 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ አንዱና አስደናቂው ነገር ፍጹም ሰው በመሆኑ ሁሉም ሰብአዊ ስሜቶች ነበሩት። አብዛኛዎቹ አማኞች ስለ ኢየሱስ ስሜቶች መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ሁሉ ልብ አይሉትም። ስለ ኢየሱስ ስሜታዊ ሕይወት ማጥናት ያለብን ለምንድን ነው? በመጀመሪያ፥ ኢየሱስን ይሰሙት የነበሩትን ልዩ ልዩ ስሜቶችን ማጥናት እውነተኛውን ሰብአዊነቱን በጥልቀት ተገንዝበን እንድናመሰግነው ይረዳናል። እርሱ እንደ እኛው ሙሉ በሙሉ ሰብአዊነት ከሰብአዊ ስሜቶች ጋር ነበሩት። ሁለተኛ፥ የኢየሱስን ስሜታዊ ሕይወት ማጥናት የእኛ ስሜታዊ ሕይወት እንዴት መሆን እንደሚገባው ለመገንዘብ ይረዳናል። ኢየሱስ ፍጹም ሰው ሆኖ የኖረ ብቸኛው ሰው ነበር። የእርሱ ስሜቶች እንዴት እንደነበረ ተገንዝበን ቢሆን ኖሮ፥ የእኛ ስሜታዊ ሕይወት እንዴት መሆን እንዳለበት መረዳት እንችል ነበር። ስለዚህ በሕይወታችን ልክ እንደ ኢየሱስ መሆን ከፈለግን እና በሕይወታችን እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት ካለብን፥ ኢየሱስ የነበረውን ፍጹማዊ ስሜት እንዲኖረን መጣር አለብን።  ምሕረት  ጥያቄ- ማቴዎስ 9:6፤ 5፡32፤ 20።4፤ ማርቆስ 1፡4፤ ሉቃስ 7፡13 አንብቡ። ኢየሱስ ዕለራራላቸው ሰዎችና ለለነበሩት ሁኔታ ዝርዝር ጻፉ። የእያንዳንዳቸውን ችግር ለማሟላት ኢየሱስ ምን እንዳደረገ ልምራችሁ በዝርዝሩ ውስጥ ያዙ።  መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ስለተሰማው ስሜት ብዙ ጊዜ የሚነግረን ምሕረቱንና ርኅራኄውን ነው። ስለ ኢየሱስ ምሕረትና ርኅራኄ የሚገልጹ ቃላት የሚያመለክቱት ለሰዎች ውጫዊ (አካላዊ) ችግር ውጤት አዘል ውስጣዊ የአዘኔታና ጥልቅ የኃላፊነት ስሜትን ነው። ኢየሱስ የሰዎችን ሥጋዊና መንፈሳዊ ችግር በተመለከተ ጊዜ፥ የተሰማው ይኸው ነበር። በማቴዎስ 9፡36 ላይ የሰዎችን አጠቃላይ የማኅበራዊ ሁኔታ በተመለከተ ጊዜ ራራ። የተመለከታቸውም ሰዎች ለሥጋዊ ሕይወታቸው የሚፈልጉት ነገር ነበረ፤ በየአካባቢአቸው በሚገኙ ሌሎች ሰዎች ተጨቁነዋል፥ በመንፈሳዊ ነገር ጠፍተዋል፥ እንደዚሁም የሚረዳቸውና የሚንከባከቧቸው መሪዎች አልነበሯቸውም።  እርሱም ይህን እንደ ተመለከተ ለሕዝቡ ችግርና ፍላጎት እገዛ የሚያደርጉ ሰዎችን እግዚአብሔር ይልክ ዘንድ፥ ደቀ መዛሙርቱ እንዲጸልዩ አላሰባቸው። ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ሕዝቡን እንዲያገለግሉ ላካቸው። በማቴዎስ 5፡32 ከሩቅ ስፍራ መጥተው ቃሉን ሲሰሙ ለነበሩና ተርበው ለነበሩ ሰዎች መራራቱን ይነግረናል። እርሱም ያንን ሁሉ ሕዝብ መገበ። እንደዚሁም በማቴዎስ 20፡34 ውስጥ ሁለት ዓይነ ሥውራን ጌታ እንዲፈውሳቸው በሁ ጊዜ፥ እንደ ራራላቸው ተጽፎአል። እርሱም በርኅራኄው ፈውሷቸዋል። በእነዚህ ሁኔታዎች ሁሉ የምንገነዘው ኢየሱስ ስለ እነርሱ ተሰምቶት ፍላጎታቸውን ለሟሟላት እንደ ችግራቸው ሁኔታ እንደ ረዳቸው ነው። በማርቆስ 1፡4ህ ላይ አንድ ለምፃም ሰው ኢየሱስ እንዲፈውሰው ለመነው። ኢየሱስም ራራለትና ፈወሰው። በመጨረሻም በሉቃስ 7፡13 አንድ ልጇ ለሞተባት መበለት መራራቱ ተጽፎአል። ጌታም ራርቶ የሞተውን ልጅዋን አስነሥቶላታል።  ጥያቄ፡- ሀ) በጎረቤቶቻችሁና በከተሞቻችሁ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ችግር ምንድን ነው? በአጭሩ ሦስት መሠረታዊ ችግሮቻቸውን ጻፉ። ለ) ስለ እነርሱ ምን ይሰማችኋል? ሐ) በ ጻፋችኋቸው ችግሮች በእያንዳንዳቸው አቅጣጫ እናንተ ልትረዷቸው የምትችሉባቸውን ሁለት ሁለት መንገዶች ጻፉ።  በአካባቢአችን ስላሉ ሰዎች ችግርም ሆነ ፍላጎት ቀዝቃዛ ስሜት ይኖረን ይሆናል። ለምሳሌም ያህል፥ ብዙ ጊዜ ድሆችን፥ በሽተኞችን አካላቸው የጎደለ ሰዎችን ወይም የሚወዷቸውን ዘመዶቻቸውን በሞት ያጡ ሰዎችን እንደዚሁም በራሳቸው ኅብረተሰብ የተጨቆኑ ሰዎችን እንመለከት ይሆናል። የእነዚህን ሰዎች ችግር ሁልጊዜ ማየታችን አንዳንድ ጊዜ ለእነርሱ የሚኖረንን ርኅራኄ ያጠፋዋል። ኢየሱስ ግን በዚህ ሁኔታ የተቸገሩትን ሰዎች እንደየችግራቸው ለይቶ በመቀበል በጥልቅ ምሕረትና ርኅራኄ ተመልክቶአቸዋል። ለችግሮቻቸውም መፍትሄውን ሰጥቶአቸዋል። የኢየሱስም ደቀ መዛሙርት ልክ እንደ እርሱ ለመኖር በመፈለግ ችግረኞችን ሰሚመለከቱበት ጊዜ ርኅራኄ ሳይርቃቸው ለችግሮቻቸው መፍትሄ በመስጠት የእርሱን ዱካ መከተል ይገባቸዋል።  ፍቅር  ጥያቄ፡- ዮሐንስ 3፡1 እና ማርቆስ 10፡21 አንብቡ። ሀ) በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እንደተጻፈው ኢየሱስ ምን ዓይነት ስሜት ነበር ያላየው? ለ) የእያንዳንዳቸው ፍላጎት ምን ነበር? ሐ) ኢየሱስ ለፍላጎታቸው እንዴት ያለ መፍትሄዎችን ለጠ?  ከኢየሱስ የርኅራኄ ስሜት ጋር የቅርብ ትስስር ያለው የፍቅር ስሜቱ ነው። ከርኅራኄው ለየት ባለ መልኩ የኢየሱስ የፍቅር ስሜት የሚገለጸው አሳሳቢ ችግር ላልነበረባቸው ሰዎች ነበር። ለምሳሌም ያህል፥ በማርቆስ 10፡21 ኢየሱስ ያንን ወጣት እንደ ወደደው ይገልጻል። ይህ ወጣት ሕይወቱ ፍጹም እንደሆነ ያስብ ነበር። ማርቆስ 10፡22 ይህ ሰው ሀብታም እንደ ነበረ ያስረዳል። ሉቃስ 18፡18 ደግሞ ወጣቱ ገዢ እንደነበርና አንድ ዓይነት ሥልጣን እንደ ነበረው ያወሳል። ማቴዎስ 19፡20 ደግሞ ወጣት እንደ ነበረ ይናገራል። ታዲያ ይህ ወጣት የብሉይ ኪዳን ሕጎችን ሁሉ የጠበቀ ይመስለው ነበር (ማርቆስ 10፡20)፡፡ ይህ ሰው በዓለም ምርጥ የተባለ ነገር ሁሉ የነበረውና ታዋቂ ሰው ነበር። ሀብት፥ ሥልጣን፥ ጉብዝና ያለውና የሞራል ሕይወቱም ጥሩ የሆነ ነበር። ይህ ሰው የሚቸግረው ነገር አልነበረም። ነገር ግን ኢየሱስ በእርግጥ ምን እንደሚያስፈልገው ደህና አድርጎ ያውቅ ነበር። ያም በነበረው ሁሉ ማለትም ባሀብት፥ በሥልጣን፥ በወጣትነት አቋምና በተሟላ ኑሮ መታበዩን ትቶ ራሱን አሳልፎ ለኢየሱስ እንክብካቤ እንዲሰጥና በእርሱ እንዲታመን ነበር። ሰውዬው ምን እንደሚያስፈልገው ባያስተውልም፥ ኢየሱስ ግን ምን እንደሚያስፈልገው አውቆአል። እናም ወደደው። በተመሳሳይ ሁኔታ በዮሐንስ 13፡1 ላይ እንደተጻፈው ከጌታ ራት ቀደም ብሎ ደቀ መዛሙርቱ ለእርስ በርሳቸው አገልጋዮች መሆን እጅግ እንደሚያስፈልጋቸው አልተገነዘቡም ነበር። ስለ ሥልጣናቸው አስፈላጊነትና ማን ከማን እንደሚበልጥ ይከራከሩ ነበር (ሉቃስ 22፡24)። ፍላጎታቸውን ስለማያውቁ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች አይመስሉም ነበር፥ እነርሱ ባያዩም ኢየሱስ ፍላጎታቸውን አይቶ ነበር። እናም ወደዳቸው።  ርኅራኄን በተመለከተ እንዳደረገው ሁሉ ኢየሱስ ፍቅር በተሰማው ወቅት ወዲያው ያላሰበውን ይፈጽም ነበር። ፍላጎታቸውን ለማሟላት አስፈላጊውን አድርጓል። ያ ሀብታም ጎበዝ በራሱና በሀብቱ ላይ የነበረውን ትምክህት በመረዳቱ ሊገዳደረው እንደሚገባ ያውቃል። ስለዚህ ሀብቱን ሁሉ ትቶ፥ በእርሱ እንዲታመንና ለዕለት ምግቡም እርሱን ተስፋ እንዲያደርግ አላሰበው። ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አገልጋይነት ውስጥ ፍቅሩን አይተው ከግለኝነት በመላቀቅ በእርስ በርስ ፍቅር አንዱ ሌላውን እንዲያገለግል አሳስቦአቸዋል።  ጥያቄ፡- ሀ) የተለየ ችግር ወይም ፍላጎት ያላቸው ስለማይመስሏችሁ አንዳንድ ሰዎች አስቡና የሁለት ወይም የሦስት ሰዎችን ስም በማስታወሻ ደብተርቻችሁ ላይ ጻፉ። ለ) እነዚህ ሰዎች ምን እውነተኛ ፍላጎቶች አሏቸው? ሐ) እነዚህን ችግሮች ቀርባችሁ በማቃለልና መፍትሄ በመስጠት የክርስቶስ ምሳሌነታችሁንና ፍቅራችሁን እንዴት ትገልጻላችሁ?  አንዳንድ ጊዜ የምናውቃቸው ሰዎች ራሳቸውን በጣም ከፍ አድርገው ስለሚመለከቱ፥ የሚጎድላቸው ነገር መኖሩ አይከሰትላቸውም። እንዲህ ያሉት ሰዎች ኃጢአታቸው በበጎ ሥራቸው ይቅር ሊባል እንደማይችል ያልተገነዘቡ በጣም ሃይማኖተኛች ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ኢየሱስ ብቻ ሊያድናቸው እንደሚችል ያላስተዋሉ ሊሆኑ ይችላሉ። የሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ የተሟላላቸው በጣም ሀብታም ሰዎችም ይሆኑ ይሆናል። ያላቸው ቁሳዊ ንብረታቸው ደስታ እንደማይሰጣቸው አይረዱም። ወይም ጤነኞችና ጠንካራ ሰዎች ጤናማ የሆኑ ቤተሰቦች ያሏቸው ሆነው፥ ይህ ሙሉ ጤንነት ድንገት ቶሉ እንደሚከዳ ላያስተውሉ ይችላሉ። እነዚህን ሰዎች ልንወዳቸውና ወዳጆቻችን ልናደርጋቸው ይገባናል። እግዚአብሔር ዕድል በሚሰጠን ጊዘ ክርስቶስ ለእነዚህ ሰዎች ሊያደርግላቸው ስለሚችለው ነገርና በምን ረገድ እንደሚያስፈልጋቸው አብረናቸው ልንወያይ ደግሞም የችግራቸው ተካፋይ ልንሆን ይገባናል።  ቁጣ  ጥያቄ፡ ማርቆስ 3፡51 10፡14፤ ዮሐንስ 11፡33፥ 38 አንብቡ። ሀ) በእነዚህ ክፍለ ምንባቦች ውስጥ ኢየሱስን የተሰማው ስሜት ምን ነበር? ላ) ኢየሱስን ይህ ስሜት እንዲሰማው ያደረጉ ሁኔታዎች ምን ነበሩ? ስለ እያንዳንዱ ሁኔታ ጻፉ።  ኢየሱስ በአንዳንድ ሁኔታ ይቆጣና ይገሥጽ እንደነበረ ሰዎች በሚሰሙበት ጊዜ ይገረማሉ። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ቁጣ ኃጢአት ነው (ኤፌሶን 4፡30) ነገር ግን ኃጢአት ያልሆነ የጽድቅ ቁጣ መኖሩ ግልጽ ሊሆን ይገባል (ኤፌሶን 4፡26)። ኢየሱስን ይሰማው የነበረው ይህን የመሰለ የጽድቅ ቁጣ ነበር። ኢየሱስ ይቆጣ የነበረው መች ነበር? በማርቆስ 10፡14 ውስጥ እንደተጻፈው ደቀ መዛሙርቱ ሕፃናት ወደ እርሱ እንዳይመጡ በከለከሏቸው ጊዜ ኢየሱስ ተቆጥቷል። በማርቆስ 3፡5 ውስጥ ደግሞ የሃይማኖት መሪዎች እጁ ከሰለለው ሰው ፈውስ ይልቅ የሰንበትን ቀን ስለመጠበቅ ሕጋቸው ትርጉም ትኩረት በመስጠታቸው ኢየሱስ ተቆጥቷል። በተለይ የሃይማኖታቸውን ሁኔታ ከፍ ለማድረግ በእግዚአብሔር ቃል አላግባብ በመጠቀማቸው ተቆጥቷል። ስለ ሥልጣናቸው ያስቡ ስለነበር ስለ ሌሎች ሰዎች ጥቅም ግድም አልነበራቸው። በኩራታቸው የእግዚአብሔርን ቃል አላግባብ በመጠቀማቸውና ስለ ሌሎች ሰዎች አለማሰባቸው ኢየሱስን አስቆጥቶታል።  ጥያቄ፡- ሀ) ወደ ኢየሱስ በሚመጡ ሰዎች ላይ ስር የሚዘጋ ሰው መቼ ነው ያያችሁት? እንዲህ ያለውን ሁኔታ ስታዩ ምን ተሰማችሁ? ለ) እናንተም ራሳችሁ ብትሆኑ ወደ ኢየሱስ በሚመጡ ሰዎች

የኢየሱስ ሰብአዊ ስሜቶች  Read More »

ኢየሱስ ፍጹም ሰው መሆኑን እንዴት እናውቃለን? 

This entry is part 16 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

2.1 ኢየሱስ ሰብአዊ አካል ነበረው።  ኢየሱስ ፍጹም ሰው እንደነበረ እንዴት ልናውቅ እንችላለን? በመጀመሪያ፥ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን ኢየሱስ ሰብአዊ አካል ነበረው።  ጥያቄ፡- ዮሐንስ 1፡1 አንብቡ። ኢየሱስ ሰው ለመሆኑ ዮሐንስ ምን ማረጋገጥ ይሰጠናል።  ዮሐንስ በመጀመሪያው መልእክቱ በቁሳዊ ዓለም ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ነገር ክፉ ነው ብለው ያስተምሩ የነበሩትን ሐሰተኛ ሰዎች እየተቃወመ ነበር። ይህን የሐሰት ትምህርት ያስተምሩ የነበሩ ሰዎች በቁሳዊ ዓለም ውስጥ የሚገኝ ሁሉ ክፉ ነው ብለው ያምኑ ስለነበርና ኢየሱስም ፍጹም ስለነበር እውነተኛ ሰብአዊ አካል አልነበረውም ብለው ያምኑ ነበር። እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ኢየሱስ የነበረው ሰብአዊ አካል የመሰለ እንጂ እውነተኛው የሰው አካል አልነበረም ይሉ ነበር። ነገር ግን ሐዋርያው ዮሐንስ ለአንባቢያኑ እንደሚያስረዳው ከሆነ፡ የኢየሱስ አካል እውነተኛው የሰው አካል እንደነበረ ነው። እርሱም አይቶታል፤ ደግሞም ዳስሶታል። የኢየሱስ አካል እንደ ማንኛውም የሰው አካል እውነተኛ ነው ሲል ያረጋግጣል።  ጥያቄ፡- ሉቃስ 2፡1-7 ድረስ እንብቡ። ኢየሱስ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም | እንዴት ባለ አኳኋን ተገለጠ?  የኢየሱስን ሰብአዊነት ከሚያጎሉት ነገሮች ዋነኛው ልደቱ ነበር። በዓለም ላይ እንደ አንድ ጎልማሳ ሰው ሆኖ አልተገለጠም። ማንኛውም ሰው በሚወለድበት አኳኋን ተወለደ። በእርግጥ የኢየሱስ ልደት በዓለም ከታየው ልደት ሁሉ ዝቅ ባለና በተዋረደ ስፍራ ውስጥ ነበር። በሴት ወይም በሆስፒታል ውስጥ በመወለድ ፈንታ፥ በእንስሳት ማደሪያ ግርግም ውስጥ ተወለደ። ወንጌላዊው ሉቃስ ስለ ኢየሱስ ልደት ሰፋ አድርጎ በዝርዝር ባይጽፍም፥ «የመውለጃዋ ወራት ደረሰ» ብሎ ሊል፥ ይህ አባባሉ ማርያም ስትወልድ የሚሰማት የምጥ ስሜት የተለመደው ዓይነት እንደሆነና እንደ ማንኛውም ወላድ አምጣ እንደ ወለደች መናገሩ ነው። በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ በኢየሱስ ልደት ዙሪያ ስለታዩት ታምራቶች እንወያያለን። የእርሱ ልደት ልዩ መሆኑ ግልጽ ነው። ነገር ግን ደግሞ ፍጹም ሰብአዊም ነው።  ጥያቄ፡- ሉቃስ 2፡52 አንብቡ። ኢየሱስ እያደገ ሲመጣ በአካሉ ላይ ምን ተከሰተ?  ወንጌል ስለ ኢየሱስ ልጅነት ሁኔታ ብዙም አይነግረንም። ስለ ልደቱና ዕድሜው አሥራ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ ወደ ቤተ መቅደስ ስለ መሄዱ ከሚናገረው ሌላ፥ ስለ ኢየሱስ የልጅነት ጊዜ የሚያወሳው ይሄኛው ጥቅስ ብቻ ነው። በዚህ ሳምንት ወደዚህ ጥቅስ ደጋግመን በመመለስ እናጠናዋለን። ለዛሬው፥ «ኢየሱስ በቁመት ያድግ ነበር።» የሚለውን አስተውሉ። እንዲህ ማለት የኢየሱስ አካል ከሌላው ሰው ባልተለየ አኳኋን የእድገት ሂደቱን ጠብቆ ያድግ ነበር ማለት ነው። የኢየሱስ አካል እንደ ማንኛውም ሰው አካል ደረጃ ውን ጠብቆ ያድግ ነበር።  ጥያቄ፡- ማቴዎስ 4፡2፤ ዮሐንስ 4፡6-7፤ ዮሐንስ 19፡28 እና ዮሐንስ 19፡34 አንብቡ። የኢየሱስ አካል የየትኛቹ ሰብአዊ ድካሞች ተሞክር ነበረው?  የኢየሱስን አካል ያጋጠመው ድካም ልክ እኛንም የሚያጋጥመን ወይም የሚሰማን ድካም ዓይነት ነው። ኢየሱስ ለተወሰነ ጊዜ ሳይበላ ቢቆይ ይርበው ነበር። ለተወሰነ ጊዜ ውኃ ሳይጠጣ ሲቆይ ይጠማው ነበር። እንደዚሁም ለብዙ ሰዓታት በእግሩ ሲሄድ ይደክመው ነበር። እንዲሁም ሰውነቱ ከተመታ፥ ከተወጋና በመስቀል ላይ በምስማር የተቸነከረ በኋላ ሞተ። ልክ ማንኛውም ሰው ሲሞት እንደሚሆነው ሁሉ ኢየሱስም በሞተ ጊዜ የልቡ ምት ቆመ፤ ሳምባውም መተንፈሱን ተወ። እነዚህ ሰብአዊ ድካሞች በኢየሱስ ዓይነ ሕሊና የታዩ ስሜቶች አይደሉም። ከላይ የተጠቀሱት ጥቅሶች በግልጽ እንደሚያስረዱት እነዚህ ሰብአዊ ፍላጎቶች እንደ ማንኛውም ሰው እርሱንም እስፈልገውታል። ኢየሱስ ልክ እንደ እኛው አካል ነበረው።  2.2 ኢየሱስ ሰብአዊ ነፍስና ሰብአዊ መንፈስ ነበረው።  ኢየሱስ ሰብአዊ አካል ብቻ አልነበረውም፤ ሰብአዊ ነፍስና መንፈስም ነበረው። ባለፈው ሳምንት ለመመልከት እንደሞከርነው ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሔር ቢሆንም እንኳ፥ እንደ ሰው ከእግዚአብሔርና ከሌሎች ሰዎች ጋር ግንኙነት ነበረው። ኢየሱስ እንደ ማንኛውም ሰው ማኅበራዊና መንፈሳዊ ሕይወት ነበረው።  ጥያቄ፡- ሀ) ማቴዎስ 26፡38 አንብቡ። ሀ) ኢየሱስ እስከ ሞት ድረስ ያሳዘነኝ ምንድን ነው አለ? ለ) ሉቃስ 23፡46 አንብቡ። ኢየሱስ በአባቱ እጅ ያስረከበው ምንድን ነው?  አንዳንድ ሰዎች ኢየሱስ በውስጥ እግዚአብሔር እንደሆነና በውጭ ሰው እንደ ሆነ አድርገው ይገምታሉ። ነገር ግን ኢየሱስ ከሰብአዊ አካል የበለጠ ነገርም ነበረው። ይኸውም ሰብአዊ ነፍስና መንፈስ ነበረው። ያለጥርጥር ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔር ነበር። ነገር ግን ሰብአዊ ሥነልቡናና ስሜቶችም ነበሩት። ሰዎች ሁሉ እንደሚያደርጉት እርሱም ከሰዎች ጋር ግንኙነት ነበረው። ልክ ሰዎች እንደሚያደርጉት ዓይነት ግንኙነት እርሱም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረው። በማቴዎስ 26፡38 ላይ ኢየሱስ ነፍሱ በጣም መጨነቋን ይገልጻል። ነገ ስለ ኢየሱስ ስሜቶች ሰፋ አድርገን እናጠናለን። ለዛሬው ኢየሱስ ሰብአዊ ነፍስ አለኝ ማለቱን አስተውሉ። በሉቃስ 23፡46 ውስጥ ሊሞት ሲል ነፍሱን አሳልፎ ለእግዚአብሔር አብ ስለማስረከቡ ይናገራል። ኢየሱስ ሲሞት ለእግዚአብሔር አብ ያስረከበው ሰብአዊ ነፍስ ነበረው። የኢየሱስ ሰብአዊነት በውጫዊው አካል ብቻ አልነበረም። በውስጣዊውም ሰብአዊ ነበር።  ጥያቄ፡- ሉቃስ 252 እንደገና አንብቡ። ኢየሱስ ያደገው በቁመት ብቻ አልነበረም። ከዚህ ሌላ በምን መንገድ ያድግ ነበር? ኢየሱስ ከማን ፊት በሞገስ አደገ?  ጥያቄ፡- ሀ) ማርቆስ 9፡21 አንብቡ። ኢየሱስ በምን ምክንያት ይህን ጥያቄ ጠየቀ? ለ) ማርቆስ 13።2 አንብቡ። ኢየሱስ ራሱ አላውቅም ያለው ምንን ነበር?  ጥያቄ፡- ሉቃስ 4፡16 እና ሉቃስ 6፡12 እንብቡ። ኢየሱስ ከእግዚአብሔር አብ ጋር የነበረውን አንድነት ለማጠንከር ምን አደረገ?  ሉቃስ 2፡52 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እጅግ በጣም አስደናቂ ከሆኑት ጥቅሶች ውስጥ አንዱ ነው። በዚህ ሕይወት እያለን ሙሉ በሙሉ የማንገነዘበው ጥቅስ ነው። ኢየሱስ በቁመት እንዴት ያድግ እንደነበረ መመልከት ቀላል ነው። እንደ ሕፃን ተወልዶ ኋላም እካሉ ስለማደጉ መረዳት አይከብደንም። ነገር ግን ይህ ጥቅስ ከኢየሱስ አካላዊ እድገት ስለሚበልጥ ነገር ይናገራል። እርሱ «በጥበብም» ያድግ ነበር ይላል። ባለፈው ሳምንት እንደተመለከትነው፥ ኢየሱስ እንደ እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል። ሆኖም ኢየሱስ እንደ ሰው በጥበብ እያደገ ልዩ ልዩ እውቀቶችን ይቀስም ነበር። ወላጆችና መምህራን ልጆችን በጊዜያቸው እንደሚያስተምሩ ሁሉ፥ ወላጆቹና መምህራኑ ኢየሱስን አስተማሩት። አንዳንድ የማያውቃቸውን ነገሮች ተማረ። በማርቆስ 13፡32 በምድር ላይ ሳለ የሚመለስበትን ጊዜ እንደማያውቅ ተናግሮአል። አብ ብቻ ያውቃል። እንደ እግዚአብሔር ኢየሱስ በእርግጥ የሚመላስበትን ጊዜ ያውቅ ነበር። ነገር ግን እንደ ሰው እርሱ ራሱ ያንን ጊዜ አያውቅም። በማርቆስ 9፡21 ላይ እንደ ሰው መረጃ ለማግኘት ይጠይቃል። ልጁ በአጋንንት ከተያዘ ምን ያህል ጊዜው እንደሆነ ለማወቅ አባትዬውን ጠይቋል። እንደ እግዚአብሔርነቱ ያ ልጅ በአጋንንት መቼ እንደ ተያዘ በእርግጥ ያውቃል። እንደ ሰው ግን መረጃ ለማግኘት ጥያቄ የሚያቀርብ ይመስላል። በሚመጡት ሳምንታት፥ ኢየሱስ በአንድ ጊዜ ሙሉ በሙሉ እንዴት እግዚአብሔር፥ እንዲሁም እንዴት ሰው እንደሚሆን በቅርብ እንመረምራለን። ይህ አንዳንድ ጊዜ «የተሠግዎ (ሥጋ የመልበስ) ምሥጢር» ተብሎ ይጠራል። ለዛሬው ኢየሱስ ያለ ኃጢአት ከመሆኑ በስተቀር፥ ልክ እንደ እኛው ሰው እንደ ነበረ እንመለከታለን። በጥበብም እንኳ አድጓል።  ሉቃስ 2፡52 ኢየሱስ በጥበብና በቁመት ብቻ ያድግ ነበር አላለም፤ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት በሞገስ ያድግ ነበር የሚል ጨምሮበታል። ኢየሱስ ከሌሎችም ጋር በነበረው ግንኙነት አደገ። ወዳጆችንም አፍርቶ ነበር። ማኅበራዊ ግንኙነትንም አዳብሯል። ከሰዎች ጋር የነበረውን ግንኙነት እያዳበረ በሄደ ቁጥር ሰዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በይበልጥ ይወዱት ጀመር። ነገር ግን ኢየሱስ ከሰዎች ጋር በነበረው ግንኙነት ማደጉ ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን ግንኙነትም እያዳበረ አድጓል። ይህ ለመቀበልም ሆነ ለመገንዘብ አስቸጋሪው የኢየሱስ ስብእና ገጽታ ነው። ኢየሱስ እንደ እግዚአብሔርነቱ ከእግዚአብሔር አብ ጋር ባለው ግንኙነት እንዴት ሊያድግ ይችላል? እንደምታስታውሱት ኢየሱስ ኃጢአትን አላደረገም፣ ስለዚህ ከኃጢአተኝነት ወደ ታዛዥነት ለማደግ አይችልም። እርሱ እንደ ሰው ሕይወቱን የጀመረው ከእግዚአብሔር ጋር በቅርበት ሆኖ ነው። በመላ የሕይወት ዘመኑም በበለጠ ቅርበትን መሥርቷል። በሉቃስ 4፡16 እና በሉቃስ 6፡12 ውስጥ ኢየሱስ እግዚአብሔር አብን ማምለኩንና ወደ እርሱም መጸለዩን እናውቃለን። ምንም እንኳን እርሱ ራሱ እግዚአብሔር ቢሆንም፥ እንደ ሰው በጸሎት ከእግዚአብሔር አብ ጋር ይነጋገር ነበር። እንደ ሰውም ከእግዚአብሔር ጋር ቅርበት ኖሮት አደገ። በእግዚአብሔር ፊትም ተወዳጅ ሆኖ አደገ።  ኢየሱስ ክርስቶስ ሙሉ በሙሉ ሰው ነበር። የሰው አካልም ነበረው። የሰው ነፍስና መንፈስ ነበረው። ከሰዎች ጋርም መልካም የማኅበራዊ ግንኙነት ነበረው። እንደዚሁም ሰብአዊ አእምሮና

ኢየሱስ ፍጹም ሰው መሆኑን እንዴት እናውቃለን?  Read More »