በብሉይና በአዲስ ኪዳን መካከል የነበረው ዘመን
የውይይት ጥያቄ፦ ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙት ነገሮች ባለፉት 100 ዓመታት ከተፈጸሙት ድርጊቶች ጋር በጥብቅ የሚተሳሰሩ ናቸው። የምኒልክ፥ የኃይለ ሥላሴ፥ የደርግና የኢሕአዴግ የአገዛዝ ዘመናት ዛሬ በአገሪቱ ውስጥ የሚፈጸሙትን ክስተቶች በእጅጉ ይወስናሉ። የኢትዮጵያ ድንበሮች፥ የመሬት ይዞታ አመለካከቶች፥ የኦርቶዶክስና የእስልምና ሃይማኖት ግንኙነቶችና የመሳሰሉት ታሪካዊ መሠረት ያላቸው ነገሮች ናቸው፤ ስለዚህም ዛሬ የዚያን ታሪክ ፍሬ እንመገባለን። ይህም ሆኖ ዛሬ የሚከሰቱት ነገሮች ሁሉ የኢትዮጵያ ታሪክ ውጤቶች ብቻ አይደሉም። በሰፊው ዓለም ውስጥ የተፈጸሙት ነገሮችም በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድረዋል። በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አውሮፓውያን አፍሪካን በቅኝ ለመግዛት ያካሄዷቸው ተግባራት፥ ለምሳሌ ጣሊያኖች አንዳንድ የኢትዮጵያ ክፍሎችን መግዛታቸው (ኤርትራን ጨምሮ) በዛሬዎቹ ክስተቶች ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል። በኃይለ ሥላሴና በደርግ ዘመን በሩሲያ (ሶቪየት ኅብረት) እና በአሜሪካ መካከል የነበረው የቀዝቃዛው ጦርነት ትግል ዛሬም በኢትዮጵያ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን ቀጥሏል። ለምሳሌ የምዕራቡ ዓለም ፈሊጥ የሆነው ፋሽን፥ ቪዲዮና የእንግሊዝኛ ቋንቋ በወጣቶቻችን ስሜትና ባህል ላይ ተጽዕኖ በማሳደር ላይ ይገኛል። በተመሳሳይ ሁኔታ፥ ከአዲስ ኪዳን ዘመን በፊትም ሆነ በአዲስ ኪዳን ዘመን በእስራኤልና በሌሎች አገሮች ውስጥ ይካሄዱ የነበሩ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን በምንገነዘብበት ጊዜ፥ ስለ አዲስ ኪዳንና ስለ ቤተ ክርስቲያን ዕድገት እጅግ ግልጽ አሳብ ይኖረናል። ክርስቶስ በእስራኤል አገር በተወለደ ጊዜ አገሪቱ በሮማውያን አስተዳደር ሥር ነበረች። ክርስቶስ ከመወለዱ ከ400 ዓመታት በፊት በእስራኤልና በአሕዛቡ ዓለም የተፈጸሙት ክስተቶችም በእስራኤልና በአይሁድ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድረው ነበር። ሐዋርያው ጳውሎስ በገላትያ 4፡4-5 ላይ እንደገለጸው፦ «ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ።» ጳውሎስ ይህን ሲል ክርስቶስ ወደ ምድር መጥቶ እንዲሞትና ቤተ ክርስቲያንን እንዲመሠርት፥ በእግዚአብሔር ዕቅድ ውስጥ ሁሉም ነገር ታሪካዊ ዝግጅት ተደርጎለት እንደነበረ መግለጹ ነበር። ቤተ ክርስቲያን በጥንቱ ዓለም በፍጥነት ልታድግና በአንድ ትውልድ ዘመን ወንጌል በዚያ ደረጃ ሊስፋፋ የቻለው ለምን ነበር? መልሱን የምናገኘው እግዚአብሔር የዓለምን ታሪክ ቀድሞ ካደራጀበት ሁኔታ ነው። ምንም እንኳ ኢየሱስ ክርስቶስ በአዳምና በሔዋን፥ ወይም በዳዊት ወይም በኢሳይያስ ዘመን ወይም ዛሬ ሊመጣ ቢችልም፥ እነዚህ ሁሉ ዘመናት ከእግዚአብሔር ጥበብ አንጻር ገና ትክክል አልነበሩም። ነገር ግን በእስራኤልና በአሕዛብ አገሮች የነበረው የታሪክ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ምቹ ሲሆን እግዚአብሔር ልጁን ላከው። ይህን ጊዜ ምቹ እንዲሆን ያደረጉት ነገሮች ምን ምን ነበሩ? ይህን ጥያቄ ለመመለስ የእስራኤል ሕዝብ በ586 ዓ.ዓ. በምርኮ ከተወሰደ በኋላ በዓለም ውስጥ የተፈጸሙትን ታላላቅ ክስተቶች መመርመር ይኖርብናል። የውይይት ጥያቄ፦ ዳንኤል ምዕራፍ 7ን አንብብና ዳንኤል በራእዩ የተመለከታቸውን የተለያዩ እንስሳት ዘርዝር። እነዚህ እንስሳት ያመለከቱት የትኞቹን ታሪካዊ መንግሥታት ነበር? በባቢሎን ምርኮ ጊዜ እግዚአብሔር ለነቢዩ ዳንኤል በቀጣይ 600 ዓመታት ውስጥ በአይሁዶች ታሪክ ውስጥ ስለሚፈጸሙት ነገሮች በግልጽ ገልጦለት ነበር። በአራት እንስሳት የተመሰሉት አራት የተለያዩ የአሕዛብ መንግሥታት አይሁዶችን በየተራ እንደሚገዙ እግዚአብሔር ለዳንኤል አሳይቶታል፦ እነዚህ አራት መንግሥታት የአይሁድን ሕዝብ በየተራ ገዝተውት ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር የመሢሑንና የቤተ ክርስቲያንን መንገድ በጥበቡ ለማዘጋጀት ሲል፥ እነዚህን አረማውያን መንግሥታት በሉዓላዊ ኃይሉ ይቆጣጠር ነበር። እነዚህ መንግሥታት እያንዳንዳቸው እግዚአብሔር ለአይሁዶች በነበረው ታሪካዊ ዕቅድ ውስጥ የየራሳቸው ታላቅ ድርሻ ነበራቸው። የባቢሎን መንግሥት (626 ዓ.ዓ. – 539 ዓ.ዓ.) የውይይት ጥያቄ፦ 2ኛ ነገሥት ምዕራፍ 25ን አንብብ። አልፎ አልፎ የአሕዛብ አገሮች ከሚሠነዝሩባት ድንገተኛ ጥቃት ውጭ፥ እስራኤል ለ900 ዓመታት ያህል (ከ1400 እስከ 586 ዓ.ዓ.) ነፃ አገር ነበረች። አይሁዶች «የእግዚአብሔር ፈቃድና የጽዮን መቅደስ ሁልጊዜም ከውጭ አገሮች ጥቃት ይጠብቀናል፤ ድርጊታችንም ሆነ ማንኛውንም ጣዖት ማምለካችን ለእግዚአብሔር አሳሳቢ ጉዳይ አይደለም። እኛ የእግዚአብሔር ልዩ ሕዝብ ስለሆንን፥ ወደ ምርኮ ሊሰድደንና ሊያጠፋን ፈጽሞ አይፈልግም» ብለው በሐሰት ያስቡ ነበር። እግዚአብሔር ነቢያትን ደጋግሞ እየላከ ሕዝቡ በንስሐ ካልተመለሰ እንደሚቀጣ ቢያስጠነቅቅም ሕዝቡ ግን አልሰሟቸውም። የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ጦር በድንገት ኢየሩሳሌምን በመክበብ ከ605 እስከ 586 ዓ.ዓ. ድረስ 3 ታላላቅ ወረራዎችን አካሄደባት። በዚህ ጊዜ የይሁዳ አገር ፈጽማ ወደመች። ታላቁ የሰለሞን ቤተ መቅደስ ሙሉ በሙሉ ሲፈርስና የእንስሳት መሥዋዕቱ ሲቆም፥ ለ500 ዓመታት ያህል ያለማቋረጥ ሲካሄድ የነበረው የቤተ መቅደሱ ዘላቂ አምልኮ ተቋረጠ። የውይይት ጥያቄ፦ በባቢሎን ምርኮ ዘመን የአይሁድን ሕይወት የለወጡ 5 ታላላቅ ክስተቶች፦ የሰባ ዓመቱ የባቢሎን ምርኮ የአይሁድ ሕዝቦችን ማኅበራዊና መንፈሳዊ ሕይወት ሙሉ በሙሉ የለወጠ መለኮታዊ ሂደት ነበር። ክርስቶስ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ የአይሁዶች አኗኗርና የአምልኮ ሁኔታ በዳዊትና በኢሳይያስ ዘመን ከነበረው ፍጹም የተለየ ነበር። በምርኮ ዘመን የተለወጡ 5 ዋና ዋና ነገሮች የሚከተሉት ነበሩ፦ የፋርስ መንግሥት (539 ዓ.ዓ. – 331 ዓ.ዓ.) የውይይት ጥያቄ፦ ዳንኤል ምዕራፍ 8ን አንብብ። የሜዶንና የፋርስ መንግሥታት ኃይልን ከማግኘታቸው ከ200 ዓመታት በፊት፥ እግዚአብሔር ቂሮስ (Cyrus) የተባለ ንጉሥ እንደሚያስነሣ ለነቢዩ ኢሳይያስ በስሙ ጠቅሶ ገልጦለት ነበር (ኢሳ. 44፡28)። ምንም እንኳ ቂሮስ እውነተኛውን አምላክ በግል ባያውቅም፥ እግዚአብሔር ግን ለአይሁድ ሕዝብ ሲል እርሱን ወደ መሪነት በማምጣት ባቢሎንን እንዲያሸንፍና ምርኮኞቹ ወደ አገራቸው ተመልሰው መቅደሱንና የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንዲገነቡ ፈቀደ። ይህ ታላቅ ግዛት ጥምር የሜዶንና የፋርስ መንግሥት ነበር። የባቢሎን መንግሥት በሥልጣን ላይ የቆየው ለ70 ዓመታት ብቻ ሲሆን፥ የፋርስ መንግሥት ግን ለ200 ዓመታት ቆይቷል። ይህም የፋርስ መንግሥት በአይሁዶች ማኅበራዊ ሕይወትና ባህል ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ለማሳደር አስችሎታል። ፋርሳዊው ቂሮስ ሜዶንን ከፋርስ ጋር በማዋሃድ አነስተኛ የነበረችውን አገር በ550 ዓ.ዓ. ኃያል የዓለም አገር አደረጋት። ቂሮስ በ546 ዓ.ዓ. ታላቁን የሊዲያን መንግሥት ሲያሸንፍ፥ በ539 ዓ.ዓ. ደግሞ ባቢሎንን ወግቶ በማሸነፍ የፋርስ ግዛት አካል አደረጋት። ስለሆነም በአጭር ጊዜ ውስጥ ቂሮስ የፋርስን መንግሥት በምሥራቅ ከፋርስ ባሕረ ሰላጤ ጀምሮ ወደ ምዕራብ ቱርክና ወደ ደቡብ ግብጽ ድረስ ለማስፋፋት ቻለ። ይህም የፋርስን መንግሥት በዘመኑ ከነበሩት ግዛቶች ሁሉ ታላቅ አድርጎታል። የአይሁድ ታሪክ ትውፊት እንደሚለው፥ ቂሮስ ድል አድርጎ ወደ ባቢሎን በገባ ጊዜ የአይሁድ መሪዎች የእርሱ መምጣትና ስሙም እንኳ ሳይቀሩ ከ200 ዓመታት በፊት በነቢዩ ኢሳይያስ መጽሐፍ መተንበዩን በክብር አሳዩት። ቂሮስ ለአይሁዶች ልዩ አዋጅ እንዲያወጣና ወደ አገራቸው እንዲመልሳቸው እግዚአብሔር ልቡን ያነሳሳበት አንዱ ታሪካዊ ምክንያት ይህ ነበር። የቂሮስ አገዛዝ ስልት ሰዎችን በግፍ ካፈናቀሉት ከባቢሎናውያንና ከአሦራውያን ፍጹም የተለየና የለዘበ ነበር። ሰዎችን አስገድዶ ወደ ሌላ ምድር ከመስደድ ይልቅ፥ በአገራቸው በሰላም እየኖሩ ለፋርስ መንግሥት ታማኝ እንዲሆኑና ግብር እንዲከፍሉ ያበረታታ ነበር። በመሆኑም ቂሮስ በሕዝቦች ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፉለትን ሁለት ታላላቅ ተግባራት አከናውኗል፦ በመጀመሪያው ዙር በዘሩባቤል አማካይነት 50,000 የሚሆኑ አይሁዶች ብቻ ነበሩ ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱት። ይህ የሚያሳየው አብዛኞቹ አይሁዶች በባቢሎን ምድር የተደላደለ የንግድ ሕይወት ይመሩ ስለነበር፥ ኋላቀርና በኢኮኖሚም ወደ ወደመችው የኢየሩሳሌም ምድር ለመመለስ ፈቃደኞች እንዳልነበሩ ነው። ይህ ሁኔታ ዛሬ በምዕራቡ ዓለም (ለምሳሌ በአሜሪካ) የሚኖሩ የብዙ አገሮች ስደተኞች ወደ ገጠሪቱና ወደ ደከመችው አገራቸው ተመልሰው ለመኖር ከማይፈልጉበት ምድራዊ ምቾት ጋር ይመሳሰላል። ይህ የዓለም ፍቅርና ምቾት አብዛኞቹ አይሁዶች እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዘሮቹ ተስፋ ወደ ገባላቸው የተቀደሰች ምድር እንዳይመለሱ ከለከላቸው። የውይይት ጥያቄ፦ የሳምራውያን መነሳትና የቤተ መቅደሱ ግንባታ ውጊያ አነስተኛው የአይሁድ ቅሬታ ወደ ይሁዳ ምድር ሲመለስ፥ ቀዳሚ ተግባራቸው የይሖዋ ቤተ መቅደስ ዳግም ግንባታ ነበር። ብዙም ሳይቆይ ግን ከባድ የፖለቲካ ተቃውሞ ተነሣባቸው። በአሦራውያን አስተዳደር ዘመን በነበረችው በሰሜኑ የእስራኤል ክፍል (ሰማርያ) ከአሦር ንጉሥ የመጡ አሕዛብና የቀሩት እስራኤላውያን ተጋብተው በመውለዳቸው ምክንያት ከፊል አይሁዳዊና ከፊል አሕዛብ የሆኑ ሕዝቦች ተፈጥረው ነበር። እነዚህ ሰዎች በአዲስ ኪዳን ዘመን ሳምራውያን (Samaritans) ተብለው ተጠርተዋል። ሳምራውያን አይሁዶች መቅደሱን መልሰው ለመገንባት መነሳታቸውን ሲያዩ፥ መጥተው በሥራው አብረው መሳተፍና መተባበር እንደሚፈልጉ አስታወቁ። ነገር ግን በዘሩባቤል የሚመሩት እነዚህ የተመለሱት አይሁዶች፥ ሳምራውያኑ በቁጥር በልጠው እንዳይቆጣጠሯቸውና ንጹሑ የእግዚአብሔር አምልኮ
በብሉይና በአዲስ ኪዳን መካከል የነበረው ዘመን Read More »
