የሕይወት እንጀራ አገልግሎት

ስለ እኔ፦ የአገልግሎቱ ራእይና ጥሪ ሰላም ለእናንተ ይሁን! እኔ አዳነው ዲሮ ዳባ እባላለሁ። ወደዚህ ድረ-ገጽ ስለመጡና የ"የሕይወት እንጀራ" ቤተሰብ ስለሆኑ እጅግ ደስ ብሎኛል። ይህ አገልግሎት የተወለደው በሕይወቴ ውስጥ ካለ አንድ ትልቅ እውነት ነው፤ እርሱም "ሰው በእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም" የሚለው መለኮታዊ ቃል ነው። 📖✨ 📜 ጥሪዬና ማንነቴ እግዚአብሔር በጸጋው በሰጠኝ ዘመን ሁሉ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ መምህር፣ ጽሐፊና ተርጓሚ በመሆን ሳገለግል ቆይቻለሁ። ቃሉን መመርመር፣ የተሰወሩ ዕንቁዎችን ማውጣትና ያገኘሁትን መንፈሳዊ ምግብ ለሌሎች ማካፈል የልቤ ትርታ ነው። ✍️ የአገልግሎቴ መሪ ቃል "ኢየሱስ፣ የነፍስ ምግብ" የሚል ሲሆን፣ ዓላማዬም በዕለት ተዕለት ሕይወት ሩጫና ድካም ውስጥ ለሚገኙ ነፍሳት የማይለወጠውንና የማይጠፋውን የክርስቶስን ወንጌል በተለያዩ ትምህርቶች ማድረስ ነው። 🌍 ከየት ወደ የት? በአሁኑ ሰዓት በዩናይትድ ስቴትስ የምኖር ቢሆንም፣ ልቤና ሐሳቤ ግን ሁልጊዜም በኢትዮጵያና በዓለም ዙሪያ ካሉ ወገኖቼ ጋር ነው። በአካል ብንራራቅም፣ በቴክኖሎጂ አማካኝነት ይህንን የወንጌል ድልድይ በመገንባት የጌታን ቃል በየቤታችሁ ለማድረስ እተጋለሁ። በተለይም በሕይወት ታሪኬና በተለያዩ የሥልጠና ጽሑፎቼ አማካኝነት እግዚአብሔር በሕይወቴ ውስጥ የሠራውን ተአምርና ያስተማረኝን ጥልቅ ትምህርቶች ለእናንተ ለማካፈል በዝግጅት ላይ እገኛለሁ። 🌱🕊️ 🤝 አብረን እንጓዝ በዚህ ድረ-ገጽ የምታገኟቸው ትምህርቶች ሁሉ ከጸሎትና ከጥልቅ ጥናት በኋላ የሚቀርቡ "የነፍስ ምግቦች" ናቸው። ዓላማዬ በክርስቶስ እንድታድጉ፣ በመንፈሳዊ ማንነታችሁ እንድትጸኑና የተሰጣችሁን የሰማይ መክሊት እንድትጠቀሙ መርዳት ነው። በዚህ የመንፈሳዊ ጉዞ አብረን እንድንጓዝ፣ እንድንማማርና አብረን እንድንጸልይ በታላቅ አክብሮት እጋብዛችኋለሁ።🙏🌟

የዘላለም ሕይወት እንዳልዎት እርግጠኛ ነዎት?

በመጀመሪያ እንኳን ወደዚህ የደህንነት ትምህረት ጥናት መጡ እያልን መጽፍ ቅዱስ ለማጥናት ላደረጉት ቆራጥ ውሳኔ ልናደንቅዎ እንወዳለን፡፡  ይህ ‹የደኅንነት ትምህርት› ኮርስ የዘላለም ሕወትዎን በተመለከተ ወሰኝ ርእሰ ጉዳይ መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡ በዚህ ጥናት ውስጥ የቀረቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እርሶ ወደ መንግስተ ሰማይ ለሚያደርጉት የጉዞ መሰናዶ በእጅጉ እንደሚጠቅሞዎት እናምናለን፡፡ በዚህ ኮርስ ውስጥ የቀረቡ ሃሳቦች የእኛን አስተሳሰብና ግምት የያዙ ሳይሆኑ በቀጥታ መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን የሚናገሩ ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱሱ ሲናገር ልንናገር፣ ዝም ሲል ደግሞ ዝም ልንል ግድ ነውና፡፡ የምናደርጋቸውን ነገሮች ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ልናደርጋቸው፣ በጽሐፉ በስማቸው የሚጠራቸውንም በግልጽ ልንጠራቸው ይገባል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚለው የነሰ፣ የበዛ፣ ወይም የተለየ ነገር ሁሉ የስህተት ትንህርት ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ቃል እውቀት ማነስ የተነሳ በተፈጠሩት በርካታ ሃይማኖቶች ምክኒያት በአለም ሕዝቦች መካከል ከፍተኛ ግራ በጋባት ይስተዋላል፡፡ በአሁኑ ሰአት በአለማችን ላይ የተለያየ አስተምህሮዎች፣ የስነ መለኮት ምልከታዎች እና አስተሳሰቦች ያልዋቸው ከ 600 በላይ ቤተ እምነቶች ይገኛሉ፡፡ በእነዚህ በርካታ እምነቶች ‹የእመን› ጥያቄ የሚቀርብላቸው የአለማችን ሰዎች ምን እና ማንን ማመን እንዳለባቸው ለመወሰን ግራ ተጋብተዋል፡፡ አዳኛችን የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በፈቃዱ በከፈለው ስቃይና ሞት ለኃጢአታችን ይቅርታ የሚያስፈልገውን ሁሉ አቅርቦልናል፡፡ በፍርድ ቀን ከሰይጣንና ከመላእክቱ ጋር ወደ ወደ ዘላለም እቶን እሳት መጣል አይገባንም፡፡ እናም ለመዳን የወንጌልን እውነት መታዘዝ ይኖርብናል፡፡ ወንጌል ምንድን ነው? ለመዳን ምን ማድረግ ይኖርብኛል? በዚህ ጥናት ውስጥ እግዚአብሔር በሰማይ ያዘጋጀልንን የዘላለም ሕይወት ስጦታ ለመውረስ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ማድረግ እንዳለብን የሚናገረውን አብረን እናያለን፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰዱ ጥቅሶች በሙሉ ጠመም/ዘመም ባለ የፊደል አጻጻፍና ደማቅ ሆነው የቀረቡ ሲሆን ለእነዚህ ጥቅሶች ልብዎንና አእምሮዎን ሊከፍቱ ይገባል፡፡ እግዚአብሔር በእነዚህ ቃሎች ውስጥ ምን ሊያስተላልፍ እንደፈለገ መግለጥ የዚህ ኮርስ ዋነኛ አላማ ነው፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰዱትን እነዚህን ጥቅሶችን ሲያነቡ ለተሰመረባቸው ቃላት ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ እናሳስባለን፡፡ “የዘላለም ሕይወት እንዳልዎት እርግጠኛ ነዎት?” የሚለው ይህ ኮርስ በ10 ትምህርቶች የተከፋፈለ ነው፡፡ ከእያንዳንዱ ትምህርት በኋላ የምርጫ እና የእውነት/ውሸት ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ የጥያቄዎቹን ትክክለኛ መልሶች ከጥያቄዎቹ ጋር በቀረቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውስጥ ያገኙዋቸዋል፡፡ ይህን ኮርስ ማጥናት በዘላለም ሕይወትዎ ላይ ታላቅ ሚና እንዲጫወት የዘወትር ጸሎታችን ነው፡፡ ማነኛውም ጥያቄ ሆነ አስተያየት ቢኖርዎ ለመምህሮ ያሳውቁ ወይም በሚከተለው አድራሻ ቢልኩልን ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ቃል እንገባለን፡፡ መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የሕይወትዎ ጌታ በማድረግ ቀሪው ዘመንዎን ለመኖር ወስነው ከሆነ፣ ይህንን ሊንክ በመጫን ስምዎንና የኢ-ሜይል አድናሻዎን ይላኩልንና፣ ለመንፈሳዊ ሕይወት እድገትዎ የሚቻለንን ሁሉ እገዛ እናደርግሎታለን።

የዘላለም ሕይወት እንዳልዎት እርግጠኛ ነዎት? Read More »

አቋማዊ (positional) ቅድስና ምን ማለት ነው?

መቀደስ ማለት ለንጽህና መለየት ማለት ነው። ሃጢአተኞች በእግዚአብሔር ጸጋ አማካኝነት በተሰጣቸው እምነት በጸጋው በኩል ከሃጢአት ሲድኑ ይቀደሳሉ (ኢፌ. 2:8-9)፤ ማለትም ለንጽህና ይለያሉ። የመዳን (የድነት) ሦስት “ደረጃዎች” አቋማዊ መቀደስ (positional sanctification)፣  ቀጣይነት ያለው መቀደስ (progressive sanctification)፣ እና የመጨረሻው መቀደስ (final sanctification) በመባል ይጠራሉ። በሌላ አነጋገር፣ አቋማዊ ቅድስናችን በክርስቶስ አማካኝነት በእግዚአብሔር ፊት ስላልን ጽድቅ (justification) ሲያውራ፣  ቀጣይነት ያለው ቅድስናችን ደግሞ በምድር ላይ ስለሚኖርን መንፈሳዊ ብስለት (spiritual maturity) ያወራል።  የመጨረሻው መቀደስ የሚያወራው ደግሞ በትንሳኤ ስለምንቅበለው ክብራችን (glorification) ነው። ጌታ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛችን በተቀበልን ቅስበት አቋማዊ ቅድስናን አግኝተናል፤ ወይም ጸድቀናል። ይህም ማለት በኃጢአታችን ምክንያት ሊደርስብን ይችል ከነበረው ቅጣት ሙሉ በሙሉ ድነናል ማለት ነው። ይህ ቅድስና የአንድ ጊዜ ክንውን እንጂ ሂደት አይደልም። ይህ ቅድስና እየተሻሻለ ወይም እያደገ የሚሄድ አይደልም፤ ፍጹምና የመጨረሻ እንጂ። አቋማዊ ቅድስናችን ማለት በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ምክንያት ያገኝነው ቅድስና ማለት ነው። ስለዚህ ቅድስና ስናወራ እያወራን ያለው ስለ ሰማያዊው ቅድስናችን፣ አሁን ሰለ ማይታየው ነገር ግን ወደፊት ሊገለጥ ስላለው ቅድስናችን፣ በክርስቶስ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ ስለ ተሰወረው ቅድስናችን፣ ወይም በክርስቶስ ዳግም ምጽዓት ሊገለጥ ስላለው ቅድስናችን ነው። ባጭሩ፣ ይህ ቅድስና ክርስቶስ ስለ እኛ በአብ ፊት የሚታየው መታየት ማለት ነው። ስለ አቋማዊ ቅድስናችን ስናወራ የምናወራው በእግዚአበሔር ፊት ተቀባይነት ስላገኘውና ፍጹም ስለሆነው ቅድስናችን ነው። አቋማዊ ቅድስናችን በክርስቶስ ለእግዚአበሔር የተለየን ሕዝቦች መሆናችንን ያሚያበስር እንጂ አሁን በምድር ላይ ስላለን መልካም ባሕሪይ አያወራም። ጉዳዩ ሰለ ስፍራችን እንጂ ስለ ባሕሪያችን አይደለም። አቋማዊ ቅድስና የሚያወሳው እኛን አስመልክቶ በሰማይ ስለተከናወነው ለውጥ እንጂ በምድር ስላልን ስነ-ምግባራዊ ለውጥ አይደልም። በምድር ስላለን ስነ-ምግባራዊ ቅድስና ስናወራ ደግሞ እያወራን ያለንው ‘’ቀጣይነት ስላለው መቀደስ (progressive sanctification)” ነው። ይህ ቀጣይነት ያለው ቅድስና፣ ከኃጢአት ልምምድ (practice of sins) እና ከኃጢአት ኃይል (the power of sin) የመዳን ሂደትን ያመለክታል። ይህ የቅድስና ደረጃ አንደ አቋማዊ ቅድስና የአንድ ጊዜ ክንውን ሳይሆን በምድር በሕይወት እስካለን ድረስ ያሚቆይ የቅድስና ጉዞ ወይም ሂደት ነው። ቀጣይነት ያለው ቅድስና ያሚያወራው ስለ ተግባራዊ ቅድስና ወይም ስለ ምግባራዊ ቅድስና ነው። በሌላ አነጋገር ይህ ቅድስና የሚያወራው በምድር ላይ ስላለን የኑሮ ቅድስና ወይም ተጨባጭ ቅድስና ነው። በዚህ ምድር ላይ ያለን የቆይታ ጊዜ ሲያበቃ ማለትም ነፍሳችን ከስጋችን ሲለይ በመጨረሻው መቀደስ (final sanctification) እንቀደሳለን። በዚህኛው የቅድስና ደረጃ ደግሞ ፈፅሞ ከኃጢአት መገኘት (presence of sin) እንድናለን ማለት ነው። በዚህ ቅድስና ውስጥ ስንገባ የመጨረሻውን ክብራችንን እንቀበላለን።     ቀጣይነት ስላልውና ስለ መጨረሻው የቅድስና አይነት እዚህ ላይ ገታ እናድርግና የዚህ ጽሁፍ ዋነኛ ጉዳይ ስለሆነ ስለ አቋማዊ ቅድስና ተጨማሪ ጉዳዮች እናውራ። ከላይ እንደተገለጸው ይህ አይነቱ ቅድስና መንፈስ ቅዱስ በአማኙ ልብ ውስጥ የሚያከናውነው የአንድ ጊዜ ድርጊት ነው። በድነት ወቅት፣ አማኞች ኃጢአተኛ መሆናቸውን ተረድተው ይናዘዛሉ፤ በራሳቸው ማንኛውም ሥራ ራሳቸውን ለማዳን እንደማይችሉ ይገነዘባሉ፤ አዳኝ እንደሚያስፈለጋቸው ይረዳሉ፤ ክርስቶስ ለኃጢአት ክፍያ በመስቀል ላይ የከፈለውን መሥዋዕት ይቀበላሉ፤ እንዲሁም በኢየሱስን ትንሣኤም ያምናሉ።  በዚያ ቅጽበት፣ አማኞች ከድቅድቅ ጨለም ወደሚያስደንቅ ብርሃን ይሻገራሉ። “በእምነት ይጸድቃሉ” ( ሮሜ 5:1 ) ከእግዚአብሔር አንጻር ስፍራቸው (አቋማቸው) ለዘላለም ይቀየራል። የአዲስ መንግስት ዜጎች ይሆናሉ። “እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን” (ቆላ. 1:13 )። አቋማዊ ቅድስና የመንፈሳዊ አድራሻ ለውጥ ማድረግ ማለት ነው። ቀድሞ የእግዚአብሔር ቁጣ የሚጠብቀን ሃጢአተኞች ነበርን። ስፍራችን፣ መለዮአችን ወይም አቋማችን ይህ ነበር። በክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ባመንን ወቅት ግን ባገኘነው አቋማዊ ቅድስና ምክንያት አድራሻችን፣ መለዮአችን ለአንዴና ለመጨረሻው ተቀይሯል፡፡ አሁን የቁጣ ለጆች ሳንሆን የተወደድን የእግዚአብሔር ልጆች ነን። ሃጢአተኞች ሳንሆን በአግዚአብሔር ፊት ፍጹማን ነን። ይህ የአቋማዊ ቅድስና ውጤት ነው፤ ማለትም የኢየሱስ የመስቀል ስራ ውጤት። የመንፈሳዊ አድራሻ ለውጣችን የክርስቶስ አካል ብልቶች እንድንሆን (1ቆሮ. 12:27 )፤ የርስቱ ወራሾች አንድንሆን (1ጴጥ. 2:9 )፤ አዲስ ፍጥረት አንድንሆን (2 ቆሮ. 5:17 )፤ ለኃጢአት አንድንሞት (ሮሜ 6:2 )፤ እና የመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች አንድንሆን (2 ጴጥ. 1:4) አድርጎናል። ድነት የመንፈስ ቅዱስ ፍጹም ስራ ስለሆነ በመንፈሳዊው ስፍራ የተደረገው መነፈሳዊ የአድራሻ ለውጥ በአማኙ ምግባር ምክንያት ዳግመኛ ያማይቀለበስ ለውጥ ነው። የአማኙ መንፈሳዊ አድራሻ ፈጽሞ አይቀየርም ወይም አይለወጥም ወይም አይጠፋም ወይም ቀድሞ ወደነበረበት አይመለስም። ይህን አቋማዊ ቅድስና በገዛ እጃችን መለወጥ አንችልም። በተለወጠው አዲስ አድራሻችን ለዘላለም እንንኖራለን።  አቋማዊ ቅድስና የእግዚአብሔር ስራ ነው። እግዚአብሔር “ከእርሱ (ከክርስቶስ) ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን” (ኤፌ. 2:6 ) የሚለው አረፍተ ነገር በሃላፊ ጊዜ መቀመጡን እናስተውል። ስፍራችን ተቀይሯል። አቋማዊ ቅድስና ማለትም ይህነኑ ማለት ነው። እርሱ ማለትም እግዚአብሔር አስቀምጦታልና አማኝ በዚህ ስፍራ ለዘላለም ይኖራል። አቋማዊ ቅድስና በእኛ ስሜት ላይ የተመሰረት ባለመሆኑ በሰማያዊ ስፍራ ያለነው ስለተሰማን ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃል የሚያረጋግጠው የድነት እውነታ ስለሆነ ብቻ ነው።  ይህንንም በእምነት እንቀበላልን።  ዛሬ በምድር ላይ ያለን ተግባራዊ ልምምድ ከመንፈሳዊ አድራሻችን አንጻር ያማይጣጣም መስሎ በሚሰማን ወቅትም ቢሆን እንኳ ስፍራችን (አቋማዊ ቅድስናችን) አይቀየርም፤ ስሜታችን የእግዚአብሔር ቃል ያወጀውን መንፈሳዊ እውነታ አይቀይረውም። አቋማዊ ቅድስና ያሚያስተላልፈውን መንፈሳዊ እውነታ በአግባቡ ላልተረዳ ሰው አማኙን መረን የሚለቅ ትምሕርት ሊመስል ይችላል። በመሰረቱ፣ አቋማዊ ቅድስና አማኙን ቀጣይነት ወዳለው ቅድስና የሚመራ የአዲስ ሕይወት መነሻ እንጂ የአሮጌው ሕይወት ልምምድ ላይሰንስ (ፈቃድ) አይደለም። ይህም በአማኙ ሕይወት ውስጥ በየጊዜው እያደገ የሚሄድ የመልካም ምግባር ፍሬን ያፈራል ማለት ነው። ዳግም ልደት ያገኙ አማኞች አዲሱ ተፈጥሯቸው ግድ ያሚላቸውን የአዲሱን ተፈጥሮ ባሕሪይ መለማምድ ይጀምራሉ። የመንፈሳዊ አድራሻ ለውጣቸው በምድር ላይ በሚኖሩት የእለት ተእለት ሕይወታቸው ላይ አወንታዊ ለውጥ ማሳደር ይጀምራል። ይህም በየእለቱ እያደገ በሚሔድ የባሕሪይ/የስነ-ምግባር ለውጥ እየታየ ይሄዳል (1ጴጥ.1:15-16)። ይህንንም ቅድስና ቢሆን፣ አቋማዊ ቅድስናን በኛ የሰራው መንፈስ ቅዱስ በታዘዝነው መጠን በእኛ ውስጥ የሚያደርገው ይሆናል። ለማጠቃለል ያህል፣ አቋማዊ ቅድስናችንን ስናገኝ፣ ቀጣይነት ያለው የመቀደስ ሂደት በሕይወታችን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል። ቀጣይነት ያለው መቀደስ ክርስቶስን እየመሰሉ የማድግ የሕይወት ዘመን ሂደት ነው። መንፈስ ቅዱስን በታዘዝነው መጠን እና ሕይወታችንን እንዲቆጣጠር በፈቀድንለት መጠን ክርስቶስን በመምሰል እናድጋለን (ሮሜ. 8:29፤ 2ቆሮ. 3:18)። አቋማዊ ቅድስናችንን ስናገኝ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ቃል እንደመሳሪያነት በመጠቀም ይህንን ቀጣይነት ያለውን የመቀደስ ሂደት በሕይወታችን እውን ያደርጋል (ዮሐ. 17:17)። ምግባራዊ ቅድስናችን የሰማያዊ ቅድስናችን ነጸብራቅ እስኪምስል ድርስ እለት ተእለት ክርስቶስን እየመሰልን እናድጋልን (1ዮሐ. 3:2)። ምንጭ፣ https://www.gotquestions.org/ ትርጉም፣ የሕይወት እንጀራ አገልግሎት

አቋማዊ (positional) ቅድስና ምን ማለት ነው? Read More »

የሰው ልጆች ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው ወይ?

ለዚህ መሰረታዊ ጥያቄ መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ ምላሽ አለው። በመጀመሪያ ደረጃ ይህንንም ሆነ ሌሎችን መነፈሳዊ ጥያቄዎችን ስንመልስ በዘፈቀደ በራሳችን ግምትና አመክኗዊ ሃሳብ ላይ ተደግፍን መሆን የለበትም። ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ገለልተኛ አድርጎ በራሱ ልምምድ እና አመክኗዊ እውቀት ላይ በመደገፍ የሚደርስበት ማንኛውም መደምደሚያ ከንቱ ነውና። ማን የእግዚአብሔር ልጅ መሆን እንዳለበት መወሰን የሰው ድርሻ አይደለም። ይህ የፈጣሪ ውሳኔ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔር ፍጥረት እንደሆኑ በግልጽ ይናገራል “የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና… ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል” (ቆላስይስ 1:16)። እግዚአብሔር መላውን ዓለም እንደሚወድም መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና” (ዮሐ 3:16)። እናም በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ልጅነት ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ የተሰጠ መብት ወይም ስልጣን ነው ብለን ስንደመድም እግዚአብሔር በፍጥረቱ ላይ ያለውን መብት ወይም ለፍጥረቱ ያልውን ፍቅር ፈጽሞ የሚጻረር አለመሆኑን በማስመር ነው። የእግዚአብሔር የፍጥረት ሁሉ አባትነት እግዚአብሔር የፍጥረት ሁሉ ባለቤት ከመሆኑ አኳያ ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ የፍጥረት ሁሉ አባት ተብሎ ተጠቅሷል። ይህ እንግዲህ፣ ሄንሪ ፎርድ “የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ አባት” ወይም ጆርጅ ዋሽንግተን እና ጆን አዳምስ “የዩናይትድ ስቴትስ መስራች አባቶች” ብለን እንደምንጠራቸው ማለት ነው።  ይህ ግን ፍጥረቱ ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር የወዳጅነት አንድነት ወይም ቤተሰባዊ ሕብረት እንዳላቸው አያረጋግጥም። እግዚአብሔር የፍጥረት ሁሉ ባለቤት መሆኑን ያረጋግጣል እንጂ። የእግዚአብሔር አባትነት ከሰው ልጅ ጋር በተያያዘ ብቻ ሳይሆን ክግኡዙ ፍጥረት ጋር በተያያዘም ተገልጿል፣ “በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ (ያዕቆብ 1:17)። በነዚህ አውዶች የተጠቀሰው የእግዚአብሔር አባትነት የፍጥረት ሁሉ ባለቤት መሆኑን የሚያሳይ እንጂ ፍጥረቱ ከእርሱ ጋር ያለውን ሕብረት ወይም ወዳጅነት አያመለክትም።   የእግዚአብሔር የእስራኤል ሕዝብ የቃል ኪዳን አባትነት በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ያለው የቃል ኪዳን ግንኙነት በአባት/ልጅ ቋንቋ ተገልጿል። እግዚአብሔር እስራኤልን “የበኵር ልጄ ነው” (ዘጸአት 4:23) በማለትና ራሱን ደግሞ “የእስራኤል አባት” ( ኤርምያስ 31:9) በማለት ለነቢያቱ ገልጿል። የእስራኤል ሕዝብ በግብፅ ባሪያዎች ነበሩ። ነገር ግን እግዚአብሔር ልዩ የሆነ አባታዊ ፍቅር በማሳየት ከባርነት ቀንበር ዋጅቶ የራሱ አደረጋቸው። ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፤ በምድር ፊት ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር መረጠህ። እግዚአብሔርም የወደዳችሁና የመረጣችሁ ከአሕዛብ ሁሉ በቍጥር ስለ በዛችሁ አይደለም፤ እናንተ ከአሕዛብ ሁሉ በቍጥር ጥቂቶች ነበራችሁና፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ስለ ወደዳችሁ ለአባቶቻችሁም የማለላቸውን መሐላ ስለ ጠበቀ፥ ስለዚህ እግዚአብሔር በጽኑ እጅ አወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ አዳናችሁ። (ዘዳ. 7:6-8) የእስራኤል ሕዝብ ከእግዚአብሔር መንገድ በሳቱ ጊዜ ደግሞ እግዚአብሔር ለሕዝቅኤል እንዲህ ብሎታል፦ እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ በእኔ ላይ ወደ ዐመፁ ወደ ዓመፀኞች ሰዎች ወደ እስራኤል ልጆች እልክሃለሁ። እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ድረስ ዐመፁብኝ። እነርሱ ፊታቸው የተጨማተረ ልባቸውም የደነደነ ልጆች ናቸው። እኔ ወደ እነርሱ እልክሃለሁ፤ አንተም፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በላቸው። (ሕዝ. 2:3-4) እግዚአብሔር ሌሎችን አማልክት የሚያመልኩትን አሕዛብ ሲያጠፋ እስራኤላውያንን ግን የኪዳን ፍቅሩን በማስብ እንዴት እንደታደጋቸው በነቢዩ ሚልክያስ አማካኝነት እንዲህ በማለት ያስታውሳቸዋል፦ “እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፤ እኔስ አባት ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር…” ሚል 1:6 ሚልክያስ 1:10 ላይ፣ “ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን?” የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል በመጥቀስ አንዳንድ ሰዎች፣ እግዚአብሔር ለፈጠረው ለእያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር ሁሉ አባት ነው ሲሉ ይሰማሉ።  ነገር ግን ይህ ያቃሉን አውዳዊ አገባብ ካለመገንዘብ የተነሳ እንጂ በክፍሉ ላይ ሚልክያስ የእግዚአብሔር አባትነት ለእስራኤላውያን መሆኑን በግልጽ አስቀምጧል፤ ቀጣይ ቁጥሮችም ያንኑ ያብራራሉ (ሚል 1:11-12) የልጅነት መብት ለክርስቲያኖች (ለአማኞች) ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቶቹ መግቢያ ላይ፣ “እግዚአብሔር አባታችን” እያለ ሲጀምር ይህ  የእግዚአብሔር አባትነት የሚመለከተው አማኞችን እንደሆነ ግልጽ ነው፦ “በእግዚአብሔር ለተወደዳችሁና ቅዱሳን ልትሆኑ ለተጠራችሁ በሮሜ ላላችሁት ሁሉ፥ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።” ሮሜ. 1:7 “ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።” 1ቆሮ. 1:3 ይህም ልጅነት የተገኘው በክርስቶስ ባገኘነው ቤዛነት በኩል እንደሆን በገልጽ ይናገራል፦   “ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ። ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ።” ገላ. 4:4-5 የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው የሚጠሩት ዳግም ከመንፈስ ቅዱስ የተወለዱ አማኞች ብቻ እንደሆኑ የሚከተሉት ጥቅሶች ያብራራሉ፦ ዮሐ. 1:12-13 “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።” ዮሐ. 11:52 “ስለ ሕዝቡም ሁሉ አይደለም፥ ነገር ግን የተበተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች ደግሞ በአንድነት እንዲሰበስባቸው ነው እንጂ።” ሮሜ. 8:15-16 “አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።” 1ዮሐ 3:1-10 “የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። …ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም።….ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔርም ተወልዶአልና ኃጢአትን ሊያደርግ አይችልም። …” በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የጠፉት ሰዎች የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው አይጠሩም ኤፌሶን 2:3 እንደሚናገረው ከመዳናችን በፊት የእግዚአብሔር ልጆች ሳንሆን “ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች” ነበርን። ሮሜ 9:8 “የሥጋ ልጆች የሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም” ይላል። ቅዱሱን የወንጌል መልእክት የሚቃወሙ አባታቸው እግዚአብሔር እንዳልሆነ ኢየሱስ ከፈሪሳውያን ጋር ባደረገው ውይይት ውስጥ በግልጽ እናያለን፦ “ኢየሱስም አላቸው፦ እግዚአብሔርስ አባታችሁ ከሆነ በወደዳችሁኝ ነበር፤ እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ መጥቻለሁና፤ እርሱ ላከኝ እንጂ ከራሴ አልመጣሁምና” (ዮሐ. 8:42)። በአንጻሩ መልእክቱን ስለተቃወሙ የማን ልጆች እንደሆኑ ሲነግራቸው በዚሁ ከፍለ ውስጥ እናነባለን፦ “እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ” (ዮሐ. 8:44)። በክርስቶስ አምነው ያልዳኑ ሰዎች የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው እንደማይጠሩ የሚከተለው ጥቅስ ይነግረናል፣ “የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ የተገለጡ ናቸው፤ ጽድቅን የማያደርግና ወንድሙን የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም” (1ዮሐ. 3:10)። የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ለመጠራት መብት ወይም ስልጣን ያገኘነው በክርስቶስ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ካገኘነው ሕብረት የተነሳ ነው፣ “እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ። ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ። ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ” ገላ. 4፡5-7። “በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን” ኤፌ. 1:5። ይህ ሃሳብ በሮሜ መልእክት ውስጥም በግልጽ ቀርቧል፣ “በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና። አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።” (ሮሜ. 8:14-17)። ከዚህ በተጨማሪ፣ የሚከተሉት ጥቅሶች በምን በኩልና በማን ምክንያት የእግዚአብሔርን ልጆች መሆን አንደምንችል ይነግሩናል፣ “በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና” (ገላ.

የሰው ልጆች ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው ወይ? Read More »

ከዘላለም ሞት ፍርድ ለመዳን ምን ማድረግ አለብኝ?

ሞትን የማይፈራ ማን ይሆን? ሞት በሰው ልጆች ሕይወት ፊት የተደቀነ ትልቅ ጠላት ነው። ሰው ብዙ ነገር ሊያሸንፍ ይችል ይሆናል። ሞትን ማሸነፍ ግን የማይታሰብ ትግል ነው። ብርቱዎች፣ ጀግኖች፣ መሪዎች፣ ፖለቲከኞች፣ ሳይንቲስቶች ሁሉ የዚህ የሞት ሰይፍ ሰለባ ናቸው። ሞት ትንሽ ትልቅ ሳይል፣ ጥቁር ነጭ ሳይለይ፣ የተማረ መሃይም ሳያስቀር ሁሉን እያጨደ፣ ሁሉን እየከመረ፣ በሁሉ ላይ ነግሶ ዘመን ጠግቧል። ብዙዎች የሚያውቁት ሞት፣ ነፍስ ከስጋ ተለይታ የምትሄድበትን የመጀመሪያ ሞት ነው። ሞት ይህ ብቻ ቢሆን ሃላፊነት የጎደላቸው፣ ኢሞራላውያን፣ እንዳሰኛቸው የፈቀዱትን እና የወደዱትን ሁሉ እያደረጉ የኖሩ ምግባረ ብልሹዎች፣ እግዚአብሔር የለም ብለው በድፍረት የተናገሩ መናፍቃን ሁሉ ከህሊና ክስ ነጽተው በሰላም ወጥተው ባደሩ ነበር። የክርስቲያኖችም የትንሳኤ ስብከት ከንቱ ድካም ነበር። ሆኖም እውነታው ያ አይደለም። ከሞት በኋላ ሌላ ሞት አለ። ከመጀመሪያው ሞት በኋላ ሁለተኛው ሞት አለ። ከአካላዊው ሞት በኋላ መንፈሳዊው ሞት አለ። ከሁሉ በላይ የሚያሰጋው ሞት ይህ ሞት ነው። ምክንያቱም ይህ ሞት እንደ አካላዊው ሞት ጊዚያዊ አይደለም። ይህ ሞት ዘላለማዊ ነው። ይህ ሞት ከመኖር ወደ አለመኖር መቀየር ማለትም ጨርሶ መጥፋት ሳይሆን ከእግዚአብሔር ተለይቶ አሳቱ በማይጠፋበት  የስቃይ ስፍራ መኖር ማለት ነው፣ ‘‘እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል። የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል’’ (ማቴዎስ 13፡40-42)። መንፈሳዊ የሆነውን ይህን ሞት መጽሐፍ ቅዱስ ሁለተኛው ሞት እያለ ይጠራዋል፣ ‘‘ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ። ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው’’ (ዮሐንስ ራዕይ 20፥14)። ‘‘ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው’’ (የዮሐንስ ራዕይ 21፥8)። ለመሆኑ ከዚህ ሁለተኛ ሞት እንዴት ማምለጥ እንችላለን? ከሲኦል እሳት፣ ከዚህ የስቃይ ስፍራ የሚድኑት እነማን ናቸው? ምን ባደርግ ነው ከዘላለም ሞት የምድነው? ከአዳም ውድቀት ጀምሮ በሰው ላይ ተነጣጥራ ያለችው የእግዚአብሔር ቁጣ መብረጃዋ አንድ ነገር ብቻ ነው። የእግዚአብሔር ቁጣ የእግዚአብሔርን ፍትህ ያሳያል። የእግዚአብሔር ፍትህ ደግሞ የእኛን ሞት ይጠይቃል (ሮሜ 6፡23)። የእግዚአብሔር ፍትህ የሃጢአተኛውን ሞት ይሻል (ዕብራውያን 9፡22)። ሁላችን ሃጢአትን ስላደረግን ለዚህ ሞት (የእግዚአብሔር ቁጣ ውጤት) ተዘጋጅቶልናል (ሮሜ 6፡23)። ሃጢአትን ያላደረገ በዚህ ምድር ላይ ስለሌለ (መክብብ 7፡20፤ 1ዮሐንስ 1፡8፤ ሮሜ 3፡10-18) ከዚህ ፍርድ ስር ያልሆነ ሰው በምድር ላይ የለም። ሆኖም ግን፣ ከዚህ ፍርድ ስር መሆናችን ያሳዘነው እግዚአብሔር የራሱን ፍትሃዊ ፍርድ ራሱ ሊቀበልልን ወሰነ። በዚህም ምክንያት ሁላችን ከምንሞት አንድ ልጁ በእኛ ፈንታ እንዲሞት ፈቀደ (የሐንስ 11፡50-52)።  ይህ ቅዱስ ልጁ፣ ኢየሱስ ይባላል። ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ነው (ዮሐንስ 1፡29)። እግዚአብሔር በእኛ ላይ ሊያፈሰው የነበረውን ቁጣ በልጁ በኢያሱስ ላይ አፈሰሰው። ኢየሱስ በእኛ ሞት ፈንታ ሞተልን። በዚህ ምትክ ሞት ምክንያት በኢየሱስ ሞት እና ትንሳኤ የሚያምኑ ሁሉ ከእግዚአብሔር ቁጣ እንዲተርፉ ሆነ። እግዚአብሔር፣ በኢየሱስ ሞትና እና ትንሳኤ ያመኑትን ሁሉ፥ ከሞት ፍርድ ያድናቸዋል (1ተሰሎንቄ 4፡14)። ‘‘በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም’’ (ዮሐንስ  3፥36)። በልጁ ሞት እና ትንሳኤ ማመን ማለት፣ የእርሱ ሞት እግዚአብሔር በእኔ ላይ የነበረውን ቁጣ እንዲያነሳና ከእኔ ጋር ሰላም እንዲያርግ (ሮሜ 5፡1) አድርጎታል ብሎ ማመን ነው። በልጁ የሚያምን ከእንግዲህ የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ የለበትም (ዮሐንስ  3፥36)። የእግዚአብሔር ጠላት (ሮሜ 5፡10) ሳይሆን ወዳጅ ሆኗል። የኢየሱስ የሚያምን ሰው የኢየሱስ ሞት ለእግዚአብሔር ቁጣ በቂ ምላሽ እንደሰጠ ያምናል። ተጨማሪ የማምለጫ ስልቶችንም አይቀየስም። የእግዚአብሔር የድነት መንገድ  (ዮሐንስ 14፡6) በቂ እና ፍጹም እንደሆነ ያምናልና። ከእግዚአብሔር ቁጣ ለመትረፍ የሚበጁ ሌሎች አማራጮች ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደሉም። በራስዎ ‘‘መልካም’’ ምግባር ወይም ስራ እግዚአብሔርን ደስ አሰኝተው ከእግዚአብሔር ቁጣ ለመትረፍ እንደሚችሉ ያስቡ ይሆን? ‘‘የተቀደሱ’’ ቦታዎች ላይ በመሄድ ከእግዚአብሔር ፍርድ የሚያመልጡ ይመስሎታል? ሃይማኖታዊ ክብረ በአላትን አዘውትረው በመጠበቅ ከቁጣው የሚሸሸጉ ይመስሎታል? የፓስተር ወይም የጳጳስ ልጅ ወይም ዘመድ በመሆንዎ የእግዚአብሔርን ፍረድ ሊያጣምምሙ የሚችሉ ይመስሎታል? ቁጣውን ለማፍሰስ በገዛ ፃድቅ ልጁ ላይ እንኳ ያልራራ (ሮሜ 8፡34)፣ ለእርሶ ጽድቅ ያውም ደግሞ የመርገም ጨርቅ ለሆነ ጽድቅዎ የሚራራ ይመስሎታል (ሮሜ 10፡2-3)? ገዳም በመግባትዎ፣ ለድሆች በመመጽወትዎ፣ ሳያጓድሉ በመጾምዎ እና በመፀለዮ፣ አዘውትረው ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድዎ ምክንያት እግዚአብሔርን ከቁጣው የሚመልሱት ይመስሎታል? እንዲህ የሚያስቡ ከሆነ እንግዲያው ክርስቶስ በከንቱ ሞተ (ገላቲያ 2፡21)። እነዚህ መልካም ነገሮች ሁሉ ከዚህ ከእግዚአብሔር ቁጣ በክርስቶስ ሞት አማካኝነት ያመለጠ አማኝ ሁሉ ሊያፈራቸው የሚጠበቁ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ (ገላትያ 5፡20) ናቸው። እናም የሚናቁ አይደሉም። ነገር ግን፣ ከእግዚአብሔር ፍርድ የማምለጫ አቋራጮች አይደሉም። ከእግዚአብሔር ቁጣ እና ፍርድ ማምለጥ የሚቻልበት ሌላ አማራጭ ቢኖር ኖሮ እግዚአብሔር ፃድቅ እና አንድያ ልጁን ለሃጢአተኞች ሞት ተላልፎ እንዲሰጥ የሚፈቅድ የመስሎታል?ቅዱስ ጳውሎስ የሰው ልጅ እንዴት ከእግዚአብሔር ቁጣ ሊድን እንደሚችል የተናገረውን ተናግረን እናጠናቅ፣ ‘‘ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን (ሮሜ 5፡9)’’። መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የሕይወትዎ ጌታ በማድረግ ቀሪው ዘመንዎን ለመኖር ወስነው ከሆነ፣ ይህንን ሊንክ በመጫን ስምዎንና የኢ-ሜይል አድናሻዎን ይላኩልንና፣ ለመንፈሳዊ ሕይወት እድገትዎ የሚቻለንን ሁሉ እገዛ እናደርግሎታለን።  

ከዘላለም ሞት ፍርድ ለመዳን ምን ማድረግ አለብኝ? Read More »

መንፈስ ቅዱስ ማን ነው?

መንፈስ ቅዱስ 1፡ ረዳት ስለ መንፈስ ቅዱስ ሰምተው ያውቃሉ? በርካታ ሰዎች ስለ መንፈስ ቅዱስ ማንንነት ግራ ይጋባሉ። ኢየሱስ በዮሐንስ 14፡16 ላይ፣ “እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤” ሲል ይናገራል። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ተለይቷቸው ወደ አባቱ በሚያርግበት ጊዜ ረዳት እንደሚያስፈልጋቸው ያውቅ ነበር። በጥቅሱ ውስጥ “ሌላ” የሚለው ቃል፣ ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሔር እንደሆነ ሁሉ፣ መንፈስ ቅዱስም እግዚአብሔር እንደሆነ ያሳያል። ኢየሱስን በተቀበልን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ሊኖር ወደ እኛ እንደሚመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። መንፈስ ቅዱስ ወደ እኛ ለምን ይመጣል? ሊረዳን እና እግዚአብሔር እንድንኖረው የሚፈልገውን ኑሮ ለመኖር የሚያስችለንን ሃይል ሊሰጠን። ብዙ ጊዜ የራሳችን መርከብ ካፒቴኖች (ሾፌሮች) መሆን እንሻለን። ነገር ግን ስፍራውን ለመንፈስ ቅዱስ ብንለቅ፣ የሕይወታችንን መሪ እንዲጨብጥ ስለፈቀድንለት እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ ሁኔታ ሕወታችንን እንዲመራ እድል እንሰጠዋለን። ብቸኞች አለመሆናችንን ማወቅ የሚያስደንቅ ነገር አይደለምን? ይህ ብቻ አይደለም፤ መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን የሚፈፅማቸውን ሌሎች ተጨማሪ የእርዳታ ተግባራት  አሉ። ለአብነት፣ መጽሐፍ ቅዱስ ስናነብ ወደ እውነት ይመራናል፣ ምስክሮቹ እንድንሆን ሃይልን ይሞላናል፣ በምንፀልይበት ጊዜ ቃልን በመስጠት ይማልድልናል፣ በሃጢአታችን ይወቅሰናል፣ ከሃጢአት ሃይል ነፃ በማውጣት በውስጣችን እንደሚኖረው እነደ ኢየሱስ ያለ ፃድቅ ባሕሪይ እንዲኖረን ያደርጋል። ስለ መንፈስ ቅዱስ የበለጠ ለማወቅ ይሻሉ? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የዮሐንስ ወንጌል ስለ እርሱ በስፋት ስለሚተርክ ይህን ክፍል ያንቡት፤ በእጅጉ ይወዱታላ። መንፈስ ቅዱስ 2፡ አዲስ ማንነት እና ሃይል ስለ መንፈስ ቅዱስ የተማርኩበትን ጊዜ አስታውሳለው። ኢየሱስ በዮሐንስ መንጌል ምዕራፍ 14 እና 15 ላይ የተናገረው ነገር ስለ መንፈስ ቅዱስ ለመረዳት በእጅጉ ጠቅሞኝ ነበር። ይህ ክፍል፣ የክርስትና ሕይወታችንን ከዛፍ ጋር ያነፃፅራል። ዛፉ በውስጡ ከሚያልፈው ፈሳሽ፣ የምግብ ንጥረ ነገሮችን እና ሃይል ያገኛል። ይህ፣ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ካለው ተግባር ጋር ይመሳሰላል። ከእርሱ ጋር ስንጣበቅ/ስንያያዝ፣ ከእግዚአብሔር የሆነ መልካም ፍሬን ማፍራት እንጀምራለን። ይህ ፍሬ የተለወጠን ሰው ሕይወት የሚወክል ከመሆኑ ባሻገር ዘላለማዊ ዋጋም ይኖረዋል። ገላቲያ 5፡22-23 ይህን ፍሬ እንዲህ በማለት ይዘረዝራል፦ ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ እና ራስን መግዛት። አስተውሉ፣ መንፈስ ቅዱስ በውጣችን መገኘቱ፣ ከውስጥ የሚነሳ የማንነት ለውጥ ያመጣል እንጂ ያለንን አሮጌ ማንነት አያሻሽልም። የፖም ተክል የፖም ፍሬን ለማፍራት መግተርተር ወይም መታገል አያስፈልገውም። ዛፉ በደረሰ ጊዜ ፍሬውን ማፍራቱ አይቀርምና። ኢየሱስን እየመሰልን እንድናድግ በውስጣችን እየሰራ ያለው እግዚአብሔር ራሱ ነው። ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጉዞህን ብትቀጥል፣ እምነትህ መልካሙን እግዚአብሔራዊ ፍሬ ሲያፈራ መመልከትህ የማይቀር ይሆናል። በመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ርዕስ ስር “ፍለጋውን መከተል” የሚለውን ክፍል፣ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን እንድታነብ እንመክራለን፣ ገላቲያ 5፡22-23 ን በቃልህ ለመያዝ ሙከራ አድርግ። መንፈስ ቅዱስ 3፡ አዲስ ማንነት ክርስቶስን ከተቀበልክ በኋላ በሕይወትህ ልዩነት አስተውለሃል? መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል” ይላል – 2ቆሮንቶስ 5፡17። ኢየሱስ በአንተ ፈንታ ስለሃጢአትህ እንደሞተ በእውነት ካመንህ፣ ያ አሮጌና ኋጢአተኛ ሕይወትህ አልፏል። ከአሮጌና ኋጢአተኛ ሕይወትህ ነፃ በመውጣት ለእርሱ እንድትኖር እግዚአብሔር አዲስ ሕይወት ሰጥቶሃል። ከዚህ ቀደም የሃጢአት እና የሞት ባሪያ እንደነበርክ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ሆኖም ግን እግዚአብሔር ከዚህ ባርነት በልጁ ሞት መልሶ በመግዛት ተቤዥቶሃል። ይህ ብቻ አይደለም፤ ኢየሱስን እንደ አዳኝ ስትቀበለው፣ እንደ ልጁ አድርጎ ተቀብሎሃል። አዲስ ማንነት ሰጥቶሃል፤ ይህም ማንንት የእግዚአብሔር ቤተሰብ ሆነህ እንድትቆጠር አድርጎሃል! የእግዚአብሔር ልጆች እንደመሆናችን መጠን ለስጋዊ ምኞቶቻችን መኖር አይገባንም። አዲስ ሕይወት ለመኖር በክርስቶስ ነፃ ወጥተናልና። “አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።” – ሮሜ 8፡15-16። ኢየሱስ የሞተው አንተን የእርሱ ባሪያ ለማድረግ ሳይሆን ከአንተ ጋር ሕብረት ማድረግ ስለሚፈልግ ነው። የእርሱ ልጆች መሆናችን የፀና መሆኑ ይረጋገጥ ዘንድ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ይሰጠናል። እኛም ከፍርሃት የተነሳ ሳይሆን እርሱ አባችን በመሆኑ ምክንያት እንታዘዘዋለን፣ ደስ እናሰኘዋለንም። ቤተሰቡ ስላደረገህ እግዚአብሔርን አመስግነኧው ታውቃለህ? እስቲ አሁን እናመስግነው። እግዚአብሔር ሆይ፣ በልጅህ በኢየሱስ በኩል ስላፈሰስክልን ፍቅር እናመሰግንሃለን። ልጆችህ ተብለን መጠራታችን ምን ማለት እንደሆነ ይበልጥ እንድንረዳው እና በዚህም እውነት መኖር እንድንችል እርዳን፣ አሜን! መንፈስ ቅዱስ 4፡ ትዕዛዝ እና ተስፋ ገላቲያ 5፡22፦23 ን በቃልህ ያዝክ? ጥቅሱ እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ ሊያፈራቸው የሚፈልጋቸውን ፍሬዎች ዝርዝር የያዘ ክፍል ነው። እነዚህ ፍሬዎች በራሳቸው ግቦች እንዳይደሉ አስተውል። ግቡ፣ ክርስቶስ በአንተ ሕይወት ውስጥ ለሌሎች መገለጡ ሲሆን፣ ፍሪዎቹ ደግሞ ለዚህ ግብ ተግባራዊ መሆን እንደ ግብዓቶች ናቸው። እግዚአብሔርን ደስ በማሰኘት እንድትኖር በውስጥህ እየሰራ ያለው መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ማወቅ የዚህ ሃሳፍ ቁልፉ ነጥብ ነው። ኤፌሶን 5፡15-18 እንዲህ ይላል፣ “እንግዲህ … እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ … የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ። መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና።” በስካር እና መንፈስ ቅዱስን “በመሞላት” መካከል ቀጥተኛ ንጽጽር አለ። ስትሰክር፣ በአልኮል መጠጡ ቁጥጥር ወይም ተጽዕኖ ስር ትሆናለህ። በመንፈስ ቅዱስ “መሞላትም” ከዚህ ሀሳብ ጋር ይመሳሰላል። መንፈስ ቅዱስ ሀሳባችንን እና ተግባራችንን እንዲቆጣጠር ልንፈቅድለት ይገባል። በውጤቱም የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎችን በሕይወታችን እናያለን። ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እና ትዕዛዝ ጭምር መሆኑን ልብ በል። ትዕዛዝ እንጂ አማራጭ አይደለም። “ይህን እንዴት ላደርግ እችላለው?” የሚል ጥያቄ አንስተህ ከሆነ መልሱ “በእምነት፣” የሚል ይሆናል። በ 1ኛ ዮሐንስ 5፡14-15 መሰረት፣ እንደፈቃዱ አንዳች ብንለምን፣ እግዚአብሔር ይሰማናል፣ ያደርገውማል። መንፈስ ቅዱስ ሕይወታችንን እንዲመራ እና እንዲቆጣጠር መፀለይ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና እንደፈቃዱ የሆነ ፀሎት መሆኑ ማንንም አያጠያይቅም። እናም፣ በቃሉ መሰረት ፀሎታችንን ሰምቶ እንደሚያደርገው ልናምነው እንችላልን። እስቲ አሁን ይህን ፀልይ። እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ትችል ዘንድ ጥበብ እና ሃይል እንዲሰጥህ መንፈስ ቅዱስን ለምን፤ እርሱም ይህንኑ ያደርጋል።    መንፈስ ቅዱስ 5፡ ጦርነት እና ውትድርና ክርስቶስን እንደ ጌታ በመቀበል የጀመርከው አዲስ የሕይወት ጉዞ አስደሳች እየሆነልህ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ። ከእግዚአብሔር ጋር ስላለን ሕብረት እና በአለም ስላለው ክፋት ተጨባጭነት የሚያወራውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላካፍልህ እፈልጋለው። መጽሐፍ ቅዱስ በ2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡3-4 ላይ እንዲህ ይላል፦ “እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል። የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍም።” ውትድርና ከባድ ሙያ ነው፤ ብዙ ጊዜ መከራንም ይጠይቃል። ወታደር መከራ የሚቀበል ብቻ ሳይሆን አጋር ወታደሮችን የሚረዳ ጭምር ነው። የአንድ ሰራዊት ሕይወት እያንዳንዱ ወታደር የግል ድርሻውን በተገቢው ሁኔታ በመፈፀሙ ላይ የተመሰረተ ነው። የክርስቲያን ሕይወት ቀላል አይደልም። ቤተ ክርስቲያን፣ እያንዳንዳችን ለጦርነት የምንዘጋጅበትና የምንከትበት ስፍራ እንጂ ተራ ማሕበራዊ ክለብ አይደለችም። አብረውን ለጦርነት የዘመቱት ሁሉ በጦርነቱ ድልን እንዲቀዳጁ ሁላችን የየበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይኖርብናል። ለዚህ ጦርነት ስንዘጋጅ ማወቅ ስላለብን ነገር መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ በማለት ያሳስበናል፦ “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ” – ኤፌሶን 6፡12። በጦርነት ውስጥ ነን ካልን ዘንድ ጠላታችን ማን ነው? ኤፌሶን 6፡10-11 ጠላታችን ዲያብሎስ፣ ወይም ሰይጣን እንደሆነ ይነግረናል። የሰይጣን እና የክፋት መንፈሳዊያን ሰራዊቱ ህልውና ተጨባጭ እውነታ ነው። እነዚህ የክፋት መንፈሳዊያን ሰራዊቶች ክርስቲያኖችን ይዋሻሉ፣ ይከሳሉ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ሕብረትም ለማጥፋት ይጥራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ሰይጣን የሃሰት አባት እንደሆነ ይነግረናል። እንዴት ነው ይህን ጠላታችንን የምንዋጋው? ልክ ኢየሱስ እንዳደረገው። የጦር መሳሪያችን እውነት ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል እና ፀሎት። በዚህ ጦርነት ውስጥ ቁልፉ ነገር በእኛ ውስጥ ያለው መንፈስ ቅዱስ በዓለም ካለው ሰይጣን እንደሚበልጥ ማወቅ ነው። እግዚአብሔር ላንተ ያለው የተስፋ ቃል እንዲህ ይነበባል፣

መንፈስ ቅዱስ ማን ነው? Read More »

ታላቁ የእግዚአብሔር የቁጣ ቀን መጥቶአል፤ ማንስ ሊቆም ይችላል? ራዕይ 6፡17

የሰው ልጅ የፈጣሪውን ትዕዛዝ በገዛ ፈቃዱ ከተላለፈባት እለት ጀምሮ ቅዱስ የሆነው ፈጣሪ፣ ከእርሱ ክብር በጎደለው (ሮሜ 3፡22-23) ፍጡሩ ላይ ተቆጥቷል። ይህ ቁጣ ሃጢአተኞችን ሁሉ ሊበላ ያለ ቁጣ ነው። እውነትን በዓመፃ በከለከሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ የሚገለጥበት ጊዜ ደርሷል (ሮሜ 1፥18)። ቅዱስ ዮሐንስ በራዕዩ ላይ የእግዚአብሔር የቁጣ ጽዋዎች ሞልተው በምድር ላይ የሚፈሱበት ሰአት እንዳለ ገልጿል (ራእይ 16፥1፤ ራእይ 15፥7)። ይህ የእግዚአብሔር ቁጣ ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ የተጠበቀ አይደለም። ለተወሰነ የሃይማኖት ተከታዮች፣ ለተወሰኑ ዘሮች ወይም ነገዶች፣ ወይም ለተወሰኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ብቻ ወይም የቆዳ ቀለም ላላቸው የተጠበቀም አይደለም። ለእርሱ በማይታዘዙ ሰዎች ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ይመጣል (ኤፌሶን 5፥6፤ ቆላስይስ 3፥6)። የእግዚአብሔር ቁጣ ሕይወታችንን ለዘላለም ከእግዚአብሔር ቅድስና ለይቶ በዘላለም እሳት ውስጥ የሚያኖር ቁጣ ነው። ይህ ቁጣ ከምናስበው በላይ ብርቱ ነው (ራእይ 19፥15)። ይህ ታላቅ የእግዚአብሔር ቁጣ ንስሃ በማይገቡ ሰዎች ላይ እንደነደደ እስከ ፍርድ ቀን ድረስ እንደሚቆይ ጳውሎስ በ ሮሜ 2፥5 እንዲህ በማለት ያሳየናል፣ ‘‘ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሐ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቍጣ ቀን ቍጣን በራስህ ላይ ታከማቻለህ።’’ ‘‘ታዲያ፣ እንዴት ከዚህ የእግዚአብሔር ቁጣ ልተርፍ እችላለው?’’ መልሱን ሐዋሪያው ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ያሳውቀናል፣  ‘‘በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም’’ (ዮሐንስ  3፥36)። ከአዳም ውድቀት ጀምሮ በሰው ላይ ተነጣጥራ ያለችው የእግዚአብሔር ቁጣ መብረጃዋ አንድ ነገር ብቻ ነው። የእግዚአብሔር ቁጣ የእግዚአብሔርን ፍትህ ያሳያል። የእግዚአብሔር ፍትህ ደግሞ የእኛን ሞት ይጠይቃል (ሮሜ 6፡23)። የእግዚአብሔር ፍትህ የሃጢአተኛውን ሞት ይሻል (ዕብራውያን 9፡22)። ሁላችን ሃጢአትን ስላደረግን ለዚህ ሞት (የእግዚአብሔር ቁጣ ውጤት) ተዘጋጅቶልናል (ሮሜ 6፡23)። ሃጢአትን ያላደረገ በዚህ ምድር ላይ ስለሌለ (መክብብ 7፡20፤ 1ዮሐንስ 1፡8፤ ሮሜ 3፡10-18) ከዚህ ፍርድ ስር ያልሆነ ሰው በምድር ላይ የለም። ሆኖም ግን፣ ከዚህ ፍርድ ስር መሆናችን ያሳዘነው እግዚአብሔር የራሱን ፍትሃዊ ፍርድ ራሱ ሊቀበልልን ወሰነ። በዚህም ምክንያት ሁላችን ከምንሞት አንድ ልጁ በእኛ ፈንታ እንዲሞት ፈቀደ (የሐንስ 11፡50-52)።  ይህ ቅዱስ ልጁ፣ ኢየሱስ ይባላል። ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ነው (ዮሐንስ 1፡29)። እግዚአብሔር በእኛ ላይ ሊያፈሰው የነበረውን ቁጣ በልጁ በኢያሱስ ላይ አፈሰሰው። ኢየሱስ በእኛ ሞት ፈንታ ሞተልን። በዚህ ምትክ ሞት ምክንያት በኢየሱስ ሞት እና ትንሳኤ የሚያምኑ ሁሉ ከእግዚአብሔር ቁጣ እንዲተርፉ ሆነ። እግዚአብሔር፣ በኢየሱስ ሞትና እና ትንሳኤ ያመኑትን ሁሉ፥ ከሞት ፍርድ ያድናቸዋል (1ተሰሎንቄ 4፡14)። ‘‘በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም’’ (ዮሐንስ  3፥36)። በልጁ ሞት እና ትንሳኤ ማመን ማለት፣ የእርሱ ሞት እግዚአብሔር በእኔ ላይ የነበረውን ቁጣ እንዲያነሳና ከእኔ ጋር ሰላም እንዲያርግ (ሮሜ 5፡1) አድርጎታል ብሎ ማመን ነው። በልጁ የሚያምን ከእንግዲህ የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ የለበትም (ዮሐንስ  3፥36)። የእግዚአብሔር ጠላት (ሮሜ 5፡10) ሳይሆን ወዳጅ ሆኗል። የኢየሱስ የሚያምን ሰው የኢየሱስ ሞት ለእግዚአብሔር ቁጣ በቂ ምላሽ እንደሰጠ ያምናል። ተጨማሪ የማምለጫ ስልቶችንም አይቀየስም። የእግዚአብሔር የድነት መንገድ  (ዮሐንስ 14፡6) በቂ እና ፍጹም እንደሆነ ያምናልና። ከእግዚአብሔር ቁጣ ለመትረፍ የሚበጁ ሌሎች አማራጮች ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደሉም። በራስዎ ‘‘መልካም’’ ምግባር ወይም ስራ እግዚአብሔርን ደስ አሰኝተው ከእግዚአብሔር ቁጣ ለመትረፍ እንደሚችሉ ያስቡ ይሆን? ‘‘የተቀደሱ’’ ቦታዎች ላይ በመሄድ ከእግዚአብሔር ፍርድ የሚያመልጡ ይመስሎታል? ሃይማኖታዊ ክብረ በአላትን አዘውትረው በመጠበቅ ከቁጣው የሚሸሸጉ ይመስሎታል? የፓስተር ወይም የጳጳስ ልጅ ወይም ዘመድ በመሆንዎ የእግዚአብሔርን ፍረድ ሊያጣምምሙ የሚችሉ ይመስሎታል? ቁጣውን ለማፍሰስ በገዛ ፃድቅ ልጁ ላይ እንኳ ያልራራ (ሮሜ 8፡34)፣ ለእርሶ ጽድቅ ያውም ደግሞ የመርገም ጨርቅ ለሆነ ጽድቅዎ የሚራራ ይመስሎታል (ሮሜ 10፡2-3)? ገዳም በመግባትዎ፣ ለድሆች በመመጽወትዎ፣ ሳያጓድሉ በመጾምዎ እና በመፀለዮ፣ አዘውትረው ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድዎ ምክንያት እግዚአብሔርን ከቁጣው የሚመልሱት ይመስሎታል? እንዲህ የሚያስቡ ከሆነ እንግዲያው ክርስቶስ በከንቱ ሞተ (ገላቲያ 2፡21)። እነዚህ መልካም ነገሮች ሁሉ ከዚህ ከእግዚአብሔር ቁጣ በክርስቶስ ሞት አማካኝነት ያመለጠ አማኝ ሁሉ ሊያፈራቸው የሚጠበቁ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ (ገላትያ 5፡20) ናቸው። እናም የሚናቁ አይደሉም። ነገር ግን፣ ከእግዚአብሔር ፍርድ የማምለጫ አቋራጮች አይደሉም። ከእግዚአብሔር ቁጣ እና ፍርድ ማምለጥ የሚቻልበት ሌላ አማራጭ ቢኖር ኖሮ እግዚአብሔር ፃድቅ እና አንድያ ልጁን ለሃጢአተኞች ሞት ተላልፎ እንዲሰጥ የሚፈቅድ የመስሎታል?ቅዱስ ጳውሎስ የሰው ልጅ እንዴት ከእግዚአብሔር ቁጣ ሊድን እንደሚችል የተናገረውን ተናግረን እናጠናቅ፣ ‘‘ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን (ሮሜ 5፡9)’’። መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የሕይወትዎ ጌታ በማድረግ ቀሪው ዘመንዎን ለመኖር ወስነው ከሆነ፣ ይህንን ሊንክ በመጫን ስምዎንና የኢ-ሜይል አድናሻዎን ይላኩልንና፣ ለመንፈሳዊ ሕይወት እድገትዎ የሚቻለንን ሁሉ እገዛ እናደርግሎታለን።

ታላቁ የእግዚአብሔር የቁጣ ቀን መጥቶአል፤ ማንስ ሊቆም ይችላል? ራዕይ 6፡17 Read More »

ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና ማለት ምን ማለት ነው?

ስለ ፋሲካ ብዙ ሰዎች የተለያየ ትርጉምና ምልከታ አላቸው። ይህ ክብረ በአል ከማንም በላይ ከአይሁድ ባህል ጋር የጠበቀ ግንኙነት ይኑረው እንጂ፣ ለክርስቲያኖች ልዩ ስፍራ አለው። ለመሆኑ ፋሲካ ምንድን ነው? በፋሲካ ምን ሆነ? የፋሲካ በአል ጥላነቱ ለማን ነው? አማናዊው ፋሲካ ማን ነው? በፋሲካ ለሰው ልጆች ምን ሆነ? ይህን ሃሳብ ለመረዳት ከሰው ልጆች ውድቀት መነሳት ግድ ስለሚል ከዛ እንጀምርና ምስጢሩን አንመርምር፡- ከዚህ በታች በቀረቡት ጥቅሶች ውስጥ ጳውሎስ፣ የሰው ልጅ በውድቀት ወቅት በእግዚአብሔር ፊት ምን ይመስል እንደነበረ እና ከዚህ ውድቀቱ እግዚአብሔር ሲታደገው ደግሞ ምን እንደሆነለት ይናገራል፡፡ ሮሜ. 3፡10-12 እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ፡- ፃድቅ የለም፣ አንድስ እንኳ፤ አስተዋይ የለም፣ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፡፡ ሁሉ ተሳስተዋል፣ በአንድነትም የማይጠቅሙ ሆነዋል፣ ቸርነት የሚያደርግ የለም አንድስ እንኳ የለም፡፡ ሮሜ. 3፡10-12 እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ፡- ፃድቅ የለም፣ አንድስ እንኳ፤ አስተዋይ የለም፣ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፡፡ ሁሉ ተሳስተዋል፣ በአንድነትም የማይጠቅሙ ሆነዋል፣ ቸርነት የሚያደርግ የለም አንድስ እንኳ የለም፡፡ ኤፌ. 2፡1-9 በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሰራው መንፈስ አለቃ እንደሆነው፣ በአየር ላይ ስልጣን እንዳለው ኑሮ፣ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሰራው መንፈስ አለቃ እንደሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፣ በፊት ተመላለሳችሁባቸው፡፡ በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ የስጋችንንና የልቦናችንን ፈቃድ እያደረግን በስጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን፤ እንደ ሌሎችም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን፤ ነገር ግን ግን እግዚአብሔር በምህረቱ ባለጠጋ ስለ ሆነ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሳ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ህይወትን ሰጠን፡፡ በፀጋ ድናችኋል፤ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የፀጋውን ባለጠግነት ያሳይ ዘንድ ከእርሱ ጋር አስነሳን፤ በክርስቶስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን፡፡ ፀጋው በእምነት አድኖአችኃልና፣ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከስራ አይደለም፡፡ ኤፌ. 2፡12 ከእስራኤል መንግስት ርቃችሁ፣ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ፣ በዚህም አለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ፡፡ ሮሜ. 5፡6-10 ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቷልና፡፡ ስለ ፃድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ገና ኃጢያተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል፡፡ ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከፀደቅን በእርሱ ከቁጣው እንድናለን፡፡ ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን ይልቁንም ከታረቅን በኃላ በህይወቱ እንድናለን፡፡ ኤፌ. 4፡17-19 እንግዲህ አሕዛብ ደግሞ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ፣ በጌታም ሆኜ እመሰክራለሁ፣ እነርሱ ባለማወቃቸው ጠንቅ በልባቸውም ደንዳንነት ጠንቅ ልቡናቸው ጨለመ፣ ከእግዚያብሔርም ሕይወት ራቁ፤ ደንዝዘውም በመመኘት ርኩሰትን ሁሉ ለማድረግ ራሳቸውን ወደ ሴሰኝነት አሳልፈው ሰጡ፡፡ ክርስቶስ ስለእኛ በመሞት ቤዛ ሆነን የሚለውን ቁም ነገር ለመጨበጥ አሁንም ከቀድሞ አባትና እናታችን (አዳም እና ሔዋን) ስህተት መነሳት ይኖርብናል። ሀ. የእግዚአብሔር ጸጋ፣ አዳምና ሔዋን ባለመታዘት እግዚአብሔርን በበደሉበት ወቅት ተገልጧል፡፡ በጥላ መልክ የተገለጠው ይህ ጸጋ ኋላ ላይ ለሚመጣው አማናዊው ጸጋ አመልካች ነበር። ለመሆኑ በአዳም ውድቀት ወቅት የተገለጠው ይህ ጥላ (ምሳሌ) ምን ነበር? ዘፍጥረት 2፡15-17 ‘‘እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በኤደን ገነት አኖረው ፡፡እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው ፡-ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ & ነገር ግን መልካምና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና፡፡” ዘፍጥረት 3፡ ፡6-7 ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፣ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፣ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ። የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፣ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ አወቁ፤ የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም አደረጉ። ፡8-12 እነርሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔርን የአምላክን ድምፅ ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ፤ አዳምና ሚስቱም ከእግዚአብሔር ከአምላክ ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ። እግዚአብሔር አምላክም አዳምን ጠርቶ። ወዴት ነህ? አለው። እርሱም አለ። በገነት ድምፅህን ሰማሁ፤ ዕራቁቴንም ስለ ሆንሁ ፈራሁ፣ ተሸሸግሁም። እግዚአብሔርም አለው። ዕራቁትህን እንደ ሆንህ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ በላህን? አዳምም አለ። ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ። ፡13 እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን፡- ይህ ያደረግሽው ምንድን ነው? አላት ፡፡ ሴቲቱም አለች ፡- እባብ አሳተኝና በላሁ፡፡” ፡20 ”አዳምም ለሚስቱ ስም አወጣ የሕያዋን እናት ናትና፡፡” ፡21-24 እግዚአብሔር አምላክም ለአዳምና ለሚስቱ የቁርበትን ልብስ አደረገላቸው፣ አለበሳቸውም። እግዚአብሔር አምላክም አለ። እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ አሁንም እጁን እንዳይዘረጋ፣ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ፣ ለዘላለምም ሕያው ሆኖ እንዳይኖር፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክ ከዔድን ገነት አስወጣው፣ የተገኘባትን መሬት ያርስ ዘንድ። አዳምንም አስወጣው፣ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ። አዳምና ሔዋን አንድ ሕግ ተሰጣቸው፤ እርሱንም አልታዘዙም፡፡ ከዚያም በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ለማግኘት ሞከሩ (ይህ የበለስ ቅጠሎች ሰፍተው በመልበሳቸው ተመስሏል፡፡) እርስ በእርሳቸው ተካሰሱ፡፡ ለአመጻቸውም የሚገባቸውን አገኙ፤ ይህም ፍትህ ይባላል፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር የማይገባቸውን ነገር ሰጣቸው፤ ይህ ደግሞ ፀጋ ይባላል፡፡ ይህም እግዚአብሔር ያዘጋጀው እንስሳ በእነርሱ ፈንታ በመታረዱ ተመስሏል፡፡ ምንም በደል የሌለበት እንስሳ በእነርሱ ኃጢያት ምክንያት ታርዷል፡፡ የዚህ እንስሳ መስዋዕት፣ ኋላ ለሚመጣውና ለሰው ልጆች ሁሉ ኃጢያት ራሱን ለመስቀል ሞት አሳልፎ ለሚሰጠው ለኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌው ነበር፡፡ ለ. ፋሲካ፣ ክርስቶስ በእኛ ምትክ/ቤዛ መሆን ምሳሌ ነው። ዘጸአት 12፡1 በግብፅ ምድር እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፡- ፡12-13 እኔም በዚያች ሌሊት በግብፅ አገር አልፋለሁ፣ በግብፅም አገር ከሰው እስከ እንስሳ ድረስ በኵርን ሁሉ እገድላለሁ፤ በግብፅም አማልክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። ደሙም ባላችሁበት ቤቶች ምልክት ይሆንላችኋል፤ ደሙንም ባየሁ ጊዜ ከእናንተ አልፋለሁ፤ እኔም የግብፅን አገር በመታሁ ጊዜ መቅሰፍቱ ለጥፋት አይመጣባችሁም። ፡21-22 ሙሴም የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠርቶ አላቸው። በየቤታችሁ ጠቦት ምረጡ፣ ወስዳችሁም ለፋሲካ እረዱት። ከሂሶጵ ቅጠልም ጭብጥ ውሰዱ፣ በዕቃ ውስጥ ባለውም ደም ንከሩት፣ በዕቃውም ውስጥ ካለው ደም ሁለቱን መቃኖችና ጉበኑን እርጩ፤ ከእናንተም አንድ ሰው ከቤቱ ደጅ እስኪነጋ ድረስ አይውጣ። ፡23 እግዚአብሔር ግብፃውያንን ይመታ ዘንድ ያልፋልና፤ ደሙንም በጉበኑና በሁለቱ መቃኖች ላይ ባየ ጊዜ እግዚአብሔር በደጁ ላይ ያልፋል፣ አጥፊውም ይመታችሁ ዘንድ ወደ ቤታችሁ እንዲገባ አይተውም ፡24-27 ለእናንተ ለልጆቻችሁም ለዘላለም ሥርዓት አድርጋችሁ ይህችን ነገር ጠብቁ። እንዲህም ይሆናል፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረ ወደ ሚሰጣችሁ አገር በገባችሁ ጊዜ ይህን አምልኮ ጠብቁት። እንዲህም ይሆናል፤ ልጆቻችሁ። ይህ አምልኮ ለእናንተ ምንድር ነው? ባሉአችሁ ጊዜ፣ እናንተ። በግብፅ አገር በእስራኤል ልጆች ቤቶች ላይ አልፎ ግብፃዊያንን በመታ ጊዜ፣ ቤቶቻችንን ያዳነ የእግዚአብሔር የማለፉ መሥዋዕት ይህች ናት ትሉአቸዋላችሁ። ፡29-30 እንዲህም ሆነ፤ እኩል ሌሊት በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር፣ በዙፋን ከተቀመጠው ከፈርዖን በኵር ጀምሮ በግዞት እስካሉት እስከ ምርኮኞቹ በኵር ድረስ፣ የግብፃውያንን በግብፅ ምድር የተገኘውን በኵር ሁሉ፣ የእንስሳውንም በኵሮች ሁሉ መታ። ፈርዖንም ባሪያዎቹም ሁሉ ግብፃውያንም ሁሉ በሌሊት ተነሡ፤ የሞተ የሌለበት ቤት አልነበረምና በግብፅ ምድር ታላቅ ልቅሶ ሆነ። ዮሐ. 1፡29 በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ ፡- እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ፡፡ 1ቆሮ. 5፡7 “ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንዲያቦካ አታውቁምን እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ፡፡ ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፡፡ እስራኤላውያን በግብፅ የባርነት ቀንበር ስር ነበሩ፡፡ ጠቦት በእነርሱ ምትክ ተገደለ፡፡ የጠቦቱ ደም ባለበት ቤት ላይ ሁሉ የእግዚአብሔር ፍርድ ይከለከል ነበር፡፡ ጌታ ደሙን በመቃኖቹ ላይ እና በጉበኑ ላይ ሲመለከት ፍርድ ከዚያ ቤት

ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና ማለት ምን ማለት ነው? Read More »

ፀሎት ምንድን ነው? ፀሎት ምን ምን ያካትታል?

ፀሎት አፅናፈ አለምን ከፈጠረና ከሚቆጣጠር፣ እንዲህ ታላቅ ሆኖ ሳለ ደግሞ ዝርዝርና ትናንሽ በሆኑ የሕይወታችን ክፍሎች ውስጥ ሳይቀር ድርሻ እንዲኖረው ከሚሻ የፍቅር አምላክ ጋር የምናደርገው ጥልቅ ውይይት ነው፡፡ እግዚአብሔርን መቅረብም ሆነ ማነጋገር የምንችለው በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ በኩል ብቻ ነው። የትኛውም መልካም ስራችን ቅዱሱ እግዚአብሔር ፊት ሊያቀርበን እንደማይችል መረዳት ይኖርብናል፡፡ በፀሎት ወደዚህ ቅዱስ አምላክ  ፊት መቅረብን እንደ ታላቅ እድል መቁጠር ይኖርብናል፡፡ በየትኛውም ውይይት ላይ እንደተለመደው፣ መስማት የውይይት ትልቁ ክፍል ነው፡፡ እግዚአብሔር በልቤ ሲናገር ወይም አንድ አዲስ ነገር ሲገልጥልኝ በማሰላሰልና በማድመጥ ጊዜውን መጠቀም ይኖርብኛል፡፡ እግዚአብሔር ዘወትር ከእርሱ አንዳች ነገር እንደ ምንጠብቅ ሆነን እንድንኖር ይወዳል፡፡ እግዚአብሔር ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚፈልጋቸውን ነገሮች ቅድሚያ መስጠት፣ ለእግዚአብሔር  ያለንን ክብርና  የሚገባውን ትክክለኛ  ስፍራ መስጠታችንን የምናረጋግጥበት አንዱ  መንገድ  ነው፡፡ ይህን ለማድረግ፣ ትራፊውን ጊዜያችንን፣ ትራፊውን ጉልበታችንን እና ትራፊውን የኛ የሆነውን ነገር ከመስጠት ወጥተን ምርጥ የምንለውን ነገራችንን ለእርሱ የማቅረብ ልምምድ ውስጥ መግባት ይጠበቅብናል፡፡ ሀ. ከእግዚአብሔር ጋር ያለኝ የውይይት (የፀሎት) ጊዜ መጠን- በሚኖረኝ የልብ ዝግጅት፣ ቅድሚያ  ስለ ምሰጣቸው ነገሮች ባለኝ እውነተኛ ግምገማ እና ስለ እርሱ ግርማ ባለኝ እውቀት መጠን እየጨመረ ይሄዳል፡፡ መዝ. 5፡3 (አ.መ.ት.) እግዚአብሔር ሆይ፤ በማለዳ ድምጼን ትሰማለህ፤ በማለዳ ልመናዬን በፊትህ አቀርባለሁ፤ ፈቃድህንም በጥሞና እጠባበቃለሁ፡፡ መዝ. 37፡7 (አ.መ.ት.) እግዚአብሔር ፊት ጸጥ በል፤ በትዕግሥትም ተጠባበቀው፤ … መዝ. 119፡147 (አ.መ.ት.) ትረዳኝ ዘንድ ጎሕ ሳይቀድ ተነስቼ እጮኻለሁ፤ ቃልህንም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ኢሳ. 50፡4 … ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፣ እንደ ተማሪዎችም ትሰማ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃል፡፡ ለ. ፀሎት እግዚአብሔርን ማድነቅ፣ ማመስገን እና መባረክን ያካትታል፡፡ መዝ. 145፡2-3 በየቀኑ ሁሉ እባርክሀለሁ፣ ስምህንም ለዘላለም ዓለምም አመሰግናለሁ፡፡ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፣ እጅግም የተመሰገነ ነው፣ ለታላቅነቱም ፍፃሜ የለውም፡፡ መዝ. 146፡1-2 ሃሌ ሉያ ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔርን አመስግኚ በሕይወቴ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ በምኖርበት ዘመን ሁሉ ለአምላኬ እዘምራለሁ፡፡ ዳን. 6፡10 ዳንኤልም ፅህፈቱ እንደ ተፃፈ ባወቀ ጊዜ ወደ ቤቱ ገባ የእልፍኙም መስኮቶች ወደ ኢየሩሳሌም አንፃር ተከፍተው ነበር ቀድሞም ያደርግ እንደ ነበር በየዕለቱ ሶስት ጊዜ በጉልበቱ ተንበርክኮ በአምላኩ ፊት ፀለየ አመሰገነም፡፡ ኤፌ. 5፡19-20 በመዝሙር እና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በእርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ፣ ሁልጊዜ ስለሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለሁሉ አመስግኑ፡፡ ፊሊ. 4፡6-7 በነገር ሁሉ በፀሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ፡፡ አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁን እና አሳባችሁን በክርስቶስ ይጠብቃል፡፡ ቆላ. 4፡2-4 ከማመስገን ጋር በፀሎት እየነቃችሁ ለእርሱ ትጉ፤ … 1ተሰ. 5፡16-17 ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፣ ሳታቋርጡ ፀልዩ፣ በሁሉ አመስግኑ፣ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና፡፡ ሐ. ፀሎት መናዘዝ፣ መታረቅን እና ሌሎችን ይቅር ማለትን ያካትታል፡፡ መዝ. 32፡5 ኃጢአቴን ላንተ አስታወቀሁ፣ በደሌንም አልሸፈንሁም፣ ለእግዚአብሔር መተላለፌን እነግራለሁ አልሁ፣ አንተም የልቤን ኃጢአት ተውክልኝ፡፡ (መዝሙር 66፡18 ይመልከቱ) ምሳሌ 28፡13 ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምህረትን ያገኛል፡፡ ማቴ. 5፡23-24 እንግዲህ መባህን በመሰዊያላይ ብታቀርብ በዚያም ወንድምህ በአንተ ላይ አንዳች በአንተ ላይ እንዳለው ብታስብ በዚያ በመሰዊያው ፊትመባህን ትተህ ሂድ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ፡፡ ማር. 11፡25 ለፀሎትም በቆማችሁ ጊዜ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት፡፡ ሮሜ. 12፡18 ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ፡፡ 1ዮሐ. 1፡9-10 በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከአመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ፃድቅ ነው፡፡ መ. ፀሎት ልመናዎችን፣ ስለ ግል ፍላጎቶቻችን ጥያቄዎች ማቅረብንም ያካትታል፡፡ ማቴ. 6፡5-8 … አንተ ግን ስትፀልይ ወደ እልፍኝህ ግባ፤ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ፀልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል፡፡ አህዛብ በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትፀልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ፡፡ ስለዚህ አትምሰሉአቸው ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና፡፡ ማቴ. 6፡25-34 … ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፣ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል … ያዕ. 1፡5 ከእናንተ ማንም ጥበብ ቢጎድለው ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን ለእርሱም ይሰጠዋል፡፡ ሠ. ፀሎት ምንም እንኳን የማይቋረጥና የሁል ጊዜ ግንኙነት ቢሆንም ለእርሱ የሚሆን የተለየ ሰዓት ሊኖረው ይገባል፡፡ መዝ. 55፡17 በማታና በጠዋት በቀትርም እናገራለሁ፣ እጮኸማለሁ፣ ቃሌንም ይሰማኛል፡፡ መዝ. 119፡62 ስለ ፅድቅህ ፍርድ በእኩለ ሌሊት አመሰግንህ ዘንድ እነሳለሁ፡፡ መዝ. 119፡164 ስለ ፅድቅህ ፍርድ ሰባት ጊዜ በቀን አመሰግንሀለሁ፡፡ ዳን. 6፡10 ዳንኤልም ፅህፈቱ እንደ ተፃፈ ባወቀ ጊዜ ወደ ቤቱ ገባ፣ የእልፍኙም መስኮቶች ወደ ኢየሩሳሌም አንፃር ተከፍተው ነበር፣ ቀድሞም ያደርግ እንደነበር በየዕለቱ ሶስት ጊዜ በጉልበቱ ተንበርክኮ በአምላኩ ፊት ፀለየ፣ አመሰገነም፡፡ ሮሜ. 12፡12 በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤ 1ተሰ. 5፡17 ሳታቋርጡ ፀልዩ፤ … በ 1ተሰ. 5፤17 ላይ የተሰጠ አስተያየት፡ #የማያቋርጥ ፀሎት፣ በሚቻል ወቅት ሁሉ የሚደረግ ቀጣይነት ያለው ፀሎት ማለት እንጂ አንድም ጊዜ የማይቆም ማለት አይደለም፡፡ ጳውሎስ ይህንን ጉዳይ ያነሳው ያለማቋረጥ ሃሳብን ለእግዚአብሔር ማስገዛት ፈታኝ በሆነበት የዕለት ተዕለት ሕይወታችን፣ በተቻለ መጠን ያለማቋረጥ ከእግዚአብሔር ሕብረት ስር የመሆንን አስፈላጊነት ለመግለፅ ነው፡፡ ረ. ፀሎት ምልጃንና ስለሌሎች ሰዎች ፍላጎቶች መፀለይን ያካትታል፡፡ 2ቆሮ. 1፡8-11 በእስያ ስለ ደረሰብን መከራችን፣ ወንድሞች ሆይ፣ ታውቁ ዘንድ እንወዳለንና፤ ስለ ሕይወታችን እንኳ ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከዓቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶብን ነበር፤ አዎን፣ ሙታንን በሚያነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን፣ እኛ ራሳችን የሞትን ፍርድ በውስጣችን ሰምተን ነበር። እርሱም ይህን ከሚያህል ሞት አዳነን፣ ያድነንማል፤ እናንተም ደግሞ ስለ እኛ እየጸለያችሁ አብራችሁ ስትረዱን፣ በብዙ ሰዎች በኩል ስለ ተሰጠን ስለ ጸጋ ስጦታ ብዙዎች ስለ እኛ ያመሰግኑ ዘንድ፣ ወደ ፊት ደግሞ እንዲያድን በእርሱ ተስፋ አድርገናል። ኤፌ. 6፡18-20 በፀሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ፀልዩ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመፅናት ሁሉ ትጉ ደግሞ የወንጌልን ምስጢር በግልጥ እንዳስታውቅ አፌን በመክፈት ቃል ይሰጠኝ ዘንድ ስለእኔ ለምኑ ስለ ወንጌልም በሰንሰለት መልዕክተኛ የሆንሁ መናገር እንደሚገባኝ ስለእርሱ በግልጥ እናገር ዘንድ ለምኑ፡፡ ቆላ. 4፡12 ከእናንተ የሆነ የክርስቶሰ ባሪያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብችኃል፡፡ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁ ፍፁማን ሆናችሁ እንድትቆሙ ሁል ጊዜ ስለ እናንተ በፀሎቱ ይጋደላል፡፡  

ፀሎት ምንድን ነው? ፀሎት ምን ምን ያካትታል? Read More »

ዳግም ልደት ማለት ምን ማለት ነው?

ዳግም ልደት ከክርስትና ዋነኛ ትምህርቶች መካከል አንዱ ነው። የሰው ልጅ ሁለት ልደቶች አሉት። አንደኛው ከስጋ ፈቃድ በሩካቤ ከአባት እና ከእናት የሚያገኘው ስጋዊ ልደት ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ ኢየሱስን በማመን እና በመቀበል የሚያገኘው መንፈሳዊ ልደት ነው፣ ‘‘ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም’’ (ዮሐንስ ወንጌል 1፡12-13)። ያለዚህ ልደት ሰው የእግዚአብሔርን መንግስት ሊወርስ አይችልም። ሰው በስጋ ልደቱ የሰው ልጅ እንደሚባል፣ በመንፈስ ልደቱ ደግሞ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። ስጋ እና ደም የእግዚአብሔርን መንግስት ሊወርሱ አይችሉም፣ የእግዚአብሔር ልጆች ግን የእግዚአብሔርን መንግስት ሊወርሱ ይችላሉ። የመጀመሪያውን ልደት ብቻ ያገኙ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣቸው የለምና ስጋ እና ደም ብቻ ተብለው ይጠራሉ። እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን መንግስት ሊወርሱ አይችሉም፣ ‘‘ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፥ የሚበሰብሰውም የማይበሰብሰውን አይወርስም’’ (1ቆሮንቶስ 15፥50)። የመጀመሪያውን ልደት ብቻ ያገኙ ፍጥረታዊ ሰዎች ይባላሉ። አካላቸው ደግሞ ፍጥረታዊ አካል ይባላል (1ቆሮንቶስ15፡46)። እነዚህ ሰዎች መንፈሳዊ የሆነውን የእግዚአብሔርን ነገር ሊያስተውሉ አይችሉም ‘‘ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም’’ (1ቆሮንቶስ 2፡14)። የመጀመሪያውን ልደት በመወለድ እንዳገኘነው፣ ሁለተኛውንም ልደት በመወለድ እናገኘዋለን። የመጀመሪያውን ስጋዊ ልደት ስጋዊ ከሆኑ ቤተሰቦቻችን እናዳገኘነው ሁለተኛውን ልደት ደግሞ መንፈሳዊ ከሆነው አባታችን በመወለድ የምናገኘው ይሆናል። የመጀመሪያውን ልደት መልካም ሰው በመሆን፣ ምጽዋት በመስጠት፣ በመፀለይ እና በመጾም እናዳላገኘነው፣ ሁለተኛውንም ልደት በእነዚህ መንገዶች አናገኘውም። የቤተሰቦቻችን ልጅ ለመሆን የከፈልነው ክፍያም ሆነ አስተዋጽዎ እንደሌለ ሁሉ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆንም የምናዋጣው መዋጮ የለም። የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን ከእኛ የሚጠበቀው አንድ ነገር ብቻ ነው። ይኸውም፣ በኢየሱስ ማመን እና እርሱን መቀበል፣ ‘‘ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም’’ (ዮሐንስ ወንጌል 1፡12-13)። ‘‘በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና’’ (ገላቲያ 3፡26)። የሰው ልጅ ሁለተኛውን ልደት ካላገኘ ወይም ዳግም ካልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግስት ሊወርስ አይችልም፣ ‘‘ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው’’ (የዮሐንስ ወንጌል 3፡5-6)። ምንም ይስራ ምን፣ ከስጋ የተወለደ ስጋ ነው። ስጋ እና ደም ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግስት ሊወርሱ አይችሉም። የተፈጥሯዊ ሰው መልካምነት እስከ አለም ዳርቻ ቢሰማም እንኳ፣ ከስጋ ከተወለደ ስጋ ብቻ ነው። ድርጊቱ ምንም ያህል የተከበረ፣ አንቱ የተባለ እና የተመሰከረለት ቢሆን፣ ተፈጥሮውን አይቀይርለትም። ሃይማኖተኛ ቢሆን፣ አዘውትሮ ረዥም ፀሎት ቢያደርግ (ማቴዎስ 23፡14) በሳምንት ሁለት ጊዜ ቢጾም ሳያጓድል ለእግዚአብሔር አስራት ቢያወጣ (ሉቃስ 18፡12)፣ ቀማኛ፣ ዓመፀኛ አመንዝራ ባይሆን (ሉቃስ 18፡11)፣ በሌላ አባባል በሰፈሩ የተመሰከረለት የሞራል ሰው ቢሆን፣ ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር ያው ስጋዊ፣ ያው ፍጥረታዊ ብቻ ነው። በእግዚአብሔር መንግስትም እድል ፈንታ የለውም። ዳግም ልደት የእግዚአብሔር ምህረት ውጤት እንጂ የእኛ መልካም ስራ ውጤት አይደለም። ‘‘እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም’’ (ቲቶ 3፡5)። በመልካም ስራ ተፈጥሯችን አይቀየርም። መልካም ስራችን በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት የሚኖረው ከአዲሱ ተፈጥሯችን ሲመነጭ ብቻ ነው። ዳግም ልደት ሰው በእግዚአብሔር መንፈስ ዳግም ሲፈጠር ወይም ሲለወጥ የሚከናወን መንፈሳዊ ድርጊት ሲሆን ይህም ድርጊት ሰው ከእግዚአብሔር መለኮታዊ ባሕሪይ ተካፋይ እንዲሆን ያስችለዋል፣ ‘‘ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን’’ (2ጴጥሮስ 1፡4)። ኢየሱስን በማመን እና በመቀበል የተገኘው ልጅነት (ዮሐንስ 1፡12)፣ እግዚአብሔርን አባት ብለን እንድንጠራው እና የእግዚአብሔር ወራሾች እንድንሆን መብትን አስገኝቶልናል፣ ‘‘በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና። አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን’’ (ሮሜ 8፡14-17)። በመጀመሪያው ልደት ከቤተሰቦቻችን (ከፊተኛው አዳም)  የወረስነው ተፈጠሮ፣ አዳማዊ ተፈጥሮ ወይም አሮጌው ሰው ይባላል። በዳግም ልደት ኢየሱስን በማመን ከእግዚአብሔር ያገኘነው አዲሱ ተፈጥሮ ደግሞ አዲሱ ሰው ይባላል፣ ‘‘እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ፥ አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር ገፋችሁታልና፥ የፈጠረውንም ምሳሌ እንዲመስል እውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል’’ (ቆላሲያስ 3፡9-10)። ‘‘ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል’’ (2ቆሮንቶስ 5፡17)። ኢየሱስን አምኖ የተቀበለ ሰው፣ በዳግም ልደት ሌላ አዲስ ተፈጥሮ ስለሚኖረው የሁለት ተፈጥሮዎች ባለቤት ይሆናል ማለት ነው። በዳግም ልደት አዲስ ተፈጥሮን እናገኛለን እንጂ የቀድሞውን አሮጌ ተፈጥሮ አናጣም። አሮጌው ተፈጥሮ እስከሞታችን ከእኛ ጋር ይኖራል። እነዚህ ሁለት ተፈጥሮዎች በባህሪይ ተቃራኒ በመሆናቸው እርስ በእርሳቸው ይቀዋወማሉ፣ ‘‘5፥17 ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ …’’ (ገላቲያ 5፡17)። ዳግም የተወለደ ሰው በፊተኛው እና እግዚአብሔርን በማያከብረው ስጋዊ ወይም አሮጌ ተፈጥሮ ቁጥጥር ስር እንዳይሆን በእግዚአብሔር ቃል እውቀት እለት እለት መታደስ ይኖርበታል። የአዲሱ ተፈጥሮ ምግብ የእግዚአብሔር ቃል ነው (ማቴዎስ 4፡4)። የአሮጌውን ተፈጥሮ ፍላጎት እንቢ እያልን የአዲሱን ተፈጥሮ ፈቃድ እየተቀበልን የምንጓዘው ጉዞ የቅድስና ጉዞ ይባላል፣ ‘‘ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ። ሰው በአሮጌው ተፈጥሮ እግዚአብሔርን ደስ ማሰኝት ስለማይችል ዳግም ልደት ያስፈልገዋል፣ ‘‘እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ (መዝሙር 51፡5)። ‘‘የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው ማንስ ያውቀዋል? (ኤርሚያስ 17፡9።) ‘‘ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤ በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም’’ (ሮሜ 8፡16-17)። ‘‘በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን’’ (ኤፌሶን 2፡3)። ዳግመኛ ልደት ያገኘ ሰው ምልክቶች ምንድን ናቸው? ዳግም የተወለደ ሰው ከሃጢአት ልምምድ ነፃ የወጣ ነው (ሮሜ 6፡14-23)። ዳግም የተወለደ ሰው የእግዚአብሔርን መንፈስ ምሪት ለመቀበል እና ለመታዘዝ መሻት ይኖረዋል (ሮሜ 8፡13-14)። ዳግም የተወለደ ሰው የጽድቅ ሕይወት ይኖረዋል (1ዮሐንስ 2፡29)። ዳግም የተወለደ ሰው ሌሎችን ይወዳል (1ዮሐንስ 4፡7)። ዳግም የተወለደ ሰው ከሃጢአት ሕይወት ይርቃል (1ዮሐንስ 3፡9፤ 5፡18)። ዳግም የተወለደ ሰው አለምን መውደድ ይተዋል (1ዮሐንስ 2፡15-16)። ኢየሱስን በማመን እና በመቀበል ይህን ዳግም ልደት ለማግኘት የሚሹ ከሆነ ይህን ሊንክ በመጫን፣ ኢየሱሰን መቀበል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ወይስ መናፍቃዊ የሚለውን ትምህርት እንዲያነቡ በትህትና እንጠይቆታለን። የመዳን ቀን አሁን ነው (2ቆሮንቶስ 6፡2)፣ ለነገ ቀጠሮ አይስጡ። ነገ የእርሶ አይደለምና። መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የሕይወትዎ ጌታ በማድረግ ቀሪው ዘመንዎን ለመኖር ወስነው ከሆነ፣ ይህንን ሊንክ በመጫን ስምዎንና የኢ-ሜይል አድናሻዎን ይላኩልንና፣ ለመንፈሳዊ ሕይወት እድገትዎ የሚቻለንን ሁሉ እገዛ እናደርግሎታለን።

ዳግም ልደት ማለት ምን ማለት ነው? Read More »

የግል ፀሎት ምንድን ነው?

አንተ ግን ስትጸልይ፣ ወደ እልፍኝህ ግባ፣ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፣ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሀል፡፡ ማቴዎስ 6፡6 ኢየሱስ ‹‹በስውር ላለው አባታችሁ ፀልዩ›› እንጂ ‹‹በስውር ስፍራ ወዳለው አባታችሁ ህልምን አልሙ፡፡›› አላለም፡፡ ፀሎት ፈቃድን ማስገዛት ይጠይቃል፡፡ ወደ እልፍኛችን ከገባንና በራችንን ከዘጋን በኋላ ልናደርግ የሚቸግረን ትልቁ ነገር ቢኖር መፀለይ ነው፡፡ አእምሮአችንን ለፀሎታችን ልንጠቀምበት በምንችለው ሁኔታ ማዘጋጀት አስቸጋሪው ሥራችን ይሆናል፡፡ የመጀመሪያ ውጊያችን የሚሆነው ሀሳባችንን ማሰባሰብና ለፀሎት ራሳችንን መግዛት ነው፡፡ በግል የፀሎት ጊዜ ያለው ታላቁ ጦርነት ሀሳባችንን ማሰባሰብና ለፀሎት ያልተዘጋጀውን አዕምሮአችንን ለዚሁ መንፈሳዊ ስራ እንዲነሳሳ ማድረግ ነው፡፡ በፈቃዳችን ላይ ለተመሠረተ እና ለታሰበበት ፀሎት አዕምሮአችንን በዲሲፕሊን መግዛት መማር ይኖርብናል፡፡ ለፀሎት የተለየ ስፍራ ሊኖረን ይገባል፡፡ ያም ሆኖ ግን ወደዚህ ስፍራችን ስንገባ ሀሳባችን መባከን ይጀምራል፣ ‹‹ይህ መሰራት አለበት››፤ ‹‹ያኛውን ደግሞ ዛሬ መጨረስ ይኖርብኛል፡፡›› የሚሉ ሀሳቦች በአዕምሮአችን መመላለስ ይጀምራሉ፡፡ ኢየሱስ ‹‹በራችሁን ዝጉ፡፡›› ነው ያለው፡፡ በፀሎት ወቅት የተረጋጋ የአዕምሮ ሁኔታን ለመፍጠር፣ የአዕምሮአችንን ደጆች ለሚያንኳኩ ስሜቶቻችን ሆን ብለን ደጃችንን በመዝጋት፣ እርሱን ብቻ ማሰብ ይኖርብናል፡፡ እግዚአብሔር በስውር አለ፡፡ ከ ‹‹ስውር ስፍራውም›› ይመለከተናል፡፡ እርሱ የሚመለከተን፣ ሰዎች እኛን ወይም ራሳችን ራሳችንን እንደ ምንመለከተው አይደለም፡፡ እግዚአብሔር እኛን በሚያየን በዚህ ‹‹ስውር ስፍራ›› መኖር መለማመድ ስንጀምር እግዚአብሔርን መጠራጠር አይሆንልንም፡፡ ከማንም እና ከምንም ነገር በላይ ስለ እርሱ እርግጠኞች እንሆናለን፡፡ ወደዚህ ‹‹ስውር ስፍራ›› ስትገባ በእለት ተዕለት ሕይወትህ እግዚአብሔር በእርግጥ ትክክል እንደሆነ ታረጋግጣለህ፡፡ በሁሉም ጉዳዮች ላይ ከእግዚአብሔር ጋር የማውጋት ልማድ ይኑርህ፡፡ የማለዳው ጎህ ሲቀድ የሕይወትህን ደጆች ወለል አድርገህ ከፍተህ እግዚአብሔርን ማስቀደም መማር ካልጀመርክ፣ የቀን ውሎህ ሁሉ በተሳሳተ መስመር ላይ መሆኑን እንዳትዘነጋ፡፡ ነገር ግን የሕይወትህን ደጆች ከፍተህ ‹‹በስውር ላለው አባትህ ፀሎት ካደረስክ››፣ በሕይወትህ የሚያለፉ ማህበራዊ ነገሮችህ ሁሉ የእግዚአብሔር የይሁንታ ማህተም ያረፈባቸው ይሆናሉ፡፡ በግለህ ወደ ፀሎት በገባህ ጊዜ የሚደርስብህን የትኩረት መበታተን ችግር ለመቀነስ፣ ወደ አይምሮህ እየመጡ የሚያስቸግሩህ እና ኋላ ላይ ልትሰራቸው የሚገቡህን ነገሮች የምታሰፍርበት ማስታወሻ ደብተር አዘጋጅ፡፡  

የግል ፀሎት ምንድን ነው? Read More »