የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ

በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተሰጡ ትምህርቶች አጠቃላይ መግለጫ (ሐዋ. 9-28)

ጥያቄ፡- የሐዋ 9፡5-22፤ 27-28፤ 31፤ 10፡1-48፤ 11፡2-18፣ 22-24፤ 13፡1-3፣ 6-12፣ 52፤ 15፡6-11፣ 27-29፤ 16፡6-10፤ 19፡1-7፤ 20፡22-24፣ 28፤ 21፡4፣ 11 አንብብ። በእነዚህ ጥቅሶች የሚገኙትን የተለያዩ የመንፈስ ቅዱስ እጎልሎች ዘርዝር።  ሀ. ጳውሎላ በዳነበት ወቅት የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት (የሐዋ. 9)። እግዚአብሔር ጳውሎስን በደማስቆ መንገድ እንዴት እንደተገናኘው የሚናገረውን ታሪክ ሁላችንም እናውቀዋለን። እግዚአብሔር ሐናንያ የተባለን ሰው ጳውሎስ በኢየሱስ ማመኑን እንዲያረጋግጥ ነገረው። ሐናንያ በጳውሎስ ላይ እጁን በመጣን ይህን አጸና። ሐናንያ በጳውሎስ ላይ እጁን በማነ ጊዜ ማየት መቻል ብቻ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስም ተሞላ። ይህ ሙላት በምን እንደተረጋገጠ አልተገለጠልንም። የምንመለከተው ነገር ወዲያውኑ ጳውሎስ መጀመሪያ በደማስቆ ቀጥሎም በኢየሩሳሌም ስለ ኢየሱስ በድፍረት የሚመሰክር ሰው ሆነ። ዛሬ ሰዎች ብዙ ጊዜ ከመንፈስ ቅዱስ ሙላት ጋር የሚያያይዟቸውን በልሳናት መናገርንና የተአምራትን ጉዳይ እዚህ ላይ አናይም።  ለ. ከታላቁ ልደት በኋላ አማኞችን ያጠነከራቸውና ያበረታታቸው መንፈስ ቅዱስ ነበር።  ሐ. መንፈስ ቅዱስ በእሕዛብ ላይ ወረደ (ይህንንም ክስተት ወደፊት በሌላ ትምህርት እንመለከታለን።)  መ. መንፈስ ቅዱስ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን ይመራቸው ነበር። ጴጥሮስን ወደ ቆሮነሌዎለ ቤት መርቶታል። ጳውሎስና በርናባስን ለወንጌል መልእክተኝነት ሥራ በመለየት ወደ መጀመሪያው የወንጌል መልእክት ጉዞአቸው የላካቸው መንፈስ ቅዱስ ነው። አሕዛብ ክመጻናቸው በፊት የብሉይ ኪዳንን ሕዓጋትን በመከተል ወደ አይሁድነት መግባት ይባቸው እንደሆነና እንዳልሆነ በሚወያዩበት ወቅት የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን የመራቸው እርሱ ነበር። ጳውሎስ በሁለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ወቅት መንፈስ ቅዱስ ወደ አንዳንድ ስፍራዎች እንዳይሄድ በመከላከል ወደ ሌሎች ስፍራዎች ቀን እንዲሄድ መርቶታል። በኢየሩሳሌም እስር እንደሚጠብቀው ቢያውቅም እንኳ እንዲሄድ ግድ ያለው መንፈስ ቅዱስ ነበር። ስለዚህ በመጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን ከመንፈስ ቅዱስ ዋነኛ አገልሎቶች አንዱ ለክርስቲያኖች በሥራቸው ምሪትን መስጠት ነበር።  ሠ. አንዳንድ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን እረኞችና መሪዎች እንዲሆኑ የሚሾም መንፈስ ቅዱስ ነበር። ጳውሎስ በኤፌሶን ለነበሩ ሽማግሌዎች የመጨረሻ የስንብት ንግግር በሚያደርግላቸው ወቅት እንደ መሪዎች የመረጣቸው መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ነግሮአቸው ነበር። ስለዚህ ለራሳቸው ሕይወትና በቤተ ክርስቲያን ላሉ ክርስቲያኖች ሕይወት መጠንቀቅ ነበረባቸው።  ረ. መንፈስ ቅዱስ አንዳንድ ሰዎች ስለ ወደፊት ጉዳይ ትንቢት እንዲናገሩ አስችሎአል። እነዚህ ሰዎች ጳውሎስ ወደ እስር ቤት እንደሚጣል አውቀው ነበር። ሆኖም ግን የሚናገሩት መልእክት ሁል ጊዜ ከመንፈስ ቅዱስ ለመሆኑ ግልጽ አልነበረም። ምከንያቱም ጳውሎስ መደ ኢየሩሳሌም እንዳይሄድ ግድ ብለውት ነበር። ይህም ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ መንፈስ ቅዱስ እንዳዘዘው ከተናገረ በኋላ በመሆኑ ጉዳዩን ስናጤነው መንፈስ ቅዱስ በሚፈልገውና ነቢያቱ በሚፈልጉት መካከል የኦሳብ ግጭት ነበር።  ጥያቄ፡- ሀ) ከእነዚህ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች መካከል ዛሬ በቤተ ክርስቲያንህ የሚያስፈልጉት የትኞቹ ናቸው? ለምን? ለ) የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እንደሚገልጸው መንፈስ ቅዱስ ለፈጸማቸው ነገሮች ሁሉ የዛሬውን ትምህርት በመከለስ ዝርዝር አዘጋጅ።  በዚህ ትምህርት የመንፈስ ቅዱስ ጥናታችንን በሐዋርያት ሥራ የተዘገበልንን በማየት ጀምረናል። በእያንዳንዱ ገጽ መንፈስ ቅዱስ ተጠቅሷል። በዓላምና በክርስቲያኖች የሚፈጸሙት ተግባራቱ ኢየሱስ ከጀመረው የአዲስ ኪዳን ዘመን ዋነኛ ምልክቶች አንዱ ነው። ክርስቲያኖች የአሳብ ልዩነት የሚያሳዩባቸውን ሰርካታ ክፍሎች በሌላ ትምህርት እናጠናለን። ነገር ግን የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን ስቃኘንበት ወቅት ከድነት (ደኅንነት) እስክ ክርስቲያናዊ እውነት ብሎም በቤተ ክርስቲያን እስከማገልገል ድረስ ያለው የማንኛውም ክርስቲያን ልምምድ የሚፈጸመው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መሆኑ ተመልክቷል። ስለ መንፈስ ቅዱስ አወዛጋቢ ጉዳዮች ስናጠና ከመንፈስ ቅዱስ አገልቀሎቶች አብዛኛዎቹ አማኞች ሁሉ የሚስማሙባቸው እንደሆኑ መዘንጋት የለብንም። የሚበጀን የምንለያይባቸውን ነጥቦች እየመዘዙ መጣላት ሳይሆን የምንስማማባቸው ሰፊ ክልሎች እንዳሉ መገንዘብ ነው። በተጨማሪ ልዩነት በምናሳይባቸው ትምህርቶችና ልምምዶች ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምር ለመረዳት በጥንቃቄ ላማጥናት ቆርጠን እንነሣ። ይህንን በሚቀጥሉት ትምህርቶች እንደግማለን። ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተሰጡ ትምህርቶች አጠቃላይ መግለጫ (ሐዋ. 9-28) Read More »

በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተሰጡ ትምህርቶች አጠቃላይ መግለጫ (ሐዋ. 3-8 )

ጥያቄ፡- የሐዋ. 4፡5-13፤ 28-31፤ 5፡1-12፤ 29-32፤ 6፡1-10፤ 7፡51፤ 8፡1፡1-25፤ 26-29፤ 39-40 አንብብ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስና ከእያንዳንዱ ክርስቲያን ጋር ስላለው ንኙነት የተጠቀሱትን የተላያዩ እውነቶች ዘርዝር።  ሀ. መንፈስ ቅዱስ በሌሎች ፊት በግልጽና በድፍረት ለመናገር የሚያስችል ኃይልና ችሎታን ሰጠ፡- በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ በተደጋጋሚ መንፈስ ቅዱስን ስለመሞላት የተጠቀሱ ክፍሎችን ስንመለከት ከተአምራት፥ በልሳናት ከመናገር ወይም ከመስበክ ጋር የተያያዙ አለመሆናቸውን ልብ ማለት መልካም ነው። ይልቁኑ በመንግሥታት መሪዎች ፊት ቆመው መልስ በሚሰጡበት ወቅት ኢየሱስ አስቀድሞ ስላ መንፈስ ቅዱስ እንደተናገረው ኃይል እንደሰጣቸው እንመለከታለን (በማቴ. 10፡17-20)። ደቀ መዛሙርት ተቃውሞን የሚቋቋሙበትንና ወንጌልን በግልጽነት የሚሰብኩበትን ድፍረት የሰጣቸው መንፈስ ቅዱስ ነው። ደቀ መዛሙርት በዚህ መልክ በሚገባ ወንጌልን ይናገሩ በነበሩበት ጊዜ የሕዝብ መሪዎች ከኢየሱስ ጋር የነበሩ መሆናቸውን እንዳወቁ እንመለከታለን የሐዋ. 4፡13)። ቆይተው ደቀ መዛሙርት የጸለዩት ተአምራትን እንዲያደርጉ ሳይሆን ወንጌልን በፍጹም ግልጽነት እንዲናገሩ ነበር። እግዚአብሔር የጸሎታቸውን መልስ ሰጠ። የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፥ «በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው።» የዚህ ሙላት ውጤት ምን ነበር? «የእግዚአብሔርን ቃል በግልጥነት መናገራቸው ነበር።» (የሐዋ. 4፡31)። እስጢፋኖስ በድንጋይ በተወገረ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በግልጥ እንዲናገር ከማስቻሉም ሌላ ወደ ሰማይ በማተኮር ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲመለከት አድርጎት ነበር።  ለ. መንፈስ ቅዱስ ደቀ መዛሙርት ታላላቅ ተአምራትን እንዲያደርጉ አስቻላቸው፡= በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ደቀ መዛሙርት ሰዎችን መፈወስን፥ አጋንንትን ማስወጣትን የመሳሰሉ ተአምራቶችን በተደጋጋሚ ማድረጋቸውን እንመለከታለን። እነዚህ ተአምራት ስደቀ መዛሙርት ሕይወት መንፈስ ቅዱስ የመኖሩ ቀጥተኛ ምልክት ሆነው የቀረቡበት ጊዜ ግን ፈጽሞ የለም። በመንፈስ ቅዱስ የመሞላት ውጤት ተደርገውም አልቀረቡም። ነገር ግን የመንፈስ ቅዱስ ህልውና አንዳንድ ክርስቲያኖችን ወንጌልን በልጽነት እንዲሰበኩ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የመልእክታቸውን እውነተኛነትና ሥልጣን ለማረጋገጥ ተአምራትን እንዲያደርጉ ችሎታን እንደሰጣቸው መገመት እንችላለን። ተአምራትን የማድረግና ወንጌልን የመስበክ ሥራ ብዙ ጊዜ ተቆራኝተው የሚቀርቡ መሆናቸው የሚያስገርም ነው። የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ትኩረት የወንጌል መስበክ ነው። ተአምራትን ማድረግ ተቀዳሚ የአገልግሎት ዓላማው ሆኖ የቀረበበት ስፍራ ፈጽሞ የለም። ደቀ መዛሙርት ያለ ወንጌል ስብከት ተአምራትን ላለማድረጋቸው የተጻፈ አንድም ስፍራ አናነብም። ተአምራትን ሳያደርጉ ወንጌል ስለመሰበካቸው ግን እናነባለን። ይህ የሚያመለክተን የደቀ መዛሙርት ተቀዳሚ ዓላማዎች የእግዚአብሔርን ቃል መስበክ እንጂ ተአምራትን ማድረግ እንዳልነበረ ነው። በተጨማሪ የ መዛሙርት ተአምራትን ያደረጉት በቅድሚያ ለክርስቲያኖች ጥቅም እንደነበረ አናነብም። ሐዋርያት ትኩረታቸው ፈውስ ላይ አልነበረም። ይልቁኑ ውላ ሆነ አጋንንትን የማውጣት ተግባር ያተኮረው በቅድሚያ ሰማያምኑ ሰዎች ላይ ነበር። «ሕዝቡም የፊልጶስን ቃል በሰሙ ጊዜ ያደርጋት የነበረውን ምልክት ባዩ ጊዜ፥ የተናገረውን በአንድ ልብ እደመጡ» ተብሎ ተጽፎአ ( የሐዋ. 8፡6)። በኋላም የሚቀጥለውን ቃል እናገኛለን። «ምልክትና ድንቅ በእጃቸው ይደረግ ዘንድ እየሰጠ ለጸጋው ቃል ስለ መሰከረው ለለ ጌታ ገልጠው እየተናገሩ ረጅም ወራት ተቀመጡ።» (የሐዋ. 14፡3)። ተአምራትን የማድረግ ሥራ እንደ ሐዋርያት ባሉ የተወሰኑ ክርስቲያኖችና እንል እስጢፋኖስ ባሉ ስጦታ በነበራቸው ሌሎች ጥቂት የቤተ ክርስቲያን መሪ የተከናወነ ይመስላል። ለሁሉም ክርስቲያኖች የሚሰጥ ስጦታ አልነበረም፡፡  ሐ. መንፈስ ቅዱስ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን በትክክል እንሩ አስችሎአቸዋል (የሐዋ. 1፡6)። የክርስቲያኖች ቁጥር ሐዋርያት በረ ሊመሯቸው ወደማይችሉበት ደረጃ ሲደርስ ለሚነሡት አንዳንድ ችግሮች መፍትሔ መስጠት እንዲቻል ሌሎች መሪዎች ተመረጡ። መመረጥ የነበረባቸው እንዴት ነበር? ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስና ጥበብ የሞላባቸውን ሰዎች እንዲመርጡ ለደቀ መዛሙርት ነገሩአቸው። የተመረጡት ሰባት መሪዎች ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዳላቸው በሕይወታቸው ያረጋገጡ ነበሩ። ይህ በሕይወታቸው የተረጋገጠው እንዴት እንደነበር አልተጻፈም። ነገር ግን ሕዝቡ ልዩነቱን ስለሚያውቁ ለመመስከር ችለው ነበር። መንፈስ ቅዱስ ከሰባቱ ጋር እንደነበር እና የእዚአብሐርን ሕዝብ ለመምራት ጥበብ እንደነበራቸው ያውቁ ነበር።  መ. ሰዎች መንፈስ ቅዱስን ሊዋሹት፥ ሊፈታተኑትና ሊቃወሙት ይችላሉ ( የሐዋ. 5፡1-11)። ይህ መንፈስ ቅዱስ ዝም ብሎ ኃይል ብቻ እንዳይደለ ነገር የን እካላዊ ህልውና ያላውና ከሰዎች ጋር ሕያው የሆነ ቀንኙነት የሚያደርግ መሆኑን ያመለክታል። መንፈስ ቅዱስ፥ ለፊልጶስ ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ እንዲያነጋግር ግልጽ የሆነ ትእዛዝ ሰጥቶታል (የሐዋ. 8፡29)።  ሠ. መንፈስ ቅዱስ ለሰማርያ አማኞች በሐዋርያት እጅ መጣን ተሰጠ። (ወደፊት በምናጠናው ትምህርት ስለዚህ ጉዳይ በጥልቀት እንመለከታለን። የሐዋ. 8፡14-17)  ጥያቄ፡- ሀ) ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ከእነዚህ አንዳንዶቹ ወይም ሁሉም የመንፈስ ቅዱስ እገልግሎቶች አስፈላጊ የሆኑት በምን መንገድ ነው? ለ) መንፈስ ቅዱስ በቤተ ክርስቲያንህ ተመሳሳይ ነገሮች ያደረበትን ጊዜ ግለጽ። ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተሰጡ ትምህርቶች አጠቃላይ መግለጫ (ሐዋ. 3-8 ) Read More »

በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተሰጡ ትምህርቶች አጠቃላይ መግለጫ (ሐዋ. 1-2 )

ኢየሱስ ወደ ሰማይ ካረገበት ቀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ እሰከወረደበት ቀን ድረስ የነበሩት አምሳ ቀናት ለደቀ መዛሙርት እጅግ በጣም የተራዘሙባቸው ነበሩ። በመቶ ከሚቆጠሩ ዓመታት በፊት በኢዩኤልና በነቢያት የተነገረው፤ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርትን በምድር ትቶ ወደ ሰማይ ከማረጉ ከጥቂት ጊዜ በፊት ያረጋገጠው የተስፋ ቃል ሊፈጸም ተቃርቦ ነበር። ሰማይና ምድር (አዲስ ዘመን) የሚጀመርበትን፥ መንፈስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ የሚሰጥበትን ቀን በናፍቆት ይጠባበቁ ነበር። በድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ድምፅና በደቀ መዛሙርት ራስ ላይ እንደተቀመጠ ታላቅ የእሳት ልሳን ሆኖ መንፈስ ቅዱስ በዚያ አነስተኛ የአማኞች ጉባኤ ላይ ወረደ። የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ተወለደች። ደቀ መዛሙርቱም ታሪክን መቀየር ጀመሩ።  የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የመጀመሪያቱን ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይዘግባል። የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የሚያሳየን መንፈስ ቅዱላ በደቀ መዛሙርት አገልግሎትና በቤተ ክርስቲያን እድገት ምን ያህል አስፈላጊ እንደነበረ ነው። አንዳንድ የሥነ መለኮት ሊቃውንት ይህን መጽሐፍ «የመንፈስ ቅዱስ ሥራ» ብለው የሚጠሩት ለዚህ ነው። የሚያሳዝነው ነገር ዛሬ በሥነ መለኮት «ካሪዝማቲክ» በሆኑ ቡድኖችና «ካሪዝማቲክ ባልሆኑት » መካከል ትልቅ ያለመግባባት እንዲፈጠር ያደረገው የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ መሆኑ ነው። ዛሬ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚያስተምረውን ነገር በአጭሩ እናያለን። ወደፊ ት በተከታታይ በምናያቸው ትምህርቶች ደግሞ ከፍተኛ ያለመግባባት ያለባቸውን ክፍሎች በጥልቀት እንመለከታለን።  ጥያቄ፡- ሀ) የሐዋ. 1፡4-8፤ 15-17 አንብብ። ከእነዚህ ጥቅሶች ስለ መንፈስ ቅዱስ ምን እንማራለን? ለ) የሐዋ. 2፡1-21፤ 32-33፤ 38-39 አንብብ። 1) መንፈስ ቅዱስ በደቀ መዛሙርት ላይ በወረደ ጊዜ ምን እንደተፈጸመ በራስህ ቋንቋ ግለጥ። 2) በእነዚህ ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ ስላ መንፈስ ቅዱስ የተነገሩ አንኳር እውነቶች ምንድን ናቸው?  1. መንፈስ ቅዱስ በሐዋ. 1-2 ውስጥ  ሀ. ስለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ የተሰጠው ተስፋ፡- የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የሚጀምረው ኢየሱስ፤ መንፈስ ቅዱስን ለደቀ መዛሙርት እንደሚል ክ በሰጠው የተስፋ ቃል ነው። መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር አብ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለደቀ መዛሙርት የተሰጠ «ስጦ ታ» ነው። በዚህ ክፍል ውስጥ በርካታ እውነቶችን ማየት ይቻላል።  1. መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስ የሚያጠምቀው በእሳትና በመንፈስ ቅዱስ እንደሆነ የተናገረ ሲሆን፥ ኢየሱስ ግን በመንፈስ ቅዱስ እንደሚያጠምቅ ብቻ ተናገረ። ይህ ምናልባት የእሳቱ ጥዏቀት ኢየሱስ በፍርድ ዳግም ላሚመጣበት ጊዜ የዘገየ በመሆኑ ይሆናል።  2. የመንፈስ ቅዱስ መምጣት የመንፈስ ቅዱስ «ጥምቀት» ተብሎ ይጠራል። በሐዋርያት ሥራ 2 ላይ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ እንጂ ተጠመቁ ያለማላቱን ልብ ማለት የሚያስገርም ጉዳይ ነው። ይህ የሚያመላክተው በሁለቱ ቃሎች መካከል ያለውን የቅርብ ግንኙነት ነው።  «ጥምቀት» የሚለውን ቃል በሁለት መንገዶች ልንጠቀምበት እንችላለን። በመጀመሪያ፥ አማኞች በኢየሱስ ሲያምኑ በውኃ መጠመቃቸውን በቀጥታ እንደሚያመላክት አድርገን ልንወስደው እንችላለን። መጥምቁ ዮሐንስ ያደረገው ይህን ነበር (ማር. 1፡4)፥ ኢየሱስ የተቀበለው ይህን ነበር (ማር. 1፡9-11)፥ ኢየሱስም ደቀ መዛሙርት ለአዲስ አማኞች እንዲያደርጉት የነገራቸውም ይህን ነበር (ማቴ. 28፡19)።  በሁለተኛ ደረጃ ፥ ቃሉ በምሳሌያዊ አቀራረብ አገልግሎት ላይ ውሎ ሊሆን ይችላል። ዮሐንስ ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን ስላመስጠቱ ለማመልከት ተጠቅሞበታል። አዲስ ኪዳን ጥምቀትን ኈሁለት ምክንያቶች በምሳሌያዊ አቀራረብ ሳይጠቀምበት አልቀረም። በመጀመሪያ፥ ከውኃ ጥምቀት ሥርዓት ጋር በቅርብ የተያያዘ ነበር። በአዲስ ኪዳን አንድ ሰው ኢየሱስን እንደ ግል እዛኙ በሚቀበልበት ጊዜና በውኃ በሚጠመቅበት ጊዜ መካከል ምንም መዘግየት አልነበረም። አንድ ሰው ኢየሱስን ሲያምን ወዲያውኑ ይጠመቅ ነበር። አንድ ሰው ኢየሱስን አምኖ ሊጠመቅ ለዚህ አዲስ ክርስቲያን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን በስጦታ መልክ ይሰጠው ነበር። ሰው ሰውኃ የሚጠመቀውና መንፈስ ቅዱስን በዚያው ጊዜ የሚቀበለው በአንድ ጊዜ ስለሆነ መንፈስ ቅዱስን መቀበል የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ተብሎ ተጠርቷል። ስሁለተኛ ደረጃ ፥ የውኃ ጥምቀት ሥርዓት ሰው ሙሉ በሙሉ እራሱን ከኢየሱስ ጋር አንድ የሚያደርግበት ምልክት ነበር። የውኃ ጥምቀት እማኙ ከክርስቶስ ሞት፥ መቀበር ና መነሣት ጋር እራሱን አንድ ማድረጉን በድርጊታዊ መግላጭ የሚያሳይበት ሥርዓት ነበር (ሮሜ. 6)። በተመሳሳይ መንገድ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት መንፈስ ቅዱስ ከአዲሱ ክርስቲያን ጋር እራሱን አንድ ለማድረግ መኖሪያውን በልቡ ሊያደርግ እና የክርስቶስ አካል ከሆነችው ከቤተ ክርስቲያን ጋር ሊያጣምረው እን ደመጣ የሚያሳይ ነበር (1ኛ ቆሮ. 12፡13)።  (ማስታወሻ፡- ወደፊት በምንመለከተው አንድ ትምህርት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን ከመንፈስ ቅዱስ ሙላት ጋር እናወዳድራለን።)  3. የመንፈስ ቅዱስ ከደቀ መዛሙርት ጋር የመሆን ጉዳይ ከኃይልና ከምስክርነት ጋር ተቆራኝቶ የቀረበ ነው። በዚህ ስፍራ የተጠቀሰው ኃይል ከተአምራትና ከፈውስ ጋር የተያያዘ ለመሆኑ የምናየው ነገር የለም። ይልቁኑ ትኩረቱ ያረፈው ለምስክርነት የሚሆን ኃይልን በማግኘት ላይ ነው (የሐዋ. 2፡19። በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ተቀዳሚ ትኩረት የተሰጠው የመንፈስ ቅዱስ ሚና ይህ ነበር። ኃይሉ በተአምራቶች ውስጥ የታየ ቢሆንም ወንጌልን ለመስበክ ከሚመጣው ኃይል ጋር ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣ ነው።  ለ.የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ሊጻፍ የመንፈስ ቅዱስ ሚና፡- ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስ በዳዊት አፍ (ወይም ቅዱሳት ጽሑፎችን በጻፈበት ብእርቹ)ተጠቅሞ የይሁዳን ጥፋት ስለግመልከቱ (የሐዋ. 1፡16) በተናገረው ንቀር በመንፈስ ቅዱስና በብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች መካከል የነበረውን የቅርብ ግንኙነት አሳይቷል።  ሐ. በበዓለ ኀምሳ ቀን የመንፈስ ቅዱስ በደቀ መዛሙርት ላይ መውረድ፡- (ወደፊት በምንደርስባቸው ትምህርቶች ይህን በጥልቀት እናጠናላን የሐዋ. 2፡1-4)።  ጥያቄ፡– እነዚህን ሦስት የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች መረዳት ዛሬ ለእኛ ምን ያህል አስፈላጊ ነው?  ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተሰጡ ትምህርቶች አጠቃላይ መግለጫ (ሐዋ. 1-2 ) Read More »

በመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችና በአምልኮ ልምምዶች ውስጥ ያሉ ልዩነቶችን እንዴት መያዝ አለብን?

በትምህርት አንድ ክርስቲያኖች እምነታቸውን እግዚአብሔር ቃል ላይ በተለያየ ጊዜ እንደማይመሠርቱ ተመልክተናል። ደስ የሚያሰኛቸውን ነገር (ማለትም ስሜታቸውን) ወይም የቤተ ክርስቲያን ልምዶችና ባሕሎችን የእውነት ምንጭ አድርገው ይጠቀሙባቸዋል። ሁለቱም አደገኞች ስለሆኑ በእነርሱ ላይ መደገፍ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስሕተትን ያስከትላል። መሠረታችንንና አመለካከታችንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስናደርግ እንኳ በተለያዩ ምክንያቶች የአመለካከት ልዩነቶች እንዳሉ ተመልክተናል። የሚያሳዝነው ነገር አንዳንድ ጊዜ ይህ በክርስቲያኖች መካከል ፀብና ያለመግባባትን ማምጣቱ ነው። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከሚከሰቱት አሳዛኝ ነገሮች አንዱ ለትክክለኛ ነገር ሳይሆን ለተሳሳቱ ነገሮች ለንጋጭ መገኘታችን ነው። ዛሬ የምንኖረው ብዙም በማያሳስቡ ነገሮች ምክንያት በቤተ ክርስቲያን የማያቋርጥ መከፋፈል እያደገ በመጣበት ዘመን ነው።  አንዳንድ ጊዜ እንደ ክርስቲያን ያለመግባባት ሁልጊዜ ስሕተት ነው ብለን እናስባለን። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ሁለት ዓይነት ያለመግባባቶች አሉ። በመጀመሪያ ትክክለኛ ያልሆኑ፥ ኃጢአት ያለባቸው ከትዕቢትና ከራስ ወዳድነት የሚመነጩ ያለመግባባቶች አሉ። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ነገሮች ትክክል በመሆናቸው የሚመጡ አለመግባባቶች አሉ። ለምሳሌ፡-  1. ክርስቲያኖች ስለሆንን ክርስቲያን ካልሆኑ ሰዎች ስደት ወይም አንዳንድ ያለመግባባት ሊያጋጥመን እንደሚችል የታወቀ ነው (ዮሐ 5፡18-21)።  2. ሌሎች ትክክለኛ ያልሆነ ነገር ለማድረግ ሲፈልጉ እኛ ግን ትክክለኛ ለሆነ ነገር ለመኖር በመወሰናችን ያለመግባባቶች ይፈጠራሉ። ይህ ክርስቲያን ካልሆኑ ስዎች ጋር ደግሞም ከዓለማዊ ክርስቲያኖች ጋር ሊፈጠር የሚችል ያለመግባባት ነው። ለምሳሌ በሥራ ገበታችን ላይ ጉቦ እንድንቀበል ብንጠየቅና ፈቃደኛ ሳንሆን ብንገኝ ሰሥራ ባልደረቦቻችን የተጠላን እንሆናለን።  3. ስሕተትን በአብያተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያስተምሩ ሐሰተኛ አስተማሪዎችን ስንቃወም ያለመግባባት ይኖራል። እግዚአብሔር ወይም የእግዚአብሔር ሕዝብ መሪዎች ለእውነት ሲሉ በግልጽ ስለመዋጋታቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ማስረጃ ዎች አሉ። የገላትያ መጽሐፍ በሙሉ ጳውሎስ እጅግ ጠቃሚ ለሆኑ እውነቶች ለመዋጋት ሲል የጻፈው ነው (ገላ. 1፡6-9 እንብብ)። የሚያሳዝነው ነገር ክርስቲያኖች ወንጌልን የሚያጣምሙ ሰዎችን የመቃወም ዝንባሌ ሳይኖረን ይልቁኑ ከእኛ እምነት ወይም ልምምድ ኢምንት ያህል የሚለዩትን ከመዋጋት አንመለስም። የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሊሠሯቸው ከሚችሉት ትላልቅ ስሕተቶች አንዱ ለእውነት ያለመታገልና ሐሰተኛ አስተማሪዎችን ያለመቋቋም ነው።  ችግሩ በአስፈላጊ ነገር ላይ መቼ መቃወም እንደሚገባንና ለአላስፈላጊ ነገር ደግሞ መቼ ዝም ማለት እንዳለብን ለይቶ ያለማወቅ ነው። እኛ ትክክል ነው ብለን ለምናስበው አመለካክት ሁሉ እንገደላለንን? ወይስ ከእነርሱ ጋር ያለመግባባትን ላለመፍጠር ላንል የፈለጉትን እንዲያደርጉና የፈለጉትን እንዲያምኑ እንተዋቸዋለን? እነዚህ ሁለቱም ዝንባሌዎች ትክክል አይደሉም። የሚያሳዝነው ግን ክርስቲያኖች ብዙ ጊዜ ከሁለት በአንዱ ውስጥ መውደቃችው ነው።  ዋና ዋና መሠረታዊ ትምህርቶችና ዋና ዋና ትእዛዛት የሚያመላክተው በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ስለሚገኙና ከምንም ዓይነት ለውጥ ልንጠብቃቸው ስለሚገቡ ትምህርቶች ነው። በዚህ ውስጥ ቀጥሉ የተመለከቱ እውነቶችን መዘርዘር እንችላለን። ሀ) የእግዚአብሔር ባሕርይ፣ ለ) ሥላሴና ሐ) የድነት (የደኅንነት) መንገድ። እነዚህ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ መሠረታዊ የእምነት ትምህርቶች ሊሆኑ ከእነዚህም እውነቶች በተቃራኒ የሚያስተምሩትን ጠንክረን ልንቋቋማቸው ይገባል። አንዳንድ ዋና የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ የእምነት ትምህርት አፍልሰው የሚያስተምሩትን እንደ ኢየሱስ ብቻ ኑፋቄ፥ እስልምና ወይም ባሃኡላህ እምነት ጋር የሚደረገው ትግል በዚህ ውስጥ ይካተታል። በሁሉም ዘመን የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ሊታዘዙአቸው የሚገቡ ግልጽ የሆኑ ትእዛዛትም በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ይካተታሉ። ለምሳሌ፡- ሀ) አታመንዝር፥ ለ) አትግደል፥ ወይም ሐ) አትዋሽ የሚሉ ይገኙበታል።  ጥያቄ፡- ሀ) በተለየ መንገድ ትምህርት ቢሰጥባቸው እጥብቀን ልንቃወማቸው የሚገቡ ሌሎች የመሠረተ እምነት ትምህርቶችን ዘርዝር። ለ) ክርስቲያኖች ሁሉ ሊታዘዙአቸው የሚገቡአቸው ባይታዘዙአቸው ቅጣት የሚያስከትሉ ሌሉች ትእዛዛትን ዘርዝር።  ሁለተኛው፣ ውጫዊ የሆኑ መሠረታዊ የእምነት አስተምህሮዎችና ትእዛዛት ናቸው። እነዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ እውነቶች ሲሆኑ የአቀራረባቸው ግልጽነት ግን መቶ በመቶ እርግጠኛ ልንሆንባቸው አንችልም። እነዚህን እውነቶች እንዴት እንደምንረዳቸውና ተግባራዊ እንደምናደርጋቸው የእግዚአብሔር ሰዎች በአሳብ ልንለያይ እንችላለን።  ጥያቄ፡– በዚህ ክልል ውስጥ ይፈረጃሉ ብለህ የምታስባቸው አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች የትኞቹ ናቸው?  ክርስቲያኖች አንድ አቋም ይይዙ ዘንድ ግልጽ ያልሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተሰጡ በርካታ ትምህርቶች አሉ። ለምሳሌ፡- ሀ) ስለመጨረሻው ዘመን ትንቢቶች ያለን አመለካከት ኢየሱስ መቼ እንደሚመጣና በምድር ላይ በሥጋ ይነግሥ እንደሆነና እንዳልሆነ ለ) በአምልኮ ውስጥ በልሳን መናገር፥ ፈውስና ትንቢት ያላቸው ስፍራ። የሚያሰክር መጠጥ አለመጠጣት ወይም ከአንድ በላይ ሚስት ያገቡ ሰዎችን ያለማጥመቅ የመሳሰሉ ትምህርቶች እዚህ ውስጥ ይካተታሉ። በዚህ የሥነ መለኮት ትምህርት መጽሐፍ ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ የምንማራቸው ትምህርቶች ሰዎች በአንድ አሳብ የማይስማሙባቸው ብዙዎቹ በዚህ ክፍል ይመደባሉ።  እነዚህ እምነቶች ክርስቲያን መሆን ወይም ያለመሆንን እውነት አይለውጡም። ክርስቲያኖች ክርስቲያንነታቸው ሳይነካ በእነዚህ እውነቶች ላይ ያላቸው መረዳት ሊለያይ ይችላል። ነገር ግን የምናምነውን ወይም በተግባር የምንለማመደውን ሌሎች ሰዎች እንዲወስኑልን መጠበቅ የለብንም። መጽሐፍ ቅዱስን በጥንቃቄ ማጥናትና መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምራቸውን ትምህርቶች ለመረዳት ተገቢውን ጥረት ማድረግ የእኛ ኃላፊነት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል ብለን ያመንበትን ነገር በተግባር የምንለውጠው ከዚህ በኋላ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ በሚመራው አእምሮአችን መገዛት አለብን። ይሁንና፥ ሌሎች ክርስቲያኖች ለእነዚህ እውነቶች የተለየ አተረጓጐም ቢሰጡም የመረዳታቸው መሠረት መጽሐፍ ቅዱስ እስከሆነና ተገቢ የአተረጓጐም መርሆዎችን እስከተከተሉ ድረስ ትርጓሜያቸውን በልበ ሰፊነት ልንቀበል ይገባል።  ሦስተኛው፣ የተለየ አምልኮ ወይም የአኗኗር ዘይቤዎች (ልምምዶች) በመባል ይታወቃል። እነዚህ ከባሕል፥ ባሕል ወይም ከሰው ሰው የሚታዩ ልዩነቶች ወይም ምርጫዎች ናቸው። ከእነዚህ ልምምዶች አንዳንዶቹ እግዚአብሔርን እንዴት እንደምናመልክ ተጽእኖ ያደርጋሉ። አንዳንድ · ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ፀጥታንና ሃይማኖታዊ እክብሮትን ይመርጣሉ። ሌሎች ደግሞ እምልኮአቸውን ለመፈጸም ማጨብጨብና በደስታ መጮህ ይቀናቸዋል። የተለየ ከመሆኑ በቀር አንዱ ከሌላው አይሻ ልም። ወይም አይብስም። ሁሉም በተለያዩ ጊዜያት ጠቃሚ ናቸው። ሌሎች ደግሞ የአኗኗር ዘይቤ ልዩነቶች ናቸው። ለምሳሌ፥ በአንዳንድ ምዕራባውያን አገሮች የአሳማ ሥጋ ይበላል። ይህ በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ባሕላዊ ተቀባይነት የለውም። አንዳንድ ክርስቲያኖች ፊልም ቤት ይገባሉ፥ ወይም እንዳንድ ክርስቲያን ልጃ ገረዶች ሱሪ ይለብሳሉ፥ ወዘተ…። በአንዳንዶች ዘንድ ይህ ተቀባይነት የለውም። እነዚህ የተለያዩ ልምምዶች የሰውን መንፈሳዊነት ከፍ ወይም ዝቅ አያደርጉም። በእርግጥ ፊልሞቹ ላመንፈሳዊ ሕይወት ጐጂ የሆኑ ወይም የሰውን ምስክርነት የሚያበላሹ ከሆነ ልንመለክታቸው አይገባም። በመንፈሳዊ ሕይወታችን ላይ ብዙ የሚጫኑት ነገር ከሌለ በእነዚህ ጉዳዮች ስንጋጭ እንዳንገኝ መጠንቀቅ እላብን። ሰይጣን በክርስቲያኖች መካከል ያለመግባባት መኖሩ ያላደስተዋል። ምክንያቱም ይህን ልዩነት ላክፍፍል ምክንያት ያደርገውና እድገት እን ዳይኖር ወንጌልም እንጃይስፋፋ ይጠቀምበታል።  ጥያቄ፡- በኢትዮጵያ የሚኖሩ ክርስቲያኖች እርስ የማይስማሙባቸው በዚህ ክፍል የሚመደቡ ምሳሌዎችን ዘርዝር።  ስለ መሠረታዊ የእምነት ትምህርት ወይም ልምምድ የልዩነት አሳቦች በሚኖሩበት ጊዜ ማድረግ ያለብን ቀዳሚ ነገር ይህ ጉዳይ በየትኛው ክብ እንደሚመደብ መወሰን ነው። ከዚህ በኋላ፥ በተቃውሞአችን በርትተን ለመግፋት ወይም የተለየ አመለካከት (እምነት) ወይም የአምልኮ ሥርዓት ስለሆነ በልበ-ሰፊነት መቀበል እንድንችል ትምህርቱን እንዴት እንደምናስተናግድ እናውቃለን። የምንጋደለው ለመሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች መሆኑን አስታወሱ። በጣም አንገብጋቢ ባልሆኑ እውነቶችና ልምምዶች ላይ ክርስቲያኖች ሊለያዩ ነፃነት እንዳላቸው መገንዘብ ያስፈልጋል። ከመካከለኛው ክብ እየራቅን በሄድን ቁጥር ለመጋጨት ያላን ዝንባሌ መቀነስ አለበት። የሚያሳዝነው ነገር ብዙ ጊዜ የምናደርገው ተቃራኒውን መሆኑ ነው። ቀንደኛ የሆኑ የሐሰት ትምህርቶች ወደ ቤተ ክርስቲያናችን እንዲገቡ በመፍቀድ የእምነታችን ማዕከል እንዲናጋ እናደርጋለን። በአንጻሩ ከእኛ እምነት ጥቂት ለየት ያለ መሠረታዊ የእምነት ትምህርት ወይም ልምምድ ያላቸውን ለመዋጋት ፈጥነን እንነሣለን።  ሆኖም ግን አንድ የማስጠንቀቂያ ቃል አለ። አንዳንድ ነገሮች በውጭ ባሉት ሁለት ክቦች ውስጥ ያሉ የሚመስሉ ሥራቸው ግን በውስጠኛው ክብ የሆነ አሉ። ለምሳሌ፡- አንድ ቡድን በልሳን መናገር ለክርስቲያን መንፈሳዊነት ብቸኛው መንገድ ነው ወይም በልሳን ካልተናገረ ወይም ካልተጠመቀ አንድ ሰው ክርስቲያን ወይም ሙሉ ክርስቲያን አይደለም ብሎ ቢያስተምር፥ እንዲህ ዓይነት ትምህርት ሰው በእግዚአብሔር ተቀባይነት ስለሚያገኝበትና እውነተኛው መንፈሳዊነት ምን እንደሆነ የሚያስተምረውን ውስጠኛውን ክብ ይነካልያ ወይም እግዚአብሔርን ስእውነት የምናመልከው እጆቻችንን ወደ ላይ ስናነሣ ብቻ ነው ቢል ሁለቱም አመለካከቶች ሰው በእግዚአብሔር ፊት ትክክል ሆኖ ጽድቅን የሚያገኝበትን ዋነኛውን መሠረታዊ የእምነት አስተምህሮ ስለሚነኩ መስተካከል አለባቸው። ይህ ማለት በውስጠኛው ክብ ውስጥ የተገለጹ

በመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችና በአምልኮ ልምምዶች ውስጥ ያሉ ልዩነቶችን እንዴት መያዝ አለብን? Read More »

መንፈስ ቅዱስን በተመለከተ የተለያዩ መረዳቶች የሚታዩት ለምንድን ነው?

እግዚአብሔር ድንቅ አምላክ ነው። ነገሮችን ሁሉ ክፈቃዱ ዓላማ አኳያ የሚቆጣጠር ብርቱና ኃይለኛ አምላክ ነው። ነገር ግን አፍቃሪና ታጋሽ አምላክም ነው። ልንገምተው ከምንችለው በላይ በሆነ መንገድ ይጠነቀቅልናል። የእግዚአብሔርን ፍቅር የምናይበት አንዱ መንገድ እምነታችን ሙሉ በሙሉ ቃሉ እንደሚያስተምረው ትክክል ባልሆነበት ጊዜ እንኳ በትዕግሥት ከእኛ ጋር ለመሥራት በመፍቀዱ ነው። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከመሥራቱ በፊት እምነታችን ወይም የመሠረተ እምነት አስተምህሮአችን ሙሉ በሙሉ ትክክል እስኪሆን አይጠብቅም። ነገር ግን ባለንበት ሁኔታ ይገናኘንና እርሱን በመምሰል እንድናድግ ያግዘናል። እግዚአብሔር ያለማቋረጥ እንድንማር እርሱንና ቃሉን የበለጠ እያወቅን ለመሄድ ጥረታችንን እንድንቀጥል ይጠብቅብናል። በጊዜው ላስተማረን እውነት በመታዘዝ በትሕትና እስከኖርን ድረስ እኛን እንደ ልጆቹ ለመዛመድ ደስ ይለዋል።  ይህ እውነት በተለይ ስለ መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ መረዳት ላላቸው ክርስቲያኖችም ይሠራል። እግዚአብሔር ስለተሳሳተ እምነታቸው አያሳድጓቸውም። በትዕግሥት እያስተማራቸውም ሳለ እንኳ፥ መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ውስጥና በእነርሱ በኩል እንዲሠራ በማድረግ እርሱም አብሮአቸው ሲሠራ ደስተኛ ነው። ነገር ግን ይህንን አጋጣሚ የእግዚአብሔርን ቃል ለማጥናት ወይም እምነታችንን የበለጠ ከተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል ጋር እንዲጣጣም ጥረት ላለማድረግ እንደ ምክንያት ልንጠቀም አይገባም። እግዚአብሔር እውነት ነው ብሎ ካስቀመጠው ቃሉ ጋር መስማማታቸውን ለማረጋገጥ እያንላንዱ ክርስቲያን እምነተቹና ተግባሮቹ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ስላላቸው ዝምድና ልምምዱን የመመርመር ኃላፊነት አለበት (2ኛ ጢሞ. 2፡15 አንብብ)። ስለ መንፈስ ቅዱስ የሥነ መለኮት ትምህርት ይህን መጽሐፍ የምናጠናው ለዚህ ነው።  ጥያቄ፡- እግዚአብሔር ታጋሽ መሆኑና ከእኛ ጋር መሥራት ከመጀመሩ አስቀድሞ በሁሉም ነገር ፍጹም ሆነን መገኘትን የማይጠብቅብን መሆኑ የሚያበረታታን እንዴት ነው?  ጥያቄ፡- በኢትዮጵያ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ላላ መንፈስ ቅዱስ ና ስለ እገልግሎቱ ከሚታወቁት የተለያዩ አመለካከቶች እንዳንዶቹን ዘርዝር። የተለያዩ አመለካከቶች የሚታዩበት ምክንያት ለምን ይመስልሃል?  ስለ መንፈስና ህልውናው ስለሚረጋገጥበት ሁኔታ ክርስቲያኖች ባሉአቸው አንዳንድ ግንዛቤዎች ላይ ይለያያሉ ብለናል። ልዩነት የሚያሳዩበት ምክንያት ምን እንደሆነ ከመመልከታችን በፊት ክርስቲያኖች ስለ መንፈስ ቅዱስ በሚሰጡ ትምህርቶች በአብዛኛዎቹ አሳቦች ላይ እንደሚስማሙ መጥቀስ አስፈላጊ ነው። የእሳብ ልዩነት በሚታይበት ወቅት የምንስማማባቸው እውነቶች ከማንስማማባቸው ሰብዙ እጅ የላቁ መሆናቸውን ለማጤን እንዘነጋለን። ምናልባት 80% ያህል መንፈስ ቅዱስን አስመልክቶ የተጻፉትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶች ሁሉም ክርስቲያኖች ያምናሉ። ልዩነት አሳይተው የሚከራከሩ 20% በሚያህሉት ሲሆን እነዚህ ልዩነቶች ሰው በእግዚአብሔር ፊት ያለውን የድነት (ደኅንነት) አቋም የሚያናጉ አይደሉም። ስለዚህ በልሳን ስለመናገር፥ ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት፥ ስለ ተአምራትና የመሳሰሉ ልዩነት ወደምናሳይባቸው አካባቢዎች በምንገባበት ወቅት፥ የሚያስማሙንን ጠቃሚ ነጥቦች በማስታወስ በትሕትናና እርስ በርስ በመቀባበል ልዩነቶቻችን ማስተናገድ ይገባናል።  በመንፈስ ቅዱስ ሚና ላይ ክርስቲያኖች ይህን ያህል ልዩነት የምናሳየው ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ነገር ግልጽ አይደለምን? እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ሰዎች እውነትን፥ በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጡ እውነቶችን እንኳ ሳይቀር የሚረዱት እንዴት እንደሆነ መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡ ዝሆን ምን እንደሚመስል ለመረዳት ስለ ሞከሩ አራት ዓይነ ስውራን የሚናገር አንድ ታሪክ አለ። ወደ ጫካ ገቡና ዝሆኑ ወዳለበት ደረሱ፤ አንደኛው ኩምቢውን ዳሰሰ፥ እንዱ እግሩን ዳሰሰ፥ ሌላኛው ጐኑን የመጨረሻው ደግሞ ጭራውን ዳሰሰ። ከዚያ በኋላ ዝሆን ምን እንደሚመስል እያንዳንዳቸው ለሌላ ሰው መግለጫ ለመስጠት ሞክሩ። ዝሆን ምን እንደሚመስል ሲናገሩ የመጀመሪያው ዝሆን እንደ ትልቅ የውኃ ማስተላለፊያ ቧንቧ ነው አለ። ሁለተኛው ዝሆን እንደ ትልቅ ግንድ ነው እለ። ሦስተኛው ደግሞ የቤት ግድግዳ ነው የሚመስለው ሲል፥ የመጨረሻው አለንጋን ይመስላል አለ። አራቱም ዓይነ ስውራን የተናገሩት በእነርሱ እምነት ያቀረቡት እውነታኛና ትክክለኛ መግለጫ ነው ብለው ያመኑበትን ነገር ነው። ሆኖም ግን እያንዳንዳቸው የተረዱት ከፊል እውነት ስለነበር ለሌሎች ያቀረቡት ሙሉ እውነት ያልያዘና ሰዎችን ወደተሳሳተ አመለካከት የሚመራ ነበር።  ማናችንም ብንሆን ስለ እውነት ፍጹም የሆነ መረዳት እንደሌለን መገንዘብ ይገባናል። የእግዚአብሔር ዘላለማዊ እውነት የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ፊት ለፊታችን ቢኖረንም እንኳ እንደ እራቱ ዓይነ ስውራን ከፊል እውነትን ብቻ እናያለን። በዓለም ላይ የሚገኙ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ክርስቲያኖች ሁሉ የሚያጠኑት አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ቢሆንም እንኳ እንዳንድ ክፍሎችን በተለያየ መንገድ የሚረዱት በዚህ ምክንያት ነው። የመጀመሪያው ምእተ ዓመት ታላቅ የሥነመለኮት አስተማሪ የነበረው ጳውሎስ እንኳ ይህን እውነት ተቀብሏል። «ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ» (1ኛ ቆሮ. 13፡12)።  መጽሐፍ ቅዱስን ከሌሎች ክርስቲያኖች በተለየ መንገድ እንድንረዳው የሚያደርጉን ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ሌሎች በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም እንኳ የእግዚአብሔርን ቃል ከሌሎች በተለየ መንገድ እንድንረዳ የሚያደርጉን ዐበይት ነጥቦች ቀጥለው ተዘርዝረዋል።  1. ያደግንበት ባሕል፡- እያንዳንዳችን ያደግነው ከወላጆቻችን በተቀበልነው ልዩ ባሕል ውስጥ ሲሆን እነርሱ ደግሞ ይህን ባሕል የተቀበሉት ከእነርሱ ቀደም ብለው ከነበሩት ወላጆቻቸው ነው። ለምሳሌ በሰሜን ኢትዮጵያ አማራ ወይም ትግሬ ሆነው ያደጉ ሰዎች እንደ ኦሮሞ ወይም ወላይታ ሆነው ካደጉ ወይም በደቡብ ኢትዮጵያ ካሉ ሌሎች ሰዎች ባሕላቸው ይለያል። ያደግንበት ባሕል አስተሳሰባችንን፥ ለለ አከባቢያችን ያላንን አመለካከትና እውነትን በምንረዳበት ሁኔታ ሁሉ ላይ ተጽእኖ ያሳድራል። ባሕላቸው ከእኛ በተለየ ሕዝቦች መካከል ስንኖር ወይም ከእነርሱ ጋር ስንሠራ ይህን እውነት ሁላችንም ተለማምደናል። በባሕላችን የሚፈቀድ አንድን ነገር መናገር ወይም ማድረግ በሌላው ባሕል የሚያስነቅፍ ሊሆን ይችላል። በዚህም ምክንያት ሌላው ሰው በተሳሳተ መንገድ ሊረዳና ምናልባትም ጸብ ሊፈጥር ይችላል። ሁላት ባሕሎች በጣም ተመሳሳይ ከሆኑ የባሕል ግጥታቸው ዝቅተኛ ይሆናል። በባሕሎች መካከል ያለው ልዩነት የሰፋ ከሆነ ያለመግባባቱም በዚያው መጠን የሰፋ ይሆናል። እንደ አሜሪካ ባሉ ምዕራባውያን አገሮች ያደጉ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል የሚረዱበት መንገድ በእስያና በአፍሪካ ካደጉ ሰዎች እጅግ የተለየ ነው። ባለን የተለያየ ባሕላዊ ልዩነት መሠረት መጽሐፍ ቅዱስን ስንመለከትና እውነቶችን ለመረዳት ስንጥር ብዙ ጊዜ እንደ እራቱ ዓይነ ስውራን ብዙ ጊዜ የምናየው የእውነትን የተለያዩ ገጽታዎች ነው።  2. ሃይማኖታዊ ልዩነት፡- ልጆች ሆነን የተማርነው የሃይማኖት ትምህርት እውነትን በምንረዳበት መንገድ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ያደርጋል። ለምሳሌ እንዱ ሙስሊም ሌላው ኦርቶዶክስ የሆኑ ሁለት ኦሮሞዎች ነገሮችን የሚረዱት ፍጹም በተለያየ መንገድ ነው። እንደዚሁም በመካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ወይም በቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ወይም በሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን ብናድግ ልዩነቶችን እናሳያለን። ልጆች ሆነን የተማርናቸው እውነቶች የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንደምንመለከትና እንዴት እንደምንረዳው ተጽእኖ ያሳድራሉ። እንደ ባሕል በአብያተ ክርስቲያናቱ መካከል ያለው ልዩነት ከፍተኛ በሆነ ቁጥር በክርስቲያኖች መካከል ያለው የአሳብ ያለመግባባት እየጨመረ ይመጣል። እንደ ሙሉ ወንጌል ባሉ ፔንትኮስታል አብያተ ክርስቲያናት ያደጉ ሰዎች እንደ መንፈስ ቅዱስ ባሉ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ያላቸው መረዳት ካሪዝማቲክ መሠረት በሌላቸው አብያተ ክርስቲያናት ካደጉቱ በጣም ይለያል። ታሪካዊ መነሻቸው ተመሳሳይ ስለሆነ የባፕቲስትና የቃለ ሕይወት አተረጓጐም በጣም ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል።   3. ዕድሜያችን፡– በሁሉም ዘመናት በወጣቶችና በእድሜ በገፉ ሰዎች መካከል ውጥረት ይታያል። ወጣቶች ከፍተኛ ምኞትና ኃይል ያላቸው፥ የሚመጣውን አደጋ ለመጋፈጥ የበለጠ ፈቃደኛ የሆኑ፥ ለለውጥ በጣም የተጋለጡና አዳዲስ ነገሮችን ለመሞከር በጣም ደፋሮች ናቸው። በዕድሜ ገፋ ያሉ ሰዎች ዝንባሌ ደግሞ ነገሮችን እንዳሉ በተረጋጋ ሁኔታ መቀጠላቸው ነው። ነገሮች እንዲለወጡና ስሜታቸው ራሳቸውን እንዲቆጣጠራቸው ብዙ የማይፈልጉ ናቸው። ስለዚህ ዕድሜ ስው እውነትን በሚረዳበትና ይህ እውነት በአምልኮውና በዕለታዊ ሕይወቱ በሚገለጽበት ሁኔታ ላይ ተጽእኖ ያደርጋል።  የቤተ ክርስቲያን ዕድሜም ልዩነት ያመጣል። ብዙ ጊዜ አዲስ አብያተ ክርስቲያናት በራእይና ለክርስቶስ ባላቸው የመጀመሪያ ፍቅር የተሞሉ ስለሆኑ ወደ ስሜተኛነት ያዘነብላሉ። አዳዲስ ትምህርቶችን ይወዳሉ። በልሳን መናገር፥ ተአምራትን ማድረግ ወይም ስሜታዊ የሆነ የአምልኮ ስብሰባን ያካሂዳሉ። በእግዚአብሔር ቃል ላይ ከማተኮር በአምልኮና በኅብረት ጉዳይ ላይ ያተኩራሉ። ነገር ግን እየበሰሉ በሄዱ ቁጥር ቤተ ክርስቲያን መቀየር ትጀምራለች። የአምልኮአቸው ጊዜ ብዙ ስስሜት ላይ ያልተመሠረተ ሆኖ በቃሉ ራሱን የገለጠውን እግዚአብሔርን ወደ መረዳት የሚያዘነብል ሲሆን፥ ሕዝቡም የእግዚአብሔርን ቃል ማጥናት ላይ ያተኩራል። በስሜታዊ አምልኮ ላይ የሚደረገው ትኩረት ይቀንስና ሚዛኑ እውነትን

መንፈስ ቅዱስን በተመለከተ የተለያዩ መረዳቶች የሚታዩት ለምንድን ነው? Read More »

ክርስቲያኖች እንደ መንፈስ ቅዱስ ባሉ መሠረታዊ የክርስትና አስተምህሮዎች ላይ ባላቸው አመለካከት ልዩነት የሚያሳዩት ለምንድን ነው?

መኮንን እና ተስፋዩ በአንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግሉ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ነበሩ። መኮንን የ55 ዓመት ሰው ሊሆን ለረጅም ዘመን ክርስቲያን ነበር። ወደ ክርስትና ከመምጣቱ በፊት መናፍስትን ያመልክ የነበረ ሲሆን ክርስቲያን ሊሆን ክቀድሞ አምልኮው ጋር የተያያዙ ነገሮችን በሙሉ እቆመ። ይኸውም በሚዘምርበትና ርኩሳን መናፍስትን በሚያመልክበት ወቅት ያደርግ የነበረውን ማጨብጨብና መወዛወዝ ማለት ነው። የአንድ ቤተ ክርስቲያን አባል ከመሆኑ ባሻገር ለዚያች ቤተ ክርስቲያን በሕይወት ዘመኑ በሙሉ ታማኝ ነበር። በዚያ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ያመልክ የነበረ ሲሆን የእነርሱን አባላት ወደ ራሳቸው ቤተ ክርስቲያን በሚወስዱ ሰዎች ላይ እጅግ ይቆጣ ነበር። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሰዎች አብዝተው እያጨበጨቡ ሊዘምሩ፥ ሲወዛወዙና በልሳናት ሲናገሩ ሲሰማ ድሮ ዲያብሎስን ያመልክ የነበረበትን ሁኔታ ስለሚያስታውሰው ደስ አይሰኝም። ከእነዚህ ልምምዶች እንዳንዶቹ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ሲገቡ፥ ትክክለኛነታቸውን ስለማያምን፥ በቤተ ክርስቲያኑ ያለውን የአምልኮ ሁኔታ በዚህ ለመለወጥ የሚጥሩትን ሁሉ ይቃወማቸዋል። መኮንን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከሁሉ የላቀው አስፈላጊ ነገር ስብከት እንደሆነ ያምናል። ምክንያቱም ለሕይወቱ ብርታት የሚሰጠው የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ስለሚያምን ነበር። በመኮንን እምነት አንድ ሰው መንፈሳዊነቱን የሚያጠነክረው ቃሉን በማጥናት የሚያሳየው ትጋት ደግሞ ቃሉን በመታዘዝ መደበኛ የሆኑትን የቤተክርስቲያን ልምምዶች በመሳተፍ (የሚያሰክር መጠጥ ባለመጣጣት፥ ፊልም ቤት ባለመሄድ፥ ወዘተ…) እንዲሁም በገላትያ 5፡22-23 የተዘረዘሩትን የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች በማሳየት ነው። ለረጅም ዘመን ክርስቲያን የነበሩ በተለይ በዕድሜ የገፉ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች መኮንን ለቀድሞው የእምነትና የአምልኮ ሥርዓት መጠበቅ በሚያደርገው ትግል አጋሮቹ ነበሩ።  ተስፋዩ የ30 ዓመት ሰው ሲሆን የክርስትና ዕድሜውም 5 ዓመት ብቻ ነበር። በጊታሮችና በጭብጨባ የሚታጀቡ ዘመናዊ ዜማዎችን ይወዳል። ወደ ተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት የሚሄድ ከመሆኑም ሌላ በተለይ ደግሞ በአምልኮ ጊዜ ልዩ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አዳዲስ የሙዚቃ ቡድኖችን በጣም ይከታተል ነበር። ተስፋዩ አንዳንድ ሰዎች በልሳን በመናገር መንፈሳዊ መስለው ሊቀርቡት በጣም ይነካ ነበር። እርሱም ይህን መንፈሳዊ ስጦታ በመሻት በልሳን መናገር ቻለ። ይህ እግዚአብሔርን በተሻለ ሁኔታ እንዲያመልክ እንደረዳውም አመነ። ስለዚህ በቤተ ክርስቲያኑ ያሉ ሰዎችን በእርግጥ መንፈሳዊ መሆን ከፈለጉ በልሳን መናገር እንዳለባቸውና በአምልኮ ጊዜም መንፈስ ቅዱስ የፈለገውን ያደርግ ዘንድ ነፃነት መስጠት እንደሚገባቸው ያስተምር ጀመር። እምልኮው እውነተኛ እንዲሆንና መንፈስ ቅዱስ በመካከላቸው መኖሩ እንዲታወቅ ማጨብጨብ፥ እልል ማለትና እጅን መዘርጋት ያስፈልጋል ብሎ ያስተምር ጀመር። በአምልኮ ጊዜ በሙሉ ስሜታቸው የማይሳተፉ ሰዎች መንፈሳዊ ያልሆኑ ነገር ግን በመንፈስ የሞቱ ናቸው ብሎ አሰበ። ለተስፋዩ በአምልኮ ጊዜ ከሁሉ የላቀው ነገር የስብከት ጊዜ ሳይሆን የመዝሙር ጊዜ ነው። ከአምልኮ ጊዜያችን ውስጥ በሙሉ ስሜታችን የምንሳተፈው እና ከልባችን ለእግዚእብሔር ክብር የምንሰጠው በዚህ ጊዜ ነው ብሎ ያምናል። ተስፋዬንና ትምህርቱን ብዙ ወጣቶች ተከተሉት።  ጥያቄ፡- ሀ) በአንተ ወይም በሌላ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ዓይነቱን መከፋፈል እንዴት ታዘብነው? ለ) የክፍፍሉ (ልዩነቱ) ሥረ መሠረት ምንድን ነበር? ሐ) በዚህ መከፋፈል የሚከሰተው ግጭት የመሠረተ እምነት ትምህርት አስተምህሮ ጉዳይ ነው ወይስ የአምልኮ ልምምዶች ጉዳይ?  መልስህን አብራራ። መ) መጽሐፍ ቅዱስ የሚደግፈው የትኛውን አቋም ይመስልሃል? ለምን? ሠ) መኮንንን በዚህ ሁኔታ ምን ትመክረዋለህ? ረ) ለተስፋዬስ ምን ትመክረዋለህ? ሰ) በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንድነት እንዲኖር ከእነዚህ ሁለቱ ሰዎች የሚጠበቀው መንፈሳዊ ባሕርይ ምንድን ነው? ሸ) በዚህ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምታገለግል ሌላ የቤተ ክርስቲያን መሪ ብትሆን ኖሮ እነዚህን ሁለት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እንዴት ትመክራቸው ነበር?  በዘመናችን ከሚታዩት ባሕርያት አንዱ በአብያተ ክርስቲያናትና በእንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንኳ ሳይቀር መከፋፈል መኖሩ ነው። አንዳንዶቹ ክፍፍሎች በእምነት ክፍሎች መካከል ባሉ የመሠረተ እምነት ትምህርት ልዩነቶች ምከንያት የሚመጡ ናቸው። ለምሳሌ፥ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ሕፃናትን ያጠምቃሉ። ሌሎቹ ደግሞ እዋቂዎችን ብቻ ያጠምቃሉ። እንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት እውነተኛ ክርስቲያኖች በልሳን መናገር አለባቸው ሲሉ፣ ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ በልሳን የመናገር ስጦታ በአንደኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ አብቅቷል ይላሉ። ነገር ግን አብዛኛዎቹ ክፍፍሎች የሚፈጠሩት በጥቃቅን ምክንያቶች ነው። ለምሳሌ፥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መዝሙር ሲዘመር ማጨብጨብ መኖር እለበት የለበትም፤ ሰዎች እጃቸውን አንስተው ሃሌሉያ ብለው መጮኽ አለባቸው የላባቸውም የሚሉት ጥቂቶቹ ናቸው።  አንድ የቤተ ክርስቲያን መሪን ከፊት ለፊቱ ተደቅነው ከሚገዳደሩት ችግሮች እንዱ እነዚህን ልዩነቶች እንዴት ማስረዳት እንዳለበት ማወቁ ላይ ነው። ሕጎችና ደንቦችን መጠቀም ነው? ወይስ እንደ ቤተ ክርስቲያን መሪነቱ ያለውን ሥልጣን በመጠቀም ለእርሱ የማይስማማውን መከልከል ነው ያለበት? ወይስ ማንኛውም የቤተ ክርስቲያን አባል መልካም ነው ብሎ የሚያመጣውን ልምምድ ሁሉ ማስተናገድ አለበት? የመሠረተ እምነት ትምህርት መመሪያዎችን ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስን ምን ያህል ማጥናት አለበት? ወይስ የተለያዩ ልምምዶችን ያስተካክል ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እንዲሠራ መፍቀድ ያላበት መቼ ነው? በዛሬው ትምህርታችን እንደ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች እነዚህን ልዩነቶች ለመረዳት የምንችልበትንና የምናስተናግድበትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መፍትሔ ለመመልከት እንሞክራለን።  የብሉይ ኪዳን ነቢያት የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት የሚለወጥበት ጊዜ እንደሚመጣ እመልክተው ነበር። ይህም እገልግሎቱ የተደበቀ ወይም የተወሰነ መሆኑ የሚያከትምበት ወቅት ነበር። ይልቁኑ በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ልጆች በሙሉ ሕይወታቸው ተለውጦ እግዚአብሔርን በመታዘዝ መኖር እስካሚችሉ ደረስ በመንፈስ ቁጥጥር ሥር የሚሆኑበት ጊዜ ነው። ኢየሱስ ምድራዊ አገልግሎቱን ሲፈጽም በቅርቡ ስለሚመጣው ስለ መንፈስ ቅዱስ አስታውቆ ነበር። እርሱም ሲመጣ የደቀ መዛሙርትን ሕይወት በመለወጥ በዓለም ሁሉ ብርቱና የተሳካላቸው የክርስቶስ ምስክሮች ያደርጋቸዋል። ኢየሱስ ይህን ብሎ ወደ ሰማይ ከዐረገ በኋላ ኀምሳ ቀናት እስኪያልፉ መንፈስ ቅዱስ አልወረደም ነበር። በበዓለ አምሳ ቀን በድንገት የደቀ መዛሙርት ሕይወትና ታሪክ በሙሉ ተለወጠ። በእነርሱ ላይ የወረደው መንፈስ ቅዱስ እጅግ ፈሪ የነበሩትን የክርስቶስ ተከታዮች በዘመናቸው የነበረውን ትውልድ የለወጡ ታላቅ አገልጋዮች እደረጋቸው። በደቀ መዛሙርት ሕይወትና በዓለም ታሪክ የታየው ታላቅ ለውጥ የተከሰተው መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር ሰዎች ላይ በአዲስ መንገድ በመውረዱ ነው።  የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ በሚቀጥሉት ሠላሳ ወይም ሠላሳ አምስት ዓመታት የሠራውን ሥራ ነው። ነገር ግን ይህን በደቀ መዛሙርት ላይ የወረደውን የመንፈስ ቅዱስን እሠራር ለመረዳት አስቸጋሪ ነው። በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የምናያቸው ታሪኮች በተላይ ተአምራታዊ ክስተቶች፥ ዛሬ ቤተ ክርስቲያን መሆን ስለሚገባት ምሳሌዎች ናቸው ወይስ የዚያ ዘመን ብቻ ልዩ ባሕርያት ናቸው? መንፈስ ቅዱስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላሚሠራው ሥራ የሚሰጡ የተለያዩ ትምህርቶች በዘመናችን መንፈስ ቅዱስ መፈጸም ስላለበት ተግባር ክርስቲያኖችን ግልጽና አንድ ወደሆነ መረዳት ከማምጣት ይልቅ ውዥንብርና አለመጣጣም ውስጥ ከትተዋቸዋል። አለመግባባቱ የሚከሰተው በአብዛኛው በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ የተደረገውን በመረዳት ጉዳይ ሳይሆን የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ መንፈስ ቅዱስ በዘመናት ሁሉ የሚሠራው በዚህ መልክ መሆኑን ለማሳየት እንደሆነና እንዳልሆነ፥ እኛም ዛሬ መጠበቅ ያለብን ተመሳሳይ ሁኔታዎችን ስለመሆን አለመሆኑ ለማወቅ በሚደረገው ሙከራ ላይ ነው። ይህ የአሳብ ልዩነት ‹ካሪዝማቲክ› ወይም «ፔንትኮስታል› የሚባሉ አብያተ ክርስቲያናትን በአንድ ወገን ነጥሎ ሲያስቀምጥ፥ መንፈስ ቅዱስ ዛሬ የሚሠራው በሐዋርያት ዘመን በሠራበት መንገድ አይደለም የሚሉ አብያተ ክርስቲያናትን ደግሞ በሌላ ወገን አስቀምጦአቸዋል።  ትክክለኛው አመለካከት የትኛው ነው? መልሱ የሐዋርያትን ሥራ መጽሐፍን በምንረዳበት መንገድ ይወሰናል። የመንፈስ ቅዱስን ሥራ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በተገለጠው መንገድ በዝርዝር ከመመልከታችን በፊት «ክርስቲያኖች በመሠረታዊ የእምነት ትምህርት ሳይስማሙ ሲቀሩ ምን ማድረግ አለባቸው?» የሚለውን አስፈላጊ ጥያቄ መጠየቅ አለብን።  ጥያቄ፡– በኢትዮጵያ ያሉ ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስን በሚመለከት ትምህርት ላይ የማይስማሙባቸውን መንገዶች ዝርዝር።  እስካሁን ድረስ ስለ መንፈስ ቅዱስ በተመለከትናቸው ጥናቶች ክርስቲያኖች ከሞላ ጐደል አንድ እምነት አላቸው። በጠቅላላው ክርስቲያኖች ሁሉ መንፈስ ቅዱስ ኃይል ሳይሆን አካል ያለው ግፃዌ መለኮት አባልና ከሥላሴ አካላት አንዱ እንደሆነ ያምናሉ። በብሉይ ኪዳንና በኢየሱስ ሕይወት የነበረውን አገልግሎት ይቀበላሉ። አንድ ሰው ጌታን አምኖ በሚድንበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በሕይወቱ ስለሚሠራቸው አብዛኛው ተግባራት በሚሰጡት ትምህርቶች ብዙዎች ክርስቲያኖች ይስማማሉ። ደግሞም ክርስቲያን በምድር በሚኖርበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በሕይውቱ ስለሚሠራቸው ሥራዎች በአብዛኛው ይስማማሉ።  ሆኖም ግን ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያን

ክርስቲያኖች እንደ መንፈስ ቅዱስ ባሉ መሠረታዊ የክርስትና አስተምህሮዎች ላይ ባላቸው አመለካከት ልዩነት የሚያሳዩት ለምንድን ነው? Read More »

ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ያስተማረው ትምህርት፤ ክፍል 2

ዮሐ 16፡5-16  ጥያቄ፡ ዮሐ 16፡5-16 እንብብ። ሀ) መንፈስ ቅዱስ ይኖረዋል ብለው እነዚህ ጥቅሶች ስለ አገልግሎቱ የሚያስተምሩትን የተለያዩ አገልግሎቶች ዘርዝር። ለ) ኢየሱስ በእርሱና በመንፈስ ቅዱስ መካከል ያለውን ግንኙነት እንዴት እንደሚያመላክት ግላጽ።  ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርት ጋር የሚቆይበት ጊዜ የተወሰነ እንደሆነ አውቆ ነበር። በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ተይዞ፥ ለፍርድ መቅረብና መሰቀል ነበረበት። ኢየሱስ ከሞት እንደሚነሣ ቢያውቅም እንኳ ከትንሣኤ በኋላ ደቀ መዛሙርትን የሚያስተምርበት ጊዘ ጥረት እንደሆነ አውቆታል። እንዲያውም ኢየሱስ ከሞት ከተነሣ በኋላ አንዳችም ጥልቅ ትምህርት ስለማስተማሩ የወንጌል ጸሐፊዎች አንዳቸውም አልዘገቡልንም። ትቶአቸው ከመሄዱ በፊት ሊረሱት የማይገባቸውን ቁልፍ እውነቶች አስታወሳቸው። ከእነዚህ ዋነኛ እውነቶች አንዱ የመንፈስ ቅዱስ መምጣትና በኢየሱስ ምትክ ስለሚሰጠው አገልግሎት ነበር። የኢየሱስ ትኩረት መንፈስ ቅዱስ በሚሰጣቸው የተለያዩ አገልግሎቶች ማለትም ተአምራትን ስላማድረግ ኃይሉ፥ ሰዎች በልሳን እንዲናገሩ ስለሚሰጠው እገዛ፥ ወይም ስጦታዎች አልነበረም። ይልቁኑ ኢየሱስ ያተኮረው መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠው አገልሎት እርሱ በምድር በነበረበት ጊዜ ከሰጠው አገልግሎት ጋር ስለሚዛመድበት ሁኔታ ነበር። እንደገና አንዳንድ ቁልፍ ጥያቄዎቹን በመጠየቅ ኢየሱስ ጥያቄዎቹን እንዴት እንደመለሳቸው እንመልከት።  1. ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ትቶአቸው መሄዱ ከሁሉም (የተመረጠው) የነበረው ለምንድን ነው?  ከሚወዱት ጓደኛ መለየት ሁልጊዜ ከባድ ነገር ነው። ኢየሱስ ተለይቶአቸው መሄዱ ለደቀ መዛሙርት ትልቅ ሐዘን እንደሚያመጣ በመገንዘብ ሊያረጋጋቸው ሞከረ። ትቶአቸው ቢሄድ እንደሚሻል ነገራቸው። ቀደም ብለን እንደተመለከትነው ኢየሱስ በምድር ላይ በተመላለሰበት ወቅት ሥጋዊ አካል ነበረው። ልክ እንደ እኛ ሰው ነበር። የኢየሱስ ሰው መሆን ከሚያስከትላቸው ችግሮች አንዱ በአንድ ጊዜ መገኘት የሚችለው በአንድ ስፍራ ብቻ መሆኑ ነበር። ስለዚህ አንዴ በገሊላ ወይም በኢየሩሳሌም ይሆን ነበር። በአንድ ጊዜ በሁለቱም ስፍራዎች አይገኝም ነበር። ቤተ ክርስቲያን ኈፍጥነት በማደግ ከኢየሩሳሌም ጀምራ ወደ ይሁዳ ሰማርያ በመጨረሻም ወደ ኢትዮጵያ ሁሉ እየተስፋፋች ነበር። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ቢፈልጉት በእነዚህ ስፍራዎች ሁሉ በሰብአዊ አካል በአንድ ጊዜ ለወመገኘት አይችልም ነበር። በሌላ በኩል ግን መንፈስ ቅዱስ በሁሉም ስፍራ በአንድ ጊዜ ይገኛል። ሥጋዊ አካል ስለሌለው በአንድ ጊዜ በሁሉም ስፍራ መገኘት ይችላል። በአንድ ጊዜ በኢየሩሳሌምና በኢትዮጵያ መሆን ይችላል። ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጆች በሙሉ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ህልውና ከእነርሱ ጋር ያለማቋረጥ እንዲሆን እያንዳንዳቸው ከኢየሱስ አካላዊ ህልውና ይልቅ የመንፈስ ቅዱስ ህልውና ያስፈልጋቸዋል።  20ኛ ጥያቄ፡- አንድ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስ ሁልጊዜ ከእርሱ ጋር እንደሚኖር ማወቅ ለምን ያስፈልገዋል?  2. መንፈስ ቅዱስ በዓለም ላይ ምን አገልግሎት ይኖረዋል?  ስለ መንፈስ ቅዱስ ስናስብ ብዙ ጊዜ የሚመጣልን በክርስቲያኖች በኩል ወይም በክርስቲያኖች ውስጥ የሚሰጠው አገልግሎት ነው። ሆኖም ግን ጌታ ኢየሱስ፤ መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያኖች ሕይወት ውስጥ የሚሠራውን ከመናገሩ በፊት በዓለም ላይ የሚሠራውን ነግሮናል። ከመንፈስ ቅዱስ ተቀዳሚ ሥራዎች አንዱ ዓለምን ስለ ኃጢአት መውቀስ ነው። ይህ አባባል መንፈስ ቅዱስ «የዓለምን ጥፋተኛነት ያጋልጣል» ተብሎ ሊተረጐም ይችላል። መውቀስ ለሚለው ቃል የግሪኩ ትርጉም የሚያመለክተው በችሎት የተቀመጠ አንድ ጳኛ በተከሳሽ ላይ የቀረበበትን ማስረጃ በሙሉ ተመልክቶ በተከሳሹ ላይ የጥፋተኝነት ብያኔ ማወጁን ነው። መንፈስ ቅዱስ በዓለም ባለው አገልግሉቱ ይህ ዓይነቱን የዳኝነት ሥራ የሚሠራው ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአተኞች መሆናቸውና ከእግዚአብሔር ፍርድ ሊያመልጡ አለመቻላቸው እንዲሰማቸው በማድረግ ነው። በሚገባ ስላላወቅን ነው ብላው ሰበብ በማቅረብ ሊናገሩ አይችሉም። የኃጢአት ይቅርታ የሚያስፈልጋቸው ኃጢአተኞች መሆናቸውን ያውቃሉ።  ጥያቄ፡- አንድ ክርስቲያን ያልሆነ ሰው ክርስቲያን ከመሆኑ በፊት ጥፋተኛ መሆኑን መገንዘቡ አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድን ነው?  ብዙ ጊዜ ክርስቲያኖች ሌሎች ሰዎች ኃጢአተኛች መሆናቸውንና ንስሐ ካልገቡ በስተቀር እግዚአብሔር የዘላለም ሞት እንደሚፈርድባቸው ለመናገር እንፈራለን። ይህ መልእክት ሰዎችን በእኛ ላይ በቁጣ እንዲሁ ያደርጋል። እኛም እንዳንድ ጊዜ ይህ ጭከና ነው ብለን እናስባለን። ነገር ግን የእኛን ቃል ወስዶ የድነት (ደኅንነት)ን እስፈላጊነት በማሳየት ሰዎችን ወደ ክርስቶስ መምራት የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው። አንድ በሽተኛ መታመሙን እስካላረጋገጠ ድረስ ሕክምና ፍለጋ ወደ ሐኪም አይሄድም። እንዲሁም አንድ ኃጢአተኛ ጥፋተኛ መሆኑንና በጥፋቱ ምክንያት ከእግዚአብሔር የዘላለም ቅጣት እንዳለበት ካልተገነዘበ በስተቀር ለመቼውም ወደ ክርስቶስ እይመለስም።  የመንፈስ ቅዱስ የወቀሳ አገልግሎት በሦስት ይከፈላል።  ሀ. ዓለምን ስለ ኃጢአት ይወቅሳል፡- ይህ አሳብ ከመጀመሪያው ሰዎችን ስለ ጥፋታቸው ስለመውቀስ ከተነገረው ጋር በጣም የተቀራረበ ነው። ኢየሱስ የሚናገረው የኃጢአተኛነታችን ውጤት ሆኖ በየዕለቱ ስለምንሠራቸው በርካታ ኃጢአቶች አይደለም። ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስ በአንድ ዋና ኃጢአት፥ ያም «ያለማመን ኃጢአት» ላይ እንደሚያተኩር ተናገረ። ሰዎች ወደ ገሃነም የሚሄዱት ኃጢአተኞች ስለሆኑ አይደለም። ወደ ገሃነም የሚጣሉት ባለማመናቸው ምክንያት ብቻ ነው። ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን። ሁላችንም የገሃነም ፍርድ ይገባናል። ነገር ግን ዘላለማዊ ቤታችን ገሃነም ወይም መንግሥተ ሰማያት እንዲሆን የሚወስነው ኃጢአት የአለማመን ኃጢአት ነው። ኢየሱስን በማመን በመስቀል ላይ የከፈለውን መሥዋዕትነት ካልተቀበልን በስተቀር መድኃኒት ቢኖርም እንኳ መድኃኒቱን አልወስድም ማለትም መሥዋዕትነቱን አለመቀበላችን ነው ወደ ኩነኔ የሚወስደን። ስለዚህ ከመንፈስ ቅዱስ ዋነኛ አገልግሎቶች አንዱ የማያምኑ ሰዎችን ጥፋተኛ የሚያደርጋቸውና የዘላለምን ፍርድ የሚያመጣባቸው ያለማመናቸው ውጤት መሆኑን ማሣየት ነው።  ያለማመን ኃጢአት እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ድነት (ደኅንነት) እጦት የሰጠውን ምላሽ እምቢ ማለትና ወደ ሌሎች የድነት (ደኅንነት) መንገዶች በማዘንበል የሚደረግ የሕሊና ውሳኔ ነው። ብዙ ሰዎች ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚያደርስ መንገድ ለራሳቸው በማበጀት ወይም የተለያዩ ዓይነት አማልክትን በመፈልሰፍና እነርሱን ደስ በማሰኘት ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ይሞክራሉ። ነገር ግን ይህን ሲያደርጉ «እግዚአብሔር ሆይ፥ የአንተን መንገድ እንፈልግም እኛ የምንፈልገው በዚያ ፈንታ የራሳችንን መንገድ ነው» ማለታቸው ነው። ይህ ዓመፃ ነው እግዚአብሔር ደግሞ ዓመቱን ሁሉ በዘላለም ሞት ይቀጣል።  ለ. ዓለምን ስለ ጽድቅ ይወቅሳል፡- ክርስቲያኖች ጽድቅ የሚለውን ቃል ብዙ ጊዜ በተሳሳተ መንገድ ይረዱታል። መሠረታዊ ትርጉሙ በመልካም ሥነምግባር መኖር ይመስላቸዋል። ጻድቅ የሚለው የግሪክ ቃል ከመንበረ ችሎት የተወሰደ ሌላው የሕግ ቃል ነው። ትርጉሙም ‹ጥፋተኛ አይደለም) የሚል ምስክርነት ከእግዚአብሔር ማግኘት ማለት ነው። ይህ ምስክርነት እንዴት ሊገኝ ይችላል? የሰው ልጆች፥ የተቻለንን ያህል ሕግን ስለምንጠብቅና መልካም ስለሆንን ጻድቆች ነን ብለው በማሰብ ክእግዚአብሔር ዘንድ ምስክርነትን ለማግኘት ይጥራሉ። ሰው በእግዚአብሔር ፊት «ጥፋተኛ አይደላህም» ሊባል የሚችልበት አንድ መንገድ ብቻ አለ። ይህም መንገድ የኃጢአታችን ዋጋ (ያለማመን ኃጢአትና ሌላ ማንኛውም ኃጢአት) በሌላ ሰው ከተከፈለ ብቻ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ «የኃጢአት ዋጋ ሞት ነው» ይላል (ሮሜ 6፡23)። ኢየሱስ በመስቀል ላይ በመሞትና የኃጢአታችንን ዋጋ በመክፈል ጽድቃችን ሆነ (ሮሜ 5፡19)። መንፈስ ቅዱስ በእንድ ሰው ልብ ካልሠራና ያ ሰው የኢየሱስ ክርስቶስን ጽድቅ ካልተቀበላ ጻድቅ ለመሆን አይችልም።  ኢየሱስ ስለ ኃጢአት የከፈለው መሥዋዕትነት በእግዚአብሔር ዘንድ ለኃጢአት ዕዳ የተከፈለ ዋጋ ለመሆኑ የመጨረሻው ማረጋገጫ ምን ነበር? የመስቀል ሞት አልነበረም። ኢየሱስ ሞቶ ቢቀር ኖሮ እግዚአብሔር ይህን መሥዋዕትነት ይቀበላው እይቀበላው አይታወቅም ነበር። ይልቁኑ የመጨረሻው ማረጋገጫ ኢየሱስ ከሙታን በመነሣቱና ወደ ሰማይ ዐርጐ በእግዚአብሔር ቀኝ መቀመጡ ነው። ትንሣኤና ዕርገቱም እግዚአብሔር መሥዋዕቱን ለመቀበሉ ምልክት ሆኖ በዚህም ሰዎች በማመን ጽድቅን የሚያገኙበት መንገድ እንደሆነ አጸደቀ። በትንሣኤ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ እንዲህ ብሎ አውጇል። «ኃጢአትህ ይቅር እንዲባልና ጻድቅ እንድትሆን ከፈለግህ ልጄ በመስቀል ላይ የከፈለውን መሥዋዕትነት በመቀስል ለአንተ ያዘጋጀልህን ጽድቅ ውሰድ።» በሰው ልብና አእምሮ ውስጥ በመሥራት ይህን እውነት ወደ ሚረዳበትና ወደ ሚቀበልበት ነጥብ ማድረስ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ነው።  ሐ. ስለ ፍርድ ዓለምን መውቀስ፡- አንድ ነገር ወይም አንድ ሰው መልካም ወይም ክፉ እንደሆነ በይፋ የሚነገርበት ሂደት ፍርድ ይባላል። ስለዚህ ከመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች አንዱ ዓለም (ለማያምኑ ሰዎች) የሚቀበለው ፍርድ የጥፋተኛነት» ወይም «ጥፋተኛ ያለመሆንን መሆኑን ማመን ነው። ኃጢአትና ኩነኔ ባለበት እግዚአብሔር ሁልጊዜ የበደለኝነት ፍርድን ያውጃል። ስለዚህ ሰዎች ኃጢአተኞች ከመሆናቸው የተነሣ በደለኞች እንደሆነ ዮስጠንቀቁ ሥራ የመንፈስ ቅዱስ ነው። ስለዚህ ከራሳቸው ጽድቅ ውጭ ሌላ ጽድቅ ካላገኙ በስተቀር ቅጣት ይቀበላሉ።  ፍርድ በሰዎች ሁሉ ላይ የሚመጣ ቢሆንም (2ኛ ቆሮ. 5፡10)፥ በኢየሱስ

ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ያስተማረው ትምህርት፤ ክፍል 2 Read More »

ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሰጠው ትምህርት፤ ክፍል 1

ለብዙ መቶ ዓመታት እግዚአብሔር ስለ አዲስ ዘመን የትንቢት መልእክት ተናር ነበር። ይህ አዲስ ዘመን የእግዚአብሔር መሢሕ በጽድቅ የሚገዛበት፥ የእግዚአብሔር መንፈስ በሕዝቡ ሁሉ ላይ የሚሆንበት ዘመን ነበር። ኢየሱስ መጥቶ በመንፈስ ቅዱስ አመራር በሠራ ጊዜ ይህ ዘመን ደረሰ። አይሁድ የተጠባበቁትም ይህንኑ ነበር። ኢየሱስ የዳዊትን መንግሥት በገሃድ ላቋቋምና የርማን ጦር ሠራዊት ድል ለማድረግ የመጣው መሢሕ እንደሆነ ቆጠሩ። በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ ግን ያ ሕልማቸው ከሰመ። ኢየሱስ የመጣው በምድር ላይ ሥጋዊ ንጉሥ ሆኖ ለመግዛት ሳይሆን ይልቁኑ ሰዎችን ከመንፈሳዊ ባርነት ለማዳን ነበር።  መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ሕይወትና አገልሎት ውስጥ ገቢራን ተሳትና የነበረው ቢሆንም የመጣው እንደተተነበየው አልነበረም። በእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ ላይ አልወረደም። ገር ን ደቀ መዛሙርት በኢየሱስ ሕይወት አይተው የመሰከሩለት የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት በእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ላይ እንደወረድ ተስፋ ሰጠ። የመንፈስ ቅዱስ ዘመን ወዲያውኑ ቀጥሎ የሚመጣ ነበር።  ጥያቄ፡- ሁለት ክርስቲያኖች ቡና እየጠጡ ስለ መንፈስ ቅዱስ ይነጋገሩ ነበር። አንደኛው ሊናገር የመንፈስ ቅዱስ ተቀዳሚ ተግባር ክርስቲያኖች በልሳን እንዲናገሩና የሥጋ ፈውስ እንዲያገኙ ጎድረግ ነው ይል ነበር። ሌላኛው ክርስቲያን ን ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ያስተማረውን ላማሳየት መጽሐፍ ቅዱሱን ገልጦ የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመለከተ። እስኪ እንተ የሚከተሉትን ጥቅሶች እንብብ። ማቴ 10፡20፤ ሉቃስ 11፡13፤ ዮሐ 1፡ 33፤ 7፡39፤ 14፡15-27፣ 26-27፤ 16፡5-16፤ 20፡22፤ የሐዋ. 1፡2፥5-8። ሀ) ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ለደቀመዛሙርቱ የሰጠው ተስፋ ምን ነበር? ለ) ከላይ በተመለከትናቸው ጥቅሶች ኢየሱስ የመንፈስ ቅዱስ ተቀጻሚ አማላ ምንድን ነው ብሎ የሚያስተምር ይመስልሃል? ሐ) ለመጀመሪያዎቹ ይነት ክርስቲያኖች እንዴት ትመልስላቸዋለህ?  የመጥምቁ ዮሐንስ ድምፁ በምድረ በዳ እንዳለ መላክት የመሢሑን የኢየሱስን መምጣት በሚያውጅበት ጊዜ የኢየሱስ የማጥመቅ አገልግሎት በሁላት ነገርች መለያነት ቀርቧል። የመጀመሪያው እሳት ሊሆን ኢየሱስ እንደ መሢሕነቱ የሚያመጣውን ፍርድ የሚያሳይ ነበር። ይህ አገልግሎት ኢየሱስ በመጀመሪያ በመጣበት ጊዜ የተፈጸመ ባይሆንም ጓግም በሚመጣበት ጊዜ ዋናው አገልግሎቱ ይሆናል። በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በሕዝቡ ሁሉ ላይ ይፈርጓል (ዮሐ 5፡22፥ 27 ተመልከት።  ሁለተኛው ደጎሞ ኢየሱስ ተከታዮቹን በመንፈስ ቅዱስ ግጥመቁ ነበር። መንፈስ ቅዱስ በሰው ሁሉ ላይ ይመጣል ከሚለው ትንቢት እኳያ ይህ የኢየሱስ አገልግሎት የጀመረው በምድር ላይ በነበረበት ወቅት ሊመስለን ይችላል። ነገር ግን በሰዎች ላይ የመጣው መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ ምድርን ለቅቆ ወደ ሰማይ ከሄደ በኋላ እንጂ ከዚያ በፊት አልነበረም፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከአሥራ ሁላቱ ደቀ መዛሙርት ጋር ስለነበረው ቀንኙነት በወንጌላት የተጠቀሰው በጥቂት ነው። ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርት ጋር አብሮአቸው በነበረ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከእነርሱ ጋር እንደሚኖር ተናግሯል (ዮሐ 14፡7)። ኢየሱስ በተጨማሪ እርሱ አብርአቸው እስካለ ድረስ መንፈስ ቅዱስ አብሮአቸው እንደማይኖርም ተናግሯል (ዮሐ 16፡7)።  ዮሐ 3፡5-8  ኢየሱስ ሕዝቡን በግልጽ ያገለገለበትን የሦስት ዓመት አገልግሎት ሲጀምር ደቀ መዛሙርቱን ለለ መንፈስ ቅዱስ ያስተማራቸው እጅግ ጥቂት ነገር ነበር። ይልቁኑ መንፈስ ቅዱስ በግልጽ በሕይወቱ ይሠራ ለለነበር በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ በሕይወቱ ምሳሌ ሆኖ በመኖር አሳያቸው። ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ በመጀመሪያ የአገልግሎት ዘመን ቀልጽ የሆነ ውይይት ያደረገው በዮሐ 3 እንደተጻፈው ኒቆዲሞላ ከተባለ የአይሁድ መምህር ጋር በተገናኘ ጊዜ ነበር። በዚያ ለፍራ ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ የሚነግረው አዲስ መንፈሳዊ ልደትን ለሰው የሚሰጠው መንፈስ ቅዱስ እንደሆነና እንደ ነፋስም በፀጥታ እንደሚሠራ ነበር።  ጥያቄ፡- ዮሐ 3፡5-8 አንብብ። ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ በዚህ ስፍራ ያስተምራቸው እውነተች ምን ምን ነበሩ?  ኢየሱስ፤ ለደቀ መዛሙርቱና ለኒቆዲሞስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ያስተማራቸው የመጀመሪያ እውነት ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለማምጣት መንፈስ ቅዱስ የሚጫወተውን ከፍተኛ ሚና ነበር። አንድ ሰው የእግዚአብሔር መንግሥት አካል ለመሆን በመጀመሪያ በውኃ (የሥጋ ልደት) ቀጥሎ ደግሞ ከመንፈስ (መንፈሳዊ ልደት) መወለድ ያስፈልገዋል። መንፈስ ቅዱስ አዲስ ሕይወትን ለማስገኘት በሰው ውስጣዊ ኑባሬ፥ በመንፈሱ ውስጥ መሥራት አለበት። ይህ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት በሥራው እንደ ነፋስ ፀጥ ያለና ድብቅ (የማይታይ) ሲሆን ነገር ቀን ለውጡ ወይም የሥራው ውጤት በግልጽ ይታያል። መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ለሰዎች አዲስ ሕይወት የመስጠት አገልግሎቱን በሌላ ትምህርት በሚገባ እንመለከተዋለን።  ኢየሱስ በምድራዊ ሕይወቱ መጨረሻ አካባቢ ወደ ሰማይ የሚመለስበት ጊዜ እየቀረበ ስለነበር እርሱ በማይኖርበት ጊዜ እንዴት እንደሚቀጥሉ ያዘጋጃቸው ጀመር። ክመሰናበቱ በፊት ካስተማራቸው ዋነኛ እውነቶች አንዱ የመንፈስ ቅዱስ ጉዳይ ነበር። እነዚህን ትምህርቶች በጥንቃቄ ማጥናት አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም ስለ መንፈስ ቅዱስ በደቀ መዛሙርቱ መምጣት የሚገባው ለምን እንደሆነ ቀልጽ ትምህርት ስለሚሰጡ ነው። በእዚህ ትምህርቶች በአንድ ክርስቲያን ሕይወት ቀጻሚ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች ናቸው ብለን ስለምናስባቸው፥ ስለ ፈውስና፡ በልሳናት ስለመናገር፥ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎችና ሌሎችም የተጠቀሰ ምንም ነገር አለመኖሩን ልብ ማለት ጥሩ ነው። ይልቁኑ ኢየሱስ ትኩረት ያደረገው መንፈስ ቅዱስ ከእርሱ ጋር ስላለው ውስጣዊ ቀንኙነት፥ እንዴት በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ የእርሱን ህልውና እንደሚተካ ነበር። መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ያለውን ተቀዳሚ ተግባር ለመረጓት ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት ለደቀመዛሙርቱ የሰጠውን ትምህርት መገንዘብ ይጠቅማል።  ስለ መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ የሰጠው አብዛኛው ትምህርቱ በዮሐ ከ14-16 ባሉት ምዕራፎች ላይ የተመሠረተ ሲሆን ይህም ከመሞቱ በፊት ለደቀ መዛሙርቱ በዋነኛነት የሰጠው የመጨረሻ ትምህርት ነው። ስለዚህ ከእነዚህ ሦስት ምዕራፎች ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚያተኩሩትን ክፍሎች በጥልቀት እንመለከታለን፡፡  ዮሐንስ 14፡15-21  ጥያቄ፡ ዮሐ 14፡15-21 በጥንቃቄ አንብብ። ሀ) በዚህ ክፍል ውስጥ ኢየሱስ ለመንፈስ ቅዱስ የሰጣቸውን የተለያዩ ስሞች ዘርዝር። እነዚህ ላሞች ስለ መንፈስ ቅዱስ ዓላማ ምን ምን ይነግሩናል? ለ) በመንፈስ ቅዱስና በደቀ መዛሙርት መካከል ምን ዓይነት የግንኙነት ለውጥ ሊደረግ ነበር? ሐ) መንፈስ ቅዱስን ላደቀ መዛሙርት የሚሰጥ ማን ነው? መ) መንፈስ ቅዱስ ክደቀ መዛሙርት ጋር የሚያየው ለምን ያህል ጊዜ ነው?  በዮሐ 14፡5-21 የሚገኘውን ትምህርት በአጭሩ ለማቅረብ ከሁሉ የተሻለው ዘዴ የተለያዩ ጥያቄዎችን መጠየቅና የዮሐንስ ወንጌል እነዚህን ጥያቄዎች እንዴት እንደሚመልስ በመመልከት ሳይሆን አይቀርም።  ሀ. መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ላይ የሚመጣው (የሚወርደው) እንዴት ነው?  ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ በአብና በወልድ መካከል ያለውን የቅርብ ግንኙነት ያስተምር ነበር (ዮሐ 14፡9-14)። አብ በወልድ፡ ወልድም በአብ ውስጥ ነበር (ቁጥር 1)። ግንኙነታቸው በጣም የቀረበ ከመሆኑ የተነሣ አንዱ ሲሠራ ሌላውም ይሠራል። ሌላውን ፈጽሞ በማይጨምር መንገድ የተሠራ ሥራ የለም። የወልድ ዓላማ ለአብ ክብርን ማምጣት ነበር (ቁጥር 1)። ይህ እጅግ የቀረበ የጋራ ግንኙነት ኢየሱስ ከደቀመዛሙርት ጋር ለነበረው ንኙነት እንደ ምሳሌ መታየት ያለበት ነበር (ቁጥር 20)። ደቀ ወመዛሙርቱ ኢየሱስ ካደረጋቸው የሚበልጡ ነገሮችን ማድረግ ነበረባቸው (ቁጥር 2)። ይህ እውነት ሊሆን የሚችለው መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ውስጥ ከኖረ ብቻ ነበር።  በደቀ መዛሙርት ሕይወት ውስጥ የመንፈስ ቅዱስን ህልውና ለመግላጽ ኢየሱስ ሁለት ዋና ዐረፍተ ነገሮችን ተናግሯል። በመታዘዝ የተደገፈ ፍቅር ለኢየሱስ ማሳየት ነበረባቸው። ኢየሱስ ከዚህ ጥቂት ቆየት ብሎ እንደሚናገረው ለእርሱ ያላቸው ፍቅርና እርስ በርሳቸው በመካከላቸው የሚያሳዩት ፍቅር የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የመሆናችው የመጨረሻ ማረጋገጫ ነው (ዮሐ 15፡12-17፤ 17፡21-23)። ኢየሱስን ከወደዱት ኢየሱስ ሌላ አጽናኝ እንዲሰጣቸው አብን ይጠይቃል።  ሁለተኛ በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ዋና ምንጭ እግዚአብሔር እብ እንደሆነ እንመለከታለን። ኢየሱስ ለአብ በሚያቀርበው ጥያቄ መንፈስ ቅዱስ ከአብ ለደቀ መዛሙርት ይሰጣል። ስለዚህ በመጨረሻ የምንላው መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ ለእግዚአብሔር ልጆች በሙሉ እንደሚመጣ ነው።  ለ. ለመንፈስ ቅዱስ የተሰጡ ሁለት ስሞች ምንና ምን ናቸው?  1 ሌላው አጽናኝ፡- አብሮአቸው በአካል ሊኖር ለነበረው ኢየሱስ ምትክ እግዚአብሔር አብ ሌላው አጽናኝ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን እንደሚልክላቸው ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ተስፋን ሰጣቸው። በመጀመሪያው መንፈስ ቅዱስ ስም ሁለት ነገሮችን ልብ ማለት እንችላለን። በመጀመሪያ፥ ሌላው የሚለው ቃል ነው። ግሪኮች «ሌላው» የሚለውን ቃል በሁለት መንገድ ይጠቀሙበታል። የመጀመሪያው ቃል ሌላ ፈጽሞ ከመጀመሪያው

ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሰጠው ትምህርት፤ ክፍል 1 Read More »

መንፈስ ቅዱስ በጌታ ኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ውስጥ

ከ400 ዓመታት ፀጥታ በኋላ የእግዚአብሔር መንፈስ እንደገና መሥራት ጀመረ። በብዙ መንገዶች አገልግሎቱ በብሉይ ኪዳን ከነበረው ጋር ተመሳሳይ ነበር። ነገር ግን በመጀመሪያ በኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት በኋላም በቀደመችው ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በብሉይና በአዲስ ኪዳን መካከል የነበረው የሽግር ጊዜ ተጀመረ። በወንጌላት ውስጥ አዲሱ ዘመንና የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በብሉይ ኪዳን ዘመን ከነበረው አገልግሎቱ ተመሳሳይ ነበር። በጥንቷ እስራኤል በብዙ መሪዎች ሕይወት እንደሆነው መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ላይ በመውረድ የእስራኤልን ሕዝብ እንዲመራና እንዲያገለግል ኃይልን አጐናጸፈው። እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት መንፈስ ቅዱስ በሁሉም የእግዚአብሔር ሰዎች ውስጥ ወደሚኖርበት ዘመን የገባንበትን የሽግግር ጊዜ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ እናገኛለን።  አንድ ቀን የእግዚአብሔር መልአክ ወደ ኤልሳቤጥ በመምጣት ከማኅፀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ የሚያድርበት ሕንን እንደምትወልድ እንደነገራት ያ የእግዚአብሔር የዘመናት ፀጥታ ተገፈፈ (ሉቃስ 1፡8)። በዚህም የመሢሑ መንገድ ጠራጊ የሆነው መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ። መንፈስ ቅዱስ በሕይወቱ መኖሩ የተረጋገጠው በተአምራት ሳይሆን ስለ መሢሑ መምጣት ባስተላለፈው ጠንካራ መልእክት ነበር።  ሀ. መንፈስ ቅዱስና የኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ  ብዙ ጊዜ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስናስብ አምላክነቱን በአንደኛ ደረጃ ፥ ሰው መሆኑን ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ እናያለን። ምንም እንኳ ኢየሱስ አምላክ ስለሆነ መንፈስ ቅዱስ ባያስፈልገውም ፍፁም ሰውም ነበር። እንዲያውም የፍጹም ሰው ሦሳሌ ነው ማለት እንችላለን። ጳውሎስ ከመጀመሪያው ሰው ከአዳም ጋር ያወዳድረዋል። እርሱ ኋለኛው እቶም፡ ሁለተኛው ፍጹም ሰው ነው (ሮሜ 5፡14-17)። ኢየሱስ ልክ እንደ እኔና እንደ አንተ ፍጹም ሰው ነበር። ሰው ስለሆነ መንፈስ ቅዱስ በሕይወቱ አስፈልጐት ነበር። በምድር ላይ በኖረው ሕይወቱ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ፍጹም የሆነ ሕይወትን እንዴት መኖር እንደምንችል የተሟላ ምሳሌ ይሰጠናል። እርሱ ልንከተለው የሚገባን ምሳሌያችን ነው።  ወንጌላትን በምናነብበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ዋና ተሳታፊ እንደነበር እናያለን። የኢየሱስ ልደት መረዳታችንን የሚያልፍ ተአምር ነበር። መንፈስ የሆነው ዘላለማዊ እግዚአብሔር የሰውን ሥጋ ለብሶ ፍጹም ሰው እንዴት ሊሆን ይችላል? እግዚአብሔር በሴት ማኅፀን ውስጥ እንደማንኛውም ሕፃን የሚያድግ ቅንጣት ዘር እስኪያክል ድረስ እራሱን እንዴት ለማሳነስ ቻላ? አናውቅም። መልሱን ግን የምናገኘው በመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ውስጥ ነው። ተአምራቱን ያደረገው መንፈስ ቅዱስ ነበር። ዘላለማዊ የእግዚአብሔር ቃል ትንሽ ዘር ሆኖ በማርያም ማኅፀን ውስጥ በማደር ማደግ ጀመረ (ሉቃስ 1፡35)። እግዚአብሔር አብ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ለኢየሱስ ሥጋዊ አካልን አዘጋጀለት (ዕብ 10፡5)። በምድር ላይ እንደ ፍጹም ሰው ኖረ። ልክ እንደ እኛ ሰው ሆኖ በሰብአዊ ውስንነት የተገደበ ነበር። ለምሳሌ ኢየሱስ እንደ መንፈስ በአንድ ጊዜ በሁሉም ስፍራ ይገኝ ነበር። ነገር ግን ከመቅጽበት በሥጋዊ አካል ተገደበና በአንድ ጊዜ በአንድ ስፍራ ብቻ የሚኖር ሆነ። ሰብአዊ ህልውናን መለማመድ እንዲችል አብዛኛዎቹ መለኮታዊ ኃይላቱ ውስን ሆኑ። በዕብራውያን መጽሐፍ ዘላለማዊ አምላክ የሆነው ኢየሱስ «በመከራው መታዘዝን ተማረ» (ዕብ. 5፡8) ተብሎ ተጽፎለታል። ኢየሱስ ለመጀመሪያ ጊዜ በሥጋዊ አካል ላይ የሚደርስ ሕመም፥ መከራ፥ ረሃብ፥ ስደት፥ ስድብና መናቅ የመሳሰሉ፥ እኛ በሰብአዊነታችን የምንለማመዳቸው ነገሮች ይደርሱበት ጀመር። ኢየሱስ የተለየ የሆነው ኃጢአታዊ ተፈጥሮ ስላልነበረው እና ኃጢአትን ስላላደረገ ብቻ ነው። ኃጢአት የሌለበት ፍጹም ሰው በመሆኑ በችግራችን ሁሉ ሊራራልን የሚችል መልካም ሊቀ ካህናችን ነው (ዕብ 4፡14-16)። ኢየሱስ የምንፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ ስለሚያውቅና የሚያስፈልገንንም ስለሚሰጠን ምንም መካከለኛ (አማላጅ) አያስፈልግም።  ጥያቄ፡-የምናልፍበትን ሐዘን ሁሉ ኢየሱስ እንደሚገነዘብ ማወቃችን በምን በምን መንገድ ያበረታተናል?  ኢየሱስ ታላቁ ሊቀ ካህናችን ስለሆነ አሁን ጊዜ ወስደህ አወድሰው። ማስታወስ ያለብን ኢየሱስ ህልውና ያገኘው መንፈስ ቅዱስ በማርያ ማኅፀን ተአምር በሠራ ጊዜ እንዳልነበር ነው። ኢየሱስ አምላክ ነው። ከእግዚአብሔር አብ ጋር በዘላላማዊ ትስስር እንደ ልጅ ሆኖ ይኖር ነበር። የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ከድንግል ሲወለድ አልነበረም። ሥጋዊ አካልና ሌላ ተፈጥሮ የተሰጠው ከድንል በተወለደ ጊዜ ነበር። የሰውን ተፈጥሮ በመውሰፋ ሰውና አምላክ ማለትም ፍፁም አምላክና ፍፁም ሰው ያለው አካል ሆነ። መንፈስ ቅዱስ በማርያም ማኅፀን ውስጥ ሰብዓዊ ተፈጥሮ ከሰጠው ቅጽበት ጀምሮ በአንድ አካል ውስጥ ፍጹም ሰውና ፍጹም አምላክ ሀነ። ለዘላለም በሁለቱም ተፈጥሮው ይኖራል።  [ማስታወሻ፡- አብዛኛው የክርስቲያን ክፍሎች የሮማ ካቶሊክና የፕርቴስታንት) ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሚለዩት በኢየሱስ ሰብዓዊና መለኮታዊ ተፈጥሮ መረዳት ላይ ነው። የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ኢየሱስ በተቀጻሚ መለኮት ሲሆን ሰብአዊ ተፈጥሮው የመለኮታዊ ተፈጥሮው ጥገኛ ሆኖ ውስንና ጊዜያዊ ነው ብላ ታስተምራለች። ይህ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን በኢየሱስ መለኮታዊ ባሕርይ ላይ እንድታተኩር አድርጓታል። በዚህ አካሄድ ኢየሱስ እውነተኛ ሰውና ላሰው ልጅም የሚራራ መሆኑ ስለማይታይ፥ ሰዎች እነርሱን የበለጠ ወደ ሚገነዘቡና በእግዚአብሔርም ፊት ሊወክሉአቸው ወደሚችሉ፥ እንደ ማርያምና ገብርኤል ወደ መሳሰሉ እማላጆች ፊታቸውን ያዞራሉ። የካቶሊክና የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት ግን ኢየሱስ በአንድ አካል ውስጥ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው መሆኑን ያምናሉ።]  ኢየሱስ በተወለደበት አካባቢ የነበሩ ሰዎችም በመንፈስ ቅዱስ በሚገባ ተነክተዋል። የዮሐንስ እናት ኤልሳቤጥ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ ኢየሱስ ልዩ እንደሚሆን ተነዘበች (ሉቃስ. 1፡41-45)። ዘካርያስም (ሉቃ. 1፡67-69) እንደ ስምዖን (ሉቃስ 2፡25-32)፥ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ነበር። መንፈስ ቅዱስ ሕፃኑ ኢየሱስ የእስራኤል መሢሕና የዓለምም አቶኝ እንደሆነ እንዲገነዘቡ አደረጋቸው።  ለ. መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ አገልግሎት  የኢየሱስ መምጣት መንገድ ጠራጊና የአክለት ልጅ የሆነው መጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎቱን በጀመረበት ጊዜ የሚመጣው መሢሕ ዋና አገልግሎቱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ማጥመቅ እንደሆነ ይናገር ነበር (ማቴ. 3፡11)። እሳት የሚያመለክተው በጰንጠቆስጤ ዕለት በሐዋርያት ላይ የወረደው (የሐዋ. 2፡1-4) እንደ እሳት የተከፋፈሉ ልሳኖችን ሳይሆን ኢየሱስ በእርሱ ባላመኑት ላይ ስለሚያመጣው ፍርድ ነበር። ንስሐ ካልገቡ በስተቀር ታላቅ የእግዚአብሔር ጽኑ ፍርድ እንደሚጠብቃቸው ዮሐንስ አስጠንቅቋቸው ነበርና።  በተጨማሪ መንፈስ ቅዱስን በእነርሱ ላይ የሚያፈስሰው ኢየሱስ እንደሆነ ዮሐንስ ለሕዝቡ ነገራቸው። በዚህም በብሉይ ኪዳን ነቢያት የተነገረለትን አዲሱን የመንፈስ ቅዱስ ዘመን የሚያስጀምረው ኢየሱስ እንደሆነ ዮሐንስ ይናገር ነበር። ስለዚህ መጥምቁ ዮሐንስ በኢየሱስና በመንፈስ ቅዱስ መካከል የሚኖረውን የቅርብ ቁርኝት አስቀድሞ እመልክቷል።  ኢየሱላ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ 30 ዓመት ሞልቶት በሕዝቡ መካከል አገልግሎቱን መስጠት እስከጀመረበት ጊዜ ድረስ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ምን ዓይነት ግንኙነት እንደነበረው ከመጽሐፍ ቅዱስ የምናገኘው ምንም ፍንጭ የለም። አንዳንድ ሰዎች ስለእነዚያ ዓመታት አስቂኝ የሆኑ ታሪኮችን ቢናገሩም መጽሐፍ ቅዱስ ግን በፀጥታ ያልፈዋል። ግልጽ የሆነው ነገር ቢኖር ኢየሱስ በሕዝቡ መካከል አገልግሎቱን በጀመረበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በቅርብ ይተባበረው እንደነበር ነው።  1. መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ላይ የወረደው በሕዝቡ ዘንድ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማስጀመር ነበር፡ ኢየሱስ በሕዝቡ መካከል የሚሰጠው እገልግሎት የተጀመረው በዮሐንስ እጅ በተጠመቀበት ወቅት ነበር። መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን ባጠመቀበት ወቅት መንፈስ ቅዱስ ከሰማይ በርግብ አምሳል በኢየሱስ ላይ ወረደ። ይህ የኢየሱስ «መቀባት» ተብሎ ይጠራል (ሉቃስ 4፡18፤ የሐዋ. 4፡27፤ ዕብ 1፡9 አንብብ)። ይህ የመንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ላይ መውረድና እርሱን መቀባት ኢየሱስ ከዚህ ጊዜ በፈት መንፈስ ቅዱስ አልነበረውም ማለት አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ ለይቶ ይህንን ባይናገርም እንኳ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላው መንፈስ ቅዱስ በማርያም ማኅፀን ውስጥ ታምራዊ ተግባሩን በፈጸመበት ጊዜ ይሆናል። ነገር ግን በብሉይ ኪዳን ዘመን ዳዊት ዘይት ተቀብተ ለንጉሥነት ሊለይ መንፈስ ቅዱስ እንደወረደበት ሁሉ፥ የኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ መቀባትም የተከናወነው ለሕዝባዊ እገልግሎቱ ላመለየት ነበር። ኢየሱስ በሕዝቡ መካከል በሰጠው አገልሎት የመንፈስ ቅዱስ ከእርሱ ጋር መሆን የእግዚአብሔርን ቃል በማወጅ ለድሀች መልካም በማድረግና ባደረጋቸው ተአምራት ይገለጥ ነበር (ኢሳ. 61፡1-2፤ ሉቃስ 4፡18-21)።  2. መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን ሞላው፡- በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ሰው መንፈስ ቅዱስ ተሞላ ልንል በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር ሆነ ማለታችን ነው። ፍጹም ሰው የሆነው ኢየሱስ ያለማቋረጥ በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር ነበር። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ለኢየሱስ በሙላት ሰጠው (ዮሐ 3፡34)። ኢየሱስን የሞላው መንፈስ ቅዱስ ስኢየሱስ ተግባራት ሁሉ ውስጥ በቅርበት ይሳተፍ ነበር።  3. መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን ይመራው ነበር፡- መንፈስ ቅዱስ ከኢየሱስ

መንፈስ ቅዱስ በጌታ ኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ውስጥ Read More »

የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት በወንጌላት

ጥያቄ፡- ዘኁል. 23፡19-20 አንብብ። ሀ) እነዚህ ቁጥሮች እግዚአብሔር ስለሚሰጠን ተስፋዎችና ስለ አፈጻጸማቸው ምን ያስተምሩናል? ለ) ሰዎች ቃል ከገቡላችሁ በኋላ እስከተወሰነ ጊዜ ያልፈጻሙላችሁን ተስፋዎች ዘርዝሩ። እዚህ የተገባላችሁ ተስፋዎች በዘግዩ ጊዜ ምን ተሰማችሁ? ) እግዚአብሔር ተስሩ ከሰጣችሁ በኋላ በፍጥነት የፈጸመላችሁን ዘርዝሩ። መ) ገና ወደፊት የሚፈጽምላችሁ ተስፋዎችስ የትኞቹ ናቸው? እግዚአብሔር እነዚህን ተስፋዎች ሳይፈጽምላችሁ ለረጅም ጊዜ የቆየበት ምክንያት ምን ይመስላችኋል?  አንድ ሰው ተሉ ሊፈጽምልን የገባውን ቃል ሳይፈጽም ቢዘገይ የሚያስከትለውን ተስፋ መቁረጥ ሁላችንም ተለማምደነዋል። አንዳንድ የሚቀርቡን ሰዎች የገቡልንን አንዳንድ ተስፋዎች ፍጹም ሳያሟሉ ሲቀሩ ይህ በልባችን ከፈጠረው ቅሬታ ጋር ዝም ብለን እንኖራለን። በመጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ ሁልጊዜ እንደሚፈጽም ተነግሮናል። እኛ በምንፈልገው ፍጥነት ወይም ባሰብነው መንገድ ባይሆንም እንደሚፈጸሙ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን አለን።  ባለፈው ሳምንት እግዚአብሔር ለሕዝቡ ለእስራኤል ሁላት ቀና የተስፋ ቃሎችን በነቢያቱ አማካይነት እንደሰጠ ተመልክተናል። የመጀመሪያው አንድ ቀን እንደ ጻዊት ያላ በመንፈስ የተሞላ መሪ በእስራኤል ብቻ ሳይሆን በዓለም ሁሉ ላይ ለመንገሥ ይመጣል የሚል ነበር። ሁለተኛው ደግሞ መንፈሱ በሰዎች ሁሉ ውስጥ የሚኖርበት፥ የእግዚአብሔር ሕግጋት በልባቸው የሚጻፍበት፥ ሰዎች ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዳይባዝኑ ከእርሱ የሚማሩበትና እርሱን በመታዘዝ የሚመላለሱበት አዲስ ዘመን በመላው ዓላም እንደሚመጣ እግዚአብሔር ቃል መግባቱ ነው።  እግዚአብሔር እነዚህን የተስፋ ቃሎች ከሰጠ በኋላ አይሁዶች አስቸጋሪ ጊዜ ገጠማቸው። በመጀመሪያ ወደ ባቢሎን ተማርከው ተወሰዱ። አይሁዶች እንደ አንድ ሕዝብ በዓለም ሁሉ ከተበተኑ በኋላ አንዳንዶቹ ተመልሰው በከነዓን መኖር ጀመሩ። ቢሆንም እንደ አንድ ሕዝብ ሁልጊዜ በማያቋርጥ የአሕዛብ መንግሥታት ተጽእኖ ሥር ወደቁ። በመጀመሪያ ባቢሎን፥ ቀጥሎ ፋርስ፥ ቀጥሎም ግሪክ፥ በመጨረሻም ሮም ተፈራርቀው ገዟቸው። የመጨረሻው የብሉይ ኪዳን ነቢይ ሚልክያስ በ400 ዓ.ዓ. ስለ መሢሑ መምጣት የማጠቃለያ አመልካች ትንቢት እስካመጣበት ጊዜ ድረስ የእግዚአብሔር አፍ ሆነው ለሕዝቡ የሚናገሩ ነቢያት ተመናምነው ነበር። ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያስተላልፍ የነበረው ትንቢታዊ መልእክት ቆመ። ከዚያ ጊዜ ወዲህ ለ400 ዓመታት እግዚአብሔር ቃሉን ለሕዝቡ እንዲናገር የላከው ነቢይ አልነበረም። ይህ ዘመን «400 የፀጥታ ዓመታት» በመባል ይታወቃል።  ጊዜው እየረዘመ ሲሄድ የእግዚአብሔር ሕዝብ ስለ መሢሑ መምጣት ሁለት የተለያዩ አቋሞችን ያዙ። ብዙዎቹ እግዚአብሔር የሰጠውን የተስፋ ቃል ለመፈጸም አይችልም ብለው ተስፋ ቆረጡ። እግዚአብሔርን የሚያመልኩት ጥልቅ ትርጉም አግኝተውበት ሳይሆን በዘልማድ ብቻ ሆነ። በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የት ነበር? ስለ መሢሑና ስለ አዲሱ ዘመን የተገቡት ተስፋዎች የሚፈጸሙት መቼ ነበር? ከዚህ በመነሣት እግዚአብሔር ሕዝቡን ትቶታል፥ ከእንግዲህ ወዲህ ለሕዝቡ የሚገደውም አይደለም አሉ።  ጥያቄ፡- ሀ) እግዚአብሔር ለሕይወትህ የገባው ቃል ተሎ በማይፈጸምበት ጊዜ እንደዚህ ዓይነት ስሜት ተሰምቶህ ያውቃልን? ስለ ሁኔታውና እግዚአብሔር በሁኔታው ውስጥ ስላስተማረህ ነገር አብራራ። ለ የገባልህ ቃል በመጨረሻ እንዴት ተፈጸመ?  ሌሎች ግን ስለ አዲሱ ዘመንና ስለ መሢሑ መምጣት የነበራቸው ጉጉት በጣም ጽኑ ነበር። ከፖለቲካ ባርነት ነክ የሚወጡባትን ቀን ናፈቁ። ነገር ግን ከመንፈሳዊ ባርነት ነፃ ወጥተው ሙሉ ለሙሉ እግዚአብሔርን መታዘዝ የሚያስችላቸውን የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ላመታጠቅ የጓጉ ጥቂቶች ብቻ ነበሩ።  ከ400 ዓመታት የፀጥታ ዘመን በኋላ በድንገት የእግዚአብሔር መንፈስ መንቀሳቀስ ጀመረ። መሢሑ የሚነግሥስት የተለሩው ፍጻሜና መንፈስ ቅዱስ ከሰው ልጅ ጋር በሚያደርገው ግንኙነት አዲስ ዘመን የሚያመጣበት ጊዜ ደረሰ። ነገር ግን ይህ የተከናወነው ሰዎች ከጠበቁት በተለየ መንገድ ስለነበረ የመንፈስ ቅዱስን ሥራ ልብ ለማለት አልቻሉም። እንዲያውም የብሉይ ኪዳን ነቢያት የተናገሩለትን መሢሑን ሰቅለው ገደሉት። የእግዚአብሔር መንገዶች ከሰው መንገዶች በጣም የተለዩ ናቸው። ደግሞም የመንፈስ ቅዱስ ሥራ አስቀድመን የምንገምተው አይደለም።  የመሢሑን ታሪክ በምንመለከትባቸው አራት ወንጌላት የመንፈስ ቅዱስን ሥራ በሁለት ዋና ገጽታዎች እንመለከታለን። በመጀመሪያ መንፈስ ቅዱስ ክመሢሑ ከኢየሱስ ጋር የተቆራኘና በአገልግሎቶቹ ሁሉ ውስጥ ዋና ተሳታፊ ነበር። ሁለተኛው መንፈስ ቅዱስ በኋላ ከሚከናወነው የደቀ  መዛሙርት ሥራ ጋርም ጥብቅ ቁርኝት ነበረው። መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ውስጥ የሚኖርበትን ዘመን ኢየሱስ ባያስጀምርም እንኳ ይህ ዘመን እርሱ ደቀ መዛሙርትን በምድር ትቶ ወደ ሰማይ ስሚሄድበት ጊዜ እንደሚሆን በአጽንኦት ተናግሮ ነበር።  ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብብ። ማቴ. 3፡11፤ 3፡16፤12፡18፤ ማር. 1፡12፤ ሉቃስ 1፡35፤ 4፡14፤ ዮሐ 3፡34፤ 15፡26፤ 20፡22፤ የሐዋ. 1፡2፤ 10፡38፤ ሮሜ 8፡11፤ ዕብ. 9፡14፤ 1ኛ ጴጥ. 3፡18። እነዚህ ጥቅሶች በመንፈስ ቅዱስና በኢየሱስ ክርስቶስ መካከል ስላለው ግንኙነት ምን ያስተምሩናል? ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት በወንጌላት Read More »