የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ስፍራ

በአንድ ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ውስጥ ቆሞ መንገዱ ወደ የት እንደሚወስድ ለመናገር መሞከር እጅግ ከባድ ነው። ምክንያቱም ወደፊት ለማየት የምንችለው ጥቂት እርምጃ ዎች ብቻ ስለሆነ ነው። ነገር ግን ከተራራ ጫፍ ላይ ቆመን የአንድን መንገድ አቅጣጫ ብናጠና ያ መንገድ ወደ የት እንደሚወለደን መመልከት እጅግ ቀላል ነው። ስለ መንፈስ ቅዱስ በምናደርገው ጥናት ወደ የት እንደምንሄድ ለመረዳት ትምህርታችን ወደ የት እንደሚወስደን በአጭሩ መረዳት ያስፈልገናል። ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥናታችንን የምንጀምረው የምንመለከታቸውን ዋና ዋና እውነቶች በሰፊው በመቃኘት ይሆናል። ይህም የጥናት መጽሐፋችን እንዴት እንደተዋቀረ ለመመልከት ያግዘናል።  «መንፈስ ቅዱስ ማን ነው?» የሚል ጥያቄ እናነሣለን። እካላዊ ህልውና የሌለው ኃይል ብቻ ነውን? ወይስ ሕያው የሆነ አካል ያለው ህልውና የሥላሴ ሦስተኛው አካል ነው? ቀጥላን መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን፥ በአራቱ ወንጌላት በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ የታየውና በሐዋርያት ሥራ የሚያስተምረውን በአጭሩ እንቃኛለን። ሰማያቋርጥ ተከታታይነት እየተገለጠ እንደሚመጣ ታሪክ ከመጀመሪያው ጀምሮ መጽሐፍ ቅዱስን እየቀጠልን ስናነብ ስለ መንፈስ ቅዱስ የበለጠ እየተማርን እንሄዳለን። ከዚያ በመቀጠል የመንፈስ ቅዱስን አገልግሎት ከፋፍለን እንመለከተዋለን። ክርስቲያኖች ባልሆኑ ሰዎች መካከል እንኳ ስላለው ተግባር እናያለን። እያንዳንዱን የዳነውን ሰው ደግሞ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወዳለ ግንኙነት እንዴት እንደሚመራው እንመለከታለን። ቀጥለን አንድን ክርስቲያን ክርስቶስን ወደ መምሰል እንዲያድግ በሕይወቱ የሚሠራበትን፥ ክርስቶስ እያንዳንዳችን እንድንሠራ የሚፈልጋቸውን ነገሮች፥ በክርስቲያን ውስጥና በክርስቲያን አማካኝነትየሚሠራበትን በርካታ የተለያዩ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች እንመለከታለን። ከዚያ በመቀጠል የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በተለይ ደግሞ በቤተ ክርስቱያን ውስጥ የተለያዩ ውዝግቦች የሚያስነሡትን ማለትም ሰልሳን የመናገር፥ የፈውስና የትንቢት ስጦታዎችን እንመለከታለን። ጥናታችንን የምናጠቃልለው በየዕለቱ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንዴት መመላለስ እንደምንችል በመመልከት ይሆናል።  ጥያቄ፡– ያለፈውን አንቀጽ አንብብ። በዚህ መጽሐፍ በምንመለከታቸው እያንዳንዱ ዋና ርእሶች እግዚአብሔር እንዲያስተምርህ ጸልይ።  ዛሬ መንፈስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር ሥራዎች በሙሉ እንዴት አስፈላጊና ጠቃሚ እንደሆነ እንመለከታለን። ዛሬ በዓለም ላይ መንፈስ ቅዱስ ስላለው ሁለት ዋና ተግባራት በአጭሩ እንጠቅሳለን።  ጥያቄ፡- ስለ መንፈስ ቅዱስ ላታስብ ወደ አእምሮህ የሚመጣው አሳብ ምንድን ነው? መንፈስ ቅዱስ ምን ይመስላል? ምን ለመሥራት ይሞክራል?  እንደ ክርስቲያኖች አብዛኛው የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀታችን ስለ እግዚአብሔር እብና ደኅንነታችንን ስለዋጀው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ስለ መንፈስ ቅዱስ ማንነትና ምን እንደሚሠራ ለማሰብ የምንወለደው ጊዜ በጣም አነስተኛ ነው። ይህም ሆኖ መጽሐፍ ቅዱስን ስጥንቃቄ ብናጠና በእያንዳንዱ የእዲስ ኪዳን ገጽ ላይ ስለ መንፈስ ቅዱስ እናነባለን። የመጽሐፍ ቅዱስ ተቀዳሚ አትኩሮት ባይሆንም እንኳ ለላ መንፈስ ቅዱስ የተጠቀሱ እውነቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ዋና ትምህርቶች ሁሉ ጋር እጅግ ክመጣመራቸው የተነሣ መንፈስ ቅዱስ እግዚእብሔር በሚሠራቸው ሥራዎች ሁሉ ውስጥ ገቢራዊ ተሳትፎ አለው።  ለምሳሌ፡- በአዲስ አበባ የምትኖር ሆነህ አንድ ቆንጆ ባለ 10 ፎቅ ሕንነ ተመላክትህ እንበል። – ይህን ሕንፃ ማን ሠራው? ከየት ተገኘ? እንዴት ህልውና ሊያገኝ ቻለ? ሕንፃውን እንደገነቡ የምናስባቸው በርካታ የተለያዩ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ሕንፃውን በአእምሮው በመቅረጽ ስሕንፃው ሥራ መጨረሻ መካተት አለባቸው ብሎ ያሰባቸውን ነገሮች በሙሉ ጨምሮ ሕንፃውን በወረቀት ላይ ያሰፈረው የንድፍ መሐንዲሱ (አርክቴክቱ) ይኖራል። ባንድፍ መሐንዲሱ የተሠራው ነገር በሙሉ በታሰበው መንገድ በሥራ ላይ መዋሉን የሚያረጋግጥ የሕንፃ ሥራ ተቋራጭ ይኖራል። በመጨረሻ ሥራውን በመሥራት ሕንፃው ተግባራዊ እንዲሆን የሚያደርጉት ግንበኞች፥ አናፂዎች የኤሌክትሪክ ሠራተኞች ወዘተ… ይኖራሉ።  ይህ መግለጫ ሥላሴዎች እግዚአብሔር አብ፥ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እንዴት እብረው እንደሚሠሩ ለማሳየት ጥሩ ምሳሌ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን በቅርበት ስንመረምር ማናቸውንም ዋና የሚባሉ ተግባራት ሥላሴ አብረው እንደሚሠሩት ያሳየናል። እግዚአብሔር አብ እንደ ንድፍ አውጪው መሐንዲስ ሆኖ ምን እንደሚፈጸም ይወስናል። እግዚአብሔር ወልድ የእግዚአብሔር አብ ዕቅድ ይፈጸም ዘንድ የበላይ ተቆጣጣሪ ሆኖ እንደሚመለከተው ተቋራጭ ነው። መንፈስ ቅዱስን ደግሞ የእግዚአብሔር አብና የእግዚአብሔር ወልድን ዓላማና ዕቅድ ወደ እውነታ የሚተረጉም የሕንፃው ሠራተኛ ሆኖ እንመለከተዋለን። መንፈስ ቅዱስ ለሕንፃው ሥራ እንደ ተቆጣጣሪ በመሆን በሠራተኞች ማለትም በእግዚአብሔር ልጆች አማካኝነት የሚያከናውናቸው ሌሎች የእግዚአብሔር ሥራዎችም አሉ።  ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት። ዘፍ 1፡1-2 እና ቆላ. 1፡16-17፤ ሉቃስ 1፡35 እና ዮሐ 3፡16፤ ዮሐ 6፡35-40 እና ቲቶ 3፡3-7። እነዚህ ጥቅሶች ሥላሴዎች አንድ ነገር በመፈጸም እብረው እንዴት እንደሚሠሩ ምን ያሳዩናል?  የሥላሴ አካላት በሙሉ ያልተሳተፉበት የእግዚአብሔር ሥራ ምናልባት አይኖር ይሆናል። ክሥላሴ አካላት አንዳቸው ለአንድ ሥራ ተቀዳሚ ኃላፊነት የሚወስዱ ቢሆንም እንኳ (ለምሳሌ ለኃጢአታችን የሞተው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው) የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን ሁሉ በአንድነት ስናጣምራቸው የቀሩትም የሥላሴ አካላት እንደተሳተፉበት እናየላን።  ሥላሴዎች የእግዚአብሔርን ዕቅዶች ለመፈጸም እንዴት እንደ ሠሩ ሦስት ምሳሌዎችን እንመልከት።  1. የመፍጠር ሥራ፡- መጽሐፍ ቅዱስን በምናጠናበት ጊዜ እንደምንመለከተው እያንዳንዱ የሥላሴ አካል በመፍጠር ሥራ ተካፍሏል። በዘፍ 1፡1 እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን እንዲፈጠረ ተገልጾልናል። በቆላ. 1፡16-17 ፍጥረታት ሁሉ የተፈጠሩት የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ እንመለከታለን። እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን በፈጠረበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም በመዘጋጀት በውኃ ላይ እንደ ርግብ ሰፍፎ እንደነበር ተነግሮናል (ዘፍ 1፡2)።  2. የክርስቶስ መወለድ፡ ዮሐ 3፡16 እግዚአብሔር አብ ልጁን ኢየሱስን ወደዚህች ምድር እንደላከው ይነግረናል። ነገር ግን ዘላለማዊ ልጁ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስን በተአምራዊ መንገድ የሰው ሥጋ ይለብስ ዘንድ ድንግል ማርያም እንድትፀንስ ያደረገው ደግሞ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ እናነባለን (ሉቃስ 1፡35)።  3. የአማኝ ድነት (ድነት (ደኅንነት))፡– ድነት (ድነት (ደኅንነት))ን የሰጠን የትኛው የሥላሴ አካል ነው? ሦስቱም ናቸው። እግዚአብሔር አብ፥ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ተካፋይ ነበሩ። እግዚአብሔር አብ፤ የሚያምኑትን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንደሰጠ ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ አንዳቸውም እንዳይጠፉ እንደሚጠብቃቸው (ዮሐ 6፡35-40) ተጽፎአል። ነገር ግን ከኃጢአት ያጠባንና ያነጻን ደግሞ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ተነግሮናል (ቲቶ 3፡3-7)።  እያንዳንዱ የሕይወታችን ክፍል የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ማኅተም አለው። የፈጠረን፥ ያበጃጀንና እከላዊ ህልውናችንን የዕጣን ቤተሰባችንን፥ እገራችንን፥ ዜግነታችንን ወዘተ… የመረጠ እርሱ ነው (መዝ (139) በእድገታችን ወቅት እየተከባከበን እርሱ የሚፈልገውን ዓይነት ሰው እንድንሆን የሕይወታችንን ልዩ ልዩ ሁኔታዎች ያደራጀልን መንፈስ ቅዱስ ነው (ዮሐ 5፡16)። በኃጢአት ሞቶ ወደ ነበረው ልባችን መጥቶ በመሥራት ክርስቶስ ለደኅንነታችን ያደረገውን ጥሪ እንድንሰማ ያደረገ በዚህም በኢየሱስ እንድናምን ልባችንን ያነሣሣና የእግዚአብሔር ልጆች እንሆን ዘንድ ያስቻለንም መንፈስ ቅዱስ ነው (ዮሐ 5፡26፤ 16፡6~1)። ኃጢአትን እንድናሸንፍ በየዕለቱ የሚያስፈልገንን ኃይል የሚሰጠን፥ (ሮሜ 8፡13) ኢየሱስ ክርስቶስን እንድናገለግል ስጦታዎችን የሚሰጠን፥ ክርስቶስን ወደ መምሰል እንድንለወጥ የሚረዳንና እግዚአብሔር ወደ ቤቱ ወደ መንግሥተ ሰማየት እስከሚወስደን ድረስ የሚጠብቀን እራሱ መንፈስ ቅዱስ ነው። አሁን የያዝነውን እኛነታችንን ያበጀው ከሥላሴ አካላት አንዱ የሆነው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው። አመስኑት! እወቁት!  ጥያቄ፡– ከእግዚአብሔር የተቀበልካቸውን በረከቶችህን ዘርዝር። ይህን ፍቅር ያሳዩህንና በረከቶችህን የሰጡህን እያንዳንዱን የሥላሴ አካላት ለማመስገን ጊዜ ውሰድ።  ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ስፍራ Read More »

መንፈስ ቅዱስን ማወቅ

ጥያቄ፡- ሀ) ዳን 11፡32 አንብብ። አምላካቸውን የሚያውቁ ሕዝቦች ምን ሲያደርጉ ነው ይህ ጥቅስ የሚናገረው? ለ) ኤፌ. 1፡17-20 አንብብ። ) ጳውሎስ ለቅዱሳን የጸለየው ጸሎት ምን ነበር? 2) እነዚህን ጥቅሶች በሕይወታችን ለመፈጸም የምንችለው እንዴት ነው? ሐ) እግዚአብሔርን ሳናየው ወዳጆቹ መሆን የምንችለው እንዴት ነው?  መንፈስ ቅዱስን ካላወቅነውና በኃይሉ ካልተመላለስን ስለ መንፈስ ቅዱስ ማወቅ ምንም አይጠቅምም። የሕይወታችን ዓላማ እግዚአብሔርን የቅርብ ጓደኛ ለማድረግ የምንችልበት መንገድ ማወቅ ሊሆን ይገባል። የሙስሊም እምነት ተከታዮችም ሆኑ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እግዚአብሔር ለመታወቅ በማይችል ሁኔታ በሩቅ የሚገኝ አድርገው ይቆጥሩታል። ብዙ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች እንደ መላእክትና ማርያም ያሉ አማላጆችን በእግዚአብሔር ፊት ይወክሉአቸው ዘንድ የሚጠቀሙበት አንዱ ምክንያት ላዚህ ነው። እግዚአብሔር ብቸኛ ታላቅና ኃያል ቢሆንም ቅሉ፥ ቅርብ ወዳጆቹ እንድንሆንና ከእርሱ ጋር በኅብረት እንድንኖር የሚፈልግ ስለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ አስደናቂ እውነትን ያስተምራል።  ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋር የቅርብ ወዳጅነት እንዴት መፍጠር እንችላለን? በምድር ላይ እንዳሉ ማናቸውም መልካም ግንኙነቶች ሊሆኑ የሚገባቸው ቢያንስ አራት ነገሮች አሉ። በመጀመሪያ እግዚአብሔርን ለማወቅ ፍላጐት እንዲኖር ያስፈልጋል። ብዙዎቻችን አንድ ወይም ሁለት የቅርብ ጓደኞች አሉን። እነኚህ ጓደኞቻችን ወደ እኛ የቀረቡት ወዳጅ ልናደርጋቸው መልካም ፈቃድና ፍላጐት ስለነበረን እነርሱም ይህ ፍላጐት ስለነበራቸው ነው። የቅርብ ጓደኝነት ብዙ ድካምን ስለሚጠይቅ፥ የቅርብ ጓደኛ የመሆን ፍላጎት ሊኖር ይገባል። እንደ አብርሃም፥ ሙሴና ዳዊት የእግዚአብሔር የቅርብ ወዳጆች ልንሆን የምንችለው ከልባችን ስንፈልግና እንደፍላጎታችን ስንኖር ብቻ ነው። እግዚአብሔር ወዳጃችን ሊሆን ይፈልጋል (ዮሐ 15፡14-15)። እኛም በምድር ላይ ካሉ ነገሮች ሁሉ በላይ የእግዚአብሔር ወዳጆች ለመሆን በመፈለግ ምላሽ መስጠት አለብን።  ሁለተኛው ጉዳይ ጊዜ የሚጠይቅ መሆኑ ነው። ማንም በአንድ ጊዜ ወዳጃ ችን አይሆንም። መልካም የቅርብ ጓደኝነት ለመመሥረት ብዙ ጊዜ ዓመታት ይጠይቃል። ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ወዳጅነት ለመመሥረትም እንደዚሁ ጊዜ ይፈልጋል።  ሦስተኛ በእግዚአብሔር ፊት ግልጽ መሆን አለብን። ልባችንና እእምሮአችንን መክፈት አለብን። የምናስበውን፥ የጐዳናንን፥ የምንመኘውን፥ የምንታገለውን ነገር ሁሉ ልናካፍለው ይገባል። ከመዝሙረ ዳዊት እንደምንረዳው ዳዊት የእግዚአብሔር የቅርብ ወዳጅ የሆነበት አንዱ ምክንያት በእግዚአብሔር ላይ መቆጣቱን እንኳ ሳይቀር ውስጣዊ ነገሩን በሙሉ ሳይደብቅ ይገልጽላት ስለነበር ነው። ወዳጆቹ ለመሆን ፍጹም ልናምነውና በፊቱ ግልጽ ልንሆን ይገባል። ከሕይወታችን ከፊሉን ለመደበቅ መሞክር ምንም አይጠቅምም። እግዚአብሔር ሁሉን ስለሚያውቅ ከእርሱ የምንደብቀው የለንም። አስተሳሰባችንና ስሜታችንን ከእግዚአብሔር ለመደበቅ ስንሞክር ከእርሱ እንዲኖረን የምናስበው የቅርብ ወዳጅነት ሳያድግ ይቀራል።   በአራተኛ ደረጃ ማንነቱን ማወቅ ይገባናል። የአንድን ሰው ማንነት ማወቅ፤ ታሪኩን፥ የሚወደውንና የሚጠላውን ባሕርይውን ማወቅን ይጠይቃል። ስለ ሰውየው ባወቅን መጠን፥ እርሱም ስለ እኛ ባወቀ መጠን አንዳችን ለሌላችን የበለጠ እየተመቸን እንሄዳለን። ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ግንኙነትም ጉዳዩ ተመሳሳይ ነው። ስለ እግዚአብሔር ባወቅን መጠን የበለጠ ወዳጁ እንሆናለን። ቀንኙነታችንም ያድጋል። ስለ እግዚአብሔር ለመማር ጊዜ ካልወሰድን፥ ምን እንደሚመስል፥ የሚወደውንና የሚጠላውን የሚያስደስተውንና የሚያሳዝነውን ካልተረዳን የእግዚአብሔር የቅርብ ወዳጅ መሆን አንችልም። ነገር ግን እግዚአብሔርን ከፈለግንና እርሱን ማወቅ የምንሻ ከሆነ፥ እግዚአብሔር እራሱን ለእኛ ይገልጥልናልግንኙነታችንም በእያንዳንዱ ዓመት እየጠለቀና እየጣፈጠ ይሄዳል።  ጥያቄ፡– እራስህን መርምር። ሀ) እግዚእብሔርን ምን ያህል በሚገባ ታውቀዋለህ? ለ) እንደ ቅርብ ወዳጅህ እርሱን ማወቅ ለአንተ ምን ያህል አስፈላጊህ ነው? ሐ) በእግዚአብሔር ፊት ምን ያህል ግልጽ ነህ? መ) የበለጠ ታውቀው ዘንድ ምን እያደረግህ ነው?  እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በልባችን ውስጥ ይኖራል። እኛ የእርሱ ቤተ መቅደስ ነን (1ኛ ቆሮ. 6፡19-20)። እንዲሁም የትውውቅ ብቻ ሊሆን ይችላል ወይም የቅርብ ወዳጃችን ሊሆን ይችላል። ምርጫው የራሳችን ነው። ወዳጆቹ የመሆን ፍላጐት አለን? ይህ ፍላጐት ታዋቂ፥ ሃብታም ወይም የተማረ ለመሆን ካለን ፍላጎት የላቀ መሆን አለበት። ከባድ ጥረት የሚጠይቅ ነው። ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ግንኙነታችንን እያዳበርን ስንሄድ እርሱ አጽናኛችን፥ መካሪያችን፥ አበረታቻችንና እጋዣችን ይሆናል። በእርሱ በኩል ከእግዚአብሔር አብና ከእግዚአብሔር ወልድ ጋር እጅግ ያማረ ኅብረት ውስጥ እንድንገባ የሚያስችለንን ኃይል ይሰጠናል። በእርግጥ በምድር ላይ ከዚህ የላቀ አስፈላጊ ነገር የለም።  እግዚአብሔር ከእኛ የራቀ መስሎ የሚሰማን ከሆነ በልባችን ያለውን መንፈስ ቅዱስን ካለመስማታችን የተነሣ ነው። ተስፋ ቆርጠን ከሆነ መንፈስ ቅዱስ እንዲያጸናንና እንዲመራን አልፈቀድንለትም ማለት ነው፡፡ በኃጢአት ክመሸነፍ ይልቅ ለክርስቶስ በድል መኖር ሊመጣ የሚችለው መንፈስ ቅዱስን በማወቅና በሕይወታችን ውስጥ የሚሠራውን ኃይሉን ስንለማመድ ብቻ ነው። ዳሩ ግን መንፈስ ቅዱስን ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው? እርሱ እንደ ነፋስ ስለሆነ መቼ እንደሚመጣና ወዴት እንደሚሄድ አናውቅም (ዮሐ 3፡8)። በዓይናችን ልናየውም አንችልም። ከጓደኞቻችን ጋር እንደምናወራው በቃላት ከእርሱ ጋር ልንነጋገር እንችልም። እግዚአብሔር በጸጋው መንፈስ ቅዱስ ራሱ በጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መንፈስ ቅዱስን ገልጦልናል። እግዚአብሔርን ማወቅ ከፈለጋችሁ፥ እና መንፈስ ቅዱስንም ማወቅ ከፈለጋችሁ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በተቀዳሚ እራሱን በቃሉ ይገልጥላችኋል። ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ በመውሰድ በቃሉ እንዲገልጥልን መጠየቅ የሚያስፈልገው ለዚህ ነው። መንፈስ ቅዱስን በእርግጠኛነት ለማወቅ ከዚህ ሌላ መንገድ ፈጽሞ የለም።  በዚህ የጥናት መምሪያ መጽሐፍ የእኔው ግብ ስለ መንፈስ ቅዱስ የጠለቀ ተጨማሪ የእእምሮ እውቀት እንዲኖራችሁ አይደለም። መንፈስ ቅዱስን እራሱን እንድታውቁት እፈልጋለሁ። መንፈስ ቅዱስን ባለማወቃቸው ምክንያት ደካማ፥ ደረቅና ውጤታማ ያልሆነ ሕይወት ያላቸው በርካታ ክርስቲያኖች አሉ። ስለ መንፈስ ቅዱስ በጥልቀት እናጥና፥ ከሁሉም በላይ ደግሞ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እራሱን እንዲገልጥልን ቃሉን ስናጠና የበለጠ እንድናውቀው ይረዳን (ያግዘን) ዘንድ እንጠይቀው።  ጥያቄ፡- የጸሎት ጊዜ በመውሰድ መንፈስ ቅዱስ በዚህ ጥናት ውስጥ እራሱን እንዲገልጥልህና የቅርብ ጓደኛው እንዲያደርግህ ጸልይ። ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

መንፈስ ቅዱስን ማወቅ Read More »

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የምንረዳበት ምንጭ

ላቱለፋዩ ጓደኛው ግርማ አዲስ የቪዲዮ ክር ሰጠው። ቪዲዮው የሚያሳየው ታላላቅ ተአምራትን እንደሚያደርግ ስለሚናገር አንድ ታዋቂ ሰባኪ ነበር። ቪዲዮው ከእነዚህ ተአምራት አብዛኛዎቹን ያሳያል። በትዕይንቱ መጨረሻ ላይ ሰባኪው እንዲህ ሲል ይደመጣል። «ተአምራትን ታደርጉ ዘንድ ይህ ኃይል እንዲኖራችሁ ብዙ ገንዘብ ላኩልኝ። መሐረቤን እልክላችሃለሁ። መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ ይመጣና እኔ አሁን የምለማመደውንም ኃይል ይሰጣችኋል።» ተስፋዩ በጣም ተደሰተ። ስለዚህ ጥሪቶቹን ለሰውዬው ላከ። ከብዙ ወራት በኋላ መሐረቡ ደረሰው። ተስፋዬ የተሰጡትን ትእዛዛት በጥንቃቄ በመከተል መንፈስ ቅዱስን በአዲስ መንገድ እንዳገኘ አመነ። በቀጥታ ወደ ጐዳና ላይ በመውጣት አዲስ የተቀበለውን ኃይል ለመለማመድ ሞከረ። ወደ አንድ በሽተኛ ለማኝ በመመልከት «ተፈወስ» ብሎ ጮኸ። ነገር ግን ምንም አልተፈጸመም። ተአምራት አልተደረገም። ከዚያም በእግዚአብሔር ላይ እያዘነና በክርስትናው እየተጠራጠረ ወደ ቤቱ ተመለሰ።  ጥያቄ፡- ክርስቲያኖች ይመላከቱት ዘንድ የሚፈልጓቸውን ተአምራትና ሌሎች አስደናቂ ድርጊቶችን የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን ዘርዝር። እነዚህ ቪዲዮዎች የሚጠቅሙ ይመላሉሃል ወይስ የሚዱ? መልስህን አብራራ።  እንደ ተስፋዬ ያሉ ክርስቲያኖች ብዙዎች ናቸው። ስለ መንፈስ ቅዱስ ከመጽሐፍ ያነባሉ ወይም ቪዲዮ ይመለከታሉ፤ የሰሙትንም ነገር ወዲያውኑ ያምናሉ። እግዚአብሔር በቃሉ ከገለጸላቸው ነገሮች ውጭ ያሉትን ትምህርቶች መፈተንና መመርመር የእያንዳንዱ ክርስቲያን ኃላፊነት መሆኑን ይዘነጋሉ። ሙሉ በሙሉ ትክክል የሆነና ሊወድቅ የማይችል እውነት ያለው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብቻ ነው።  ጥያቄ፡- ሀ) ክርስቲያኖች አንድ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ቃል ውጭ የሆነን ትምህርት ሲያስተምራቸው ባለመፈተናቸው ወደ ስሕተት የወደቁባቸውን ሁኔታዎች ግለጽ። ለ) በኢትዮጵያ ያሉ ክርስቲያኖች ስለ መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ ትምህርቶች የሚያገኙባቸውን ምንጮች ዘርዝር።  ስለ እግዚአብሔር እውቀትን የምናገኘው ከየት ነው? ስለ መንፈስ ቅዱስና ስለ ተግባሩ የሚገልጸውን እውቀት የምናገኘው ከየት ነው? ከሰብአዊ ችሎታችን አንጻር እውቀታችን እርግጠኛ መሆኑን የሚያሳየን ምንጭ ወይም ስፍራ የምናገኝበት ሁኔታ አለን?  አንዳንድ ሰዎች እርግጠኛ እውነትን የምናገኝበት ስፍራ የለም ይላሉ። ስለ እውነት የተለያዩ መረዳቶች አሉ። ሰው እስካመናቸው ድረስ ሁሉም ተቀባይነት አላቸው ይላሉ። ስለዚህ ሙስሊሞች የሚያምኑት ለሙስሊም ትክክል ነው፤ ክርስቲያኖች የሚያምኑት ደግሞ ለክርስቲያን ትክክል ነው ይላሉ። እነዚህ ሰዎች እንደሚሉት አሳቦች፥ ፍልስፍናዎች፥ ሃይማኖቶችና ተግባራት ሁሉ ሊመዘኑ የሚችሉበት እንድ ፍጹም እውነት የለም።  ጥያቄ፡- ሀ) ይህን ትምህርት ማመን ለእኛ አደገኛ የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? ለ) ይህን የሚያምን ሰው አጋጥሞህ ያውቃልን? እንዲህ ዓይነቱ ሰው ምን እንደሚያምን አብራራ።  እንደ ክርስቲያን ይህን ትምህርት በጥብቅ መቃወም አለብን። እውነት የሆነውን ካልሆነው ለመለየት የምንሄድበት ስፍራ አለን። በአሳቦች፥ በፍልስፍናዎች፥ በሃይማኖቶችና በተግባራት ሁሉ ላይ ሊፈርድ የሚችል ምንጭ አለን። እርሱም መጽሐፍ ቅዱስ ነው።  ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብብ፡- መዝ (119፡9፥ 89+105፥ 33፤ ማቴ. 5፡7-18፤ 2ኛ ጢሞ 3፡16-17፤ 2ኛ ጴጥ 1፡20-2፤ ዕብ 4፡12። ሀ) እነዚህ ጥቅሶች መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ራሱ ስለሚናገረው ምን ያስተምሩናል? ለ) ይህ ሰዎች አዳዲስ ትምህርቶችን ይዘው ሊመጡ ምን ማድረግ እንዳለብን ያሳያል? ትክክል መሆኑንና ያለመሆኑን በምን እናውቃለን? እውነትን የምንመዝንበት ፍጹም የሆነ እውነተኛ ሚዛን መጽሐፍ ቅዱስ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ እራሱ ያስተምረናል። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ራሱ የሚሰጠው ምስክርነት የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ፥ ስሕተት እንደሌለበት እና የሐሰት ትምህርትን ለማስተማር እንደማይቃጣ ነው። በዚህ የጥናት መጽሐፍ የምናጠናው መንፈስ ቅዱስ በሰዎች ልብ በመሥራት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የላፉት ሁሉ እግዚአብሔር ለሰዎች ሊያስተላልፈው የፈለገውን መልእክት ብቻ እንዲሆን አድርጓል። ርቀትን ለመለካት የምንጠቀምበት መለኪያ ሜትር እንደሆነ ሁሉ በምድር ላይ ያሉ ትምህርቶች ሁሉ የሚመዘኑበት መስፈርት መጽሐፍ ቅዱስ ነው።  እውነት ሁሉ የሚዳኝበት መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሆነ ለመቀበል ብዙ ክርስቲያኖች ፈቃደኛ ቢሆኑም፥ ብዙ ክርስቲያኖች ደግሞ እምነታቸውን የሚመሠርቱት በዓል ለማተቻቸው፥ ወይም ከሌሎች ስሚሰሟቸውና በመሳሰሉት ሌሎች ምንጮች ላይ መሆኑ የሚያሳዝን ነገር ነው። ይህ ክርስቲያኖችና ቤተ ክርስቲያንን እጅግ አደገኛ የሆነ አቋም ላይ ይጥላቸዋል፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስን ለእምነታችን የመጨረሻው ባለሥልጣን አድርገን ካልተጠቀምንበት በፍጥነት ከስሕተት ላይ እንወድቃለን። ቀጥለን የምንመለከታቸው ነገሮች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን ሁሉ ሊያሳስቧቸው የሚገቡ ናቸው።  1. በቤተ ክርስቲያን ከሚስፋፉት ትምህርቶች አብዛኛዎቹ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የላቸውም።  ጥያቄ፡- 2ኛ ጢሞ. 4፡1-5 አንብብ። ሀ) የመጨረሻዎቹ ዘመናት ባሕርያት ምን እንደሚመስሉ ግለጽ። ለ) እነዚህ ባሕርያት በዛሬይቱ ቤተ ክርስቲያን ምን ያህል ይዘወተራሉ? ሐ) የእግዚአብሔር ሰው ምን ማድረግ አለበት?  በ2ኛ ጢሞ. 4፡1-5 ጳውሎስ፥ በመጨረሻው ዘመን ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ የሕይወታቸው መመሪያ መሆኑን እንደማይቀበሉ ይነግሩናል። በዚህ ምትክ ሕይወታቸውን ስም ስት ነገሮች ላይ ይመሠርታሉ። በስሜቶቻቸው፥ ዓይኖቻቸው በሚያዩትና በትውፊታቸው።  1. የስሜቶቻቸው መላኪያ (መመዘኛ)፡- የሰሙትና የሚያደርጉት ነገር መልካም እንደሆነ ከተሰማቸውና ሌሎችን የማይጐዳ ከሆነ ትክክለኛና ለማድረግ የተፈቀደ አድርገው ይቆጥሩታል። ለምሳሌ አንድ ሰው በቤተ ክርስቲያን መካከል ተነሥቶ ቢያንስና የለበሳቸውን ልብሶች በሙሉ አውጥቶ ቢጥል ይህን ለሚያደርገው ሰው መልካም ሊመስል ይችላል። ትክክል ይሁን ወይም ስሕተት የምናውቀው ግን በምንድን ነው? ትክክል ይሁን ወይም ስሕተት የሚወስነው የእርሱ ወይም የእርሷ ስሜት ነውን? አይደለም። ስማቶቻችን ሊዋሹ ይችላሉ። የአንድ ነገር ትክክለኛነት ወይም ትክክላኛ ያለመሆን ቀጥተኛ እውነተኛ መመዘኛዎች አይደሉም። ብዙ ወጣቶች በፍትወተ ሥጋ ኃጢአት የሚወድቁት ጊዜያዊ የሆነ አስደሳች ስሜት ስለሚሰማቸው ነው። የእግዚአብሔርን ቃል መመዘኛነት በመተው ስሜታቸውን እንደ መመዘኛ ይቀበላሉ። ስለ መንፈስ ቅዱስ በቤተ ክርስቲያኖቻችን በዛሬው ጊዜ የሚሰጡ ትምህርቶች መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት ከሚደረግ ጥረት የመነጩ ሳይሆን በሰዎች ላሜት ላይ የተመሠረቱ ናቸው።  ጥያቄ፡- ሀ) የእግዚአብሔርን ቃል ለመከተል ከመፈለግ ሳይሆን በስሜቶቻቸው ላይ ብቻ በመመሥረት ሰዎች የሚያደርጓቸው ሌሎች ምሳሌዎችን ጥቀስ? ላ) እነዚህ ነገሮች በ2ኛ ጢሞ 4፡1-5 ሰዎች በመጨረሻ ዘመን ከሚኖራቸው ዝንባሌ ጋር የሚመሳሰሉት እንዴት ነው?  እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር ድርጊቶችን ያከናውን ዘንድ አእምሮን፥ ስሜትንና ሥጋዊ አካልን ፈጥሮላታል። እነዚህ ሦስቱም የሰው ክፍሎች መልካምና ሚዛናዊ ተደርገው ተፈጥረዋል። የእግዚአብሔር ዕቅድ አእምሮ ስሜትና ተግባራዊ ድርጊትን በበላይነት እንዲቆጣጠርና እንዲመራ ነበር።  ሰይጣን ወደ አዳምና ሔዋን በመጣ ጊዜ ይህን ሥርዓት ቀየረው። ስሜት በአእምሮ ላይ የበላይ ሆኖ እንዲገዛና የተሳሳተ ድርጊት እንዲፈጠር አቀነባበረ። ሔዋን የተከለከላውን ፍሬ ስትመለከት ለመብላት መልካም እንደመሰላትና እግዚአብሔር እንዳትበላ እንደከለከላት ብታውቅም እንኳ እንደበላች አስታውስ። ስሜቶቿ አእምሮዋን አሸነፉና ውጠቱ ኃጢአት ሆነ። ሰይጣን የምንሠራቸውን ኃጢአቶች በሙሉ የሚያስፈጽመን ስሜቶቻችን አእምሮአችንን እንዲያሸንፉ በማድረግ ነው። ብዙ ጊዜ ኃጢአት የምንሠራው ትክክለኛ የሆነውን ነገር ባለማወቃችን ሳይሆን ላላሜቶቻችን በመሸነፍና ትክክለኛ ያልሆነውን ነገር በማድረግ ነው። ለዚህም ነው መጽሐፍ ቅዱስ አእምሮአችንን እንድንቆጣጠር፥ አእምሮአችንም ስሜቶቻችንን እንዲቆጣጠርና በአንድነት እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ለመሥራት ዘወትር የሚያሳስበን። አእምሮአችን፥ ስሜቶቻችንና ተግባራችን በተገቢው ሚዛን በሚሆኑበት ጊዜ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ኑሮ ልንኖር እንችላለን።  ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት፥ ኢሳይያስ 26፡3፤ ማር. 12፡30፤ ሮሜ 1፡28፡12፡2፤ 1ኛ ቆሮ. 14፡13-5 እያንዳንዱ ጥቅስ አእምሮአችንን በተመለከተ ምን ይላል?  መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ጊዜ አእምሮአችንን በአግባብ ስለመጠቀም ይናገራል። ኢሳይያስ 26፡3 ሁኔታዎች አስቸጋሪ በሚሆኑበት ጊዜ እንኳ በእግዚአብሔር ላይ እእምሮአችን በማሳረፍ ሰላምን ልናገኝ እንደምንችል ይናገራል። ማርቆስ 12፡30 እግዚአብሔርን በሚገባ ላመከተል በሙሉ አሳባችን አእምሮአችን) እግዚአብሔርን መውደድ እንዳለብን ማለትም አስተሳሰባችን ለእርሱ መማረክ እንዳለበት ይናገራል። ሮሜ 1፡28 ወደ ተሳሳተ ድርጊት የሚመራ ኃጢአት እንዴት ከማይረባ አእምሮ እንደሚመጣ ያሳያል። ሮሜ 12፡2 ደግሞ እንደ ክርስቲያን ማደግ የሚመጣው አእምሮአችን ሲታደስ ብቻ እንደሆነ ይናገራል፤ 1ኛ ቆሮ. 14፡13-5 ደግሞ እግዚአብሔር በምናመልከው ጊዜ ስሜቶቻችንን (መንፈሳችንን) እንዳንጠቀም የማይቃወም ቢሆንም አእምሮእችን በመንፈሳችን ላይ ገዥ ሆኖ እግዚአብሔርን በመረዳት ማመስገናችን የላቀ ዋጋ እንዳለው ይነግረናል።  ዛሬ በቤተ ክርስቲያን የምንመለከተው ሁኔታ ግን ስሜቶቻችን በመረዳታችን ላይ ገዥ መሆናቸውን እንድናምን ያደርገናል። አንዳንድ መዝሙሮችን እየደጋገምን ከ6 ደቂቃ በላይ የምንዘምረው የሰዎች ስሜት ከፍ እያለ እንዲሄድ ነው። ይህ አምልኮአችንን የበለጠ መንፈሳዊ እንደሚያደርገው እናስባለን። ይህ እውነት መሆኑን እጠራጠራለሁ። በምንዘምርበት ጊዜ አእምሮእችን ያለማቋረጥ ከስሜቶቻችን ጋር የማይሠራ ከሆነ፤ የምንዘምረው ነገር ምን እንደሆነ በእርግጥ ካላሰብን እግዚአብሔርን ማምለክ አቁመን ለሚቶቻችን በባዶ ሜዳ እየጋለቡ ናቸው ማለት

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የምንረዳበት ምንጭ Read More »

ሥነ መለኮት ምንድን ነው?

በዚህ የትመማ መጽሐፍ የመንፈስ ቅዱስን ሥነ መለኮት እናጠናለን። ሥነ መለኮትን ስለ ማጥናት ስንነጋገር ስለ ሁለት ነገሮች መናገራችን ነው።  አንደኛ፥ ስለ አንድ ርእሰ ጉዳይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ እውነቶችን በሙሉ በአንድነት ለማሰባሰብ መፈለጋችንን ያመለክታል። መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው እውነተችን (ርእሰ-ጉዳዮችን) በየመስካቸው ከፋፍሎ በሚያስቀምጥ መንገድ አይደለም። ይልቁንም መጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን፥ ትረካዎችን ደብዳቤዎችን የያዘ ሲሆን እነዚህም እግዚአብሔር ምን እንድናውቅ እንደሚፈልግ ያስተምሩናል። በእያንዳንዱ ትረካ ወይም ደብዳቤ ውስጥ በርካታ እውነቶች ወይም ርእሰ ጉዳዮች ተጠቅሰዋል። ስለ እግዚአብሔር፥ ስለ ድነት (ድነት (ደኅንነት)) ወይም ስለ መንፈስ ቅዱስ ያሉትን እውነቶች በሙሉ በአንድ ስፍራ እጢቃልሉ የያዘ ክፍል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። ስለሆነም፥ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሥነ መለኮት እናጠናለን ስንል መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚያስተምራቸውን እውነቶች በአንድነት በማድረግ በሥርዓት እናጠናቸዋለን ማለታችን ነው።  ሁለተኛ፥ ሥነ መለኮት እናጠናለን ስንል የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን እንዴት እንደምንረጻ እንመለከታለን ማለታችን ነው። የሥነ መለኮት ትምህርትን የመረዳታችን መጠን ሁልጊዜ ውሱን ነው። መረዳቶቻችንን ሁልጊዜ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን ያነሱ አድርገን ልንመለከት ይገባል። ሥልጣን ያለው መጽሐፍ ቅዱስ እንጂ የእኛ መረዳት አይደለም። የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን በሙላት በትክክል የመረዳት ችሎታ ማናችንም የለንም። እውነትን የማወቃችን ችሉታ ውስን የሆነው በባሕላዊ መረዳሞቻችን፥ በማንነታችን ወይም በቤተ ክርስቲያን ልማዳችን እንኳ ተጽእኖ ስለሚደርስበት ነው። የመንፈስ ቅዱስን ሥነ መለኮት እናጠናለን ስንል የእግዚአብሔር ቃል ስለ መንፈስ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምረን ያለንን መረጻት ሥርዓት ባለው የአጠናን ዘዴ እንመለከተዋለን ማለታችን ነው።  ስለ እግዚአብሔርና ስለ ቃሉ ያለን መረዳት ውሱንና ከፊል እንደሆነ ሁልጊዜ መዘንጋት የለብንም። ቢሆንም እንኳ መረዳታችንን ለማሳደግ የእግዚአብሔርን ቃል ያለማቋረጥ ማጥናት ኃላፊነታችን ነው። ይሁንና፥ ከእኛ በተለየ ሁኔታ እውነትን ከሚረዱ ሌሎች ክርስቲያኖች የአመለካከት አቅጣጫ ሆነን ለማየትም ጥረት ማድረግ ይገባናል። በዚህ የጥናት መጽሐፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምር እንመለከታለን። በተጨማሪ ሌሎች ክርስቲያኖች በዚህ ጉዳይ ላይ ያላቸውን የተለየ አቋም በመመልከት ያንን አቋም ለምን እንደምንቀበል ወይም እንደማንቀበልም እንገልጻለን። ይህንን የምናደርገው በፍቅርና በዚህ ጉዳይ ላይ ለሁሉም ነገር መልስ እንደ ሌለን በማመንም ጭምር ነው። ትልቁ ፍላህታችን በአንድነት ወደ መጽሐፍ ቅዱስ በመመልከት «መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?» የሚለውን ጥያቄ እንድናነሣ ነው።  ጥያቄ፡- እንደ መንፈስ ቅዱስ ያሉ ጉዳዮችን ማጥናት አስፈላጊ ነው ብለህ የምታስበው ለምንድን ነው? ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

ሥነ መለኮት ምንድን ነው? Read More »

ስለ መንፈስ ቅዱስ ለምን እናጠናለን?

ጥያቄ፡- ክርስቲያኖች ስለ መንፈስ ቅዱስ ማጥናታቸው አስፈላጊ እንደሆነ የምታስበው ለምንድን ነው?  ዛሬ ዓለማችንን ብንመለከት ከብዙ ችግሮች ጋር በሚታገል ዓላም እንዳለን እንገነዘባለን። ከእነዚህ ችግሮች ጥቂቶቹ ጦርነቶች፥ ረሃብ፥ የዘር ልዩነት ውጥረትና ድህነት ናቸው። ከፍቅሩ የተነሣ የሰው ልጆች እነዚህን ችግሮች እንዲያሽንፉ የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ለማድረግ እግዚአብሔር ጽኑ አቋም አላው። ይህንንም በሁለት መንገዶች ያደርጋል። በመጀመሪያ እግዚአብሔር በዓለም ላይ ላሉ ችግሮች ሁሉ መነሻ ለሆነው የሰው ኃጢአተኛነት ዴስ ቅዱስ መንፈስ ቅዱፅዚአብሔርጽታት መፍትሔ ለመስጠት ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ላከው። እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ድነት (ድነት (ደኅንነት))ን ሰጥቶአል። ይህ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጠው ተቀዳሚ ስጦታ ነው። (2ኛ ቆር. 9፡5) ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በመሞት የኃጢአትን ዋጋ ከፍሎ የሰው ልጆች ወደ እግዚአብሔር የሚመጡበትንና ኅብረት የሚፈጥሩበትን መንገድ ከፍቶአል።  ቀጥሎ ደግሞ እግዚአብሔር መንፈሱን በመላክ በሕይወታችን ኃጢአት እንዳይቆጣጠረን ድል የምንነሳበትን ኃይል ሰጥቶናል። እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጠው ሁለተኛው ታላቅ ስጦታ መንፈስ ቅዱስ ነው። ኃጢአትን ድል ይነሣ ዘንድ ለመርዳት መንፈስ ቅዱስ ለሰዎች ተሰጠ። መንፈስ ቅዱስ ክርስቶስን እንድንመስል ያደርገናል። የተሰጠን መንፈስ ቅዱስ ኃጢአትን በሕይወታችን ድል እንድንነሣ ብቻ ሳይሆን፥ በዚህ ምድር ወኪሎቹ ለመሆን ኢየሱስን እንድናገለግለው ያግዘናል።  ብዙ ሰዎች እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሰጣቸውን የድነት (ድነት (ደኅንነት)) ስጦታ እንደማይጠቀሙበት ሁሉ ብዙ ክርስቲያኖች የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ በሕይወታቸው አይጠቀሙበትም። በዚህም ምክንያት ያለማቋረጥ ከኃጢአት ጋር ይታገላሉ። ወይም ከመንፈስ ቅዱስ የአገልግሎት ስጦታዎች በአንዱ ላይ ብቻ በማተኮር ወደ ስሕተት ይወድቃሉ። ባለድል ሕይወት እንድንኖር በባሕርያችንም ሆነ በአገልግሎታችን እግዚአብሔር እንደሚፈልግብን እንድንሆን ከተፈለገ በርካታ የተለያዩ የመንፈስ ቅዱስ የአገልግሎት ስጦታዎችን በሕይወታችን ልናውቅና ልንላማመድ ይገባናል።  ስለ መንፈስ ቅዱስ የምናጠናባቸው በርካታ ምክንያቶች አሉ። ከምክንያቶቹ ጥቂቶቹ ቀጥሎ ተጠቅሰዋል።  1. የክርስቲያን ሕይወት ተቀዳሚ አላማ እግዚአብሔርን ማወቅ ነው። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከሥላሴ አካላዊ ሕልውናዎች አንዱ ነው። ስለዚህ ልናውቀው ይገባል።  በዘመናት ሁሉ ክርስቲያኖች እውነተኛው አምላክ እራሱን የገለጠው በቅድሚያ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደሆነ አጥብቀው ተናግረዋል። እውነት ምን እንደሆነ በተለይ እውነተኛው አምላክ ማን እንደሆነ የሚገልጥ የተሟላ ትክክለኛ፥ ስሕተት የሌለበት መመሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ማለትም ብሉይ ኪዳንና አዲስ ኪዳን ነው። ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን በጥንቃቄ ካጠኑ በኋላ እግዚአብሔር በሦስት አካላዊ ሕልውና የተገለጠ ማለትም እግዚአብሔር አብ፥ እግዚአብሔር ወልድ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ እንደሆነ ያምናሉ።  የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና ጭብጥ ስው ስላመፀና ኃጢአትን ስላደረገ ከእግዚአብሔር መለየቱን መግለጽ ነው። እግዚአብሔር ግን በፍቅርና ስምሕረት ከሰው ልጅ ጋር ኅብረት ለማድረግ ያለማቋረጥ ጥረት ያደርጋል። በምድር ላይ ያሉ የቅርብ ጓደኞቻችንን እንደምናውቃቸው ሁሉ እግዚአብሔር እንድናውቀው ይፈልጋል። እንደዚሁም እግዚአብሔር መንፈስ ውቅርፅ ጓደኞታች ያለማቋረጥ ጥረት በፍቅርና ቅዱስ እንድናውቀውና በዕለታዊ ሕይወታችን እርሱን እንድንለማመደው ይፈልጋል።  ጥያቄ፡– ኤፌሶን 1፡21 አንብብ። ሀ) ጳውሎስ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ግንኙነት ምን እንደሆነ ነው የሚጸልየው? ለ) ክርስቲያን ከሆንክ ጀምሮ ከእግዚአብሔር አብ፥ ከእግዚአብሔር ወልድና ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋር ያለህ ቀንኙነት እንዴት እንደተለወጠ ግለጽ።  2. ክርስቲያን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለው ግንኙነት ጥልቀት ከሌለው እግዚአብሔርን በሚያስከብር መንገድ ለመኖር አይችልም።  እግዚአብሔርን ለማወቅ በምናደርገው ነገር ሁሉ እርሱን በመታዘዝ ሕይወት መመላላስ ይጠበቅብናል (ዮሐንስ 14፡2)። መንፈስ ቅዱስን እንዴት ማዳመጥ እንደሚገባን ካልተማርን በስተቀር የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ስለማናውቅ እርሱን ደስ ለማሰኘት አንችልም። ከኃጢአት ተለይተን በቅድስና አንኖርም። ኃጢአትን ለማሸነፍ ወይም በድፍረት ለመመስከር ወይም በቤተ ክርስቲያን እንደሚገባ ለማገልገል ኃይል አናገኝም።  3. መንፈስ ቅዱስ በሚናገርበት ጊዜ እንዴት ልናደምጠው እንደምንችል ካላወቅን በእግዚአብሔር ድምጽና በሰይጣን ድምጽ መካከል ያለውን ልዩነት ለማወቅ አንችልም።  መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስረዳን ሰይጣን ብዙ ጊዜ የብርሃን መልአክ መስሎ ወደ ሰዎች ይመጣል (2ኛ ቆሮ. 11፡14 ተመልከት)። ይህም ማላት ወደ እኛ የሚመጣው መልካም መስሎ ነው ማለት ነው። እውነታው ሲታይ ግን የሚያደርገው ወይም የሚያስመስልበት ነገር የክፋትና የጥሩት ነው። ሰይጣን ውሸት የሆነውን እንድናምን ያለማቋረጥ ይሞክራል። እግዚአብሔር ግን የእውነት አምላክ ስለሆነ እውነትን እንድናውቅ ይፈልጋል። ትክክል የሆነውን ነገር ካልሆነው እንዴት ለመለየት እንችላለን? የሰይጣን ድምፁ የቱ እንደሆነና የእግዚአብሔር ድምፁ ደግሞ የቱ እንደሆነ ካላወቅን፤ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል በመጠቀም መንገዱን እንዴት እንደሚያሳየን ካላወቅን ትክክለኛ የሆነውን ነገር ካልሆነው ለይተን ለማወቅ አንችልም (ዮሐንስ 10፡14-16)። መንፈስ ቅዱስ መቼ እንደሚናገረን ካልተረዳን በስተቀር በሕይወታችን ሚዛናዊነት እናጣና ወደ ስሕተት እንወድቃለን። (ማስታወሻ መንፈስ ቅዱስ ለእኛ የሚናገርበት ተቀዳሚ መንገድ በእግዚአብሔር ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት መሆኑን ማወቅ አስፈላጊ ነው። ለዚህ ነው ስብከቶችን መስማትና፤ የቪዲዮ ዝግጅቶችን መመልከት ወዘተ… ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብና ማጥናት አስፈላጊ የሚሆነው።) 5ኛ ጥያቄ፡- ስለ መንፈስ ቅዱስ ለማጥናት ምክንያት የሆኑት ከላይ የተመለከትናቸው እነዚህ ሁለት ነጥቦች በዚህ ዘመን ላለችው ቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልጉበትን መንገዶች ግለጽ።  4. መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚያስተምረውን ነገር ካላወቅን በስተቀር በመሠረታዊ የክርስትና እምነት ትምህርታችን ስሕተት ላይ እንወድቃለን።  አብያተ ክርስቲያኖቻችን የተሞሉት በደካማና ሁልጊዜ በሚታገሉ ክርስቲያኖች ነው። ሚዛን-ለቀቅ በሆኑ አስተማሪዎች የሚዛመቱ ወይም በቪዲዮዎች የሚታዩ እንግዳ ትምህርቶች እንደ ብርቱ አውሎ ነፋስ ምድራችንን እያናወጡት ሲሆን፥ ከዚህም የተነሣ ብዙዎች በተለያዩ ስህተቶች ወስጥ የመግባት እዴጋ አንዣቦባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚያስተምረውን ማወቅ ያለብንና መንፈስ ቅዱስን ለመለማመድ፡ በሕይወታችን በሚከሰት ኃጢአት ላይ ያለውን ኃይሉን ለመገንዘብ፡ እንዲሁም ወደ እውነት ሁሉ ሊመራን ለማድመጥ እንድንችል ክእርሱ ጋር ሥር የሰደደ ኅብረት ማድረግ የሚገባን ለዚህ ነው (ዮሐንስ 14፡25-26)።  5. በሕይወታቸው የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ባለመለማመዳቸው ምክንያት በመንፈሳዊ ሞት አደጋ ላይ ያሉ ክርስቲያኖች በርካታ ናቸው።  ክርስትና በአንድ ወይም በሌላ መልኩ ለብዙ ሺህ ዓመታት በኢትዮጵያ ኖሯል። በፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት እንኳ መንፈስ ቅዱስ በደቡብ መሥራት ከጀመረና በርካታ ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ካመጣ 70 ዓመታት አልፈዋል። አንድ ትውልድ እልፎ ሌላ ትውልድ ተተክቷል። እስካሁን ድረስ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ ላሉ ክርስቲያኖች ቶርነቱን ስላላጓደለ፥ በስደቱ ምክንያትም ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ የመሞቷ አዝማሚያ ተገትቷል። በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍሎች ግን የመንፈስ ኃይል በመቀነስ ላይ ይመስላል። ሰዎች አሁን ካሉበት መንፈሳዊ ሁኔታ ይልቅ በትውፊታቸውና በቀድሞ ታላቅ ታሪካቸው ላይ ትኩረት ያደርጋሉ። ኃጢአት በገፍ ነው። የአምልኮ መልክ ተላብሳው የመንፈስ ቅዱስ እውነታ ግን የሌላቸው ብዙዎች ናቸው። (2ኛ ጢሞ. 3፡5 ተመልከት)። የመንፈስ ቅዱስን ኃይል እንደገና እንደ አዲስ ካልተለማመድንና ቅድስና ስሜት እንደገና ካልተሞላን እንደ መሳፍንት ዘመን የአባቶቻቸውን አምላክ የማያውቅ ሌላ ትውልድ የሚነሣበት ጊዜ እሩቅ አይደለም (መሳፍንት 2፡10-11)። እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ እሳትን በብዙዎች ሕይወት እንደገና የሚያቀጣጥልበት እንዲሆን ስለ መንፈስ ቅዱስ ማወቅ ብቻ ሳይሆን መንፈስ ቅዱስን አውቀን ኃይሉም በሕይወታችን እንዲረጋገጥ እሻለሁ።  ጥያቄ፡- የመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንዳንድ ጊዜ በሕይወትህም ሆነ በቤተ ህክርስቲያን ሲቀንስ እንዴት እንዳየህ ግለጽ። ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

ስለ መንፈስ ቅዱስ ለምን እናጠናለን? Read More »

መግቢያ

ዮሐንስ ጌታን የሚወድ አዲስ ክርስቲያን ነበር። ኢየሱስ ከኃጢአቱ እንዳዳነው ያውቃል። ልቡ በደስታ የተሞላ ከመሆኑ የተነሣ እግዚአብሔር በሕይወቱ ስላደረገው ለውጥ ላገኛቸው ሰዎች ሁሉ ይናገር ነበር። አንድ ቀን አንድ ክርስቲያን አገኘውና መንፈስ ቅዱስ ተሞልተሃልን? በማለት ጠየቀው። ጥያቄውም ራ አጋባው። «ወመንፈስ ቅዱስ እርሱ ማን ነው? ወይም ምንድን ነው? መንፈስ ቅዱስ እንደተሞላሁ እንዴት አውቃለሁ?» በአእምሮው ጥርጣሬ ሞላሰትና ወዲያውኑ ደስታው ከእርሱ ተለየ። በርካታ ክርስቲያኖችን ስለ መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ ጥያቄዎች መጠየቅ ጀመረ። አንዳንዶች ላላ መንፈስ ቅዱስ መጨነቅ አያስፈልግህም ኢየሱስ ብቻ ይበቃል አሉት። ይህን ወዳሉት ክርስቲያኖች ሕይወት ሲመለከት ግን ሕይወታቸው ደስታ፥ ኃይል እና መታዘዝም የማይታይበት መሰለው። ሌሎች ደግሞ ስለ መንፈስ ቅዱስ ከመጠን በላይ ይናገራሉ። እንዳ በሆኑ ቋንቋዎች እየጮችና ሰውነታቸው እየተንቀጠቀጠ ይጸልያሉ። ለመንፈስ ቅዱስ መገኘት እውነተኛ ምልክት ይህ ነውን? ትክክለኛው ማን ነበር? ሰው ስለ መንፈስ ቅዱስ እውነተኛውን ነገር ለማወቅ ወደየት ነው መሄድ ያለበት?  ጥያቄ፡– መንፈስ ቅድስን በሚመለከት በክርስቲያኖች መካከል ያለውን እንዲህ ያለ ግራ መጋባት እንዴት አየኸው?  እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም ዙሪያ እጅግ አስደናቂ በሆኑ መንገዶች እየሠራ ለመሆኑ ምንም የሚያጠራጥር ነገር የለም። በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በእምነት ወደ ክርስቶስ እየመጡ እየጻኑ ነው። ሰዎች መንፈሳዊና ሥጋዊ ፈውስን እያገኙ ናቸው። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ክፍተኛ መንፈሳዊ ረሃብ በሕዝቡ ሕይወት ይታያል። በዚህች ታላቅ ምድር ለመኖርና ለመሥራት መታደላችን እንዴት ደስ የሚያሰኝ ነው!  ይሁንና፥ ይህ ዘመን በርካታ አብያተ ክርስቲያኖቻችንን እየበከሉ ኑፋቄዎችና ሐሰተኛ ትምህርቶች በምድሪቱ በፍጥነት የሚስፋፉበትም ነው። እራሱን የብርሃን መልአክ አድርጐ የሚያቀርበው ሰይጣን (2ኛ ቆሮ. 11፡14) በሥራ ላይ ነው። አብዛኛው የሰይጣን ሐሰተኛ ትምህርት የሚያተኩረው በመንፈስ ቅዱስ፥ ህልውናው በሚረጋገጥበት መንገድ እና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባለው ተቀዳሚ ሚና ላይ የተሳሳቱ አሳቦችን በመናኘቱ ተግባር ላይ ነው። ሰይጣን ግራ መጋባትን ለመፍጠርና የእግዚአብሔርን ሥራ ለማደናቀፍ የሚያደርጋቸውን ሙከራዎች ነቅተን መገንዘብ አለብን።  አንድ ሰው ስለ መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ለመጻፍ በሚነሣበት ወቅት ከአሳቡ ጋር የማይስማሙ በርካታ ክርስቲያኖች ሊገጥሙት እንደሚችሉ ገና ከጅምሩ ያውቀዋል። መንፈስ ቅዱስ ማን ነው? ዛሬ በዓለም ላይ የሚሠራው ሥራና ዓላማው ምንድን ነው? ህልውናው የሚገለጠው እንዴት ነው? በልሳናት በመናገርና በተአምራታዊ ፈውሶች ነውን? እነዚህ ጥያቄዎች በሺህ በሚቆጠሩ ክርስቲያኖች የሚጠየቁ ሲሆን፥ በበርካታ የተለያዩ መንገዶችም ክርስቲያኖች መልስ ይሰጡባቸዋል። የሚያሳዝነው ሰይጣን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑት እውነቶች አንዱ የሆነውን የመንፈስ ቅዱስ በክርስቲያኖች ማደር ጉዳይ ወደ ጸብና ክርክር መለወጡ ነው። አንድነታችን እንቆብርና በኃይል ተሞልተን ወንጌል የሚጠይቀውን ዓይነት ሕይወት መኖር እንድንችል እግዚአብሔር ላቤተ ክርስቲያን የሰጠውን መንፈስ ቅዱስ ሰዎች በተሳሳተ መንገድ ይረዱታል። በዓለም ዙሪያ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ታላቅ መከፋፈልን ላማምጣት ሰይጣን ይህን ሁኔታ እየተጠቀመበት ነው። ይህ እንዴት አሳዛኝ እውነታ ነው! በክርስቲያኖች መካከል በሚከናወን እንዲህ ዓይነት መከፋፈል አንጀቱ የሚርሰው ሳይጣን ብቻ ነው።  ጥያቄ፡- በኢትዮጵያ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት በመንፈስ ቅዱስ ወይም ከአገልግሎቶቹ በአንዱ ክርስቲያኖች እንዴት ሊለያዩ እንዳየህ ግለጽ።  የዚህ የጥናት መጽሐፍ ዓላማ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚያስተምረውን መመርመር ነው። ጌታን የሚወዱና የሚያገለግሉ ግን ስለ መንፈስ ቅዱስ የተለዩ እምነቶች ያሏቸው ክርስቲያኖች እንዳሉ ሰላማውቅ፥ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሚዛናዊ የሆነ አመለካከትን ለማቅረብ እሞክራለሁ። ጸሎታችን እግዚአብሔር በአብያተ ክርቲያናት መካከል አንድነትን ለማምጣት ይህን መጽሐፍ እንዲጠቀምበትሩ ክርስቲያኖች ዛሬ በየአብያተ ክርስቲያናቱ ሾልከው በመግባት የሚሰጡትን ትምህርቶች በመቀበል ወደ ስሕተት እንዳይወድቁና ሁሉ በላይ ደግሞ «በመንፈስ እንመላለስ። (ገላ. 5፡5) ዘንድ እንዲረዳን ነው። መልስ የምንሰጥበት ተቀዳሚ ጥያቄ «መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚያስተምረው ምንድን ነው?» የሚለውን ነው። ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

መግቢያ Read More »