የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ

መንፈሳዊ ስጦታ (ሮሜ 12፡1-8)

ጥያቄ፡- ሮሜ 12፡1-8 በጥንቃቄ አንብብ። ሀ) እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገው መሥዋዕት ወይም መንፈሳዊ የአምልኮ ተግባር ምን ዓይነት ነው? ለ) መለወጥ ያላበት የእኛነታችን ክፍል የትኛው ነው? የመላወጡስ ውጤት ምንድን ነው? ሐ) እራሳችንን ከሌሎች ጋር እያወዳደርን በምናይበት ጊዜ ራሳችንን እንዴት መመልከት እንዳለብን ጳውሎስ የሰጠን ማስጠንቀቂያ  ምንድን ነው? መ) ለእያንዳንዱ ሰው ‹የእምነትን መጠን› የሚሰጠው ማን ነው? ሠ) ቤተ ክርስቲያን ከአንድ አካል ጋር የምትመሳሰለው እንዴት ነው? ረ) በዚህ ስፍራ የተጠቀሱት ስጦታዎች ምን ያህል ናቸው? ሰ) በስጦታዎች መካከል ካለው ልዩነትና ከስጦታዎች አጠቃቀም በዚህ ክፍል ልንማር የምንችላቸው ጠቃሚ እውነቶች ምንድን ናቸው?  የሮሜ 12፡1-8 መሠረት  የሮሜ መጽሐፍ እግዚአብሔር ለድነት (ደኅንነት) ያለው ዕቅድ በአጭሩ የቀረበበት ነው። በዚህ መጽሐፍ የመጀመሪያዎቹ ምዕራፎች ጳውሎስ ዓለም ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት በመሥራት ምክንያት ጥፋተኛ መሆኑን አሳውቋል። ማንኛውም ሰው የሚድንበት ብቸኛው መንገድ ደግሞ በእምነት ወደ ክርስቶስ በመመለስ እንጂ የእርሱን ጽድቅ በመፈለግ ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመድረስ የራሱን መንገድ በመፈለግ እንዳልሆነ አስረድቶአል። የሮሜ መጽሐፍ ከሚያተኩርባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች አንዱ እግዚአብሔር ለአይሁድ ሕዝብ የሰጠው የብሉይ ኪዳን ሕግ ከአዲሱ የእግዚአብሔር ሕዝብ ማለትም ክርስቲያኖች ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ማጤን ነው። ጳውሎስ ሲናገር የብሉይ ኪዳን ሕግ መልካምና እግዚአብሔር የተጠቀመበት ቢሆንም እንኳ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከእንግዲህ በኋላ አስፈላጊ አይደለም ይላል። ታዲያ የብሉይ ኪዳን ሕግጋትን የተለማመዱትና (ለምሳሌ የአሣማ ሥጋን የማይበሉ) የራሳቸው ባሕል ያላቸው ክርስቲያን አይሁዶች፥ በአብዛኞቹ የብሉይ ኪዳን ሕግጋት ሥር ከማይተዳደሩት (ለምሳሌ የአሣማ ሥጋን ከሚበሉት) የአሕዛብ ክርስቲያኖች ጋር አብረው የሚኖሩት እንዴት ነው?  (ሮሜ 12-16 ለዚህ ተግባራዊ ችግር መልስ በመስጠት ላይ ያተኩራል።  ሮሜ 12፡1-2  ሮሜ 12፡1-2 ጳውሎስ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ጨምሮ ሌሎች ትምህርቶቹን ሁሉ የመሠረተበትን አጠቃላይ የመከራከሪያ አሳብ የሚያቀርብበት ክፍል ነው። በመጀመሪያ፥ ጳውሎስ ሲናገር ክርስቲያኖች በእግዚአብሔር ምሕረት ላይ አትኩሮት ማድረግ አለባቸው ይላል። የአይሁድ ክርስቲያኖች ፈጽሞ የተላየ ታሪካዊ መሠረት ካላቸው ከአሕዛብ ጋር ተስማምተው ለመኖር ፈቃደኛ የሚሆኑት የሚያድናቸው ባሕላቸው ቅርሳቸው ወይም የብሉይ ኪዳን ሕግጋትን መጠበቃቸው ሳይሆን የእግዚአብሔር ምሕረት መሆኑን ከተነገዘቡ ብቻ ነው። የዳንንና ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ ግንኙነት ያለን ማንኛችንም አብረን መኖር የምንችልበት መሠረት የእግዚአብሔር ምሕረት ነው። ከተለያየ ብሔር መውጣታችንን ለመክፋፈላችን ምክንያት ካደረግን መሠረታዊውን እውነት ዘንግተናል ማለት ነው። ከየትኛውም ባሕል ወይም ነገድ እንውጣ፥ ምንም ያህል ድሃ ወይም ሀብታም ብንሆን፥ ወንድም ሆነ ሌት እንሁን በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት እኩል እንቀርባለን (ገላ. 3፡28-29)። በዚያ ያለነው ክምሕረቱ የተነሣ ብቻ ነው። በክርስቲያኖች መካከል ስለ መንፈስ ቅዱስ እንኳ የሚደረግ የቃላት ጦርነት በእግዚአብሔር ምሕረት ላይ ከማተኮር ይልቅ በትዕቢት በራስ ጽድቅ በማጉላት ላይ ያነጣጠረ ነው።  ጥያቄ፡- ሀ) በኢትዮጵያ ያሉ ክርስቲያኖች ብዙ ጊዜ የሚጋጩባቸውን ነገሮች በምሳሌነት ዘርዝር። ለ) በሚጋጩበት ጊዜ ያዳናቸውን የእግዚአብሔር ምሕረት የረሱ መሆኑን ይህ እንዴት ያሳያል?  በሁለተኛ ደረጃ ፥ ጳውሎላ የሚነግረን ኃጢአተኞች ሳለን እግዚአብሔር ስላደረገው ምሕረት ስናስብ ከእኛ ዘንድ የሚጠብቀው ምላሽ ሰውነታችንን የተቀደሰ መሥዋዕት አድርጐ ማቅረብ መሆኑን ነው። መሥዋዕቶች ምን እንደሆኑ አይሁድም ሆኑ አሕዛብ ያውቁ ነበር። በብሉይ ኪዳን ሥርዓት አምልኮና አሕዛብ የአምልኮተ ጣዖት ሥርዓት መሥዋዕቶች የተለመዱ ነበር። በመሥዋዕት ውስጥ ሁልጊዜ የእንስሳት ሞት አላ ማለት ይቻላል ሰዎች በቀድሞ ዘመን እንስሳትን መሥዋዕት ያቀርቡ የነበረ ቢሆንም፥ ጳውሎስ ግን በቤተ ክርስቲያን እዲስ ዓይነት መሥዋዕት መኖሩን ገለጸ። ይህም እራሳችንን መልስን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ማድረግ ነው። ለመሥዋዕት የሚቀርበው እንስሳ እንደሚሞት እንሞታለን ማለት አይደለም። ይልቁኑ ይህ ሥዕላዊ እገላላጽ ነው። በሮማ 6 ጳውሎስ የሚያስተምረው ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንደምንኖር ነው። ጳውሎስ ይህንኑ አባባል በሮሜ 12 ላይ በመጠቀም የሚያስተላልፍልን መልእክት፥ ስለ እኛ ለተደረገው የእግዚአብሔር ምሕረት ተመጣጣኝ ምላሽ የሚሆነው እራሳችንን ለእግዚአብሔር መልሰን ማስረከብ መሆኑን ነው። ለራሳችን የላዊ ፈቃድ መሞት አለብን። በሌላ ስፍራ ጳውሎስ በዋጋ ተገዝተናል ይላል (1ኛ ቆሮ. 6፡20)። እራሳችንን መሥዋዕት አድርገን ለእግዚአብሔር መስጠት ማለት ያለ ምንም ቅደመ-ሁኔታ ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ ለእርሱ እንሰጣለን ማለት ነው። አንተ ገዝተኻኛል እኔ የአንተ ነኝ በእኔ የምትፈልገውን – እድርግ። ወደ ፈልክበት ላከኝ ማለታችን ነው ዕቅዳችንን፥ ሕልማችንንና ፍላጐታችንን ሁሉ ለእርሱ ሰጠን ማለት ነው።  ጳውሎስ እንደሚናገረው እራሳችንን ሕያውና ቅዱስ መሥዋዕት አድርጐ የማቅረብ ዝንባሌ «መንፈሳዊ የአምልኮ ተግባር» ነው። የአምልኮአችን፥ የዝማሬአችን፥ የስብከታችን፥ አሥራትን የመስጠታችንና መንፈሳዊ ስጦታዎችን የመጠቀማችን መሠረቱ በሙሉ እራሳችንን መሥዋዕት አድርጐ የማቅረብ ዝንባሌ መሆን አለበት። እራሳችንን ለመስጠት ካልፈለግን የምናደርጋቸው ማናቸውም ነገሮች በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እያገኝም። ድምጻችን እስኪዘጋ ድረስ ብንዘምርም እንኳ መላ ሕይወታችንን ለእግዚአብሔር እስካልሰጠን ድረስ ቃላትን መለፍለፍ ብቻ ይሆናል። እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ያለንን ገንዘብ ሁሉ ብንሰጥም እንኳ መላ ሕይወታችንን ካልሰጠነው የምናደርገው ሁሉ ከንቱ ነው። 1ኛ ቆሮ. እንደሚያስተምረን የፍቅር መንፈስ ሊሰፍን ይገባል። ይህ የሚሆነው ደግሞ እራሳችንን ለእግዚአብሔር አሳልፈን ስንሰጥ ብቻ ነው።  በሦስተኛ ደረጃ፥ ጳውሎስ የሚለው ከእግዚአብሔርና ከእኛ እጅግ ከሚለዩ ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖረን እእምሮአችን መለወጥ አለበት። ክርስቲያኖች ከመሆናችን በፊት እናስባቸው የነበሩ ነገሮች፥ ለእኛ እጅግ ጠቃሚ የነበሩ ነገሮች፥ ይቆጣጠሩን የነበሩን ባሕላዊ ነገሮች ሁሉ አሁን መለወጥ አለባቸው። አስተሳሰባችንን የምንቀይረው እግዚአብሐር የሚፈልጋቸውን ነገሮች ለማድረግ በመፍቀድ ነው። እግዚአብሔር እንድናስባቸው የሚፈልጋቸውን ነገሮች ስናስብ፥ እግዚአብሔር አስፈላጊ ናቸው ያላቸውን ነገሮች ስናደርግ ያኔ እግዚአብሔር እንዴት እንድንመላለስ እንደሚፈልግ እናውቃለን። በሌላ አባባል ጳውሎስ እንዳለው «የእግዚአብሔርን ፈቃድ» እናውቃለን። ይህንን ስናደርግ የእግዚአብሔር መንገድና፥ «ፈቃድ መልካም ፍጹምና ደስ የሚያሰኝ» የመሆኑን እውነታ እንለማመዳለን (ሮሜ 12፡2)።  ጳውሎስ በዚህ ቦታ ባይናገረውም እንኳ ሌሎች ክፍሎችን የምናጠና ብንሆን እራሳችንን ለእግዚአብሔር ማቅረብ አስተሳሰባችንንና ተግባራችንን መቀየር ስሰብአዊ ጥረት ብቻ ሊደረግ እንደማይቻል የተረዳን መሆኑን ማየት እንችል ነበር። ይልቁኑ ይህ በውስጣችን የሚሠራው የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ነው።  ጥያቄ፡– ከላይ የተጠቀሱትን ሦስት ነገሮች ብናስታውስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከፍተኛ ስምምነት የሚኖረው እንዴትና በምን ዓይነት መንገድ ነው?  ሮሜ 12፡3-8  ጳውሎስን ያሳሰበው ነገር አስተሳሰባችን የተለየ መሆን እንደሚገባው ብቻ አልነበረም። አእምሮአችን መታደስ ያለበት ተግባራችንም እንዲለወጥ ነው። ተግባራችን በኢየሱስ ክርስቶስ አካል ውስጥ የሚኖረንን የእርስ በርስ ግንኙነት ይወስናል። ጳውሎስ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በታደሰ አእምሮ ቁጥጥር ሥር ከመኖር፥ ሰውነቱን ሕያው መሥዋዕት አድርጐ ከማቅረብ ጋር በጥብቅ ያቆራኘዋል። በዚህ ክፍል ውስጥ የሚከተሉትን እውነቶች ልብ በል።  1. መንፈሳዊ ሕይወቱና እግዚአብሔር የሰጠውን መንፈሳዊ ስጦታዎች ማወቅ የእያንዳንዱ ክርስቲያን ኃላፊነት ነው። ጳውሎስ ለክርስቲያኖች ሲናገር «እንደ ባለ አእምሮ ስለማሰብ» ተናግሯል። የዚህ ክፍል ቀዳሚ መልእክት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች አጠቃቀም ጉዳይ ነው። ይህ ዐረፍተ ነገር የሚያሳየን ልንጠነቀቅባቸው የሚገቡ ሁለት በተለያየ አቅጣጫ የከረሩ አሳቦች መኖራቸውን ነው። የመጀመሪያው፥ የትዕቢት አሳብ ነው። በመታበይ ስለ ራሳችን በምናስብበት ጊዜ ለመገምገሚያ የምንጠቀመው የተሳሳተ መመዘኛን ነው። እራሳችንን ከሌሎች ከእኛ የባሱ ናቸው ብለን ከምናስባቸው ጋር እናወዳድራለን። በልባችን ትዕቢት በሚኖርበት ጊዜ የበላይነት ስሜት ያድርብናል። እኔ ወንድ ነኝ አንቺ ለት ነሽ ስለዚህ ከአንቺ እሻላለሁ። እኔ ከተማረ ቤተሰብ ሆንህ አንተ ከወዛደር ቤተሰብ ነህ። እኔ ከምርጥ ጐሳ ነኝ፤ እንተ የባሪያ ጐሳ ነህ። በዓለምም ሆነ በቤተ ክርስቲያን ፀብን የሚጋብዙ እንደነዚህ ዓይነት ዝንባሌዎች ሁሉ የሚመነጩት ክትዕቢት በሚወጣ እኔ እበልጥ እንተ ታንስ ባይነት ነው። ለላ ራሳችን ባላን በትዕቢት የተሞላ ግምት ሰዎች ሲያፋጥጡን ቁጡና ቀናተኞች ሆነን እንታያለን። ይህም ወደ ፀብና ክፍፍል ይመራናል።  መንፈሳዊ አቋማችንን በመመልከት እራሳችንን ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር በማወዳደር ከእነርሱ የተሻልን እንደሆንን ካሰብን መንፈሳዊ ትዕቢት ይዞናል ማለት ነው። ወይም ስጦታዎችንንና ችሎታችንን ከሌሎች ጋር ስናወዳድር ወደ ትዕቢት ውስጥ እንገባለን። ከእከሌና ከእከሌ በተሻለ ሁኔታ ለማስተማር እችላለሁ የሚለው ብዙ ጊዜ በአእምሮኦችን ብልጭ የሚል አሳብ ነው። ማወዳደር ስንጀምር፥ እኛ ከሌሎች እንደምንቫል እራሳችንን በማሳመን ጥሩ ስሜት እንዲሰማን እናደርጋለን። በርካታ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች

መንፈሳዊ ስጦታ (ሮሜ 12፡1-8) Read More »

መንፈሳዊ ስጦታ ምንድን ነው?

ጥያቄ፡- ሀ) መንፈሳዊ ስጦታ ምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ እንዴት ትመልሰዋለህ? ለ) መንፈሳዊ ስጦታ ከተፈጥሮአዊ ችሎታ የሚለየው እንዴት ነው?  ዛሬ በቤተ ክርስቲያን በመንፈሳዊ ስጦታ ምንነት ላይ በርካታ የተላያዩና የተምታቱ አሳቦች አሉ። አንዳንዶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጥሩ ዘማሪ ይሰውና የመዘመር መንፈሳዊ ስጦታ አለው ይላሉ። የመዘመር ችሎታ ስጦታ ሲሆን ይህን ስጦታ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎችን ለማገልገል ልንጠቀምበት እንችላለን። ነገር ግን ክርስቲያን ያልሆኑ በርካታ ሰዎች የማከም ችሎታ አላቸው። ብዙ ጊዜ ጌታን የማያከብር ዜማ ያዜማሉ። ስለዚህ ዜማ ከእግዚአብሔር የሚገኝ ስጦታ ቢሆንም ለክርስቲያኖችና ክርስቲያን ላልሆኑም የሚሰጥ ተፈጥሮአዊ ችሎታ ነው። ስለዚህ የመዘመር ችሎታ በራሱ መንፈሳዊ ስጦታ አይደለም። ሌሎች ደግሞ አንዳንድ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያደርጉትን እንደ ተአምራትና ፈውስ የመሳሰሉ አስደናቂ ሁኔታዎችን ብቻ መንፈሳዊ ስጦታዎች ናቸው ብለው ያስባሉ። ሆኖም ቀን ብዙ ጊዜ መንፈሳዊ ስጦታዎች ሌሎችን እንደ መርዳት ሳሉ ቀላል ነገሮች የሚገለጡም ናቸው (ሮሜ 12፡6-8)።  አንድ ሰው መንፈሳዊ ስጦታ «የክርስቶስን አካል የምናገለግልበት የጸጋ ስጦታ ነው» ብሏል። መንፈሳዊ ስጦታ፥ «ቤተ ክርስቲያንን ማለትም የክርስቶስን እካላ እንዲያገለግልበት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለእያንዳንዱ ክርስቲያን የሚያድላው ነፃ ስጦታ» ሲሆን አገልጋዩ የክርስቶስ አካል ለሆነችው ለቤተ ክርስቲያን ሰዎችን በማዝ አገልግሎቱን ይሰጥ ዘንድ የሚያስችላውን ሁኔታ የሚፈጥር ነፃ ስጦታ ነው።  ይኸውም፡-  የቤተ ክርስቲያን ጌታ የሆነውን ክርስቶስን ማምልከ እንዲችሉ፥  ክርስቶስን ወክለው ለቤተ ክርስቲያን ይናገሩ ዘንድ፥  ክርስቶስን እየመሰሉ ያድጉ ዘንድ ሌሎችን እንዲረዱ፥  ክርስቶስን ወክለው የሌሎችንም ክርስቲያኖች ፍላጎት እንዲያገለግሉ።  ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በዓለም ፊት እንዲወክሉ የሚያስችልበት መንገድ ነው።  ቀጥሎ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በተመለከተ ዋና የሚባሉ ትምህርቶችን በአጭሩ እንመለከታለን።  1 እግዚአብሔር ለክርስቲያኖች እንደ ስጦታ የሚሰጣቸው ነገር ነው። ከእግዚአብሔር ጸጋ የሚመጣ ስለሆነ ሠርተን ወይም በጣም መንፈሳዊ በመሆናችን የምናገኘው አይደለም። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከራሱ ፍላጐት በነፃ ለክርስቲያኖች የሚሰጠው ነገር ነው።  2. የሚሰጠው ለክርስቲያኖች ብቻ እንጂ ክርስቲያን ላልሆኑት አይደለም። ስለዚህ አንድ ሰው ከመዳኑ በፊት ሳይሆን ከዳነ በኋላ ብቻ የሚያገኘው ነው። ይህ ማለት ተፈጥሮአዊ ችሎታዎች በራሳቸው መንፈሳዊ ስጦታ ፧ አይደሉም ማለት ነው። ከተፈጥሮ ችሎታ ጋር ሊያያዙ ቢችሉም እንኳ መንፈሳዊ ስጦታዎች ከእግዚአብሔር የሚሰጡ ልዩ ስጦታ ስለሆኑ ከተፈጥር ችሎታ የላቁ ናቸው።  3. የመንፈሳዊ ስጦታዎች ዓላማ ኢየሱስን ወክሎ ሌሎችን ማገልገል ነው (ኤፌ. 4፡1-13፤ 1ኛ ጴጥ. 4፡10-11፤ 1ኛ ቆሮ. 12፡7፥ 21-26፥ 14፡26፤ ሮሜ 12፡4-5)። ስለዚህ ትኩረቱ የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ናት። ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ይናገር ዘንድ ይረዳል። ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኢየሱስን እየመሰሉ እንዲያድጉ ይረዳል። ቤተ ክርስቲያን በውስጧ ያሉት ሰዎች እርስ በርሳቸውም ሆነ በዓለም ያሉትን ያገላሉ ዘንድ ይረዳቸዋል። የእግዚአብሔርን ጸጋ ለሌሎች የምናገለግልበት መንገድ ነው (1ኛ ጴጥ. 4፡10)።  4 መንፈሳዊ ስጦታዎች በርካታ ዓይነት ናቸው። እያንዳንዱ ክርስቲያን ቢያንስ አንድ ስጦታ ማለትም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግልበት አንድ ችሎታ አለው (1ኛ ቆሮ. 12፡7፥1፥ 27፤ ሮሜ 12፡6)። ስጦታዎችን በሙሉ አጠቃሎ የያዘ ክርስቲያን የለም (ሮሜ 12፡4-5፤ 1ኛ ቆሮ. 12፡29-30)።  በዚህ ክፍል የተዘረዘሩት ስጦታዎች ስጦታዎችን በሙሉ ያጠቃለሉ እንደሆነ አናውቅም። ሁሉም ዝርዝሮች የተላያዩ መሆናቸው የሚያሳየው፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት ስጦታዎች ናሙናዎች መሆናቸውንና ሌሎችም መንፈሳዊ ስጦታዎች ተብለው መጠቀስ የሚችሉ ነገሮች መኖራቸውንም ይመስላል። ስለዚህ በአዲስ ኪዳን ከተጠቀሱት ከአሥራ ሰባት ወይም ከአሥራ ስምንት የሚበልጡ መንፈሳዊ ስጦታዎች እንዳሉ ማመን የበለጠ ትክክለኛ ነው።  5. መንፈሳዊ ስጦታ የአገልግሎት ቦታ አይደለም። አንድ ሰው የማስተማር ስጦታ ሳይኖረው ‹መምህር› ተብሎ ሊጠራ ይችላል። መንፈሳዊ ስጦታ የሚለካው አንድ ሰው በአገልግሎቱ በሚያስገኘው ፍሬ እንጂ ለሥራው በመቀጠሩ አይደለም።  6. መንፈሳዊ ስጦታን በማግኘትና በመንፈሳዊ ሕይወት በመብሰል መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት የለም። በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ያልበሰሉ ክርስቲያኖች ሁሉ እንኳ መንፈሳዊ ስጦታ አላቸው። አንድ ክርስቲያን መንፈሳዊ ስጦታዎችን በሚገባ እየተጠቀመ (ለምሳሌ በልሳን ሊናገር ይችላል) መንፈሳዊነት ግን ላይኖረው ይችላል። የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በመካከላቸው በነበረው መከፋፈልና የሥነ ምግባር ጉድለት የተነሣ ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮ. 3፡1-4 ቤተ ክርስቲያናቸውን ዓለማዊ ብሎ ጠርቷታል (1ኛ ቆሮ. 3፡5)። ነገር ግን መንፈሳዊ ስጦታዎች በሙሉ እንደነበራቸው ደግሞ ተናግሯል (1ኛ ቆሮ. 1፡7)። እነዚህ ክርስቲያኖች ስልሳናት እየተናገሩ በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ቁጥጥር ሥር ግን አይኖሩም ነበር።  7. ማንም ሰው መንፈሳዊ ስጦታዎችን በሥራው ሊያገኛቸው ባይችልም ከእግዚአብሔር መጠየቅ እንደሚቻል ቀን ተጽፏል (1ኛ ቆሮ. 12፡31፤ 14፡1። መንፈሳዊ ስጦታዎቻችንን ቶል ብለን ልንተዋቸው ወይም በልምምድና በሥልጠና ልናነሣሣቸው እንደምንችል የሚያመለክቱ ማስረጃ ዎች አሉ። በአዲስ ኪዳን ውስጥ የእግዚአብሔር ሰዎች የሆኑ መሪዎች በመንፈስ ቅዱስ መሪነት መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለሌሎች ክርስቲያኖች ለማስተላለፍ እንደቻሉ በበርካታ ስፍራዎች እንመለከታለን (1ኛ ጢሞ. 4፡14፤ 2ኛ ጢሞ. 16)።  ጥያቄ፡- ከላይ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች በአጭሩ የተመለከትነው አሳብ የምታውቃቸው በርካታ ክርስቲያኖች ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ካላቸው አመለካከት ጋር የሚነጻጸሩት እንዴት ነው?  በአዲስ ኪዳን ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚነግሩን አራት ክፍሎች አሉ። ሮሜ. 12፡1-8፤ 1ኛ ቆሮ. 12-14፤ ኤፌ. 4፡7-13፤ 1ኛ ጴጥ. 4፡7-11። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚያስተምራቸውን ነገሮች በግልጽ ለመረዳት እነዚህን ክፍሎች በጥንቃቄ መመርመር አለብን። በመጀመሪያ አግግርቹን ክፍሎች እናጠናና ቀጥሎ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ክሚያስተምሩት ክፍሎች ዋነኛው የሆነውን 1ኛ ቆሮ. 12-14 እናጠናለን። ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

መንፈሳዊ ስጦታ ምንድን ነው? Read More »

ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች መግቢያ

ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮ. 12፡1 አንብብ። ሀ) ጳውሎስ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ቸል እንዳይሉ ወይም እንዲያውቁ ይፈልግ የነበረው ነገር ምን ነበር? ለ) ዛሬም ክርስቲያኖች በተመሳሳይ መንገድ ቸልተኛ የሆኑበት ወይም የማያውቁት ነገር አለን? መልስህን አብራራ ሐ) በቤተ ክርስቲያንህ መንፈሳዊ ስጦታዎች ያሏቸውን አንዳንድ ሰዎች ጥቀስ። አንዳንድ መንፈሳዊ ስጦታዎች እንዳሏቸው እንድታምን ያደረገህ በሕይወታቸው ያየኸው ነገር ምንድን ነው? መ) አብዛኛዎቹ ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ስጦታዎቻቸውን እግዚአብሔር በሚፈልገው መንገድ እየተጠቀሙ ይመስልሃልን? መልስህን አብራራ።  እግዚአብሔር በእኛ በልጆቹ ላይ በርካታ ስጦታዎችን አፍስሷል። ከድነት (ደኅንነት) ሌላ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ከተቀበልነው ሁሉ ታላቁ ነው። መንፈስ ቅዱስ በልባችን ስላሚኖር ሁሉ ነገራችን ይለወጣል። የእግዚአብሔር ጠላቶች የነበርን እኛ ልጆቹ እንሆናለን። የቀድሞ አባታችን የነበረውን ዲያብሎስን ከመምሰል አሁን አባታችን የሆነውን እግዚአብሔርን ወደ መምሰል እንለወጣለን። የእግዚአብሔር ልዩ ልጅ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንመስል ዘንድ መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን ሁልጊዜ ይሠራል። እንደ ኢየሱስ እንድንኖር፥ እንደ ኢየሱስ ተግባራችንን እንድናከናውንና እንደ ኢየሱስ እንድንሠራ ይረዳናል። በምስክርነታችን፥ በአምልኮአችንና በጸሎታችን ባለን የሕይወት ዘርፍ ሁሉ መንፈስ ቅዱስ ሊረዳን ከእኛ ጋር አለ። ምን ዓይነት ወዳጅ ነው ያለን! መንፈስ ቅዱስ እጅግ በጥልቀት በሕይወታችን ከሚሠራቸው ነገሮች አንዱ የክርስቶስ አካል የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን እናገለግል ዘንድ መንፈሳዊ ስጦታዎችን መስጠቱ ነው።  በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአሳብ ልዩነት ምክንያት ከፍተኛ ክርክር ከሚካሄድባቸው ርእሶች እንዱ የመንፈሳዊ ስጦታዎች ጉዳይ ነው። በአንድ በኩል የመንፈሳዊ ስጦታዎችን ጉዳይ የሚያናንቁ ክፍሎች አሉ። ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ሲናገሩ ወይም ሲያስተምሩ አይታዩም። ከዚህም የተነሣ፥ በቤተ ክርስቲያናቸው መንፈሳዊ ስጦታዎች በአገልግሎት ላይ አይውሉም። ስለዚህ ጥቂት ሰዎች ብቻ መሪ የሚሆኑበትና የሚያገላግሉበት፥ አብዛኞቹ ግን ተሳትፎ ሳያደርጉ ዳር ቆመው የሚያዩበት ቤተ ክርስቲያን ሆኖ ይቀራል። እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት በአምልኮአቸው ወይም በአገልግሎታቸው ያለው መንፈሳዊ ኃይል አነስተኛ ነው።  በሌላኛው ጽንፍ ደግሞ በመንፈሳዊ ስጦታዎች በተለይ በድንቃ ድንቅ የታጀቡ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚያስደስቷቸው ይገኛሉ። ትኩረት የሚያደርጉበት የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ይህ ብቻ ነው። ለመንፈስ ቅዱስ ህልውና ብቸኛ ማረጋገጫ የሚሆኑት መንፈሳዊ ስጦታዎች፥ በተለይም በልሳን እንደ መናገር ያሉ ትኩረት የሚስቡ ሁኔታዎች ናቸው፤ እነዚህ ነገሮች ከሌሉ መንፈስ ቅዱስ አላ ማለት አይቻልም ብለው ያስተምራሉ።  እነዚህ ሁለቱም ክፍሎች ሚዛናዊ ስላልሆኑ ለቤተ ክርስቲያን አደገኞች ናቸው። እንደገና ማስታወስ ያለብን የክርስቲያን ሕይወት ሚዛናዊ መሆኑን ነው። መንፈሳዊ ስጦታዎችን መካድ ወይም መገደብ ስሕተት ሲሆን ይህን ስናደርግ መንፈስ ቅዱስ በክርስቶስ አካል ውስጥ የሚሠራውን የመገንባት ሥራ እናስተጓጉላላን። በመንፈሳዊ ስጦታዎች እጅግ በመፈንደቅ በመንፈስ ቅዱስ ላይም ሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለሚሰጡ ሌሎች ትምህርቶች እኩል ትኩረት አለመስጠት ስሕተት ነው።  ጥያቄ፡ ሀ) በኢትዮጵያ በምትገኝ በዛሬይቱ ቤተ ክርስቲያን እነዚህን ሁላት ዝንባሌዎች የምታየው እንዴት ነው? ላ) ይህ ሚዛናዊነት ማጣት ምን ምን ችግሮችን ፈጠረ?  ይህ ጉዳይ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እጅግ የሚከፋፍል ርእስ ስለሆነ በሚቀጥሉት በርካታ ሳምንታት አዲስ ኪዳን ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚያስተምረውን እንመለከታለን። መንፈሳዊ ስጦታዎች ስለ ነበራቸው ሰዎች ብሉይ ኪዳን የሚጠቃቅስ ቢሆንም መንፈሳዊ ስጦታዎች ምን እንደሆኑና እንዴት ልንገለገልባቸው እንደሚገባ ብዙ አሳብ አልተሰጠም። ለዚህ ትምህርት የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች በተለይ ደግሞ ሐዋርያው ጳውሎስ ባለውላታችን ነው።  ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት። ሮሜ 12፡1-8፤ ኤፌ. 4፡1-16፤ 1ኛ ጴጥ. 4፡7-11 ። እነዚህ ጥቅሶች እያንዳንዳቸው መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በመስጠት ላላለው ሚና ምን ያስተምራሉ?  መንፈስ ቅዱስ የመንፈሳዊ ስጦታዎች ሰጪ  መንፈስ ቅዱስ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች እንዱ አንድ ሰው ወደ ክርስትና ሲመጣ ሰውዬውን ወደ ክርስቶስ አካል መጨመር ነው። ይህን የመንፈስ ቅዱስ ሥራ (ማጥመቅ› ብለነው ነበር። አንድ ክርስቲያን በክርስቶስ አካል ከተጨመረ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ምን ያደርጋል? መልሱ ክሚከተሉት ሦስት ነገሮች አንዱን መፈጸም የሚያስችሉትን መንፈሳዊ ስጦታዎች መንፈስ ቅዱስ ለእያንዳንዱ ክርስቲያን ይሰጣል የሚል ነው።  ህ የክርስቶስ አካል አባል እንደመሆኑ መጠን ከሌሎች ጋር በኅብረት እግዚአብሔርን ማመለክ እንዲችል ይረዳዋል።  2. በክርስቶስ አካል ውስጥ ያሉትን ሌሎችን በእምነት ለማሳደግ ያገላግል ዘንድ ይረዳዋል።  3. ከክርስቶስ አካል ውጭ የሆኑት ወደ ክርስቶስ አካል ይመጡ ዘንድ እንዲያገለግል ይረዳዋል። በአጭሩ ክርስቲያኖች ኢየሱስን እንዲያመልኩ፥ የክርስቶስ አካል የሆነችውን ቤተ ክርስቲያንን) እንዲያሳድጉና በኢየሱስ ስፍራ ሆነው ለዓለም አገልግሎት እንዲሰጡ ይረዳዋል።  አዲስ ኪዳን የሚያስተምረን መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለመስጠት ኃላፊነት ያላበት የሥላሴ አካል መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ነው። በ1ኛ ቆሮ. 2፡1 እንደዚህ የሚል አሳብ ተነግሮናል «ይህን ሁሉ ግን (መንፈሳዊ ስጦታዎችን) ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል።» በዚህ ጥቅስ የምናየው መንፈስ ቅዱስ ለእያንዳንዱ መንፈሳዊ ስጦታዎችን እንዴሰጠ ነው። መንፈስ ቅዱስ በተቀዳሚ ስጦታውን ሰሚቀበለው ሰው ፍላጎት ሳይሆን በራሱ ፈቃድ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ይሰጣል። በ1ኛ ቆሮ. 2፡7 ቀደም ብሎ እነዚህ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች «መንፈስ ቅዱስን መግለጥ» ተብለው ተጠቅሰዋል። ይህ የሆነበት ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ህልውናውን ክሚያረጋግጥባቸው መንገዶች አንዱ ሰዎች መንፈሳዊ ስጦታዎቻቸውን እንዲጠቀሙ ማድረግ ስለሆነ ነው። መንፈሳዊ ስጦታዎች ከሌሉ መንፈስ ቅዱስ እንደሌለ ለመጠርጠር እንችላለን። ወይም መንፈስ ቅዱስ እራሱን እንዳይገልጥ የተከላከለበት መንገድ አለ ማለት ነው። ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች መግቢያ Read More »

ሰይጣንን ድል የማድረግ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት

መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ኃይል ለእኛ ዝግጁ እንዲሆን ያደርጋል። (የሐዋ.1፡8)  ጥያቄ፡- የሐዋ 1፡4፥ 8 አንብብ። ሀ) ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በኢየሩሳሌም እንዲቆዩ የነገራቸው ለምንድን ነው? ለ) ደቀ መዛሙርት መንፈስ ቅዱስን በሚቀበሉበት ጊዜ ምን እንደሚሆን ነው ኢየሱስ ተስፋ የገባላቸው?  ኢየሱስ ወደ መንግሥተ ሰማያት የመመላሻው ወቅት በደረሰ ጊዜ ላደቀ መዛሙርት ግልጽ ትእዛዛትን ሰጣቸው። በኢየሩሳሌም ቆዩ አላቸው። ወደ ቀድሞ ኑሮአቸው ወደ ገሊላ መመለስ አልነበረባቸውም። ስለ ኢየሱስ ሕይወት ለሌሎች የመመስከር አገልግሎታቸውንም መጀመር አልነበረባቸውም። ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን እስኪልክ ድረስ መቆየት ነበረባቸው። መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ በሚወርድበት ጊዜ የእግዚአብሔር ኃይል በእጃቸው እንደሚሆን ነበር። ለኢየሱስ ለመሥራት ዝግጁ መሆን የሚችሉት በዚያን ጊዜ ብቻ ነበር። ስለዚህ ማንኛውም ሰው ሲድን መፈጸም ከሚጀምሩት ዐበይት የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች አንዱ አዲሱ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔርን በሚያስከብር አኗኗር እንዲኖር ኃይል ማስታጠቅ ነው።  ብዙ ጊዜ ስለ መንፈስ ቅዱስ ኃይል ስናስብ ውጫዊ የሆኑትን የሚስቡ ነገሮችን እናስባለን። አስደናቂ የሆነ ፈውስና አጋንንት ማስወጣት መንፈስ ቅዱስ በሰው ሕይወት ውስጥ በኃይል ለመሥራቱ ማረጋገጫ ነው ብለን እናስባለን። የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ግን ሰሌሎች የተለያዩ መንገዶችም ይታያል። ውጤታማ በሆነ መንገድ መስክሮ ሰዎችን በኢየሱስ በኩል ወደሚያድን እምነት ለማምጣት ኃይል ይጠይቃል። አዲስ ክርስቲያን በሕይወቱ አድጐ ኢየሱስን እስኪመስል ባሕርይው እንዲለወጥ ለመርዳት ኃይል ይጠይቃል። ለደት ውስጥ በጽናት ለመቆየትና ያለ ፍርሃት ለኢየሱስ ለመኖር ኃይል ይጠይቃል። የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በክርስቲያን የትኛውም የሕይወት አቅጣጫ ተፈላጊ ነው።  እዚህ ስፍራ ላይ በአጭሩ ልንነጋገርበት የሚገባን፥ ለመንፈሳዊ ሕይወትና አገልግሎት የግድ አስፈላጊ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል እቅጣሚ አለ። ይህም ሰይጣንና አጋንንትን በቁጥጥር ሥር የሚያደርግ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ዓለም በሁለት ዓይነት ሰዎች እንደምትከፈል ያሳየናል። እነርሱም የጻኑና ያልዳኑ፥ የጨለማው መንግሥት አካል የሆኑና የብርሃን መንግሥት አካል የሀኑ፥ ሰይጣን አምላካቸው የሆኑና እግዚአብሔር አምላካቸው የሆኑ ናቸው (ኤፌ 2፡1-3፤ 5፡8–13፤ 2ኛ ቆሮ. 4፡3-4፤ ዮሐ 12፡31፤ 16፡11)። አዳምና ሔዋንን ከመፈተኑ በፊት በኃጢአት ከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ ሰይጣን እግዚአብሔርንና ዕቅዱን ለመዋጋት የሚችለውን ሁሉ አድርጓል። እግዚአብሔርን የሚዋጋበት ልዩ መንገድ የእግዚአብሔርን ሕዝቦች በማጥቃት ነው። በአዲስ ኪዳን በተደጋጋሚ ከሰይጣን ማጥቃት እንድንጠነቀቅና እንድንዋጋው ማስጠንቀቂያ የተሰጠን ለዚህ ነው (ኤፌ. 6፡11-12፤ ያዕ. 4፡7፤ 1ኛ ጴጥ. 5፡6-9)።  ሰይጣን ክርስቲያን ያልሆኑ ሰዎችን መዋጋት አያስፈልገውም። ምክንያቱም እንዴ በእርሱ ኃይልና ቁጥጥር ሥር የገቡ ስለሆኑ ነው። በእነርሱ ላይ የሚሠራው እንዳያምኑ መከላከልን ብቻ ነው። ነገር ግን በእግዚአብሔር ልጆች ላይ ጥቃቱን ያነጣጥራል። በንቃት ለእግዚአብሔር ክብር የማይኖሩና የማይመሰክሩ ዓለማዊ ክርስቲያኖችንም ሰይጣን አያጠቃቸውም። አንዴ አሸንፎአቸዋልና።  ጥያቄ፡– ሰይጣን እማኞችን በማጥቃት ሊያሸንፋቸው የሚጥርባቸውን መንገዶች ዘርዝር።  ሰይጣን ብዙ ጊዜ የሚያጠቃው እግዚአብሔርን በመፍራት የሚኖሩ ንቁ ከርቲያኖችን ነው። ይህንን በተላያዩ መንገዶች ያደርጋል። ኃጢአታዊ ተፈጥሮአቸውን የማባበልና የመሳብ ኃይል ያላትን ዓለምን በመጠቀም ያጠቃቸዋል። ዓላማውም ኃጢአትን አድርገው የክርስቶስን ስም እንዲያሰድቡ ነው። ስሜታቸውንና ሥነ ልቡናቸውን በማጥቃት ተላሩ እንዲቆርጡና ለኢየሱስ የድል ሕይወት እንዳይኖሩ ያደርጋቸዋል። አገልግሎታቸውን በማጥቃት ፍሬያማ እንዳይሆኑ ለማድረግ ይጥራል። ለእግዚአብሔር ክብር እንዳይኖሩ በጨለማው መንግሥት ላሉ ሌሎች ሰዎች ምስክር እንዳይሆኑ ለማድረግ ቤተሰባቸውን፥ ጓደኞቻቸውን፥ ጤንነታቸውንና ሌሎች ነገሮቻቸውንም ሁሉ ይዋጋል። በአንዳንድ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ በተለይ ክርስቲያኑ ወይም የቤተሰቡ አባላት ከዚህ ቀደም በአንዳንድ የጥንቆላና የመተት አሠራር የተያያዙ ከነበሩ ወይም ወንጌል ከዚህ ቀደም ፈጽሞ ተሰብኮ በማይታወቅበት ቦታ የደረሰ ከሆነ ሰይጣን ክርስቲያኖችን በታላቅ ኃይል ይጫጫናቸዋል።   ክርስቲያኖች ስለ ሰይጣን ኃይልና በሰይጣን ሥራ ላይ ጽኑ የሆነ ተቃውሞን ስለማድረግ ሁለት እጅግ የተራራቁ አስተሳሰቦች አሏቸው። አንድ ሰው እንዲህ ብሏል። ሰይጣን የሐሰት ትምህርቶቹን ሁልጊዜ የሚያመጣው ሰዎች ከሁላት በአንዱ እንዲወድቁ ለማድረግ በሁላት አቅጣም ጥንድ ጥንድ እያደረገ ነው። ሰው ቢስት በሁለቱም አቅጣጫ መትረፍ በማይችልበት ነጠላ ግንድ ወንዝን እንደ መሻገር ያህል፥ ሰይጣን በአንድ ወይም በሌላ የሐሰት ትምህርት የክርስቲያኑን ውድቀት ይጠብቃል። ሰይጣን ይህን ሁኔታ አምርሮ እንዲቃወም ክርስቲያኑን በማነሣሣት ወደ ተቃራኒው ጽንፍ ተስፈንጥሮ በስሕተት ላይ እንዲወድቅ ያደርገዋል። ይህ ክርስቲያኖች ሰይጣንንና ሥራዎቹን በሚረዱባቸው የተለያዩ ሁኔታዎች ላይ ተከስቷል። በርካታ ክርስቲያኖች በተላይ በምዕራባውያን አገሮች የሚገኙ ስለ ዲያብሎስ እንቅስቃሴዎች እጅግ ተጠራጣሪ የሆኑና ሰይጣን ክርስቲያኖችን የሚዋጋባቸውን የተለያዩ በርካታ መንገዶች የማያውቁ አሉ። እነዚህ ሰዎች፥ በምድር ላይ የሚደረግ ማንኛውም ነገር በስተጀርባ ሆነው የሚያንቀሳቅሱት ሰይጣንና አጋንንት (በኃጢአት ምክንያት የተጣሉ መላእክት ናቸው ብለው የሚያስቡ አንዳንድ አክራሪዎችን ያያሉ። እነዚህ ክርስቲያኖች፥ በሽታዎች ሁሉ መልካም ያልሆኑ አጋጣሚዎች ሁሉ፥ አደጋዎች ሁሉ፥ ሐዘን ሁሉ፥ ወዘተ… ቀጥኛ የሆነ የሰይጣን ውጊያ ነው ሲሉና ሰይጣንን በመገሰጽ ሊያስወግዱት ሲጥሩ ያያሉ። ስለዚህ፥ ወደ ተቃራኒው ጽንፍ ከመስፈንጠርና ማንኛውንም የሰይጣን ልዕለ-ተፈጥሮአዊ እንቅስቃሴ እቅልሎ በማየት በሕይወታቸው ሊመጣ የሚችለውን የሰይጣን ውጊያ ትኩረት ይነፍጉታል። በዚህ ምክንያት በሰይጣን ውጊያ ብዙ ጊዜ ይሸነፋሉ። ሰይጣን በዓለም ላይ ስላላው ኃይልና እንቅስቃሴ እናሳ ግምት ይሰጣሉ። የሰይጣንን ጥቃቶች አውቀው እራሳቸውን ስለማያዘጋጁ በቀላሉ ይሸነፋሉ። እነርሱና ቤተ ክርስቲያኖቻቸው ኃይል የሌላቸውና ውጤት አልባ ናቸው።  በሌላኛው ጽንፍ ያሉት ሰይጣን ከሁሉ ነገር በስተጀርባ አለ በማለት ከሁሉ ነገር ውስጥ ሰይጣንን ለማስወጣት የሚሞክሩት ናቸው። ከበረዳቸው ሰይጣንን ያስወጣሉ። በቤተ ክርስቲያን ፕሮግራም ከመጀመራቸው በፊት ሰይጣንን ከሕንፃው ያስወጣሉ። በትምህርት ቤት ከፈተና ከወደቁ ሰይጣንን ያስወጣሉ። ሰይጣንን እጅግ ስለሚፈሩ ለሰይጣን የማይገባውን ስፍራ ይሰጡታል። እውነቱ በእነዚህ ነገሮች መካከል ላይ ስለሆነ ከእነዚህ ከሁለት አጽናፍ ስሕተቶች በአንዱ ላይ እንዳንወድቅ እጅግ መጠንቀቅ አለብን።ይህ የክርስትና ሕይወት ወደ የትኛውም ጽንፍ ክመስፈንጠር ተጠብቆ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ሚዛን አደላድሎ መኖር መሆኑን እንደገና ያስታውሰናል።  ጥያቄ፡- ህ) እነዚህን ሁለት ጽንፎች በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያየኸው እንዴት ነው? ለ) ሚዛናዊ የሆነው አመለካከት የትኛው ነው ትላለህ?  እንደ ክርስቲያኖች ሰይጣን መንፈሳዊ ሕይወታችንን፥ ስለ ኢየሱስ የምንሰጠውን ምስክርነትና በአኗኗራችን የምንሰጠውን ምስክርነት ለመደምሰስ ባለው ዕቅድ ላይ መንቃት አለብን። ሰይጣን እጅግ ኃይለኛ የሆነ ጠላታችን መሆኑን ብንገነዘብም እርሱን በመፍራት ግን መኖር የለብንም። ሁልጊዜ በእርሱ ላይ በድል ለመኖር እንችላለን። መኖር አለብን። ሰሚደርስብን ነገር ሁሉ ውስጥ የሰይጣን እጅ እንዳለ ማሰብ ግን ክሚገባው በላይ ለእርሱ ክብርንና ተፈሪነትን መስጠት ይሆናል።  ሰይጣን በሕይወታችን ወይም በአገልግሎታችን አንዳንድ አቅጣጫዎች በብርቱ ሊያጠቃን እንደሚተጋ ካወቅን እንዴት እንቋቋመዋለን? ልናስታውሳቸው የሚገቡ ሦስት መሠረታዊ እውነቶች አሉ።  ሀ. ሰይጣን ኃይለኛና ያልተሸነፈ ጠላት አይደለም። ይልቁኑ የተሸነፈ፥ በክርስቲያኖች ላይ ያለው ኃይል የተወሰደበት፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሊመለስ በእግዚአብሔር የሚሰጠውን ፍርድ ሊቀበል የሚጠባበቅ ነው። በቆላ. 2፡5 ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሰይጣንና አጋንንትን በስፍራው «ኃይላትንና ሥልጣናትን» ተብለው የተጠቀሱትን ስለማሸነፍ ተጠቅሷል። (ዕብ 2፡14-15 ደግሞ ተመልከት።) ሰይጣን ክርስቲያኖችን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአተኞችና የኃጢአት ደመወዝ ደግሞ ሞት ስለሆነ (ሮሜ 6፡23) ዘላለማዊ ቅጣት የሚገባቸው እንደሆነ አድርጐ የሚከስበትን ሥልጣን በመስቀል ላይ ተቀምቷል። ኃጢአታችንን ሁሉ በራሱ ላይ በማድረግና ስፍራችንን ወስዶ በመሞት ኢየሱስ ዕዳችንን ከፍሎ ጥፋተኛና ሞት የሚገባን ካደረገን ማንኛውም የሰይጣን ክስ ነፃ አድርጐናል። ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛችን ስንቀበልና በእምነት ሞቱ በእኛ ምትክ እንደሆነ ስናውጅ በእግዚአብሔር ፊት ፈጽሞ ዳግመኛ በጥፋተኛነት ለፍርድ እንቀርብም። ምክንያቱም ኃጢአታችን በሙሉ በክርስቶስ ደም ተሸፍኗል። ኃጢአትን በምናደርግበት ጊዜ ከኢየሱስ ጋር ያለን ግንኙነት ይበላሻል። ነገር ግን ከዘላለም ፍርድ በታች ወደሚጥለን የጥፋተኝነት ስፍራ እንደገና አንመለስም። ክርስቲያኖች ጥፋተኞች እንደሆኑ እንዲያስቡ በማድረግ ሊያታልላቸው መሞከሩን አይተውም። ነገር ግን በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም (ሮሜ 8፡1)።  ሰይጣን የሥልጣንና የኃይሉን ስፍራ እንዳጣ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ሊታገልና ሊዋጋ በቅርቡ ወደ ምድር ይጣላል (ራእ. 12፡12)። ይሁን እንጂ እንደሚጠፉ የተረጋገጠ ነው። እርሱና ተከታዮቹ፥ ማለትም አጋንንትና የማያምኑ ሰዎች ሁሉ ወደ እሳት ባሕር ይጣላሉ (ራእ 20፡10፥ 14-5)። ሰይጣን ሙሉ ለሙሉ በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ነው። የመጨረሻ ፍርድ የተወሰነበት ስለሆነ ስለ ፍርቶ ሊያደርግ የሚችለው

ሰይጣንን ድል የማድረግ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት Read More »

መንፈስ ቅዱስ የክርስቲያኖች ሕይወት ኢየሱስን እንዲመስል የሚሰጠው አገልግሎት

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በጀርመን አገር ለተራቡ ሰዎች ምግብ ያድሉ ስለነበሩ የቃል ኪዳን አገሮች ወታደሮች የሚነገር ታሪክ አለ። በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ስለ ጦርነት ብቻ የሚያውቅ አንድ ትንሽ ልጅ ምግቡ ሊታደል ተራ ደርሶት ድርሻውን በሚቀበልበት ጊዜ ለወታደሩ እንዲህ ብሎ እንደጠየቀ ይነገራል «ጋሼ፥ እርስዎ ኢየሱስ ነዎት እንዴ?»  ትናንትና ከእግዚአብሔር አብና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንድናደርግ ስላሚረዳን የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ተመልክተናል። ይህ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ስልባችን የሚኖረውን ዘላለማዊ አምላክ እንድናመልክና ወደ እርሱ እንድንጸልይ የሚረዳበት ነው። ዛሬ ኢየሱስን እንድንመስል ስለሚያደርገው የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት እናጠናለን። ትንሹ ልጅ ወታደሩን የጠየቀው ጥያቄ ዛሬም ዓለም እኛን በየዕለቱ የሚጠይቀን ጥያቄ ነው። ኢየሱስን እንመስል እንደሆነ ለማረጋገጥ ይከታተሉናል። ኢየሱስን እንመስል ዘንድ በልባችን ውስጥ መሥራት የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ነው። ጌታ ወዳለበት እስክንደርስ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት እይቋረጥም። መንፈስ ቅዱስ በባሕርያችንና በተግባራችን ኢየሱስን እንመስል ዘንድ ዕለት በዕለት በዝግታ፥ ቢሆንም ግን በእርግጠኝነት ውስጣዊ ኑባሬአችንን ለመለወጥ ይሠራል።  ጥያቄ፡– በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ ያሉና እግዚአብሔርን በሚፈሩ ክርስቲያኖች ሕይወት የሚታዩ ባሕርያትን ዘርዝር።  ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት። 2ኛ ቆሮ. 3፡17-18፤ 4፡16፤ 1ኛ ዮሐ 3፡2-3፤ ሮሜ 8፡29። ሀ) በእነዚህ ጥቅሶች ለክርስቲያኖች የተሰጡ ተስፋዎች ምንድን ናቸው? ለ) ኢየሱስን የምንመስልባቸው ናቸው ብለህ የምታስባቸውን ከአንዳንድ ምሳሌዎች ጋር ጥቀስ።  ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት። ሮሜ. 8፡29፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡47-49፤ 2ኛ ቆሮ. 3፡18-19፤ ፊልጵ. 3፡20-21፤ 1ኛ ዮሐ 3፡2። ሀ) የበለጠ ኢየሱስን እንድንመስል መንፈስ ቅዱስ የሚያደርጋቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? ለ) መንፈስ ቅዱስ ይህንን በማድረግ በሕይወትህ እንድታድግ ለመርዳት የሚጫወተውን ሚና ያየኸው እንዴት ነው?  መንፈስ ቅዱስ በልባችን ያድር ዘንድ ወደ ሕይወታች ሊመጣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የበለጠ ወደ መምሰል እንድንለወጥ ወዲያውኑ ሥራውን ይጀምራል። አንዳንድ ጊዜ ለብዙ ዓመታት በባርነት ገዝቶን የነበረ ኃጢአትን ወይም ልማድን ለማሸነፍ እንድንችል መንፈስ ቅዱስ ከመቅጽበት ይረዳናል። ለምሳሌ፡= ሰካራም የነበሩ አንዳንድ ሰዎች ወደ ክርስቶስ ሊመጡ ወዲያውኑ አልኮል መጠጥ የመጠጣት ፍላጐታቸው ይሞታል። ብዙ ጊዜ ግን መንፈስ ቅዱስ በጊዜ ብዛት ኢየሱስ እንድንሆን ወደሚፈልገው ደረጃ እንድንደርስ በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ይሠራል። ይህ ሂደት በሽንኩርት ሊመሰል ይችላል። ሽንኩርት ብዙ የተደራረቡ ቆዳዎች ያሉት እንደመሆኑ መጠን መንፈስ ቅዱስም ለውጣችንን የሚያከናውነው ደረጃ በደረጃ ነው። መንፈስ ቅዱስ ኃጢአታችንን በሙሉ በአንድ ጊዜ በቅጽበት ክሕይወታችን አያስወግድም። (ማለትም እርሱን የሚያስከብሩ መጥፎ ልማዶቻችንንና፥ የተሳሳቱ የአስተሳሰብ ዘይቤዎቻችንን ወይም ባሕላዊ ልምምዶቻችንን በአንድ ጊዜ አያስወግድም) ይልቁኑ በሕይወታችን በአንድ ጊዜ አንድን የሕይወታችንን ክፍል በማሳየት ያንን እንድናስተካክል ያደርጋል። ኢየሱስን የማያስከብሩ ልማዶቻችንን ስናስወግድ ወደ ሌላ የሕይወት ክፍል ደግሞ ያልፋል። የዚህን ሂደት ጥሩ ምሳሌ «የመናኝ ጉዞ» በሚለው መጽሐፍ ውስጥ እናገኛለን።  ቀደም ባለው ትምህርት በዳንን ወቅት መንፈስ ቅዱስ ኃጢአታችን እንዳጠበልን ተመልክተናል። ኃጢአት ብናደርግም እንኳ መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ደም ስለሚሸፍነን በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ተብለን እንጠራለን።  እግዚአብሔር ጻድቅ ብሎ የሰጠንን ደረጃ ልናሟላ አንድ መንፈስ ቅዱስ በሕይወታን መሥራት ይጀምራል። ይህ ክርስቶስን እንመስል ዘንድ በሕይወታችን የምናልፍበት የመለወጥ ሂደት ‹መቀደስ) ይባላል።  ጥያቄ፡– የሚከተሉትን ጥቅሶች እንብብ። ኤፌ 1፡4፤ 4፡21-24፤ 5፡25-27፤ ቲቶ 2፡11-12፤ ዕብ 12፡14፤ 2ኛ ጢሞ 2፡21። እግዚአብሔር እንቀደስ ዘንድ ስላ መፈለጉ እነዚህ ጥቅሶች ምን ያስተምራሉ?  ሀ. በንጽሕና በመኖር የኃጢአት ተፈጥሮአችንን በመቆጣጠርና በሕይወታችን ያሉ ኃጢአቶችን በማሸንፍ ኢየሱስን እንድንመስል መንፈስ ቅዱስ ይረዳናል (ሮሜ. 6፡16፤ 2ኛ ተሰ 2፡13፤ 1ኛ ጴጥ 1፡2፤ ሮሜ. 2፡29፤ 8፡4-13፤ ገላ 5፡16)። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተደጋጋሚ እግዚአብሔር «እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ ቅዱሳን ሁኑ» ብሎ አዞናል (ዘሌ 11፡44፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡4-15)። በአዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች ከዓለም ተለይተው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የእግዚአብሔር በመሆናቸው «ቅዱሳን” ተብለው ይጠራሉ።  በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቅድስና ወይም መቀደስ መሠረታዊ ትርጉሙ ‹መለየት» ማለት ነው። ሁለት ዓይነት ቅድስናዎች አሉ። የመጀመሪያው፥ የአቋም ቅድስና ነው። በትምህርት 6 እንደተመለከትነው በዳንንበት ወቅት መንፈስ ቅዱስ ከሠራቸው ሥራዎች አንዱ ከኃጢአታችን እኛን ማጠር እንደሆነ ተመልክተናል (ቲቶ 3፡15)። በኢየሱስ ክርስቶስ በምናምንበት ወቅት ደሙ ኃጢአታችንን በመሸፈን በእግዚአብሐር ዓይን ፊት ንጹሕ ያደርገናል። ነገር ግን በአቋም መቀደሳችንን ወደ ተግባር እንድንለውጠው እግዚአብሔር ይፈልጋል። በሁለተኛ ደረጃ ፥ የምግባርና የአኗኗር ቅድስና አለ። በፊልጵ. 2፡12-13 «በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ መዳናችንን እንድንፈጽም» የታዘዝነው ለዚህ ነው። ከእግዚአብሔር የተቀበልነው ድነት (ደኅንነት) ሊተገበርና እርሱን እንመስል ዘንድ ባሕርያችን ሊለወጥ ይገባዋል።  ይህ ሁለተኛው ዓይነት ቅድስና ሦስት መልኮች አሉት። በመጀመሪያ፥ መቀደስ ማለት ከዓለም ክፉ ሥርዓት መለየት አለብን ማለት ነው። የምንመራው ሕይወት፤ አስተሳሰባችን በልባችን ያለው ውስጣዊ ዝንባሌ ከዓለም ሕይወት ፈጽሞ የተለየ መሆን አለበት።  በሁለተኛ ደረጃ ፥ ከኃጢአት መለየት አለብን። ቅድላና ማለት የኃጢአት ሕይወት አንኖርም ማለት ነው። ከኃጢአት ስመሽሽ እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ መንገድ እንኖራለን።  በሦስተኛ ደረጃ ፥ ለእግዚአብሔር ተለይተን ለአገልግሎት የተሰጠን ልንሆን ይገባል። የኃጢአት ሁሉ መሠረት ዓመፅ ነው። ኃጢአትን በምናደርግበት ጊዜ እግዚአብሔር በሕይወታችን ባደረጋቸው ሕጐች ላይ እናምፃለን ማለት ነው። በቅድስና ስንኖር ግን እግዚአብሔር ለሕይወታችን በደነገጋቸው ሕጐች ለመኖር እራሳችንን ሰጠን ማለት ነው። በቅድስና መራመድ ማለት ሕይወታችንን ለእግዚአብሔር በመስጠት ለራሳችን ሳይሆን ለእግዚአብሔር ክብር እንኖራለን ማለት ነው።  ጥያቄ፡– ክርስቲያን ቅዱስ ሊሆን የሚችልባቸውን ሦስት መንገዶች በምሳሌነት ስጥ።  መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ሁሉ የላቀው እንድንቀደስ እኛን መርዳቱ ነው። ይህ ማለት ከኃጢአት ቁጥጥር ውጭ የሆነ የተለየ ሕይወት እንድንኖር ማስቻሉ ነው። በብሉይ ኪዳን ዘመን እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን በርካታ ሕግጋትን በመስጠት እንዲታዘዟቸው ነገራቸው። ይሁንና የመንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው የማደርና ኃይልን የማስታጠቅ አገልግሎት በዚያ ዘመን ስላልነበር ሕግጋቱን መጠበቅ አልቻሉም። በዚህ ምትክ እነዚህ ሕግጋት ኃጢአትን የማድረግ ፍላጐት እንዳሳደሩባቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይነገረናል (ሮሜ ፡14-24)። እግዚአብሔር የብሉይ ኪቶን ሕግጋትን ከሰጠባቸው ዓላማዎች አንዱ ሰው ምን ያህል ኃጢአተኛ እንደሆነ በማሳየት ለደኅንነታችን ለእግዚአብሔር አንድ ነገርን ለመሥራት ከመታገል ይልቅ ምሕረትን ፍለጋ ወደ እርሱ ዞር እንድንል ለማድረግ ነበር (ገላ 3፡21-25)።  በአዲስ ኪዳን ግን እግዚአብሔር ሰውን ቅዱስ ለማድረግ የሚሠራበትን መንገድ ለወጠ። በመጀመሪያ፥ የእግዚአብሔር አትኩሮት የኃጢአት ፍሬ በነበረው ውጫዊ ተግባር ላይ አልነበረም። ይልቁኑ የኃጢአት ሥር በሆኑት ውስጣዊ ዝንባሌዎች ላይ ነው (ማቴ. 5፡20-48)። አሁን እግዚአብሔር አትኩርት የሚሰጥበት ነገር ለእርሱና ለሌሎች በሚገለጥ ፍቅር ላይ ነው። በእነዚህ ሁለት ውስጣዊ ዓላማዎች የብሉይ ኪዳን ሕግጋት በሙሉ ተጠቃለው ይፈጸማሉ (ማቴ. 22፡37-39፤ ሮሜ 3፡8-10)፥ በሁለተኛ ደረጃ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን በክርስቲያኖች ሕይወት እንዲኖር ስለሰጠ ኃጢአትን የማድረየ ፍላጐትን ለማሸነፍ አሁን ጉልበት አላቸው።  ይሁን እንጂ በኢየሱስ በምናምንበት ጊዜ እግዚአብሔር ኃጢአት የማድረግ ችሎታችንን ከእኛ ይወለዳል ማለት አይደለም። እንደ እውነቱ ከሆነማ መጽሐፍ ቅዱስ በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ኃጢአትን እንደምናደርግ ያስተምራል። በምድር ላይ እያላን ኃጢአት ወደሌለበት ፍጹምነት እንደምንደርስ መጽሐፍ ቅዱስ አያስተምርም። ይህንን ለሚያስተምሩ ክርስቲያኖች ሐዋርያው የሚሰጠው መልስ የሚከተለው ነው «ኃጢአት የለብንም ብንል እራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም። (1ኛ ዮሐ 1፡8)።  ጥያቄ፡– ገላ. 5፡16-25 እንብብ። ሀ) በልባችን ስለሚካሄድ ጦርነት እነዚህ ጥቅሶች ምን ያስተምሩናል? ላ) ይህንን ጦርነት እንዴት እንዳየህ ከሕይወትህ ምሳሌ በመስጠት ግለጽ።  ክርስቲያን በምንሆንበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ አዲስ ተፈጥሮ ይሰጠናል። ይህ አዲስ ተፈጥሮ ከእግዚአብሔር የሚገኝና እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት የሚፈልግ ተፈጥሮ ነው። ነገር ግን ከውስጥ ከልባችን፥ በእግዚአብሔር ላይ ለማመፅና ኃጢአትን ለማድረግ የሚፈልግ ተፈጥሮ ተሰውሮ ይኖራል። በገላ. 5፡16–26 እነዚህ ሁለት ተፈጥሮዎች በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ እንደሚኖሩና በእያንዳንዱ የክርስቲያን ሕይወት እንቅስቃሴ የበላይ ሆኖ ለመቆጣጠር እርስ በርስ በጦርነት ላይ እንደሚሆኑ እናነባለን። በሰይጣን ተጽዕኖ ሥር ያለ ኃጢአታዊ ተፈጥሮ የክርስቲያንን አእምሮና ተግባር በመቆጣጠር በእግዚአብሔር ላይ እንዲያምጽ ለማድረግ ይጥራል። ይህ እግዚአብሔር በልባችን ዙፋን እንዲቀመጥና ለእርሱም በመታዘዝ እንድንኖር ከመፍቀዱ ይልቅ፥ እኔነትን በሕይወታችን ዙፋን ላይ ማስቀመጥና ፍላጎታችንን መፈጸም መሆኑ ተገልጿል። በመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ ሥር ያለው

መንፈስ ቅዱስ የክርስቲያኖች ሕይወት ኢየሱስን እንዲመስል የሚሰጠው አገልግሎት Read More »

መንፈስ ቅዱስ እንድናመልክ ይረዳናል

መንፈስ ቅዱስ አንድ ሰው ከእግዚአብሔር አብና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲያደርግና እንዲያመልክ በልቡ ውስጥ የሚሰጠው አገልግሎት።  በቤትህ ውስጥ ለብቻህ ሆነህ መጽሐፍ ቅዱስህን አንሥተህ ታነባለህ። የመነቃቃት መንፈስ በውስጥህ ይሰማህና ልዩ መዝሙር በመዘመር መጸለይ ትጀምራለህ። የእግዚአብሔር እውነት በጣም ያስተምርሃል። በጣም ቅርብህ እንደሆነና ባለህበት ክፍል ውስጥ እንዳለ ያህል ይሰማሃል። ወይም፥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቁጭ ብለህ ስትዘምር፥ መዘምራን ሲዘምሩ ወይም ሰባኪው ሲሰብክ ስማዳመጥ ላይ ሳለህ በድንገት በኃይለኛ ስሜት ምስጋና ከውስጥህ ፈንቅሎ እስኪወጣ ድረስ የእግዚአብሔር ህልውና ይሰማሃል። ይህ ታላቅ የእግዚአብሔር ህልውና ስሜት የሚመጣው ከየት ነው? ስሜትህ ብቻ ነው ወይስ እየተፈጸመ ያለ ልዩ ነገር አለ? መልሱ፥ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔርን ለአንተ እውን ስላደረገልህ ነው።  ጥያቄ፡- እግዚአብሔር በቅርብህ እንዳለ የተሰማህን አጋጣሚ ሁኔታ ግለጽ። ያ ጊዜ ልዩ የሆነልህ እንዴት ነው?  ከመንፈስ ቅዱስ ዋና አገልግሎቶች አንዱ በሕይወታችን የእግዚአብሔርን ህልውና እውን ማድረግ ነው። እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ዘመን እንዳደረገው አሁን በሰው ሠራሽ ቤት ውስጥ አይኖርም። እግዚአብሔር የሚኖረው በቤተ ክርስቲያንም ሕንፃ ውስጥ አይደለም። እግዚአብሔር የሚኖረው በሰዎች ውስጥ ነው። እያንዳንዱ ክርስቲያንም ሆነ የክርስቲያኑ ማኅበረሰብ «የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ» ናቸው። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በዚያ ይኖራል። በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ህልውና አሑዱ ሥሉስ የሆነው አምላክ በዚያ ይገኛል። ስለዚህ ልባችን አሁን አምልኮ የሚካሄድበት ማዕከል ሆኗል ማለት ነው። መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን በሚኖርበት ጊዜ ኅብረታችንን ከእግዚአብሔር ጋር እውን የሚያደርጉና እርሱን እናመልከው ዘንድ የሚያነሣሡንን የተለያዩ አገልግሎቶች ይፈጽማል።  ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብብ። ሮሜ 8፡16፡26-27፤ 2ኛ ቆሮ. 13፡14፤ ገላ. 4፡6፤ ኤፌ. 2፡18፥ 22፣ 6፡17-18፤ ፊልጵ. 2፡1፤ 1ኛ ዮሒ ፡24፤ 4፡13 ይሁዳ 19። ሀ) በዚህ ስፍራ የተገለጹትን የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች ዘርዝር። ለ) እነዚህ አገልግሎቶች እያንዳንዳቸው ማበረታቻ የሚሆኑህ በምን መንገድ ነው?  ከላይ ባነበብካቸው ጥቅሶች መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ግንኙነት ይረዳን ዘንድ በውስጣዊ ሕይወታችን እንደሚሠራ ለመመልከት እንችላለን። ይህ ቀንኙነት የበለጠ እውን ይሆን ዘንድ የሚያደርጋቸው ነገሮች አንዳንዶቹ ቀጥለው ተዘርዝረዋል (ቀርበዋል)።  ሀ. አሐዱ ሥሉስ የሆነው እግዚአብሔር በውስጣችን እንደሚኖር ያስገነዝበናል (1ኛ ዮሐ 3፡24፤ 4፡13፤ ኤፌ. 2፡19-22)። እግዚአብሔር ያለው ሊደረስበት በማይችል ሩቅ ሰማይ ላይ አይደለም። እንዲሰማን መጮህ የለብንም። እግዚአብሔር በቅርባችን ነው። በልባችን ይኖራል። ሆኖም ቀን ሥጋዊ አካል ስለሌለው በቅርባችን መኖሩ ብዙ አይሰማንም። የልብ ራጅ ብንነሣ እንኳ እግዚአብሔር በዚያ መኖሩን ማረጋገጥ እንችልም። ስላ ህልውናው በስሜታችን ባንገነዘብም እንኳ እርሱ ከእኛ ጋር እንዳለ እናውቃለን። ይህን እንዴት እናውቃለን? በልባችን የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ለመንፈሳችን ህልውናውን ይመሰክርልናል በመመስከር ያረጋግጥልናል)። ክርስቲያኖች ሕያዋን ድንጋዮች መሆናቸውንና እኛም ለኃያሉ እግዚአብሔር መኖሪያ የሚሆን ሕያው ቤተ መቅደስ ሆነን እንድንሠራ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም «ሕያዋን ድንጋዮች» አድርጎ እንደሚገጣጥመን፥ ጳውሎስ ከትላልቅ ውቅር ድንጋዮች የተሠራውን ጥንታዊ ቤተ መቅደስ ስማነፃፀሪያነት በማቅረብ ይነግረናል (ኤፌ 2፡19-22፤ 1ኛ ጴጥ. 2፡4-5)።  ለ. መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆንን ይመሰክርልናል (ሮሜ 8፡16፤ ገላ. 4፡6)። እግዚእብሔርን ማምለክ አስገራሚ የሆነ የተለያዩ ስሜቶች ቅንብር ነው። በአንድ በኩል ‹ፍርሃት» እለ፤ የምናመልከው እግዚአብሔር ታላቅ፥ ብርቱ፥ ግርማ የተሞላና ቅዱስ ነው። እግዚአብሔር የሚባላ እሳት እንደሆነ ተጽፎልናል (ዕብ. 12፡29)። በመጽሐፍ ቅዱስ ሰው ወደ እግዚአብሔር በቀረበባቸው ማናቸውም ጊዜያት በእግዚአብሔር ፊት በፍርሃት ለመስገድ እንደሚገደው ተጽፏል። እግዚእብሔርን ሁሉን ቻይ ፈጣሪ አድርገን ማክበር ካለብን በልባችን ፍርሃትና አክብሮት ሁልጊዜ መኖር ይገባናል።  በሌላ በኩል ደግሞ ጠንካራ የፍቅርና የቀረቤታ ስሜት አለ። ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርት ከዚህ በኋላ ወዳጆች እንጂ ባሮች አይደላችሁም ብሎ ተናግሮአቸዋል (ዮሐ 5፡13-15)። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙ አስደናቂ እውነቶች አንዱ ለጥፋት የተዘጋጀን የእግዚአብሔር ጠላቶች ሆነን ሳላን የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን ነው (ዮሐ 1፡12)። የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባል ነን። ይህን እንዴት እናውቃለን? መሆን ያለብንን ያህል ጻድቅ ሳንሆንም እንኳ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን በማወቃችን የሚመነጨውን ይህን እጅግ የተትረፈረፈ የፍቅር ስሜት የሚሰጠን ምንድን ነው? በልባችን ውስጣዊ ክፍል መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን በሹክሹክታ ድምፅ ይመሰክርልናል፥ ይነግረናል፥ ያሳስበናል። በእግዚአብሐር እጅግ የተወደድን የኢየሱስ ወንድሞችና እህቶች ነን። ኃጢአትን በምናደርግበት ጊዜ እንኳ መንፈስ ቅዱስ ይህን አስደናቂ እውነት በየጊዜው ያስታውሰናል።  ጥያቄ፡- የመንፈስ ቅዱስን የመጀመሪያ ሁለት አገልግሎቶች በሕይወትህ እንዴት እንደተለማመድካቸው ግልጽ።  ሐ. መንፈስ ቅዱስ ወደ እግዚአብሔር ፊት የመቅረብ ዕድልን ይሰጠናል (ኤፌ 2፡18፤ 6፡17-18፤ ይሁዳ 19)። ወደ ከፍተኛ ባለሥልጣን ቢሮ ስንሄድ ወደ እርሱ ከመድረሳችን በፊት ማለፍ ያለብን በርካታ መሳናክሎች አሉ። በመጀመሪያ በቅጥሩ መግቢያ ላይ ወታደሮች ያጋጥሙናል። ቀጥሎ በቢሮው በራፍ ወታደር ያጋጥመናል። በመጨረሻም ቀጠሮ እየተቀበላች የምታገናኝ የባለሥልጣኑን ጸሐፊ እናገኛለን። ይህ ሁሉ የሚደረገው ሰዎች ወደ ባለሥልጣኑ ዘንድ በቀላሉ መቅረብ እንዳይችሉ ነው። እንድ ጠላት መሆኑ በግልጽ የሚታወቅ ሰው ወደ ባለሥልጣኑ ቢሮ ለመግባት ሲሞክር ፈጽሞ አይሳካለትም። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙ አስደናቂ እውነቶች አንዱ እግዚአብሔር ሰውን ከግራቅ ይልቅ ወደ እርሱ ይቀርብ ዘንድ መንገዱን ቀላል ማድረጉ ነው። አዎን የእግዚአብሔር ጠላቶች ነበርን። ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕዳችንን በመስቀል በመክፈሉ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት እንዳንችል የሚያደርጉንን ዋነኛ መሰናክል አስወገደልን። ዋነኛው መሰናክል የተወገደ ቢሆንም እንኳ ወደ እግዚአብሔር አብ ህልውና የሚያቀርበን ያስፈልገናል። ይህም የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ነው። ወደ እግዚአብሔር ህልውና የሚያቀርበን እርሱ ነው። ይህንን እንዴት ያደርጋል? በተቀዳሚ በጸሎታችን አማካኝነት ነው። የአንድ ዕጣን ሽታ ከጢሱ ጋር እንደሚመጣ መንፈስ ቅዱስ ከጸሎታችን ጋር በመሆን ጸሎታችንንና እኛን ወደ እግዚአብሔር ህልውና ያስገባናል። ስለዚህ የምንጸልየው እጅግ ርቆ በሰማይ ላለና ልንደርስበት ወደማንችል እግዚአብሔር አይደለም። መንፈሳችን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወደ እግዚአብሔር ህልውና ይቀርብና ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ለማድረግ እንችላለን። ምን ዓይነት አስደናቂ አሳብ ነው። በመካከላችን አንዳችም መሰናክል ሳይኖር በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ እንደምንገኝ ሁልጊዜ ብንገነዘብ ጸሎታችን እንዴት እውነተኛ ይሆን ነበር!  መ. መንፈስ ቅዱስ እንድንጸልይ መርዳት ብቻ ሳይሆን ራሱም °ጸልይልናል (ሮሜ 8፡26-27)። ሁለት ልጆች ስለነበሩት አንድ ንጉሥ አስብ፥ ንጉሡ እንደሚወድህ ታውቃለህ። ያ ብቻ ሳይሆን ከሁለት ልጆቹ ጋርም ልዩ ግንኙነት አለህ። አንድ ቀን ችግር ውስጥ ወደቅህ። ይህን ሁኔታህን ሁለቱም ልጆች እውቁት። ወደ ንጉሥ ቀርበህ ስለ ችግርህ ከመናገርህ በፊት እነዚህ የንጉሥ ልጆች ተራ በተራ ወደ አባታቸው በመቅረብ ላለ ችግርህ ላንጉሡ ያጫውቱታል። እንድ ላይ በመሆን ከችግርህ ትወጣ ዘንድ እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ተመካከሩ። ወደ ንጉሡ ፊት ስትቀርብ ችግርህን እንዴት እንደምትፈታ ነገሩህ። ኃላፊነት በመውሰድ ችግርህን ሙሉ በሙሉ ለማቃለልም ፈቃደኞች ሆኑ።  ጳውሎስ በሮሜ 8 ላይ በሥዕላዊ አገላለጽ ያቀረበው ይህ ነው። ጳውሎስ የእግዚአብሔር ልጆች የሚደርስባቸውን አብዛኛዎቹን ችግሮች ያውቅ ነበር። በውስጥ ኃጢአተኛና ደካማ የሆነ ተፈጥሮ በውጭ ደግሞ ጠላቶች፥ ስደትና ሞትም ይታገሏቸው ነበር። የሚያጋጥሙን ችግሮች አብዛኛዎቹ እኛ መፍትሔ ልናገኝላቸው የምንችል አይደሉም። በእንደዚህ ዓይነት ጥልቅ ችግር ውስጥ በምንሆንበት ጊዜ ሊረዳንና ሊያበረታታን የሚችለው ምንድን ነው? ጳውሎስ ወደ ሦስት ነገሮች ያመለክተናል። በመጀመሪያ፥ እጅግ የሚወደን አባት አለን፥ ጥልቅ ከሆነ ፍቅሩም የሚለየን የለም (ሮሜ. 8፡39)። በሁለተኛ ደረጃ ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ቀኝ ሆኖ ይማልድልናል። ጳውሎስ በዚህ ስፍራ ለማለት የፈለገው እግዚአብሔር አብ በእኛ ደስ ስለማይሰኝ ሊቀጣን እንደሚፈልግ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ቅጣቱን ለማስቀረት እንደሚማልድልን አይደለም። ይልቁኑ እግዚአብሔር አብ ይወድደናል። ነገር ግን ይህ በቂ ባይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእብ ጋር በመሆን ለችግሮቻችን መፍትሔ ይፈልጋሉ። በሦስተኛ ደረጃ ፥ ይህም በቂ ካልሆነ መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ጋር በመሆን መፍትሔ እንድናገኝ ይረዳናል። እርሱም ደግሞ ስለ እኛ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር አብ ይማልድልናል።  እግዚአብሔር አብ፥ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሁላቸውም ስለ እኛ ይሠራሉ። ይህ ምን ዓይነት መተማመን ይሰጠናል! ከእቅማቸው በላይ የሚሆን ምንም ችግር የለም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ያሸንፈናል? ከእግዚአብሔር ፍቅር ማን ይለየናል? ታላቁ ጠላታችን ሞትም ቢሆን እንኳ ይህን ለማድረግ አይችልም (ሮሜ

መንፈስ ቅዱስ እንድናመልክ ይረዳናል Read More »

የመንፈስ ቅዱስ አማኞችን ወደ እግዚአብሔር ፈቃድ የመምራት አገልግሎት

ጥያቄ፡- ሀ) ከእግዚአብሔር ጋር በአንድ ቤት ውስጥ የምንኖር ቢሆን ኖሮ ኑሮአችን ምን ይመስል ነበር? ለህ ተግባራችንና አኗኗራችን እንዴት ይላወጥ ነበር? ሐ) 1ኛ ቆሮ. 3፡16፥ 6፡19 ተመልከት። ከእግዚአብሔር ጋር የምንኖረው በምን ዓይነት መንገድ ነው?  በፈለግነው ሰዓት በፊቱ ለመቅረብና የፈለግነውን ለመጠየቅ ቀጠሮ ሳያስፈልገን በአንድ ንጉሥ ቤት ውስጥ እንደምንኖር አድርገን እናስብ። የዓለም ሁሉ ንጉሥ ጓደኛችን ፥ አማካሪያችንና፥ የሚወድደን አሳታችን መሆኑን በዓይነ ሕሊናችን እንመልከት። የንጉሥ ሥልጣን በጨመረ ቁጥር ያለን ጥቅምም ይጨምራል።  በአዲስ ኪዳን ውስጥ እንደሚኖር ክርስቲያን ይህ የምንጠቀመው መብታችን ነው። በልባችን ህልውናውን በመሠረተው በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት፥ እግዚአብሔር አብ በልባችን ይኖራል። እካላችን አሁን ማደሪያው፥ ቤተ መቅደሱ ሆኗል። ልባችን ዙፋኑ ሆኗል። በምንፈልገው በቀኑ በማንኛውም ሰዓት ወደ እርሱ ልንቀርበውና የምንፈልገውን ሁሉ ልንጠይቀው እንችላለን። ለእኛ እርሱ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ሊያደርግልን ሙሉ ኃይል አለው። አንዳችም የሚያቅተው ነገር የላም። ከጠላቶቻችን የትኛውም ቢሆን ከእርሱ የሚበልጥ ኃይል የለውም። እኛ ልጆቹ ስለሆንን መንግሥቱንና ብልጽግናውን ሁሉ እንወርሳለን።  አስደናቂ የሆነ መብት ልናገኝ የቻልነው እንዴት ነው? የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው። ይህ ኃጢአተኛ የሆነ ድንኳን አካላችንን እንጽቶ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያደርገናል። ይህ መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ክርስቶስ አካል ውስጥ በሚጨምረን ወቅት በእኛና በእግዚአብሔር መካከል ከሚፈጠረው አዲስ ግንኙነት የሚመነጭ ነው።  በትምህርት 6 በኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመንን መንፈስ ቅዱስ አስደናቂ ሥራውን በሕይወታችን እንደሚጀምር ተምረናል። ይህን ሥራ በተለያዩ ሰርካታ መንገዶች መግለጽ ይችላል። ድነናል፥ ተዋጅተናል፥ ነጽተናል፥ ታትመናል፥ ደግሞም ሕይወታችንን መኖሪያ የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ተሰጥቶናል። ነገር ግን በሕይወታችን የተፈጸመውን ለመግለጽ ደንበኛው መንገድ፥ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ባለን ግንኙነት ምን እየተፈጸመ እንዳለ ማየቱ ነው። በመጀመሪያ፥ ልክ እንደ ዳንን «በክርስቶስ አካል» ውስጥ እንመራለን። መንፈሳዊ በረከቶቻችን ሁሉ የተገኙት «በክርስቶስ» ውስጥ ነው።  ጥያቄ፡– ኤፌ. 1፡3–2፡22 አንብብ። ሀ) «በእርሱ» ወይም «በክርስቶስ» የሚለው ቃል ስንት ጊዜ ተጠቅሷል? ለ) በክርስቶስ በመሆናችን የእኛ የሚሆኑትን በረከቶች ጥቀስ።  በሁለተኛ ደረጃ ፥ በአቋም በክርስቶስ ውስጥ ከሆንንበት ቅጽበት ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስን መልክ የምንመስልበትን ለውጥ ማከናወን ይጀምራል። ይህ ማለት መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን መሥራት ይጀምራል (ሮሜ 8፡29፤ ፊልጵ. 3፡21)። በብዙ መንገዶች ክርስቶስን መምሰል እንጀምራለን። በመጀመሪያ፥ በባሕርይ ክርስቶስን እንመስላለን። የበለጠ ቅዱስ ፥ ጻድቅ፥ አፍቃሪና ታማኝ እንሆናለን። በሁለተኛ ደረጃ ፥ በተግባራችን የበለጠ ክርስቶስን እንመስላለን። በክርስቶስ አካል ውስጥ ላሉ ሌሎች ወገኖቻችንና በመንፈሳዊ ስጦታዎቻችን አማካኝነት ደግሞ በዓለም ላሉት የምናደርጋቸው ነገሮች ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ያደረጋቸው ናቸው። ሦስተኛ፥ ለዓለም ክርስቶስን የምንወክል እንሆናለን። እንደ ክርስቶስ አምባሳደር የእርሱ አፈ ቀላጤዎች እንሆናላን (2ኛ ቆሮ. 3፡18፤ 5፡18-20)።  ሦስተኛ፡ መንፈስ ቅዱስ በመጨረሻ ፍጹም፥ የበሰልንና ኢየሱስ ክርስቶስን በሁሉ መንገድ የምንመስል በምንሆንበት ሂደት ውስጥ ያሳልፈናል። ሂደቱ ወደ ሚጠናቀቅበት ወደ መንግሥተ ሰማያት ይወስደናል። በመስተዋት አምሳላችንን እንደምናይ ስመንግሥተ ሰማያት ኢየሱስ ክርስቶስን እንመስላለን።  ጥያቄ፡– ትምህርት 6ን ተመልከትና አንድ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያምን መንፈስ ቅዱስ የሚያደርጋቸውን የተለያዩ ነገሮች ዝርዝር።  በትምህርት 6 አንድ ሰው በክርስቶስ አምኖ የእግዚአብሔር ልጅ በሚሆንበት ጊዜ መፈስ ቅዱስ በሕይወቱ ስለሚሠራቸው በርካታ የተለያዩ ሥራዎች አጥንተናል። የመንፈስ ቅዱስ አንዱ አገልግሎት (ማጥመቅ፣ እንደሆነም ተመልክተናል። ይህ የውኃ ጥምቀት አይደለም። ይልቁኑ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነው። መንፈስ ቅዱስ እያንዳንዱን ክርስቲያን ማደሪያው በማድረግ የክርስቶስ አካል ወደ ሆነችው የዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን የሚጨምርበት አገልግሎት ነው። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በተለያዩ የክርስቲያን ቡድኖች ጽኑ ክርክርን ያስነሣ ለመሆኑ ባለፉት ሁለት ትምህርቶቻችን ተመልክተነዋል። መንፈስ ቅዱስ ክርስቲያኖችን ሁሉ ለአንዴና ለሁልጊዜ በክርስቶስ አካል ውስጥ የመጨመር አገልግሎቱን ስናይ ከአዲስ ኪዳን መረጃ ዎች አንፃር እውነትነቱ የበለጠ የሚያመዝን ነው። ከዚህ በተነጻጻሪ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት አገልግሎት ግን እራሳቸውን በሰጡ ክርስቲያኖች ሕይወት መንፈስ ቅዱስ የበላይነት የሚወስድበትና ለእምልኮና ለአገልግሎት ኃይልን እንዲለብሱ የሚያደርግበት ተደጋጋሚ ድርጊት ነው።  (ማስታወሻ፡- ክርስቲያኖች የሚሰባሰቡበት ሕንፃ፥ በሚለውና ከየትኛውም ክፍለ እምነት ኢየሱስን እንደ አዳኛቸው በትክክል የተቀሰሉ ክርስቲያኖች፥ የክርስቶስ አካል በሆነችው ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ታቅፈው በአካባቢያቸው የሚመሠርቱት ኅብረት በመባል በሚሰጠው የቤተ ክርስቲያን ትርጉም መካከል ያለውን ልዩነት በአእምሮአችን መያዝ ጠቃሚ ነው። በአዲስ ኪዳን (ቤተ ክርስቲያን› የሚለው ቃል ሁልጊዜ የሚያመላክተው ክፍለ እምነታዊ መሠረታቸው ሳይታሰብ በኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑ ሰዎችን ሁሉ ነው።)  በዚህ ሳምንት መንፈስ ቅዱስ ክርስቲያኖች ኢየሱስ ክርስቶስን እየመሰሉ እንዲሄዱ በሚያደርግበት የመለወጥ ሂደት ውስጥ ከሚሰጣቸው የተላያዩ አገልግሎቶች በኦንዳንዶቹ ላይ እናተኩራለን።  ጥያቄ፡– የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት። የሐዋ. 8፡29፥ 10፡19፥ 11፡12፥ 15፡28፥ 16፡6፥ 20፡22፤ ሮሜ 8፡14፤ 1ኛ ቆሮ. 2፡10። ሀ) በእያንዳንዱ ጥቅስ ላይ የተጠቀሰውን የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ተናገር። ላ) ይህ አገልግሎት ምን ምን እንደሚያጠቃልል አጭር መግለጫ ስጥ። ሐ) ይህን አገልግሎት በሕይወትህ ውስጥ ያስመሰከርኸው እንዴት ነው? 5ኛ ጥያቄ፡- ሀ) አንዲት ውብ ወጣት እንደተዋወቅህና ልታገባት እንዳሰብክ ገምት። ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑንና አለመሆኑን በምን ታውቃለህ? ለ) ሰዎች ብዙ ጊዜ ላሕይወታቸው የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ለማወቅ የሚፈልጉባቸውን ሌሎች ሁኔታዎች ጥቀስ። ሐ) ክርስቲያኖች (የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ የሚጠቀሙባቸውን የተለያዩ ነገሮች ጥቀስ።  በታሪክ ሁሉ እግዚአብሔር ፈቃዱን ለሕዝቡ ገልጿል። በብሉይ ኪዳን ዘመን አንዳንድ ጊዜ ላሰዎች ሕልሞችንና ራእዮችን ይሰጥ ነበር፥ ነቢያትን ይልክ ነበር፥ ለሰዎች በቀጥታ ወይም በተጻፈው ቃሉ አማካይነት ይናገር ነበር። ኢየሱስ ቆይቶ መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ውስጥ ለመኖር በሚመጣበት ወቀት ወደ እውነት ሁሉ እንደሚመራቸው ለደቀ መዛሙርቱ ተስፋ ሰጣቸው (ዮሐ 16፡13)። ክጰንጠቆስጤ ዕለት ጀምሮ እግዚአብሔር ለልጆቹ በሕይወታቸው ውስጥ የሚኖረውን መንፈሱን ሰጥቶአቸዋል። የእግዚአብሔርን ልጆች ወደ እግዚአብሔር ፈቃድ መምራት የመንፈስ ቅዱስ አንዱ ኃላፊነት ነው።  የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ መንፈስ ቅዱስ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ሰዎች የመራበትን የተለያዩ መገዶች ያሳየናል። ለምሳሌ፡- መንፈስ ቅዱስ ለፊልጶስ በቀጥታ በመናገር ትእዛዝን ሰጥቶታል (የሐዋ. 8፡29)። የተናገረው በሚሰማ ድምፅ ይሁን እይሁን አናውቅም። ይህ በመንፈስ ቅዱስ ለተሞላው ሰው የሚገባው ሰልብ ውስጥ በፀጥታ የተነገረ የመንፈስ ቅዱስ ድምፅ ሊሆን ይችላል። መንፈስ ቅዱስ ጴጥሮስ ምን ማድረግ እንዳለበት ራእይን በማሳየትና በራእዩ ውስጥ ድምፅን በማሰማት ነገረው (የሐዋ. 10፡9-19)። በኢየሩሳሌም የነበሩ መሪዎች የብሉይ ኪዳን ሕግን በመጠበቅና በአሕዛብ ድነት (ደኅንነት) መካከል ስላለው ግንኙነት በሚከራከሩበት ወቅት በንግግራቸው ውስጥ መንፈስ ቅዱስ መገኘቱንና ወደ ትክክለኛ ውሳኔም እንደ መራቸው ተገነዘቡ። ይህን እንዴት እንዳወቁ እርግጠኞች አይደለንም፤ ምናልባት ግን መንፈስ ቅዱስ በመካከላቸው በፈጠረው የመንፈስና የአእምሮ አንድነት ሊሆን ይችላል (የሐዋ. 15፡28)። ጳውሎስ በአንዳንድ የእስያ ክፍሎች ወንጌልን ሊሰብክ አስቦ በተዘጋጀበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ እንደ ከለከላው ተጽፎአል (የሐዋ. 16፡6)። መንፈስ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ አንድ ቦታ እንዳይሄድ በምን መንገድ እንደ ገለጸለት እናውቅም። ምናልባትም ከዚያ ቀጥሎ እንዳየው ዓይነት ስራእይ ሊሆን ይችላል። ምናልባትም ሁኔታዎች ትክክል ስላልነበሩ ወደዚያ ስፍራ መሄዱን እግዚአብሔር እንዳልፈቀደ ጳውሎስ ተረድቶት ይሆናል። ምናልባትም እግዚአብሔር ለልቡ ተናግሮት ይሆናል። በተጨማሪ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያት በምን መንገድ መሄድ እንዳለባቸው በእግዚአብሔር ቃል እማካኝነት ይናገራቸው ነበር (የሐዋ. 1፡16-22)። ነቢያትንም በተለያዩ መንገዶች ተጠቅሞባቸዋል (የሐዋ. 11፡27-28)።  ብዙ ጊዜ ክርስቲያኖች ከሚጠይቋቸው ጥያቄዎች አንዱ «የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዴት አውቃለሁ?» የሚለው ነው። አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ከሰማይ «መንገዴ ይህ ነው በዚህ ተመላለስ» የሚል ድምፅ እንዲያሰማን እንመኛለን። እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ እንደዚህ ሊያደርግ ይችላል፤ ግን ብዙ ጊዜ አይደለም። ታዲያ እግዚአብሔር ፈቃዱን ለእኛ የሚያሳውቀው እንዴት ነው? የእግዚአብሔር ፈቃድ ስንልስ ምን ማለታችን ነው?  ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ ስንነጋገር ስለ ሦስት ነገሮች መናገራችን ነው። በመጀመሪያ፥ ነገሮችን ሁሉ የሚቆጣጠርና የሚመራ የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ፈቃድ ስለ መኖሩ ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንረዳው በምድር ላይ የሚፈጸሙ ነገሮች ሁሉ ፍቅርና ጥበብ በተሞላው በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ናቸው። እግዚአብሔር ሳያውቀውና ሳይቆጣጠረው በምድር ላይ የሚፈጻም አንዳችም ነገር የለም። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን እግዚአብሔር ዓላማትንና የሰውን ልጅ ታሪክ

የመንፈስ ቅዱስ አማኞችን ወደ እግዚአብሔር ፈቃድ የመምራት አገልግሎት Read More »

በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ልሳን በመናገር መካከል ያሉ ግንኙነቶች

ጥያቄ፡- «በልሳናት ካልተናገርክ በስተቀር የመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ሙሉ ህልውና የለህም። በልሳናት ካልተናገርህ በስተቀር በመንፈስ ቅዱስ እልተጠመቅህም።» ሀ) እነዚህንና የመሳሰሉትን አባባሎች እንዴት እንደሰማህ ግለጽ። ለ) ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት እስካሁን ካጠናኽው ጥናትህ እነዚህን አባባሎች እንዴት ትመልሳቸዋለህ?  የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ስልሳናት መናገርን ማስከተል አላበት የሚለውን አሳብ ሁሉም ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች የሚያጠብቁት ባይሆንም እንኳ በብዙ ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች አእምሮ ውስጥ ለመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ተቀዳሚ ማረጋገጫው በልሳን መናገር መሆኑ የጸና ነው። ይህ እሳብ የመጣው ከየት ነው? ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚያቀርቡት ማረጋገጫ ምንድን ነው? ለዚህ ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ወደ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ፊታቸውን ይመልሳሉ። ስላ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ያላቸው መረዳት፥ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በክርስቲያኖች ላይ ሲወርድ የመንፈስ ቅዱስ ህልውናው እንዲረጋገጥ ተአምራዊ በሆነው በልሳናት የመናገር ምልክት መታጀብ እንዳለበት ያስተምራል የሚል ነው። ብዙ ክርስቲያኖች ዛሬ በሚለወጡበት ጊዜ በልሳናት ስለማይናገሩ መንፈስ ቅዱስ በኃይል በመምጣት በልሳን ንግግር የሚረጋገጥበት ግልጽ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ «ሁለተኛ ሥራ» መኖር አለበት በማለት ይከራከራሉ።  ጥያቄው የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በእርግጥ በልሳናት መናገርን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አስፈላጊ ምልክት አድርጐ ያቀርበዋልን ? በክርስቲያኖችን ሕይወት መታየት ያለበት ነገር ነውን? በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ በልሳናት መናገር ከመንፈስ ቅዱስ ህልውና ጋር ተያይዞ የቀረበባቸው ሦስት ቦታዎች ብቻ አሉ። በሐዋርያት ሥራ 2፡4 ላይ መንፈስ ቅዱስ በ120 አማኞች ወይም የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ላይ ካመኑ በኋላ እንደወረደ እንመለከታለን። በሐዋርያት ሥራ 10ና 19 ላይ መንፈስ ቅዱስ በአሕዛብ ክርስቲያኖችና በመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ላይ ባመኑ ጊዜ እንደወረደ እንመለከታለን። በሦስቱም ቦታዎች ላይ በልሳናት መናገር የመንፈስ ቅዱስ ህልውና የተረጋገጠበት መንገድ ነው።  ጥያቄ፡- የሐዋርያት ሥራ 2፡1-4፤ 10፡44-47፤ 19፡1-7 አንብብ። ሀ) [በእነዚህ ሦስት ስፍራዎች በልሳናት መናገር የቻሉት እነማን ነበሩ? ላ) በትናንትናው ትምህርት ላይ በመመሥረት መንፈስ ቅዱስ እነዚህን ሰዎች በልሳናት እንዲናገሩ ያስቻለበትን ምክንያት ዘርዝር። መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያን ውስጥ ስለመገኘቱና ከድነት (ደኅንነት) በኋላ የመንፈስ ቅዱስ «ዳግሞ ሥራ» ሆኖ ስለመገለጡ ያለማወላወል እንድናምን እነዚህ ሦስት ሁኔታዎች በቂ ማረጋገጫ የሚሰጡን ይመስልሃልን? መልስህን አብራራ።  ክርስቲያኖች ከደኅንነታቸው በኋላ ለሚቀበሉት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ማረጋገጫው በልሳናት መናገራቸው ነው ለሚለው የሥነ መለኮት ትምህርታቸው የጰንጠቆስጤ ክርስቲያኖች ማስረጃ አድርገው ለማቅረብ የሚጠቀሙባቸው በልሳን ስለመናገር የሚያወሱትን እነዚህን ሦስት ሁኔታዎች ነው። ሉቃስ እነዚህን ታሪኮች የጻፈው መንፈስ ቅዱስ በታሪክ ሁሉ ውስጥ ለሚሠራው ሦስቱ ሁኔታዎች ምሳሌ መሆናቸውን ለማሳየት ነው የሚል መረዳት አላቸው። ነገር ግን ሁኔታው እንደዚህ ነውን? መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ ሁሉ በልሳናት የተናገሩበትን እነዚህን ሦስት ታሪኮች ስንመለከት በልሳናት የመናገር ችሎታ ያረጋግጥ የነበረው የመንፈስ ቅዱስ ህልውናን ነበር? በሥነ መለኮታቸው ካሪዝማቲክ ባልሆኑ ክርስቲያኖች አመለካከት እግዚአብሔር በእነዚህ ሦስት ሁኔታዎች በልሳናት መናገርን እንደ ምልክት አድርጐ የሰጠበት አንድ ልዩ ነገር እየተካሄደ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው። ቀጥለን እያንዳንዱን ታሪክ ለየብቻ እንመለከታለን።  1) የሐዋርያት ሥራ 2፡— በሐዋ. 2 ላይ 120 ደቀመዛሙርት (ያመኑት 3000 ሳይሆኑ) በመንፈስ ቅዱስ በተጠመቁና በተሞሉ ጊዜ ሁሉም በልሳናት መናገር ጀመሩ። ጴጥሮስ እየተፈጸመ የነበረው ምን እንደሆነ ለማያምኑት እይሁድ በሚናገርበት ጊዜ ወደ ብሉይ ኪዳን አመለከታቸው። ጴጥሮስ በልሳን በመናገራቸው ህልውናው የሚረጋገጥበት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ፥ እግዚአብሔር በኢዩ. 2 የተናገረውን ትንቢት መፈጸም ለመጀመሩ ለእስራኤል ማረጋገጫ ነው ይላቸዋል። የሰቀሉት ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት የሚያመጣው መሢሕ እንደሆነ ይገልጽላቸዋል። ሕፃን የነበረችው ቤተ ክርስቲያን የብሉይ ኪዳን ተስፋ የተፈጸመባት የእግዚአብሔር ሕዝብ ሆነች። አይሁዳውያን በብሉይ ኪዳን ሥርዓት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡበት ጊዜ እከተመ። ይልቁኑ የአይሁድ ሕዝብም እንዲድኑና በብሉይ ኪዳን ቃል የተገቡላቸውን በረከቶች በሙሉ እንዲቀበሉ ከተፈለገ፥ ወደ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መምጣት አለባቸው።  ጴጥሮስ የሚሰብከው ነገር በእርግጥ እውነት መሆኑን እይሁዶች እንዴት ይወቁ? እግዚአብሔር ኢየሱስን ከተከተለ ከዚህ ትንሽ ቡድን ጋር እንደነበረ እንዴት ይወቁ? ምንም የማያወዛግቡና ግልጽ ምልክቶች ካላዩ በስተቀር አይሁዳውያን ይህን ናዝራውያን» በመባል የሚታወቀውን የተናቀ እፈንጋጭ የሰሜነኞች አናሳ ቡድን፥ እግዚአብሔር ለገባላቸው የብሉይ ኪዳን ተስፋዎች መፈጸሚያ ነው ብላው ለማመን ያዳግታቸው ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔር ከዚህ ቡድን ጋር እንደነበረ፥ የሚናገሩትም መልእክት እውነት እንደሆነ በግልጽ ለማረጋገጥ እግዚአብሔር በልሳናት የመናገር ስጦታ ለደቀ መዛሙርት ሰጠ። ምልክቱ ትንቢት ወይም ሌላ ልዩ ተአምራት ያልሆነው በልሳናት መናገር የሆነው ለምን ነበር? እርግጠኛ ሆነን በዚህ ምክንያት ነው ለማለት አንችልም። ምክንያቱም ኢዩኤል እራሱም የጠቀሰው ትንቢት እንጂ በልሳናት መናገርን አልነበረም። በዚህ ጊዜ ከዓለም ዙሪያ የመጡ እግዚአብሔር ከደቀ መዛሙርት ጋር ስለመሆኑ የሚታይ ማረጋገጫ የሚሹ አይሁዳውያን ስለነበሩ በልሳን መናገርን እግዚአብሔር እንደ ምልክት ተጠቅሞ ይሆንን? በሚታወቁ ልሳናት መናገር፥ ወንጌልና መንፈስ ቅዱስ፥ ለአይሁድ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ሕዝቦች የተሰጡ ዓለም አቀፍ ስጦታዎች መሆናቸውን ለአይሁድና ለደቀ መዛሙርት የሚያሳይ ስለሆነ ይሆንን? የምንችለው መገመት ብቻ ነው። ግልጽ የሆነው ነገር በልሳናት መናገር የሚያረጋግጠው በኢዩ. 2 ላይ የተሰጡት የተስፋ ቃል ኪዳኖች በመጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን በሚገኙ በእነዚህ ጥቂት ክርስቲያኖች አማካኝነት መፈጻም መጀመራቸውን ነው። ቤተ ክርስቲያን እሁን የእግዚአብሔር ሕዝብ እንጂ የእስራኤል ሕዝብ ወይም በብሉይ ኪዳን እንደ ነበረው የአይሁድ ሕዝብ አልነበረችም።  2. የሐዋርያት ሥራ 10፡- እግዚአብሔር በአይሁድ ሕዝብ እጅግ የተጠሉ ለነበሩት ለአሕዛብ መንፈስ ቅዱስን የመስጠቱ ጉዳይና ህልውናውንም ለአይሁድ ክርስቲያኖች መጀመሪያ በሰጠበት መንገድ ማረጋገጡ ለመጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን እጅግ ጠቃሚ የሆነ እውነት ነበር። እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነታቸው ምክንያት ብቻ ወደ ክርስቶስ አካል እንደ ጨመራቸው ይህ ምልክት ሆኗል። አሕዛብ ላመዳንም ሆነ የቤተ ክርስቲያን አባል ለመሆን አስቀድመው አይሁድ መሆን አይጠበቅባቸውም ነበር። በሐዋርያት ሥራ 11፡1-3 ላይ እይሁድ ሐዋርያው ጴጥሮስ ወደ አንድ አሕዛብ ሰው ዘንድ እንደ ሄደና ወንጌልን እንደ ሰበከላት በሰሙ ጊዜ ያሳዩትን ምላሽ አስታውስ። ጴጥሮስ ለዚህ ጉዳይ የሰጠውን መግለጫ የተቀበሉት መንፈስ ቅዱስ በአሕዛብ ላይ እንደ ወረደ በሰሙ ጊዜ ብቻ ነበር። በሐርያት ሥራ 15 ላይ የተጻፈውን በኢየሩሳሌም ጉባኤ ላይ የተደረገውን ኃይለኛ ክርክር ታስታውሳለህን? ከብዙ ዓመታት በኋላ በርካታ አይሁዳውያን ክርስቲያኖች አሕዛብ ኢየሱስን እንደ መሢሐቸውና አዳኛቸው አድርገው ለመቀበል አስቀድመው አይሁድ መሆን አለባቸው እያሉ ይከራከሩ ነበር። አሕዛብ ወደ ይሁዲነት የሚመጡት በመገረዝና የአይሁድን ሕግ በመጠበቅ ነበር። እግዚአብሔር አሕዛብን እንደ ተቀበላ ለአይሁዳውያን ክርስቲያኖች የሚያረጋግጥበትን ብቸኛ መንገድ መጠበቅ ሳያስፈልግ እግዚአብሔር ለእነርሱም መንፈስ ቅዱስን መስጠቱና ሙሉ ክርስቲያኖች መሆናቸውን ማሳየቱ ነበር። አይሁዳውያን አሕዛብ መንፈስ ቅዱስን እንደ ተቀበሉ እርግጠኞች የሚሆኑበት መንገድ ደግሞ አንድ ልዕለ ተፈጥሮአዊ የሆነ ምልክትን ማየት ነበር። ስለሆነም እግዚአብሔር በፍጹም የእኩልነት ደረጃ መቀበሉን ላማሳየት ከዚህ ቀደም ለአይሁድ የሰጠውን ያንኑ ምልክት ተጠቀመ። ሰው የሚድነው በእምነት ብቻ እንደ ሆነ በግልጽ ለማሳየት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ለአሕዛብ ባወረደ ጊዜ በልሳናት መናገርን ሰጣቸው። ለአሕዛብ ሙሉና ፍጹም ክርስቲያን ለመሆን መገረዝም ሆነ የአይሁድን ሕግ መጠበቅ አላስፈለጋቸውም። እግዚአብሔር ሌላ ምልክት ተጠቅሞ ቢሆን ኖሮ ምልክቶችን በማወዳደር የእኔ ይበልጣል የሚል ክርክር ይነሣ ነበር።  3. የሐዋርያት ሥራ 19፡- መጥምቁ ዮሐንስ ከታላላቅ ነቢያት አንዱ እንደ ነበር ኢየሱስ እራሱ ተናግሯል (ማቴ. 11፡11)። በአገልግሎቱ ጥቂት ዓመታት ዮሐንስ በርካታ ደቀ መዛሙርትን በማፍራቱ ሮም በምትገዛበት ዓለም ሁሉ ተሰራጭተው ነበር። ብዙዎቹ ዮሐንስ በተገደለበት ጊዜ ፍልስጥኤምን ትተው ስለወጡ ለኢየሱስ ሞት፥ ቀብርና ትንሣኤ ምክንያት የሆኑትን ሁኔታዎች አልተመላከቱም ነበር። መጥምቁ ዮሐንስን በምታከብረው ቤተ ክርስቲያን ዓይንስ የሚታዩት እንዴት ነበር? የዮሐንስ ጥምቀት (የደቀ መዛሙርቱን ንስሐ መግባት ያስከተላ) በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሊያደርጋቸው ይችል ነበርን? እግዚአብሔር በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ለመጨረሻ ጊዜ በልሳናት መናገርን ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ ጠቃሚ ትምህርት ለማስተማር እንደ ምልክት ተጠቀመበት። የዮሐንስ ጥምቀት ማዳን የሚችል አልነበረም። አንድ ሰው የሚድነው በኢየሱስ ሲያምን ብቻ ነው። እነዚህ ሰዎች መቼ በትክክል እንደ ዳኑ እንዴት መናገር ይቻል ነበር? የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት እርሱን ይከተሉ ሰነበረ ጊዜ ያልተደረገ፥ ነገር

በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ልሳን በመናገር መካከል ያሉ ግንኙነቶች Read More »

በክርስቲያኖች መካከል ከፍተኛ ልዩነት የሚፈጥሩ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ክፍሎች (ክፍል 2)

የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የሽግግርን ዘገባ የያዘ መጽሐፍ መሆኑን ተመልክተናል። እግዚአብሔር በአንዱ ክፍለ ሕዝብ ማለትም ከአይሁድ ሕዝብ ጋር ከመሥራት ከዓለም ሁሉ ጋር ወደ መሥራት እንዴት እንደተሻገረ ይነግረናል። የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን ለሚፈልጉ ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመናቸውና የመንፈስ ቅዱስ ህልውናን ማግኘታቸው ሁለት ዋና አጣማሪ ኃይል ስለመሆናቸው ይነግረናል። በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ምዕራፍ 2 መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በነበሩት ላይ በመውረዱ አዲስ የእግዚአብሔር ሕዝብ፥ ይኸውም ቤተ ክርስቲያን አድርጐ መሠረታቸው። በሐዋርያት 8 ላይ የቤተ ክርስቲያን ስር እንዴት ለሳምራውያን እንደ ተከፈተና በአዲሱ የእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ በእኩል አቋም አንድ ክፍለ ሕዝብ እንደተጨመረ እናያለን። በእርግጥ እኩል መሆናቸውን ለሁሉም ለማረጋገጥ እግዚእብሔር ለመጀመሪያው የሳምራውያን ክርስቲያኖች የመንፈስ ቅዱስ ህልውናን በልዩና አስደናቂ መንገድ አጐናጸፈ። ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ወደ ሌላ ክፍላ ሕዝብ እንዴት እንደተስፋፋች እንመለከታለን።  1. መንፈስ ቅዱስ በአሕዛብ ላይ ወረደ (የሐዋ. 10)  ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ወንጌል ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በይሁዳ፥ በሰማርያ፥ ከዚያም ለአሕዛብ እስከ ምድር ዳርቻ ሁሉ እንደሚሰበክ ነግሮአቸው ነበር። ደቀ መዛሙርት በመጀመሪያ ያጋጠማቸው ከዘር ጋር የተዛመደ በመዝለል ወንጌልን ለታሪካዊ ጠላቶቻቸው ለሰማርያ ሰዎች ማዳረስ ነበር። ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ደግሞም ለእይሁድ እንዳደረገው መንፈስ ቅዱስን ለሰማርያ ሰዎችም በመስጠት፥ የሰማርያ ክርስቲያኖች በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ እኩል ደረጃ እንዳላቸው እግዚአብሔር ለአይሁድ ክርስቲያኖች እስተማራቸው። ሆኖም ግን ሊያልፉት የሚገባ ሌላ እንድ መሰናክል ነበረባቸው። ይህም ወንጌልን ለአሕዛብ የመስበክ ጉዳይ ነበር። ለብዙ መቶ ዓመታት አይሁዳውያን አሕዛብ ከእግዚአብሔር ጸጋና ድነት (ደኅንነት) ውጪ ናቸው የሚል አስተሳሰብ ነበራቸው። ከእግዚአብሔር ቁጣ ሥር ለጥፋት ተመድበው ይኖራሉ የሚል አሳብ ነበራቸው። ከሳምራውያን ይብስ የተጠሉ ነበሩ። ሳምራውያን በግማሽ ጐናቸው አይሁድ የነበሩ፥ ሙሴንና እግዚአብሔርን የሚያከብሩ ነበሩ። እሕዛብ ጣዖትን የሚያመልኩ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያስተምራቸው ትምህርቶች ሁሉ ጋር የሚቃረኑ ነበሩ። አይሁዳውያን፥ እግዚአብሔር ለአሕዛብ ግድ እንደሌለው ያስቡ ነበር። ስለዚህ ይህን ገደብ ማለፍ እንዲችሉ እግዚአብሔር እንደገና በእስደናቂ መንገዶች ለመሥራትና አሕዛብንም መውደዱን ለማሳየት የሐዋርያቱን ዓይኖች መክፈት ነበረበት።  የመጨረሻውን ግድግዳ ለማፈራረስና ቤተ ክርስቲያንን ለሰው ዘር በሙሉ ክፍት ለማድረግ የመጀመሪያው አሕዛብ ክርስቲያን ቆርኔሌዎስ የእግዚአብሔር መሣሪያ ሆነ። መንፈስ ቅዱስ ለእርሱና ከእርሱ ጋር ላነበሩ ሌሎች አሕዛብ የተሰጠበትን ሁኔታ፥ እግዚአብሔር እሕዛብ ከአይሁድና ከሳምራውያን ጋር እኩል መሆናቸውን ላማሳየት የተጠቀመበት ምልክት ነው።  ጥያቄ፡- የሐዋ. 10፡1-10፤ 23-48 እንብብ። ሀ) ቆርኔሌዎስ ከመዳኑ በፊት የነበረበትን ሁኔታ ግላጽ። ለ) ጴጥሮስ በቁ. 28 ላይ ምን ተምሬያለሁ በማለት ይናገራል? ሐ) ለሌሎች አሕዛብ ገና የማመናቸው ውጫዊ ምልክት እንኳ ሳይፈጸም መንፈስ ቅዱስን የላከላቸው ለምን ነበር? ሀ) መንፈስ ቅዱስ በአሕዛብ ላይ በወረደ ጊዜ የእይሁድ ምላሽ ምን ነበር? ረ) መንፈስ ቅዱስ በአሕዛብ ላይ የመውረዱ ውጫዊ ምልክት ምን ነበር?  1. የሮም ወታደር የነበረው ቆርኔሌዎስ እግዚአብሔርን የሚወድና ከብሉይ ኪዳን ሕጐች ብዙዎቹን የሚጠብቅ ነበር። ነገር ግን አይሁድ በሚሆንበት ሥርዓት አላለፈም። ስለ ኢየሱስም አልሰማም ነበር። ወይም ኢየሱስን ለማመን የሚያበቃ በቂ መረጃ አላገኘም ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔር ለአሕዛብ የድነት (ደኅንነት) በር የሚከፈትበትን ወቅት በወሰነ ጊዜ ቆርኔሌዎስ ካጴጥሮስ ጋር እንዲገናኝና ወንጌልን እንዲሰማ አደረገ። አሁንም እንደገና የምንመለከተው እግዚአብሔር ሐዋርያት ወንጌልን ወደ አሕዛብ እንዲወስዱ ሲያስገድዳቸው ነው። ነገሩ በመጀመሪያ የሐዋርያት ምርጫ እንኳ አልነበረም።  2. ለሁለተኛ ጊዜ እግዚአብሔር ጴጥሮስን የድነት (ደኅንነት) በር ከፋች እድርጐ ተጠቀመበት።  3. እግዚአብሔር ይህን ሁኔታ ጴጥሮስን እጅግ ጠቃሚ ትምህርቶችን ለማስተማር ተጠቀመበት። ይኸውም፥ አሕዛብን ያልነጹ እና የረከሱ ብሎ መናገር እንደሌለበት ነው። ደግሞ እግዚአብሔር እንደማያዳላም መማር ነበረበት። ይልቁኑ «እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ ከእርሱ የተወደደ ነው» (የሐዋ. 10፡35)። እግዚአብሔር ለጴጥሮስና ለቀሩት አይሁድ በሙሉ እርሱ አሕዛብን ልክ እንደ አይሁድ እንደሚወድና በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ በእኩልነት እንደተቀበላቸው ማስተማር ነበረበት።  4. ጴጥሮስ መልእክቱን እንኳ ሳያጠናቅቅ እግዚአብሔርን ይፈሩ የነበሩ አሕዛብ ኢየሱስን ለማመን ገሃድ እንቅስቃሴ ለማድረግ ዕድል ከማግኘታቸው በፊት መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው። ይህ ሙላት ቆርኔሌዎስም ሆነ ሌሎቹ ከማመናቸው በፊት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለዋል ማለት እይደለም። እነዚህ ሰዎች ልባቸው የተዘጋጀ፥ እግዚእብሔርን የሚወዱና የሚያመልኩ ነበር። የቀራቸው ነገር ኢየሱስን ለማመን የሚያስችለውን የመጨረሻ ቃል ማግኘት ብቻ ነበር። ይህንን በሰሙ ጊዜ ያመኑት ወዲያውኑ ነበር።  5. አሕዛብ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት ባመኑበት ቅጽበት እንጂ በወንጌል ካመኑ በኋላ አልነበረም። መንፈስ ቅዱስ አሕዛብ ከዳኑ በኋላ ወደ ሕይወታቸው የመጣበት ሁለተኛ በረከት የሚባል ነገር አልነበረም። ይልቁኑ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ሙላት በአንድ ጊዜ ነው የተፈጸመው።  6. የመንፈስ ቅዱስ በአሕዛብ ልብ ውስጥ መሆኑ የተረጋገጠው፥ በጴንጠቆስጤ ቀን ለአይሁድ በሆነው መንገድ ነበር። እነዚህም፥ እግዚአብሔርን ያመሰግኑና በልሳናት ይናገሩ ነበር። ልሳናቱ በሚታወቁ የሰው ቋንቋዎች ይሁኑ አይሁኑ በቂ መረጃ የለንም። የእሕዛብ ክርስቲያኖች በልሳናት መናገርን የሚያጠኑት ነገር አልነበረም። ምክንያቱም ስጦታው የመጣው በቅጽበት ስለነበር ነው።  7. አሕዛብ መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ የተደረገው አይሁድ በአሕዛብ ላይ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እንደፈሰሰ እንዲያዩ ነበር (የሒ 10፡45)። የአይሁድ ክርስቲያኖች ከዚህ ጊዜ በኋላ አሕዛብን ለመለየት፥ ወይም የእግዚአብሔር ሕዝብ ተብለው ተቀባይነት ከማግኘታቸው በፊት ወደ ይሁዲነት እንዲገቡ ላማስገደድ አልቻሉም። ጴጥሮስ በአይሁድ ክርስቲያኖች ሕግ ተላልፈሃል ተብሎ ሲከሰስ እንዲህ አለ። «…በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላመነው ለእኛ ደግሞ እንደ ሰጠን ያን ስጦታ ለእነርሱ ከሰጠ፥ እግዚአብሔርን ለመከልከል እችል ዘንድ እኔ ማን ነበርሁ?» (የሐዋ. 11፡17)። ከብዙ ዓመታት በኋላ እሕዛብ ወደ ይሁዲነት ሃይማኖት ሳይመለሱ ወደ ቤተ ክርስቲያን የመምጣታቸው ነገር አከራካሪ ነጥብ ሆኖ በተነሣበት ወቅት ጴጥሮስ እንዲህ ብሏል «ልብንም የሚያውቅ አምላክ ለእኛ ደግሞ እንደሰጠን መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሰከረላቸው» (የሐዋ. 15፡8)። እንደ አይሁድና የሰማርያ አማኞች ሁሉ መንፈስ ቅዱስ በአሕዛብ ላይ መውረዱ በእኩልነት ደረጃ የእግዚአብሔር ልጆች ሆነው ተቀባይነት ለማግኘታቸው ዋነኛ ማረጋገጫ ነበር።  8. እግዚአብሔር አዲስ ማኅበረሰብን ወደ ቤተ ክርስቲያን ለማስገባት እንዲያነሣሣ ጴጥሮስን ለመጨረሻ ጊዜ የተጠቀመው በዚህ ወቅት ነው። በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ወደ ክርስቶስ የሚመጡ ከአሕዛብ  መንፈስ ቅዱስን ለመቀበላቸው ምልክት የሆነውን በልሳን የመናገር ስጦታ ለመጨረሻ ጊዜ የተቀበሉት አሁንም ነው።  ጥያቄ፡- በዚህ ገጽ ላይ ያሰፈርካቸውን መልሶችህን ከልስ። በክፍሉ ምንባብ ላይ ከተሰነዘረው ውይይት እኳያ መልሶችህን እንዴት ትለውጣቸዋለህ?  መንፈስ ቅዱስ በሦስት የተለያዩ ዘሮች ላይ የወረደበት ጊዜ ንጽጽር  1. እግዚአብሔር ለክርስቲያኖች በተለይ ደግሞ ለአይሁድ ክርስቲያኖች፥ እያንዳንዱን ክፍለ ሕዝብ እግዚአብሔር እንደተቀበለው ለማሳየት መንፈስ ቅዱስን ከነማረጋገጫ ምልክቶቹ ልዩ ስሆነ መንገድ ላከ።  2. በሦስቱም ሁኔታዎች፡ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስ በሚወርድበት ወቅት ከፍተኛ ሚና ነበረው። በመጀመሪያው ጊዜና ቆርኔሌዎስ ባመነበት ወቅት፥ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን የላከው በቀጥታ ቢሆንም ወንጌልን በማብራራት የተናገረው ግን ጴጥሮስ ነበር። በሌላ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በሳምራውያን ላይ እንዲወርድ መሣሪያ ሆኗል።  3. ለአይሁድና ለአሕዛብ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበላቸው ምልክቱ በልሳን መናገር ነበር። ለሳምራውያን ግን መንፈስ ቅዱስን የመቀበል ምልክት የሆነው ነገር ምን እንደነበር አልተጠቀሰም።  4. ከእነዚህ ቡድኖች ለማናቸውም ቢሆን በሚድኑበት ጊዜም ሆነ ከዳኑ በኋላ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን በተመሳሳይ ድንቅ መንገድ የላከበት ጊዜ የለም። ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ በአስደናቂ መንገድ የተላከበት ተቀዳሚ ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እኩልነት እንዳለ ለማሳየት ነበር። እነዚህ የመንፈስ ቅዱስ አሰጣጥ ሁኔታዎች ሰው በሚያምንበት ጊዜ ሁሉ ወይም አንድ ሰው ፍጹም የሆነ መንፈሳዊ ክርስቲያን ሊሆን መከናወን የሚገባቸው ለመሆኑ የሚያመለክት ምንም ነገር የለም።  5. እሕዛብ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት እንዳመኑ ወዲያውኑ ነው። መንፈስ ቅዱስን ካመኑ በኋላ የተቀበሉት ሳምራውያን ብቻ ናቸው።  ጥያቄ፡– ሀ) በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ባሕላዊ ክፍፍሎች ግለጽ። ለ) እግዚአብሔር የክርስቶስ አካል በሆነችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እነዚህ ሁሉ በእኩልነት ተቀባይነት እንዳገኙ ማስታወሱ ላምን ይጠቅመናል? ሐ) በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በዘር፥ በኑሮ ደረጃ ና በጾታ ልዩነት የሚደረግባቸው አንዳንድ መንገዶች ምን ምን ናቸው? መ) መንፈስ ቅዱስ ክርስቲያኖችን ሁሉ በክርስቶስ አንድ

በክርስቲያኖች መካከል ከፍተኛ ልዩነት የሚፈጥሩ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ክፍሎች (ክፍል 2) Read More »

በክርስቲያኖች መካከል ከፍተኛ ልዩነት የሚፈጥሩ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ክፍሎች (ክፍል 1)

ጥያቄ፡- ሀ) በሕይወትህ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ህልውና ልዩ እውነታ ያደረገባቸውን ጊዜ ግለጽ። ላ) ይህ ጊዜ ከሌሎች ጊዜያት የተላየ ያደረገው ምንድን ነበር? ሐ) የመንፈስ ቅዱስ ህልውናና ኃይል በሕይወትህና በኦገልግሎትህ የተሰማህ ሌሎች ጊዜያት ነበሩን? አንቶንዶቹን ግለጽ። ) እነዚህ ልምምዶች ይበልጥ የሚመስሉት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን ነው ወይም የመንፈስ ቅዱስ ሙላትን ወይስ ሁለቱንም ይመስልሃልን? መልስህን በአብራራ።  ባለፈው ሳምንት በካሪዝማቲክና ካሪዝማቲክ ባልሆኑ ክርስቲያኖች ዘንድ ሰመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና በመንፈስ ቅዱስ ሙላት ላይ ያለውን ክርክር ተመልክተናል። የሐዋርያት ሥራን መጽሐፍና የመልእክቶችን ተዛማጅ ክፍሎችም ተመልክተናል። ከጥናታችን የደረስንበት ማጠቃለያ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ሁለት የተለያዩ አገልግሎቶች መሆናቸውን ነው። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በክርስቲያኖች ሁሉ ሕይወት ውስጥ የተፈጸመ ኃላፊ ተግባር እንደሆነ ነው የተመለከትነው። የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ግን በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ በተደጋጋሚ የሚፈጸምና ክርስቲያኖች አጥብቀን እንድንፈልገው እንኳ የታዘዝነው ነገር ነው። በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ለአንዴና ለመጨረሻ የተፈጸመ ሆኖ ወደኋላ የሚጠቀስ ነው (የሐዋ. 1፡5-17)። ነገር ግን በአማኞች ሕይወት ዘመን በሙሉ ተደጋጋሚ የመንፈስ ቅዱስ ብዙ ሙላቶች እንዳሉ አይተናል።  ጴንጠቆስጤ ያልሆኑ ክርስቲያኖች የመንፈስ ቅዱስን ሥራ በቸልታ የተው ሲሆን ጴንጠቆስጤ ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ትኩረት እንደተሰጠው ሁሉ በእማኞች ሕይወት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ስለሚያከናውናቸው ትኩረት መስጠታቸው ትክክለኛ ነገር ነው። ጰንጠቆስጤዎች በአገልግሎት ውስጥ የእግዚአብሔርን ኃይል አስፈላጊነት በተገቢ መንገድ ስላተኮሩበት እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ባርኳል። ነገር ግን ከሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ አካሄድና ከመልእክቶች ትምህርት ጋር ያለአንዳች ማወላዳት ተጣጥሞ እንዲታይ ከተፈለገ፥ አብዛኛዎቹ በሕይወታቸውና በአገልግሎታቸው የሚለማመዱትና ልዩ ኃይልንም የሚሰጣቸው የመንፈስ ቅዱስ ሙላት እንጂ እነርሱ እንደሚሉት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አይደለም። ከድነት (ደኅንነት) በኋላ በርካታ ጴንጠቆስጤ አማኞች የሚለማመዱት ታላቅ የመንፈስ ቅዱስ ልምምድ መንፈስ ቅዱስ ለእነርሱ ታላቅ ኃይልን የሚያጎናጽፍበት የሙላት አገልግሎት ነው። ጆን ዊምበር የተባላ በሥነመለኮት ትምህርቱ ሳይሆን በልምምዱ ጰንጠቆስጤ የሆነ የትልቅ ቤተ ክርስቲያን መጋቢ እንዳለው የጰንጠቆስጤ ልምምዶች ከሥነመለኮት ትምህርቶቻቸው የተሻሉ ናቸው።  ለእምነታቸው መረማመጃ ስላሆኑትና በሁሉም ክርስቲያኖች ሕይወት መገላጽ ይገባዋል የሚሉትን የጰንጠቆስጤ ሥነመለኮት ቁልፍ ትምህርት፥ ገና ከሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ክፍሎች ማጥናት ይኖርብናል። እነዚህን ክፍሎች የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ሁልጊዜ ራሱን በልሳን የሚገልጸው የመንፈስ ቅዱስ ልዩ የድኅረ-ድነት (ደኅንነት) ሥራ መሆኑን ያስተምራሉን? ወይስ እነዚህ ክፍሎች ሌላ ትርጉም ይኖራቸው ይሆንን? በውዝግቡ ምንጭነት የታወቁ ክፍሎችን ከሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት እናጠናለን።  የመጀመሪይቱ ቤተ ክርስቲያን ታሪካዊ መጽሐፍ የሆነውን የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ለመረዳት ቀላል መጽሐፍ ሊመስለን ይችላል። በአንድ በኩል ትክክል ነው። የተፈጸሙት ታሪኮች ግልጽ የሆኑና ለመረዳትም እጅግ የቀለሉ ናቸው። በሌላ በኩል ግን የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እንደ ሌሎች ታሪካዊ መጻሕፍት ለመተርጐምና ከአሁኑ ዓለም ሁኔታ ጋር ለማዛመድ ያስቸግራል። የሐዋርያት ሥራን መጽሐፍ ጨምሮ ታሪካዊ መጻሕፍትን በሙሉ ለመረዳት አስቸጋሪ የሚሆነው ገላጭ» ስላልሆኑ ነው። ዓላማቸው ምን እንደተፈጸመ በመግለጽ ዛሬም እንዴት መኖር እንዳለብን ጠቃሚ ትምህርት ለመስጠት ነው። ነገር ግን፥ ጸሐፊው ስለተፈጸመ አንድ ድርጊት መልካምነትና ልንከተለው የሚገባ ስለመሆኑ ሳይገልጽ ምን ጊዜ ትረካ ብቻ እንደሚያቀርብ ወይም በታሪኩ ውስጥ እንደተጠቀሰው ሰው እንድንሆን ወይም የተገለጸው ድርጊት ለሁልጊዜ በምሳሌነት ልንከተላው የሚገባ መሆኑን መቼ እንደሚናገር ለማወቅ አስቸጋሪ ነው። ለምሳሌ፡- የሳምሶንን ታሪክ ብንወስድ፡ ሳምሶን በምሳሌነቱ ልንከተለው የሚገባ ሆኖ ነው ታሪኩ የተጻፈው ወይስ ንጽሕና የጐደለውን ኑሮ መኖር ውጤቱ ምን እንደሆነ ለማስጠንቀቅ ይሆን?  በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በቀረበው የገላጭ ትረካ ዓላማ ላይ የተነጣጠረው ይህ ውዝግብ በካሪዝማቲክና ካሪዝማቲክ ባልሆኑ ክርስቲያኖች መካከል መለያየት ከፈጠሩት ምክንያቶች የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ከዘገባቸው አስደናቂ ታሪኮች ውስጥ ጳውሎስ በልብሱ ቁራጭ ወይም በመሐረቡ ሰዎችን ይፈውስ እንደነበር ወይም ጴጥሮስ በመንገድ በሚያልፍበት ወቅት ጥላው ያረፈባቸው በሽተኞች እንደተፈወሱ የሚናገሩ ይገኙበታል (የሐዋ. 5፡12-16፤19፡11-12)። መንፈስ ቅዱስ ለመጀመሪያ በእነርሱ ላይ በወረደ ጊዜ በልሳን የተናገሩ ሰዎች ታሪክም ተጽፏል። ብዙ ካሪዝማቲክ ያልሆኑ ክርስቲያኖች እነዚህ ታሪኮች የተጻፉት እግዚአብሔር የወንጌልን ሥልጣን ለማሳየትና ለማረጋገጥ በመጀመሪያ ክፍል ዘመን ያደረጋችው አስደናቂ ሥራዎች ናቸው ብለው ያምናሉ። እነርሱ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን እንደሚረዱት ከሆነ እነዚህ ድርጊቶች የተጻፉት ዛሬ በዘመናችን መራመድ ስለሚገባቸው ወይም ገና ለሚፈጸሙት በምሳሌነት ለመሆኑም ፍንጭ የላም። ብዙ ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ግን እነዚህ ታሪኮች የተሰጡት መንፈስ ቅዱስ በማንኛውም ዘመን እንዴት እንደሚሠራ ለማሳየት ነው። ስለዚህ የጴጥሮስ ጥላ በቀደመው ጊዜ ፈውስን ካስገን ዛሬም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ጥላ ፈውስን ማምጣት አለበት በማለት ይከራከራሉ። እንደገና የምንመለከተው እመለካከታችን ወይም አስቀድሞ ያለን መረዳት መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እንደምንረዳ እንደሚወስን ነው። ቀደም ብሎ የነበረንን መረዳት ስንዘነጋ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ምን እንደሚያስተምር በጥንቃቄ መመልከት አለብን። በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ያላውን ልምምድ በመልእክቶች ውስጥ በግልጽ ከተሰጡት ትምህርቶች ጋር ማወዳደር አለብን።  ጥያቄ፡– ሁለት ክርስቲያኖች ከድነት (ደኅንነት) በኋላ ስለሚሆነው የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ይነጋገራሉ። አንደኛው መንፈስ ቅዱስ ወደ ክርስቲያኖች የሚመጣው በሚድኑ ጊዜ ነው ይላል። ሌላው ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ወደ ክርስቲያን የሚመጣው ከድነት (ደኅንነት) በኋላ እንደ ሁለተኛ የጸጋ ሥራ ሆኖ ነው ይላል። ስለዚህ ስለ መንፈስ ቅዱስ መምጣትና በልሳናት ከመናገር ጋር ስላለው ዝምድና ምን እንደሚያስተምር የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን በአንድነት ለማጥናት ወሰኑ። የሚከተሉትን ጥቅሶች በጥንቃቄ አንብብ። የሐዋ. 2፡1-13፤ 8፡14-17፤ 10፡23–48፤ 19፡1-7። ሀ) በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ያገኘሃቸውን፥ የሚከተሉትን እሳቦች የሚደግፉትን እውነቶች በዝርዝር ጻፍ። ) መንፈስ ቅዱስ ወደ ክርስቲያን ሕይወት የሚመጣው በዳነበት ቅጽበት መሆኑን፤ 2) መንፈስ ቅዱስ የሚመጣው ከዳነ በኋላ መሆኑን፤ ለ) በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ የባላጠ ድጋፍ ያገኘው የትኛው አመለካከት ነው? ሐ) ስለ እያንዳንዱ ተግባር አፈጻጸም ሠንጠረዥ አዘጋጅና የሚከተሉትን ዘርዝር። ) መንፈስ ቅዱስን የተቀበለው ማን ነው? 2) የመንፈስ ቅዱስ መምጣት ምልክት ተደርጐ የተጠቀሰው ነገር ምን ነበር? 3) በቡድኑ ውስጥ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ ስንቶች ናቸው? 4) መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ሰዎች ምን ማድረግ ነበረባቸው? 5) መንፈስ ቅዱስን በመስጠት ላይ አንዳንድ ጊዜ መዘግየት የነበረው ለምን ይመስልሃል? 6) መንፈስ ቅዱስን ወደሌሎች እንዲያስተላልፍ እግዚአብሔር የተጠቀመበት ማን ነበር? ) መንፈስ ቅዱስ እንዲተላለፍ ምክንያት በሆነው ሰው አማካኝነት ምን ድርጊት ተፈጸመ? መ) በእነዚህ ጥቅሶች ላይ ስለተመሠረተው የሁለቱ ክርስቲያኖች ውይይት ምን ትመልሳለህ?  ከላይ የሰፈሩትን ጥቅሶች ከመመልከታችን በፊት የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የሚናገረው እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር ይሠራ ለነበረው ሥራ የሽግግር ወቅት መሆኑን ማስታወስ አለብን። የብሉይ ኪዳን ዘመን አልፎ ነበር። ኢየሱስ እዲስ ኪዳንን መሥርቷል። ነገር ግን የአዲስ ኪዳን በረከቶችን እጠቃለው ያልተቀበሉ በርካታ የብሉይ ኪዳን አማኞች ነበሩ። እግዚአብሔር እዲሱ ኪዳን በሚገባ ከተደላደለ በኋላ በሠራው ዓይነት መንገድ በመጀመሪያዪቱ ቤተ ክርስቲያን በነበሩ እማኞች ዘንድ ለጥቂት ዓመታት ያልሠራበትን ምክንያት ለመረዳት ይህ ሁኔታ ይጠቅመናል።  1. መንፈስ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ በአይሁድ ላይ መውረዱ (የሐዋ. 2)።  ከአብርሃም ዘመን ጀምሮ እግዚአብሔር የአይሁድ ሕዝብ ለእርሱ የተመረጡ ልዩ ሕዝብ እድርጐ ለያቸው። የአብርሃም በረከት ተካፋይ ለመሆን የሚፈልጉ ሁሉ አይሁድ ሊሆኑና የአይሁድን ባሕል በሙሉ ሊለምዱ ይገባ ነበር። የብሉይ ኪዳን ነቢያት በአዲስ ዘመን የእግዚአብሔር በረከት በአሕዛብ ሁሉ ላይ አልፎ እንደሚፈስስ ቢናገሩም እንኳ የነቢያቱ ትኩረት መሢሑና መንፈስ ቅዱስ ለእይሁድ በሚያመጡት በረከት ላይ ነበር። ኢየሱስ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ የአይሁድ ምድር በነበረችው ፍልስጥኤም እንደ እንድ አይሁድ ኖረ። ደቀመዛሙርቱም አይሁዳውያን ነበሩ።  ሆኖም ግን ወደ መንግሥተ ሰማያት ከመመለሱ በፊት ለደቀ መዛሙርት ወንጌል በአይሁዶች መካከል ብቻ መቅረት እንደሌለበት ተናገረ። ይልቁኑ ደቀ መዛሙርት በዚያን ጊዜ ከነበሩበት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ፤ የአይሁዶች አገር ወደሆነችው ይሁዳ፥ ሰማርያና ወደ ዓለም ሁሉ መስፋፋት ነበረበት።  (የሐዋ. 1፡8 አንብብ።)  ቤተ ክርስቲያን በጴንጠቆስጤ ዕለት መጀመሪያ የተቆረቆረችው በአይሁድ መካከል ነበር። መንፈስ ቅዱስ በአይሁዶች ላይ ወረደ። የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የመጀመሪያዎቹ ስምንት ምዕራፎች መንፈስ ቅዱስ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ በአይሁዶች መካከል

በክርስቲያኖች መካከል ከፍተኛ ልዩነት የሚፈጥሩ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ክፍሎች (ክፍል 1) Read More »