የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ

የብሉይ ኪዳን ነቢያት መሢሑ የሚመጣበትን ወቅትና የመንፈስ ቅዱስ አገልግሉት የሚለወጥበትን ጊዜ እስቀድመው አመልክተው ነበር

ጥያቄ፡ ኢሳ 1-5፤ 42፡1-4፤ 61፡1-3 አንብብ። ሀ) እነዚህ ጥቅሶች በሚመጣው መሣሕ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ምን እንደሆነ ያስተምሩናል? ለ) ይህ አገልግሎት በኢየሱስ የተፈጸመው እንዴት ነበር? ኢሳ 44፡3፤ 59፡21 ሕዝ 11፡9፤ 36፡27 ና 37፡14፤ 39፡29፤ ኢዩ፤ 2፡28-29። ሐ) እዚህ ጥቅሶች ስለ መጨረሻዎቹ ቀናት የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ምን ያላተምሩናል?  የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት በብሉይ ኪዳን ዘመን ታላቅ እንደነበር ሁሉ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት የሚለወጥበት አዲስ ዘመን እንደሚመጣም ነቢያት ተገንዝበው ነበር። በመጀመሪያ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ልዩ ግንኙነት ያለው ሰው እንደሚመጣ ነበር። ይህ ሰው ከዳዊት ዘር የሚመጣው ንጉሥ መሢሑ ነበር (ኢሳ. 11፡23 42፡1)። ላለ መሢሑ በተነገረበት በእነዚህ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ተቀዳሚ ትኩረት እግዚአብሔርን በሚያስከበር መንገድ የእግዚአብሔርን ሕዝብ እንዲመራ መሢሑን በማስቻል ላይ ነበር። ከሌሎች መሪዎች በተለየ መንገድ በጥበብና በእውቀት የተሞላ ሆኖ ጌታን በመፍራት ይኖራል። በምድር ላይ ጽድቅን ያመጣል። የታሠሩትን ነፃ ሚያወጣና ልባቸው የተሠበረባቸውን የሚፈውስ የምሥራች ቃል ይሰብካል።  ሁለተኛ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ለሁሉም የሚዳረስ ስለመሆኑ ነበር። በእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል ያለውን በእግዚአብሔር ላይ የማመጽ ዝንባሌ ማለትም የድንጋዩን ልብ ይወለድና በሚታዘዝ ልብ ይቀይራል። መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል በሕዝቡ ፊት ያላማቋረጥ እንዲገኝ ያደርጋል። መንፈስ ቅዱስ ልዩ አገልግሎት በሚሰጡ በጥቂት ነቢያትና የፖለቲካ መሪዎች ላይ ብቻ መሆኑ ይቀርና የዕድሜና የዘር ልዩነት ሳያደርግ አሕዛብም ሲሆኑ አይሁድ በሁሉም የእግዚአብሔር ሕዝቦች ላይ ይወርዳል። በእነዚህ ምርጥ ሰዎች ላይ ለተወሰነ ጊዜ ይወርድ እንደነበረው ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር ሰዎች ሕይወት ውስጥ ይኖራል። የትንቢት ስጦታ ለፖለቲካ መሪዎች ወይም ነቢያት ብቻ የሚታደል መሆኑ ቀርቶ ይህ ለመንፈስ ቅዱስ ህውና ምልክት (ማስረጃ ) የሆነው ስጦታ ለሰዎች ሁሉ ይሰጣል።  ጥያቄ፡- መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ዘመን የሰጠውን አገልግሎት ክልስ። ሀ) በዚያ ዘመን የመንፈስ ቅዱስ ተቀዳሚ ሚና ምን ይመስል ነበር? ላ) ዛሬ መንፈስ ቅዱስ ከሚሠራባቸው መንገዶች ጋር ምን ተመሳሳይነት [አላው? ሐ) ዛሬ መንፈስ ቅዱስ ከሚሠራባቸው መንገዶች ጋር ልዩነቶቹስ ምን ምን ናቸው? መ) ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ስላለን ንኙነት በብሉይ ኪዳን ከነበረው አገልግሎቱ ልንማራቸው የምንችላቸው ነገሮች ምን ምን ናቸው?  ብዙ ጊዜ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሥራ ስናስብ አንዳንድ ጊዜ ከሚያደርጋቸው ድንቅ ነገሮች አኳያ ብቻ እንመለከተዋለን፤ ወይም በአንድ የአገልግሎት ገጽታው ላይ ብቻ በማተኮር ስለ መንፈስ ቅዱስ ያለን ሥነ መለኮታዊ መረዳት ሚዛናዊነትን ያጣል። መንፈስ ቅዱስ ግን መጠነ-ሰፊ በሆኑ ጉዳዮች ውስጥ ይሠራል። ከእዚህም ብዙዎቹ የማይታዩና በሚሩጸሙበት ጊዜ እንኳ የማናስተውላቸው ናቸው። የሕይውት መገኝትም ሆነ ዘላቂነቱ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የተደገፈ ነው። እግዚአብሔር ሕይወታችንን የሚያስተምርበትም ሆነ የሚመራበት አገልግሎት በመንፈስ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ነው። በብሉይ ኪዳን የምንመለከተው የመንፈስ ቅዱስ ተቀጻሚ አገልግሎት ቀን እግዚአብሔር የመረጣቸው መሪዎች ሕዝቡን እንዲመሩ ማድረግ ነበር። ይህ ችሎታ አንዳንድ ጊዜ እንደ ሳምሶን ብርታትና እንደ ሳኦል ትንቢት ተአምራዊ ተግባራትን ያካተተ ቢሆንም ብዙ ጊዜ ግን የመንፈስ ቅዱስ ህልውና የሚታየው በመሪዎች ጥበባዊ አመራር፥ ከጠላት የመታደግና ሕዝቡን በእግዚአብሔር ፊት የተቀደሰ ኑሮ እንዲኖሩ በማስቻል በማድረግ) ችሎታቸው ውስጥ ነው።  የብሉይ ኪዳን ዘመን ሲፈጸም እግዚአብሔር ለሕዝቡ አዲስ ሥራን ሲሠራ መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል የሠራበትን መንገድ እንደሚለውጥ ተነግሮናል። አገልግሎቱ ምን ይመስል ነበር? በብሉይ ኪዳንና በአዲስ ኪዳን ዘመናት መካከል ያለው ልዩነት ምን ይሆናል? በሚቀጥለው ሳምንት መንፈስ ቅዱስ በወንጌላት ውስጥ ስለ ሰጠው አገልግሎት በተለይ ደግሞ በኢየሱስ ሕይወትና ትምህርት ውስጥ ስለነበረው አገልግሎት እንመለከታለን። ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

የብሉይ ኪዳን ነቢያት መሢሑ የሚመጣበትን ወቅትና የመንፈስ ቅዱስ አገልግሉት የሚለወጥበትን ጊዜ እስቀድመው አመልክተው ነበር Read More »

መንፈስ ቅዱስ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንዲጽፉ በመምራት የሰጠው አገልግሎት

ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከቱ። 2ኛ ሳሙ 23፡1-4፤ ዕዝ. 2-4 ሚክ 3፡8፤ ማቴ. 22፡43-44፤ የሐዋ. 1፡16፤ 2ኛ ጢሞ 3፡16፤ 2ኛ ጴጥ. 2። ሀ) እነዚህ ጥቅሶች መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ዘመን የእግዚአብሔርን ቃል የመግለጥ ሚና እንደነበረው ምን ያስተምሩናል? ለ) እግዚአብሔር የተጻፈውን ቃሉን ይሰጠን ዘንድ ስለ ሠራው ሥራ ምን ያስተምረናል? ሐህ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ማመን ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው? ምን ጥቅም ይሰጣል?  ሰይጣን በዘመናት ሁሉ ውስጥ የእግዚአብሔርን ሕዝብ እምነት ለመደምሰስ ከተጠቀመባቸው መንገዶች አንዱ የእግዚአብሔርን ቃል ቸል እንዲሉ ማድረግ ነው። ይህንን የሚያደርገው በሁለት መንገዶች ነው። በርካታ የተከበሩ ክርስቲያኖች በሥራ እጅግ በመጠመዳቸው የእግዚአብሔር ቃል አያነቡም። ደግሞም አያጣኑም። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን በግልጥ ቢናገሩም እንኳ በተግባር ስንመለከታቸው ስለማይሰሙትና ስለማይታዘዙት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ቃል አይደለም።  ሌሎች ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል ትክክለኛነት በመጠራጠር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ ይላሉ። ይህ አመለካከታቸው መጽሐፍ ቅዱስ የጥሩ ሰዎች ጽሑፍ ስለሆነ መልካም ሥነ ምግባርን ያስተምራል እንጂ ከዚህ ሌላ ምንም አይደለም ወደ ማለት ያደርሳቸዋል። የእግዚአብሔርን ቃል ትክክለኛነት የሚጠራጠር ማንኛውም ክርስቲያን አደገኛ ጐዳና ላይ ሲሆን የዚህ አካሄድ መጨረሻም እምነትን መካድ ነው።  ጥያቄ፡- ሀ) በእግዚአብሔር ቃል ላይ ያሉ እነዚህን ሁለት አመለካከቶች በኢትዮጵያ እንዴት አየኸው? ለ) በሰዎች መንፈሳዊ ሕይወት የሚያስከትለው የመጨረሻ ውጤት ምንድን ነበር? ሐ) እንተ ወይም የምታውቃቸው በርካታ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔርን ቃል ቸል የምትሉት እንዴት ነው?  መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለሰዎች በመግለጥ የፈጸመውን ነገር ለማስረዳት ትምህርተ ዘለቆች (ምሁራን) ሁለት የተለያዩ ቃሎችን ይጠቀማሉ። የመጀመሪያው «መገለጥ» የሚለው ነው። ይህ ቃል ተሰውሮ የነበረውን ነገር እግዚአብሔር ለሰዎች የገለጠበትን ሂደት ያሳያል። እነዚህ ነገሮች ስለ ባሕርይው፥ ስለ ፍላጐቶቹና ወደፊት ስለሚሆን ጉዳይ ያሉ እውነቶች ሊሆኑ ይችላሉ። እግዚአብሔር ፈቃዱን የገለጠባቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ «ነቢያት» በመባል ይጠሩ ነበር።  ሁለተኛው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፎ ለሚገኘው የእግዚአብሔር ቃል የተሰጠ በእግዚአብሔር መንፈስ መነዳት የሚል ትርጉም የያዘ ቃል ነው። ይህ ቃል ከ2ኛ ጢሞ. 3፡16 የተገኘ ሲሆን፤ የግሪኩ ቃል አቻ ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር እስትንፋስ” ነው ይላል። ስለዚህ ሊቃውንት መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር መንፈስ ተነድተው የጻፉት ነው ሊሉ እንዲህ ማለታቸው ነው። ምንም እንኳ ጽሑፎቻቸው የግል አስተሳሰባቸውንና ማንነታቸውን ቢያንፀባርቁም በኩረ ጽሑፋት ስሕተት የሌለባቸው፥ በተሟላ ሁኔታና በትክክል የእግዚአብሔርን አሳብ፥ ዓላማና ቃሎች እንዲያስተላልፉ ከሰብአዊ ጸሐፊዎች ጋር አብሮ የሠራው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው።  መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚብሔር ሰዎች ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር መንፈስ ተነድተው የጻፉት ነው ስንል ምን ማለታችን ነው? በዚህ ጉዳይ ልንረዳቸው የሚገባን በርካታ ቁልፍ መመሪያዎች አሉ።  1) በመጀመሪያዎቹ ጸሐፊዎች ስለተጻፉት የመጀመሪያዎቹ ጽሑፎች መናገራችን ነው። ቅጂዎችን በማብዛትና ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች በመተርጐም ሂደት ውስጥ ስሕተት ሊታይ ይችላል (ለምሳሌ ዕዝራ 2፡3-70 ከነህ. 7፡4-73 ጋር አወዳድር)። ይሁን እንጂ የመጀመሪያዎቹ ጽሑፎች ሙሉ በሙሉ ትክክል እንደነበሩ እርግጠኞች መሆን እንችላለን። ይህ ማለት በእጃችን የሚገኘውን መጽሐፍ ቅዱስ መጠራጠር አለብን ማለት ነውን? አይደለም። ነገር ግን በታሪክ ሂደት ውስጥ በነበረው የትርጉምና ቅጂዎችን የማዘጋጀት ተግባር አንዳንድ ቀላል የሆኑ ለውጦች የተደረጉ ስለሆነ አሁን በእጃችን የሚገኘው ቅጂ ስሕተት ፈጽሞ የሌለበት ነው ማለት እንችልም። አሁን በእጃችን በሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ላለን እምነት መሠረቱ በታሪክ ሁሉ ይዘቱን ጠብቆ የተላለፈ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያህል ሌላ ጥንታዊ ጽሑፍ ያለመኖሩ አስደናቂ እውነታ ነው። በተለያዩ ቅጂዎች ውስጥ ባሉ በአንዳንድ ቃሎች ላይ እጅግ ቀላል የሆኑ ልዩነቶች ሲኖሩም እንኳ በእነዚህ ልዩነቶች ምክንያት የተፋለሰ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት የላም። የሒንዱ መጻሕፍትንና ቁርአንን በመሳሰሉ ሌሎች መጻሕፍት ውስጥ ይህ ሐቅ አይታይም። አንዳንድ ጊዜ እስላሞች በቅጂ ሂደት የሚታዩትን ተራ ግድፈቶች ነቅሰው በማውጣት መጽሐፍ ቅዱስ በስሕተት የተሞላ ነው የሚሉት ሰዎች በእግዚአብሔር መንፈስ ተነድተው ጻፉት ስንል ምን ማለታችን እንደሆነ ስላልተረዱ ነው።  2) መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው የጻፉት ነው ስንል መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ ትክክል ነው ማለታችን ነው። የሚያስተምረው ሙሉ በሙሉ እውነት ነው ማለታችን ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ የድነት (የደኅንነት) ብቸኛ መንገድ ኢየሱስ ነው ሲል እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተናገረው እውነት መሆኑን በእርግጠኝነት እናውቃለን።  (ማስታወሻ፡- መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዘመኑ ሰዎች አስተሳሰብ የሚናገረውንና ለለ አመለካከታቸው የሚያቀርበውን ማብራሪያ በመሠረታዊነት ከሚያስተምረው እውነት ለይተን ለማየት ጥንቁቅ መሆን አለብን። ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ ፀሐይ ትጠልቃለች ይላል። ይህ አባባል በዚያን ዘመን የነበሩ ሰዎች ስለ ፀሐይ መጥለቅ የነበራቸውን ትክክለኛ መረዳት የሚዘግብ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ሳይንሳዊ መጽሐፍ የተጻፈ ስላልሆነ ምድር ከፀሐይ ጋር ስላላት ቀንኙነት የሚናገረው ምንም ነገር የለም። አሳባቸው ሳይንሳዊ መሆኑንና አለመሆኑን ሳያስረግጥ ሰዎች ዓላማቸውን (አካባቢያቸው) እንዴት ያስተውሉት እንደነበር አስፍሯል።  3. መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው የጻፉት ነው ማለት የእግዚአብሔር ሙሉ ሥልጣን አለው ማለት ነው። የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ እግዚአብሔር ከፊታችን ቆሞ አንድ ነገር በሚነግረን ወቅት የሚኖረውን ያህል ሥልጣን እለው። በእርግጥ ይህን የሚያህል ሥልጣን ያለው መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። ዛሬ የምናልመው ሕልም ወይም መገለጦች ወይም የምንሰማቸው ድምጾች ወዘተ… የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል ያህል ሥልጣን የላቸውም። የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ቃል ወይም እስትንፋሰ-እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው።  ጥያቄ፡- መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ መንገድ የእግዚአብሔርን መንፈስ የተላበሰና የራሱ የእግዚአብሔር ቃል ከሆነ፥ ይህ እውነታ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ አስፈላጊነት፥ ለምን ማጥናትና ማወቅ፥ ደግሞም ግንዛቤያችንን ሰዎች በሚያስቡትና በሚያስተምሩት ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቃል ላይ መመሥረት እንደሚገባን ምን ያሳያል?  በብሉይ ኪዳን ዘመን እግዚአብሔር መልእክቱን ለሕዝቡ የሚያስተላልፍበት ተቀጻሚ መሣሪያ ነቢያቶች ሲሆኑ የእግዚአብሔርን መላእክት የመግለጥ ተቀዳሚ ኃላፊነት የወሰደው የሥላሴ አካል መንፈስ ቅዱስ ነበር። [ማስታወሻ፡- ኢሳ. 6፡8-10 ከሐዋ. 28፡25-27 ጋር ሲወዳደር ለኢሳይያስ የተናገረው መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ግልጽ ይሆንልናል]። ከእነዚህ ነቢያት አብዛኞቹ መልእክቶቻቸውን አልጻፉትም። ይልቁኑ ለትውልዳቸው የእግዚአብሔር አፈ ጉባኤ ነበሩ። አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ለነቢያት በቀጥታ ድምፅ ተናግሯቸዋል (ዘፀአ 19፡9፥ 17-19፤ 1ኛ ሳሙ. 3፡1-14)። በሌላ ጊዜ ደግሞ በሕልም (ዘፍ 20፡3-7፤ 31፡24) እና በራእይ ይናገር ነበር (ዘፍ 15፡1፤ ኢሳ 1፡1)።  እግዚአብሔር ጥቂት ነቢያትን ተጠቅሞ በሁሉም ዘመናት ላሉ ሕዝቦች ሁሉ ፈቃዱ እንዲተላለፍ ዘላለማዊ መጽሐፍ የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን እንዲጽፉ አደረገ። ከመንፈስ ቅዱስ ዋና አገልግሎቶች እንዱ ብዙ መተ ዓመታት (2000 ዓመታት ያህል የፈጀውን እና የተለያዩ ጸሐፊዎች የጻፉትን የእግዚአብሔርን ቃል የመጻፍ ሥራ ሂደት በበላይነት መቆጣጠር ነበር። በ2ኛ ጴጥ. 1፡21 ላይ እንደምንመለከተው የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና ምንጭ እግዚአብሔር እራሱ ነው። እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስን እንዲጽፉ ሰዎችን ተጠቅሟል። ሰዎችን መሣሪያ እድርጐ የተጠቀመ ብቸኛው የመጽሐፉ ደራሲ ግን መንፈስ ቅዱስ ነው። ለዚህም ነው የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ክብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በሚጠቅሱበት ጊዜ ቃሎቹ የመንፈስ ቅዱስ እንደሆኑ የሚናገሩት (ለምሳሌ ማቴ. 22፡43፤ የሐዋ. 1፡16፤ 4፡24-25፤ 28፡25-27፤ ዕብ 3፡7፤ 10፡6-17)፡፡ ኢየሱስ እራሱ ሲናገር ዳዊት የጻፈው በመንፈስ ቅዱስ እንደነበር መላክሯል (ማር. 12፡36)።  ስለዚህ የአዲስ ኪዳን ጻሐፊዎች ብሉይ ኪጓንን የእግዚአብሔር መንፈስ ያረፈበት (ያለበት) አድርገው ማየታቸው ግልጽ ነው ደሞም መጽሐፍ ቅዱስ የራሱ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ለማረጋገጥ የሥላሴ አንዱ አካል የሆነው መንፈስ ቅዱስ ከጸሐፊዎቹ ጋር አብሮ እንዲሠራ እርግጠኛ ነው ይናገራሉ። አዲስ ኪዳንም በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ የተጻፈ መህኑን ለማረጋገጥ ትንሽ ያስቸግራል፤ ምክንያቱም አዲስ ኪጻን የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን የሚናገሩ የአዲስ ኪዳን ጥቅሶች ጥቂት ስለሆኑ ነው። ነገር ን ሙሉው አዲስ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ ጸሐፊዎችን በሚጣጠርበት አሠራሩ በመጠቀም ያላገኘው የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ለማመን በቂ ማረጋገጫ እለ። ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ተለይቶ ከሄደ በኋላ፥ መንፈስ ቅዱስ ከሚያደርጋቸው ተግባራት አንዱ እርሱ ያስተማራቸውን ነገሮች ማስታወስ እንደሚሆን ኢየሱስ የገባውን ተስፋ ወደፊት እንመለከታለን ( ዮሐ 14፡26)። ይህ

መንፈስ ቅዱስ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንዲጽፉ በመምራት የሰጠው አገልግሎት Read More »

የእግዚአብሔርን ሕዝብ ይመሩ ዘንድ መሪዎችን ብቁ በማድረግ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት

ጥያቄ፡- ሀ) በቤተ ክርስቲያን መሪ ሆኖ ማገልገል በጣም ከባድ የሚሆነው ለምንድን ነው? ለ) የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እጅግ የቀረበ ግንኙነት እንደሚያስፈልጋቸው ይህ ምን ያሳየናል?  ምናልባት በምድር ላይ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ከመምራት የበለጠ እጅግ እስቸጋሪ ተግባር አይኖርም። ጳውሎስ ለወንጌል ብሉ ከተቀበላቸው መከራዎች ሁሉ በላይ ለአብያተ ክርስቲያናት ያለበት ኃላፊነት በጣም አስቸጋሪ እንደነበር ተናግሯል (2ኛ ቆር. 11፡23-29 ተመልከት)። የእግዚአብሔርን ሕዝብ የመምራት ኃላፊነታቸውን በቀላሉ የሚያዩ በርካታ መሪዎች አሉ። ሥልጣናቸውን ለራሳቸው ጥቅም ይገለገሉበታል። ከሕዝቡ ገንዘብ ይወስዱና ትላልቅ ቤቶችን ለራሳቸው ይሠራሉ። በሚገባ ለመምራትና ለእግዚአብሔር መንጋ መልካም እረኛ መሆን ግን እጅግ ከባድ ሥራ ነው። ያለ መንፈስ ቅዱስ እርዳታ ይህንን ሥራ (ተግባር) ማከናወን የማይቻል ነው።  ትናንት እንዳነበብነው መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ዘመን በሥራ የተጠመደ ነበር። በብሉይ ኪዳን ታሪክ ተቀዳሚው ትኩረት የተሰጠው እርሱ ባይሆንም ሕይወትን በመፍጠርና በማቆየት ሥራ ምን ያህል ተካፋይ እንደሆነ ተመልክተናል። አንዳንድ ሰዎች ለእግዚአብሔር አንድ ተግባርን እንዲፈጽሙ ልዩ ችሎታዎችን በመስጠት ተሳታፊ ነበር። በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረው የመንፈስ ቅዱስ ዋና ተግባር ሕዝቡን በሚገባ ይመሩ ዘንድ መሪዎችን ብቁ ማድረግ ነበር።  ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት። ዘፍ 41፡38-40፤ ዘኁል. 11፡16-18፥ 24-29፤ 27፡18-19፤ ዘዳ 34፡9፤ መሳፍ 3፡9-10፤ 6፡34፤ 11፡29፤ 13፡24-25፤ 14፡6፤ 1ኛ ሳሙ. 10፡9-10፤ 11፡6፤ 16፡13፤ 19፡20-23፤ ዳን 4፡8፤ 5፡11-14 2ኛ ነገ 2፡9-14። ሀ) የእግዚአብሔር መንፈስ በላያቸው ላይ እንደነበር የተነገረላቸውን የተለያዩ ሰዎች ዘርዝር። ለ) መንፈስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር ይሠሩ ዘንድ እነኚህን ሰዎች ምን እንዳስቻላቸው ግለጽ?  መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ዘመንና እጅግ በብዛት የተጠቀሰበት ሁኔታ መሪዎች ለእግዚአብሔር ክብርን የሚያመጣ ተግባር ይፈጽሙ ዘንድ ብቁ ማድረጉ ነው። ዮሴፍ የነበረው ህልሞችን የመተርጐም ጥበብ በውስጡ ካለው የእግዚአብሔር መንፈስ ጋር የተያያዘ ነበር። መንፈስ ቅዱስ በመሪዎች ላይ የመውረዱ ጉዳይ በቅድሚያ የታየው በዘኁል. 1 ላይ ነበር። እስራኤላውያን በምድረ በዳ በነበሩበት ጊዜ እግዚአብሔር በሚያስደንቅ ተአምራት ህልውናውን ቢያሳያቸውም ያላማቋረጥ በእርሱ ላይ ዐመፁ። ∫አንድ ቀን እግዚአብሔር እየመጎባቸው ከነበረው ከመና ይልቅ ሌላ ሥጋን ይሰጣቸው ዘንድ ሙሴን ጠየቁት። ሙሴ እጅግ ከመናደዱ የተነሣ መሪ መሆኑን ለመተው ፈለገ፤ እንዲያውም እግዚአብሔር እንዲገድለው ጠየቀ። የእግዚአብሔር መልስ ምን ነበር? እግዚእብሔር ለሙሴ አመራር እገዛ እንዲያደርጉ 70 ሽማግሌዎችን ለየ። እግዚአብሔር ለሙሴ ሲናገር በእንተ ላይ ያደረግሁትን ይህን መንፈስ በ70 ዎቹም ላይ እደርጋለሁ። ስለዚህ የሕዝቡን ሸክም ለብቻህ አትከምም አለው። እነዚህ 70 ሰዎች የእግዚአብሔር መንፈስ እንዳለባቸው ማረጋገማው ምን ነበር? የእግዚአብሔርን መንፈስ እንደተቀበሉ ትንቢት ተናገሩ። ግን አንድ ጊዜ ብቻ ተናገሩ እንጂ ከዚያ በኋላ አልደገሙትም። መንፈስ ቅዱስ የተሰጣቸው ነቢያት እንዲሆኑ አልነበረም። ለሕዝቡ የእግዚአብሔር አፈ ጉባኤ ሆኖ የሚናገር ሙሴ ነበር። ነገር ግን እነዚህ 70 ሰዎች በእግዚአብሔር እንደተመረጡና ላመሪነታቸው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንደተሞሉ ለሕዝቡ ለማሳየት የመተንበይ ችሎታ እግዚአብሔር ለአጭር ጊዜ ሰጣቸው። መንፈስ ቅዱስ ከእነርሱ ጋር በመቆየት ይመሩ ዘንድ እገዛቸው እንጂ ከእነርሱ ጋር ለመሆኑ ማረጋገጥ ድጋሚ ትንቢት እንዲናገሩ አላደረገም።  የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ከ70 ዎቹ ጋር ባልነበሩት በሁለቱም ሰዎች ላይ መርዶ እንደ ነበር መመልከት እስደናቂ ነው (ዘኁል. 11፡26)። እግዚአብሔር ይህን ለምን እንዳደረገ አናውቅም። ይህን ያደረገው ምናልባት የእግዚአብሔር መንፈስ በሰው ቁጥጥር ሥር የሚሆንና እንዴት እንደሚሠራ የሚወስንለት እንዳልሆነ ለማሳየት ይሆናል። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ለፈለገው ሁሉ በፈለገው ጊዜ የመስጠት መብቱ ሁልጊዜ እንደተጠበቀ ነው። የሙሴ ምላሽ ግን ሁላችንም ልናስታውሰው የተገባ ነው። የሙሴ ረዳት የነበረው ኢያሱ ሙሴ የእግዚአብሔርን መንፈስ እንዲቆጣጠር ፈለገ። ኢያሱ ቀናተኛ ነበር፤ ሙሴ ግን ኃይሉን ለመከላከል እልቃጣም። የእግዚአብሔር ሰዎች በሙሉ መንፈስ ቅዱስን ቢለማመዱና ለመተንበይ ቢችሉ ምኞቱ እንደሆነ ለኢያሱ ነገረው። ስሉዓላዊነቱ መንፈሱን እንደ ፈቃዱ የሚያድል እግዚአብሔር ስለሆነ፥ ሙሴ እግዚአብሔርን መቆጣጠር የተገባው አልነበረም። 16ኛ ጥያቄ፡- ብዙ ክርስቲያን መሪዎች ሌሎችን ሰዎች ከእነርሱ በተሻለ መንገድ እግዚአብሔር ሲጠቀምባቸው ሲያዩ ያላቸው አመለካከት ሙሴ ከነበረው በጣም የሚለየው እንዴት ነው?  የብሉይ ኪዳን ታሪክ እንደሚናገረው (በግልጽ እንዳስቀመጠው) ይህ መሪዎችን ብቁ የማድረግ ተግባር ሊቀጥል እንመለከታለን። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ለሁላም መሪዎች የተሰጠ አልነበረም። ኢያሱ ከሙሴ የተላለፈበት የጥበብ መንፈስ እንደነበረው እናነባለን። መንፈስ ቅዱስን የማስተላላፍ ተግባር በሙሴ የግል ውሳኔ የሆነ ቢመስልም እግዚአብሔር ለሙሴ አስቀድሞ እርሱን የሚተካው መሪ ኢያሱ እንደሚሆን ነግሮት ነበር (ዘጻ 1፡38)። ኢያሱ በእግዚአብሔር የተመረጠ መሪ መሆኑን ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ለማሳየት ሙሴ በኢያሱ ላይ እጆቹን በመጫን በሾመው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከሙሴ ወደ ኢያሱ በግልጽ አለፈ።  ጥያቄ፡– መሳ. 13–16 አንብብ። መንፈስ ቅዱስ የተጠቀሰባቸውን የተለያዩ ጊዜያትና በሳምሶን ሕይወት ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ምን ምን መማር እንደምትችል ዘርዝር።  በመሳፍንት ዘመን የነበሩ መሪዎች መሳፍንት በመባል የሚታወቁ ነበሩ። እነዚህ በመሠረቱ ወታደራዊ መሪዎች ሲሆኑ ለእግዚአብሔር ሕዝብ ጊዜያዊ አርነትን እንዲያስገኙ በእግዚአብሔር የሚሾሙ ነበሩ። ብዙዎቹ መንፈስ ቅዱስ እንደወረደባቸው ይነገራል። ከዋና ዋናዎቹ አትናጐልቶ ጌዴዎን ዮፍታሔና ሳምሶን ይገኙበታል። መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ዘመን ስለ ሠራው ሥራ ታላቅ ምሳሌ የሚሆን መስፍን ሳምሶን ነበር። እግዚአብሔር ሳምሶንን የእስራኤል መሪ እድርጐ የመረጠው በእናቱ ማኅፀን ሳለ ነበር። ለእግዚአብሔር አገልግሎት ለመለየቱ ውጫዊ ምልክት (መለያ) ይሆን ዘንድ የሚያሰክር መጠጥ እንዳይጠጣ፥ በድን እንዳይነካና ፀጉሩን እንዳይቆረጥ እግዚአብሔር እዝዞ ነበር። ወጣቶች ሳለን እንደተነገረን የጌታ መንፈስ ሳምሶንን ያነቃቃው ጀመረ (መሳ. 23፡25)። መንፈስ ቅዱስ በሳምሶን ላይ መሆኑ ኲመንፈሳዊ ሕይወቱ ጋር ምንም ቀንኙነት እልነበረውም። የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በግልጽ ጥሶ ከአሕዛብ ሌት አገባ። ሴተኛ አዳሪዎች ቤት ይሄድ ነበር። ሳምሶን የተገባለትን ቃል ኪዳን እንኳ ጥሶ በድን አንበሳ ነክቷል። ወይን ጠጅም ጠጥቷል። ነገር ግን በተዴጋጋሚ የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ላይ በኃይል እንደወረደ እናነባለን (መሳ. 14፡6፥ 19፣ 5፡14)። በእርግጥ ሳምሶን ከእግዚአብሔር እጅግ በመራቁና የመጨረሻውን ቃል ኪዳን ጥሶ ፀጉሩን በመላቱ መንፈስ ቅዱስ ተላየው። ይህ ሁሉ ሲሆን ሳምሶን እግዚአብሔር እንደተወው አላወቀም ነበር (መሳ. 16፡20)። ከዚህ የምንመለከተው በብሉይ ኪዳን ዘመን አንድ መሪ ልዩ የሆነ ተግባር መፈጸም እንዲችል መንፈስ ቅዱስ ይወርድበት እንደነበር ነው። ሆኖም ይህ የተለየ ተግባር ሲፈጸም መንፈስ ቅዱስ ከሰውዬው ተለይቶ ይሄድ ነበር። ሳምሶን እግዚአብሔር የሚፈልገውን ይፈጽም ዘንድ መንፈስ ቅዱስ በተደጋጋሚ ተሰጥቶት ነበር። ሳምሶን ካለመታዘዝ ይልቅ እግዚአብሔርን በመታዘዝ ቢኖር ኖሮ ለእግዚአብሔር ምን ባደረገ ነበር!  መንፈስ ቅዱስ በውስጡ መንፈሳዊነት በሌለው ሰው እንኳ እንደሚጠቀም ሳምሶን ጥሩ ምሳሌ ነው። ይህን የሚያደርገው የእግዚአብሔር መንፈስ ሰዎች በፈለጉት መንገድ የሚሄድ ሳይሆን በአንድ ሰው ሕይወት ወይም አገልግሎት ውስጥ አንድ ታላቅ ነገር ሲፈጸም ኃይሉ የመንፈስ ቅዱስ እንጂ የዚያ ሰው እንዳልሆነ ለማሳየት ነው። ሆኖም ግን ብዙውን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ሥጋዊ ክርስቲያንን ኃይልን በሚገልጥ መንገድ አይጠቀምም።  ጥያቄ፡- ህ) ሰዎች ለእግዚአብሔር በማይኖሩበት ጊዜ እንኳ መንፈስ ቅዱስ እነርሱን በኃይል መጠቀሙን እንዴት ትመለከታለህ? ለ) በመጨረሻ በእነዚህ ሰዎች ላይ ምን ይሆናል? ሐ) ከሳምሶን ሕይወት ምን ማስጠንቀቂያ መውሰድ ይገባናል?  በነገሥታት የመጀመሪያ ዓመታትም መንፈስ ቅዱስ ለአመራር በተመረጡ በአንዳንዶች ላይ ይወርድ እንደነበር ተጽፏ። ሳኦል ንጉሥ ይሆን ዘንድ በሳሙኤል ከተቀባ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ወረደበት። አዲስ ንጉሥ በእስራኤል በሚነግሥስት ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ ህልውና በእርሱ ላይ የሚረጋገጠው በተለያዩ መንገዶች ነበር። በሙሴ ዘመን የነበሩት 70 ዎቹ ሽማግሌዎች መንፈስ ቅዱስ በወረደባቸው ጊዜ ትንቢትን እንደተናገሩ ሳኦልም መንፈስ ቅዱስ በወረደበት ጊዜ ትንቢት ተናገረ። ነገር ግን በሳኦል ላይ ሌላም ለውጥ ታየ («እንደ ሌላም ሰው ሆነህ ትላወጣለህ» 1ኛ ሳሙ. 10፡6)። ሳኦል ድፍረትና ጠላቶችን በጦር ሜዳ የሚያሸንፍበት ኃይል ተሰጠው። ሳኦል በተላይ ለጦርነት በሚዘጋጅበት ጊዜ በተደጋጋሚ መንፈስ ቅዱስ ይወርድበት እንደነበር እናነባለን (1ኛ ሳሙ. 11፡6)። ነገር ቀን ሳኦል ኃጢአትን በሠራና እግዚአብሔርም የእስራኤል ንጉሥ እንዳይሆን በናቀው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ተወሰደበት 1ኛ ሳሙ. 15፡10፥22-23)። መንፈስ ቅዱስ

የእግዚአብሔርን ሕዝብ ይመሩ ዘንድ መሪዎችን ብቁ በማድረግ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት Read More »

መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን

ንጋቷ መንፈስ ቅዱስ በሕይወቷ እንዲሠራ የምትፈልግ ንቁ ክርስቲያን ነበረች። እግዚአብሔር እንዲጠቀምባት ትፈልግ ስለነበር ከእግዚአብሔር ጋር ያላትን ግንኙነት የሚያበላሽ ማንኛውም ዓይነት ኃጢአት በሕይወቷ እንዳይኖር ትጠነቀቅ ነበር። ነገር ግን አንድ ቀን በፍትወት ኃጢአት ወደቀች፤ መንፈስ ቅዱስ ወቀሳትና ወደ መዝሙር 51፡11 በመሄድ ዳዊት መንፈስ ቅዱስ ከሕይወቱ እንዳይወሰድበት እግዚአብሔርን የለመነበትን ጸሎት አነበበች። እርሷም እግዚአብሔር መንፈሱን እንዳይወስድባት ለመነች። የውይይት ጥያቄ፦ ንጋቷ ይህን ያደረገችው በቅንነት ሲሆን ጸሎቷም እጅግ የተቀጣጠለና ጽኑ ነበር። ነገር ግን ጸሎቷ ትክክለኛ ነበር? ይህ ጸሎት እንደ ዳዊት ላሉ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትክክል ነበር። ነገር ግን ከኢየሱስ ሞት በኋላ ለሚኖሩ ክርስቲያኖች ሕይወት መንፈስ ቅዱስ ሊወሰድ እንደሚችል መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራልን? ከዚህ በታች መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ከሠራባቸው መንገዶች ጋር ተመሳሳይ የሆኑ በርካታ አገልግሎቶች በአዲስ ኪዳን ቢኖሩም ያሉትን ልዩነቶችም እንዳሉ እንመለከታለን። አሮጌው ኪዳን ከአዲስ ኪዳን የተለየ ነው። በብሉይ ኪዳን የነበረው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በአዲስ ኪዳን ካለው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ የተለየ ነው። በዘመናት ሁሉ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ቃልና ዕቅዶች በመረዳት ማመንና መጸለይ ከፈለግን በሁለቱ ኪዳኖች መካከል ያለውን ተመሳሳይነትና ልዩነት ማስተዋል አለብን። የልዩነቶቹን ማዕከላዊ ስፍራ የያዘው የመንፈስ ቅዱስ ሥራና አገልግሎት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን መንፈስ ቅዱስ በጰንጠቆስጤ ዕለት ሲወርድ በመንፈስ ቅዱስና በአማኞች መካከል በሚኖረው ግንኙነት አንድ ታላቅ ለውጥ ተከናወነ። የአዲስ ኪዳን ትምህርት እንደሚያመለክተው ከጰንጠቆስጤ ዕለት ጀምሮ አንድ ክርስቲያን ኃጢአት ባደረገ ጊዜ ሁሉ መንፈስ ቅዱስ ትቶት አይሄድም የሚል ይመስላል። እግዚአብሔር መሐሪና ታጋሽ ስለሆነ ሥነ-መለኮታዊ ግድፈታችንን አይቆጥርብንም። በሥነ-መለኮታዊ ይዘቱ ፍጹም ያልሆነ ነገር ብንነግረውም እንኳ ማዳመጡን አይተውም። ባይሆንማ ኖሮ በመረዳታችን መቶ በመቶ ትክክል የሆንን ስለሌለን እግዚአብሔር ከጸሎታችን የትኛውንም አይሰማም ነበር። ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል የሚለውን በትክክል ብንረዳና ለእምነታችን መሠረት ብናደርገው ምንኛ የተሻለ ይሆናል። የእግዚአብሔርን ቃል ለማጥናትና የሚያስተምራቸውን ትምህርቶች ለመረዳት ጊዜ ባለመስጠታችን፤ አንድ ሰው «ጓደኛዬ ነው» እያለ እየተመካብን ስማችንን ለማወቅ እንኳ ጥረት ሳያደርግ ሲቀር የሚሰማንን ዓይነት ስሜት እግዚአብሔር ይሰማዋል። የዚህ የጥናት መምሪያ መጽሐፍ አንዱ ዓላማ መንፈስ ቅዱስን የበለጠ እንድናውቀው ማስቻል ነው። የውይይት ጥያቄ፦ ኤር. 31፡31-34፤ ኢዩ. 2፡28-32 አንብብ። የሚያድግ መገለጥ (Progressive Revelation) የእግዚአብሔርን ቃል በምናጠናበት ጊዜ ልናስታውሳቸው የሚገቡ ሁለት አስፈላጊ ነገሮች አሉ። በመጀመሪያ የእግዚአብሔር ፍጹም እውነት በአንድ ጊዜ የተሰጠ ሳይሆን በጊዜ ሂደት ቀስ በቀስ እየተገለጠ የመጣ እንደነበር ማስታወስ ይገባናል። ይህ በሥነ-መለኮት ትምህርት ቋንቋ የሚያድግ መገለጥ ይባላል። ይህም እግዚአብሔር በዘመናት ውስጥ ፈቃዱን ደረጃ በደረጃ መግለጡን ያሳያል። ለምሳሌ፦ አንድ ሳይንቲስት የአንድ ዓመት ሴት ልጁን ለማስተማር ጀመረ እንበል፦ «ልጄ ሆይ፥ ዛሬ ስለ አቶሚክ ኃይል የሚታወቁ እውነቶችን በሙሉ እነግርሻለሁ» በማለት የተማራቸውንና ለብዙ ዓመታት ያጠናቸውን ነገሮች በሙሉ ሊነግራት ቢሞክር የሚገባት ይመስላችኋል? አይገባትም። እንደ ልጅ ልትረዳው የምትችለው የተወሰነ የእውቀት ገደብ አለ። ነገር ግን በዓመታት ውስጥ እያደገች ስትሄድ ስለ ሳይንስና ስለ አቶሚክ ኃይል ትንሽ በትንሽ ቢያስተምራት አባቷ የሚለውን ነገር ቀስ በቀስ መረዳት ትችላለች። ይህ ምሳሌ እግዚአብሔር ሰዎችን እንዴት እንደሚያስተምር ይገልጻል። እግዚአብሔር ለሙሴም ሆነ ለእስራኤላውያን ስለ ራሱም ሆነ ስለ ፈቃዱ ያለውን እውነት በሙሉ በአንድ ጊዜ አልነገራቸውም። ይህን ለማድረግ ሞክሮ ቢሆን ኖሮ አይገባቸውም ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ፈቃዱን በዘመናት ውስጥ ደረጃ በደረጃ ገለጠላቸው። በእርግጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለሰው ልጅ ያለውን ሁሉ ገልጦ እስከሚጨርስ እግዚአብሔር ከ1500 ዓመታት በላይ ወስዶበታል። በዚህ ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር ሰዎች ስለ እርሱ ያላቸው እውቀት ደረጃ በደረጃ እንዲጨምር አድርጎላቸዋል። ይህ ሐቅ መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እንደምንረዳ በብዙ አቅጣጫ ያሳያል። በመጀመሪያ በብሉይ ኪዳን ሕዝብ ሕይወት ውስጥ ስለነበሩ፥ እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላላገሠጻቸው በኋላ ግን ለእኛ ስሕተት መሆናቸው ስለተነገረን ጉዳዮች እናነባለን። ለምሳሌ በብሉይ ኪዳን የነበሩ ቅዱሳን አብዛኞቹ ከአንድ በላይ ሚስቶችን አግብተው ነበር። ይህ ተግባር የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዳልሆነ በአዲስ ኪዳን ሰፍሮ ይታያል። ሆኖም ግን እግዚአብሔር የብሉይ ኪዳን ቅዱሳንን ሌሎች ነገሮችን ያስተምራቸው ነበር። ከአንድ በላይ የሆኑ ሚስቶችን የማግባት ልምምድን መቃወም ግን በእነዚህ ትምህርቶቹ ውስጥ አልተካተተም ነበር። እግዚአብሔር ወደ መንፈሳዊ ብስለት ሲያመጣንና ሲያሳድገን የሚያደርገው እንደዚሁ ነው። በተወሰኑ የሕይወታችን ጉዳዮች ደረጃ በደረጃ ይሠራል። በአንድ ጊዜ ፍጹም የሆነ ለውጥን ለማምጣት አይሞክርም። የውይይት ጥያቄ፦ እግዚአብሔር በሕይወታችን ያሉትን ችግሮቻችንን በአንድ ጊዜ ከማስወገድ ይልቅ ረጅም ጊዜ ወስዶ በትዕግሥት ሲያከናውነው የሚያሳዝነን (የሚፈትነን) ለምንድን ነው? በሁለተኛ ደረጃ አንዳንድ ቁልፍ የሆኑ የእምነት አስተምህሮዎች የተገለጡት በጊዜ ሂደት ውስጥ ነው። እግዚአብሔር እውነትን ሁሉ የገለጠው በአንድ ጊዜ ሳይሆን ደረጃ በደረጃ ነው። ይህንን ስለ መንፈስ ቅዱስ ስናጠና እንመለከተዋለን። የሥላሴን ትምህርትና የመንፈስ ቅዱስን ህልውና በሚገባ የምንረዳው እግዚአብሔር በአዲስ ኪዳን የሰጠውን መገለጥ ስንረዳ ብቻ ይሆናል። መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን የነበረውን ሥራ ለመረዳት የአዲስ ኪዳን መገለጥ ያስፈልገናል። በሦስተኛ ደረጃ ልንመለከተው የሚገባን እግዚአብሔር በዘመናት ውስጥ ነገሮችን ያከናወነበትን (የፈጸመበትን) አንዳንድ መንገዶች መለወጡን ነው። በብሉይ ኪዳን ዘመን የሠራበት መንገድ በአዲስ ኪዳን ከሠራበት መንገድ በአንዳንድ ሁኔታዎች ይለያል። ለምሳሌ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር በተቀዳሚ የሠራው በአይሁዳውያን በኩል ነበር። በአዲስ ኪዳን ደግሞ እግዚአብሔር አንዳችም የዘር ልዩነት ሳያደርግ ከሕዝቡ ሁሉ ጋር በእኩልነት ይሠራል። በብሉይ ኪዳን ባለን መረዳት ላይ ብቻ ብንመሠረት በትውልዳችን አሕዛብ ስለሆንን ማናችንም የእግዚአብሔር ሕዝብ አካል መሆን አንችልም ነበር። ይህ እውነት ለመንፈስ ቅዱስ ያለንን መረዳትም ይነካል። በብሉይ ኪዳን ዘመን እግዚአብሔር መንፈሱን ለተወሰኑ ሰዎች ለተወሰነ አገልግሎት ይሰጥና በኋላ ላይ መልሶ ይወስድ ነበር። ዳዊት መንፈስ ቅዱስ እንዳይወሰድበት የለመነው ለዚህ ነበር (መዝ. 51፡11)። በአዲስ ኪዳን ግን የመንፈስ ቅዱስ ህልውና ለክርስቲያኖች ሁሉ በዋስትና ተሰጥቷል፤ ለዚህም ነው መንፈስ ቅዱስ ከእውነተኛ ክርስቲያኖች የሚወሰድበት ወቅት ስለመኖሩ ምንም መረጃ የሌለን። ይህ ከሆነ የብሉይ ኪዳን የመንፈስ ቅዱስ አሠራር ከብሉይ ኪዳን ዘመን ወዲህ እስከ ዛሬ ስለተለወጠ እግዚአብሔር መንፈሱን እንዳይወስድብን እንደ ዳዊት መጸለይ አያስፈልገንም። መጽሐፍ ቅዱስን ለመተርጎም ልንጠቀምባቸው የሚገቡ መመሪያዎች የውይይት ጥያቄ፦ መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት ልናስተውለው የሚገባ ሁለተኛው ዋና እውነት ያንን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እግዚአብሔር መጀመሪያ ለሕዝቡ በሰጠበት ወቅት የነበረውን ልዩ ሁኔታ ማሰብ ነው። ለምሳሌ በኤርምያስ 31 ላይ እግዚአብሔር የቀድሞውን ኪዳን አዲስ ከሚመጣው ኪዳን ጋር ያነፃፅራል። ስለዚህ አንድን ጥቅስ በምንመለከትበት ወቅት ያ ጥቅስ ለብሉይ ኪዳን ብቻ የተሰጠና በአዲስ ኪዳን ግን የተለየ እንደሆነ ወይም ለሁለቱም ኪዳኖች እኩል ይሠራ እንደሆነ መመልከት ተገቢ ነው። በኢዩኤል 2 ላይ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን የሚጠቀምበት መንገድ እንደሚለወጥ ተጽፏል። መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠው ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ለእግዚአብሔር ሕዝቦች በሙሉ ይሆናል። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ከነበረው ሚና በተለየ መልክ በአዲስ ኪዳን እንደሚያከናውን መጠበቅ እንችላለን። በክርስቲያኖች መካከል ከፍተኛ የመረዳት ልዩነት ከሚታዩባቸው መጻሕፍት አንዱ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ነው። በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ አንዳንድ ጥቅሶች ብቻቸውን ካየናቸው ሌላ ትርጉም የሚሰጡና ትክክለኛ ትርጉማቸውን ለማግኘት በመልእክቶች ብርሃን ልናያቸው የሚገቡ አሉ። የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የሽግግር መጽሐፍ ነው። ከብሉይ ኪዳን ወደ አዲስ ኪዳን የተደረገውን ሽግግር ያሳየናል። አንድ አዲስ መንግሥት ወደ ሥልጣን ሲመጣ አዲሱ የመንግሥት መመሪያ በግልፅ እስኪሰፍር ድረስ ጊዜ ይወስዳል። አንዳንድ ጊዜ አዲስ ሕገ-መንግሥት እስኪጻፍ ድረስ ጊዜያዊ መመሪያዎች ይወጣሉ። በተመሳሳይ መንገድ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን ዘመን የሚሆነውን ፖሊሲ (መመሪያ) በሙላት እስኪገልጥ ድረስ የነበረውን የሽግግር ሂደት በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እናያለን። ስለዚህ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን በመልእክቶች ውስጥ ባሉ ግልጽ ትምህርቶች ብርሃን ልንረዳው ያስፈልጋል። የውይይት ጥያቄ፦ የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከቱ፦ ማቴ. 5፡21–48። እግዚአብሔር በአንድ ዘመን ከሰጠው መገለጥ በተከታዩ ዘመን የሚሰጠው የሚለየው በምን መንገድ ነው? እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን በተመለከተ በዚህ መንገድ ያደረገውን ለውጥ ለመረዳት ከብሉይ ኪዳን ዘመን ጀምረን ኢየሱስ በወንጌላት ውስጥ

መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን Read More »

መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ አምላክ መሆኑን ያሳየናልን?

መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ሥላሴ እንደሆነ በአንድ አምላክ ውስጥ ሦስት አካላት መኖራቸውን እንደሚያስተምር ተመልክተናል። እውን መጽሐፍ ቅዱስ የመንፈስ ቅዱስን አምላክነት በእርግጥ ያስተምራል?  ጥያቄ፡– የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት፡- መዝ 139፡7-10፤ ሉቃስ 35 ዮሐ 14፡26፤ 16፡3የሐዋ. 5፡3-4 ሮሜ 8፡2፤ 5፡30፣ ዕብ 9፡14። መንፈስ ቅዱስ አምላክ መሆኑን እነዚህ ጥቅሶች እንዴት ያሳዩናል?  መንፈስ ቅዱስ መለኮት ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ በርካታ ማረጋገጫዎች አሉት።  1. መንፈስ ቅዱስ መለኮት መሆኑን የሚያመለክቱ ስሞች አሉት።  ለምሳሌ «የእግዚአብሔር መንፈስ» ተብሎ ተጠርቷል (ታብሷል) (2ኛ ቆር. 3፡3)። እንዲያውም «እግዚአብሔር» እንኳ ተብሎ ተጠርቷል። ሐናንያ መሬቱን ሽጦ ከሚስቱ ጋር ተስማምቶ ለቤተ ክርስቲያን ሊሰጥ ስላመጣው ገንዘብ በዋሹ ጊዜ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስን እንደዋሹ በዚህም እግዚአብሔርን መዋሸታቸውን ያለአንዳች ልዩነት ተናግሯል (የሐዋ. 5፡3 4)። «የሕይወት መንፈስ» (ሮሜ 8፡2) ተብሎም ተጠርቷል። ሕይወት የሚሰጥ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ተቀዳሚ ስሙ የሆነው «ቅዱስ» የሚለው ቃለ እግዚአብሔር ብቻ ልዩ መሆኑንና ፍጹም ንጹሕናውን ያመለክታል (ያስረግጣል)። ይህም እውነት የሚሆነው ለእግዚአብሔር(ለእርሱ ብቻ ነው)። 2. መንፈስ ቅዱስ አምላክ መሆኑን የሚያሳዩ ባሕርያት አሉት።  ሀ. መንፈስ ቅዱስ «የዘላለም» መንፈስ ነው «ዕብ. 9፡14)። እንደ እግዚአብሔር አብና እንደ እግዚአብሔር ወልድ መንፈስ ቅዱስ ከዘላለም ነበር። መንፈስ ቅዱስ ያልነበረበት ጊዜ አልነበረም። ደግሞም እርሱ እልተፈጠረም። ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሳይለወጥ ይኖራል። ይህ የሚባለው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው። እግዚአብሔር በስተቀር ነገሮች ሁሉ ጅማሬ አላቸው። ዘላለማዊ አይደሉም።  ለ. መንፈስ ቅዱስ በአንድ ጊዜ በሁሉም ስፍራ ይገኛል (መዝ. 139. 7 10)። ከሌሎች ፍጥረታት በተለየ መልኩ እግዚአብሔር በአንድ ጊዜ በእንድ ቦታ ብቻ የሚወሰን አይደለም። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስንም ጨምሮ በእኩልነት በአንድ ጊዜ በሁሉም ስፍራ ይገኛል። በኢትዮጵያም ሆነ በእንግሊዝ በአንድ ጊዜ ይገኛል። በአንድ ጊዜ በሰማይም በምድርም ይገኛል። መንፈስ ቅዱስ በሁሉም ስፍራ ይገኛል። የምናውቃቸው ነገሮች በሙሉ በአንድ ጊዜ የሚገኙት በአንድ ስፍራ ብቻ ነው። በመሆኑም ይህንን እውነት ለመረዳት እንቸገራለን።  ሐ. መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን አሳብ በሙላት ያውቃል (1ኛ ቆሮ. 2፡10-10። ሁሉን ነገር ያውቃል። ልክ እንደ እግዚአብሔር አብ ምንም ነገር መማር አያስፈልገውም። እውቀቱ ሙሉና ፍጹም ነው። ሁሉን ነገር የሚያውቅ እግዚአብሔር ብቻ ስለሆነና መንፈስ ቅዱስ ደግሞ የእግዚአብሔርን አሳብ በሙሉ ማወቁ ከእግዚአብሔር አብ የተለየ አካል መሆኑን ብቻ ሳይሆን አምላክ መሆኑንም ያሳያል።  መ. ኢየሱላ «እውነት» እንደተባለ መንፈስ ቅዱስም «እውነት» ተብሎ ተጠርቷል (ዮሐ 14፡6፤ 1ኛ ዮሐ 5፡6)። ዮሐንስ በዚህ ቦታ የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ ወይም ኢየሱስ እውነት እንደሚያውቁ ወይም እውነትን እንደሚናገሩ አይደለም። ለነገሩ ይህም እውነት ነው። ዮሐንስ የሚናገረው ግን ኢየሱስም መንፈስ ቅዱስም እውነት እንደሆኑ ነው። በኑባሬአቸው እውነት ሁለንተናቸው ትክክልና ልክ የሆኑ ነገሮች ሁሉ የሚመነጩት ከእነርሱ ውስጥ ነው።  3. መንፈስ ቅዱስ የመለኮት ተግባራትን ይፈጽማል።  ሀ. መንፈስ ቅዱስ በፍጥረት ሥራ ውስጥ ተካፍሏል (ዘፍ 1፡2፤ መዝ. [33]፡6፤ [14]፡30)። እግዚአብሔር አብ የፍጥረትን ሥራ እንደሚያቅድ መሐንዲስ እግዚአብሔር ወልድ ደግሞ ሥራውን በኃላፊነት ወስዶ እንደሚሠራ ተቋራጭ ሲሆኑ፥ ዋናው ሠራተኛ ግን መንፈስ ቅዱስ ነበር።  ለ. የእግዚአብሔርን ቃል ሲጽፉ ሰዎችን የመራቸው መንፈስ ቅዱስ የመጽሐፍ ቅዱስ ደራሲ ነው (2ኛ ጴጥ. 1፡21፤ 2ኛ ጢሞ. 3፡16)። መንፈስ ቅዱስ የጥንት ሰዎች ምን መጻፍ እንዳለባቸው እና እንደሌለባቸው ቃል በቃል አልነገራቸውም። ነገር ግን የጥንት ሰዎች በሚጽፉበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ የሚጽፉትን ቃላት እንኳ በመቆጣጠር ጽሑፋቸው ሲጠናቀቅ እያንዳንዱ የጻፉት ነገር የእግዚአብሔር ቃል ተብሎ እንዲጠራ አድርጓል። ለዚህም ነው ኢየሱስ በእርግጠኛነት የዓለም ፍጻሜ እስኪሆን ድረስ አንድም ነቁጥ (ነጥብ) እንኳ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሊወድቅ እንደማይችል የተናገረው (ማቴ. 5፡17-18)።  ሐ. መንፈስ ቅዱስ ሕይወትን ይሰጣል (ኢዮብ 33፡4፤ ሮሜ 8፡2፥10። ይህ ሁለት እውነታዎችን ይዟል። በመጀመሪያ ደረጃ ላሥጋዊ ሕይወት እንኳ ምንጩ መንፈስ ቅዱስ ነው። በሴት ማኅፀን ውስጥ ፅንሱን ሕይወት የሚያስጀምረው መንፈስ ቅዱላ ነው። የራሱን ባሕርይ፥ ተሰጥኦዎችና ችሎታዎች በመስጠት የማንኛውንም ሰው እድገት የሚቆጣጠር እርሱ ነው። በሁለተኛ ደረጃ መንፈሳዊ ሕይወትንም የሚሰጥ እርሱ ነው። በኃጢአት የሞተን ነፍስ የሚያቀናና ለእግዚአብሔር ሕያው የሚያደርገው እርሱ ነው። ለመንፈሳዊ ነገር እውር ለሆነ ሰው የመንፈስ ዓይኖቹን የሚከፍት እርሱ ነው።  መ. ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል እንዲወለድ ያደረገው መንፈስ ቅዱስ ነው (ሉቃስ 1፡35)። ይህ እንዴት እንደሆነ አሁን ላናውቅ እንችላለን። ዘላለማዊ የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ሥጋ እንዴት እንዴላበሰ እንደ ሕናን ለመወለድ በማኅፀን እንዴት እንደተዋሰበ (ማኅፀን እንዴት እንደበቃው) ምስጢር ነው። ይህን ሁሉ ያከናወነው መንፈስ ቅዱስ ነበር።  ጥያቄ፡- ሀ) መንፈስ ቅዱስ መለኮት ስለመሆኑ የተሰጡ ማረጋገጫዎችን እንደገና ተመልክት። ለ) መንፈስ ቅዱስ በልብህ እንደሚኖር መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። (1ኛ ቆሮ. 6፡19 ተመልከት።) በመንፈስ ቅዱስ ባሕርይ እማካኝነት እግዚአብሔር በልብህ የመኖሩን እውነታ ስትመለከት ምን ያህል ትበረታታለህ? ሐ) እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን የጸሎት ጊዜ ወስደህ አመስግነው።  የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያረጋግጥ ለማስረዳት ይህን ያህል ጊዜ መውሰድ እስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ብዙዎቻችን ይህን ክፍል ስናጠና ስለ ሥላሴ እውነታ ጥያቄ አንስተንም፥ ተጠራጥረንም እናውቅምና ምን ያስፈልጋል እንል ይሆናል? እስኪ የሚከተሉትን ምክንያቶች እናስተውል።  በመጀመሪያ፥ በኢትዮጵያ ውስጥ እግዚአብሔር በአካል ሦስት መሆኑን የማይቀበሉና በርካታ ክርስቲያኖችን የሚያስቱ የሃይማኖት ቡድኖች ስላሉ ነው። ብዙ ክርስቲያኖች ስላልተማሩና መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምር ስለማያውቁ በሐሰተኛ አስተማሪዎች አሳብ ይማረካሉ። የሚያሳዝነው ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር የሚያስተምረውን ቆም ብለው የሚጠይቁት አልፎ አልፎ ብቻ መሆኑ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ስለማያጠኑና የብያኔ መሣሪያቸው አድርገው ስለማይጠቀሙበት ለሰው የመከራከሪያ አሳብ ይሸነፋሉ። እርግጥ ነው የሥላሴን እውነት መረዳት እጅግ ከባድ ነው። እግዚአብሔር ከአስተሳሰባችን በላይ ነው። ባይሆንማ ኖሮ እርሱ አምላክ አይሆንም ነበር። እግዚአብሔር ራሱን በአንድነትና በሦስትነት የገላጻውን በማመን ልንደገፍበት ይገባል።  በሁለተኛ ደረጃ ፥ አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ሥራ አገልግሎት እስካልተረዳና ከእያንዳንዱ የሥላሴ አካል ጋር ያለውን ግንኙነት እስካላሳደገ በእምነቱና እግዚአብሔርን በማወቅ ለማደግ አይችልም። ስለ እግዚአብሔር አብና ስለ እግዚአብሔር ወልድ ማሰብ ነገር ግን የመንፈስ ቅዱስንና አካላዊ ህልውናና አገልግሎት ያላመረዳት በመንፈሳዊ ሕይወታችን ልፍስፍስና ውጤት አልባ ያደርገናል በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፥ በእግዚአብሔር አብና በእግዚአብሔር ወልድ መካከል ያለው ግንኙነት።  በክርስቲያኖች መካከል ለዘመናት ሲያከራክር የቆየ በመንፈስ ቅዱስ መለኮትነት ላይ ያተኮረ አንድ የሥነ መለኮት ርእሰ ጉዳይ አለ። ይህም መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር አብና ከእግዚአብሔር ወልድ ጋር ያለው ግንኙነት ነው። መንፈስ ቅዱስ የመጣው ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ ብቻ ነው? ወይስ ከእግዚአብሔር አብና ከእግዚአብሔር ወልድ? ይህ ርእስ በቀድሞዪቱ ቤተ ክርስቲያን እከራካሪ ሆኖ የቆየና በመጨረሻም ቤተ ክርስቲያንን የካቶሊክና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናት በመባል እንዲከፈሉ እድርጓል። ይህ የመከራከሪያ አሳብ በዕለታዊ ሕይወታችን ላይ ብዙ ተጽዕኖ ስለሌለው በዝርዝር ለማጥናት ጊዜ አንወስድም። የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስ የሚወጣው ከእግዚአብሔር አብ ብቻ ነው በማለት ስታስተምር፥ የቀረው የክርስቲያን ኅብረተሰብ ግን መንፈስ ቅዱስ በእኩል ደረጃ ከአብና ከወልድ ይመጣል በማለት ያስተምራሉ (ዮሐ 14፡26፥ 16፡7 ተመልከት)።  የበታችነት ሳይኖር የአንዱ ለሌላው መገዛት  የሥላሴ አካላትን የእርስ በርስ ግንኙነት በጥንቃቄ ስንመለከት በርካታ እውነተች ግልጽ እየሆኑ ይመጣሉ። በመጀመሪያ፥ ግፃዌ መለኮት እያንዳንዳቸው በባሕርይ ሙሉ በሙሉ እኩል ናቸው። ሁሉም ምሉዕ አምላክ ናቸው ኃይላቸው፥ እውቀታቸው፥ ዘላለማዊነታቸው፥ ፍቅራቸው፥ ወዘተ… ሁሉም እኩልና አንድ ዓይነት ነው። አካላዊ ህልውናቸውን በተመለከተ አንዳቸው ከሌላቸው የሚያንሱበት ምንም ሁኔታ የለም።  በሁለተኛ ደረጃ ፥ በግንኙነትና በተግባር ተደጋጋፊነት አለ። እያንዳንዱ የሥላሴ አካል በባሕርይ እኩል ቢሆንም የግንኙነት ሥርዓት እንዳለና ይህም በአንዳንድ መንገዶች እርስ በርስ ያላቸውን ግንኙነቶች ለማሳየት እንጂ የበታችነትን ለማንፀባረቅ እንዳልሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። መጽሐፍ ቅዱስ ሁል ጊዜ የሚያሳየን የመጨረሻው ባለሥልጣን እግዚአብሔር አብ እንደሆነ ነው። ይህንን በበርካታ መንገዶች እናየዋለን። ኢየሱስ የዓለም አዳኝ እንዲሆን የላከው እግዚአብሔር አብ ነው (ዮሐ 3፡16)። ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ዘመን ሁሉ አሳቱን እንደታዘዘ ተናግሯል። ያደረጋቸው ሥራዎች በሙሉ አባቱ እንዲያከናውን

መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ አምላክ መሆኑን ያሳየናልን? Read More »

መንፈስ ቅዱስ፤ ሦስተኛው የሥላሴ አካል

አንድ ቀን በአውቶብስ ማቆሚያ ስፍራ አውቶቡላ ለጠብቅ «ኢየሱስ ብቻ» በሚባለው ሐሰተኛ ትምህርት ውስጥ የሚገኝ አንድ ሰው ወደ እኔ ቀረበ። «በሰማይ ስንት ዙፋን አለ?» የሚል ጥያቄ አቀረበልኝ። በሰማይ ያላው አንድ ዙፋን ብቻ ስለሆነ በአንድ አምላክ ውስጥ ሦስት አካላት ሊኖሩ ፈጽሞ የማይቻል እንደሆነ በጥንቃቄ ሊያረጋግጥልኝ ሞከረ። ከመጽሐፍ ቅዱስ እጅግ ከባድ ትምህርቶች አንዱ የሥላሴ እውነት ማለትም እንደ ክርስቲያን ስም ስት አካል በሚገኝ አንድ አምላክ ማመናችን ነው። ይህ ከሰብዓዊ መረዳታችን በላይ ነው። ላማስረዳትም አስቸጋሪ ነው። ሆኖም ቀን ለአእምሮ የማይቻል በመምሰሉ ነገር ከመረታታችን በፊት ወደ መጽሐፍ ቅዱስ በመሄድ ምን እንደሚል ማረጋገጥ አላበን። መጽሐፍ ቅዱስ የሥላሴን ትርጉም ባይሰጥም እንኳ ለመግለጽ አስቸጋሪ በሆነ መንገድ እግዚአብሔር አንድም ሦስትም እንደሆነ ያስተምረናል።  ጥያቄ፡- ሀ) የሥላሴ ሦስት አካላት እነማን ናቸው? ለ) የሥላሴን ትርጉም በአጭሩ ግለጽ። ሐ) ስለ ሥላሴ አስቀድሞ ሰምቶ ለማያውቅ ክርስቲያን ላልሆነ ሰው ስለ ሥላሴ እንዴት እንደምትገልጽላት በአጭሩ ጻፍ።  መንፈስ ቅዱስ አካል እንዳለውና በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ያላ ኃይል ወይም ግዑዝ አካል እንዳልሆነ ከተረዳን በኋላ ሌላ ጥያቄ ለመጠየቅ እንገደዳለን። መንፈስ ቅዱስ ማን ነው? እንደ መልአክ በእግዚአብሔር የተፈጠረና በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ያለ መንፈስ ነውን? ወይስ ከእግዚአብሔር አብና ከእግዚአብሔር ወልድ ጋር እኩል የሆነ አምላክ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?  የክርስትና ታሪክ ክርስቲያኖች በዘመናት ሁሉ ስም ስት አካላት የተገለጠ አንድ አምላክን እንዳመላኩ ያስተምራል። ይህ ስለ እግዚአብሔር ለራሳችን ለመረዳትም ሆነ ለሌሎች ለመግለጽ እጅግ አስቸጋሪ ከሆኑ ትምህርቶች አንዱ ነው። ልንቀበላቸው የማይገቡ ሁላት የከረሩ አቋሞች አሉ። የመጀመሪያው፥ አንዳንዶች በእግዚአብሔር አንድ መሆን ላይ ብቻ ከሚገባ በላይ በማተኮር ኢየሱስም ሆነ መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር እብ ጋር እኩል አምላክ መሆናቸውን ይክዳሉ። ይህ አመለካከት አንዳንዶቹን በብሉይ ኪዳን ዘመን አንዱ አምላክ ይሖዋ በመባል ይጠራ ነበር እያሉ እንዲያስተምሩ አድርጓቸዋል። ይኸው እንድ አምላክ በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ ተብሏል። በቤተ ክርስቲያን ዘመን ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ተብሏል ይላሉ። በዚህም ስሞች ይቀያየራሉ እንጂ ያለው አንድ አምላክ ብቻ ነው ይላሉ። ሌሎች ደግሞ ኢየሱስና መንፈስ ቅዱስ እንደ እግዚአብሔር አብ አምላክ አይደሉም። ይልቁኑ አነስ ያሉ አማልክት ናቸው ይላሉ። በታላቁ እምላክ የተፈጠሩ ትናንሽ አምላኮች ናቸው። ልናመልካቸው እንችላለን ነገር ግን እንደ ታላቅ አንድ አምላክ ስላልሆኑ ዘላለማዊና ከእርሱ እኩል የሆኑ ናቸው ማለት የለብንም ይላሉ።  ጥያቄ፡- በእግዚአብሔር እንድነት ላይ እጅግ በማተኮር በሥላሴ የማያምኑ በኢትዮጵያ የሚገኙ የእምነት ክፍሎችን ዘርዝር።  በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ሃይማኖታዊ ቡድኖች ወይም ኑፋቄዎች ስለ እግዚአብሔር ከላይ የተመለከትነውን ዓይነት የተሳሳተ አሳብ ያላቸው አሉ። ሙስሊሞች አንድ አምላክ ብቻ እንዳለ አጥብቀው ይናገራሉ። ለመቀበልም ሆነ ለመረዳት ከሚያስቸግራቸው ትምህርቶች አንዱ የሥላሴ ትምህርት ነው። (ይህ ብዙ ጊዜ የሚሆነው ክርስቲያኖች ሥላሴ ስንል ሦን ማለታችን እንደሆነ ለመግለጽ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምር በሚገባ ባለመረዳታችን ነው።) የሐዋርያት እምነት ቤተ ክርስቲያን እንድ አምላክ እንዳለ በተላያዩ የታሪክ ወቅቶችም የተለያዩ ስሞች እንዳሉት ይናገራሉ። የይሖዋ ምስክሮች ኢየሱስ ከእግዚአብሔር የሚያንስ እምላክ እንደሆነ ያስተምራሉ። ራሱን ክርስቲያን አድርጐ የሚቆጥር ነገር ግን ያልሆነ አንድ የሃይማኖት ቡድንን ወይም የሐሰት ትምህርትን ከምንለይባቸው መንገዶች እንዱ ሥላሴን ለማመን ፈቀደኛ አለመሆናቸው ነው።  በሁለተኛ ደረጃ ልናስወግደው የሚገባ ሌላ የከረረ አቋም አለ። እግዚአብሔር እብ፥ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሦስት ፍጹም የተለያዩ አምላኮች ናቸው የሚሉ አስተማሪዎች አሉ። ይህ ሦስት የተለያዩ ሰዎች ቆመው እንደ ማየት ነው። እያንዳንዳቸው የራሳቸው አካል፥ የራሳቸው ፈቃድና የራሳቸው ማንነት አላቸው። በምስት ሰዎች መካከል እንድነት ሊኖር አይችልም። እነዚህ ሰዎች ክርስቲያኖች የላት አማልክትን እግዚአብሔር አብ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ያመልካሉ ይላሉ። በዚህም ክርስቲያኖች ብዙ አማልክትን ከሚያመልኩ ክሂንዱዎች፥ ከቡድሒስቶች ወይም ከዓረማውያን አይላዩም ይላሉ።  ሙስሊሞችና ይሁዲዎች ክርስቲያኖችን ሦስት አምላክ ታመልካላችሁ ብለው ይከሱናል። ስለዚህ ክርስቲያኖች ስለ እግዚአብሔር ምን እንደምናምን ለሙስሊሞችና ለይሁዲዎች መግለጽ እንድንችል ግልጽ መረዳት ያስፈልገናል።  ስለሆነም ክርስቲያኖች የሚያምኑት ምንን ነው? ወይም የተሻለ ጥያቄ የሚሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ሥላሴ ስላሆነው አምላክ ምን ያስተምረናል?  1. ክርስቲያኖች ሦስት የተለያዩ አማልክትን ሳይሆን አንድ አምላክ ብቻ ያምናሉ።  ጥያቄ፡– የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አንብብ። ዘዳ 6፡4 5፤ ኢሳ. 45፡5-6፤ ኛ ቆሮ 8፡4-6፤ ያዕ.2፡19። እነዚህ ጥቅሶች ስለ እግዚአብሔር ምን ያስተምራሉ?  በብሉይ ኪዳን የነበረው ታላቁ ትኩረት እግዚአብሔር ለሕዝቡ ለእስራኤል ለማስተማር የፈለገው ዋና እውነት እርሱ ብቻ እግዚአብሔር እንደሆነ ነው። ብዙ አማልክት ሳይሆን አንድ አምላክ ብቻ ነው ያለው ( በግ 6፡4-5) በዚያን ጊዜ የነበረው ዓለም ሁሉ ብዙ አማልክት እንዳሉ ያምን ነበር። ግብጽና ከነዓን የየራሳቸው አማልክት ነበሯቸው። በወንዞች ላይ፥ ከዋክብት ላይ በፀሐይ ላይ አማልክት ነበሩ። እግዚአብሔር እራሱን ለእስራኤል ሲገልጥ በተደጋጋሚ ያስተማራቸው አንድ አምላክ ይሖዋ፥ የእስራኤል አምላክ እርሱ እንደሆነ ነበር። አንዱ አምላክ ዓለምን ፈጠረ ሕዝቡን እስራኤልንም መረጠ። «አማልክት» በመባል የተጠሩት ሌሉቹ ሁሉ ዋጋ የሌላቸው፥ ኃይልም የሌላቸው፥ በሰው ግምት የተፈጠሩ ሰውን የሚመስሉ ደካሞችና በቁጥጥር ሥር የሚውሉ ጣዖታት ነበሩ። እግዚአብሔር ብቻ ዘላለማዊ፥ ያልተፈጠረ የነገሮች ሁሉ ተቆጣጣሪ ነው (ኢሳ. 45፡5-6)።  እግዚአብሔር አንድ የመሆኑን እውነታ ኢየሱስ ክርስቶስም ሆነ የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች አረጋግጠዋል። ታላቂቱ ትእዛዝ እግዚአብሔር እንድ እንደሆነ ማመንና እርሱንም በሙሉ ልባችን፥ ነፍሳችን፥ አእምሮአችንና ኃይላችን እንድንወደው ኢየሱስ ተናግሯል (ማር. 12፡29)። ጳውሎስ አንድ እምላክ ብቻ አላ ብሏል (1ኛ ቆሮ. 8፡4-6)። ያዕቆብ ሰዎች አንድ እግዚእብሔር ብቻ እንዳለ ማመን እንደሚገባቸው በአጽንኦት ተናግሯል (ያዕ. 2፡19)።  ምንም ልንረዳው ወይም ልንገልጸው አስቸጋሪ ቢሆንብንም እንኳ እንደ ክርስቲያን አንድ አምላክን ብቻ እንደምናመልክ ማስታወስ አለብን።  2. ክርስቲያኖች አንዱ እግዚአብሔር ምሥጢራዊ በሆነ መንገድ እራሱን በሦስት አካላት እንደገለጠ ያምናሉ። እግዚአብሔር አብ፥ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ።  እሰካሁን ድረስ የተመለከትነው መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስን አንደ ተራ ኃይል እግዚአብሔር ዕቅዱን ለመፈጸም የሚጠቀምበት አካል እንደሌለው ኃይል እድርጐ ፈጽሞ እንደማያቀርበው ነው። ይልቁኑ መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስን የሚያቀርበው እንደ አካል ነው። ሥጋ እንደለበሰ እካል ሳይሆን ሥጋ እንደሌለው መንፈሳዊ አካል ያቀርበዋል። በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን በአኅዳዊነት እንደሚያቀርበው ማለትም እግዚአብሔር እንድ አምላክ እንደሆነ ተመልክተናል። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማረጋገጫዎችን ልናቀርብላቸው የሚገቡ ሁለት እጅግ ጠቃሚ ጉዳዮች አሉ። የመጀመሪያው እግዚአብሔር በኑባሬ ከአንድ በላይ ነው ወይስ አንድ ብቻ ስለሚለው ነው። ይህ «የኢየሱስ ብቻ» ተከታዮችን ከወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት እምነት የሚለያቸው ዋነኛ ነጥቦች አንዱ ነው። ሁለተኛው ጉዛይ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ አምላክ የመሆኑና በዚህም ከሥላሴ አካላት አንዱ የመሆኑ ጉዳይ ነው።  መጽሐፍ ቅዱስ አንድ አምላክ ሦስት በአንድ የሆነ አምላክ መሆኑን ያስተምራልን?  ጥያቄ፡- አንድ የኦርቶዶክስ ክርስቲያንን በተለይ ካህን የሆነውን ሰው በግዕዝ ቋንቋ ሥላሴ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ጠይቀው። ይህ ቃል እግዚአብሔር አንድ እንደሆነና ደግሞም ሦላት እንደሆነ የሚጠቅሱትን አሳቦች እንዴት ያጣምራቸዋል?  በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙ ትምህርቶች ከሁሉ የላቀው ከባድ ትምህርት የእግዚአብሔር አንድም ሦ ለትም መሆን ነው። ስለ እግዚአብሔር የሚያስረዳው የዚህ እውነት ሥነ መለኮታዊ አጠራር «ሥላሴ» የሚል ነው። ይህ የሥነ መለኮት ቃል የተመረጠው በመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች ሲሆን ትርጉሙም አንድና ሦስት በአንድ ውስጥ ሦስት ማለት ነው።  እግዚአብሔር አንድና ሦስት መሆኑን የምንረዳበትን ችሎታ የሚሰጠን ሰብዓዊ መረዳት ወይም ልምምድ በእርግጥ ፈጽሞ የለንም። ስለዚህ ሰመጨረሻ ወመቀበል ያለብን ጉዳይ ይህ እውነት ከሰብዓዊ መረዳት ወይም ገለጻ ያለፈ መሆኑን ነው። የምንሰጠው ማናቸውም ዓይነት ማስረጃ በቂ አይደለም። ነገር በኢሳ. 5፡8-9 ላይ እግዚአብሔር አሳቡ ከአሳሳችን የላቀ ስለመሆኑ የተናገረውን በትሕትና ልናስታውሰው ይገባናል።  ለ2000 ዓመታት ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ በሦስት አካላት እራሱን የገላጠ አንድ አምላክ እንደሚያስተምር ሲያምኑ ኑረዋል። እነዚህም ሦስት አካላት እግዚአብሔር አብ፥ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ናቸው። ይህ ትምህርት የመጣው ክየት ነበር? መልሱ ከመጽሐፍ

መንፈስ ቅዱስ፤ ሦስተኛው የሥላሴ አካል Read More »

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ማን ነው?

ጥያቄ፡- ሀ) «መንፈስ ቅዱስ ማን ነው?» እንዴት ታብራራዋለህ? ተብለህ ብትጠየቅ ምን ትል ነበር? ከምን ጋር ታወዳድረዋለህ? ለ) በመጀመሪያው ቀን «የኢየሱስ ብቻ » ተከታዮች ደግሞም የኦርቶዶክስ ቀሳውስት የሰጡህን መልሶች ከልስ። እነርሱ ስለ መንፈስ ቅዱስ የገለጡበት [መንገድ አንተ ከተረዳህበት መንገድ በምን ይለያል?  ብዙዎቻችን እግዚአብሔር አብንና እግዚአብሔር ወልድን ለመረዳት አንቸገርም። ይህ የሆነበት ምክንያት ምናልባት በምድር ላይ የምናየውም የአባትና ልጅ ዛንኙነት እግዚአብሔር አብና እግዚአብሔር ወልድን ለመረዳት ስለሚያግዘን ይሆናል። በተጨማሪ አብዛኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሚያተኩረው በእግዚአብሔር አብና በእግዚአብሔር ወልድ ላይ ነው። መንፈስ ቅዱስ ማን እንደሆነ ለመረዳት እንሞክር ግን መንፈስ ቅዱስን በምድር የሚመስለው ስለሌለ በቀላሉ ለመገንዘብ ያስቸግረናል። ስሙ የተገኘው «ነፋስ» ከሚለው ቃል የሆነበት ምክንያት አለመታየቱንና ነገር ግን በእርግጥ መኖሩን ለማመልከት ነው።  ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ እንደ ነፋስ የማይታይ ኃይል ያለውና ግን ሕይወት የሌለው ነውን? ወይስ በቤታችን ውስጥ በሽቦ ገመዶች ተደብቆ እንዳለና ማብሪያና ማጥፊያውን ስንነካ እንደሚሠራ ኤሌክትሪክ ነውን? እግዚአብሔር የፈጠራቸው ሆነው ታላቅ ኃይል እያላቸው ግን ሕይወት የሌላቸው ኑባሬዎች አሉ? እሳት ትላልቅ ጫካዎችን ማውደም ይችላል። ነፋስ ትላልቅ መኪናዎችንም ሆነ ቤቶችን መገልበጥ ይችላል። ነገር ግን እነዚህ ነገሮች በራሳቸው ሕይወት የላቸውም። አያስቡም፥ አያቅዱም፥ በፈቃዳቸው አያደርጉም። መንፈስ ቅዱስ ይህን የሚመስል ነውን?  እግዚአብሔር የፈጠራቸውና ሕያው የሆኑ ነገር ግን ሰብአዊ ህልውና የሌላቸው ብዙ ነገሮች አሉ። እንደ ውሻ ያሉ እንስሳት ሕይወት አላቸው፥ ፈቃድ እላቸው የተወሰነ ደረጃ ም ቢሆን የማሰብ ኃይል አላቸው። ነገር ግን የእነርሱ ሕይወት ሰዎች ካላቸው ሕይወት የተለየ መሆኑ ግልጽ ነው። መንፈስ ቅዱስ ያላው እንደዚህ ዓይነት የእንስሳት ሕይወት ነውን?  የሕይወት ከፍተኛ ደረጃ ው ሰብአዊ ህልውና ሲኖር ነው። ሰዎች መኖርና መተንፈስ ብቻ ሳይሆን ላማሰብ፥ ለማቀድና አንድ ነገር ለመፍጠር የሚችሉ ናቸው። እንደዚህ ዓይነቱ ሕይወት በእግዚአብሔርና በአምሳያው በተፈጠረው በሰው ሕይወት ውስጥ ብቻ ያለ ነው። መንፈስ ቅዱስ ያለው እንደዚህ ዓይነቱ ሕይወት ነውን?  በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ዛሬም ቢሆን እንኳ መንፈስ ቅዱስ እንደ እግዚአብሔር ዓይነት እውነተኛ ሕይወት የለውም በማለት የሚያስተምሩ እሉ። ይልቁኑ ሴቶችን ለማፈራረስ ከፍተኛ ኃይል እንዳለው ነፋስ መንፈስ ቅዱስም ሕይወት የሌለው እግዚአብሔር ፈቃዱን ለመፈጸም የሚጠቀምበት ኃይል ነው ይላሉ። የራሱ ፈቃድ የለውም፥ ሕይወት ያለው አይደለም። እግዚአብሔርም እይደለም። እግዚአብሔር አብ የራሱ አካላዊ ህልውና ቢኖረውም መንፈስ ቅዱስ ግን በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር የሆነ እንደ እሳትና ነፋስ ያለ ነገር ነው። እካላዊ ህልውና ስለሌለው አያስብም፥ አያቅድም፥ አይሠራም ወይም እካላዊ ህልውና ያላቸው ሌሎች ካላቸው ባሕርይ እንድም የለውም ይላሉ። (ማስታወሻ፡ አንድ ነገር አካላዊ ህልውና አለው ስንል ለማሰብ፥ ለማቀድ፥ ለመንደፍ፥ ለመፍጠር ስሜት ሊኖረው የሚችለውን የሰውን ክፍል መናገራችን ነው።)  አንዳንድ የሐሰት ትምህርቶችና ለዘብተኛ-ክርስቲያኖች ካላቸው አሳቦች ጥቂቶቹ ቀጥለው ተዘርዝረዋል።  1. የይሖዋ ምስክሮች፡- ይህ የሐሰት ትምህርት መንፈስ ቅዱስ አገልጋዮቹ ፈቃዱን እንዲያደርጉ የሚያንቀሳቅሳቸው የማይታይ ገቢራዊ የሆነ የሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ኃይል ነው ብለው ያስተምራሉ። በእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱሳቸው መንፈስ ቅዱስ አምላክ እንደሆነ የሚያመለክት የቃላት አጠቃቀም እንዳያደርጉ ይጠነቀቃሉ። (ይኽውም፥ Holy የሚለውን holy, Spirit የሚለውን spirit በማለት ነው።) የመንፈስ ቅዱስን አምላክነት ይክዳሉ።  2. የዓለም አቀፍ መንገድና ኢየሱስ ብቻ “The Way International and Jesus Only”፡- እነዚህ መናፍቃን እንደሚከተለው ያስተምራሉ። መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር አብ ጋር አንድ ነው። በሥላሴ ውስጥ ያሉ የተለያዩ አካላት አይደሉም። የእግዚአብሔር ኃይል የሆነው መንፈስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር ልጆች ሊሰጥ ይችላል።  3. ዓለም አቀፍ የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን “The Word wide Church of God” ስታስተምር መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ህልውና ያለው አይደለም። እኛ የኤሌክትሪክ ኃይልን ብርሃን ለማግኘትና ሌሎች እቃዎችን ለመጠቀም እንደምንገለገልበት ሁሉ እግዚአብሔር እብም መንፈስ ቅዱስን እንዲሁ ይጠቀምበታል። ለእግዚአብሔር መንፈሱ፥ አሳቡ፥ ኃይሉ፥ ባሕርዩ ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር አብና እንደ ክርስቶስ ራሱን የቻለ አካላዊ ሕልውና የለውም።  4 አንዳንድ ለዘብተኛ ክርስቲያኖች እና ራሳቸውን “Unitarians” ብለው የሚጠሩና የሥላሴን ጽንሰ አሳብ የሚክዱ የክርስቶስን መለኮታዊነት የሚጠራጠሩ፤ የመንፈስ ቅዱስን መላኮታዊነትና አካላዊ ህልውና ይክዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሲጠቅስ፥ እግዚአብሔር አብ በዓለም ውስጥ ስላለው ተግባር መናገሩ ነው ይላሉ።  ብዙዎቻችን መንፈስ ቅዱስ ግዑዝ ኃይል ነው ብለን ብናምንም በተግባር ግን ዓላማችንን በማስፈጸም እንዲያገለግላን እንደፈለግን የምንናቆረቁረውና የምንቆጣጠረው ኃይል አድርገን እንቆጥረዋለን። አንዳንድ ኦርቶዶክሶችና ሙስሊሞች ከክፉ የሚጠብቀን ኃይል ነው በማለት የአስማት ክታብ በአንገታቸው እንደሚያስሩ፥ አንዳንዶቻችንም መንፈስ ቅዱስን በዚህ መልክ እናስተናግደዋለን። መንፈስ ቅዱስን መቆጣጠርና እንደፈለግነው መጠቀም የምንችል ይመስለናል። ልናውቀው የምንችለው የራሱ አካላዊ ህልውና እንዳለው ከእርሱ ጋር ግንኙነት መመሥረትና ማዳበር እንደሚገባን አድርገን እንቆጥረውም። ይህ ዝንባሌ በተለያየ መንገድ ይታያል። አንዳንድ ሰዎች መንፈስ ቅዱስን አንድ ነገር እንጠይቀውና በኢየሱስ ስም በመጸለያችን ብቻ ክፍላጐታችን ጋር እንዲስማማ የምናስገድደው ይመስለናል። መንፈስ ቅዱስን የአምልኮ መንፈስ እንዲፈጥር ለማስገደድ የጉባኤን ስሜት በሚፈልገው አቅጣጫ ለመጠቀም ሙከራ ይደረጋል። ላሰዎች ለመጻላይ ብቻ መንፈስ ቅዱስ እንዲፈውሳቸው ለማስገደድ ይሞክራሉ።  ጥያቄ፡- ሀ) ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን በተለይም ደግሞ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ለመቆጣጠር የሚሞክሩባቸውን ሌሎች መንገዶች ጥቀስ? ለ) ይህ ስሕተት ይመስልሃልን? ለምን? 15ኛ ጥያቄ፡– ሕይወት ባለውና ሕይወት በሌለው ነገር ግን ኃይል ባለው ነገር መካከል የሚታየው ልዩነት ምንድን ነው።  ሥጋዊ አካል ያለን ፍጡራን በመሆናችን እውነተኛ ሕይወትና አካላዊ ህልውና ሥጋዊ አካል ሊኖረው ያስፈልጋል ብለን እናስባለን። ብዙውን ጊዜ እካላዊ ህልውናና ሕይወት ያላን ሥጋዊ አካል ስላለን ነው ብለን እናስባለን። ነገር ግን ሥጋዊ አካል ሕይወት ወይም ነፍስ የሚኖርበት ቤት ነው። አንድ ሰው በሥጋው ሲሞት ህልውናው እያከትምም። አካላዊው ሕልውና ወይም ነፍሱ ትኖራለች። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው አንድ ክርስቲያን ሊሞት አካላዊ ህልውናው ሕያው ሆኖ በመቀጠል ከጌታው ጋር ይሆናል (ፊልጵ. 1፡20-24)። ስለዚህ እራሳችንን፤ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ህልውና አለው ወይስ ቁስ ነው የሚለውን ጥያቄ ስንጠይቅ አካላዊ ህልውና ምን ማለት እንደሆነ ቀደም ብሎ የነበረንን አሳብ መለወጥ አለብን። መንፈስ ቅዱስ ሥጋዊ አካል ባይኖረውም እንኳ አካላዊ ህልውና ሊኖረው እንደሚችል ልብ ልንል ይገባል።  መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል? መንፈስ ቅዱስና አካላዊ ሕልውና፥ ፈቃድ፥ እእምሮና ስሜት እንደሌላቸው ነፋስና እሳት ነውን? ወይስ አካላዊ ህልውና ያለው ለማሰብ ለማቀድ የሚችልና ስሜት ያለው ወዘተ… ነውን?  ጥያቄ፡– የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት 1ኛ ቆሮ. 2፡10-13፤ ኤፌ. 4፡30፤ 1ኛ ቆሮ. 12፡7-11፤ ዮሐ 14፡26፤ ሮሜ 8፡14፤ የሐዋ. 8፡29፤ የሐዋ. 10፡19-21፤ የሐዋ. 5፡3፤ የሐዋ. 7፡51፤ ማቴ. 12፡31። ሀ) ስለ መንፈስ ቅዱስ ከአካላዊ ህልውናው ጋር በተዛመደ እነዚህ ጥቅሶች የሚያስረዱበትን ነጥቦች ዘርዝር። ለ) እነዚህ ጥቅሶች ስለ መንፈስ ቅዱስ ዓይነት ሕይወት ምን ያስተምሩናል?  1. መንፈስ ቅዱስ ማንኛውም አካላዊ ህልውና ያለውን ባሕርይ በሙሉ ይዟል።  እንደ ሰውና እንደ እግዚአብሔር አካላዊ ህልውና ያለው ሆኖ ለመገኘት መሟላት ያለባቸው ብዙ ነገሮች አሉ። አእምሮ መኖር እለበት፥ የማሰብ፥ የማቀድና የመወሰን ችሎታ ማለት ነው። ፈቃድ መኖር አለበት፥ ለመወሰንና እቅዶቹን ለመተግበር የሚያግዘው ውስጣዊ ዓላማ ማለት ነው። ስሜቶች መኖር አለባቸው፥ ከአእምሮና ከፈቃዱ ጋር በጥምረት የሚሠሩ ስሜቶች ባለቤት የመሆን ችሎታ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚናገረውን ስናጠና እርሱ ሕያው ጭብጥ እንጂ ሕይወት የለሽ ኃይል ብቻ እንዳልሆነ እንገነዘባለን። ከላይ በተዘረዘሩት ጥቅሶች ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚከተሉትን ነገሮች መመልከት እንችላለን።  ሀ) መንፈስ ቅዱስ አእምሮ አለው፡- ነገሮችን የማወቅ፥ የእግዚአብሔር የሆኑትን ነገሮች የመፈለግና ውሳኔ የማድረግ ችሎታ አለው። የሚያውቀውን እውነት ለሰዎች ማስተማር ይችላል (1ኛ ቆሮ. 2፡10-13፤ ኤፌ. 1፡17፤ ሮሜ 8፡2)።  ለ) መንፈስ ቅዱስ ልማቶች አሉት፡- አማኞች ኃጢአትን ሲያደርጉ ያዝናል (ኤፌ 4፡30)። በከፍተኛ ችግሮች ውስጥ ስንሆን ከእኛ ጋር ያዝናል፥ ይቃትትልናልን (ሮሜ 8፡26)። ደግሞም ይወደናል (ሮሜ 5፡30)።  ሐ) መንፈስ ቅዱስ ፈቃድ አለው፡- አንድ ነገር ወስኖ ዕቅዶቹን መፈጸም ይችላል። ለተለዩ ሰዎች የትኞቹን ስጦታዎች መስጠት እንዳለበት

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ማን ነው? Read More »

የመንፈስ ቅዱስ ተምሳሌቶች

ጥያቄ፡- ሀ) ለሰዎች ባሕርያቸውን ለመግለጽ የምንሰጣቸውን ስሞች [[እንደ አንበሳ) ዘርዝር። ላ) እነዚህ ላሞች የትኛውን ባሕርይ ይገልጻሉ?  አንዳንድ ነገሮችን ለመግላጽ ብዙ ጊዜ ምልክቶችን እንጠቀማለን። ለምሳሌ፡ አንድ ሰው ፍርሃት የማያውቅና ጠንካራ መሆኑን ለመግለጽ «አንበሳው» እንላዋለን። አንዳንድ ሰዎች እራሳቸውን «የቤተ ክርስቲያን አህዮች» ነን በማለት ሲናገሩ ሰምቼአለሁ፤ ይህን ሲሉ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች መሆናቸውንና ሸክሟን እንደተሸከሙ መናገራቸው ነው። በተመሳሳይ መንገድ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ባሕርይ ለመግለጽ ምልክቶችን ይጠቀማል። ለምሳሌ፥ ኢየሱስ አንበሳና በግ ተብሎ ተጠርቷል (ራእይ 5፡5-6)። እግዚአብሔር ዓለት እንደሆነ ተጽፎአል (ዘፍ 49፡24)። እምባ መሆኑም ተገልጧል (2ኛ ሳሙ. 22፡2)። እያንዳንዱ ምልክት ስለ እግዚአብሔር ባሕርይ የሚገልጣቸው ነገሮች አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ የመንፈስ ቅዱስን ባሕርይ ወይም ሥራ ለመግለጽ የተለያዩ ምልክቶችን ተጠቅሟል።  ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት። ሉቃስ 24፡49፣ 3፡22፤ 2ኛ ቆሮ. 1፡22፤ የሐዋ. 2፡3፤ ሉቃስ 4፡18፤ ዮሐ 7፡38-39፤ 3፡8 ሀ) መንፈስ ቅዱስን ለመግለጽ የሚጠቅሙ ወይም ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ምልክቶች ወይም መግለጫዎች ጥቀስ። ላ) እያንዳንዱ ምልክት ምን ማለት ይመስልሃል? መንፈስ ቅዱስ በዚህ ምልክት የተገለጠው ለምን ይመስልሃል?  1. መንፈስ ቅዱስ እንደ ልብስ (ሉቃስ 24፡48-49)  ይህን ጥቅስ ለመረዳት ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርት የገባው ቃል ኪዳን ምን እንደሆነና ወንጌልን የመስበክ ሥራ ከመጀመራቸው በፊት መጠበቅ ያላባቸው ምን እንደነበር ማረጋገጥ መቻል አለብን። ሉቃስ በዚህ ስፍራ በገለጠው ታሪክ በሐዋ. 1፡8 በተጻፈበት ሁኔታ ኢየሱስ የሚናገረው ስለ መንፈስ ቅዱስ እንደ ነበር ግልጽ ነው። ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ የሰጣቸው ተስፋም መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ እንደሚወርድ ነበር። መንፈሱም ልክ እንደ ልብስ ስመለኮታዊ ኃይሉ ስለሚሸፍናቸው ስለ ኢየሱስ በብቃት እንዲመሰክሩ ያስችላቸዋል። (ኢየሱስ! በአእምሮው ያለው ነገር ምናልባት ኤልያስ ለኤልሳዕ ያስተላለፈው መጐናጸፊያ ይሆናል)። ልብ በል ልብሱ ላደቀመዛሙርቱ ይሰጣቸዋል እንጂ እነርሱ በእራሳቸው አይለብሱትም ነበር። በተመሳሳይ ሁኔታ መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር በነፃ የተሰጠ ስጦታ እንጂ ሠርተን ወይም ጸልየን የምናገኘው አይደለም። መንፈስ ቅዱስ እኛን የሚያለብስበት ተቀዳሚ ዓላማ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ኃይል እንድንሸፈን ነው። ይህ ኃይል ይጠብቀናል (ልብስ ከብርድ እንደሚከላከለን ሁሉ) በተጨማሪ እግዚአብሔርን በመወከል እንድናገለግል ይረዳናል። እንደ አንዳንድ ምሁራን አመለካከት መንፈስ ቅዱስን መልበስ በእግዚአብሔር ቅድስና መሽፈን እንደሆነ (ኤፌ. 4፡24) ይህም የክርስቶስ መሆንን እንደሚያሳይ ይናገራሉ።  2. መንፈስ ቅዱስ እንደ ርግብ ነው (ሉቃስ 3፡22)  ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ በተጠመቀ ጊዜ ከሰማይ የወረደ ርግብ በኢየሱስ ላይ እንዳረፈ ተጽፋል። ይህ ርግብ መንፈስ ቅዱስ እንደ ሆነም ተነግሮናል። ሕዝቡ ሁሉ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነና በእግዚአብሔር መንፈስ እንደተሞላ ያውቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በኢየሱስ ላይ ወረደ። ታልሙድ በመባል የሚታወቀው የአይሁድ ሥነ ጽሑፍ በዘፍ 1፡2 ላይ አሳብ ሲሰጥ የእግዚአብሔር መንፈስ እንደ ርግብ ሆኖ በውኃ ላይ ሰፍፎ እንደነበር ይናገራል። ይህ ማለት ለአይሁድ ርግብ የመንፈስ ቅዱስ ምልክት መሆኑ የተላመደ ነበር ማለት ነው።  የርግብ ምልክት ትርጉም ምንድን ነው? ይህ ምልክት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አገልግሎት ላይ የዋለው ብዙ ጊዜ ስላይደላ ስለ ትርጉሙ እርግጠኞች መሆን አንችልም። ሆኖም ግን ስለዚህ ጉዳይ ሁለት ዋና አስተሳሰቦች አሉ። በመጀመሪያ በማቴ. 10፡16 ላይ እንደ ርግብ የዋሆች» እንድንሆን ተመክረናል። የዋህ የሚለው ቃል ንጹሕ መሆንና የተደባለቀ የውስጥ አሳብ ያለመኖርን ያሳያል። ስለዚህ ለአይሁድ ርግብ የየዋህነትና ንጹሕ የመሆን ምልክት ነበር። ርግብ የሰላም ፇልክትም ሆኖ አገልግሏል። የተባበሩት መንግሥታት ዓርማ የሆነው ለዚህ ነው። ርግብ የሚያመለክተው ይህን ከሆነ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ወደ ኢየሱስ ሲልከው ንጹሕና ሰላማዊ የሆነው መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ላይ የወረደው የእግዚአብሔር ልጅ መሢሑ ኢየሱስ ንጹሕና ሰላማዊ እንደሆነ ለሰዎች ለማሳየት ነበር።  ሁለተኛ፡ ርግብ በብሉይ ኪዳን ጊዜ ድሆች ሰዎች ከሚሠውት መሥዋዕት እንዱ ነበር (ዘሌዋ 12፡8)። ኢየሱስ እንደ ተወለደ ወላጆቹ ሁለት ርግቦች መሥዋዕት አድርገው እንዳቀረቡ ታስታውሳላችሁ (ሉቃስ 2፡24)። ስለዚህ አንዳንድ ምሁራን ርግብ የሚያመለክተው ኢየሱስ ለዓለም መሥዋዕት የመሆኑን ጉዳይ ነው ብለው ያስባሉ።  ርግብ የሚያመለክተው ኢየሱስን ለምድራዊ አገልግሎቱ ያዘጋጀው ዘንድ በእርሱ ላይ የወረደውን መንፈስ ንጽሕናና ቅድስና ሳይሆን አይቀርም። ንጹሕ የሆነው መንፈስ ቅዱስ ቅድስናውን ወደ ኢየሱስ አስተላለፈ። ኢየሱስ ያለኃጢአት ስለነበር መንፈስ ቅዱስ «ቅዱስ» አላደረገውም። ይልቁኑ ርግብ የሚያመለክተው ኢየሱስ ንጹሕና ቅዱስ እንደሆነ በተለይ ደግሞ የእስራኤል መሢሕ ይሆን ዘንድ በእግዚአብሔር እንደተመረጠ ነው። ይህ ክስተት ኢየሱስ እግዚአብሔር የሰጠውን ሥራ ይፈጽም ዘንድ በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ይፋ አገልግሎቱን መጀመሩን ያሳየናል (ዮሐ 17፡14)። የርግብ ከሰማይ መውረድ መንፈስ ቅዱስ ከሰማይ የመጣ መሆኑን ያሳየናል።  3. መንፈስ ቅዱስ እንደ ማኅተም፥ እንደ ቃል ኪዳን፥ ወይም እንደ መያዣ (2ኛ ቆሮ. 1፡22፤ 5፡5፤ ኤፌ. 1፡13-14) በጥንት ጊዜያት አንድ ሰው እንደ ንብረት ሊገዛ የተወሰነ ገንዘብ ቀድሞ በመያዣነት ይከፍልና የቀረውን ደግሞ በተወሰኑ ጊዜያት እንደሚከፍል መስማማቱን በወረቀት ላይ ይፈርማል። ይህ ስምምነት የእርሱ እንደሆነና በስምምነቱ መሠረት እንደሚፈጽም በጣቱ ያለ የቤተሰቡ ዓርማ ያለበት ቀለበት አውጥቶ እንደ ማኅተም በመጠቀም በሰም ላይ ያደርጋል። (ለምሳሌ ሐጌ 2፡23) ማኅተሙ (ቃል ኪዳኑን)፥ ወደፊት ሙሉ ክፍያውን እንደሚፈጽም የተሰጠ ዋስትና ነው።  መንፈስ ቅዱስ ከዚህ ማኅተም፥ ወይም መያዣ ጋር ይነፃፀራል። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ለእያንዳንዱ ክርስቲያን እንደ ሰጠ እና ይህ መንፈስ በእያንዳንዱ ክርስቲያን ልብ እንደ ማኅተም እንደ ተመታ ወደፊት እንመለከታለን። ማኅተም ብዙ ነገሮችን ያሳያል። በመጀመሪያ፥ ባለቤትነትን ያሳያል። ስማችንን በመጽሐፉ ላይ ስንጽፍ መጽሐፉ የእኛ እንደሆነ ማረጋገጣችን እንደመሆኑ ሁሉ የመንፈስ ቅዱስ ማኅተምም የእግዚአብሔር መሆናችንን ያሳያል። ሁለተኛ፥ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር በክርስቲያኖች ልብ የጀመረው ሥራ እንደሚፈጸም የሚያመላክት ተስፋ ነው። አንድ ቀን በእግዚአብሔር ለክርስቲያኖች የተሰጡ በረከቶች ሁሉ ሙሉ በሙሉ በሰማይ ይላሉ።  4. እሳት (የሐዋ. 2፡3)  የበዓለ ኀምሳ ቀን በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ልዩ ቀን ነበር። ይህ ቀን ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችበት ቀን ነበር። ያችን ቀንና የቤተ ክርስቲያንን ዘመን ከብሉይ ኪዳን ጊዜያት ለመለየት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱሳን እንደሚልክ ተስፋ ሰጥቶ ነበር (ኢዩ. 2፡28-32)። ይህንን በበዓለ ኅምሳ ቀን አደረገው። ሰተዘጋው ክፍል ውስጥ በነበሩ ደቀ መዛሙርት ላይ የወረደው መንፈስ ቅዱስ በሁለት ነገሮች ታጅቦ ነበር- ነፋስና እሳት (ወይም በርካታ የእሳት ነበልባሎች) እነዚህም የመምጣቱ ማረጋገጫዎች ነበሩ።  በኢሳ. 4፡4 መንፈስ ቅዱስ «የሚያቃጥል መንፈስ» ተብሎ ተጠርቷል። ሰሉቃስ 3፡16 ደግሞ ኢየሱስ ሕዝቡን «በመንፈስ ቅዱስና በእሳት» እንደሚያጠምቅ ተነግሯል። ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እሳት ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ተቆራኝቶ ቀርቧል። እሳት ምንን ያመለክታል? በብሉይ ኪዳን ውስጥ ሁሉ እሳት እጅግ ጠቃሚ ተምሳሌት ሆኖ የቀረበ ሲሆን የሚክተሉትን መልእክቶች ያስተላልፋል፡  ሀ. እግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል ስለመሆኑ፡- ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር እራሱን ለሕዝቡ በቀጥታ ወይም በሚታይ ራእይ ሲገልጥ በእሳት ይከበብ ነበር። (ለምሳሌ ዘጸአ 3፡2፤ 13፡21፤ ሕዝ. 1፡4-5)  ለ. እግዚአብሔር ሕዝቡ የሚያደርገውን ለማረጋገጥ ሲፈልግ (ዘሌዋ. 9፡24)  ሐ. የእግዚአብሔር ጥበቃ (ዘጸአ 14፡19-25)  መ. የእግዚአብሔር የፍርድ፥ የማንጻት እና የማጥራት ሥራ (ዘሌዋ. 10፡2፤ ኢሳ. 6፡9-8)  በበዓለ ኀምሳ ቀን የወረደው መንፈስ ቅዱስን የሚያመላክተው እሳት ለደቀ መዛሙርት እነዚህን ነገሮች ሁሉ ሳያመለክት አልቀረም። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በመካከላቸው መሆኑን ያሳያቸው ነበር። ደቀ መዛሙርት ከኃጢአታቸው ነጽተው ነበር። እግዚአብሔር የተቀደሱ ልጆቹ እንደሆኑ አረጋግጦላቸው ነበር። የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ሆነው ለመቆም ዝግጁ ነበሩ።  5. ዘይት (ሉቃስ 4፡18፤ የሐዋ. 10፡38፡ 2ኛ ቆሮ. 1፡21-22፤ 1ኛ ዮሐ 2፡20)  በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ሰውን ለአገልግሎት ሲለይ በዘይት ይቀቡ ነበር (ዘጸኢ 40፡9-16፤ 1ኛ ሳሙ. 10፡1፤ 16፡13)። ዳዊት በዘይት በተቀባ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ላይ ወዲያውኑ ወረደ። መሪዎችን የመቀባት ተግባር በእስራኤል ሁሉ ውስጥ የታወቀ ከመሆኑ የተነሣ የእስራኤል የመጨረሻ ንጉሥ የሚሆነው መሢሑ ወይም ክርስቶስ የተቀባው» የሚል መጠሪያ ተሰጥቶት ነበር። በዕብራይስጥ መሢሕ በግሪክ ደግሞ ክርስቶስ የሚሉት ቃሎች ትርጉም «የተቀባ» ማለት ነው። ኢየሱስ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እንደተቀባ ተናግሯል (ሉቃስ

የመንፈስ ቅዱስ ተምሳሌቶች Read More »

የመንፈስ ቅዱስ ስሞች

ጥያቄ፡- ምሳ. 810 «የእግዚአብሔር ስም የጸና ምብ ነው ጻድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል፡- ሀ) የእግዚአብሔር ስም ለእግዚአብሔር ሕዝብ መሸሸጊያ የሚሆነው በምን መንገድ ነው? ለ) የጌታን ስምና ትርጉሙንም ማወቅ እንዴት እንደሚያበረታታህ ዓለጽ? ሐ) ከአበረታቱህ የእዚአብሐር ስሞች አንዳንዶቹን ጥቀስ።  ትናንትና ባካሄድነው የቃለ ምልልስ ሥራ ስለ እግዚአብሔርና ስለ መንፈስ ቅዱስ በጠየቅሃቸው ጥያቄዎች እጅግ የተለያዩ መልሶች እንዳገኘህ እንገምታለን። ለለ መንፈስ ቅዱስ ጉዳይ በክርስቲያኖች መካከል ተራ የሚያጋቡ በርካታ አሳቦች አሉ። ይህ ራ መጋባት የተፈጠረው ለምንድን ነው? ለዚህ ተቀዳሚው ምክንያት ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምርና እነዚህን ጥያቄዎች እንዴት እንደሚመልስ ለማወቅ ጊዜ ስለማይሰጡ ነው። የዚህ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተጻፈ የጥናት መጽሐፍ ተቀዳሚ ዓላማ መጽሐፍ ቅዱስን በመቃኘት ለእነዚህና ሌሎች ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ነው።  ጥያቄ፡- ሀ) ወመንፈስ ቅዱስ «ቅዱስ መንፈስ» ተብሎ የተጠራበት ምክንያት ምንድን ነው ብለህ ታስባለህ? ለ) ቅዱስ ማለት ምን ማለት ነው? ሐ) መንፈስ ማለት ምን ማለት ነው? መ) የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት። ዘፍ 2 ማቴ. 3፡16 የሐዋ. 16፡7፤ ሮሜ 8፡9፤ ራእ. 14። የመንፈስ ቅዱስን ሌሎች ስሞች ጥቀስ።  ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔርን ስም ዝም ብለን ከመጥራትና ከመጠቀም በስተቀር ምን ማለት እንደሆነና እግዚአብሔር በዚያ ስም ለሦን እራሱን እንደገለጠልን ቆም ብለን አናስብም። የእግዚአብሔር ስሞች በተቀዳሚ ባሕርይውን ለመመለጥ የተሰጡ ናቸው። ለምሳሌ እግዚአብሔር አብ «አባት» ተብሎ የተጠራው በኢየሱስ ክርስቶስ ላመኑ ለልጆቹ ያለውን የፍቅር እመለካከት ለማሳየት ነው። «ኢየሱስ» ማለት ድነት (ድነት (ደኅንነት)) ማለት ሲሆን በመስቀል ላይ በመሞት ድነት (ድነት (ደኅንነት))ን ለሰው ልጆች መስጠት ተቀዳሚ ተግባሩ ሆኑን ያሳያል። «መንፈስ ቅዱስ» የሚለው ስም ለሦስተኛው የሥላሴ አካል የተሰጠበት ምክንያት ደግሞ አለ።  ጥያቄ፡- «መንፈስ» የሚለውን ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ላይ ተመልከት። ትርጉሙ ምንድን ነው?  በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ በተለያየ ስም ይጠራል። ለምሳሌ አንዳንድ ጊዜ የኢየሱስ መንፈስ የሐዋ. 16፡7) ወይም እግዚአብሔር መንፈስ በፀኤ 31፡3) በመባል ይጠራል። ነገር ግን ተቀዳሚ ስሙ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው። ይህ ስም መንፈስ ቅዱስን በተመለከቱ ሦ ለት የተላያዩ እውነቶች ላይ ያተኩራል።  1. መንፈስ መንፈስ ቅዱስ የሚለው ስም የመጀመሪያ ክፍል «መንፈስ» በሚል ስም ላይ ያተኩራል። በዕብራይስጥ፥ በግሪክና በአማርኛ «መንፈስ» የሚለው ቃል የመጣው ትንፋሽ ወይም «ነፋስ» ከሚለው ቃል ነው። ይህ ቃል ከእግዚአብሔር ጋር አዛምደን ስናየው በታላቅ ኃይል የሚንቀሳቀስ የብርቱ ሩስ ሥዕል በአእምሮአችን ለመፍጠር አገልግሏል። አሳቡ ታላቅ የእግዚአብሔር ኃይል በተግባር ላይ መዋሉን የሚያሳይ ነበር።  መንፈሳዊ ጭብጦች እንደ ነፋስ በዓይን የማይታዩ ናቸው። አናያቸውም። አንነካቸውም። ብዙ ጊዜ መኖራቸውንም እንኳ አናውቅም። እንደ ነፋስ መንፈሳዊ ጭብጦች መኖራቸውን የምናውቀው በተግባራቸው ነው። ነፋስ በሚነፍስበት ጊዜ ፊታችንን በመንካቱ ወይም የዛፎችን ቅጠሎች በማንቀሳቀሱ እናውቀዋለን። ነፋስ በታላቅ ኃይል በሚነፍስበት ጊዜ ፍችን ካሥራቸው ይነቅላቶዋል። የቤት ክዳን ቆርቆሮዎችን ይነጥላል። በተመሳሳይ ሁኔታ መንፈሳዊ ጭብጦችን የምናረጋግጠው ሰው ስዊድንበት፡ በሚፈወስበት ወይም ሕልዎ በሚያይበት ጊዜ ነው።  የታላቅ ነፋስን አሳብ አንድ አካላዊ ህልውና ካለው ነገር ጋር አዛምዶ መናገር አስቸጋሪ ነው። ይህ ጉዳይ ለእኛ አስቸጋሪ ቢሆንም እንኳ ላጥንት ሰዎች አስቸጋሪ አልነበረም። መንፈስ የሚለው ቃል ለመንፈስ ቅዱስ ብቻ በሚሆንበት ጊዜ ምሥጢራዊ ንብረቱ የማይታይ ህልውናውን ያመለክታል። የጥንት ሰዎች ግን መንፈስ ቅዱስ ሕይወት የሌለው ነፋስ እንዳልሆነ ያውቁ ነበር። ይልቁኑ አካላዊ ህልውና ነበረው። ያፈቅር፥ ይወስን፥ ይፈርድ ነበር። ይህንን ማድረግ የሚችለው ሕይወት ያለው ነገር ብቻ ነው።  «መንፈስ» የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ መንገዶች አገልግሎት ላይ ውሏል።  ሀ. የሰው መንፈሳዊ የሆነው ክፍል ከሥጋዊ አካሉ ተቃራኒ ሆኖ የቀረበበት ሁኔታ፡- የሰው መንፈስ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ለማድረግ ችሎታ ያለው ቁሳዊ ያልሆነው የሰው ክፍል ነው። በኢየሱስ በማመን ሕያው እስከሚሆን ድረስ ሙት ሆኖ የሚቆየው ይህ የሰው ክፍል ነው (ኤፌ. 2፡1-6)።  ለ. ሥጋዊ አካል የሌላቸው መንፈሳዊ ኑባሬዎች፡- መንፈሳዊ ኑባሬዎች ሕያው የሚያደርጋቸው ባሕርያት በሙሉ ያላቸው እንጂ ሕይወት እንደሌላቸው እንደ ፋላ ወይም ሥጋዊ አካል ብቻ እንዳላቸው እንደ እንስሳ ፈጽሞ አይደሉም። ከሰው የተለየ የሚያደርጋቸው ሥጋዊ አካል የሌላቸው መሆናቸው ብቻ ነው። በዚህ ክፍል ውስጥ የሚጠቃለሉ ሁለት ዋና ኑባሬዎች አሉ። 1. የተፈጠሩ መንፈሳዊ ኑባሬዎች፡- መጽሐፍ ቅዱስ አካላዊ ተፈጥር የሌላቸውን ኑባሬዎች በውሉ እግዚአብሔር እንደፈጣራቸው ያስተምረናል። እነዚህ መንፈሳዊ ኑባሬዎች መልካም (ከተለያዩ ዓይነት መላእክት እንደ አንዱ) ወይም ክፉ (እንደ ሰይጣን እና አጋንንት) ሊሆን ይችላሉ (ማስታወሻ፡- ሰይጣን በእግዚአብሔር ላይ በማመጽ በኃጢአት ክመውደቁ በፊት መልካም ከሆኑት መላእክት አንዱ ነበር። እግዚአብሔር ሰይጣንና አጋንንትን ክፉ አድርጐ አልፈጠረም።) እነዚህ መንፈሳዊ የሆኑ ኑባሬዎች ሕይወት ያላቸው ናቸው። በዙሪያችን ያሉ ቢሆኑም እንኳ ሥጋዊ አካል ስለሌላቸው በሥጋዊ ዓይናችን ልናያቸው አንችልም። አንጓንድ ጊዜ እዚህ መንፈስ የሆኑ ኑባሬዎች የሰው ቅርጽ ሊወስዱና ሥጋዊ አካል ያላቸው መስለው ሊቀርቡ ይችላሉ። በተፈጥሮአዊ አቋማቸው ቀን ሥጋዊ አካል የላቸውም። ሥጋዊ አካል የሚወስዱት ለሰው መታየት እንዲችሉ ሲፈልጉ ብቻ ነው።  2. እግዚአብሔር፡- ሥላሴ የሆነው እግዚአብሔር መንፈስ ነው። ከዘላለም በፊት ጀምር እግዚአብሔር ሁል ጊዜ የኖረው በመንፈስ መልክ ነው። እግዚአብሔር ሁልጊዜ የኖረው መንፈስ ሆኖ ነው። ከተፈጠሩት መናፍስት በተቃራኒ እርሱ ፍጡር አይደለም። መጀመሪያም የለውም። ስለዚህ እኛ እንደምናውቀው ዓይነት ሥጋዊ ዓይን፥ ጆሮዎች ወይም እርች የሉትም። መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህን ቃሎች ለእግዚአብሔር ሊጠቀምበት እግዚአብሔር ነገርችን ለማየት፥ ለመስማትና ለማድረግ ያለውን ችሎታ ሥዕላዊ በሆነው የሰው ቋንቋ መግለጹ ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ እጅግ አስደናቂ ምሥጢራዊ እውነቶች አንዱ እንደ እግዚአብሔር አብ ከዘላለም ጀምሮ መንፈሳዊ የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ሥጋ መልበሱ ነው። በምድር ላይ ሰው ቢሆንም እንኳ ዘላለማዊ መንፈሳዊ ተፈጥሮውን ግን አልተወውም ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው በመሆን ለዘለዓላም በመንግሥተ ሰማይ ይኖራል (ዕብ 2፡14፥ 17፤ 4፡14-16)።  ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ «መንፈስ» የተባለው እንደ ሰዎች ሥጋዊ አካል ስለሌለው ነው። ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ጊዜ ሕይወት እንደሆነው የእግዚአብሔር «እስትንፋስ» ሥጋዊና መንፈሳዊ ሕይወት የሚሰጥ መንፈስ ቅዱስ ነው። ፋስ ባይታይም እንኳ ብርቱ እንደሆነ ሁሉ መንፈስ ቅዱስም አይታይም፡ መኖሩን የምናውቀው በሕይወታችን በሚሠራው ሥራ ውጤት ነው።  2. ቅዱስ  ጥያቄ፡- «ቅዱስ» የሚለውን ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ተመልከት። ይህ ቃል ምን ማለት ነው?  የመንፈስ ቅዱስ ስም ሁለተኛ ክፍል «ቅዱስ» የሚለው ነው። «ቅዱስ» የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙ እጅግ አስፈላጊ ቃሎች እንዱ ነው። እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ እራሱን «ቅዱስ» ብሎ ይጠራል። ደሞም ከእርሱ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ቅዱስ እንዲሆኑ ይጠይቃል። (ዘሌዋ. 1፡44-48፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡16)። ስለዚህ ቅዱስ መሆን ከእግዚአብሔር መሠረታዊ ባሕርያት አንዱ ነው። ይህ የቅድስና ባሕርይ ለመንፈስ ቅዱስ እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ከስሙ ጋር ተያይዞ እናገኘዋለን።  «ቅዱስ» ወይም «ቅድስና» የሚለው ቃል የመጣው መለየት፥ መራቅ፥ ልዩ መሆን ከሚለው አሳብ ነው። በብሉይ ኪዳን አንድ እንስሳ «ቅዱስ» የሚባለው ከእንስሳት መንጋ ውስጥ ተመርጦ ለእግዚአብሔር ለመሠዋት ሲለይ ነበር። ቅዱስ የሚባል ሰው ከዓለምና ከኃጢአት ለእግዚአብሔር የተለየ ሰው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስን «ቅዱስ» ብሎ ሲጠራ በውስጡ የተካተቱ ሁለት መሠረታዊ አሳቦች አሉ።  በመጀመሪያ፥ ልዩ የመሆን አሳብ በውስጡ አለ። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው። ምክንያቱም በምድር ላይ የሚመላለው ምንም የለም። እርሱ ሰው አይደለም። ነገር ግን እግዚአብሔር ነው። አልተፈጠረም። ነገር ግን ዘላለማዊ ነው። የእግዚአብሔር ወይም የኢየሱስ ባሕርይ የሆኑ በሙሉ የመንፈስ ቅዱስ ባሕርያት ናቸው። በኃይሉ፥ በችሎታውና በባሕርይው ከእግዚአብሔር አብና ከወልድ በስተቀር በሰማይም ሆነ በምድር የሚመስላው የለም።  በሁለተኛ ደረጃ ፥ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ የሆነው ከኃጢአት የተለየ በመሆኑ ነው። ኃጢአትን አድርጐ አያውቅም። በህልውናውም ሆነ በባሕርይው ኃጢአት ብለን ልንጠራው የምንችለው ነገር ፈጽሞ የለም። ስስታምነት ወይም ጥላቻ ወይም ምግባረ ብልሹነት የለበትም። ብርሃንና ጨለማ ፈጽም እንደማይስማሙ ሁሉ ቅድስናና

የመንፈስ ቅዱስ ስሞች Read More »

የመንፈስ ቅዱስ ዋና ኃላፊነቶች ምንና ምን ናቸው?

ጥያቄ፡- ሀ) የመንፈስ ቅዱስ ዋና ኃላፊነቶች ምንና ምን ይመስሉሃል? ለ) የሚከተሉትን ጥቅሶች በማንበብ ከኃላፊነቶቹ ጥቂቶቹን /አንዳንዶቹን ጥቀስ። ዮሐ 15፡26፥ 16፡6-15፤ ሮሜ 8፡2፥ 4-6፥ 11፥ 14-16፣ 23፥26–27፤ 1ኛ ቆሮ. 9፡9-12፥23-25  ከዚህ ቀደም እንደጠቀስነው ክርስቲያኖች ብዙ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ጉዳይ ላይ በከፍተኛ ደረጃ የማይስማሙባቸው ነጥቦች አሏቸው። አንዳንዶች የሚያስተምሩት መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ሕይወት ወይም በቤተ ክርስቲያን ታምራትን ለማድረግ እንደተሰጠ ነው። የመንፈስ ቅዱስ ተቀዳሚ ተግባር በልሳን ማናገር ወይም ታምራትን ማድረግ ይመስላቸዋል። ሌሎች ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ተቀዳሚ ተግባር እኛን መቀደስ እንደሆነ ያምናሉ። ሌሎች መንፈስ ቅዱስ እኛን የእግዚአብሔር ልጆች በማድረጉ ሥራ ላይ ያተኩራሉ። ትክክለኛው የትኛው ነው? ሚዛናዊ የሆነ መልስ መፈለግ አለብን። መንፈስ ቅዱስ በሁሉም የሕይወታችን ገጽታ ውስጥ ይገባል። እነዚህን እገልግሎቶቹን በቅደም ተከተል የማስቀመጫ መንገድ አለን? የዚህ ጥናት መጽሐፍ ጸሐፊ የመንፈስ ቅዱስ ገጸ-ብዙ አገልግሎቶች በሁለት ዋና ሥራዎቹ ተጠቃልላው መቅረብ ይችላሉ ብሎ ያምናል።  1. መንፈስ ቅዱስ የተሰጠን እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ መኖር ይችል ዘንድ ነው።  ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብብ። ዘጸአ 25፡8፥ 22፥ 29፡42 46፥ 33፡7፤ 1ኛ ቆሮ. 3፡16፥ 6፡19። ሀ) ስለ መገናኛው ድንኳን ዓላማ ምን ያስተምሩናል? ለ) አማኞችና ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ማደሪያ ስፍራ ስለ መሆናቸው ምን ያስተምሩናል?  የብሉይ ኪዳን ታሪክ ተቀዳሚ ዓላማ እግዚአብሔር እስራኤላውያን ከሚባሉ ልዩ ሕዝቦች ጋር ስላለው ግንኙነት ማውሳት ነው። እግዚአብሔር በምድር ላይ ካሉ ሕዝቦች በሙሉ ለይቶ በመምረጥ ልዩ ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር ገባ። እግዚአብሔር ይህን ካደረገባቸው ዓላማዎች አንዱ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር እጅግ ቅርብ በሆነ መልኩ ግንኙነት እንዲኖረው ላማድረግ ነበር። እግዚአብሔር እንደ አብርሃምና ዳዊት ያሉ ሰዎችን የመረጠ ቢሆንም እንኳ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለመጠበቅ የሚያመልኩበት አንድ የሚታይ ስፍራ ከሌላቸው በስተቀር አስቸጋሪ ሆኖ አግኝተውታል። ሰዎች ዛፎችን፥ ፀሐይንና ጨረቃን ወዘተ የመሳሰሉ የሚታዩ ነገሮችን የማምላክ ፈተና ሁልጊዜ ነበረባቸው። ስለዚህ እግዚአብሔር የእርሱን ህልውና ሕዝቡ ዘወትር የሚያስብበትን አንድ የሚታይ ነገር ላመሥራት ወሰነ። ከእስራኤላውያን ዘንድ የሚያደርገውን ልዩ መገኘት የሚያመላክት እንድ ሕንፃ እንዲሠሩ አዘዘ። እግዚአብሔር የእርሱን ልዩ መገኘት ማለትም የክብሩ ደመና የሚያርፍበትን፥ በመጀመሪያ የመገናኛ ድንኳን በኋላ ደግሞ ቤተ መቅደሱ እንዲሠራ አደረገ። . እግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል ለማደር ፈለገ (ዘፀኦ 25፡8)። ሕዝቡ እንዲያመልኩት እርሱም ቅርብ እንዲሆናቸው ፈለገ። የሚያሳዝነው እውነታ ግን የመገናኛው ድንኳንና የክብሩ ደመና በመካከላቸው እያለ እንኳ እስራኤላውያን ወደ ጣዖት አምልኮ አዘነበሉ።  በመጀመሪያ እግዚአብሔር ያለምንም ሕንፃ እራሱን ከግለሰቦች ጋር አዛመደ። ቀጥሎም ለእርሱ ልዩ መገኘት ሕንጻ እንዲሠራ አደረገ። በአዲስ ኪዳን ግን እግዚአብሔር እራሱን ከሕዝቡ ጋር የሚያዛምድበትን መንገድ እንደለወጠ እናያለን። እግዚአብሔር በሕዝቡ ውስጥ ለመኖር ወሰነ። ይህን ያደረገው እንዴት ነበር? እግዚአብሔር አብ በልጆቹ ሁሉ ውስጥ ይኖራልን? ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በልባቸው ይኖራልን? በአንዳንድ መንገድ እግዚአብሔር እብና ኢየሱስ ክርስቶስ በልባችን የሚኖሩ ቢሆኑም እንኳ በሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች ልብ ውስጥ የሚኖረው የሥላሴ አካል እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው። በተቀዳሚ እርሱ በሕይወታችን በመኖሩ እግዚአብሔር እብና እግዚአብሔር ወልድ በልባችን ይኖራሉ (ዮሐ 4፡23)። አስደናቂው እውነት አሁን የእግዚአብሔር ልጅ በሆነ ሁሉ መንፈስ ቅዱስ በሕይወቱ በቋሚነት መኖሩ ነው። መንፈስ ቅዱስ አንድ ጊዜ ወደ ሕይወታችን የሚመጣ በሌላ ጊዜ ደግሞ የሚሄድ አይደለም። እርሱ ሁል ጊዜ በዚያ ይገኛል። ወዳጃችን ነው። መንፈስ ቅዱስ አጽናኛችንና ጠበቃችን ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት እውነተኛ ለማድረግ በዚያ አለ።  ዘላለማዊና ኃያሉ አምላክ በልብህ ውስጥ ይኖራል! ምን ዓይነት አስደናቂ እውነት ነው!  ጥያቄ፡- ሀ) እግዚአብሔር በልብህ ውስጥ የመኖሩ እውነታ የሚያበረታታህ እንዴት ነው? ለ) ማስጠንቀቂያ የሚሆንህስ እንዴት ነው?  ዓለምን የፈጠረው በአንተ ውስጥ ይኖራል! ይሁንና፥ ይህ በአንተ ውስጥ የሚኖረው እስራኤላውያንን ባለመታዘዛቸው በከባድ ሁኔታ የቀጣቸው እግዚአብሔር ነው። ምን ዓይነት አበረታችና አስፈሪ እውነት ነው። በምንዋሽበት ጊዜ በውስጣችን ያለው መንፈስ ቅዱስ ይሰማና ያዝናል። የፍትወተ ሥጋ ኃጢአት ስንፈጽም በውስጣችን ያለው መንፈስ ቅዱስ ሁልጊዜም ይመለክተናል። መልካም ሆነ ክፉ ስሆንንበት ጊዜ ሁሉ መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር ነው።  2. የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በተቀዳሚ ኢየሱስ ክርስቶስን ማሳየት ነው።  ጥያቄ፡- ዮሐ 16፡5-15 አንብብ። እነዚህን ጥቅሶች ስለ መንፈስ ቅዱስ ሥራ ምን ያስተምሩናል?  መንፈስ ቅዱስ አምላክ ቢሆንም እንኳ እርሱ ትሑት ስለሆነ ለራሱ አትኩሮትን ወይም ከብርን ለማግኘት አይፈልግም። ግቡ ሰዎች ወደ እርሱ እንዲመለከቱ ወይም እርሱን እንዲያመልኩት አይደለም። የብርሃን ጨረር የሰዎችን አትኩሮት ወደ ሌላ ነገር እንደሚያመላክት የመንፈስ ቅዱስ ተቀዳሚ ተግባር ትኩረቶቻችንን በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እንድናደርግ ነው። ይህንንም በአራት ዋና ዋና መንገዶች ይፈጽማል።  1. መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ዓይኖቻችን በመክፈት ለደኅንነታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንድንመለከት ያደርጋል።  2. ኢየሱስ ክርስቶስን እንድናመልክ የሚረጃን መንፈስ ቅዱስ ነው።  3. የመንፈስ ፍሬን በማፍራት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንድንመሰል በሕይወታችን የሚሠራው መንፈስ ቅዱስ ነው።  4. መንፈሳዊ ስጦታዎችን በመስጠት ኢየሱስ ክርስቶስን ወክለን የክርስቶስ አካል የሆነችውን ቤተ ክርስቲያንና ዓለምን እንድናገለግል የሚያደርግ መንፈስ ቅዱስ ነው።  ጥያቄ፡- መንፈስ ቅዱስ በሕይወትህ እነዚህን እራት ነገሮች እንዴት እንዳደረገ ምሳሌዎችን ዘርዝር።  ጥያቄ፡- ሀ) በዚህ ዘመን ያሉ ሰዎች አትኩሮታቸውን ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚያደርጉት ወይም ጨርሶ እንደሌለ አድርገው የሚቆጥሩት ለምን ይመስልሃል? ለ) ከዚህ ትምህርት ስለ መንፈስ ቅዱስ በጥንቃቄ የማጥናትን አስፈላጊነት በተመለከተ ምን ልትማር ትችላለህ? ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

የመንፈስ ቅዱስ ዋና ኃላፊነቶች ምንና ምን ናቸው? Read More »