ሰይጣን – አጋንንት

ሀ) መግቢያ – የተወሰኑ መላእክት በእግዚአብሔር ተጥለዋል – 2ጴጥ 2፡4፤ ይሁዳ 6 – ርኩሳን መናፍስት በሰዎች ውስጥ ሊያድሩ ይችላሉ – ማቴ 12፡43፤ ማር 1፡26፤ 5፡9፤ 7፡24-30፤ 9፡14-27፤ 16፡19 – የማያምኑ ሰዎች እርኩሳን መናፍስትን ለማስወጣት ቢሞክሩ ያለው አደጋ – ሐዋ 19፡12-16 – አጋንንት አታላይ መናፍስት በመባል ተጠርተዋል – 1ጢሞ 4፡1 – አጋንንት የሚሉትን ፈፅመው አይመኑ፣ ውሸተኞች ናቸውና – ዮሐ 8፡44 – ከአጋንንት ጋር አያውሩ – አስወጧቸው እንጂ – ማር 16፡15-18 – አጋንንት እግዚአብሔር እንዳለ ያምናሉ – ያዕ 2፡19 – ተአምራትና ማድረግ ይችላሉ – ራዕ 16፡14፤ 2ተሰ 2፡9-12፤ ማቴ 24፡24፤ ዘጸ 7፡11፣ 22 ለ) አማኞች በአጋንንት ላይ ስልጣን አላቸው – በእኛ ውስጥ ያለው ኢየሱስ በአለም ካለው ሰይጣን ይበልጣል – 1ዮሐ 4፡4 – አጋንንት ያለፈቃድ በአሳማዎቹ ውስጥ አልገቡም – ማቴ 8፡30-32 – ሐዋሪያት በአጋንት ላይ ስልጣን ተሰጣቸው – ሉቃስ 9፡1 – ሰባ የሚሆኑ የኢየሱስ ተከታዮች አጋንንትን እንዲያወጡ ተላኩ – ሉቃስ 10፡1፣ 17 – ደቀ መዛሙርት ሁሉ አጋንንትን እንዲያወጡ ሥልጣን ተሰጣቸው – ማቴ 10፡1፤ ማር 16፡17 – ክፉ መናፍስት ለማውጣት የተሰጠ ተስፋ – ሉቃስ 10፡18-20 – ጳውሎስ የጥንቆላ መንፈስን አስወጣ – ሐዋ 16፡16 – አጋንንት በእምነት ቃል እና በሥልጣን ይወጣሉ – ሉቃስ 4፡32-36 ሐ) ሰይጣን – ስያሜዎቹና ታሪኩ 1) የሰይጣን ስያሜዎች፣ በሕሪያቶቹን ይገልጣሉ – ሉሲፈር (የብርሃን መልአክ) በሰማይ ሳለ የሚጠራበት ስሙ – ኢሳ 14፡12 – ሰይጣን (ተቃዋሚ) – ማቴ 4፡10፤ 1ዜና 21፡1፤ ኢዮብ 1፡6፤ ዘካ 3፤ 1 – እባብ፣ የጥንቱ እባብ – ዘፍ 3፡1፣ 4፤ ራዕ 12፡9 – ዘንዶ፣ እባብ፣ ዲያብሎስ፣ ሰይጣን – ራዕ 12፡9፤ 20፡2 – ዲያብሎስ (ሃሰተኛ ከሳሽ) – ማቴ 4፡1፣ 5፣ 8፤ ኤፌ 6፡11-12፤ ራዕ 12፡9 – ፈታኝ – ማቴ 4፡3፤ 1ተሰ 3፡5 – ብዔልዜቡል (የእበት አምላክ) – ማቴ 12፡24፤ ማር 3፡22 – የአጋንንት ወይም የዲያብሎስ አለቃ – ማቴ 12፡24፤ ማር 3፡22 – ክፉው – ማቴ 13፡19 – የዚህ አለም ገዢ – ዮሐ 13፡31፣ 14፡30፤ 16፡11 – ነፍሰ ገዳይ፣ ሃሰተኛ – ዮሐ 8፡44 – የዚህ አለም አምላክ – 2ቆሮ 4፡4፤ ዮሐ 12፡31፤ 14፤ 30፤ 16፡11 – ቤልሆር (ምናምንቴነት) – 2ቆሮ 6፡15 – በአየር ላይ ያሉ መንፈሳዊያን ኀይላት ገዢ – ኤፌ 2፡2 – ባላንጣ፣ ዲያብሎስ (ጠላት) – 1ጴጥ 5፡8 – አታላይ – ራዕ 12፡9 – የወንድሞች ከሳሽ – ራዕ 12፡10 – ከዚህ በታች ያሉ ስሞችም ለሰይጣን የተሰጡ ስያሜዎች ሳሆኑ አይቀሩም – የጥልቁ ጉድጓድ መልአክ – ራዕ 9፡11 – አጶልዮን፣ አብዶን (አጥፊ) – ራዕ 9፡11 2) ሰይጣን ከሚከተሉት ጋር ተነጻጽሯል – እባብ – ዘፍ 3፡1፤ ራዕ 12፡9፤ 20፡2 – አዳኝ ወፎች (fowler) – መዝ 91፡3 – እንክርዳድ ዘሪ – ማቴ 13፡25 – ተኩላ – ዮሐ 10፡12 – የሚያገሳ አንበሳ – 1ጴጥ 5፡8 3) ስለ ሰይጣን አጠቃላይ ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ሰለሰይጣን በርካታ ትምህርቶች አሉ፡፡ – ፍጡር ነው – ሕዝ 28፡13 – በሰማይ ሳለ “ሉሲፈር” በመባል ይጠራ ነበር – ኢሳ 14፡12 – በእግዚአብሔር፣ ጠባቂ ኪሩብ ተብሎ ተቀብቶ ነበር – ሕዝ 28፡14 – በተቀደሰው በእግዚአብሔር ተራራ – ሕዝ 28፡14 – የፍፅምና ተምሳሌት (የጥበብና የውበት) ነበረ – ሕዝ 18፡12፣ 15 – በእግዚአብሔር ገነት፣ በዔደን ነበር – ሕዝ 18፡13 – በመጀመሪያ በሰማይ ነበር ከዛ ተባረረ – ሉቃስ 10፡18 – በእግዚአብሔር ላይ አመጸ – 1ዮሐ 3፡8 – በደል በእርሱ ተገኘ – ሕዝ 28፡15 – በውበቱ ምክንያት በመኩራት – ሕዝ 28፡17 – የሰይጣን መውደቅ ምክንያቶች – ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ – ኢሳ 14፡13 – ዙፋኔንም ከእግዚአብሔ ከዋክብት በላይ ከፍ አደርጋለሁ – ኢሳ 14፡13 – … በተራራ ላይ እቀመጣለሁ – ኢሳ 14፤ 13 – ከደመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ – ኢሳ 14፡14 – በልዑል እመሰላለሁ – ኢሳ 14፡14 – የክፉ መናፍስት አለቃ፣ ክፉ መላእክት፣ አጋንንት – ማቴ 12፡24-28 – አንዳንድ ሰዎች ሰይጣን፣ አዳም ከመፈጠሩ በፊት፣ በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ባለቤት ለመሆን እንደፈለገ ያምናሉ፡፡ – ሰይጣን አለም የእርሱ እንደሆነች ተናግሯል – ማቴ 4፡8-9 – አዳም ምድርን እንዲያስተዳድር በእግዚአብሔር ተሰጥቶት ነበር – ዘፍ 1፤ 28 – ሔዋንን በዔደን ገነት አሳታት – ዘፍ 3፡1-7 – በእግዚአብሔር ተረገመ – ዘፍ 3፡14 – የሰው ልጅ ጠላት ነው – ዘፍ 3፤ 15 – በኢዮብ ዘመን፣ ሰይጣን ወደ እግዚአብሔር ይቀርብ ነበር – ኢዮብ 1፡6 – አሁንም ድረስ የወንድሞች ከሳሽ በመባል ይጠራል – ራዕ 12፡10 – ኢየሱስን ባይሳካለትም ፈተነው – ማቴ 4፡3፣ 4 – የብርሃን መልአክ መስሎ ሊቀርብ ይችላል – 2ቆሮ 11፡14 መ) የሰይጣንና የመላእክቱ የመጨረሻ እጣ ፈንታ – ቅዱሳን በመላእክት ላይ ይፈርዳሉ – 1ቆሮ 6፡3 – ሰይጣን በእግዚአብሔር ስልጣኑ ይነጠቃል – ዘፍ 3፡15፤ ራዕ 20፡10 – ሰይጣን ከሰማይ ሲወድቅ ኢየሱስ መመልከቱን ተናገረ – ሉቃስ 10፡18 – በአየር ላይ ላሉት መንፈሳዊያን ኀይላት ገዢ – ኤፌ 2፡2 – ሰይጣን ከእግዚአብሔር ተራራ ተጥሏል – ሕዝ 28፡16 – በምድር ላይ ተጥሏል – ሕዝ 28፡17፤ ራዕ 12፡10-13 – ለአንድ ሺ አመት በሰንሰለት ይታሰራል – ራዕ 20፡1-3 – ሰይጣን በእሳት ባሕር ይጣላል – ማቴ 25፡41፤ ሕዝ 28፡18፤ ራዕ 20፡10 – የመዳን ተስፋ የላቸውም – ይሁዳ 6፤ 2ጴጥ 2፡4፤ ማቴ 25፡41 – የዘላለም እሳት ተዘጋጅቶላቸዋል – ማቴ 25፡41 ሠ) ሰይጣን – ሥልጣንና ግብሩ 1) አካል አለው፣ የሆነ ሃይል ወይም ተጽእኖ ፈጣሪ አይደለም – ኢየሱስን በፈተነው ወቅት ከኢየሱስ ጋር ምልልስ አድርጓል – ማቴ 4፡1-11 – ይናገራል – ዘፍ 3፡1፤ ማቴ 4፡3 – ኢየሱስ ነፍሰ ገዳዩ፣ ውሸታም ብሎ ጠርቶታል – ዮሐ 8፡44 – ተንኮለኛ ነው፣ ራሱን መለዋወጥ ይችላል – 2ቆሮ 11፡3፣ 14 – ከእግዚአብሔር ጋር ምልልስ አድርጓል – ኢዮብ 1፡6-12፤ 2፡1-6 – ይራመዳል፣ ያገሳል – 1ጴጥ 1፡8 – ሊታሰር ይችላል – ራዕ 20፡1-3 2) የሰይጣንና የወደቁ መላእክቶቹ ስልጣንና ግብር – ጻድቃንን መቃወምና ማሰቃየት – ኢዮብ 1፡12-19፤ 2፡5-7፤ ዘካ 3፡1 – በበሽታ – ሉቃስ 13፡16፤ ማቴ 17፡15-16 – በአጋንንት – ማር 5፡15፤ 6፡13፤ 16፡19 – ሰዎችን ለማጥፋት መሞከር – በፈተናዎች – 1ዜና 21፡1፤ 1ተሰ 3፡5 ሔዋን – ዘፍ 3፡1-7 ዳዊት – 1ዜና 21፡1 ይሁዳ – ሉቃስ 22፡1-6 ኢዮብ – ኢዮብ 1፡6-12 ክርስቶስ – ማቴ 4፡1-11 ሃናንያና ሰጲራ – ሐዋ 5፡1-11 – በውሸት – ዮሐ 8፡44 – በሞት ላይ ኀይል አለው – ዕብ 2፡14-15 – ወንጌል ለማጥፋት ይጥራል – ማቴ 13፡19፤ 2ቆሮ 4፡4 – የእግዚአብሔርን ሥራና ሠራተኞቹን መቃወም – ዘካ 3፡1፤ 1ተሰ 2፡18፤ ዳን 10፡19-14 – ቅዱሳት መጻሕፍትን ማጣመም – ማቴ 4፡6 እና መዝ 91፡11-12 – ምልክቶችና ድንቆችን ማድረግ ይችላል – 2ተሰ 2፡8-9፤ ራዕ 13፡11-15 – የአጋንንት ጥናት (ሥነ-አጋንንት በተጨማሪ ይመልከቱ – ክፍል ሐ5) 3) የሰይጣን ኀይልና የስልጣን ገደብ – ኢየሱስ የሰይጣንን ሥራ ለማፍረስ መጣ – ዕብ 2፡14፤ 1ዮሐ 3፡8 – ኢየሱስን የፈተነበት ወጥመድ አልተሳካም – ሉቃስ 4፡13 – ሰይጣን በኢየሱስ ላይ ምንም ኀይል የለውም – ዮሐ 14፡30 – ኢየሱስ ርኩሳን መናፍስትን አስወጥቷል – ሉቃስ 11፡20፤ 13፡32 – ደቀ መዛሙርት አጋንንትን ያወጡ ዘንድ ኀይል ተሞልተው ነበር – ማቴ 10፡1፤

ሰይጣን – አጋንንት Read More »