አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ጉዲፈቻ (የማደጎ ልጅ) 

This entry is part 85 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

በደኅንነታችን ውስጥ ካገኘናቸው በረከቶች መካከል በጣም የሚያስደስተንና የሚያጽናናን የእግዚአብሔር ጎልማሳ ልጆች ከመሆናችን የተነሣ ያለን የተትረፈረፈ የርስት ዋስትና ነው። በዚህ ረገድ እግዚአብሔር አዲስ ሕይወትን፥ ከክርስቶስ ጋር ኅብረትን እንዲሁም ከበደላችን ነፃ መውጣትን የሰጠን ብቻ ሳይሆን በተጨማሪም የራሱ ልጆችና የሰማያዊ ክብር ወራሾችም እንድንሆን መብት ሰጥቶናል። የእግዚአብሔር አዋቂ (ጎልማሳ) ልጆች የመሆን በረከት የ«ጉዲፈቻ የማደጎ ልጅ» መሆን ማለት ነው።  ጥያቄ፡- ኤፌ 1፡5ን አንብብ፡፡ እግዚአብሔር ምን እንድንሆን ነበር የመረጠን?  ጥያቄ፡- ገላ.4፡1-7 አንብብ፡፡ ሀ) ገና ሕፃን ወራሽ የሆነ ልጅ ሁኔታ ምን ይመስላል (ቁ. 1-2)? ለ) እኛስ በዚህ ዓይነት ሁኔታ የነበርነው መቼ ነው? (ቁ 3) ሐ) ክርስቶስ ባዳነን ጊዜ ምንን ተቀበልን (ቈ 5)? መ) አሁን የእግዚአብሔር ልጆች እንደ መሆናችን መጠን በተጫማሪ እግዚአብሔር ምን አድርጎልናል (ቈ 7)?  ጥያቄ፡- ርሜ 8፡14-17 አንብብ። ሀ) በእግዚአብሔር መንፈስ ስለሚመሩት ያለው እውነታ ምንድን ነው (ቈ 14)? ለ) ምን ዓይነት መንፈስ ነው እና ያልተቀበልነው (ቁ 15 )? ሐ) የተቀበልነውስ ምን ዓይነት መንፈስ ነው (ቁ 15)?  መ) ያ መንፈስ ምንን ይመሰክርልናል (ቁ 16)? ሠ) የእግዚአብሔር ልጆች በመሆናችን በተጨማሪ የተረጋገጠልን ምንድን ነው ( 17)?  ጥያቄ፡- ሮሜ 8፡23 አንብቡ። ምንን እንጠባበቃለን?  ስለ ልጅነት ያለውን የደኅንነት በረከት ሁኔታ ከመገንዘባችን በፊት፥ ለለ ልጅነት ወይም እንደ ራስ ልጅ አድርጎ ስለ መቀበል፥ በአዲስ ኪዳን ዘመን የነበረውን ባሕል ማወቅ ይገባናል። ዛሬ በብዙ ባሕሎች በአዲስ ቤተሰቦች ውስጥ ልጆች ለማደጎ የሚወሰዱት የራሳቸው ወላጆች ሳይኖራቸው ሲቀር ብቻ ነው። የአንድ ሕፃን አባት ወይም እናት ሲሞቱ ወይም ልጃቸውን ሲጥሉ፥ በዚህን ጊዜ ለልጁ እንደ ወላጅ የሚሆኑ አዲስ አሳዳጊዎች ልጁን ይወስዱና እንደ ወለዱት ልጅ አድርገው ያሳድጉታል። ሆኖም፥ በአዲስ ኪዳን ዘመን ሮማውያን ያልወለዱትን ልጅ ወስደው ማደጎ የሚያሳድጉበት ለየት ያለ ባሕል ነበራቸው። ይህም አንድ ሰው ልጅ ያልወለደ ከሆነ፣ የሕፃኑ ወላጆቹ በሞት ባይለዩትምና በሚገባ ቢንከባከቡትም እንኳ የሌላ ቤተሰብን ልጅ ተቀብሉ በማደጎ ደንብ እንደ ራሱ ልጅ አድርጎ ያሳድገዋል። አንድ ሮማዊ የሌላውን ቤተሰብ ልጅ በማደጎ ወስዶ የሚያሳድገው ያፈራው ሀብትና ንብረት ወራሽ እንዲሆንለት ነው። ስለዚህ በርማውያኑ ባሕል የሌላውን ልጅ ወስዶ እንደ ራሱ ልጅ አድርጎ የማሳደግ ዓላማ የሀብትና ንብረት ወራሽ እንዲሆን የቤተሰቡ አባል የማድረግ ሂደት ነበር።  1. እንደ ራስ ልጅ በማደጎ ተቀብሎ የማሳደግ ሁኔታ በኃላፊው ዘላለም ውስጥ፡ ኤፌ. 1፡5  አዲስ ኪዳን በእግዚአብሔር ቤተሰብ እንደ ልጅ የተደረግንበትን ሁኔታ በሦስት ደረጃ ዎች ይመለከተዋል። ይህ መንፈሳዊ ሂደት ሦስት መሠረታዊ ደረጃ ዎች ያሉት ሲሆን፥ እያንዳንዱ ደረጃም ልጅ የመደረግ ሂደትን የተለየ አፈጻጸም አጽንኦት ይሰጥበታል። የዚህ እንደ ልጅ ወደ እግዚአብሔር ቤተሰብ የመምጣት ሁኔታ የመጀመሪያው ደረጃ ልጅነታችንን ለማረጋገጥ እግዚአብሔር ቀደም ባለው ዘመን የፈጸመው ተግባር ነው። በኤፌ 1፡5 ላይ «ልጆቹ እንድንሆን አስቀድሞ ወሰነን» ይላል። ሰኛው ትምህርት ላይ እንደተመለከትነው፥ እግዚአብሔር አስቀድሞ ባደረገው ምርግ መሠረት የወራሽነት መብት ሊሰጠን የቤተሰቡ አካል አድርጎ በልጅነት ተቀበለን። ነገር ግን እግዚአብሔር ለውርስ የደረስን ጎልማሳ ልጆቹ አድርጎ እንዴት ይቀበለናል? ዛሬስ የቤተሰቡ አካል አድርጎ ሊቀበለን ምን አድርጎአል?  2. በአሁኑ ደኅንነታችን እንደ ማደጎ ልጅ መሆናችን፡ ገላ. 4፡1-7  ጳውሎስ በገላ. 4፡1-7 ውስጥ እንደተናገረው፥ በኋለኛው ጊዜ እግዚአብሔር እንደ ልጆቹ አድርጎ እንዴት እንደ ተቀበለን ይገልጻል። ገለጻውንም በመቀጠል አንድ ልጅ ምንም እንኳን የወራሽነት መብት ቢኖረውም፣ በሕፃንነት ዕድሜ ባለበት ጊዜ በውርሱ ላይ ሥልጣን እንደሌለውና በዚህን ጊዜ ሁሉም ነገር በሞግዚቶች እጅ እንደሚሆን ያስረዳል። ሕፃኑ በዚህ ዕድሜው በሚገኝበት ጊዜ በአመዛኙ ከባርያ የማይለይ በመሆኑ የዚቶቹ ታዛዥ ሆኖ እንደሚቆይና እንደ ባለ ሙሉ ሥልጣን ወራሽ ሆኖ እንደማይታይ ያላነዝባል። ጳውሎስ እንደሚለው ሁላችንም በእምነት ወደ ክርስቶስ ከመምጣታችን በፊት የነበርንበት ሁኔታ ያን ይመስላል። የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ለመጠራትም ሆነ የእርሱ ወራሾች ለመሆን ምንም ዓይነት ሕጋዊ መብት አልነበረንም። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ሕጋዊ መብት እንዳለው ልጅ ሳይሆን በባርነት ደረጃ ላይ የነበርን ሰዎች ነን። ሙሉ በሙሉ ለዓለም ሥርዓቶች የተገዛን ነበርን።  ጳውሎስ ለዓለም ሥርዓቶች የተገዛችሁ ነበራችሁ ሲል ምን ማለቱ ነው? «ከዓለም መሠረታዊ ትምህርት» ሲል በጊዜው ለዚህ ማብራሪያ በሥራ ላይ የነበረው የግሪክ ቃል የሰማይን አካላት (ክዋክብትንና፡ ፕላኔቶችን) ይቆጣጠራሉ የተባሉ የግሪክ የሐሰት አማልክትንና የዓለምን ሕዝቦች የሚያመለክት ነበር። እነዚህ የሐሰት አማልክት የፍጥረትና የሕዝቦች «መሠረታዊ ተቆጣጣሪ» ኃይላት ነበሩ። በጊዜው ግሪክኛ ይናገሩ የነበሩ አይሁዳውያንም ይህን ቃል እግዚአብሔር በእነርሱ አማካይነት ሕጉን ለሙሴ የሰጠባቸውን መላእክትና (ገላ 3፡19፤ የሐዋ. 7፡53) በዓለም ሕዝቦች ላይ ተቆጣጣሪዎች ናቸው ብለው የሚያምኑባቸውን መላእክት ለመግለጽ ይጠቀሙበት ነበር። የእስራኤል ሕዝብም ሆነ የአሕዛብ የቅርብ ተቆጣጣሪዎች ነበሩ ባይ ናቸው። በዚያን ዘመን የሰዎችን ሕይወት ይቆጣጠራሉ ተብለው የሚታወቁ መሠረታውያን የዓለም ትምህርቶች ክፉና መልካም መላእክትን የሚያጠቃልሉ ኃይላት ነበሩ። ጳውሎስ ሊል የፈለገው አንድ ጊዜ እኛ በእነዚህ መናፍስት ኃይላት ቁጥጥር ሥር ነበርን፥ ዛሬ ግን ነፃ ነን ለማለት ነው። እውነትም ከአጋንንታዊ ኃይላት ማለትም ግሪኮች ይሰግዱላቸው ከነበሩት ዓይነት ሐሰተኛ አማልክት ቁጥጥር ነፃ ነን። ደግሞም መልካም በሆኑ መላእክት ከተሰጡት ሕጎች ቁጥጥር ነፃ ነን። ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት እንዲኖረን መልካም ይሁኑ ክፉዎች የማናቸውም መናፍስት ኃይላት አማላጅነት አያስፈልገንም። ስለዚህ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ሊያደናቅፉብን አይችሉም። ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት እንዲኖረን እንደ ግርዛት ያሉትን የአይሁዳውያንን ሥርዓት ከመከተል ነፃ ነን።  ከእነዚህ መናፍስት ኃይላት ነፃ የሆንነው እንዴት ነው? እግዚአብሔር ጌታ ኢየሱስ ሰው ሆኖ እንዲወለድ በላከው ጊዜ፥ የሕግ ባሪያዎች ከመሆን አድኖ እንደ ልጆቹ አድርጎ በመቀበል የቤተሰቡ አካል አደረገን። እንደ ጎልማሳ ልጆች መብትን ሰጠን። ከዚያ በፊት በመናፍስት ኃይላት ቁጥጥር ሥር የነበርንና የሌላ ቤተሰብ አካል ነበርን። አይሁዳውያን በሙሴ ሕግ ሥርዓት ሥር ነበሩ። ነገር ግን ::ግዚአብሔር እኛን እንደ ራሱ ልጆች የቤተሰቡ አካል አድርጎ ተቀበለን። ለውርስ የምንበቃ ጎልማሳ ልጆቹ አድርጎ የወራሽነት መብትን ሰጠን። መንፈስ ቅዱስም በውስጣችን አድሮ እኛ የእርሱ ቤተሰብ አካል መሆናችንን እንዲያሳስበንና እንዲያረጋግጥልን አደረገ። በዚሁ መሠረት እግዚአብሔር የመለኮታዊ ውርሱ ወራሾች እንድንሆን ጎልማሳ ልጆች አደረን።  ጥያቄ፡- ሀ) በአካባቢአችሁ የሚኖሩ ሰዎች በምን አኳኋን የመናፍስት ኃይላትን አማላጅነት ይሻሉ? ለ) ይህ ክፍል ለእነዚህ ሰዎች ምን መልእክት ይሰጣቸዋል? ሐ) በእናንተ አካባቢ ያሉ ሰዎች የብሉይ ኪዳንን ሥርዓተ አምልኮ መከተል እንደሚገባቸው የሚያስቡት በምን አኳኋን ነው? መ) ይህ ክፍል ለእዚህ ሰዎች ምን ትምህርት ይሰጣቸዋል? ገላ. 3፡23-25 እና 5፡1ን አንዳንድ አሳቦችን ላለመጨበጥ ያክል ተመልከት።  ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ሰዎች በመናፍስት ኃይል ቁጥጥር ሥር ያሉ ይመስላቸዋል። ብዙ ሰዎች መንፈሳዊ ኃይላትን ማክበርና የሕይወትን በረከት ለማግኘት፥ እንደዚሁም ከሚያጋጥማቸው ሁሉ ለመጠበቅ የመንፈሳዊ ኃይላት አማላጅነት የሚያስፈልጋቸው አድርገው ያምናሉ። ሌሎች ሰዎች ደግሞ መላእክትን ማክበርና ለአማላጅነት እነርሱን ለመማጠን ወደ እነርሱ ዘንድ መቅረብ እንዳለባቸው ይሰማቸዋል። አንዳንዶቹ ደግሞ ለመናፍስት ስጦታና መሥዋዕት ማቅረብን ተግባራቸው አድርገው ይይዛሉ፡ አንዳንድ ሰዎች እንዲጠብቋቸው ወይም በረከት እንዲያገኙ ለመናፍስት ማለትም ውቃቢ ወይም ዛር ስጦታና መባ ማቅረብ እንዳለባቸው ይሰማቸዋል። እርግጥ ሰዎች ክርስቶስን እንደ መድኃኒታቸው አድርገው ከመቀበላቸው በፊት እነዚህ ክፉ መናፍስት ተጽዕኖ ሊያደርጉባቸው ችለው ይሆናል። ነገር ግን ገላ. 4፡1-7 እንደሚነግረን፥ ማንኛውም ሰው አንዴ በክርስቶስ ካመነ በኋላ በመናፍስት ቁጥጥር ሥር ሊውል አይችልም። ያመኑ ሰዎች የመላእክትንም ሆነ የሌሎች መናፍስትን አማላጅነት አይሹም። ስጦታም ሆነ መሥዋዕት ለመናፍስቱ ማቅረብ አይኖርባቸውም። እግዚአብሔር ከማንኛውም መናፍስት ባርነት ነፃ አውጥቶ የቤተሰቡ አካል አድርጎአቸዋል። እግዚአብሔር እንደ ጎልማሳ ልጆቹ በመቀበል ለተትረፈረፈ ውርሱ ወራሾች አድርጎአቸዋል። ልጆቹ መሆናቸውንም እንዲያረጋግጥላቸው መንፈስ ቅዱስን ሰጥቶአቸዋል። እግዚአብሔር እኛን እንደ ልጆቹ ተቀብሎ የቤተሰቡ አካል አደረገን ማለት በምንም ዓይነት (ከአሁን ወዲያ እኛ) በክፉ መናፍስት ቁጥጥር ሥር ልንሆን አንችልም ማለት ነው።  ዛሬም ቢሆን በኢትዮጵያ ውስጥ አንዳንድ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ለመቀራረብና ቤተኛ ለመሆን የብሉይ ኪዳንን ሥርዓተ

ጉዲፈቻ (የማደጎ ልጅ)  Read More »

ጽድቅና ይቅርታ፥ ክፍል አንድ 

This entry is part 84 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

የደኅንነት በረከተች – ክፍል 2  በትምህርት 11ና 12 ውስጥ ከኃጢአታቸው የተነሣ በሰዎች ስለሚደርሰው አላከሪ ሁኔታ ተመልክተናል። በመጀመሪያ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች ሆነው በመወለዳቸው፥ እንደዚሁም በዮላቸው ኃጢአት ከመሥራታቸው ሁሉም በመንስ ሞተዋል! ደሞ በሥጋ ይሞታሉ። ሁለተኛ፤ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኛነትን ባሕርይ ይዘው ስለ ተወለዱና በየግላቸውም ኃጢአትን በመሥራታቸው፥ ሁሉም በእግዚአብሔር ፊት ከኃጢአታቸው የተነሣ በደለኞች ናቸው። ነገር ን እግዚአብሔር እነዚህን የኃጢአት ውጤቶች ሁሉ የምናሸንፍበትን ብዙ አስደናቂ የደኅንነት በረከቶችን ሰጥተናል። ባለፈው ሳምንት ስለ እነዚህ የደኅንነት በረከቶች አጥንተናል። በጥናታችንም ጊዜ ሰዎች በእምነት ንስሐ ሲገቡና ወደ እግዚአብሔር ሊመለሱ፥ እርሱም ከክርስቶስ ጋር በሚያደርጉት ኅብረት አዲስ ሕይወትን የሚሰጣቸው መሆኑን ተገንዝበናል። በክርስቶስ አዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትም ዳግም መወለድ በኃጢአት ምክንያት ለመጣው የመጀመሪያ ችግር መፍትሔ የሚሰጥ ነው። እግዚአብሔር በመንፈስ ለሞቱት ሕያውነትን ይሰጣል! እንደዚሁም በሥጋቸው ለሞቱ የዘላለም ሕይወትን ለመስጠት ቃል ይገባል። ነገር ን ኃጢአት በሰዎች ላይ ሞትን ብቻ እያስከትልም፥ አክሎም በሰዎች ሁሉ ላይ በዴላን ያመጣና ከእግዚአብሔር ይለያቸዋል። በዚህ ሳምንት የደኅንነት በረከቶች ስለሆኑት ስለ መጽደቅና ይቅርታ እንዲሁም ስለ እግዚአብሔር ልጅነትና ቅድስና እንማራለን፡ መጽደቅና ይቅርታ ከበደላችን እኛን ነፃ በድረ በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኞች ያደርጉናል። የእግዚአብሔር ልጅነትና ቅድስና ደሞ እኛን የእግዚአብሔር ቤተሰብ አካል በማድረግና ከኃጢአት በመለየት በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ እንድንገባን እንድንደሰት ያደርጉናል።  ጽድቅና ይቅርታ፥ ክፍል አንድ  ሰዎች ከሚሸከታቸው ሸክሞች አንዱ የኃጢአት በደል ነው። በትምህርት 1 እና 2 ውስጥ እንደ ተመለከትነው፥ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች ሆነው ተመልፍል፡ ሰኞች ሁሉ ኃጢአትን ይሠራሉ፡ ሁላችንም በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች መሆናችንን እናውቃለን። የኃጢአታችን በደል ስለ ወደፊቱ ሁኔታ ትልቅ ፍርሃትና መጠራጠርን ያስከትልብናል። ብዙ ሰዎች እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን ይቅር እንደሚላቸው እርግጠኞች አይደሉም፡፡  1ኛ ጥያቄ፦ ስለታውቃቸው ሰዏች አስብ። ሀ) አንድ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን የህነን ሰው እግዚአብሔር ፍርፋን በሚሰጥበት ጊዜ ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል+ በምንም ኃጢአት ስለኛ አይደለህም እንደሚለው እርጠኛነቱን የምትጠይቀው ቢሆን ን የሚል ይመስልሃል? ሀ) እንዲሁም አንድ ሙስሊም የሆነን ሰው እግዚአብሔር ፍርፋን በሚሰጥበት ጊዜ ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል፥ ምንም ዓይነት የኃጢአት በደል የለብህ” እንደሚለው እርጠኝነቱን የምትጠይቀው ቢሆን ምን ምላሽ ይሰጥህ ይሆን? ሐህ አን፥ የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን አባል የሆነን ሰው እዚአብሖር በሚፈርድበት ጊዜ ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል፥ ምንም ዓይነት የኃጢአት በደል የለህም እንደሚለው እርግጠኛነቱን የምትጠይቀው ቢሆን ምን ምላሽ ይሰጥ ይሆን?  ዛሬ ብዙ ሰዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ፈራጅ በሆነው በእግዚአብሔር ፊት በሚቆሙበት ጊዜ የኃጢአታቸውን ይቅርታ እንደሚቀበሉ እርግጠኛች አይደሉም። እንዴዚሁም እግዚአብሔር በእርሱ ዘንድ መጽደቃቸውን እንደሚያውጅላቸው እርግጠኞች አይደሉም። ብዙ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ይቅር ባይነት እርገጠኞች ነን ብሎ መናገርን እንደ አጉል ድፍረትና እብሪት ይቆጥሩታል። ብዙ ሰዎች ደግሞ በርካታ ኃጢአት መሥራታቸው ይሰማቸዋል። ስለዚህ ተስፋ የሚያደርጉት እግዚአብሔር በምሕረት ዓይኑ ተመልክቶ ኃጢአታቸውን እንደሚተውላቸው ነው። ሌሎች በርካታ ሰዎች ደግሞ እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን ይቅር እንዲላቸው የእግዚአብሔርን ሕግ ለመፈጻም እንደሚጣጣሩና እግዚአብሔርም ይህን መልካም ምግባራቸውን አስቦ ይቅር እንደሚላቸው ተስፋ ያደርጋሉ። በአንጻሩ ደግሞ ብዙ ሰዎች እግዚአብሔር ፈራጅ ሆኖ ሲመጣባቸው ምን ሊደርስ እንደሚችል ማሰብ አይፈልጉም። የኃጢአት በደል እንዳለባቸው ያውቃሉ፣ ሆኖም የኃጢአታቸው ውጤት ምን እንደሚያመጣባቸው ማዕብ አይሹም፡፡  ነገር ግን እግዚአብሔር ለአማኞች ሁሉ በደኅንነታቸው ውስጥ አስደናቂ በረከትን ሰጥቶአቸዋል። ይህ በረከትም የኃጢአት ይቅርታና ጽድቅ ነው። «ጽድቅ» ማለት እግዚአብሔር፥ በኢየሱስ የሚያምኑ ሁሉ ከኃጢአትና ከበደል ነፃ ናቸው ብሎ አውጆአል ማለት ነው። ጽድቅ ማለት በኢየሱስ ለሚያምኑት ሁሉ እግዚአብሔር ለኃጢአታቸው ይቅርታን ይሰጣቸዋል፥ ከእርሱ ጋር የታረቁ መሆናቸውንም በይፋ አስታውቋል ማለት ነው። ባለፈው ሳምንት እግዚአብሔር በሚያድነን ጊዜ ሁለት በረከቶችን እንደምንቀበል ተነጋግረን ነበር። እነዚህም ዳግም መወለድና ከክርስቶስ ጋር መተባበር ናቸው። እግዚአብሔር አዲስ መንፈሳዊ ሕይወትን በመስጠት ከእርሱ ጋር እና ለዘላለም ሐሰት በማድረግ ሕይወት እንድንኖር አዲስ ሰው አድርጎ በመመለስ ብቻ አላበቃም። ከእርሱ ጋር አንድ እንድንሆን የተባበርን ብቻ አይደለንም፥ ነገር ግን እግዚአብሔር የኃጢአት ይቅርታን በመስጠት ከኃጢአታችን ነፃ መሆናችንንም ያስታውቃል። እኛ በእርሱ ዘንድ መጽደቃችንንም ይፋ ያደርገዋል። በዚህም እግዚአብሔር መጽደቃችንን ያረጋግጥልናል።  ጥያቄ፡- ሮሜ 3፡20-26 አንብብ። በዚህ ክፍለ ምንባብ ውስጥ ስለ ጽድቅ ልታገኝ የምትችለውን እውነት አንድ በአንድ ጻፍ።  ጥያቄ፦ ገላ. 2፡16፥ 21ና 3፡6፥ 11-13፣ 24 አንብብ። ሀ) ላው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ የማይሆነው እንዴት ነው? ለ) ሰው በእግዚአብሔር ፊት የሚጸድቀውስ እንዴት ነው? ሐ) ሰው በሕግ የሚጸድቅ ከሆነ (ገላ 3፡6)፥ ክርስቶስ ሞት እውነትነት ምን በሆነ ነበር? ) ክርስቶስ እኛን ለማዳን ምን ደረሰበት (ገላ 2፡21)?  ጥያቄ፡- ሉቃስ 18፡9-14 አንብብ። ሀ) በእግዚአብሔር ፊት ከሁለቱ ሰዎች የትኛው ጽድቅን አገኘ? ለ) ሌላኛው ላይሆን ይሄኛው ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጽድቅን ማግኘቱ በምን ምክንያት ነው?  ዮሐንስ 3 ስለ ዳግም መወለድ ቁልፍ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንደሆነ ሁሉ፣ ሮሜ 3ም ጽድቅን በተመለከተ ቁልፍ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው። ዛሬና ነገ ስለ ጽድቅ የሚናገሩ ብዙ ክፍሎችን እናጠናለን፡ ሆኖም ውይይታችንን የምንከፍተው በርማ ምዕራፍ 3 ይሆናል። እነዚህ ክፍሎች ስለ ይቅርታና ስለ ጽድቅ ስምንት ጠቃሚ እውነቶችን እንደሚያስተምሩን እናጠናለን።  1. ለእግዚአብሔር ሕግ በመታዘዝ ማንም በእግዚአብሔር ፊት የሚጸድቅ የለም።  ሮሜ 3፡20 ሐዋርያው ጳውሎስ ከሮሜ 1፡18 ጀምሮ ለሰጠው ትምህርት እንደ ማጠቃለያ የተጠቀመበት ክፍል ነው። ይህም ማንም ሰው ሕግን በመፈጸም አይጸድቅም የሚለው ነው። ሰዎች ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋል። ሁሉም የእግዚአብሔርን ሕግ ጥሰዋል። ይህ ሕግም በሙሴ አማካይነት ለአይሁድ የተሰጠ ሕግ ወይም እግዚአብሔር በሰዎች ሁሉ ሕሊና ላይ የጻፈው ሕግ ሊሆን ይችላል (ሮሜ 2፡14-15)። ሁሉም የበደሉ በመሆናቸውና የእግዚአብሔርንም ሕግ ስለ ጣሱ፣ ሕግን በመጠበቅ ማንኛውም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሊሆን አይችልም። በሮሜ 3፡20-26 ባለው ክፍል ስለ ጽድቅ የምንማረው የመጀመሪያው እውነት ሕግን በመጠበቅ ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሊሆን እንደማይችል ነው። ጳውሎስ ይህን እውነት ለገላትያ ሰዎች ደግሞ ሊነግራቸው፥ ማንም ሰው ሕግን በመፈጸም እንደማይድን አሳስቦአቸዋል (ገላ. 2፡16፤ 3፡11)። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ አንድ ሰው ሕግን በመጠበቅ የሚጸድቅ ቢሆን ኖሮ፣ የክርስቶስ ሞት ከንቱ በሆነ ነበር (ገላ. 2፡21)። ሕግን በመጠበቃችን በእግዚአብሔር ዘንድ ብንጸድቅ ኖሮ፣ ክርስቶስ በመስቀል ላይ መሞት ባልተገባው ነበር።  ጥያቄ፡- እንተ የምታውቃቸው ሰዎች ለእግዚአብሔር ሕግ በመታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት እንዲጸድቁ የሚያደርጉት ጥረት ምንድን ነው?  ዛሬ ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ሕግ በመጠበቅ በእግዚአብሔር ዘንድ ጻድቅ ለመሆን ይጥራሉ። አንዳንድ ሰዎች ሕጎችን ሁሉ ለመጠበቅ ይጣጣራሉ። ነገር ትን ችግሩ ማንም ሰው ሕጎችን ሁሉ አሟልቶ መጠበቅ ወይ መታዘዝ አይችልም (ሮሜ 3፡9-10 እና 19-20)። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ እንድ ዝረት ወይም ጥምቀት ያሉትን ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችን በመፈጻም በእግዚአብሔር ዘንድ ሊጸድቁ ይሻሉ። ነገር ግን ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችን በመፈጸም ለመጽደቅ መሞከር፥ በእግዚአብሔር ዘንድ እኛን በማጽደቅ ፈንታ ከእግዚአብሔር ይለዩናል (ገላ. 5፡2)። ሌሎች ሰዎች ደግሞ በጸሎት፥ በጾምና የዚህን ዓለም ደስታ ሁሉ በመናቅ ጽድቅን ይሻሉ። ምንም እንኳን መንፈሳዊ ሥርዓት ክርስቲያናዊ ሕይወትን ለመኖር አጋዥ ቢሆንም፥ በእግዚአብሔር ዘንድ ጽድቅ ሆኖ ሊቆጠርልን አይችልም። ማንም ሰው ቢሆን ሕግን በመጠበቅ በእግዚአብሔር ዘንድ ሊጸድቅ እንደማይችል የመጽሐፍ ቅዱስ አቋም ግልጽ ነው። 2. በእግዚአብሔር ዘንድ ጽድቅ የሚገኘው በእምነት ነው።  ሮሜ ምዕራፍ 3 የተጻፈው ቃል እንደሚያረጋግጥልን ከሆነ፥ በእግዚአብሔር ፊት ሊያጸድቅ የሚችል ሌላ መንገድ አለ። ይህ መንገድም አሁን በእግዚአብሔር የተገለጠ ነው። ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ ስለ መጽደቅ የሚያስገነዝበው ሌላው መንገድ ምንድን ነው? ይህ መንገድ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኝ ነው። ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምን ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ጻድቃን ይሆናል (ሮሜ 3፡22)። በሮሜ 3፡20-26 ባለው ክፍል ስለ ጽድቅ የምንማረው ሁለተኛው እውነት በእምነት በእግዚአብሔር ፊት እንደምንጸድቅ መታወቁ ነው። ጳውሎስ ለዚህ እውነት በገላትያ መልእክቱም ላይ አጽንዖት ሰጥቶታል። ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ ባላቸው እምነት ይጸድቃሉ (ገላ. 2፡16፤ 3፡24)፤ ልክ አብርሃም እንደጸደቀው ማለት ነው (ገላ. 3፡6)። በእምነታቸው ጻድቃን

ጽድቅና ይቅርታ፥ ክፍል አንድ  Read More »

ከክርስቶስ ጋር መተባበር – ከክርስቶስ ጋር የመተባበር በረከቶች ምንድን ናቸው? 

This entry is part 82 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

በትናንትናው ዕለት ከክርስቶስ ጋር መተባበር ምን ማለት እንደሆነ ማጥናት ጀምረን ነበር። በጥናታችን ወቅትም ከክርስቶስ ጋር መተባበር ማለት ከክርስቶስ ጋር ሞተን የተነሣን፥ እግዚአብሔር ክርስቶስን በሚመለከትበት ዓይኑ እንደሚያየን፥ ክርስቶስ በውስጣችን እንደሚኖርና እኛም በምድር ላይ የሚታየው የክርስቶስ አካል መሆናችንን አስተውለናል። ይህ ከክርስቶስ ጋር የምንተባበርበት እያንዳንዱ ሁኔታ አስደናቂ በረከት ነው። ሆኖም አማኞች ከክርስቶስ ጋር ባላቸው ኅብረት የተነሣ የሚመጡ ብዙ የተትረፈረፉ በረከቶችም አሉ። እንደ እውነቱ ከሆነ እያንዳንዱ የደኅንነት በረከት ከክርስቶስ ጋር ካለን ኅብረት ጋር የሚዛመድበት ሁኔታ አለ። ዛሬ የምናጠናው ክፍል ከክርስቶስ ጋር ባለን ኅብረት ስለምናገኛቸው በረከቶች ይሆናል።  1. ከክርስቶስ ጋር ባለን ኅብረት ምክንያት እግዚአብሔር ማንኛውንም መንፈሳዊ በረከት ይሰጠናል።  ጥያቄ፡– ኤፌ 1፡3 አንብብ። በክርስቶስ ኢየሱስ የተባረክነው በምንድን ነው?  ኤፌ. 1፡3-14 ያለው ክፍል እግዚአብሔር ወደ እርሱ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚመጡት ሁሉ ስለሚያደርገው ተግባር በሚገባ ገልኦ የሚያስረዳ ነው። ስለዚህ ኤፌ. 1፡3 የመላው አንቀጽ ማጠቃለያ አሳብ ነው፦ ከክርስቶስ ጋር ባለን ኅብረት የተነሣ እግዚአብሔር ስለ ሰጠን በረከት ሁሉ ሐዋርያው ጳውሎስ አምላኩን ያወድሳል። ስለሆነም እኛ ከክርስቶስ ጋር ኅብረት የሌለን ቢሆን ኖሮ ምንም ዓይነት መንፈሳዊ በረከቶችን ማግኘት አንችልም ነበር። ስለዚህ ከክርስቶስ ጋር ኅብረት ያለን ስለሆንን ልናስበው የምንችለውን በረከት ሁሉ የማግኘት ዕድል አለን። ከክርስቶስ ጋር ኅብረት ስላለን እግዚአብሔር መረጠን (ቁ 4)። ከክርስቶስ ጋር ኅብረት ስላለን እግዚአብሔር ልጆቹ አድርጎ ተቀበለን (ቁጥር 5)። እንደዚሁም ከክርስቶስ ጋር ባለን ኅብረት እግዚአብሔር ተቤዥን (ቁ 7)። ደግሞም ከክርስቶስ ጋር ባለን ኅብረት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ሰጠን (ቁ 13)። ያገኘናቸውን በረከቶች ሁሉ ልናገኝ የቻልነው ከክርስቶስ ጋር ካለን ኅብረት የተነሣ ነው።  ከክርስቶስ ጋር ባለን ኅብረት ምክንያት ያገኘናቸውና አዲስ ኪዳን የሚጠቅላቸው ሌሎች አንዳንድ በረከቶች ምንድን ናቸው?  1.1 ከክርስቶስ ጋር ኅብረት ስላላን እግዚአብሔር ይቅር ይለናል፥ ደግሞም በበደላችን እንደማንቀጣም ተስፋ ይሰጠናል።  ጥያቄ፡- ሮሜ 8፡1 አንብብ። በክርስቶስ ኢየሱስ ስላሉት እውነተኛው ነገር ምንድን ነው?  ጥያቄ፡- ኤፌ 4፡32 አንብብ። እኛ በክርስቶስ ኢየሱስ በመሆናችን እግዚአብሔር ምን አደረገልን?  ከክርስቶስ ጋር ኅብረት ያለን በመሆናችን እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር ከማለቱም በላይ በኃጢአታችን ምክንያት በደለኞች እንደማንባል አስታውቋል። ኤፌ. 4፡32 እኛ በክርስቶስ በመሆናችን እግዚአብሔር ይቅር ብሎናል ይላል። በሮሜ 8፡1 ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት ያላቸው ኩነኔ የለባቸውም ይላል። ከክርስቶስ ጋር ኅብረት ያለን በመሆናችንና ከእርሱ ጋር አንድ ስለሆንን፥ እግዚአብሔር ኃጢአታችንን አይቆጥርብንም። ደግሞም ከኃጢአታችን የተነሣ በደለኞች ሆነን እንደማንታይ እግዚአብሔር ራሱ ተስፋ ሰጥቷል። እኛ በደለኞች ሆነን ስላለመታየታችንና በዚህም ምክንያት ቅጣት እንደማይደርስብን የሚያውጀውን ክፍል በሚመጣው ሳምንት የጽድቅ በረክት የሚለውን በምናጠናበት ጊዜ እንማረዋለን፡፡ 1.2 ከክርስቶስ ጋር ኅብረት ያላቸው ሁሉ የእግዚአብሔር የተለየ ሕዝብ አካል ከመሆናቸውም በላይ እግዚአብሔር ተስፋ የሰጠበት የሰማይ ክብር ወራሾች ይሆናሉ።  ጥያቄ- ኤፌ 2፡13፥ 19 አንብብ። አሕዛብ ከክርስቶስ ጋር በመተባበራቸው ምን አገኙ?  ጥያቄ፡– ኤፌ 3፡6 አንብብ። አሕዛብ በኢየሱስ ክርስቶስ» በመሆናቸው ከእስራኤላውያን ጋር ምንን ይካፈላሉ?  ጥያቄ፦ ገላ. 3፡28-29 አንብብ። የክርስቶስ የራሱ ከሆኑ፣ እነዚህ የእግዚአብሔር ተስፋ መራሽ የሆኑ ሕዝብ ሁሉ እንዴት ያሉ ናቸው?  ጥያቄ፦ ሮሜ 8፡17 አንብብ። ከክርስቶስ ጋር ወራሾች በመሆናችን ምን የተረጋገጠልን ነገር አለ?  ጥያቄ፦ ቆላ 1፡27 አንብብ። ክርስቶስ በውስጣቸው ያለ ምን አላቸው?  ጥያቄ፦ 1ኛ ጴጥ. 5፡10 አንብብ። በክርስቶስ ወደ ምን ተጠርተናል?  በብሉይ ኪዳን ዘመን፥ የእግዚአብሔር ምርጥ ሕዝብ እስራኤላውያን ነበሩ፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ብዙ መንፈሳዊ ስጦታዎችን የሰጣቸው ሲሆን፥ ብዙ የተለዩ ተስፋም ገብቶላቸው ነበር። ነገር ግን አሁን፣ በክርስቶስ አማካይነት ወደ እግዚአብሔር የሚመጡ ሁሉ የእግዚአብሔር የራሱ ሕዝብ አካል የመሆን መብት አላቸው። አሕዛብ በኢየሩሳሌም ባለው መቅደላ ወደ ቅድስቱ መግባት አይፈቀድላቸውም ነበር። ለዚህ ምክንያቱ አይሁዳውያን አሕዛብን ርኩሶችና ከእግዚአብሔር የተለዩ ሰዎች አድርገው ይጥሯቸው ስለነበረ ነው። ነገር ግን በኤፌ 2፡13 እና 19 ውስጥ እነዚሁ አሕዛብ ከክርስቶስ ጋር ባላቸው ኅብረት ምክንያት አሁን የእግዚአብሔር ሕዝብ አካል መሆናቸውን ራሱ እግዚአብሔር ይናገራል። በክርስቶስ ደም አማካይነት ወደ እግዚአብሔር ቀርበዋል፤ ከዚህም የተነሣ በእዚአብሐር ሕዝብ መካከል ከእስራኤላውያን ጋር አቻ ዜጎችም ሆነዋል። ኤፌ 3፡6 ከእስራኤላውያን ጋር እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሰጣቸው ተስፋዎች ሁሉ ወራሽ ሆነዋል ይላል። ገላ. 3፡28-29 ከክርስቶስ ጋር ኅብረት ያላቸው ሁሉ እንደ እግዚአብሔር ልዩ ሕዝብ አንድ ሆነዋል፤ ስለዚህ በአይሁዳዊና በአሕዛብ፥ በአገልጋይና በጌታ፥ በወንድና በሴት ልዩነት የለም ይላል። ሁሉም የእግዚአብሔር ሕዝብ አካል ናቸው። ሁሉም ከእግዚአብሔር ሕዝብ ውርስ ተካፋዮች ናቸው።  ከክርስቶስ ጋር ኅብረት ያላቸው የሚካፈሉት እጅግ በጣም የላቀው ተስፋ የሰማይ ክብር ተስፋ ነው። ቆላ. 1:27 ላይ የተጻፈው ቃል ባለፉት ዘመናት ተሰውሮ የነበረውን ምሥጢር እግዚአብሔር ገለጠው ይላል። ይህም ክርስቶስ አሁን ከአሕዛብ ጋር ኅብረት ስላለውና በእነርሱም ውስጥ ስለሚያድር እነርሱም ሳይቀሩ የሰማያዊ ክብር የተስፋ ቃል ተጠቃሚዎች ናቸው። በሮማ 8፡17 ከክርስቶስ ጋር ወራሾች የሆኑ ሁሉ የክብሩ ተካፋዮች ለመሆናቸው እርግጠኞች ናቸው ይላል። በ1ኛ ጴጥ. 5፡10 እግዚአብሔር የክርስቶስ የሆኑትን ወደ ዘላለማዊ ክብሩ ጠርቷቸዋል ይላል። ከክርስቶስ ጋር የሚኖር ኅብረት ከእግዚአብሔር ከራሱ ሕዝብ ተገልለው የነበሩትን የራሱ የሰማያዊ ልዩ ሕዝብና የክብሩ ተስፋ ወራሾች ያደርጋቸዋል።  1.3 ከክርስቶስ ጋር ኅብረት ያላቸውን እግዚአብሔር ከሕግ ነፃ ያደርጋቸዋል።  ጥያቄ፡- ገላ. 2፡4 አንብብ። በዚህ ክፍል ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ የሚጠቅሰው ስለ የትኛው ዓይነት ነጻነት ነው?  ጥያቄ፡- ገላ 5፡6 አንብብ። «በክርስቶስ ዘንድ» ዋጋ ቢስ የሆነ ነገር ምንድን ነው?  ሦስተኛውና ከክርስቶስ ጋር በመተባበር የሚገኘው በረከት፥ ከብሉይ ኪዳን የሕገ ሥነ ሥርዓት ነፃ መውጣት ነው። በገላትያ መልእክት ውስጥ እንደምናነበው ሐሰተኞች መምህራን ወደ ክርስቲያኖች ዘንድ መጥተው ስለ ደኅንነታቸው በክርስቶስ ብቻ ማመን በቂ እንዳልሆነ ይነግሩአቸው ነበር። ክርስቲያናዊ እምነታቸው የተሟላ ይሆን ዘንድ፥ መገረዝና በሙሴ ሕግ ውስጥ የተጠቀሱትን ሥነ ሥርዓቶች መፈጸም እንዳለባቸው ነገሩዋቸው። ጳውሎስ ግን ይህን የሐሰት ትምህርት አጥብቆ ተቃወመ። በዚህ ምክንያት ሙሉውን የገላትያ መልእክት የጻፈው በዳኑ ጊዜ ከክርስቶስ ጋር የመተባበራቸው እንደኛው ውጤት ከሕግ ሥርዓት ነፃ እንዳደረጋቸው ለማሳሰብ ነበር፡ በገላ. 2፡4 ውስጥ ጳውሎስ ሲያስነዝባቸው አንዳንድ ሐሰተኛ ወንድሞች ከክርስቶስ ጋር ካላቸው ኅብረት የተነሣ የተቀዳጁትን ነጻነት ስላዩ መልሰው የሙሴ ሕግ ተገዢዎች ሊያደርጉአቸው እንደ ፈለጉ ነገራቸው። ጳውሎስ በገላ. 5፡6 ውስጥ ሲናገር፣ የግርዛት ሥነ ሥርዓት ተካፋዮችም ይሆኑ ወይም ሳይገረዙ ይቅሩ ይህ ምንም እንደማያጎድልባቸውና የሚጠቅመው በውጪአዊ የፍቅር ድርጊት አማካይነት ራሱን የሚገልጽ እምነት መያዝ መሆኑን ያስገነዝባቸዋል። በክርስቶስ የሚያምኑ ሁሉ ከክርስቶስ ጋር የተባበሩ ስለሆኑ ደኅንነታቸውን ለማሟላት ወይም ራሳቸውን የበለጠ ቅዱላን ለማድረግ እንደ እርዛት ያለ ተግባር መፈጸም አይኖርባቸውም። በዚህ ፈንታ በእግዚአብሔር በማመንና ሌሎችን በመውደድ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው በየጊዜው ማደግ ይጠበቅባቸዋል። በአንጻሩ፣ ክርስቲያኖች ለአይሁድ ሕግ ከመታዘዝ ነፃ ናቸው ሊባል እንደ ፈለጉት ይኖራሉ ማለትም አይደለም። ነጻነታችንን በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድና ኃይል መሠረት በመጠቀምና እርስ በርሳችን አንዱ ሌላውን በማገልገል በተግባር ልንገልጠው ይገባል (ገላ. 5፡13 እና 16)።  1.4 ከክርስቶስ ጋር ኅብረት ላላቸው፥ እግዚአብሔር መንፈሳዊ ግንዛቤን ይለግሳቸዋል።  ጥያቄ፡- 2ኛ ቆሮ. 3፡14 አንብብ። በክርስቶስ የተወገደው ምንድን ነው?  ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮ. 1፡4-5 አንብብ። የቆሮንቶስ ሰዎች በክርስቶስ በመሆናቸው ምን አገኙ?  አማኞች ከክርስቶስ ጋር በሚተባበሩበት ጊዜ እግዚአብሔር ቀድሞ ያልነበራቸውን መንፈሳዊ ግንዛቤና የቃሉን እውቀት ይሰጣቸዋል። በ2ኛ ቆሮ. 3፡12-18 ውስጥ የአይሁድ ሕዝብ በምን ምክንያት ስለ ክርስቶስ እውነተኛውን ነገር እንዳልተገነዘቡ ጳውሎስ ሲገልጽ ሙሴን እንደ ምሳሌ አድርጎ ይጠቀማል። እንደዚሁም ጳውሎስ በመቅጠል ሙሌ ወደ እግዚአብሔር ቀርቦ ክብሩን ካየ በኋላ የእግዚአብሔር ክብር መንጸባረቅ ከፊቱ በሚወጣበት ጊዜ እስራኤላውያን እንዳያዩ ፊቱን ሸፍኖ እንደ ነበረ ለአንባቢዎቹ ያስታውሳቸዋል። ከዚያ ወዲህም ቢሆን የብሉይ ኪዳንን በሚያነቡበት ጊዜ የፊታቸው መሸፈኛ አይለያቸውም ነበር ይላል። አይሁዶች ብሉይ ኪዳን ሲነበብ በሚያዳምጡበት ጊዜ፥ ክብሩ ከፊል፣ ያልተሟላና እየደበዘዘ መሆኑ አይገባቸውም ነበር። አርጌው ኪዳን በክርስቶስ መፈጸም

ከክርስቶስ ጋር መተባበር – ከክርስቶስ ጋር የመተባበር በረከቶች ምንድን ናቸው?  Read More »

ከክርስቶስ ጋር መተባበር – ከክርስቶስ ጋር መተባበር ማለት ምን ማለት ነው? 

This entry is part 83 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ክርስቲያኖች ሊደሰቱበት ከሚገባቸው እጅግ በጣም ጥልቅና ምሥጢራዊ የሆኑ የደኅንነት በረከቶች አንዱ ከክርስቶስ ጋር የሚኖራቸው ኅብረት ነው። በአንድ አኳኋኑ ሲታይ ከክርስቶስ ጋር ኅብረት ሲባል፥ የደኅንነትን በረከቶች ሁሉ የሚሸፍን አሳብ ነው። በብዙ ክፍለ ምንባቦች ላይ «በክርስቶስ» መሆን ወይም «ከክርስቶስ ጋር መተባበር» ሲባል፥ ሐረጉ ክርስቲያን ወይም በክርስቶስ አማኝ መሆን ማለት ይሆናል። ይህን የተላመደ ማዕከላዊ ሃሳብ በተለየ ርእስ በመውሰድ ስለ ደኅንነት ና በረከቶች ብዙ የምንቀስማቸው ትምህርቶች አሉ።  ጥያቄ፡– ኤፈ 5፡31-32 አንብብ። ሀ) ሐዋርያው ጳውሎስ የክርስቶስንና የቤተ ክርስቲያንን ኅብረት ምን ብሎ ይጠራዋል? ለ) ሐዋርያው የክርስቶስንና የቤተ ክርስቲያንን ኅብረት ለማመልከት እንዴት ካለው ሰብአዊ ግንኙነት ጋር ያመሳስለዋል?  ጥያቄ፡- ቆላ. 1፡26-27 እንብብ። ሐዋርያው ጳውሎስ አሕዛብ እንዲያውቁት ያደረገው ምሥጢር ምን ነበር?  ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቶስ ከአማኞች ጋር ያለውን ኅብረት እንደ ምሥጢር አድርጎ ይገልጸዋል። ምሥጢር ማለት ቀደም ሲል የተደበቀ ጻሩ ግን አሁን እግዚአብሔር ግልጽ ያደረገው እውነት ማለት ነው። እግዚአብሔር አሁን በጳውሎላ አማካይነት ጥንት ተደብቆ የነበረ አስደናቂ እውነትን ገልጧል። ይህ እውነትም በክርስቶስ አምነው ደኅንነቱን የተቀበሉ ከክርስቶስ ጋር የተባበሩ መሆናቸው ነው። በኤፌ. 5:31-32 ውስጥ ጳውሎስ በባልና በሚስት መካከል ስላለው ግንኙነት ያስተምራል። አንድ ወንድና አንዲት ሴት በሚጋቡበት ጊዜ የወላጆቻቸውን ቤት ትተው የራሳቸውን አዲስ ቤት ይመሠርቱና አዲስ ቤተሰብ ይሆናሉ። ይህ ግንኙነታቸውም ከሥጋዊ ንኙነት በላይ ስለሆነ፣ በስሜት፣ በማኅበራዊና በመንፈሳዊ ሁኔታቸውም አንድ ይሆናሉ። ጳውሎስ ይህንን ግንኙነት በክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን መካከል ያለው የመተባበር ምሳሌ ነው ይላል። እግዚአብሔር አሁን ክርስቶስና አማኞች ጥልቅና ምሥጢራዊ በሆነ መንገድ የተባበሩ መሆናቸውን ግልጽ እንዲታወቅ አድርጎአል። በቆላ. 1፡26-27 ውስጥ ጳውሎስ ሲናገር ቀድሞ ተደስቶ የነበረውን ምሥጢር እግዚአብሔር እንደ ገለጠለትና ያ ምሥጢር አሁን በይፋ እንዲታወቅ የተደረገ መሆኑን ያብራራል። ይህ ምሥጢር ክርስቶስ ከአማኞች ሁሉ ጋር፥ ከአሕዛብም እንኳን ሳይቀር አብሮ መተባበሩ ነው። ከዚህ ኅብረት የተነሣ አሕዛብ በእግዚአብሔር ዘንድ የዘላለም ሕይወት ተካፋዮች የመሆን ተስፋ አላቸው።  ነገር ግን አማኞች ከክርስቶስ ጋር ተባበሩ ሲባል ምን ማለት ነው? ምንም እንኳን ይህ ጥልቅና ምሥጢራዊ እውነት ቢሆንም፥ እግዚአብሔር አሁን ይህን እውነት ለአማኛች ግልጽ አድርጎታል። እንግዲህ ዛሬ የምናጠናቸው እነዚህና ሌሎች ጥቅሶች ከክርስቶስ ጋር መተባበር ምን ማለት እንደሆነ ያብራሩልናል።  1. ከክርስቶስ ጋር መተባበር ማለት ከክርስቶስ ጋር ሞተን ከእርሱ ጋር ተነሣን ማለት ነው።  ጥያቄ፡- ገላ 2፡20 እንብብ። ጳውሎስ ከክርስቶስ ጋር ምን አደረግሁ አለ?  ጥያቄ፡- ሮሜ 6፡3-5፥8 አንብብ፡፡ እኛስ ከክርስቶስ ጋር ምን አደረግን?  ጥያቄ፡– ኤፌ 2፡5-6 አንብብ። እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ምን አደረገልን?  ጥያቄ፡- ቆላ. 2፡13፥ 20 አንብብ። እኛ ከክርስቶስ ጋር ምን አደረገን?  ጥያቄ፡- 2ኛ ቆሮ. 5፡17 አንብብ። በክርስቶስ የሆኑ ሁሉ ምን ሆነላቸው?  በመጀመሪያ ነገር ለአማኞች ከክርስቶስ ጋር መተባበር ማለት፥ ከክርስቶስ ጋር በሞቱና በትንሣኤው አንድ ሆነናል ማለት ነው። ኢየሱስ ሞቶ በተነሣ ጊዜ ከእርሱ ጋር ሞተን ከእርሱ ጋር ተነሥተናል። እኛ በክርስቶስ ከማመናችን በፊት የነበረ አሮጌው ሰው ከሞተ በኋላ፥ በክርስቶስ ባመንን ጊዜ አዲሱ ሰው ሕያው ሆኖ ተነሣ። በአዲስ ኪዳን ውስጥ ብዙ የተለያዩ ክፍለ ምንባቦች የኢየሱስ አማኞች በሞቱም ሆነ በትንሣኤው ከእርሱ ጋር የተባበሩ መሆናቸውን ያስተምራሉ። በገላ. 2፡20 ጳውሎስ ራሱ ከክርስቶስ | ጋር እንደ ተሰቀለ ይናገራል። በሮሜ 6፡3-5፥ 8 ውስጥም ጳውሎስ | እንደሚገልጸው ከኢየሱስ ጋር አንድ ለመሆን የተጠመቅን ሁሉ የሞቱም ተካፋዮች ነን ይላል። በሃያኛው ትምህርታችን ውስጥ እንደምንመለከተው በአዲስ ኪዳን ዘመን ለሰቡ በይፋ እንዳመነ ወዲያውኑ ጥምቀት ይደረግለት ነበር። ስለዚህ የጥምቀቱና ንስሐ ገብቶ የመለወጡ ወቅት አንድ ነበር። ጳውሎስ እንዳለው ሰዎች ወደ ክርስቶስ በሚመጡበት ጊዜ አብረውት ሙተው አብረውት ይነሣሉ፤ ከዚያም አብረውት ይኖራሉ። በኤፌ. 2፡5-6 ውስጥ ጳውሎስ ሲናገር፥ ከክርስቶስ ጋር የሞትን ብንሆንም ከክርስቶስ ጋር ሕይወትን ሰጥተናል ከክርስቶስም ጋር በሰማይ አስቀምጦናል ይላል። በቆላ. 2፡ ውስጥ በኃጢአታችን የሞትን ስንሆን እግዚአብሔር በክርስቶስ ሕያዋን አድርጎናል በማለት ጳውሎስ ያስረዳል። እንደዚሁም በቆላ. 2፡20 ውስጥ ከክርስቶስ ጋር ሞትን ይላል። ሌላው በ2ኛ ቆሮ. 5፡17 ጳውሎስ ሊያስረዳ ማንም በክርስቶስ ቢሆን እርሱ አዲስ ፍጥረት ነው፥ አርጌው ፍጥረት አልፎአል፥ በእርሱ ስፍራ አዲሱ ሰው ተተክቷል በማለት ይናገራል። ከርስቶስን እንደ ግል አዳኛችን ተቀብለን ባመንበት ጊዜ አዲስ ሕይወትን በአዲስ ሁኔታ መኖር የምንችል ሰዎች ሊያደርገን እግዚአብሔር በውስጣችን ሥራን ሠርቷል።  ኢየሱስን የግል አዳኛችሁ በማድረግ የምታምኑበት ከሆናችሁ፥ በእውነት እናንተ አዲስ ሰዎች ናችሁ! በኢየሱስ ከማመናችሁ በፊት የነበረው ሰው ክርስቶስ በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅሎ ሞቶአል። «አዲሱ ማንነታችሁ» ኢየሱስ ከሙታን በተነሣ ጊዜ አብሮ ሕያው ሆኖአል። ስለዚህ ከክርስቶስ ጋር መተባበር ማለት አዲስ ሕይወትን አገኛችሁ ማለት ነው። ይህ ከክርስቶስ ጋር የሚደረግ ኅብረት ባለፉት ሁለት ቀናት ትምህርታችን ውስጥ ያጠናነው ርእሰ ጉዳይ ማለትም የዳግም ልደት በረከት መሠረት ነው። ከክርስቶስ ጋር በሞቱና በትንሣኤው የተባበርን በመሆናችን፣ በአዲስ ሕይወት አዲስ ሰዎች ሆነናል።  ጥያቄ፡– ሮሜ 6፡11 አንብብ። ሀ) እኛ ራሳችንን እንደሞትን የምንቆጥረው ለምንድን ነው? ለ) ራሳችንን ሕያዋን እንደሆንን የምንቆጥረው ለምንድን ነው?  ጥያቄ፡– ኤፌ. 2፡10 አንብብ። እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት በምን ምክንያት ፈጠረን?  ከክርስቶስ ጋር ስላለን ኅብረት ምላሻችን ምን ሊሆን ይገባል? ከክርስቶስ ጋር ሞተን ስለ ተነሣን፣ እንደ አዲስ ሰዎች መኖር አለብን። በሮሜ 6፡11 ውስጥ ጳውሎስ አሮጌው የኃጢአት ሕይወታችን ሞቶአል፥ ስለዚህ ራሳችንን ለኃጢአት እንደ ሞትን አድርገን መቁጠር አለብን ይላል። ራሳችንን ለኃጢአት እንደ ሞትን አድርገን መቁጠር ማለት፥ የቀድሞ ሕይወታችን እንደ ሞተ አድርገን መቀበል ማለት ነው። በክርስቶስ አዲሱ ሕይወታችን ተጀምሯል። በክርስቶስ ለእግዚአብሔር ሕያዋን መሆናችንን መገንዘብ አለብን። ለእግዚአብሔር ራሳችንን ሕያዋን አድርጎ መቁጠር ማለት አዲሱ ሕይወታችን መጀመሩን መገንዘብ ማለት ነው። ለምሳሌ ያህል፥ አንድ ሰው ሚስት በሚያገባበት ጊዜ የብቸኝነት አሮጌ ሕይወቱ አበቃ ማለት ነው። እርሱም የብቸኝነት አሮጌ ሕይወቱ ማብቃቱን ይቀበላል። እንደ ብቸኛ ሰው መኖርን ትቶ ትዳርን እንደ መሠረተ አባወራ ሆኖ አዲስ ሕይወትን ይኖራል። ጳውሎስ አሮጌው ሕይወታችን አልፎአል ይላል። አሮጌው ሕይወታችን ማክተሙን ተገንዝበን በአዲስ ሕይወት መኖር መጀመር አለብን። በኤፌ. 2፡10 ውስጥ ጳውሎስ ሲናገር፥ ከክርስቶስ ጋር ሞተን የተነሣን ስለሆንን (ቁ 4-6)፥ እግዚአብሔር ለእርሱ መልካም ሥራዎችን እንድንሠራ አዲስ ሰው አድርጎናል ይላል። እግዚአብሔር ያዳነንና ከክርስቶስ ጋር እንድንተባበር ያደረገን ለዓላማው ነው። ስለዚህ ለአዲስ ፍጥረቱ የሚፈጽመው አስደናቂ ዕቅድ አለው።  ጥያቄ፡- ሀ) ክርስቶስን ከማወቃችሁ በፊት በአርጌ ሕይወታችሁ ውስጥ ከነበረ ተግባርና ስሜት አሁን ምን ያህሉ በውስጣችሁ ቀርቷል? ለ) ምን መልካም ሥራዎችን እንድትፈጽሙ ነው እግዚአብሔር ያጻናትሁ?  ክርስቲያኖች ሁሉ ክርስቶስን ከማወቃቸው በፊት ከነበሩት አሮጌ ኃጢአታዊ ተግባራትና ዝንባሌዎች አንዳንዶቹን ይዘው ይጓዛሉ፡፡ ሁላችንም ብንሆን አሁንም ራሳችንን ወዳዶችና የሌሎችን ሀብትና ንብረት የምንመኝ ነን። አሁንም ትዕቢተኞችና ለዝናና ለክብር የምንቋምጥ ሰዎች ነን። አሁንም ፍትወታዊ ድርጊቶችንና በኃጢአት የተበከሉ ደስታዎችን እንፈልጋለን። አሁንም ሁላችንም እንቆጣለን፥ እንመቀኛለን፥ ምሬት እናሳያለን፥ ደግሞም እንጨነቃለን። ታዲያ እነዚህ ሁሉ የአርጌው ሕይወት ቅሪቶች መሆናቸውን አውቀን እንድንቀበል እግዚአብሔር ይፈልጋል። እነዚህ ተግባራትና ስሜቶች ከክርስቶስ ጋር ከተባበረው ሕይወት ጋር አይስማሙም። እግዚአብሔር በዚህ ፈንታ ያቀደልንን መልካም ሥራ እንድንፈጽም ይፈልጋል። እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን እንድናግዝ ይሻል። ለጠፉትም ወንጌልን እንድናካፍል ይፈልጋል። እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያናችን ታማኞች እንድንሆን ይጠብቅብናል። ሌሎች ክርስቲያኖችን እንድናበረታታና እንድናንጽ ይሻል።  2. ከክርስቶስ ጋር ኅብረት ማድረግ ማለት፥ እግዚአብሔር እኛን ከክርስቶስ ጋር አንድ አድርጎ ተመለከተን ማለት ነው፡- እግዚአብሔር ወደ እኛ ሲመለከትም የሚያየው ኢየሱስን ነው።  ከክርስቶስ ጋር መተባበር ማለት ከክርስቶስ ጋር ሞተን ተነሣን ማለት ብቻ አይደለም። እንዲህ ማለት ከክርስቶስና ከእግዚአብሔር ጋር አብረን ሆነን ተገኘን ማለት ነው። እግዚአብሔር አሁን በሚመለከተን ጊዜ ቀድሞ የነበርነውን ዓይነት ሰዎች አድርጎ አይመለከተንም። እግዚአብሔር አሁን ሲመለከተን፣ ኢየሱስን ያያል። እግዚአብሔር ሲመለከተንም ልክ ኢየሱስ ያለውን የጽድቅ ስፍራ እኛም እንደ ያዝን አድርጎ ይመለከታል። 

ከክርስቶስ ጋር መተባበር – ከክርስቶስ ጋር መተባበር ማለት ምን ማለት ነው?  Read More »

ዳግም መወለድ፥ ክፍል 2 

This entry is part 81 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

በትናንትናው ዕለት ስለ ዳግም መወለድ ማጥናት ጀምረናል። ስለ ዳግም መወለድም እንደ ቁልፍ የሆነ ጥቅስ ያጠናን ሲሆን፥ እርሱም ዮሐ 3፡1-8 ነበር። በዚህ ጥቅስ ላይም ዳግም መወለድ ሊባል የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አዲስ መንፈሳዊ ሕይወት ሊሰጠን የሚፈጽመው ሉዓላዊ የማንጻት ተግባር እንደሆነ ተምረናል። ዛሬ ደግሞ በተቀሩት የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ስለ ጳም መወለድ ወይም ልደት የሚነግሩንን ቁልፍ የሆኑ ጥቅሶችን በመቃኘት ጥናታችንን እንቀጥላለን።  ጥያቄ፡- ዮሐ 1፡12-13 አንብብ። ሀ) የእግዚአብሔር ልጅነትን መብት ያገኙ እነማን ነበሩ? ለ) የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑት ያልተወለዱት ከምንና ከምን ነው? ሐ) የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑት ከምን ተወለዱ?  ጥያቄ፡- ዮሐ 3፡14-16 አንብብ። ሀ) ኢየሱስ በሙሴ የተሰቀለውን የነሐስ እባብ ምንን ለማመልከት ተጠቀመበት? ለ) በልጁ የሚያምን ምንን ይቀበላል?  ጥያቄ፡- ዮሐ. 5፡24 አንብብ። የኢየሱስን ቃል የሚሰማ የላከውንም የሚያምን ምንን ያገኛል?  ጥያቄ፡- 1ኛ ጴጥ. 1፡3 አንብብ። ሀ) አዲሱ ልደት በምን አማካይነት ይገኛል? ለ) የአዲስ ልደት መጨረሻ ውጤት ምንድን ነው?  ጥያቄ፡- 1ኛ ጴጥ. 1፡23 አንብብ። አዲስ ልደት በምን አማካይነት ይገኛል?  ጥያቄ፡- ያዕ. 1፡18 አንብብ። ሀ) አዲስ ልደት በምን አማካይነት ይገኛል? ለህ የአዲስ ልደት መጨረሻ ውጤት ምንድን ነው?  ጥያቄ፡- 1ኛ ዮሐ 5፡1 አንብብ። ሀ) ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ስለሚያምን ለው የተረጋገጠለት ምንድን ነው? ለ) 1ኛ ዮሐ 2፡29፤ 3፡9፤ 4፡7፤ 5፡4፥ 18 አንብብ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ከእግዚአብሔር ስለተወለዱት የተነገረውን እውነታ ሁሉ ጻፍ።  ጥያቄ፡– ኤፌ. 2፡4-5 እና ቆላ. 2፡13 አንብብ። ሀ) እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ ጣልቃ ከመግባቱ በፊት የነበረን ሁኔታ ምን ይመስል ነበር? ለ) እግዚአብሔር ጣልቃ በገባ ጊዜ ምን አደረገልን?  ጥያቄ፡- 2ኛ ቆሮ. 5፡17 አንብብ። «በክርስቶስ ለሆኑት» የተረጋገጠላቸው ነገር ምንድን ነው?  ጥያቄ ቲቶ 3፡3-8 አንብብ። ሀ) እንዴት ያለን ሰዎች ነበርን? (ቈ 3) ለ) እግዚአብሔር እንዲህ ካለው ሕይወት መቼ አዳነን? ሐህ እግዚአብሔር እንዲህ ካለው ሕይወት እንዴት አድርጎ አዳነን? (ቁ 5) መ) እግዚአብሔር የሰጠን ዳግም የመወለድ ውጤቶች ምንድን ናቸው? (ቁ. 7-8)  1. ዳግም መወለድ የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ሥራ ነው።  በመጀመሪያ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ስለ ዳግም መወለድ የምናገኘው ትምህርት ላም መወለድ ማለት የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ተግባር መሆኑን የሚያስረዳ ነው። ትናንትና በዮሐ 3፡8 ላይ እንደተመለከትነው፣ መንፈስ ቅዱስ አዲስ ልደትን ለእኛ በመስጠት ተግባሩ በነፋስ እንደሚመሰል ነው። ሰዎች ነፋስን ሊቆጣጠሩም ሆነ ሙሉ ለሙሉ ሊገነዘቡት አይችሉም፤ እንዳሻው ወዳሻው ይነፍሳል። መንፈስ ቅዱስም እኛን በማይገባን ሁኔታ በፈቀደው መንገድ ሥራውን ይፈጽማል። በዮሐ 1፡13 ላይ የተጻፈው ቃል የእግዚአብሔር ልጅ መሆንን የሰው ልጅ ከመሆን ሁኔታ ጋር ያነጻጽረዋል። ልጆች በወላጆቻቸው ውሳኔና ተግባር ከወላጆቻቸው ይወለዳሉ። ነገር ግን እኛ በእግዚአብሔር መንፈስ ውሳኔና ተግባር ከመንፈስ እንወለዳለን።  2. ዳግም መወለድ ከኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ይገኛል።  ሁለተኛው ስለ ዳግም መወለድ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የምናገኘው ትምህርት ዳግም መወለድ ወይም ልደት ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ እንደሚገኝ ነው። በዮሐንስ 3 ውስጥ ኢየሱስ ከኒቆዲሞስ ጋር ውይይቱን በቀጠለ ጊዜ፣ የመስቀል ሥራውን ሙለ በምድረ በዳ ከሰቀለው የነሐስ እባብ ጋር በማመሳሰል ተናግሯል። በዘዳግም 21 ውስጥ እስራኤላውያን ስለ አጉረመረሙ እግዚአብሔር መርዘኛ እባቦች እንዲነድፉአቸው ወደ ሰፈራቸው ሰደደባቸው። ይህን ጊዜ ሕዝቡም ወደ ሙሴ ፊት ቀርበው ኃጢአታቸውን በመናዘዝ ወደ እግዚአብሔር እንዲጸልይላቸው ለመኑት። ይህን ጊዜ እግዚአብሔር ሙሴ የነሐስ እባብ ሠርቶ በሕዝቡ መኖሪያ መሃከል በዓላማ ላይ እንዲሰቅለው አዘዘው። ከዚያም እባብ የነከሰው ሁሉ ወደ ነሐሱ እባብ በተመለከተ ጊዜ ይድናል። በዚህም እግዚአብሔር ቸርነቱን በእምነት ለተቀበሉት ሕዝቡ አዲስ ሥጋዊ ሕይወትን ሰጣቸው። ኢየሱስም ለኒቆዲሞስ ሲያስረዳው፥ ሙሴ ሕዝቡ ሁሉ ይመለከተው ዘንድ የነሐሱን እባብ ከፍ አድርጎ በዓላማ ላይ እንደ ሰቀለው እንዲሁ፥ ሁሉም ይመለከቱት ዘንድ የሰው ልጅ ከፍ ብሎ ተሰቅሉ ይታያል አለው። ይህን ሲልም በኋላ ራሱ በመስቀል ላይ እንደሚሰቀል ሲገልጽለት ነበር። በእግዚአብሔር ያመኑ እስራኤላውያን በነሐስ እባብ አማካኝነት ሥጋዊ ፈውስን እንዳገኙ ሁሉ፥ እግዚአብሔር ስኢየሱስ የመስቀል ሞት አማካይነት የሰጠውን የኃጢአት ይቅርታ አምነው ለሚቀበሉ ሁሉ መንፈሳዊ ሕይወትን ይሰጣቸዋል። እግዚአብሔር አዲስ ሕይወትን የሚሰጠው በመስቀል ላይ በተፈጸመው በኢየሱስ ሞት አማካይነት ነው። እንደዚሁም 1ኛ ጴጥ. 1፡3 እግዚአብሔር አዲስ ሕይወትን በኢየሱስ ትንሣኤ በኩል እንደሚሰጥ አክሎ ይናገራል። በ8ኛውና በ14ኛው ትምህርታችን ላይ እንደተመለከትነው፣ የክር ስቶስ ሞትና ትንሣኤ ደኀንነትን፥ እርቅን፣ የእግዚአብሔርን ከጽድቃዊ ቁጣው መመለስን እና በኃጢአትና በሰይጣን ላይ ድልን ይሰጠናል። እግዚአብሔር ስለ ኃጢአታችን የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ መሥዋዕት አድርጎ ስላቀረበ፣ እርሱ በፈጸመው ለሚያምኑት ሁሉ አዲስ ሕይወትን ይሰጣቸዋል።  3. ዳግም ልደት በእግዚአብሔር ቃል አማካይነት ይገኛል።  ዳግም መወለድ በክርስቶስ የመስቀል ሞት ላይ የተመሠረተ ሲሆን፥ በመንፈስ ቅዱስ ሉዓላዊ ሥራ አማካይነትም ይፈጸማል። ነገር ግን እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ሰው ሕይወት ውስጥ ዳግም መወለድን ለማምጣት በተለያዩ መንገዶች ይጠቀማል። የዳግም ልደት ከፍተኛውና ዓይነተኛው መንገድ የእግዚአብሔር ቃል ነው። 1ኛ ጴጥ. 1፡23 ካማይጠፋው ከእግዚአብሔር ቃል ጻም መወለጻችንን ይነግረናል። ያዕ. 1፡18 ደግሞ እግዚአብሔር የፍጥረቱ ሁሉ መጀመሪያ እንድንሆን በገዛ ፈቃዱ በእውነት ቃል ወለደን ይላል። ስለዚህ እግዚአብሔር ሰዎችን ወደ አዲስ ሕይወት ለማምጣት በመጀመሪያ የሚጠቀመው በቃሉ ነው።  ጥያቄ፡– ዳግም መወለድ በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ሥራና በቃሉ አማካይነት የሚመጣ ከሆነ፥ ቤተሰቦቻችንና የምናውቃቸውን ሁሉ ወደ እዲስ ልደት በማምጣት ረገድ የእኛ ኃላፊነት ምንድን ነው?  አዲስ ልደት ከእግዚአብሔር ሉዓላዊ ሥራ የሚገኝ በመሆኑ፣ ሰዎች በክርስቶስ እንዲያምኑ ለማድረግ በማግባባትና በስሜታዊ አቀራረብ ብቻ ልባቸውን ለማምጣት እንደማንችል ማወቅ ይኖርብናል። ሰዎችን ለማሳመን ምንም ያህል ብንማፀን፥ በልመናና በመለማመጥ አሳምነን ወደ ክርስቶስ ልናመጣቸው አንችልም። እንደዚሁም ስለ መንግሥተ ሰማይ ድንቅነት፥ በአንጻሩም ስለ ገሃነም አስፈሪነት ምንም ያህል ብንነግራቸው፣ በራሳችን ኃይልና እውቀት ወደ እግዚአብሔር እንዲመጡ ማድረግ አንችልም። በልባቸው ውስጥ የሚሠራ የእግዚአብሔር ሥራ ብቻ አሳምኖ ወደ አዲስ ሕይወት ሊያመጣቸው ይችላል። የእኛ ኃላፊነት ሊሆን የሚችለው የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ሥራ በልባቸው ውስጥ ፍሬ ያፈራ ዘንድ መጸለይ ነው። እንዲሁም እግዚአብሔር ኃጢአታቸው ተሰምቷቸው ንስሐ እንዲገቡ እንዲያደርግ መጸለይ ይገባናል። በተጨማሪም እግዚአብሔር ወደ ራሱ እንዲስባቸው እርሱን መለመን አለብን። እግዚአብሔር የሚሰጠውን ዘላለማዊ ሕይወት በጉጉት የሚሹ እንደሚያደርጋቸውና በተጨማሪም እግዚአብሔር ወደ እምነት ያመጣቸው ዘንድ መጸለይ ይኖርብናል።  ሆኖም፥ የእግዚአብሔርን ሥራ ከማያምኑ ወዳጆቻችንና ጎረቤቶቻችን ጋር የመወያየትና የመካፈል ኃላፊነት አለብን። እግዚአብሔር ሰዎችን ወደ ራሉ የሚያመጣበት መንገድ ቃሉ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ እንዴት እንደሚሠራ በየአጋጣሚው ሁሉ ለሰዎች መመስከር አለብን። እንዲሁም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተማርነውን አሳልፈን ለሌሎች በማሰማት የእግዚአብሔር ቃል እንዲደርሳቸው ማድረግ ይጠበቅብናል። ሰዎች እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን አዲስ ሕይወት እንዴት ባለ ሁኔታ ሊያገኙ እንደሚችሉ በመግለጽ የእግዚአብሔር ቃል እንዲደርሳቸው ለማድረግ ምን ጊዜም ዝግጁዎች ልንሆን ይገባናል። አንዳንድ ጊዜ ይህን የታዘዝነውን ኃላፊነት ለመወጣት በምናደርገው ጥረት ላይ ለምእመናን ስብከትን እንደምናሰማው ዓይነት በዛ ላሉ ሰዎች ቃሉን እንድናካፍል እግዚአብሔር ዕድል ይሰጠናል። በሌላ ጊዜ ደግሞ ከግለሰቦች ጋር በግላቸው ቃሉን አብረን እንድንካፈል ዕድል ያዘጋጅልናል። በእነዚህ ሁሉ አጋጣሚዎች ላይ አንድ ማስተዋል ያለብን ነገር እግዚአብሔር ወደ እነዚህ ሰዎች ለመቅረቢያና ወደ አዲስ ሕይወት እንዲመጡ ለማድረግ የሚገለገልበት መሣሪያ ቃሉ መሆኑን ነው። ከሁላችን የሚጠበቀው ኃላፊነት ታዲያ ቃሉን ከሰዎች ጋር ለመካፈል ዝግጁ መሆን ነው።  ጥያቄ፡- አንድ ጊዜ አማኝ ስላልሆኑ ወዳጆቻችሁና ጎረቤቶቻችሁ አስቡ። ከዚያም የሦስቱን ስም ጻፉ። በሦስቱም ስሞች ጎን በየአጋጣሚው አብራችኋቸው ልትወያዩ የምትችሉዋቸውን፥ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣቸውን እምነት ሊሰጧቸው የሚችሉትን አንዳንድ ነገሮች ከእግዚአብሔር ቃል ጻፉ።  4. ዳግም መወለድ በእምነት ይገኛል።  አዲስ ኪዳን ስለ ዳግም መወለድ በግልጽ የሚሰጠው አራተኛው ትምህርት በእምነት እንደሚገኝ ነው። ዮሐ 1፡12 ኢየሱስን ተቀብለው በስሙ የሚያምኑ ብቻ የእግዚአብሔር ልጆች እንደሚሆኑ ይናገራል። ኢየሱስ የነሐሱን እባብ ምሳሌ አድርጎ በተናገረ ጊዜ (ዮሐ 3፡14-15)። «በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለምን ሕይወት እንዲያገኙ» እግዚአብሔር ልጁን ከፍ ያደርገዋል ብሏል። ኢየሱስ ለኃጢአት ዕዳችን

ዳግም መወለድ፥ ክፍል 2  Read More »

ዳግም መወለድ፥ ክፍል 1 

This entry is part 80 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

የደኅንነት በረከቶች – ክፍል አንድ  በዛሬው ትምህርታችን እግዚአብሔር ስለሚሰጠን የደኅንነት በረከተች እናጠናለን። እንደሚታወቀው እኛ በኃጢአት የተወለድን ከመሆናችንም በላይ እያንዳንዳችን ብዙ የኃጢአት ተግባራትን ስለምንፈጽም በኃጢአታችን ሙታን ነን። ስለዚህ እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ ጣልቃ ገብቶ ከኃጢአታችንና ከሚያስከትልብን ክፉ መዘዝ ሁሉ ሊያድነን ይገባል። ትዝ እንደሚላችሁ ደኅንነት እንደሚያስፈልገን በትምህርት 11ና 12 ላይ አጥንተናል። እግዚአብሔር እኛን መርጦ ወደ ራሱ ሊያቀርበን በማለት በክርስቶስ ሞት አማካይነት ለደኅንነታችን አስፈላጊ የሆነውን ነገር ሁሉ ፈጽሞልናል። በትምህርት 13ና 14 ላይ እግዚአብሔር ደኅንነትን ሊሰጠን ስለፈጸመው ተግባር አጥንተናል። ለደኅንነት የበቃነው እግዚአብሔር በራሱ ተነሣሽነት ባዘጋጀው ዕቅድ ማለትም ባደረገልን ምርጫና ጥሪ ሲሆን፣ ከዚሁ ጋር አብሮ የሚሄደው ደግሞ የእኛ ንስሐ መግባትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ፥ እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ሲል በኢየሱስ ሕይወት፥ በሞቱና በትንሣኤው የፈጸማቸውን ተግባራት በማመን ምላሽ መስጠታችን ነው። ስለዚህ የደኅንነት መንገድ በትምህርት 15 እና 16 ላይ መማራችን ትዝ ይለናል። በንስሐ ወደ እርሱ ተመልሰን በክርስቶስ በምናምንበት ጊዜ እግዚአብሔር የደኅንነቱን በረከቶች በላያችን ላይ ያፈስሳቸዋል። ታዲያ እነዚህ በረከቶች ምንድን ናቸው? በዚህ ሳምንት ውስጥ እነዚህን በረከቶች ማጥናት እንጀምራለን።  ዳግም መወለድ፥ ክፍል 1  በትምህርት 11ና 12 ትምህርቶቻችን ውስጥ በዓለም ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች ሆነው እንደ ተወለዱና ሁላቸውም ኃጢአትን እንደሚሠሩ አስተውለናል። ከኃጢአታችን የተነሣ፥ ሁላችንም ከእግዚአብሔር የተለየን በመንፈሳችንም የሞትንና የታወርን ነበርን። ይህ ኃጢአታችንም በእኛና በእኛ አካባቢ ባሉ ሰዎች ሁሉ ሕይወት ላይ ሞትንና ጥፋትን አስከትሏል። ስለዚህ ከዚህ አሰቃቂ ከሆነ የኃጢአት መዘዝ ለመዳን እያንዳንዳችን አዲስ ሕይወትን እንሻለን። እንደዚሁም አርጌውና ኃጢአታዊው ተፈጥሮአችን ሙሉ በሙሉ ወደ አዲስ ተፈጥሮ ሊለወጥ ይገባል። በመንፈሳችን ሙታን ስለሆንን፣ መንፈሳዊ ሕይወትን መቀበል አለብን። እግዚአብሔር የሚሰጠን የመጀመሪያው የደኅንነት በረከት ይህ አዲስ ሕይወት ነው። እግዚአብሔር ደኅንነትን በሚሰጠን ጊዜ ሕይወታችንን ይለውጠውና የተሟላ አዲስ ተፈጥርን ይሰጠናል። መንፈሳዊ ሕይወትን የተላበስን አዲስ ሰዎች ያደርገናል። እግዚአብሔር በዚህ አኳኋን የሚሰጠን አዲስ ሕይወት «ዳግም መወለድ» ይባላል።  ጥያቄ፦ ዮሐ 3፡1-8 አንብብ። ኒቆዲሞስ ስለ ኢየሱስ ያስተዋለው ምን ነበር? (ቁ 2)  ጥያቄ፡- ኢየሱስ ኒቆዲሞስ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት እንዲችል ምን ማድረግ እንዳለበት ነገረው? (ቁ. 3)  ጥያቄ፡- ኒቆዲሞስ ኢየሱስ የተናገረውን ያላስተዋለው እንዴት ነበር? (ቁ. 4)  ጥያቄ፡- ኢየሱስ «ዳግም መወለድ» ብሎ ለተናገረው ቃል ምን ማብራሪያ ሰጠ? (ቁ 5)  ጥያቄ፡- ሀ) የሥጋዊ ልደት ውጤት ምንድን ነው? ለ) የመንፈሳዊ ልደትስ ውጤት ምንድን ነው? (ቁ. 6)  ጥያቄ፡- መንፈስ የሰውን ሕይወት በመለወጥ ረገድ እንዴት ባለ ሁኔት በነፋስ ይመሰላል?  ጥያቄ፡- ዘሌዋ. 17፡17-19 አንብብ። ሀ) እንደዚህ ክፍል አነጋገር እስራኤላውያን ከኃጢአታቸው የሚነጹት እንዴት ነው? ለ) መዝ. 50፡7 አንብብ። ዳዊት እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያነጻው ተናገረ?  ጥያቄ፡- ኢሳ 55፡1 አንብብ። እስራኤላውያን በልተውና ጠጥተው እንዲደሰቱ የተጠሩት ወዴት ነው? ለ) ዘካ. 14፡8-9 አንብብ። እግዚአብሔር በመላው ምድር ላይ በሚነግሥበት ጊዜ ከኢየሩሳሌም ምን ይመነጫል? ሐ) ኤር. 2፡13 አንብብ። የእስራኤል የሕይወት ውኃ ምንጭ ማን ነው?  ጥያቄ፡- ኢሳ. 44፡1-3 አንብብ። እስራኤላውያን በእግዚአብሔር የተመረጡ የተለዩ ሕዝብ እንደ መሆናቸው ምን ሁለት ነገሮች ይፈስሱባቸዋል?  ጥያቄ፡ ሕዝ 36፡24-27 አንብብ። እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ወደ ምድራቸው መልሶ በሚያመጣቸው ጊዜ ምን ያደርግላቸዋል?  ጥያቄ ኢሳ. 32፡15 አንብብ። የጽድቅ ንጉሥ በሚነግሥበት ጊዜ እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ምን ያደርግለታል?  እግዚአብሔር ስለሚሰጠን ስለ አዲሱ ሕይወት ዘርዝሮ የሚያስረዳን ክፍል በዮሐ 3፡1-21 የተጻፈው ነው። ዛሬ መላው ትምህርታችን በዚህ ርእስ ላይ ያተኮረ ይሆናል። የዮሐንስ ምዕራፍ 3 በኢየሱስና በፈሪሳዊው በኒቆዲሞስ መካከል የተካሄደ ውይይት ዘገባ ነው። ኒቆዲሞስ ወደ ኢየሱስ የመጣው ኢየሱስ የፈጸማቸውን ታምራት ስላየና የበለጠ ስለ እርሱ ማወቅ ስለፈለገ ነበር። በዮሐ 3፡2 ውስጥ፣ ኒቆዲሞስ ስለ ኢየሱስ ታምራት የጠቀሰ ቢመስልም፥ እውነታው ግን በተዘዋዋሪ መንገድ አንተ ማን ነህ? በምትፈጽማቸው ተአምራት ላይ በመመሥረት ስለ ራስህ ምን ትላለህ? የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሣቱ ነበር። ኢየሱስ ግን እርሱ ለጠየቃቸው ጥያቄዎች መልስ ከመስጠት በላይ አድርጓል። እንዲያውም ኒቆዲሞስ አዲስ ልደት እንደሚያስፈልገው ወዲያው በመንገር አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ጥሎታል። ምንም እንኳን እርሱ መንፈሳዊ ግምት መውሰድ ለምሳሌ፥ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር መሆኑን መረዳት) የሚችል ፈሪሳዊ አድርጎ ራሱን ቢቆጥርም፥ ለእግዚአብሔር መንግሥት ገና ያልበቃ ሰው ነበር። ማንም ቢሆን ዳግም ካልተወለደ በስተቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይም ሆነ ሊነዘብ አይችልም።  1. «ዳግም መወለድ» ማለት ምን ማለት ነው?  ኢየሱስ ኒቆዲሞስን ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ለመገንዘብም ሆነ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ዳግም መወለድ አለብህ ሲለው ምን ማለቱ ነበር? ወደ አማርኛ (ዳግም፥ ዳግመኛ) በአዲሱ ትርጉም (እንደገና) ተብሎ የተተረጎመው የግሪኩ ቃል ሁለት ትርጉሞች አሉት። እንደገና ወይም ከላይ የሚል ፍቺ ሊኖረው ይችላል። ዮሐንስ በወንጌሉ በሌሎች ክፍሎች ውስጥ ይህንኑ አሳብ ለመግለጽ «ከላይ» በሚለው ቃል ይጠቀማል ( ዮሐ. 3፡31፤ 19፡11፥23)፣ ይህንንም ሊል ምናልባት «ከላይ መወለድ» እንዳለብን ለመግለጽ ሊሆን ይችላል። አንድ ሰው በሥጋ ከተወለደ በኋላ «ከላይ መወለድ» ካለበት፥ ጻግሞ መወለድ ይኖርበታል ማለት ነው። ስለዚህ ኢየሱስ ኒቆዲሞስን ዳግም ልትወለድ» ይገባሃል በሚልበት ጊዜ፣ እነዚህ ሁለት ልደቶች በአሳቡ የነበሩ ሳይሆን አይቀርም። ስለዚህ ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ የነገረው፣ ሥጋዊ ልደትህ በቂ ስላልሆነ፥ ሁለተኛ ጊዜ መወለድ አለብህ፥ ይህም ከላይ መወለድ ነው» የሚል ነበር። ዮሐንስ ቀደም ሲል በወንጌሉ ደም ውስጥ ለአንባቢያኑ፥ ኢየሱስን የተቀበሉትና በስሙም ያመኑ ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ በመወለድ የእግዚአብሔር ልጆች ሆነዋል ሲል ነግሮአቸዋል (ዮሐ 1፡12-13)። አንባቢዎቹም ዮሐ 3፡3። በሚያነቡበት ጊዜ እነዚህን ቃላት እንዲያስታውሱ ይፈልጋል። ከእግዚአብሔር መወለድና የእግዚአብሔር ልጅ መሆን ከላይ መወለድ ከሚለው ጋር አንድ ነው።  ሆኖም፣ ኒቆዲሞስ የሰማው ትምህርት አልገባውም ነበር። ለእርሱ የገባው ኢየሱስ ስለ አንዳች ዳግመኛ ሥጋዊ ልደት የሚናገር መስሎት ነው። ከዚህም የተነሣ ሰው ዳግመኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ መወለድ ይችላልን ብሎ ኢየሱስን ጠየቀ።  ኢየሱስም የሚናገረው ስለ ዳግመኛ ሥጋዊ ልደት አለመሆኑን በመግለጽ ለኒቆዲሞስ መለሰለት። «ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ የሚችለው ከውኃና ከመንፈስ በሚወለድበት ጊዜ ብቻ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ የነገረው የዘላለም ሕይወትን ለማግኘት በመንፈስ ቅዱስ መንጻት እንዳለበት ነው።  2. «ከውኃና ከመንፈስ መወለድ» ማለት ምን ማለት ነው?  ኢየሱስ ኒቆዲሞስ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንድትገባ «ከውኃና ከመንፈስ መወለድ አለብህ» ባለው ጊዜ ምን ማለቱ ነበር? ምላሽ ይሆናሉ ተብለው የሚታሰቡ ቢያንስ አራት አሳቦች ይቀርባሉ፦  1) አንዳንዶቹ እንደሚያስቡት ኢየሱስ ስለ ውኃ መጥቀሱ ስለ ክርስቲያኖች ጥምቀት ሲናገር ነው ይላሉ። ይህን የሚሉት ሰዎች አንድ ሰው ለመዳን በእምነት ከመንፈስ ቅዱስ መወለድና መጠበቅ አለበት ይላሉ። ምንም እንኳ ብዙዎች ይህን ጥቅስ በዚህ ዓይነት ግንዛቤ ቢቀበሉትም፥ የክፍሉን ዓውደ አሳብ በተመለከተ ይህ ጥሩ ንዛቤ አይደለም። ኢየሱስ ሞቶ እስከሚነሣ ድረስ ክርስቲያናዊ የጥምቀት ሥርዓትን አልመሠረተም ነበር (ማቴ. 28፡19-20)። በኢየሱስና በኒቆዲሞስ መካከል የተካሄደው ይህ ውይይት ከኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ በፊት ቀደም ብሎ ስለነበር፣ ኢየሱስ ስለ ክርስቲያናዊ ጥምቀት ነግሮት ቢሆን ኖር ኒቆዲሞስ አሳቡ ሊገባው የሚችል አይሆንም ነበር። በቁጥር 10 ውስጥ ኢየሱስ ኒቆዲሞስ የእስራኤል መምህር እንደ መሆኑ መጠን የነገረውን ሊገነዘብ ይገባው እንደ ነበር ያሳስበዋል። ኢየሱስ መጠመቅ እንደሚያስፈልግ እስከ ሞቱና ትንሣኤው ድረስ ትእዛዝ ስላልሰጠ፣ እርሱ የሚናገረው ለኒቆዲሞስ ይገባዋል ብሎ ሊጠብቅ አይችልም ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ ስለ ክርስቲያናዊ ጥምቀት እየተናገረ አልነበረም። ከዚህም በስተቀር፣ የክፍሉ ሙሉ መልእክት ስለ ሥጋዊና መንፈሳዊ ሁኔታ ማነጻጸር ነበር። ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ የነገረው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዲገባ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የሚፈጸም መንፈሳዊ ልደት እንዲኖረው ነው። ስለዚህ፣ በዚህ ክፍል የተጠቀሰው ስለ ውኃ የሚናገረው ሐረግ በእርግጥ ስለ ክርስቲያናዊ ጥምቀት ነው ለማለት ያስቸግራል።  2) አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ኢየሱስ የተናገረው ስለ ዮሐንስ መጥምቁ ጥምቀት ነው ይላሉ። የዮሐንስ ጥምቀት ግን የንስሐ ጥምቀት ነበር (ሉቃስ 3፡3፤ የሐዋ. 19፡6)። ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ ጥምቀት ተናግሮ ቢሆን ኖሮ፣ ኒቆዲሞስ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዲገባ

ዳግም መወለድ፥ ክፍል 1  Read More »

እምነት ከታዛዥነት ጋር እንዴት ይዛመዳል? 

This entry is part 79 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

1. መርሆ፡- ታዛዥነትና መልካም ሥራ የሚያድን እምነት ማረጋገጫዎች ናቸው።  ባለፉት ሦስት ቀናት ወደ ደኅንነት ስለሚያደርሱ መንገዶች ስናጠና ነበር። አዲስ ኪዳን ግልጽ እንደሚያደርገው ሰዎች የክርስቶስን ደኅንነት ለመቀበል እንዲችሉ አንድ ነገር ማድረግ አለባቸው፡- በራሳቸው መታመንን ትተው ወደ ክርስቶስ መመለስ አለባቸው። ይህም ስለ ደኅንነታቸው በበጎ ሥራቸው ላይ ማተኮርን በመተው በኢየሱስና እርሱ በሞቱና በትንሣኤው ባከናወናቸው ድርጊቶች ላይ መመርኮዝ ይጠበቅባቸዋል። አንዳንድ ጊዜ ይህ የደኅንነት አንድ የሆነ ነገር «ንስሐ» ተብሎ ይጠራል። ይህም ራስን ትቶ ወደ ክርስቶስ መመለስ ማለት ነው። አንዳንዴ ይህ አንድ ለደኅንነት አስፈላጊ የሆነ ነገር «እምነት» ተብሎም ይታወቃል። ይህም በራሳችን ላይ በመደገፍ ፈንታ በኢየሱስ ላይ መመርኮዝ ማለት ነው። በሌላ ጊዜ ደግሞ ይኸው ሁኔታ «ወደ እግዚአብሔር መመለስ» ይባላል። ይህም በኢየሱስ በኩል ወደ እግዚአብሔር መመለስ ሲሆን፥ በአንጻሩ ለደኅንነት ያበቃናል የምንለውን ማንኛውንም ሌላ መመኪያ ትተን ወደ እግዚአብሔር መመለስ ማለት ነው። ንስሐ፥ እምነትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ እነዚህ ሦስቱ ሰዎች የክርስቶስን ደኅንነት ለመቀበል በአጠቃላይ ሊገልጽዋቸው የሚገባ የአንዱ የመመለስ አሳቦች ናቸው። እነዚህ ሦስቱም አሳቦች ደኅንነት በበጎ ሥራችን ሳቢያ የሚመጣ ሳይሆን፥ በበጎ ሥራችን መታመናችንን አቁመን በክርስቶስ ብቻ መታመን ስንጀምር መሆኑን በግልጽ ያስረዳሉ።  ሆኖም፥ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ለእግዚአብሔር ስለ መታዘዝና ስለ መልካም ሥራ የሚገልጹ ብዙ ጥቅሶች ይገኛሉ። አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ጥቅሶች መልካም ሥራም ለደኅንነት አስፈላጊ እንደሆነ አድርገው የማቅረብ ዝንባሌ ያላቸው መስለው ሊታዩ ይችላሉ። ዛሬ ከእነዚህ ጥቅሶች ስለ ጥቂቶቹ እንማራለን። መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ጊዜ ስለ መልካም ሥራ ጠቃሚነት በሚናገርበት ወቅት፥ መልካም ሥራና ታዛዥነት የሚያድን እምነት መገለጫና ክርስቶስን የሚከተል ደቀ መዝሙር ፍሬ ናቸው ማለቱ መሆኑን እናያለን፡፡ ስለሆነም መልካም ሥራና ታዛዥነት ወደ ደኅንነት መድረሻው መንገድ ሳይሆን፥ የደኅንነት ውጤት ናቸው።  2. መርሖውን የሚያረጋግጡ ክፍለ ምንባቦች  2.1 ያዕቆብ 2፡14-26፡- አዳኝ የሆነ እምነት መልካም ሥራን ያፈራል።  ጥያቄ፡- ያዕቆብ 2፡14-26 አንብቡ። ሐዋርያው ያዕቆብ በዚህ ክፍል ስለ እምነትና መልካም ሥራ የተናገረውን እናንተ ደግሞ በአንድ ዓረፍተ ነገር አጠቃልላችሁ አቅርቡ።  ጥያቄ፡- አሁን ደግሞ መለስ ብላችሁ የዚህን ክፍል ጥቅሶች አንድ ባንድ አንብቡ። ሀ) ያዕቆብ 2፡14-16 አንብቡ። ሐዋርያው ያዕቆብ እምነት አለኝ እያለ ግን መልካም ሥራ ስለሌለው ሰው ምን አለ? ለ) ያዕቆብ 2፡17 አንብቡ። አንድ ሰው መልካም ሥራ ባይኖረው፥ ሕይወት ያለው እምነት ሊኖረው ይችላል? ሐ) ያዕቆብ 2፡18 አንብቡ። ሐዋርያው እምነት እንዴት ይገለጣል አለ? መ) ያዕቆብ 2፡19 አንብቡ። አጋንንት ማንን ያምናሉ? ሠ) ያዕቆብ 2፡20-26 አንብቡ። የአብርሃምና የረዓብ ታሪክ ምን ያስተምራል? ይህን መልስ ለማግኘት በተለይም ቁጥር 22ን ፣ አጥኑ።  አንዳንድ ጊዜ የያዕቆብ መልእክት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉ መልእክቶች ሁሉ እጅግ በጣም አደናጋሪ የሆነ ክፍል ሆኖ ይታያል። ኤፌሶን 2፡8-9 እና ሮሜ 45ን በምናነብበት ጊዜ፥ ደኅንነት የሚገኘው በሥራ ሳይሆን በጸጋ መሆኑን እንገነዘባለን። ነገር ግን ወደ ያዕቆብ ምዕራፍ 2 መጥተን ስናነብ ደግሞ፣ ያዕቆብ መልካም ሥራ የሌለው እምነት ምውት ነው ይለናል። ታዲያ ሐዋርያው ያዕቆብ የተናገረው ሐዋርያው ጳውሎስ ካጻፈው ቃል ጋር ይቃረናል? በፍጹም፣ ሁለቱም ሐዋርያት የጻፉዋቸው መልእክቶች እርስ በርስ አይቃረኑም። የጳውሎስ ትኩረትና አጽንኦት ሰዎች የሚድኑበትን ሁኔታ ለማስረዳት ነው። ሰዎች ሁሉ ስለ ደኅንነታቸውና ደኅንነታቸውን ለማግኘት በክርስቶስ ላይ መደገፍ ይኖርባቸዋል። ያዕቆብ ሊያመላክት የፈለገው የተለያዩ የእምነት ዓይነቶች ስላሉ አዳኝ የሆነ እምነት ውጤት ምን እንደሆነ ለማሳየት ነው። ስለዚህ ሐዋርያው ያዕቆብ እውነተኛና አዳኝ የሆነ እምነት ሁልጊዜ መልካም ሥራን ሊያፈራ መቻሉን ነው የሚያስተምረን።  በያዕቆብ 2፡14-16 ውስጥ መልካም ፍሬ የማያፈራ እምነት ሰውን ሊያድን አይችልም ይላል። ማንኛውም ሰው በኢየሱስ አምናለሁ እያለ መልካም ሥራ ሳይሠራ፣ ይህ ሰው የሚያድነውን ዓይነት እምነት አላገኘም ማለት ነው። ይህ ሰው ሕያውና አዳኝ በሆነ እምነት ፈንታ የሞተ እምነት ይኖረዋል ማለት ነው (ያዕቆብ 2፡17)። እውነተኛና አዳኝ የሆነ እምነት ራሱን የሚገልጠው በመልካም ሥራ ብቻ ነው (ያዕቆብ 2፡18)።  አንድ ሰው በመልካም ሥራ አማካይነት የማይገለጥ ምን ዓይነት እምነት ሊኖረው ይችላል? ያዕቆብ በቁጥር 19 ውስጥ አንድ ምሳሌ ያቀርባል። ይህም አጋንንት ካላቸው እምነት ጋር ይመሳሰላል። አጋንንት የእግዚአብሔርን መኖር ያምናሉ። አንድነቱንም ያምናሉ። ስለ እግዚአብሔር አንዳንድ ነገሮች እውነት መሆናቸውንም ያምናሉ። ነገር ገን በእግዚአብሔር ላይ ማመፃቸውን ትተው ለመዳን በእርሱ አያምኑም። አንዳንድ ሰዎችም ይህንኑ አጋንንት ያላቸውን እምነት የመሰለ እምነት አላቸው። በእግዚአብሔር ሕልውና ያምናሉ። አንዳንድ ነገሮች ስለ እግዚአብሔር እውነት እንደሆኑ ይቀበላሉ፤ ያምናሉ። ለምሳሌ ያህል፥ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ እንደሆነና ፍጥረታቱን ሁሉ በሉዓላዊነት ሥልጣን እንደሚመራና እንደሚያስተዳድር ያምኑ ይሆናል። እግዚአብሔር ቅዱስና ጻድቅ መሆኑን የሚያምኑ ይመስላል። እግዚአብሔር አፍቃሪና መሐሪ አምላክ መሆኑንም ያምኑ ይሆናል። ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር እውነት የሆኑትን እነዚህን ነገሮች ቢያምኑም፥ በአንጻሩ ደኅንነትን ለማግኘት በኢየሱስ ብቻ አያምኑም። እነዚህን የመሰሉ ሰዎች እምነት አላቸው፣ ግን እምነታቸው የሚያድን እምነት አይደለም። አጋንንት ካላቸው እምነት ያልተለየ እምነት አላቸው።  ያዕቆብ አዳኝ የሆነ እምነት ሁልጊዜ መልካም ፍሬ ያፈራል ይላል። ማንም እምነት አለኝ እያለ መልካም ሥራ የማይሠራ ሰው እምነት ከንቱ ነው ይላል (ያዕቆብ 2፡20)። የሚያድነው እምነት አይደለም። አዳኝ ስለሆነ እምነት ያዕቆብ ሁለት ምሳሌዎችን ይሰጣል። የመጀመሪያው ምሳሌ አብርሃም ነው። አብርሃም እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ የሚወርስ ልጅ እንደሚሰጠው የሰጠውን ተስፋ አመነ። ከዚያም እግዚአብሔር ለአብርሃም ይስሐቅን ሰጠው። ላም አብርሃም ይስሐቅን እንዲሠዋለት አዘዘው። አብርሃም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ተቀብሉ ይስሐቅን ሊሠዋለት ተዘጋጀ። ይህ እንግዲህ አብርሃም እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ ወራሽ የሆነ ልጅ እንደሚሰጠው በእርሱ ለማመኑና በእርሱም ላይ ፍጹም የሆነ አለኝታ እንደነበረው ያረጋግጥልናል። ያዕቆብ በቁጥር 22 ውስጥ እንደሚለው በእምነቱ ሥራው ተፈጸመ። የእርሱ እውነተኛ እምነት በመልካም ሥራው ተረጋግጦ ታወቀ። በተመሳሳይ መንገድ ረዓብም ሁለቱን ዕብራውያን ሰላዮች ተቀብላ በረዳቻቸው ጊዜ ስእግዚአብሔር ላይ እምነት እንደ ነበራት አረጋግጣለች። ረዓብ አስቀድማም በእስራኤል አምላክ እንደምታምን አስታውቃለች። ቀጥላም በእስራኤል አምላክ በእውነት የምታምን መሆንዋን ሰላዮቹን ተቀብላ በረዳቻቸው ጊዜ የእምነትዋን እርግጠኝነት አሳይታለች። እውነተኛ የሆነ እምነቷም በመልካም ሥራዋ ታይቷል፥ ተረጋግጧል፡፡  የያዕቆብ መልእክት ምዕራፍ 2 ለአማኞች ሁሉ በጣም ጠቃሚ የሆነ መልእክት ነው። ትናንትና ከተማርናቸው ክፍሎች ጋር አይቃረንም። ሰዎች በበጎ ሥራቸው ይጸድቃሉም ብሎ እያስተምርም። በምትኩ የሚለው እውነተኛና አዳኝ የሆነ እምነት ወደ መልካም ሥራ ፍሬ ይመራል ነው። ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት የኖረው የጀርመን ተሐድሶ አራማጅ ማርቲን ሉተር፥ የጳውሎስንና ያዕቆብን ትምህርት እንዲህ በማለት ያጠቃልለዋል፡ እምነት ብቻውን ያድናል፥ ግን የሚያድን እምነት ደግሞ ፈጽሞ ብቻውን አይደለም። ሉተር ይህን ሲል የሚያድን እምነት ያላቸው ሰዎች ሁልጊዜ መልካም ሥራ ይሠራሉ ማለቱ ነው።  2.2 ከጳውሎስ መልእክቶች አንዳንዶቹ፡- የሚያድን እምነት የታዛዥነትንና የመልካም ሥራ ፍሬዎችን ያፈራል ይላሉ።  ጥያቄ፡– ኤፌሶን 2፡8-10 አንብቡ። ሀ) እኛን በማዳን ረገድ የመልካም ሥራ ድርሻ ምንድን ነው? (ቁጥር 8-9) ለ) የደኅንነታችን ዓላማ ምንድን ነው? (ቁጥር 10)  ጥያቄ፡- 1ኛ ተሰሎንቄ 1፡2-3 አንብቡ። ሐዋርያው ጳውሎስ በሚጸልይበት ጊዜ ሁሉ ስለ ተሰሎንቄ ሰዎች ምንን እንደሚያስታውስ ተናገረ?  ጥያቄ፡- ሮሜ 1፡5 አንብቡ። ሐዋርያው ጳውሎስ ጸጋንና ሐዋርያነትን ለምን ዓላማ ተቀበለ?  እስከዚህ ድረስ በያዕቆብ ምዕራፍ 2 ውስጥ የተማርነውን ትምህርት የሚያብራሩ በዛ ያሉ ክፍሎች በአዲስ ኪዳን ውስጥ ይገኛሉ። በኤፌሶን 2፡8-9 ውስጥ ጳውሎስ እኛ የዳነው በጸጋው በማመን እንጂ በመልካም ሥራችን አለመሆኑን በግልጽ ይናገራል። ነገር ግን ወዲያውኑ እግዚአብሔር እኛን ያዳነበት ዓላማ እና መልካም ሥራ እንድንሠራ ነው ይላል። በእውነት የዳነ ሰው ይህን የእግዚአብሔርን ዓላማ ለመፈጸም መልካም ሥራ ይሠራል።  መልካም ሥራ የእምነታችን ውጤት ሲሆን ለእምነታችን ምስክር ነው። በ1ኛ ተሰሎንቄ ። ውስጥ ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ክርስቲያኖች በሚጸልይበት ጊዜ ሁሉ «የእምነታቸውን ሥራ» እንደሚያስታውስ ነግሮአቸው ነበር። «የእምነት ሥራ» የተባለው ሐረግ «ከእምነታችሁ የተነሣ የተገኘ የሥራ ፍሬ» ማለት ነው። ጳውሎስ ስለ ተሰሎንቄ ሰዎች መልካም ሥራ ያስታወሰበት ምክንያት

እምነት ከታዛዥነት ጋር እንዴት ይዛመዳል?  Read More »

ወደ እግዚአብሔር መመለስ ወይም «መለወጥ» 

This entry is part 78 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ ለደኅንነት አስፈላጊ ስለሆኑ ነገሮች ተምረናል። በዚህን ጊዜ ለደኅንነት አንድ ነገር ብቻ እንደሚያስፈልግ ተመልክተናል። ነገር ግን ይህ አንድ ነገር ደግሞ በሦስት ልዩ ልዩ መንገዶች እንደሚገለጽ አስተውለናል። አንዳንድ ጊዜ ይህ ነገር «ንስሐ» ተብሎ ይገለጻል። ስለዚህ ለመዳን ከራሳችን ይልቅ ወደ ክርስቶስ ብቻ መመለስ አለብን። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ይህ የደኅንነት አንድ ነገር «እምነት» ይባላል። ስለዚህ ለመዳን በመልካም ሥራችን መታመን ትተን በክርስቶስ፥ በእርሱ ሞትና በትንሣኤው መታመን መጀመር አለብን። በአዲስ ኪዳን ውስጥ የደኅነት መንገድ በሦስተኛው መንገድ የተጠቀሰበት ሁኔታም አለ። ይህ የደኅንነት አንዱ መንገድ በሦስተኛው ሌላው መንገድ የተገለጸው «ወደ እግዚአብሔር መመለስ” በሚል ነው። በሌላ ጊዜ ደግሞ ይህ «መለወጥ» ተብሎ ይጠራል፡ መለወጥ የሚለው ቃል ገቢራዊና ተንቀሳቃሽ የሆነ ቃል ነው። ሰዎች የደኅነትን ስጦታ ለማግኘት ሲሉ የሚኖራቸውን ስሜትና ድርጊት ያመለክታል። እዚህ ላይ ለደኅንነት «ወደ እግዚአብሔር መመለስ» ሲባል ምን ማለት ነው?  1. መለውጥ በብሉይ ኪዳን ውስጥ፡- በሐሰተኛ አማልክት ፈንታ በያሕዌ መታመንና መታዘዝ  ጥያቄ፡- ኢሳይያስ 31፡6 አንብቡ። ሀ) እግዚአብሔር እስራኤላውያንን እንዴት ይገልጻዋል? ለ) እግዚአብሔር እስራኤላውያን ምን እንዲፈጽሙ ይጠራቸዋል?  ጥያቄ፡- ሆሴዕ 11፡12 እና 12፡6 አንብቡ፡፡ ሀ) እስራኤል በእግዚአብሔር ላይ ምን አደረገ? ለ) እስራኤል ምን እንዲያደርግጠራው?  ጥያቄ፦ አሞጽ 4፡1፥ 4፥6 አንብቡ። ሀ) እስራኤል ምን ኃጢአት ሠራ? ለ) እግዚአብሔር እስራኤልን ቢቍጣውም ገና አልፈጸመም ያለው ምንድን ነው?  እግዚአብሔር ሰዎች እንዲለወጡ ወይም ወደ እርሱ እንዲመለሱ ወደ እርሱ ሊጠራቸው ምን ማለቱ እንደሆነ ብሉይ ኪዳን የዚህን መነሻ ምክንያት ይሰጠናል። የእግዚአብሔር ሕዝብ የሆኑት እስራኤልና ይሁዳ አንዱን እውነተኛ አምላክ ማምለክ ትተው ስለ ተመለሱ የብሉይ ኪዳን ነቢያት ሰበኩ፣ ደግሞም ጻፉ። በዙሪያቸው ያሉ ሕዝቦችን ሐሰተኞች አማልክትን ማምለክ ጀመሩ። እነዚህን ሐሰተኞች አማልክት እንዴት እመላኩዋቸው? የእነዚህን ሐሰተኛ አማልክት መቅደሶች ጎበኙ። እነዚህ ሐሰተኛ አማልክት መልካም ሰብል እንዲሰጡዋቸው፣ ከበሽታ እንዲጠብቁዋቸውና በጦር ሜዳ ድልን እንዲያጎናጽፉአቸው መሥዋዕትንና መባን አቅርበው ሰዉላቸው። ለወደፊቱ ስለሚሆነው ነገር ምክርና መመሪያን ከሐሰተኞቹ አማልክት ጠየቁ። በእነዚህ የሐሰት አማልክት ፊት ሞገስ ለማግኘት ሲሉ ትእዛዞቻቸውን ሁሉ ፈጸሙ። በእውነተኛው አምላክ ላይ በመደገፍ ፈንታ በሐሰተኞች አማልክት ላይ ተደገፉ። እነዚህ አማልክት እንደሚንከባከቡዋቸው ተማመኑባቸው። እግዚአብሔር በበኩሉ በእነዚህ ሐሰተኞች አማልክት መታመናቸውን ትተው ወደ እርሱ እንዲመለሱና በእርሱ ላይ እንዲመረኮዙና በእርሱ ብቻ እንዲታመኑ ጥሪ አቀረበላቸው። መሥዋዕታቸውንና ስጦታቸውን ለያህዌ ብቻ እንዲያደርጉ አሳስባቸው። መልካም መከር፥ ከበሽታ መዳንን እና በጦር ሜዳም ድልን እንዲያገኙ ወደ ያህዌ እንዲጸልዩና በእርሱ እንዲታመኑ ነገራቸው። ስለ ወደፊቱ ሁኔታም መመሪያ ያህዌን ቀርበው እንዲጠይቁ እሳሰባቸው። እምነታቸው በእርሱ ላይ ስለመሆኑ ለማስመስከር የያህዌን ትእዛዝ እንዲፈጽሙ ነገራቸው።  ስለዚህ እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ነቢያት አማካይነት ሕዝቡ ወደ እርሱ ይመለስ ዘንድ ጥሪ አቀረበ። በኢሳይያስ 31፡16 ውስጥ እንደተጻፈው እግዚአብሔር ዐመፀኞች የነበሩ እስራኤላውያን ወደ እርሱ ይመለሱ ዘንድ ነገራቸው። በሆሴዕ 12፡6 ውስጥ ሸንጋዮችንና ዐመፀኞች እስራኤላውያን ወደ እርሱ እንዲመለሱ ጥሪ ያቀርብላቸዋል። በአሞጽ 4፡6ም ላይ ሰካራሞችና በደለኞች የሆኑ እስራኤላውያን የቤቴልንና የጌልጌላን ሐሰተኞች አማልክትን ስላመለኩ በጥፋታቸው ቢቀጣቸውም ከኃጢአታችው አሁንም ያልተመለሱ መሆናቸውን እግዚአብሔር ይናገራቸዋል። የብሉይ ኪዳን ሕዝቦች ወደ ሐሰተኞች አማልክት በመመለስ በእነርሱ መታመን በሚጀምሩበት ጊዜ ሁሉ ወደ እርሱ ተመልሰው እንዲመጡ እግዚአብሔር ይጠራቸው ነበር።  ሐዋርያትም ወንጌልን መስበክ በጀመሩ ጊዜ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ ዘንድ ይህንኑ የመሰለ ጥሪ ነበር ያቀረቡት። ነገር ግን የእነርሱ ስብከት አትኩሮት የሚለየው ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስና በሥራው አማካይነት ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ ነበር።  2. መለወጥ በአዲስ ኪዳን ውስጥ፡- ወደ ኢየሱስ መመለስ ወደ እግዚአብሔር ለመምጣት ብቸኛው መንገድ ነው።  ጥያቄ፡- የሐዋ. 3፡19 አንብቡ። ጴጥሮለ ሕዝቡን ኃጢአታችሁ የሚደመሰሰው ምን ልታደርጉ ነው አለ?  ጥያቄ፡- የሐዋ. 9፡35 አንብቡ። ጴጥሮስ ኤንያን በፈወሰው ጊዜ የልዳና የሰርና ሕዝብ ምን አደረገ?  ጥያቄ፡- የሐዋ. 1፡19-21 እንብቡ። የቆጵርለና የቀሬና አማኞች ወንጌልን ፡ ባሰሙዋቸው ጊዜ በአንኪያ የነበሩ ብዙ ሰዎች ምን አደረጉ?  ጥያቄ፡- የሐዋ. 15፡19 አንብቡ። ጳውሎስና በርናባስ ወንጌልን የሰበኩላቸው አሕዛብ ስማት እንዴት እንደነበረ ነው ያዕቆብ የገለጻው?  ጥያቄ፡- የሐዋ. 26፡20 አንብቡ። ሐዋርያው ጳውሎስ በሄደበት ስፍራ ሁሉ ምንን እንደሚሰብክ ለንጉሥ አግሪን ነገረው?  ጥያቄ፡- 2ኛ ቆሮንቶስ 3፡13-16 አንብቡ። እንደ ቁጥር 16 ከእስራኤላውያን ዓይን መጋረጃ ው ይገፈፍ ዘንድ ምን መደረግ አለበት?  ጥያቄ፦ 1ኛ ተለሎንቄ 1፡9 አንብቡ። ሐዋርያው ጳውሎስ ለደቀረበው መልእክት የተሰሎንቄ ሰዎች ምላሽ ስሜት ምን ነበር? ጥያቄ፡- 1ኛ ጴጥሮስ 2፡25 እንብቡ። ሐዋርያው ጳውሎስ አንባቢዎቹ ምን እንዲያደርጉ ነገራቸው?  ሐዋርያት ሰዎች ወንጌልን ከሰሙ በኋላ ማድረግ ስለሚገባቸው አንደኛው መንገድ ደጋግመው ሲገልጹ ይህ መንገድ ወደ እግዚአብሔር መመለስ መሆኑን ይናገራሉ። በሐዋርያት ሥራ 3፡19 ውስጥ እንደምናገኘው ሽባው ሰው ከተፈወሰ በኋላ ለተሰበሰቡ አይሁዶች ጴጥሮስ ስብከት ባሰማቸው ጊዜ ኃጢአታቸው እንዲደመሰስ ንስሐ ገብተው ወደ እግዚአብሔር መመለስ እንዳለባቸው አበክሮ ነግሮአቸዋል። ጴጥሮስ አክሎ የእግዚአብሔርን መሢሕ እንደ ሰቀሉት ገልጾላቸዋል። አሁን ስለ ኢየሱስ የነበራቸውን አስተሳሰብ ቢለውጡና እርሱ እግዚአብሔር የሚሰጠው ደኅንነት መንገድ መሆኑን ቢያምኑ እግዚአብሔር ለዚህ ኃጢአታቸው ሁሉ ይቅርታን ይሰጣቸዋል። ጴጥሮስ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ በነገራቸው ጊዜ ኢየሱስን መናቅ ትተው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ብቸኛው መሢሕና መድኅን መሆኑን ተቀብለው ወደ እርሱ እንዲመለሱ ነበር። በሐዋርያት ሥራ 26፡20 ውስጥ ጳውሎስ ይህንኑ የመሰለ ሁኔታ ለንጉሥ አግሪጳ በነገረው ጊዜ ከሰማይ ራእይ ከመጣለት በኋላ ከኃጢአታቸው ተመልሰው በንስሐ ወደ እግዚአብሔር ዘንድ በመምጣት ይቅርታ ይቀበሉ ዘንድ ለአይሁዶችና ለአሕዛብ ወንጌልን እንደ ሰበከ ገልጦለታል (ቁጥር 18)። ይቅርታን ለማግኘት በሌላ በማንም ላይ መመርኮዝ ሳይኖርባቸው በኢየሱስ ላይ ብቻ መደገፍ ነበረባቸው። በእነዚህ በሁለት ጥቅሶች ላይ ጴጥሮስና ጳውሎስ «ንስሐ» እና «ወደ እግዚአብሔር መመለስ” የሚሉ ቃላትን ወንጌልን የሰሙ ሰዎች ስለሚኖራቸው ስሜትና ምላሽ ለመግለጽ ተጠቅመውባቸዋል። በሁለቱም ጥቅሶች ላይ «ንስሐ» እና ወደ እግዚአብሔር መመለስ» የሚሉት አሳቦች ተመሳሳይ ናቸው። የሐዋርያት ሥራ 11፡21 በአንጾኪያ የነበሩ በተለይም አሕዛብ፥ የቀሬናና የቆጵሮስ ሰዎች «ስለ ጌታ ኢየሱስ ወንጌል» ስሰበኩላቸው ጊዜ ምላሻቸው ምን እንደነበረ ያስረዳል። የምሥራቹን ቃል ከሰሙ በኋላ አምነው ወደ ጌታ ተመለሱ። ስለ ጌታ የደኅንነት የምሥራቹን ወንጌል ከሰሙ በኋላ ወደ ኢየሱስ ተመለሱ። በዚህ ክፍል እምነትና ወደ ኢየሱስ መመለስ ሁለቱም ተመሳሳይ አሳቦች ናቸው። በሐዋርያት ሥራ 9፡35 ውስጥ ኤኒያ ሲፈወስ ያዩ ሰዎች ላግታቸውን ወደ ጌታ በመመለስ ገልጠዋል። በሐዋርያት ሥራ 59 ውስጥ እንደተጠቀሰው በኢየሩሳሌም ሸንጎ ላይ ሐዋርያው ያዕቆብ በአንጾኪያ የነበሩ አሕዛብ ወደ ክርስቶስ መምጣታቸውን ጳውሎስና በርናባስ ባደረጉት የመጀመሪያው የወንጌል አገልግሎት ጉዞ ሳቢያ ጌታን የተቀበሉትን «ወደ እግዚአብሔር የተመለሱትን» ሲል የሰዎቹን ሁኔታ ገልጾአል። በሐዋርያት ሥራ ውስጥ ባሉ በእነዚህ ጥቅሶች በእያንዳንዳቸው «ወደ እግዚአብሔር መመለስ» የሚለው አሳብ ከንስሐና ከእምነት ጋር በጣም ተመሳሳይ ነው። «ወደ እግዚአብሔር መመለስ» ማለት በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛ ሆኖ የኃጢአት ይቅርታን ለማግኘት በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ብቻ መደገፍ ማለት ነው።  «ወደ እግዚአብሔር መመለስ» የሚለው አሳብ በአንዳንድ መልእክቶችም ውስጥ ይገኛል። በ2ኛ ቆሮንቶስ 3፡13-16 ጳውሎስ አይሁዶች አሮጌው ኪዳን ሰዓይኖቻቸው ላይ እንደሚደረግ ዐይነ ርግብ ስለሆነ፣ ጊዜያዊ መሆኑንና ለደኅንነትም ብቁ እንዳልሆነ ለማስተዋል አልቻሉም ይላል። ጨምሮም ሲናገር፣ ማንኛውም ሰው ወደ እግዚአብሔር በሚመለስበት ጊዜ፣ መጋረጃ ው ይወገዳል ይላል። ወደ ጌታ መመለስ ማለት ለደኅንነት በአሮጌው ኪዳን ሥርዓትና ሕግ መታመንን ትቶ መመለስና በኢየሱስ መታመን ማለት ነው። በ1ኛ ተሰሎንቄ 1፡9 ውስጥ ጳውሎስ ለተሰሎንቄ አማኞች ሲናገራቸው ከሐሰተኛ አማልክት አምልኮ ወደ እግዚአብሔር የተመለሱ መሆናቸውን ያሳስባቸዋል። ለእንክብካቤ እነርሱን ለመከላከል ለመምራት ባለው ሁኔታ በሐሰተኞች አማልክት መተማመናቸውን ትተው እውነተኛ በሆነው አምላክ መታመን ጀምረዋል። በመጨረሻውም ላይ፣ በ1ኛ ጴጥሮስ 2፡25፣ በኢሳይያስ 53 ውስጥ የተጻፈውን በማስታወስ ጴጥሮስ ሰዎቹን እንደ ባዘኑ በጎች እንደ ነበሩና፣ ክርስቶስ በመስቀል ላይ መሞቱን ባመኑ ጊዜ ወደ ነፍሳቸው እረኛና ጠባቂ መመለሳቸውን ገለጸላቸው።  አንድ በጣም ማስታወስ የሚገባን ነገር በእነዚህ

ወደ እግዚአብሔር መመለስ ወይም «መለወጥ»  Read More »

የመዳኛ መንገድ፡- ንስሐ እምነትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ 

This entry is part 77 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ባለፈው ሳምንት ወደ ደኅንነት ስለ መድረሻ መንገዶች ተምረን ነበር። ምንም እንኳን እግዚአብሔር ሰዎች ሁሉ መጥተው ደኅንነቱን እንዲቀበሉ ቢጠራቸውም፥ በራሳቸው ነፃ ምርጫ አምላካዊ ጥሪውን ሳይቀበሉ ቀሩ። ነገር ቀን እርሱ በምሕረቱ ጥቂቶችን መርጦ ወደ እርሱ እንደሚጠራ ተገንዝበናል። ይህ ውጤታማ ጥሪም የተጠሩት ጥሪውን ተቀብለው ወደ እርሱ እንዲመጡ አድርጓል። ይህም ውጤታማ ጥሪ በንስሐና በእምነት ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ አድርጓል። በዚህ ሳምንት ደግሞ ሰዎች የእግዚአብሔርን ደኅንነት ለመቀበል ስላለባቸው ኃላፊነት እናጠናለን። ስለሆነም የእኛ ኃላፊነት ንስሐ መግባትና ማመን ነው።  የመጀመሪያ ቀን  ንስሐ  ጥያቄ፡- በአካባቢአችሁ የሚኖሩ ሰዎችን አንድ ሰው ለመዳን ምን ማድረግ አለበት ብላችሁ ብትጠይቋቸው፥ መልሳቸው ምን የሚል ይሆናል?  ጥያቄ፦ ማርቆስ 1:15 አንብቡ። ኢየሱስ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለች ብሎ ሕዝቡን ባስተማረ ጊዜ ምን እንዲያደርጉ አሳሰባቸው?  ጥያቄ፡- ሉቃስ 24፡46-47 አንብቡ። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ እንዲሰብኩ ባዘዛቸው ጊዜ ምን ነገራቸው?  ጥያቄ፡- የሐዋ. 3፡19 አንብቡ። ሐዋርያው ጴጥሮለ ለሕዝቡ የመጽናናት ዘመን እንዲመጣላቸው ለማድረጎ የኃጢአታቸውን ይቅርታ ለመቀበል እንዲችሉ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ነበር የነገራቸው?  ጥያቄ፡- የሐዋ. 1፡18 አንብቡ። እግዚአብሔር ለአሕዛብ ምንን ሰጠ?  ጥያቄ፡- የሐዋ. 17:30 አንብቡ። ሐዋርያው ጳውሎስ፥ እግዚአብሔር በየክፍሉ ያለውን ሕዝብ ምንን ያዝዘዋል ብሎ ለአቴናውያን ነገራቸው?  ጥያቄ፡- የሐዋ. 20፡21 አንብቡ። ሐዋርያው ጳውሎስ ለአይሁድና ለአሕዛብ ምን መልእክትን ሰጣቸው?  ጥያቄ:- 2ኛ ቆሮንቶስ 7፡10 አንብቡ። ሀ) እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ወዴት ይመራል? ለ) ዓለማዊ ኀዘን ምንን ያመጣል?  ጥያቄ፡- 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡25-26 አንብቡ። ሰዎች ከዲያብሎስ ወጥመድ ወደጊያመልጡበት፥ ወደ እውነተኛው እውቀት የሚያደርስ ምንድን ነው?  ዛሬ አንዳንድ ሰዎች በኢትዮጵያ ውስጥ የእግዚአብሔርን ደኅንነት ለማኘት ሲሉ ብዙ ነገሮችን ማድረቅ እንዳለባቸው ያምናሉ። ለምሳሌም ያህል፡ መቆም፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት መፈጸም፥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መጠመቅ፥ እንደዚሁም ያለማቋረጥ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድና ለድሆች መመጽወትና ለቤተ ክርስቲያን መባ መስጠት የመሳሰሉትን ያደርጋሉ። ዳሩ ግን መላውን የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ስንመለከት፥ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርት ለወንጌል መልእክት መልስ ሊሰጥበት የሚገባ አንድ ጥሪ ብቻ ያቀርባሉ። አንዳንዴ ይህ ጥሪውን ሰምቶ ምላሽ የመስጠት ነገር ንስሐ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፤ በሌላ ሁኔታ ደግሞ እምነት ወይም በክርስቶስ ማመን ይባላል። እንዲሁም ይኸው ጥሪን መቀበልና ውጤት ማሳየት መለመጥ ወይም ወደ እግዚአብሔር መመለስ ሊሆን ይችላል። ግን በንስሐ፥ በእምነትና በመመለስ ወደ እግዚአብሔር መምጣት ሦስቱም ለደኅንነት ሁኔታ ተለያይተው የሚታዩ ሳይሆኑ፥ አንድ ሰው ለመዳን በየደረጃ ው ሊያሟላቸው የሚገባ ግዴታዎች ናቸው። እንዲህ ማለትም እግዚአብሔር ለደኅንነት ያለው አንድ ሁኔታን የምንመለከትባቸው ሦስት መንገዶች ናቸው። ስለሆነም ንስሐ፥ እምነትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ እግዚአብሔር ለደኅንነት ያለውን አንድ ሁኔታ በሦስት መንገዶች የመገንዘብና የማብራራት ነገር ነው። ከዚህ በመነሣት የንስሐን የእምነትና ወደ እግዚአብሔር ስለመመለስ ሁኔታ በማጥናት፥ አንድ ሰው የእግዚአብሔርን የደኅንነት ስጦታ ለመቀበል ምን የጥሪ መልስ መስጠት እንዳለበት መገንዘብ እንችላለን። ስለሆነም ዛሬ ስለ ንስሐ ባለው አስተሳሰብ ላይ ጥናት እናካሂድና ነገ ደግሞ ስለ እምነት ከተማርን በኋላ በሦስተኛው ቀን ወደ እግዚአብሔር መመለስ ሲባል ምን ማለት እንደሆነ እናጠናለን።  1. እግዚአብሔር ንስሐ ለሚገቡት ደኅንነትን ይሰጣል።  ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወንጌልን በሰበኩ ጊዜ ቃሉን በንስሐ መንፈስ እንዲቀበሉ ጥሪ አቀረቡላቸው። በማርቆስ 1፡15 ውስጥ በሚገኘው በኢየሱስ የአገልግሎት መጀመሪያ ላይ እርሱ ያደረገው ሰዎች ንስሐ እንዲገቡና በወንጌል እንዲያምኑ ነበር፥ የዚህንም ምክንያት ሲያስረዳ የእግዚአብሔር መንግሥት መቅረቧን በመግለጽ ነበር። በሉቃስ 24፡46-47 ባለው ክፍል፥ በአገልግሎት ፍጻሜ ላይ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ሄደው የንስሐ ስብከት ለዓለም ሕዝቦች እንዲሰብኩ አዘዛቸው። ሕዝቦች ሁሉ የኃጢአታቸውን ይቅርታ ሊያገኙ የሚችሉት በንስሐ ብቻ ነው። ደቀ መዛሙርቱም ለጌታ ትእዛዝ ተገዙ። በሐዋርያት ሥራ 3፡19 ውስጥ ጰጥሮስ ሽባውን ሰው ከፈወሰ በኋላ በኢየሩሳሌም በነበረው ቤተ መቅደስ ውጭ ለነበሩት ሁሉ ሰበከላቸው። በስብከቱም ላይ ንስሐ እንዲገቡና ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ፥ ይህን ሲያደርጉ ለኃጢአታቸው ይቅርታ እንደሚያገኙና የመጽናናት ዘመንም | እንደሚሆንላቸው ነገራቸው። ይህም እግዚአብሔር ደኅንነትን፥ የሰላም | መንግሥትን፥ ብልጽግናን እንዲሁም ፍትሕንና የተትረፈረፈ በረከትን ለእስራኤል እንደሚሰጥ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሰጠው ተስፋ ፍጻሜ ነው። በዚህ ንስሐ አማካይነት ብቻ ይህን የደኅንነት በረከት ተቀብለው ወደዚያኛው መንግሥት ሊገቡ ይችላሉ። በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 10 ውስጥ ጰጥሮስ ለቆርኔሌዎስ ከሰከለት በኋላ፥ በኢየሩሳሌም ለነበረችው ቤተ ክርስቲያን የአይሁድ መሪዎች ስለ ሁኔታው ዘገባ አቀረበ። እግዚአብሔር የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ለአሕዛብ ስለ መስጠቱ በሰሙ ጊዜ እግዚአብሔር እንዳዳናቸው ተረዱ። በሐዋርያት ሥራ 11፡18 ውስጥ ስሜታቸውን ሲገልጹ፥ እግዚአብሔር ለአሕዛብ ለአዲስ ሕይወት የሚያበቃቸውን ንስሐ ሰጥቷቸዋል አሉ። እንግዲህ አዲስ ሕይወትን የሚሰጠው በንስሐ አማካይነት ነው። ጳውሎስ ለአቴናውያን ስብከቱን ሊያሰማ በየትም ያሉ ሕዝቦች በፍርዱ ቀን ጻድቃን ሆነው እንዲገኙ ንስሐ መግባት እንዳለባቸው እግዚአብሔር ያዝዛል ብሏቸው ነበር። በሐዋርያት ሥራ 20፡21 ውስጥ ጳውሎስ ለአይሁድም ሆነ ለአሕዛብ በየትም ስፍራ በሰበከ ጊዜ፥ በንስሐ ወደ እግዚአብሔር መመለስ እንዳለባቸውና በኢየሱስ ማመን እንዳለባቸው የመሠከረ መሆኑን ለኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ነግሮአቸው ነበር። እንዲሁም በ2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡25-26 ባለው ውስጥ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ እግዚአብሔር የሚሰጠው ንስሐ ከዲያብሎስ ወጥመድ ሊያወጣ ወደሚችል የእውነት እውቀት ያደርሳል ነበር ያለው። በእነዚህ ክፍለ ምንባቦች ላይ በግልጽ እንደተብራራው እግዚአብሔር ይቅርታን፥ ሕይወትን፥ የእውነት ዕውቀትንና የደኅንነቱንም በረከት የሚሰጠው በንስሐ ወደ እርሱ ለሚመጡት ነው።  2. ንስሐ ምንድን ነው?  2.1 ንስሐ ስለ ኃጢአት፥ ስለ ኢየሱስና ስለ ደኅንነት «አሳባችንን መለወጥ» ማለት ነው።  አንድ ሰው ለመዳን ቢፈልግ ንስሐ መግባት አለበት። ነገር ግን «ንስሐ» ምን ማለት ነው? በግሪኩ ቃል «ንስሐ» ማለት «አስተሳሰብን መለወጥ» ወይም «ስለ አንድ ነገር ለየት ባለ መንገድ ማሰብ» ማለት ነው። ንስሐ መግባት መጸጸት ወይም አሳብን መለወጥ ማለት ነው። ንስሐ ከበፊቱ የተለየ አስተሳሰብ መኖር ነው። ታዲያ ሰዎች ስለ ምን ጉዳይ ነው አሳባቸውን የሚለውጡት፥ ወይም ለየት አድርገው የሚያስቡት? በዚህ ክፍለ ምንባብ እንደ ተመለከትነው አሳባቸው የሚለወጠው ስለ ኃጢአት፥ እንደዚሁም ስለ ክርስቶስና ስለ ይቅርታ የሚያስቡበትን መንገድ ነው። በሉቃስ 24፡46-47 ውስጥ ኢየሱስ ሲናገር ንስሐና ጸጸት የኃጢአትም ይቅርታ «በክርስቶስ ስም» ሊሰበክ ይገባል ይላል። ሰዎች የኃጢአትን ይቅርታ ለመቀበል እንዲችሉ ስለ መሢሑ ያላቸውን አስተሳሰብ መለወጥ አለባቸው። ኢየሱስን እንደ መሢሕ አድርገው ሲቀበሉ ብቻ የኃጢአትን ይቅርታ በእርሱ አማካይነት ሊያገኙ እንደሚችሉ በመግለጽ እርሱን ሊቀበሉ ይገባቸዋል፡ ኢየሱስ ስለ መሢሑ ሞትና ትንሣኤ ብሉይ ኪዳን የተነበየ መሆኑን ደፋ መዛሙርቱን አስታውሶአቸው ነበር። በዚህም ሊያስገነዝባቸው የፈለገው ሰዎች የኃጢአት ይቅርታን ሊቀበሉ እንዲችሉ በሞቱና በትንሣኤው አማካይነት ደኅንነትን ማግኘት እንዳለባቸው ሲያሳስባቸው ነው። ስለዚህ ሰዎች አሳባቸውን በመለወጥ፥ በኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ የሚገኘው የኃጢአት ይቅርታ መቀበል አለባቸው።  በሐዋርያት ሥራ 3፡19 ውስጥ ተመሳሳይ አሳብ እናገኛለን። ጰጥር በኢየሩሳሌም ከቤተ መቅደስ ውጭ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ኢየሱስ ለሰቀሉት ሰዎች ስብከትን ያሰማ ነበር። እርሱም ኢየሱስን እንደ ሰቀሉ፡ አስታወሳቸውና ቀጥሎም ይህም እግዚአብሔር በነቢያት አማካይነት በብሉ ኪዳን ውስጥ የተናገረው ትንቢት ፍጻሜ እንደሆነ አስገነዘባቸው። ሕዝቡና ይህን በሰሙ ጊዜ ስለ ኢየሱስ የነበረውን አሳባቸውን መለወጥ ነበረባቸው እርሱን ሞት የሚገባው መሢሕ አድርገው በመመልከት ፈንታ እንደ እግዚአብሔር እውነተኛ መሢሕ ሊቀበሉት ይገባ ነበር። ይህን ቢያደርጉ ኖሮ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተሰጠው የደኅንነት በረከት ይህ በሆነባቸው ነበር። እንደዚሁም ኢየሱስን በገደሉት ጊዜ ኃጢአት መሥራታቸውን አምነው መቀበል ይኖርባቸው ነበር። የኃጢአታቸውንም ይቅርታ ለማግኘት እርሱን መቀበል ነበረባቸው። ስለ ኢየሱስ፥ ስለ መስቀል ሞቱና እንዴት ይቅርታን እንደሚያገኙ እንዲሁም የእግዚአብሔርን የደኅንነት በረከት እንዴት እንደሚቀበሉ ጸጸትና ንስሐ አሳባቸውን እያስለወጣቸው ነበር።  በሐዋርያት ሥራ 10፡34-43 ጴጥሮስ ለቆርኔሌዎስና ለቤተሰቡ ስብከትን ያቀርብ ነበር። ኢየሱስ እንደ ተሰቀለ፥ ከሙታን እንደ ተነሣና ብዙዎችም እንዳዩት ነገራቸው። ኢየሱስ በሰዎች ላይ የሚፈርድ እርሱ ብቻ ነው። በእርሱ የሚያምኑት ብቻ የኃጢአት ይቅርታን ይቀበላሉ። ጴጥሮስ በትምህርቱ ላይ የኃጢአት ይቅርታ የሚያገኙት በኢየሱስ የሚያምኑ ብቻ መሆናቸውን እንደ ነገራቸው መንፈስ ቅዱስ በቆርኔሌዎስና በቤተሰቡ ላይ ወረደ።

የመዳኛ መንገድ፡- ንስሐ እምነትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ  Read More »

ስለ እግዚአብሔር ምርጫና ለደኅንነት ስለሚያደርገው ጥሪ ጥያቄዎች 

This entry is part 76 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

በዚህ ሳምንት ውስጥ ሰዎችን ለደኅንነት ስለሚያበቃው አስቸጋሪ ስለሆነ የምርግ ርእሰ ጉዳይና ስለ ውጤታማ ጥሪ ስናጠና ቆይተናል። በዚህ ትምህርታችን ውስጥም ሰዎች እንዴት ወንጌልን ሰምተው የእርሱን ደኅንነት እንደሚቀበሉ ለመገንዘብ ችለናል። ነገር ግን ሰዎች በኃጢአታቸው ምክንያት ምርጫው ለእነርሱ ቢተው፥ ለእግዚአብሔር ጥሪ ስፍራ ስለማይሰጡት ላይቀበሉት ይቀራሉ። እግዚአብሔር አንዳንድ ሰዎችን መርጦ ወደ ራሱ እንደሚጠራቸው መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ የሚያስተምር መሆኑን አስተውለናል። ስለዚህ የእግዚአብሔር ምርግና ጥሪ ሰዎች ጥሪውን ተቀብለው መቀበላቸውን እንዲገልጹ ይረዳቸዋል።  ብዙ ክርስቲያኖች በእነዚህ አስቸጋሪ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ላይ ጥያቄዎች አሉዋቸው። እንዲህ ይላሉ፡- እግዚአብሔር አንዳንድ ሰዎችን መርጦ ሊጠራ፥ ሌሎችን በመተው እነርሱም እርሱን ችላ ማለታቸውን ቢቀጥሉበት ታዲያ ይህ ፍትሐዊ ነውን? እንግዲህ ቀደም ሲል እንዲህ ላሉት አንዳንድ ጥያቄዎች ሮሜ ምዕራፍ 9 መልስ ሊሰጥ ተመልክተናል። ሮሜ ምዕራፍ 9 እግዚአብሔር አንዳንድ ሰዎችን መርጦ ለምን ወደ ደኅንነት እንደሚጠራቸው ሦስት እውነታዎችን ያስታውሳል፡  1. ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔርን ስላልተቀበሉት ለእግዚአብሔር ቁጣ በቅተዋል። ስለዚህ ማንም ሰው የእርሱን ምሕረት በራሱ ለማግኘት ብቁ አይደለም። ስለዚህ ሰዎች ሁሉ ለቁጣው የተገቡ ሆነው ሳለ ምሕረቱን ለአንዳንዶቹ በመስጠቱ ፍትሐዊ አይደለም ሊባል አይችልም። ምሕረት ምሕረት እንዲሆን ምሕረቱን ለመቀበል ብቁ ላልሆነው ሰው ሉዓላዊ ክፍል በሥልጣኑ መርጦ ሊሰጠው ይገባል።  2. እግዚአብሔር ፍጹም ጠቢብና ሁሉን ቻይ ነው። የሚሰጠውም ምሕረት የተመሠረተው በጥበቡ፥ በጻድቅነቱና በቁጥጥሩ ላይ ነው። ለውሳኔምቹ ሁሉ መልካም ዓላማ አለው።  3. እግዚአብሔር ምሕረቱን ለሌሎች ለመስጠት የተቀሩት በነፃ ፈቃዳቸው እርሱን መተዋቸውን ይመለከታል።  ዛሬ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ምርጫና ጥቂቶቹን ወደ ደኅንነት ስለ መጥራቱ የሚያቀርቡዋቸውን ሌሎች ጥያቄዎች ለመመለስ እንሞክራለን። እግዚአብሔር አስቀድሞ በማወቁ ጥሪው እንዴት ይመጣል?  ጥያቄ፡- ሮሜ 8፡29 አንብቡ። እግዚአብሔር፥ የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ እነማንን መረጠ?  ጥያቄ፡- 1ኛ ጴጥሮስ 1፡2 አንብቡ። እግዚአብሔር ሕዝቡን በምን መሠረት መረጠ?  ጥያቄ፡- ዘፍጥረት 4፡1 አንብቡ። አዳም ሚስቱን አወቀ ሲል ምን ማለት ነው?  ጥያቄ፡– ኤርምያስ 1፡5 አንብቡ። እግዚአብሔር ኤርምያስን አስቀድሞ መች አውቀው?  ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮንቶስ 8፡3 አንብቡ። እግዚአብሔርን ስለሚወድ ሰው የተረጋገጠለት ምንድን ነው?  ጥያቄ፡- ሮሜ 11፡2 አንብቡ። እግዚአብሔር እነማንን አልጣላቸውም?  በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተለያዩ ስፍራዎች የእግዚአብሔር ጥሪ የመጣው አስቀድሞ ከሚያውቀው አኳያ መሆኑን እንማራለን። በሮሜ 8፡29 ውስጥ አስቀድሞ የመረጣቸውን የልጁን መልክ እንዲመስሉ ወሰነ ይላል። 1ኛ ጴጥሮስ 1፡2፣ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን መረጠ ይላል። ታዲያ እንዲህ ማለት ለዘላለም ባለፉት ጊዜያት ውስጥ እግዚአብሔር በጊዜ አማካይነት አሻግሮ ሲመለከት ሰዎች በነፃ ምርጫ የሚያደርጉትን ውሳኔ ካስተዋለ በኋላ ባየው ላይ በመመሥረት መረጣቸው ማለት ነው? ይህ አጠያየቅ ስእነዚህ ጥቅሶች ጽንሰ-አሳብ ላይ ያተኮረ ቢመስልም፣ እንደ እውነቱ ከሆነ ጥቅሶቹ የሚገልጹት አሳብ ይህ አይደለም። «አስቀድሞ ማወቅ» የሚለው አሳብ እግዚአብሔር የሚሆነውን ያውቃል ማለት አይደለም። «አስቀድሞ ማወቅ» ማለት እግዚአብሔር አስቀድሞ እነዚህን ሰዎች ስለሚያውቃቸው በዘመናት አስቀድሞ እንደ ራሱ ሕዝብ አብሮአቸው ግንኙነት ነበረው ማለት ነው። በዘፍጥረት 4፡1 ውስጥም ስለ አዳም ሚስቱን ስለማወቅ የተጠቀሰው ተመሳሳይ ቃል ነው። አዳም ስለ ሚስቱ አንዳንድ ነገሮችን ብቻ የሚያውቅ አልነበረም። እንደ ሰው በግል በሚታወቅ ሁኔታ ሁሉ ያውቃት ነበር። በኤርምያስ 1፡5 ውስጥ ተመሳሳይ ቃል የተጠቀሰ ሲሆን፥ ቃሉ እግዚአብሔር ኤርምያስ ከመወለዱ አስቀድሞ ስለ እርሱ አንዳንድ ነገሮችን ያውቅ ነበር አይልም። በዚህ ፈንታ ቃሉ፥ እግዚአብሔር ኤርምያስ ከመወለዱ በፊት በግል ያውቀው ነበር ነው የሚለው። 1ኛ ቆሮንቶስ 8፡3። ውስጥ ያለውም ቃል ይህንኑ የመሰለ ስለሆነ እግዚአብሔርን የሚወድ ሰው በእግዚአብሔር ይታወቃል ይላል። ስለዚህ እግዚአብሔር ስለሚወደው ሰው አንዳንድ ነገሮችን ብቻ የሚያውቅ አይደለም። እግዚአብሔር ስለሚወደው ሰው ከቅርብና ከተወዳጀ ሁኔታ በመነሣት ያውቀዋል። ስለዚህ እግዚአብሔር ከሚወደው ሰው ጋር ግንኙነት አለው። ሮሜ 112 ተመሳሳይ በሆነ ቃል በመጠቀም እግዚአብሔር አስቀድሞ የሚያውቀውን ሕዝቡን እስራኤልን አልጣለም ይላል። እግዚአብሔር ስለ እስራኤል አንዳንድ ነገሮችን ብቻ አልነበረም የሚያውቀው። ነገር ግን እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ቀንኙነትም ነበረው። እነርሱ ሕዝቡ ሲሆኑ፣ እርሱ ደሞ አምላካቸው ነበር። ስለዚህ እንግዲህ «አስቀድሞ ማወቅ» ሲባል፣ «አስቀድሞ ስለ አንድ ሰው አንዳንድ ነገሮችን ማወቅ» ማለት አይደለም። በመሆኑም «አስቀድሞ ማወቅ ሲባል፣ «አስቀድሞ ከአንድ ሰው ጋር እንኙነትን መመሥረት» ማለት ነው። ስለዚህ ሮሜ 8፡29 እና 1ኛ ጴጥሮስ 1፡2 የሚያስተምሩት እግዚአብሔር ስለ ሰዎች በሚያውቀው ላይ በመመሥረት እንደሚመርጣቸው አይደለም። ይልቅስ፣ እነዚህ ጥቅሶች የሚሉት ከዘመናት በፊት በእነርሱ ላይ ባለው ፍቅርና ከእነርሱ ጋር ባለው ግንኙነት መሠረት መረጣቸው ነው የሚሉት።  እግዚአብሔር ሰዎች ሁሉ ለጥሪው መልስ እንዲሰጡት ሁኔታዎችን አመቻችቷል?  ጥያቄ፡- ዮሐንስ 1፡9 አንብቡ። ሀ) እውነተኛው ብርሃን፥ ለእነማን ብርሃን ይሰጣል? ለ) ዮሐንስ 1፡10-11 አንብቡ። ኢየሱስን አውቀው ያልተቀበሉት እነማን ናቸው? ሐ) ዮሐንስ 1፡12-13 እንብቡ። ኢየሱስን እነማን ተቀበሉ? መ) ዮሐንስ  3፡19-21 እንብቡ፡ ይህ ብርሃን ምን ያደርጋል?  በዚህ ሳምንት ትምህርት ውስጥ እንደተመለከትነው እግዚአብሔር ወደ ራሱ ከሳባቸው በስተቀር ሌሎች ለእግዚአብሔር ጥሪ መልስ እንዳይሰጡ ኃጢአታቸው ከልክሎአቸው ነበር (ዮሐንስ 6፡37፥44፤ 8፡34 ኤፌሶን 2፡1-10፤ 4፡18፤ ሮሜ 3፡11፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡6-16፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡3-4)። ሰዎች ሁሉ ወደ ክርስቶስ ሊመጡ እንዲችሉ እግዚአብሔር በልባቸው ውስጥ ሥራ ሠርቷልን? ዮሐንስ 1፡9 እውነተኛው ብርሃን የሆነው ኢየሱስ ብርሃኑን በሰዎች ሁሉ ላይ አበራ ይላል። እንዲህ ማለት ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ ዘንድ ለመምጣት ይችሉ ዘንድ ኢየሱስ ራሱን ገልጦላቸው ነበር ማለት ነውን? አይደለም። ዮሐንስ 1፡9 ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ ይመጡ ዘንድ ኢየሱስ አመቻችቶላቸዋል አይልም። ዮሐንስ 1፡9 የሚለው ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም በመጣ ጊዜ በሰዎች ልጅ ውስጥ የነበረውን ይፋ አውጥቶ ለማሳየት ብርሃኑን በእያንዳንዱ ሰው ላይ አበራ ነው። በዚህ ክፍል “ብርሃን” ተብሎ የተጠቀሰው ቃል ወደ መንፈሳዊ ንዛቤ ስለሚመጣ ሰው እንዲገለጽ ተደርጎ በጥቅም ላይ አልዋለም። ዮሐንስ 1፡10–13 ያለው ክፍል የዮሐንስ 1፡9ን ቃል ትርጉም ግልጽ ያደርገዋል። ዮሐንስ 1፡10-11 የተጻፈው ቃል እውነተኛ ብርሃን የነበረውን ኢየሱስን ያልተቀበሉትን ክፉዎች አድርጎ አቅርቦአቸዋል። ዮሐንስ 1፡12-13 በአንጻሩ ኢየሱስን የተቀበሉትን ወገኖች ጻድቃን አድርጎ አቅርቦአቸዋል። ዮሐንስ ይህንኑ አሳብ በወንጌሉ በምዕራፍ 3፡19-21 ባለው ላይ በድጋሚ ሊናገር ኢየሱስ ወደ ዓለም ያመጣው ብርሃን በእያንዳንዱ ሰው ሥራ ላይ በማብራት በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ የነበረውን አሳየ ብሎ ነው። ዮሐንስ 1፡9 የኢየሱስ ብርሃን እያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ያለውን ገልጦ ማሳየት እንጂ የእርሱ ብርሃን ሰዎች ሁሉ ማንነቱን አውቀው ወደ እርሱ ይመጡ ዘንድ ማድረግ እንዳልነበረ ያስተምራል።  ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ ይመጡ ዘንድ የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለምን?  ጥያቄ፡- 2ኛ ጴጥሮስ 3፡9 አንብቡ። እግዚአብሔር እነማን ወደ ንስሐ ይመጡ ዘንድ ይላል?  ጥያቄ፡- 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡3-4 አንብቡ። እግዚአብሔር እነማን ይድኑ ዘንድ ይፈልጋል? ጥያቄ፡- ሕዝቅኤል 18፡23 አንብቡ። እግዚአብሔርን የሚያስደስተው ምንድን ነው?  ጥያቄ፡- 1ኛ ጴጥሮስ 2፡15፤ 4፡2 አንብቡ። ሀ) በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ «የእግዚአብሔር ፈቃድ የተባለው አገላለጽ ትርጉም ምንድን ነው? ለ) 1ኛ ጴጥሮስ 3፡17፤ 4፡19 አንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች መሠረት «የእግዚአብሔር ፈቃድ” ተብሎ የቀረበው አገላለጽ ትርጉም ምንድን ነው?  ጥያቄ፦ 2ኛ ሳሙኤል 2፡15 አንብቡ፡ ሀ) እግዚአብሔር በኤሊ ልጆች ላይ ምን ሊያደር ፈልጎ ነበር? ለ) ኦሪት ዘዳግም 28፡63ን አንብቡ፡ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን በማይታዘዙበት ጊዜ፥ ምን ሊያደርግባቸው ይፈቅድ ነበር?  እግዚአብሔር ሰውን ሁሉ ለማዳን ፈቃዱ መሆኑን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተለያዩ ክፍሎች እናነባለን። በ2ኛ ጴጥሮስ 3፡9 ውስጥ ሰዎች ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲመጡ ፈቃዱ ነው ይላል። በ1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡3-4 ደግሞ እግዚአብሔር ሰዎችን ሁሉ ለማዳን ይፈልጋል ይላል። እንዲሁም በሕዝቅኤል 18፡23 ውስጥ እግዚአብሔር ክፉዎችን በመቅጣት እንደማይደሰትና ሰዎች ከክፉ መንገዳቸው ተመልሰው ንስሐ ሊገቡ ደስ እንደሚለው ይናገራል። እንግዲህ እግዚአብሔር ሰው ሁሉ እንዲድን ከፈለገ ጥቂቶች ብቻ ወደ ደኅንነቱ እንዲመጡ ይመርጣቸዋል እንዴት ይባላል? መጽሐፍ ቅዱስ «ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ» በሁለት መንገዶች ይናገራል። አንዳንድ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ ሲናገር በትእዛዛቱ ውስጥ እንደተገለጠው ለፍጥረቱ

ስለ እግዚአብሔር ምርጫና ለደኅንነት ስለሚያደርገው ጥሪ ጥያቄዎች  Read More »