የሕይወት እንጀራ አገልግሎት

ስለ እኔ፦ የአገልግሎቱ ራእይና ጥሪ ሰላም ለእናንተ ይሁን! እኔ አዳነው ዲሮ ዳባ እባላለሁ። ወደዚህ ድረ-ገጽ ስለመጡና የ"የሕይወት እንጀራ" ቤተሰብ ስለሆኑ እጅግ ደስ ብሎኛል። ይህ አገልግሎት የተወለደው በሕይወቴ ውስጥ ካለ አንድ ትልቅ እውነት ነው፤ እርሱም "ሰው በእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም" የሚለው መለኮታዊ ቃል ነው። 📖✨ 📜 ጥሪዬና ማንነቴ እግዚአብሔር በጸጋው በሰጠኝ ዘመን ሁሉ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ መምህር፣ ጽሐፊና ተርጓሚ በመሆን ሳገለግል ቆይቻለሁ። ቃሉን መመርመር፣ የተሰወሩ ዕንቁዎችን ማውጣትና ያገኘሁትን መንፈሳዊ ምግብ ለሌሎች ማካፈል የልቤ ትርታ ነው። ✍️ የአገልግሎቴ መሪ ቃል "ኢየሱስ፣ የነፍስ ምግብ" የሚል ሲሆን፣ ዓላማዬም በዕለት ተዕለት ሕይወት ሩጫና ድካም ውስጥ ለሚገኙ ነፍሳት የማይለወጠውንና የማይጠፋውን የክርስቶስን ወንጌል በተለያዩ ትምህርቶች ማድረስ ነው። 🌍 ከየት ወደ የት? በአሁኑ ሰዓት በዩናይትድ ስቴትስ የምኖር ቢሆንም፣ ልቤና ሐሳቤ ግን ሁልጊዜም በኢትዮጵያና በዓለም ዙሪያ ካሉ ወገኖቼ ጋር ነው። በአካል ብንራራቅም፣ በቴክኖሎጂ አማካኝነት ይህንን የወንጌል ድልድይ በመገንባት የጌታን ቃል በየቤታችሁ ለማድረስ እተጋለሁ። በተለይም በሕይወት ታሪኬና በተለያዩ የሥልጠና ጽሑፎቼ አማካኝነት እግዚአብሔር በሕይወቴ ውስጥ የሠራውን ተአምርና ያስተማረኝን ጥልቅ ትምህርቶች ለእናንተ ለማካፈል በዝግጅት ላይ እገኛለሁ። 🌱🕊️ 🤝 አብረን እንጓዝ በዚህ ድረ-ገጽ የምታገኟቸው ትምህርቶች ሁሉ ከጸሎትና ከጥልቅ ጥናት በኋላ የሚቀርቡ "የነፍስ ምግቦች" ናቸው። ዓላማዬ በክርስቶስ እንድታድጉ፣ በመንፈሳዊ ማንነታችሁ እንድትጸኑና የተሰጣችሁን የሰማይ መክሊት እንድትጠቀሙ መርዳት ነው። በዚህ የመንፈሳዊ ጉዞ አብረን እንድንጓዝ፣ እንድንማማርና አብረን እንድንጸልይ በታላቅ አክብሮት እጋብዛችኋለሁ።🙏🌟

እግዚአብሔር ወልድ – የኢየሱስ መለኮታዊነት

በርካታ ሰዎች ኢየሱስ በስጋ የተገለጠ አምላክ መሆኑን በመካድ ሃሰተኛ ሃይማኖትን መስርተው ከእዉነት መንገድ ሸሽተዋል። በተጨማሪ ሃሰተኛ ወንጌሎች የሚለውን ይመልቱ። ሀ) ኢየሱስ ስለራሱ ምን ይላል? – ከሰማይ መጥቷል በሰማይም ይኖራል – ዮሐ 3፡13 – በሁሉም ስፍራ ይኖራል – ማቴ 18፡20 – የሰንበት ጌታ እንኳ ሳይቀር እንደሆነ ተናግሯል – ማር 2፡27-28 ይህ በእግዚአብሔር ነገር ሁሉ ላይ ስልጣኑን ያሳያል – እግዚአብሔርን አባቴ ብሎ ይጠራል – ዮሐ 5፡17-18 ትርጓሜውም ከእግዚአብሔር ጋር እኩል እንደሆነ ያሳያል – ዮሐ 5፡ 17-18 – ከአባቱ ጋር አንድ ነው፣ ስለዚህም እግዚአብሔር ነው – ዮሐ 5፡30-33 – ኢየሱስ በአባቱ ስም መምጣቱን ተናገሯል – ዮሐ 5፡43 – እርሱን ማየትና መወቅ አብን ማየትና ማወቅ ነው – ዮሐ 14፡7-11 – በመጽሐፍ ቅዱስ ስልጣን ያወራል – ማቴ 5፡21-22፣ 27-28 – “እኔ ነኝ” የሚል ስያሜን ለራሱ ይጠቀማል – ዮሐ 18፡5-8። “እኔ ነኝ” የሚለው ስያሜ የእግዚአብሔር ስያሜ ነው – ዘጻ 3፡ 14 – ከአብርሃም በፊት መኖሩን ተናግሯል – ዮሐ 8፡58 – ንጉስና ፈራጅ እንደሆነ ተናግሯል – ማቴ 25፡31-46። ብሉይ ኪዳን ያህዊን እንደፈራጅ ያሳየናል – ዘፍ 18፡25፤ ኢዮ 3፡18 – ስልጣን በሰማይና በምድር የእርሱ መሆኑን ይናገራል – ማቴ 28፡18-20 ለ) ሌሎች ስለ ኢየሱስ ምን አሉ? – ‹‹ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው›› ብሎ ጳውሎስ ፅፏል – ሮሜ 9፡5 – የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ብሏል ብለው አይሁድ ተናግረዋል – ዮሐ 19፡7 – ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሏል ብሎ ዮሐንስ ተናግራል – ዮሐ 5፡18 – ጻፎች እግዚአብሔር ብቻ የሚያደርገውን ያደርጋል ብለውታል – ማር 2፡5-7 – ዘላለማዊ፣ ፈጣሪ፣ እግዚአብሔር መሆኑ ተፅፎለታል – ዮሐ 1፡1-5 – ቶማስ ‹‹ጌታዬና አምላኬ›› ብሎታል – ዮሐ 20፡28 – አለማት በእርሱ ተፈጠሩ – ዕብ 1፡2፤ ዮሐ 1፡3፤ ቆላ 1፡16 – ኢየሱስ የእግዚአብሔር ፍፁም ምሳሌ ነው – ዕብ 1፡3 – ፍጥረት ሁሉ በኢየሱስ ተጋጥሟል – ዕብ 1፡3፤ ቆላ 1፡17 – ኢየሱስ በመላዕክት አምልኮ ቀርቦለታል – ዕብ 1፡6 – ወልድ “እግዚአብሔር” ተብሏል – ዕብ 1፡8 – ዘላለማዊ ነው – ዕብ 1፡12 – እርሱ መልአክ ሳይሆን ከመላዕክት በላይነው – ዕብ 1፡4፤ 1ጴጥ 3፡22 – ከሙሴ በላይ ነው – ዕብ 3፡1-6 – ከብሉይ ኪዳን ሊቀካህናት በላይ ነው – ዕብ 4፡14-5፡10 – የእግዚአብሔር ባሕሪይ ባሕሪዩ ነው – ፊል 2፡6-11 – የማይታየው አምላክ አምሳል ነው – ቆላ 1፡15-20 – የመለኮት ሙላት በክርስቶስ አካል ውስጥ ይኖራል – ቆላ 1፡15-20 -‹‹ጌታ›› የሚለው ስያሜ ለአብና ወልድ ጥቅም ላይ ውሏል አብ – ማቴ 1፡20፤ 9፡38፤ 11፡25፤ ሐዋ 17፡24፤ ራዕ 4፡11 ወልድ – ሉቃስ 2፡11፤ ዮሐ 20፡28፤ ሐዋ 10፡36፤ 1ቆሮ 2፡8፤ ራዕ 19፡16 ሐ) አምላካዊ አምልኮን ተቀብሏል – የጥበብ ሰዎች አምልከውታል – ማቴ 2፡11 – ደቀ መዛሙርት አምልከውታል – ማቴ 14፡3 – ከነናዊቷ ሴት አምልካዋለች – ማቴ 15፡25 – የተፈወሰው ሰው አምልኮታል – ዮሐ 9፡38 – ሁለቱ ማርያሞች አምልከውታል – ማቴ 28፡9 – ከእርገቱ በኋላ ደቀ መዛሙርት አምልከውታል – ሉቃስ 24፡52 – የእግዚአብሔር መላእክት አምልከውታል – ዕብ 1፡6 – አራቱ ሕያዋን ፍጡራን እና ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች አምልከውታል – ራዕ 5፡8 መ) እግዚአብሔር አብ ስለእርሱ ምን ይላል? – የአባትና – ልጅ ግንኙነት – ማቴ 3፡17፤ ማቴ 17፡5፤ ዮሐ 8፡16-19፤ 1ዮሐ 5፡9 ይህ ግንኙነት ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን እኩልነት ያመለክታል – ዮሐ 5፡17-18

እግዚአብሔር ወልድ – የኢየሱስ መለኮታዊነት Read More »

የእግዚአብሔር አባትነት

የእስራኤል ሕዝብ ለአባት የተለየ ክብር አላቸው፡፡ አባት የሚለው ስያሜ ለእስራኤል ሕዝብ ፓትሪያርክ ለነበሩት አብርሃም፣ ይስሃቅና ያዕቆብ ትልቅ ክብር ለመስጠት ጥቅም ላይ ውሏል (ሉቃስ 3፡8፤ ዮሐ 8፡39)፡፡ ስለዚህ ስለ ‹‹አባት›› ያልተሳሳተ ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል፡፡ ሀ) የ ‹‹አባት›› ትርጓሜ – ‹‹አባት›› ብዙ ጊዜ የአንድ ነገር ምንጭ ወይም ጀማሪ ትርጓሜን ይይዛል፡፡ ያባል በድንኳን የሚቀመጡት የዘላኖች አባት – ዘፍ 4፡20 ዮባል በገናንና መለከትን ለሚይዙ አባት – ዘፍ 4፡21 – ‹‹አባት›› ማለት ተፈጥሮዉን ‹‹ለልጆቹ›› የሚያስተላልፍ ማለት ነው፡፡ አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን፤ አንተም ሠሪያችን ነህ – ኢሳ 64፡8 – ‹‹አባት›› ማለት ስልጣን ያለው ማለት ነው፡፡ – ማር 13፡32 – ምድራዊ ልጆች ሰውነታቸውንና ነፍሳቸው ከወላጆቻቸው ይወስዳሉ፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሔር አብ ‹‹አንድያ ልጅ›› ነው፡፡ የኢየሱስ መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው – ሉቃስ 1፡35፤ ዮሐ 3፡16፤ ቆላ 2፡9 ለ) እግዚአብሔር የሰው ልጆች ሁሉ ‹‹አባት›› – አባታችሁ፣ ፈጣሪያችሁ – ዘዳ 32፡6፤ ሚል 2፡10፤ ዮሐ 1፡18 – የመናፍስት አባት – ዕብ 12፡9 – አባት ለሌላቸው (ድሃ አደግ) አባት – መዝ 68፡5 – እግዚአብሔር አባት ብለን እንድንጠራው ይጠብቅ ነበር – ኤር 3፡19 – የቤተክርስቲያን መሪዎች ክብርን ለመቀበል አባት የሚለውን ስያሜ ሊቀበሉ አይገባቸውም – ማቴ 23፡9 ሐ) እግዚአብሔር የአማኞች ሁሉ አፍቃሪ አባት – በተጨማሪ ልጅነት የሚለውን ክፍል ይመልከቱ – ክፍል ሠ8 – ከቅድስና ባሕሪው እንካፈል ዘንድ – ዘሌ 20፡8፤ 1ጴጥ 1፡2 – የአማኞች ሁሉ አባት – ሮሜ 4፡11 – ኢየሱስ እግዚአብሔር ‹‹አባታችን›› ብሎ ጠርቷል – ወደ አባቴና አባታችሁ እመለሳለሁ – – በሰማይ ያለው አባታችሁ – – በሰማይ ያለው አባታችሁ መልካም ስጦታን ይሰጣችኋል – – የማያዳላ አባት – – በሰማይ ያለ አባታችን – – ሐዋሪያት አባታችን እያሉ ጠርተውታል – ‹‹አባ፣ አባት›› ብለን የምንጮህበት የልጅነት መንፈስ – ሮሜ 8፡15፤ ገላ 4፡6 – የአብ ታላቅ ፍቅር – እኛ፣ የእግዚአብሔር ልጆች – 1ዮሐ 3፡1 – ሕብረታችን ከአብ ጋር ነው – 1ዮሐ 1፡3 ሰ) እግዚአብሔር የኢየሱስ አባት፣ ኢየሱስ አንድያ ልጅ – ኢየሱስ የሰማይ አባቱን በትክክል ይወክላል – ፊል 2፡5-6፤ ዕብ 1፡3 – መሲህ (ኢየሱስ ክርስቶስ) ‹‹የዘላለም አባት›› ተብሎ ተጠርቷል፡፡ ኢሳ 9፡6 – አብ ለኢየሱስ ሲናገር፡- እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ ይላል – መዝ 2፡7፤ ዕብ 1፡5 – አብ ልጁን የአለም አዳኝ አድርጎ ላከው – 1ዮሐ 4፡14 – ኢየሱስ ስለ አባቱ የተናገረው አባ፣ አባት – ማር 14፡36 አባት ሆይ ፈቃድህ ቢሆን – ሉቃስ 22፡42 አባት ሆይ ይቅር በላቸው – ሉቃስ 23፡34 – እናንት የአባቴ ብሩካን – ማቴ 25፡34 – ከወልድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም – ማቴ 11፡27 – እኔና አብ አንድ ነን – ዮሐ 10፡30 – አባት ልጁን ይወዳል – ዮሐ 3፡35 ሸ) እግዚአብሔር የሰማይ አባታችን እንደመሆኑ መጠን ከእኛ ጋር በብዙ ነገር ተዛምዷል – ያፈቅረናል – 2ተሰ 2፡16፤ ዮሐ 16፡27 – ኢየሱስ በእኛ ፈንታ ይሞትልን ዘንድ ልኮልናል (ምህረት) – ገላ 1፡4 – ኢየሱስ ከሙታን መካከል አስነስቶታል (ሕይወትን ሊሰጠን) – ገላ 1፡1 – ይቀጣናል፣ ያርመንማል – ዕብ 12፡5-7፤ ራዕ 3፡19 – በመንፈሳዊ በረከት ይባርከናል – ኤፌ 1፡3 – የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ከእርሱ ዘንድ ይመጣል – ሐዋ 2፡33 – እርሱ ከሁሉ በላይ የሚሆን፣ በሁሉም የሚሠራ፣ በሁሉም የሚኖር ነው – ኤፌ 4፡6 – ክብርን ሁሉ ሊቀበል ይገባዋል – ፊሊ 4፡20፤ ራዕ 7፡12

የእግዚአብሔር አባትነት Read More »

የእግዚአብሔር ስራ (ምግባሩ) ምነድን ነው?

ሀ) መግቢያ – በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትን ፈጠረ – ዘፍ 1፡1 ይህ የሆነው ምናልባት መላዕክት በተፈጠሩበት ጊዜ ሊሆን ይችላል፡፡ – የምድርና ቅርብ ያሉ ሰማያት መፈጠር – ዘፍ 1፡1-31 ይህ ስለምድርና አካባቢዎ ስላሉ ፍጥረታት ይመለከታል ለ) የፍጥረት ልደት – እግዚአብሔር አጽናፈ አለሙን ካለመኖረ ወደ መኖር አመጣ – ዘፍ 1፡1፤ ኢሳ 42፡5፤ ዓሞጽ 5፡8 እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ደግሞ ሊያበጅ ይችላል (ያበጃልም) – አሳ 65፡17፤ ራዕ 21፡1 – የተፈጠረው ነገር ሲፈጠር እጅግ መልካም ነበር – ዘፍ 1፡31 የክፋት ችግር ከዚህ የፍጥረት ልደት በኋላ የመጣ ነው የክፋት ችግር ከሰው እንጂ ከእግዚአብሔር አልመጣም – የፍጥረት ባለቤት አብ – ሮሜ 11፡36 ወልድ፣ ቃሉ – ዮሐ 1፡1-3 መንፈስ ቅዱስ – ዘፍ 1፡2 – በምድር ለሚኖሩ ሕዝቦች እስትንፋስን የፈጠረ እግዚአብሔር ነው – ኢሳ 42፡5፤ ዘካ 12፡1 – መንፈሳዊ ሃይላትንና ስልጣናትን የፈጠረው እግዚአብሔር ነው – ቆላ 1፡16-17 እግዚአብሔር ብቻውን መናፍስትን ሊያጠፋ ይችላል – ማቴ 10፡28፤ ሉቃስ 12፡4-5 – እግዚአብሔር በአፉ ቃል ፈጠረ – ዘፍ 1፡3፤ መዝ33፡6፣ 9፤ ዕብ 11፡3 እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ፣ አላማና ጥበብ – ኤፌ 1፡11፤ ራዕ 4፡11 – እግዚአብሔር የሁሉ ነገር ፈጣሪ ስለሆነ፣ ከዋክብትን፣ መናፍስትን፣ ጣኦትን፣ ሰዎችን፣ እፅዋትን ወይም እንስሳትን ልናመልካቸው አይገባም – ሮሜ 1፡20-25 ሐ) መግቦቱና መገኘቱ አይቋረጥም – እግዚአብሔር ሁሉን ነገር በቃሉ ደግፎ ይይዛል – ዕብ 1፡3 – እርሱ ለሁላችንም ቅርብ ነው – ሐዋ 17፡27-28 በተለይም ለአማኞች ግድ ይለዋል – ዕብ 13፡5 እንደያዕቆብ፣ መገኘቱን ላናስተውል እንችላለን – ዘፍ 28፡16 – የምንኖረው በእግዚአብሔር ያልተቋረጠ መግቦት ነው – መዝ 36፡6 – እግዚአብሔር ፍላጎቶችን ይሞላል – መዝ 23፡1-6፤ 147፡1-9፤ 1ጴጥ 5፡6-7፤ ማቴ 5፡45፤ 6፡25-34፤ ሐዋ 14፡17 – እግዚአብሔር ይጠብቀናል ያድነናል – ዘፍ 28፡15፤ ዘዳ 32፡11፤ ኢሳ 25፡4፤ ማቴ 23፡37፤ ዮሐ 17፡11፤ ፊል 4፡6-7፤ 2ተሰ 3፡3፤ ይሁዳ 24-2 – እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ ከተፈጥሮ ሥርዐት ውጪ በተአምራት ይሰራል – ክፍል ለ2 መ) እግዚአብሔር ድነትን ለሁሉ አቅርቧል – ክፍል ሠ ሠ) እግዚአብሔር በሚከተሉት መልኮች ከሰው ልጅ ጋር ሕብረት ማድረጉን አላቋረጠም፡ – እንደ አባት – የእግዚአብሔር አባትነት የሚለውን ይመልከቱ – ክፍል ለ7 – እንደ ፈጣሪ – የፍጥረት ልደት የሚለውን ይመልቱ – እንደ ባል – ለእስራኤል – ኤር 3፡20 – እንደ ንጉስ – የእግዚአብሔር መንግስት የሚለውን ይመልከቱ – ክፍል መ6 – እንደ ፈራጅ – ሞትና የመጨረሻው ዘመን የሚለውን ይመልከቱ – ክፍል ሸ – እንደ አዳኝ – ደኅንነት የሚለውን ይመልከቱ – ክፍል ሠ – እንደ መምህር – መንፈስ ቅዱስ/የእግዚአብሔር ቃል የሚለውን ይመልቱ – ክፍል ለ12 እና ለ13 – እንደሙሽራና ባል – ሞትና የመጨረሻው ዘመን የሚለውን ይመልከቱ – ክፍል ሸ ረ) እግዚአብሔር ሰማያትና እና ምድርን ዳግመኛ ይፈጥራል – ራዕ 21፡5 – የመጀመሪያው ሰማይና የመጀመሪያው ምድር ይጠፋሉ – ራዕ 21፡1 – አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር – ራዕ 21፡1፣ 5፤ ኢሳ 65፡17 – በእዚያ ሃዘን፣ ሞትና በሽታ የሉም – ራዕ 21፡4 – እኛም ኢየሱስን እንመስላለን – 1ዮሐ 3፡2

የእግዚአብሔር ስራ (ምግባሩ) ምነድን ነው? Read More »

የእግዚአብሔር ባሕሪይ

ሀ) የእግዚአብሔር መልካምነት ማቴ 19፡16-17 ለ) የእግዚአብሔር ምህረትና ጭከና ሮሜ 11፡22 ሐ) ቅዱስ ራዕ 4፡8 – እንደእግዚአብሔር ያለ ቅዱስ የለም 1ሳሙ 2፡2፤ ራዕ 15፡4 – እግዚአብሔር ቅዱስ፣ ፍጹም ነው ሌዋ 19፡2፤ ማቴ 5፡48 – ከቅድስናው ተካፋዩ ልንሆን ይገባል ዕብ 12፡10፣ 14፤ 1ጴጥ 1፡16 – መንፈስ ቅዱስ ሊቀድሰን ይመጣል ሮሜ 15፡16 – ቅድስና ውብ ነው 2ዜና 20፡21፤ መዝ 29፡2 – ቅድስና-ንጽሕና የሚለውን ርዕስ በተጨማሪ ይመልከቱ ክፍል ሠ11 መ) ጻድቅና ትክክል ራዕ 16፡15፤ 19፡2 – እግዚአብሔር ኅጢአትን ይጸየፋል ዕብ 1፡8-9 – በመንግስቱ ክፋት አያድርም 1ቆሮ 6፡9-10 – በተጨማሪ እነዚህን ጥቅሶች ይመልከቱ ኢዮብ 34፡12፤ መዝ 7፡9፤ 116፡5፤ 119፡137 – ጽድቁን ልንካፈል ይገባል 1ዮሐ 3፡7 – ኃጢአትን ልንጠላ ይገባል ዕብ 12፡4፤ 1ዮሐ 3፡8-9 ሠ) አፍቃሪና ርኅሩኅ ዮሐ 3፡16፤ መዝ 69፡16፤ ሰ.አር 3፡22-23 – እግዚአብሔር ፍቅር ነው 1ዮሐ 4፡8፤ ቲቶ 3፡4-5 – ፍቅሩን ልንካፈል ይገባል ዘሌ 19፡18፤ ሉቃስ 10፡27፤ ሮሜ 13፡9፤ ገላ 5፡14 – እግዚአብሔርን ለእኛ ያለው ፍጹም ፍቅር ፍርሃታችንን አስወግዶ ይጥላል 1ዮሐ 4፡18 – ወደ እግዚአብሔር በድፍረት መግባት ሆኖልናል ዕብ 4፡16 – ከእግዚአብሔር ፍቅር የሚለየን የለም ሮሜ 8፡38-39 – ከፍቅር ጋር በተያያዘ ለትምህርት የሚሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል 1ቆሮ 13፡4-7 ረ) ታማኝና እውነተኛ ኢሳ 25፡1፤ ራዕ 3፡14፤ 19፡11 – ሰው ሃሰተኛ ቢሆንም እንኳ እግዚአብሔር ታማኝ ሆኖ ይኖራል ሮሜ 3፡4፤ ዮሐ 17፡3 – ተስፋን የሰጠው አምላክ የታመነ ነው ዕብ 10፡23፤ 11፡11 – ለመታደስ እርሱን ተስፋ እናደርጋለን 1ተሰ 5፡23-24፤ 2ጢሞ 1፡12 – ከኃጢአት ሊያስመልጠን እርሱ የታመነ ነው 1ቆሮ 10፡13 – ታማኝ የሆኑ ሰዎችን ማግኘት አስቸጋሪ ነው ምሳሌ 20፡6 – እግዚአብሔር እንደ እርሱ ታማኝ የሆኑ ሰዎችን ይፈልጋል (ራዕ 2፡10፤ 17፡14፤ 2ጢሞ 2፡2) ሙሴ – ዘኁ 12፡7፣ ዳንኤል – ዳን 6፡4፣ ኤጳፍራ፣ ቲኪቆስ፣ አናሲስም – ቆላ 1፡7፤ 4፡7፣ 9፣ ዳዊት – 1ሳሙ 22፡14፣ ኢየሱስ – ራዕ 19፡11 – እግዚአብሔር ታማኞችን ይጠብቃል – መዝ 31፡23 – የእግዚአብሔር አይኖች በታማኞች ላይ ነው – መዝ 101፡6 – እግዚአብሔር ታማኝ ባሪያን ይሸልማል – ማቴ 25፡21 ሰ) ለጋስ – እግዚአብሔር ይሰጣል ቅዱሳት መጻሕፍትን – 2ጢሞ 3፡16 አንድያ ልጁን – ዮሐ 3፡16፤ ሮሜ 8፡32 መንፈስ ቅዱስን – ሉቃስ 11፡13፤ 1ተሰ4፡8፤ ሮሜ 5፡5 ንስሃን – 2ጢሞ 2፡25 የዘላለም ህይወት ስጦታን – ሮሜ 6፡23፤ 1ዮሐ 5፡11 ለትሁታን ጸጋን – 1ጴጥ 5፡5፤ ያዕ 1፡5 ለደካማው እረፍትን – ማቴ 11፡28 ጥበብን – ዳን 2፡23፤ ያዕ 1፡5 በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ድልን – 1ቆሮ 15፡57 የማገልገል ብቃትን – 1ጴጥ 4፡11፤ ኤፌ 3፡7 ለፍጥረት ሁሉ ምግብን – መዝ 136፡25 ኅ ብት የማፍራት ችሎታን – ዘዳ 8፡18 ለምድራዊ ገዢዎች ስልጣንን – ዳን 2፡37 – ከእግዚአብሔር የልግስና ባሕሪ ልንካፈል ይገባል። መስጠት የሚለውን ክፍል በተጨማሪ ይመልከቱ – ክፍል ሰ8 ሸ) የእግዚአብሔር ታላቅነት ሁሉን አዋቂ – በሁሉ ስፍራ የሚገኝ – ሁሉን ማድረግ የሚችል – ዘላለማዊ – የማይለወጥ ቀ) እግዚአብሔር ጠቢብ፣ ሁሉን አዋቂ ነው – ሮሜ 16፡27 – እግዚአብሔር አዋቂ ጌታ ነው – 1ሳሙ 2፡3 – ጥበቡ ጥልቅ ናት – ኢዮብ 9፡4 – ከሰው መረዳት በላይ ነው – መዝ 139፡4-6፤ ሮሜ 11፡33 – የእግዚአብሔር ጥበብ ባሕርይ – ያዕ 3፡17 ንጹሕ – ከሃሰት ጋር የማይቀየጥ ሰላማዊ – ጠብን የማይጭር ጨዋ – አስቸጋሪ/የማይመች ወይም ግትር ያልሆነ መኀሪ – ሕግን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፍቅር የሚገልጥ የማያዳላ – ለራስ ወይም ለወገኔ ይጠቅማል በሚል የማይሰራ ግብዝነት የሌለበት – የሚለውን የሆነ – እግዚአብሔርዊ ያልሆነ ጥበብ ባሕሪይ አለማዊ፣ ሥጋዊ፣ የአጋንንት ጥበብ – ያዕ 3፡14-16 ለእግዚአብሔር ሞኝነት የሆነ – 1ቆሮ 3፡18-20 – ለአማኞች ጥበብ ተዘጋጅቷል – ያዕ 1፡5-7፤ ቆላ 1፡9፤ ኤፌ 1፡17 ክርስቶስ ጥበባችን ነው – 1ቆሮ 1፡24፤ ቆላ 2፡2 የክርስቶ ቃል ጥበባችን ነው – ቆላ 3፡16 – የጥበብ ቃል መንፈሳዊ ስጦታ – ክፍል ረ11 በ) እግዚአብሔር በሁሉ ቦታ በአንድ ጊዜ ይገኛል – መዝ 139፡7-12 – ስለዚህ በየትኛውም ስፍራ ብንጸልይ እርሱ ይሰማናል፡፡ – ሁሉን ነገር በሁሉ ረገድ ይሞላል – ኤፌ 1፡22-23 – ከማናችንም ሩቅ አይደለም – ሐዋ 17፡27-28፤ ኤር 23፡23 – በሲኦል፣ በሰማይ – መዝ 139፡8፤ ዓሞጽ 9፡2-3 – ከእርሱ ልንደበቅ አንችልም – ኤር 23፡24 – ይህ ማለት እግዚአብሔር በሁሉም ነገር ውስጥ አለበት ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ሰዎች በሚከተሉት ነገሮች ሲወቅሳቸው እናነባለን፡ ጣኦትንና ዲያብሎስን ሲያመልኩ – ኢሳ 2፡8-11፤ 20-21፤ ራዕ 9፡20 የተፈጠሩትን ሲያመልኩ – ሮሜ 1፡25 መላዕክትን ሲያመልኩ – ቆላ 2፡18፤ ራዕ 22፡8-9 የሙታን መናፍስትን ሲያመልኩ – ዘሌ 20፡6፤ ዘጻ 18፡9-11፤ ኢሳ 8፡19 – ማስታወሻ፡ በድፍረት መጸለይ እንችላለን – ኤር 33፡3 ተ) እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው – እርሱ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ ነው – ዘፍ 1፡1 – ሁሉም ነገር በአንድ ላይ ተያይዞ የጸናው በእርሱ ነው – ቆላ 1፡17 – ሃይሉ ታላቅ ነው – ኢዮብ 9፡4 – ስለዚህ ሊያድንና ሊታደግ ይችላል – ኢሳ 50፡2 – ሁሉ ለእግዚአብሔር ይቻላል – ማቴ 19፡26፤ ኤር 32፡17 – ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? – ኤር 32፡27 – የእግዚአብሔር ድካም ከሰዎች ብርታት ይበረታል – 1ቆሮ 1፡25 – ሃይሉን ልንካፈል ይገባል – ኢዮ 3፡10፤ 2ቆሮ 12፡10፤ ዕብ 11፡34 – በእግዚአብሔር ጸጋ ልንበረታ ይገባል – 2ጢሞ 2፡1 – በሃይ ልንበረታ ይገባል – ኤፌ 6፡10 – ሰይጣንን ለመርታት ልንበረታ ይገባል – 2ቆሮ 10፡3-5 – በእምነት ልንበረታ ይገባል – ሮሜ 4፡20 – ለመበርታትና ለመበዝበዝ – ዳን 11፡32 ቸ) እግዚአብሔር ዘላለማዊ ነው – 1ዮሐ 5፡20 – ከዘላለም እስከዘላለም – መዝ 90፡1-2 – መጀመሪያና መጨረሻ – ራዕ 22፡13 – ያለ፣ የነበረና፣ የሚመጣው – ራዕ 1፡8 – ከእርሱ በፊትና በኃላ ምንም የለም – ኢሳ 43፡10 – ዘላለማዊ ሕይወቱን መካፈል እንችላለን – ዮሐ 3፡15-16፤ ሮሜ 6፡23፤ 1ዮሐ 5፡11-13 – የሰጠነውን አደራ ይጠብቃል – 2ጢሞ 1፡12 ነ) እግዚአብሔር አይለወጥም – ሚል 3፡6 – ስለዚህ የፍቅር ስጦታው ሊታመን ይችላል፡፡ – ኢየሱስ ክርስቶስ ትላንትና፣ ዛሬ፣ ወደፊት ያው ነው – ዕብ 13፡8 – በእርሱ ዘንድ መለዋወጥ የለም – ዕብ 1፡17 – እርሱን ለመምሰል መለወጥ አለብን – 1ዮሐ 3፡2፤ 1ቆሮ 15፡51-53

የእግዚአብሔር ባሕሪይ Read More »

የእግዚአብሔር ማንነት

ሀ) የእግዚአብሔር ሶስትነትና አንድነት እግዚአብሔርን የመምሰል ምስጢር ታላቅ ነው 1ጢሞ 3፡16 የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ማን ሊመረምር ይችላል ኢዮብ 11፡7-8 እነዚህ ሦስቱም መለኮታዊ ናቸው አብ – ክፍል ለ7 ይመልከቱ ወልድ – ክፍል ለ8፣ ለ9፣ ለ10፣ ለ11 ይመልከቱ መንፈስ ቅዱስ – ክፍል ለ12፣ ለ13 ይመልከቱ ሦስቱም አንድ ናቸው እግዚአብሔር አንድ ነው ዘዳ 6፡4-5፤ ማር 12፡29፤ ያዕ 2፡19 ኢየሱስ እርሱና አብ አንድ እንደሆኑ ተናግሯል ዮሐ 10፡30 “ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር” ብዙ ቁጥር ዘፍ 1፡26 “ማንን እልካለሁ?’’ (ነጠላ ቁጥር) ‘‘ማንስ ይሄድልናል?’’ (ብዙ ቁጥር) ኢሳ 6፡8 “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ (ብዙ ቁጥር) ስም (ነጠላ ቁጥር) እያጠመቃችኋቸው…” ማቴ 28፡19-20 ለ) መንፈስ – እግዚአብሔር መንፈስ ነው ዮሐ 4፡24 ስለዚህ የተቀረጸ ምስል፣ ጣኦቶች አይኑርህ ዘዳ 5፡8፤ ኢሳ 42፡8፤ 1ዮሐ 5፡21 ስለዚህ መንፈሳዊ አምልኮ አስፈላጊ ነው ዮሐ 4፡24 ስለዚህ ሃሰተኛ ሃይማኖት ዋጋ ቢስ ነው ክፍል ረ6 ፣ ሰ5 ይመልከቱ ስለዚህ በመንፈስ መወለድ የግድ ይሆናል ዮሐ 3፡3-8፤ 1ቆሮ 15፡30 ሐ) በራሱ ሕልው (ህያው) ነው በመጀመሪያ እግዚአብሔር ዘፍ 1፡1፤ ዮሐ 1፡1 አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ወልድ በራሱ ሕይወት አለው ዮሐ 5፡26 እርሱ የሕይወት ምንጭ ነው መዝ 36፡9፤ ኤር 17፡13 ለተፈጥሮ ሕይወትን የሚሰጥ እርሱ ነው ዘፍ 2፡7 ለዳግም ልደት ሕወትን የሚሰጥ እርሱ ነው ዮሐ 3፡6፤ 1ቆሮ15፡45 የዘላለምን ሕይወት የሚሰጥ እርሱ ነው ራዕ 21 መ) የእግዚአብሔር ልዩነትና አንድነት ‹‹አንዱ አምላክ›› ዮሐ 5፡44፤ ይሁዳ 25 ጌታ አንድ ነው ዘዳ 4፡35፤ ማር 12፡29 ከእርሱ በፊትም ሆነ በኋላ ማንም የለም ኢሳ 43፡10-13፤ ራዕ 1፡8 አንድ እግዚአብሔር 1ቆሮ 8፡4፤ 1ጢሞ 2፡5 ወደ እርሱ የሚያደርስ አንድ መንገድ ብቻ አለ ዮሐ 14፡6 ሊመለክና ሊታዘዙት የሚገባ እርሱ ብቻ ነው ዘጻ 20፡2-3፤ ዕብ 5፡9

የእግዚአብሔር ማንነት Read More »

የእግዚአብሔር ስሞች

የእግዚአብሔር ሰዎች ባሕሪያቶቹን ይገልጻሉ እግዚአብሔርን ለመሰየም በእብራይስጥ ቋንቋ በርካታ ቃላት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ እነዚህ ስያሜዎች ወደአማርኛ ሲመለሱ “እግዚአብሔር” ወይም “ጌታ” ወይም “ጌታ እግዚአብሔር” ተብለው ተተርጉመዋል፡፡ ከዚህ በታች የተወሰኑ በእብራይስጥ ቋንቋ የእግዚአብሔር ስያሜዎችና ትረጉሞቻቸው ቀርበዋል፡ ሀ) ያህዌ፡ በራሱ ህያው የሆነ በፍጥረት መጀመሪያ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ስያሜ ዘፍ 2፡4 – ያህዌ- ይርኤ እግዚአብሔር ያዘጋጃል አብርሃም ይስሃቅን እንዲሰዋ በተጠየቀ ጊዜ የተናገረው ዘፍ 22፡13-14 – ያህዌ- ራፋ እግዚአብሔር ይፈውሳል እግዚአብሔር ለሚሰሙትና ለሚታዘዙት ቃል ሲገባ ዘጸ 15፡26 – ያህዌህ- ንሲ እግዚአብሔር አላማችን (ሰንደቃችን) ነው ሙሴ አማሌቃዊያንን ድል ባደረገ ጊዜ የተናገረው ዘጸ 17፡15 – ያህዌ- ሰላም እግዚአብሔር ሰላማችን ነው ጌዴዎን የተናገረው መሳ 6፡24 – ያህዊ- ራ-አህ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው ዳዊት ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው ሕብረት መዝ 23፡1 – ያህዌ-ጽድቄኑ እግዚአብሔር ጽድቃችን ነው እግዚአብሔር ወደምድር በሚመጣበት ጊዜ የሚጠራበት ስያሜ ኤር 23 – ያህዌ -ሻማህ እግዚአብሔር በዚያ አለ የእግዚአብሔር ከተማ ስም ሕዝ 48፡35 – ያህዌ- ሳቦት የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እግዚአብሔር የባቢሎናዊያንን ሠራዊት በደመሰሰ ጊዜ ኤር 28፡2 – ያህዌ- መቅደሽ እግዚአብሔር ቀዳሽ ለተቀደ ሕዝብ የተቀደሰ ሰንበት እንደምልክት ዘጸ 31፡13 ለ) ኤሎሂም ወይም ኤል፡ ብርቱ የሆነ – ኤል ኤሊዩን – ልዑል እግዚአብሔር መልከ ጼደቅ አብርሃምን ሲገናኘው ዘፍ 14፡18፣ 19 እዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሔር የሰማይና የምድር ባለቤት እንደሆነ ተገልጻጿል የአስራት ስጦታ ለመጀመሪያ የተጠቀሰበት ስፍራ ነው ዘፍ 14፡20 – ኤል ኤሊዮን – ሉሲፈር  (በልዑል) እመሰላለሁ ብሎ ተናገረ ኢሳ 14፡14 – ኤል-ሻዳይ ብርታትን የሚሰጥ -አብርሃም በ99 አመቱ የልጅ ተስፋ ተሰጠው ዘፍ 17፡1 – ኤል- ኦላም ዘላለማዊው -አብርሃም ከፍልስጤማዊያን ጋር ስምምነት አደረገ ዘፍ 21፡33 – ኤል ጊቦር ብርቱዉ /ሃያሉ/ ስለሚመጣው መሲህ ትንቢት ኢሳ 9፡6 ከዚህ በተጨማሪ ድንቅ መካር (መካሪ) የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተሰኝቷል ኢሳ 9፡6 ሐ) አዶናይ ጌታ /አለቃ/ አብርሃም ስለልጅ እጦት መሚያጉረመንምበት ጊዜ- ዘፍ 15፡2 መ) እኔ አኔ ነኝ ወይም እኔ ነኝ ዘጸ 3፡14 ሙሴ፣ እግዚአብሔርን ለእስራኤላዊያን ምን ብሎ ማስተዋወቅ እንዳለበት ግራ በተጋባበት ጊዜ ዘጸ 3፡13 ሠ) ቀናተኛ ዘጸ 34፡14 እግዚአብሔር የጣኦት አምልኮን ይቃወማል ረ) አባት ክፍል ለ7 ይመልከቱ ሰ) ኢየሱስ (አዳኝ) ክፍል ለ8፣ ለ9፣ ለ10፣ ለ11 ይመልከቱ ሸ) መንፈስ ቅዱስ ክፍል ለ12፣ ለ13 ይመልከቱ

የእግዚአብሔር ስሞች Read More »

እግዚአብሔር ራሱን ለሰዎች እንዴት ይገልጣል?

ሀ) በተአምራት ተአምራቶቹ እግዚአብሔርን ያከብራሉ – ዘኅ 14፡22 አንዳንዶች እንዲያምኑ ያደርጋቸዋል – ዮሐ 2፡23 ነገር ግን አንዳንዶች ላያምኑ ይችላሉ – ዮሐ 12፡37 እውነተኛ ተአምራት የሚነድ ቁጥቋጦ – ዘፍ 3 በግብጻዊያን ላይ ወረርሽኝ – ዘዳ 4፡12 የቀይ ባሕር መከፈል – ዘፍ 14 የዮርዳኖስ ወንዝን መሻገር – ኢያሱ 3 ኤሊያስ – 1ነገ 17-18፤ 2ነገ 1 ኢሳያይስ – 2ነገ 20 ኤልሳዕ – 2ነገ 2፡-6፡፤ 13 የኢየሱስ ተአምራት – ክፍል ለ9 ይመልከቱ የደቀ መዛሙርት ተአምራት – ክፍል F9፣ ረ11 ይመልከቱ አንዳንድ ተአምራት በሰይጣን ሊደረጉ ይችላሉ – ዘዳ 13፡1-3፤ ዘጻ 7፡9-12፤ ረዕ 13፡14፤ 16፡14፤ 19፡20 ለ) በፍርድ ፈርኦን – ዘጸ 4፡12 ናቡከደነጾር – ዳን 4፡28-37 ብልጣሶር – ዳን 5 አናንያና ሰጲራ – ሐዋ 5፡1-11 ሄሮድስ – ሐዋ 12፡22-23 የክፉው ሰራተኞች በሙሉ – ራዕ 20፡10፣ 14-15 ሐ) በሕልምና ራዕዮች አንዳንድ ሕልሞችና ራዕዮች እግዚአብሔርንና የእርሱን አላማዎች ይገልጣሉ፡፡ – የሚከተሉት መጻሕፍት እግዚአብሔርን የሚገልጡ በርካታ ሕልሞችና ራዕዮችን አካተዋል – ሕዝቅኤል፤ ዳንኤል፤ ዘካሪያስ፤ ዓሞጽ፤ ናሆም፤ የሐዋሪያት ሥራ፤ ራዕይ ሕልሞችና ራዕዮች በእግዚአብሔር ሊፈቱ ይገባቸዋል ለዮሴፍ – ዘፍ 41፡15-16 የዮሐንስ ራዕዮች ራዕ 1፡20፤ 7፡13-14 ለዳንኤል – ዳን 2፡27-28 የጴጥሮስ ራዕይ – ሐዋ 10፡11-15፣ 34-35 ሕልሞችን፣ ራዕዮችንና ትንቢቶችን ለመመዘን ከዚህ በታች ያሉትን የእግዚአብሔር መስፈርቶች አይዘንጉ፡- ሁሉን በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ይፈትሹ – መዝ 138፡2፤ ምሳሌ 30፡5-6 መንፈስን ሁሉ አይመኑ – 1ዮሐ 4፡1-3 ሁሉንም ነገሮች ይመካከሩባቸው – ምሳሌ 11፡14፤ 15፡22 ምስክርነት እስኪያገኙ ይታገሱ – ማቴ 18፡16፤ 1ቆሮ 14፡29፤ 2ቆሮ13፡1 እግዚአብሔር ለእርሱ ያለንን ፍቅር ሊፈትን ሃሰተኛ ቃላት በሕይወታችን እንዲያልፉ ሊፈቅድ ይችላል – ዘዳ 13፡3 ከእግዚአብሔር ፈቀቅ የሚያደርጎት ከሆነ ይህ ከሃሰት ነው – ዘዳ 13፡1-3 ተጨባጭ ተአምር ሃሰት ሊሆን ይችላል – ዘዳ 13፡1-3 የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ከሕልም፣ ወዘተ በላይ ናቸው – ዘዳ 13፡4 ሃሰትን ከመካከላችን ልናስወግድ ይገባል – ዘዳ 13፡5 ሕልሞችና ራዕዮች መጽናናትን ሊያመጡ ይችላሉ ለአብርሃም – ዘፍ 15፡1 ለጳውሎስ – ሐዋ 18፡9 ሕልሞችና ራዕዮች ከእግዚአብሔር ዘንድ ማስጠንቃያን ሊያመጡ ይችላሉ ጌዴዎን የሰማው ሕልም – መሳ 7፡13-15 ዮሴፍ ከግብጽ ወደ እስራኤል ተመራ – ማቴ 2፡19 ዮሴፍ ወደገሊላ ተመራ – ማቴ 2፡22 አናኒያ ለጳውሎስ እንዲጸልይ ተመራ – ሐዋ 9፡10 ጳውሎስ ለአናኒያ መምጣት ተዘጋጀ – ሐዋ 9፡12 ጳውሎስ ወደሜቄዶኒያ እንዲጓዝ ተመራ – ሐዋ 16፡9 ሕልሞችና ራዕዮች ስህተት ሊሆኑ ይችላሉ የአንድ ሰው የገዛ ልብ ክፋትን ሲመኝ – ኤር 14፡14፤ ኤር 23፡16 ሕልሞች – ኤር 23፡25፣ 32 አንዳንድ ሕልሞች ከእግዚአብሔር ያርቁናል – ኤር 23፡27 እነዚህን የሃሰት ሕልሞች መከተል የለብንም – ኤር 27፡9 የገዛ ራሳችን ሕልሞች ሃሰተኛ ሊሆኑ ይችላሉ – ኤር 29፡8 ሃሰተኛ ሕልሞች ወደ ሃሰተኛ ትንቢቶች ሊመሩ ይችላሉ – ሕዝ 13፡7 ሃሰተኛ ሃይማኖቶች ሃሰተኛ ሕልሞችና ራዕዮችን ያቀርባሉ – ዘካ 10፡2 አንዳንድ ሕልሞችና ራዕዮች ግልጽ ቅዠቶች ናቸው በመራብና በመጠማት ምክንያት – ኢሳ 29፡8 የሥራ ብዛት ውጤት – መክ 5፡3፣ 7 አንዳንድ ሕልሞች ፍፁም ስጋዊ ናቸው – ይሁዳ 1፡8 አልኮልና አደንዛዥ እጾች የሃሰተኛ ሕልሞችና ራዕዮች ምንጭ ሊሆኑ ይችላሉ – ኢሳ 28፡7 መ) እግዚአብሔር በሕልም ይናገራል – ኢዮብ 33፤ 15-18 ብሉይ ኪዳን አቤሜሌክ – ዘፍ 20፡3-7 ያዕቆብ – ዘፍ28፡12፤ 31፡10 ላባ – ዘፍ 31፡24 ዮሴፍ – ዘፍ 37፡5-9 ሰሎሞን – 1ነገ 3፡5-15 ናቡከደነጾር – ዳን 2፡1፣ 31፤ 4፡5፣ 8 ዳንኤል – ዳን 7 አዲስ ኪዳን ዮሴፍ- ማቴ 1፡20-21፤ 2፡13፣ 19-20 የጥበብ ሰዎች – ማቴ 2፡11-12 የጲላጦስ ሚስት – ማቴ 27፡19 ሠ) እግዚአብሔር በራዕይ ይናገራል – ኢዮብ 33፡15-18፤ መዝ 89፡19 ብሉይ ኪዳን አብርሃም – ዘፍ 15፡1 ያዕቆብ – ዘፍ 46፡2 ኢሳያይስ – ኢሳ 6፡1-8 ዳንኤል – ዳን 2፡19፤ እና ምዕረፍ 7፣ 8፣ 10 ናሆም – ናሆም 1፡1 ዓሞጽ – ዓሞጽ 7፡1-9፤ 8፡1-6፤ 9፡1 ዘካርያስ – ዘካ 1፡8፤ 3፡1፤ 4፡2፤ 5፡2፤ 6፡1 ሕዝቅኤል – ሕዝ 1፣ 8፣ 10፣ ወዘተ… ናቡከደነጾር – ዳን 2፡28 አዲስ ኪዳን ጳውሎስ – ሐዋ 9፡3፣ 6፣ 12፤ 16፡9፤ 18፡9፤ 22፡18፤ 27፡23፤ 2ቆሮ 12፡1-4 አናኒያ – ሐዋ 9፡10-11 ጴጥሮስ – ሐዋ 10፡9-17 ቆርነሊዎስ – ሐዋ 10፡3 ዮሐንስ – የዮሐንስ ራዕይ

እግዚአብሔር ራሱን ለሰዎች እንዴት ይገልጣል? Read More »

ስለ እግዚአብሔር እንዴት መማር እችላለሁ?

ሀ) መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ያስተምረናል የእግዚአብሔር ቃል እምነት ሊጣልበት የሚችል መሆኑ – ሉቃስ 21፡33 የእግዚአብሔርና የቃሉ ስልጣን – ማቴ 4፡4፤ ዮሐ 10፡35 መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ የተደረሰ መጽሐፍ ነው – 2ጢሞ 3፡16 መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የተጻፈ ነው – 2ጴጥ 1፡21 ለ) መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን ለእኛ ለመግለጽ ሰዋዊ የሆኑ መግለጫዎችን ይጠቀማል ክንድና እጅ – ዘጸ 3፡20፤ ዘዳ 4፡34፤ ዘጸ 5፡15 ፊት – ዘፍ 4፡14፤ 33፡10፤ ኢሳ 59፡2 አይኖችና ጆሮዎች – ኢሳ 37፡17፤ መዝ 11፡4፤ 34፡15፤ መሳ 15፡3፤ ዘካ 4፡10 መሄድና መምጣት – ዘፍ 11፡5፤ ኢሳ 64፡1-3፤ መዝ 18፡9-19 የእግዚአብሔር ድምጽ ለአዳምና ለሙሴ ተሰማ – ዘፍ 3፡9፣ 10፤ ዘዳ 4፡12 የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማት እንችላለን – ዘዳ 5፡24፤ ሐዋ 22፡14 ሐ) እግዚአብሔር፣ ሰዎች ሊረዱት በሚችሉት መንገድ ይገለጣል በራዕይ – ዳን 7፡9፣ 13፤ ራዕ 4፡3፤ 5፡7 በቀጥታ – አዳም – ዘፍ 3፡8-10 – ያዕቆብ – ዘፍ 32፡24-30 – አብርሃም – ዘፍ 18 ኢያሱ – ኢያሱ 5፡13-15 – ዳንኤል – ዳን 3፡ 25 እግዚአብሔር በኢየሱ በኩል – ማቴ፣ ማር፣ ሉቃ እና ዮሐ መ) የፈጠራቸውን ነገሮች በመመልከት (ተፈጥሮን) በ (ሮሜ 1፡18-25) የተጠቀሰውን ትምህርት ይመልከቱ። ሰማያት የእግዚአብሔር ክብር ይናገራሉ – መዝ 19፡1 ተፈጥሮ የእርሱን ዘላለማዊ ሃይልና መለኮትነት ያበስራል – ሮሜ 1፡20 ህሊናችንና/ልባችን የእግዚአብሔርን ሕግ ያውቃል – ሮሜ 2፡14-16 የምድር በረከት ምስክር ነው – ሐዋ 14፡15-17 የእግዚአብሔር እውቀትና ጥበብ – መዝ 19፡1-6፤ 104 የእግዚአብሔር ሃይልና ግርማ ሞገስ – መዝ 18፡7-15፤ 29፤ 66፡1-7 ሠ) እግዚአብሔርን በተፈጥሮ ውስጥ ብቻ የማወቅ ጎዶሎ ጎኖች ተፈጥሮ ሙሉዉን ድነት ለመረዳት በቂ አይደለም። የማያምኑ ሰዎች አእምሮ በሰይጣን ታውሯል – 2ቆላ 4፡4 ሰባኪ ያስፈልጋል – ሮሜ 10፡14 የአዳም መውደቅ በተፈጥሮ ውስጥ የነበረውን የእግዚአብሔር ምስል በክሎታል። ለአብነት – በምጥ ጊዜ ያለ ህመም – ዘፍ 3፡16፤ አድካሚ ስራ፤ እሾህና አሜኬላ – ዘፍ 3፡17-18፤ ፍጥረት ሁሉ ለመታደስ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል – ሮሜ 8፡18-25 ረ) እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ በሙላት ተገልጧል ወልድ ለሚወደው ሁሉ አብን ይገልጥለታል – ማቴ 11፡27፤ ሉቃስ 10፡22 እኔን ያየ አብን አየ – ዮሐ 14፡6-7፤ 10፡30 ቃልም እግዚአብሔር ነበረ…ቃልም ሥጋ ሆነ – ዮሐ 1፡1-14 ሰ) እግዚአብሔር መንፈስ ነው (ዮሐ 4፡24) ስለዚህ እራሱን ሊገልጥልን ይገባል – 1ሳሙ 3፡21 አንዳንድ ነገሮች ምስጢር እንደሆኑ ይቆያሉ – ዘዳ 29፡29 አንዳንድ ነገሮችን ለሰው ልጅ ይገልጻል – ዓሞጽ 3፡7፤ ኤፌ 3፡5 ሙሴ የእግዚአብሔርን ድምጽ ሰማ ነገር ግን እግዚአብሔርን አልተመለከተውም – ዘጸ 4፡12 ሰው እግዚአብሔርን አይቶ በሕይወት መቆየት አይችልም – ዘጸ 33፡20 ማስታወሻ፡- እግዚአብሔር መንፈስ ስለሆነ ራሱን ሊገልጥልን ይገባል፡፡ ሸ) እግዚአብሔር ለሰዎች ራሱን ለምን ይገልጣል? በመከራ ጊዜያቸው ወቅት ሊያድናቸው – 2ሳሙ 22፡7፤ መዝ18፡6 ኖሕ ከጥፋት ውሃ ዳነ – ዘፍ 6፡1 – 9፡17 አብርሃም ከ ጣኦት አምልኮ ዳነ – ዘፍ 12፡1 – 22፡19 ሙሴ ከባርነት ነጻ ለመውጣት – ዘጸ 3፡-14፡ ድነትን ለመስጠት – ማቴ 1፡21 የሰይጣንን ስራ ለማፍረስ – 1ዮሐ 3፡8 ስለመጻኢ ጊዚያት ለማስጠንቀቅ – ዓሞጽ 3፡7፤ ራዕ 1፡-22

ስለ እግዚአብሔር እንዴት መማር እችላለሁ? Read More »

መጽሐፍ ቅዱስ- ከስህተት የጸዳ፣ እንከን የሌለው፣ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ በመነዳት የጻፉት የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ- ከስህተት የጸዳ፣ እንከን የሌለው፣ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ በመነዳት የጻፉት የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ የጥናቱ ማውጫ ሀ1. መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ይናገራል ሀ2. መጽሐፍ ቅዱስ ከስሕተት የጸዳ ነው ሀ3. መጽሐፍ ቅዱስ በማናቸውም ርዕስ ጉዳዮች ላይ ስሕተት የለበትም ሀ4. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስት ያሉ ቃላት በተመረጡ ሰዎች አማካኝነት ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጡ ናቸው ሀ5. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ አስተምህሮዎን ለምን አጠናለሁ፣ ለምንስ እታዘዛቸዋለሁ? ሀ6. የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮዎችን እንዴት ልማራቸው እችላለሁ? 1. መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ፣ ስለ ራሱ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ይናገራል “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።’’ (2ጢሞ 3፡16) “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” የሚለው የተጻፈውን የእግዚአብሔርን ቃል ያመለክታል፡፡ “ቅሱሳት መጻሕፍት ሁሉ” የሚለው ብሉይና አዲስ ኪዳንን ያመለክታል፡፡ ኢየሱስ ብሉይ ኪዳንን ቅዱሳት መጻሕፍት ብሎታል (ሉቃስ 24፡27፣ 44፣ 45፤ ዮሐ 5፡39፣ 46፣ 47) ጴጥሮስ የጳውሎስን ደብዳቤዎች ቅዱሳት መጻሕፍት ብሏቸዋል (2ጴጥ 3፡15፡16) መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈ የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ፣ በዚህ ቃል ላይ የሚጨምርም ሆነ የሚቀንስ የእግዚአብሔር ፍርድ በእርሱ ላይ ይሆናል፡፡ “ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል፤ ’’ (ራዕ 22፡18፣ 19) 2. መጽሐፍ ቅዱስ ከስህተት የጸዳ ነው የእግዚአብሔር መንፈስ “ቅዱሳን የእግዚአብሔር ሰዎችን” (2ጴጥ 1፡21) በማንጻት፣ እንዲጽፉት በማድረግ በመጽሐፍ ቅዱስ ሰፍረው የሚገኙት ቅዱሳት መጻሕፍት ያለስህተት ተጠብቀው እንዲቆዩ አድርጓል፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ፣ መለኮታዊ በሆነ ምሪት የእነዚህን ቅዱሳት መጽሐፎች ፀሃፊዎች በመምራት፣ እግዚአብሔር ማለት የፈለገው እንዲሰፍር እና የመጀመሪያዎቹ ቅጂዎች ሁሉ ከስህተት የጸዱ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃላት በእግዚአብሔር ከስህተት እንዲጸዱ ተደርገዋል (ኢሳ 40፡8፤ ማቴ 24፡35) ሐ) ብሉይ ኪዳን ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣ ነው፣ ስለዚህም ስህተት የለበትም (ኢያሱ 1፡8፤ 2ነገ 22፡8፣ 11፣ 13) መ) ያለምንም ልዩነት፣ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ስህተት ሊገኝ አይችልም ክርስቶስ እንዲህ አለ፣ “መጽሐፉ ሊሻር አይችልም – ’’ (ዮሐ 10፡35)፡፡ ኢየሱስ በእብራይስጥ፣ አራማይክና ግሪክ ቋንቋዎች ውስጥ ያሉን የቋንቋዎቹን ምቶች፣ የድምጽ ጥብቀትና መላላት ሕግጋቶች ሳይቀር ያለስህተት በመጠቀም ሰብኳል፡፡ እነዚህ ቋንቋዎች መጽሐፍ ቅዱስ በመጀመሪያ የተጻፈባቸው ቋንቋዎች ናቸው፡፡ “ከሕግ እንዲት የውጣ (የእብራይስጥ ትንሳሿ ፊደል) ወይም አንዲት ነጥብ (በፊደል ላይ በመቀመጥ መጥበቅና መላላቱን የምታመለክት ጭረት) ከቶ አታልፍም፣ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ” (ማቴ 5፡18)፡፡ 3. መጽሐፍ ቅዱስ በማናቸውም ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስህተት የለበትም ኢየሱስ፣ ብሉይ ኪዳን ከስህተት የጸዳ መሆኑን አረጋግጧል። በብሉይ ኪዳን ተአምራዊ ታሪኮችን በመጥቀስ፤ ቅዱሳት መጻሕፍቱ እዉነተኛ፣ ትክክለኛ፣ ከስህተት የጸዱ እና በማናቸውም ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተሳሳተ ነገር እንደሌለባቸው አረጋግጧል፡፡ ዘፍጥረት የፍጥረት ታሪክ መዝገብ እንደሆነ አረጋግጧል (ማቴ 19፡4) አዳምና ሔዋን (ማቴ 19፡4-6፤ ዘፍ 1፡26፣ 27፣ 2፡7፣ 18) ቃየልና አቤል (ማቴ 23፡35፤ ዕብ 11፡4፤ ዘፍ 4፡1-15) ሰይጣን (ሉቃስ 11፡18፤ ሕዝ 28፡11-19) ኖህ (ማቴ 24፡37፣ 38፤ ዘፍ 6፡1-14) ዮናስ (ማቴ 12፡39፣ 40፤ ዮናስ 1፡7) የሎጥ ሚስት (ሉቃስ 17፡32፤ ዘፍ 19፡26) መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ፣ እያንዳንዱ ቃል እውነት እንደሆነ፣ ሙሉ በሙሉም ሊታመን እንደሚገባ ኢየሱስ አሳይቶናል፡፡ ብሉይ ኪዳን በማናቸውም ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከስህተት የጸዳ መሆኑን ክርስቶስና ሐዋሪያት አረጋግጠውልናል። አንዳንድ ዘመነኛ የሃይማኖት ሊቃውንት ግን በሚከተሉት መጻሕፍት ላይ ጥርጣሪያቸውን አሳይተዋል፡፡ ለእነዚህ ሰዎች ምላሽ ይሆንዎ ዘንድ እነሆ፡- ዘፍጥረት፣ ዘጸአት፣ ዘሌዋዊያን፣ ዘኁልቁ፣ ዘዳግም- እነዚህ መጻሕፍት በሙሴ የተጻፉ ሲሆኑ ኢየሱስ እውቅና ሰጥቷቸዋል፡፡ ዮሐ 5፡46፣ 47 ይመልከቱ፡፡ በእነዚህ ሊቃውንት በሰፊው ለጥቃት ከተጋለጠው የዘዳግም መጽሐፍ ኢየሱስ ክርስቶስ – በ ማቴ 4፡4፣ 7-10 እንደተገለጸው ሰይጣንን ድል ለመንሳት ጠቅሷል (ዘዳ 6፡16 እና 10፡20)፡፡ እነዚህ መጻሕፍት “… የመንፈስ ቅዱስ ሰይፍ … የእግዚአብሔር ቃል …” (ኤፌ 6፡17) ባይሆኑ ኖሮ፣ ኢየሱስ ጠቅሶ ይጠቀማቸው ነበርን? ፈጽሞ! ሊጠቀምባቸው አይችልም! እንግዲያው እነዚህ መጽሐፍት የእግዚአብሔር ቃል ናቸው፡፡ ኢሳያስ – አዲስ ኪዳን ውስጥ ሃያ-አንድ ጊዜያት ያህል ተጠቅሷል፡፡ ጥቂት ምሳሌዎችን ያገናዝቡ፡- ማቴ 15፡7-9 እና ኢሳ 29፡13፤ ማቴ 3፡3 እና ኢሳ 40፡3፤ ሐዋ 8፡28-33 እና ኢሳ 53፡7፣ 8። እነዚህ ሦስት ጥቅሶች ከኢሳያስ መጽሐፍ የተለያዩ ሦስት ክፍሎች የተውጣጡ ናቸው፡፡ ዳንኤል – ኢየሱስ፣ ዳንኤል በእግዚአብሔር መንፈስ የተነዳ የመጪው ዘመን ጠቋሚ ነቢይ እንደሆነ ጠቅሷል (ማቴ 24፡15፤ ማር 13፡14)፡፡ ዮናስ – ኢየሱስ፣ የዮናስን መጽሐፍ ትክክለኛነትን በማቴ 12፡40፣ 41 ላይ አረጋግጧል፡፡ 4. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ቃላት በተመረጡ ሰዎች አማካኝነት ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጡ ናቸው፡፡ ሀ) “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ያላባቸው ናቸው፤ …” (2ጢሞ 3፡16) “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው” የሚለው የግሪክ አቻው theopneustos ሲሆን የቃል በቃል ፍቺውም “የእግዚአብሔር እስትንፋስ” ማለት ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ደራሲ ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ከቅዱሳት ሰዎች አንደበትና ብዕር የወጡት ቃላት “የእግዚአብሔር እስትንፋስ” ውጤቶች ናቸው (2ጴጥ 1፡21)፡፡ ለ) ዳዊት፣ ጽሑፎቹ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የተገኙ እንደሆነ ሲያረጋግጥ እናያለን፡፡ ዳዊት በርካቶቹን የዳዊት መዝሙር ክፍል የጻፈ ሰው ነው፡፡ ዳዊት እንዲህ ይላል፡- “የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ተናገረ፤ … (2ሳሙ 23፡2፤ በተጨማሪ 1ዜና 28፡11፣ 12 ይመልከቱ)፡፡ 5. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ አስተምህሮዎችን ለምን አጠናለሁ፣ ለምንስ እታዘዛቸዋለሁ? ሀ) ለመንፈሳዊ እድገት ቅዱሳት መጻሕፍት የመንፈሳዊ እድገታችን መንፈሳዊ ምግቦች ናቸው (ኤር 15፡16፤ ሕዝ 3፡1-3፤ 1ጴጥ 2፡2፤ 1ቆላ 3፡1፣ 2፤ ዕብ 5፡12-14) ለ) ከኀጢአት ለመጠበቅ የእግዚአብሔር ቃል ከኀጢአት እንዲርቁ ያደርጎታል፡፡ በአንጻሩ ኀጢአት ደግሞ ከእግዚአብሔር ቃል ያርቆታል (መዝ 119፡ 9፣ 11፣ 133) ሐ) ጤናንና ፈውስን ለመለማመድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትእዛዛትን መታዘዝ፣ አካላዊ ጤናና የፈውስ ውጤት አላቸው (ዘዳ 15፡26፤ መዝ 107፡20፤ 119፡50)፡፡ መ) ለመበልጠግ ኢያሱ መጽሐፍ ቅዱስ የያዘ የመጀመሪያ ሰው ነበር፡፡ ይህንን መጽሐፍ በማንበብና በመታዘዝ በረከትና ብልጥግና እንደሚያገኝ ቃል ኪዳን ተቀበለ (ኢያሱ 1፡8)፡፡ ፍሪያማና ውጤታማ ለመሆን የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮዎችን ያሰላስሉ (መዝ 1፡1-3)፡፡ ሠ) በእግዚአብሔር መንገድ ለመጓዝና አለማስተዋልን ለመበቀል ቅዱሳት መጻሕፍት የመንገዳችን መብራቶ ናቸው (መዝ 119፡104፣ 105)፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት አለማስተዋልን ይገፋሉ (መዝ 119፡130)፡፡ 6. የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮዎችን እንዴት ልማራቸው እችላለሁ? (ዮሐ 20፡31)፡፡ (ዮሐ 5፡39)፡፡ በየምዕራፉና በእየገጾቹ ላይ ኢየሱስን ይፈልጉ፡፡ (ሉቃስ 24፡44)፡፡ ሀ) በመንፈስ ቅዱስ መገለጥ ይማራሉ “ቃሉን ከመመገቦ” በፊት በጾሎት በእግዚአብሔር ፊት ይሁኑ፡፡ መንፈስ ቅዱስ እንዲያስተምርዎና ማስታልዎን እንዲቀባ ይጠይቁ (ዮሐ 14፡26፤ 1ቆሮ 2፡12-14፤ 1ዮሐ 2፡27)፡፡ ከአይኖችዎና ልብዎ ላይ መጋረጃ እንዲነሳና ብሉይ ኪዳንን መረዳት እንዲችሉ ይጸልዩ (2ቆሮ 3፡14-16)፡፡ መንፈስ ቅዱስ ማስተዋልዎን ይከፍትልዎ ዘንድ ይጸልዩ (ሉቃስ 24፡25፣ 27፣ 44፣ 45)፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በሚያነቡበት ወቅት “…የጥበብና የመገለጥ መንፈስ…” በልብዎና በአእምርዎ ላይ እንዲሆን ይጸልዩ (ኤፌ 1፡ 17፣ 18)፡፡ ለ) በመደበኛ ንባብ ይማራሉ በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስ ለማንበብ ቢያንስ 30 ደቂቃ ይፀልዩ፡፡ በየዕለቱ አንድ የመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ቢያነቡ መዝሙረ ዳዊትን በአመት ሁለት ጊዜ ማንበብ ይችላሉ ማለት ነው፡፡ ከምሳሌ መጽሐፍ በየዕለቱ አንድ ምዕራፍ ቢያነቡ ይህን መጽሐፍ በወር አንድ ጊዜ ያነባሉ ማለት ነው፡፡ ከብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ሦስት ገጾችን በየዕለቱ ቢያነቡ፣ በአመት ውስጥ ይህን መጽሐፍ አንብበው መጨረስ ይችላሉ፡፡ ከአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ሦስት ገጾችን በየዕለቱ ቢያነቡ፣ በአመት ውስጥ ሦስት ጊዜ ይህንን መጽሐፍ ያነባሉ ማለት ነው፡፡ በሚያነቡበት ወቅት፣ እርሳስ ወይም ሀይላይተር በመጠቀም እርሶ ስላሉበት ሁኔታ የሚናገሩ ክፍሎችን ወይም የባረኮት ጥቅስ ስር ያስምሩ፡፡ ሐ) በተቀናጀ አጠናን ይማራሉ በእዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ማጣቀሻ /Topical concordance/ ስር ያሉትን ዝርዝሮች በየዕለቱ ለ25 ደቂቃዎች ያጥኑ፡፡ ትምህርቶቹን በሚያጠኑበት ወቅት የሚያገኙዋቸውን እያንዳንዱን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ያንብቡ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስዎ ላይ ከጥቅሶቹ ትይዩ ወይም ግርጌ የግልዎን ማስታወሻዎች ያስፍሩ፡፡ ከ 55 ደቂቃ ንባብዎ ውስጥ አንድ ጥቅስ በመምረጥ ጥቅሱን ያጥኑ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ- ከስህተት የጸዳ፣ እንከን የሌለው፣ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ በመነዳት የጻፉት የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ Read More »

እግዚአብሔር በኃጢአት ልምምድ ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖችን ጸሎት ይሰማል?

ዛሬ ማለዳ ወደ መስሪያ ቤቴ እየሄድኩ በአይምሮዬ አንድ ሃሳብ ይዤ ከራሴ ጋር እሟገት ነበር። በልቤ ወደ እግዚአብሔር አንድ ጸሎት ጸለይኩ። በጸሎቴ ማብቂያ ላይ “እግዚአብሔር ጸሎቴን የሚሰማበት ምክንያት ምንድን ነው?” ብዬ ራሴን ጠየኩ። ሁላችን በክርስቶስ ስራ በአብ ፊት የመታየት ድፍረትና መብት እንዳለን ባውቅም፤ ጸሎታችንም ስለስሙ በአብ ዘንድ እንደሚሰማልን ብረዳም፤ ጉዳዩ እዚህ ላይ ብቻ እንደማያበቃና የኔ ድርሻ እንደሚቀር ያወቀችው ነፍሴ ነች እንግዲህ ይህን ጥያቄ እንዳነሳ የሞገተችኝ። እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል፤ የማንኛውንም ሰው ጸሎት ይሰማልም። መስማት ባይችል፣ ሁሉን አዋቂ አያደርገውምና (1ዮሐ. 3:20፤ መዝ. 139:1-4)። ሆኖም እዚህ ቦታ ላይ የተነሳው ጥያቄ እንድምታ እግዚአብሔር ያደምጣል/አያድምጥም ሳይሆን፣ በኃጢአት ልምምድ ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖችን ጸሎት ሰምቶ ምላሽ ይሰጣል ወይ ነው። ስለ ጸሎት አንስተን ስናወራ ከእግዚአብሔር ጋር ስላለን ጤናማ ሕብረት ማንሳታችን የግድ ነው። ጸሎት እና ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ጤናማ ሕብረት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸውና። ይህ ሕብረት ጤናማና ጠንካራ ሲሆን በእግዚአብሔር ፊት ጸሎታችን ሞገስ ይኖረዋል። ሲታመም ወይም ሲታወክ ደግሞ እግዚአብሔር ለጸሎቶቻችን ጀርባውን ይሰጣል። ለመሆኑ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ጤናማ ሕብረት ማለት ምን ማለት ነው? ጤናማ ሕብረት ማለት ያለሃጢአት መኖር ማለት አይደለም። እንዲህ አይነቱ ሕይወት በምድር ላይ የለምና። የጤናማ ሕብረት መለኪያዎች መንፈስ ቅዱስና ሕሊናችን ናቸው። በአሁኑ ሰአት ነፍሳችን ከመንፈስ ቅዱስና ከሕሊናችን ወቀሳዎች ነጻ ከሆነች፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ሕብረት ጤናማ ነው ማለት ነው። ነፍሳችን ከመንፈስ ቅዱስና ከሕሊናችን ወቀሳዎች ነጻ ናት ማለት ግን ፈጽሞ ሃጢአት የለብንም ማለት እንዳልሆነ ልብ ይበሉ። «ሕሊናዬ ንፁሕ ነው፤ ይህ ግን ጥፋት አልባ መሆኔን አያረጋግጥም፤ በእኔ ላይ የሚፈርድ ጌታ ነው።» (1ቆሮ 4፣4 አዲሱ መደበኛ ትርጉም) ከሕሊና ክስ ነጻ መሆናችን የሚያረጋግጠው ከበደል ነጻ መሆናችንን ሳይሆን ዛሬ ላይ (አሁን) ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ሕብረት ጤናማ መሆኑን ብቻ ነው። በተጓዳኝ፣ በመንፈስ ቅዱስ አልተወቀሰንም ማለት ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ሕብረት ጤናማ መሆኑን ያሳያል እንጂ ፍጹም (ከበደል የነጻን) መሆናችንን ከቶ አይናገርም። ይህንን ጉዳይ ይበልጥ ለመረዳት ከዚህ በታች የቀረበውን ምሳሌ አብረን እንመልከት። በሃሳባችን ወደ አንድ የቤታችን ክፍል ውስጥ እንግባ። በክፍሉ ያለውን አየር ስንቃኝ ሁል ጊዜ በአግባቡ የምንይዘው ክፍል ስለሆነ ንጹህ መስሎ ሊታየን ይችላል። ይህ ንጽህና ከእኛ እይታ አንጻር ነው። በክፍሉ አሁን ካለው ብርሃን የበለጠና የደመቀ የብርኃን ጨረር ቢያበራ ግን በቅፅበት በአየሩ ላይ ቀድሞ ያላስተዋልነውን ቁጥር ስፍር የሌለውን አቧራ ማየት እንጀምራለን። ይሄ እይታ ደግሞ የእግዚአብሔር እይታን ይወክላል፡፡ በዚህ መሳሌ ውስጥ አይናችን ሕሊናችንን፣ ደማቁ የብርሃን ጨረር ደግሞ መንፈስ ቅዱስን ይወክላሉ። በልባችን ያለውን ቆሻሻ አላየንም ማለት ቆሻሻው በልባችን ውስጥ ፈጽሞ የለም ማለት አይደለም። ከሕሊናችን ለጊዜ ተሰውሯል ማለት እንጂ። በልባችን ውስጥ ያለውን ቁጥር ስፍር የሌለው ሃጢአት አልተገነዘብንም ማለት የሃጢአቱን አለመኖር አያረጋግጥም። እግዚአብሔር ለጊዜው በእነዚህ ሃጢአቶች ተጠያቂ ሊያደርገን አልፈቀደም ማለት እንጂ። እግዚአብሔር ሁሉንም ሃጢአቶቻችንን በአንድ ጊዜ ወደ ግንዛቢያችን በማምጣት (ብርሃኑን በማብራት) ተገቢውን ምላሽ እንድንሰጥ አያደርግም። ይህ ሂደት የሕይወት ዘመን ነው። እንደደረስንበት መንፈሳዊ አቅም፣ በጊዜው የእኛን ትኩረት ሊያገኝ በፈለገው ጉዳይ (አቧራ) ላይ ብቻ ተጠያቂ እንድንሆን ያደርገናል፡፡ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚሰራው አንደ እንደ ደረስንበት የብስለት ደረጃ እና ከእርሱ ለመማር እንደምናሳየው ፈቃድ መጠን መሆኑን አንዘንጋ፡፡ መኖራቸውን ባላወቅን ወቅትም ቢሆን እንኳ የአቧራ ብናኞቹ በቦታቸው መኖራቸውን መዘንጋት የሌለብን ነጥብ ነው፡፡ ይህ ማለት ሃጢአተኝነት በማይሰማንም ወቅት ቢሆን እንኳ ሃጢአተኞች ነን ማለት ነው። ነገር ግን ይህ አይነቱ ሃጢአተኝነት አይደልም ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ሕብረት የሚያውከው። በመንፈስ ቅዱስ ብርሃን ለሕሊናችን አይን የተገለጡትና ዛሬ ላይ የምንወቀስበት ሃጢአቶች እንጂ። እዚህ ላይ የእኛ ሃላፊነት ሊሆን የሚገባው፣ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የነቃ ሕብረት በማድረግ የትኞቹን መረዳቶቻችንን እና የትኞቹን ባሕሪያቶቻችንን ሊለውጥ እንደፈለገ ማወቅና የንስሃ ምላሽ መስጠት ነው፡፡ ከላይ እንደተገለጠው ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ሕብረት ያሚታወከው ወይም ጸሎታችን ምላሽ ያሚያጣው መንፈስ ቅዱስ ወይም ሕሊናችን ዛሬ ተጠያቂ በሚያደርገን ማለትም በሚወቅሰንና ባልተናዘዝነው ሃጢአት ምክንያት ብቻ ነው። በልባችን ክፋትን ይዘን (መዝ. 66:18)፣ በአመጻችን ለመኖር ወስነን፣ ያለ እግዚአብሔር ፍርሃት ለመኖር መርጠን (ምሳሌ 1:28-30) እግዚአብሔር ጸሎታችንን ሰምቶ ምላሽ እንደሚሰጠን ብንጠብቅ ተሳስተናል። “በልቤስ በደልን አይቼ ብሆን ጌታ አይሰማኝም ነበር።” መዝ. 66:18 “ሃጢአትን በልቤ አስተናግጄ ቢሆን ኖሮ፣ ጌታ ባልሰማኝ ነበር።” መዝ. 66:18 (አዲሱ መደበኛ ትርጉም) “የዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፥ እኔ ግን አልመልስም፤ ተግተው ይሹኛል፥ ነገር ግን አያገኙኝም። እውቀትን ጠልተዋልና፥ እግዚአብሔርንም መፍራት አልመረጡምና፤ ምክሬን አልፈቀዱምና፥ ዘለፋዬንም ሁሉ ንቀዋልና፤” ምሳሌ 1:28-30 “እጃችሁንም ወደ እኔ ብትዘረጉ ዓይኔን ከእናንተ እሰውራለሁ፥ ልመናንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደም ተሞልተዋል።” ኢሳ. 1:15 “ሕግን ከመስማት ጆሮውን የሚመልስ ጸሎቱ አስጸያፊ ናት።” ምሳሌ 28:9 “ትለምናላችሁ ግን አትቀበሉም፤ ለራሳችሁ ስጋዊ ደስታ በማሰብ በክፉ ምኞት ትልምናላችሁና።” ያእቆብ 4:3 አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለታወከው ሕብረታችን ብቸኛው መፍትሄው ንስሃ መግባትና ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ሕብረት ማደስ ነው። ጸሎት ከዚህ ይጀምራል። ሕብረታችን ታሞ ልናደርግ የምንችለው የሚሰማ ጸሎት ቢኖር አንድ ብቻ ነው። እርሱም የንስሃ ጸሎት ይባላል (1ዮሐ. 1:9)። ከዛ በተረፈ ሕብረታችን ታውኮ ማለትም መንፍስ ቅዱስና ሕሊናችን ተጠያቂ በሚያደርገን ሃጢአት ላይ ጀርባ ሰጥተን የምንጸልየው ጸሎት የእግዚአብሔርን ፊት አያይም። ከንቱ ድክም ብቻ ይሆናል። ከዚህ የፍቅር አምላክ ጋር ጤናማ ሕብረት ፈጥረን ያምንኖርበትን ጸጋ እንያዝ። ጸሎታችንም በፊቱ ሞገስ ያግኝ። አሜን!!!

እግዚአብሔር በኃጢአት ልምምድ ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖችን ጸሎት ይሰማል? Read More »