በልሳናት ስለመናገር ተጨማሪ ጉዳዮች (ክፍል 2) የተለያዩ ዓይነት ልሳናት አሉን?
በካሪዝማቲክና ካሪዝማቲክ ባልሆኑ ክርስቲያኖች መካክልና በካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች በራሳቸውም መካከል እንኳ የተለያዩ ዓይነት ልሳናት የመኖራቸው ወይም ያለመኖራቸው ጉዳይ ሌላው አከራካሪ ነጥብ ነው። ጥያቄ፡- በአብዛኛዎቹ በካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች የሚነገሩት ልሳናት በሐዋርያት ሥራ 2 ላይ በሐዋርያት ከተነገሩት ልሳናት የተለዩ ናቸውን? እንደዚህ ብለህ የምታስበው ለምንድን ነው? ክርስቲያኖች እነዚህን ጥያቄዎች የሚመልሱባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ። 1. በልሳናት መናገር ሁልጊዜ በሰው ቋንቋ መናገር ነው። ይህን አመለካከት የሚያንጸባርቁ በአዲስ ኪዳን በልሳናት የሚናገሩ ሁሉ በሰው ቋንቋ እንደተናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ዎች ግልጽ ያደርጋሉ ይላሉ። ልሳን የሚያሰኘው ለሚናገረው ሰው የማይታወቅ ቋንቋ መሆኑ ነው። ሆኖም ግን አንዳንድ ጊዜ ቋንቋውን ለሚላዩ ሰዎች የታወቀ ነበር። ወይም ለሚያዳምጡት ሰዎች የታወቀ ባይሆንም እንኳ ሰብዓዊ ቋንቋነቱ የታወቀ ነበር። ይህ ዛሬም ለሚነገሩ አንዳንድ ልሳኖች እንኳ የሚሠራ እውነት ነው። በደቡብ አሜሪካ ወንጌልን ሰምተው ያመኑ እጅግ ኋላ ቀር የሆኑ የአንድ ጐሣ አባላት ነበሩ። ትንሽ ቆይተው በአጐራባች ክልላቸው ወደሚገኙና ታሪካዊ ጠላቶቻቸው ወደሆኑ የአንድ ጐሣ አባላት ወንጌላውያንን ለመላክ ወሰኑ። የዚህ ጐሣ አባላት የሚገኙበት ቦታ የበርካታ ቀናት የእግር ጉዞ የሚጠይቅና የሚናገሩት ቋንቋም እነርሱ ከሚያውቁት ፈጽሞ የተለየ ነበር። ወንጌላውያኑ ቋንቋውን የማያውቁ ቢሆኑም እንኳ ወደዚያ ስፍራ በደረሱ ጊዜ ወንጌልን ሊያካፍሏቸው በመቻላቸው ብዙዎች አመኑ። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ወንጌላውያኑ አዲሱ ጐሣ ወደሚገኝበት ስፍራ በደረሱ ጊዜ ከዚህ ቀደም ፈጽመው የማያውቁትን ቋንቋቸውን እንዲናገሩ ችሎታ ተሰጣቸው። ስለ ጌታ እየመሰከሩ ሳሉ ያልተላመደ ነገር መፈጸሙን እንኳ አላወቁም ነበር። ሚሲዮናውያን በአንድ ስብሰባ ላይ በተገኙበት ወቅት በልሳናት የሚናገሩ ሰዎች ይሠሩበት የነበረ እካባቢ ቋንቋን የተናገሩበትና እነርሱም በትክክል ቋንቋውን ሰምተው የተረዱበት ሁኔታም አለ። የሚያሳዝነው ግን አንዳንዴ የሚነገረው ነገር እግዚአብሔርን የማያሰከብር ሆኖ ይገኝ ነበር። በእንደዚህ ዓይነት ጊዜያት የልሳናቱ ባለቤት ሰይጣን እንጂ መንፈስ ቅዱስ አልነበረም። ይህን አመለካከት በአቋምነት የያዙ እመላካከታቸውን ለመደገፍ የሚከተሉትን ምክንያቶች ይሰጣሉ። 1. በልሳናት የመናገር ጉዳይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰው በሐዋርያት ሥራ 2 ላይ ነው። በልሳናት የተናገሩት የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት በሰው ቋንቋ መናገራቸው ግልጽ ነው። -ከሌላ የዓለም ክፍል የመጡት አይሁዳውያን በራሳቸው ቋንቋ የተነገረውን መረጻታቸው ይህን ያመለክታል። በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍም ሆነ በሌላ የአዲስ ኪዳን ክፍሎች በልሳናት መናገር ከሚታወቅ ቋንቋ ወደ ሌላ ነገር መቀየሩን የሚያመለክት አሳብ አናገኝም። 2. በልሳናት ስለመናገር ለማመልከት ብዙ ጊዜ በሥራ ላይ የዋለው የግሪክ ቃል «ግሎሳ» የሚለው ነው። በአዲስ ኪዳን በአጠቃላይ በግሪክ ሥነ-ጽሑፎች በሙሉ ስላ ሰብዓዊ ቋንቋ ለመናገር አገልግሎት ላይ የዋለው ቃል ይህ ነው። 3. በሐዋ 2፡6፥ 8 ላይ የተፈጸመውን ነገር ለመግለጥ አገልጎሎት ላይ የዋለው የግሪክ ቃል ዳይሬክተስ» የሚል ሲሆን ቃሉ ሁልጊዜ ሰብዓዊ ቋንቋን ለመግለጽ አገልግሎት ላይ የሚውል ነው። 4. በ1ኛ ቆሮ. 12፡10 ላይ ጳውሎስ ስለተለያዩ ልሳናት ይናገራል። «የተለያዩ ዓይነት» የሚለው የግሪክ ቃል የተለያዩ የቋንቋዎች ቤተሰቦችን ወይም ቡድኖችን የሚያሳይ ነው። ለምሳሌ አማርኛ አንድ ቋንቋ ቢሆንም እንኳ የሽዋ፥ የመንዝ፥ የጐንደርና የወሎ ወዘተ… እማርኛ አለ። ወይም በሊማትክ የቋንቋ መደብ ውስጥ ግዕዝ፥ ትግርኛ አማርኛ፥ ዕብራይስጥና ዐረብኛ አሉ። ጳውሎስ በዚህ ቦታ ይህን ቃል የተጠቀመው የተለያዩ ዓይነት ሰብዓዊ ቋንቋዎችን ለማመልከት ነው። 5. በ1ኛ ቆሮ 14 ጳውሎስ በልሳናት የመናገርን ዓላማ ለመግለጽ ኢሳ. 28፡11-2ን ይጠቅሳል። ከዚህ ጥቅስ በግልጽ እንደምንረዳው ‹ልሳናት› የተባለው የአሶራውያን ቋንቋ ስለሆነ ቋንቋ መሆኑ ግልጽ ነው። 6. በ1ኛ ቆሮ. 14 ጳውሎስ በጉባኤ የተነገረ ልሳን መተርጐም እንዳለበት ይናገራል። መተርጐም የመቻሉ ነገር ዝም ብሎ የሚመጣ ድምጽ ሳይሆን የሰው ቋንቋ መሆኑን የሚያመለክት እንደሆነ አንዳንዶች ያስባሉ። ስለዚህ ይህ አመለካከት ያላቸው ሰዎች እውነተኛው በልሳናት የመናገር ስጦታ አንድ ሰው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተሞልቶ የራሱ ባልሆነ፥ አስቀድሞ ባልተማረውና ባላጠናው የሰው ቋንቋ መናገር ነው ይላሉ። 2. በልሳናት መናገር የሰው ቋንቋ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ብቻ የሚታወቅ ሰማያዊ ቋንቋም ሊሆን ይችላል። ሌሎች ክርስቲያኖች ደግሞ በልሳናት መናገርን ተፈጥሮአዊ ያልሆነ ቋንቋ የመሆኑን ሁኔታ በግልጽ ስለተላማመዱ በልሳናት መናገር አንዳንድ ጊዜ የተለየ ቋንቋ መሆኑን ያምናሉ። በእግዚአብሔር ወይም በመላእክት አገልግሎት ላይ የሚውል ቋንቋ ነው። በአዲስ ኪዳን እነዚህን አሳቦች ምናልባት የሚደግፉ በርካታ ጥቅሶች አሉ። የ1ኛ ቆሮ. 13፡1 ጳውሎስ ስለ ሰውና መላእክት ልሳናት ጠቅሷል። ስለዚህ ጳውሉላ በዚህ ቦታ የሚናገረው ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ሆኖ በተለይ ደግሞ በልሳናት የመናገርን ስጦታ ያለ አግባብ በሥራ ላይ ስለ ማዋል ስለነበር በልሳናት መናገር የሰው ባልሆነ የመላእክት ቋንቋ ሊሆን ይችላል ይላሉ። የመጀመሪያውን አመለካከት በአቋምነት የያዙ ግን ሊመልሱ ጳውሎስ ሊናገረው የፈለገውን ነገር በግልጽና ክፍተኛ አትኩሮት ሰጥተ ለመናገር በማጋነን የተጠቀመበት ዘይቤያዊ አነጋገር እንጂ ሌላ አይደለም ይላሉ። ይህ ቀጥሎ በተመላከቱት ጥቅሶች የበለጠ ግልጽ ይሆናል። የካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች እንኳ እንድ ሰው በእምነት ስጦታ እየተዘዋወረ ተራሮችን ሲነቃቅል ለማየት አይጠብቁም። ልሳናት ሰማያዊ ቋንቋ ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚያምኑት 1ኛ ቆሮ. 14፡2ን ይጠቅሳሉ። በዚያ ስፍራ ጳውሎስ ሰው በልሳናት በሚናገርበት ወቅት የሚናገረው ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው እይደለም ይላል። የሚረዳውም እግዚአብሔር እንጂ ሰው አይደለም። ስለዚህ ሰው በልሳናት በሚናገርበት ወቅት መንፈሱ ከእግዚአብሔር ጋር ይነጋገራል። ይህ ማለት በልሳናት መናገር ሰማያዊ ቋንቋ መናገር ማለት ነው ይላሉ። በልሳናት መናገር ሰብዓዊ ቋንቋ ነው የሚል አቋም ያላቸው ደግሞ ሲመልሱ ቋንቋውን የሚረዳ ማንም ሰው እስከሌለ ድረስ ይህ ጥቅስ ሰብዓዊ ቋንቋን እንዳያመለክት የሚያግድ ምንም ነገር የለም ይላሉ። 3. በልሳናት መናገር የግድ የሰውም ሆነ የመለኮት ቋንቋ መሆን እያስፈልገውም። የልብን ስሜት የሚገልጥ መቃተት ወይንም ድምጽ ብቻ ሊሆን ይችላል። በሮሜ 8፡26 መንፈስ ቅዱስ በማይነገር መቃተት እንደሚማልድልን ተጽፏል። ይህን አቋም የሚያንጸባርቁ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ እኛን ወክሎ ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል ማለት እንደሆነ እምነታቸው ነው። እርሱ ይህን በሚያደርበት ጊዜ ክርስቲያን በጸሎቱ ለመረዳት የማይቻል ድምጽ ያወጣል። እነዚህ ቋንቋዎች ሳይሆኑ ትርጉም የሌላቸው ድምጾች ናቸው። ትርጉም የለሽ የሆኑት ለእኛ ለሰዎች ነውና እንደ ቋንቋ ልንቆጥራቸው ወይም ልንመድባቸው አንችልም። የመንፈስ ቅዱስን አእምሮ የሚያውቀው እግዚአብሔር ቀን የሚነገረውን ነገር ያውቃል። ካሪዝማቲክ ያልሆኑና በርካታ ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ይህን አቋም ውድቅ ያደርጋሉ። በመጽሐፍ ቅዱሳችን «ግሎሳ» የሚለው ቃል ትርጉም የማይሰጡ ድምጾችን በሚመስል ሁኔታ ፈጽሞ የላም ይላሉ። ሁልጊዜ በጥቅም ላይ የዋለው ሰብዓዊ ወይም መለኮታዊ ቋንቋን ለመግለጽ ነው። እነዚህ ልሳናት መተርጐም አለባቸው የሚለው እውነታ 1ኛ ቆሮ. 1) የሚተረጐም ቋንቋ መኖር እንዳለበት ያሳረጥልናል። ይህን ሦስተኛውን አመለካከት የሚያንጸባርቁ ብዙዎች አዳዲስ ክርስቲያኖች ለብቻ ይወስዱና እንዴት በልሳናት መናገር እንዳለባቸው ያስተምራሉ። «ሃሌሉያ። የመሳሰለ ድምፅን ደጋግመው እንዲናገሩ በማድረግ የሚደጋግሙት ቃሎች እስኪደበላለቁ ድረስ እንዲቀጥሉ ያደርጋሉ። በዚያ መካከል በቅጽበት ትርጉም የማይሰጡ ቃሎች ያሉበት ድምፅ ከአፉ ውስጥ ይወጣል። በዚህ ጊዜ ለሰውዬው በመንፈስ ቅዱስ እንደተጠመቀና በልሳናት በዚህ ጊዜ ለሰውዬው በምንም እየተናገረ እንደሆነ ይነግሩታል። ብዙ ጊዜ ይህ በሚፈጸምበት ወቅት አእምሮ መጋበት ወቅት አእምሮ ሥራውን ያቆማል። አእምሮ እንዳይሠራ መዘውሩ ይቆለፍና ለማቅ (መንፈስ) የሚፈልገውን ሁሉ እንዲያደርግ ነህ ይሆናል። ይህ ልምምድ በጰንጠቆለጤዎችና በካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ዘንድ በዓለም ዙሪያ ሁሉ የተለመደ ቢሆንም ልምምዱ ምንም ዓይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የለውም። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በየትም ስፍራ በልሳን እንዴት እንደሚጸልይ ሰው የተማረበት አንድም ማስረጃ የለም። በልሳናት የመናገር ስጦታ በቅጽበት የሚሰጥ ነው። ይህ ዛሬ ብዙዎች በላሳናት መናገር ነው ብለው የሚጠቅሱት ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ልሳን ነው ብሎ ከመደበው – ልምምድ ጋር አብሮ የሚሄድ ያለመሆኑን የሚያመለክት ነገር ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነው ልሳን ካልሆነ ታዲያ ምንድ ነው? ይህ ለመመላስ አስቸጋሪ የሆነ ጥያቄ ሲሆን የተለያዩ ሰዎች ለጥያቄው የሚሰጧቸው መልሶች ይለያያሉ። ሀ) ይህ ድምጽ በሙከራና በሥልጠና የተገኘ ከዚያም የመጣ የእንዴት ቃል ነው ብለው አንዳንዶች ያምናሉ። ለ) ሌሎች ደግሞ እውነተኛ ልሳን ነው ይላሉ። ሐ) ሌሎች ደግሞ በተላይ
በልሳናት ስለመናገር ተጨማሪ ጉዳዮች (ክፍል 2) የተለያዩ ዓይነት ልሳናት አሉን? Read More »
