አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

የደኅንነት ትርጉም፡- ከኃጢአትና ከኃጢአት ውጤቶች ሁሉ መዳን 

This entry is part 65 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ስለ «ደኅንነት» በምንናገርበት ጊዜ ምን ማለታችን ነው? «ደኅንነት» የሚለው ቃል አንድ ሰው ከአንድ ነገር መዳኑን የሚያመለክት ከሆነ፥ እኛ የዳንነው ከምንድን ነው?  ጥያቄ፡- ሀ) በለፈራችሁ የሚገኙ ሰዎችን ስለ ደኅንነት ትርጉም ወይም ምንነት፥ ወይም መዳን ምን ማለት እንደሆነ ብትጠይቋቸው መልሳቸው ምን የሚሆን ይመስላችኋል? ለ) ዛሬውኑ ጥቂት ቆየት ብላችሁ ቢያንስ ለሦስት ሰዎች ይህንኑ ጥያቄ አቅርቡላቸው። ሰዎቹም፡- ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፥ ከሙስሊሙ አማኝና ከወንጌል አማኞች መካከል ሊሆኑ ይችላሉ። ሰዎቹን እግኝታችሁ ከጠየቃችኋቸው በኋላ ተመልሳችሁ፥ እነርሱ የሚሰጧችሁን መልሶች እናንተ ቀደም ብላችሁ ከጻፋችኋቸው አሳቦች ቀን አስፍሩ።  እኔ አንድ ጊዜ ራሱን ክርስቲያን አድርጎ ከሚቆጥር ሰው ጋር እነጋገር ነበር። እናም ሰውዬውን፡- «እስቲ እግዚአብሔር አንተን ስላዳነበት ጊዜ ንገረኝ» አልኩት። እርሱም አንድ ጊዜ የመኪና አደጋ አጋጥሞት ከሞትና ከመቁሰል እግዚአብሔር እንደ ጠበቀው አጫወተኝ። በሌላ ጊዜ ደግሞ ራስዋን ክርስቲያን አድርጋ ከምትቆጥር ወይዘሮ ጋር እነጋገር ነበር። እርሷ ከእግዚአብሔር መዳንን ስላገኘችበት ጊዜ እንድትነግረኝ ጠየቅኋት። እርሷም ወንዝ ልትሻገር ስትል ጅብ ስለ መጣባት፥ ቅዱስ ገብርኤል እንዲያድናት ተማጽናው ጅቡ ሳይበላት ትቷት እንደ ሄደና ቅዱስ ገብርኤል እንዳዳናት ነገረችኝ። በእነዚህ ሁለት ሰዎች አስተሳሰብ «ደኅንነት» ወይም መዳን ማለት፥ በአካል ላይ ጉዳት ወይም ሞት ሳይደርስ መትረፍ ማለት ነው።  ጥያቄ፡- ሀ) ኢያሱ 2፡12-13 አንብቡ። ረዓብ ክን ለመዳን ፈለገች? ለ) መዝሙር 33፡18-19 አንብቡ። እግዚአብሔር የሚፈሩትን ሰዎች ከምን ያድናቸዋል?  መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ጊዜ ከጉዳትና ከሞት ስለ መዳን፥ ማለትም ስለ አካላዊ ደኅንነት ይናገራል። ለምሳሌ ያህል፥ በኢያሱ 2፡12-13 ውስጥ እንደምንመለከተው ረዓብ ኢያሱ ወደ ኢያሪኮ ለላካቸው ሁለቱ ሰላዮች እስራኤላውያን ከተማይቱን በሚይዙበት ጊዜ እርሷንና ቤተሰብዋን ከሞት እንዲያድኑዋቸው ተማጸነቻቸው። ዳዊት በመዝሙር 33፥18-19 ውስጥ እግዚአብሔር የሚፈሩትን ከሞትና ከረሃብ የሚያድን በመሆኑ ውዳሴ አቅርቦለታል። ሆኖም ሰው ከሥጋዊ ወይም ከአካላዊ ሞት በሚድንበት ጊዜ፥ ደኅንነቱ ጊዜያዊ ብቻ ነው። በመጨረሻው ላይ ሰዎች ሁሉ ሟቾች ናቸው (ዕብ. 9፡27)። ምንም እንኳን እግዚአብሔር ሰውን በረሃብ ወይም በመኪና አደጋ ከሚከሰት ሞት ወይም በጅብ ከመበላት ቢያድነውም፣ ከእነዚህ ሁሉ ድኖ የሚቆየው ለተወሰነ ጊዜ ሲሆን፥ በሌሎች ምክንያቶች መሞቱ የማይቀር ነው። ከሥጋ ሞት ከመዳን እጅግ የሚበልጠውና ጠቃሚው ከመንፈስ ሞት መዳን ነው። አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ተለይቶ ሳለ የሥጋ ሞት ቢሞት፥ ሰውዬው ለዘላለም ይሞታል፥ ከእግዚአብሔርም ለዘላለሙ ተለይቶ ይቀራል። ስለዚህ እጅግ ጠቃሚው የደኅንነት ዓይነት ከሥጋዊ ሞት መዳን ሳይሆን፥ ከእግዚአብሔር በመንፈስ ከመለየት መዳን ነው።  በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነው የደኅንነት ዐይነት፥ ከጭቆናና ከድህነት የሚገላግል ደኅንነት እንደሆነ አድርገው ያምናሉ። ለዚህም የሚሰጡት ምክንያት በዓለም ላይ ብዙ ሕዝቦች ድሆችና የሚሠቃዩ መሆናቸውን ነው። ሀብታሞችና ኃይለኞች የሆኑ ሰዎች ብዙ ጊዜ ይጨቁኗቸዋል። ስለዚህ እንዲህ ያሉ ሰዎች ከሚደርስባቸው ጭቆናና ድህነት ሊድኑ ይገባል። አንዳንድ ጊዜ እስራኤላውያን በግብፅ በባርነት ቤት በነበሩበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር ይደርስባቸው የነበረውን ጭቆናና ድህነት ተመልክቶ እንዳዳናቸው በመጥቀስ ይናገራሉ። ከግብፅ ባርነት ነፃ መውጣት (ዘጸአት) የተጨቆኑ ሕዝቦች ሊያገኙት የሚገባቸው መዳን ምሳሌ ነው ይላሉ።  ጥያቄ፡- ሀ) መዝሙር 35፡10 አንብቡ። እግዚአብሔር ለድሆችና ለተቸገሩ ምን| ያደርግላቸዋል? መዝሙር 72፡12-14 አንብቡ። እግዚአብሔር የተቸገሩትን ከምን ያድናቸዋል? ለ) መዝሙር 82፡2-4 አንብቡ። እግዚእብሔር ለደካሞች፥ ለተቸገሩና ለድሆች ምን እንዲደረግላቸው ያዝዛል?  የእኛ አምላክ በድሆችና በተጨቆኑት ጎን የሚቆም እምላክ ነው። መዝሙር 35፡10 ውስጥ እንዲህ ይላል፡- «ችግረኛን ከሚቀማው እጅ፥ ችግረኛንና ድሀውንም ከሚነጥቀው እጅ ታድነዋለህ።» እንዲሁም በመዝሙር 72፡12-14 ባለው ክፍል፡- «ምስኪኖችን ከሞት ያድናል፥ ሕይወታቸውንም ከግፍና ከአስጨናቂዎች ያድናል» ይላል። በመዝሙር 82፡2-4 ውስጥ፡ ደካሞችን፥ ምስኪኖችንና ድሆችን ኃጢአተኞች ከሚያደርሱባቸው ጭቆና እንድንታደጋቸውና መብታቸውን እንድናስከብር እግዚአብሔር ያዝዛል።  መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ሕዝብ ድሆችንና የተጨቆኑትን እንዲረዱ ያዝዛል። ለተበደሉት ፍትሕን ለማምጣት መጣር አለብን። የድሆችንና የሚሠቃዩ ሰዎችን ችግር ለማቃለል መሞከር ይገባናል። ሆኖም በዚህ ምድር ላይ የፍትሕ መጓደልና ድኅነት ሊኖር የቻለው በኃጢአት ምክንያት ነው። የግለሰቦች ኃጢአት የፍትሕ መጓደልንና ድኅነትን ያስከትላል። የፍትሕ መጉደልና የድኅነት ችግር መፍትሔ ሊያገኝ የሚችለው የጨቋኞች ልብና ሕይወት ሲለወጥ ብቻ ነው። ከእግዚአብሔር መራቃቸው ሲቀርና ሌሎችን መጨቆናቸው ሊገታ ከዚያም ለፍትሕ መቃናት መሥራት ሲጀምሩ ያን ጊዜ መፍትሔ ያገኛል። ከእግዚአብሔር ጋር ሊታረቁና ነገሮች ትክክል ሲሆኑ ብቻ ነው በዚህ ምድር ላይ ትክክለኛ ድርጊት የሚፈጽሙት።  ነገር ግን ክርስቶስ ወደዚህ ምድር ዳግም ተመልሶ እስከሚመጣ ድረስ፥ ሌሎችን በመጨቆን የፍትሕ መጓደልንና ድህነትን የሚያመጡ ኃጢአተኞች የሆኑ ሰዎች ምን ጊዜም ይኖራሉ። ክርስቶስ ፍጹም የሆነ የጽድቅ መንግሥቱን ለማቋቋም ወደ ምድር በሚመለስበት ጊዜ ብቻ እግዚአብሔር የፍትሕ መጓደልንና ድህነትን ያስወግዳል። ድሆችና የተጨቆኑ ሁሉ ካሉበት አሰቃቂ ኑሮ ተላቅቀው ደኅንነትን የሚያገኙት ወደ እግዚአብሔር የጽድቅ መንግሥት ለመግባት እርግጠኞች ሲሆኑ ብቻ ነው። ስለዚህ ወደፊት የሚመጣው ፍጹም የሆነው የእግዚአብሔር መንግሥት ተሳታፊዎች ለመሆን፥ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ይኖርባቸዋል። ከድህነትና ከፍትሕ እጦት ለመዳን ያለው ፍላጎት የላቀ ነው። ነገር ግን ከዚህ የሚበልጠው ከእግዚአብሔር ፊት ሰዎችን ከሚለየው ከኃጢአት መዳን ነው። በመሆኑም፥ ሰዎች ከኃጢአታቸው ከዳኑ በኋላ ብቻ፥ የፍትሕ መጓደልንና ድህነትን ለማስወገድ ሊሠሩ ይችላሉ። እንዲሁም ሰዎች በምድር ላይ ሆነው የእግዚአብሔር ፍጹማዊ መንግሥት ተካፋዮች ሊሆኑ የሚችሉት ከኃጢአታቸው ከዳኑ በኋላ ብቻ ነው።  ጥያቄ፦ ሀ) ዮሐንስ 3፡16-17 አንብቡ። እግዚአብሔር ልጁን ወደዚህ ዓለም የላከው ለምንድን ነው (ቁጥር 17? ለ) በልጁ ለሚያምን ምን ይሆንለታል (ቁጥር 16)?  ጥያቄ፡- ሀ) ዮሐንስ 11፡25-26 አንብቡ። በኢየሱስ ለሚያምኑት ምን ይሆንላቸዋል?  ጥያቄ፡- ሀ) ሮሜ 1፡16-17 አንብቡ። ሰዎች የሚድኑበት የእግዚአብሔር ኃይል ምንድን ነው (ቁጥር 16)? ለ) በወንጌል ውስጥ ምን ተገለጠ (ቁጥር 17)?  መጽሐፍ ቅዱስ አበክሮ እንደሚገልጸው፥ የሰው ልጆች ትልቁ ችግር ኃጢአት ነው። ኃጢአት ሰዎችን ከእግዚአብሔርና ሰዎችን ከሰዎች ለይቶአቸዋል። ኃጢአት ሕይወትን አሰቃቂ የሚያደርጉትን ሞትን፥ ጥፋትንና ጭቆናን አምጥቷል። በሞት የሚመጣው ችግር ሰዎች የኃጢአትን ተግባር መፈጸማቸው ብቻ አይደለም። ባለፈው ሳምንት እንደተመለከትነው፥ ሰዎች ሁሉ በኃጢአት ተወልደዋል። እንደዚሁም ሰዎች ሁሉ በተበላሸና በኃጢአት በተበከለ ባሕርይ ተወልደዋል። አእምሮአችን በኃጢአት ጨልሟል።  ምኞታችንም በኃጢአት ረክሷል። ፈቃዳችንም የኃጢአት ባሪያ ሆኖአል። በኃጢአት ስለተወለድን ከእግዚአብሔር ጋር የነበረንን ግንኙነት ለማደስና እንደ ቀድሞው ለማድረግ ምንም መልካም ተግባር ለማድረግ አቅም የለንም። ይህ በመሆኑ ሰዎች የሚያስፈልጋቸው፥ ከኃጢአትና እርሱ ከሚያስከትላቸው የከፉ ችግሮች ሊታደጋቸው የሚችል መድኅን ማግኘት ነው።  መጽሐፍ ቅዱስ ትልቅ ትኩረት ወይም ክብደት የሚሰጠው ይህን ለመሰለው ደኅንነት ነው። በዮሐንስ 3፡17 ውስጥ ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ እግዚአብሔር ዓለሙን ከኃጢአት ለማዳን ልጁን ወደ ምድር እንደ ላከው ነግሮታል። ይህ ታዲያ ምን ዓይነት ደኅንነት ነው? ከዚህ ቀደም ብሎ በተጠቀሰው በዮሐንስ 3፡16 ውስጥ ኢየሱስ ይህ ደኅንነት የዘላለም ሕይወት እንደሆነ ገልጾአል። የሥጋ፥ የመንፈስና ዘላለማዊ ሞት ሁሉም የኃጢአት ውጤቶች ናቸው። ሥጋዊ፥ መንፈሳዊና የዘላለም ሕይወት ደግሞ ልጁ የሚያመጣቸው የደኅንነት ውጤቶች ናቸው። በልጁ የሚያምኑ ሁሉ መንፈሳዊ ሕይወት ይኖራቸዋል። በዚህም ከእግዚአብሔር ጋር ባላቸው ግንኙነትና አንድነት ደግሞ ይተሳሰራሉ። በምንም አኳኋን ዳግም በመንፈሳቸው አይሞቱም (ዮሐ 11፡26)። በልጁ የሚያምኑ ሁሉ ሥጋዊና ዘላለማዊ ሕይወት ይኖራቸዋል። ቢሞቱም እንኳ ከእግዚአብሔር ጋር በአንድነት ለመኖር በዳግም ትንሣኤ ይነሣሉ (ዮሐ 11፡25)። ኢየሱስ የሚያመጣው ደኅንነት፥ በእርሱ ለሚያምኑት ሁሉ የዘላለም ሕይወትን በመዋጀት፥ በኃጢአት ምክንያት ለተከሰተው ችግር መፍትሔውን ይሰጣል።  ሐዋርያው ጳውሎስም የኢየሱስ ደኅንነት፥ ከኃጢአት መዳን እንደሆነ ያስተምራል። በሮሜ 1፡16 ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ ሲናገር፥ ወንጌል የሚያምኑትን ሁሉ ለማዳን የእግዚአብሔር ኃይል ነው። ታዲያ ወንጌል ምንን ያመጣል? የሚቀጥለው ቁጥር (ሮሜ 1፡17) ጽድቅን ያመጣል ይላል። ደኅንነት ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቀናል። እንደዚሁም ደኅንነት፥ ሰዎች ከእግዚአብሔር ለተለዩበት ችግር መፍትሔውን ይሰጣል።  ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ደኅንነት በብዙ አኳኋን የሚናገር ቢሆንም፥ ትልቅ አጽንኦት የሰጠው ኢየሱስ በሕይወቱ ወደዚህ ዓለም ስላመጣው ከኃጢአት መዳን፥ ደግሞም ስለ ሞትና ትንሣኤው ነው። ኃጢአት የሰው ልጅ መሠረታዊ ችግር ስለሆነ፥ በኢየሱስ የተገኘው የኃጢአት ደኅንነት፥ ማንም ሰው ከሚያገኘው

የደኅንነት ትርጉም፡- ከኃጢአትና ከኃጢአት ውጤቶች ሁሉ መዳን  Read More »

ይቅርታ የማይደረግበት ኃጢአት ምንድን ነው? 

This entry is part 64 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

አንዳንድ ሰዎች ይቅርታ የማይደረግበት አንድ ኃጢአት አለ ብለው ይፈራሉ። ስለዚህ ይህን ኃጢአት ብናደርግ ደኅንነትን እናጣለን፥ ይቅርታም አይደረግልንም ብለው ይጨነቃሉ። ታዲያ ይህ «ይቅርታ የማይደረግለት ኃጢአት» ተብዬው ምንድን ነው?  ጥያቄ፡- ማቴ. 2፡22-32 አንብብ። ሀ) ፈሪሳዊያን ኢየሱስን በሰይጣን ኃይል አጋንንትን ያወጣል ማለታቸው በምን ምክንያት ሞኝነት ሆኖ ተቀጠረባቸው? (ቁ 26) ለ) ኢየሱስ አጋንንትን በእግዚአብሔር ኃይል የሚያወጣ ከሆነ፥ ይህ ምንን ያረጋግጣል? (ቁ 28)  በማቴ. 12፡22-32 ውስጥ ኢየሱስ ጋኔን ያደረበት ዓይነ ሥውርና ዱላ ሰው መፈወሱ ተጽፎአል (ቁ 22)። ይህን ተአምር የተመለከቱ ሰዎች ድርጊቱ መሢሐዊ ድርጊት መሆኑን ወዲያውኑ አስተዋሉ (ቁ 23)። እንደ መዝ (146)፡8፤ ኢሳ. 29፡18፤ 38፡5-6 ካሉት የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች በመነሣት መሢሑ እንዲህ ያሉ ተአምራትን ይፈጽማል ብለው ይጠባበቁ እንደ ነበር ተጽፎአል። ስለዚህ «ይህ ሰው ኢየሱስ በእውነት መሢሑ የዳዊት ልጅ ይሆንን?» ሲሉ በአድናቆት ጠየቁ። ፈሪሳውያን ግን ስለ ኢየሱስ ኃይል ሌላ የሚሉት ነገር ነበራቸው። በብዔል ዜቡል ኃይል ይጠቀማል ሲሉ ከሰሱት፥ ብዔል ዜቡል የሰይጣን ሌላ ስሙ ነው (ቁ 24)።  ኢየሱስ ግን ፈሪሳውያን የመሠረቱበትን ክስ በሦስት መንገዶች መለሰ። በመጀመሪያ፥ ሰይጣን የራሱን ሥራ የሚያበላሽ ሞኝ አይደለም በማለት ትክክለኛ ያልሆነ ክሳቸውን ውድቅ አደረገው። ሰይጣን የሰውን ሕይወት በውስጡ በሚኖረው አጋንንት የሚያጠፋ ከሆነ አጋንንቱ ከሰውዬው እንዲወጣና ሰውዬውም ሕይወቱ ዳግም ታድሶ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት እንዲኖረው ፈጽሞ አያደርግም። ይህ ደግሞ በሰውዬው ሕይወት ውስጥ የሚፈጽመውን ክፉ ሥራ የሚገታና መንግሥቱን የሚያፈርስበት ነው። ሰይጣን ደግሞ የራሱ የሆነ አጋንንትን አባሮ በማውጣት በፍጹም መንግሥቱን አያፈርስም አላቸው (ቁ 25-26)። ኢየሱስ በመጀመሪያ ለፈሪሳውያን የመለሰላቸው መልስ ሰይጣን ራሱን ስለማያጠፋ ክሳቸው ሐሰት መሆኑን የሚያመለክት ነው።  የኢየሱስ ሁለተኛው መልስ እርሱ አጋንንትን ያወጣበት የኃይሉ ታላቅነት፥ ያደረገው ታምራት ከእግዚአብሔር ዘንድ እንጂ ከሰይጣን አለመሆኑን በማረጋገጥ ክሳቸው ከእውነት የራቀ መሆኑን የሚያሳይ ነበር። እርሱ አጋንንትን ያወጣበትን ኃይል፥ እንዳንድ አይሁዳውያን ከሚፈጽሙት አጋንንትን የማስወጣት ሙከራ ጋር አመዛዝኖታል (ቁ. 27)፡፡ እነዚህ አጋንንትን እናስወጣለን የሚሉ አይሁዳውያን እንደተጠቀሱት የአስቄዋ ሰባት ልጆች ዓይነት ነበሩ (በሐዋ. 19፡13-16)። እነዚህ ሰዎች አጋንንትን በማውጣት ረገድ በመጠኑም ቢሆን የተሳካላቸው ይመስል ነበር። ግን ውጤታቸው የተወሰነና ጊዜያዊ ነበር። ይህ ሊሆን የቻለው እውነተኛ የሆነ መንፈሳዊ ኃይል ስላልነበረባቸው ነው። ከአይሁዶች ይልቅ የኢየሱስ አጋንንት አወጣጥ የሰይጣን መንግሥት በማፈራረስ ረገድ የበረታ ነበር። ታዲያ ፈሪሳውያንና ሕዝቡ የእነርሱ ወገን የሆኑ አጋንንትን እናወጣለን ሲሉ በሰይጣን ኃይል ትጠቀማላችሁ ብለው አይከስሱም ነበር። ግን ተአምራቶቹ በኃይል የተሞሉና የሰይጣንን መንግሥት ደምሳሽ የሆነ ኢየሱስ በሰይጣን ኃይል ትጠቀማለህ ብለው መከሰሳቸው እንዴት ሞኝነት ነበር? ለነገሩ ኢየሱስ አጋንንትን ያወጣ የነበረው በእግዚአብሔር ኃይል ነበር።  ፈሪሳውያን ተአምራቶቹን ከሰይጣን ኃይል ጋር ማያያዛቸው እንዴት ጅልነት (ሞኝነት) እንደ ነበረ የኢየሱስ የመጀመሪያዎቹ ሁለት መልሶች አረጋግጠዋል። በቁጥር 28 ውስጥ በሚገኘው በሦስተኛው መልሱ ፈሪሳውያን ተአምሩን ካዩ በኋላ ወደ ምን ዓይነት ድምዳሜ መድረስ እንደ ነበረባቸው አሳይቷቸዋል። እርሱ በተለየ ሁኔታ በመንፈስ ቅዱስ የተቀባ መሆኑን ተረድተው፥ «የእግዚአብሔር መንግሥት» እንደ መጣላቸው መቀበል ነበረባቸው። ማለት እርሱ የእስራኤል መሢሕ መሆኑን መገንዘብ ይገባቸው ነበር። ፈሪሳውያን ይህንን ማወቅ ለምን ነበረባቸው? ኢሳ 11፡1-5፤ 42፡1 እና 61፡1፤ እነዚህ ክፍሎች ሁሉ መሢሑ በልዩ ሁኔታ በእግዚአብሔር መንፈስ የተቀባ መሆኑን ይገልጻሉ። ኢየሱስ አጋንንትን የማስወጣት ከፍተኛ ኃይሉ፥ ይህን ልዩ ቅባት ለመቀባቱ ምስክር መሆኑን ተናግሮአል። በሌላ አነጋገር፥ አጋንንትን ሲያስወጣ፥ እርሱም መሢሑ፥ የእግዚአብሔር ንጉሥና የእግዚአብሔርን መንግሥት ወደ ምድር የሚያመጣ መሆኑን ማስመስከሩ በቁጥር 29 ውስጥ፥ አጋንንትን ማውጣቱ የመሢሕነቱ ማረጋገጫ ለመሆኑ ምሳሌ ያቀርባል።  አንድ ሌባ ወደ ኃይለኛ ሰው ቤት ገብቶ ንብረቱን ለመዝረፍ ያለው ብቸኛ መንገድ አስቀድሞ ኃይለኛውን ሰው ማሰር ነው ይላል። ኢየሱስ ያን ሲል ሰይጣንን በኃይለኛው ሰው ማስመሰሉ ነው። የሰይጣን አጋንንት ተሸነፉ  ማለት ሰይጣን ራሱ ተሸንፎ ታሰረ፥ ስለታሠረም አጋንንቱን ሊረዳቸው አይችልም ማለት ነው። ሰይጣን በኢየሱስ ከተሸነፈ፥ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መሢሕ መሆኑ ነው። ለፈሪሳውያን የሰጠው ሦስተኛው የኢየሱስ መልስ አጋንንትን ያወጣበት ልዩ የሆነ የኃይል አጠቃቀም ሁኔታ እርሱ እግዚአብሔር ተስፋ የሰጠበት መሢሕ መሆኑን እንደሚመሰክር ነበር።  እነዚህ ፈሪሳውያን የእግዚአብሔርን መሢሕና የእግዚአብሔርን መንግሥት የሚጠባበቁ መሆናቸውን የሚናገሩ ሰዎች ነበሩ። መሢሑ ሊመጣ እንደሚቀበሉት ያወሱ ነበር። ነገር ግን ስማቴ. 12፡25-29 ውስጥ እንደተጻፈው ኢየሱስ «እኔ መሢሕ መሆኔን በልባችሁ ታውቃላችሁ ይላቸው ነበር። የብሉይ ኪዳንንም ትንቢቶች ታውቃላችሁ። ግልጽ ምስክር ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችንም በዓይናችሁ አይታችኋል። በአእምሮአችሁም እኔ መሢሕ መሆኔን አውቃችሁ ደምድማችኋል። ነገር ግን ይህን ሁሉ እያወቃችሁ አልተቀበላችሁኝም። እኔ መሢሕ መሆኔን እያወቃችሁ አልተቀበላችሁኝም፥ ሥራዩንም የሰይጣን ሥራ አደረጋችሁት» አላቸው። በዚሁ ምዕራፍ ከቁጥር 30-32 ባሉት ቁጥሮች ኢየሱስ ንግግሩን ያጠቃልላል። በልቡ ኢየሱስ ማን እንደሆነ እያወቀ የማይቀበለው የእርሱ ጠላት ነው (ቁ. 30)። ኢየሱስ መሢሕ መሆኑን በግልጽ የሚያረጋግጡ ሥራዎች መንፈስ ቅዱስ በሕይወቱ ውስጥ ሲፈጽም እነዚህ ሥራዎቹም መሢሕ መሆኑን እንደሚመሰክሩ የተረዳ፥ ነገር ግን አሁንም እርሱን በመሢሕነቱ የማይቀበል፥ እርሱ ይቅር አይባልም (ቁ 31)። እናም ኢየሱስ መሢሕ መሆኑን እያወቀ፥ እርሱ ከሰይጣን ነው ብሎ የሚከስውም ይቅርታ ውጭ ነው (ቁ 32)። እንዲህ ያለው ሰው ልቡን ያደነደነ ሰው በመሆኑ ወደ ክርስቶስ መጥቶ እንደ መሢሕ፣ እንደ መድኅንና ጌታ አድርጎ ሊቀበለው አይችልም።  ስለዚህ በማቴ. 12፡31 ውስጥ፥ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የስድብ ቃል የተናገረ ይቅር አይባልም የተባለው ምን ማለት ነው? ይህ እንግዲህ መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ብቻ አይደለም። እግዚአብሔርን መናቅም ብቻ አይደለም። ወንጌልንም ሰምቶ ክርስቶስን አለመቀበልም ብቻ አይደለም። እነዚህ ሁሉ የከፉ ተግባራት ስለሆኑ እግዚአብሔር ይቀጣቸዋል። ነገር ግን ማቴዎስ በምዕራፍ 12፡31 መንፈስ ቅዱስን ስለ መሳደብ ሲናገር ስለ እነዚህ ጥፋቶች መናገሩ አይደለም። ከጥቅሱ ጭብጥ እንደምንረዳው መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ማለት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ በልዩ ሁኔታ የተቀባ መሢሕና አዳኝ መሆኑን እያወቁ ነገር ግን ልብን አደንድኖ ሆን ብሎ እርሱን አለመቀበልና ሥራውንም መቃወም ነው። ፈሪሳውያን ይህን ባደረጉ ጊዜ፥ ኢየሱስን ላለመቀበል ልባቸውን አጠነከሩ። ስለዚህም የእርሱን ይቅርታ ሳይቀበሉ ቀሩ።  ዛሬስ ቢሆን አንድ ሰው መንፈስ ቅዱስን በመሳደብ ይህንኑ ኃጢአት ሊሠራ ይችላል? መልሱ አዎን እና አይደለምም ይሆናል። ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሠራቸውን ታምራት ማንም ሰው ዛሬ በትክክል በግንባር እንደነበረው ሁኔታ ሊያይ አይችልም። ስለሆነም ማንም ሰው ይህን ፈሪሳውያን የሠሩትን ኃጢአት ራሱን መልሶ መሥራት አይችልም። በሌላ በኩል ግን የማያምኑ ሰዎች አሁንም ቢሆን በጣም ተመሳሳይ ኃጢአትን ሊፈጽሙ ይችላሉ። ዛሬም ቢሆን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ስለመሆኑና የዓለም መድኃኒት ስለመሆኑ ብዙ ምልክቶችን ያሳያል። አሁንም የእርሱ መንፈስ በመጽሐፍ ቅዱስ በተሰበከው ቃል፥ በአማኞች ሕይወትና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተደረጉ ታምራት አማካይነት እየሠራ ነው። የማያምን ሰው እነዚህን የኢየሱስ ሥራዎች ተመልክቶ እርሱ በእውነት ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣ ክርስቶስ የዓለም አዳኝ መሆኑን አውቆ ነገር ግን ችላ ቢለውና ባይቀበለው፥ ይህ ሰው ወደ ክርስቶስ ዘንድ በሚያድን እምነት ሊመጣ እስከማይችል ልቡን ያደነድናል።  እንግዲህ በማቴዎስ ምዕራፍ 12 ውስጥ መንፈስ ቅዱስን በመሳደብ ምክንያት ይቅር የማይባለው ኃጢአት፥ በዚህ ረገድ በማያምኑ ሰዎች የሚፈጸም ኃጢአት ነው እንጂ በእውነት ዳግም በተወለዱ ክርስቲያኖች የሚፈጸም በደል አይደለም። ስለሆነም ኢየሱስ ማን እንደሆነ እያወቁ በአንጻሩ እርሱን ያለመቀበል ኃጢአት ነው። ይቅርታ የማይደረግለት ኃጢአት ነው የተባለበት ምክንያት አንድ ሰው ክርስቶስ ማን እንደሆነ ካወቀ በኋላ ችላ ቢል፥ ልቡን ፍጹም ስለሚያደነድን እርሱን እንደ አዳኙ ለመቀበል በምንም ዓይነት አይመርጥም ማለት ነው። አንድ ሰው ሌላው ሰው ይህን ኃጢአት መፈጸሙን ሊያውቅ ይችላል? ኢየሱስ ፈሪሳውያን ይህን ኃጢአት መፈጸማቸውን አውቆ ነበር። ነገር ግን ዛሬ አንድ ሰው ሌላው ሰው ይህን ኃጢአት ለመፈጸሙ እርግጠኛ ሊሆን አይችልም። በሰብአዊና በውስን ግንዛቤአችን የሌላውን ሰው ልብና አእምሮ ማወቅ አንችልም። አንድ ሰው የክርስቶስን ማንነት ፍጹም ተገንዝቦ ሲያበቃ፥ ነገር ግን ከናካቴው ችላ በማለት ሳይቀበለው መቅረቱን ጠንቅቀን ማወቅ ፈጽሞ

ይቅርታ የማይደረግበት ኃጢአት ምንድን ነው?  Read More »

አንዳንዱ ኃጢአት ከሌላው የባሰ ነውን? 

This entry is part 63 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

አንዳንድ ክርስቲያኖች ኃጢአትን የምር መጥፎ የሆኑና እምብዛም መጥፎ ያይደሉ በማለት ይከፋፍሏቸዋል። በዚሁ ሁኔታ አንዳንዶቹ ኃጢአቶች የእግዚአብሔር ካባድ ቅጣት እንደሚያስፈልጋቸው ሌች ደግሞ ይህን ያህል የማያስቀጡ አድርገው ይመለከቷቸዋል። ይህ ብቻ አይደለም፥ አንዳንደ ኃጢአቶች ደኅንነትን የሚያሳጡዋቸው ሆነው ሲታዩዋቸው፥ ሌሎች የኃጢአት ዓይነቶች ደግሞ ደኅንነትን የማያሳጡዋቸው መስለዉ ይታዩዋቸዋል። ይሁንና አንዳንድ ኃጢአቶች ከሌሎቹ ይልቅ የባሱ ናቸው?  2.1 ኃጢአቶች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እኩል በደለኞች ያደርጉናል።  ጥያቄ፡– ገላ 3፡10 እና ያዕ. 2፡10 እንብብ። ከትእዛዛቱ መካከል አንዱን እንኳን በማይታዘዙት ላይ ምን ደረሰባቸው?  መጽሐፍ ቅዱስ ኃጢአቶች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እኩል በደለኞች እንደሚያደርጉን ያስተምረናል። አንድ ኃጢአት ምንም ያህል ትንሽ ቢሆንም የኃጢአትን ቅጣት ያመጣብናል። ገላ. 3፡10 ከሕጎች አንዱን ያፈረሰ ሰው የተረገመ ነው ይላል። ያዕ. 2፡10 ደግሞ ከሕግ ትእዛዛት አንዲቱን ያጎደለ መላውን ያፈረሰ በደለኛ ሆኖ ይቆጠራል ይላል። በዚህ አኳኋን ኃጢአት ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በደለኛ ያደርገናል።  2.2 አንዳንድ ኃጢአቶች ከሌሎቹ ይልቅ ከእግዚአብሔርና ከሌሎችም ሰዎች ጋር ያሉንን ግንኙነቶች በበለጠ ይጎዱዋቸዋል።  ጥያቄ፡- ሕዝ 8፡6 አንብብ። እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን ምን ታያለህ አለው? ጥያቄ፡- ዮሐ 19፡11 አንብብ። ኢየሱስ ለጴንጤናዊው ጲላጦስ አሳልፈው ስለ ሰጡት ምን አለ?  ጥያቄ፡- ማቴ. 23፡23 አንብብ። ኢየሱስ ፍርድን፥ ምሕረትን እና ታማኝነትን ምን ብሎ ጠራ?  ጥያቄ፡- ሉቃስ 10፡10 አንብብ። የትኞቹ ከተሞች የከፋ ቅጣትን ይቀበላሉ? ለምን?  ጥያቄ፡- ሉቃስ 12፡42-48 አንብብ። ሀ) የጌታውን ፈቃድ እያወቀ በማይፈጽም አገልጋይ ላይ ምን ይደርስበታል? ለ) የጌታውን ፈቃድ በሚያውቀውና በሚያደርገው እገልጋይ ላይላ ምን ይደርስበታል?  ጥያቄ፡- ያዕ. 3፡1 አንብብ። የእግዚአብሔርን ቃል በሚያስተምሩት ላይ ምን ይደርሳል?  ኃጢአቶች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በደለኛች የሚያደርጉን ሲሆን፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስንመለከት አንዳንድ ኃጢአቶች ከሌሎቹ ብሰው የሚታዩበት ሁኔታ ያለ ይመስላል። እግዚአብሔር ለሕዝቅኤል፥ ካየው የበለጠ እጅግ አስነዋሪ የሆነ ነገር ገና እንደሚያይ ነግሮታል (ሕዝ. 8፡6)። ኢየሱስም ለጴንጤናዊው ጲላጦስ አሳልፈው ስለ ሰጡት ሲናገር፥ አሳልፈው የሰጡት ከጲላጦስ የባለ ኃጢአት እንደሚያደርጉ አስጠንቅቆአቸዋል (ዮሐ 19፡1)። እንዲሁም፥ ከሕግ ውስጥ ፍርድ፥ ምሕረትና ታማኝነት ዋና ቁም ነገሮች ናቸው ብሏል (ማቴ. 23፡23)። በዚህም ኢየሱስ፥ አንዳንድ ኃጢአቶችን ከሌሎች የበለጠ የሚከብዱ መሆናቸውን ሊያስገነዝበን አንዳንዶቹ የሕግ ትእዛዛትም ከሌሎቹ የተለዩ ናቸው። በሉቃስ 10፡10-5 ውስጥ እንደተጻፈው የቅፍርናሆምንና የቤተ ሳይዳን ከተሞች ከሰዶም፥ ከጢሮስና ከሊዶን ከተሞች የበለጠ ቅጣት እንደሚደርስባቸው ኢየሱስ ፈርዶባቸዋል። የበለጠ ቅጣትን የሚቀበሉበትም ምክንያት ከሌሎቹ ከተሞች ይልቅ እነዚህኞቹ በኢየሱስና በሠራቸው ተአምራት ውስጥ እግዚአብሔርን በላቀ መገለጥ ስላዩት ነው። ከእግዚአብሔር ታላቅ መገለጥ ሲመጣ እያዩ ኃጢአት የሚሠሩ ሰዎች በአነስተኛ መገለጥ ውስጥ ሆነው ኃጢአት ከሚሠሩት የበለጠ በደል ይፈጽማሉ። በሉቃስ 12፡42-48 ውስጥ ኢየሱስ በምሳሌ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እያወቁ የማያደርጉት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ካለማወቃቸው የተነሣ ከማያደርጉት የበለጠ ቅጣት እንደሚደርስባቸው ገልጾአል። እያወቁ በድፍረት ኃጢአት የሚሠሩ ሰዎች ምንም እንኳን ኃጢአት እንደ ፈጸሙ ቢገነዘቡም የባሰ ኃጢአት ያደርጋሉ።  እንደዚሁም አንዳንድ ኃጢአቶች የእግዚአብሔርን ስም የሚያጎድፉ ወይም ራሳችንና ሌሎች አማኞችን ጭምር የሚጎዱ ከሆኑ ከሌሎች ይልቅ ክብደት የሚሰጣቸው ወይም የባሱ ሆነው የሚቆጠሩ ይመስላሉ።  ጥያቄ፡- አንዳንድ ኃጢአቶች በእግዚአብሔር፥ በራሳችንና በሌሎች ሰዎች ላይ ትልቅ ጉዳትን እንዴት እንደሚያመጡ ምሳሌ ጠቅሳችሁ ጻፉ።  አንዳንድ የኃጢአት ዓይነቶች ከሌሎች በበለጠ እግዚአብሔርንና ስሙን፥ እኛንና ሌሎችን ይጎዳሉ። ለምሳሌ ያህል፥ አንድ ሰው የጎረቤቱን መኪና ቢመኝ የእርሱ ያልሆነውን ተመኝቷል እና በደለኛ ይሆናል። ነገር ግን ያንን መኪና ቢሰርቅ የባሰ ኃጢአት ይሠራል። ምክንያቱም በእግዚአብሔር ስም ላይ ትልቁ ሐፍረትን በጎረቤቱም ላይ ጉዳትን ያደርሳልና ነው። እንዲሁም አንድ ሰው ሚስቱ ያልሆነችውን ሴት ለግብረ ሥጋ ቢመኛት፥ ኃጢአት ስለሚሆንበት በእግዚአብሔር ዘንድ በደለኛ ይሆናል። ነገር ግን ከሴትዮዋ ጋር የተረጋገጠ ግብረ ሥጋ ግንኙነት ቢያደርግ፥ የባሰ ኃጢአት ያደርጋል። ምክንያቱም እርስዋን አሳስቶ ኃጢአት እንድትሠራ ከማድረጉም በላይ፥ የእግዚአብሔርንም ስም የሚያረክስ ተግባር ፈጽሟልና ነው። አግብቶ ከሆነ ደግሞ ሚስቱን፥ ልጆቹንና ትዳሩን ይጎዳል። ሴትዮዋም ያገባች ከሆነች ደግሞ ባለቤትዋን፣ ልጆቿንና ጋብቻዋን ትጎዳለች። እርሱም ሆነ ሴትዮዋ ሁለቱም ያላገቡ ከሆኑ ይህ ተግባር የወደፊት የጋብቻ ዕድላቸውን ያበላሻል። ጳውሎስ የግብረ ሥጋ ኃጢአት የሰውን አካል የሚያረክስ ከመሆኑም በላይ ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረንን አንድነት የሚያበላሽ መሆኑን ሰፋ አድርጎ አስተምሯል (1ኛ ቆሮ. 6፡15-18)። ስለዚህ አንዳንዶቹ ኃጢአቶች የእግዚአብሔርን ስም፥ ኃጢአት የሚሠራውን ሰውና ሌሎች ሰዎችንም ስለሚጎዱ ከሌሎች ኃጢአቶች የባሱ ናቸው።  በተጨማሪም፥ እግዚአብሔር በተለይ ክርስቲያን መሪዎችን በኃጢአታቸው ይጠይቃቸዋል። ያዕቆብ 3፡1 የእግዚአብሔርን ቃል የሚያስተምሩ መምህራን የባሰ ፍርድ እንደሚቀበሉ ያስገነዝባል። አንድ ክርስቲያን የሆነ መሪ ኃጢአት በሚሠራበት ጊዜ በተለይ የእግዚአብሔር ስም ይሰደባል። ስለዚህ የክርስቲያን መሪ ኃጢአት ከሌላው ክርስቲያን ኃጢአት የበለጠ ነው። ሁሉም ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት በደለኛ ያደርገናል። ሁሉም ኃጢአት ደግሞ ይቅር ሊባል ይችላል። አንዳንድ ኃጢአቶችን ሰዎች በእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚያስጠይቁ እያወቁ ይፈጽሟቸዋል። ስለሆነም አንዳንዶቹ ኃጢአቶች በእግዚአብሔር፥ በራሳችንና በሌሎች ሰዎች ላይ ጉዳትን ያደርሳሉ። በተለይም በክርስቲያን መሪዎች የሚፈጸሙ ኃጢአቶች በእግዚአብሔር ስም ላይ ኀፍረትን ያመጣሉ። እግዚአብሔር እነዚህን ኃጢአቶች ከሌሎች የባሱ ሆነው ስለሚያያቸው በዚያኑ መጠን የባሰ ቅጣት ይሰጣል። ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

አንዳንዱ ኃጢአት ከሌላው የባሰ ነውን?  Read More »

ሕፃናት በእርግጥ ኃጢአትን ለመሥራት ከደረሱበት ጊዜ በፊት የኃጢአት በደለኞች ይባላሉ? 

This entry is part 62 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

የተወሰኑ ሰዎች ልጆች ኃጢአትን ለመሥራት እስካልደረሱ ድረስ የኃጢአት በደል አለባቸው አይባልም ይላሉ። ግን መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ልጆች የኃጢአት በደል ምን ይላል?  ጥያቄ፡- መዝ (51)፡5 አንብቡ። ሀ) ዳዊት ከመቼ ጀምሮ ኃጢአተኛ ተባለ? ላ) መዝ. (58)፡3 አንብብ። ለ) ክፉዎች ከመቼ ጀምረው ይሳሳታሉ?  ጥያቄ፡- ሮሜ 5፡14 አንብብ። ከአዳም እስከ ሙሴ ድረስ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ባላፈረሱት ላይ ሳይቀር ምን ነግሦ ነበር? \ጥያቄ፡- 1ኛ ሳሙ 12፡23 አንብብ። ጳዊት ከቤርሳቤሕ የወለደው ልጅ መች ሞተ? በዚያን ጊዜ ዳዊት የት እንደሚያገኘው ተናገረ?  ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተማርናቸው ትምህርቶች ውስጥ እንደተከታተልነው ሰዎች ሁሉ በኃጢአት ስለ ተወለዱ፥ በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች ናቸው። ዳዊትም ገና በእናቱ ማኅፀን ውስጥ እያለ ኃጢአተኛ እንደ ነበረ ይናገራል። እንዲሁም ክፉዎች ተለዩ፣ ደግሞም ከማኅፀን ጀምር ሳቱ ይላል። እንዲህም ማለት እግዚአብሔር ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ ኃጢአተኞች አድርጎ ይመለከታቸዋል ማለት ነው። በሮሜ ምዕራፍ 5 ውስጥ ከአዳም የተነሣ፥ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች እንደሆኑና የኃጢአት ቅጣት የሆነው ሞት እንደ ተበየነባቸው ያስረዳል። ሮሜ 5፡14 እንደ አዳም ሕግን በመተላለፍ ኃጢአት ያልሠሩት እንኳ ሳይቀሩ ክአዳም እስከ ሙሴ ባሉት ዘመናት የነበሩ ብዙ ሰዎች ሞተዋል ይላል። በአዳም ኃጢአት ምክንያት እነርሱም በደለኞች ስለሆኑ ሞቱ። አንዳንድ ሕፃናትም ስለሚሞቱ እነርሱም ቢሆኑ የአዳም ውርስ ኃጢአት ቅጣት እየተቀበሉ እንደሆነ መደምደም እንችላለን። ምንም እንኳን በእርግጥ ኃጢአት የፈጸሙ ሳይሆኑም፥ ከኃጢአት ጋር ስለ ተወለዱና ይህም በደል ስለሆነ ይሞታሉ። ምንም እንኳን ሕፃናት ኃጢአትን ለመሥራት ከመድረሳቸው በፊት በአዳም ምክንያት ኃጢአት አለባቸው ቢባልም፣ የሚሞቱ ሕፃናት ወደ ሲኦል ወይም ገሃነም ይወርዳሉ ማለትም አይደለም። ከቤርሳቤሕ የወለደው ልጁ በሞተ ጊዜ ዳዊት ተመልሶ ወደ ሕይወት እንደማይመጣና ከሞት በኋላ እንደሚያገኘው ገልቆአል (2ኛ ሳሙ. 12፡23)። ዳዊት ይህን ማለቱ አንድ ቀን እንደሚሞትና ወደ ሙታን ስፍራ እንደሚሄድ አይደለም። ነገር ን፥ “እኔም ወደ እርሱ ዘንድ እሄዳለሁ» አለ። ዳዊት ልጁን በእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚገናኘው ተስፋ ነበረው። ከዚህ በሕፃንነታቸው የሚሞቱ የአማኞች ልጆች ወደ መንግሥተ ሰማይ እንደሚሄዱ አሳብ ልናገኝ እንችላለን። ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስ ሕፃናት ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማይ ይሄዳሉ ብሎ በግልጽ ባይነግረንም፥ ሕፃናት ወደ መንግሥተ ሰማይ የሚገቡ ይመስላል። ሆኖም ግን፣ ከአዳም በደል የተነሣ ሕፃናት ከኃጢአት ጋር ይወለዳሉ። ሕፃናት ሲሞቱ እግዚአብሔር የክርስቶስን ደም የማዳን ኃይል በመጠቀም ከበደላቸው አንጽቶ ከኃጢአት ዕዳ ይቤዣቸዋል። ሕፃናቱ ስለ ተጠመቁ ወይም ስለ ተገረዙ እግዚአብሔር አያድናቸውም። እንዲሁም ወላጆቻቸው መልካም ሥራ ስላደረጉ እግዚአብሔር አያድናቸውም። እግዚአብሔር የሚያድናቸው ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ለኃጢአታቸው ቤዛ ስለሆናቸውና በምሕረቱና በጸጋውም ነው። ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

ሕፃናት በእርግጥ ኃጢአትን ለመሥራት ከደረሱበት ጊዜ በፊት የኃጢአት በደለኞች ይባላሉ?  Read More »

ኃጢአት በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ 

This entry is part 61 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ትናንትና ሁሉም ሰው ኃጢአት እንደ ሠራ ተገንዝበን ነበር። ታዲያ ይህ ክርስቲያኖችን ሁሉ ያጠቃልላል? ክርስቲያኖችስ ቢሆኑ ከኃጢአት ነህ ናቸው ወይስ አሁንም ቢሆን ኃጢአት ያለበት ተግባርን እየፈጸሙ ናቸው? ዛሬ በኢየሱስ ክርስቶስ በሚያምኑ ሰዎች ሕይወት ውስጥ ስለሚሆነው ኃጢአት እንማራለን።  1. ክርስቲያኖች ከኃጢአት ተግባር ነፃ አይደሉም።  አንዳንድ ክርስቲያኖች በክርስቶስ የሚያምኑ እውነተኛ ክርስቲያኖች ከእንግዲህ ወዲያ ኃጢአት አይሠሩም ብለው ያምናሉ። ሌሎች ደግሞ ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ልምምድ ውስጥ ስለሚገቡ በመቀጠል ኃጢአት አይሠሩም ይላሉ። ክርስቲያኖች ከኃጢአት ነፃ ስለ መሆናቸውም ሆነ ነፃ ስላለመሆናቸው ወይም ነፃ ለመሆን ስለ መቻል አለመቻላቸው መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?  ጥያቄ፡- 1ኛ ዮሐንስ 1፡8፥10 አንብብ። ሀ) ሐዋርያው ኃጢአት አልሠራንም፥ ወይም ኃጢአት የለብንም ስለሚሉት ምን ይላል? ለ) 1ኛ ዮሐንስ 2፡12-14 } 2 5፡13 አንብብ። የዮሐንስ አንባቢያን እማኞች ወይስ የማያምኑ ሰዎች ነበሩ?  ጥያቄ፡– ሮሜ 7፡14-20 አንብብ። ሀ) ጳውሎላ በቁጥር 14 ራሱን እንዴት ይገልጻል? ለ) ይህን ሲል ምን ማለቱ ይመስላችኋል? ሐህ ከቁጥር 5-20 ድረስ ባለው ጳውሎስ ምን ማድረግ እንደ ፈለገ ነው የሚናገረው? መ) ጳውሎስ በእውነት ስለሚያደርገው ነገር ምን አለ? ሠ) ሐዋርያው ላደርገው አልፈልግም ያለው ምንን ነበር? ረ) ጳውሎስ በእርግጥ አላደርገውም ያለው ምን ነበር?  ጥያቄ፡– በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደ ምሳሌ የሚጠቀሱ ኃጢአት የሠሩ አማኞችን ታስታውሳላችሁ? ቢያንስ ሁለት ምሳሌዎች ጻፉ።  ሐዋርያው በ1ኛ ዮሐንስ መልእክቱን የጻፈው በኢየሱስ ክርስቶስ አማኞች ለሆኑት ነው። በ1ኛ ዮሐንስ 2፡12-14 የጻፈው ኃጢአታቸው ይቅር ለተባለላቸውና አብን ለሚያውቁ ልጆች እንዲሁም አብን ለሚያውቁ አባቶችና ክፉውን ላሸነፉ ወጣት ወንዶች ነው። በ1ኛ ዮሐንስ 3፡2 ደግሞ የእግዚአብሔር ልጆች ለሆኑት እንደ ጻፈ ይናገራል። እንዲሁም በ1ኛ ዮሐንስ 58 ውስጥ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለሚያምኑትና የዘላለምን ሕይወት ላገኙት መጻፉን ይናገራል። የ1ኛ ዮሐንስ መልእክት በግልጽ የተጻፈው ለሚያምኑ ክርስቲያኖች ነበር። በ1ኛ ዮሐንስ 1፡8 ማንኛቸውም ኃጢአት የለብንም ቢሉ ራሳቸውን እንደሚያታልሉና እውነትም እንደሌለባቸው አንባቢዎቹን ያስጠነቅቃቸዋል። ደግሞም በ1ኛ ዮሐንስ 1፡10 አንባቢዎቹ ኃጢአት የለብንም ቢሉ እግዚአብሔርን ውሸታም እንደሚያደርጉት ይገልጻል። እነዚህ ጥቅሶች ክርስቲያኖችም ቢሆኑ ኃጢአት መሥራታቸውን እንደሚቀጥሉ በግልጽ ያመለክታሉ። ስለዚህ ክርስቲያኖችም ጭምር ከኃጢአት ነፃ አይደሉም።  በሳል መንፈሳዊ ክርስቲያኖችም እንኳን ኃጢአትን ለመፈጸም ይፈተናሉ፤ አንዳንዴም ተሸንፈው ኃጢአት የሆኑ ተግባራትን ይፈጽማሉ። በሮሜ 7፡14 20 ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ ራሱ ክርስቲያን ከሆነ በኋላ እንኳን ምን ያህል ከኃጢአት ጋር ይታገል እንደ ነበረ ይገልጻል። (ርማ 77 ውስጥ ጳውሎስ አማኝ ከመሆኑ በፊት የነበረውን ስለ ራሱ ይገልጻል። በቁጥር 14 ደግሞ አማኝ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን ይናገራል። በርሜ 14 በየጊዜው ያጋጥመው ከነበረ ኃጢአት ጋር ያደርግ ስለነበረው ብርቱ ትል፥ ጠንካራ በሆኑ ሐረጎች ተጠቅሞ ይገልጻል። እንዲህ ይላል፥ «የኃጢአት ባሪያ ልሆን ተሸጥሁ።» እነዚህ ቃላት እንዲህ ተብለው ሊተረጎሙ ይችላሉ «አሁንም ወደ ኋላ ተመልሼ የኃጢአት ባሪያ ልሆን ራሰን እሸጣለሁ።» ምንም እንኳን እግዚአብሔር ጳውሎስ የኃጢአት ባሪያ እንዳይሆን ቢቤዠውም (ሮሜ 6፡5-23) ኃጢአትን ለመሥራት የተፈተነባቸው ጊዜያት ነበሩ። እንዲያውም ወደ የኃጢአት ባርነት ገበያ የተመለሰበትም ጊዜ ነበር። እናም በሮሜ 7፡5-19 በውስጡ የነበረው የአሮጌው የኃጢአት ተፈጥሮ ፍላጎትና በክርስቶስ ካመነ በኋላ በተለወጠው አዲሱ ሰው ፍላጎት መካከል ስላጋጠመው ጦርነት መግለጹን ይቀጥላል። በክርስቶስም በማመኑ ምክንያት የሚጣላቸው ነገሮች (ቁ15)፥ ማድረግም የማይፈልጋቸው ኃጢአታዊ ነገሮች ነበሩ (ቁ16)፥ ይሁን እንጂ እነዚሁኑ ነገሮች ሲሠራ ራሱን ያገኛል (ቁ15)። በሌላ በኩል እንደ ክርስቶስ ተከታይ በእውነት ሊያደርጋቸው ይፈልግ የነበረ መልካም ነገሮች ነበሩት። ይሁን እንጂ እነዚህንም ለመፈጸም የሚያዳግተው ጊዜም ነበር (ቁ.18-19)። ሥጋው ወይም አሮጌውና ኃጢአታዊው ተፈጥሮው (ቁ17፥20) እየፈተነው በክርስቶስ ያገኛቸውን አዳዲስ ፍላጎቶች መታገሉን ቀጠለ (ቁ17)።  ጳውሎስ ለዘመናት ከኖሩት ጠንካራና ኃይለኛ ከነበሩ አማኞች መካከል አንዱና በሳል አማኝ ነበር። ስለዚህም ለብዙ ዓመታት በክርስትና ሕይወትና በአገልግሎት ተግባር ላይ ከቆየ በኋላ የሮሜን መልእክት ጽፎአል። ሆኖም ግን በዚህን ጊዜም እንኳን ኃጢአትን ለመሥራት ይፈተንና አንዳንድ ጊዜም ኃጢአት ይሠራ ነበር። በሮሜ 7 ውስጥ ያለው የጳውሎስ ገጠመኝ ሁሉም ክርስቲያኖች ኃጢአትን እንደሚሠሩ ለእኛ ጠቃሚ ማስታወሻ ነው።  ከዚህም በስተቀር መጽሐፍ ቅዱስ ኃጢአትን የሠሩ ብዙ አማኞችን በምሳሌነት አካትቶአል። ምናልባትም ጎላ ጎላ ያሉት ምሳሌዎች እነ ዳዊትና ጴጥሮስ ሊሆኑ ይችላሉ። እግዚአብሔር ዳዊትን «እንደ ልቤ የሆነ ሰው» ብሎ ጠርቶት ነበር (1ኛ ሳሙኤል 13፡14)። ነገር ግን የማመንዘርንና ነፍስ የመግደልን ኃጢአት ፈጸመ። ጴጥሮስ ከኢየሱስ ሦስት የቅርብ ደቀ መዛሙርት መካከል አንዱ የነበረና ታዳጊዋን ቤተ ክርስቲያን እንዲጠብቅ ኢየሱስ አደራ የጣለበት ነው (ዮሐንስ 21፡15-17)። ይሁን እንጂ ጰጥርስ ሦስት ጊዜ ካደው። እንዲሁም እጅግ በጣም ጠንካሮችና የበሰሉ አማኞች አልፎ አልፎ በኃጢአት ውስጥ እንደ ወደቁ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንገነዘባለን።  አማኞች ሁሉ በሕይወታቸው ውስጥ አንዳንድ ጊዜ ኃጢአት መሥራታቸው እውነት ከሆነ ደኅንነትን ያጣሉ ማለት ነው? ይህ ካልሆነ አማኞች ኃጢአት በሚያደርጉበት ጊዜ ምን ይደርስባቸዋል?  2. ክርስቲያኖች ኃጢአት በሚሠሩበት ጊዜ ምን ይደርስባቸዋል?  2.1 ክርስቲያኖች ኃጢአትን በሚሠሩበት ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ያላቸው ሕጋዊ ደረጃቸው ዝቅ አይልም፥ አይለወጥም። ዘላለማዊ ደኅንነታቸውም አያጡም።  ጥያቄ፡- ሮማ 8፡1 አንብብ፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ ለሆኑት የተረጋገጠላቸው ምንድን ነው?  ጥያቄ፡- 1ኛ ዮሐንስ 2፡1 አንብብ። ኃጢአትን የሚሠሩ ክርስቲያኖች በመንግሥተ ሰማይ ምን አላቸው?  ጥያቄ፡- ሮሜ 6፡23 እና ኤፌሶን 2፡8-9 አንብብ። ሀ) ደኅንነት እንዴት ይገለጻል? ለህ ደኅንነት እንዴት ይገኛል?  ወደ ኋላ ላይ በክርስቶስ የሚያምኑ እውነተኛ ክርስቲያኖች ደኅንነትን ያጡ ወይም አያጡ እንደሆነ ስለሚነሣው ጥያቄ እናጠናለን። በዚህ ትምህርት ላይ ግን ኃጢአት አማኞች ደኅንነትን እንዲያጡ ሊያደርግ እንደማይችል ደህና አድርጎ መገንዘብ ይጠቅማል። ሮሜ 6፡3 እና ኤፌሶን 2፡8-9 ደኅንነት በግለሰቦች መልካም ሕይወት ላይ የተመሠረተ አይደለም። እንዲሁም ደኅንነት ኃጢአት መሥራትን ለአቆሙ የሚሰጥ አይደለም። ደኅንነት በክርስቲያኖች ውስጥ ሊቆይ የሚችለው እነርሱ መልካሞች ስለሆኑ ወይም ኃጢአት መሥራት ስለአቆሙም አይደለም። ደኅንነት በክርስቶስ ላይ በሚኖረን እምነት እግዚአብሔር የሚቸረን ነፃ ስጦታ ነው። ሮሜ 8፡1 በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ጳውሎስ በርሜ 7 ላይ እንደገለጸው ከኃጢአት ጋር እየታገሉ ላሉትም ቢሆን እንኳ ኩነኔ የለባቸውም ይላል። በ1ኛ ዮሐንስ 2፡1 ላይ ማንም ኃጢአት ቢሠራ፥ በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን ይላል። ክርስቲያኖች ኃጢአት ቢሠሩ ስለ እነርሱ አሁንም የሚሟገት ኢየሱስ አለ። በሕጋዊ መንገድ አሁንም ቢሆን ልጆቹ ናቸው።  በክርስቶስ የሚያምኑ ክርስቲያኖች ኃጢአት በሚፈጽሙበት ጊዜ የእግዚአብሔር ልጆች ሆነው የሚቆዩ ከሆነ ኃጢአታቸው ክብደት የለውም ማለት ነው? እንዲህ አይደለም። ክርስቲያኖች ኃጢአትን በሚሠሩበት ጊዜ ደኅንነትን ባያጡም ከባድ ሁኔታ ያጋጥማቸዋል። ኃጢአት በሚፈጽሙበት ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ባላቸው ግንኙነት ላይ ምን ይደርሳል?  2.2 ክርስቲያኖች ኃጢአት ሲሠሩ ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት ይቋረጣል፥ ሕይወታቸው ይበላሻል፥ ወደ ንስሐ እንዲመጡም የእግዚአብሔርን ቅጣት ይቀበላሉ።  ጥያቄ፡- 1ኛ ዮሐ 1፡6 አንብብ። አንድ ሰው በጨለማ ውስጥ ቢሄድ ይህ ጥቅስ ምን ይደርስበታል ሊል ያስተምራል?  ጥያቄ፡- መዝ (38)፡1-4 አንብብ። ጻዊት በሠራው ኃጢአት ስለደረሰበት ሁኔታ ምን አለ?  ጥያቄ፡- ዕብ 12፡6፥9-11 አንብብ። ሀ) እግዚአብሔር ለሚወዳቸውና እንይ ልጆቹም ለሚቆጥራቸው ምን ያደርግላቸዋል? ለ) እግዚአብሔር በምን ምክንያት ይገሥጸናል? ሐ) የእግዚአብሔር ሣጹ ውጤት ምንድን ነው?  ጥያቄ፡- ዮሐ 15፡4 አንብብ። አማኞች በሕይወታቸው ውስጥ ፍሬ ለማፍራት ምን ማድረግ ይኖርባቸዋል?  ጥያቄ፡- ዮሐ 8፡34 አንብብ። ኃጢአትን በሚሠሩ ሁሉ ላይ ምን ይደርሳል?  ኃጢአትን የሚሠሩ አማኞች ደኅንነታቸውን እያጡም። ሆኖም ሌሎች አስቸጋሪና የሚያሠቃዩ ሁኔታዎች ይደርሱባቸዋል። በመጀመሪያ፥ ክርስቲያኖች ኃጢአትን ቢፈጽሙ፥ ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸው አንድነትና ግንኙነት ይቋረጣል። እግዚአብሔር ሰዎች ከእርሱ ጋር ግንኙነትና ቅርበት እንዲኖራቸውና በእርሱም ደስ እንዲሰኙ አድርጎ ፈጥሯቸዋል። ባለፈው ሳምንት እንደ ተከታተልነው አዳምና ሔዋን ኃጢአት እንደ ሠሩ ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸው ደስ የሚል ግንኙነት ተቋረጠ። ሰዎች በክርስቶስ በሚያምኑበት ጊዜ፥ ከእግዚአብሔር ጋር አዲስና አስደናቂ የሆነ ግንኙነት ይጀምራሉ። እግዚአብሔርንም ማወቅና በእርሱም መደሰት ይጀምራሉ። ግን ኃጢአት በሚሠሩበት ጊዜ፥ ያን ግንኙነት ያጣሉ። 1ኛ ዮሐ 1፡6 ሲናገር፥

ኃጢአት በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ  Read More »

ሁሉም ሰው የኃጢአት ተግባርን ፈጽሟል 

This entry is part 60 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ባለፈው ሳምንት ትምህርት፥ ሁሉም ሰዎች ከአዳም ኃጢአት የተነሣ በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች መሆናቸውን ተመልክተናል። ትናንትና ደግሞ በአዳም ኃጢአት ምክንያት ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች ሆነውና የኃጢአትን ተፈጥር ተላብሰው የተወለዱ መሆናቸውን ተገንዝበናል። ከዚሁ ከእቶም ኃጢአት የተነሣ ሰዎች በደለኛች እንደ ሆኑ ወይም ከኃጢአት ጋር እንደ ተወለዱ አንዳንድ ሰዎች አምነው አይቀበሉም። ለምሳሌ ያህል፥ ሙስሊሞች ኃጢአተኞች ሆነን መወለዳችንን ወይም መበደላችንን አምነው አይቀበሉም። ሌሎች ሰዎች ደግሞ አዳም በበደለ የእኛ ሥቃይን መቀበል ተገቢ አይደለም ባይ ናቸው። እንዲሁም አዳም በፈጸመው ኃጢአት ምክንያት እኛ የኃጢአት በደለኞች ወይም የኃጢአት ተፈጥሮ ለብሳችሁ ከኃጢአት ጋር የተወለዳችሁ ናችሁ መባላችን አግባብ አይደለም ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስገነዝበው ከሆነ ግን የኃጢአት በደለኞች ሆነንና በኃጢአት መወለዳችን ብቻ ሳይሆን፥ ሁላችንም ኃጢአተኞች እንደሆንን ያስተምራል። በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች፣ የኃጢአት ባለዕዳዎችና የኃጢአት ባሪያዎች ሊያደርጉን የሚችሉ ብዙ የኃጢአት ተግባራትን ፈጽመናል። በዛሬው ትምህርታችን ሰዎች ሁሉ የኃጢአት ተግባራትን ስለ መፈጸማቸው እንማራለን።  1. ሰዎች ሁሉ ኃጢአትን የፈጸሙ መሆናቸውን ብሉይ ኪዳን ያስተምራል።  ጥያቄ፡– 1ኛ ነገሥት 8፡46 አንብብ። እንደ ንጉሥ ሰሎሞን አባባል ስንት ሰዎች ኃጢአትን ይሠራሉ?  ጥያቄ፡- መጽሐፈ መክብብ 7፡20 አንብብ። ስንት ሰዎች ኃጢአትን ላይሠሩ ሁልጊዜ መልካም ተግባርን ይፈጽማሉ።  ጥያቄ፡- መዝሙር (143)፡2 አንብብ። በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ማን ነው?  ጥያቄ፡- መዝሙር 14፡1-3 አንብብ። ሀ) በጎ ነገርን ማን ያደርጋል? ለህ እግዚአብሔርንስ ማን ይሻል? ሐ) ማን ዐመፀ፥ ማንስ ረከሰ?  ጥያቄ፡- መዝሙር (3)፡1-3 እንብብ፡ እግዚአብሔር ከመዝሙር 4፡1-3 ጋር ተመሳሳይ የሆነ ቃል በምን ምክንያት የደገመ ይ«መስልሃል?  ብሉይ ኪዳን በግልጽ እንደሚያስረዳው ሰዎች ሁሉ ኃጢአት በመሥራታቸው ምክንያት በእግዚአብሔር ፊት ራሳቸውን ክፉዎች አድርገዋል። በ1ኛ ነገሥት 8 ላይ ንጉሥ ሰሎሞን የኢየሩሳሌምን ቤተ መቅደስ ሲመርቅ ባሰማው ታላቅ አሉት ሰዎች ሁሉ ኃጢአት መሥራታቸውን ተናግሯል። በተጨማሪም በመክብብ 7፡20 ላይ ንጉሥ ሰሎሞን በምድር ላይ ሁልጊዜ መልካምን የሚሠራ ኃጢአትንም የማያደርግ ጻድቅ አይገኝም ይላል። እንዲሁም ዳዊት በመዝሙር (148)፡2፥ አንድም ጻድቅ የለም ይላል። በመዝሙር 14፡1-3 ሲናገር መልካም ነገርን የሚያደርግ የለም ይላል። ለመሆኑ ዳዊት ይህን ሲል ምን ማለቱ ነበር? ይህን ሊል ማንም ሰው ሌሎች መልካም የሚሉትን ተግባር ሊፈጽም አይችልም ማለቱ ነበር? አይደለም፥ እንዲህ አላለም። ሰዎች ብዙውን ጊዜ የሚወዱዋቸውንና ሌሎችንም ሰዎች የሚረዱ መልካም ተግባራትን ያከናውናሉ። ዳዊት ለመናገር የፈለገው አሳብ ከቁጥር 2-3 ተገልጾአል። እግዚአብሔርን የሚሻ ሰው የለም። ሰዎች ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊታቸውን አዙረዋል፥ ከዚህም የተነሣ ራሳቸውን አርክሰዋል። በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር በጎ ነው ብሎ የተቀበለውን ተግባር የፈጸመ ማንም የለም። በእግዚአብሔር ፊት ሊያቀርበው የሚችል በጎ ተግባር የፈጸመ ማንም አይገኝም። መዝሙር (53)፡1-3 ከመዝሙር 14፡1-3 የቃል በቃል ድግግሞሽ ያህል በጣም የተቀራረበ መልእክት ነው። እግዚአብሔር እነዚህን ቃላት የደጋገመበት ምክንያት ሰዎች የእግዚአብሔርን ዒላማ በመሳታቸው፥ ራሳቸውን በእግዚአብሔር ፊት እንዳረከሱና በደለኞች እንደሆኑ በግልጽ እንድንገነዘብ ለማድረግ ነው።  ምናልባትም ሰዎች ሁሉ በግላቸው ኃጢአት ስለ መሥራታቸው የሚያስረዳ እጅግ በጣም ኃይል ያለው ጥቅስ በሮሜ 3፡9-20 ያለው ነው።  ጥያቄ፡- ሮሜ 3፡9 እንብብ። ቀደም ባሉት በሮማ መልእክት ምዕራፎች ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ለተናገረው ቃል ማጠቃለያ ምንድን ነው?  ጥያቄ፡- ሮሜ 3፡10–20 አንብብ። ጳውሎስ በእነዚህ ከብሉይ ኪዳን በተጠቀሱ ቁጥሮች ላይ የተናገራቸውን ሁሉ በአንድ ዓረፍተ ነገር አጠቃልለህ ጻፍ።  ጥያቄ፡– ሮሜ 3፡10-12 አንብብ። ሀ) በሥራው በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛ ሆኖ ሊቆም የሚችል ማን ነው? ለ) እግዚአብሔርን ለማወቅና ደስ ለማሰኘት ከልብ የሚሻ ማን አለ? ሐ) እግዚአብሔርን ለማስደሰት በቂ መልካም ሥራ የሠራ ማን አለ?  ጥያቄ፡– ሮሜ 3፡13-14 አንብብ። ሐዋርያው ጳውሎስ እዚህ ላይ የገለጻቸውን የአፍ ኃጢአቶችን በዝርዝር ጻፍ።  ጥያቄ፡- መዝሙር 5፡4-10 አንብብ። ሮሜ 3፡13 ከዚህ ምንባብ ላይ የተወሰደ ነው። ሐሰትን በሚናገሩ በክፉዎች ላይ ምን ይደርሳል?  ጥያቄ፡– መዝሙር (140)፡1–3 አንብብ። እንደዚህ ጥቅስ አገላለጽ ሰዎች «ምላሳቸው እንደ መርዛም እባብ ነው» ሊባል ምን ማለት ነው?  ጥያቄ፡- ሮሜ 3፡15-18 አንብብ። እነዚህ ጥቅሶች በምን በምን ኃጢአቶች በደለኞች ያደርጉናል?  በሮሜ 3፡9 ላይ ጳውሎስ በሮሜ ውስጥ በሌሎች ምዕራፎች ላይ የተናገረውን ሁሉም ሰው አይሁድ ይሁን አሕዛብ ኃጢአት በመሥራታቸው በኃጢአት ኃይልና ቅጣት ሥር ናቸው በማለት ያጠቃልላል። አሕዛብ በልባቸውና በሕሊናቸው የእግዚአብሔርን እውነት ያወቁ ቢሆንም ግን ችላ ብለውት ወደ ኃጢአት ገብተዋል። አይሁዶች ምንም እንኳን የእግዚአብሔርን ቃል የመልማት ዕድል ቢኖራቸውም፥ እነርሱም ቃሉን ችላ በማለታቸውና ባለመታዘዛቸው ምክንያት ወደ ኃጢአት ገብተዋል።  ጳውሎስ ሰዎች ሁሉ በየግላቸው ኃጢአተኞች መሆናቸውን ለማረጋገጥ ወደ ብሉይ ኪዳን ያመራል። ሁሉም ሰው ኃጢአት ለመሥራቱ ማስረጃ ለማቅረብ የተለያዩ ጥቅሶችን ያቀርባል። እነዚህ ጥቅሶች 2 ነጥቦችን ያስተጋባሉ፡- ሀ ሁሉም ኃጢአት ሠርተዋል 2) ኃጢአት ገዳይ የሆነ ክፉ ውጤትን ያመጣል።  ጳውሎስ፥ በሮሜ 3፡10-12 ባለው ክፍል መዝሙር 14፡1-3 እና መዝሙር (53)፡1-3 ያለውን ይጠቅሳል። ቀደም ሲል እነዚህን ጥቅሶች በመጀመሪያው በብሉይ ኪዳን ጽንሰ አሳባቸው አኳያ ተመልክተናቸዋል። እነርሱም ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ፍጹም እንዳልሆነ፥ በእውነት እርሱን የሚፈልግ እንደሌለ ያስገነዝቡናል። በብሉይ ኪዳን ውስጥ እንዳነበብነው፥ እነዚህ ጥቅሶች ሰዎች መልካም የተባለ ሥራ ከቶ አይሠሩም አይሉም፡ የሚሉት ሰዎች የሚሠሩት መልካም ሥራ በእግዚአብሔር ፊት እነርሱን መልካም ለማድረግ ብቁ ሆነው አይገኙም ነው። ብዙ ሰዎች መልካም ሥራዎችን እንደሚፈጽሙ የታወቀ ነው። ግን እነዚያ መልካም ሥራዎች በእግዚአብሔር ፊት ቀርበው ሊመዘኑ ጻድቃን ሊያደርጓቸው አይችሉም። እነዚህን መልካም ነገሮች ቢሠሩም ከኃጢአታቸው የተነሣ በእግዚአብሔር ፊት የረከሱና በደለኞች ናቸው። እኛም ብንሆን መልካም ነገርችን ብንሠራም እንኳ ከኃጢአታችን የተነሣ አሁንም ቢሆን መጥፎ ሰዎች ነን። አሁንም ኃጢአተኛች ነን ማለት በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች ነን ማለት ነው።  በቁጥር 13 ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ መዝሙር 5፡9 እና መዝሙር (140)3ን ይጠቅሳል። እንዲሁም በቁጥር 14፥ መዝሙር 10፡7ን ይጠቅሳል። በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ ከአፍ ኃጢአት የተነሣ ሁሉም በደለኞች ናቸው ይላል። «ጉርርአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው» ሲል፣ ይህን ማለቱ ነው። ሰዎች ሁሉ ወደ ሞት የሚያደርሷቸው ኃጢአቶች በአፋቸው አማካይነት ይፈጽማሉ። እዚህ ላይ ስለ ምን ዓይነት ኃጢአቶች ይናገራል? የሚናገረው ስለ ውሸት ስለ መራገምና ስለ ምሬት ነው። ውሸት ማለት እውነት ያልሆነ ነገር መናገር ወይም ማድረግ ነው። እንዲሁም ትንሽም ቢሆን እውነቱን ነገር ለእኛ በሚጠቅመን ዘዴ ለውጥ አድርገን መገኘት ራሱ መዋሸት ነው። መዝሙር 5፡9 የሚዋሹና የሚያጭበረብሩ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በደለኛች ስለሆኑ በፊቱ ሊቆሙ አይችሉም ይላል። ስለዚህ እንዲህ ያሉ ሰዎች ይጠፋሉ፥ ይወገዳሉም። መራገም፥ ንጹሕ ያልሆኑ ነገርችን መናገር፥ ወይም የእግዚአብሔርን ለም ክብር በሌለበትና በግድየለሽነት ሁኔታ ማንግት ነው። ምሬት ደሞ ሌላውን ሰው የሚጎዳ ነገር በቀጥታ ለራሱ ወይም ከበስተኋላው መናገር ወይም ማድረግ ነው። በመዝሙር (140)፡1-3 ላይ መዝሙረኛው ሲናገር፥ የእባብ መርዝ በከንፈሩ ያለው ሰሙነ በሌሎች ላይ ዓመፅንና ጉዳትን የሚያስከትሉ ነገሮችን የሚናገር ሰው መሆኑን ይገልጻል።  ብዙ ሰዎች፥ ከአፍ የሚወጡ እንደ መዋሸት፥ መራገምና ስለ ሌሎች ሰዎች የምራት ታላን መናገር ያሉ ነገሮችን ማድረሳ መጥፎ ኃጢአቶች እንዳልሆኑ አድርገው ያስባሉ። እንዲያውም ብዙ ክርስቲያኖች እነዚህን 5 የመሳሰሉ ኃጢአቶችን እየፈጸሙ፥ ምንም የከፋ ነገር እንዳላደረጉ ያስባሉ። ጳውሎስ ቀን እኛ ሁላችን ኃጢአተኞች ነን፥ ኃጢአታችንም በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች አድርጎናል ሲል የጠቀሰው እነዚህን የመጀመሪያ ኃጢአተች አድርጎ ነው።  ከቁጥር 5-7 ባለው ክፍል ጳውሎስ ኢሳይያስ 5፡7-8ን ይጠቅሳል። በዚህም የሰዎች ኃጢአት የሌሎችን ሰላም እንደሚያናውጥ ይናገራል። በጣም ጥቂት ሰዎች ሌላውን ሰው ይገድሉ ይሆናል፥ ግን ሌሎችን ያልጠላ አንድም ሰው አይገኝም። በሌሎች ላይ ክፉ ተግባራትን በመፈጸም ወይም በመናገር ሕይወታቸው እንዲጎሳቆል ያላደረገ ማንም ሰው የለም። እንዲሁም ሁሉም ሰው የሌሎች ሰዎችን ሰላም አደፍርሷል። እነዚህም ጥቅሶች ሰዎች ከኃጢአታቸው የተነሣ በከፋ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ከሚገልጸው የኢሳይያስ የትንቢት መጽሐፍ አጠቃላይ ምዕራፍ አንዱ ክፍል ናቸው። ስለሆነም ሰዎች ከኃጢአተኝነታቸው የተነሣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ውሸታሞች፥ የታወሩ፥ ሙታን፥ ጠበኞች፥ ከእግዚአብሔርም የተለዩና የእግዚአብሔር ቁጣ የሚጠብቃቸው ተብለዋል።

ሁሉም ሰው የኃጢአት ተግባርን ፈጽሟል  Read More »

የደኅንነት አስፈላጊነት- ሰዎች ኃጢአተኛ በሆነ ባሕርይ ተወለዱ ማለት ምን ማለት ነው?

This entry is part 56 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ባለፈው ሳምንት ለለ ኃጢአትና በክርስቶስ የሚሰጠው ደኅንነት በምን ምክንያት እንደሚያስፈልገን የሁለት ሳምንት ትምህርት መጀመራችን ትዝ ይላችኋል። በዚሁ ጊዜ ኃጢአት ማንኛውንም ነገር ከእግዚአብሔር ማስቀደም እንደሆነ ለመመልከት ችለናል። በመሆኑም ማንኛውንም ነገር ከእግዚአብሔር በምናስቀድምበት ጊዜ የእግዚአብሔርን ባሕርይና ሕግ በተግባራችንና በአመለካከታችን ወይም በፍጥረታችን እንጥላለን። ባለፈው ሳምንት የራሳችን ፍላጎት ከእግዚአብሔር ፍላጎት እንዲቀድም ስናደርግ ያኔ ኃጢአት እንደምንሠራ ተገንዝበናል። እንደዚሁም የኃጢአት ውጤት ሥጋዊ፥ መንፈሳዊና ዘላለማዊ ሞት ወይም ከእግዚአብሔር መለየት መሆኑን አስተውለናል። በመጨረሻውም ከአዳምና ከሔዋን ኃጢአት የተነሣ ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች መሆናቸውን ተምረናል። በዚህ ሳምንት ስለ ኃጢአት የጀመርነውን ጥናት እንቀጥላለን። በአዳምና በሔዋን ኃጢአት ምክንያት ወደ ሰዎች ሁሉ ስለሚተላለፈው የኃጢአት ተፈጥሮና የአማኞችንም ሆነ የማያምኑ ሰዎችን ኃጢአት ጨምሮ ግላዊ ኃጢአትም እናጠናለን።  መጀመሪያ ቀን- ሁላችንም የኃጢአትን ተፈጥሮ ከአዳም ኃጢአት ወርሰናል።  ኃጢአተኛች ስለ መሆናችን ሰዎች የተለያየ አስተሳሰብ አላቸው። ሙስሊሞችም ሆኑ ብዙ ምዕራባውያን ማንም ኃጢአተኛ ሆኖ አይወለድም ይላሉ። የአዳምና የሔዋን ኃጢአት በምንም ዓይነት አይነካንም ብለው ያምናሉ። ሰዎች በመሠረቱ መልካሞች ሆነው ይወለዳሉ፥ ግን አንዳንድ ጊዜ በሕይወታቸው ውስጥ ስሕተት ሊያደርጉ ይችላሉ ይላሉ።  ጥያቄ፡- ሰዎች በተፈጥሮአቸው እንዴት ኃጢአተኞች ስለ መሆናቸው፥ የምታውቋቸው ሰዎች የሚያምኑት ምንድን ነው? እናንተ የምታስቡትንም በጽሑፍ አስፍሩ። በኋላም ሦስት ሰዎችን ማለትም አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን፥ አንድ ወንጌላዊ ክርስቲያንና አንድ ሙስሊምን ለማነጋገር ሞክሩ። ይህን ጥያቄም ጠይቋቸው፡= ሰዎች ከኃጢአት ተፈጥሮ ጋር ተወልደዋል ወይስ ንጹሕ ሆነው ወይስ ከሁለቱም ላይሆኑ? ተመልሳችሁ ኑና መልሶቻቸውን በማስታወሻ ደብተሮቻችሁ ውስጥ አስፍሯቸው።  ምንም እንኳን ብዙ ሰዎች ኃጢአተኞች ሆነን መወለዳችንን ባያምኑና፡ ሰዎች በመሠረቱ መልካም ሆነው ተወልደዋል ሲሉም፥ ከአዳምና ከሔዋን ኃጢአት የተነሣ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች ሆነው እንደሚወለዱ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። ሰዎች ሁሉ በኃጢአት ተበክለው ይወለዳሉ። በዛሬው ትምህርታችንም ኃጢአተኞች ሆነን ስለ መወለዳችን ወይም በተፈጥር ኃጢአተኞች ስለ መሆናችን የሚናገሩትን ብዙዎቹን ቅዱሳት መጻሕፍት እናጠናለን።  1. ሰዎች ሁሉ በኃጢአት ተፈጥሮ ተወልደዋል።  ጥያቄ፡– መዝሙር (51)፡5 አንብብ። ዳዊት ከመቼ ጀምሮ ነው ኃጢአተኛ የነበረው?  ጥያቄ፡- መዝሙር (58)፡3 አንብብ። ክፉዎች የተለዩት፥ የሳቱትና ውሸትን መናገር የጀመሩት ከመቼ ጀምሮ ነው?  ጥያቄ፡– ኤርምያስ 17፡9 አንብብ። ኤርምያስ ልብን እንዴት ይገልጸዋል?  ብሉይ ኪዳን ሰዎች ኃጢአትን እንደሚፈጽሙ ብቻ ሳይሆን፥ ነገር ግን በተፈጥሮአቸውም ኃጢአተኛች መሆናቸውን ያስተምረናል። መዝሙር (5) ዳዊት ከቤርሳቤህ ጋር ኃጢአት ከሠራ በኋላ የጸለየው የንስሐ መዝሙር ነው። ነገር ግን ዳዊት በመዝሙር (505 ውስጥ ከቤርሳቤህ ጋር ያደረገውን ኃጢአት ብቻ አልተናዘዘም። ጨምሮም ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ኃጢአተኛ መሆኑን ተናዝዟል። እንዲያውም በእናቱ ማሕፀን ከተረገዘበት ጊዜ ጀምሮ ኃጢአተኛ እንደ ነበረ ተናዝዛል። እንዲህ ማለትም እናቱ በምንዝርና አርግዛዋለች ማለት አይደለም። ማለት የተፈለገው ዳዊት ከተረገዘበት ቅጽበት ጀምሮ ፍጥረቱ ኃጢአትን ተላብሷል ማለት ነው። በመዝሙር (58)3 ደግሞ ዳዊት ስለ ሌሎች ሰዎች ይህንኑ የመሰለ ቃል ይናገራል። ከእናታቸው ማሕፀን ጀምሮና ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮም ኃጢአተኞች ናቸው። ኤርምያስ 17፡9 የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኮለኛና ክፉ ነው ይላል። እንዲህ ማለትም ሰዎች ኃጢአትን መሥራትን የእግዚአብሔርንም ሕግ መተላለፍን ባለማስተዋል ይመርጣሉ፥ ምክንያቱም ልባቸው ኃጢአት ክፉ አለመሆኑን እየነገረ ስለሚያታልላቸው ነው። አሳባቸውና ተግባራቸው እግዚአብሔርን ደስ አያሰኘውም፥ ራሳቸውንም ለማረም የሚያደርጉት ነገር የለም። የሰዎችን ልብ ክፉና አሳች ተፈጥሮ የሚያድን መድኃኒት የለም። ብሉይ ኪዳን ሰዎች ተወልደው ኃጢአት ከመሥራታቸው በፊት ሳይቀር ኃጢአተኞች መሆናቸውን ይገልጻል። እንዲህም ማለት የሰው ልጆች ከተፈጥሮአቸው ጀምሮ ኃጢአተኞች መሆናቸውን ያሳያል።  ጥያቄ፡– ኤፌሶን 2፡3 አንብብ። ጳውሎስ ሁላችንም በተፈጥሮ ምንድን ነን ይላል?  ጥያቄ፡- ሮሜ 7፡18 አንብብ። ጳውሎስ በሥጋዩ ውለጥ ምን ይኖራል ይላል?  ጥያቄ፡– ቲቶ 1፡15 አንብብ። ጳውሎስ ለርኩሳን ምን የለም አለ?  አዲስ ኪዳንም በበኩሉ ሰዎች በተፈጥሮ ኃጢአተኞች ስለ መሆናቸው ያስተምረናል። ኤፌሶን 2፡3 እኛ ሁላችን «ከፍጥረታችን» የቁጣ ልጆች ነበርን ይላል። እንዲህም በተፈጥሮአቸው ኃጢአተኘች ስለነበሩ የእግዚአብሔር የጽድቅ ቁጣ በላያቸው ላይ ነበር ማለት ነው። የሰው ልጆች በተግባር ከፈጸሙት ኃጢአት ውጭ የእግዚአብሔር ቁጣ በሰው ሁሉ ላይ ነው። ሰዎች ሁሉ ከተፈጥሮአቸውና ከውልደታቸው ኃጢአተኞች በመሆናቸው በማንነታቸው የተነሣ የእግዚአብሔር ቁጣ ሰፍኖባቸዋል። ጳውሎስ በሮሜ 7፡18 ውስጥ በሥጋው ውስጥ ምንም መልካም ነገር እንደሌለ ይናገራል። «በሥጋዩ» ሲል ጳውሎስ ስለ ኃጢአተኛ መግለጹ ነው። እንደዚሁም ከክርስቶስ ውጭ ስላለው እርሱነቱ ሁሉ መናገሩ ነው። ምንም እንኳን እርሱ የዳነ ሰው ቢሆንም፥ አሮጌው ተፈጥሮ አሁንም አብሮት እንዳለ ሲጠቁም ነው። እናም በዚያ አርጌ ተፈጥሮ ውስጥ ምንም መልካም ነገር ሊኖር አይችልም አለ። የሰው ልጆች ሁሉ ከክርስቶስ ውጭ እና ከመወለጻቸው ጀምሮ ያላቸው ማንነት ሁሉ ክፉ ነው። ከክርስቶስ ውጭ በተፈጥሮአችን ማንኛውም ነገር መልካምነት የለውም። በቲቶ 15 ርኩሶች «አእምሮአቸውም ሆነ ሕሊናቸው የረከሰ ነው» ይላል። «ርኩሶች» ከክርስቶስ የተለዩ ሰዎች ናቸው። ስንወለድ ርኩሶች ነበርን ማለት እእምሮአችንም ሆነ ሕሊናችንም ርኩስ ነው ማለት ነው።  መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች በተፈጥሮአቸው ኃጢአተኞች መሆናቸውን ብቻ አያስተምርም። ስለሆነም መጽሐፍ ቅዱስ በዝርዝር ሲያስተምር ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኛች ሆነው እንደ ተወለዱና በተፈጥሮአቸውም (በባሕሪያቸውም) ኃጢአተኞች እንደሆኑ ያስነዝባል።  2. ሰዎች ኃጢአተኛ በሆነ ባሕርይ ተወለዱ ማለት ምን ማለት ነው?  2.1 በራላችን የምናደርገው ነገር ሁሉ እግዚአብሔርን አያስደስተውም።  ጥያቄ፡– ሮሜ 8፡7-8 አንብብ። ሀ) ስለ ሥጋዊ ነገር የሚያስብ እእምር የሚታወቅበት እውነት ምንድን ነው? ለ) በሥጋ ስላሉትስ እውነቱ ምንድን ነው?  ጥያቄ፡- ኢሳይያስ 64፡6 አንብብ። እንደ እግዚአብሔር አስተሳሰብ፥ የጽድቅ ሥራችን ምንድን ነው?  ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኛ ሆነው ተወለዱ፥ በባሕርያቸው ኃጢአተኞች ናቸው ስንል ምን ማለት ነው? የመጀመሪያው የተፈጥሮ ኃጢአት ስላለን በራሳችን የምናደርገው እግዚአብሔርን የሚያስደስተው ነገር የለም ማለት ነው። ምክንያቱም ሰዎች ኃጢአተኞች ሆነው ስለ ተወለዱ በእግዚአብሔር ፊት ራሳቸውን መልካም አድርገው ማቅረብ አይችሉም። ሮሜ 8፡7-8 ስለ ሥጋ የሚያስብ አእምሮ የእግዚአብሔር ጠላት ነው ካለ በኋላ፥ እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ እግዚአብሔርን ደስ አያሰኙም ይላል። እንግዲህ ሥጋ ሁላችንም የተወለድንበት ኃጢአተኛው ተፈጥሮአችን ነው። ማንም የሥጋን ፈቃድ የሚከተል እግዚአብሔርን ማስደሰት አይችልም። እንደዚሁም በሥጋ ፈቃድ ቁጥጥር ሥር የሆኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላቶች ናቸው። ኢሳይያስ 646 ጽድቃችን ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው ይላል። እንዲህ ማለት ደኅንነትን ያላገኘ ሰው ምንም ያህል መልካም ምግባሮች ይኑረው፥ ምግባርቑ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አይኖራቸውም፤ እግዚአብሔርንም ደስ አያሰኙትም። ሥራዎቹ ያን ሰው ከእግዚአብሔር ጋር አያቀራርቡትም። እግዚአብሔር በሕይወታቸው ውስጥ ጣልቃ ገብተ ካላዳናቸውና እርሱን ደስ እንዲያሰኙ ካሳደረጋቸው በስተቀር፥ ሰዎች በዛ ፍላጎታቸው ተነሣሥተው እግዚአብሔርን ሊያስደስቱት አይችሉም። እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሰሕይወታቸው ውስጥ ጣልቃ ገብቶ ከራሱ በማለታረቅ ወዳጆቹ እስካላደረጋቸው ድረስ ሰዎች ጠላቶቹ ሆነው ይኖራሉ። እንዲሁም ኃጢአተኞች ሆነን ከመወለዳችን የተነሣ በዛ ኃይላችን ተነሥተን እግዚአብሔርን ልናስደስተውም ሆነ በፊቱ ራሳችንን ብቁዎች አድርገን ማቅረብ አንችልም፡፡  2.2 መንፈሳዊ ነገሮችን መገንዘብ አንችልም።  ጥያቄ፡– ኤፌሶን 4፡18 አንብብ። አማኞች ስላልሆኑ አረማውያን እውነት የሆኑ ምን ሁለት ነገሮች አሉ?  ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡14 አንብቡ። የእግዚአብሔር መንፈስ ስለሌለበት ሰው እውነት የሆነው ምንድን ነው?  ሁለተኛው ነገር ሁላችንም ኃጢአታዊ ባሕርይ አለን ሲባል ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ነገርን አንነዘብም ማለት ነው። ኤፈሶን 18 የማያምኑ «አእምሮአቸው ጨልሞአል» ይላል። እንዲህ ማለት አእምሮአቸው ስለታወረ የእግዚአብሔርን ነገር መገንዘብ ተሳነው ማለት ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡14 የእግዚአብሔር መንፈስ ስለሌለበት ሰው ይናገራል። ይህ እንግዲህ ስለማያምን ሰው ነው ሮሜ 8፡9 ተመልከቱ)። የእግዚአብሔር መንፈስ የሌለባቸው ሰዎች የእግዚአብሔር መንፈስ ሊገልጥላቸው የሚፈልገውን ማንኛውንም ነገር ሊነዘቡ አይችሉም። የእግዚአብሔርን እውነት ከሞኝነት ይቆጥሩታል። ስለዚህ አይቀበሉትም። እነዚህ ጥቅሶች ስንወለድ ከኃጢአት ጋር መወለዳችንንና ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ ጣልቃ ገብቶ እስካልገለጠልን ድረስ መንፈሳዊ ነገሮችን የማይነዘብ ተፈጥሮ እንደ ነበረን ያስረዳናል። እኛ በራሳችን ኃጢአተኞች ነን። በኃጢአት ተወለድን ማለት ደግሞ እግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ እስካልገለጠልን ድረስ መንፈሳዊ እውነታን ለመገንዘብ የማንችል ነበርን ማለት ነው።  2.3. እግዚአብሔር ዓይኖቻችንን እስካልከፈተልን ድረስ ለእርሱ የምንሰጠው መልስ አይኖርም።  ጥያቄ፡–

የደኅንነት አስፈላጊነት- ሰዎች ኃጢአተኛ በሆነ ባሕርይ ተወለዱ ማለት ምን ማለት ነው? Read More »

ሁላችንም ከአዳም ኃጢአት በደልን ወርሰናል

This entry is part 59 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ከሁለት ቀናት በፊት አዳምና ሔዋን በገነት ውስጥ ስለፈጸሙት ኃጢአት ተምረናል። ይህ የአዳምና የሔዋን ኃጢአት በእነርሱ ላይ ብቻ ተወስኖ አልቀረም። ከእነርሱ በኋላ የመጣውን የሰው ዘር ሁሉ ኃጢአታቸው በክሎአል። ለመሆኑ ከአዳምና ከሔዋን የተገኙትን የሰው ዘሮች ሁሉ የእነርሱ ኃጢአት እንዴት ሊበክላቸው ቻለ? ይህ የሆነው በሁለት መንገዶች ነው። በመጀመሪያ ነገር፥ አዳምና ሔዋን ኃጢአት በመሥራታቸው የተነሣ ሰዎች ሁሉ በደለኞች ሆነዋል። ሁለተኛ ደግሞ፥ አዳምና ሔዋን ኃጢአት ከመሥራታቸው የተነሣ ሰዎች ስኃጢአት የተበከለ ተፈጥሮ ተላብሰዋል። ዛሬ ከአዳምና ከሔዋን ኃጢአት የተነሣ ሰዎች ሁሉ በደለኞች ስለመሆናቸው እናጠናለን። በሚመጣው ሳምንት ደግሞ አዳምና ሔዋን ኃጢአት ከመሥራታቸው የተነሣ ሰዎች ሁሉ በተፈጥሮአቸው ኃጢአተኞች ስለመሆናቸው እንማራለን።  2. የአዳም ኃጢአት በሰዎች ሁሉ ላይ ሞትን አመጣ።  ጥያቄ፡– ሮሜ 5፡12 አንብቡ። ሀ) ኃጢአት እንዴት ወደ ዓለም ገባ? ለ) ኃጢአት ወደ ዓለም በገባ ጊዜ፥ ምን ወደ ዓለም አብሮት ገባ? ሐ) ሰዎች ሁሉ በምን ምክንያት ይሞታሉ?  ጥያቄ፡– ሮሜ 5፡13-14 አንብቡ። ሀ) ሐዋርያው ጳውሎስ፥ «ሕግ በሌለበት ጊዜ ኃጢአት አይቆጠርም ሲል ምን ማለቱ ነበር? ለ) ከአዳም እስከ ሙሴ ድረስ ሞት በማን ላይ ነገሠ?  ጥያቄ፡- ሮሜ 4፡15 አንብቡ። ሀ) ሕግ ምንን ያመጣል? ለ) ሕግ ከሌለ ምን ሌላ ነገር የለም?  ጥያቄ፡- ሮሜ 5፡5 አንብቡ። ሀ) በአንድ ሰው መተላለፍ የተነሣ ምን መጣ? ለ) ሮሜ 5፡16 አንብብ። ኩነኔ ከየት መጣ? ሐ) ሮሜ 5፡17 አንብብ። በአንድ ሰው በአዳም መተላለፍ የተነሣ ምን ሊመጣ ቻለ? መ) ሮሜ 5፡18 አንብብ። አዳም በሠራው አንድ የመተላለፍ ኃጢአት ምን ውጤት መጣ?  በሮሜ 5፡12-21 ድረስ ሐዋርያው ጳውሎስ አማኞች ስለ ዘላለማዊ ደኅንነታቸው እርግጠኛች ሊሆኑ እንደሚችሉ ያስተምራል። እንደዚሁም እማኛች ስለ ዘላለማዊ ደኅንነታቸው እርግጠኞች መሆናቸውን ለማሳየት ሐዋርያው በአዳምና በክርስቶስ መካከል ስላለው ሁኔታ በማነጻጸር ይጠቅሳል። ከአዳም በተወለዱት ሁሉ ላይ ሞት እንደ መጣ ሁሉ፣ በእምነት በክርስቶስ ለሆኑት ሁሉ ዘላለማዊ ሕይወት መጣ በማለት ጽፎአል። እንዲሁም በሮሜ 5፡12 አዳም በበደለ ጊዜ ኃጢአትን ወደ ዓለም አመጣ፥ ከዚያም የኃጢአት ዋጋ የሆነውን ሞትንም ወደ ዓለም እንዲመጣ አደረገ በማለት ይገልጻል። ስለሆነም ኃጢአት ከመኖሩ በፊት ሞት አልነበረም፡ የኃጢአት ጅማሬ የሞት ጅማሬ ሆነ። አዳም ኃጢአት ከመሥራቱ የተነሣ ሞት ብቻ አልመጣበትም። አዳም በመበደሉ ምክንያት ሞት በሰዎች ሁሉ ላይ መጣ። ምክንያቱም አዳም ስለ በደለ ሁሉም በድለዋል ወይም ኃጢአትን ሠርተዋል።  ሐዋርያው ጳውሎስ “ሁሉም ኃጢአትን ሠሩ» ሲል ሁሉም በግሪ በሠሩት ኃጢአታቸው ምክንያት ይሞታሉ ማለቱ ነበር? አይደለም፥ እዳ። ኃጢአትን በመሥራቱ ሁሉም ይሞታሉ ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ነው በአንድ በኩል አዳም ከበደሉ የተነሣ ሰዎች ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋል ስለዚህ ሁሉም የኃጢአት ዋጋ በሆነው ሞት ይቀጣሉ። ሐዋርያው ጳውሎ ከአዳም ኃጢአት የተነሣ ሁሉም ኃጢአተኞች ስለሆኑ መሞት አለባቸው ያላበት ሦስት ምክንያቶች አሉት።  1) ሮሜ 5፡12 ሰዎች በየግላቸው በሚሠሩት ኃጢአት ምክንያት ይሞታሉ አይልም። ምክንያቱም ሰዎች ሁሉ በግል ኃጢአታቸው መሞታቸው እውነት ስላልሆነ ነው። ሕፃናት በግላቸው የሚፈጽሙት ኃጢአት ባይኖርም፥ ይሞታሉ።  2) ጳውሎስ በሮሜ 5፡13-14 ላይ ሲናገር፥ በግል ኃጢአት ባልሠሩት ሰዎች ላይ እንኳን ሞት ሥልጣን አገኘ ይላል። ይህም በአዳምና በሙሴ መካከል ባሉት ዘመናት ሆነ። እንዴዚሁ በቁጥር 3 ላይ እግዚአብሔር ለሙሴ በሲና ተራራ ላይ ሕጉን እስከ ሰጠበት ጊዜ ድረስ ዓለም በኃጢአት ተሞልታ እንደ ነበረች ያስረዳል። ሆኖም ያ ኃጢአት አይቆጠርም ነበር። ሕግ በሌለባት ኃጢአት እንደ ኃጢአት አይቆጠርም ብሎ ሲል ምን ማለቱ ነው? ሮሜ 4፡15 ላይ ያለው ቃል በሮሜ 5፡13 ላይ የተጻፈውን ጥቅስ ለማብራራት ይረዳናል። ሮሜ 4፡15 የሚነግረን ሕግ በሌለበት መተላለፍም ሆነ ቅጣት አለመኖሩን ነው። ኃጢአት ምን ጊዜም ኃጢአት ነው። መተላለፍ ሁልጊዜም መተላለፍ ነው። ነገር ግን የሚተላለፈው ሕግ ከሌለ አንድ ሰው ሕግ ተላለፈ ሊባል አይችልም። ሕግ እስካልተሰጠ ድረስ አንድ ሰው ሕግ አፈረሰ ተብሎ ሊቀጣ አይችልም።  በእርግጥ እግዚአብሔር በአዳምና በሙለ ዘመን መካከል ለኖሩ ሰዎች አንዳንድ ትእዛዛትን ሰጥቶአቸዋል። ለምሳሌ ያህል፥ ደም ያለበትን ሥጋ እንዳይበሉና ሰውን እንዳይገድሉ አዝዞአቸው ነበር (ዘፍጥ. 9፡4-6)። በተማሪ እያንዳንዱ ሰው በልቡ ውስጥ የተጻፈ ሕግ አለው (ሮሜ 2፡5)። ይህን ሕግን ሲተላለፉ መቀጣት ነበረባቸው (ሮሜ 2፡12)። ነገር ግን ከአዳም እስከ ሙሴ በነበረው ዘመን ገና ሕግ ተጽፎ ስላልተሰጠ እግዚአብሔር የሚፈቅዳቸውንም ሆነ የሚጠላቸውን ነገሮች በውል ለይቶ ለማወቅ አስቸጋሪ ነበር። በዚያን ዘመን ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ ለይቶ ለመገንዘብ የሚያስችል መጽሐፍ ቅዱስ አልነበረም። እግዚአብሔር ገና ሕጉን በመዘርዘር ጽፎ አልሰጠም ነበር። ሆኖም የሙሴን ሕግ ጽፎ ከሰጠ ወዲያ ፈቃዱ ግልጽ ሆነ። ከዚያም በኋላ ሰው ሁሉ ለሚሠራው ኃጢአት ሰበብ ማቅረብ የማይችልበትና ኃላፊነትን የሚሸከምበት ጊዜ መጣ። ሰዎች ኃጢአትን ሲፈጽሙ ሕግን ማፍረሳቸው ስለሆነ ቅጣታቸውም ሞት ሆነ። ይሁን እንጂ በአዳምና በሙሉ መካከል በነበረው ረጅም ዘመን የኖሩት ከእግዚአብሔር የተሰጠ ግልጽ የሆነ ሕግ ያላፈረሱትም ሳይቀሩ ሁሉም ሞቱ። ታዲያ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ግልጽ የሆነ ሕግ ካልተላለፉ በምን ምክንያት ሞቱ? እንዲሁም በግላቸው ካልበደሉስ በምን ሰበብ እንዲሞቱ ሆኑ? ይህ ሊሆን የቻለበት ምክንያት አላም በፈጸመው ኃጢአት እነርሱም በደለኞች ስለሆኑ፥ የኃጢአትን ቅጣት ሞትን እንዲቀበሉ ተፈረደባቸው። ስለዚህ ከአዳም የውርስ ኃጢአት የተነሣ በአዳምና በሙሴ ዘመን መካከል የነበሩ ሰዎች እንዲሞቱ ሆነዋል። ይህ እንግዲህ በግልጽ የሚያስረዳን፥ ለዘመናት የኖሩትና የሚኖሩት የሰው ልጆች ሁሉ በአዳም መተላለፍ ምክንያት ኃጢአተኞችና በደለኞች መደረጋቸውን ነው።  3) በሮሜ 5፡15-18 ባለው ክፍል ሐዋርያው ጳውሎስ አራት ጊዜ ደጋግሞ ሞት በአዳም ኃጢአት ምክንያት ወደ ሰዎች ሁሉ ዘንድ መጣ ይላል። ሰዎች ራሳቸው በፈጸሙት ኃጢአት የተነሣ ሞት መጣባቸው አይልም። እርሱ በግልጽ የሚለው አዳም በፈጸመው አንድ ኃጢአት ሰበብ ሞት በሰዎች ሁሉ ላይ መምጣቱን ነው። እንዲሁም በሮሜ 5፡5 ውስጥ በአንድ ሰው በአዳም በደል ብዙዎች ይሞታሉ ይላል። በሮሜ 5፡16 ውስጥ አንድ ሰውም ኃጢአትን በማድረጉ ኩነኔ መጥቷል ይላል። ይህም አንድ ሰው የተባለው አዳም ነው። በሮሜ 5፡17 ውስጥ በአንዱ በአዳም በደል ሞት ነገሠ ይላል። እንዲሁም በሮሜ 5፡18 ውስጥ ይደግምና በአንዱ በደል ምክንያት ፍርድ ለኩነኔ ወደ ሰው ሁሉ እንደ መጣ ይገልጻል።  በዚህ ክፍል በቁጥር 18 ላይ የአንዱ የክርስቶስ የጽድቅ ሥራ ብዙዎችን ነፃ አድርጎ፥ «ሕይወትን ይሰጣል» ስለሚል ይህ ጥቅስ ሰዎች ሁሉ እንደሚድኑ ይናገራል ብለው አንዳንድ ሰዎች ሊያስቡ ይችሉ ይሆናል። ሐዋርያው ግን የሚናገረው ከአዳም ዘር የሆኑት ኃጢአትን ወርሰው በመወለድ አዳማውያን እንደሆኑ ሁሉ በእምነት በክርስቶስ ስለሆኑት ነው። በዚህም ሐዋርያው የክርስቶስ ወገንና የአዳም ወገን ስለሆኑት መናገሩ ነው። ከሮሜ 3፡21 – 4፡25 ድረስ ባለ ክፍል ጳውሎስ አንድ ሰው የክርስቶስ ለመሆን በእርሱ ማመን ይኖርበታል ይላል። ጳውሎስ ቀደም ሲል ስለዚህ ነጥብ ደህና አድርጎ ያብራር በመሆኑ እዚህ ላይ አልደገመውም። ሐዋርያው ጳውሎስ በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ ማስገንዘብ የፈለገው ቁም ነገር በልደት አዳማውያን የሆኑት የሞት ሥቃይን እንደሚቀበሉ ሁሉ፥ እንዲሁም ይህን ነጥብ የበለጠ ግልጽ በማድረግ የአዳም የኃጢአት ውጤት ሰዎች ሁሉ የዚያን ኃጢአት መቀጫ ሰሞት እንደሚከፍሉ ያስተምራል።  ስለዚህ በሮሜ 5፡12 ውስጥ ጳውሎስ የሚናገረው አዳም ኃጢአት ባደረገ ጊዜ ከእርሱ ዘር የሚወለዱት ሁሉ ማለትም የሰው ዘር የሆኑ ሁሉ ከእርሱ ጋር ኃጢአትን መፈጸማቸውን ነው። ስለሆነም ከአዳም ኃጢአት የተነሣ ሁሉም በድለዋል። በዚህ በአዳም ኃጢአት ምክንያት እያንዳንዱ ሰው የኃጢአት ቅጣት የሆነውን ሞትን ይቀበላል።  2. አዳም ሰዎችን ሁሉ የሚወክል በመሆኑ፥ የእርሱ ኃጢአት ሞትን አመጣ።  ለመሆኑ አዳም የሠራው ኃጢአት እንዴት አድርጎ የሰውን ዘር ሁሉ ሊነካ ቻለ? አዳም የሰውን ዘር ሁሉ ይወክላል። እርሱ ኃጢአትን ባደረገ ጊዜ ምርጫውን ለራሱ ብቻ መወሰኑ አልነበረም። የእርሱ ምርግ ለተቀሩት የሰው ዘሮችም ሁሉ የተደረገ ነበር። ለዚህ የሚሆን ጥሩ ምሳሌ በዲሞክራሲያዊ መንግሥት ውስጥ ያለው ሁኔታ ነው። ዲሞክራሲያውያን በሆኑ አገሮች የሚገኙ ሕዝቦች እነርሱን በምክር ቤት

ሁላችንም ከአዳም ኃጢአት በደልን ወርሰናል Read More »

የኃጢአት ውጤት፡- ሞት 

This entry is part 58 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

አንዳንድ ሰዎች ኃጢአት የከፋ ውጤት እንደሚያመጣባቸው አያውቁም። ስለዚህ «ምንም ያህል ስሕተት ብሠራ፥ እግዚአብሔር ይቅር ስለሚለኝ የምፈልገውን ማድረግ እችላለሁ» ይላሉ። እንዲሁም፥ «እኛ የምንፈጽመው ኃጢአት ይህን ያህል ከባድ ጉዳይ በእኛም ሆነ በሌሎች ሰዎች ላይ አያደርስም፥ እንዲያው ብቻ ትንሽ ነገር ነው» ይላሉ።  ጥያቄ፡- በታማኝነት ባለፈው ሳምንት ውስጥ ስለ ፈጸማችሁት ኃጢአት መለስ ብላችሁ አስቡ። ከዚያም በዚህን ጊዜ ከፈጸማችሁት ውስጥ የማትጎዳ ትንሽ ኃጢአት ናት የምትሉአትን ለይታችሁ ጻፉ።  ሁላችንም ብንሆን ይህን ያህል ከባድ ጉዳት አያደርስብንም ብለን በመዘናጋት ኃጢአት የምንፈጽምበት ጊዜ አለ። ችግሩ በዚህ ሁኔታ ኃጢአትን በምንፈጽምበት ጊዜ ኃጢአት ምን ያህል መጥፎ መሆኑን ከልብ አንዓዘብም። እንዲሁም የኃጢአት ውጤት ምን ያህል እንደሚከፋ አንረዳም። ታዲያ የኃጢአት ውጤት ምንድን ነው?  ጥያቄ፡- ዘፍጥረት 2፡17 አንብብ። አዳምና ሔዋን ክፉና በጎውን ከምታስታውቀው ዛፍ ፍሬ በበሉ ቀን ምን እንደሚሆን ነበር? ለ) ዘፍጥረት 3፡8 አንብብ። አዳምና ሔዋን ኃጢአት ከሠሩና እግዚአብሔር ወደ አትክልቱ ውስጥ ሊመጣ ድምፁን በሰሙ ጊዜ ምን አደረጉ? ሐ) ዘፍጥረት 3፡22-23 አንብብ። እግዚአብሔር አዳምና ሔዋንን በምን ምክንያት ከኤድን ገነት አውጥቶ አባረራቸው?  ጥያቄ፡– ሮሜ 5፡12 አንብብ። በአንድ ሰው ኃጢአት ምክንያት ወደ ዓለም ምን መጣ?  ጥያቄ፡- ሮሜ 6፡23 አንብብ። የኃጢአት ውጤቶች ምንድን ናቸው?  ጥያቄ፡- ሮሜ 75 አንብብ። ኃጢአተኛው ምኞታችን ምን ፍሬ ያፈራል?  ጥያቄ፡- ያዕቆብ 1፡15 አንብብ። ኃጢአት ካደገች በኋላ ምንን ትወልዳለች?  ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮንቶስ 5፡50-57 አንብቡ። ሞት በመጨረሻ የሚደመሰሰው መቼ ነው?  ጥያቄ፡- ሮሜ 8፡20-21 አንብቡ። ሀ) ፍጥረት ለከንቱነት እንዲገዛ አልፎ ለምን ተሰጠ? ለ) ፍጥረት ለከንቱነት ከመገዛት መች ነፃ ይወጣል?  የኃጢአት ውጤት ወይም ዋጋ በመሆን በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ በብዛት የተጠቀሰው ሞት ነው። ሮሜ 5፡12 ኃጢአት በአንድ ሰው ማለትም በአዳም ወደ ዓለም ወይም በዓለም ባሉ ሰዎች ሁሉ ላይ መጣ ይላል። እንዲሁም ሮሜ 6፡23 ላይ ሰዎች ከሥራቸው ክፍያ ደመወዝ እንደሚቀበሉ ሁሉ፥ ለኃጢአታቸውም ዋጋ ሞትን ያለጥርጥር ይቀበላሉ ይላል። ሮሜ 7፡5 ላይ ደግሞ ኃጢአት የሰፈነበት ምኞታችን የሞትን ፍሬ ያፈራል ይላል። በያዕቆብ 1፡5 ደግሞ፥ ኃጢአት ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች በማለት ይናገራል። ትክክለኛው የኃጢአት ውጤት ወይም ዋጋ ሞት ነው።  ታዲያ ሞት ምንድን ነው? ሞት መለየት ነው። የሥጋ ሞት የመንፈስ ከአካል መለየት ነው። የመንፈስ ሞት ደግሞ የሰው ከእግዚአብሔር መለየት ነው። ዘላለማዊ ሞት ደግሞ ለዘላለም ከእግዚአብሔር መለየት ነው። እንግዲህ ኃጢአት ከእነዚህ የመለየት ዓይነቶች ቢያንስ አንዱን ያመጣል። እንደዚሁም ኃጢአት ሁልጊዜ ከእነዚህ የሞት ዓይነቶች አንዱን ያስከትላል።  1. ኃጢአት የሥጋ ወይም የአካል በሞት መለየትን ያመጣል።  እግዚአብሔር አዳምና ሔዋን መልካምና ክፉን ከሚያሳውቀው ዛፍ ፍሬ አትብሉ ባላቸው ጊዜ እንዲህ ነበር ያላቸው፥ «ከዚህ ዛፍ ፍሬ በበላችሁበት ቀን በእርግጥ ትሞታላችሁ።» ነገር ግን በዘፍጥረት ምዕራፍ 3ና4 ላይ ከተጻፈው ክፍል በግልጽ እንደምንረዳው አዳምና ሔዋን ከዛፉ ፍሬ በበሉበት ቀን ወዲያውኑ የሥጋ ሞት አልሞቱም ነበር። ታዲያ ምን ሆኑ? የሆነው ነገር ይህን ፍሬ ከተመገቡበት ዕለት ጀምሮ አዳምና ሔዋን የሥጋ ሞት መሞት ጀመሩ። ግን የዚህን ዛፍ ፍሬ ባይመገቡ ኖሮ፥ ለዘላለም ሕያዋን ሆነው በኖሩ ነበር። ግን ምን ያደርጋል። ኃጢአት ከሠሩበት ቀን ጀምሮ ሁለቱም አካላቸው ማለትም ሥጋቸው መበስበስ ጀመረ። በመጨረሻም ሟች ሆነ።  ከዚህ ሰበብ የተነሣ ሥጋቸው ማለትም ሰውነታቸው ያረጅ ጀመር። ይህም ብቻ አይደለም፥ አካላቸውን ታማሚ የሚያደርጉ በሽታና ጀርሞች ወደ ዓለም ገቡ። ለዘላለም እንዲኖሩ ሊያደርጋቸው ከሚችለው የዛፍ ፍሬ እንዳይባሉ እግዚአብሔር ከለከላቸው (ዘፍጥረት 3፡22-28)። ከዚህ የተነሣ አዳምና ሔዋን ከዚህ የዛፍ ፍሬ ከተመገቡበት ቀን አንሥቶ በአካል መሞት ጀመሩ።  የአካል ወይም የሥጋ ሞት በኃጢአት ምክንያት እንደሚመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡54-5 «ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሲለብስ፥ በዚያን ጊዜ፡- ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ» ይላል። ይህ እንግዲህ የሥጋ ሞት የኃጢአት ውጤት መሆኑን ያስረዳናል። ሮሜ 8፡18-25 እንደሚለው ከኃጢአት ውጤት የተነሣ የሰው ተፈጥሮ ሁሉ የተሸነፈበት የሚያበቃው ክርስቶስ ለሕዝቡ ደኅንነትን በመጨረሻ በሚያመጣበት ጊዜ ነው። ይህ የሚያመለክተን በሞት ምክንያት የሚመጣው መበስበስ የኃጢአት ውጤት መሆኑን ነው። 2 ኃጢአት በመንፈስ ሞት መለየትን ያመጣል አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ በአካላቸው መሞት ጀመሩ። እንዳይበሉ ከታዘዙት ፍሬ በበሉበት ቀን በተለይም በመንፈሳቸው ሞቱ። አዳምና ሔዋን ይህን ኃጢአት ከመፈጸማቸው በፊት ከእግዚአብሔር ጋር ደስታ የሞላበት አንድነት ነበራቸው። ኃጢአት ከሠሩ በኋላ እግዚአብሔር ሊገናኛቸው ሊመጣ ፈርተው ተሸሸጉ (ዘፍጥረት 3፡8)። ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸው ቅርበትና አንድነት ከዚህ ዕለት ጀምሮ መቋረጡንና ራሳቸውን ከእግዚአብሔር መለየታቸውን ተረዱ። የመንፈስ ሞት የሚባለው የሰዎች ከእግዚአብሔር መለየት ማለት ነው። አዳምና ሔዋን ኃጢአትን በፈጸሙበት ቀን ከእግዚአብሔር ተለዩ።  መጽሐፍ ቅዱስ ራሳችንን ከእግዚአብሔር ስለ መለየታችን ሲገልጽ ራሳችንን የእግዚአብሔር ጠላቶች ማድረግ፥ እግዚአብሔርን መጥላትና ቁጣውንም በእኛ ላይ ማምጣት መሆኑን ያስገነዝባል። 34ኛ ጥያቄ፡- ዘዳግም 7፡10 አንብብ። ለእግዚአብሔር የማይታዘዙት፥ በዚህ ክፍል | በምን ሁኔታ ተገለጹ?  ጥያቄ፡- መዝሙር (106)፡40 አንብብ። አቁጥር 39=40 ያለው ክፍል የእግዚአብሔር ሕዝብ ለለፈጸሙዋቸው የኃጢአት ዓይነቶች ዘርዝር ይዟል። በቁጥር 40 ላይ እግዚአብሔር ምን አደረገ?  ጥያቄ፡– ኤርምያስ 4፡4 አንብብ። ሕዝቡ በፈጸሙት ክፋት ምክንያት ምን ሆነ?  ጥያቄ፡- ያዕቆብ 4፡4 አንብብ። የዓለም ወዳጅ በሚሆን ሰው ላይ ምን ይደርሳል?  ጥያቄ፡- ቆላስይስ 1፡21 አንብብ። በአሳባቸውና በክፉ ሥራቸው ባሕርይ የሚመሩ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት እንዴት ነው?  ጥያቄ፡- ሮሜ 1፡18 አንብብ። ከሰዎች ክፋት የተነሣ እግዚአብሔር በሰዎች ላይ ምንን ይገልጣል?  ሰዎች ኃጢአትን በሚፈጽሙበት ጊዜ የእግዚአብሔር ጠላቶች በመሆን ከእግዚአብሔር ራሳቸውን ይለያሉ። እግዚአብሔርም በኃጢአታቸው ላይና ኃጢአትን በመሥራታቸው በእነርሱም ላይ ቁጣውን ያወርዳል። እግዚአብሔር እነዚህን ሰዎች ይቆጣቸዋል ሲባል ደግሞ ሰዎቹን በሰውነታቸው ይጠላል ማለት አይደለም። እነዚህ ሰዎች በኃጢአት ምክንያት ራሳቸውን የእርሱ ጠላቶች ቢያደርጉም፥ ደግሞም ከእርሱ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ቢያቋርጡም፥ እግዚአብሔር ግን ይህ ሁሉ ሆኖ ኃጢአታቸውን ብቻ ይጠላል። እግዚአብሔር ራሳቸውን ጠላቶቹ ባደረጉት ሁሉ ላይ ያሚያወርደው ቁጣ የጻድቅነቱ ምላሽ ነው። በዘዳግም 7፡10 ላይ የተጻፈው ቃል ኃጢአትን የሚሠሩትንና የማይታዘዙትን እግዚአብሔርን እንደ ጠሉ አድርጎ ይገልጻቸዋል። መዝሙር (106)፡34-39 ደግሞ እስራኤላውያን የፈጸሙዋቸውን ብዙ ዓይነት ኃጢአቶች ዘርዝሮ ይገልጻል። በቁጥር 40 ላይ ደግሞ እግዚአብሔር እንደ ተቆጣቸው ይናገራል። ምንም እንኳን የእርሱ ወራሾች ቢሆኑም፥ ኃጢአታቸው ከእርሱ እንዲለዩ በማድረግ ቁጣውን ሊያመጣባችው ቻለ። ኤርምያስ 4፡4 ሲናገር በክፉ አድራጊዎች ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ይወርዳል ይላል። ይህ ቁጣውም ማንም ሰው ሊያጠፋ እንደማይችለው እሳት ተገልጾአል። የእግዚአብሔር ቁጣ ሲባል ጨርሶ ትዕግሥቱን አሟጧል ማለትም አይደለም። ይልቁን ይህ ባሕርዩ የሆነውን የእርሱን ንጹሕና በጎነት ለሚጻረር ማንኛውም ነገር እርሱ የሚሰጠው የጽድቅ ምላሽ ነው። ይህ ምላሽም ለዓለም እንደሚበጅ እርሱ ያውቃል። ያዕቆብ 44 በዓለም ውስጥ የእግዚአብሔርን ጠላቶች መከተል በፈቀድንበት ጊዜ ራሳችንን የእግዚአብሔር ጠላቶች እናደርጋለን ማለት ነው። ቆላስይስ 1፡21 ደግሞ ወደ ክርስቶስ ያልተመለሱ ሰዎች ያላቸው ክፉ ባሕርይ የእግዚአብሔር ጠላቶች እንዲሆኑ አድርጎአቸዋል ይላል። ሮሜ 1፡18 በኃጢአታቸውና በክፋታቸው ምክንያት የእግዚአብሔር ቁጣ ከሰማይ ይገለጥባቸዋል በማለት ያስጠነቅቃል።  ማስታወስ የሚገባችሁ ቁም ነገር እግዚአብሔር ራሱን የሰዎች ጠላት ለማድረግ ያልመረጠ መሆኑን ነው። ነገር ግን ሰዎች ኃጢአትን በሚሠሩበት ጊዜ የእግዚአብሔር ጠላቶች መሆንን ይመርጣሉ። ራሳቸውን ከእግዚአብሔር ለመለየት ይመርጣሉ። ሰዎች በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን መሥራት በሚመርጡበት ጊዜ የእግዚአብሔር ጠላት ይሆኑና የእግዚአብሔርን የጽድቅ  ቁጣ በራሳቸው ላይ ያመጣሉ።  ጥያቄ፡- ሆሴዕ 11፡1-4 አንብብ። ሀ) እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ ስለ እስራኤል የነበረው ልማት እንዴት ነበር? ለ) እግዚአብሔር ለሕዝቡ ለእስራኤል ምን አደረገ? 41ኛ ጥያቄ ሆሴዕ 11፡5-7 አንብብ። ከኃጢአታቸው የተነሣ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ምን ደረሰ?  ይህ ትንቢተ ሆሴዕ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ምን ያህል ፍቅር እንዳለውና ኃጢአት በሚሠሩበትም ጊዜ እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የሚሰማውን ስሜት ደህና አድርጎ የሚገልጽ መጽሐፍ ነው። በሆሴዕ ከምዕራፍ 1-3 ባለው ክፍል እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን ከሆሴዕ አመንዝራ

የኃጢአት ውጤት፡- ሞት  Read More »

ኃጢአት ከየት መጣ? 

This entry is part 57 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ኃጢአት ከየት መጣ? ለምን ኃጢአትን እናደርጋለን? ደግሞስ ለምን በኃጢአት በተሞላ ዓለም ውስጥ እንኖራለን? ኃጢአትን እንዴት እንደምንከላከል ወይም ለኃጢአት ችግር መፍትሔ የምናገኝበትን መንገድ ከመረዳታችን በፊት ኃጢአት ከየት እንደ መጣ ለማወቅ በመጀመሪያ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልሶችን ማግኘታችን ወሳኝ ነው።  ጥያቄ፡- ሀ) እናንተ የምታውቁዋቸው አብዛኛዎቹ ሰዎች የኃጢአት ዋና ምንጭ ምንድን ነው ይላሉ? ለ) እነዚህ ሰዎች ለኃጢአት ችግር እጅግ ተመራጩ መፍትሔ ምንድን ነው ይላሉ?  አንዳንድ ሰዎች ኃጢአት ከድንቁርና ወይም ከእውቀት ማነስ ይመጣል ይላሉ። ኃጢአት ከዕውቀት ማነስ የሚመጣ ከሆነ እኛን ከኃጢአት የሚያድነን ትልቁ ነገር ትምህርት ነው ማለት ነው። ሌሎች ሰዎች ደግሞ ሰዎች በድህነትና በጭቆና ቀንበር ሥር ከመኖራቸው የተነሣ ኃጢአት በዚህ ምክንያት ይመጣል ይላሉ። እንግዲህ ኃጢአት ከድህነትና ከጭቆና የሚመጣ ሆኖ ከተገኘ፥ እኛን ከኃጢአት የሚያድነን ትልቁ ቁም ነገር ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ለውጥ ነው ማለት ነው። አንዳንዶቹ ደግሞ ሰዎች ከሰዎች ተለይተው ባዕዳን ሲሆኑና ከአካባቢያቸው ኅብረተሰብ ሲገለሉ፥ ያኔ ኃጢአት ይከሰታል ባይ ናቸው። በመሠረቱ ሰዎች ከኅብረተሰብ በመገለላቸው ኃጢአት የሚመጣ ከሆነ በጣም ተገቢ የሚሆነው ተግባር ሰዎች የማኅበረሰባቸው ጠቃሚ አካል እንዲሆኑ ማድረግ ነው። በእነዚህ አስተሳሰቦች ሁሉ ውስጥ ጥቃቅን እውነቶች አሉ። ነገር ግን ማንኛቸውም መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኃጢአት ምንጭ ምንነት የሚያስተምረውን ሐቅ አያንጸባርቁም። ስለሆነም፥ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ብቸኛ የኃጢአት እውነተኛ ምንጭ ምን ሊሆን ይችላል።  1. ኃጢአት ሊመጣ የሚችለው ለምኞታችን ከእግዚአብሔር የበለጠ ስፍራ ስንሰጥ ነው።  ጥያቄ፡- ያዕቆብ 1፡3 አንብቡ። ሀ) ሰዎች በሚፈተኑበት ጊዜ ምን አይብሉ? ለ እንደዚህ ጥቅለ አገላለጽ ለእግዚአብሔር የሚሳኑት ሁለት ነገሮች ምንድን ናቸው?  ጥያቄ፡- ያዕቆብ 1፡14-15 አንብቡ። ሀ) የኃጢአት ምክንያት ምንድን ነው? ለ የኃጢአትስ ውጤት ምንድን ነው?  ጥያቄ፡- ዘዳግም 32፡4 አንብቡ። ሀ) የእግዚአብሔር ሥራና መንገድ እንዴላ ተገለጹ? ለ) እግዚአብሔር ራሱ እንዴት ተገለጸ?  ያዕቆብ 1፡13-5 ያለው ክፍል ስለ ፈተናና ብዙ ሰዎች በምን ምክንያ፡ ኃጢአት እንደሚሠሩ ይገልጻል። ከዚህ ክፍል በመጀመሪያ የምንማረግ እግዚአብሔር ማንንም ሰው ኃጢአት እንዲሠራ እንደማይፈትነው ነው ሰዎች በገዛ ምኞታቸው ኃጢአት ሲሠሩ ስሕተታቸውን በእግዚአብሔር ላ ሊያላክኩ አይገባም። እርግጥ ሰዎች በእምነታቸው እንዲያድጉ እግዚአብሔ ሰዎችን የሚፈተንበት ጊዜ ሊኖር ይችላል። ግን እግዚአብሔር በማንም ሰd ላይ ኃጢአትን እንዲሠራ የሚገፋፋ ምኞት አያመጣበትም። እንዲሁና ዘዳግም 32 ላይ የእግዚአብሔር ሥራ ሁሉ ፍጹም ነው፥ መንገዱም ፍጹ ነው ይላል። እንግዲህ ፍጹም የሆነ አምላክ ኃጢአትን አይሠራም፡ ደግሞ፡ ማንም ሰው ቢሆን በምኞቱ ተፈትኖ ኃጢአት እንዲፈጽም ከቶ አያደርግም ዳሩ ግን አንዳንድ ጊዜ እኛው ራሳችን ስለ ኃጢአታችን እግዚአብሔርን እንድናማርር እንፈተናለን። እንዲህ የሚል አስተሳሰብም ሊቀረጽብን ይችል ይሆናል፥ «እግዚአብሔር እንድፈተን ባያደርግ ኖሮ ኃጢአት ባልሠራሁ ነበር።» አያችሁ ኃጢአት ወይም ኃጢአትን የመሥራት ምኞትና ዝንባሌ የሚመጣው ከእግዚአብሔር ነው ብሎ መናገር ራሱ እግዚአብሔርን መሳደብ ወይም ክብሩን ማዋረድ ነው። በግልጽ መታወቅ ያለበት ነገር እግዚአብሔር ራሱ ኃጢአትን የመፈጸም ምኞት ወይም ዝንባሌ እንደሌለው ሁሉ፥ ማንም ሰው ሲሆን ኃጢአትን የመሥራት ፍላጎት እንዲያድርበት አድርጎም አያውቅም፥ ወደፊትም አያደርግም። ኃጢአት ያለበት ምኞት ወይም ፍላጎት ከእግዚአብሔር ዘንድ አይመጣም። –  እውነቱ ይህ ከሆነ፥ የኃጢአት ፈተናዎች ከየት ይመጣሉ? በቁጥር 14 ውስጥ ካለው ጥቅስ የምንማረው ሁለተኛው ነገር «እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል» የሚለው ቃል ነው። ከጅምሩ አብዛኛዎቹ ምኞቶች ለሰዎች የተሰጡት ከእግዚአብሔር ሲሆን፥ እንደ እርሱ ፈቃድና ፍላጎት ከተፈጸሙ መልካም ናቸው። ሆኖም እነዚህን በእርሱ ፈቃድ የተሰጡንን ምኞቶች በሚገባ በመጠቀም ፈንታ ዓላማቸውን ስተው ወደ ክፉ አቅጣፃ ስበው እንዲወስዱን በመታለል ከፈቀድንላቸው ሕይወታችንን ለጥፋት ይዳርጉታል። በአማርኛ ቋንቋ፡- «አታለለ» የሚለው ቃል በግሪኩ አገላለጽ በዓሣ ወጥመድ ወይም መንጠቆ ጫፍ ላይ የሚደረግ ምግብን ያመለክታል። ዓሣው በወጥመዱ ጫፍ ላይ የተደረገለትን ምግብ ካየ በዚያ ይላብና ለመብላት ይሞክራል። ይህን ጊዜ በመንጠቆው ይያዛል፣ ወይም መረቡ ውስጥ ጥልቅ ይላል። ከዚያም አጥማጁ ከባሕሩ ወይም ከወንዙ ውስጥ ስቦ ይወስደዋል። በተመሳሳይ መንገድ፡ የራሳችንን ምኞቶች በተቻለ መንገድ ሁሉ ለመፈጸም ከአግባብ ያለፈ ስንሯሯጥ በእነዚሁ ምኞቶቻችን ተጠምደን ወደ ኃጢአት እንወሰዳለን። ለመሆኑ ምኞቶቻችን አጥምደውን እንዲወስዱን እንዴት ዕድል እንሰጣቸዋልን? ይህን የምናደርገው ምኞታችን በሕይወታችን ውስጥ ዋናውን ስፍራ ይዞ እንዲንሠራፋ ስንፈቅድለት ነው። በተለይም ምኞታችን ወደ ባሰ ጥፋት የሚያደርሰን ከእግዚአብሔር አምላክ አስበልጠን በሕይወታችን ውስጥ ስፍራ በመስጠት እርሱኑ ለመፈጸም ማንኛውንም አማራጭ መጠቀምን ምርጫችን ስናደርግ ነው። ይኸውም ትክክለኛ ባልሆነ መንገድም እንኳ ቢሆን ይህን ምኞት ለማሳካት እስከምንጠመድ እንወስዳለን ማለት ነው።  ሰዎች ይህን እግዚአብሔር አስቀድሞ ለበጎ ዓላማ የሰጠን ምኞት ለክፉ ተግባር ሊያውሉት ቢመርጡ ቀድሞ መልካም የነበረው ምኞት ይለወጥና ተጣሞ የክፉ መካተቻ ይሆናል።  ለምሳሌ ያህል፥ የምግብ ፍላጎት መልካም ነገር ነው። ለመኖር መብላት አለብን። ነገር ግን ለመብል ያለንን ፍላጎት ለማሟላት ትክክለኛ ባልሆነ መንገድ ብንጠቀምና ከገደብ ውጭ ብንበላ፥ የሆዳምነት ኃጢአት እንፈጽማለን። የእንቅልፍ ፍላጎት ስጎ ነገር ነው። ሁላችንም ብንሆን ለመኖር ዕረፍት ያስፈልገናል። ነገር ግን የእንቅልፍን ዓላማ አጣምመን ሌላ ትርጉም በመስጠት ልንጠቀምበት ብንፈልግ፥ ይህ ምኞት ወደ ስንፍና ኃጢአት ይመራናል። አንድ ሰው ከባለቤቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለመፈጸም ያለው ፍላጎት የተፈቀደና ጤናማም ነው። ነገር ግን ከተፈቀደው ውጭ ወጥተን ሕገ-ወጥ ግብረ ሥጋ ግንኙነት ብንፈጽም፥ ይህ የፍትወተ ሥጋ ምኞት የወሲባዊ ምግባረ ብልሹነትና የዝሙት ኃጢአትን መፈጸም ነው። የራስን ቤተሰብ ለማስተዳደርም ሆነ ድሆችን ለማገዝ ገንዘብ ለማግኘት መመኘት ጥሩ ነው። ግን ብዙ ገንዘብ አግኝቶ ለመበልጸግና የተለያዩ ነገሮችን ለመግዛት ስለ ገንዘብ የሚነሣሣው ምኞት የስስትና ራስን የመውደድ ኃጢአት ነው። እንዲሁም አንድ ሰው የሌላውን ሰው ገንዘብ ወስዶ ለመጠቀም ቢመኝ፥ ይህን የመሰለው ምኞት የሌብነት ኃጢአት ይሆናል። ለእግዚአብሔር ታላላቅ ሥራዎችን የመፈጸም ፍላጎት ድንቅ ነው። ነገር ግን እንዲህ ያሉትን ተደናቂ ሥራዎችን የምንፈጽመው ታዋቂነትን፥ ዝነኛነትን ለማትረፍ ከሆነ፥ የዚህ ፍላጎት ፍጻሜ ትዕቢትና ራስን የመውደድ ከንቱ ምኞት ሆኖ ይቀራል። እንዲሁም ሥራም ሆነ ትምህርትን ለማግኘት መመኘት መልካም ነው። ዳሩ ግን በቃለ መጠይቅ ወይም በምናቀርበው ማመልከቻ በማጭበርበር ሥራ ለማግኘት አልያም ትምህርት ቤት ለመግባት ብንሞክር፥ ይህ የሥራ ወይም የትምህርት ፍላጎታችን የማጭበርበርና የማታለል ኃጢአት ሆኖ ይቆጠርብናል።  የገዛ ምኞታችን መልሶ እንዲቆጣጠረን በምንፈቅድለት ጊዜና በተለይም ይህን ምኞታችንን ከእግዚአብሔር በላይ አድርገን በምንመለከትበት ወቅት ኃጢአትን እንፈጽማለን። ስለሆነም ለምኞታችን ከእግዚአብሔር አስበልጠን ስፍራ ስንሰጠው እርሱኑ መፈጸም በሕይወታችን ውስጥ ዋናውን ስፍራ ይይዛል። ይህን ምኞት ለመተግበር በምናደርገው ሁሉ ሕይወታችን ወጥመድ ውስጥ ይገባል። ከዚህም የተነሣ ምኞታችንን ለመፈጸም ከአግባብ ውጭ የሆኑ መንገዶችን ወደ መጠቀሙ አዝማሚያ እንሳባለን። ከዚያም አንድ ጊዜ ምኞታችን እንዲያጠምደን ካደረግነው ሐዋርያው ያዕቆብ እንዳለው፥ ምኞት ትፀንሳለች ኋላም ያረዝችው ምኞት ኃጢአትን ትወልዳለች።  የኃጢአት ዋጋ ደግሞ ሞት ነው። በሚቀጥለው ትምህርታችን ውስጥ መለስ ብለን የኃጢአት ዋጋ ሞት ስለ መሆኑ እንማራለን። 2. ለእግዚአብሔር ካለን ምኞት ልቀው የሚገኙ ሦስት የኃጢአት ምኞቶች የሚከተሉት ናቸው፡- ተድላ፥ ቁሳቁሶችና ስኬት (ውጤታማነት) ናቸው።  2.1 1ኛ ዮሐንስ 2፡15-16  ጥያቄ፡- 1ኛ ዮሐንስ 2፡5-16 አንብቡ፡ ሐዋርያው ዮሐንስ ሲናገር ከአባት የማይመጡ ነገር ግን ከዓለም የሚመጡ ብሎ የጠቀሳቸው ሦስቱ ነገሮች ምንድን ናቸው?  ሐዋርያው ዮሐንስ በ1ኛ ዮሐንስ 2፡15-16 ባለው መልእክቱ ሦስት የፈተና ምንጮችን ይገልጻል። እነርሱንም፥ «የሥጋ ምኞት፥ የዓይን አምሮትና የኑሮ ትምክህት» (ቁ. 16) ይላቸዋል። እነዚህ ነገሮች እያንዳንዳቸው በመሠረቱ በእግዚአብሔር የተሰጡና በራሱ መልካም የሆነ ነው። ነገር ግን እያንዳንዳቸው እግዚአብሔር በማይፈቅደው መንገድ በተግባር ላይ ሲውሉ ስሕተት ስለሚሆኑ ድርጊቱ ኃጢአትን መሥራት ነው። የሥጋ ምኞቶች ሲባል እኛን ደስ እንዲያሰኙን የተሰጡን ምግብ፥ መጠጥና ግብረ ሥጋን የመሳሰሉት ናቸው።  እነዚህን ምኞቶች የምንፈጽምበት ተገሲና እግዚአብሔርን የሚያስደስት መንገድ አለ። ነገር ግን እነዚህ የሚያስደስቱንን ነገሮች ያለአግባብ በመጠቀም እንዲቆጣጠሩን ወይም እንዲወስዱን ከፈቀድን ከእግዚአብሔር እንዲበልጡብን እናደርጋቸዋለን። እነዚህ ምኞቶች ከእግዚአብሔር በሚበልጡብን ጊዜ በተሳሳተ መንገድ እንጠቀምባቸዋለን ማለት ነው። ያም ኃጢአት ይሆንብናል። በዚህም ሆዳሞች እንሆናለን፥

ኃጢአት ከየት መጣ?  Read More »