የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመስጠት ጸጋ፣ ክፍል 1 (ቆሮንቶስ 8፡1-24)

 ከጳውሉስ ሦስተኛ የሚሲዮናዊነት ጉዞ አበይት አገልግሎቶች አንዱ በይሁዳ ለሚኖሩ ድሀ ክርስቲያኖች ልዩ «የርዳታ ስጦታ» ማድረግ ነበር። ጳውሎስ ከዚህ በፊት አንድ ጊዜ የዚህ ዓይነት አገልግሎት ያበረከተ ሲሆን (የሐዋ. 11፡27-30)፥ አሁንም ተመሳሳይ ግልጋሎት ለመስጠት ደስተኛ ነበር። የተዘነጋውንና «ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው» (የሐዋ. 20፡35) የሚለውን የጌታችን ብፅዕና ያስታወሰው ጳውሎስ እንደ ነበር መረዳት አስፈላጊ ነው።  ይሁንና ድሆችን በገንዘብ ከመርዳትም በተጨማሪ በጳውሎስ አእምሮው ውስጥ የሚመላለሱ ሌሎችም በረከቶች ነበሩ። ከባሕር ማዶ ለሚገኙ የአይሁድ ማኅበራት የአሕዛብ አብያተ-ክርስቲያናት የሚያደርጉትን እርዳታ በማስታወስ፥ ይህ የቤተ ክርስቲያን አንድነት በበለጠ እንዲጠናከር ይፈልግ ነበር። ጳውሎስ አሕዛብ የአይሁድ «ባለ ዕዳዎች» እንደ ሆኑ አድርጎ ይመለከታል (ሮሜ 15፡25-28)፤ ልዩ የርዳታ አሰባሰቡም ያንኑ ዕዳ ለመክፈል አንድኛው መንገድ ነበር።  እንዲሁም ይህ ስጦታ ለአይሁድ አማኞች (አሁንም አንዳንዶቹ ለሕጉ ይቀኑ ነበር) ጳውሎስ እንደሚወራበት የአይሁዶች ወይም የሙሴ ጠላት እንዳልነበር የሚያረጋግጥ ማስረጃ ነበር (የሐዋ. 20 ከቁ 17 ጀምሮ)። ጳውሎስ በአገልግሎቱ መጀመሪያ አካባቢ ድሆችን ለማሰብ ተስፋ የሰጠ ሲሆን (ገላ 2፡6-10)፥ ያንኑ የተስፋ ቃል ለመጠበቅ በትጋት ይሠራ ነበር፤ ሆኖም ግን እግረ መንገዱንም የአይሁዶችን የቅናት መንፈስ ለመስበር በማሰብ ከአሕዛቦች የሚደረግላቸው እርዳታ እንዲጠናከር ያበረታታ ነበር።  የሚያሳዝነው፥ የቆሮንቶስ ሰዎች የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ አልነበረም። እንደ ብዙዎቹ ሰዎች፥ የተስፋ ቃሎችን ቢሰጡም፥ ዳሩ ግን አልፈጸሙም ነበር። እንዲያውም፥ አንድ ዓመቱ በሙሉ በከንቱ ባክኗል (2ኛ ቆሮ.8፡10)። ለዚህ ምክንያቱ ምን ነበር? የቤተ ክርስቲያኗ በዝቅተኛ መንፈሳዊ ደረጃ ላይ መገኘቷ ነበር። ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ እስካልሆነች፥ በልግስና ልትሰጥ አትችልም። ሌላው ምክንያት ደግሞ የሚችሉትን ያህል ገንዘብ ከቤተ ክርስቲያን ሳይዘርፉ ያልቀሩት የአይሁድ ሃይማኖት አስፋፊዎች ወረራ ነበር (11፡7-12፥ 20፤ 12፡14)።  ጳውሎስ ክርስቲያኖችን ለዚህ የልግስና ስጦታ ተካፋይ ማድረጉ ቀላል እንደማይሆን ስለ ተረዳ፥ ልመናውን ወደ ከፍተኛ መንፈሳዊ ደረጃ ያሳድገዋል፡- መስጠት የጸጋ ተግባር እንደ ሆነ ያስተምራቸዋል። ጳውሎስ ስጦታውን ለማመልከት በዘጠኝ የተለያዩ ቃላት ቢጠቀምም ዳሩ ግን ከሁሉም በላይ የተገለገለበት «ጸጋ» በሚባለው ቃል ነበር። መስጠት በመሠረቱ ሌሉችን የሚረዳ አገልግሉትና ኅብረትን የሚያሳይ (8፡4) ቢሆንም፥ ዳሩ ግን የመመንጫው ምክንያት በልብ ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ሊሆን ይገባል። ጳውሎስ ይህ የርዳታ አሰባሰብ የአሕዛቦች ዕዳ መቅረፊያና (ሮሜ 15፡27) የክርስቲያናዊ ሕይወታቸው ፍሬ (ሮሜ 15፡27) ፍሬ እንደ ሆነ ቢያውቅም በሌላ በኩል ደግሞ ከዚህም የላቀ ምክንያት እንደ ነበረው ተረድቶ ነበር፤ ከሁሉም በላይ የእግዚአብሔር ጸጋ በሰው ልብ ውስጥ የመሥራቱ ውጤት መሆኑን ያምንበት ነበር።  ስለዚህ ክርስቲያኖች ከልብ መስጠት ከመቀበል ይልቅ የተባረከ መሆኑን አምነው፥ ወደ መስጠት ጸጋ በሚገቡበት ጊዜ አስደናቂ ነገር ይሆናል። ጥያቄው ግን «በጸጋ መስጠትን» እየተለማመድን መሆኑን እንዴት ልናውቅ እንችላለን? የሚለው ነው። ጳውሎስ ስጦታችን በጸጋ የተነቃቃ ለመሆኑ ማስረጃ የሚሆኑ ምልክቶች እንዳሉ አመልክቷል።  በሁኔታዎች ሳንገደብ ስንሰጥ (2ኛ ቆሮ.8፡1-2)  ጳውሎስ በምሳሌነት የጠቀሳቸው የመቄዶንያ አብያተ ክርስትያናት፥ የራሳቸው የሆኑ ከፍተኛ ችግሮች ቢኖሩባቸውም፥ ዳሩ ግን በልግስና ለመስጠት ወደ ኋላ አላሉም ነበር። «በብዙ መከራ ተፈትነው» (ቁ 2) ነበር እንጂ፥ እንዲሁ በ«መከራ» ውስጥ ብቻ ያለፉ አልነበሩም። በከፍተኛ ድህነት ማለትም «በመናጢነት» ደረጃ ላይ ነበሩ። በዚህ ሥፍራ የተጠቀሰው ቃል ምንም ነገር የሌለውንና ለወደፊትም ምንም ነገር የማግኘት ተስፋው የመነመነን ለማኝ የሚገልጽ ነው። ይህ አስቸጋሪ ሁኔታቸው የመነጨው ምናልባትም ክርስቲያን በመሆናቸው የተነሣ፥ ከሥራቸው በመፈናቀላቸው ወይም ከጣዖት አምልኮ ጋር ለመተባበር ባለመፈለጋቸውና ከንግድ ማኅበራት በመገለላቸው ምክንያት ሊሆን ይችላል።  ይሁንና የነበሩባቸው ሁኔታዎች ከመስጠት አላቀቡዋቸውም ነበር። እንዲያም፥ በደስታና በልግስና ሰጡ። ማንኛውም ኮምፒውተር ይህንን የሚከተለውን አስደናቂ ስሌት ሊገነዘብ አይችልም፡- ትልቅ መከራና ጥልቅ ድህነት ሲደመር ጸጋ ለ ብዙ ደስታና ብዙ ልግስና! ይህም በጳውሎስ አገልግሎት ውስጥ የነበረውን የተቃራኒ ነገሮች ዝርዝር ያስታውሰናል፡- «ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለጠጎች እናደርጋለን። (6፡10)። በተጨማሪም የመገናኛው ድንኳን (ዘጸ. 35፡5-6) እና ቤተ መቅደሱ (1ኛ ዜና 29፡6-9) በተሠሩ ጊዜ የተሰጡትን የልግስና ስጦታዎች ያስታውሰናል።  አንተም የእግዚአብሔርን ጸጋ በሕይወትህ ውስጥ እስከ ተለማመድህ ድረስ ለሌሎች ለመስጠት አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ማመካኛ አድርገህ አትጠቀምባቸውም። ለነገሩማ እንዲያውስ ሁኔታዎች የመስጠት አገልግሎታችንን ያበረታቱበት ወቅት ጨርሶ ይኖር ይሆን? በመጀመሪያው የመጋቢነት አገልግሎቴ ወቅት፥ አዲስ ቤተ ክርስቲያን  ማነጽ በጣም ያስፈልገን ነበር፤ ዳሩ ግን አንዳንድ ሰዎች «ከኢኮኖሚው ሁኔታ» የተነሣ ተቃወሙት። በዚያን ወቅት የብረትና የሌሎችም ፋብሪካዎች ሥራቸውን በአድማ ለማቆም የተነሣሡበት ነበር። በተጨማሪም የባቡር ሐዲዶችና የነዳጅ ማደያዎችም ችግር ፈጥረው ነበር ..ስለሆነም ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ የማይቻል ይመስል ነበር። ዳሩ ግን «በጸጋ መስጠት»ን የሚያምኑ በቂ ሰዎች ስለ ነበሩ፥ ቤተ ክርስቲያኗ አዲስ ሕንፃ ለማሠራት ቻለች ያንን ሁሉ የኢኮኖሚ ችግር በመወጣት! በጸጋ መስጠት ማለት በሁኔታዎች ሳይገደቡ መስጠት ማለት ነው።  በፍላጎት ስንሰጥ (2ኛ ቆሮ.8፡3-4)  በልግስና መስጠትና ደግሞም ያለ ፍላጎት መስጠት፥ ሁለቱም ይቻላሉ። አንድ ቆንቋና ምዕመን፥ «ሰባኪው እስኪጎዳኝ ድረስ መስጠት እንዳለብኝ ይናገራል፤ ለእኔ ግን፥ ስለ መስጠት ማሰቡ ራሱ ይጎዳኛል» እስከ ማለት መድረሱ ይነገራል። የመቂዶንያ አብያተ ክርስቲያናት፥ እንደ ቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን መቀስቀስ ወይም ማስታወስ አላስፈለጋቸውም። እንዲያውም ከሚሰባሰበው ገንዘብ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ ለማዋጣት ፈቃደኞች ነበሩ። ይህም ዕድል እንዲሰጣቸው እስከ መማጸን ደርሰዋል። ለመሆኑ አንድ ክርስቲያን ስጦታውን ሌላው እንዲቀበለው እስከ መለመን የደረሰበት ሁኔታ ስንት ጊዜ አጋጥሞህ ይሆን?  ስጦታቸው ፈቃደኝነትና ግብታዊነት የሚታይበት ነበር። የጸጋ እንጂ፥ ከመገደድ የተነሣ የተፈጸመ አልነበረም። ለልግስናው የተሽቀዳደሙት የእግዚአብሔርን ጸጋ ስለ ተለማመዱና ለመስጠት ስለፈለጉ ነበር። ጸጋ ከኃጢአት ማንጻት ብቻ ሳይሆን፥ ከራሳችንም ያነጻናል። የእግዚአብሔር ጸጋ ልብህንና እጅህን ይፈታዋል። የምትሰጠውም በቀዝቃዛ የሂሳብ ስሌት ተመርተህ ሳይሆን፥ ዳሩ ግን ከሙቅ ልብ በሚመነጭ ሐሤት ነው።  እንደ ኢየሱስ ስንሰጥ (2ኛ ቆሮ.8፡5-9)  በአገልግሎትም ይሁን በመከራ፥ ወይም ራስን በመሠዋት ሁሉ አማኙ ሊከተለው የሚገባው ከሁሉም የላቀውን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌነት ነው። የኢየሱስ ክርስቶስን ፈለግ በመከተል የመቄዶንያ ክርስቲያኖችም ራሳቸውን ለእግዚአብሔርና ለሌሎች አሳልፈው ሰጥተዋል (ቁ 5)። ራሳችንን ለእግዚአብሔር ከሰጠን፥ ንብረታችንን ለእግዚአብሔር መስጠቱ ብዙም አይከብደንም። እንዲሁም ራሳችንን ለእግዚአብሔር ከሰጠን፥ ለሌሎችም ደግሞ ራሳችንን እንሰጣለን። እግዚአብሔርን እየወደዱ የባልንጀራችንን ችግር ችላ ማለት የማይቻል ነገር ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ለእኛ ሲል ሰጥቶአል (ገላ. 1፡4፤ 2፡20)። እኛስ ራሳችንን ለእርሱ መስጠት የለብንም? የሞተልን ለራሳችን ሳይሆን፥ ዳሩ ግን ለእርሱና ለሌሉች እንኖር ዘንድ ነው (2ኛ ቆሮ. 5፡15)።  የመቄዶናውያን ስጦታ፥ ልክ እንደ ክርስቶስ በፍቅር አነሣሽነት የተከናወነ ነበር (8፡7-8)። ይህ በመንፈሳዊ በረከቶች ለበለጸጉት የቆሮንቶስ ሰዎች ምንኛ ተግሣጽ ነበር (1ኛ ቆሮ.8:4-5)። እነርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ዙሪያቸውን ታጥረው ስለ ነበር፥ የመንፈስ ቅዱስን የጸጋ ስጦታዎችንም ሆነ በጸጋ ተነሣሥተው መለገስን ዘንግተው ነበር። የመቄዶንያ አብያተ – ክርስቲያናት «ጥልቅ ድህነት» (2ኛ ቆሮ. 8፡2) ደርሶባቸው ሳለ፥ ዳሩ ግን አብዝተው ሊሰጡችለዋል። የቆሮንቶስ ሰዎች ግን በርካታ መንፈሳዊ ስጦታዎች ቢኖሯቸውም፥ ዳሩ ግን ተስፋ የሰጡትን ቃል ለመጠበቅና በሚሰበሰበው ገንዘብ ውስጥ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ግድ የለሾች ነበሩ።  የመንፈሳዊ ስጦታዎችን አገልግሎት በልግስና ለማከናወን የመስጠት ተግባር ምትክ ሊሆን ይችላል ብለን ልንከራከር አይገባም። «በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ስለማስተምር፥ መስጠት አያስፈልገኝም» የሚለው ማመካኛ እንጂ፥ አጥጋቢ የማሳመኛ ነጥብ አይደለም። ስጦታዎቹ በእርግጥም ስጦታዎች እንደ ሆኑ የሚያስብ ክርስቲያን ምን ጊዜም የሚነሣው ለሌሉች ለመስጠት እንጂ በጌታ አገልግሎት ሽፋን «ልደበቅ» አይልም። እኔንም ቢሆን፥ አንዳንድ ሙሉ ጊዜያቸውን ለጌታ አገልግሎት በማዋላቸው፥ ለመስጠት እንደማይገደዱ በመግለጽ የተከራከሩኝ መጋቢዎችና ሚሲዮናውያን አጋጥመውኛል። ጳውሎስ ከዚህ የሚቃረን አሳብ ነበረው፡- ከእግዚአብሔር ዘንድ ግሩም ስጦታ ስለ ተሰጣችሁ፥ አብልጣችሁ ለመስጠት መሻት አለባችሁ።  ከዚህም ሌላ ጳውሎስ እንዲሰጡ ያዘዛቸው ራሱ እንዳልሆነ በግልጽ እንዲያውቁት ይጠነቀቅ ነበር። እንዲያውም የቆሮንቶስን ሰዎች አመለካከትና ከመቄዶንያ ሰዎች ጋር እያነጻጸረ ነበር። የመቄዶንያ ክርስቲያኖች የጌታን ምሳሌ እየተከተሉ መሆናቸውን በግልጽ መሰከረ፡ ድሆች ሆነው ሳሉ ሰጡ። ከዚህም በመነሣት የቆሮንቶስ ሰዎች ጳውሎስን እንደሚወዱት ይናገሩ ስለ ነበር፥ በሚሰበሰበው ገንዘብ ውስጥ ተካፋይ

የመስጠት ጸጋ፣ ክፍል 1 (ቆሮንቶስ 8፡1-24) Read More »

ሙታን የሚነሡት መቼ ነው? (1ኛ ቆሮ. 15፡20-28)

ጳውሎስ ይህን ጥያቄ ለመመለስ ሦስት ምሳሌዎችን ተጠቅሞአል።  የመከር በኩራት (1ኛ ቆሮ 15፡20፡23)። ቀደም ሲል የዚህን ማጣቀሻ ከብሉይ ኪዳን በዓል ጋር ማያያዛችን ይታወሳል (ዘሌዋ. 23፡9-14)። ኢየሱስ በፋሲካ ዕለት የእግዚአብሔር በግ ሆኖ ሞተ። እንደ በኩረ መከር ነዶ፥ ከሦስት ቀናት በኋላ በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ከሙታን ተነሣ። ካህኑ የበኩር መከሩን ነዶ ከጌታ ፊት ሲወዘውዝ፥ መላው መከር የእርሱ ለመሆኑ ምልክት ነበር። ኢየሱስ ከሙታን መነሣቱ፥ እኛም አንድ ቀን የመጻኢው መከር አካል ሆነን እንደምንነሣ የእግዚአብሔር ማረጋገጫ ነበር። ለአማኞች፥ ሞት «እንቅልፍ» ብቻ ነው። ሥጋ ያንቀላፋል፤ ነገር ግን ነፍስ ከጌታ ጋር ናት (ፊልጵ. 1፡21-23፤ 2ኛ ቆሮ 5፡1-8)። በትንሣኤ ጊዜ ሥጋም «ይቀሰቀስና» ይከብራል።  አዳም (15፡21-22)። ጳውሎስ በአዳም ውስጥ ክርስቶስን የሚመስል ምሳሌ በንጽጽር አየ (ሮሜ 5፡12-21ን ተመልከት።) የመጀመሪያው አዳም የተበጀው ከአፈር ነበር፥ ነገር ግን የመጨረሻው አዳም (ክርስቶስ፥ 15፡45-47) ከሰማይ መጣ። የመጀመሪያው አዳም እግዚአብሔርን ባለመታዘዝ ኃጢአትንና ሞትን ወደ ዓለም አመጣ። ነገር ግን የመጨረሻው አዳም እግዚአብሔርን በመታዘዝ ጽድቅንና ሕይወትን አመጣ።  (በቁጥር 23 ተራ የሚለው ቃል መጀመሪያ ያመለክት የነበረው በጦር ሠራዊት ውስጥ ያለውን ተዋረድ ነበር። እግዚአብሔር በትንሣኤ ውስጥ ተራ፥ ቅደም ተከተል አለው። እንደ ዮሐንስ 5፡25-29 ያሉ ምንባቦች እና ራእይ 20 መጽሐፍ ቅዱስ «አጠቃላይ ትንሣኤ» ብሎ ነገር እንዳላስተማረ ያሳያሉ። ኢየሱስ ክርስቶስ በአየር ውስጥ በሚመለስበት ጊዜ፥ ቤተ ክርስቲያኑን ወደ ሰማይ ይወስዳታል። በዚያን ጊዜ እርሱን ያመኑትንና በእምነታቸው ሆነው የሞቱትን ከሞት ያስነሣቸዋል (1ኛ ተሰ. 4፡13-18)። ኢየሱስ ይኸኛውን «የሕይወት ትንሣኤ» ብሎታል (ዮሐ 5፡29)። ኢየሱስ ወደ ምድር በፍርድ በሚመለስበት ጊዜ፥ የጠፉት «በፍርድ ትንሣኤ» ይነሣሉ (ዮሐ 5፡29፤ ራእይ 20፡11-15)። የመጀመሪያ ትንሣኤን ያገኘ ማንም አይጠፋም፥ ይሁን እንጂ በሁለተኛ ትንሣኤ የሚገኝ ማንም አይድንም።  የእርሱ መንግሥት (15፡24-28)። ኢየሱስ ወደ ምድር ለመፍረድ በሚመጣበት ጊዜ፥ ኃጢአትን ለአንድ ሺህ ዓመት ያጠፋና መንግሥቱን ያቋቁማል (ራእይ 20፡1-6)። አማኞች ከእርሱ ጋር በመንገሥ ክብሩንና ሥልጣኑን ይጋሩታል። በብሉይ ኪዳን ትንቢት የተነገረለት ይህ መንግሥት በነቢያዊ አስተማሪዎች «ሺሁ ዓመት» የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። ቃሉ በላቲን «ሚሊየን» የሚል ሲሆን፥ ሚሌ-ሺህ። አነም-ዓመት ማለት ነው።  ነገር ግን ከሺሁ ዓመት በኋላም እንኳ ኢየሱስ ክርስቶስ በገዛ ኃይሉ የሚያጠፋው አንድ የመጨረሻ ዓመፅ በእግዚአብሔር ላይ ይከሰታል (ራእይ 20፡7-10)። ከዚያ በኋላ የጠፉት ይነሣሉ፥ ፍርድ ተቀብለው ወደ እሳት ባሕር ውስጥ ይጣላሉ። ከዚያ በኋላ ሞት ራሱ ወደ ገሃነም ይጣልና የመጨረሻውም ጠላት ይደመሰሳል። ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ነገር ከእግሩ በታች ያደርጋል! ከዚያም መንግሥቱን ለአብ ያስረክብና ዘላለማዊ መንግሥት- አዲሱ ሰማይና አዲስ ምድር– ይስተናገዳሉ (ራእይ 21-22)።  መልካምና መንፈሳዊ የሆኑ የቃሉ ተከታዮች በእግዚአብሔር ትንቢታዊ መርሐ ግብር ዝርዝር ጉዳይ ሁልጊዜም አይስማሙበትም፥ ሆኖም ዋነኞቹ እውነቶች ግልጽ ይመስላሉ። ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬ በሰማይ ነግሦ ይገኛል፥ ሥልጣንም ሁሉ ከእግሩ በታች ነው [መዝ. (110)፤ ኤፌ. 1፡15-23]። ሰይጣንና ሰው አሁንም ምርጫቸውን መፈጸም ይችላሉ፥ ነገር ግን እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ በሥልጣኑ ላይ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬ በሰማይ ዙፋኑ ነው (መዝ 2)። የዳኑ ሰዎች ትንሣኤ ገና አልተፈጸመም፥ የጠፉትም ትንሣኤ ቢሆን ገና ነው (2ኛ ጢሞ. 2፡17-18)።  ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያኑ የሚመለሰው መቼ ነው? ማንም አያውቅም፤ ግን በሚሆንበት ጊዜ፥ «በድንገት በቅጽበተ ዓይን» (15፡52) ይፈጸማል። መዘጋጀት ያስፈልገናል (1ኛ ዮሐ 2፡28–3፡3)። ጽሑፍ – በዋረን ዌርዝቢ፣ ትርጉም – በፈቃዱ ገብሬ፣ እርማት–በጌቱ ግዛው

ሙታን የሚነሡት መቼ ነው? (1ኛ ቆሮ. 15፡20-28) Read More »

የወደፊት ተስፋ አለን (2ኛ ቆሮ. 5፡1-8)

«ይህ አገልግሎት አለን … ይህ መዝገብ … አለን .. ያው አንዱ የእምነት መንፈስ አለን … ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንፃ (አለን)» (4፡1፥ 7፥ 13፤ 5፡1)። ይህ ጳውሎስ ስለ ክርስትና እምነት እውነታ የሰጠው ምስክርነት ምንኛ ድንቅ ነው!  በጥቅሱ ውስጥ «የእግዚአብሔር ሕንፃ» ተብሎ የተገለጸው በዮሐንስ 14፡1-6 ውስጥ የምናገኘው ቃል የተገባለት የአማኙ ሰማያዊ ቤት ሳይሆን፥ የሚለብሰው የከበረ አካል ነው። ጳውሎስ ድንኳን ሠሪ ሲሆን (የሐዋ. 18፡1-3)፥ በዚህ ስፍራ ድንኳንን የአሁኑ ምድራዊ ሕይወታችን መግለጫ አድርጎ ተጠቅሞበታል። ድንኳን ደካማ፥ መሠረቱ ጊዜያዊ የሆነና ብዙም ውበት የሌለው ሲሆን፥ ዳሩ ግን ወደፊት የምናገኘው የከበረው አካል፥ ዘላለማዊ፥ ውብና የድካም ወይም የመበስበስ ምልክት የማይታይበት ነው(ፊልጵ. 3፡20-21 ተመልከት)። ጳውሎስ የሰውን ሰውነት እንደ ምድራዊ ዕቃ (2ኛ ቆሮ 4፡70 እና ጊዜያዊ ድንኳን አድርጎ ይመለከታል፤ ዳሩ ግን አማኞች አንድ ቀን ከድንቅኛው የመንግሥተ ሰማይ ድባብ ጋር የሚስማማ ውብና የከበረ አካል እንደሚለብሱ ያውቅ ነበር።  በዚህ አንቀጽ ውስጥ የጳውሎስን ምስክርነት መመልከት አስደሳች ነው።  እናውቃለን (2ኛ ቆሮ. 5:10)። እንዴት እናውቃለን? በእግዚአብሔር ቃል ስለምንተማመን። ማንኛውም ክርስቲያን ወደፊት ምን እንደሚሆን ወይም ከሞት በኋላ ስለሚሆነው ነገር ለማወቅ፥ ዕድል-ተንባይ፥ ጨሌጣይ፥ መናፍስት ጠሪ፥ ወይም ሞራ ገላጭ ማማከር አያሻውም። እግዚአብሔር ማወቅ የሚያስፈልገንን ነገር ሁሉ በሰፈረባቸው ገጾች ላይ አስቀምጧል። ጳውሎስ «እናውቃለን» የሚለው በ4፡14 ላይ ከሚገኘው «እውቀት» ጋር የተያያዘ ሲሆን፥ ከኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ይዛመዳል። እርሱ ሕያው ስለ ሆነ፥ ሞት በእኛ ላይ እንደማይሰለጥን እናውቃለን። «እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ» (ዮሐ 14፡19)።  ድንኳናችን «ቢወድቅ» መሥጋት የለብንም። ሰውነት የምንኖርበት ቤት ብቻ ነው። አንድ አማኝ በሚሞትበት ጊዜ፥ ሰውነቱ ወደ መቃብር ይገባል፤ ዳሩ ግን መንፈሱ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለመኖር ወደ ሰማይ ይሄዳል (ፊልጵ. 1፡20-25)። ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ሲመለስ፥ የሞተውን ሰውነት በክብር ያስነሣውና፥ ሰውነትና መንፈስ በመንግሥተ ሰማይ ለዘላለም በክብር ለመኖር ይዋሃዳሉ (1ኛ ተሰ. 4፡13-18፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡35-58)።  እንቃትታለን (2ኛ ቆሮ. 5፡2-5):: ጳውሎስ ለመሞት ያለውን ከፍተኛ መሻት እየገለጸ አልነበረም። እንዲያውም ዓረፍተ ነገሩ የዚህ ተገላቢጦሽ ነው። የከበረውን አካል «ይለብስ ዘንድ» ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲመለስ ያለውን ጉጉት የሚያሳይ ነበር። ጳውሎስ ሰውነትን በድንኳን በመመሰል ሦስት አስተያየቶችን አቅርቦአል፡- 1) ሕያው – በድንኳን ውስጥ የሚኖር፤ 2) ምውት – እርቃኑን ያለ፥ ከድንኳን ውጭ የወጣ፥ 3) ልብስ የደረበ – ክርስቶስ ሲመለስ የሚፈጸመው የሰውነት መለወጥ። ጳውሎስ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚመለስበት ጊዜ ሕያው ሆኖ በምድር ላይ እንደሚኖርና በሞት ልምምድ ውስጥ እንደማያልፍ ተስፋ ያደርግ ነበር። ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 15:51-58 ውስጥ በተመሳሳይ መግለጫ የተጠቀመ ሲሆን፥ በሮሜ 8፡22-26 ውስጥ ደግሞ የ«መቃተት»ን አሳብ አቅርቧል።  የከበረው አካል በ2ኛ ቆሮንቶስ 5፡1 ላይ «በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ … ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንጻ» ተብሎ ሲጠራ፥ በቁጥር 2 ላይ ደግሞ «ከሰማይ የሚሆነው መኖሪያችን» ተብሏል። ይህ ከምድር አፈር ከተሠራው ሟች ሥጋችን ጋር የሚቃረን ነው። «የዚያን የመሬታዊውን መልክ እንደ ለበስን የሰማያዊውን መልክ ደግሞ እንለብሳለን» (1ኛ ቆሮ. 15፡49)። ጳውሎስ የሚቃትተው ሰብዓዊ ሰውነት ለብሶ ስለሚኖር ሳይሆን፥ ዳሩ ግን ኢየሱስ ክርስቶስን ለማየትና የከበረ አካል ለማግኘት ስለ ናፈቀ መሆኑን መረዳት አስፈላጊ ነው። ለክብር እየቃተተ ነበር!  ይህም አባባሉ ሞት ክርስቲያኖችን ለምን እደማያሸብር ግልጽ ያደርግልናል። ጳውሎስ ምድራዊ ሞቱን «መለየት» ብሎታል (2ኛ ጢሞ. 4፡6)። የዚሁ የግሪክ ቃል አንድኛው ትርጉም፥ «ድንኳን ነቅሉ ወደ ሌላ ስፍራ መጓዝ» የሚል ነው። ሆኖም ግን እኛ አንድ ቀን የጌታችንን የከበረ አካል የሚመስል አዲስ አካል እንደሚኖረን እንዴት እርግጠኞች መሆን እንችላለን? እርግጠኞች መሆን የምንችለው መንፈስ ቅዱስ ከውስጣችን ስለሚኖር ነው። ጳውሎስ በ2ኛ ቆሮንቶስ 1፡22 ላይ የመንፈስ ቅዱስን ማተምና መያዣነት ጠቅሶአል (በተጨማሪም ኤፌ. 1፡13-14 ተመልከት)። በአማኙ ውስጥ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ፥ የከበረውን አካል ጨምሮ፥ የወደፊቱን ውርስ የሚያረጋግጥ «መያዣ» ነው። በዘመናዊ የግሪክ ቋንቋ፥ መያዣ ተብሎ የተተረጎመው ቃል «የእጮኛ ቀለበት» ማለት ነው። ቤተ ክርስቲያን ለኢየሱስ ክርስቶስ የታጨች ስትሆን ፥ ሙሽራው መጥቶ ወደ ሠርጉ ሥነ-ሥርዓት እንዲወስዳት እየተጠባበቀች ነው።  ሁልጊዜም ተማምነን እንኖራለን (2ኛ ቆሮ. 5፡6-8):: የእግዚአብሔር ሕዝብ ሊገኝ የሚችለው ከሁለቱ በአንድኛው ስፍራ ነው በሰማይ ወይም በምድር (ኤፌ 3፡15)። ከእግዚአብሔር ሕዝብ ውስጥ አንድም ሰው ቢሆን በመቃብር፥ በሲዖል፥ ወይም በሰማይና በምድር መካከል በሚገኝ በማንኛውም «መካከለኛ ስፍራ» ሊኖር አይችልም። በምድር ላይ የሚኖሩት አማኞች «ሰሥጋ ያድራሉ»፥ የሞቱት አማኞች ደግሞ «ከሥጋ ተለይተዋል»። በምድር ላይ የሚኖሩ አማኞች «ከጌታ ተለይተው በስደት የሚኖሩ» ሲሆኑ፥ በሰማይ ላይ ያሉት አማኞች ግን «በጌታ ዘንድ የሚያድሩ» ናቸው።  ጳውሎስ የዚህ ዓይነት መተማመኛ ስለ ነበረው፥ ለመከራና ለሥቃይ፥ ወይም ደግሞ ለአደጋዎች አይሠጋም ነበር። ይህ ማለት ደግሞ አጓጉል የድፍረት እርምጃዎች በመውሰድ ጌታን ተፈታተነ ማለት ሳይሆን፥ ዳሩ ግን ለክርስቶስና ለወንጌሉ አገልግሎት «ሕይወቱን ለማጣት» ፈቃደኛ ነበር ማለት ነው። በእምነት እንጂ በማየት አልተመላለሰም። ለዘላለም የሚኖረውን የማይታይ ነገር እንጂ፥ ለጊዘው የሚታየውን አልመረጠም (2ኛ ቆሮ. 4፡18)። ለጳውሎስ፥ መንግሥተ ሰማይ የመድረሻው ግብ ብቻ ሳይሆን የሚያነቃቃውም ተስፋ ጭምር ነበር። በዕብራውያን 11 ውስጥ እንደምናገኛቸው የእምነት ጀግኖች ሁሉ፥ ሰማያዊቷን ከተማ በመመልከት ሕይወቱን ከዘላለማዊ እሴቶች አንጻር መርቷል።  ይህንን የ2ኛ ቆሮንቶስ ክፍል በምንከልስበት ጊዜ፥ ጳውሎስ የገጠሙትን ችግሮች ለመቋቋም እንዴት ብርታት እንደ ነበረውና ተስፋ እንዳልቆረጠ ልንመለከት እንችላለን። ሕይወትን የለወጠ ክቡር አገልግሎት ነበረው። በሰውነቱ ምድራዊ ዕቃ ውስጥ ውድ መዝገብ ነበረውና ያንኑ መዝገብ ለሚጠፋው ዓለም ለማጋራት ፈለገ። ፍርሃትን ድል የሚነግ አስተማማኝእምነትና መድረሻና ማነቃቂያ ሆኖ ያገለገለው ብሩህ የወደፊት ተስፋ ነበረው።  ስለዚህ ጳውሎስ «ከአሸናፊዎች የሚበልጥ» መሆኑ (ሮሜ 8፡37) ያን ያህል የሚያስደንቅ አይሆንም!  በኢየሱስ ክርስቶስ ያለው እያንዳንዱም አማኝ ከጳውሎስ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ድንቅ በረከቶች ስላሉት፥ ማንኛውንም የሚያጋጥመውን ችግር በእነርሱ አማካኝነት በብርታት ሊወጣ ይችላል። 

የወደፊት ተስፋ አለን (2ኛ ቆሮ. 5፡1-8) Read More »

ውድ መዝገብ አለን (2ኛ ቆሮ. 4፡7-12)

ጳውሎስ ንጽጽሩን ከአዲስ ፍጥረት ክብር ወደ ሸክላው ዕቃ ውርደት ያሻግራል። አማኙ «የሸክላ ዕቃ» ሲሆን፥ ውድ የሚያደርገው በሸክላው ውስጥ የተቀመጠው ዕቃ (መዝገብ) ክቡርነት ነው። የዕቃው ምስል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተደጋግሞ የተገለጸ በመሆኑ፥ ከዚህ ውስጥ ብዙ ነገሮችን ልንማር እንችላለን።  በመጀመሪያ ደረጃ፥ እግዚአብሔር በእኛነታችን የፈጠረን፥ እንድንፈጽመው የሚፈልግብንን ሥራ ለማከናወን እንድንችል ነው፡ እግዚአብሔር ስለ ጳውሎስ ሲናገር፥ «ይህ በአሕዛብ …. ዘንድ ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና» (የሐዋ. 9፡15) ብሏል። ማንኛውም ክርስቲያን ስጦታዎች ወይም ችሉታዎች እንደ ሌሉት በመግለጽ፥ ወይም በውስንነቶቹ ወይም በአካለ-ስንኩልነቱ ምክንያት በእግዚአብሔር ላይ ማንጎራጎር የለበትም። መዝሙር (139)፡13-16 የዝርያ መዋቅራችን በእግዚአብሔር እጆች ውስጥ እንዳለ ይናገራል። እያንዳንዳችን እኛነታችንን ተቀብለን በእኛነታችን መኖር አለብን።  ስለ ዕቃው የሚፈለገው ነገር ቢኖር ንጹሕ፥ ባዶና ለአገልግሎት ተዘጋጅቶ መቅረቡ [መገኘቱ ነው። እያንዳንዳችን «ለክብር የሚሆን፥ የተቀደሰም [የተለየ]፥ ለጌታውም የሚጠቅም ለበጎም ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ዕቃ» (2ኛ ጢሞ. 2፡21) ለመሆን መጣር አለብን። እኛ እግዚአብሔር የሚጠቀምብን ዕቃዎች ነን። ሸክላ ዕቃዎች ስለ ሆንን፥ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን ኃይል አንደገፍም።  በመሆኑም በዕቃው ውስጥ ባለው መዝገብ ላይ እንጂ በዕቃው ላይ ማተኮር የለብንም። እንግዲህ ጳውሎስ በበኩሉ መዝገቡን እስከ ጠበቀ ጊዜ ድረስ፥ እግዚአብሔር ዕቃውን እንደሚጠብቅ ስለሚያውቅ፥ የሚደርስበትን ሥቃይ ወይም መከራ አልፈራም ነበር (1 ጢሞ. 1፡11፤ 6፡20 ተመልከት)። እግዚአብሔር መከራዎች እንዲመጡ ይፈቅዳል፤ እግዚአብሔር መከራዎችን ይቆጣጠራል፤ እንዲሁም እግዚአብሔር መከራዎችን ለራሱ ክብር ይጠቀምባቸዋል። እግዚአብሔር በደካማ ዕቃዎች በኩል ክብርን ያገኛል። የቻይናን ማዕከላዊ ክፍል ለወንጌል የከፈቱት ሚስዮናዊ ጄ. ሃድሰን ቴይለር፥ «የእግዚአብሔርን ሥራ ያከናወኑት ሰዎች ሁሉ እርሱ ከእነርሱ ጋር እንዳለ በመተማመን ብቻ ታላላቅ ተግባራትን የፈጸሙ ደካማ ሰዎች ነበሩ» ብለዋል።  አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ዕቃዎቹ ከያዟቸው መዛግብት ጢቂት በመፍሰስ ሌሉችን እንዲያንጹ ዕቃዎቹ እንዲጋጩ ይፈቅዳል። መከራ የሰውን ደካማነት ብቻ ሳይሆን፥ ዳሩ ግን የእግዚአብሔርንም ክብር ይገልጻል። ጳውሎስ በዚህ በተጠቀሰው አንቀጽ ውስጥ የተቃራኒ ነገሮችን ዝርዝር ያስቀምጣል፡- ሸክላ ዕቃዎች – የእግዚአብሔር ክብር፤ የኢየሱስ ሞት – የኢየሱስ ሕይወት፤ ሞት በሥራ ላይ – ሕይወት በሥራ ላይ። ይሁን እንጂ ተፈጥሮአዊ አእምሮ የዚህ ዓይነቱን መንፈሳዊ እውነት ሊረዳ ስለማይችል፥ ለምን ክርስቲያኖች በመከራ ላይ ድልን እንደሚቀዳጁ ለመረዳት ያዳግተዋል።  በዕቃው ሳይሆን በመዝገቡ ላይ ማተኮር እንደሚገባን ሁሉ፥ እንደዚሁም በአገልጋዩ ላይ ሳይሆን በጌታ ላይ ማተኮር አለብን። መከራ ብንቀበል፥ ስለ ኢየሱስ ብለን ነው። እኔነታችንን የምንገድለው፥ የክርስቶስ ሕይወት እንዲገለጽብን ነው። በመከራ ውስጥ ብናልፍ፥ ክርስቶስ እንዲከብርብን ነው። ይህ ሁሉ ደግሞ ለሌሎችም ጥቅም ነው። ክርስቶስን ስናገለግል፥ ሞት በእኛ ላይ ይሠራል፤ ዳሩ ግን ለምናገለግላቸው ሰዎች ሕይወት ይሆንላቸዋል።  ዶክተር ጆን ሄንሪ ጆውት፥ «ምንም ዋጋ የማያስከፍል አገልግሎት፥ ምንም ነገር አይሠራም» ብለዋል። ትክክል ናቸው። አንድ ጊዜ እኔና በመጋቢነት የሚያገለግሉ ወዳጄ አንድ ወጣት ግሩም ስብከት ሲያቀርብ ሰምተን ነበረ፤ ሆኖም ስብከቱ አንድ የሚጎድለው ነጥብ ስለ ነበረ፥ ለወዳጄ፥ «አንድ ነገር ይጎድለዋል» ስል አሳቤን እካፈልኩት። እርሱም ፥ «አዎን» ብሉ መለሰና በማከልም ፥ «የወጣቱ ልብ እስካልተሰበረ ድረስ ጉድለቱ ሊሟላ አይችልም። ለአፍታ ያህል መከራ ከተቀበለ በኋላ ግን፥ ተስማሚ ስብከት የማዘጋጀት ብቃት ይኖረዋል» በማለት መለሰልኝ።  የአይሁድ ሃይማኖት አስፋፊዎች መከራ አልተቀበሉም። በመሆኑም ደኅንነት ያላገኙትን ነፍሳት ለመማረክ በመጣር ፈንታ፥ ጳውሎስ በመሠረታቸው አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚገኙትን የዳኑትን ሰዎች በአቋራጭ ይሰርቁ ነበር። ለሕዝቡ መሥዋዕት በመሆን ፈንታ፥ ሕዝቡ ለእነርሱ መሥዋዕትነት እንዲከፍል ያደርጉ ነበር (11፡20)። እነኝህ የሐሰት አስተማሪዎች ለሌሉች የሚያካፍሉት መዝገብ አልነበራቸውም። ከእጃቸው ውስጥ የሚገኙ ነገሮች ቢኖሩ ስለ ቀድሞው ኪዳን የሚያወሩ አንዳንድ የመዘክር ቁርጥራጮች፥ የሰውን ሕይወት ሊመግቡ የማይችሉ የደበዘዙ ቅርሳ ቅርሶች ብቻ ነበሩ።  በበኩሌ፥ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት አንድ መጋቢ ሕዝቡን በሚያገለግልበት ጊዜ ለጌታ ታማኝ ለመሆን ስለሚከፍለው ዋጋ ምንም ነገር እንደማያውቁ ተገንዝቤአለሁ። ይህም ርዕስ በ2ኛ ቆሮንቶስ ውስጥ ከተጠቀሱትና የጳውሎስን መከራዎች ከሚዘረዝሩት ሦስት ክፍሉች አንደኛው ነው። ሌሎቹ ሁለቱ ክፍሎች 6፡1-10 እና 11፡16-12:10 ናቸው። የእውነተኛ አገልግሎት መፈተኛው ሽልማት ሳይሆን ጠባሳ ነው። «እኔ የኢየሱስን ማኅተም ጠባሳዎች] በሥጋዩ ተሸክሜአለሁና ከእንግዲህ ወዲህ አንድ ስንኳ አያድክመኝ» (ገላ. 6፡17)።  ተስፋ ቆርጦ ከማቆም እንዴት እንድናለን? የምንድነው፥ በሸክላ ዕቃዎቻችን ውስጥ የወንጌሉ መዝገብ እንዲቀመጥ ዕድል እንደ ተሰጠን በማስታወስ ነው!

ውድ መዝገብ አለን (2ኛ ቆሮ. 4፡7-12) Read More »

የሚራራ ልብ (2ኛ ቆሮ. 2፡1-11)

ከቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን አንዱ ጳውሎስን በእጅጉ አሳዝኖት ነበር። ይህ ሰው ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 5 ውስጥ የጠቀሰውና በግልጽ በዘማዊነት ኃጢአት የተጠመደው ሰው ይሁን፥ ወይም የጳውሎስን የሐዋርያነት ሥልጣን በይፋ የተፈታተነው ሌላው ሰው፥ በርግጠኛነት ልንናገር አንችልም። ጳውሎስ ይህንኑ ችግር ለመፍታት በፍጥነት ወደ ቆሮንቶስ የገሰገሰ ሲሆን (2ኛ ቆሮ. 2:14፤ 13፡1)፥ በተጨማሪም ስለ ሁኔታው የሚያሳዝን ደብዳቤ ጽፎላቸዋል። በዚህም ሁሉ፥ የርኅራኄ ልብ አሳይቷል። የጳውሎስን ፍቅር የሚያመለክቱትን የሚከተሉትን መረጃዎች ልብ በል።  በመጀመሪያ፥ ለሌሎች ቅድሚያ ሰጥቷል (2ኛ ቆሮ. 2፡1-4)። ስለ ራሱ ስሜቶች ሳይሆን፥ በመጀመሪያ ለሌሎች ሰዎች ስሜቶች ያስብ ነበር። በክርስትና አገልግሎታችን፥ ትልቅ ደስታ የሚያመጡልን ሰዎች ትልቅ ሐዘንም ሊፈጥሩብን ይችላሉ፤ ጳውሎስም እያለፈበት የነበረው ይህንኑ ዓይነት ልምምድ ነበር። ከልቡ ከተሰማው ጭንቀት የፈለቀና በክርስቲያን ፍቅር የታጀበ ጠንካራ ደብዳቤ ይጽፋል። ዓቢይ መሻቱም ቤተ ክርስቲያኗ የእግዚአብሔርን ቃል እንድታከብር፥ አጥፊውን እንድትቀጣና ለማኅበረ-ምዕመናኑም ንጽሕናና ሰላም እንድታመጣ ነበር።  «የወዳጅ ማቁሰል የታመነ ነው፤ የጠላት መሳም ግን የበዛ ነው» (ምሳሌ 27፡6)። ጳውሎስ የተጠቀማቸው ቃላት የሚወዳቸውን ወገኖች ሊያሳዝኑ እንደሚችሉ ያውቅ ስለነበር፥ ልቡ በሐዘን ተነክቶ ነበር። ዳሩ ግን (ማንኛውም አፍቃሪ አባት እንደሚያውቀው) ሰውን ስለ ፍቅር ብሎ በመጉዳትና በጠላትነት በማጥቃት መካከል ያለውንም ትልቅ ልዩነት ያውቅ ነበር። አንዳንድ ጊዜ የሚወዱን ሰዎች ራሳችንን እንዳንጎዳ ሲሉ ሊቀጡን ይገባል።  ጳውሎስ ሐዋርያዊ ሥልጣኑን በመጠቀም ሰዎች እንዲያከብሩትና እንዲታዘዙት ለማድረግ ይችል ነበር፤ ይሁንና በፍቅርና በትዕግሥት ማገልገሉን መረጠ። እግዚአብሔር የጳውሎስ ዕቅዶች መለወጥ ቤተ ክርስቲያንን ከተጨማሪ ሕመም የመጠበቅ ዓላማ እንደ ነበረው ያውቅ ነበር (2ኛ ቆሮ. 1፡23-24)። ፍቅር ሁልጊዜም የሌሎችን ስሜቶች በማጤን ከማንኛውም ነገር በፊት ለእነርሱ የሚበጀውን ያስቀምጣል።  እንዲሁም ፍቅር ለሌሎች ይሻሻሉና ያድጉ ዘንድ ለመርዳት ይሻል (2ኛ ቆሮ 2፡5-6)። እዚህ ላይ ጳውሎስ፣ የተቃወመውንና የቤተ ክርስትያንን ቤተሰብ የከፋፈለውን ሰው ስም እንዳልጠቀሰ ማስተዋል ጠቃሚ ነው። ይሁንና ጳውሎስ ለራሱ ለሰውየው ጥቅም ሲል ቤተ ክርስቲያኗ ይህንኑ ሰው እንድትቀጣ አሳስቧል። ይህ በ1ኛ ቆሮንቶስ 5 ውስጥ የተጠቀሰው ዘማዊው ሰው ከሆነ፥ ቤተ ክርስቲያን ጉባዔ ተቀምጣ እንደ ቀጣችውና እርሱም ከኃጢአቱ ንስሐ ገብቶ እንደ ተመለሰ እነዚሁ ቁጥሮች ያመለክታሉ።  እውነተኛ ቅጣት የፍቅርን መኖር ያመለክታል (ዕብ 12 ተመልከት)። ልጆችን በማሳደጉ ረገድ «ዘመናዊ እይታ» ያላቸው አንዳንድ ወጣት ወላጆች ከመጠን በላይ እንደሚወዷቸው በመናገር፥ የማይታዘዙላቸውን ለመቅጣት አይፈልጉም። ዳሩ ግን በርግጥ ልጆቻቸውን ቢወዱ ኖሮ፥ ጥፋታቸውን በማሳየት እንዲታረሙ በረዷቸው ነበር።  የቤተ ክርስቲያን የሥነ-ሥርዓት እርምጃ ተወዳጅነት ያለው ወይም በስፋት የሚሠራበት ዓይነት አይደለም። እጅግ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ይህን ዓይነቱ ሁኔታ ሲያጋጥማቸው ቅዱሳት መጻሕፍትን በመታዘዝ፥ «እውነትን በፍቅር በመናገር» (ኤፌ 4፡15) ምትክ፥ ብሉም ሁኔታውን በድፍረት ከመጋፈጥ የሚመርጡት፥ ነገሩ ወደ ጎን ገሸሽ አድርገው መተውን ነው። ንጽሕና ሳይኖር፥ እውነተኛ መንፈሳዊ ሰላም ሊኖር ስለማይችል፥ «የሆነውን ሁሉ ዋጋ ከፍሎ በሰላም መኖር» የሚለው መርሆ ጨርሶ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም (ያዕ.3፡15-18)። ወደ ጎን ገሸሽ ተደርገው የተተዉት ችግሮች በኋላ የመባዛትና ከቀድሞውም የከፉ ችግሮችን የመፍጠር ዕድል አላቸው።  ጳውሎስ ያጋለጠውና ቤተ ክርስቲያን የቀጣችው ወንድም ፍቅር ያለበት አትኩሮት ተሰጥቶት ርዳታ አግኝቷል። ልጅ ሳለሁ፥ ምንም እንኳ ከተቀበልሁት የሚልቅ ቅጣት እንደሚገባኝ መናዘዝ ቢኖርብኝም፥ ቤተሰቦቼ የሚሰጡኝን ቅጣት ሁልጊዜም አልወድም ነበር። ዳሩ ግን አሁን ወደ ኋላ ተመልሼ ሳስብ፥ ራሴን ለባሰ ጥቃት እንዳላጋልጥ ለመከላከል ሲሉ ቤተሰቦቼ ከፍቅራቸው የተነሣ እስኪጎዱኝ ድረስ ጨክነው ሊቀጡኝ በመውደዳቸው እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። «ይህን ማድረጋችን አንተን ከሚጎዳው በላይ እኛንም ይጎዳናል» ሲሉ ይናገሩኝ የነበረው ምን ማለት እንደ ሆነ፥ አሁን በግልፅ ተረድቼዋለሁ።  በመጨረሻም፥ ፍቅር ይቅር ይላል፤ ያበረታታልም (2ኛ ቆሮ. 2፡7-11)። ጳውሎስ የቤተ ክርስቲያኗ ቤተሰብ ያንን ሰው ይቅር እንዲል ያበረታታ ሲሆን፥ ይህንኑ ምክር ከሥራ ላይ እንዲያውሉት ጠንካራ ምክንያቶችን ያቀርባል። በመጀመሪያ ደረጃ፥ ለሰውየው ይቅርታ መደረጉ «ከልክ ባለፈ ኃዘን እንዳይዋጥ» (ቁ 7-8)፥ ለራሱ ጥቅም ሲባል ነበር። ይቅርታ የተሰበረውን ልብ ለመጠገን የሚረዳ መድኃኒት ነው። ቤተ ክርስቲያን ይህንኑ ንስሓ የገባ ሰው የፍቅሯ ተካፋይ የማድረጓን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነበር።  በራሴ የመጋቢነት አገልግሎት ውስጥ፥ የሥነ-ሥርዓት እርምጃ የተወሰደባቸው አባላት ይቅርታ ተደርጎላቸው ወደ ኅብረቱ በተቀላቀሉባቸው ጉባዔዎች ላይ መልእክት አካፍያለሁ፤ እነዚህም በሕይወቴ ውስጥ ከፍተኛና የተቀደሱ ሰዓታት ነበሩ። የቤተ ክርስቲያኗ ቤተሰቦች ይቅርታ ለተደረገለት ወንድም ወይም እህት ኃጢአታቸው እንደ ተዘነጋና ወደ ኅብረቱ እንደ ተመለሱ ሲያረጋግጡላቸው አካባቢው ድንቅ በሆነ በጌታ ሕልውና ይሞላል። ልጁን የሚቀጣ ወላጅ ሁሉ ከቅጣቱ አስከትሉ ፍቅርና ይቅርታው ከልብ የመነጨ ለመሆኑ ዋስትና መስጠት አለበት፤ ይህ ካልሆነ ግን ቅጣቱ ከማቃናት ይልቅ የባሰ ጠማማነትን ያስከትላል።  ክርስቲያኖች ለጌታ ሲሉ ይቅር ለተባለው ወንድም ፍቅራቸውን ያለማጓደል መለገስ አለባቸው (ቁ 9-10)። እንዲሁም ቅጣት ለወንድም መሰጠት ያለበት ግዴታ የመሆኑን ያህል፥ ለጌታም የመታዘዝ ኃላፊነትን ያቀፈ ጉዳይ ነው። ይህን የመሰለው ችግር የሚንፀባረቀው ባዘነው ሐዋርያና ኃጢአትን በፈጸመው ወንድም መካከል ብቻ ሳይሆን፥ ኃጢአትን በፈጸመው ወንድምና በሚያዝነው አዳኝ መካከልም ጭምር ነው። ያ ወንድም በእርግጥም በቤተ ክርስቲያን እና በጳውሎስ ላይ በደል ቢፈጽምም፥ ዳሩ ግን ከሁሉም በላይ በጌታ ላይ ኃጢአትን ሠርቷል። ፍርሃት የሚያጠቃቸው የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ይህን የመሳሰለውን ሁኔታ በታማኝነት በመጋፈጥ ምትክ «አለባብሰው» ሲያልፉት፥ የጌታን ልብ ያሳዝናሉ።  ጳውሎስ ሦስተኛ ምክንያትም ሰጥቷል፡- ጥፋት የፈጸመውን ወንድም ለቤተ ክርስቲያኗ ደኅንነት ሲሉ ይቅር ማለት ነበረባቸው (ቁ 11)። ለኃጢአት ተገቢ የሆነ መጽሐፈ ቅዱሳዊ መፍትሔ እንዳይገኝለት ከምዕመናኑ አንዱ እንቅፋት ሲሆንና ይቅርታ ለማድረግ ሳይፈቅድ ሲቀር፥ ሰይጣን በማኅበረ-ምዕመናን ውስጥ ተልዕኮውን የሚፈጽምበት ቀላል «መነሻ» ያገኛል። ይቅርታን የማያደርግ መንፈስ ካለን፥ መንፈስ ቅዱስን በማሳዘን «ለዲያብሎስ ፈንታ» (ኤፌ 4፡27-32) እንሰጣለን።  ከሰይጣን «ማታለያ ዘዴዎች» አንዱ ኃጢአት የሠሩ አማኞች ፍጹም ተስፋ እንዲቆርጡ መክሰስ ነው። በእኔም በኩል፥ ከሰይጣን ጭቆናና ክስ በታች በመውደቃቸው ምክንያት እርዳታ ሽተው ደብዳቤ የጻፉልኝ ወይም ስልክ የደወሉልኝ ሰዎች በብዛት አጋጥመውኛል። መንፈስ ቅዱስ የሚወቅሰን፥ ኃጢአታችንን ተናዝዘን ለመንጻት ወደ ክርስቶስ እንድንመለስ ሲሆን፥ ዳሩ ግን ሰይጣን ተስፋ ቆርጠን የእምነት ጉዞአችንን እንድንተው ይከሰናል።  ያጠፋው ወንድም ወይም እህት ከመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ አኳያ ከተቀጡና ንስሐ ከገቡ በኋላ፥ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቤተሰብ ይቅርታ በማድረግ እንደ ቀድሞው ሊያቅፏቸው ይገባል፤ ነገሩም ዳግመኛ ላይታወስ መደምደም አለበት። (ዳግም ላይወሳ)። የቤተ ክርስቲያኒቱ ቤተሰብ ወይም ከቤተሰቡ ውስጥ ማንኛውም ሰው ይቅርታን የማያደርግ መንፈስ ካለው፥ ሰይጣን በቤተ ክርስቲያን ላይ አዳዲስ ጥቃቶችን ለማስከተል በዚሁ ቀዳዳ ይጠቀማል።  ጳውሎስ ንጹሕ ሕሊናና የሚራራ ልብ ስለ ነበረው፥ ከፊቱ የተጋረጡትን ችግሮች ለማሸነፍ ችሏል። ዳሩ ግን ለድል ያበቃው ሦስተኛው መንፈሳዊ ሀብት ቀጥሎ የተጠቀሰው ነበር::

የሚራራ ልብ (2ኛ ቆሮ. 2፡1-11) Read More »

አጽናናቸው (2ኛ ቆሮ. 13፡9-14)

በመጀመሪያ፥ ጳውሎስ ለእነርሱ ባቀረበው ጸሎት የቆሮንቶስን ሰዎች ያጽናናል (ቁ 9)። «ኪንግ ጄምስ ቨዥን» በሚባለው የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ «እንመኛለን» ተብሎ የተተረጎመው ቃል፥ በአማርኛ መጽሐፋችን ውስጥ «እንጸልያለን» ተብሉ ተጽፎአል። ጳውሎስ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ ጸልዮአል፤ ይህም ኃጢአት የሌለበት ፍጹምነት ሳይሆን፥ «መንፈሳዊ ብስለት» ነበር። ይህ ቃል በግሪኩ፥ «ብቁ መሆን፥ መታጠቅ» የሚሉት ቃላት ወገን ነው። የሕክምና ቃል እንደ መሆኑ፥ «የተሰበረ አጥንት መጠገን፥ ተጠምዝዞ የዞረውን እግር ወይም እጅ ማስተካከል» ማለት ነው። እንዲሁም ደግሞ፥ «አንድን መርከብ ለጉዞ ብቁ ማድረግ» እና «ሠራዊትን ለጦርነት ማስታጠቅ» የሚሉ ትርጉሞች ይኖሩታል። በማቴዎስ 4፡21 ላይ «መረብ ማበጀት» ተብሎ ተተርጉሞአል።  ከሙታን ከተነሣው ከጌታችን አገልግሎቶች አንዱ ሕዝቡን ፍጹም በማድረግ ማዘጋጀት ነው (ዕብ 13፡10-21)። በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ኅብረት ውስጥ (ኤፌ. 4፡11-16) ሕዝቡን ለሕይወትና ለአገልግሉት ለማስታጠቅ፥ በእግዚአብሔር ቃል ይጠቀማል (2ኛ ጢሞ. 3፡16-17)። እንዲሁም መከራን ለመቋቋም መዘጋጃ መሣርያ አድርጎ ይጠቀምበታል (1ኛ ጴጥ. 5፡10)። ክርስቲያኖች እርስ በርሳቸው በጸሉት ሲደጋገፉ (1ኛ ተሰ. 3፡10) እና በግልም ሲረዳዱ (ገላ.6፡1 «አቅኑት» የሚለው ከዚሁ ፍጹም ተብሉ ከተተረጎመው ቃል ጋር አንድ ዓይነት ነው)፥ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ ያደረገው ጌታ ቤተ ክርስቲያኑን ያገለግላታል – ለአገልግሉትም ብቁ ያደርጋታል።  በመነጣጠል ሕይወት ውስጥ፥ ሚዛናዊነትን የጠበቀ ክርስቲያናዊ ዕድገትና አገልግሎት ተግባራዊ ይሆናል ብሎ ከቶውንም አይታሰብም። አንድ ሰው ሲናገር፥ «አንድን ክርስቲያን ከኅብረቱ ነጥሉ ማሳደግ ማለት፥ አንድን ንብ ከመንጋው ነጥሉ እንደማሳደግ ያህል የማይሞከር ነው» ብሏል። ክርስቲያኖች እርስ በርስ የሚኖሩና እርስ በርስ የሚፈላለጉ ናቸው። አንድ ሕፃን ልጅ ሚዛናዊነቱ ተጠብቆ በመልካም ሁኔታ እንዲያድግ ከተፈለገ፥ በሚያፈቅር ቤተሰብ ውስጥ ማደግ አለበት። ዛሬ አንድን ክርስቲያን በአጥቢያ ማኅበረ-ምዕመናን ውስጥ ካለው ስፍራ ነጥሎ «በግል የክርስትና» ልምምድ እንዲመላለስ የማድረጉ አትኩሮት፥ የተሳሳተና በጣም አደገኛ ነው። እኛ በጎች ስለ ሆንን፥ በአንድ ላይ ልንሰማራ ይገባል። የአንድ አካል ክፍሉችም ስለ ሆንን፥ አንዳችን ሌላችንን ልናገለግል ይገባል።  በ2ኛ ቆሮንቶስ 13፡10፥ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች ሁለተኛውን መጽናኛ ሰጥቷል – የእግዚአብሔር ቃል። ጳውሎስ ይህንን ደብዳቤ የጻፈው የአንድን ማኅበረ-ምዕመናን ጉድለት ለመሸፈን ሲሆን፥ ዳሩ ግን በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል አካል በመሆኑ ዛሬ እኛም እንጠቀምበታለን። ይህ ደብዳቤ የሐዋርያውን በመካከላቸው በአፀደ-ነፍስ የመገኘት ያህል ሥልጣን ተሸክሞአል። የጳውሎስ ትልቁ ፍላጎት ማኅበረ-ምዕመናኑ ለደብዳቤው የሚኖራቸው መታዘዝ ችግሩን እንዲፈታውና እርሱ በሚጎበኛቸው ጊዜ በሥልጣኑ ላለመጠቀም ነበር።  አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል አገልጋይ ከማነጹ በፊት ለመናድና ለማፍረስ የሚገደድበት ጊዜ አለ። (ኤር. 1፡7-10 ተመልከት)። ገበሬው ዘር ከመዝራቱና መልካም ምርት ከመሰብሰቡ በፊት፡ አካባቢውን መመንጠር አለበት። ጳውሎስ እውነትን በልባቸውና በአእምሮአቸው ውስጥ ከማነጹ በፊት፥ ከክርስቲያኖች አእምሮ ውስጥ የተሳሳተውን አስተሳሰብ ማስወገድ ነበረበት (2ኛ ቆሮ. 10፡4-6)። ምንም እንኳ ትልቅ ፍላጎቱ ማነጽ ቢሆንም፥ የቆሮንቶስ ሰዎች አሉታዊ አመለካከት ግን ጳውሎስን ወደ ማፈራረሱ እንዲያመራ አስገደደው።  በራሴ የአገልግሎት ዘመን ውስጥ፥ ሁለት የማነጽ ፕሮግራሞችንና ሁለት እንደ ገና መልሶ የማዋቀር ፕሮግራሞች አከናውኛለሁ። ምንም እንኳን የሚጠይቁዋቸው ልፋቶች ከፍተኛ ቢሆኑም፥ ለእኔ የማነጽ (የግንባታ) ፕሮግራሞች ይቀሉኛል። አንድን አሮጌ ሕንፃ አፍርሶ ከመሥራት ይልቅ፥ አንድን አዲስ መዋቅር በአዲስ መሬት ላይ ማነጹ ቀላልም፥ ጊዜ የማያባክንም ነው። እንደዚሁም፥ የቆየውን አማኝ የተሳሳተ አሳብ ለማስለወጥ ከመሞከር ይልቅ፥ አንድን አዲስ አማኝ ወስዶ የእግዚአብሔርን ቃል ማስተማሩ ቀላል ተግባር ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ በአእምሮአችን ውስጥ የተከማቸውን የተሳሳተ የአስተሳሰብ ግድግዳ እስኪንደው ድረስ፥ የተሳሳቱ አሳቦች ለረዥም ጊዜ እውነትን «ለመቋቋም፥ ለመከላከል» ይችላሉ።  ጳውሎስ ቅዱሳኑ ጸጋን፥ ፍቅርንና ሰላምን እንዲከታተሉ ያበረታታቸዋል (ቁ. 11-12)። «ደኅና ሁኑ» ተብሎ የተተረጎመው ቃል «ጸጋ» የሚል ትርጉም ሲኖረው፥ በዚያን ዘመን የተለመደ የሰላምታ ዓይነት ነበር። «ተደሰቱ» ተብሎም ሊተረጎም ይችላል። ፍጹማን ሁኑ የሚለው ትዕዛዝ፥ በቁጥር 9 ላይ ጳውሎስ ካቀረበው ጸሎት ጋር የተያያዘ ሲሆን፥ «የበሰላችሁ፥ የጸናችሁና ለሕይወት የምትመቹ የሆኑ» የሚል አሳብ አለው። «በአንድ ልብ ሁኑ» የሚለው «ተጽናኑ» የሚል ትርጉም ይኖረዋል ። ከእነዚያ ሁሉ ኃጢአቶቻቸውና ችግሮቻቸው ባሻገር፥ ለመጽናናት የሚያስችሉ በቂ ምክንያቶች ነበሯቸው።  በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ መከፋፈል ስለ ነበር፥ በሰላም ኑሩ የሚለው አስፈላጊ ምክር ነበር (12:20 ተመልከት)። በፍቅር ቢመላለሱና በአንድ ልብ ለመኖር ቢፈልጉ የእርስ በርስ ጦርነቶቹ አብቅተው፥ በኅብረታቸው ውስጥ ሰላም ይኖር ነበር። በአንድ ልብ መሆን ማለት ሁላችንም በሁሉም ነገር ላይ እንስማማለን ማለት ሳይሆን፥ ዳሩ ግን አላስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ አለመግባባትን ለማስወገድ እንችላለን ማለት ነው።  አምላካችን «የፍቅርና የሰላም አምላክ» ነው (13፡11)። ታዲያ ከውጭ ያለው ዓለም ከአኗኗራችንና የቤተ ክርስቲያንን ሥራ ከምናከናውንበት ሁኔታ በመንሣት የእኛን የፍቅርና የሰላም ሕይወት ለረዳው ይችል ይሆን? ከደኅንነት ርቆ የጠፋው ዓለም ስለ ቀደመችው ቤተ ክርስቲያን፥ «አቤት እንዴት ይዋደዳሉ!» ይል ነበር፤ እነሆ በዛሬው ጊዜ ግን ቤተ ክርስቲያን የዚህ ዓይነቱን ምስጋና ከተቀበለች ረዥም ጊዜ ሆኖአታል።  ከጥንት ጀምሮ፥ መሳሳም የሰላምታ ዓይነትና እንደዚሁም የፍቅርና የኅብረት መግለጫ ነበር። ይሁንና ብዙውን ጊዜ የሚከናወነው በተመሳሳይ ጾታዎች መካከል ነበር። የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን አማኞች እርስ በርስ የነበራቸውን ፍቅርና መተሳሰብ ለማመልከት፥ የሰላምንና የፍቅርን መሳሳም ያከናውኑ ነበር። ለኢየሱስ ክርስቶስ ከነበራቸው መሰጠት የተነሣ፥ ክንውኑ «የተቀደሰ አሳሳም» ነበር። ለቀድሞዋ ቤተ ክርስቲያን አባላት፥ አዳዲስ አማኞችን የጥምቀት ሥርዓታቸውን ከፈጸሙ በኋላ፥ መሳምና ወደ ኅብረቱ መቀላቀል (አቀባበል ማድረግ) እንግዳ ነገር አልነበረም።  የእግዚአብሔር ሕዝብ ዕለታዊ ኅብረት ለቤተ ክርስቲያን አስፈላጊ ነው። ስጉባዔው ኅብረት ውስጥም ሆነ በሌሎች ስፍራዎች እርስ በርሳችን ሰላምታ ልንለዋወጥና አንዳችን ለሌላችን ያለንን አሳቢነት ልንገልጽ ይገባል። በቁጥር 12 ላይ ይህንን ምክር በመስጠት ጳውሎስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከሚገኙ ከባድ ችግሮች በአንዱ ላይ እያነጣጠረ ነበር – ይኸውም በመከፋፈላቸውና እርስ በርስ ሊተሳሰቡ ባለመቻላቸው ላይ ነበር።  በቁጥር 14 ላይ የሚገኘው የማጠቃለያ ቡራኬ፥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እጅግ ተወዳጁና አዘውትሮም በአገልግሎት ላይ የሚውል ነው። ይህም በሥላሴ አንድነት ምሥጢር ላይ (ማቴ. 28፡19 ተመልከት) እና የእግዚአብሔር ንብረት በመሆናችን በምናገኛቸው በረከቶች ላይ ያተኩራል። የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፥ እኛን ሀብታም ለማድረግ እርሱ ድሀ በሆነበት ጊዜ የተፈጸመውን የልደት ታሪክ ያስታውሰናል (2ኛ ቆሮ. 8፡ 9 ተመልከት)። የእግዚአብሔር ፍቅር እግዚአብሔር ልጁን ለኃጢአታችን መሥዋዕት አድርጎ ወደሰጠበት ወደ ጎልጎታ ይወስደናል ( ዮሐ 3፡16)። የመንፈስ ቅዱስ ኅብረት፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ስለ ወረደበትና ቤተ ክርስቲያንን ስለ መሠረተበት ሁኔታ ያስታውሰናል (የሐዋ. 2)።  በዚያን ጊዜ የቆሮንቶስ ለአማኞች፥ በዛሬው ጊዜ ደግሞ ለሁሉም አማኞች፥ የጸጋ፡ የፍቅርና የኅብረት በረከቶች በጥብቅ ያስፈልጉአቸዋል። ይሁንና፥ በዚያን ዘመን የአይሁድ ሃይማኖት አስፋፊዎች፡ ዛሬ ደግሞ መናፍቃን፥ ከጸጋ ይልቅ በሕግ ከፍቅር ይልቅ በመለየት፥ እንዲሁም ከኅብረት ይልቅ በመነጣጠል ላይ ያተኩራሉ። መከፋፈልን ያስከተለው የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ውድድር ሊቀረፍ የሚችለው ሕዝቡ በእግዚአብሔር ጸጋና ፍቅር ሲመላለስ ብቻ ነበር።  ቤተ ክርስቲያን ተአምር ስለ ሆነች፥ ልትቆም የምትችለውም በእግዚአብሔር የተአምር አገልግሎት ብቻ ነው። ምንም ያህል ሰብዓዊ ጥበብ፥ ብቃት፥ ወይም ዕቅድ ቤተ ክርስቲያን መሆን የሚገባትን እንድትሆን አያደርግም። ይህንን ሊያደርግ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው። እያንዳንዱ አማኝ በእግዚአብሔር ጸጋ ላይ የሚደገፍ፥ በእግዚአብሔር ፍቅር የሚመላለስ፥ በሥጋ ከመመላለስ ይልቅ በመንፈስ ቅዱስ ኅብረት ውስጥ የሚሳተፍ ከሆነ፥ መፍትሔ ሰጪ እንጂ ችግር ፈጣሪ አይሆንም። ይህም ሲሆን ሕይወቱ የተባረከ ይሆናል። በረከቱም ለሌሎች ይተርፋል!  እግዚአብሔር ይህን ዓይነት ክርስቲያን እንዲያደርግህ በጸሎት ጠይቀው።  ተጽናና – ሌሎችንም አጽናና። 

አጽናናቸው (2ኛ ቆሮ. 13፡9-14) Read More »

አስጠነቀቃቸው (2ኛ ቆሮ. 13፡1-8)

ጳውሎስ ደብዳቤውን ለመዝጋት በሚቃረብበት ወቅት፥ ለቆሮንቶስ ሰዎች የነበረው ታላቅ ፍቅር አንድ የመጨረሻ ልመና እንዲያቀርብ ገፋፋው። በቤተ ክርስቲያናቸው የሚያደርገው ሦስተኛው ጉብኝቱ ለእርሱም ሆነ ለእነርሱ የሚያሳዝን ነገር እንዲሆን አልፈለገም ነበር። ለእነርሱ ልቡን ከፍቶላቸዋል፤ ስለ አገልግሉቱ ማብራርያ ሰጥቶአቸዋል፤ ለነቀፋዎቻቸው ምላሽ ሰጥቷል፤ እንዲሁም ለእግዚአብሔር ቃል እንዲገዙና ጌታን እንዲታዘዙም ገፋፍቶአቸዋል። እንግዲህ ከዚህ በላይ ምን ሊያደርግ ወይስ ምን ሊል ይችል ነበር?  በዚህ በደብዳቤው መዝጊያ ክፍል ውስጥ ጳውሎስ የቆሮንቶስ ሰዎችን ወደ መታዘዝና መገዛት ለማምጣት በሚያደርገው ጥረት፥ በሦስት የአቀራረብ ዘዴዎች ተጠቅሟል።  አሳፈራቸው (2ኛ ቆሮ. 12:11-21) ልጆች በነበርን ጊዜ፥ ከወላጅም ይሁን ከጎረቤት«ኀፍረት አይሰማህም!» የሚል ቃል ሲሰነዘርብን፥ ስንት ጊዜ ሰምተን ይሆን? ሰዎች ስለ ክፉ ነገራቸው ወይም አመለካከታቸው ማፈራቸው መልካም ነው። አንድ ጥፋተኛ ሰው የኀፍረት ስሜት የማይሰማው ከሆነ፥ ደንዳና ልብና የደነዘዘ ሕሊና እንዳለው ይታወቃል። «ርኩስን ነገር ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፤ እፍረትንም አላወቁም» (ኤር. 6፡15)።  በመጀመሪያ፥ ጳውሎስ የቆሮንቶስን ሰዎች ሊያመሰግኑት ባለመፈለጋቸው በመውቀስ ያሳፍራቸዋል (2ኛ ቆሮ. 12፡11-13)። እርሱን ለትምክህት ከመገፋፋት ይልቅ፥ ስለ እርሱ በትምክህት ሊናገሩ ይገባቸው ነበር። ከዚህ ይልቅ ግን፥ የቆሮንቶስ ሰዎች ተወዳጅነትን አትርፈው ቤተ ክርስቲያናቸውን በመቆጣጠር ላይ ስለነበሩት «ምጡቅ-ሐዋርያት»፥ የአይሁድ ሃይማኖት አስፋፊዎች በትምክህት ይናገሩ ነበር።  ጳውሎስ ከእነዚህ ሰዎች ያንስ ነበር? በምንም ዓይነት! የቆሮንቶስ ሰዎች ጳውሎስን በተግባር አይተውታል፤ እንዲያውም፥ ነፍሳቸውን ጭምር ወደ ትክክለኛ አቅጣጫ የመራላቸው ባለውለታቸው ነበር። በመካከላቸውም ሐዋርያነቱን የሚያረጋግጡ ተአምራዊ ነገሮችን አድርጎ ነበር (ዕብ. 2፡1-4)። ውጫዊ ስደትንና ውስጣዊ ችግሮችን ተጋፍጦ፥ በቆሮንቶስ ውስጥ በአገልግሎቱ ጸንቶ ነበር። ከቤተ ክርስቲያኗ ምንም ነገር አልወሰደም ነበር። ጳውሎስ አሁንም «በእናንተ ላይ ሸክም ሳልሆን ከመቅረቴ በቀር፥ ከሌሎች አብያተ-ክርስቲያናት እናንተን ያሳነስሁአችሁ በምንድነው? ይህም ጥፋት ሆኖ ከተቆጠረ ይቅር በሉኝ» (2ኛ ቆሮ. 12፡13 – አዲስ ትርጉም) በማለት በረቀቀ ቅኔአዊ አነጋገር ተጠቅሟል።  ከክርስትና ሕይወት አደጋዎች አንዱ፥ በረከቶቻችንን እንደ ልማዳዊ ነገሮች አድርገን መውሰዳችን ነው። ፈሪሃ-እግዚአብሔር ያደረበት መጋቢ ወይም የሰንበት ትምህርት ቤት አስተማሪ ብዙ ነገር ሊያደርግልን ይችላል፤ እኛ ግን እንደ ተራ ነገር እንቆጥረዋለን። (ላለማዳላት፥ አንዳንድ ጊዜ መጋቢዎች የቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በረከቶችን እንደ ተራ ነገር ቆጥረው እንዲቀበሉ በማድረጉ በኩል ጥፋት እንዳለባቸው ለመግለጽ እወዳለሁ።) በዚህ ዝንባሌ በመመራት ካለፃመስገናቸው የተነሣ ጳውሎስ ሲያሳፍራቸው እናያለን (ቁ 14-18)።  ይህን የመሳሰሉ ችግሮች ቢኖሩም ቅሉ፥ ጳውሎስ ግን የቆሮንቶስን ሰዎች በመጎብኘት ታማኝ ነበር፤ እናም አሁን ሦስተኛውን ጉብኝት ሊያደርግ ነበር (13፡1 ተመልከት)። በማመስገን ፈንታ፥ የቆሮንቶስ ሰዎች ጳውሎስስ ዕቅዱን በመቀየሩ ወቀሱት። ጳውሎስ ከቤተ ክርስቲያን ምንም ድጋፍ አላገኘም ነበር፤ ይልቁንም፥ ለቤተ ክርስቲያን በመሥዋዕትነት ሰጥቷል። ይሁን እንጂ እነርሱ ደግሞ ከሌሎች ጋር በመካፈል አመስጋኝነታቸውን ለማሳየት ፈቃደኞች አልነበሩም። ጳውሎስ ይበልጥ ሲወዳቸው፥ እነርሱ ደግሞ ባነሰ ሁኔታ የሚወዱት ይመስል ነበር። ለምን? ምክንያቱም ለክርስቶስ እውነተኛ ፍቅር አልነበራቸውምና ነው (ቁ. 13)። ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያንን ለመርዳት ያለውን ነገር ለማካፈል ይፈልግ ነበር።  የአይሁድ ሃይማኖት አስፋፊዎች ቤተ ክርስቲያንን ለመበዝበዝ የማታለያ ዘዴዎችን ይጠቀሙ ነበር (4፡2 ተመልከት)፤ ዳሩ ግን ጳውሎስ ግልጽና ከአታላይነት የራቀ ነበር። ጳውሎስ የፈጸመው ብቸኛው «በደል» ከእነርሱ የገንዘብ ድጋፍ አለመቀበሉ ነበር። በዚህ ትጥቃቸውን ስላስፈታቸው፥ ገንዘብ ብቻ እንደሚፈልግ አድርገው ለሚያቀርቡት ክስ ምንም ምላሽ ሊሰጡ አይችሉም ነበር። ከእርሱ ጋር አብረው ከሚያገለግሉት ጳውሎስ የላካቸው ሰዎችም ቢሆኑ፥ አንዳቸውም በምንም መንገድ አልበዘበዙዋቸውም ወይም መጠቀሚያ አላደረጉዋቸውም ነበር።  ልጆች ወላጆቻቸው ለሚያደርጉላቸው በጎ ነገር ሳያመሰግኑ ሲቀሩ እጅጉን ያሳዝናል። እንዲሁም ደግሞ የእግዚአብሔር ልጆች «መንፈሳዊ ወላጆቻቸው» ለሚያደርጉላቸው ነገሮች ባለውለታነታቸውን ሲዘነጉ አሳዛኝ ይሆናል። ለዚህ ለምስጋና እጦት መነሻው ምንድነው? ጳውሎስ በቀጣዩ አንቀጽ ውስጥ ገልጾታል – የቅድስና መታጣት (ቁ. 19-21)። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የከፉ ኃጢአቶች ነበሩና ጳውሎስ ለጉብኝት ከመምጣቱ በፊት ፍርድ ተሰጥቶባቸው እንዲወገዱ ይፈልጋል። ይህ ካልሆነ ግን የአሁኑም ጉብኝቱ በሌላ አሳዛኝ ልምምድ ይቋጫል።  ምናልባትም አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባላት፥ «ጳውሎስ ዳግም ሊጎበኘን ከመጣ፥ ተጨማሪ ችግሮችን ይፈጥርብናል» ብለው እየተናገሩ ይሆናል። ጳውሎስ መሻቱ ችግሮችን መቅረፍና አብያተ ክርስቲያናትን ማጠናከር እንደ ሆነ በግልጽ ይናገራል። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙትን ኃጢአቶች ለማስወገድ በታማኝነት መጋፈጥንና ድፍረትን ይሻሉ። «አለባብሶ ማረሱ» ግን፥ የበለጠ ለክፋት ይዳርጋል። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኝ ኃጢአት በሰው ሰውነት ውስጥ እንዳለ ካንሰር ነው .ተቆርጦ መውጣት አለበት።  እስኪ ቤተ ክርስቲያኒቱ የወደቀችባቸውን ኃጢአቶች እናስብ – በመናዘዝና ንስሐ በመግባት ሊወገዱ የሚገባቸው ኃጢአቶች። እርስ በርሳቸው ስለሚመቀኛኙ ይጣሉ (ይከራከሩ) ነበር። ገንፍሎ የሚወጣ ቁጣም ነበረባቸው። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሥጋዊ ሤራዎችን፥ አድመኛነትንና ሐሜትን ያስፋፉ ነበር። ይህም ሁሉ ከትዕቢትና የራስን አስፈላጊነት ከፍ አድርጎ ከመመልከት የመነጨ ሲሆን፥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁከትን አስከትሏል (2ኛ ቆሮ. 12፡20)። ይህንን የኃጢአቶች ዝርዝር ከ1ኛ ቆሮንቶስ 13 ጋር ብናወዳድር፥ በማኅበረ-ምዕመናኑ መካከል የፍቅር መተሳሰብ እንዳልነበረ እንመለከታለን።  ከእነዚህ «የመንፈስ ኃጢአቶች» ጎን (7፡1)፥ ታላላቅ የሥጋ ኃጢአቶችም ነበሩ- ዝሙትና ፍትወት። ጳውሎስ ስለ እነዚህ ኃጢአቶች በ1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 5-6 ውስጥ ገልጾአል፤ ዳሩ ግን አንዳንድ ጥፋተኞች ባለመታዘዛቸው ጸንተው ነበር። ለአዲሱ ሕይወት ራሳቸውን ከመስጠት ይልቅ፥ አሮጌው ሕይወታቸው ዳግመኛ በላያቸው ላይ ግዛቱን እንዲያስፋፋ ይፈቅዱለት ነበር(1ኛ ቆሮ. 6፡9-10።  ጳውሎስ ለዚህ ለሦስተኛው ጉብኝት ብዙም አልጓጓም ነበር። ቤተ ክርስቲያን እንደሚፈልጋት ሳትሆን ቀርታ ላለማየት ከመሥጋቱም፥ እርሱም እንደሚፈልጉት ሆኖ ሳይገኝ እንዳይቀር ፈርቶ ነበር። ይሁን እንጂ፥ ምንም እንኳ በሁኔታው ማፈሩና ማዘኑ ባይቀርም (የቃሉ ትርጉም «ለሞተ ሰው ዘን»ን ያመለክታል)፥ ዳሩ ግን ነገሮችን የተቃና ለፃድረግ አሁንም በሥልጣኑ እንደሚጠቀም ቃል ይገባላቸዋል። ለእነርሱ የነበረው ፍቅር እጅግ ታላቅ በመሆኑ፥ እነዚህን ችግሮች ችላ በማለት ቤተ ክርስቲያኒቱን ማዳከማቸውን እንዲቀጥሉ ሊፈቅድላቸው አይሻም ነበር።  የቆሮንቶስ ሰዎች ማፈር ሲገባቸው ሳለ፥ እነርሱ ግን አላፈሩም ነበር። ጳውሎስ መልእክቱን በትክክል ማስተላለፉን ለማረጋገጥ ሲል፥ ቀጥሎ በምንመለከተው ሁለተኛው የአቀራረብ ዘዴ ይጠቀማል።  አስጠነቀቃቸው (2ኛ ቆሮ. 13፡1-8)  በዚህ ስፍራ ሁለት ማስጠንቀቂያዎች ቀርበዋል።  «ራሳችሁን አዘጋጁ» (2ኛ ቆሮ. 13፡1-4)። በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኃጢአትን ለማስወገድ በምንጣጣርበት ጊዜ፥ የምንመራው በሐሜቶች ሳይሆን በሐቆች መሆን አለበት። ጳውሎስ ዘዳግም 19፡15ን የጠቀሰ ሲሆን፥ ተመሳሳይ አሳብ ያላቸውን ምንባቦች ከዘኁልቁ 35፡30 እና ከማቴዎስ 18፡16፥ እንዲሁም ከ1ኛ ጢሞቴዎስ 5፡19 ላይ እናገኛለን። በተለይ የቤተ ክርስቲያን ምዕመናን እርስ በርሳችው በማይስማሙበት ጊዜ የምስክሮች መኖር የነገሩን እውነትነት ለማረጋገጥ ይረዳል።  የቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ኢየሱስ በማቴዎስ 18፡15-20 የሰጣቸውን ትዕዛዛት ቢከተሉ ኖሮ፥ ራሳቸው ብዙዎቹን ችግሮቻቸውን ለመፍታት ይችሉ ነበር። አማኞች የጌታችንን ትዕዛዛት ባለማክበራቸው ምክንያት ብቻ፥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አናሳ አለመግባባቶች ወደገዘፉና የተወሳሰቡ ችግሮች ሲሸጋገሩ ተመልክቻለሁ። ጉዳዩ የሚመለከታቸው ግለሰቦች በእውነተኛነት መፍትሔ እስካልፈለጉ ድረስ፥ መጋቢውና ማህበረ-ምዕመናኑ ጣልቃ መግባት የለባቸውም።  የአይሁድ መምሕራን ጳውሎስን ደካማ ነው በማለት ከሰውታል (2ኛ ቆሮ. 10፡7-11 ተመልከት)። የጳውሎስ አገልግሉት የውሃትና ገርነት የሚታይበት ሲሆን (1፡24 ተመልከት)፥ የእነርሱ ግን ጠንካራና አምባገነናዊ ነበር። አሁን ግን ጳውሎስ እንዴት ጠንካራ ሊሆን እንደሚችል እንደሚያሳያቸው ያረጋግጥላቸዋል – ችግሮቹን ለመቅረፍ የሚያስፈልገው ይኸው ከሆነ። ማስጠንቀቂያውም፥ «አልራራላችሁም!» የሚል ነበር። የተጠቀመውም «በጦርነት ውስጥ መራራት» ን የሚያመለክት ቃል ነው። ባጭሩ፥ ጳውሎስ የእግዚአብሔርን ቃል ሥልጣን በሚቃወም በማንኛውም ሰው ላይ ጦርነት እያወጀ ነበር።  ባላንጣዎቹ፥ «እስኪ ጳውሎስ እውነተኛ ሐዋርያ መሆኑን ያረጋግጥ» ብለው ነበር። የጳውሎስም ምላሽ፥ «የደከምሁ በምመስልበት ወቅት፥ እኔም እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ብርቱ ነኝ» የሚል ነበር። በመስቀል ላይ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ደካማነትን አሳይቷል፤ ይሁንና መስቀሉ አሁንም «የእግዚአብሔር ኃይል» ነው (1ኛ ቆሮ. 1፡18)። ጳውሎስ ቀደም ብሎ የመንፈሳዊ ውጊያውን ዘዴ የገለጸ ሲሆን (2ኛ ቆሮ. 10፡1-6)፥ አንባቢዎቹም ነገሮችን ላይ ላዩን በመመልከት ምትክ በጥልቀት እንዲያጤኑ አስጠንቅቋቸዋል።  በዓለም መመዘኛ መሠረት፥ ጳውሎስና ኢየሱስ ሁለቱም ደካሞች ነበሩ፤ ዳሩ ግን በጌታ መመዘኛ መሠረት፥ ሁለቱም ብርቱዎች ነበሩ። ለምሳሌ በአንድ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሥነ-ሥርዓት ጉዳዮችን ፈር በሚያስይዝበት ጊዜ፥ መቼ «መድከም» እና መቼ «መበርታት»

አስጠነቀቃቸው (2ኛ ቆሮ. 13፡1-8) Read More »

ሰባኪው በገነት (2ኛ ቆሮንቶስ 12፡1-10)

ይህ ክፍል ጳውሎስ ስለ ሐዋርያነቱ ለመከላከልና ለቆሮንቶስ አማኞች የነበረውን ፍቅር ለማረጋገጥ የሚያቀርበውን አሳብ በከፍተኛ ደረጃ የሚገልጽበት ነው። ጳውሎስ ስለ እነዚህ የግል ልምምዶቹ ለመጻፍ ባይፈልግም፥ ዳሩ ግን ችግሩን ለመቅረፍ ሌላ መንገድ አልነበረውም። እንዲያውም ራሱን ከፍ ከፍ ላለማድረግ፥ ጳውሎስ ልምምዱን የገለጸው በአንደኛ መደብ ሳይሆን በሦስተኛ መደብ ነበር። ለአንባብያኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያገኛቸውን ሦስት ልምምዶች አካፍሏል።  ክብር – እግዚአብሔር አከበረው (2ኛ ቆሮ. 12፡ 1-6)  የአይሁድ ሃይማኖት አስፋፊዎች ክብር ለማግኘት ይጣደፉ ነበርና «በድጋፍ ደብዳቤያቸው» ይመኩ ነበር(3 ከቁጥር 1 ጀምሮ)። ጳውሎስ ግን ክብርን ከሰው አልፈለገም ነበር፤ እርባና ያለው ክብር ከእግዚአብሔር ብቻ በመሆኑ፥ እርሱም በዚህ መንገድ ብቻ ለመከበር ፈለገ፡፡  በመጀመሪያ፥ እግዚአብሔር ራእዮችንና መገለጦችን በመስጠት አከበረው። ጳውሎስ ደኅንነትን አግኝቶ በተለወጠበት ዕለት፥ የከበረውን ክርስቶስን ተመልክቷል (የሐዋ.9፡3፤ 22፡6)፤ ሐናንያ ሊያገለግለው ሲመጣም በራእይ አይቷል (9፡ 12)፤ እንደዚሁም ለአሕዛብ እንዲያገለግል በተጠራ ጊዜም ከእግዚአብሔር ዘንድ ራእይ አይቷል (22፡7)።  በአገልግሉቱ ጊዜ፥ ለምሪትና ለብርታት እንዲሆነው፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ራእዮችን ይቀበል ነበር። ወደ መቄዶንያ የተጠራው በራእይ ነበር (16፡9)። የቆሮንቶስ አገልግሎቱ እንደ አቀበት አስቸጋሪ በሆነበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር ጳውሎስን በራእይ አበረታታው (18፡9-10)። በኢየሩሳሌም ከታሰረ በኋላም፥ እግዚአብሔር ጳውሎስን በራእይ አጽናንቶታል (23፡1)። በማዕበሉ መሀል አንድ መልአክ ብቅ ብሉ እርሱና ሌሎችም መንገደኞች እንደሚድኑ አረጋገጠለት (27፡23)።  ከጥሪውና ከአገልግሉቱ ጋር ከተያያዙ ከእነዚህ ልዩ ራእዮች ጋር፥ መለኮታዊ እውነትን የሚገልጹ መንፈሳዊ መገለጦችም ተሰጥተውት ነበር (ኤፌ. 3፡1-6 ተመልከት)። እግዚአብሔር ለአሁኑ ዘመን ትውልድ ያለውን ዕቅድ የሚያስተውልበትን ጥልቅ መረዳት ሰጠው። በመሆኑም ጳውሎስ የእግዚአብሔርን ምሥጢራት ተረድቶ ነበር።  እንዲሁም እግዚአብሔር ጳውሎስን ወደ መንግሥተ ሰማይ በመውሰድና መልሶም ወደ ምድር በመላክ አከበረው። ይህም አስደናቂ ልምምድ የተፈጸመው የቆሮንቶስ ደብዳቤውን ከመጻፉ ከ14 ዓመታት በፊት ማለትም በ43 ዓ.ም. አካባቢ ነበር። ይህም ጳውሉስ ወደ ጠርሴስ በሄደበት (የሐዋ. 9፡30) እና በርናባስን ባገኘበት (11፡25-26) ጊዜ መካከል የተፈጸመ ይሆናል። ስለዚህ ክስተት የተሰጠ ዝርዝር ነገር የለም፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ጊዜን ሰውቶ መመራመሩም የሚፈይድ አይደለም።  የአይሁድ የሃይማኖት ምሁራን (ራቢዎች) ስለ ራሳቸው ሲናገሩ፥ በሦስተኛ መደብ የመናገር ልማድ ነበራቸውና ጳውሎስም በቆሮንቶስ ውስጥ ለሚገኙ ወዳጆቹ (እና ጠላቶቹ ስለ ራሱ ልምምድ ለመግለጽ ያንኑ ልማድ ይጠቀማል። ልምምዱ እጅግ አስደናቂ ስለ ነበር፥ እግዚአብሔር በአካላዊው ሁኔታው እንዳለ ወደ ሰማይ ይውሰደው ወይም መንፈሱ ከሥጋው ተለይቶ ይሂድ ጳውሎስ እርግጠኛ አልነበረም። (እስኪ በቅርጫት «በመውረድ» እና ወደ ሦስተኛው ዓለም «በመውሰድ» መካከል ያለውን ልዩነት ያነጻጽሩ።) እዚህ ላይ ጳውሎስ የመንግሥተ-ሰማይን ኅልውናና እግዚአብሔርም ሰዎችን ወደዚያ ለመውሰድ እንደሚችል አረጋግጧል። ሦስተኛው ሰማይ ከ«ገነት» ጋር አንድ ሲሆን፥ እግዚአብሔር በክብሩ የሚኖርበት ሰማየ-ሰማይ ነው። ለዘመናዊው ሳይንስ ምስጋና ይግባውና ዛሬ ሰዎች ደመናት የሚንሳፈፉበትን ሰማያቸውን ጎብኝተዋል (ከደመናት በላይ በአውሮፕላን እንበራለን)፤ ወደ ፕላኔቶች ሰማያትም ይሄዳሉ (ሰዎች በጨረቃ ላይ ለመንሸራሸር በቅተዋል)፤ ይሁንና ሰው ያለ እግዚአብሔር እርዳታ ወደ እግዚአብሔር ሰማይ ሊደርስ አይችልም።  የሚያስገርመው ነገር ጳውሎስ ለ14 ዓመታት ስለዚህ ልምምድ ትንፍሽም አለማለቱ ነው! በእነዚያ ዓመታት፥ ጳውሎስ «በሥጋው መውጊያ» ይሰቃይ ነበርና ሰዎች ለምን እንዲህ ያለ ሸክም እንደ ተጫነበት በማሰብ ሳይገረሙ ላይቀሩ ይችላሉ። ምናልባትም የአይሁድ ሃይማኖት አስፋፊዎች እንደ ኢዮብ አጽናኞች፥ «ይህ ሥቃይ የደረሰበት በእግዚአብሔር ቅጣት ምክንያት ነው! » ሳይሉ አይቀሩም ይሆናል። (በመሠረቱ መውጊያው ከእግዚአብሔር የተሰጠው ስጦታ ነበር።) ከጳውሎስ ደህና ወዳጆች አንዳንዶቹም፥ «አይዞህ፥ ጳውሎስ፥ አንድ ቀን በመንግሥተ ሰማይ ታርፋለህ» በማለት ሊያጽናኑት ሞክረው ይሆናል። ይህን ቢሉትም ደግሞ ጳውሎስ፥ «ይህ መውጊያ የተሰጠኝ ለዚሁ ነው – ወደ ሰማይ ሄጄ ነበር» ሲል ሊመልስላቸው በቻለ ነበር።  እግዚአብሔር ለጳውሎስ ራእዮችንና መገለጦችን በመስጠትና በተለይም ወደ ሰማይ በመውሰድ አከበረው፤ ዳሩ ግን በሰማይ ሳለ «የማይነገሩ ቃላት» በማሰማትም በተጨማሪ አክብሮታል። በሰማይ ብቻ የሚደመጡትን መለኮታዊ ምስጢራት ሰማ። እነዚህ ነገሮች በእግዚአብሔር እና በሰማይ በሚገኙ ፍጥረታት ብቻ እንጂ፥ በሰዎች አይነገሩም ነበር።  ለመሆኑ የአይሁድ ሃይማኖት አስፋፊዎችስ እንዲህ ስላለ አንድ ልምምድ እንኳን ሊናገሩ ይችሉ ይሆን? የእግዚአብሔር ወዳጅ የነበረው ሙሴ እንኳ፥ ከእግዚአብሔር ጋር የተገናኘው በተራራ ጫፍ ላይ ነበር፤ ይሁንና ጳውሎስ ጌታን በገነት ተገናኘው። ጳውሎስ ይህንን ልምምድ ለማንም ስላልተናገረ፥ በእነዚያ 14 ዓመታት ውስጥ ትልቅ መንፈሳዊ ራስን መግዛት ተለማምዷል። ይህም የእግዚአብሔርን ክብር የሚያመለክት ራእይ ጳውሎስን በሕይወቱና በአገልግሎት ዘመኑ ውስጥ በጽናት እንዲቆም ካስቻሉት ኃይሉች አንዱ እንደ ነበር የሚያጠራጥር አይደለም። የትም ስፍራ ሲኖር – በእስር ቤት፥ በባሕር ላይ፥ በአስቸጋሪ ጉዞዎች – እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንደ ነበረና በመልካም ሁኔታም ላይ እንዳለ ያውቅ ነበር።  እኔና አንተ ግን እስክንሞት ወይም ጌታችን እስኪመለስ ድረስ ወደ ሰማይ አንሄድም። ዳሩ ግን ዛሬውኑ ከክርስቶስ ጋር በሰማያዊ ስፍራዎች መቀመጣችንን ስናስበው በእጅጉ ያጽናናናል (ኤፌ. 2፡6)። «ከሁሉም በላይ» (ኤፌ. 2፡21-22) የከበረ የሥልጣንና የድል ሥፍራ አለን። እንደ ጳውሎስ የእግዚአብሔርን ክብር ባንመለከትም፥ አሁንም የእግዚአብሔር ክብር ተካፋዮች ነን (ዮሐ 17፡22)፤ አንድ ቀንም ወደ ሰማይ ደርሰን የክርስቶስን ክብር እናያለን (ቁ 24)።  እንዲህ ዓይነቱ ክብር ብዙዎችን ያኩራራል። ሌላ ሰው ቢሆን ኖሮ ለ14 ዓመታት ዝም ብሉ በመቆየት ፈንታ፥ ከመቅጽበት ለዓለም ባሳወቀም ነበር። ዳሩ ግን ጳውሎስ እንዲህ አላደረገም። ከቆይታ በኋላም እውነቱን ገለጸ እንጂ፥ ከንቱ ትምክህት አላሳየም – እውነቶች ለራሳቸው ይናገሩ። ጳውሎስን በጣም ያሳሰበውም ማንም ሰው የእግዚአብሔርን ክብር ቀምቶ ለእርሱ እንዳይሰጠው ነበር። ሌሉች ስለ ራሱና ስለ ሥራው ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ፈለገ (ሮሜ 12፡3 ተመልከት)።  ጳውሎስ እንደዚህ ትልቅ ልምምድ እያለው፥ እንዴት ትሁት ሊሆን ይችላል? ይህ የሆነው እግዚአብሔር በሕይወቱ ውስጥ ካስገኘለት ከሁለተኛው ልምምድ የተነሣ ነው።  በጎነት – እግዚአብሔር ትሁት አደረገው (2ኛ ቆሮ. 12፡7-8)  ጌታ ሕይወታችንን እንዴት ሚዛናዊ ማድረግ እንደሚቻል ያውቃል። በረከቶች ብቻ ቢትረፈረፉልን፥ ልንታበይ እንደምንችል ያውቃል፤ በመሆኑም፥ ሸክሞችም እንዲኖሩን ይፈቅዳል። ጳውሎስ በሰማይ የተመለከተው ልምምድ፥ በምድር ላይ የነበረውን አገልግሎት ሊያከስመው በቻለ ነበር፤ ዳሩ ግን፥ እግዚአብሔር በበጎነቱ ጳውሎስን ከመታበይ ለመታደግ፥ ሰይጣን መውጊያውን እንዲያሳርፍበት አደረገ።  በዚህ ምድር ላይ የሰብዓዊ ሰቆቃ ምሥጢር ሙሉ ለሙሉ እልባት ሊያገኝ አይችልም። አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በመሆናችን ብቻ እንሰቃያለን። በዕድሜ እየገፋን ስንሄድ፥ ሰውነታችን ለተለመዱ የሕይወት ችግሮች ይጋለጣል። ምቾቶችን ሊያመጣልን የሚችለው ይኸው አካል ሕመሞችንም ያመጣብናል። የሚያስደስቱን የቤተሰብ አባላትና ወዳጆቻችን መልሰው ልባችንን በኀዘን ሊሰብሩት ይችላሉ። ይህ «ከሰብዓዊ ተፈጥሮ አስቂኝ» ባሕርያት አንዱ ሲሆን፥ ማምለጫ መንገዱም ከሰብዓዊነት ዝቅ ማለት ነው። ይሁንና እንደዚህ ለማድረግ የሚፈልግ ሰው ደግሞ የለም።  አንዳንድ ጊዜ ሞኞችና ለጌታ የማንታዘዝ በመሆናችን እንሰቃያለን። አንድም የራሳችን ዓመፅ ይጎዳናል፤ አሊያም ጌታ በፍቅሩ ሊቀጣን ይችላል (ዕብ 12 ከቁ 3 ጀምሮ ተመልከት)። ንጉሥ ዳዊት በኃጢአቱ ምክንያት ብዙ ተሠቃይቷል፤ የኃጢአት ውጤቶች በሥቃይ የተሞሉ ሲሆኑ፥ የእግዚአብሔርም ቅጣት እንዲሁ ነበር [2 ሳሙ. 12፡1-22፤ መዝ (51) ተመልከት]። እግዚአብሔር በጸጋው፥ ከኃጢአታችን ይቅር ይለናል፤ ዳሩ ግን በአገዛዙ፥ የምንዘራውን እንድናጭድ ያደርጋል።  እንዲሁም መከራ እግዚአብሔር ፈሪሃ-እግዚአብሔር ያለበትን ባሕርይ የሚያንጽበት መሣሪያ ነው (ሮሜ 5፡1-5)። በመሠረቱ፥ ጳውሎስ በሕይወቱ ውስጥ በተፈጸሙ አሰቃቂ ልምምዶች፥ እግዚአብሔር እንዲቀርጸውና እንዲያንጸው ስለ ፈቀደ፥ የበለጸገ የክርስቲያን ባሕርይ ነበረው። በውቂያኖስ ዳርቻ አካባቢ ስትንሸራሸር፥ ጸጥታ ባለበት ቦታዎች የሰሉትን ድንጋዮች ትመለከታለህ፤ ነገር ግን እየተላጋ ማዕበል ያለ ማቋረጥ በሚለትማቸው አካባቢዎች ያሉት ድንጋዮች ውጫዊ ክፍላቸው ለስላሳ ሆኖ ይታያል። እግዚአብሔር እኛ የምንፈቅድለት ከሆነ፥ የሕይወትን «ማዕበሉችና» ነፍሳት በመጠቀም ሊሞርደን ይችላል።  ለጳውሎስ የሥጋ መውጊያ የተሰጠው እርሱን ከኃጢአት ለመጠበቅ ነበር። ወደ ሰማይ ደርሶ የመመለስ ዓይነት አስደናቂ መንፈሳዊ ልምምዶች፥ ሰብዓዊ ራስ-ወዳድነትን የማጎልበት ጠባይ አላቸው፤ ትዕቢት ኩራት ደግሞ ኃጢአትን ወደሚያለማምዱ በርካታ ፈተናዎች ይመራል። የጳውሎስ ልብ በትዕቢት ተሞልቶ ቢሆን ኖሮ፥ እነዚያ ቀጣይ 14 ዓመታት በስኬታማነት ፈንታ ሰውድቀት ይታጀቡ ነበር።  የጳውሎስ የሥጋ መውጊያ ምን እንደ ነበር አናውቅም። መውጊያ ተብሎ የተተረጎመው ቃል፥ «ሰውን ለማሰቃየት ወይም ለመውጋት የተበጀ

ሰባኪው በገነት (2ኛ ቆሮንቶስ 12፡1-10) Read More »

ለቤተ ክርስቲያን የነበረው ሥጋት (2ኛ ቆሮ. 11፡ 16-33)

የዚህ ረዥም ክፍል ቁልፍ አሳብ ቁጥር 28 ሲሆን፥ አሳቡን እንደሚከተለው ለመግለጽ ይቻላል፡- «አዎን፥ በብዙ መከራዎች ውስጥ አልፌአለሁ፤ ይሁንና ከሁሉም የሚበልጠው መከራ፥ ከሁሉም የሚከብደው ሸክም፥ ለአብያተ ክርስቲያናት ያለኝ አሳብ ነው!» አሳብ ተብሎ የተተረጎመው ቃል፡ «ውጥረት፥ ጭንቀት፥ ሥጋት» ማለት ነው። ሌሉች መከራዎች ውጫዊና ወቅታዊ ሲሆኑ፥ ዳሩ ግን የአብያተ ክርስቲያናት ሸክም ውስጣዊና ዘለቄታነት ያለው ነበር።  ሄንሪ ዎርድ ቢቸር፥ «ራሳችን ወላጆች እስክንሆን ድረስ የወላጆችን ፍቅር በፍጹም አንረዳም» ብለው ነበር፤ ትክክል ናቸው። ታላቁ ልጃችን ሕፃን በነበረ ጊዜ፥ አንድ አሻንጉሊት ከኤሌክትሪክ ሶኬት ውስጥ አስገባለሁ ሲል ኮረንቲ ይዞ እንዳስደነገጠው አስታውሳለሁ። እርሱም በተራው ልጅ ወለደና፥ ይህን ልጁን አንድ ቀን ከሶኬት ጋር ሲጫወት ያየዋል፥ እናም ገና ዓመት ባልሞላው በዚያ ሕፃን ላይ በመጮህ ያስደነግጠዋል። ወዲያውኑም ወደ እኔ ስልክ በመደወል፥ «ሕፃን ሳለሁ አንተና እማማ ስለ እኔ እንዴት ትጨነቁ እንደ ነበረ የተረዳሁት አሁን ነው» በማለት አጫወተኝ። «ወላጅ መሆን የራሱ የሆነ ደስታና ፍርሃት አለው አለ።»  ጳውሎስ ያለፈባቸውን የተለያዩ የመከራ ዓይነቶች ከመዘርዘሩ በፊት፥ በዚህ ዓይነት ለምን «እንደሚመካ» ለመግለጽ ጥንቃቄ አድርጓል። ጳውሎስ ስለ ክርስቶስ ለመመካትና ስለ መከራዎቹ ለመናገር ምንም ችግር አልነበረውም፤ ዳሩ ግን ሁልጊዜም የእግዚአብሔር ባሪያ እንደ መሆኑ ስለሚጋፈጣቸው ከባባድ መከራዎች ለመናገር ያመነታ ነበር። ጳውሎስና መጥምቁ ዮሐንስ፥ «እርሱ [ክርስቶስ] ሊልቅ፥ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል» በሚለው አሳብ ይስማማሉ (ዮሐ. 3፡30)። «የሚመካ ግን በጌታ ይመካ» (2ኛ ቆሮ. 10፡17)።  ጳውሎስ ስለ ራሱ እንዲጽፍ በእነዚህ ባለፈባቸው የመከራ ልምምዶች እንዲመካ (እንዲኮራ) ያስገደደ፥ ጥሬና መንፈሳዊነት የጎደለውና የቆሮንቶስ ሰዎች አመለካከት ነበር። በመሆኑም ይህንን ክፍል (11፡1) የጀመረው ስለ መመካቱ በቅድሚያ ይቅርታ በመጠየቅ ሆኖ በቁጥር 16 ላይም ይህንኑ ዓረፍተ-ነገር ይደግማል። በቁጥር 17 ላይ፥ ጳውሎስ የቃላቱን የመንፈስ ቅዱስ ምሪት አይክድም፤ ዳሩ ግን በመመካቱ፥ ከጌታ ባሕርይ ጋር የማይዛመድ ነገር ላለማድረጉ ይገልጻል (10፡1 ተመልከት)። ይሁንና ለቆሮንቶስ ሰዎች የነበረውን ፍቅር ለመግለጽና በዚህም ዓይነት ወደ ጥፋት ከሚመሩዋቸው ሐሰተኞች ለመጠበቅ ይህንኑ ተግባር መፈጸም ነበረበት።  ቀድሞ ነገር፥ የሐሰት አስተማሪዎቹ ለመመካት አላፈሩም ነበር፤ የቆሮንቶስ ሰዎችም መመካታቸውን ለመቀበል ፍርሃት አላደረባቸውም ነበር። ጳውሎስ፥ «በኅብረታችሁ ውስጥ ዋና ነገር መመካት ስለ ሆነ፥ እኔም እመካለሁ» የሚል ይመስላል። ጳውሎስ የምሳሌ 26:5ን መመሪያ በአእምሮው የያዘ ይመስላል፡- «ለራሱ ጠቢብ የሆነ እንዳይመስለው፥ ለሰነፍ እንደ ስንፍናው መልስለት።»  በተጨማሪም፥ ጳውሎስ የተመካው ቤተ ክርስቲያንን ለመርዳት ሲሆን፥ የሐሰት መምህራን ግን ከቤተ ክርስቲያን ሊያገኙ የሚችሉትን ጥቅም አስተማማኝ ለማድረግና «ራሳቸውን ለመርዳት» ይመኩ ነበር። የጳውሎስ ዓላማ ንጹሕ ሲሆን፥ የእነርሱ ግን በራስ-ወዳድነት የተበከለና የረከሰ ነበር። ቁጥር 20 የአይሁድ ሃይማኖት አስፋፊዎች ቤተ ክርስቲያንን የበዘበዙባቸውን የተለያዩ መንገዶች ይዘረዝራል።  ባሪያዎች አደረጉአቸው፡- ከጸጋው ወንጌል ጋር የሚቃረን የሕግ ትምህርት ያስተምሩ ነበር።  በሉአቸው፡- በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሊያገኙ የሚችሉትን ነገር ሁሉ «በማጋበስ በልተዋል»። መዋዕለ ንዋይ የማግኘት መብታቸውን በመጠቀም በዘበዙአቸው።  ቀሙአቸው፡- «ቀሙዋቸው፥ » አሞኙአቸው። ምስሉ የሚያመለክተው በወጥመድ የተያዘችውን ወፍ ወይም በማጥመጃ የተጠመደውን የዓሣ ሁኔታ ነው። «በወጥመዳቸው ላይ የሚጥም ነገር አኑረው አጠመዱአችሁ!»  ኮሩባቸው፡- ራሳቸውን እንጂ፥ ኢየሱስ ክርስቶስን ከፍ ከፍ አላደረጉም ነበር፤ ሰዎች እንዲያከብሯቸውና እንደ ታላላቅ መሪዎች እንዲቆጥሩአቸው ወደዱ።  መቱአቸው፡- ይህ ከሥጋዊ ጥቃት ይልቅ፥ የቃላት ተቃውሞን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም፤ የአይሁድ ሃይማኖት አስፋፊዎች የቆሮንቶስን ሰዎች «ፊት በጥፊ ለመምታት» እና በሕዝብ ፊት ለማሳፈር አልቦዘኑም ነበር።  ጳውሎስ እነዚህን መንፈሳዊነት የጎደላቸውን የአይሁድ ሃይማኖት አስፋፊዎች አመለካከቶችና ተግባራት ገለጻ የደመደመው፥ አንዳንድ «የመንፈስ ምሪት ያለባቸውን ቅኔዎች» በማከል ነበር። «ደካሞች መስለን እንደ ነበርን በውርደት እላለሁ» (ቁ 2)። የቆሮንቶስ ሰዎች የጳውሎስ የዋህነት ብርታት ሆኖ ሳለ፥ ድክመት ነው ብለው አሰቡ። የአይሁድ ሃይማኖት አስፋፊዎች ትዕቢት ደግሞ ኃይል መሰላቸው። ቅዱሳን አንዳንድ ጊዜ አላዋቂ ሆነው ሲገኙ የቱን ያህል ያስደንቅ!  የአይሁዳዊነት ዝርያን በተመለከተ፥ ሐሰተኛ አስተማሪዎቹ ከጳውሎስ ጋር እኩል ነበሩ፤ ዳሩ ግን የክርስቶስን አገልግሎት በተመለከተ፥ «ቁንጮው ወይም ምጡቁ-ሐዋርያ» ጳውሎስ እንጂ፥ የአይሁድ ሃይማኖት አስፋፊዎች አልነበሩም። እስቲ ጳውሎስ ለክርስቶስና ለአብያተ ክርስቲያናት ብሎ የታገሣቸውን መከራዎች እናስታውስ።  ለክርስቶስ የተቀበላቸው መከራዎች (2ኛ ቆሮ. 11፡23-25)። ጳውሎስ ሐዋርያ ባይሆን ኖሮ፥ እነዚህን መከራዎች ባልተቀበለ ነበር። ከአሕዛብም ሆነ ከአይሁድ «ከልክ ያለፈ ግርፋት» ተቀብሏል። አሕዛብ ሦስት ጊዜ በበትር መቱት፤ አይሁድ ሦስት ጊዜ 39 ጅራፍ ገረፉት። በሐዋርያት ሥራ ውስጥ የተጠቀሰው አንድ ጊዜ እንደ ደበደቡት (16፡22) እና አንድ ጊዜ በድንጋይ እንደ ወገሩት(14፡19) ብቻ ነው።  ጳውሎስ ገና ከአገልግሉቱ ጅማሬ ላይ ስለ ክርስቶስ መከራ እንደሚቀበል ያወቀው ከመሆኑም (የሐዋ. 9፡15-16)፡ አገልግሎቱን ቀጥሉ ሳለም እግዚአብሔር ይህንኑ በድጋሚ አረጋግጦለታል (የሐዋ. 20፡23)። ሌሉች ስለ እምነታቸው መከራ እንዲቀበሉ ምክንያት የሆነው ሰው፥ ራሱ ስለ እምነቱ መከራ መቀበል ነበረበት።  ተፈጥሮአዊ ችግሮች (ቁ 25-27)። በዚያን ጊዜ ማንኛውም ተጓዥ ለማለት ይቻላል፤ ከእነዚህ ችግሮች አንዳንዶቹ ሊያጋጥሙት ይችሉ ነበር፤ ጳውሎስ የተጋፈጣቸውን ዓይነት ችግሮች ግን የጌታን ሥራ ለማደናቀፍ ጠላት የተጠቀመባቸው ናቸው ከማለት በስተቀር ሌላ የምንሰጠው አጥጋቢ ምክንያት አናገኝም። የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 27 ከሦስት የመርከብ ስብራት አደጋዎች አንዱን ይዘግባል። ስለ ተቀሩት ሁለቱ ግን የምናውቀው ነገር የለም። ጳውሎስ በዚህ ጉዞ ምን ያህል የግል ንብረቶቹን እንዳጣ ማሰባችን የማይቀር ነው።  ጳውሎስ ባለማቋረጥ ይጓዝ ስለ ነበር፥ ለጉዞ አደጋዎች የተጋለጠ ሰው ነበር። የአይሁድ ሃይማኖት አስፋፊዎች ሰላም ወደሰፈረባቸው ስፍራዎች ይሄድ ነበር። ዳሩ ግን ጳውሎስ ተራ ተጓዥ ሳይሆን፥ ተለይቶ የታወቀ ሰው ነበር። ከአይሁድም ሆነ ከአሕዛብ ጠላቶች ነበሩት፤ አንዳንዶችም ሞቱን ይመኙ ነበር።  ሁለተኛ ቆሮንቶስ 11፡27 የዚህን አስቸጋሪ ጉዞ ውጤቶች ይገልጻል። እኔ እንኳን ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወርሁ በማከናውነው ውስን አገልግሎቴ፥ አመቺ በሆኑ መኪኖችና አውሮፓላኖች እጓዛለሁ፤ ይሁን እንጂ ከቦታ ቦታ መጓዝ ምን ያህል እንደሚያዝለኝና እንደሚያሰለቸኝ መናዘዝ ይኖርብኛል። ታዲያ ለጳውሎስ የቱን ያህል ከዚህ የበለጠ አሰልቺና አስቸጋሪ ሆኖበት ይሆን! በድካምና በሕመም የተጎሳቆለና የተሰቃየ መሆኑ የሚያስደንቅ አይሆንም። ብዙውን ጊዜ ምግብ፥ መጠጥና እንቅልፍ ያጣ ነበር፤ እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ለሰውነቱ በቂ ሙቀት የሚለግስ ልብስ እንኳ አያገኝም ነበር።  ምንም እንኳ እነዚህን የመሳሰሉ ችግሮች ማንኛውም ሌላ ተጓዥ ሊገጥሙት ቢችሉም፥ ጳውሎስ ግን ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ከነበረው ፍቅር የተነሣ ይህን ሁሉ ችግር ያለ አንዳች ማማረር በጽናት ተቋቋመ። ከሁሉም የሚልቀው ሸክሙ፥ በዙርያው ከሚመለከተው ነገር የተፈጠረ ሳይሆን፥ ከውስጡ የሚመነጨው ስሜት ነበር – የእነዚያ ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ደኅንነት ነበር ጭንቀቱ! ግን ለምን ይህን ያህል ተጨነቀ? ምክንያቱም ራሱን ከአማኞች ጋር በይፋ አንድ በማድረጉ ነው (ቁ 29)። በመንፈሳዊ «ልጆቹ» ላይ የሚደርሰው ነገር ሁሉ ልቡን ይነካው ስለ ነበር፥ ጥሎአቸው ሊሔድ አልቻለም ነበር።  ጳውሎስ ይህን በችግር የመፈተን ትረካውን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያደርሰው፥ እርሱን የመሰለ ታላቅ ሐዋርያ፥ በቅርጫት ውስጥ ተጨምሮ በቅጥር ላይ በማለፍ፥ ከደማስቆ ከተማ የወጣበትን የውርደት ልምምድበመግለጽነው(ቁ. 32-33)። ከአይሁድ ሃይማኖት አስፋፊዎች መካከል እንዲህ ዓይነቱን ታሪክ ለመናገር የሚደፍር ይኖር ይሆን? በፍጹም አይኖርም! ጳውሎስ ስለ መከራዎቹ በሚተርክበት ጊዜ እንኳ፥ ክብሩን የሚቀበለው ክርስቶስ እንጂ ራሱ እንዳይሆን ይጠነቀቅ ነበር።  እነዚህን ቁጥሮች በምናነብበት ጊዜ፥ የሐዋርያውን ብርታትና መሰጠት ሳናደንቅ አናልፍም። እያንዳንዱ መከራ በሕይወቱ ውስጥ ምልክት እየጣለ ቢያልፍም፥ እርሱ ግን ጌታን እያገለገለ ወደ ፊት ይራመድ ነበር። «ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ» (የሐዋ.20፡24)።  ጳውሎስ ለቤተ ክርስቲያን የነበረውን ፍቅር በርግጥ አረጋግጧል፤ አሁን ቤተ ክርስቲያን ለጳውሎስ የነበራትን ፍቅር ማረጋገጥ ነበረባት።  ዛሬ በወንጌሉ በረከቶች እንደሰት ዘንድ፥ ሌሎች አስቀድመው የካፈሉዋቸውን መሥዋዕቶች እንደ ዋዛ-ፈዛዛ እንዳንመለከት እግዚአብሔር ይርዳን።

ለቤተ ክርስቲያን የነበረው ሥጋት (2ኛ ቆሮ. 11፡ 16-33) Read More »

አባት ከሁሉም በላይ ያውቃል (2ኛ ቆሮንቶስ 11፡1-15)

ለምሳሌ አንተ ክርስቲያናዊ አገልጋይ ብትሆን፥ በቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ የሚገኙትን ምዕመናን በርግጥ የምትወዳቸው መሆኑን እንዴት አድርገህ ልታሳምናቸው ትችላለህ?  ጳውሎስ ይህንን ደብዳቤ በሚጽፍበት ጊዜ ያጋጠመው ከዚህ ተመሳሳይ የሆነ ችግር ነበር። በመካከላቸው የፈጸመውን ሥራ ቢያስታውሳቸው፥ «ጳውሎስ በትምክህት እየተናገረ ነው» የሚሉ ዓይነት ሰዎች ነበሩ። በቆሮንቶስ ስለ ነበረው አገልግሉት ምንም ባይናገር ደግሞ፥ የአይሁድ ሃይማኖት አስፋፊዎቹ፥ «ተመልከቱ፥ ጳውሎስ ምንም ነገር እንዳልሠራ ነግረናችሁ አልነበር?» ማለታቸው የማይቀር ነው።  ስለዚህ ጳውሎስ ምን አደረገ? በግሩም መግለጫ ማወዳደርያ እንዲጠቀም የእግዚአብሔር መንፈስ መራው፤ ይህም ወደ ቆሮንቶስ አማኞች ልብ ጠልቆ እንደሚገባ የማያጠራጥር ነበር። በዚህም መግለጫው ውስጥ ያደረገው ራሱን ለቤተሰቡ ከሚጠነቀቅ «መንፈሳዊ አባት» ጋር በማወዳደር ማቅረብ ነበር። ከዚህ በፊት፥ እንደ «አባት» በወንጌሉ አማካኝነት እንደ ወለዳቸውና አስፈላጊ መስሎ ከተሰማው ሊቀጣቸው እንደሚችል ለማስታወስ፥ ይህንኑ ምሳሌ ተጠቅሟል (1ኛ ቆሮ. 4፡14-2)። እነርሱ የተወደዱ መንፈሳዊ ልጆቹ ነበሩና የሚመኝላቸው ሁሉ ከሁሉም የተሻለውን ነገር እንዲያገኙ ነበር።  ጳውሎስ ለነርሱ ስለ ነበረው አባታዊ ፍቅር ሦስት መረጃዎችን ይሰጣል። በቤተ ክርስቲያን ላይ የነበረው ቅንዓት (2ኛ ቆሮ. 11፡1-6፥ 13-15) እውነተኛ ፍቅር ከቶውንም አይመቀኝም፤ ዳሩ ግን በሚወዳቸው ላይ የመቅናት መብት አለው። ባል በሚስቱ ይቀናል፤ እርስ በርስ የሚኖራቸውን ፍቅር ለማሻከር በሚፎክር በማንኛውም ተቀናቃኝ ላይ ደግሞ ጥላቻና ተቃውሞ የማቅረብ መብቱን ማንም የማይነፍገው ነው። አንድ እውነተኛ የአገር ፍቅር ያለው ዜጋ በነጻነቱ ላይ የመቅናትና ይህንኑም ለማስጠበቅ የመዋጋት ሙሉ መብት አለው። እንደዚሁም ማንኛውም አባት (ወይም እናት) በልጆቹ ላይ ስለሚቀና፥ ከሚጎዳቸው ከማንኛውም ነገር ሊጠብቃቸው ያላቋረጠ ክትትል ያደርጋል።  በዚህ ስፍራ የቀረበው መግለጫ፥ ለጋብቻ የታጨች ልጃገረድ ልጅ ያለችውን አፍቃሪ አባት የሚያመለክት ነው። እርስዋን በንጽሕና መጠበቅና ለባሏ በኃዘን ሳይሆን በደስታ ማስረከቡ፥ መብቱና ሃላፊነቱ እንደ ሆነ ይሰማዋል። ጳውሎስ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለማግባት እንደ ታጨች ሙሽራ አድርጎ ይመለከታል (ኤፌ. 5 ከቁጥር 22 ጀምሮ እና ሮሜ 7፡4 ተመልክት)። ኢየሱስ ክርስቶስ ለሙሽራዪቱ እስኪመጣ ድረስ ያ ጋብቻ አይፈጸምም (ራእይ 19፡1-9)። እስከዚያው ድረስ፥ ቤተ ክርስቲያን ( ማለትም ክርስቲያኖች) ወዳጄን ለመገናኘት ራስዋን አዘጋጅታ በንጽሕና መጠበቅ አለባት።  እንግዲህ ይህን በመሰለው ግንኙነት ላይ አደገኛ ሁኔታ የሚፈጠረው፥ ልጃገረዲቷ ለእጮኛዋ ሳትታመን ስትቀር ነው። የታጨች ሴት ፍቅሯንና ታማኝነቷን ሁሉ ለአንድ ሰው ብቻ ትሰጣለች . ለእጮኛዋ። ከሌላ ሰው ጋር ስትዳራ ብትገኝ፥ ታማኝነቷን ባለመጠበቋ በደለኛ ትሆናለች። በ2ኛ ቆሮንቶስ 11፡3 ላይ ቅንነት ተብሎ የተተረጎመው ቃል፥ «ታማኝነት፥ ለአንድ ወገን ራስን መስጠት» የሚል ትርጉም ይሰጣል። የተከፋፈለ ልብ ወደ ተበላሸ ሕይወትና ወደ ረከሰ ግንኙነት ያመራል።  የፍቅርና የጋብቻ መግለጫ፥ እንዲሁም የታማኝነት አስፈላጊነት፥ ብዙ ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሷል። ነቢዩ ኤርምያስ የእስራኤል ሕዝብ ለእግዚአብሔር የነበረውን ፍቅር እያጣ ሲሄድ ተመለከተና አስጠነቀቃቸው። «እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ የብላቴንነትሽን ምሕረት፥ የታጨሽበትንም ፍቅር፥ በምድረ በዳ ዘር ባልተዘራበት ምድር እንደ ተከተለኝ አስቤአለሁ» (ኤር. 2፡2)። የይሁዳ ሕዝብ «የጫጉላ ቤት ፍቅሩን» አጥተ ጣዖታትን በማምለክ በደል ውስጥ ወደቀ። ኢየሱስም በኤፌሶን የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን ሲያስጠነቅቅ፥ በተመሳሳይ መግለጫ ተጠቅሟል – «ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና» (ራእይ 2፡4)።  ጤናማውን ግንኙነት ከበስተጀርባ ሆኖ ያደፈረሰው ሳይጣን ሲሆን፥ በጥቅሱ ውስጥ በእባብ መልክ ተገልጾአል ። ይህም የሚያመለክተው ወደ ዘፍጥረት ምዕራፍ 3 ነው። ጳውሎስ ይህንን ደብዳቤ ለቆሮንቶስ ሰዎች በሚጽፍበት ጊዜ፥ ስለ ከሳሹ ዲያብሎስ ብዙ የሚለው ነገር እንደ ነበር መረዳቱ ጠቃሚ ነው። ሰይጣን አማኞችን ለማጥቃት በርካታ መሣሪያዎች እንደ ነበሩት በመግለጽ ያስጠነቅቃል። ኃጢአት የፈጸሙትን አማኞች ሕሊና ሊያከብድ (2ኛ ቆሮ. 2፡10-11)፥ የማያምኑትን አእምሮ ሊያሳውር (4፡4)፥ ወይም የአማኛችን አእምሮ ሊያሳስት (11፡3)፥ ብሉም የእግዚአብሔርን አገልጋዮች ሰውነት ሊጎስም (12፡7) ይችላል።  ሰይጣን ሐሰተኛ ስለ ሆነና ሐሰቶቹን እንድንሰማ፥ እንድናሰላስልና ከዚያም እንድናምንባቸው ስለሚፈልግ፥ ያለ የሌለው ትኩረቱ ሁሉ የአእምሯችንን አስተሳሰብ በመለወጥ ላይ ነው። ስለዚህም ነው በዚህ ክፍል ውስጥ በተለይ በአእምሯችን ላይ ለሚደርሰው ፈተና ልዩ ክብደት የተሰጠው ሰይጣንም በሔዋን ላይ የፈጸመው ይህንኑ ነበር። በመጀመሪያ፥ የእግዚአብሔርን ቃል እንድትጠራጠር አደረገ («እግዚአብሔር እንዲህ ብሎአልን .?)፤ ከዚያም የእግዚአብሔርን ቃል ካደ («መሞትን አትሞቱም! » )፤ ቀጥሎም የራሱን ውሸት ምትክ አድርጎ አቀረበ («እንደ እግዚአብሔር ትሆናላችሁ …») (ዘፍ. 3፡1፥ 4-5)።  በመሠረቱ ሰይጣን አታላይ ነው። አማኞች ውሸትን ወዲያው እንደማይቀበሉ ስለሚያውቅ፥ «ወጥመዱን በሚማርክ ነገር ማበጀትና» የሚሰጠንን ነገር እንድንቀበል ማድረግ መቻል አለበት። ከሰይጣን መሠረታዊ ባሕርያት አንዱ አስመሳይነት ነው – እግዚአብሔር የሚያደርገውን ነገር ይቀናና የእርሱ ስጦታ በማስመሰል ከእግዚአብሔር እንደሚበልጥ አድርጎ ሊያሳምነን ይጣጣራል። ይህንን የሚያደርገው እንዴት ነው? እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ መስለው ሰይጣንን በሚያገለግሉ አስመሳይ ሰዎች በመጠቀም ነው።  ሰይጣን፥ ሌላ አዳኝና ሌላ መንፈስ የሚገኝበት አስመሳይ ወንጌል አለው (ገላ 1፡6-12)። የሚያሳዝነው የቆሮንቶስ ሰዎች የጸጋና የሕግ ድብልቅ የሆነውንና ከቶውንም እውነትነት የሌለበትን ይህንኑ «አዲስ ወንጌል» «መቀበላቸው» ነው። አንድ ወንጌል ብቻ ስላለ፥ ሊኖር የሚችለው አንድ አዳኝ ብቻ ነው (1ኛ ቆሮ. 15 ከቁጥር 1 ጀምሮ)። ስለዚህ አንተም በአዳኙ በምታምንበት ጊዜ በልብህ ውስጥ የእግዚአብሔር መንፈስ ገብቶ ያድራል፤ ያለውም አንድ መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው።  የዚህ የሐሰተኛ ወንጌል ሰባኪዎች (ዛሬም በእኛ መካከል የሚገኙ)፣ በ2ኛ ቆሮንቶስ 11፡13-15 ውስጥ ተገልጸዋል። እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች መለኮታዊ ሥልጣን እንዳላቸው ይናገሩ ነበር፤ ይሁንና ሥልጣናቸው ውሸት ነበር። እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋዮችንም አስመሳዮች ናቸው ብለው በማሳጣት ወነጀሉ። ጳውሎስንም የከሰሱት በተመሳሳይ ሁኔታ ነበር። ራሳቸውንም ከጳውሎስ እጅግ ልቀው እንደሚገኙ «የመጠቁ-ሐዋርያት» አድርገው ያቀርቡ ነበር። በተራቀቀው የአነጋገር ችሉታቸው፥ አላዋቂ አማኞችን ሳቡዋቸው፤ ጳውሎስንም የመናገር ስጦታ የለውም በማለት ያሳጡት ጀመር (ቁ 6፤ 10፡10)። በመሆኑም በእምነታቸው ወላዋይ የሆኑት አማኞች በታማኝ ሰባኪዎችና አስተማሪዎች በተሰጧቸው የወንጌሉ መሠረታዊ እውነቶች ጸንቶ በመቆም ፈንታ፥ በሰይጣን አገልጋዮች «ማራኪ ንግግር» መደለላቸው ምን ያህል የሚያሳዝን ነገር ነበር!  ጳውሎስ፥ «እነርሱ ከቶውንም የመጠቁ-ሐዋርያት አይደሉም። በማለት ሕዝቡን ያስጠነቅቃል። «እነርሱ የውሸት ሐዋርያት ናቸው!» አነሳሽ ምክንያታቸውም እግዚአብሔርን ማስከበር ሳይሆን፥ ያመኑትን ሰዎች በማጥመድ የግል ጥቅም ማግኘት ነው። ዘዴዎቻቸው የማታለያ ብልሃቶች ናቸው (2፡17፤ 4፡2)። በዚህ ስፍራ ላይ የተመለከተው ዋንኛ አሳብ ዓሣን ለማጥመድ በወረንጦው ላይ የሚንጠለጠለው መታለያ ምግብ ነው። ለቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በአዲስ ኪዳን ውስጥ ከተገለጸው «የበለጠ ክርስቲያናዊ ሕይወት እንዳለ በማስመሰል ያቀርባሉ፤ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የሌለው የሕግና የጸጋ ድብልቅ ሕይወት ይሰብካሉ።  እነዚህ አገልጋዮች የሚሠሩት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሳይሆን በሰይጣን ኃይል ነው። ጳውሎስ ሥራቸውን በማስመልከት፥ ለሦስት ጊዜ ያህል መለወጥ በሚለው ቃል ተጠቅሟል (11፡ 13፥ 14፥ 15 ተመልከት)። የዚህ ቃል የግሪኩ ትርጉም «ማንነትን ላለማስነቃት በአልባሳት መጀቦን፥ ጭምብል ማጥለቅ» የሚል ነው። ከውጭ ለውጥ ይታያል፤ ዳሩ ግን ከውስጥ የተለወጠ ነገር የለም። እንደ ሰይጣን ሁሉ፥ የሰይጣን ሠራተኞችም እውነተኛ ባሕርያቸውን ይዘው አይቀርቡም፤ ሁልጊዜም እነርሱነታቸውን የሚሸሽግ አልባሳት ደርበውና በመጋረጃ ውስጥ ተጠልለው ይመጣሉ።  ይህን መጽሐፍ በምጽፍበት ወቅት፥ በርካታ «የሰይጣን አስመሳይ አገልጋዮች» ወደ ቤቴ መጥተው ነበር። ከነዚህ ሰዎች መካከል፥ አንዲት ውብ ወጣት ሴት፥ ለዓለም ሰላም እንደምትሠራ ልትነግረኝ ሞክራ ነበር። ጻሩ ግን ማንነቷን ስነግራት፥ የኑፋቄ ቡድን አባልነቷን አመነች። ሁለት አለባበሳቸውን ያሳመሩ ወጣት ወንዶች፥ «እኛ በዚህ ስፍራ የተገኘነው ኢየሱስ ክርስቶስን በመወከል ነው» በማለት ራሳቸውን አስተዋወቁኝ። እኔም የትኛውን ቡድን እንደሚወክሉ የማውቅ መሆኔን ወዲያውኑ ነገርኋቸውና በሩን ዘጋሁ። «ደህና ሁኑ» እንኳ አላልኋቸውም። ይህን በማድረጌ ትርነት የጎደለብኝ የሚመስላችሁ ከሆነ፥ 2ኛ ዮሐንስ 5-11ን አንብቡና እንደ ትእዛዙ ፈጽሙ።  ጳውሎስ ከሐሰተኛ አስተማሪዎች ጥቃት በመጠበቅ ለቤተ ክርስቲያን የነበረውን ፍቅር አረጋግጧል፤ ይሁንና የቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ለአይሁድ ሃይማኖት አስፋፊዎች ተታልለው በመቀበል ወደ ቤተ ክርስቲያናቸው እንዲገቡ በር ከፈቱላቸው። የቆሮንቶስ ሰዎች «የመጀመሪያ ፍቅራቸውን ስለ ተዉ»፥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ከሙሉ ልብ የመነጨ አምልኮ እያቀረቡ አልነበረም። ፊታቸውን የመለሱት ከጳውሎስ ብቻ ሳይሆን ከክርስቶስም ጭምር ነበር፤ ይህ ደግሞ እጅግ የከበደ ጥፋት

አባት ከሁሉም በላይ ያውቃል (2ኛ ቆሮንቶስ 11፡1-15) Read More »