የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ

በልሳናት ስለመናገር ተጨማሪ ጉዳዮች (ክፍል 2) የተለያዩ ዓይነት ልሳናት አሉን?

በካሪዝማቲክና ካሪዝማቲክ ባልሆኑ ክርስቲያኖች መካክልና በካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች በራሳቸውም መካከል እንኳ የተለያዩ ዓይነት ልሳናት የመኖራቸው ወይም ያለመኖራቸው ጉዳይ ሌላው አከራካሪ ነጥብ ነው።  ጥያቄ፡- በአብዛኛዎቹ በካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች የሚነገሩት ልሳናት በሐዋርያት ሥራ 2 ላይ በሐዋርያት ከተነገሩት ልሳናት የተለዩ ናቸውን? እንደዚህ ብለህ የምታስበው ለምንድን ነው?  ክርስቲያኖች እነዚህን ጥያቄዎች የሚመልሱባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ።  1. በልሳናት መናገር ሁልጊዜ በሰው ቋንቋ መናገር ነው።  ይህን አመለካከት የሚያንጸባርቁ በአዲስ ኪዳን በልሳናት የሚናገሩ ሁሉ በሰው ቋንቋ እንደተናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ዎች ግልጽ ያደርጋሉ ይላሉ። ልሳን የሚያሰኘው ለሚናገረው ሰው የማይታወቅ ቋንቋ መሆኑ ነው። ሆኖም ግን አንዳንድ ጊዜ ቋንቋውን ለሚላዩ ሰዎች የታወቀ ነበር። ወይም ለሚያዳምጡት ሰዎች የታወቀ ባይሆንም እንኳ ሰብዓዊ ቋንቋነቱ የታወቀ ነበር።  ይህ ዛሬም ለሚነገሩ አንዳንድ ልሳኖች እንኳ የሚሠራ እውነት ነው። በደቡብ አሜሪካ ወንጌልን ሰምተው ያመኑ እጅግ ኋላ ቀር የሆኑ የአንድ ጐሣ አባላት ነበሩ። ትንሽ ቆይተው በአጐራባች ክልላቸው ወደሚገኙና ታሪካዊ ጠላቶቻቸው ወደሆኑ የአንድ ጐሣ አባላት ወንጌላውያንን ለመላክ ወሰኑ። የዚህ ጐሣ አባላት የሚገኙበት ቦታ የበርካታ ቀናት የእግር ጉዞ የሚጠይቅና የሚናገሩት ቋንቋም እነርሱ ከሚያውቁት ፈጽሞ የተለየ ነበር።  ወንጌላውያኑ ቋንቋውን የማያውቁ ቢሆኑም እንኳ ወደዚያ ስፍራ በደረሱ ጊዜ ወንጌልን ሊያካፍሏቸው በመቻላቸው ብዙዎች አመኑ። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ወንጌላውያኑ አዲሱ ጐሣ ወደሚገኝበት ስፍራ በደረሱ ጊዜ ከዚህ ቀደም ፈጽመው የማያውቁትን ቋንቋቸውን እንዲናገሩ ችሎታ ተሰጣቸው። ስለ ጌታ እየመሰከሩ ሳሉ ያልተላመደ ነገር መፈጸሙን እንኳ አላወቁም ነበር። ሚሲዮናውያን በአንድ ስብሰባ ላይ በተገኙበት ወቅት በልሳናት የሚናገሩ ሰዎች ይሠሩበት የነበረ እካባቢ ቋንቋን የተናገሩበትና እነርሱም በትክክል ቋንቋውን ሰምተው የተረዱበት ሁኔታም አለ። የሚያሳዝነው ግን አንዳንዴ የሚነገረው ነገር እግዚአብሔርን የማያሰከብር ሆኖ ይገኝ ነበር። በእንደዚህ ዓይነት ጊዜያት የልሳናቱ ባለቤት ሰይጣን እንጂ  መንፈስ ቅዱስ አልነበረም።  ይህን አመለካከት በአቋምነት የያዙ እመላካከታቸውን ለመደገፍ የሚከተሉትን ምክንያቶች ይሰጣሉ።  1. በልሳናት የመናገር ጉዳይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰው በሐዋርያት ሥራ 2 ላይ ነው። በልሳናት የተናገሩት የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት በሰው ቋንቋ መናገራቸው ግልጽ ነው። -ከሌላ የዓለም ክፍል የመጡት አይሁዳውያን በራሳቸው ቋንቋ የተነገረውን መረጻታቸው ይህን ያመለክታል። በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍም ሆነ በሌላ የአዲስ ኪዳን ክፍሎች በልሳናት መናገር ከሚታወቅ ቋንቋ ወደ ሌላ ነገር መቀየሩን የሚያመለክት አሳብ አናገኝም።  2. በልሳናት ስለመናገር ለማመልከት ብዙ ጊዜ በሥራ ላይ የዋለው የግሪክ ቃል «ግሎሳ» የሚለው ነው። በአዲስ ኪዳን በአጠቃላይ በግሪክ ሥነ-ጽሑፎች በሙሉ ስላ ሰብዓዊ ቋንቋ ለመናገር አገልግሎት ላይ የዋለው ቃል ይህ ነው።  3. በሐዋ 2፡6፥ 8 ላይ የተፈጸመውን ነገር ለመግለጥ አገልጎሎት ላይ የዋለው የግሪክ ቃል ዳይሬክተስ» የሚል ሲሆን ቃሉ ሁልጊዜ ሰብዓዊ ቋንቋን ለመግለጽ አገልግሎት ላይ የሚውል ነው።  4. በ1ኛ ቆሮ. 12፡10 ላይ ጳውሎስ ስለተለያዩ ልሳናት ይናገራል። «የተለያዩ ዓይነት» የሚለው የግሪክ ቃል የተለያዩ የቋንቋዎች ቤተሰቦችን ወይም ቡድኖችን የሚያሳይ ነው። ለምሳሌ አማርኛ አንድ ቋንቋ ቢሆንም እንኳ የሽዋ፥ የመንዝ፥ የጐንደርና የወሎ ወዘተ… እማርኛ አለ። ወይም በሊማትክ የቋንቋ መደብ ውስጥ ግዕዝ፥ ትግርኛ አማርኛ፥ ዕብራይስጥና ዐረብኛ አሉ። ጳውሎስ በዚህ ቦታ ይህን ቃል የተጠቀመው የተለያዩ ዓይነት ሰብዓዊ ቋንቋዎችን ለማመልከት ነው።  5. በ1ኛ ቆሮ 14 ጳውሎስ በልሳናት የመናገርን ዓላማ ለመግለጽ ኢሳ. 28፡11-2ን ይጠቅሳል። ከዚህ ጥቅስ በግልጽ እንደምንረዳው ‹ልሳናት› የተባለው የአሶራውያን ቋንቋ ስለሆነ ቋንቋ መሆኑ ግልጽ ነው።  6. በ1ኛ ቆሮ. 14 ጳውሎስ በጉባኤ የተነገረ ልሳን መተርጐም እንዳለበት ይናገራል። መተርጐም የመቻሉ ነገር ዝም ብሎ የሚመጣ ድምጽ ሳይሆን የሰው ቋንቋ መሆኑን የሚያመለክት እንደሆነ አንዳንዶች ያስባሉ።  ስለዚህ ይህ አመለካከት ያላቸው ሰዎች እውነተኛው በልሳናት የመናገር ስጦታ አንድ ሰው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተሞልቶ የራሱ ባልሆነ፥ አስቀድሞ ባልተማረውና ባላጠናው የሰው ቋንቋ መናገር ነው ይላሉ።  2. በልሳናት መናገር የሰው ቋንቋ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ብቻ የሚታወቅ ሰማያዊ ቋንቋም ሊሆን ይችላል።  ሌሎች ክርስቲያኖች ደግሞ በልሳናት መናገርን ተፈጥሮአዊ ያልሆነ ቋንቋ የመሆኑን ሁኔታ በግልጽ ስለተላማመዱ በልሳናት መናገር አንዳንድ ጊዜ የተለየ ቋንቋ መሆኑን ያምናሉ። በእግዚአብሔር ወይም በመላእክት አገልግሎት ላይ የሚውል ቋንቋ ነው።  በአዲስ ኪዳን እነዚህን አሳቦች ምናልባት የሚደግፉ በርካታ ጥቅሶች አሉ። የ1ኛ ቆሮ. 13፡1 ጳውሎስ ስለ ሰውና መላእክት ልሳናት ጠቅሷል። ስለዚህ ጳውሉላ በዚህ ቦታ የሚናገረው ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ሆኖ በተለይ ደግሞ በልሳናት የመናገርን ስጦታ ያለ አግባብ በሥራ ላይ ስለ ማዋል ስለነበር በልሳናት መናገር የሰው ባልሆነ የመላእክት ቋንቋ ሊሆን ይችላል ይላሉ።  የመጀመሪያውን አመለካከት በአቋምነት የያዙ ግን ሊመልሱ ጳውሎስ ሊናገረው የፈለገውን ነገር በግልጽና ክፍተኛ አትኩሮት ሰጥተ ለመናገር በማጋነን የተጠቀመበት ዘይቤያዊ አነጋገር እንጂ ሌላ አይደለም ይላሉ። ይህ ቀጥሎ በተመላከቱት ጥቅሶች የበለጠ ግልጽ ይሆናል። የካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች እንኳ እንድ ሰው በእምነት ስጦታ እየተዘዋወረ ተራሮችን ሲነቃቅል ለማየት አይጠብቁም።  ልሳናት ሰማያዊ ቋንቋ ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚያምኑት 1ኛ ቆሮ. 14፡2ን ይጠቅሳሉ። በዚያ ስፍራ ጳውሎስ ሰው በልሳናት በሚናገርበት ወቅት የሚናገረው ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው እይደለም ይላል። የሚረዳውም እግዚአብሔር እንጂ ሰው አይደለም። ስለዚህ ሰው በልሳናት በሚናገርበት ወቅት መንፈሱ ከእግዚአብሔር ጋር ይነጋገራል። ይህ ማለት በልሳናት መናገር ሰማያዊ ቋንቋ መናገር ማለት ነው ይላሉ።  በልሳናት መናገር ሰብዓዊ ቋንቋ ነው የሚል አቋም ያላቸው ደግሞ ሲመልሱ ቋንቋውን የሚረዳ ማንም ሰው እስከሌለ ድረስ ይህ ጥቅስ ሰብዓዊ ቋንቋን እንዳያመለክት የሚያግድ ምንም ነገር የለም ይላሉ።  3. በልሳናት መናገር የግድ የሰውም ሆነ የመለኮት ቋንቋ መሆን እያስፈልገውም። የልብን ስሜት የሚገልጥ መቃተት ወይንም ድምጽ ብቻ ሊሆን ይችላል።  በሮሜ 8፡26 መንፈስ ቅዱስ በማይነገር መቃተት እንደሚማልድልን ተጽፏል። ይህን አቋም የሚያንጸባርቁ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ እኛን ወክሎ ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል ማለት እንደሆነ እምነታቸው ነው። እርሱ ይህን በሚያደርበት ጊዜ ክርስቲያን በጸሎቱ ለመረዳት የማይቻል ድምጽ ያወጣል። እነዚህ ቋንቋዎች ሳይሆኑ ትርጉም የሌላቸው ድምጾች ናቸው። ትርጉም የለሽ የሆኑት ለእኛ ለሰዎች ነውና እንደ ቋንቋ ልንቆጥራቸው ወይም ልንመድባቸው አንችልም። የመንፈስ ቅዱስን አእምሮ የሚያውቀው እግዚአብሔር ቀን የሚነገረውን ነገር ያውቃል።  ካሪዝማቲክ ያልሆኑና በርካታ ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ይህን አቋም ውድቅ ያደርጋሉ። በመጽሐፍ ቅዱሳችን «ግሎሳ» የሚለው ቃል ትርጉም የማይሰጡ ድምጾችን በሚመስል ሁኔታ ፈጽሞ የላም ይላሉ። ሁልጊዜ በጥቅም ላይ የዋለው ሰብዓዊ ወይም መለኮታዊ ቋንቋን ለመግለጽ ነው። እነዚህ ልሳናት መተርጐም አለባቸው የሚለው እውነታ 1ኛ ቆሮ. 1) የሚተረጐም ቋንቋ መኖር እንዳለበት ያሳረጥልናል።  ይህን ሦስተኛውን አመለካከት የሚያንጸባርቁ ብዙዎች አዳዲስ ክርስቲያኖች ለብቻ ይወስዱና እንዴት በልሳናት መናገር እንዳለባቸው ያስተምራሉ። «ሃሌሉያ። የመሳሰለ ድምፅን ደጋግመው እንዲናገሩ በማድረግ የሚደጋግሙት ቃሎች እስኪደበላለቁ ድረስ እንዲቀጥሉ ያደርጋሉ። በዚያ መካከል በቅጽበት ትርጉም የማይሰጡ ቃሎች ያሉበት ድምፅ ከአፉ ውስጥ ይወጣል። በዚህ ጊዜ ለሰውዬው በመንፈስ ቅዱስ እንደተጠመቀና በልሳናት በዚህ ጊዜ ለሰውዬው በምንም እየተናገረ እንደሆነ ይነግሩታል። ብዙ ጊዜ ይህ በሚፈጸምበት ወቅት አእምሮ መጋበት ወቅት አእምሮ ሥራውን ያቆማል። አእምሮ እንዳይሠራ መዘውሩ ይቆለፍና ለማቅ (መንፈስ) የሚፈልገውን ሁሉ እንዲያደርግ ነህ ይሆናል።  ይህ ልምምድ በጰንጠቆለጤዎችና በካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ዘንድ በዓለም ዙሪያ ሁሉ የተለመደ ቢሆንም ልምምዱ ምንም ዓይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የለውም። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በየትም ስፍራ በልሳን እንዴት እንደሚጸልይ ሰው የተማረበት አንድም ማስረጃ የለም። በልሳናት የመናገር ስጦታ በቅጽበት የሚሰጥ ነው። ይህ ዛሬ ብዙዎች በላሳናት መናገር ነው ብለው የሚጠቅሱት ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ልሳን ነው ብሎ ከመደበው – ልምምድ ጋር አብሮ የሚሄድ ያለመሆኑን የሚያመለክት ነገር ነው።  መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነው ልሳን ካልሆነ ታዲያ ምንድ ነው? ይህ ለመመላስ አስቸጋሪ የሆነ ጥያቄ ሲሆን የተለያዩ ሰዎች ለጥያቄው የሚሰጧቸው መልሶች ይለያያሉ።  ሀ) ይህ ድምጽ በሙከራና በሥልጠና የተገኘ ከዚያም የመጣ የእንዴት ቃል ነው ብለው አንዳንዶች ያምናሉ።  ለ) ሌሎች ደግሞ እውነተኛ ልሳን ነው ይላሉ።  ሐ) ሌሎች ደግሞ በተላይ

በልሳናት ስለመናገር ተጨማሪ ጉዳዮች (ክፍል 2) የተለያዩ ዓይነት ልሳናት አሉን? Read More »

በልሳናት ስለመናገር ተጨማሪ ጉዳዮች (ክፍል 1)

ጥያቄ፡- ሀ) በቆሮንቶስ የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን ሁኔታ በዘመናችን ከሚገኙ አብዛኛዎቹ አብያተ ክርስቲያናት ጋር አወዳድር። እንዴት ይመሳሰላሉ? ለ) ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ከሰጣቸው ትምህርቶች የተማርካቸውን ጠቃሚ ነገሮች ጥቀስ።  አንድ ድርጊት የሚያስከትለው አጸፋዊ ምላሽ አለ። ይህ ከሳይንስ ሕጐች አንዱ ነው። ይህ ስለ ሰብዓዊ ተፈጥሮም የሚሠራ እውነት ነው። አንድ ሚዛናዊ ያልሆነ ድርጊት ወደ ሌላ ሚዛናዊ ያልሆነ ድርጊት የሚወስድ አጸፋዊ ምላሽ አለው። አንዲት ቤተ ክርስቲያን ከሚገባ በላይ ወግ አጥባቂነትን የምትከተልና መንፈሳዊ ኃይል የሚጐድላት ከሆነ በመጨረሻ የምታመራው የማይታይ ድንቃ ድንቅ ነገሮችን ወደሚያሳድድ ጭልጥ ያለ ስሜታዊነት ነው። ይህ ደግሞ በበኩሉ ወግ አጥባቂ ከሆኑ ቤተ ክርስቲያኖች የሚሰነዘር፥ ሌላ ብርቱ የተቃውሞ አጸፋዊ ምላሽን ያስከትላል። ይህ ዑደት እየቀጠለ በመሄድ ክርስቲያኖች እየተፋጩ አብያተ ክርስቲያናት ይከፋፈላሉ።  ይህን የድርጊቱን አጸፋዊ የድርጊት ዑደት በእውነት የሚሰብር ብቸኛው መንገድ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መመላለና ምን ማድረግ እንዳለብን እግዚአብሔርን መጠየቅ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ ያልተሰጡ ትምህርቶችን ሰዎች ላይ እንዳንጭን ቁርጥ አቋም ሊኖረን ይገባል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ ያልተከለከሉ ልምምዶችን እንዳያደርጉ ሰዎችን ከማሰናከልም መጠንቀቅ አለብን። እያንዳንዱ ሰው ስላ አቋሙ በእግዚአብሔር ፊት መልስ ይሰጣል። (2ኛ ቆሮ. 5፡10) ሌላው ክርስቲያን የእኛ ሳይሆን የሕያው እግዚአብሔር አገልጋይ ነው።  ስለ መንፈስ ቅዱስ ባደረግነው ጥናት የመንፈስ ቅዱስን አጠቃላይ አገልግሎት ስትኩረት ውስጥ ማስገባት እንዳለብን አበክረን ተናግረናል። በመንፈስ ቅዱስ አንድ አገልግሎት ላይ በምናተኩርበትና ያንን አገልግሎት እንደ መንፈስ ቅዱስ ሥራ በምንቆጥርበት ማንኛውም ጊዜ ሚዛናዊነትን እናጣለን። ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች በተለይ ደግሞ በልሳናት ስላመናገርና ስለ ትንቢት በዝርዝር በማጥናታችን የትኩረት አድማሳችንን የመዘንጋት አደጋ አለብን። መንፈስ ቅዱስ ከሚሰጣቸው በርካታ የተለያዩ አገልግሎቶች አንዱ ለእግዚአብሔር ልጆች መንፈሳዊ ስጦታዎችን መስጠቱ ነው። መንፈስ ቅዱስ ለክርስቲያኖች ከሚሰጣቸው በርካታ ስጦታዎች አንዱ በልሳናት መናገርን ነው። ስለዚህ በመንፈሳዊ ስጦታዎችና በልሳናት በመናገር ላይ ባተኮርን ቁጥር ሰፊውን ገጽታ እንዳንዘነጋ መጠንቀቅ አለብን።  በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን እንደነበረው በዚህ ዘመን በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ስለ ትንቢት፥ በልሳናት ስለ መናገርና ስለ ፈውስ መንፈሳዊ ጦታዎች በርካታ ግራ የሚያጋቡ ውዥንብሮች አሉ። እነዚህ ውዥንብሮች ቤተ ክርስቲያንን እየከፋፈሉና የኢየሱስን ስም እያሰደቡ ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እነዚህ ስጦታዎች የሚናገረው ምንድን ነው ብለን መጠየቅ አለብን።  ዛሬ በልሳናት የመናገር መንፈሳዊ ስጦታ ላይ አተኩረናል። በሚቀጥለው ሳምንት የትንቢት የፈውስና ተአምራትን የማድረግ ስጦታዎችን እንመለከታለን። ለእነዚህ ትምህርቶች በየትኞቹም ጉዳዮች ለመረዳት የማያሻሙ መንገዶችን የሚያሳዩ ወሳኝ መልሶችን አላቀርብም። ይልቁኑ . ጥያቄዎችን በማንሣት ልዩነት የሚታይባቸው ትምህርቶች በተንሰራፉበት በዚህ ዘመን ልናስታውሳቸው የሚገቡ ጉዳዮችን እጠቁማለሁ። ከሁሉ በላይ የሚያስፈልገው ነገር መልሱ አለኝ ብሎ ማሰብ አለመሆኑን አስታውስ። እግዚአብሔርን የሚፈሩ ክርስቲያኖች በጉዳዮች ለረጅም ጊዜ ስለተከራከሩ ብቸኛው መልስ ያላው እኛጋ አለመሆኑን በቅንነት መቀበል አለብን። ሆኖም ግን እራሳችንን ከሁለቱም የከረረ አመለካከቶች መጠበቅ አለብን። በልሳናት መናገር ሁልጊዜ ከአጋንንት ነው የሚለው የከረሩ አመለካክት አደገኛ ነው። አዎን ሰይጣን በልሳናት መናገርን መክፋፈልን ለማምጣት አንዳንዶችንም ከቀንበሩ ሥር ለማድረግ ሊጠቀምበት ይችላል። ይህ ማለት ግን ልሳናት ሁሉ ከሰይጣን ናቸው ማለት አይደለም። በልሳናት መናገር ከሁሉ የላቀ ስጦታና ለመንፈስ ቅዱስ ህልውና ማስረጃ ነው የሚለው ሌላው ጽንፍም እንደ መጀመሪያው አደገኛ ነው። በሁለቱ ጽንፎች መካከል በነህነት ለመለማመድ ሰፊ ዕድል አለ። በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ልዩነቶች ፍቅርና መቻቻል ሊሠለጥኑባቸው ይገባል። ከእኛ የተለየ አመለካከት ያላቸውን ክርስቲያኖች ለንቃወም ክጠላታችን ክለይጣን ጋር ወግነን እንዳንገኝ መጠንቀቅ አለብን። እርስ በርስ እንደ ጠላት መተያየት የአንድ አገር አየር ኃይል ከጠላት ጋር በሚዋጋበት ጦርነት የራሱን ወገን ሠራዊት እንደ ጠላት የመቁጠሩን ያህል የከሩ ነው።  የተለያዩ ቡድኖች አንዱ በሌላው አቋም ላይ ያለው ዋንኛው ሥጋት ምንድን ነው?  ነገሮች፥ ከሚገባ በላይ በሆነ መንገድ ወይም ሚዛን ባጣ ሁኔታ ሊፈጸሙ ሰዎች አምርረው ይቃወማሉ። ለምሳሌ አብዛኛዎቹ መድኃኒቶች በበቂ መጠን ካልተወሰዱ የሚሰጡት ውጤት መናኛ ስለሚሆን ወሳጆቹ በሽታቸው ብዙ ሳይቆይ ይመለስባቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ከሚፈለገው መጠን በላይ ከተወሰዱ መርዛማነታቸው አይሎ እስከ መግደል ይደርሳሉ። ስለዚህ መድኃኒት የሚፈለገውን ውጤት ያስገኝ ዘንድ መጠኑ ተላከተ በትክክለኛው ጊዜ ለተፈቀደ የጊዜ ርዝመት ብቻ መወሰድ አለበት። መድኃኒትን በመጠኑ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ መውሰድ ምንም መድኃኒት ካለመውሰድ የበለጠ አደገኛ ነው። የሚጠበቀው ውጤት ሳይጨበጥ ሲቀር መድኃኒቱን አሳንሶ ለመውሰድም ሆነ አብዝቶ ለመውሰድ የሞከረው የሚኖራቸው አጸፋዊ ምላሽ አንድ ዓይነት ነው። በትክክለኛው መጠን በመውሰድ ፈውስ ሊያመጣላቸው ይችል የነበረውን መድኃኒት ይጠራጠራሉ።  በሚዛናዊነት እጦት የሚከሰተው ተመሳሳይ አጸፋዊ ድርጊት ካሪዝማቲክ የሆኑትንም ሆነ ያልሆኑትን እኩል ይጐዳል። የካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች የአንዳንድ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ትክክለኛነት የማይቀበሉ ወግ አጥባቂ ክርስቲያኖችን አምልኮና ሕይወት እንደዚሁም የአንዳንዶቻቸውን ዝቅተኛ ሕይወትና ኃይል ይመለከታሉ። በዚህ መንገድ አምልኮአቸውን የሚያካሄዱትን ሁሉ ሕይወትና ኃይል አልባ አድርገው ይቆጥሩአቸዋል። ካሪዝማቲክ ያልሆኑትና ከመንፈሳዊ ስጦታዎች አንዳንዶችን የሚጠራጠሩ ሁሉ የእግዚአብሔርን ሥራ እንደሚገድቡና የመንፈስ ቅዱስን ሥራ እንደሚያፍኑ ያስባሉ። በልሳናት መናገርና ትንቢት ምን ስሕተት አለው? ብለው ይጠይቃሉ። እግዚአብሔር በሚፈልገው መንገድ ከሰዎች ጋር ኅብረት ማድረግ አይችልምን? ይላሉ። ቅድመ-ግምታችን እግዚአብሔር በአንድ የተወሰነ መንገድ አይሠራም ወደሚል እምነት የሚመራን ከሆነ በሕይወታችን ባሉ የተወሰኑ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ እግዚአብሔር እንዳይመራን ራሳችንን እያራቅንና ከሚያንጹን ነገሮችም እየተገላልን ነው ማለት ነው። በአምልኮአችን ወቅት የእግዚአብሔርን ህልውና ማወቅ ይሳነናል ደግሞም መንፈስ በሕይወታችን ሊሠራ ያለውን በማጥፋት ሙት በሆነ አክራሪነት ውስጥ እንዘፈቃለን። ስለዚህ መንፈሳዊ መሆናችንን ለማሳየት፥ እራሳችንንም ከመንፈሳዊ ሙትነት ለመከላከል ሰዎች ሁሉ በልሳን እንዲናገሩ፥ በአምልኮ ጊዜ እጆቻቸውን ወደ ላይ በማንሣት እንዲያመልኩ፥ ሃሌሉያ እያሉ እንዲጮችና በመሰብሰቢያው መተላለፊያ መንገዶች ወድቀው በኃይለኛ ሳቅ እንዲንፈራፈሩ እንጠብቃለን። ሙት አምልኮን የመቋቋም ዝንባሌ ካሪዝማቲኮችን ቤተ ክርስቲያንን ወደ ሚከፋፈሉና የእግዚአብሔርን ክብር ወደሚያርቁት አክራሪ ልምምዶች ብዙ ጊዜ ይገፋፋቸዋል።  ካሪዝማቲክ ያልሆኑትም ካሪዝማቲኮች በሚያሳዩት ሚዛን አጥነት ላይ አጸፋዊ ምላሽ ይሰነዝራሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰዎች ወድቀው ሲንፈራፈሩና እንደ ውሾች ሲያባርቁ የምናየው በየትኛው ቦታ ነው? ይላሉ። እንደዚህ ዓይነቱን ልምምድ በቴሊቪዥን ሲመለከቱ ካሪዝማቲኮች በሙሉ እንደዚህ ናቸው ብለው ያስባሉ። ካሪዝማቲክ ያልሆኑ ክርስቲያኖችን የሚያሳስባቸው ነገር ለልሳናትና ትንቢት ስጦታዎች ባለው ከፍተኛ ጉጉት በእነዚህ ስጦታዎች በኩል የሚመጣው የእግዚአብሔር መልእክት ከመደበኛው የእግዚአብሔር ቃል ጋር እኩል ተደርጐ ወደ መቆጠር ያመራል የሚል ነው። ከእግዚአብሔር ቃል ጋር እኩል ከሆኑ ደግሞ እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሚሰጣው ተጨማሪ መገለጥ እንደቀጠለ ነው ማለት ነው። ይህ ማለት መጽሐፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር በተሰጠን መገለጥነቱ በቂ አይደለም ማለት ነውን? ለሕይወትና ለተቀዴሰ ኑሮ የሚበቃ ነገር እግዚአብሔር አልሰጠንምን? (2ኛ ጴጥ. 1፡3) መጽሐፍ ቅዱስ በቂ ከሆነ ተጨማሪ መገለጥን ከእግዚአብሔር ለምን እንፈልጋለን? ሰዎች ከእግዚአብሔር መገለጥ እንዳገኙ ሲናገሩ የሚናገሩትን ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እኩል ማድረጋቸው አይደለምን? «የእግዚአብሔር መንፈስ እንዲህ ይላል» በማለት ካሪዝማቲኮች መልእክት ሲያመጡ ይህንን ማለታቸው አይደለምን? የሚያመጡት ቃል በእርግጥ የእግዚአብሔር ቃል ከሆነ እንዳንጽፈውና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እኩል እንዳናደርገው የሚያግደን ምንድን ነው? ይህ ከሆነ ደግሞ የአንዳንድ መናፍቃንን ስሕተት መድገም አይሆንምን? የእዚህን መገለጦች ትክክለኛነት የምናረጋግጠው እንዴት ነው? በሰዎች ስሜታዊ ቁጥጥር ሥር እንዳንወድቅ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ማተኮር ብቻ አይሳላንም? ሰመጽሐፍ ቅዱስ መላኪያዎች ለመኖር በመወሰንና ትክክለኛ የመሠረታዊ እምነት ትምህርትን በመያዝ ከስሕተት ትምህርቶች ተጠብቆ ጤናማ መሆን የተሻለ አይደለምን?  ጥያቄ፡– ሀ) እነዚህ ሁሉ ሥጋቶች ዋጋ ያላቸው የሚሆኑት በምን በምን መንገድ ነው? ለ) እነዚህ ሁለቱ ሥጋቶች የካሪዝማቲኮች ሆኑ ካሪዝማቲክ ያልሆኑት እምነት ከመሆን ይልቅ በጉዳዮቹ ላይ ከሚገባ በላይ ከሚሰነዘር አጸፋዊ ምላሽ የመነጩ የሚሆኑት በምን መንገድ ነው?  በልሳናት ስለመናገር ክርስቲያኖች ያሏቸው የተለያዩ አቋሞች ምንድን ናቸው?  እስካሁን ድረስ በጥናታችን የተመለከትነው መጽሐፍ ቅዱስ በልሳናት ስለመናገርና ስለ ትንቢት ምን እንደሚያስተምር ነው። ሆኖም ግን፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሻሚ ነገሮች አሉ። እንደ እብዛኛዎቹ ነገሮች በልሳናት በመናገር ላይም በርካታ የተለያዩ አመላካክቶች አሉ። ነገር ግን በመሠረቱ

በልሳናት ስለመናገር ተጨማሪ ጉዳዮች (ክፍል 1) Read More »

መንፈሳዊ ስጦታዎችና የማያምኑ ሰዎች (1ኛ ቆሮንቶስ 14፡20-40)

ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮ. 14፡20-40 አንብብ። ሀ) ጳውሎስ በአምልኮ ስብሰባዎች ላይ በልሳናት ስለመናገርና ትንቢት ስለመናገር የሰጣቸውን የተለያዩ መመሪያዎችን ዝርዝር። ለ) የአምልኮ ስብሰባዎችን «ሥርዓት ያላቸው» ያደርጋሉ ብለህ የምታምንባቸውን አንዳንድ ነገሮች ጥቀስ።  ጳውሎስ በልሳናት መናገር በተቀዳሚ ለአምልኮ ስብሰባዎች የተሰጠ ስጦታ እንዳልሆነ መግለጹን ይቀጥላል። የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በልሳናት በመናገር ላይ ባላቸው አቋም እንደ ልጅ ያደርጋቸው ነበር። ሌሎችን ከማነጽ ይልቅ በራስ ወዳድነት የራሳቸውን ክብር የሚያሳድዱ ነበሩ። የልሳን አጠቃቀማቸው መንፈሳዊ መሆናቸውን ሳይሆን ጨቅላነታቸውን ነበር የሚያሳየው። ሰለዚህ በልሳናት መናገር ላይ ከሚገባው በላይ ማተኮር በክርስቲያኑ ሕይወት መብሰልን ሳይሆን ጨቅላነትን ወደሚያመለክት ሚዛን አልባነት ያደርሳል።  የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በልሳናት መናገር ተግባር ላይ የነበራቸውን አመላካከት መለወጥ ነበረባቸው። የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ልጆች የመሆናቸው ዋነኛው ማረጋገጫ በልሳናት መናገር እንደሆነ ያስተምሩ ነበር። እንዲያውም መንፈሳዊ የመሆናቸው ዋነኛው ማረጋገጫ ይኸው እንደሆነ ይናገሩ ነበር። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ በልሳናት የመናገር ዓላማ ይህ እንደሆነ ነው የሚያስተምረው? የሚያምኑ ሰዎችን በተመለከተ በልሳናት መናገርና ትንቢት የሚዛመዱት እንዴት ነው? በዚህ ክፍል ውስጥ በልሳናት ስለመናገር ሁለት እውነቶችን እንመለከታለን።  በመጀመሪያ፥ በልሳናት መናገር እግዚአብሔርን በማያምኑ ላይ ስለሚያመጣው ፍርድ ምልክት ነው። ጳውሎስ በልሳናት በመናገርና በትንቢት መካከል ያደረገውን ንጽጽር ለማስተዋወቅ በብሉይ ኪዳን ወደሚገኘው ኢሳ. 28፡9-13 ይመለሳል። (ክፍሉን አንብበው።) ኢሳይያስ የሚተነብየው እስራኤልና ይሁዳ እንደሚማረኩ ነበር። ከይሁዳ ምድር እንደሚሄዱ ነበር። እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ አሶርና ባቢሎን ባሉ የአሕዛብ መንግሥታት እጅ አሳልፎ በመስጠትና ወደ አገራቸው እንዲያግዟቸው በማድረግ በሄዱበት ምድር የማያውቁትን ሕዝብ ልሳናት (የማይታወቁ ቋንቋዎች) እንዲሰሙ አስገደዳቸው። የሌሎችን ልሳናት መስማት ችሮታ ከመሆን ይልቅ በቅጣት መልክ የምርኮአቸው ውጤት ሆኖ እንመለከታለን። ስለዚህ ለእስራኤላውያን የማይታወቁ ቋንቋዎች መስማት የበረከት ሳይሆን የፍርድ ምልክት ነበር። ልባቸውን የነካ አልነበረምና እስራኤላውያን ልሳናት በመስማት እግዚአብሔርን መታዘዝ አልተማሩም። የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በልሳናት መናገር የእግዚአብሔር በረከት ምልክት እንደሆነ ያስቡ ነበር። ሆኖም ግን በልሳናት መናገር ለአማኞች ምልክት ሳይሆን ለማያምኑ ሰዎች ምልክት ነበር። ግን ምን ዓይነት ምልክት ነበር? በብሉይ ኪዳን «ምልክት» የሚለው ቃል አዎንታዊና ለምሳሌ ቀስተ ደመና (ዘፍ 9፡12) አሉታዊ ለምሳሌ (ዘኁ. 26፡10) በሆኑ መንገዶች ይታወቅ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ «ምልክት» የሚለውን ቃል ሲጠቀም እግዚአብሔር በአንድ ጉዳይ ላይ ስላለው አመላካከት ነበር። ይህ የሚገልጸው ደስታውን ወይም ቁጣውን ሊሆን ይችላል። የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በልሳናት መናገር እግዚአብሔር በመካከላቸው ስለመኖሩ ለማያምኑ ሰዎች ምልክት እንደሆነ ያስቡ ነበር። ነገር ግን ያልተተረጐመ ልሳን አሉታዊ ምልክት መሆኑን አልተገነዘቡም ነበር። በብሉይ ኪዳን ዘመን ልሳናት እግዚአብሔር ፍርድን ለማምጣት መወሰኑን የሚያመለክቱ ነበር። ስለዚህ ያልተተረጐሙ ልሳኖችን በቤተ ክርስቲያን መናገር ወደ ጉባኤው ለሚመጡና መልእክቱ ለማይገባቸው የማያምኑ ሰዎች የፍርድ ምልክት ነው። የእግዚአብሔርን እጅ አይተው ንስሐ ስለማይገቡ በፍርድ ሥር ይኖራሉ። (የእግዚአብሔር ሕዝብ አካል ይሆኑ ዘንድ ክርስቶስን እንደ መሢሑ ባለመቀበላቸውና በክርስቶስ ላይ እምነት ባለማድረጋቸው ለአይሁድ ልዩ የፍርድ ምልክት ነበር።) ያልተተረጐሙ ልሳኖች የፍርድ መልእክትን የሚያውጁ ስለሆነ ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን ወደሚገኝ የሚያድን እምነት ሊደርሱ አይችሉም ነበር።  ሁለተኛ ፥ በልሳናት መናገር ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጡ የማያምኑ ሰዎች ለሚሰሙት የወንጌል መልእክት መሰናክል ነበር። የማያምኑ ሰዎች ክርስቲያኖች በልሳን ሲናገሩ በሚሰሙበት ጊዜ እግዚአብሔር እንደሚናገር ከመገመት ይልቅ ተናጋሪዎቹ ያበዱ ወይም እጋንንት ያደረባቸው ይመስላቸው ነበር። ስለዚህ በመካከላቸው የእግዚአብሔር ኃይል እንዳለ ምስክር ከመሆን ይልቅ ለወንጌል ዕንቅፋት የሚሆን ነበር።  የትንቢት ስጦታ ግን ለሚያምኑም ሆነ ለማያምኑ በረከት ነበር። የእግዚአብሔር ፍርድ አሉታዊ ምልክት ከመሆን ይልቅ የእግዚአብሔር ህልውና አዎንታዊ ምልክት ነበር። አንድ ሰው ከእግዚአብሔር መልእክት ሲቀበልና ለአማኞች ጉባኤ በግልጽና በሚገባቸው ቋንቋ ሲያስተላልፈው እግዚአብሔር ጉባኤውን እንደተቀበለው የሚያሳይ ምልክት ይሆናል። እግዚአብሔር በመካከላቸው የመሆኑ፥ ችሮታው በእነርሱ ላይ የመሆኑና ፈቃዱን እየገለጠላቸው የመሆኑ ምልክት ነው። ወደዚህ ጉባኤ የማያምን ሰው ቢመጣና በኅብረት አምልኳቸው ትንቢት ሲነገር ቢሰማ እንዳበዱ ወይም አጋንንት እንዳደረባቸው ከማሰብ ይልቅ እግዚአብሔር በመካከላቸው መኖሩን ያውቃል። እንዲያውም በትንቢት በሚመጣው ቃል በሰውየው ሕይወት ውስጥ ያሉ የተደበቁ ነገሮች ሊገለጡና ወንጌልን ሰምቶ የማመን ዕድል ሊያገኝ ይችላል። ስለዚህ ሳይተረጐም የሚነገር ልሳን ለወንጌል ዕንቅፋት ሊሆን የሚችል ሲሆን ትንቢት ግን የወንጌል መሣሪያ ነው። ስለዚህ የቆርንቶስ ሰዎች የትንቢት ስጦታ በልሳናት ከመናገር የበለጠ አስፈላጊ እንደሆነ መረዳት ነበረባቸው። ይህም የማይተረጐሙ ልሳናትን በጉባኤ መካከል እንዳይነገሩ ለመቆጣጠር እንዲችሉ የሚረዳቸው ነበር።  የዚህን ክፍል ዝርዝር አሳብ መረዳት አስቸጋሪ ቢሆንም የጳውሎስ አጠቃላይ ትምህርት ግን ግልጽ ነው። በልሳናት መናገር ለማያምኑ ሰዎች የፍርድ ምልክት በመሆኑ በጉባኤ መካከል በልሳናት ሲነገር ቢሰሙ ክርስቲያኖች «አብደዋል» በማለት ወደ እምነት ከመምጣት ይልቅ ይሰናከላሉ። በሌላ በኩል ግን ትንቢት ለአማኞች ምልክት ከመሆኑም ባሻገር የማያምኑ ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ለመምራት ትልቅ መሣሪያ ነው። ስለዚህ በአምልኮ ስብሰባ ወቅት በልሳናት በመናገር ላይ ከማተኮር ይልቅ ግልጽ የእግዚአብሔር ፈቃድ ማስተላለፊያ መንገድ በሆነው በትንቢት ላይ ማተኮር ነበረባቸው።  ጥያቄ፡- ሀ) ይህን ትምህርት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በልሳናት መናገርና ትንቢት ያላቸውን ሚና ከሚያውቁ ሰዎች ቁጥር ጋር አወዳድር። ተመሳሳይ የሆነው ወይም የሚለየው እንዴት ነው? ለ) አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት በእነዚህ ጥቅሶች የተሰጡትን ትምህርቶች የበለጠ ትክክለኛ በሆነ መንገድ ያንጸባርቁ ዘንድ መለወጥ ያለባቸው እንዴት ነው?  1ኛ ቆሮንቶስ 14፡26-36 በአምልኮ ስብሰባዎች ወቅት የሥነ ሥርዓት አስፈላጊነት  ጳውሎስ በኅብረት አምልኮ ወቅት አማኞችን በሙሉ የማያንጸው በልሳናት መናገር የትንቢትን ያህል አስፈላጊ እንዳልሆነ ከተናገረ በኋላ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በልሳናት መናገርና መተንበይ እንዴት መከናወን እንዳለባቸው መመሪያዎችን ወደ መስጠት ይዞራል። በኅብረት አምልኮ ምን መደረግ እንዳለበት ግልጽና የማያሻሙ ደንቦችን ይሰጣል።  በኅብረት አምልኮ ወቅት መደረግ ስላለባቸው ነገሮች ምሪት የሚሰጡ ሁለት መሠረታዊ መርሆዎች በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ይገኛሉ። በመጀመሪያ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ የሚደረጉ ማናቸውም ነገሮች ሁሉም በሚረዱበትና እምነታቸውን በሚያንጹበት መንገድ መሆን አለባቸው። ስለዚህ ማንኛውም ልሳን ሰዎች የተነገረውን ነገር ለመረዳት ይችሉ ዘንድ መተርጐም አላበት። ሁለተኛ አምልኮ በሥርዓት፥ በሰላምና በሚስማማን መንገድ መካሄድ አለበት። ሰዎች ሁሉ በአንድ ጊዜ በመናገራቸው ወይም በክርስቲያኖች መካከል በሚደረግ አምባጓሮ ግራ መጋባትና ውዥንብር መፈጠር የለበትም።  ጥያቄ፡- ሀ) ከዚህ ቀደም ተካፍላኽው የምታውቀው ሥርዓተ አልበኝነት የተጸናወተውና ስርአት የጠፋበትን የአምልኮ ስብሰባ አስብ። እግዚአብሔርን በሙሉ ልብህ እንዳታመልክ የተከላከለና ሁከትን የፈጠረ ምን ነገር ተፈጸመ? ለ) አንድ የአምልኮ ስብሰባ ሥርዓት ያለው ወይም የሌለው፥ ተገቢ የሆነ አምልኮ የሚታይበት ወይም ተገቢ ያልሆኑ አዋኪ ድምጾች ያለበት እንዲሆን የሚያደርጉትን ነገሮች ዝርዝር፡፡  ጳውሎስ የሰጠውን የተለያዩ ትእዛዛት ለመረዳት የሰጠውን መመሪያዎች አንድ በአንድ በመጥቀስ ማብራሪያ እንሰጥባቸዋለን።  1. በኅብረት አምልኮዎች ሰዎች ለራሳቸው እንዴት እንደሚባረኩ ከማሰብ አልፈው ለሌሎች የሚገዳቸው መሆን ይገባቸዋል። የኅብረት አምልኮ እግዚአብሔርን ለማክበር ከመፈለግ ባሻገር እያንዳንዱ በቤተ ክርስቲያን ያለ ሰው በሚታነጽበት መንገድ የሚፈጸም መሆን አለበት (1ኛ ቆሮ. 14፡26)።  በቆርንቶስ ቤተ ክርስቲያን የነበረው ችግር ብዙ ሰዎች በአንድ ጊዜ በልሳናት በመናገራቸው ከፍተኛ ግራ መጋባት ተፈጥሮ ክርስቲያኖች ሁሉ ወደ በረከት ከመምራት ይልቅ አንዳንድ አማኞች ይረበሹ እንደነበር ነው። ይህ እውነት በሕይወታችን በተለያዩ መንገዶች ተግባራዊ ይሆናል።  ሀ. የተለያዩ ስብዕናዎችና የአምልኮ ዘይቤዎች ያሏቸው ክርስቲያኖች እርስ በርስ በአምልኳቸው በጋራ እንዲባረኩ መሥራት አለባቸው። በልሳናት መናገርንና የተፈታ ነፃነት ያለበትን የአምልኮ ዘይቤ የማይወዱ ሰዎች አገልግሎት በሕግና ሥርዓት ጠፍንገው አምልኳቸው ሕይወት ያለው እንዲሆን የሚፈልጉትን ሰዎች ነፃነት እንዳይጋፉ መጠንቀቅ አለባቸው። በአምልኳቸው በጌታ መደሰታቸውን ለመግለጥ የሚፈልጉ ሰዎችን መሸክም መቻል አለባቸው። ስሜታዊ ደስታ የሞላበትን አምልኮዎችን ሁኔታዎች የሚወዱ ክርስቲያኖችም ጸጥታና ዝግ ያለ መንፈስ ያለበትን አምልኮ የሚወዱ ሰዎችን ስሜት መጠበቅ አለባቸው። ስለዚህ በከፍተኛ ድምጽ ሃሌሉያና እልል፥ ወዘተ… በማለት በሙላት ፍላጐታቸውን በማሰብ ለመግለጽ ከመሞከር ይልቅ ጸጥተኛ የሆነ አምልኮን የሚወዱ እንዳይርቁ በመገንዘብ ከነፃነቶቻቸው አንዳንዶቹን መሥዋዕት ማድረግ አለባቸው። ሁላችንም አንድ አካል ስለሆንን ተቀዳሚ ትኩረታችን ሁላችንንም በሚያንጽ መንገድ እግዚአብሔርን እናመልክ ዘንድ አንዳችን ሌላችንን

መንፈሳዊ ስጦታዎችና የማያምኑ ሰዎች (1ኛ ቆሮንቶስ 14፡20-40) Read More »

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 14፡1-19)

ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር በአንድ ክፍል ውስጥ ስብሰባ እያደረግህ ነው። የተሰበሰባችሁበት ዓላማ በመዝሙር እግዚአብሔርን ለማምለክና ለተወሰነ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ ልታመሰግኑትና ደግሞም በሕይወታችሁ ይሠራ ዘንድ ልትጠይቁት ነው። በመጀመሪያ አንድ ሰው፣ ከዚያም ሁለት ሰዎች፣ በመቀጠልም ሶስት ሰዎች፣ በመጨረሻም በክፍሉ ውስጥ ያሉት ሰዎች ሁሉ በልሳናት መናገር ይጀምራሉ። የስብሰባው መሪ አንተ ነህ። በዚህ ጊዜ ምን ልታደርግ ትችላለህ? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በተለይ ደግሞ በልሳናት መናገርን በተመለከተ ሕዝብ በተሰበሰበት የአምልኮ ስብሰባ ላይ እንዴት አገልግሎት ላይ መዋል እንዳለባቸው የሚናገር መመሪያ አለን?  ጥያቄ፡- ሀ) የስብሰባው መሪ በሆንክበት ከላይ የተገለጸው ሁኔታ ቢፈጸም ምን ታደርጋለህ? ለ) እንዲህ ዓይነቱን ስብሰባ ማካሄድ የቤተ ክርስቲያን ሰብሰባን ከማካሄድ የሚለይበት መንገድ አለን? ሐ) መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ትክክለኛው አምልኮተ እግዚአብሔር ምን ይመስልሃል?  በ1ኛ ቆሮ. 12-13 የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በልሳናት የመናገርን ስጦታ ያለአግባብ ስለተጠቀሙባቸው አንዳንድ ሁኔታዎች ጳውሎስ ይናገራል? በ1ኛ ቆሮ. 12 ላይ በልሳናት መናገር ከመንፈሳዊ ስጦታዎች አንዱ ብቻ እንደሆነና ይህንንም መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንን ለመገንባት ለቤተ ክርስቲያን እንደሰጠ አበክሮ ይናገራል። ስለዚህ ክርስቲያኖች በልሳናት የመናገር የተናጠል ትኩረታቸውን መንፈሳዊ ስጦታዎችን በሙላት መጠቀምን በማበርታትና በመጨመር ሚዛናዊ ማድረግ አለባቸው። መንፈሳዊ ስጦታዎች በሙሉ ድንቀኛ የሆኑትና ልዕለ-ተፈጥሮአዊነታቸው ምንም የማያሻማው በአንድ ወገን፥ ዘልማዳዊና ልዕለ-ተፈጥሮአዊ ኃይል በቀላሉ የማይታይባቸው በሌላ ወገን ሆነው በአንድነት መንፈስ ቅዱስ በመካከላቸው የመኖሩ ማረጋገጫ ናቸው። የትኛውም ስጦታ ከየትኛውም ተለይቶ መታየት የለበትም። ደግሞም የትኛውም ስጦታ ግንዛቤ ውስጥ ሊገባ እስከማይችል ድረስ ችላ መባል የለበትም።  በ1ኛ ቆሮ. 13 ላይ ጳውሎስ የመንፈሳዊ ስጦታዎች መሠረት መሆን ስላለበት ትክክለኛ ዝንባሌ ትኩረት ይሰጣል። በእውነት መንፈሳዊ መሆን ትፈልጋለህ? መልሱ መንፈሳዊ ስጦታዎችን መጠቀም ላይ አያርፍም። ይልቁኑ መልሱ ያለው እውነተኛ በሆነና ራሱን በሚሠዋ ፍቅር ላይ ነው። መንፈሳዊ ስጦታዎች በፍቅር እስካልተደረጉ ድረስ ምንም ያህል ድንቀኛ ቢሆኑም እንኳ ለቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለግለሰቡ የማይጠቅሙ እንዲያውም ጐጂ ናቸው። የዘላለም ጌታ ከተመለሰ በኋላ እንኳ ቢሆን የሚኖር ፍቅር እንጂ መንፈሳዊ ስጦታዎች አይደሉም። ቀጥሎ በ1ኛ ቆሮ. 14 ላይ ጳውሎስ በተለይ በልሳናት የመናገር ስጦታን ያለአግባብ ስለመጠቀም አጥብቆ መናገር ይጀምራል። ጳውሎስ የሚናገረው በግል የአምልኮ ጊዜ አለመጠቀም ሳይሆን በሕዝባዊ የአምልኮ ስብሰባ ላይ ስለመጠቀም ነው። ጳውሎስ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች የአምልኮ ስብሰባ በሚመሩበት ጊዜ ሊረዱአቸው የሚገቡ ሁለት ዋነኛ መርሆዎችን ይሰጣቸዋል።  በመጀመሪያ፥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚደረጉ ነገሮች ግልጽ የሆኑና ሕዝቡ የሚረዳቸው መሆን አለባቸው (1ኛ ቆሮ. 14፡1-5)። መንፈሳዊ ስጦታዎች ለሁሉም የጋራ ጥቅም ሲውሉ፥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ሰዎች በሙሉ ሰምተው ሲረዱና እራሳቸውን ሲያንጹ ብቻ እውነተኛ ፋይዳ ይኖራቸዋል። ስለዚህ ክርስቲያኖች መልእክቱ በሚመጣበት ወቅት ሰዎች ሊረዱት እንዲችሉት በትንቢት ስጦታ ላይ እንጂ ትርጉሙ በማይታወቀው በልሳናት መናገር ላይ ማተኮር የለባቸውም። ትንቢቶች ግልጽ የሚነገሩ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የሚመጡ መልእክቶች ናቸው። ክርስቲያኖችም ሆኑ ክርስቲያን ያልሆኑ ሰዎች ይረዷቸዋል። ስለዚህ በቤተ ክርስቲያን አገልሎት ውስጥ ዋጋ አላቸው። በልሳናት መናገር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተከለከለ ባይሆንም እንኳ ቁጥጥር ሊደረግበት ግን ይገባል። መንፈሳዊ ስጦታ ስለሆነ ስሕተት አይደለም። ሆኖም ግን በሕዝብ የአምልኮ ስብሰባ ላይ የሚሰጠው ጥቅም የተወሰነ ነው። በሕዝብ የአምልኮ ስብሰባ ላይ በልሳናት መናገር ካስፈለገ የሚናገሩት ጥቂት ሰዎች ሆነው ልሳኑ መተርጐም አለበት። የማይተረጐም ልሳን ለሕዝቡ የሚሰጠው ጥቅም ስለሌላ በሕዝብ የአምልኮ ስብሰባ ላይ ዋጋ ቢስ ነው።  ሁለተኛ፣ የአምልኮ ስብሰባ ሥርዓት ያለበት እንጂ የውዥንብርና የግራ መጋባት ስብሰባ መሆን የለበትም (1ኛ ቆሮ. 14፡26-40)። የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ለአምልኮ በሚሰበሰቡበት ጊዜ ሁሉም ሰው በአንድ ላይ መናገር ይፈልግ ነበር። ሁሉም በአንድነት በልሳን ይናገሩ ነበር። እጅግ ግራ የሚያጋባ ሁኔታ ነበር። በዚህ ምክንያት እግዚአብሔርን ለማምለክ አስቸጋሪ ሁኔታ ከመፈጠሩም በላይ ወደ ስብሰባቸው ተጋብዘው ለሚመጡ የማያምኑ ሰዎች መሰናክል በመሆን ለወንጌል መስፋፋት እንቅፋት ነበር። ጳውሎስ የሚናገረው አምልኮ ሥርዓት ያለው፥ ለእግዚአብሔር ክብርን የሚያመጣና የሚያምኑ ሰዎችንም የሚስብ መሆን አለበት። የልሳናት ንግግሮችም በሙሉ በሥርዓት እንዲደረጉ መቆጣጠር የመሪዎች ኃላፊነት ነው።  ጥያቄ፡- ሀ) እነዚህ ሁለት መርሆዎች በጣም ጠቃሚ የሆኑት ለምን?። ለ) በአምልኮአቸው መንፈሳዊ መስለው ለመታየት ሲሉ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት እነዚህን ሁለት መመሪያዎች የሚተላለፉት እንዴት ነው? ሐ) በዚህ ምዕራፍ በመጀመሪያው አንቀጽ የተገለጸው ሁኔታ ሲኖር የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ምን ማድረግ አለባቸው? እዚህ ሁለት መርሆዎችስ የሚጠቅሙት እንዴት ነው?  ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮ. 14፡1-19 አንብብ። ሀ) ጳውሎስ ትንቢት በልሳናት ከመናገር ይሻላል ያለው ለምንድን ነው? ለ) በልሳናት መናገርንና ትንቢት መናገርን አወዳድር። የእያንዳንዳቸው ዓላማ ምንድን ነው? ሐ) በግልጽ ለመረዳት የሚቻሉ ንግግሮች በሕዝቡ አምልኮ ጊዜ በልሳናት ከመናገር ይልቅ የተሻሉ የሚሆኑት ለምንድን ነው? መ) ጳውሎስ ክርስቲያኖች የበለጠ እንዲጠቀሙ የሚያበረታታቸው መንፈሳዊ ስጦታዎች ምን አይነት ናቸው? (ቁጥር 2) ሠ) በልሳናት የሚናገር ሰው የሚጸልየው ምን መሆን አለበት? ለምን?  1ኛ ቆሮ. 14ን በምናጠናበት ጊዜ ጳውሎስ የሚናገረው ምን እንደሆነ መረዳት እጅግ አስፈላጊ ነው። ካሪዝማቲክ የሆኑትም ሆኑ ያልሆኑ ክርስቲያኖች የጳውሎስ ትምህርት እርሱ ሊለው ከሚፈልገው ውጭ መረዳት የለባቸውም። 1ኛ ቆሮ. 14ን ማጥናት ከመጀመራችን በፊት የሚከተሉትን ነገሮች መረዳት አለብን።  1. ጳውሎስ ክርስቲያን በገዛ ቤቱ ስለሚያደርገው የግል አምልኮ መናገሩ እይደለም። ይልቁኑ ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን በአንድነት ለማምለክ በሚፈልጉበትና በሚሰበሰቡበት ጊዜ በሚሆነው ላይ ነው የሚያተኩረው። አዲስ ኪዳን በልሳናት መናገር በግል የአምልኮ ጊዜ ስለሚኖረው ድርሻ በግልጽ አይናገርም።  2. ጳውሎስ በልሳናት መናገር ከመንፈሳዊ ስጦታዎች ሁሉ ያነሰና መተው ያለበት ነው አላለም። ይልቁኑ ሁለቱን ስጦታዎች ማለትም በልሳናት መናገርና ትንቢት በሕዝቡ የአምልኮ ስብሰባ ላይ ያላቸውን ጥቅም ብቻ ያወዳድራል፤ በሕዝቡ የአምልኮ ስብሰባ የትኛው የበለጠ ጠቃሚ ነው? በማለት ይጠይቃል። ሁሉም የሚረዳውና መላውን የክርስቶስን አካል የሚገነባ ስለሆነ ትንቢት ይበልጣል በማለት መልስ ይሰጣል።  3. ጳውሎስ ትንቢት ከሁሉ የላቀ ስጦታ ነው ማለቱም አይደለም። ከሐዋርያነት ወይም ከማስተማር ይበልጣል አላለም። እርሱ የሚለው፣ በሕዝብ የአምልኮ ሰብሰባ ላይ ትንቢት በልሳናት ከመናገር እንደሚበልጥ ነው፡፡ በልሳናት የመናገርና የትንቢት ስጦታ ንጽጽር የሚከተለውን አጥና፡-  በልሳናት መናገር                                           ለእግዚአብሔር ብቻ መናገር ነው (1ኛ ቆሮ. 14፡2-3) እግዚአብሔር ብቻ ይረዳዋል (1ኛ ቆሮ. 14፡2-3፣ 14-15) ተናጋሪውም ሆነ ሌሎች የማይረዱትን ምሥጢራትን (ሰዎች የሚረዱት እውነት አይደለም) ይናገራል (1ኛ ቆሮ. 14፡3) እራሳችንን ብቻ ያንጻል (1ኛ ቆሮ. 14፡4) መልካም ነው (1ኛ ቆሮ. 14፡5) ለማያምኑ ምልክት ነው (1ኛ ቆሮ. 14፡22) ሕዝብ በተሰበሰበበት መጠቀም ውዥንብርን ያመጣል (1ኛ ቆሮ. 14፡24) ሕዝብ በተሰበሰበት ለሁለት ወይም ለሦስት ተናጋሪዎች ብቻ የሚፈቀድ ነው (1ኛ ቆሮ. 14፡27፣ 29) ካልተተረጎመ መነገር የለበትም (1ኛ ቆሮ. 14፡29) ትንቢት መናገር ለሰዎች መናገር ነው (1ኛ ቆሮ. 14፡2-3) ሰዎች ይረዱታል (1ኛ ቆሮ. 14፡2-3፣ 14-15) ሰዎች የሚረዱትና ሊያጠነክራቸው ሊያበረታታቸውና ሊያጽናናቸው የሚችል ቃል ይነገርበታል (1ኛ ቆሮ. 14፡3) ቤተ ክርስቲያንን ያንጻል (1ኛ ቆሮ. 14፡4) ብዙ ሰዎችን ስለሚያንጽ የተሻለ ነው፡፡ (1ኛ ቆሮ. 14፡5) ለሚያምኑ ምልክት ነው (1ኛ ቆሮ. 14፡22) ሕዝብ በተሰበሰበበት መነገሩ ሰዎችን ወደ ንስሐ ያደርሳል (1ኛ ቆሮ. 14፡24) ሕዝብ በተሰበሰበበት ለሁለት ወይም ለሦስት ተናጋሪዎች ብቻ የሚፈቀድ ነው፡፡ (1ኛ ቆሮ. 14፡27፣ 29) መፈተን አለበት (1ኛ ቆሮ. 14፡29) 1ኛ ቆሮንቶስ 14፡1-5  በዚህ ክፍል የምንመለከተው ጳውሎስ ሰዎች በልሳናት ከመናገር ይቆጠቡ ዘንድ መምከሩን አይደለም። ይልቁኑ በልሳናት መናገር በተላይ በሕዝብ የአምልኮ ስብሰባ ላይ ያለውን ድርሻ ሰዎች እንዲያውቁት ነው የሚፈልገው። በአምልኮ ስብሰባ ላይ ትንቢት ሰዎች ሁሉ በሚገባቸው ቋንቋ ስለሚነገር ሰዎችን በእምነታቸው ለመገንባት ይጠቅማል። በጉባኤ የተገኙትን ሰዎች ያነጻል። መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚሰጡት በተቀዳሚ ለክርስቲያኖች ሁሉ ጥቅም ስለሆነ በልሳናት ከመናገር ይልቅ ትንቢት ይህን የመንፈሳዊ ስጦታዎችን ዓላማ ያሟላል።  1ኛ ቆሮንቶስ 14፡6-12 ንግግር ሰዎችን ሊያንጽ የሚችለው ሰዎች ሲረዱት ብቻ ነው። ሌላውን ሰው ሊያንጸው የሚችለው የሚገባው ነገር ብቻ ነው። በቤተ ክርስቲያን የሚደረጉ

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 14፡1-19) Read More »

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 13)

አንድ ሰው እንዲህ ይላል «በልሳናት የመናገር ስጦታ አለኝ። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በምፈልገው መንገድ እጠቀምበት ዘንድ እንድትተውኝ እፈልጋለሁ። የመንፈስ ቅዱስ ሥራን እንዴት ልትቆጣጠሩ ትችላላችሁ? ሌላው ሰው ደግሞ «እኔ የዚህ ቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ ነኝ። ልሳን ሁከት ፈጣሪ ነው የተማርነውም እንደዚህ ስላልነበረ በልሳናት እንድትናገር ልፈቅድልህ አልችልም» ይላል። ስለዚህ በልሳናት መናገር በአምልኮ ስብሰባ አንዱ ክፍል እንዲሆን በሚፈልጉና ሊቆጣጠሩት በሚፈልጉ መካከል ክርክሩ ይቀጥላል። ሁለቱም ከፊል እውነት አላቸው። ነገር ግን የየራሳቸውን መንገድ ብቻ ከፈለጉ ቤተ ክርስቲያን በዓመታት ውስጥ እንደሆነችው ትከፋፈላለች።  በካሪዝማቲክና ካሪዝማቲክ ባልሆኑ ክርስቲያኖች በሚደረጉ ክርክሮች ከስጦታዎች ሁሉ በላይ የሆነ ብዙ ጊዜ የሚጐድል አንድ ነገር አለ። ይህ የጐደለ ነገር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ላለ አንድነት ሲባል የራስን ፍላጐትና አመለካከት በፈቃድ የሚያስተው ፍቅር ነው።  ጥያቄ፡- ስለ መንፈስ ቅዱስ ወይም ስለ አምልኮ አይነት የአሳብ ልዩነት በሚያሳዩ ክርስቲያኖች መካከል የፍቅር ጉድለት መኖሩን የምትመሰክርባቸውን ምሳሌዎችን ጥቀስ። ለ) ያለ መግባባት የሚያስከትላቸውን ውጤቶች የፍቅር አመለካከት እንዴት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሊለውጥ ይችል እንደነበር ግለጽ።  ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮ. 13 አንብብ። ሀ) ያለ ፍቅር ከንቱ መሆናቸው የተነገረላቸውን የተለያዩ መንፈሳዊ ስጦታዎች ዘርዝር። ከቁ 4-7 የተገለጸው የፍቅር ባሕርይ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በመሳሰሉ ነገሮች ያለመግባባት ሲኖር የሚጠቅመው እንዴት ነው? ሐ) እንደሚያልፉ የተጻፈላቸው ነገሮች ምን ምን ናቸው? ጳውሎስ ይህን ያለው ለምን ይመስልሃል? መ) ጳውሎስ በ 1 ና 2 ላይ እውነትን የሚያውቀው በከፊል ብቻ እንደሆን በገለጸበት ወቅት የነበረው ዝንባሌ ምንድን ነው? ይህ ዝንባሌ በሌላ ሰው ላይ የተለየ አመለካክት ሲኖረን የሚጠቅመው ለምንድን ነው?  በአዲስ ኪዳን ውስጥ ከሚገኙ እጅግ ውብ ምዕራፎች አንዱ 1ኛ ቆር. 13 ነው። ብዙ ጊዜ በሠርግ በዓል ላይ ይጠቀሳል። ነገር ግን በዚህ ምዕራፍ ላይ የተጠቀሰው በመንፈሳዊ ስጦታዎች ላይ በተለይም በልሳን በመናገር ስለሚፈጠር ያለመግባባት ነው። ይህንን ምዕራፍ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ላሉ ልዩነቶች ተግባራዊ ብናደርገው በቤተ ክርስቲያን ባሉ ሰዎች መካከል ያለው አብዛኛው መከፋፈል ወደ ፍጻሜ ይመጣ ነበር። ስለዚህ ምዕራፍ ብዙ ነገሮችን ማለት እንችላለን። ነገር ግን በመንፈሳዊ ስጦታዎች አንጻር ስናየው የሚከተሉትን እውነቶች መማር እንችላለን።  1. መንፈሳዊ ስጦታ ምንም ያህል ታላቅና አስደናቂ ቢሆንም በፍቅር መንፈስ የሚደረግና በአማኞች መካከል ፍቅርን የሚጠብቅ ካልሆነ በስተቀር በእግዚአብሔር ዓይን ምንም ዋጋ የለውም። ያለ ፍቅር ልሳናት የመላእክት ቋንቋ ቢሆኑም እንኳ የማይጠቅም ባዶ ጩኽት ናቸው። ጳውሎስ በልሳናት የጀመረው የቆርንቶስ ክርስቲያኖች ችግር ያለው በዚህ ጉዳይ ላይ ስለነበር ሳይሆን አይቀርም። ትንቢትና ተአምራት ሰዎችን ምንም ያህል የሚያስገርሙ ቢሆኑም እንኳ ያለ ፍቅር በእግዚአብሔር ዓይን ፊት ዋጋ የላቸውም። በሕይወታችን ከሁሉ የላቀውን ነገር ብንሰጥና ሕይወታችንን መሥዋዕት እስከማድረግ ለወንጌል ብንሞት እንኳ የፍቅር ሕይወት ካልኖርን በእግዚአብሔር ዓይን አንዳችም ክብር የለውም። መንፈሳዊ ስጦታዎቻችንን በፍቅር ካልተጠቀምንባቸው ብንጠቀምባቸውም እንኳ የተሰጡበትን ዓላማ ስተናል ማለት ነው። የክርስቶስን አካል በመገንባት ይልቅ አፍርሰነዋል ማለት ነው። ይህ በሌላ አባባል በገላ. 5፡22-23 የምናገኘው የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ከወመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች የላቀ ነው ማለት ነው።  2. ጳውሎስ የሚናገረው መንፈሳዊ ስጦታዎችን ያለ ፍቅር መጠቀም ስጦታዎች የሚያስገኙትን ጥቅም ስለማስቀረቱ ብቻ ሳይሆን ለጦታውን በተሳሳተ መንገድ የሚጠቀመውን ሰው በአሉታዊ መንገድ እንደሚጐዱ ነው። ያላ ፍቅር የሆነ ልሳን ባለ ስጦታውን እንደሚንሿሿ ባዶ ጸናጽል ያደርገዋል። ትንቢት፥ ተአምራትን ማድረግ ወይም መሥዋዕት ሆኖ ማለፍ ያለ ፍቅር ሰውን ወደ ባዶ ቀፎነት ይለውጣል። ጳውሎስ የሚለው በልሳናት በመናገር ችሎታችን ክብር ብናገኝ፥ እውነትን ብናውቅ፥ ተአምራትን ብናደርግ መንፈሳዊ የሚያደርገን ይህ ነው ብለን ካሰብን ሙሉ ለሙሉ የተሳሳትን እንደምንሆን ነው። መንፈሳዊ ስጦታዎች በራሳቸው ስለ ሰው መንፈሳዊ ሕይወት አንዳችም ነገር አይናገሩም። አንድ ሰው በእውነት መንፈሳዊ የመሆኑ ማስረጃ ፍቅር ብቻ ነው። መንፈሳዊ ስጦታዎች የክርስቶስን አካልም ሆን የግለሰብ ክርስቲያን ሕይወትን እንዲጠቅሙ ከተፈለገ በፍቅር መዋሃድ አለባቸው።  3. ፍቅር ለሚለው ትርጉም የግሪኩ ቃል «ኦጋፔ» ነው። ጳውሎስ ስላ ፍቅር የሚሰጠውን ስናነብ መንፈስ ቅዱስ ለክርስቲያኖች የሚሰጠው ፍቅር እንጂ ተፈጥሮአዊ ፍቅር እንዳይደላ በቀላሉ እንረዳለን። የመንፈስ ፍሬ የተባለውም ለዚህ ነው። ይህ ፍቅር ከራስ ወዳድነት ተላቅቆ ለሌሎች ድነት (ደኅንነት) እራስን መስጠት ነው። ፍቅር በመሠረቱ ስሜት ሳይሆን በገዛ ፈቃድ እራስን ለሌላው መስጠት ነው። ፍቅር የሚወደደው ሰው መልካምና ተፈቃሪ እንዲሆን አይጠብቅም። ነገር ግን የኢየሱስ ትእዛዝ ስለሆነ ሌላን ሰው ለመውደድ መወሰን ነው። ኢየሱስ ለእያንዳንዳችን ኃጢአት በመስቀል ላይ በሞተ ጊዜ ያሳየው አይነት ፍቅር ነው (ዮሐ 13፡34-35/ 1ኛ ዮሐ 3፡16)።  4. ጳውሎስ ፍቅርን በሚገልጥበት ወቅት ፍቅር ባለአለመግባባት መካከል እራሱን እንዴት እንደሚገልጥ ለማሳየት ትኩረት አድርጓል። የእግዚአብሔር መንፈስ ያልተግባባነውን ሰው ወደ ብስለት እስኪያመጣ ድረስ የሚታገሥ ነው። የበለጠ የሚታይና የሚደነቅ ስጦታ ባላቸው ሰዎች አይቀናም። የእርሱ ስጦታ ከሌሎች እንዴት የላቀ እንደሆነ በማሰብ አይመካም። ሰዎች ሳይረዱትና ከእርሱ ጋር ሳይግባቡ ሲቀሩ አይቆጣም። በአለመስማማት መካከል ያለአግባብ ቢከሰስና ወይም የሚያስቆጣ ንግግር ቢደረግበትም አይበሳጭም። ፍቅር ያልተግባባናቸው ሰዎች ንጹሕ ውስጣዊ መነሻ አሳብ እንዳላቸውና ልክ እንደ እኛ እግዚአብሔርን ለመከተል ፈልገው እንዳደረጉት በመረዳት ላለመግባባት ስፍራ ይነሳል።  5. መንፈሳዊ ስጦታዎች ጊዜያዊ ሲሆኑ ፍቅር ግን ዘላለማዊ ነው። ሊቃውንት በ1ኛ ቆሮ. 13፡8-11 ባለው አጠቃላይ አሳብ ላይ ይስማሙበታል። ትንቢት በልሳናት መናገርና እውቀት የሚቆሙበት ጊዜ ይመጣል። ግን የሚቆሙት መቼ ነው? ጳውሎስ «ፍጹም የሆኑና፡ «ፍጹም ያልሆኑ» የሚላቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? ስለዚህ ጉዳይ የተለያዩ አሳቦች አሉ።  በመጀመሪያ ካሪዝማቲክ ያልሆኑ ብዙ ክርስቲያኖች እንደሚያምኑት ፍጹም ያልሆነው የሚለው ቃል የሚያመላክተው የአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን መልክ የያዘችባቸውን ጊዜያት ነው። ጳውሎለ ቤተ ክርስቲያን ወደተሳሰረ እንድነት እየገባች እንደሆነ ያውቅ ነበር። የአመራርና የመሠረተ እምነት ትምህርት ይዞታም ገና እያደገ ነበር። ከሁሉም በላይ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ገና አልተጠናቀቁም ነበር። ፍጹም የሆነችውና የበሰለች ቤተ ክርስቲያን የተገኘችው ከብሉይ ኪዳን ወደ አዲስ ኪዳን የተደረገው ሽግር ከተፈጸመ በኋላ እና አዲስ ኪዳን ከተጻፈ በኋላ ነበር። ሰዎች በእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፈውን ሙሉውን መጽሐፍ ቅዱስ ካገኙበት ጊዜ ጀምሮ በልሳናት የመናገር፥ የትንቢትና የእውቀት ስጦታዎች አያስፈልጋቸውም ይላሉ። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እነዚህን ስጦታዎች አዲስ ኪዳን ተጠናቆ ከተጻፈበት ከ100 ዓ.ም ጀምሮ መሰጠቱን አቁሟል ይላሉ። አዲስ ኪዳን ተጠናቅቆ ከተጻፈበት ጊዜ ጀምሮ እነዚህ ስጦታዎች አያስፈልጉንም፤ ምክንያቱም የሚያስፈልጉን ትንቢቶችና እውቀቶች በሙሉ በእጃችን ባለው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛሉ ይላሉ።  መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ያለቀበትን ጊዜ የፍጹምነት ጊዜ አድርገው የሚቆጥሩት ለምንድን ነው? ካሪዝማቲክ ያልሆኑ ክርስቲያኖች ከካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ጋር ካሏቸው ልዩነቶች አንዱ ትንቢትን የሚረዱበት መንገድ ነው። የትንቢት ስጦታ እስካሁን እየሰራ ነው ብለን ካመንና ይህ ትንቢት በኢሳይያስ በኤርምያስ፥ ወይም በጳውሎስ እንደነበረው ዓይነት ሥልጣን አለው ካልን መጽሐፍ ቅዱስ ገና አልተጠናቀቀም ማለታችን ነው። የትንቢት ስጦታ ያላቸው ሰዎች እያንዳንዳቸው አዲስ መጻሕፍትን መጻፋቸውን መቀጠል አለባቸው ማለት ነው። ይህ ደግሞ መናፍቃን የሚያደርጉት ነው (ለምሳሌ—የይሖዋ ምስክሮች፥ ሞርሞናውያን፥ የባሃኢ ተከታዮች)። ስለዚህ ይህ ስጦታ ቢያንስ በመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት ጸሐፊዎች ዘንድ እንደነበረው ዓይነት መንፈስ ቅዱስ ያረፈበት የትንቢት ስጦታ አክትሟል ብለው ያስተምራሉ። ያሳሰባቸው ነገር ትልቅ ዋጋ ያለው ቢሆንም በዚህ ዘመን የሚነገሩት ትንቢቶች የተጻፈውን የእግዚአብሔርን ቃል ያህል ሥልጣን እንደሌላቸው ግልጽና እንዲያውም በእግዚአብሔር ቃል የመፈተናቸው አስፈላጊነት የማያወላዳ ቢሆንም ጳውሎስ የተናገረው ፍጹምነት ግን ይህ አይደለም።  በሁለተኛ ደረጃ፣ ጳውሎስ የሚናገርለት ፍጹምነት ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ከተመለሰ በኋላ የሚሆን ሳይሆን አይቀርም። እስከዚያ ድረስ መንፈስ ቅዱስ ምንም ያህል የእውቀት ስጦታን፥ የትንቢት ስጦታ፥ ወይም በልሳናት የመናገር ስጦታን ቢሰጠንም እንኳ እውቀታችን የተወሰነ መሆኑ አይቀሬ ነው። ያለን እውቀት ከፊል ብቻ ይሆናል። በመረዳታችን ወደ ፍጹም ሙላት የሚመጣው ኢየሱስን ፊት ለፊት ስናየው ብቻ ነው። በዚያን ጊዜ የእውቀት፥ የትንቢትና ወይም በልሳናት የመናገር ስጦታ አያስፈልጉንም። ፍጹምነት የሚያመላክተው ለለመጨረሻው ጊዜያት ነው ብለን ካመንን

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 13) Read More »

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡12-31 )

ዮሐንስና ጸጋዬ በአንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ሁላት መሪዎች ነበሩ። ጻሩ ቀን በጣም የተለያዩ ስጦታዎች ነበሯቸው። ዮሐንስ ብዙ ሰዎች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመለሱ ዘንድ እግዚአብሔር የሚጠቀምበት ወንጌላዊ ነበር። ጸጋዩ ሰዎችን የእግዚአብሔርን ቃል ጥልቀት ባለው መንገድ ለማስረዳት የሚችል አስተማሪ ነበር። ነገር ግን ጸጋዬ በዮሐንስ ይቀና ነበር። ምክንያቱም ዮሐንስ ብዙ ሰዎችን ለክርስቶስ የማረከና በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሰዎች የሚያመሰኑት ስለ ነበር ነው። ስለዚህ ጸጋዬ በዮሐንስ ላይ በማሴር የቤተ ክርስቲያንን ሽማግሌዎች በእርሱ ላይ እንዲነሡ ለማድረግ ጣረ። በመጨረሻ ቤተ ክርስቲያን ዮሐንስን አባራ ጻጋዩን በወንጌላዊነት ቀጠረች።  ጥያቄ፡- ሀ) ይህ ታሪክ ስለ ክርስቶስ አካልና እግዚአብሔር መንፈሳዊ [ስጦታን እንዴት እንደሚሰጥ ትክክለኛ ግንዛቤ ማጣትን እንዴት ያሳያል? ላ) የዮሐንስና ጸጋዬ አብረው ቢሠሩ ኖሮ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ጠንካራ ትሆን ነበር? ሐ) የወንጌላዊነት ስጦታ ያልነበረው ጸጋዩ እንደ ወንጌላዊ ሆኖ ለመሥራት በመሞከሩ ቤተ ክርስቲያን የምትክመው በምን ዓይነት መንገድ ነበር? መ) ይህ ታሪክ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለ አገልግሎት ያለውን የተሳሳተ አመለካከት እንዴት ያሳየናል? ሀ) እንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች በቤተ ክርስቲያንህ እንዴት እንደተከሰቱ ምሳሌዎችን ስጥ።  ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮ. 12፡12-31 አንብብ። ሀ) እግዚአብሔር አካልን የሠራበት መንገድ በልዩነቶች ውስጥ ያላ አንድነት መሆኑን የአካል ብልቶች ንጽጽር እንዴት አድርጐ ያሳያል? ለ) የክርስቶስ አካል የሆነቸው ቤተ ክርስቲያን ከሰው አካል ጋር ያላት ተመሳሳይነት እንዴት ነው? ሐ) መንፈስ ቅዱስ እንዴት መንፈሳዊ ስጦታዎችን እንደሚሰጥና ስጦታዎችን ሁሉ በአንድነት እንደሚሠሩ ዋና ዋና መርሆዎችን ዘርዝር። መ) ዮሐንስና ጸጋዬ ይህን እውነት በሚገባ ተገንዝበው ቢሆን ኖር እንዴት ይረጻቸው ነበር? ሠ) በሠንጠረዥ ላይ አዳዲሶችን መንፈሳዊ ስጦታዎችና ትርጉማቸውን መሙላትህን ቀጥል።  የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች አንድነት ይኖር ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ሁልጊዜ በአንድ መንገድ መሥራት አለበት በሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ ውስጥ ነበሩ። ለእያንዳንዱ ክርስቲያን ተመሳሳይ ስጦታን በተለይ ደግሞ በልሳናት የመናገር ስጦታን መስጠት አለበት ይሉ ነበር። የሰውነት አካል እንዴት እንደሚሠራ አልገባቸውም ነበር። ጳውሎስ የሚያስተምረው ሥጋዊ አካል ይሠራ ዘንድ በአንድነት ውስጥ ያሉ ልዩነቶች መኖር እንዳለባቸው ነው። የክርስቶስ አካል ይሠራ ዘንድ በመንፈሳዊ ስጦታዎችና በአጠቃቀማችን ልዩነት መኖር አለበት።  ቤተ ክርስቲያን እማኞች የሚሰበሰቡበት ሕንፃ አይደለም። እውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን አካል ናት። ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያንን የክርስቶስ አካል ብሎ ይጠራታል። ስለ ቤተ ክርስቲያን በሚናገርበት ጊዜ እንኳ ቤተ ክርስቲያንን ክርስቶስ ብሎ ይጠራታል (1ኛ ቆሮ. 12፡12)። ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያንን በሚያሳድድበት ጊዜ ኢየሱስ ጳውሎስን ስለምን ታሳድደኛለህ በማላት ወቅሶት እንደነበር ታስታውሳለህ (የሐዋ. 9፡4)። እግዚአብሔር የአማኞች አካል በአንድ ቦታ እንደተሰበሰቡ በሚመለከትበት ጊዜ የሚያመለክተው የሆኑ የተለያዩ ግለሰቦችን አይደለም። ነገር ግን «አካልን» ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስን በምድር ላይ የምትወክል መሆኗን ነው የሚመለከተው።  የአንድ አጥቢያ ክርስቲያኖችን በቡድን አካል የሚያደርጋቸው ምንድን ነው? መንፈስ ቅዱስ ነው። የልዩነታቸውና የአንድነታቸው ምንጭ ነው። የአንድነታቸው መነሻ ሁላቸውም በመንፈስ ቅዱስ መጠመቃቸው ነው። እያንዳንዱ ክርስቲያን በዳነ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሏል። በዚያን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ አማኞችን ወደ አንድ የክርስቶስ አካል ልምሮአቸዋል። የተለያዩ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በአንድ አካል ውስጥ የሚሰጥ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ የልዩነቶቻቸው ምንጭ ስለሆነ ነው።  ጳውሎስ በዚያን ዘመን የነበረችው ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ዘመን ካሉት ጋር የምትመሳሰልበት ሁኔታ በቀጥታ አላ ባይልም እንኳ በልሳናት የመናገር ስጦታዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመጡ የተላያዩ ሁኔታዎች ይከሰታሉ። ብዙ ጊዜ በልሳናት መናገር የሚጀምሩት እራሳቸውን እንደ መንፈሳዊ ሰዎች ይመለከታሉ። የተመረጡና መንፈስ ቅዱስ ያላቸው እነርሱ ` ብቻ ይመስላቸዋል። እነዚህ ውስጣዊ ወገኖች አካሎቻቸው በተለይ ደግሞ በተግባራቸው ለቀሪው ጉባኤ እኛ ከእናንተ እንሻላለን፥ መንፈስ ቅዱስ አለን። ለዚህ ማረጋገጥ በልሳናት እንናገራለን። እናንተ ስለማትናገሩ እንደ እኛ መንፈሳዊ አይደላችሁም የሚል ገጽታ አላቸው። ወዲያውኑ መከፋፈል ይሆንና ቡድኖች መፈጠር ይጀምራሉ።  ቀጥሎ ሦስት ነገሮች ይሆናሉ። ብዙዎች መንፈሳዊ ለመሆን በመፈለግ ማስመሰል ይጀምራሉ። ለሌሎች መንፈሳዊ መለለው መታየት ስለሚፈልጉ በልሳናት የሚናገሩ ያላመስላሉ። ሃሌሉያ እያሉ ይጮኻሉ፡ እዞቻቸውን ያነሣሉ። በሌሎች ፊት መንፈሳውያን ለመምሰል ይወዛወዛሉ። ይህ የግብዝነት ኃጢአት ነው።  ሁለተኛ፣ አንዳንድ ክርስቲያኖች ቤተ ክርስቲያኖቻቸውን በመልቀቅ ወደ ሌላ ቤተ ክርስቲያን ይገባሉ። ወይም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለቡድኑ ወገናዊነት የማይሰማቸው እጅግ ዝምተኞች ይሆናሉ። እንደ ሌሎች መንፈሳውያን ለምን እንዳልሆኑ በማሰብ ይደነቃሉ።  ሦስተኛ፣ አንዳንዶች የመጀመሪያውን ቡድን አጥብቀው የሚቃወሙ ይሆናሉ። እነርሱ እራሳቸውን የበለጠ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አድርገው ስለሚያስቡ ይታበያሉ። እነዚህ ስሜታውያን ብቻ ናቸው ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስን ስለማያውቁ እውነተኛ ክርስቲያኖች እንደሚያደርጉት አይለማመዱትም ሰማላት ይሳለቁባቸዋል። የእነዚህም ትዕቢት የመጀመሪያዎቹን ያህል ክፉ ነው።  ጥያቄ፡– ይህስ ነገር በቤተ ክርስቲያን ሲፈጸም እንዴት እንዳየህ ግለጥልን።  የሚያሳዝነው ግን እነዚህ ቡድኖች የተሳሳቱ መሆናቸው ነው። ሁላቸውም ጳውሎስ ለክርስቶስ አካል ያስተማረውን ዘንግተዋል። ለዚህ ነው ጳውሎስ መንፈስ ቅዱስ ለቤተ ክርስቲያን የሰጠው የስጦታዎች ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ የአካል እንድነት አስፈላጊ ስለመሆኑ እነዚህን ሦስት ቡድኖች እያንዳንዳቸውን ለማስተማር የጻፈው።  1ኛ ቆሮ. 12፡12-31 ላይ ሰብዓዊ አካልን ከመንፈሳዊ አካል ጋር ከሚያነጻጽረው ክፍል የሚከተሉትን ነገሮች እንማራለን።  1. የክርስቶስ አካል እርስ በርሱ የተሳሰረ አንድ ቅንጣት ነው። እንደ አንድ አብሮ ለመሥራት የተቀናጀ ነው። በሌሎች ቦታዎች ክርስቲያኖች በአእምሮና በመንፈስ አንድ እንዲሆኑ ጳውሎስ ይለምናቸዋል (ፊልጵ. 2፡1-4)።  2. የክርስቶስ አካል የተለያዩ ክፍሎች ወይም የተላያዩ ስጦታዎች ያሉት ነው። በዚህ ልዩነት ውስጥ እንድነት አለ።  3. የክርስቶስ አካል የተለያዩ ክፍሎች ወይም ሰዎች ሁሉ ከመንፈሳዊ ስጦታዎች ጋር በክርስቶስ አካል ውስጥ ይፈለጋሉ። ድንቀኛ ስጦታ የሌለው ማንኛውም ግለሰብ እንኳ ላመለየት መብት የለውም። ሌላ ማንኛውም ሰው ደግሞ ይህንን ሰው አንተ የአካሉ ክፍላ አይደለህም የማለት መብት የለውም። እያንዳንዱን ሰው በክርስቶስ አካል ውስጥ ያስቀመጣው መንፈስ ቅዱስ ከሆነ እያንዳንዱ ሰው ለዚያ አካል ጤንነትና ተግባር ተፈላጊ መሆኑን መገንዘብ አለብን።  በልሳናት በመናገር ስጦታዎች የሚመኩ ሰዎች ሌሎች እንደ እነርሱ እንዲሆኑ ለማስገደድ ወይም ኅብረቱን ትተው እንዲሄዱ እንዳይገፉ መጠንቀቅ አለባቸው። በልሳናት የማይናገሩት ደግሞ በልሳናት የሚናገሩትን እንደ እነርሱ ለማድረግ እንዳያስገድዱ መጠንቀቅ አለባቸው። በልሳናት ባለመናገራቸው ምክንያት መንፈሳውያን እንዳልሆኑ የሚመስላቸው፥ በልሳን የሚናገሩት እግዚአብሔርን እንደሚያከብሩበት ያለ የተለየ ስጦታ በመንፈስ ቅዱስ ለእነርሱም እንደተሰጠ ማስታወስ አለባቸው። ስለዚህ በልሳናት የማይናገርና የመምከር ስጦታ ብቻ ያለው ሰው በልሳናት በሚናገረው ሰው ምክንያት ስጋት ሊሰማው አይገባም።  4. የቤተ ክርስቲያን ንነት የሚገኘው እያንዳንዱ አካል በተገቢው ሁኔታ ተግባሩን ሲፈጽም ነው። ዓይናችንና ጆሮአችን፥ በተናጠልና በተደጋጋፊነት መሥራት አለባቸው። ስለዚህ ደግሞ በአካሉ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ሰው የራሱን ስጦታ መጠቀም አለበት። ይህን በማድረጉ የቤተ ክርስቲያንን አንድነትና ጥንካሬ ያጐላብታል።  5. ማንኛውም ዓይነት ስጦታ ከሁሉም የላቀ እንደሆነ በሚታሰብበት ጊዜ አካሉ ሚዛን ያጣ ይሆናል። ለአካሉ ስትክክል መሥራት እያንዳንዱ ሰው መንፈሳዊ ስጦታውን መጠቀም አለበት። አንዱ ስጦታ በሌላው ስጦታ ላይ ጥገኛና ደግሞም የሌሎችን ስጦታዎች ሚዛን የሚጠብቅ ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን ስጦታዎችን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ለመጠበቅ መቻል አለባት። ሰዎች ድንቀኛ በሆኑት በልሳናት መናገርና ፈውስና ሌሎችም ላይ ከሚገባው በላይ ካተኮሩ አካል እንድ ትልቅ ዓይን ብቻ መስሎ አስቀያሚ መልክ ይይዛል። የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በሙሉ ሊከበሩና ተግባር ላይ ሲውሉ ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር በቀደሳት መንገድ ሚዛናዊና ውብ መሆን ትችላለች።  6. ድንቀኛ ያልሆኑ መንፈሳዊ ስጦታዎች ለቤተ ክርስቲያን ተግባር እጅግ ጠቃሚ የሆኑና እንዳንድ ጊዜ ድንቀኛ ከሚሆኑት ስጦታዎች እንኳ የበለጠ ሊከበሩ የተገቡ ናቸው። በልሳናት የሚናገሩት ክርስቲያኖች በማይናገሩት ላይ የበላይነት ከተሰማቸውና ካሪዝማቲክ ያልሆኑ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዳይኖሩ የሚመኙ ከሆኑ ጥንቃቄ ቢያደርጉ ይሻላቸዋል። በዚህ መንገድ ሊመጻደቁና በልሳናት በመናገር ላይ የማያተኩሩትን ሊያባርሩ መብት የላቸውም። ካሪዝማቲክ ያልሆኑት ክርስቲያኖች በካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ላይ ስለሚኖራቸው አመለካከት ተመሳሳይ ነገር ማለት ይቻላል።  መንፈሳዊ የሆንን እኛ በተለይ እግዚአብሔር በጣም የሚታይ ስጦታ የሰጠን ድንቀኛ ስጦታ የሌላቸውን ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን በጣም የሚፈለጉትን ሰዎች የምናከብርበትን መንገድ እንድንፈልግ ታዝዘናል። የመምከር ስጦታ፥ ያላቸው ሰዎች

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡12-31 ) Read More »

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡4-11 )

ጥያቄ፡- «መንፈስ ቅዱስ እንዳላህና በሕይወትህ በሙላት መኖሩን ለማወቅ በእርግጥ ከፈለግህ በልሳን መናገር አለብህ። ላል አባባል በትናንትናው ትምህርት በመመሥረት እንዴት ምላሽ ትሰጣለህ።  በ1ኛ ቆሮ. 12፡1-3 ላይ በተሰጣው በትናንትናው ትምህርት ላይ ለመንፈስ ቅዱስ ህልውና ማረጋገጫ በልሳናት መናገር ክሚሆን ይልቅ ህልውናው ይበልጥ የሚገለጸው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚቀዳጀው ክብር መጠን መሆኑን ጳውሎስ አመልክቷል። ጳውሉላ አሁን ደግሞ በልሳናት መናገር ከስጦታዎች አንዱ ብቻ እንደሆነ መናገሩን ይቀጥላል። መንፈስ ቅዱስ ለቤተ ክርስቲያን በርካታ የተለያዩ ድንቀኛና ድንቀኛ ያልሆኑ ስጦታዎችን ይሰጣል። ሁሉም ያስፈልጋሉ፤ ደግሞም ሁሉም ለክርስቶስ አካል ጥቅም የሚውሉ ናቸው።  ጥያቄ፡- ሀ) «የተለያዩ» የተባሉትን ነገርች ዘርዝር። ለ) «ተመሳሳይ ናቸው» የተባሉትን ነገሮችም ዘርዝር። ሐህ የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ የተሰጠው ለማን ነው? መ) የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ የተሰጠው ለምን ነበር? ሠ) ባለፈው ሳምንት በጀመርካቸው ሁላት ሠንጠረዦችህ ላይ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ዘርዝር። በጹሑፍ ለእያንዳንዱ ስጦታ አጭር መግለጫ ለጥ። ረ) መንፈሳዊ ስጦታዎችን የሚሰጠው የሥላሴ አካል የትኛው ነው? ሰ) ማን [የትኛውን ስጦታ እንደሚያገኝ የሚወሰን ማን ነው?  ቀጥሎ በዚህ ክፍል ውስጥ የተጠቀሱትን ዋና ዋና እውነተች እንገልጻለን።  1 በልዩነት ውስጥ ያለ አንድነት ምንጩ አሐዱ ሥሉስ የሆነው አምላካዊ ባሕርይ ነው።  ክርስቲያኖች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንድነት መኖር አለበት ስንል ሁሉም አንድ እይነት መሆን አለበት የሚል የተሳሳተ አሳብ ይይዛሉ። የሚያምኑት ነገር ሙሉ በሙሉ እንድ መሆን አለበት። እንድ ዓይነት ተግባር እንዲኖራቸው ይጠብቃሉ። የቤተ ክርስቲያን ተግባራቸውን አንድ ዓይነት መሆን አለበት ይላሉ። ለምሳሌ አንዳንድ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ሁሉም ክርስቲያኖች በልሳን መናገር አለባቸው! ሰው መንፈሳዊ የመሆኑ ምልክት በልሳን መናገሩ ነው የሚል አስተሳሰብ ነበራቸው።  በ1ኛ ቆሮ. 12፡4-11 ክፍል ውስጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መንፈሳዊነትና መንፈሳዊ ብስለት በአንድነት ውስጥ ያለ የልዩነቶች ውጤት መሆኑን ይናገራል። በዚህ ክፍል ውስጥ ሁለት ቃሎች ያለሟቋረጥ ተደጋግመዋል። እዚህም «ልዩ ልዩ» ና «አንድ» የሚሉ ቃሎች ናቸው። ይህ በግልጽ መሰጠቱን ለመረዳት የሚከተለውን ተመልከት።  ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው።  አገልግሎት ልዩ ልዩ ነው ጌታ ግን አንድ ነው።  አሠራር ልዩ ልዩ ነው እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።  ጳውሎስ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚሰጠውን አጠቃላይ ገለጻ የሚጀምረው በልዩነት ውስጥ ላላ አንድነት ከሁሉ የላቀ ምሳሌ የሆነውን – እግዚአብሔርን በማመልከት ነው። በአንድ በኩል አንድ እግዚአብሔር፡ አንድ ጌታ፥ አንድ መንፈስ አላ። ነገር ግን በዚህ የእግዚአብሔር አንድነት ልዩነት አለ። እዚአብሔር በሦስት ውስጥ ያለ አንድ የሆነ እሑድ ሥሉስ አምላክ ነው። ከዚህ ከአንዱ እግዚአብሔር የተላያዩ ስጦታዎችና አገልግሎቶች ይወጣሉ። እነዚህ ለጦታዎች አገልግሎቶችና አሠራሮች ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚናገሩ ሲሆኑ ኋላ ደሞ የመንፈስ ቅዱስ መገለጦች ተብለዋል። አንዱ እግዚአብሔር የመንፈሳዊ ስጦታዎች ሁሉ ምንጭ የመሆኑ እውነት እግዚአብሔር የሚሰጠው መንፈሳዊ ስጦታ አንድ ዓይነት ብቻ ነው ማለት አይደለም። በልሳናት የመናገር ስጦታ እግዚአብሔር ሊሰጥ ከሚችላቸው ስጦታዎች አንዱ ብቻ ነው። እግዚአብሔር ልዩነቶችን የሚወድ ሊሆን የተለያዩ ስጦታዎችን በመስጠት አንድነትን ያበረታታል። በአንድነት መካከል ያላ ይህ ልዩነት እግዚእብሔር ለቤተ ክርስቲያን ያለው ዓላማ ነው። እንዲያውም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መንፈሳዊ ብስለት ከሁሉ በላቀ ሁኔታ የሚረጋገጥበት መንገድ የተላያዩ ስጦታዎች ያላቸው የተለያዩ ሰዎች አንዱን እግዚአብሔርን ለማገልገል በአንድነት መሥራታቸው ነው።  ልዩነቶች ለአንድነት ወይም ለመከፋፈል መሣሪያ ላሆኑ ይችላሉ። ሰይጣን ልዩነቶች ወዳሉባቸው ስፍራዎች በመምጣት ሰዎች ወይም አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፋፈሉ መንገድ መጥረግ ይወዳል። የተለያዩ ዝርያዎች ነገዶች፥ ጾታዎችና ስጦታዎች መኖራቸው ሰይጣን ዓለምንና ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል የሚጠቀምባቸው ናቸው። የእግዚአብሔር ዕቅድ ቀን ልዩነቶቻችንን በመጠቀም እርስ በርስ መደጋገፍና አንድነትን እንድናጐለብት ነው። ለሰዎች ሌሎች ነገዶች፥ ሌሎች ባሕሎች ሌሎች መንፈሳዊ ስጦታዎች ወዘተ…) እንደሚያስፈልጋቸው በማሳየት ሰዎች ፡ በኅብረት ለአንድነት እንዲሠሩ ያደርጋል። በልዩነቶች መካከል ያለው አንድነት እዚአብሔር ላፍጥረትና ለሕዝቡ ያለው ዕቅድ ነው።  ጥያቄ፡- በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ልዩነቶች አንድነትን ሊያግ እንዴት እንዳየህ ምሳሌዎችን ዘርዝር።  2. የመንፈስ ቅዱስ መገለጦች ለእያንዳንዱ ክርስቲያን የተሰጡ ናቸው።  መንፈሳዊ ስጦታዎች ለጥቂት ሰዎች ብቻ የሚሰጡ አይደሉም። ይልቁኑ እያንዳንዱ ክርስቲያን ቢያንስ አንድ ስጦታ ይሰጠዋል። በልሳናት ይናገሩ የነበሩ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በልሳናት መናገራቸው የተለዩ የተሻሉና መንፈሳዊ ያደረጋቸው ይመስላቸው ነበር። የራሳቸው ቡድን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነበራቸው። በልሳናት የመናገር ስጦታዎች የሌላቸውን ሌሎች ክርስቲያኖችን የበታች አድርገው ይመለክቱ ነበር። ጳውሎላ አበክሮ የተናገረው እግዚአብሔር መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለሁሉም እንጂ ላጥቂት ምርጦች ያለ መስጠቱን ነው። በአዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ክርስቲያን ከሌሎች የተለዩ ስጦታዎች ስላሉት ከሌሎች የተሻለ የተመረጠና ልዩ እንደሆነ አድርጐ ራሱን ለሚያቀርብበት መንፈሳዊ ትዕቢት ምንጭ ስፍራ የለም።  3. የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ የሚሰጠው ለጋራ ጥቅም ነው።  አንዳንድ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ስለመንፈሳዊ ስጦታዎች ያላቸው አስተሳሰብ የተሳሳተ ነበር። መንፈሳዊ ስጦታዎች ለግል ጥቅም ለእያንዳንዱ ክርስቲያን መንፈሳዊ እድገትና ክብር የተሰጡ አድርገው ይገምቱ ነበር። ለእነርሱ በልሳናት መናገር የአንድ ሰው መንፈሳዊነት የሚታወቅበት በደረት ላይ የሚለጠፍ ምልክት ዓይነት ምልክት ነበር። በተለይ ይህ ችሎታ ያላቸው መንፈሳዊ፥ የሌላቸው ደግሞ መንፈሳዊ ያልሆኑ አድርገው ያስቡ ነበር።  ግን መንፈሳዊ ስጦታዎች በአጠቃላይ በልሳናት መናገርን ዉር የክርስቲያኑን ማኅበረሰብ በአጠቃላይ ለመጥቀም በመንፈስ ቅዱስ የተሰጡ ነበሩ። መንፈሳዊ ስጦታዎች አንድን ክርስቲያን ታዋቂ ለማድረግ ወይም የበለጠ መንፈሳዊ ለማድረግ የሚሰጡ አይደሉም። ይልቁኑ የቤተ ክርስቲያን አባላትን ለመገንባት የሚሰጡ ናቸው። ይህ ማለት ቀን አንዳንድ መንፈሳዊ ላጦታዎች ላግላሰብ ክርስቲያኖች እድገት አይጠቅሙም ማለት አይደለም። ይህ ጥቅስ በራሱ በልሳናት መናገርን ለግል የአምልኮ ጊዜ መጠቀምን አይከለክልም። ሆኖም ግን የለጦታዎች ሁሉ የመጨረሻ ግብ የክርስቶስ አካል የሆኑ ምእመናንን በሙሉ ለመገንባት ነው።  4.  መንፈሳዊ ስጦታዎች «የመንፈስ ቅዱስ መገለጦች» ተብለው ይጠራሉ።  መንፈሳዊ ስጦታዎች የክርስቲያኖች ዋናና ተቀዳሚ ትኩረት አይደሉም። ይል መንፈሳዊ ስጦታዎችን በሙሉ በሚሰጠው መንፈስ ቅዱስ ላይ ልናተኩር ይገባል። ሆኖም ቀን መንፈስ ቅዱስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚታየው እንዴት ነው? እዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በቤተ ክርስቲያን ለመሥራቱ ማረጋገጫው ምንድን ነው? ከማረጋገጥምቹ አንዱ መንፈሳዊ ስጦታዎች ናቸው። ጳውሎስ የሚዘረዝራቸው መንፈሳዊ ስጦታዎች እያንዳንዳቸው መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያኖች መካክል የሚሠራባቸው መንገዶች ናቸው። ጳውሎላ እያንዳንዱ ሰው ከእዚአብሔር ስጦታን ማግኘቱን እንዲያውቅ የሚፈልግ ቢሆንም በጣም ተፈላጊው ቀን ክርስቲያኖች በሚሠሩት የተለያዩ ስጦታዎች አማካኝነት የእዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ህልውና እንዲገነዘቡ ነው። በቤተ ክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስን ህልውና አንድ ስጦታ ከሌላው አብዝቶ ሊገልጠው አይችልም።  5. ስጦታዎችን በሙሉ አካቶ የያዘ ክርስቲያን የለም።  መንፈስ ቅዱስ በራሱ ሙሉ ሥልጣን ላሚፈልጋቸው ሁሉ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ያድላል። አንዱን ስጦታ ለአንድ ሰው ሌላውን ስጦታ ደግሞ ለሌላው ሰው ይሰጣል። የጳውሎስ አትኩሮት መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ ስጦታዎችን ለተላያዩ ሰዎች እንደሚሰጥ ነው። ለሁሉ ሰው አንድ ዓይነት ስጦታ አይሰጥም። ጳውሎስ በግልጥ ባይናገረውም እንኳ እግዚአብሔር ላአንድ ላሰብ ስጦታዎችን በሙሉ እንደማይሰጥ ያመለክታል። አንድ ሰው ሁሉም መንፈሳዊ ስጦታዎች ካሉት የቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማንም ሰው አያስፈልግም ማለት ነው። ነገር ቀን መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠውን ስጦታ – በመመጠን አንዳችን ለሌላችን እንድናስፈልግ ያደርገናል።  6. መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን በብስለት ታድግ ዘንድ የተለያዩ ስጦታዎችን ይሰጣል።  መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ መንፈሳዊ ስጦታዎችን እንዴት እንደሚሰጥ ለማስረዳት አውሉላ የተለያዩ ስጦታዎችን ይዘረዝራል። ስለ እነዚህ ስጦታዎች የሚከተሉትን ነገሮች ልብ ማለት አስፈላጊ ነው። በመጀመሪያ፥ ጳውሎስ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በሙሉ ለመዘርዘር እየሞከረ አይደለም። መንፈስ ቅዱስ በርካታ የተለያዩ ስጦታዎችን እንደሚሰጥ ለማሳየት ናሙና ብቻ ሊሆን የሚችል ዝርዝር መስጠቱ ነው። ክርስቲያኖች በልሳናት እንደ መናገር ባለ አንድ ስጦታ ላይ በማተኮር መንፈስ ቅዱስ የሚሰጣቸውን ሌሎች ለጦታዎችን መዘንጋት የለባቸውም። በአዲስ ኪዳን የምናገኛቸው 20 ወይም 21 የተለያዩ ስጦታዎች የመንፈሳዊ ስጦታዎችን ዝርዝር በሙሉ ያካተቱ ለመሆናቸው ምንም ማስረጃ የለንም። ይልቅ መንፈስ ቅዱስ ለሚሰጣቸው ስጦታዎች ምሳሌ አድርጐ መረዳቱ የተሻለ ነው።  በሁለተኛ ደረጃ፣ በ1ኛ ቆሮ. 12፡28 ከተሰጠው በተጻራሪ ስየና ር. 12፡4-1 የተዘረዘሩት መንፈሳዊ ስጦታዎች ቅደም ተከተላ በአስፈላጊነታቸው አኳያ ለመሆኑ

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡4-11 ) Read More »

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡1-3)

ጥያቄ፡ ሀ) በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ላይ ባለው የግንዛቤ ልነታት ምክንያት በኢትዮጵያ በሚገኙ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት መካከል የተፈጠሩትን ችግሮች ግላጽ። ለ) ክርስቲያኖች በልዩነት የሚከራከሩበት ቁላው ጉዳይ ምንድን ነው?  «ምነው እንደ እዲስ ኪዳን ቤተ ከርስቲያን ስሆንን ኖሮ! መንፈሳዊ እንሆን ነበር፥ እግዚአብሔርም በአስደናቂ መንገዶች በመካከላችን ሰውራ ነበር። እንደ አዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን እንድንህን መወለላ ያስፈልገናል»። እንደዚህ ዓይነት አባባሎች ሰምተህ ታውቃለህን? ክርስቲያኖች በተለይ ደግሞ ከካሪዝማቲክ ወገን የሆኑት እንደዚህ ሲናገሩ መስማት የተለመደ ነው። ፍላጐታቸው፥ ሕልማቸውና ዓላማቸው ሁሉ እንደ አዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን መሆን ነው። ይህንን ሊሉ የክርስቲያኖች የጠበቀ እንኙነትና ኅብረት+ የመንፈስ ቅዱስን በሙላት መገለጥና የአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን መለያ የሆነው ተአምራት መደረጉን መናገራቸው ነው። እነዚህ ሁላችንም በጽኑ ልንፈልጋቸው የሚገቡ መልካም ምኞቶች ናቸው። ነገር ግን የአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን የምናስባትን ያህል ንጹሕ ነበረችን?  በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በቤተ ክርስቲያን ምሥረታ የመጀመሪያዎቹን ወቅቶች ስንመለክት አስደናቂ የሆነው የእግዚአብሔር ኃይል የተገለጠበትን ሁኔታ እናያለን። ቢሆንም ስለ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያዎቹ ሠላሳ ዓመታት ዕድሜ የተጻፉትን የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍና ሌሎች መልእክቶች በጥንቃቄ ብናጠና ነገርች እንደምናስበው መልካም እንዳልነበሩ እናያለን። ዛሬ ሰብዙዎቻችን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ እንደሚሆነው ግብዝነት ነበር (ለምሳሌ፡- ሐናንያና ሰጲራ) [ሐዋ. 5]። በብሐር ልዩነቶች ምክንያት መከፋፈሉች ነበሩ። (ለምሳሌ ቀሪክ አይሁዳውያን ተገቢውን የምግብ እርዳታ ድርሻ እንዳላገኙ ያስቡ ነበር [የሐዋ. 6])። ክርስቲያኖች ነን የሚሉ ቀን ለግል ጥቅማቸው ሲሉ የሚያስመስሉ ሰዎች ነበሩ (ለምሳሌ ጠንቋዩ ስምዖን [የሐዋ. 8]። የሥነ ሦግባር ጉድለት ነበር (ለምሳሌ በ1ኛ ቆሮ. 7 የተጠቀሰው ሰው)። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመከፋፈል ነበር (ለምሳሌ በቆርንቶስ ያሉ ክርስቲያኖች [ኛ ቆሮ. 11፥ (ኤድያንና ሌንጠኪን [ፊልጵ. 42። የመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ክርስቲያኖች እንደማንኛችንም ዓይነት ነበሩ እንጂ ጨርሶ የተለዩ አልነበሩም። እንደ እኛው ችግር ነበረባቸው። በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እንደ እኛው ማደግ የሚሹ ነበሩ።  የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ትግል ታደርግባቸው ከነበረችባቸው ነገሮች አንዱ የመንፈሳዊ ስጦታዎች ጉዳይ ነበር። መንፈሳዊ ስጦታዎች በተለይ ደግሞ በልሳናት የመናገር ስጦታ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላለው ድርሻ በነበረው የአሳብ ልዩነት መከፋፈል ነበር። አንዳንድ ክርስቲያኖች አንድ ሰው በመንፈስ ቅዱስ ላመሞላቱና መንፈሳዊ ለመሆኑ ዋናው ምልክት በልሳናት መናገር ነው ብለው ሲያስተምሩ የነበሩ ይመስላል። ሌሎች ደግሞ ከቁጥጥር ውጭ የሆነን በልሳናት መናገር በመቃወም አበክረው እንዲቆም ይፈልጉ ነበር። በአምልኮ ጊዜያት የተሳሳተ የልሳን አጠቃቀም ስለነበር የአምልኮ ፕሮራም አገልግሎቶች ረብሻ የሞላባቸውና እግዚአብሔርን የማያስከበሩ ነበሩ። በዚህ ያለመግባባት መካከል በቆሮንቶስ የሚገኙ ክርስቲያኖች በልሳናት የሚናገሩትን ምን ማድረግ እንዳለባቸው ምክር ለመጠየቅ ላጳውሎስ ጻፉለት። በልሳናት በመናገር ላይ የሚያተኩረው ይህ ክፍል በመንፈሳዊ ስጦታዎች ላይ በአዲስ ኪዳን ከተሰጡት ትምህርቶች ሁሉ በላቀ ሁኔታ ጥልቀት ያለው ነው።  ጥያቄ፡- ሀ) በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን የነበረው ሁኔታ ዛሬ በብዙ አብያተ ክርስቲያናት ካለው ሁኔታ ጋር የሚመሳሰለው ወይም የሚለያየው እንዴት እንደሆነ ለማሳየት አወዳድር። ላ) ዛሬ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ግልጽ የሆነ ግንዛቤ መኖሩ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?  ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚናገሩትን የመጀመሪያዎቹን ሦስት ክፍሎች ባጠናንበት ወቅት የትምህርቱ አትኩሮት መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለመግለጽ ከመሆኑ ይልቅ ስጦታዎች በክርስቶስ አካል ውስጥ ሊያመጡ የሚገባቸውን አንድነት ማሳየት ነበር። ጸሐፊዎቹ ለክርስቲያኖች አበክረው ለማሳየት የፈለጓቸው ሁለት እውነተች ነበሩ። የመጀመሪያው መንፈሳዊ ስጦታዎችን አጠቃልሎ የያዘ ማንም ስለሌለና እያንዳንዱ ክርስቲያን ስጦታዎች ስላሉት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎች በሙሉ አስፈላጊዎችና ጠቃሚዎች ናቸው የሚል ነው። የክርስቶስ አካል ጤነኛ ይሆን ዘንድ ክርስቲያኖች ሁሉ ስጦታዎቻቸውን በመጠቀም በአንድ ላይ መንቀሳቀስና መሥራት አለባቸው። በሁለተኛ ደረጃ ጸሐፊዎቹ ሊያስተምሩን የፈለጉት ነገር ተፈላጊው ስጦታዎቻችንን መጠቀሙ ብቻ ሳይሆን ስንጠቀምበት የሚኖረን ዝንባሌ መሆኑን ነው። ዝንባሌያችን ትክክል ካልሆነ ለጦታዎቻችን አንድነትን የሚገነቡ ከመሆን ይልቅ የጥፋት መሣሪያ ይሆናሉ።  በዚህ ክፍል ለለ መንፈሳዊ ስጦታዎች በዋናነት የሚያስተምረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል 1ኛ ቆሮ. 12-3 እናጠናለን። ጳውሎላ ለለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ያሉትን እውነቶች በሙሉ ሊያስረጻን የፈለገ ሳይሆን ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ዓላማ፥ በመንፈሳዊ ስጦታዎችን የምንጠቀምባቸው ትክክለኛ ዝንባሌዎችና ከመንፈሳዊ ስጦታዎች አንዳንዶቹን በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዴት እንደምንጠቀምባቸው በርካታ ነገሮችን ለመማር እንችላለን።  ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮ. 12-14 በፍጥነት አንብብ። ጳውሎስ በዚህ ስፍራ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሰጠውን ትምህርት በእንድ ገጽ አሳጥረህ ጻፍ።  የ1ኛ ቆሮንቶስ 12-14 መሠረተ አሳብ  የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ጳውሎስ እራሱ የ1ኛ ቆሮንቶስ መልእክቱን ከመጻፉ አምስት ዓመታት በፊት የመሠረታት ነበረች። ቤተ ክርስቲያኗ በጳውሎስ፥ በአጵሎስና በሌሎች ስጦታ ባላቸው ሰዎች አገልግሎት ያደገች ነበረች፡ ነገር ግን በግልጽ ባልታወቀ ምክንያት የሐሰት ትምህርት ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሰርጐ መግባት ጀመረ። የተለያዩ ትምህርቶች በቤተ ክርስቲያኒቱ ሲስፋፉ ቤተ ክርስቲያኒቱ መከፋፈል ጀመረች። ከፊሉ ሰው አንድን ነገር ሲያምን ሌላው ደግሞ ሌላ ነገር ያምን ጀመረ። በ1ኛ ቆሮ. 1-6 ጳውሎስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መከፋፈል እንደፈጠሩ ስሰማቸው ጉዳዮች ላይ በቀጥታ እንደጻፈ እንመለከታለን። ቀጥሎ በ1ኛ ቆሮ. 1-5 ጳውሎስ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በጠየቋቸው ጥያቄዎች ላይ ሲጽፍ እንመለከታለን።  ጳውሎስ መከፋፈል የፈጠሩትን የተለያዩ ነገሮች በማንሣት በዝርዝር ከመጻፍ ይልቅ ምክሩ ያተኮረው ዘመርሆዎች ላይ ነበር። ብዙ ጊዜ መልሱን በሁለት መልክ ይሰጣል። በመጀመሪያ ስለ ክርስትና ነት ክርስቲያኖችን ያሳስባቸዋል። ሕይወታችንን ሰው ሰራሽ በሆኑ ሕጐች መምራት የለብንም። ይልቁኑ መንፈስ ቅዱስ ለእያንዳንዱ ክርስቲያን በሕይወቱ ያስተማረውን ለማመንና ለመተግበር የሚችልበትን ፃነት መጠበቅ አለብን። ክርስቲያኖች ቅዱሳት መጻሕፍት በግልጽ ለሚያስተምሩት ትምህርት ተገዝተው እለከኖሩ ድረስ ሌሎች ዝርዝር የሕይወት ጉዳዮቻቸውን የሚመሩበት መንገድ የራሳቸው መብት ስለሆነ በዚህ ሌሎች ሊቆጣጠሩአቸው አይገባቸውም። በሁለተኛ ደረጃ የሚያሳስባቸው በክርስቶስ አካል ውስጥ ስላለ የእርስ በርስ ኃላፊነት ነው። ተገቢ የሆነ ዝንባሌ በተለይ አንዱ ለሌላው ማሳየት የሚገባው ፍቅር ልናደርጋቸው ከተፈቀዱልን ነገሮች ሁሉ የበለጠ አስፈላጊ ነው። ሊደረ ያልተከለከላ ማንኛውም ነገር በተሳሳተ ዝንባሌ እስከተደረገ ድረስ ኃጢአት ነው።  1ኛ ቆሮ. 12-14 የሰፋ ትምህርት አንዱ ክፍል ነው። ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮ. 11-5 በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከሚደረግ የአምልኮ ስብሰባ ጋር የተያያዙ የተለያዩ ነገሮችን ያስተምረናል። በመጀመሪያ፥ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ክርስቲያን እህቶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያገኙትን አዲስ የአምልኮ ነነት ያላ አግባብ እየተጠቀሙበት ስለ ነበር ሳይሆን አይቀርም ጳውሎስ በአምልኮ ለብሰባ ውስጥ የሴቶች ድርሻ ምን እንደሆነ ያስተምራል (1ኛ ቆሮ. 1-1-16)። ሁለተኛ፥ የጌታ እራት ሥርዓትን አላአግባብ በመጠቀም ጉዳይ ትምህርት ይሰጣል (1ኛ ቆሮ. 11፡7-34)። ሦስተኛ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በመረዳትና በመጠቀም ስለሚታዩት አግባብ ያልሆኑ ነገሮች በተለይ ደግሞ የአምልኮ ስብሰባዎችን እያወኩ ስለነበሩት እንደ ልሳን ስጦታ ስላሉትም አስተምሯል (1ኛ ቆሮ. 12-14)። በመጨረሻ፥ እሑድ እሑድ የሚሰበከው ወንጌል በተላይ ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት የመነሣቱና ይህም ከትንሣኤ ተስፋችን ጋር እንዴት እንደሚያያዝ የሚገልጸው እውነት ያላመበረዙን ማረጋገጥ ፈልጐ ነበር (1ኛ ቆሮ. 15)።  በ1ኛ ቆሮ. 12-14 ድረስ ጳውሎስ ሰላ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚችለውን በሙሉ እንዳላስተማረ መረዳት እጅግ ጠቃሚ ነው። ለምሳሌ፥ ጳውሎስ የዘረዘራቸው አብዛኛዎቹ መንፈሳዊ ስጦታዎች ስለ እዚያ ስጦታዎች በትክክል ምን ማለቱ እንደሆነ በምናውቃቸው መንገዶች የተገለጹ እይደሉም። እያንዳንዱ የመንፈሳዊ ስጦታዎች መዘርዝር በቅደም ተከተሉም ሆነ ባካተታቸው ስጦታዎች ምንነት የተለያየ ነው። ስለዚህ ጳውሎስ ለቤተ ከርስቲያን ያሉትን ስጦታዎች በሙሉ ስለመጥቀሱ እንኳን ማረጋገጫ የለም። ለቤተ ክርስቲያን ሌሎችም ይኖራሉ በማለት ነው። ጳውሎስ መንፈሳዊ ስጦታዎችን የፈረጃቸው በተግባራቸውና በአስፈላጊነታቸው አንጻር ሳይሆን ያለ ምንም ልዩነት ነው የዘረዘራቸው። ይህ የሆነበት ምክንያት ጳውሎስ በሮማ መጽሐፍ ወንጌልን በዓል ያስቀመጠውን ያህል ለለ መንፈሳዊ ስጦታዎች የተሟላ ትምህርትን ባለ መስጠቱ ነው። ከዚህ ይልቅ የጳውሎስ ዓላማ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ለተፈጠሩት ችግሮች ምክንያት የሆኑ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በሚመለከቱ አንዳንድ እውነቶች ላይ ትኩረት መስጠት ነበር። የጳውሎስ ትምህርት ትኩረት መንፈሳዊ ስጦታዎቻችን ምን እንደሆኑ እንድናውቅ ሳይሆን እግዚአብሔርን በመፍራት እግዚአብሔር ያስቻለንን ሁሉ በማድረግ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ እንድንሳተፍ ለማበረታታት ነው። በትሕትና እየተመላለስን እግዚአብሔርንና የክርስቶስ አካል የሆነችውን

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡1-3) Read More »

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ጴጥሮስ 4፡7-11 )

ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ስንነጋገር ልናስታውሳቸው ከሚገቡን እጅግ ጠቃሚ ነገሮች አንዱ ለግለሰቦች ብቻ የታቀዱ ያለመሆናቸውን ነው። መንፈሳዊ ስጦታዎች በመንፈስ ቅዱስ የተሰጡት ለዓላማ ነው። ለታላቅ ዓላማ ማላትም የክርስቶስን አካል ለመገንባት የተሰጡን መሣሪያዎች ናቸው። መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለሌሎች አገልግሎት ላይ የሚውሉት እንዴት እንደሆነ ከማሰብ ይልቅ በስጦታነታቸው ላይ ስናተኩር ችግሮች መፈጠር ይጀምራሉ። መንፈሳዊ ትዕቢት ተሽሎክልኮ ይገባል። ቅናቶች ይነሣሉ። መከፋፈል ይመጣል። በአዲስ ኪዳን ስጦታዎች በተጠቀሱባቸው ስፍራዎች – ሁሉ የተገላጺት ሌሎችን በማገልገል መንፈስ ነው። ለእኛ ሊያደርጉልን ስለሚችሉት ነገር በሚናገር መልኩ የተጠቀሱበት ቦታ ፈጽሞ የለም። የአዲስ ኪዳን ደራሲ በሆነው በመንፈስ ቅዱስ በተደጋጋሚ የሚነገረን ለጦታዎቻችንን የምንጠቀምበት ዝንባሌ ስጦታዎቹን ራሳቸውን ከመለማመድ በላቀ ሁኔታ ተፈላጊ ስለመሆኑ ነው። ተራርችን ከስፍራቸው ከሚያንቀሳቅላና ተአምራትን ከሚያደርግ እምነት ይልቅ ፍቅር ይበልጣል። ሰጦታዩን እኔ በምፈልገው መንገድ ለመጠቀም ካለኝ ችሎታ ይልቅ አንድነት ይበልጣል። ላእግዚአብሔር ክብርን ማምጣት የሁሉም ተቀዳሚ ዓላማ ስለሆነ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች በምንነጋገርበት ወቅት ዋናው አትኩሮት የሚሰጥበት ጉዳይ የእዚአብሔር ክብር መሆን አለበት። በእያንዳንዱ ስጦታ ምንነትና በቤተ ክርስቲያን እንዴት እንደምንጠቀምበት በዝርዝር እንመለክት ልንለያይ ብንችልም ጸሎቴ እነዚህን መመሪያዎች እንዳንዘነጋ ነው።  ጥያቄ፡- ሀ) መንፈሳዊ ስጦታን በተሳሳተ መንገድ መጠቀም እንዳት እንደሚሠራ ወይም በምን ዝንባሌ እንደሚሠራ) ለእዚአብሐር ክብርን መንፈጉን ያየህበትን ሁኔታ ቀላጽ። ለ) ከላይ የተመለከትናቸው መመሪያዎች በዚህ ሁኔታ ለእግዚአብሔር ክብርን በሚመጣ መንገድ መንፈሳዊ ላጦታዎችን መጠቀሙ እንዴት ሊረዳ ይችል እንደነበር ልጽ።  ጥያቄ፡ 1ኛ ጴጥ 4፡7-11 አንብብ። ሀ) በመንፈሳዊ ስጦታዎች ላይ ውይይት የተካሄደበትን ክፍል ዋና አሳብ አድርገህ ተናዢ። ላ) የታ መምጣት በቀረበ ቁጥር ባሕርያችን ምን መሆን እንዳለበት የሰላም የተለያዩ ነገሮችን ዘርዝር። ሐ) መንፈሳዊ ስጦታ ያለው ሰው ሁሉ በመንፈሳዊ ስጦታው ምን ማድረሳ አለበት? ) ቀደም ሲል በጀመርከው ሠንጠረዥ ላይ የተጠቀሱትን የተለያዩ ስጦታዎች በመዘርዘር ስለ እያንዳንዱ ስጦታ ገለጻ ስጥ። ሠ) ከእያንዳንዱ ስጦታ ጋር አብሮ መሄድ ያለበት አመለካከት ምንድን ነው? ረ) ስጦታችንን በሚገባ መጠቀም የዘለቄታ ዓላማ ምንድን ነው? ሰ) ከዚህ ክፍል ስለ መንፈሳዩ ስጦታዎች እና ላላ አጠቃቀማቸው የተጠቀሱ መመሪያዎችን ዘርዝር።  የ1ኛ ጴጥ. 4፡7-11 መሠረተ አሳብ (ዳራ)  ጴጥሮስ በትንሹ እላያ ለተበተኑት ክርስቲያኖች ሲጽፍ እዚኦብሔርን በሚያከብር መንገድ እንዲኖሩ ሊያበረታታቸው ፈለገ፡ ክርስቲያኖች ሰማያምኑ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰደዱ ነበር። ከዚህ ለደታ ለገላዋ ሲሉ እንደ ዓላማውያን ለመኖር እስኪፈተኑ ይደርሱ ነበር። ሆኖም ቀን ጴጥሮስ ክርስቲያኖች የተለዩ መሆናቸውን ያሳለባቸዋል። የእግዚአብሔር ስለሆኑ እግዚአብሔርን በመታተዝ መኖር አለባቸው። የዘመን ፍጻ እንደደረሰና ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሶ የሚመጣበት ጊዜ በደች እንደሆነ አበክሮ ነገራቸው። ኢየሱስ የሚመላለበትን ጊዜ በትዕሥት ሲጠባበቁ በጥንቃቄ እርሱን በሚያስከብር መንገድ መኖር ነበረባቸው፡ ኢየሱስን ክበር ምን ምንን ይዉምራል? ጴጥሮስ በምናጠናው በዚህ ክፍል እንዳንዶቹን ይገልጻል።  1ኛ ጴጥሮስ 4፡7-9  ክርስቲያኖች ብዙ ጊዜ ስደት የሚደርስባቸው አናሳ የኅብረተሰብ ክፍሎች ስለሆኑ በቤተ ክርስቲያን ላይ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ብዙ ተጽዕኖዎች ይመጣሉ። ከውጭ ላደት ከውስጥ ደግሞ የሐሰት ትምህርቶችና መከፋፈል ይከሰታሉ። ቤተ ክርስቲያን በዚህ ሁሉ ውስጥ ማለፍ እንዴት ትችላለች? ጴጥሮስ ክርስቲያኖች ሁልጊዜ ሊኖራቸው ስለሚገባ ሦስት አመለካከቶች ይናገራል።  1. በመጀመሪያ ንጹሕ አእምሮ ያላቸውና የሚዝ መሆን ይገባቸዋል። ቤተ ክርስቲያን ያለችበትን ሁኔታ እንዳላወቀ ወይም 1ድ እንደ ሌለው ከመሆን ይልቅ ከርስቲያኖች ልጽ አስተሳሰብ ሊኖራቸው እንደሚገባ ይናገራል። የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ ዕቅድና የኢየሱስን መመለስ መርሳት የለባቸውም። የሚያጋጥሙአቸውን የተለያዩ ትምህርቶችና ችግሮች በጥንቃቄ በመመርመር እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ መንገድ እንዴት ማስተናገድ እንዳላባቸው ማሰብ አለባቸው። በመንፈስ ቅዱስና በእግዚአብሔር ቃል ሥልጣን ሥር በመኖር እእምሮአቸውንዝንባሌያቸውንና ተግባራቸውን መቆጣጠር ነበረባቸው። ይህ ሁሉ እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ መንገድ ይጸልዩ ዘንድ እንዲረዳቸው ነበር።  2. እርስ በርስ በመዋደድ ላይ ማተኮር ነበረባቸው። አንድ ክርስቲያን ሌላውን ክርስቲያን ሊጐዳ የሚችል ነገር የሚያደርግባቸው ጊዜያት እንደሚኖሩ ጥርስ ያውቅ ነበር። በዚህ ጊዜ የሚሆነው ተፈጥሮአዊ ዝንባሌ ያለ እባብ መፍረድና ለመበቀል መሞከር ነው። ፍቅር ቀን አንድነትን ይጠብቃል። በመካክላቸው የነበረ ኃጢአት ያመጣውን መቆሳሰል ይሸፍንላቸው ነበር።  3. አንዱ ለሌላው መልካም አቀባበልን ማድረግ ነበረበት። ይህ ትእዛዝ በዚህ ሰፍራ መቅረብ ያለበት አይመስልም። መልካም አቀባበል ቀን የፍቅር ተቀጥላ ነው። በጳጥርስ ዘመን አንድ ሰው አማኝ በሚሆንበት ጊዜ በአብዛኛው ሁኔታ ከቤቱ ይባረር ነበር። ሌላ ቤት እስኪያገኝና ኑሮውን እስኪያደራጅ ድረስ ሌላውን ጠለላ ማድረጎ ዴታው ነበር። ባሪያ ወይም እገልጋይ የነበረ ከሆነ ደሞ ለሕይወት የሚያስፈልገውን ነገር በሚያገኝበት ሁኔታ ላይ ወድን መንግድ አጻሪ ይሆን ነበር። ይህ ሁኔታ ሴት በነበራቸው ሰዎች ላይ ተደራራቢ ሸከም ይጨምራል። በመንግሥት ዘንድ በጥርጣሬ ይታዩ የነበሩትን ክርስቲያኖች በማስጠጋት ሕይወታቸውና ቤታቸው የባሰ አደጋ ላይ ይወድቅ ነበር። ቤትና ሥራ ላላቸው ክርስቲያኖች የረመዷቸው፥ የሚያለብሏቸውና ሌሎች እንክብካቤዎች የሚያደርጉላቸውን ሰዎች መጨመር በከፍተኛ የማይመች ነገርን ይፈጥርባቸው ነበር። በርካታ ሃብታም የህኑ ክርስቲያኖች ኑርአቶውንና ቤታቸውን ከአደጋ ለመከላከል ሲሉ የተጣሉትንና የተገፉትን ላለማስጠጋትና ላለመቀበል ይፈተኑ ነበር። ጴጥሮስ ቀን የሚያሳስባቸው አንድነቱ ይቀጥል ዘንድ መልካም የእን አቀባበል ልምድ መቀጠል እንደነበረበት ነው። •ልካም የእንግዳ አቀባበል ደግሞ ማጉተምተም ሳይሆን በትክክለኛ ዝንባሌ ማለትም በደስታ መደረግ ነበረበት።  ጥያቄ፡- ሀ) እነዚህ ሦስት ባሕርያት በቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ የሚያስፈልጉት እንዴት ነው? ላ) በቤተ ክርስቲያንህ በእነዚህ ባሕርያት ሕይወቱ የተመሰከረለትና የምታውቀውን አንድ ሰው በምሳሌነት ጥቀለ። ውጤቱ ምንድን ነው?  1ኛ ጴጥ. 4፡10-11  ጴጥሮለ በስደት ጊዜ ለአንድነት መሠረት ከሚሆኑት ከእነዚህ ባሕርያት መለስ ይልና ይህን አንድነት ጠብቆ ለማቆየት በመርዳት መንፈሳዊ ስጦታዎች ስላላቸው ስፍራ ያውሳል። የሚከተሉትን እውነተች አስተውል፡-  1. እያንዳንዱ ሰው መንፈሳዊ ስጦታዎች አላው። መንፈሳዊ ስጦታዎች ላአንዳንዶች ተሰጥተው ላሌሎች የተከለከሉ አይደሉም።  2. የስጦታው ዓላማ «ሌሎችን ማገልገል» ነው። መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚሰጡበት ተቀዳሚ ዓላማ ለራስ ጥቅም አይደለም። በአገልግሎት ላይ መዋል የሚገባቸው ሌላውን ለማገልገል ነው።  3. እያንዳንዱ ክርስቲያን መንፈሳዊ ስጦታውን የመጠቀም ኃላፊነት አለበት። ሌሎችን ለመገንባት እንዴት እንደሚጠቀም ታማኝ መሆን አለበት። ይህ ማለት ለመጠቀም ቸል ከማለት ወይም በተሳሳተ መንገድ ከመጠቀም መጠበቅ አለበት ማለት ነው። ታማኝ መሆን ማለት መንፈሳዊ ስጦታዎቻችንን ከትክክለኛ ዝንባሌ በመነሣት ለትክክለኛ ዓላማ ልንጠቀምባቸው ይገባል ማለት ነው።  4. መንፈሳዊ ስጦታዎች በእግዚአብሔር ጸጋ የሚሰጡ ናቸው። ለለ መንፈሳዊ ታላቅነታችን ወይም ስላደረግነው ማንኛውም ነገር የሚሰጥ አይደለም። በምንም ነገር ላይ ካልተመሠረተ ልዩ ችርታ የሚመነጭ ህ ስጦታ ነው።  5. መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚመጡት በተለያዩ መልኮች ነው። መንፈሳዊ ስጦታዎች ብዙ ዓይነት እንጂ አንድ ዓይነት እይደሉም። በእርግጥ በአዲስ ኪዳን ከተዘረዘሩ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚኖሩን እንዳንዶች ብቻ ሳይሆኑ አይቀሩም። ክርስቲያኖች በክርስቶስ አካል ውስጥ የሚያደርጓቸው በርካታ ሌሎች ነገሮችም እንደ ስጦታዎች ሊመደቡ ይችላሉ።  ጴጥሮስ ቀጥሎ ለጦታዎች ናቸው ብለን ፈጽሞ የማናስባቸውን ተራና የተላመዱ ሁለት ስጦታዎችን ይጠቅሳል።  1 መናገር፡- ይህ ስጦታ ከሌሎች ስጦታዎች ጋር ተጣምሮ የሚቀርብ ሳይሆን አይቀርም። የነቢይነት የማስተማር፣ የመምከር፡ በልሳናት የመናገርና በልሳናት የተነገሩትን የመተርጐም ስጦታዎች በሙሉ በመናገር ላይ የተመሠረቱ ናቸው።  2 ማገልገል፡- ይህ ስጦታ በሮሜ 12፡7 ላይ የተጠቀሰ ሲሆን ‹ዲያቆን› ከሚለው ጋር አንድ ዓይነት ቃልን ይጠቀማል። የሌሎችን ፍላጐት ለማሟላት የማገልገልን ጉዳይ ያመለክታል። ይህ የክርስቶስን አካል ተግባራዊ በሆኑ መንገዶች የማገልገል ስጦታ ነው።  የጴጥሮስ አትኩሮት አንድ ሰው ለጦታውን መለማመዱ ወይም አላመለማመዱ ላይ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ስጦታውን በሚጠቀምበት ወቅት ባለው ዝንባሌ ላይም ጭምር ነበር። ከላይ በተመለከቱት በሁለቱም ስጦታዎች ጴጥሮስ ክርስቲያኖችን የሚያስታውሰው ስጦታዎቻቸውን ስለ ሚጠቀሙበት መንገድ ነው።  1. የሚናገር ሰው የእግዚአብሔርን ቃል እንደሚናገር ይናገር። ይህ ዐረፍተ ነገር ሁለት ጐኖች አሉት። የመጀመሪያው ጐኑ በድፍረት የመናገር ጉዳይን ያመለክታል። ትክክለኛው ነገር ይህ ይመስለኛል እያሉ በጥርጣሬ መንፈስ ከመናገር እርግጠኛ ሆነን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ለማለት መቻል አለብን። ሌላው ጐኑ ግን የተጠያቂነት ጉዳይ ነው። በቤተ ክርስቲያን የምንናገረው ነገር የራሳችን አስተሳሰብ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቃል ለመሆኑ በእርግጠኛነት እናደርገው ዘንድ የምንናገረው ቃል በእግዚአብሔር ቃል

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ጴጥሮስ 4፡7-11 ) Read More »

መንፈሳዊ ስጦታ (ኤፌሶን 4፡1-16 )

ጥያቄ፡- ሀ) ብዙ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸው ዋና ኃላፊነት ምንድን ነው ብለው ያስባሉ? ለ) መጽሐፍ ቅዱስ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ዋና ኃላፊነት ነው ብሎ የሚያስተምረው ምን ይመስልሃል?  የመሪዎች · ዋና ኃላፊነት ምንድን ነው? ነገሮች ሁሉ በተገቢ ሁኔታ እንዲሄዱ ቤተ ክርስቲያንን ማስተዳደር ነውን? በኃይልና በሥልጣን ሰዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው መንገር ነውን? ሰዎች ምን ማመን እንዳለባቸው ማስተማር ነውን? ለቤተ ክርስቲያን ራእይንና ምሪትን መስጠት ነውን? ለቀሩት የቤተ ክርስቲያን አባላት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሥራዎችን መሥራት ነውን? የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ብዙ ጊዜ የሚያስቡት ዋና ኃላፊነታቸው ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች አንዱ እንደሆነ ነው። ከላይ የተጠቀሱት በሙሉ ከቤተ ክርስቲያን መሪዎች ኃላፊነቶች አንዳንዶቹ ቢሆኑም እንኳ ዋናዎቹ ቀን አይደሉም። በኤፌ. 4፡1-2 የተጠቀሱትን የመሪነት ስጦታዎች ስናጠና ይህ ዋና ኃላፊነት ምን እንደሆነ እንማራለን። –  ጥያቄ፡- ኤፌ. 4፡1-16 አንብብ። ሀ) ጳውሎስ ክርስቲያኖች የሆንን እኛ አሁን እንዴት መመላለስ አለብን ይላል? ለ) የእኛ ባሕርዮች ሆነው ማንም (እኛን ሊለይባቸው የሚችሉ ዝንባሌዎች ምንድን ናቸው? ሐ) በቁ. 3 ላይ የተጠቀሰው የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ምንድን ነው? መ) በዚህ ክፍል «አንድ» ናቸው ተብለው የተጠቀሱ ነገሮችን ዘርዝር። ሠ) በዚህ ክፍል መሠረት ስጦታዎችን የሚሰጠን ማን ነው? ረ) በዚህ ቦታ የተጠቀሱ የአመራር ወይም የመንፈሳዊ ስጦታዎች አምስት አቋሞችን ዘርዝር። ሰ) [በእነዚህ አቋሞች ላሚበረክተው አገልግሎት ዓላማው ምንድን ነው? ሸ) በቁ. 13 ና 15 ላይ የተገለጹት የእነዚህ ስጦታዎች የመጨረሻ ግብ ምንድን ነው? ቀ) እነዚህን መንፈሳዊ ስጦታዎች በተገቢው መንገድ መጠቀም ምእመናንን የምንን ከመምሰል ይጠብቃል? )  ሮሜ 12፡1-8 በትኩረት መንፈሳዊ ስጦታዎችን ከቤተ ክርስቲያን አባላት አቅጣም የሚያይ ሲሆን የክርስቶስ አካል ጠንካራ ይሆን ዘንድ ስጦታዎች ሁሉ እንዴት በአንድነት እንደሚሠሩ ይናገራል። ሆኖም ግን የኤፌ. 4፡1-16 ትኩረት በቤተ ክርስቲያን የመሪነት ላጦታ ላይ ሆኖ የእነዚህ ስጦታዎችን ተገቢ የሆነ አጠቃቀም ወደ ጠቅላላው ቤተ ክርስቲያን ያመጣዋል።  የኤፌ. 4፡1-16 መሠረት አሳብ (ዳራ)  የኤፌሶን መጽሐፍ ትኩረት ኢየሱስ ክርስቶስ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ባለው ግንኙነትና በኢየሱስ ክርስቶስ ከማመናችን የተነሣ ባገኘናቸው በርካታ መንፈሳዊ በረከቶች ላይ ነው። በክርስቶስ ከሆንን የእግዚአብሔር አብ ብልጽግናዎች ሁሉ የእኛ ናቸው። ከእነዚህ ብልጽግናዎች አንዱ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ነው። ነገር ግን በክርስቶስ ከሆንን አኗኗራችን መለወጥ አለበት። ኤፌ. 4-6 የሚነግረን የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንን ምን ዓይነት ሰዎች መሆን እንዳለብን ነው።  ኤፌ. 4፡1-6  ኤፌ. 4፡1-6 ልናጠና የሚከተሉት እውነቶች በትምህርት መልክ ተሰጥተው እናያለን።  1 ኤፌ. 4፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ላለው ትምህርት መሠረት ነው። የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንንና በእግዚአብሔር ክተባረክን መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን የሚኖር ከሆነ ሕይወታችን መቀየር ያለበት እንዴት ነው? ጳውሎስ የሚናገረው ለተጠራንበት መጠራት የሚገባ ክብር ያለው ኑሮ እንድንኖር ነው። ይህንን እንዴት እናደርጋለን? በተለይ ደግሞ በክርስቶስ አካል በሆኑት መካከል የተለወጥንና የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ እንደሆንን የሚያረጋግጥ ሕይወት እንዴት እንኖራለን? ጳውሎስ አስደናቂ በሚባሉ እንደ ተአምራትና ስልሳናት መናገር ላይ ትኩረት አላደረገም። እነዚህ አስፈላጊ ቢሆኑም እንኳ ሕይወታችንን በሚገባው መንገድ እየኖርን መሆናችንን አያረጋግጡም። ጳውሎስ በቀረው የኤፌሶን ክፍል የሚናገረው ለወንጌል የሚገባ ሕይወት እንዴት መኖር እንዳለብን ነው።  2. ብዙ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለወንጌል የሚገባ ሕይወት መኖር ማለት በተቀዳሚ ሰዎች በሚሠሩት ውጫዊ ተግባራት ላይ ያተኮረ እንደሆነ ያስተምራሉ። ለምሳሌ አንድ ሰው በኢየሱስ ባመነበት ቅጽበት እንዳይጠጣ፥ እንዳያጨስ፥ እንዳያመነዝር፥ ከአንድ በላይ ሚስቶች ካሉት ከአንዱ በስተቀር ሌሎችን እንዲተው ወዘተ… ይነገረዋል። እነዚህ አስፈላጊ ቢሆኑም እንኳ ጳውሎስ ሁልጊዜ የሚያስተምረው ለወንጌል የሚገባ ሕይወት መኖር የሚጀመረው ተገቢ የሆነ የተስተካከለ አቋም ወይም ባሕርይ በመያዝ መሆኑን ነው። በኤፌ. 4፡2-3 ጳውሎስ የሚያስተምረን በተገቢ ሁኔታ መኖር ከልብ እንደሚጀምር ነው። ትህትናን፥ ጨዋነትን፥ ትዕግሥትንና ፍቅርን ይጨምራል። በሌላ አባባል እንደ እግዚአብሔር ልጆች ለአዲሱ አቋማችን ተገቢ የሆነን ኑሮ መኖር ማለት የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ በሕይወታችን አለ ማለት ነው (ገላ. 5፡ 22-23 ተመልከት)።  መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን የሚያፈራቸው ውስጣዊ ባሕርይዎች ለሌሎች የሚረጋገጡበት ተቀዳሚ መንገድ ምንድን ነው? ከእዚህ ዋና  መንገዶች አንዱ በክርስቶስ አካል ውስጥ የሚፈጠረው «አንድነት ነው። ይህ አንድነት መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን የሚሠራው ሥራ ቀጥተኛ ውጤት ነው። ጳውሎላ አንድ እንደሆኑ የገለጣቸውን ሰባት የተለያዩ ነገሮች አስተውል።  አንድ አካል፡- ይህ ጳውሎስ እንድነት ይኖር ዘንድ ፍላጐቱ የነበረበት የክርስቶስ አካል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የተላያዩ የእምነት ክፍሎች (ዲኖሚኔሽኖች) መኖራቸውን የሚከለክል ባይሆንም እንኳ በእግዚአብሔር አእምሮ ያለችው አንድ የክርስቶስ አካል የሆነች ቤተ ክርስቲያን ናት። በመንግሥተ ሰማያት ቃለ ሕይወት፥ ሙሉ ወንጌል፥ መካነ ኢየሱስ ወዘተ… የሚባሉ አብያተ ክርስቲያናት አይኖሩም። የክርስቶስ ኢየሱስ አካል ብቻ ናት የምትኖረው።  አንድ መንፈስ፡- ይህ በእያንዳንዳችን ሕይወት ለመኖር የመጣው መንፈስ ቅዱስ ነው። ቤተ ክርስቲያን በተባለች አንድ አካል ውስጥ የሚጨምረን መንፈስ ቅዱስ ነው።  አንድ ተስፋ፡- የእግዚአብሔር ልጆች ስለሆንን በምንሞትበት ጊዜ ሁላችንም ወደ እንድ ሥፍራ ወደ መንግሥተ ሰማያት የመሄዳችን ተስፋ ነው። ክርስቲያኖች በሚሞቱበት ጊዜ የሚሄዱበት የተለያዩ ስፍራዎች የሉም። በምድር ላይ የየትኛይቱም ቤተ ክርስቲያን አካል ቢሆኑም እውነተኛ ክርስቲያኖች ሁሉ ወደዱም ጠሉ የሚሄዱት ወደ አንድ ስፍራ ነው። ይህ ተስፋ እውነት የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ለእኛ ባደረገው ሥራ ምክንያት ነው።  አንድ ጌታ፡- ልናመልከውና ልናከብረው የሚገባው አንድ ጌታ ለእርሱ እራሳችንን በማስገዛት ልንኖርለት የሚገባን እርሱ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።  አንድ እምነት፡- ይህ ሁለት ነገሮችን ሊያመለክት ይችላል። ሁላችንም የጻንንበት ብቸኛ መንገድ ማለትም በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለንን እምነት ሊያመለክት ይችላል። ወይም እንድንበት ዘንድ ሁላችንም ልናምነው የሚገባንን አንዱን ወንጌል ሊያመለክት ይችላል።  አንድ ጥምቀት፡- አንዳንዶች ይህ የሚያመለክተው የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን ነው ብለው ቢያስቡም እንኳ የኤፌሶን ክርስቲያኖች ሁሉ ባመኑበት ጊዜ የተላማመዱት የውኃ ጥምቀት ሳይሆን አይቀርም።  አንድ እግዚአብሔር፡- የሁላችንም አባት እግዚአብሔር የነገሮች ሁሉ ዋና ምንጭ ነው። አሕዛብ እንደሚያስተምሩት ብዙ አማልክት የሉንም። እንድ አምላክ ብቻ አለ።  ** ጳውሎስ ሥላሴን የአንድነትና የብዛት ምሳሌ አድርጐ እንዴት እንዴጠቀሰ ልብ በል። ሦስቱንም በተናጠል ቢጠቅሳቸውም ቀን ሁሉም በአንድነት እንደሚሠሩና እርስ በርስ እንደማይለያዩ ግልጽ በሚያደርግ ሁኔታ ነው።  ኤፌሶን 4፡7-11  በኤፌ 47-16 ጳውሎስ በክርስቶስ አካል ውስጥ ያለው አንድነት እንዴት እንደሚጠናከር መለስ ብሎ ይናገራል። በዚህ ስፍራ ጳውሎስ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ይናገራል። ጳውሎስ ላማሳየት የፈለገው አንድነት ሊኖር የሚችለው በልዩነት ውስጥ መሆኑን ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ለሁሉም አንድ ስጦታን አይሰጥም። የተለያዩ ስጦታዎችን ለእያንዳንዱ ሰው ይሰጣል። አንድነትና ጥንካሬ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይኖሩ ዘንድ ከተፈለገ ልዩነቶችም መኖር አለባቸው። እንደ ክርስቲያን በሰዎች ሰብዕናና መንፈሳዊ ስጦታዎች መካከል ያሉት ልዩነቶች ለመከፋፈል ሳይfን ለአንድነት ምክንያት እንዲሆኑን እንዴት እንደምንጠቀምባቸው መማር አለብን። ጳውሎላ በኤፌ. 47 ላይ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች የጠቀሳቸውን ቀጥሉ የተዘረዘሩትን መግቢያ ነገሮች አስተውል።  1 የተሰጠው ለእያንዳንዱ ነው። በዚህ ስፍራ እንደገና የምንመለከተው ነገር በክርስቶስ አካል እያንዳንዱ ሰው ቢያንስ አንድ መንፈሳዊ ስጦታ እንዳለው ነው። ኢየሱስ ለእካሉ ማላትም ለቤተ ክርስቲያን ለመስጠት የሚሻው ስጦታዎች ሁሉ እንዲኖሩን እንዳችን ሌላችንን ስለምንፈልግ ይህን እንድነት እንዲያሳድግ የታለመ ነው።  2. የተሰጠን በጸጋ ነው። ሠርተን ወይም ለፍተን የምናገኘው አይደለም። ለደኅንነታችን ነፃ የጸጋ ስጦታ እንደሆነ ሁሉ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታም ነፃ ስጦታ ነው (ኤፌ. 2፡8ን ተመልከት)።  3 በክርስቶስ የተሰጠን ነው። ሌሎች ክፍሎች መንፈሳዊ ስጦታዎችን የሚሰጠው መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ቢናገሩም ጳውሎስ ግን እዚህ ላይ የሚጠቅሰው ክርስቶስን ነው። ይህ የሚያመለክተው በቤተ ክርስቲያን ሥራ ውስጥ መንፈስ ቅዱስና ኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸውን የቅርብ ግንኙነት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችን በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት መንፈሳዊ ስጦታዎችን ይሰጠናል።  4 ማን የትኛውን ስጦታ እንደሚያገኝ የሚወለን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እንደፈለገው የሚያከፋፍል እርሱ ነው። የስጦታዎች ድልድል ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ አላመሆኑ በአካሉ ውስጥ ምንም ዓይነት የቅናትና የትዕቢት

መንፈሳዊ ስጦታ (ኤፌሶን 4፡1-16 ) Read More »