የሕይወት እንጀራ አገልግሎት

ስለ እኔ፦ የአገልግሎቱ ራእይና ጥሪ ሰላም ለእናንተ ይሁን! እኔ አዳነው ዲሮ ዳባ እባላለሁ። ወደዚህ ድረ-ገጽ ስለመጡና የ"የሕይወት እንጀራ" ቤተሰብ ስለሆኑ እጅግ ደስ ብሎኛል። ይህ አገልግሎት የተወለደው በሕይወቴ ውስጥ ካለ አንድ ትልቅ እውነት ነው፤ እርሱም "ሰው በእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም" የሚለው መለኮታዊ ቃል ነው። 📖✨ 📜 ጥሪዬና ማንነቴ እግዚአብሔር በጸጋው በሰጠኝ ዘመን ሁሉ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ መምህር፣ ጽሐፊና ተርጓሚ በመሆን ሳገለግል ቆይቻለሁ። ቃሉን መመርመር፣ የተሰወሩ ዕንቁዎችን ማውጣትና ያገኘሁትን መንፈሳዊ ምግብ ለሌሎች ማካፈል የልቤ ትርታ ነው። ✍️ የአገልግሎቴ መሪ ቃል "ኢየሱስ፣ የነፍስ ምግብ" የሚል ሲሆን፣ ዓላማዬም በዕለት ተዕለት ሕይወት ሩጫና ድካም ውስጥ ለሚገኙ ነፍሳት የማይለወጠውንና የማይጠፋውን የክርስቶስን ወንጌል በተለያዩ ትምህርቶች ማድረስ ነው። 🌍 ከየት ወደ የት? በአሁኑ ሰዓት በዩናይትድ ስቴትስ የምኖር ቢሆንም፣ ልቤና ሐሳቤ ግን ሁልጊዜም በኢትዮጵያና በዓለም ዙሪያ ካሉ ወገኖቼ ጋር ነው። በአካል ብንራራቅም፣ በቴክኖሎጂ አማካኝነት ይህንን የወንጌል ድልድይ በመገንባት የጌታን ቃል በየቤታችሁ ለማድረስ እተጋለሁ። በተለይም በሕይወት ታሪኬና በተለያዩ የሥልጠና ጽሑፎቼ አማካኝነት እግዚአብሔር በሕይወቴ ውስጥ የሠራውን ተአምርና ያስተማረኝን ጥልቅ ትምህርቶች ለእናንተ ለማካፈል በዝግጅት ላይ እገኛለሁ። 🌱🕊️ 🤝 አብረን እንጓዝ በዚህ ድረ-ገጽ የምታገኟቸው ትምህርቶች ሁሉ ከጸሎትና ከጥልቅ ጥናት በኋላ የሚቀርቡ "የነፍስ ምግቦች" ናቸው። ዓላማዬ በክርስቶስ እንድታድጉ፣ በመንፈሳዊ ማንነታችሁ እንድትጸኑና የተሰጣችሁን የሰማይ መክሊት እንድትጠቀሙ መርዳት ነው። በዚህ የመንፈሳዊ ጉዞ አብረን እንድንጓዝ፣ እንድንማማርና አብረን እንድንጸልይ በታላቅ አክብሮት እጋብዛችኋለሁ።🙏🌟

ኀጢአትና ሕግ

ሀ) የሕግ፣ የተወሰነ ጊዜ አገልግሎት – ሕጉ የሚጠይቀው ጽድቅ እስኪፈጽም ድረስ ይኖራል – ማቴ 5፡18 – ክርስቶስ ኢየሱስ ሕግን ፈፅሟል – ማቴ 5፡17-18፤ ሉቃስ 24፡44 – በመንፈስ በምንመላለስ በእኛ – ሮሜ 8፡3-5 – ፍቅር ሕግን ይፈጽማል – ሮሜ 13፡8-10፤ ገላ 5፡14፤ ያዕ 2፡8 – አንዱ የሌላውን ሸክም በመሸከም ሕግ ይፈጸማል – ገላ 6፡2 ለ) ድነት በተስፋ (ጸጋና እምነት) – ሕግ ከመስጠቱ በፊት – በአብርሃም ውስጥ – – አብርሃም ሕግ እንደፈጸም ሆኖ ተቆጠረለት – – ሕግ ከተሰጠ በኃላ – በኢየሱስ ውስጥ – – ሕግ እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ ይሰራ ነበር – ሉቃስ 16፡16 – ከመጥመቁ ዮሐንስ በኃላ ወንጌል ተሰበከ – ሉቃስ 16፡16 ሐ) የሕጉ ይዘት – የብሉይ ኪዳን ይዘት – አስርቱ ትዕዛዛት – ዘጸ 20፡3-17፤ ዘዳ 5፡7-21 – የሌዋዊያን ሕጎች – ዘጸ፤ ዘሌ፤ ዘዳ – በአዲስ ኪዳን ያለው የሕግ መረዳት – ታላቂቱ ትዕዛዝ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብ መውደድ ነው – ማቴ 22፡36-40፤ ሉቃስ 10፡26-27 – ቀጣዩ ታላቅ ትዕዛዝ ደግሞ ሌሎችን እንደራስ አድርጎ መውደድ ነው – ማቴ 22፡39፤ ሉቃስ 10፡27 – የሕግ ዋነኞች – ፍትሕ፣ ምሕረት፣ ታማኝነት – ማቴ 23፡23 – ኢየሱስ ከሕግ በላይ ነው – ዮሐ 8፡5-9፤ ማቴ 12፡8 መ) የሕግ አላማ – ለኀጢአተኞች ተሰጠ – 1ጢሞ 1፡9 – ሕግ ለተዋጁ ሳይሆን ፈሪሃ እግዚአብሔር ለሌላቸው ተሰጠ – ሮሜ 4፡15 – ሕግ ፊሪሃ እግዚአብሔር በሌላቸው ላይ የእግዚአብሔርን ቁጣ ይገልጣል – ገላ 3፡19 – ሕግ በሰው አምሳል ተገልጧል – ገላ 3፡23 – እምነት ሲመጣ ከሕግ ነፃ ወጥተናል – ገላ 3፡23 – በእግዚአብሔር መንፈስ ከኀጢአት እስራት ነፃ ወጥተናል – ገላ 5፡13-18 – ሕጉ ወደ ፊት ሊመጡ ላሉት ጥላ ነው – ዕብ 10፡1 – የኀጢአት ግንዛቤ (እውቀት) እንዲኖረን ያደርጋል – ሮሜ 3፤ 20፤ 7፡7 – ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያደርስ ሞግዚታችን ነው – ገላ 3፡23-29 ረ) የሕጉ ውጤቶች – ለኀጢአት ኀይል ሰጠው – 1ቆሮ 15፡56 – ያለሕግ ኀጢአት አይቆጠርብንም – ሮሜ 5፡13 – ሰዎች ሕግን መጠበቅ አልቻሉም – – ፍፁም መታዘዝን ይጠይቃል – ዘዳ 27፡26፤ ገላ 3፡10-11፤ ያዕ 2፡10 – ማንም ሙሉ በሙሉ ሕግን ሊታዘዝ አይችልም – ሮሜ 3፡10 – እስራኤላውያን ሕግን መጠበቅ አልቻሉም – ኢሳ 42፡24፤ ኤር 9፡13፤ ዳን 9፡11 – ሰው ሁሉ በእግዚአብሔር ጸጋ ሊጸድቁ ይገባል – ሮሜ 3፡19-24 – ከሰው ኀጢአተኝነት የተነሳ ሕግ ሊያድን አልቻለም – ሮሜ 8፡3 – ሕጉ ማንንም ፍጹም ሊያደርግ አልቻለም – ዕብ 7፡19፤ ገላ 2፡16 – ለእግዚአብሔር ለመኖር በሕግ በኩል ለሕግ ሞተናል – ገላ 2፡19-21 ሠ) ክርስቶስ ኢየሱስ የሕግ ፍፃሜ ነው – ሕጉ እስከ መጥምቁ ዮሐንስ በስራ ላይ ነበር – ሉቃስ 16፡16 – ከመጥምቁ በኃላ ግን ወንጌል መሰበክ ተጀመረ – ሉቃስ 16፡16 – ቤተ ክርስቲያን የሙሴን ሕግ የመጠበቅ ግዴታ የለባትም – ሐዋ 15፡5-12፤ ሮሜ 6፡14 – ይህ ግን የኀጢአት ፈቃድ አይደለም – ሮሜ 6፡15 – ሕግን በመፈጸም ሳይሆን በእምነት ጸድቀናል – ሮሜ 3፤ 28 – ክርስቶስ የሕግን ፍላጎት ፈጽሟል – ማቴ 5፡17 – ክርስቶስ በሞት ሕግን ሻረ – ኤፌ 2፡15-17፤ ሮሜ 10፡3-4 – ክርስቶስ ከሕግ እርግማን ነፃ አወጣን – ገላ 3፡13 ሸ) ከእግዚአብሔር ጋር አዲስ ኪዳን – አዲሱ ኪዳን (ጸጋና እምነት) የሕጉን ፍላጎት በልባችን ይፈጽማል – ዕብ 8፡10-13፤ 10፡16-17 – ወንጌል የሚለውን ርዕስ ይመልከቱ – ክፍል ረ3

ኀጢአትና ሕግ Read More »

የኀጢአት ምንነት

ሀ) ሃጢአት ማለት ምን ማለት ነው? የሚከተሉት ንዑስ ርዕሶች ኀጢአትን ይበይናሉ፡፡ ኀጢአት በእግዚአብሔር ማመጽ ማለት ነው፡፡ ሁሉ ኃጢአትን ስለሠሩ (ሮሜ 3፡23)፣ ከእግዚአብሔር ፍቅር በመለየት ሁሉም ከአግዚአብሔር ጋር ጠላቶች ሆነዋል – ዘዳ 9፡7-8፤ ኢያሱ 1፡18፤ ኢሳ 59፡2 – የመጀመሪያው ኀጢአት ግንኙነታችንን አበላሸ – ዘፍ 3፡1-24 – ጣኦትን ማምለክ ኃጢአት ነው – ዘጸ 32፡31፤ 1ነገ 12፡28-30፤ ኢሳ 31፡7፤ ኤር 17፡3፤ 32፡3፤ 32፡35፤ ሕዝ 23፡49፤ ሆሴዕ 13፡2 – ለሃሰተኛ አማልክት ዕጣን ማጠን ኃጢአት ነው- ኤር 44፡23 – ጥንቆላ ኃጢአት ነው- 1ሳሙ 15፡23 – ሕግን መተላለፍ ኃጢአት ነው – ዘሌ 16፡16፤ ነህ 1፡6-7፤ 1ዮሐ 3፡4 – ለእግዚአብሔር ትዕዛዛት አለመታዘዝ ኃጢአት ነው – ዘጸ 9፡27፣ 34፤ 10፡16-17፤ ዘሌ 5፡17 – ኀጢአት ባለማስተዋል (ሳያውቁ) ሊሰራ ይችላል – ዘሌ 4፡2፣ 13፣ 22፣ 27፤ 5፡15፣ 17 – ኀጢአት በድብቅ ሊሰራ ይችላል – መዝ 90፡8፤ ምሳሌ 28፡13 – ዐመጽ ሁሉ ኃጢአት ነው- 1ዮሐ 5፡17 – ወሲባዊ ኢ-ሞራላዊነት ኃጢአት ነው፣ ትዳርና ቤተሰብ የሚለውን ርዕሰ ጉዳዩ ይመልከቱ – ክፍል ሰ9. – ግብረ ሰዶማዊነት ኃጢአት ነው – ዘፍ 9፡22፤ 18፡20፤ 19፡5-9፤ ዘሌ 18፡22፤ ሮሜ 1፡24-27፤ 1ቆሮ 6፡9 – ከእንስሳት ጋር ወሲብ መፈጸም ኃጢአት ነው – ዘሌ 18፡23 – ከዘመድ ጋር ወሲብ መፈጸም – ዘፍ 19፡33-39፤ ዘሌ 18፡6-20 – በዘመድ መካከል በተደረገ ግንኙነት የተገኘ ዘር ኀጢአት ነው (ሞአብና አሞን) – ዘዳ 23፡3፤ መሳ 10፡6፤ 1ነገ 11፡4፣ 7፤ 2ነገ 21፡ – ምንዝርና ኃጢአት ነው – ማቴ 5፡32፤ ሐዋ 15፡20-29፤ 1ቆሮ 5፡1፣ 11፤ 10፡8 – ጣኦት ማምለክ ኃጢአት ነው – ዘፍ 20፡7-9፤ 39፡7-10፤ 1ቆሮ 6፡9፤ 7፡2፤ ገላ 5፡19 – መልካምን ነገር ማድረግ እንዳለብን እያወቅን አለማድረግ ኃጢአት ነው – ዘሌ 5፡1፤ ያዕ 4፡17 (ባለማድረግ የሚሠራ ኀጢአት) – የስንፍና አሳብ ኃጢአት ነው – ምሳሌ 24፡9 – ከንቱ ንግግር ወይም የቃል ብዛት ኃጢአት ነው – ምሳሌ 10፡19 – ንቀት፣ ትዕቢት ኃጢአት ነው – ምሳሌ 14፡21፤ 21፡4 – አለማመን እና ያለእምነት የሚደረግ እርምጃ (ድርጊት) ኃጢአት ነው – ሮሜ 14፡23፤ ዕብ12፡16፤ ራዕ 2፡14፣ 20፤ 9፡21 ለ) ኀጢአት በሚከተሉት መንገዶች ተገልጿል – በአዳም አማካኝነት ወደ አለም ገባ – ዘፍ 3፡1,24፤ ኢሳ 43፡27፤ ሮሜ 5፡12 – የዲያብሎስ ነው – 1ዮሐ 3፡8፤ ዮሐ 8፡44 – የጨለማ ሥራ ነው – ኤፌ 5፡11-14 – ለማጥቃት በበር ቆሞ ያደባል – ዘፍ 4፡7 – ከልብ ይመነጫል – ማቴ 15፡19-20 – የምኞት ውጤት ነው – ያዕ 1፡15 – በዘር በኩል ይመጣል – ዘጸ 20፡5፤ መዝ 37፡28፤ ምሳሌ 14፡11 – የሰው ልጆች መከራና ጭንቀት ምክንያት ነው – ኢዮብ 15፡20፤ ምሳሌ 13፡15፤ ሮሜ 2፡9ማመካኛ የለውም – ሮሜ 1፡20፤ 2፡1፤ ዮሐ 15፡22 ሐ) ኀጢአት ያደረገ  ወይም ያለበት ማነው? – ኀጢአትን ያላደረገው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው – 2ቆሮ 5፡21፤ ዕብ 4፡15፤ ዕብ 7፡26፤ 1ዮሐ 3፡5 – ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የሰው ልጅ ከኀጢአት በታች እንደሆኑ ይናገራሉ – ገላ 3፡22፤ መዝ 53፡3 ፤ ኢሳ 53፡6 – ሁሉ ኀጢአትን አድርገዋል – 1ዮሐ 1፡8፤ 1ነገ 8፡46፤ ሮሜ 3፡23 – በዘር ሁላችን ኀጢአተኞች ነን – ኢዮብ 15፡14፤ ኢዮብ 25፡4፤ መዝ 51፡5፤ ሮሜ 5፡12-19፤ 1ቆሮ 15፡21-22 – ሴት የኀጢአተኛው አዳም አምሳል ነበር – ዘፍ 5፤ 3 – በሁለንተናችን ኀጢአትን ሰርተናል – በተግባራችን (በአካላችን /በሰውነታችን) – ገላ 5፡17-21 – በዝንባሌዎቻችን (በነፍሳችን) – ማቴ 5፡21-22፤ ያዕ 2፡8-9 – በኀጢአት ሁኔታ ውስጥ ነን (በመንፈሳችን) – ዮሐ 16፡8-9 – ስለዚህ ሁሉ ኀጢአተኛ ነው – ሮሜ 3፡23 መ) የኀጢአት ውጤት – ከእግዚአብሔር ይለያል – ዘፍ 3፡23፣ 24፤ ኢሳ 59፡2 – ኀጢአተኞችን ከመንግስተ ሰማይ ይለያቸዋል – 1ቆሮ 6፡9፤ ገላ 5፡19-21፤ ኤፌ 5፡5-7፤ ራዕ 21፡27 – ሞትን ያመጣል – ዘፍ 3፡2-3፤ 19፤ ያዕ 1፡15፤ ሮሜ 6፡23፤ ሕዝ 18፡4 – የእግዚብሔርን ቁጣ ያመጣል – ዘጻ25፡16፤ ምሳሌ 6፡16-19፤ 1ነገ 16፡2 – የእግዚአብሔርን እርግማን ያመጣል – ምድር በኀጢአት ምክንያት ተረገመች – ዘፍ 3፡17-18 – ድካምና ላብ የኀጢአት ውጤቶች ናቸው – ዘፍ 3፡16፣ 17፣ 19፤ ኢዮብ 14፡1 – በምጥ ጊዜ ሕመም የኀጢአት ውጤት ነው – ዘፍ 3፡16 – ፍጥረት በእስራት ውስጥ – ሮሜ 8፡21-22 – አደጋ ያስከትላል – ድርቅ – ኤር 5፡24፤ 2ዜና 6፡26-28፤ – ጦርነት – 2ዜና 6፡36-39 – በሽታ – መዝ 38፡3 – አገራዊ ችግር – ምሳሌ 14፡34፤ ኤር 8፡14-16፤ 2ዜና 25፡4 – የእግዚአብሔርን ፍርድ ያመጣል – የአሁን ጊዜ – ኢሳ 13፡11፤ አሞፅ 3፡2፤ ኤር 5፡25፤ ሉቃስ 12፡47፤ ሮሜ 2፡8-9 – የሚመጣ ጊዜ ቅጣት – ማቴ 18፡18፤ ማር 3፡29፤ ሉቃስ 3፡17፤ 2ተሰ 1፡9፤ 2ጴጥ 2፡9፤ ራዕ 14፡11፤ ራዕ 20፡15 ሠ) ለኀጢአት ችግር እግዚአብሔር ያዘጋጀው መፍትሄ – ወንጌል የሚለውን ርዕስ ይመልከቱ – ክፍል ረ3 ፣ ረ4 ፣ ረ5 – ድነት የሚለውን ርዕስ ይመልከቱ – ክፍል ሠ2 – ሞትና የመጨረሻው ዘመን የሚለውን ርዕስ ይመልከቱ – ክፍል ሸ

የኀጢአት ምንነት Read More »

ጥንቆላ

ሐ6. የክፋትና የአስማት ሰራተኞች ሀ) ምዋርት (ጥንቆላ፣ አስማት፣ መናፍስት መጥራት) የአሕዛብ አገሮች አስማትን፣ ምዋርትንና የሙታን መንፈስ መሳብን ተለማምደዋል፡፡ – የኀጢአተኛ ባሕሪ ((አዳማዊ ባሕሪ) ተግባራት (ጥንቆላ) – ገላ 5፡19-21 – በልዓም ለምዋርቱ ዋጋን ተቀበለ – ዘኁ 22፡7 – ፍልስጤማዊያን ምዋርተኞች ነበራቸው – 1ሳሙ 6፡2 – የባቢሎን ንጉሥ ምዋርትን ተጠቅሟል – ሕዝ 21፡21-23 – ፈርኦን አስማተኞቹን አማክሮ ነበር – ዘፍ 41፡24 – የናቡከደነጾር አስማተኞች ሕልሙን ሊፈቱ አልቻሉም – ዳን 2፡2፤ 4፡7 – በርያስስ ወይም ኤልማስ ጠንቋይ ነበር – ሐዋ 13፡6-12 – የጥንቆላ መንፈስ ያደረባት ሴት – ሐዋ 16፡16 – በኤፌሶን የጥንቆላ መጻሕፍት ተቃጠሉ – ሐዋ 19፡17-20 – የእርኩሷ ከተማ ባቢሎን አስማት – ራዕ 18፡23 የተከለከለና በእግዚአብሔር የሚያስቀጣ ነው – ማንኛውም አይነት አስማት ሥራ በእግዚአብሔር ዘንድ ፈፅሞ የተከለከለ ነው – ዘዳ 18፡9-13 – አስማትና ከሙታን መንፈስ ጋር ማውራት በእግዚአብሔር የተከለከለ ነው – ኢሳ 8፡19-20 – የምስራቅ ሰዎች ከንቱ አምልኮና ምዋርት በፍርድ ስር ሆንዋል – ኢሳ 2፡6 – እግዚአብሔር መተተኞችን አጠፋለሁ በማለት ዝቷል – ሚክ 5፡12 – በእግዚአብሔር አይን ሁሉም የጣኦት አምል አፀያፊ ነው – 2ነገ 17፡17 – እግዚአብሔር በመተተኞች ላይ ይፈርዳል – ሚኪ 3፡5 – አስማተኞች ወደ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም አይገቡም – ራዕ 21፡8 – እግዚአብሔር መናፍስት ጠሪዎችን ይቃወማቸዋል – ዘሌ 20፡6 – ሳኦል የሳሙኤልን የሙት መንፈስ ፈለገ – 1ሳሙ 28፡11 – ሳኦል መናፍስት ጠሪን ስለጠየቀ ሞተ – 1ዜና 10፡13 32 – መተተኛ በሕይወት እንዲኖር አይፈቀድለትም ነበር – ዘጸ 22፡18 – ወደመናፍስት ጠሪዎና ጠንቋዮች መሄድ ያረክሳል – ዘሌ 19፡31 ለ) ሐሰተኛ ምልክቶችና ተአምራት – የሰይጣን አገልጋዮች አስደናቂ ምልክቶች ሊያደርጉ ይችላሉ – ራዕ 16፡14፤ 2ተሰ 2፡9-12፤ ማቴ 24፡24፤ ዘጸ 7፡11፣ 22 – በሕገወጥ መሪዎች ዘመን ሐሰተኛ ምልክቶችና ድንቆች – ማቴ 7፡22-23 – የመጨራሻው ዘመን ሐሰተኛ ምልክቶችና ድንቆች – ማቴ 24፡24 – ሁለተኛው አውሬ ድንቅና ታላላቅ ተአምራቶችን ያደርጋል – ራዕ 13፡13 – ስድስት የቁጣ ድንቆች – አጋንንት ድንቅን ያደርጋሉ – ራዕ 16፡13-14፤ 19-20 ሐ) እግዚአብሔር ከአስማት ሃይል በላይ ብርቱ ነው – የፈርኦን አስማተኞች ተአምራትን አደርገዋል – ዘጸ 7፡11 – አስማተኞቹ ከውሃ ውስጥ ጓጉንቸሮች እንዲወጡ አደረጉ – ዘጸ 8፡7 – ሳኦል የገለጋት በዓይንዶር ትገኝ የነበረች መናፍስት ጠሪ – 1ሳሙ 28፡7-9 – ጠንቋዮ ስምኦን – ሐዋ 8፡9-11 – ሐሰተኛ ነቢይና ጠንቋዩ በርያስስ ወይም ኤልማስ – ሐዋ 13፡6-8 – የጥንቆላ መንፈስ የነበረባት ሴት – ሐዋ 16፡16

ጥንቆላ Read More »

ሰይጣን – አጋንንት

ሀ) መግቢያ – የተወሰኑ መላእክት በእግዚአብሔር ተጥለዋል – 2ጴጥ 2፡4፤ ይሁዳ 6 – ርኩሳን መናፍስት በሰዎች ውስጥ ሊያድሩ ይችላሉ – ማቴ 12፡43፤ ማር 1፡26፤ 5፡9፤ 7፡24-30፤ 9፡14-27፤ 16፡19 – የማያምኑ ሰዎች እርኩሳን መናፍስትን ለማስወጣት ቢሞክሩ ያለው አደጋ – ሐዋ 19፡12-16 – አጋንንት አታላይ መናፍስት በመባል ተጠርተዋል – 1ጢሞ 4፡1 – አጋንንት የሚሉትን ፈፅመው አይመኑ፣ ውሸተኞች ናቸውና – ዮሐ 8፡44 – ከአጋንንት ጋር አያውሩ – አስወጧቸው እንጂ – ማር 16፡15-18 – አጋንንት እግዚአብሔር እንዳለ ያምናሉ – ያዕ 2፡19 – ተአምራትና ማድረግ ይችላሉ – ራዕ 16፡14፤ 2ተሰ 2፡9-12፤ ማቴ 24፡24፤ ዘጸ 7፡11፣ 22 ለ) አማኞች በአጋንንት ላይ ስልጣን አላቸው – በእኛ ውስጥ ያለው ኢየሱስ በአለም ካለው ሰይጣን ይበልጣል – 1ዮሐ 4፡4 – አጋንንት ያለፈቃድ በአሳማዎቹ ውስጥ አልገቡም – ማቴ 8፡30-32 – ሐዋሪያት በአጋንት ላይ ስልጣን ተሰጣቸው – ሉቃስ 9፡1 – ሰባ የሚሆኑ የኢየሱስ ተከታዮች አጋንንትን እንዲያወጡ ተላኩ – ሉቃስ 10፡1፣ 17 – ደቀ መዛሙርት ሁሉ አጋንንትን እንዲያወጡ ሥልጣን ተሰጣቸው – ማቴ 10፡1፤ ማር 16፡17 – ክፉ መናፍስት ለማውጣት የተሰጠ ተስፋ – ሉቃስ 10፡18-20 – ጳውሎስ የጥንቆላ መንፈስን አስወጣ – ሐዋ 16፡16 – አጋንንት በእምነት ቃል እና በሥልጣን ይወጣሉ – ሉቃስ 4፡32-36 ሐ) ሰይጣን – ስያሜዎቹና ታሪኩ 1) የሰይጣን ስያሜዎች፣ በሕሪያቶቹን ይገልጣሉ – ሉሲፈር (የብርሃን መልአክ) በሰማይ ሳለ የሚጠራበት ስሙ – ኢሳ 14፡12 – ሰይጣን (ተቃዋሚ) – ማቴ 4፡10፤ 1ዜና 21፡1፤ ኢዮብ 1፡6፤ ዘካ 3፤ 1 – እባብ፣ የጥንቱ እባብ – ዘፍ 3፡1፣ 4፤ ራዕ 12፡9 – ዘንዶ፣ እባብ፣ ዲያብሎስ፣ ሰይጣን – ራዕ 12፡9፤ 20፡2 – ዲያብሎስ (ሃሰተኛ ከሳሽ) – ማቴ 4፡1፣ 5፣ 8፤ ኤፌ 6፡11-12፤ ራዕ 12፡9 – ፈታኝ – ማቴ 4፡3፤ 1ተሰ 3፡5 – ብዔልዜቡል (የእበት አምላክ) – ማቴ 12፡24፤ ማር 3፡22 – የአጋንንት ወይም የዲያብሎስ አለቃ – ማቴ 12፡24፤ ማር 3፡22 – ክፉው – ማቴ 13፡19 – የዚህ አለም ገዢ – ዮሐ 13፡31፣ 14፡30፤ 16፡11 – ነፍሰ ገዳይ፣ ሃሰተኛ – ዮሐ 8፡44 – የዚህ አለም አምላክ – 2ቆሮ 4፡4፤ ዮሐ 12፡31፤ 14፤ 30፤ 16፡11 – ቤልሆር (ምናምንቴነት) – 2ቆሮ 6፡15 – በአየር ላይ ያሉ መንፈሳዊያን ኀይላት ገዢ – ኤፌ 2፡2 – ባላንጣ፣ ዲያብሎስ (ጠላት) – 1ጴጥ 5፡8 – አታላይ – ራዕ 12፡9 – የወንድሞች ከሳሽ – ራዕ 12፡10 – ከዚህ በታች ያሉ ስሞችም ለሰይጣን የተሰጡ ስያሜዎች ሳሆኑ አይቀሩም – የጥልቁ ጉድጓድ መልአክ – ራዕ 9፡11 – አጶልዮን፣ አብዶን (አጥፊ) – ራዕ 9፡11 2) ሰይጣን ከሚከተሉት ጋር ተነጻጽሯል – እባብ – ዘፍ 3፡1፤ ራዕ 12፡9፤ 20፡2 – አዳኝ ወፎች (fowler) – መዝ 91፡3 – እንክርዳድ ዘሪ – ማቴ 13፡25 – ተኩላ – ዮሐ 10፡12 – የሚያገሳ አንበሳ – 1ጴጥ 5፡8 3) ስለ ሰይጣን አጠቃላይ ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ሰለሰይጣን በርካታ ትምህርቶች አሉ፡፡ – ፍጡር ነው – ሕዝ 28፡13 – በሰማይ ሳለ “ሉሲፈር” በመባል ይጠራ ነበር – ኢሳ 14፡12 – በእግዚአብሔር፣ ጠባቂ ኪሩብ ተብሎ ተቀብቶ ነበር – ሕዝ 28፡14 – በተቀደሰው በእግዚአብሔር ተራራ – ሕዝ 28፡14 – የፍፅምና ተምሳሌት (የጥበብና የውበት) ነበረ – ሕዝ 18፡12፣ 15 – በእግዚአብሔር ገነት፣ በዔደን ነበር – ሕዝ 18፡13 – በመጀመሪያ በሰማይ ነበር ከዛ ተባረረ – ሉቃስ 10፡18 – በእግዚአብሔር ላይ አመጸ – 1ዮሐ 3፡8 – በደል በእርሱ ተገኘ – ሕዝ 28፡15 – በውበቱ ምክንያት በመኩራት – ሕዝ 28፡17 – የሰይጣን መውደቅ ምክንያቶች – ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ – ኢሳ 14፡13 – ዙፋኔንም ከእግዚአብሔ ከዋክብት በላይ ከፍ አደርጋለሁ – ኢሳ 14፡13 – … በተራራ ላይ እቀመጣለሁ – ኢሳ 14፤ 13 – ከደመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ – ኢሳ 14፡14 – በልዑል እመሰላለሁ – ኢሳ 14፡14 – የክፉ መናፍስት አለቃ፣ ክፉ መላእክት፣ አጋንንት – ማቴ 12፡24-28 – አንዳንድ ሰዎች ሰይጣን፣ አዳም ከመፈጠሩ በፊት፣ በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ባለቤት ለመሆን እንደፈለገ ያምናሉ፡፡ – ሰይጣን አለም የእርሱ እንደሆነች ተናግሯል – ማቴ 4፡8-9 – አዳም ምድርን እንዲያስተዳድር በእግዚአብሔር ተሰጥቶት ነበር – ዘፍ 1፤ 28 – ሔዋንን በዔደን ገነት አሳታት – ዘፍ 3፡1-7 – በእግዚአብሔር ተረገመ – ዘፍ 3፡14 – የሰው ልጅ ጠላት ነው – ዘፍ 3፤ 15 – በኢዮብ ዘመን፣ ሰይጣን ወደ እግዚአብሔር ይቀርብ ነበር – ኢዮብ 1፡6 – አሁንም ድረስ የወንድሞች ከሳሽ በመባል ይጠራል – ራዕ 12፡10 – ኢየሱስን ባይሳካለትም ፈተነው – ማቴ 4፡3፣ 4 – የብርሃን መልአክ መስሎ ሊቀርብ ይችላል – 2ቆሮ 11፡14 መ) የሰይጣንና የመላእክቱ የመጨረሻ እጣ ፈንታ – ቅዱሳን በመላእክት ላይ ይፈርዳሉ – 1ቆሮ 6፡3 – ሰይጣን በእግዚአብሔር ስልጣኑ ይነጠቃል – ዘፍ 3፡15፤ ራዕ 20፡10 – ሰይጣን ከሰማይ ሲወድቅ ኢየሱስ መመልከቱን ተናገረ – ሉቃስ 10፡18 – በአየር ላይ ላሉት መንፈሳዊያን ኀይላት ገዢ – ኤፌ 2፡2 – ሰይጣን ከእግዚአብሔር ተራራ ተጥሏል – ሕዝ 28፡16 – በምድር ላይ ተጥሏል – ሕዝ 28፡17፤ ራዕ 12፡10-13 – ለአንድ ሺ አመት በሰንሰለት ይታሰራል – ራዕ 20፡1-3 – ሰይጣን በእሳት ባሕር ይጣላል – ማቴ 25፡41፤ ሕዝ 28፡18፤ ራዕ 20፡10 – የመዳን ተስፋ የላቸውም – ይሁዳ 6፤ 2ጴጥ 2፡4፤ ማቴ 25፡41 – የዘላለም እሳት ተዘጋጅቶላቸዋል – ማቴ 25፡41 ሠ) ሰይጣን – ሥልጣንና ግብሩ 1) አካል አለው፣ የሆነ ሃይል ወይም ተጽእኖ ፈጣሪ አይደለም – ኢየሱስን በፈተነው ወቅት ከኢየሱስ ጋር ምልልስ አድርጓል – ማቴ 4፡1-11 – ይናገራል – ዘፍ 3፡1፤ ማቴ 4፡3 – ኢየሱስ ነፍሰ ገዳዩ፣ ውሸታም ብሎ ጠርቶታል – ዮሐ 8፡44 – ተንኮለኛ ነው፣ ራሱን መለዋወጥ ይችላል – 2ቆሮ 11፡3፣ 14 – ከእግዚአብሔር ጋር ምልልስ አድርጓል – ኢዮብ 1፡6-12፤ 2፡1-6 – ይራመዳል፣ ያገሳል – 1ጴጥ 1፡8 – ሊታሰር ይችላል – ራዕ 20፡1-3 2) የሰይጣንና የወደቁ መላእክቶቹ ስልጣንና ግብር – ጻድቃንን መቃወምና ማሰቃየት – ኢዮብ 1፡12-19፤ 2፡5-7፤ ዘካ 3፡1 – በበሽታ – ሉቃስ 13፡16፤ ማቴ 17፡15-16 – በአጋንንት – ማር 5፡15፤ 6፡13፤ 16፡19 – ሰዎችን ለማጥፋት መሞከር – በፈተናዎች – 1ዜና 21፡1፤ 1ተሰ 3፡5 ሔዋን – ዘፍ 3፡1-7 ዳዊት – 1ዜና 21፡1 ይሁዳ – ሉቃስ 22፡1-6 ኢዮብ – ኢዮብ 1፡6-12 ክርስቶስ – ማቴ 4፡1-11 ሃናንያና ሰጲራ – ሐዋ 5፡1-11 – በውሸት – ዮሐ 8፡44 – በሞት ላይ ኀይል አለው – ዕብ 2፡14-15 – ወንጌል ለማጥፋት ይጥራል – ማቴ 13፡19፤ 2ቆሮ 4፡4 – የእግዚአብሔርን ሥራና ሠራተኞቹን መቃወም – ዘካ 3፡1፤ 1ተሰ 2፡18፤ ዳን 10፡19-14 – ቅዱሳት መጻሕፍትን ማጣመም – ማቴ 4፡6 እና መዝ 91፡11-12 – ምልክቶችና ድንቆችን ማድረግ ይችላል – 2ተሰ 2፡8-9፤ ራዕ 13፡11-15 – የአጋንንት ጥናት (ሥነ-አጋንንት በተጨማሪ ይመልከቱ – ክፍል ሐ5) 3) የሰይጣን ኀይልና የስልጣን ገደብ – ኢየሱስ የሰይጣንን ሥራ ለማፍረስ መጣ – ዕብ 2፡14፤ 1ዮሐ 3፡8 – ኢየሱስን የፈተነበት ወጥመድ አልተሳካም – ሉቃስ 4፡13 – ሰይጣን በኢየሱስ ላይ ምንም ኀይል የለውም – ዮሐ 14፡30 – ኢየሱስ ርኩሳን መናፍስትን አስወጥቷል – ሉቃስ 11፡20፤ 13፡32 – ደቀ መዛሙርት አጋንንትን ያወጡ ዘንድ ኀይል ተሞልተው ነበር – ማቴ 10፡1፤

ሰይጣን – አጋንንት Read More »

መላእክት – የእግዚአብሔር መልእክተኞች

ሀ) መላእክቶች ማን ናቸው? መላእክት በመጽሐፍ ቅዱስ በርካታ ጊዜ የተጠቀሱ ቢሆንም፣ የተጠቀሱበት አላማ እኛን ስለ መላእክት ለማስተማር ታስቦ አይደለም፡፡ በተጠቀሱባቸው ጥቅሶች ውስጥ የምንማረው ነገር ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ግንኙነትና አላማውን ለማስፈጸም እንደመሳሪያ ማገልገላቸውን ነው፡፡ “መልአክ” የሚለው ቃል ትርጉም በእብራይስጥም ሆነ በግሪክ ቋንቋ “መልእክተኛ” ማለት ነው፡፡ – ሊመለኩ አይገባቸውም – መሳ 13፡16-18፤ ቆላ 2፡18፤ ራዕ 19፡10፤ 22፡8-9 – ሁለት የመላእክት ክፍሎች አሉ፣ መልካምና ክፉ – ራዕ 12፡7 – ስለ ክፉ መላእክት ለማወቅ ሐ2 እና ክፍል ሐ5 ላይ የሚገኘውን የዲያቢሎስ ጥናት የሚለውን ይመልከቱ። – መላእክት ከሚለው ስማቸው በተጨማሪ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ስም ተሰይመዋል፡- – ጠባቂዎች – ዳን 4፡13፣ 17፣ 23 – የሰማይ መላእክት – ማቴ 24፡36 – የሰማይ ሠራዊት – ሉቃስ 2፡13 – መናፍስት – ዘካ 6፡5፤ ዕብ 1፡4፣ 14 – የእግዚአብሔር ልጆች – ኢዮብ 1፡6፤ 2፡1፤ 38፡7 – ስልጣናት፣ ኀይላት፣ ዙፋናት፣ ገዦች፣ ባለ ስልጣናት – ቆላ 1፡16፤ ሮሜ 8፡38፤ 1ቆሮ 15፡24፤ ኤፌ 6፡12፤ ቆላ 2፡ 15 – መላእክት ከዚህ በታች በተጠቀሱ ስያሜዎች ተጠርተዋል – ገብርኤል – ዳን 8፡16፤ 9፡21፤ ሉቃስ 1፡11-20፣ 26-38 – ሚካኤል – ዳን 10፡13፣ 21፤ 12፡1፤ ይሁዳ 9፤ ራዕ 12፡7 – ሰይጣን (ከተጨማሪ ሌሎች ስሞች ጋር) – ክፍል ሐ3 ይመልከቱ – መንፈሳዊ አካላቱ የተለያዩ ማእረጋትና ቅደም ተከተሎች አሏቸው – ሰማያዊ ፍጡራን – 2ጴጥ 2፡10-11 – ሱራፌል – ኢሳ 6፡2፣ 6 – ኪሩቤል – ዘፍ 3፡24፤ ዘጸ 25፡18፤ መዝ 18፡10፤ ሕዝ 10፡2-9 – ሰይጣን ኪሩብ ነበር – ሕዝ 28፡14-16 – የመላዕክት አለቃ – 1ተሰ 4፡16፤ ይሁዳ 9 – በእግዚአብሔር አብና ወልድ ተፈጥረዋል – ነሕ 9፡6፤ ቆላ 1፡16 – ከሰው መፈጠር በፊት ነበሩ – ኢዮብ 38፡1-7 – መንፈሳዊ አካላት ናቸው (ሥጋና ደም የላቸውም) – ኤፌ 6፡12፤ ዕብ 1፡14፤ መዝ 104፡4 – ነገር ግን አንድ አንድ ጊዜ በሰው መልክ ይገለጻሉ – ዘፍ 18፡2-33፤ 19፡1-22፤ መሳ 6፡11-22፤ ዮሐ 20፡1 – ሳናውቀው መላዕክትን ልናስተናግድ እንችላለን – ዕብ 13፡2 – በቁጥጥር በጣም ብዙ ናቸው – ዘዳ 33፡2፤ ዳን 7፡10፤ ማቴ 26፡53፤ ሉቃስ 2፡13፤ ዕብ 12፡22 – ብርቱዎች ናቸው – 2ነገ 19፡35፤ መዝ 103፡20፤ 2ተሰ 1፡7፤ 2ጴጥ 2፡11፤ ኢሳ 37፡36 – ጠቢቦች ናቸው ነገር ግን ሁሉን አዋቂዎች አይደሉም – 2ሳሙ 14፡20፤ ማቴ 24፡36፤ 1ጴጥ 1፡12 – ክርስቶስ ኢየሱስ ከመላእክት በእጅጉ ይበልጣል – ዕብ 1፡4-2፡15 ለ) የመልካም መላእክት ተግባራቸው ምንድን ነው? – እግዚአብሔርን ማምለክና ማመስገን – ዕብ 1፡6፤ ራዕ 5፡11-12 – የሙሴ ሕግ በመላእክት በኩል ተሰጠ – መዝ 68፡17፤ ገላ 3፡19፤ ሐዋ 7፡53 – ለኢየሱስ ይታዘዛሉ – ኤፌ 1፡20-22፤ ቆላ 2፡10፤ 1ጴጥ 3፡22 – መዳንን የሚወርሱትን ያገለግላሉ – ዕን 1፡7፣ 14 – እርዳታቸው የሚገኘው ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ ነው – ማቴ 26፡53፤ ሐዋ 12፡5-7 – የእግዚአብሔርን ፍርድ ያስፈፅማሉ – 2ሳሙ 24፡16፤ 2ነገ 19፡35፤ መዝ 35፡5-6፤ ሐዋ 12፡23፤ ራዕ 16፡1 – በመጨረሻው ዘመን መከሩን የሚሰበስቡ (አጫጆች) ናቸው – ማቴ 13፡39-41፣ 49-50፤ 24፡31 – ሕፃናትን ይጠብቃሉ – ማቴ 18፡10 – የእግዚአብሔርን ሕዝብ ይጠብቃሉ – ዳን 6፡22፤ መዝ 34፡7፤ 91፡11 – ከኢየሱስ ዳግም ምፅአት ጋር አብረው ይገለጣሉ – ማቴ 16፡27፤ 25፡31፤ ማር 8፡38፤ 1ተሰ 4፡16፤ 2ተሰ 1፡7 – በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ ታላላቅ ትዕይንቶችን አብስረዋል ፅንሱን – ሉቃስ 1፡31 ትንሳኤውን – ሉቃስ 24፡23 ዳግም ምፅአቱን – ሐዋ 1፡11 ልደቱን – ሉቃስ 2፡10-12 እርገቱን – ሐዋ 1፡11 ሐ) መላእክት በርካታ ሰዎችን አገልግለዋል – አጋር፣ ሳራን ተለይታ ስትሄድ – ዘፍ 16፡7-13 – ሎጥ፣ ሰዶም ከመጥፋቷ በፊት – ዘፍ 19፡1-22 – አጋርና እስማኤል – ዘፍ 21፡17-19 – አብርሃም፣ ከይስሃቅ ጋር በተራራ በነበረ ጊዜ – ዘፍ 22፡11-18 – ያዕቆብ፣ የመሰላል ራዕይ ባየ ጊዜ – ዘፍ 28፡12 – የላባን በጎች በተመለከተ ባየው ራዕይ ውስጥ – ዘፍ 31፡11 – ኤሳውን ለመገናኘት ከላባ በሄደ ጊዜ – ዘፍ 32፡1 – ሙሴ፣ በሚነደው ቁጥቋጦ ስፍራ – ዘጸ 3፡2 – እስራኤል፣ በደመናው አምድ – ዘጸ 14፡19-20 – እስራኤልን በመምራት – ዘጻ 23፡20-23፤ ዘኁ 20፡16 – በልአምና አህያው – ዘኁ 22፤ 22-35 – ኢያሱና እስራኤል – መሳ 2፡1-5 – ጌዲዮን፣ እስራኤልን እንዲመራ ሲመረጥ – መሳ 6፡11-22 – የሶምሶን ቤተሰቦች – መሳ 13፡2-23 – ዳዊት ሕዝቡን ሲቆጥር – 2ሳሙ 24፡15-17፤ 1ዜና 21፡16-30 – ኤልያስን ለማጠንከር – 1ነገ 19፡5-8 – አሦራዊያንን ለመግደል – 2ነገ 19፡35፤ 2ዜና 32፡21፤ ኢሳ 37፡36 – ሲድራቅ፣ ሚሳቅና፣ አብድናጎ በእሳት ውስጥ – ዳን 3፤ 25-28 – ዳንኤል፣ አንበሳ ጉድጓድ ውስጥ – ዳን 6፤ 22 – መልአኩ ገብርኤል ስለመጪው ዘመን ለማሳየት – ዳን 8፡16፤ 9፡21 – ዘካሪያስ በመላእክት በርካታ ነገር አየ – ዘካ 1፡9፤ 4፡1-6 – ዮሴፍ፣ የማርያም እጮኛ – ማቴ 1፡20-21 – ወደ ግብጽ እንዲሄድና እንዲመለስ – ማቴ 2፤ 13፤ 2፡19 – ኢየሱስ፣ መላአክ አገለገለው – ማቴ 4፡11፤ ማር 1፤ 13 – ሕጻናት መላእክት አሏቸው – ማቴ 18፡10 – ሴቶች፣ በኢየሱስ መቃብር – ማቴ 28፤ 2-8፤ ዮሐ 20፡11-13 – ዘካሪያስ ገብርኤልን በመቅደሱ ተመለከተ – ሉቃስ 1፡11-19 – ማርያም፣ የኢየሱ እናት ገብርኤልን ተመለከተች – ሉቃስ 1፡26-38 – እረኞች፣ በኢየሱስ ልደት ወቅት – ሉቃስ 2፡8-16 – ኢየሱስ፣ በደብረዘይት ተራራ ሲያለቅስና ሲጸልይ – ሉቃስ 22፡43 – ለበሽተኞች፣ ውኃ ማናወጥ – ዮሐ 5፤ 4 – ሐዋሪያትን ከእስራት ለማስፈታት – ሐዋ 5፡19-20 – ፊሊጶስ ለኢትዮጵያዊው እንዲመሰክር – ሐዋ 8፡26 – ቆርነሊዎስ ጴጥሮስን እንዲጠራ – ሐዋ 10፡3-8 – ጴጥሮስ ከሄሮድስ እስር ቤት እንዲያመልጥ – ሐዋ 12፡6-11 – ሄሮድስን መቶ ለመግደል – ሐዋ 12፡21-23 – ጳውሎስ፣ መርከቡ ከመሰበሩ በፊት – ሐዋ 27፡23-24 – ዮሐንስ፣ በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ – የራዕይ መጽሐፍ

መላእክት – የእግዚአብሔር መልእክተኞች Read More »

የመንፈስ ቅዱስ ግብር

በብሉይ ኪዳን ወቅት አብ በግልጽ ይታይ ነበር፡፡ ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት፣ ወልድ በግልጽ ይታይ ነበር፡፡ በአሁኑ ዘመን ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በግልጽ ይታያል፡፡ ሀ) በብሉይ ኪዳን የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት – በፍጥረት ሥራ – ዘፍ 1፡2 – ትንቢትን በመስጠት – ሕዝ 2፡2፤ 8፡3፤ 11፡1-5 በልአም – ዘኁ 24፡2-9 ሳኦል – 1ሳሙ 10፡6፣ 10 ዳዊት – ሐዋ 1፡16 – ችሎታን በመስጠት ለባስልኤል የግንባታ ጥበብ – ዘጸ 31፡2-5 – የመንግስት አስተዳደር ጥበብ የሴፍ – ዘፍ 41፡38-44 ሙሴና 70ዎቹ ሽማግሌዎች – ዘኁ 11፡14-17፣ 25-29 ጎቶንያል – መሳ 3፡9-10 ሳምሶን – መሳ 14፡19፣ 15፡14 ዳዊት – 1ሳሙ 16፡13 ጌዴዎን – መሳ 6፡34 ሳኦል – 1ሳሙ 10፡10 – አኗኗርን በመቀየር ፍትህ፣ ጻድቅና ሰላም – ኢሳ 32፡15-20 ለጌታ አምልኮ – ኢሳ 44፡3-5 አዲስ ልብ – ሕዝ 36፡26-28 ለ) መንፈስ ቅዱስ ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር ያለው ግንኙነት – የቅዱሳት መጽሐፍ ደራሲ መንፈስ ቅዱስ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር እንዲናገሩ መራ – 2ጴጥ 1፡20-21 ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የ “እግዚአብሔር እስትንፋ” (መንፈስ) ውጤቶች ናቸው – 2ጢሞ 3፡16 መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳት መጻሕፍት ይናገራል – ራዕ 2፡7፣ 11፣ 17፣ 29 – የእግዚአብሔርን ጥበብ የሚፈታ (የሚገልጥ፣ የሚያብራራ) – 1ቆሮ 2፡9-14፤ ኤፌ 1፡17፤ ዮሐ 15፡26-16፡15 ሐ) ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት – መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ አገልግሎት ውስጥ የነበረው ሚና ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ተጸነሰ – ሉቃስ 1፡35፤ ማቴ 1፡18 ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን በጥምቀቱ ወቅት ተቀበለ – ሉቃስ 3፡21-22 ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ በሰይጣን ይፈተን ዘንድ ወደ ምድረበዳ ተመራ – ማር 1፡12፤ ማቴ 4፡1 ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ተጓዘ – ሉቃስ 4፡14 ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ቅባት ሰበከ – ሉቃስ 4፡18 ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ አጋንንትን አስወጣ – ማቴ 12፡28 ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሃሴት አደረገ – ሉቃስ 10፡21 ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ከሞት ተነሳ – ሮሜ 8፡11 – መጥምቁ ዮሐንስ በማሕፀን ውስጥ ሳለ በመንፈስ ተሞላ – ሉቃስ 1፡15 መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ላይ ሲመጣ አየ – ማቴ 3፤ 16፤ ዮሐ 1፡31 ኢየሱስ በመንፈስ ያጠምቃል ብሎ መሰከረ – ማር 1፡7-8 መ) በቤተ ክርስቲያን ዘመን የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት – መንፈስ ቅዱስ፣ ከእስራኤል ሌላ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ድርሻ ያላቸው መኖራቸውን አስታወቀ። – የአሕዛብ መካተት ምስጢር – ኤፌ 3፡5-8 – በአሕዛብ ሁሉ ላይ የመንፈስ ቅዱስ መፍሰስ – ኢዩ 2፤ 28 ከ ሐዋ 2፤ 16-18 ጋር ሠ) ስለ መንፈስ ቅዱስ የአስተምህሮ ምንባብ – ዮሐ 14፡16-16፡15 በኢየሱስ ስም ከአብ ዘንድ የተላከ – ዮሐ 14፡26 ከአብ ዘንድ በኢየሱስ የተላከ – ዮሐ 15፡26 ስለ ኢየሱስ የሚመሰክር – ዮሐ 15፡26-27 ኃጢአተኞችን የሚወቅስ – ዮሐ 16፡7-8 ወደ እውነት የሚመራን – ዮሐ 16፡13 ስለ አብና ወልድ የሚናገር – ዮሐ 16፡14-15 ረ) ስለ መንፈስ ቅዱስ ግብር የአስተምህሮ ምንባብ – ሮሜ 8፡1-39 ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ነፃ አወጣን – ሮሜ 8፡2 የሕግን ፈቃድ በመንፈስ በመጓዝ እናሟላለን – ሮሜ 8፡4 ለ ሰውነታችን ሃይልን ይሰጣል – ሮሜ 8፡11 በመንፈስ ሰላምና ሕይወት አለን – ሮሜ 8፡5-6 ክፉ ተግባሮቻችን በመንፈስ ተወግደዋል – ሮሜ 8፡13 በድካማችን እንድንጸልይ ይረዳናል – ሮሜ 8፡26 በመንፈስ አማካኝነት የእግዚአብሔር ልጆች እንጂ ባሮች አይደለምን – ሮሜ 8፡15-17 ሰ) መንፈስ ቅዱስ በኤፌሶን መጽሐፍ የእግዚአብሔር መሆኔን በምን አውቃለሁ? በክርስቶስ፣ በመንፈስ – ኤፌ 1፡13-14 መንፈስ እንዴት ይረዳናል? የጥበብና የመገለጥን መንፈስ በመስጠት – ኤፌ 1፡17 በሰማይ ወደ አለው አብ እንዴት መቅረብ እችላለሁ? በመንፈስ ወደ አብ መግባት እንችላለን – ኤፌ 2፡18 እግዚአብሔር በመካከላችን (በቤተ ክርስቲያን በመቅደሱ) እንዴት ይኖራል? እግዚአብሔር በመንፈስ አማካኝነት በመካከላችን ያድራል – ኤፌ 2፡22 አሕዛብ በኢየሱስ አማካኝነት ምህረት እንደ ተደረገላቸው እግዚአብሔር እንዴት ገለጠው? የእግዚአብሔር መንፈስ ለሐዋሪያትና ነቢያት ገለጠው – ኤፌ 3፡4-6 ኢየሱስ በልባችን ይኖር ዘንድ እንዴት ልንጠነክር እንችላለን? የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጥ ሰውነታችን ያጠነክረናል – ኤፌ 3፡16-17 በውስጣችን ካለው የእግዚአብሔር መንፈስ ጋር እንዴት በሰላም እንኖራለን? መራርነትና ንዴት የመሰሉትን በማስወገድ – ኤፌ 4፡30-32 ለሕይወቴ የእግዚአብሔር ፈቃድ ምንድን ነው? በመንፈስ ቅዱስ እንድሞላ – ኤፌ 5፡17-18 ከመከላከያ የዘለለው የእግዚአብሔር የጦር እቃ ምንድን ነው? የመንፈስ ሰይፍ (የእግዚአብሔር ቃል ) – ኤፌ 6፡17 – በመንፈስ ቅዱስ መጸለይ – ኤፌ 6፡18 – መንፈስ ቅዱስ ደኅንነታችንን (ድነታችንን) ያረጋግጥልናል/በሕይወታችንም እንድናጣጥመው ያደርገናል – ስለኃጢአት፣ ጽድቅና ፍርድ ይወቅሰናል – ዮሐ 16፡7-8 – ከመንፈስ መወለድ አለብን – ዮሐ 3፤ 3-6፤ ቲቶ 3፡5 – ከዚህ ልደት በኋላ መንፈስ በአማኙ ውስጥ ያድራል/ይሞላል – ሐዋ 2፡4፤ ኤፌ 5፡18፤ 1ቆሮ 6፡19 – በኃጢአት ጸንቶ የማይኖር ሕይወት እንድንኖር ሃይል ይሰጠናል – ሮሜ 8፡2 – የእግዘዚአብሔርን አገልግሎት እንድናገለግል በሃይል ይሞላናል – ዮሐ 14፡11-17፤ ሐዋ 1፡8፤ 1ቆሮ 2፤ 4 – ይመራናል ያስተምረናል – ዮሐ 14፡26፤ 16፡13 – በአማኙ ሕይወት ውስጥ የመንፈስ ፍሬን ያፈራል – ገላ 5፡22-23

የመንፈስ ቅዱስ ግብር Read More »

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ – የመንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔርነት

ሀ) መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስን ለመጥራት የሚጠቀምባቸው ስያሜዎች መንፈስ – ማር 1፡10፤ ገላ 5፡5፤ ራዕ 22፡17 መንፈስ ቅዱስ – ኢሳ 63፡10-11፤ ሉቃስ 11፡13፤ 1ተሰ 4፡8 የእግዚአብሔር መንፈስ – ዘፍ 1፡2፤ ኢዮ 2፡28፤ ሮሜ 8፡14፤ 1ቆሮ 3፡16 የአብ መንፈስ – ማቴ 10፡20 የወልድ መንፈስ – ገላ 4፡6 የኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ – ፊሊ 1፡19 የክርስቶ መንፈስ – 1ጴጥ 1፡11 የጌታ መንፈስ – 2ቆሮ 3፡17፤ ኢሳ 63፡14 የጸጋ መንፈስ – ዕብ 10፡29 የእውነት መንፈስ – ዮሐ 14፡17፤ 15፡26፤ 1ዮሐ 5፡6 የሕይወት መንፈስ – ሮሜ 8፡2 የክብር መንፈስ – 1ጴጥ 4፡14 የልጅነት መንፈስ – ሮሜ 8፡15 አጽናኝ – ዮሐ 14፡16፤ 16፡7 የጥበብ መንፈስ፣ የማስተዋል፣ የምክር፣ የኃይል፣ የእውቀት፣ እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ – ኢሳ 14፡16፤ 16፡7 ለ) ስሙ እንደ እግዚአብሔር ስም ጥቅም ላይ ውሏል – መንፈስ ቅዱስን መዋሸት – ሐዋ 5፡3 – እግዚአብሔርን መዋሸት – ሐዋ 5፡4 – የመንፈስ ቅዱስ ቤተመቅደስ – 1ቆሮ 6፡19፣ 20 – የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ – 1ቆሮ 3፡16፣ 17 – መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን ከሞት አስነሳው – ሮሜ 8፡11 – እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሞት አስነሳው – ሐዋ 2፡24፣ 32 – በመንፈስ ሃይል እየሰበኩ – 1ቆሮ 2፡4 – በእግዚአብሔር ሃይል እየሰበኩ – 1ቆሮ 2፡5 ሐ) መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ባሕሪይ አለው መንፈስ ቅዱስ ፈጣሪ ነው – ዘፍ 1፡2 መንፈስ ቅዱስ ሁሉን ያውቃል – 1ቆሮ 2፡10-11፤ ዮሐ 16፡13 መንፈስ ቅዱስ ሃያል ነው – ሉቃስ 1፡35፤ ሮሜ 15፡19 መንፈስ ቅዱስ ዘላለማዊ ነው – ዕብ 1፡10-12፤ ዕብ 9፡14 መ) መንፈስ ቅዱስ አካል ያለው እንጂ ሃይል ወይም የእግዚአብሔር ተፅእኖ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ “ነገር” እያለ ሳይሆን “እሱ” እያለ ይጠራዋል – ዮሐ 16፡13-14፤ ኤፌ 1፡13-14 ኢየሱ፣ እንደ እርሱ የሆነ “ሌላ አጽናኝ” እንደሆነ ተናገረለት – ዮሐ 14፡16 መንፈስ ያስተምራል – ዮሐ 14፡26 ለማን ስጦታ መስጠት እንዳለበት ይወስናል – 1ቆሮ 12፡11 ስለቅዱሳን በመቃተት ይማልዳል – ሮሜ 8፡26 መንፈስ ቅዱስን ማሳዘን (መከላከል) ትክክል አይደለም – ኤፌ 4፡30፤ ሐዋ 7፡51 መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ኃጢአት ነው – ማቴ 12፡31፤ ማር 3፡29

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ – የመንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔርነት Read More »

ኢየሱስ – ፍጹም ሰውና ፍጹም እግዚአብሔር

ሀ) ልደቱ – ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የዳዊት ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ – ማቴ 11 – ከሴት የተወለደ – ገላ 4፡4፤ ሉቃስ 1፡29-33 – በቤተልሔም የተወለደ – ማቴ 2፡1 – ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ – 1ጢሞ 2፡5 – የሰው ልጅ ተባለ – ማቴ 12፡8፤ 16፡13፤ 25፡31፤ ዮሐ 3፡14፤ 8፡28፤ 13፡31 – በሥጋና በደም ሰውነታችንን ተካፈለ – ዕብ 2፡4፤ 1ዮሐ 4፡፡14 – መንፈስ፣ ኢየሱስ በሥጋ እንደመጣ ይመሰክራል – 1ዮሐ 4፡2-3 ለ) በአካሉ ተወሰነ – ደከመ – ዮሐ 4፡6-8 – ሲደክመው ተኛ – ማር 4፡38 – በጥበብና በቁመት በተፈጥሮ ሕግ አደገ – ሉቃስ 2፡52 – በተወጋው ጎኑ ደምና ውሃ ወጣው – ዮሐ 19፡32-34 – ተራበ – ማቴ 4፡1-11፤ ማር 11፡12 – አዘነ – ማቴ 26፡38፤ ዮሐ 11፡35 – ተቆጣ – ማር 10፡14 ሐ) የሰውና የመለኮት ባሕሪያት አንድ መሆን (መዋሀድ) – የመለኮት ሙላት በሰውነቱ ተገልጧል – ቆላ 1፡14 – ሁለቱም ተፈጥሮዎች በአንድ ምንባብ ስር ተጠቅሰዋል ቃል-ሥጋ ሆነ – ዮሐ 1፡14 የዳዊት ዘር – የእግዚአብሔ ልጅ – ሮሜ 1፡3-4 የእግዚአብሔር ልጅ – በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ – ሮሜ 8፡3 ክርስቶ በሥጋ መጣ – ከሁሉ በላይ አምላክ ነው – ሮሜ 9፡5 ከሴት የተወለደው – የእግዚአብሔር ልጅ – ገላ 4፡4 ምሳሌ ተገኘ – ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው – ፊል 2፡7፣ 11 – ሰዋዊ መለያ ባሕሪይ ከ መለኮታዊ ስያሜ ጋር ድንግል ወንድ ልጅን ትወልዳለች – “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” ይባላል – ማቴ 1፡23 ፤ ኢሳ 7፡14 – የኢየሱስ ደም “የእግዚአብሔር ደም” ተብሏል – ሐዋ 20፡28 – እግዚአብሔር እንደመንፈስነቱ “ደም” የለውም፡፡ የኢየሱስ “ደም” እንደ “እግዚአብሔር ደም” መቆጠሩ ኢየሱስና እግዚአብሔር ያላቸውን መለኮታዊ አንድነት ይገልጣል፡፡ – ተሰቀለ – የክብር ጌታ – 1ቆሮ 2፡8 – መለኮታዊ መለያ ባሕሪይ ከ ሰዋዊ ስያሜ ጋር ከሰማይ መጣ – የሰው ልጅ – ዮሐ 3፡13 የሰው ልጅ – ወደ ሰማይ አረገ – ዮሐ 6፡62 ክርስቶ በሥጋ መጣ – ከሁሉ በላይ አምላክ ነው – ሮሜ 9፡5

ኢየሱስ – ፍጹም ሰውና ፍጹም እግዚአብሔር Read More »

ኢየሱስ እግዚአብሔር የሆነውን ሁሉ ነው

ሀ) እግዚአብሔር ፈጣሪ፣ ኢየሱስ ፈጣሪ ዘፍ 1፡1 ዘፍ 2፡7 ዮሐ 1፡3፣ 10 1ቆሮ 8፡6 ኢዮብ 33፡4 መዝ 33፡6 ኤፌ 3፡9 ቆላ 1፡12-17 መዝ 104፡30 ኢሳ 40፡28 ዕብ 1፡ 8-12 ራዕ 4፡8-11 ኢሳ 44፡24 ኢሳ 45፡11-18 ራዕ 10፡6 ራዕ 14፡6-7 ሚል 2፡10 ራዕ 21፡5-7 ራዕ 22፡3 ራዕ 7፡17 ለ) እግዚአብሔር ቤዛና አዳኝ፣ ኢየሱስ ቤዛና አዳኝ መዝ 78፡34-35 ኢሳ 47፡4 1ዮሐ 4፡14 1ጴጥ 2፡21-24 ኢሳ 46፡6፣ 24 ኢሳ 43፡3-11 ሐዋ 20፡28 ገላ 3፡13 ኢሳ 45፡21 ኢሳ 49፡26 ሉቃስ 24፡21-29 ሉቃስ 2፡10-11 መዝ 106፡21 ሉቃስ 1፡46-47 ዮሐ 4፡40-42 ሐዋ 12፡23 1ጢሞ 1፡1 ቲቶ 1፡14 ፊል 3፡20 1ጢሞ 1፡1-3 1ጢሞ 4፡10 ቲቶ 2፡10-13 ቲቶ 1፡4 1ጴጥ 1፡10-11 ይሁዳ 25 ሐ) እግዚአብሔር ይመጣል፣ ኢየሱስ ይመጣል ዘካ 14፡3-5 1ተሰ 4፡13-18 1ተሰ 3፡11-13 ማቴ 25፡31-46 ራዕ 19፡11፣ 16 መዝ 50፡1-6 ቲቶ 2፡11-13 መ) እግዚአብሔር አለት፣ ኢየሱስ አለት ዘዳ 32፡3-4 1ሳሙ 2፡2 ማቴ 16፡17-19 2ሳሙ 22፡2 መዝ 18፡2 ዘኁ 20፡1-11 ከ 1ቆሮ 10፡4 ጋር መዝ 31፡1-4 መዝ 78፡35 ኢሳ 28፡16 ከ ኤፌ 2፡20-22 ጋር መዝ 89፡26 ኢሳ 17፡10 1ጴጥ 2፡6-8 ሠ) እግዚአብሔር መጀመሪያና መጨረሻ፣ ኢየሱስ መጀመሪያና መጨረሻ ኢሳ 41፡4 ኢሳ 43፡10-11 ራዕ 1፡17 ኢሳ 44፡6-8 ራዕ 1፡8 ራዕ 22፡13 ረ) እግዚአብሔር፡- እኔ፣ እኔ ነኝ ኢየሱስ፡- እኔ፣ እኔ ነኝ ዘዳ 3፡13-14 ኢሳ 43፡10 ዮሐ 18፡5-8 ራዕ 1፡17-18 ኢሳ 43፡25 ዮሐ 8፡24-28 ሰ) እግዚአብሔር ንጉስ፣ ኢየሱስ ንጉስ መዝ 47፡2፣ 6 መዝ 44፡4 ማቴ 2፡1-6 ሉቃስ 19፡35-38 መዝ 74፡12 ዘካ 14፡9 ሉቃስ 23፡3 ዮሐ 18፡37 ኢሳ 44፡6 ኤር 10፡10 ዮሐ 19፡21 1ጢሞ 6፡13-16 ራዕ 15፡1-4 ራዕ 19፡11-16 ቀ) እግዚአብሔር እረኛ፣ ኢየሱስ እረኛ መዝ 23፡1 ኢሳ 40፡10-11 ዮሐ 10፡8-12 1ጴጥ 2፡21-25 መዝ 100፡3 ዕብ 13፡20 1ጴጥ 5፡4

ኢየሱስ እግዚአብሔር የሆነውን ሁሉ ነው Read More »

ኢየሱስ እግዚአብሔር ብቻ ሊያደርገው የሚችለውን ስራ አድርጓል

ሀ) ኃጢአትን ይቅር ብሏል ይህም እግዚአብሔር ብቻ ሊያደርገው የሚችለው ነው – ማቴ 9፡2-7 /ማር 2፡5-12/ ሉቃስ 5፡ 20-26/ ለ) የኢየሱስ ተአምራት (በማቴዎስ ማርቆስ ሉቃስ ዮሐንስ ወንጌላት) – በተፈጥሮ ላይ ያለው ስልጣን ውሃን ወደ ወይን – 2፡7-111 በአሳ ጠመዳ ወቅት – 5፡4-9 ወጀብን ማስቆም – 8፡23-27 – 4፡37-41 – 8፡22-25 ምግብ ማበርከት – 14፡15-21 – 6፡35-44 – 9፡12-17 – 6፡5-14 በውሃ ላይ መሄድ – 14፡25-27 – 6፡47-51 – 6፡19-21 ምግብ ማበርከት – 15፡32-38 – 8፡1-9 ከአሣ ውስጥ ገንዘብ – 17፡24-27 የበለስ ዛፍን መርገም – 21፡19 – 11፡12-23 ለሁለተኛ ጊዜ በአሳ ጠመዳ ወቅት – 21፡4-7 – በሰይጣንና በዲያቢሎስ ላይ ያለው ስልጣን በምኩራብ የነበረ ዲያብሎስ – 1፡23-27 – 4፡32-36 ዲያቢሎስ – 8፡28-34 – 5፡1-17 – 8፡26-39 ዲዳ ጋኔን – 9፡32-33 ዲዳና ደንቆሮ ጋኔን – 12፡22 – 11፡14 ወጣቷ ልጃገረድ – 15፡22-28 – 7፡25-30 የሚሰቃየው ልጅ – 17፡14-18 – 9፡17-29 – 9፡37-43 የድካም መንፈስ – 13፡10-17 – በበሽታ በአካል ደዌዎች ላይ ያለው ስልጣን የጴጥሮስ አማት – 8፡14-15 – 1፡29-31 – 4፡38-39 ለምጽ – 8፡2-4 – 1፡40-45 – 5፡12-15 የመቶ አለቃው አገልጋይ – 8፡5-13 – 7፡2-10 ድውይ – 5፡5-18 አይነሰውር ማብራት – 9፡27-31 – 9፡1-38 አይነስውር ማብራት – 20፡30-34 – 10፡46-52 – 18፡35-43 ሽባ – 9፡2-8 – 2፡3-12 – 5፡18-26 እጁ የሰለለ – 12፡10-15 – 3፡1-6 – 6፡6-11 የሚደማ ደም ቆመ – 9፡20-22 – 5፡25-34 – 8፡43-48 ዲዳና ደንቆሮ – 7፡32-37 ሆዱ የተነፋ – 14፡2-6 የማልኮስ ጆሮ – 22፡50-51 – በሞት ላይ ያለው ስልጣን የመበለቲቱ ልጅ – 7፡11-17 የኢያኢሮስ ሴት ልጅ – 9፡18-26 – 5፡35-43 – 8፡41-56 አላዛር – 11፡1-45 የኢየሱስ ትንሳኤ – 28፡1-20 – 16፡1-14 – 24፡1-53 – 20፡1-31

ኢየሱስ እግዚአብሔር ብቻ ሊያደርገው የሚችለውን ስራ አድርጓል Read More »