የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ
መንፈስ ቅዱስን፣ አገልግሎቱንና መንፈሳዊ ስጦታዎችን በቅደም ተከተል ያጥኑ።
ስለ ጥናቱ
ይህ የጥናት መምሪያ የሚያተኩረው በቤተ ክርስቲያን እገልግሎት ላይ በተሰማሩ ሰዎች ላይ ሲሆን የጥናት መምሪያውን በብዙ የተለያዩ መንገዶች መጠቀም ይቻላል። በግል የእግዚአብሔርን ቃል ለማጥናትም ሆነ በአዋቂዎች የሰንበት ትምህርት ቤት ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት መጠቀም ይቻላል።
የጥናቱን መመሪያ ያንብቡ
ይሁንና መምሪያው የተዘጋጀው በትምህርት-መለኮት ማስፋፊያ ( ትመማ) መልክ ነው። በመሆኑም ይህ መጽሐፍ መምህርን ተክቶ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርተ-መለኮት ወይም አገልግሎት ለተማሪው ጠቃሚ ትምህርቶችን ያስተላልፋል። ተማሪው በዚህ የጥናት መጽሐፍ እየተመራ ጥያቄዎችን በመመለስና የተማረውን ከሕይወቱ ጋር በማዛመድ በቀን አንድ ሰዓት ያህል ጊዜ ያሳልፋል። ከሁሉም የላቀ ትርፍ የሚገኘው ደግሞ ተማሪዎቹ በሳምንት አንድ ቀን ተሰባስበው የተማሩትን ሲከልሱና የእግዚአብሔር ቃል እንዴት ካሉበት ሁኔታ ጋር እንደሚዛመድ ሲወያዩ ነው።
ምንጭና አጠቃቀም
ጽሑፍ በቲም ፌሎስ፤ ትርጉም በጌቱ ግዛው።
ሙሉ መግለጫውን ያንብቡ
“የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡
የትምሕርቶቹ ማውጫ
ክፍልን ከፍተው ርእስ ይምረጡ።
13 ክፍሎች • 76 ርእሶች
