ሰዎች የክርስቶስን መልእክት ሳይሰሙ ሊድኑ ይችላሉ?
እንግዲህ ዛሬ ስለ ደኅንነት ከሚነሡ ከባድ ከሆኑ ጥያቄዎች አንዱን ለመመለስ እንሞክራለን። ስለ ክርስቶስ ስፍጹም ሰምተው የማያውቁ አንዳንድ ሰዎች በእግዚአብሔር በማመናቸው ይድናሉ? ከአንድ መቶ ዓመት በፊት አካባቢ፥ በደቡብ ኢትዮጵያ ኢሳ የተባለ ነቢይ ተነሥቶ ነበር። ይህ ነቢይ በሕይወቱ ዘመን በአብዛኛው በኢትዮጵያ ደቡባዊው ክፍል እየተዘዋወረ፥ ሰዎች ለርኩስ መናፍስት መስገዳቸውን ትተው አንዱን በሰማይ የሚኖር እውነተኛ አምላክ እንዲያመልኩ ያስተምራቸውና ያሳስባቸው ነበር። እስከምናውቀው ድረስ፣ ኢሳ የክርስቲያኖችን ወንጌል ጨርሶ አልሰማም ነበር። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውም አምላክም ሆኖ ወደዚህ ዓለም በመምጣት የንጽሕና ሕይወትን በመኖር የመሥዋዕትነትን ሞት እንደ ሞተ በፍጹም አልሰማም። እንዲሁም ከኃጢአቱ ለመዳን ሲል በክርስቶስ የማመን ዕድልም አላገኘም። ሆኖም ግን ኢሳ የሰማይ አምላክ የሆነውን አንዱን እግዚአብሔርን የማምለክ ዝንባሌ ይታይበት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ኢሳን ስለ መሰሉ ሰዎች የሚናገረው ነገር አለው? እግዚአብሔር እንደ ኢሳ ያለ፥ በእርሱ የሚያምን፥ ግን የክርስቶስን መልእክት ለመስማት ዕድል ያላገኘን ሰው ያድን ይሆን? እግዚአብሔር በክርስቶስ ሞት የተገኘው ትሩፋት፥ እንደ ኢሳ ያሉ ስለ ክርስቶስ ጨርሰው ያልሰሙ ወይም በእርሱ ያላመኑ ሰዎች እንዲድኑበት ያደርግ ይሆን? 1. የአዲስ ኪዳን አጠቃላይ ዓላማ ሰዎች የክርስቶስን መልእክት ሰምተው፥ ደኅንነቱን ስለ መቀበላቸው በእምነታቸው አማካይነት እንዲያስታውቁ ነው። ጥያቄ፡- ዮሐ 14፡6 አንብብ። ወደ አብ የሚያደርሰው ብቸኛው መንገድ ማን ነው? ጥያቄ፡- የሐዋ. ሥራ 4፡12 አንብብ። ሰዎች በማን ስም ብቻ ይድናሉ? ጥያቄ፡- ሮሜ 1፡18-23 አንብብ። ሀ) ሰዎች ሁሉ ለለ እግዚአብሔር ምን ያውቃሉ? (ቁጥር 20) ለ) ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ባላቸው በዚህ እውቀት ምን ያደርጋሉ? (ቁጥር 18፣ 21-23) ጥያቄ፡- ሮሜ 10፡13-14 እንብብ። ሀ) የሚድነው ማን ነው? (ቁጥር 13) ለ) ሰዎች የጌታን ስም መጥራት እንዲችሉ ምን ያስፈልጋቸዋል? (ቁጥር 14) አዲስ ኪዳን በግልጽ እንደሚናገረው፥ የደኅንነት አጠቃላይ ዓላማ፥ የክርስቶስን መልእክት ማድመጥና የሰሙትንም በእምነት መግለጥ ነው። በዮሐንስ 14፡6 ውስጥ ኢየሱስ ራሱ፥ ማንም ቢሆን በእርሱ በኩል ካልሆነ ወደ አብ ሊመጣ እንደማይችል ተናግሮአል። ብዙ ምንባቦችን ከጻፈ በኋላ ሰዎች መዳን ከፈለጉ እምነታቸውን በኢየሱስ ላይ ማድረግ እንዳለባቸው ዮሐንስ ጽፎአል (ምሳሌዎቹ፡- ዮሐንስ 1፡12፤ 3፡15፤ 16፣ 36)። በግልጽ እንደሚታየው፥ ኢየሱስ የተናገረው፥ ወደ አብ ለመድረስ የሚቻለው በእርሱ በማመን ብቻ መሆኑን ነው። ቀደም ባሉት የሐዋርያት ሥራ ምዕራፎች እንደተጻፈው፥ ሐዋርያት በኢየሱስ አማካይነት ስለሚገኘው ደኅንነት ስለ ሰበኩ፥ የአይሁድ መሪዎች ተቆጥተው ነበር። ልክ እንደ ሐዋርያት፥ እነዚህ የአይሁድ መሪዎችም በእስራኤል አንድ አምላከ ያምኑ ነበር። እንዲሁም መዳን የሚገኘው በእርሱ መሆኑን ያወቁ ነበር። ነገር ግን በሐዋርያት ሥራ 4፡10-12 ውስጥ፥ ጴጥሮስ አንዱንና የደኅንነት መንገድ እርሱ ብቻ የሆነውን ክርስቶስን አለመቀበላቸውን ነገራቸው። ስለሆነም እነዚህ የሃይማኖት መሪዎች ደኅንነትን ለማግኘት በሰማይ የሚኖር አንዱን እውነተኛ አምላክ ማመናቸው ብቻ አይበቃም ነበር። ደኅንነትን ለማግኘት እንዲችሉ በኢየሱስ ማመን ነበረባቸው። ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱም እንደሚያስተምረው፥ በሰማይ ስለሚኖረው አምላክ ማወቅ ብቻ አይበቃም ይላል። ቀጥተኛው የደኅንነት መንገድ ስለ ክርስቶስ የሚታወጀውን ቃል መስማትና የሰሙትን በእምነት መግለጥ ነው። በሮሜ ምዕራፍ 1 ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚለው፥ ሰዎች ሁሉ ስለ ሰማዩ አምላክ የተወሰነ እውቀት አላቸው። ነገር ግን ይህ እውቀት ሊያድናቸው የሚበቃ አይደለም። በሰማይ ስለሚኖረው አምላክ የሚያውቁት «ዘላለማዊ ኃይሉንና አምላክነቱን» ነው (ሮሜ 1፡20) ይላል። ታዲያ ሰዎች በዚህ እውቀት እንዴት ይጠቀሙበታል? «እውነቱን ሸፈኑበት» እግዚአብሔርን በማክበር ፈንታ፥ ፍጥረታትን አመለኩ (ሮሜ 1፡18፥21-23)። በፍጥረታት አማካይነት ስለ እግዚአብሔር ማወቅ ደኅንነትን ለማስገኘት በቂ አይደለም። ብዙ ጊዜ ሰዎች ይህን እግዚአብሔርን የማወቅ ሁኔታ ትተው ፊታቸውን ያዞሩና እግዚአብሔር የፈጠራቸውን ነገሮች ያመልካሉ (ሮሜ 1፡25)፡፡ ጳውሎስ በሮሜ 10፡13-14 እንደሚናገረው፥ ሰዎች መዳን ከፈለጉ የጌታን ስም መጥራት አለባቸው፡፡ ጳውሎስ፥ «የጌታ ስም» በሚልበት ጊዜ፥ በትክክል ስለ ጌታ ኢየሱስ ማሰቡ ነው። (በሮሜ 10፡9 ውስጥ የተጻፈውን ዐውደ ንባብ ተመልከት።) ሰዎች፥ የጌታን ስም ለመጥራት ስለ ክርስቶስ የተነገረውን መልእክት ሰምተው በእምነት ሊገልጡት ይገባል (ሮሜ 10፡14)። የደኅንነት ዓላማ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወትና ሞት የተነገረውን ሰምተው ለደኅንነታቸው በእርሱ ማመን ነው። 2. ሰዎች ሁሉ ስለ ክርስቶስ ሳይሰሙ እንዲድኑ እግዚአብሔር በቂ ፍንጭ ሰጥቶአል? ቢያንስ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ሁለት ጥቅሶች ስለ ክርስቶስ ጨርሶ ያልሰሙና በእርሱ አምነው ደኅንነትን ስላላገኙ ሰዎች እግዚአብሔር የሚለው ፍንጭ እንዳለ ይጠቁማሉ። እነዚህ ጥቅሶች ለእኛ ምን ይሉናል? ጥያቄ፡- ዮሐ 1፡9 አንብብ። ሀ) ጌታ ኢየሱስ ወደ ዓለም በመጣ ጊዜ ለእነማን ብርሃንን ሰጠ? ለ) ዮሐንስ 1:5፥10 አንብብ። ኢየሱስ ግን እንደ ነበረ ሁሉም አውቀው ነበር? ሐ) ዮሐ 1:12 አንብብ። እነማን በእውነት የእግዚአብሔር ልጆች ሆኑ? ጥያቄ፡- የሐዋ. ሥራ 14፡16-17 አንብብ። ባለፉት ዘመናት እግዚአብሔር ለሕዝቦች ሁሉ ምን አደረገላቸው? ዮሐንስ 1፡9 እንደሚናገረው ኢየሱስ ወደ ዓለም በመጣ ጊዜ ለእያንዳንዱ ሰው የሚያበራ ብርሃን ነበር ይላል። ነገር ግን ይህን ክፍል ሲመለከቱት መሠረተ አሳቡ ግልጽ እንደሚያደርገው የኢየሱስ መምጣት ሰዎች ሁሉ ለመዳን እግዚአብሔርን በበቂ ሁኔታ እንዲያውቁ አላደረጋቸውም የሚል ነው። ኢየሱስ የሚያበራው ብርሃን፥ በሰዎች ልቦና ላይ የሚበራ ብርሃን ነው። በልባቸው ውስጥ ያለውን ጨለማ ወደ ብርሃን አውጥቶ ያሳያል ( ዮሐንስ 1፡5)። እርሱ ራሱ እግዚአብሔር ለሰዎች የገለጠው ዋናው መገለጫ ነው። ይህን ብርሃን ያዩ ብዙዎች ግን እንደ ፈጣሪያቸው አድርገው አላወቁትም፥ ደግሞም እግዚአብሔርን የሚገልጥ ብርሃን አድርገው አልተቀበሉትም (ዮሐንስ 15፥10)። ነገር ግን ስለ እርሱ የሰሙት፥ ሰምተውም በእምነት የተቀበሉት የእግዚአብሔር ልጆች ስመሆን ደኅንነትን አገኙ ዮሐንስ 1፡12)። ዮሐንስ 1፡9 እግዚአብሔር፥ ሰዎች ሁሉ ስለ ክርስቶስ ዉርሶ ባይሰሙም፥ ይድኑ ዘንድ በቂ ብርሃን ይሰጣል ብሎ አያስተምርም። ምክንያቱም የጥቅሉ መሠረተ አሳብ፥ ሰዎች የእግዚአብሔር ልጆች ለመሆን ሲፈልጉ፥ አስቀድመው ሊቀበሉት እንደሚገባ በግልጽ ያስተምራል (ዮሐ 1፡12)። በሐዋርያት ሥራ 14፡16-17 ውስጥ እንደተጻፈው፥ እግዚአብሔር ሕዝቦች ሁሉ በገዛ ራሳቸው መንገድ እንዲሄዱ ትቶአቸው ነበር። ይሁን እንጂ እርሱ እንዴት ያለ ቸር አምላክ መሆኑን የሚመሰክር መልካም ሥራ ማድረጉን አልተወም ነበር። ልብ በሉ እነዚህ ጥቅሶች እግዚአብሔር ለሕዝቡ ደኅንነትን ሰጠ አይሉም። በዚህ ፈንታ እነዚህ ጥቅሶች በርሜ ምዕራፍ 1 ውስጥ ካለው ጋር አንድ ዓይነት አሳብ ይናገራሉ። እርሱም እግዚአብሔር ሰዎች ስለ እርሱ የሚያውቁትን እንዳላወቁ ሆነው የራሳቸውን መንገድ ተከትለው ወደ ኃጢአት እንዲሄዱ አድርጎ ነበር። አሁን ግን በክርስቶስ ወደ ደኅንነት ይጠራቸዋል። ምንም እንኳን በመረጡት መንገድ እንዲሄዱ እርሱ ቢተዋቸውም፥ በተፈጥሮ አማካይነት ስለ ቸርነቱ በአጠቃላይ ሁኔታ መግለጡን ቀጠለ። የሐዋርያት ሥራ 14፡16-7 ያለው ክፍል፥ እግዚአብሔር ስለ ክርስቶስ ጨርሰው ያልሰሙ ሰዎችን ያድናል ብሎ አያስተምርም። አንዳንድ ጊዜ ቆርኔሌዎስ ስለ ክርስቶስ ከመስማቱ በፊት በእግዚአብሔር አምኖ የዳነ ሰው ምሳሌ ሆኖ የሚቀርብበት ጊዜ አለ። እግዚአብሔር ቆርኔሌዎስን ስለ ክርስቶስ ከመስማቱ በፊት ነበር ያዳነው? የሐዋርያት ሥራ 10፡2 ቆርኔሌዎስና ቤተሰቡ ሃይማኖተኛችና እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ነበሩ ይላል። ከኢየሱስ የተነገራቸውን መልእክት ከመስማታቸውም በፊት ቢሆን፥ አንዱን እውነተኛ የእስራኤል አምላክን ያመልኩና እርሱንም ለመታዘዝ ይጥሩ ነበር። ቢሆንም፣ ቆርኔሌዎስና ቤተሰቡ የእስራኤል አምላክ አንዱና እውነተኛው አምላክ መሆኑን ተረድተው ሊያመልኩት ይጥሩ የነበሩ አሕዛብ ነበሩ። ነገር ግን የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 10 ቆርኔሌዎስ ለለ ኢየሱስ ከመስማቱ በፊት ጻነ አይልም። ታዲያ እግዚአብሔር እንዲህ ለሚያከብረውና እንዲያድነውም ለሚፈልገው ለቆርኔሌዎስ ምን እደረገለት? ሐዋርያው ጴጥሮስ ሄዶ ስለ ክርስቶስ እንዲሰብክለት ላከው። ቆርኔሌዎስ፥ «በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአት ይቅርታ ያገኛል» (የሐዋ. ሥራ 10፡43) የሚለውን የጴጥሮስ መልእክት እንደ ሰማ፥ እርሱና ቤተሰቡ በኢየሱስ አመኑ፥ መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ። ስለ ኢየሱስ የተናገራቸውን መልእክት ከሰሙ በኋላ ነበር ሙሉ የአዲስ ኪዳን አማኞች በመሆን ሙሉውን የአዲስ ኪዳን ደኅንነትን ያገኙት። ስለዚህ የቆርኔሌዎስ ታሪክ እንደሚያመለክተው፥ በአንድ እውነተኛ አምላክ ለማምለክ የሚፈልጉ ሰዎች ካሉ፥ እግዚአብሔር ስለ ክርስቶስ የሚናገር መልእክት የሚያቀርብላቸው ሰው እንደሚልክላቸው ነው። እግዚአብሔር የእርሱን ደኅንነት ለማግኘት በእርሱ ለማመን የሚፈልጉትን አይኮንናቸውም። 3. ክርስቶስ ለኃጢአት ሲል ለመሞት ከመምጣቱ በፊት ሰዎች ቀድሞ በብሉይ ኪዳን
ሰዎች የክርስቶስን መልእክት ሳይሰሙ ሊድኑ ይችላሉ? Read More »
