ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

አሕዛብ በታሪክና በትንቢት

This entry is part 42 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. አሕዛብ በእግዚአብሔር ዕቅድ  መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በታሪክና በትንቢት መሠረት ሦስት ዓበይት የሰው ልጆች ከፍሉችን ለማጤን ይቻላል። 1ኛ ቆሮንቶስ 10፡32 ውስጥ በተመለከተው መሠረት የእግዚአብሔር ዓላማ ከአይሁዶች፥ ከአሕዛብና ከቤተ ክርስቲያን ጋር የሚገናኝ መሆኑ ተመልክቷል። ከዚህ ጋር የሰብአዊ ታሪክ ወይም ትንቢት ዓቢይ እካል ሆኖ የማይቆጠረው ለመላእክትና በነሱ በኩል የሚደረገው የእግዚአብሔር አገልግሎት ሊታከል ይችላል።  እግዚአብሔር እስራኤልን የመለኮት መገለጫ፥ የክርስቶስ መምጫ ልዩ መንገድ ከማድረጉና የጸጋው መግለጫ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን ካለው ዓላማ ጋር ሲነጻጸር፥ ለአሕዛብ ያለው ዓላማ ክብሩንና ሁሉን ቻይነቱን ካመግለጥ ጋር የተዛመደ ነው።  ለ. አሕዛብን የሚመለከቱ ቀደምት ትንቢቶች  በአንድ በኩል፥ ለአሕዛብ ትንቢት የተጀመረው ኤደን ገነት ውስጥ ነው። የዚህ ምክንያቱ በተወሰነ ደረጃ አሕዛብ የእግዚአብሔር የድነት ዓላማ ተካፋዮች በመሆናቸው ነው። በዘፍጥረት መጽሐፍ መጀመሪያ ላይ በኖኅ ዘመን ከርሱና ከቤተሰቡ በስተቀር የሰውን ዘር ጠራርጎ ስላጠፋው የጥፋት ውኃ ትንቢት ተነግሯል። በተመሳሳይ ሁኔታ፥ ሰባቢሎን ግንብ ጊዜ እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ያወረደው ፍርድ ታሪክም ተመዝግቧል (ዘፍጥ. 11፡1-9)። ከዘፍጥረት ምዕራፍ 12 ጀምሮ ግን የሰው ዘር በሁለት ምድቦች ተከፍሏል። ይኽውም ከአብርሃም፥ ከይስሐቅና ከያዕቆብ የሚመጣውን የተስፋ ቃል ዘር እግዚአብሔር መግለጥ መጀመሩ ነው። ሌሎቹ ሁሉ በአሕዛብነታቸው ቀጠሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ያደረጋቸው መሠረታዊ ነገሮች ሁሉ ከእስራኤል ጋር በተያያዘ መልኩ ነው።  የመጀመሪያዋ ታላቅ የአሕዛብ መንግሥት ሆና የምትታወቀው ግብፅ ናት። በመጀመሪያዎቹ አምስት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ እንደተመዘገበው፥ እስራኤላውያን ከትንሽ ቤተሰብነት ወደ ትልቅ ሕዝብነት ያደጉት ግብፅ ውስጥ ነበር። በዳዊትና ሰለሞን ዘመን እስራኤላውያን ታላቅ ሕዝብ ለመሆን ቢበቁም፥ በ721 ዓ.ዓ. አሥሩ ነገዶች ሁለተኛይቱ ኃያል የአሕዛብ መንግሥት በነበረችው በአሦር ተማርከዋል። በአሦራውያን አማካይነት በእስራኤል ላይ የደረሰው የእግዚእብሔር ፍርድ ቀደም ብሎ የተተነበየ ሲሆን፥ እንደተሳለው በትክክል ተፈጽሟል።  ይህም ሆኖ፥ ከእስራኤል ጋር በተያያዘ ሁኔታ የአሕዛብ ዓቢይ ሚና የተጀመረው በባቢሎን መንግሥት ነበር። ባቢሎን ሦስተኛዋ ኃያል የአሕዛብ መንግሥት ስትሆን፥ በዳንኤል ትንቢቶች ውስጥ ከሚገኙት አራት መንግሥታት ግን የመጀመሪያዋ ናት።  ሐ. የአሕዛብ ዘመናት  ከሦስቱ የእግዚእብሔር ዕቅዶች ሁለቱ ለነብዩ ዳንኤል ተገልጠውለታል። እነሱም እግዚአብሔር ለእስራኤልና ለአሕዛብ ያሉት ዕቅዶች ናቸው። ዳንኤል ምዕራፍ 2 ውስጥ እንደተገለጠው ናቡከደነፆር በተመለከተው ሕልም ተጀምሮ ለዳንኤል በታዩት ራእዮች በቀጠለው ተከታታይ መልኮታዊ መገለጥ፥ ከባቢሎን ጀምሮ እራት ኃያላን የአሕዛብ መንግሥታት እስራኤልን እንደሚገዙ እግዚአብሔር ገልጧል። ይህም ዳንኤል ምዕራፍ ሁለት ውስጥ በታየው ታላቅ ምስል ውስጥ ተገልጧል፤ የወርቁ ራስ ባቢሎንን፥ ከላይ ብር የሆነው ሜዶንና ፋርስን፥ የታችኛው የነሐስ ገጽታ ግሪከን፥ እና ብረት የሆኑት እግሮች ሮምን ያመስክቱ ነበር። ይህ እውነት ዳንኤል ምዕራፍ 7 ውስጥ ተጠናክሯል። በዚህ ምዕራፍ አራቱ አራዊት አራቱን መንግሥታት አመልክተዋል።  ዳንኤል በትንቢት መጽሐፉ አምስተኛ ምዕራፍ እንደተጠቀሰው፥ ሁለተኛው መንግሥት (ሜዶንና ፋርስ) በ539 ዓ.ዓ. ባቢሎንን ሲያሸንፍ በሕይወት ኖሮ ለመታዘብ በቅቷል። ከሁለት መቶ ዓመታት በኋላ የግሪክ መንግሥት በታላቁ እስክንድር እየተመራ የፋርስና ሜዶንን መንግሥት ቅሬታዎች አሸነፈ። ከክርስቶስ ልደት በፊት በሁለት መቶ ዓመት ደግሞ የሮም መንግሥት ወደ ኃያልነቱ እየተሸጋገረ መጥቶ ከሁሉም ዘመን መንግሥታት ወደላቀ ደረጃ ደረሰ።  ከባቢሎን ጀምሮ የነበሩት የአራት መንግሥታት ዘመን በክርስቶስ (የአሕዛብ ዘመን” ተብሎ የተጠራ ሲሆን (ሉቃስ 21፡24)፥ መለያ ባሕርዩም የኢየሩሳሌም በአሕዛብ አገዛዝ ሥር መውደቅ ነው። ምንም እንኳ በኢየሩሳሌም ላይ የነበረው የአሕዛብ አገዛዝ ለአጭር ጊዜ የተነሣ ቢሆን፥ ክርስቶስ ዳግም እስኪመለስ ድረስ የኢየሩሳሌም ከአሕዛብ መንግሥታት አገዛዝ መሳቀቅ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ የሚሆን ጉዳይ አይደለም።  በባቢሎን፥ ሜዶን-ፋርስ፥ ግሪክና ሮም መነሣትና መውደቅ እንደታየው፥ አብዛኛው የአሕዛብ ዘመን ቀደም ብሎ ተፈጽሟል። ዳንኤል ምዕራፍ ሁለት ውስጥ እንደተመለከተው በምስሉ እግርና በዳንኤል 7 እሥር ቀንዶች ባሉት አውሬ የተመሰለው የመጨረሻው ደረጃ የሮም መንግሥት ግን በቀጥተኛ ትርጉሙ አልተከናወነም። እንደ  መጽሐፍ ቅዱስ አገላለጥ፥ እራተኛው አውሬ ከሰማይ በሚመጣው የሰው ልጅ (ክርስቶስ) ይደመሰሳል። ይህም ዳንኤል ምዕራፍ ሰባት ውስጥ እንደተመለከተው ወይም ምዕራፍ ሁለት የናቡከደናፆርን ምስል እንደሚያወድም በተጠቀሰው ድንጋይ ተመስሏል።  በነዚህ ትንቢቶች ላይ በመመሥረት፥ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች የሮም መንግሥት ወደፊት ዳግም እንደሚነሣ ያምናሉ። መንግሥቱ ቤተ ክርስቲያን ወደ ሰማይ ክተነጠቀች በኋላና ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ዳግም ከመመለሱ በፊት እንደሚነሣ ያስረዳሉ። ይህ ክስተት መጽሐፍ ቅዱስ የፍጻሜው ዘመን (ዳን. 11፡35) እያለ በሚጠራው ጊዜ የሚከናወን ሲሆን፥ ወደ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ከሚያመራው ጊዜ ጋር ስለሚዛመድ፥ በዓለም ታሪከና ትንቢት ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ ይኖረዋል።  ክርስቶስ ዳግም ወደ ምድር ሲመለስ፥ የአሕዛብ ዘመን ፍጻሜ ይሆናል። በዚህም ጊዜ የዳኑና በሺህ ዓመቱ ዘመን በምድር ላይ የሚገኙ እሕዛብ ከእግዚአብሔር ዘንድ ልዩ በረከትን ይቀበላሉ። ይህን ጉዳይ ወደ ኋላ ስለ ሺህ ዓመቱ መንግሥት በምንነጋገርበት ክፍል እንደገና እናየዋለን።  በአጠቃሳይ መልኩ፥ አሕዛብን አስመልክቶ የቀረሰው መጽሐፍ ቅዱሳዊ የትንቢት አስተዋጽኦ የዓለም ታሪክ አስተዋጽኦ ነው። ይህም የቀደሙትን አያሌ ክሥተቶች የሚያብራራና በወደፊቱም ላይ ጥላውን የሚጥል ነው። አሁን በዓለም ላይ የሚታዩት ሁኔታዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ጋር የሚስማሙ ሲሆኑ፥ የመጨረሻውን ዘመን ፈጣን ፍጻሜ የሚጠቁሙ ይመስላሉ። ከመጨረሻው ዘመን መከሠት ቀደም ብሎ ቤተ ክርስቲያን ትነጠቃለች። በማጠቃለያው ከዘመኑ ጋር የሚዛመዱ ነገሮች ሁሉ ተግባራዊ ከመሆናቸውም በላይ፥ ክርስቶስ የሺህ ዓመት መንግሥቱን ለመመሥረት ይመጣል።  አሁን ያለንበት ዘመን ስለ አሕዛብ የተነገረው ወይም በብሉይ ኪዳን የተመለከተው ዕቅድና ትንቢት መፈጸሙን አያመለክትም። ትንቢቱ በበዓለ ኀምሳ የተቋረጠና ከመነጠቅ በኋላ የሚቀጥል ይመስላል። በአሁኑ ጊዜ በዓለም እድገት ውስጥ የሚገኙ ነገሮችም የዘመኑን ፍጻሜ የሚጠቁሙ ይመስላሉ። በዚሁ መሠረት የዘመኑን ወደ ፍጻሜው መቃረብና ስስ አሕዛብ የተነገረው ትንቢት ክንውን እንደገና መጀመር ምልክት ይታያል። ስለሆነም፥ ስለ አሕዛብ የተነገረውን ትንቢት ማጥናቱ፥ የጠቅላሳው ትንቢታዊ ዕቅድ አስፈላጊ ገጽታ ሲሆን፥ እግዚአብሔር ዛሬ ምን በማድረግ ላይ እንዳለና ወደፊትም ምን ለማድረግ እንደሚፈልግ ለመረዳትም ያስችላል። ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

አሕዛብ በታሪክና በትንቢት Read More »

ሰንበት እና የጌታ ቀን

This entry is part 41 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. ሰንበት በብሉይ ኪዳን  [በአማርኛ “ሰንበት” የሚለው ቃል እሁድ እንደሆነ ቢታሰብም በመጽሐፍ ቅዱስ ለአይሁድ ሰባተኛ ቀን የሆነውን ቅዳሜ የሚያመለክት ነው (ዘፀ. 16፡23-29፤ 20፡10፤ ዘሌዋ. 23፡3፤ ዘዳግ. 5፡14)። ይህን የእረፍት ቀን” (ሰንበት) በመጠበቅ አይሁዶች ለእግዚአብሔር የተለዩ ሕዝቦች መሆናቸውን የሚያሳዩበት መለያቸው ነበር (ዘፀ. 31፡13)። በሙሴ ሕግ (የሚያርሱበትን” ምድር ሰሰባተኛው ዓመት የሚያሳርፉበት “የዓመት እረፍት የሚባል ሥርዓት ደግሞ ነበራቸው (ዘሌዋ. 25፡2-8፤ 26፡34-35፥ 43፤ 2ኛ ዜና . 36፡21)። በዚህ መጽሐፍ “ዕንበት” የሚለው ቃል ቅዳሜን ማለትም “እረፍት ቀን” በመሳል ለአይሁድ የተሰጠውን ቀኝ እና ሊጠብቁት የሚጎባውን ዕለት የሚያመለክት ነው።] እግዚአብሔር ከራሱ የፍጥረት ሥራ በመጀመር፥ የሁሉንም ጊዜ አንድ ሰባተኛ እጅ ለመቀደስ ወይም ለመለየት መርጧል። ለእስራኤላውያን ሰባተኛው ቀን የእረፍት ቀን እንዲሆን ወሰነ። በሰባተኛው ዓመት ምድሪቱ እንድታርፍ ተደርጓል (ዘዳ. 23፡10-11፤ ዘሌ. 25፡2-7)። ለሰባተኛው ዓመት ለሰባተኛ ጊዜ ለማሰብም ኀምሳኛው ዓመት እንደ ኢዮቤልዩ ይከበር ነበር። በተላያዩ ዝርዝር ጉዳዮች የሰንበትና የኢዮቤልዩ ዓመታት ለእግዚአብሔር መንግሥት ትንቢታዊ ናቸው። ይህ የእግዚአብሔር መንግሥት ሰባተኛና የመጨረሻ የአገዛዝ ሥፍረ-ዘመን ሲሆን፥ የሚታወቀውም ለፍጥረት ሁሉ የሚፈጸም የሰንበት እረፍት ሰመሆን ነው። በአሁኑ ዘመን የሚከበረው ዕለት ከአዲሱ ፍጥረት ጅማሬ ሳቢያ ሰመለኮታዊ አሠራር ከሰባተኛው ወደ አንደኛው ቀን ቢለወጥም፥ በጊዚ አከፋፈል አሁንም ለእረፍት የሚውለው ተመሳሳይ መጠን፥ ማለትም ከሰባቱ ቀናት አንዱ ሆኗል።  “ሰንበት” የሚለው ቃል መተውን ወይም ከሥራ ሙሉ በሙሉ ማረፍን ያመለክታል። ክማያቋርጡት የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችና በዓላት ባሻገር፥ ዕለቱ በምንም መልኩ የአምልኮ ወይም የአገልግሎት ጊዜ አይደለም።  ሰንበትን አስመልክቶ የሚታየውን ግራ መጋባት ለማቃለል፥ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ትክክለኛ መልእክት በጥንቃቄ ማጥናቱ አስፈላጊ ነው።  ሰንበትን ከተለያዩ የዘመን ክፍሎች ጋር ስናገናዝብ፥ በተወሰነ ደረጃ ግልጥ ማስረጃ ለማግኘት ይቻላል።  ከአዳም እስከ ሙሴ በነበረው ጊዜ እግዚአብሔር የስድስት ቀናት ሥራውን ጨርሶ እንዳረፈ ሲገለጥ (ዘፍጥ. 2፡2-3፤ ዘዳ. 20፡10-11፤ ዕብ.4፡4)፥ ሰውን በተመለከተ ስለ ሰንበት በዚህ ወቅት የተጠቀሰ ነገርን አናነብም። እስራኤላውያን ከግብፅ እስከወጡበት ጊዜ ድረስ፥ ሰው የሰንበትን ቀን እንዳከሰረ የሚያመለክት አሳብ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ አልተጠቀሰም።  መጽሐፈ ኢዮብ የእምነት አባቶችን ሃይማኖታዊ ሕይወትና ልምምድ ይገልጣል። ምንም እንኳ እነዚህ አባቶች ለእግዚአብሔር የነበራቸው የተለያዩ ኃላፊነቶች ቢገለጡ፥ ስለ ሰንበት ዕለት ግዴታ የሚናገር አሳብ ግን አልተጠቀሰም። በሌላ በኩል ግን የሰንበት በሙሴ እጅ ለእስራኤላውያን መሰጠት፥ ሰንበት በሰው ልጆች ዘንድ መከበር የጀመረበት ጊዜ መሆኑን በግልጥ ያመለክታል (ዘጸ. 16፡29፤ ህ . 9፡14፤ ሕዝ. 20፡12)።  በተመሳሳይ ሁኔታ፥ መጀመሪያ ከተደነገገው ሰንበት አንድ ሳምንት ወይም ሰባት ቀናት ቀደም ብሎ፥ የእስራኤል ልጆች የሰንበትን ሕግ በማፍረስ ረዥም መንገድ ተጉዘው ከኤሊም ወደ ሲና ምድረ በዳ እንደመጡ ከመጀመሪያዎቹ የሰንበት ድንጋጌ ዘገባዎች ለመረዳት ይቻላል (ዘጸ. 16፡1-35)። በዚያ ምድረ በዳ ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ በማጉረምረሙ፥ በዕለቱ ከሰማይ ምግብ ይወርድላቸው ጀመር። ምግቡ ለስድስት ቀናት እንጂ፥ በሰባተኛው ቀን መሰብሰብ አልነበረበትም። ስለዚህ በሰንበት ዕለት ጉዞ ማድረጋቸው የሚያስረዳው፥ ዕለቱን እንደ ሰንበት ያላከበሩት መሆኑን ነው።  ከሙሴ እስከ ክርስቶስ በነበረው ዘመን፥ የሰንበት ሕግ ሥራ ላይ ውሏል። ሰንበት የማከበሩ ጉዳይ ሕግ ውስጥ የተካተተ ሲሆን (ዘጸ. 20፡10-11)፥ የሰንበትን ሕግ ለተላለፈ ሰው ይደረግ የነበረው መለኮታዊ መፍትሔም በመሥዋዕቶች ሕግ ውስጥ ተካቷል። እዚህ ላይ የሰንበት ሕግ ለአሕዛብ እንዳልተሰጠና በያህዌና በእስራኤል መካከል የሚከናወን ልዩ ምልክት እንደነበር መገንዘቡ ተገቢ ነው (ዘጸ. 31፡12-17)። ከእስራኤል ኃጢአቶች መካከል ሰንበትን ለማክበርና ለምድሪቱም እረፍት እለመስጠታቸው የተለየ አጽንኦት የተደረገባቸው ናቸው።  በዚህ የሕግ አማካይ ክፍለ ጊዜ፥ ሆሴዕ በእስራኤል ላይ ከሚደርሱት ፍርዶች አንዱ የሰንበታቶቿ ማክተም መሆኑን ተንብዮአል (ሆሴዕ 2፡11 )። ይህ ትንቢት ከእግዚአብሔር አፍ የወጣ ነውና አንድ ቀን መፈጸሙ የግድ ነበር።  ከሞቱ ቀደም ሲል በነበረው ጊዜ የክርስቶስ ምድራዊ ሕይወትና አገልግሎት ክሕግ በታች ነበር። በዚህም ምክንያት ክርስቶስ ሕግን እንደሚጠብቅ፥ እንደሚተነትንና በሥራ ላይ እንደሚያውል ታይቷል። በመሆኑም ክርስቶስ የሰንበት ሕግ በሰዎች ትውፊትና ትምህርቶች እንደተዛባ በመገንዘብ በዘመኑ ካሉ አስተማሪዎች የተለየ ትምህርት አስተምሯል። ስለዚህ ሰንበት ለሰው ልጅ ጥቅም እንደተሰጠና ሰው ከሰንበት ወጎች የተነሣ ቀኑ ሸክም ይሆንበት ዘንድ እንደማይገባ እስተምሯል (ማር. 2፡27)። ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ሰንበትን ላካተተው የሙሴ ሕግ ሁሉ በታማኝነት ይታዘዝ ነበር። ይህ የሆነው ጌታ በነበረበት ዘመን ሕግ በሥራ ላይ ስለነበረ ነው። ይሁን እንጂ፥ ይህ ሁኔታ በጸጋ ዘመንና በሌላ ሥፍረ-ዘመን የሚኖረው ክርስቲያን የክርስቶስን የሰንበት አክባሪነት ምሳሌ ሊከተል ይገባል ለሚል ትምህርት አባባል መሠረት ሊሆን የማይችል መሆኑን ይህ ግልጥ እውነት ያስገነዝባል።  ለ. ሰንበት ሰአሁኑ የቤተ ክርስቲያን ዘመን  ከክርስቶስ ትንሣኤ በኋላ፥ በአዲስ ኪዳን በስሕተት እንኳ ሰንበትን ያከበረ አማኝ አልተጠቀሰም። ከይሁዲነት ወደ ክርስትና የተመለሱ እያሌ እማኞች ሰንበትን ማከበራቸው ግልጥ ቢሆንም፥ እንዲህ ዓይነቱ አከባበር በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ አልተጠቀሰም። እንደዚሁም፥ ከክርስቶስ ትንሣኤ በኋላ ለአይሁዶች፥ ለአሕዛብ ወይም ለክርስቲያኖች ሰንበትን ያከብሩ ዘንድ የተሰጠ ትእዛዝ አናገኝም፡፡በሰንበት ቀን መሥራትም እንደ ኃጢአት የተቆጠረበት ሁኔታ አልተመለከተም።  በተቃራኒው ግን በጸጋ ዘመን የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑ አማኞች የሰንበትን ሕግ እንዳይጠብቁ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።  ገላትያ 4፡9-10 ቀናትን፥ ወራትን፥ ወቅቶችንና ዓመታትን የማክበሩ ተግባር የማያስፈልግ መሆኑን የሚያሳይ አሳብ አለ። እነዚህ ነገሮች የሚከበሩት በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ያስገኛሉ ከሚል አስተሳሰብ ሲሆን፥ አክባሪዎቹም በአንድ ወቅት እግዚአብሔርን የሚያስቡና በሌላ ጊዜ ግን በግዴለሽነት የሚኖሩ ሰዎች ናቸው።  ዕብራውያን 4፡1-13 ሰንበት እግዚአብሔር ከሥራው ያረፈበትና አማኝም በሚድንበት ጊዜ የሚገባበት የእረፍት ስፍራ መሆኑን ያስረዳል።  ቆላስይስ 2፡16-17 ውስጥ የሰፈረው ቃል የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው ከሰንበት እከባበር ጋር በተያያዘ ሊፈረድበት የማይገባ መሆኑን በግልጥ ያስረዳል። አሁን አዲስ ፍጥረት ለሆነው አማኝ ክርስቶስ ከሆነለት ሁኔታ አንጻር፥ በሰንበት ላይ የዚህ ዓይነት እመለካከት መያዙ ትክክል ነው (ቆላ. 2፡9-17)። በዚህ ምንባብ ውስጥ የተጠቀሱት የሥርዓታዊ ሕግ አካላት የሆኑት ልዩ ወይም ተጨማሪ ሰንበታት ሳይሆኑ፥ ሳምንታዊዎቹ ሰንበታት ይሆኑ ይሆናል፥ ለምሳሌ (ዘሌዋ. 16፡31)። እንድ እማኝ በራሱ አእምሮ ሲረዳ ቀናትን ሁሉ በእኩልነት ሊመለከት እንደሚችል ሮሜ 14፡5 ውስጥ ተጎልጧል። ይህ ሁኔታ በታማኝነት ማምለክን ገለል የሚያደርግ ሳይሆን፥ እንዲህ ላለው ሰው ቀናት ሁሉ ለእግዚአብሔር በመገዛት የተሞሉ መሆናቸውን ያስረዳል።  አዲስ ኪዳን ውስጥ ሰንበትን በመጠበቅ ረገድ የክርስቲያንን ሕይወትና አገልግሎትን አስመልክቶ እንደ ሕግ የተሰጠ ነገር የለም። ስለዚህ በሙሴ በተሰጠው የሰንበት ሕግ ፈንታ፥ ሰአዲሱ ፍጥረት የጌታ ቀን ሰሚለው የተተካ መሆኑን መገንዘቡ ጠቃሚ ነው። ይህ የጌታ ቀን በክብሩ፥ በከፈተው መብትና በረከቶቹ ከሰንበት እጅግ የሚልቅ ነው።  ሐ. ሰንበት በሚመጣው ዘመን  ከአዲስ ኪዳን ትምህርት ጋር ሙሉ ለሙሉ በተዛመደ መልኩ፥ አዲሱ የጌታ ቀን የሚሠራው ለቤተ ክርስቲያን ብቻ ነው። የሰንበት ሕግ እንደገና በሥራ ላይ እንደሚውል ተተንብዮአል። የቤተ ክርስቲያን መጠራት ከተፈጸመና ከዓለም ከተነጠቀች በኋላ፥ የሰንበት ሕግ የጌታን ቀን በመተካት የሚሠራ መሆኑ ነው የተገለጠው። በዚህ ዘመን ፍጻሜና በእግዚአብሔር መንግሥት መካከል ጣልቃ በሚገባው የታላቁ መከራ አጭር ወቅት እንኳ የሰንበት አሳብ ይንጸባረቃል (ማቴ. 24 ፡20)። ሰንበት የሚመጣው መንግሥት ዘመን ዋነኛ ጉዳይ እንደሚሆንም በትንቢት ተመልከቷል (ኢሳ. 66፡23፤ ሕዝ. 46፡1)።  መ. የክርስቶስ ትንሣኤና የሳምንቱ መጀመሪያ ዕለት  ከክርስቶስ ትንሣኤ እንሥቶ እስከዛሬ ድረስ የሳምንቱ የመጀመሪያ ዕለት በቤተ ክርስቲያን በመከበር ላይ ነው። ይህ እውነት በአዲስ ኪዳን ዘገባዎች፥ በቀደምት አባቶች ጽሑፎችና በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የተረጋገጠ ነው። ከሞላ ጎደል በሁሉም ክፍለ ዘመናት፥ እግዚአብሔር ሰአዲሱ ፍጥረት ሊሠራ ያቅደውን የእሁን ዓላማ ሳይገነዘቡ ሰባተኛውን የሰንበት ዕለት ለማክበር የተነሡ ሰዎች ነበሩ። ሰባተኛውን ቀን ማክበር ያስፈልጋል በማለት የሚያስተምሩት፥ ትምህርታቸው ከቃሉ ውጭ በሆኑ ነጥቦች የተደገፈና ሌላ እምነት ያላቸው ናቸው። በሰንበት ጉዳይ ውዝግብ የሚነሣው የአማኞች አምልኮ በሙሴ የሰንበት ሕግ እንደሚመራ ተደርጎ ሲወሰድ ነው። ይህ ሲሆን አዲስ ኪዳን የሚያስተምረው የአዲስ ፍጥረት” እውነት ይዘነጋል።  ሠ. አዲሱ ፍጥረት  የዚህ ሥፍረዘመን የእግዚአብሔር ዓላማ ቤተ

ሰንበት እና የጌታ ቀን Read More »

ቤተ ክርስቲያን፡- የክርስቶስ አካልና ሙሽራ፥ የሚጠብቃት ሽልማቷ

This entry is part 40 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. ሰባቱ የክርስቶስና የቤተ ክርስቲያኑ ተምሳሌቶች  በክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን መካከል ያለውን ግንኙነት ለመግለጥ፥ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰባት ተምሳሌቶች ተጠቅሰዋል።  1. መዝሙር 23 ውስጥ የተመለከተው የእረኛና የበግ ተምሳሌት ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ውስጥ ክርስቶስ እረኛ፥ በርሱ የሚያምኑ ደግም በጎች ህንኩ ስተለኩሰት ክፍል ተጠቅሷል። ከዚህ ምንባብ እንደምንመለከተው፡- (ሀ ክርስቶስ የመጣው በበሩ፥ ማለትም በተወሰነው በዳዊት የዘር ሐረግ አማካይነት ነበር፥ (ለ) እርሱ በጎች የሚከተሉት እውነተኛ እረኛ ነው፥ (ሐ) ክርስቶስ የበጎች በር፥ ማለትም ወደ ድነትም ሆነ ወደ ዋስትና የሚገባበት በር ነው (ዮሐ. 10፡28-29)፣ (መ) ምግብና ሕይወት ለበጎቹ በእረኛው አማካይነት ይቀርባል፥ (ሠ) ከእውነተኛው እረኛ ጋር ሲነጻጻሩ፥ ሌሎቹ እረኞች ለበጎች ሕይወታቸውን የማይሰጡ ቅጥረኞች ናቸው፥ (ረ) በእረኛውና በበጎቹ መካከል ኅብረት አለ። አባት ልጁን እንደሚያውቀውና ልጅም አባቱን እንደሚያውቀው፥ ሰጎቹ እረኛቸውን ያውቁታል፥ (ሰ) ምንም እንኳ በብሉይ ኪዳን ዘመን እስራኤል ሌላ መንጋ የነበረች ብትሆን፥ በአሁኑ ዘመን ያለው መንጋና እረኛ ግን አንድ ብቻ ነው። ይህ ነው እይሁዳውያንም ሆኑ አሕዛብ ድነትን የሚያገኙበት አንድ መንገድ (ዮሐ. 10፡16)፥ (ሸ) ክርስቶስ በእረኛነቱ ነፍሱን ሰጎች አሳልፎ መስጠት ብቻ ሳይሆን፥ ይማልድላቸውና መንፈሳዊ ሕይወት ብሎም የሚያስፈልጋቸውን ምግብ ይሰጣቸው ዘንድ ዘላለም በሕይወት ይኖራል (ዕብ. 1፡25)። መዝሙር 23፡1 ውስጥ፥ “እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም” ይለዋል።  2. ክርስቶስ እውነተኛው የወይን ግንድ ሲሆን፥ እማኞች ደግም ቅርንጫፎች ናቸው። ምንም እንኳ ብሉይ ኪዳን ውስጥ እስራኤል በወይን ምሳሌነት ከእግዚአብሔር ጋር የተዛመደች ብትሆን፥ ዮሐንስ ምዕራፍ 15 ውስጥ እንደተገለጠው፥ ክርስቶስ እውነተኛው የወይን ግንድ፥ አማኞች ደግሞ የወይኑ ቅርንጫፎች ናቸው። ምሳሌው ከክርስቶስ ጋር የሚደረገውን ኅብረትና አንድነት ያመለክታል። ከክርስቶስ ጋር በዚህ የማይቋረጥ ግንኙነት እንዲኖሩ ተመከረዋል (15፡10)። በርሱ የመኖር ውጤቶች ደግሞ መንጻት ወይም መገረዝ (ቁ.2)፥ ፍሬያማ ጻሎት (ቁ.7)፥ ዘላቂ ደስታ (ቁ, 11) እና ዘላለማዊ እውነት ናቸው (ቁ, 16)። የወይኑ ግንድና የቅርንጫፎቹ ማዕከላዊ እውነት፥ አንድ እማኝ እውነተኛ የወይን ግንድ ከሆነው ክርስቶስ ጋር ሕያው ግንኙነት ካልኖረው በክርስትና ሕይወት ደስ የማይሰኝ ወይም በአገልግሎቱ ፍሬያማ የማይሆን መሆኑ ነው።  3. ክርስቶስ የማዕዘን ድንጋይ ሲሆን፥ ቤተ ክርስቲያን በሕንጻው ያሉ ድንጋዮችን ይዛለች። እስራኤል ቤተ መቅደስ ውስጥ ታመልክ ከነበረበት የብሉይ ኪዳን ዘመን ጋር ሲነጻጸር (ዘፀ. 25፡8)፥ ቤተ ክርስቲያን ራሷ ቤት መቅደስ ነች (ኤፌ. 2፡21)። በዚህ ምሳሌ ክርስቶስ የማዕዘኑ ራስ ድንጋይ ሲሆን፥ እማኞች ደግሞ የሕንጻው ድንጋዮች ሆነው ተጎልጠዋል (ኤፌ. 2፡19-22)። የአሁኑ ዘመን የእግዚአብሔር ዓሳማ፥ ቤተ ክርስቲያንን ማነጽ ነው (ማቴ. 16፡18)። ቤተ ክርስቲያንን እንደ ሕንጻ በመገንባቱ ሂደት ውስት፥ እያንዳንዱ ድንጋይ የመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋይ በመሆኑ ሕያው ድንጋይ ነው (1ኛ ጴጥ. 2፡5)። ክርስቶስ የማዕዘኑ ራስና መሠረት ሲሆን (1ኛ ቆሮ. 3፡11፤ ኤፌ. 2፡20-22፤ 1ኛ ጴጥ. 2፡6)፥ ሕንጻው በጠቅላላው “ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ” ይሠራል (ኤፌ. 2፡22)። በሕንጻው ምሳሌ መሠረት፥ እያንዳንዱ አማኝ የማዕዙ ራስና መሠረት በሆነው ክርስቶስ ላይ መደገፉ ግልጥ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ፥ የሕንጻው ድንጋዮች እማኞች ሲሆኑ፥ በነርሱ መደጋገፍና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የእግዚአብሔር መቅደስ የሆነው ሕንጻ የሚሠራ መሆኑ ተገልጧል።  4. በአዲስ ኪዳን ክርስቶስ ሊቀ ካህን፥ አማኞች ደግም ኋማኝካህናት” ሆነው ተገልጠዋል። ቀደም ሲል በዚህ መጽሐፍ ጥናታችን ውስጥ እንደተገለጠው፥ እማኝ ካህን” አራት መሥዋዕቶችን ያቀርባል፤ (ሀ) ራሱን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለእግዚአብሔር በማቅረብ፥ የመሥዋዕትነትን አገልግሎት ይሰጣል (ሮሜ 12፡1-2)። (ለ) ለእግዚአብሔር ምስጋናና ውዳሴ በማቅረብ፥ የአምልኮን አገልግሎት ይሰጣል (ዕብ. 13፡15)። ይህም የምልጃንና ለራሱ ችግሮች መጻለያን ያካትታል (ሮሜ 8፡26-27፤ ቆላ . 4፡12፤ 1ኛ ጢሞ. 2፡1፤ ዕብ. 10፡19-22)። ክርስቶስ ጎልጎታ ላይ የፈሰሰ ደሙን ይዞ እንደ ሊቀ ካህናችን ወደ ሰማይ ገብቷል (ዕብ. 4፡14-16፤ 9፡24፤ 10፡19-22)። አሁን ስለ እኛ በመማለድ ላይ ነው (ሮሜ 8፡34፤ ዕብ. 7፡25)።  አማኞች እንደ ንጉሣዊ የክህነት አባላት፥ (ሐ) የሰናይ ምግባራትና (መ) የቁሳዊ ነገሮች መሥዋዕት ከማቅረብ ባሻገር፥ ሰውነታቸውን እንደ ሕያውና ቅዱስ መሥዋዕት አድርገው ማቅረብ ያስባቸው መሆኑን መገንዘቡ መልካም ነው (ዕብ. 13፡16)።  5. ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን ራስ ቤተ ክርስቲያን ደግም እንደ አካል ተደርገው የተገለጡት ምሳሌ በአሁኑ ዘመን የሚሠራውን የእግዚአብሔርን ዓላማ ያሳያል። ይህ ምሳሌ ሰፋ ብሎ ለብቻው በዚሁ ምዕራፍ ወደኋላ ይቀርባል።  6. ክርስቶስ እንደ መጨረሻው አዳም፥ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ አዲስ ፍጥረት ሆና በተለጠችበት ምሳሌ፥ ክርስቶስ ከሞት በመነሣቱ የአሮጌው ሥርዓት ራስ የነበረውን አዳምን ይተካዋል፤ አዲስ ፍጥረት ለሆኑትም ራስ ይሆናል። ምሳሌው በክርስቶስ ትንሣኤ እርግጠኛነትና በትንሣኤው ባዋቀረው አዲስ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ ነው። በአዳም ውስጥ ከመሆን ጋር ሲነጻጸር፥ አማኝ በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካይነት ክርስቶስ ውስጥ መሆኑ ተገልጧል። ባገኘው አዲስ ስፍራ አማካይነትም ክርስቶስ በርሱ ምትክ ጽድቅና አዲስ ሕይወት ለመስጠት ባከናወነው ነገር ሁሉ ተካፋይ ይሆናል። ክርስቶስ የአዲሱ ፍጥረት ራስ ስለሆነ፥ አዲስ የመታሰቢያ ዕለት ማለት በአሮጌው ሥርዓት ይከበር የነበረው የሰንበት ዕለት ተነጻጻሪ የሆነ መታሰቢያ የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን አስፈላጊ ሆኗል።  7. ክርስቶስ እንደ ሙሽራ፥ ቤተ ክርስቲያን ደግም እንደ ሙሽሪት መገለጣቸው ለአሁኑም ሆን ወደፊት በክርስቶስና በቤተ ክርስቲያኑ መካከል ለሚኖረው ግንኙነት ትንቢታዊ ምሳሌ ነው። ብሉይ ኪዳን ውስጥ ታማኝነትን እንዳጎደሰች ሚስት ከተገለጠችው እስራኤል በተነጻጻሪነት፥ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ ኪዳን የሙሽራዋን መምጣት እንደምትጠባበቅ ሙሽሪት ተገልጣለች። ይህ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ በስፋት የምንመለከተው እሳብ ይሆናል። ቤተ ክርስቲያን እንደ ክርስቶስ አካል የተገለጠችበት ምሳሌ የአሁኑን ዘመን የእግዚአብሔር ዓላማ የሚገልጥ ሲሆን፥ የክርስቶስ ሙሽራ የመሆኗ አሳብ ደግሞ ወደፊት ቤተ ክርስቲያን ከክርስቶስ ጋር የሚኖራትን ግንኙነት የሚያመለክት ነው።  ለ. ቤተ ክርስቲያን እንደ ክርስቶስ አካል  ቀደም ሲል የተመለከትነው የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት፥ የአዲስ ኪዳንን የቤተ ክርስቲያን መገለጥ በማጣመር የክርስቶስን አካል መሥርቷል። ይህም 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡13 ውስጥ እንደተገለጠው፥ በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካይነት የተከናወነ ነው፤ “አይሁድ ብንሆን፥ የግሪክ ሰዎችም ብንሆን፥ ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን፥ እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናል። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።” በዚህ ገለጣ ሦስት ዓበይት እውነቶች ቀርበዋል፤ (1) ቤተ ክርስቲያን ራሷን የምታንጽ አካል ናት፥ (2) የአካሉ ክፍሎች ልዩ ልዩ ስጦታዎች የተሰጧቸውና፥ ለልዩ አገልግሎት የተሾሙ ናቸው፤ (3) አካሉ ሕያው አንድነት ነው።  1. ቤተ ክርስቲያን ራሷን የምታንጽ አካል እንደመሆኗ መጠን፥ ኤፌሶን 4፡11-16 ውስጥ እንደተገለጠው መንፈሳዊ ስጦታዎች ያሏቸውን ግለሰቦች ታካትታለች። በዚሁ መሠረት አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሉች ነቢያት፥ ወንጌላውያን፥ ወይም መጋቢያንና አስተማሪዎች ናቸው። ማዕከላዊው እውነት አማኞች በተለያዩ ችሎታዎች እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ መሰረታታቸው ብቻ ሳይሆን፥ እግዚአብሔር የሰጣቸውን እንድ ሁነኛ ተግባር ያከናውኑ ዘንድ ብቃት የተሰጣቸው መሆኑ ነው። አንድ አማኝ ተገቢውን አገልግሎት የሚፈጽመው፥ በክርስቶስ አካል ውስጥ የተወሰነለትን ተግባር ሲወጣና የክርስቶስን እካል ፍጹም በማድረጉ ክንውን ተካፋይ ሆኖ ሲገኝ ነው (ኤፌ. 4፡13)።  2. የክርስቶስ አካላት እንደየስጦታቸው የተወሰነ እገልግሎት እላቸው። በሰው ሰውነት ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የእካል ክፍሎች ልዩ ልዩ ተግባራትን እንደሚያከናውኑ ሁሉ፥ የክርስቶስ አካል ክፍሎችም እንዲሁ ናቸው። እያንዳንዱ አማኝ እግዚአብሔር የትኛውን ስጦታ እንደሰጠው ለማወቅ ራሱን በጥንቃቄ ሊመረምርና ስጦታውን ለእግዚአብሔር ከብር ሊያውለው ይፃባል። ዋና ዋናዎቹ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ሮሜ 12፡3-8 እና 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡28 ውስጥ ተገልጠዋል። አማኞች ሁሉ መንፈሳዊ ስጦታዎች ያሏቸው ሲሆን፥ ከአንድ በላይ ስጦታዎች ያሏቸውም አሉ። አንዳንዴ የሚዛመዱበት ሁኔታ ቢኖርም፥ መንፈሳዊ ስጦታዎች ከተፈጥሮ ችሉታ ጋር መደናገር አይኖርባቸውም። ለምሳሌ አንድ ሰው በተፈጥሮው የማስተማር ብቃት ሊኖረው ይችላል። መንፈሳዊ ነገሮችን የማስተማር ስጦታ የሚሰጠው ግን ከእግዚአብሔር ብቻ ነው።  መንፈሳዊ ስጦታዎችን ፈልጎ ማግኘት አይቻልም። ዳሩ ግን “መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻ እያካፈለ ያደርጋል” (1ኛ ቆሮ. 12፡11)። በሐዋርያት በተመሠረተች ቤተ ክርስቲያን ጀምረው እስካሁን ድረስ የቀጠሉ አንዳንድ ስጦታዎች አሉ። ሌሎች የምልክት ስጦታዎች ግን ከመጀመሪያው የክርስቲያኖች ትውልድ በኋላ ያበቁ ይመስላል። ያም ሆነ ይህ፥ እያንዳንዱ ስጦታ ለእግዚአብሔር

ቤተ ክርስቲያን፡- የክርስቶስ አካልና ሙሽራ፥ የሚጠብቃት ሽልማቷ Read More »

ቤተ ክርስቲያን፡- አደረጃጀትና ሥርዓቷ

This entry is part 39 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር  ቤተ ክርስቲያን እንደ ክርስቶስ አካልነቷ፥ በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካይነት የአካሉ ራስ ከሆነው ክርስቶስ ጋር የተባበረውን ማንኛውንም ክርስቲያን ታካትታለች። አካል እንደ መሆኗ፥ የዕውን የአካል ክፍል በሚመስል አኳኋን ተዋቅራለች። እያንዳንዱ የሰውነት ክፍል ከሌላው ጋር ይገናኝና፥ ጠቅላላውን አካል ከሚመራው ራስ ጋር ይዛመዳል። የክርስቶስ አካል የሆነችው እውነተኛ ቤተ ክርስቲያን ግንኙነት መንፈሳዊና መለኮታዊ እንደ መሆኑ፥ ድርጅታዊነትን እንደ ዋና ነገር አድርገን መውሰድ እንችልም።  ይህም ሆኖ፥ በቀደመው ዘመንም ሆነ ዛሬ፥ ለአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የተወሰነ አደረጃጀት አስፈላጊ ይመስላል። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ሦስት የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዓይነቶች ይገኛሉ። እነዚህ የአስተዳደር ዓይነቶች ከሐዋርያት ዘመን ጋር የተያያዙ ናቸው።  1. በኤጵስቆጶሳዊ” የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ለጵጵስና ወይም ሌላ ዓይነት የማዕረግ ስያሜ ለአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መሪ ይሰጣል (1ኛጢሞ. 3፡1)። ይህ ዓይነቱ የቤተ ክርስቲያን ተሰያሚ በሚሰጠው ሥልጣን መሠረት ቤተ ክርስቲያኒቱን ይመራል። እንዲህ ያለው አደረጃጀት ወደ ከፍተኛ ድርጅታዊነት በማደጉ፥ ጳጳሳት በተወሰኑ እካባቢዎች የአብያተ ክርስቲያንን እንቅስቃሴዎች በበላይነት ለመቆጣጠር ይሾማሉ። እንዲህ ዓይነቱ አሠራር በሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፥ በእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያንና በሜተዲስት ቤተ ክርስቲያን የተላመደ ነው።  2. ቀተወካዮች” የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በአግባቡ የሚወከሉ ግለሰቦችን ሥልጣን ይቀበላል። እነዚህ ተወካዮች በአብዛኛው በመልክዓ-ምድራዊ ክልል የሚወሰኑ ሲሆን፥ በፕሬስቢቲሪያንና ሪፎርምድ አብያተ ክርስቲያን ውስጥ የተለመዱ ናቸው። ብዙውን ጊዜ አንድ አካባቢ ያለ የአብያተ ክርስቲያን የተወካዮች ቡድን ከርሱ በበለጠ አካል ወይም ሲኖዶስ ሥር የሚንቀሳቀስ ይሆናል። ሲኖዶሱም በበኩሉ ከርሱ ስላቀ አጠቃላይ ጉባኤ ይገዛል። ምንም እንኳ ደንቦችና የሥልጣን ደረጃዎች ቢለያዩ፥ ዋናው አሳብ በተገቢው መንገድ የተመረጡ ተወካዮች የቤተ ክርስቲያንን ሥልጣን የሚይዙ መሆናቸው ነው።  3. በጉባኤያዊ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዓይነት ሥልጣኑን የሚይዘው የእግቢያ ጉባኤ ነው። በዚህ የአስተዳደር ዓይነት ለዋነኞቹ ጉዳዮች ውሳኔ የሚሰጠው፥ የሌሎቹን አብያተ ክርስቲያን ወይም ባለሥልጣናት ሥልጣን ከግንዛቤ ሳያስገባ ጉባኤው ብቻ ነው። ይህን ዓይነቱ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር እንደ ባፕቲስት አብያተ ክርስቲያን በመሳሰሉት ይዘወተራል። ምንም እንኳ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ለበላይ አካላት፥ ኮሚቴዎች ወይም ኃላፊዎች በተወሰነ ደረጃ ሊገዙ የተገባ ቢሆንም፥ የዚህ ዓይነቱ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዋነኛ አሳብ፥ ጉባኤዎች የራሳቸውን ጉዳዮች የሚወስኑ አገልጋዮች የሚሾሙና የራሳቸውን መዋዕለ ንዋይ አጠቃቀም የሚመሩ መሆኑን ነው።  በመጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን ሦስቱም የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ቅርፆች በተወሰነ ደረጃ አገልግለዋል። ሐዋርያት ቀዳሚ ሥልጣን የነበራቸው መሆኑን ብዙዎቹ የቀድሞ አብያተ ክርስቲያን ተገንዝበዋል። ይሁንና፥ ይህ ከመጀመሪያው ክርስቲያን ትውልድ ጋር ያለፈ ይመስላል። ሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 15 ውስጥ እንደተገለጠው፥ ሐዋርያትና በኢየሩሳሌም የሚገኙ ሽማግሌዎች፥ አብያተ ክርስቲያን ላነሱዋቸው የአስተምህሮ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጡ ተወካዮች ነበሩ። ይህን ካለንበት ዘመን የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር አሠራር አንጻር ስናየው ግን፥ እነዚህ ሰዎች ተመራጮች ወይም የቤተ ክርስቲያን ተወካዮች አልነበሩም። አብያተ ክርስቲያን እየበሰሉ መጥተው የሐዋ ርያትን ተቆጣጣሪነት ከማይፈልጉበት ደረጃ ላይ በደረሱ ጊዜ፥ የአብያተ ክርስቲያን አስተዳደር ለአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የተላለፈ ይመስላል። ራእይ 2-3 ውስጥ የተጠቀሱትን ሰባት የእስያ አብያተ ክርስቲያን በተመለከተ እውን የነበረ ይመስላል። እነዚህ አብያተ ክርስቲያን ከራሱ ከክርስቶስ በቀር ለማንኛውም ሰብአዊ ሥልጣን አይገዙም ነበር። ከዚህ አንጻር ሲታይ፥ በአሁኑ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚታየው የረቀቀና የተወሳሰበ አስተዳደር በመጽሐፍ ቅዱስ የሚደገፍ መሆኑ አጠራጣሪ ስለሆነ፥ ወደ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ግንዛቤ መመለሱ ተገቢ ነው።  ለ. የቤተ ክርስቲያን መሪዎች  በመጀመሪያው ዓመተ ምህረት የነበሩ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች እንደ “ኤጲስ ቆጶስ” ወይም “ሽማግሌዎች ተሰይመው እጥቢያይቱን የሚመሩት ሰዎችን ያካትታል። ምንም እንኳ ስሞቻቸው በመጠኑ ቢለያይ፥“ኤጵስ ቆጶሳትን እና “ሽማግሌዎች” አንድ ዓይነት ሰዎች ሳይሆኑ አይቀሩም።  ምናልባትም የአዲስ ኪዳን የሽማግሌዎች ፅንሰ-አሳብ የተወሰደው፥ በእስራኤል ላይ ሥልጣን ከነበራቸው ሽማግሌዎች አሠራር ሆኖ (ማቴ. 16፡21፤ 26፡47÷ 57፤ ሐዋ. 4:5፥ 23)፥ በአስተሳሰቡ የበሰለና ሥልጣን ሊይዝ የሚገባውን ሰው ያመለክት ነበር። ስለሆነም፥ ሽማግሌ ለመሪነት የሚያበቁትን መመዘኛዎች የሚያሟላ ሰው እንደነበረ እንረዳለን። “ኤጲስ ቆጶስ” የሚለው ቃል የሰውን ሥልጣን ወይም አገልግሎት የሚገልጥ ነው። ኤጲስ ቆጶስ ሁልጊዜ ሽማግሌ ሲሆን፥ ሽማግሌ ግን በተወሰኑ ሁኔታዎች ምክንያት ኤጲስ ቆጶስ ሊሆን አይችል ይሆናል። ማለት ሥልጣ ሳይኖረው ብቃቱ ሲኖረው ይችላል። በቀድሞይቱ ቤተ ክርስቲያን ሁለቱም ቃላት በተመሳሳይነት ያገለገሉ ይመስላል (ቲቶ 1፡5፥ 7)።  ኤጲስ ቆጶስና ሽማግሌዎች ቤተ ክርስቲያንን የማስተዳደር (1ኛ ጢሞ. 3፡4-5፤ 5፡17)፥ ቤተ ክርስቲያንን ከግብረ ገባዊ ወይም ሥነ-መለኮታዊ ስሕተት የመጠበቅ (ቲቶ 1፡9) እና እረኛ መንጋውን እንደሚንከባካብ ቤተ ክርስቲያንን የመንከባከብ ወይም የመቆጣጠር የመሳሰሉ ኃላፊነቶችን መወጣት ነበረባቸው (ዮሐ. 21፡16፤ ሐዋ. 20፡28፤ ዕብ. 13፡17፤ 1ኛ ጴጥ. 5፡2)። የመጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች በሐዋርያት የተሾሙ ቢመስልም፥ አብያተ ክርስቲያኑ እየበሰሉ ሲመጡ የመሾሙን ተግባር ራሳቸው ሳያካሂዱት አልቀሩም። ሹመቱ የሰዎቹን የመሪነትና መንፈሳዊ ብቃት ያገናዘበ ነበር (ሐዋ. 14፡23፤ 20፡28፤ ቲቶ 1፡5፤ 1ኛ ጴጥ. 5፡2)።  ከሽማግሌዎችና ኤጲስ ቆጶሳት ባሻገር ሌሎች አገልጋዮች ዲያቆናት ተብለው ይሾሙ ነበር። ዲያቆናት በቀድሞይቱ ቤተ ክርስቲያን ምንም እንኳ መንፈሳዊ ስጦታዎች ሊኖራቸው ቢችል፥ ቀዳሚ ትኩረት የሚሰጡት ግን ችግረተኞችን በመርዳቱና ቁሳዊ አገልግሎት በማበርከቱ ተግባር ላይ ነበር (ሐዋ. 6፡1-6፤ 1ኛ ጢሞ. 3፡8-13)። እንደ ሽማግሌዎቹ ሁሉ ዲያቆናት በቀድሞይቱ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያት (ሐዋ. 6፡6፤ 13፡3፤ 1ኛ ጢሞ. 1፡6) ወይም በሽማግሌዎች ሳያሾሙ አይቀሩም (1ኛ ጢሞ. 4፡14)። በኤጲስ ቆጶስና ሽማግሌዎች አገልግሎት እንደሚደረገው፥ በድቁና ሹመትና ዲያቆኑ በሚያበ ረክተው አገልግሎት መካካል ልዩነት ሊደረግ ይገባል። ፊልጶስ በመንፈሳዊ ስጦታው ወንጌላዊ ቢሆንም፥ የድቁና ሥልጣን ነበረው (ሐዋ. 6፡5፤ 21፡8)።  ዛሬ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያን መጋቢውን እንደ አንድ ብቸኛ ሽማግሌ፥ እድርገው ይመለከቱታል። በመንፈሳዊ ጉዳዮች የሚረዱትን ሌሎች ሰዎች ደግሞ እንደ ዲያቆናት ይመለከቷቸዋል። ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልምምድ አይመስልም።  ሐ. የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶች  አብዛኛዎቹ የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያን ሁለት ሥርዓቶችን፥ ማለት ጥምቀትንና የጌታ እራትን ብቻ ነው እንደ ሥርዓት የሚቀበሉት። ከነዚህ አብያተ ክርስቲያን አንዳንዶቹ ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጠበበትን ምሳሌ (ዮሐ. 13)፥ እንደ ሥርዓት አድርገው በመውሰድ በተግባር ይፈጽሙታል። የሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በነዚህ ላይ ሌሎች ጥቂት ሥርዓቶችን ይጨምራሉ። ከሞላ ጎደል በሁሉም የተለመዱ ሥርዓቶች ጥምቀትና ቅዱስ ቁርባን ብቻ ናቸው።  1. በቤተ ክርስቲያን ታሪክ፥ የውኃ ጥምቀት ሥርዓት ከፍተኛ ውዝግብ ያስከተለ ሲሆን፥ ለቤተ ክርስቲያን ክፍፍልም እስተዋጽኦ አድርጓል። በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የሚነሡ ክርክሮች በአጠቃላይ ሁለት ዓበይት ችግሮችን ያካትታሉ፤ () የውኃ ጥምቀት ሥርዓት ብቻ ነው? ወይስ ለተጠማቂው የሚያበረክተው መለኮታዊ ጥቅም አለ? (2) አፈጻጻምን በተመለከተ፥ የውኃ ጥምቀት የሚከናወነው በመጥለቅ ብቻ፥ ወይስ በተጠማቂው ላይ ውኃ በማፍሰስና በመረጨትም ሊሆን ይችላል?  የውኃ ጥምቀት፥ ሥርዓት ብቻ መሆኑን የሚያምኑ ሰዎች ድርጊቱ መንፈሳዊ እውነትን እንደሚያካትት፥ ነገር ግን ለተጠማቂው የሚያስተላልፈው ምንም ዓይነት ጸጋ ወይም ሕይወት እንደሌለ ያስረዳሉ። የውኃ ጥምቀት ሥርዓት ብቻ መሆኑን የሚያመለክተው ገለጣ የተሻለ አተረጓጎም ነው። የውኃ ጥምቀት አንዳች ልዩ ጸጋ እንደሚያስገኝ የሚያምኑ ሰዎች ድርጊቱ ለተጠማቂው የሚያስገኘውን የበረከት መጠን በተመለከተ በእጅጉ ይለያያሉ። አንዳንዶች ጥምቀትን ከዳግም ልደት ጋር በማነጻጸር፥ በአንድ ሰው ዳግም ልደት ውስጥ ድርሻ እንዳለው ይናገራሉ። ሌሎች ደግሞ እንዲሁ ጸጋን እንደሚያስገኝ ወይም ወደ እምነትና ለወንጌሉ ወደ መታዘዝ እንደሚመራ ያምናሉ። ጥምቀት ሥርዓት ብቻ የመሆኑን አሳብ የሚቃወሙ ወገኖች የውኃ ጥምቀት፥ ከመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ከአማኙ ዳግም ልደት ጋር በማይነጣጠል መልኩ የተጣመረ መሆኑን ይገልጣሉ።  ባፕቶ” የሚለው የግሪኩ ቃል “አንድን ነገር ፈሳሽ ውስጥ መንከር” የሚል ትርጉም አለው። ይህ ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ ሦስት ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን በአማርኛ “ነከረ” (ሉቃስ 16:24)። “አወቀሰ” (ዮሐ. 13:26)፥ “ተረጨ” (ራዕይ 19፡13) በሚል ተተርጉሟል።  “ባፕቲዞ የሚለው የግሪኩ ቃል ባፕቶ” ከሚለው የመጣ ሲሆን በአዲስ ኪዳን የተለያየ ትርጉም አለው። “ማጥመቅ” የሚለው የግሪክ ቃል ባፕቲዞ” ሲሆን፤ ይህ ቃል በአዲስ ኪዳን የተለያየ ትርጉም ይዞ እናገኘዋለን።* [* በግሪኩ ጥምቀት

ቤተ ክርስቲያን፡- አደረጃጀትና ሥርዓቷ Read More »

ቤተ ክርስቲያን፡- አምልኮዋ በጸሎትና በምስጋና

This entry is part 38 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሮሜ 12፡1-2 እና ዕብራውያን 13፡15-16 ውስጥ እንደተገለጠው፥ ክርስቲያን እንደ አማኝ ካህን አራት መሥዋዕቶችን ያቀርባል። እነዚህም፡- (1) የሰውነቱን መሥዋዕት (ሮሜ 12፡1-2)፥ (2) የምሥጋና መሥዋዕት (ዕብ. 13፡15)፥ (3) የሰናይ ምግባራት መሥዋዕት (ዕብ. 13፡16) እና (4) የገንዘብ አስተዳደር ወይም ዕብራውያን 13፡16 ውስጥ እንደተመለከተው ማካፈልን አትርሱ” ተብሎ ተጻፈው መሠረት የማካፈል መሥዋዕት ናቸው። ሰናይ ምግባራትንና ቁሳዊ ሀብት የማካፈል መሥዋዕቶችን ቀደም ብለን የተመለከትኝ መሆኑ፥ እንደ ካህን የተቆጠረው አማኝ በጸሎቱና ለእግዚአብሔር በሚያቀርበው ምስጋና የሚያከናውነውን ተግባር ቀጥለን እንመለከታለን።  በዚህ ዘመን፥ አምልኮ የሥርዓት ጉዳይ አይደለም። ክርስቶስ ለሰማርያይቱ ሴት እንደተገለጠሳት፥ እግዚአብሔር መንፈስ ስለሆነ የሚያመልኩት ሁሉ በእውነትና በመንፈስ ሊያመልኩት ይገባል (ዮሐ. 4፡24)። በመሆኑም፥ አምልኮ በታላሳቅ አብያተ ከርስቲያናት ውስጥ በሚፈጸሙ ቅዱስ አገልግሎቶች የተወሰነ አይደለም። ክርስቲያን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለሰማያዊ አባቱ ምስጋናና ምልጃ ከልቡ የሚያቀርብበት ውዳሴ ነው። ጸሎትና ምስጋና የአምልኮ ዋነኛ ገጽታዎች ሲሆኑ፥ ሰዎች በቀጥታ ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙባቸው ተግባራት ናቸው። ብሉይና አዲስ ኪዳናት ውስጥ የጸሎትና የምስጋናን አስተምህሮ በምናጠናበት ጊዜ፥ እያደገ የሚሄደውን መገለጥና እየጨመረ የሚሄደውን ልምምድና ከእግዚአብሔር ጋር ያላ የቀረበ ግኑኝነትን እንመለከታለን።  ሀ. ጸሎት ከክርስቶስ መምጣት በፊት  በዘመናት ሁሉ ጸሎት እግዚአብሔርን በሚፈልጉ ግለሰቦች ሲቀርብ ቢቆይም። የቤተሰቡ ኃላፊ በሚያስተዳድራቸው ሰዎች ምትክ (ኢዮብ 1፡5)፥ ካህናትና ገዢዎች ደግሞ በሕዝባቸው ምትክ ይጸልዩ እንደነበር ይታወቃል። ይህ ሁኔታ በተለይ በሙሴና በክርስቶስ መምጣት መካከል በነበረው ጊዜ ይሠራበት ነበር። በነዚህ ምዕተ ዓመታት የጸሎት መሠረቶች የያህዌ ቃል ኪዳን (1ኛ ነገሥት 822-26፤ ነህ. 9፡32፤ ዳን. 9፡4) እና ቅዱስ ባሕርዩ ነበሩ (ዘፍ. 18፡25፤ ዘዳ. 32፡11-14)። ይህም የመሥዋዕትን ደም ተከትሉ የሚመጣ ነስር (ዕብ. 9፡7)።  ለ. የመንግሥትህ ትምጣ ጸሎት  የእስራኤል ሕዝብ የክርስቶስን መሢሕነትና በርሱም በኩል የሚመጣውን መንግሥት ላመቀበል አልፈለገም። ክርስቶስ ግን በመጀመሪያዎቹ ዓመታት ባቀረባቸው ስብከቶችና መንግሥትን ለእስራኤል ስለሚሰጥበት ወቅት፥ ደቀ መዛሙርቱ የእግዚአብሔር መንግሥት በምድር ላይ እንድትመሠረት ይጸልዩ ዘንድ አስተማራቸው።  ማቴዎስ 6፡9-13 ውስጥ የተመለከተውና የታወቀው የጌታ ጸሎት “መንግሥትህ ትምጣ” የሚል ልመና ታክሎበታል (ማቴ. 6፡10)። ይህ ጻሎት በዋናነት በሺህ ዓመቱ ዘመን ክርስቶስ በሉዓላዊነት ምድርን የሚገዛ መሆኑን ያሳያል።  ጸሎቱ ማቴዎስ 6፡13 ውስጥ “መንግሥት ያንተ ናትና፥ ኃይልም፥ ክብርም፥ ለዘላለሙ አሜን” በማለት ይደመድማል። ይህ የጸሎት ክፍል በብዙዎቹ የማቴዎስ ወንጌል ጥንታዊ ሰነዶች ውስጥ የማይገኝ ከመሆኑም በላይ፥ ሉቃስ 11፡2-4 ውስጥ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ምንባብም አልተጻፈም። ከዚህም የተነሣ፥ ብዙ ሰዎች ይህ ክፍል መጽሐፍ ቅዱስን የገለበጡ ሰዎች ድምዳሜውን ለማሳመር የጨመሩት እንደሆነ አድርገው ያስባሉ። ዳሩ ግን ክፍሉ በመጀመሪያው የማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ኖረም አልኖረ፥ ስለ ወደፊቱ የእግዚአብሔር መንግሥት ትክክለኛ አስተምህሮ አለው።  የጌታ ጸሎት ለሁሉም ዘመናትና ሁኔታዎች የሚስማሙ ነጥቦችን ስለሚያካትት፥ ብዙ ጊዜ እንደ ሞዴል ጸሎት ሲጠቀስ ኖሯል። በጸሎቱ ውስጥ ለአብ የቀረበ ውዳሴ፥ የዕለት እንጀራ ልመና፥ ከፈተና የመዳን ተማጽኖና ሌሎችም ነጥቦች በሞዴልነት አገልግለዋል። ዮሐንስ 17 ውስጥ ሰፋ ያለ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸሎት ይገኛል። ጌታችን በዚያ ጸሎቱ እግዚአብሔር በዚህ ዘመን ለቤተ ክርስቲያን ያለውን ዓላማ ሙሉ ለሙሉ በመገንዘብ ለቤተ ክርስቲያኑ ማልዷል።  አንዳንዶች ማቴዎስ ወንጌል ውስጥ የሚገኘው የጌታ ጸሎት በአሁኑ ዘመን አላግባብ ግልጋሎት ላይ የሚውል መሆኑን ይናገራሉ። ይሁን እንጂ፥ ብዙ በጊዜ የማይወሰኑ ሁኔታዎቹና ቀለል ብሎ የመቅረቡ ነገር በብዙ አማኞች ዘንድ ተወዳጅ አድርጎታል። በተጨማሪም፥ ለዛሬዎቹ አማኞች የሺህ ዓመቱን መንግሥት መምጣት በጸሎት መጠባበቁ አግባብ ያልሆነ ነገር አይደለም። ይህ የእግዚአብሔር መንግሥት ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት በፊት በሰዎች ጥረት እንደሚመጣ እድርገው የሚረዱ አሉ። ትክክለኛው አሳብ ግን ክርስቶስ ሰኃይሉና በሥልጣኑ በምድር ላይ መንግሥቱን የሚመሠርትበት ጊዜ እንደሚመጣ ነው።  ሐ. የክርስቶስ ጻሉት  ዮሐንስ ምዕራፍ 17 ውስጥ የቀረበው እውነተኛ “የጌታ ጸሎት”፥ በእብና በወልድ መካከል ያለውን የላቀ ሙግባባትና ነጻነት ይገልጣል። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ክርስቶስ የሊቀ ካህናቱን ተግባር ሲያከናውን እንመለከታለን። የጸሎቱ ጭብጥ ከዕለተ በዓለ ኀምሳ በኋላ በሚኖረው ዘመን አማኞች በምድር ላይ በሚያስፈልጓቸው ነገሮች ላይ ያተኮረ ነበር።  ከርስቶስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ፥ ከመሞቱ ቀደም ብሎ ለረዥም ጊዜ ይጸልይ ነበር (ማቴ. 14፡23)። ሌሊቱን ሁሉ ሳይቀር (ሉቃስ 6፡12)፥ ጸሎቱ ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 17 ውስጥ እንደተጠቀሰው፥ ከአብ ጋር በጥሩ ኅብረት የተከናወነ መሆኑ እውን ነው። የክርስቶስ ጸሎት በተስፋ ቃሎች ወይም በቃል ኪዳኖች ላይ ሳይሆን፥ ሰማንነቱና በካህናዊ የመሥዋዕትነት ሥራው ላይ ነው። የክርስቶስ ጸሉት በተለይም ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 17 ውስጥ የሚገኘው በአብ ቀኝ ሆኖ የሚያከናውነው የምልጃ ተግባር መገለጥ ነው። ይህ የምልጃ ተግባር በአሁኑም ሥፍረዘመን ይቀጥላል።  መ. ጸሎት በጸጋ ግንኙነት ሥር  ጸሎት በዘመናት ሁሉ አንድ ዓይነት ገጽታ የለውም። እንደ ሌሎች ሰብአዊ ኃላፊነቶች ሁሉ፥ ከተለያዩ ሥፍረ-ዘመናት ጋር የሚዛመድ ነው። ጸሎት በአዲስ ኪዳን በተሰጠው ሰፊ መገለጥ አዲስ ደረጃ አግኝቷል። ይኸውም በመስቀል ላይ በተፈጸመው መሥዋዕት በተገኘው ሙሉ መገለጥና በክርስቶስ ስም የሚካሄድ መሆኑ ነው።  በጸጋ ዘመን ባለ አማኝ ሕይወት ውስጥ ከሚገኙ ሰባት ታላላቅ ነገሮች መካከል ጻሉት አንደኛው ነው። እነዚህም ሰባት ነገሮች ክርስቶስ በሰገነት ላይና በጌቴሴማኒ የጠቀሳቸው ናቸው (ዮሐ. 13፡1-17፡26)። ክርስቶስ በዚህ እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ላይ ያቀረበው ትምህርት በሦስት ምንባቦች ውስጥ ተመልክቷል (ዮሐ. 14፡12-14፤ 15 ፡7፤ 16፡23-24)። ከዚህ የክርስቶስ ቃል እንደምንረዳው፥ በአሁኑ የጸጋ ዘመን ጸሎት ከምድራዊ ውሱንነቶች በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ከመሆን የተነሣ ወደማይወሰኑ ልዩ ግንኙነቶች ተሸጋግሯል። የዚህ ዓይነቱ ጸሎት በአራት መልኩ ሊታይ ይችላል።  1. በጸሎት አገልግሎት ውስጥ የሚካተተው ምስጋና ብቻ ሳይሆን፥ እማኝ የራሱን ችግሮች ለኔታ የሚያቀርብበትና ለሌሎችም ያሚማልድበት ነው። የራሽናሊዝም አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች፥ ሁሉን አዋቂ የሆነው አምላክ ስለ አንድ ነገር ከሚጸልይ ሰው ይበልጥ የሚያስፈልገውን ነገር ስለሚረዳ መጸለይ አስፈላጊ አይደለም ይላሉ። ይሁንና፥ እግዚእብሔር ፈቃዱን ለመፈጸም ጸሎትን እንደ መሣሪያ አድርጎ በሉዓላዊነቱ የደነገገ ከመሆኑም በላይ፥ በርሱ የሚያምኑ ሰዎች ልመናዎቻቸውን እንዲያቀርቡ አስተምሯል። የጸሎት አስፈላጊነት ዮሐንስ 14፡13-14 ውስጥ የተጠቀሰ ሲሆን፥ ክርስቶስም በስሙ የሚጠየቀውን ሁሉ እንደሚሰጥ የተስፋ ቃል ገብቷል። ስለሆነም፥ እግዚአብሔር የራሱን ድርጊት ሰአማኑ ጸሎት እንዲፈጻም እስከማድረግ ድረስ ለጸሎት ከፍተኛ ስፍራ ሰጥቷል።  እግዚአብሔርን የመጠየቅ ኃላፊነት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለ ኅብረት ጉዳይ ነው። በመሆኑም፥ ትርጉም ይሰጣል ወይም አይሰጥም የሚል ሁኔታ ሳይሆን፥ ራስን ከተሰጠው ትእዛዝ ጋር የማስማማት ጉዳይ ነው። ጸሉት ውስጥ የተካተተውን ሁሉ ልቅም አድርገን ልናውቅ ባንችልም፥ የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑ ሁሉ በጸሎት አገልግሎት አማካይነት ወደ ላቀ የተግባር ተካፋይነት እንደሚመጡ እናውቃለን። ይህ ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ የመሥራት ዕድል፥ ያለ ጸሎት ሊከናወን አይችልም። ክርስቲያን የመጭው ክብር ተካፋይ እንደመሆኑ፥ በሥራ የመካፈል ዕድልም ተሰጥቶታል። ይህ የተሳትፎ ጉዳይ ለአማኞች እንደተሰጠ ልዩ ፈቃድ የሚቆጠር ሳይሆን፥ የመሥዋዕትነት ደም ለፈሰሰላቸው (ዕብ. 10፡19-20) እና አዲስ ፍጥረት ከክርስቶስ ጋር ለተባበሩ ሁሉ የተሰጠ አገልግሎት ነው። ስለሆነም፥ የክርስቶስ ሕያው አካል የሆነ እማኝ የአገልግሉቱም ሆነ የክብሩ ተካፋይ የመሆኑ እግባብነት ግልጥ ነው (ኤፌ. 5፡30)።  ክርስቶስ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል” (ዮሐ. 14፡12) ያለው ከዚሁ አዲስ የጸሎት ሥልጣን ተካፋይነት አዋጅ ጋር በተዛመደ መልኩ መሆኑ ሊጤን ይገባል። ክርስቶስም ለዚህ የጸሎት አገልግሎት መልስ የሚሰጠው እርሱ ብቻ መሆኑን ወዲያውኑ በተናገረው የዋስትና ቃል ገልጧል። በጸሎትና የጸሎት ውጤትን በሚያመጣው መለኮታዊ ኃይል መካከል ያለው አንድነት ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው በመሆኑ ነው አማኝ “ከዚህም የሚበልጥን ተግባር ሊያከናውን የሚችል መሆኑን ክርስቶስ የተናገረው።  2. በጸጋ ዘመን ለእያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጅ የተሰጠው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የመጸለይ ሥልጣን፥ ከዚህ በፊት ከነበሩ ጸሎቶች ሁሉ የላቀ ጸሎትን እንዲጸልይ ያደርገዋል። ስለሆነም የአማኙን ጸሎት ከክርስቶስ መክበር በፊት ከነበሩ የጸሎት ዓይነቶች ሁሉ የላቀ የሚያደርገው፥ ከስሙ ጋር ያለ በአንድነት የመሥራት ኅብረት ነው። ክርስቶስ፥ “እስካ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም” ሲል (ዮሐ. 16፡24)። ከዚያ በፊት የነበረውን

ቤተ ክርስቲያን፡- አምልኮዋ በጸሎትና በምስጋና Read More »

ቤተ ክርስቲያን፡- አገልግሎቷና አደራዋ

This entry is part 37 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. አገልግሎቷ ለእግዚአብሔር  ለሌላው ይጠቅም ዘንድ የሚከናወን ማንኛውም ተግባር አገልግሎት ይባላል። ይህን ጉዳይ ከመጽሐፍ ቅዱስ በምናጠናበት ጊዜ፥ በብሉይና በአዲስ ኪዳን መካከል አያሌ ተመሳሳይና ተነጻጻሪ ሁኔታዎች እንመለከታለን። የአዲስ ኪዳን አብዛኛው አስተምህሮ ብሉይ ኪዳን ውስጥ የተተነበየ ስላሆነ፥ በአዲሱ እስኪፈጸም ድረስ የብሉይ ኪዳን እስተምህሮ ጎደሎ ነው። የአገልግሎትንም ጉዳይ ስንወስድ ከዚህ የተለየ አይደለም። ስለ አገልግሎት ስናጠና በአብዛኛው የብሉይ ኪዳኑ አባባሎች እንደ ጥላ የነበራቸው ትርጉሞች በአዲስ ኪዳን ፍጻሜ ሲያገኙ እናያለን።  በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ሥርዓት ከእግዚአብሔር የሆነ አገልግሎት ከህነት ግንኙነት የሚጠቀላል ነው። በብሉይ ኪዳን ሥርዓት ከህነት በተዋረድ የሚካሄድ ሲሆን፥ ካህናቱ በሊቀ ካህኑ ሥልጣን ሥር ያገለግሉ ነበር። በአዲስ ኪዳን ሥርዓት ግን እያንዳንዱ አማኝ ለእግዚአብሔር ካህን ነው (1ኛ ጴጥ. 2፡5-9፤ ራእይ 1፡6)። የአዲስ ኪዳን ክህነት ጠቅላላ የአጎልግሎት እውነተኛ ሊቀ ካህን በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ሥልጣን ሥር የሚካሄድ ነው። ሌሎች ሊቀ ካህናት እውነተኛ ሊቀ ካህን ወደሆነው ክርስቶስ የሚያመለክቱ ጥላዎች ብቻ ነበሩ። ስለሆነም በአዲስ ኪዳን ሥርዓት መሠረት፥ አማኞች ከእግዚአብሔር ጋር ባላቸው የክህነት ግንኙነት ላይ በመመሥረት በተመሳሳይ ደረጃ ያገለግላሉ። በክህነት አገልግሎታቸው፥ እንደ ብሉይ ኪዳን ክህነት ሁሉ የአዲስ ኪዳን ካህናትም እግዚአብሔርንና ሰውን እንዲያገለግሉ ተሹመዋል።  በብሉይ ኪዳን ዘመን ለአሕዛብ የሚሰበክ ወንጌል ሰላልነበረ፥ አገልግሎቱ የሚያካትተው ከእግዚአብሔር የተሰጡትን ሥርዓቶች በመገናኛው ድንኳን ወይም ቤተ መቅደስ ውስጥ ማከናወንን ብቻ ነበር። ከዚህ ጋር ሲነጻጸር፥ የአዲስ ኪዳን የክህነት አገልግሎት በደረጃው የላቀና ሰፊ ነው። ይኸውም እግዚአብሔርንና ሌሎች አማኞችን ብቻ ሳይሆን፥ በሁሉም ስፍራ የሚገኙ ሰዎችን ሁሉ የሚያጠቃልል መሆኑ ነው።  1. የመሥዋዕት አገልግሎት በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ተመሳሳይ ነበር። አንድ የብሉይ ኪዳን ካህን የሚቀደሰው ወይም የሚለየው፥ በሌዊ የካህንነት ቤተሰብ ውስጥ በመወለድና በተገቢው ሥርዓት ለክህነት አገልግሎት በመሾም ነበር። ሹመቱም ተሿሚው በሕይወት እስካለ ድረስ የጸና ነው። ካህኑ በአገልግሎቱ መጀመሪያ ላይ አንድ ጊዜ ለዘላለም በመታጠብ እንዲነጻ ይደረጋል (ዘጸ. 29፡4)።  የብሉይ ኪዳኑ ካህናት አገልግሎታቸውን በመንጻት እንደሚጀምሩ፥ በአማናዊነት የሚፈጽም የአዲስ ኪዳን አማኝ ካህን” ድነትን ሲያገኝ ለአንዴና ለዘላለም በመንጻት ነው እገልግሉቱን የሚጀምረው (ቆላ. 2፡13፤ ቲቶ 3፡5)። ከድነቱም የተነሣ ለእግዚአብሔር ተለይቷል። እንደዚሁም በአዲስ ልደት አማካይነት እግዚእብሔር ቤተሰብ ሆኗል። ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ፥ የአዲስ ኪዳን ካህን በፈቃደኝነት ራሱን ለእግዚአብሔር መስጠቱ የተለየ መመዘኛ ሆኖ የሚታይ ነው።  ራስን ስለ መስጠት፥ “እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ” (ሮሜ 12፡1) የሚል ቃል እናነባለን። በእግዚአብሔር ርኅራኄ” የሚለው ሐረግ ሮሜ መጽሐፍ ውስጥ ቀደም ብሎ የተጠቀሱትን ታላላቅ የድነት እውነታዎች ያመለክታል። እያንዳንዱ እማኝ ድነት በሚያገኝበት ቅፅበት ይህንኑ ምሕረት ያገኛል። ሰውነትን እንደ ሕያው መሥዋዕት ማቅረብ የሚለው ቃል፥ አማኝ ራሱንና ያለውን ሁሉ ሰውዴታው ለእግዚአብሔር ፈቃድ መስጠቱን ያመለክታል። እግዚአብሔርም አማኙ የሚሰጠውን ሁሉ ተቀብሎ በፈቀደበት ስፍራ ላአገልግሎት ያስቀምጠዋል (ኤፌ. 2፡10)።  እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አገላለጥ፥ ይህ የመቀበልና ስፍራ የመስጠት ተግባር መቀደስ ነው። ስለሆነም፥ አማኝ-ካህን ራሱን ለእግዚአብሔር የመስጠት እንጂ፥ ራሱን ለእግዚአብሔር የመቀደስ ብቃት የለውም። የሚቀድስ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ከመለኮታዊ የመቀደስ ተግባር ጋር በተያያዘ፥ በአሁኑ ዘመን ኢየሱስ ክርስቶስ የአማኞችን አገልግሎት እንደ ሊቀ ካህን በመቀበል የተቀደሰ ያደርገዋል፥ ይህ በመምራትና ሰማዕተዳደር የሚያከናውነው ተግባር፥ የብሉይ ኪዳን ካህን የሌዊን ልጆች ሰሚቀድስበት አገልግሎት ውስጥ በጥላነት የተመለከተ መሆኑ ሊጤን ይገባል።  አማኝ-ካህን ራሱን ለእግዚአብሔር በመስጠትና ወደፊት ይህን ዓለም ሳለመምሰል፥ በውስጡ ሰሚያድረው መንፈስ ቅዱስ አማካይነት የተለወጠ ሕይወት ይኖረዋል። በዚያውም ኃይል አማካይነት “የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደሆነ” ፈጥኖ ሊያውቅ ይችላል (ሮሜ 12፡2)።  ሰእዲስ ኪዳን ሥርዓት፥ ሰመሥዋዕትነት ለእግዚአብሔር የሚቀርበው የክህነት አገልግሎት አራት ገጽታዎች አሉት፡- (ሀ) “ሰአእምሮ የሚመች አገልግሎት” (ሮሜ 12፡1) ወይም ደግሞ ይበልጥ በቀጥተኛ ትርጉም “መንፈሳዊ አምልኮ” የተባለው ራስን የመስጠት ተግባር። ራሱ ክርስቶስ መሥዋዕት አቅራቢና መሥዋዕት እንደነበረ ሁሉ፥ አማኙም ሰውነቱን በሙሉ ለእግዚአብሔር እንደ ሕያው መሥዋዕት በማቅረብ ሊያስከብረው ይችላል፤ (ለ) የከንፈር መሥዋዕት ማለትም የምሥጋና ድምፅ ባለማቋረጥ ሊቀርብ ይገባል (ዕብ. 13፡15)፣ (ሐ) የቁሳዊ ነገር መሥዋዕት (ፊልጵ. 4፡18)፣ (መ) የሰናይ ምግባራት መሥዋዕት (ዕብ. 13፡16)።  የካህናትን መንጻት አስመልክቶ፥ የብሉይ ኪዳን ካህን ወደ ቅዱስ አገልግሎቱ በሚገባበት ጊዜ ጠቅላሳ ሰውነቱን በመታጠብ አንድ ጊዜ ለዘላለም ይነጻ እንደነበር በድጋሚ መገንዘቡ አስፈላጊ ነው። ይህም የመታጠብ ተግባር በራሱ በካህኑ ሳይሆን በሌላ ሰው ይከናወን ነበር (ዘዳ. 29፡4)። ከዚያ በኋላ፥ ምንም እንኳን ሰውነቱን ሁሉ የታጠበ ቢሆን፥ በተደጋጋሚ ከፊል የመታጠብ ተግባሩን ሐስ ሳህን ላይ እንዲያከናውን ይጠየቃል። ይህም የትኛውንም የክህነት አገልግሎት ከማበርከት አስቀድሞ ይከናወናል። የዚህን ምሳሌያዊ ጠቀሜታ ለመፈጸም፥ የአዲስ ኪዳን ካህን ምንም እንኳ ድነትን ባገኘ ጊዜ የነጻና ይቅርታ የተደረገለት ቢሆን፥ ሁልጊዜ ልቡ የሚያውቃቸውን ኃጢአቶች መናዘዝ ይኖርበታል። ይህ የሚሆንበት ምክንያቱ ለመንጻትና ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት የማድረግ ብቃት ይኖረው ዘንድ ነው (1ኛ ዮሐ. 1፡9)። የብሉይ ኪዳን ካህን ሹመት ለዘላለም እንደሆነ ሁሉ፥ የአዲስ ኪዳን ካህንም ለዘላላም የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው።  2. የአምልኮ አገልግሎት በቀጣዩ ምዕራፉ ውስጥ በስፋት ይቀርባል)፥ በአሁኑ ዘመን የእያንዳንዱ አማኝካህን የአገልግሎት ሕይወት ክፍል እንደን መመልከት ይቻላል። በብሉይ ኪዳን የሁሉም ካህን አገልግሎት እንደነበረው ማለት ነው። የተቀደሰው ስፍራ አሠራሮች በብሉይ ኪዳን ሥርዓት የካህኑን እምልኮ ሰተምሳሌትነት እንደሚያመለክቱና፥ የስፍራው ገጽታና አሠራር ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደሚናገር፥ የእማኝም አምልኮ በክርስቶስ አማካይነት ብቻ የሚሆን ነው። አሁንም በአገልግሎት መልክ ለእግዚአብሔር የሚቀርሰው የአማኝ አምልኮ፥ ራስን ለእግዚአብሔር ማቅረብ (ሮሜ 12 ፡1)፥ ከልብ የመነጨ ምስጋናና ውዳሴ ለእግዚአብሔር መሠዋት (ዕብ. 13፡15)፥ ወይም የመሥዋዕትነት ስጦታዎችን ለርሱ ማቅረብ ሊሆን ይችላል።  ከብሉይ ኪዳን ካህናት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ሁኔታ ሁለት የተከለከሉ ነገሮች ተመዝግበዋል። እነዚህም ተምሳሌታዊ ፍች አላቸው። “እንግዳ” ወይም ሌላ ዕጣን ማቅረብ አይቻልም (ዘዳ. 30፡9)። ይህም ለእግዚአብሔር በሚቀርብ አገልግሎት ውስጥ ልባዊ ያልሆነ ሥርዓትን ያመለክታል። “እንግዳ” ወይም ሌላ እሳት ማቅረብም አይቻልም (ዘሌዋ. 10፡1)። ይህ ደግሞ ለክርስቶስ በመንፈስ አማካይነት እውነተኛ መሰጠት ሊኖረን ሲገባ፥ ሥጋዊ ስሜቶችን መተካትን ወይም ለክርስቶስ ልንሰጠው የሚገባንን ፍቅር በተራ ነገሮች መሸፈንን በተምሳሌትነት የሚያሳይ ነው (1ኛ ቆሮ. 1፡11-13፤ ቆላ. 2፡8፥16-19)።  3. በቀጣዩ ምዕራፍ ውስጥ የምንመለከተው የምልጃ አገልግሎትም ካህን የተሳለው እማኝእስፈላጊ ተግባር ነው። ነቢይ ለሕዝቡ የእግዚአብሔር ወኪል እንደሆነ ሁሉ፥ ካህን ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ የሕዝብ ወኪል ነው። ክህነት መለኮታዊ ሹመት እንደመሆኑ፥ ሁልጊዜም ወደ እግዚአብሔር የመቅረቢያው መንገድ ነበር። ቢሆንም በብሉይ ኪዳን ዘመን ካሊቀ ካህናቱ በቀር የትኛውም ካህን ወደ ቅድስተ ቅዱሳን እንዲገባ አይፈቀድለትም ነበር። እርሱም ቢሆን በዓመት አንድ ጊዜ የመሠዊያ ደም ይዞ ነበር የሚገባው (ዕብ. 9፡7)።  በዚህ ሥፍረ-ዘመን ክርስቶስ እንደ ሊቀ ካህን በራሱ ደም ወደ ሰማያዊቷ መቅደስ ገብቷል (ዕብ. 4፡14-16፤ 9፡24፤ 10፡19-22)። ስለሆነም የርሱ ለሆኑትና በዓለም ለሚገኙት በመማለድ ላይ ነው (ሮሜ 8፡34፤ ዕብ. 7፡25)። ክርስቶስ በሞተበት ቅፅበት የቤተ ክርስቲያን መጋረጃ ለሁላት ተቀዷል። ይህም ለዓለም ሳይሆን በፈሰሰው የክርስቶስ ደም በኩል ወደ እግዚአብሔር ለሚመጡ ሁሉ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚወስደው መንገድ እንደተካፈተ ያመለክታል (ዕብ. 10፡19-22)።  የአዲስ ኪዳን ካህን ከክርስቶስ ደም የተነሣ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ስለሚችል፥ በምልጃ የማገልገል ዕድል አለው (ሮሜ 8፡26-27፤ ዕብ. 10፡19-22፤ 1ኛ ጢሞ. 2፡1፤ ቆላ. 4 ፡12)።  ለ. የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ለሰው  ሮሜ 12፡1-8 ውስጥ የተጠቀሰው እውነት በመለኮት የተደረገ የቅደም ተከተል እቀማመጥ አለው። በሌሎችም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንደተመለከተውና፥ በዚህ ክፍልም እንደተጠቀሰው፥ የመሰጠትና የቅድስና ሕይወት እስካልታዩ ድረስ ክርስቲያናዊ አገልግሎት የተባለ ነገር አይኖርም። እነዚህን መሠረታዊ ነገሮች ተከትሎ መለኮታዊ ጸጋ ስጦታዎች ለአገልግሎት ተሰጡ። ከዚሁ ጋር በተገናዘበ ሁኔታ መጽሐፍ ቅዱስ “ስጦታ” የሚለውን ቃል በሚጠቀምበት መንገድና በተለመደው አገላለጥ መካከል ያለውን ሰፈ ልዩነት

ቤተ ክርስቲያን፡- አገልግሎቷና አደራዋ Read More »

ቤተ ክርስቲያን፡- ዓላማና ተልእኮዋ

This entry is part 36 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

በአሁኑ ዘመን እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን አማካይነት ጥበቡንና ጸጋውን ለሰማያዊ ሠራዊት በመግለጥ ላይ ነው (ኤፌ. 3፡10)። ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ጸጋ ምን ሊሠራ እንደሚችል ለመግለጥ ምስክር ሆና ትቀርባለች (ኤፌ. 2፡7)። በዚህ ጠለቅ ባለ አገላለጥ መሠረት የቤተ ክርስቲያን መለኮታዊ ተልእኮ ከአጠቃላዩ አካል ይልቅ ለእያንዳንዱ አማኝ የተሰጠ ነው። እንደ ቤተ ክርስቲያን ራስነቱ ክርስቶስ እያንዳንዱን አማኝ በጌታ ፈቃድ መንገዶች የመምራት ብቃት አለው። ይህ የሚሆነው ከግል ስጦታዎቹና እግዚእብሔር ለግሰሰቡ ሕይወት ካለው ዓላማ ጋር በተስማማ መልኩ ነው። ይህ ሁሉ ታዲያ እግዚእብሔር በአሁኑ ዘመን ለቤተ ክርስቲያን ካለው እጠቃላይ ዓሳማ ጋር በመስማማት ይካሄዳል። ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአጠቃላይ እግዚአብሔር የአሁኝ መለኮታዊ ዓላማውን ሰመፈጸም ላይ ሲሆን፥ ይህም ልክ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈው በመከናወን ላይ ነው፡፡  ሀ. ዓለም ውስጥ የአሁኑ መለኮታዊ ዓላማ  የዚህ ዘመን መለኮታዊ ዓላማ ዓለምን መለወጥ አይደለም። ይልቁንም በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው የክርስቶስን አካል፥ ማለትም ቤተ ክርስቲያንን የሚመሠርቱ ሰዎች መጥራት ነው። ዓለም የምትለወጥና በምድር ላይ የጽድቅ መንግሥት የሚመሠረት መሆኑ እውነት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ይህ እውነት በክርስቲያን አገልግሎት የሚመጣ አይደለም። ይህ የሚፈጸመው ክርስቶስ ሲመላስና የእርሱ በአካል መገኘትና የዓለምን ሥርዓት በመለወጥ ኃይሉ በግልጥ በሚሠራበት ወቅት ነው።  የሰማይ አምላክ በምድር ላይ ዘላለማዊ መንግሥት የሚመሠርተው (በዳን. 2፡44-45)፥ የክርስቶስ ተምሳሌት ያለው ድንጋይ መፈንቀል የሚያመለክተው አሳብ ፍጻሜ ካገኘ በኋሳ ነው። ጌታ ተመልሶ ከክብር ዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ በኋላ ሰቀኙ የሚቆሙ በጎቹን ወደተዘጋጀላቸው ምድራዊ መንግሥት ይመራቸዋል (ማቴ. 25፡31-34)። በተመሳሳይ ሁኔታ፥ ክርስቶስ በምድር ላይ ለሺህ ዓመታት የሚነግሠው ከሰማይ ሲመጣ በግልጥ ከታየ ሰኋላ ነው (ራእይ 19፡11-20፡9ን ከሐዋ. 15 ፡13-19፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡20-25 ጋር ያነጻጽሩት)።  የዚህን ዘመን ልዩ ገጽታዎች አስመልክቶ (ማቴ. 13፡1-50) ጌታችን ሦስት ዓበይት ሁኔታዎችን ገልጧል፡- (1) እስራኤል በዓለም ያላት ስፍራ ለእርሻ ውስጥ እንደተሸሽገ መዝገብ ይሆናል (ማቴ. 13፡44)፤ (2) ክፋት እስከ ዘመኑ ፍጻሜ ይቀጥላል (ማቴ. 13፡4፥ 25፥ 33+ 48)፤ (3) በስንዴ፥ የከበረ ዋጋ ባላት ዕንቁና በመልካም ዓሣ የተመሰሉት የመንግሥት ልጆች ይሰበሰባሉ (ማቴ. 13፡30፥ 45፥ 46፥ 48)።  – ከነዚህ ሦስት የዘመኑ ባሕርያት የመጨረሻው ወይም የመንግሥት ልጆች መሰባሰብ በአሁኑ ዘመን የእግዚአብሔር ዋነኛ ዓላማ መሆኑ ተገልጿል። በዚሁ መሠረት ሮሜ 11፡25 ውስጥ እንደተገለጠው፥ የአሁኑ ዘመን የእስራኤል ዕውርነት የሚቆየው፥ እስከ ቤተ ክርስቲያን ዘመን ፍጻሜ (ኤፌሶን 1፡22-23ን ተመልከት)፥ ማለትም እግዚአብሔር አሕዛብን እየጠራበት ያለው ልዩ የበረከት ዘመን እስከሚያበቃ ብቻ ነው።  እንደዚሁም “የዓመፅ ምሥጢር” ወይም በአሁኑ ዘመን የሚታየው ክፋት የእግዚአብሔር መንፈስ ስፍራ እስኪሰቅለት ድረስ ማዕቀብ ያሰበት ቢሆንም፥ የሚቀጥል መሆኑ ተገልጧል (2ኛ ተሰ. 2፡7)። መንፈስ ቅዱስ የሚሄደው የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ ከፈጸመ በኋላ ብቻ እንደመሆኑ፥ የእግዚአብሔር ቀጣይ ዓላማ በዓለም ክፋትን ማሻሻል ሳይሆን፥ የሚያምኑትን ሁሉ መለየት ነው። የእስራኤል ቃል ኪዳኖች ገና ይፈጸማሉ (ሮሜ 11፡27 ፥ ክፋት ከምድር ይወገዳል (ራእይ 21፡1)። የአሁኑ የእግዚአብሔር ዓላማ ቤት ክርስቲያንን ወደ ሙላቱ ማድረስ ነው።  ሐዋርያት ሥራ 15፡13-19 ውስጥ እንደተገለጠው፥ የያዕቆብ ንግግር ፍሬ አሳብ ኢየሩሳሌም ውስጥ በተካሄደው የመጀመሪያ ጉባኤ ፍጻሜ ላይ ተብራርቷል። ጉባኤው የተጠራው ከአሁኑ የእግዚአብሔር ዓሳማ ጋር በሚመሳሰለው ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ነበር። በመጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በብዛት የሚገኙት አይሁዶች በመሆናቸው፥ ይህ አዲስ ወንጌል ወደ አሕዛብ መድረሱን እየተመለከቱ አይሁድነታቸው ምን የተለየ ነገር እንዳለው ግራ አጋብቷቸው ነበር። ያዕቆብ የጴጥሮስን ልምምድ በመመርኮዝ ጴጥሮስ አሕዛብ በነበረው ቆርኔሌዎስ ቤት በመገኘት ያከናወነው ነገር የሚያመለክተው፥ እግዚአብሔር ሕዝብን ለራሱ ይሰበስብ ዘንድ መጀመሪያ አሕዛብን በመጎብኘት ላይ እንዳለ የሚያሳይ ነው ብሏል። ያዕቆብ ከዚያ በኋላ፥ ጌታ እንደሚመለስና ለእስራኤልም ሆነ ለአሕዛብ ዓላማዎቹን ሁሉ እንደሚያሟላ በመግለጥ ንግግሩን ቀጥሏል።  ይህ ሁሉ ጥናት ለዚህ ጉዳይ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ቢኖር፥ በአሁኑ ዘመን ግለሰብ አማኝ ዓለምን ለማሻሻል በእግዚአብሔር ያልተሾመ መሆኑን ነው። የአማኝ መጠራት ለክርስቶስና ለሚያድን ጸጋው በዓለም ሁሉ ምስክር ይሆን ዘንድ ነው። በዚህ የወንጌል ስብከት አገልግሎት አማካይነት ነው የእግዚአብሔር መንፈስ የዘመኑን ድንቅ ዓላማ ከግቡ የሚያደርሰው።  ለ. የቤተ ክርስቲያን አመሠራረት  ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያኑን እንደሚመሠርት ተንብዮ ነበር (ማቴ. 16፡18)። ሐዋርያው ጳውሎስም ቤተ ክርስቲያንን “ሕንጻ ሁሉ እየተጋጠመ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስታ ወደ መሆን ከሚያድግበት ሕያው ድንጋይ ጋር አነጻጽሯታል። “በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ ቅዱስ አብራችሁ ትሠራላችሁ” (ኤፌ. 2፡21-22)። የአማኙ የነፍሳት ምርኮኛ የክርስቶስን አካል የማነጹ አገልግሎትም የሚቀጥል ይሆናል። ይህ ለዘላለም ሳይሆን “ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ ነው (ኤፌ. 4፡13)። የክርስቶስ የሙላቱ ልክ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው፥ ሰዎች ክርስቶስን ወደ መምሰል ማደጋቸውን ሳይሆን፥ የክርስቶስ እካል ወደ ፍጻሜው ማደጉን ነው (ኤፌ. 1፡22-23)። ኤፌሶን 4፡16 ውስጥም የአካሉ ክፍሎች ልክ እንደ ሰብአዊ አካል ሕያው ሕዋሳት፥ የማያቋርጥ የነፍሳት ምርኮ ተግባር እንደሚፈጽሙና በዚህም አካሉን የሚያሳድጉ የመሆኑ እውነት ተገልጧል።  ሐ. የአማኙ ተልእኮ  ክርስቶስ የዚህ ዘመን መግለጫ በሆነው ዙር የመዝራት ምሳሌ፥ ከእራቱ እጅ እንዱ “ስንዴን እንደሚያስገኝ ተንብዮአል (ማቴ. 13፡1-23)። ምንም እንኳ የወንጌሉ ስብከት ከሕይወትም ሆነ ከሞት ጋር የሚዛመድ ቢሆን (2ኛ ቆሮ. 2፡16)፥ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ እማኝ የጠፉትን ለመመለስ በጊዜውም አለጊዜውም እንዲተጋ ተልኳል። እምነት ከመስማት፥ መስማትም ከእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ በመገንዘብ (ሮሜ 10፡17)፥ ወደ ዓለም ሁሉ እኝዲሄድና ለፍጥረት ሁሉ ወንጌልን እንዲሰብክ ተሹሟል (ማር. 16፡15)። በተጨማሪም፥ ሰከርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ዮነበረው እግዚአብሔር የማስታረቅን ቃል የሰጠን መሆኑ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡19 ውስጥ ተገልጧል። እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልእክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን” (2ኛ ቆሮ. 5፡20)።  ይህ አገልግሎት አማኞች ሁሉ ሊፈጽሙት የሚገባና፥ በብዙ መንገዶች ተግባር ላይ የሚውል ነው።  1. ወጎጌልን ለዚሁ ዓላማ ስምንሰጠው ገንዘብ አማካይነት ላልዳነ ሰው ማሰራጨት ይላል። ነፍሳትን ለክርስቶስ ለመማረክ የሚሹ ትጉህ አማኞች መኖራቸው የተረጋገጠ ቢሆንም፥ ለዚህ ዓላማ ከፍጻሜ መድረስ የሚፈለግባቸውን የገንዘብ ስጦታ ለማቅረብ ደግሞ ቸል የሚሉ መኖራቸውም እውን ነው። መልእክተኛው እስካልተላከ ድረስ አያሄድም። የሚልከውም በመሄድ ከሚያገለግል ጋር ዘላለማዊ ብድራትን ይካፈላል።  2. ወንጌል ላልዳነ ሰው የጸሎት መልዕ ህኖ ሊቀርብ ይችላል። “ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ” (ዮሐ. 14፡14) ያለው ጌታ ለጸሎት መልስ በመስጠት ሠራተኞችን ወደ መከሩ እንደሚልክ የሚያረጋግጥ ነው። የእግዚአብሔር ልጅ ለሆነ አንድ አማኝ ከጸሎት የላቀ ፍሬያማ እገልግሎት እንደሌለ በቀላሉ ተረጋግጧል። በዚህ አገልግሎት ነፍሳት እንደሚድኑ የሚገነዘቡ ግን በጣም ጥቂት ብቻ ናቸው።  3. ወኝጌል ላልዳነ ሰው በቃል ሊቀርብለት ይችላል። ሁሉም ለዚህ ተግባር የተላኩ እንደመሆናቸው፥ የሚከተሉትን ነገሮች በሚገባ ማስተዋል ወሳኝ ነው። (ሀ) መልእክተኛው መንፈስ ቅዱስ በሚያኖረው ስፍራ ሁሉ ለመሆን መፍቀድ አለበት፤ (ላ) እንዲያውጅ የተሾሙባቸውን የጸጋ ወንጌል እውነቶች መማር አለበት! (ሐ) በመንፈስ ቅዱስ መሞላት አለበት። ይህ ካልሆነ ለሚጠፉ ነፍሳት ምርኮ አገልግሎት ያለ ፍርሃትና ያለ ድካም እንዲነሣሣ የሚገፋፋ ፍቅር ሊኖረው አይችልም። ክርስቶስ፥ “መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ … ምስክሮቼ ትሆናላችሁ” (ሐዋ. 1፡8) ብሏል። ይህ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ከሌለ፥ ወንጌሉን የመመስከር አደራ አይኖርም። በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ አማኝ ግን መለኮታዊ ርኅራኄ ከውስጡ እየፈሰሰ ዝም ሊል አይችልም (ሐዋ. 4 ፡20)።  4. በተጨማሪም ወንጌል እንደ ሥነ-ጽሑፍ፥ ሬድዮ፥ ቴሌቪዥንና መንፈሳዊ መዝሙሮች በመሳሰሉት መንገዶች ሊቀርብ ይችላል። ዘዴው ምንም ይሁን ምን፥ እውነቱ መንፈስ ቅዱስ በሚገለገልበት መንገድ ሁሉ ሊቀርብ ይገባል።  5. እግዚአብሔር ወንጌልን ለማሰራጨት በሌሎች ብዙ መንገዶች እንደሚጠቀም ጥርጥር የለውም። ምንም እንኳ እያንዳንዱ ክርስቲያን ወንጌልን በቀጥታ በመስበክ እኩል ስኬታማ ባይሆንም፥ ወንጌል ለሰው ሁሉ መሰበኩን በማረጋገጡ ረገድ የሚጋራው ኃላፊነት አለ፡፡ ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ

ቤተ ክርስቲያን፡- ዓላማና ተልእኮዋ Read More »

ቤተ ክርስቲያን፡- ምእመኖቿ

This entry is part 35 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. ቤተ ክርስቲያን- የዚህ ዘመን የእግዚአብሔር ዓላማ  ቤተ ክርስቲያን የዚህ ዘመን የእግዚእብሔር ማዕከላዊ ዓላማ መሆኗ እዲስ ኪዳን ውስጥ ተገልጧል። እግዚአብሔር ለብሉይ ኪዳን ግለሰቦችና አገሮች ከነበሩት ዓላማዎችና ለእስራኤልም ከነበረው ሰፋ ያለ ዓላማ ጋር ሲነጻጸር፥ ቤተ ክርስቲያን ከሌሎች ሕዝቦችና ከአይሁዶች የተዋቀረች የአማኞች አንድነት ሆና ተገልጣለች። እነዚህም ከዓለም ተጠርተው በመውጣት በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካይነት ሕያው አንድነት የተሳሰሩ ናቸው።  በአጠቃላይ፥ የቤተ ክርስቲያን ፅንሰ-አሳብ በሁለት ዓበይት ምድቦች ይከፈላል። አዲስ ኪዳን ውስጥ የምንመለከተው የመጀመሪያ ፅንሰ-አሳብ፥ ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ውስጥ የሚገኙ እውነተኛ አማኞች ሁሉ ሕያው ጥምረት መሆኗን ነው። ይህም መንፈስ ቅዱስ ከወረደበት ዕለተ ጰንጠቆስጤ አንሥቶ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያኑ ዳግም በመመለሱ የሚደመደም ልዩ እውነት ነው። ጌታ በሚመለስበት ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ከዓለም መነጠቅ ወደ ሰማይ ትወሰዳለች።  ሌላው ፅንሰ-አሳብ፥ ስለ አጥቢያ ወይም ስለ ተደራጀች ቤተ ክርስቲያን የተገለጠው ነው። ይህ በአንድ አጥቢያ የሚገኙ አማኞች ወይም ይህን የመሰሉ ጉባኤዎች የአማኞች ስብሰብ ነው (1ኛ ቆሮ. 1፡2፤ ገላ. 1፡2፤ ፊልጵ. 1፡1)።  ቤተ ክርስቲያን” የሚለው ቃል “ኤክሌዢያ” ከሚለው ግሪክኛ የተተረጎመ ሲሆን፥ ቃሉ ለየትኛውም ዓይነት የሕዝቦች ስብሰባ ወይም ጉባኤ በተደጋጋሚ አገልግሏል። የተሰብሳቢዎቹ ዓላማ ሃያማኖታዊ ወይም ፖለቲካዊ ሊሆን ይችላል። የቃሉ ፍች ደተጠርተው የወጡ” ማለት ነው። በጥንታዊቱ ግሪክ፥ ብዙዎቹ ከተሞች የሚተዳደሩት ነጻ በሆን ዲሞክራሲ ነበር። በመሆኑም፥ እያንዳንዱ ዜጋ በጋራ ጉዳዮች ላይ ተግባራዊ እርምጃ ሰመውሰድ ይሰበሰባል። ከወትሮው ተግባራቸው ድምፅ ወደሚሰጡበት ስብሰባ ተጠርተው ሲመጡ፥ ቃሉ፥ ተጠርቶ የመውጣት ውጤት ወይም የተሰበሰቡ ሰዎች የሚል ፍች ሊሰጠው በቃ።  ይህ ቃል የብሉይ ኪዳን የተለያዩ ጉባኤዎችን ለማመልከት የብሉይ ኪዳን የግሪክ ትርጓሜ በሆነው ሰፕቱዋጄንት ውስጥ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል። እንደ የሐዋርያት ሥራ 7፡38 እና 19፡32 በመሳሰሉ ምንባቦች ውስጥ የሰዎችን ስብስብ በሚገልጥ መልኩ ተጠቅሶ እናገኛለን። ይሁንና ቃሉ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ክርስቶስ አካል ለማመልከት በሚያገለግልበት ጊዜ ከዓለም ተጠርተው በክርስቶስ ሕያው ኅብረት የፈጠሩ ሰዎችን ለማመልከት ያገለግላል። ምንም እንኳ እስራኤላውያን አንዳንድ ጊዜ ለሃይማኖታዊ ዓላማዎች መሰባሰባቸው ቢታወቅ፥ ይሄ ፅንሰ-አሳብ ብሉይ ኪዳን ውስጥ አይገኝም። ቃሉ የዳኑትን በሚያመለክትበት ጊዜ ደግሞ የሚያመለክተው፥ በአሁኑ ዘመን በምድርም ሆነ ሰሰማይ ድነት ያገኙት ሰዎች ኅብረት ነው።  ለ. ቤተ ክርስቲያን- የአዲስ ኪዳን መገለጥ  ዘላሰማዊ ሕይወት በማግኘት የተባበሩ አይሁዳውያንና አሕዛብ ያሉበትን ቤተ ክርስቲያን ፅንሰ-አሳብ ከብሉይ ኪዳን ውስጥ አናገኝም፤ አዲስ ኪዳን ብቻ ነው የዚህን ዋና ጉዳይ መለኮታዊ መገለጥ የሚያስጨብጠን። በእግዚአብሔር ዕቅድ ውስጥ መጀመሪያ የክርስቶስ መምጣት፥ በመስቀል ላይ መሞት፥ ከሞት መነሣትና ወደ ሰማይ ማረግ የግድ አስፈላጊ ክንውን ነበር። የመንፈስ ቅዱስ በበዓለ ኀምሳ ዕለት መምጣት ግን፥ እግዚአብሔር በአሕዛብና በእስራኤል መካከል ልዩነት ሳያደርግ ልዩ የአማኞች ኅብረት ለመፍጠር ያለውን ዓላማ እውን አደረገበት። በዚህም መሠረት በእስራኤልና በአሕዛብ መካከል ልዩነት ሳይደረግ ሁለቱም በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዓላማ ውስጥ ስፍራ አግኝተዋል።  በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ሁለት ውስጥ እንደተመለከተውና በዚሁ መጽሐፍ ምዕራፍ አሥር ቆርኔሌዎስ ገጠመኝ እንደተረጋገጠው፥ በክርስቶስ የሚያምኑ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀው (1ኛ ቆሮ. 12፡13) አንዳቸው የሌላው አባል ሆነዋል። ይህም በመንፈስ ቅዱስ መምጣት የተከናወነ ተግባር ነው። ከዕለተ በዓለ ኀምሳ በመለስ፥ እያንዳንዱ አማኝ ድነትን ሲያገኝ ቀደም ሲል በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ውስጥ እንደተገለጠው የክርስቶስ አካል ክፍል ይሆናል። ቤተ ክርስቲያን ዘመኗ ተፈጽሞ ወደ ሰማይ በምትነጠቅበት ጊዜ፥ መለኮታዊው ዓላማ በአይሁዶችና ሰአሕዛብ መካከል ወዳለው የተለመደ ልዩነት ይመለሳል። ይህ ከመነጠቅ በኋላ በሚኖረው የመከራ ወቅትና በሺህ ዓመቱ መንግሥት ውስጥ የሚያምኑትን አይሁዶችና አሕዛብ የሚመለከት ነው።  ሐ. አይሁድ፥ አሕዛብና ቤተ ክርስቲያን  በአሁኑ ዘመን፥ ሦስት ዓበይት ሰብአዊ ክፍፍሎች እንዳሉ መጽሐፍ ቅዱስ ይዘረዝራል። እነዚህም አይሁዶች፥ አሕዛብና ቤተ ክርስቲያን ናቸው (1ኛ ቆሮ. 10፡32)። እግዚአብሔር ለዚህ ዘመን ያለውን ዓላማ ለመረዳት እነዚህን ልዩነቶች ማጤኑ እጅግ  እስፈላጊ ነው።  1. አይሁዶች ወይም እስራኤላውያን ከአብርሃም አብራክ ወጥተው ለይስሐቅና በያዕቆብ የዘር ሐረግ የተዋለዱ ሲሆኑ፥ ከመለኮታዊ ዓላማና የተስፋ ቃል የተነሣ የተመረጡ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ናቸው። የአይሁድ ሕዝብ እስካሁን በተአምራዊ መንገድ ተጠብቆ የቆየ ሲሆን፥ በሚመጣው የእግዚአብሔር መንግሥት ዘመን በምድር ላይ ኃያልና የተከበረ ሕዝብ እንደሚሆን ትንቢቶች ያስረዳሉ (ኢሳ, 62፡1-12)።  ያህዌ ለነዚህ ሕዝቦች የገባላቸው ዘላለማዊ የተስፋ ቃላት ሊለወጡ አይችሉም። የተስፋ ቃላቱ ከሚያካትቷቸው ነገሮች መካክል ብሔራዊ ነጻነት (ኤር. 31፡36)፥ መሬት (ዘፍጥ. 13፡15)፥ ዙፋን (2ኛ ሳሙ. 7፡13) ፥ ንጉሥ (ኤር. 33፡20-21) እና መንግሥት (2ኛ ሳሙ. 1፡16) ይገኙባቸዋል። እነዚህ ምድራዊ ባሕርይ ያላቸው የተስፋ ቃላት በእግዚአብሔር ታማኝነት እስካዛሬ በመፈጸም ላይ ናቸው። ተስፋዎቹ ዘላለማዊ በመሆ ናቸው ለዘላለም እንዲሁ ይፈጸማሉ። በነዚህ ሕዝቦች የሚፈጸመውን የመለኮታዊ ዓላማ አሠራር የሚከተሉት አራት ቃላት ይገልጧቸዋል፡- “የተመረጡ”፥ “ተበተኑ”፥ “የተሰበሰቡ” እና “የተባረኩ”። አይሁዶች በእግዚአብሔር መመረጣቸውና አሁን በምድር ሕዝቦች ሁሉ መካከል መበታተናቸው ግልጥ ነው። መሰባሰባቸውና መባረካቸው ግን አይቀሬ ነው። የዚህ ሕዝብ ልዩ እገልግሎት ሮሜ 9፡4-5 ውስጥ ተገልጧል (ከዘፍጥረት 12፡3 ጋር ያነጻጽሩት)።  አሕዛብ እስራኤላውያንን ሳይጨምሩ ከአዳም ዘመን እሰከ ዛሬ የኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ሲሆንተቆጥረው እስከማይለቁ ድረስ እጅግ ብዙ ናቸው። ከተወሰኑ ግለሰቦች በስተቀር፥ ከአዳም እስከ ክርስቶስ ዘመን በነበረው የጊዜ ገደብ እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ምን ዓይነት ልዩ ግንኙነት እንዳደረገ ወይም ምን ዓይነት የቅርብ የተስፋ ቃላት እንዳደረገ የሚያመለክት ዘገባ አናገኝም። ወደፊት በምድር ላይ በሚመሠረተው መንግሥት ውስጥ ግን፥ አሕዛብ ታላቅ ምድራዊ በረከቶችን እንደሚያገኙ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ያመለክታሉ። በአሁኑ ዘመንም አሕዛብ ከእይሁዳውያን ጋር የወንጌሉ ዕድል ተካፋዮች ናቸው።  3. ቤተ ክርስቲያን ሚያመለክተው፥ የተደራጀችን አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እባልነት ሳይሆን፥ በአሁኑ ዘመን ያሚድኑትን ሰዎች አጠቃላይ ኅብረት ነው። እነዚህ ሰዎች የሚከተሉት ነጥቦች ምክንያት የተለዩ ናቸው።  ሀ) በዚያ ኅብረት ውስጥ የሚገኙ ግለሰቦች ሁሉ ዳግም የተወሰዱ በመሆናቸው፥ ወዷ እግዚአብሔር መንግሥት ይገባሉ (ዮሐ. 3፡5)። ክርስቶሰን ይመስሉ ዘንድም ከቀድሞው የተወሰኑ ናቸው (ሮሜ 8፡29)።  (ለ) ከእንግዲህ አዳምን ተከትለው የእሮጌውን ተፈጥሮ ውድቀት የሚካፈሉ አይሆኑም (2ኛ ቆሮ. 5፡17)። ይልቁንም ክርስቶስን ተከትለው እርሱ በትንሣኤው ሕይወትና ክብር የሆነውን ሁሉ የሚሆኑ እና የአዲሱ ተፈጥሮ ተካፋዮች ናቸው (ኤፌ. 1፡3፤ ቆላ. 2፡10)።  (ሐ) በእግዚአብሔር እይታ ዜግነታቸው ተለውጧል፤ ምክንያቱም ሰዎች አይሁዳዊ ወይም እሕዛብ ተብለው ወደማይለዩበትና ክርስቶስ ሁሉ በሁሉም ወደሆነበት አዲሰ ሕይወት መጥተዋልና(ቆላ. 3፡11)።  (መ) አሁን የሰማይ ዜጎች ስለሆኑ (ፊልጵ. 3፡20፤ ቆላ. 3፡3)፥ የተስፋ ቃላቶቻቸው፥ ሀብቶቻቸውና ሰፍራቸው ሰማያዊ ነው (2ኛ ቆሮ. 5፡17-18)። እነዚህ ሰማያዊ ዚጎች ከምድራውያኑ በብዙ አኳኋን ይለያሉ።  መ. ከአይሁድና ከአሕዛብ የተመሠረተች ቤተ ክርስቲያን  የአይሁዶችና የአሕዛብ ምድራዊ ስፍራ ቀደም ብሎ ተገልጧል። በተጨማሪም እግዚአብሔር በአሁኑ ዘመን ለጸጋው ዓላማዎች አሕዛብንም ሆነ አይሁዶችን በእንድ ዓይነት መሠረት ላይ ያስቀመጣቸው መሆኑን መገንዘቡ ተገቢ ነው (ሮሜ 3:9)። ሁሉም “ከኃጢአት በታች” መሆናቸውና መዳን የሚችሉት ሰጸጋ ብቻ መሆኑ ተገልጿል።  መለኮታዊው ፕሮግራም በክርስቶስ ሞት ተለውጧል። ይሄውም ከእንድ የተመረጠ ሕዝብ ይልቅ፥ አይሁድ ወይም አሕዛብ ሳይል ግለሰቦችን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መቀበሉ ነው። ይህ መለኮታዊ አሠራር አይሁዶች ሊገነዘቡ ያልቻሉት ነገር ነበር። ቃል ኪዳኖቹ ለጊዜው ወደ ጎን የተደረጉ እንጂ ያልተሻሩ መሆናችውን አልተረዱም። በሐዋርያት ሥራ ውስጥ እይሁዶች ይህን አለመረዳታቸውን የሚያሳይ አሳብ እናነባለን።  አይሁዶች ካላቸው የተሳሳተ መረዳት የተነሣ በዚህ ዘመን ያለውን የእግዚአብሔር ፕሮግራም እይቀበሉትም። ቤተ ክርስቲያን እስክትነጠቅ ድረስ አይሁዶች በዚህ አስተሳሰባቸው እንደሚቆዩም ትንቢት ተነግሯል (ሮሜ 11፡25)። ከዚያ በኋላ ነጻ አውጪው ከፅዮን ስመምጣት፥ አለማመንን ከያዕቆብ ቤት ያስወግዳል። እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን እንደሚያስወግድ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን የገባበት ጉዳይ መሆኑን ይህ ያመለክታል (ሮሜ 11፡26-27)። ያም ሆነ ይህ፥ አይሁዶችም ሆኑ አሕዛብ በወንጌል ስብከት በመዳን ላይ ናቸው። ቤተ ክርስቲያንም በዚህ በመሟላት ላይ ነች። ሐዋርያው ወንጌሉ መጀመሪያ ለአይሁዶች እንዲሰበክ ያስታወቀ ሲሆን (ሮሜ 1፡16)፥ የርሱም አገልግሎት ከዚሁ ፕሮግራም አኳያ የተዋቀረ ነው (ሐዋ. 17፡1-3)።  ቀደም ሲል እንደተገለጠው፥ ለሐዋርያው

ቤተ ክርስቲያን፡- ምእመኖቿ Read More »

መለኮታዊ ምርጫ

This entry is part 34 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. የምርጫ ውሳኔ  መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን የሚገልጠው፥ በራሱ ምርጫ ዓለማትን እንደፈጠረና አስቀድሞ ባቀደው መሠረት ታሪክን የሚመራ ፍጹም ሉዓላዊ አምላክ መሆኑን ነው። እግዚአብሔር ሉዓላዊና ደስ ያሰኘውን የማድረግ ብቃት ያለው መሆኑ የሚታመነው፥ ሁሉን ቻይና የማይደረስበት አምላክ ከመሆኑ አሳብ ጋር ተያይዞ ነው። ይሁንና ስለዚህ ዓይነቱ የእግዚአብሔር አሠራር የሰው ልጆች የሚኖራቸው የግንዛቤ አቅም ማነስ እጅግ ብዙ ችግሮችን ያስከትላል። በተለይም በእግዚአብሔር አሠራር በተፈጠረው ዓለም ሰው የቱን ያህል ሰነጻነትና በተጠያቂነት መሥራት የሚኖርበት መሆኑን መረዳቱ የዋዛ አልሆነም።  ሰብአዊ የአስተሳሰብ ዘዴዎች የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ዓላማ በፍጹማዊነት ወደሚስተናገድበት ወይም ደግሞ የእግዚአብሔር ቁጥጥር እስኪነጋ ድረስ የሰው ነጻነት ወደሚጋነንበት እክራሪ የአስተሳሰብ ዘዬዎች ሲያጋድሉ ኖረዋል። እንዲህ ዓይነቱን አስቸጋሪ ጉዳይ ለማቃለል ብቸኛው መፍትሔ፥ መለኮታዊውን መገለጥ መጠየቅና ሰብእዊውን ልምምድ መጽሐፍ ቅዱስ በሚያስተምረው መሠረት ለመፍታት መሞከር ነው።  መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተገለጠው፥ የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ዓላማ ግለሰቦችንም ሆነ አገሮችን ይመለከታል። እስራኤል በእግዚአብሔር የተመረጠ ሕዝብ መሆኑ ተገልጧል (ኢሳ. 45፡4፤ 65 : 9፥ 22)። “ምርጥ” የሚለው ቃል ለድነት ለተመረጡ ሰዎች መጠሪያነት በተደጋጋሚ አገልግሷል (ማቴ. 24፡22፥ 24፥ 31፤ ማር. 13፡20፥ 22፥ 27፤ ሉቃስ 18፡7፤ ሮሜ 8፡33፤ ቆላ. 3፡12፤ 1ኛ ጢሞ. 5፡21፤ 2ኛ ጢሞ. 2፡10፤ ቲቶ 1፡1፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡2፤ 5፡13፤ 2ኛ ዮሐ. 1 እና 13)። ስለ ክርስቶስም ይኸው አገላለጥ አገልግሏል (ኢሳ. 42፡1፤ 1ኛ ጴጥ. 2፡6)። “ምርጥ” ከሚለው ቃል በተጨማሪ የምርጫ እውነታም ተጠቅሷል (ሮሜ 9፡11፤ 11፡5፥ 7፥ 28፤ 1ኛ ተሰ. 1፡4፤ 2ኛ ጴጥ. 1፡10)። ምርጫ ውስጥ የሚገኘው ፅንሰ አሳብ የሚያመለክተው፥ የተጠቀሰው ግለሰብ ወይም ቡድን ላአንድ መለኮታዊ ዓላማ መመረጡን ሲሆን፥ ብዙውን ጊዜ ከድነት ጋር ይዛመዳል።  “ምርጥ” የሚለው ቃል ለእስራኤል (ኢሳ. 44፡1)፥ ለቤተ ክርስቲያን (ኤፌ. 1:4፤ 2ኛ ተሰ. 2: 13፤ 1ኛ ጴጥ.2፡9)፥ ለሐዋርያት መጠሪያነት (ዮሐ. 6፡70፤ 13፡18፤ ሐዋ. 1፡2) አገልግሏል።  ምርጫን በተመለከተ የተለያዩ ገለጣዎች አሉ፤ ለምሳሌ አስቀድሞ ማወቅን (ሮሜ 8፡29-30፤ ኤፌ. 1፡5፥ 11፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡20)፥ የመሳሰሉ በሐዋርያት ሥራ 4፡28 እንደተመለከተው ቅድመ ውሳኔን፥ ወይም ይሁዳ 4 እና ኤፌሶን 2፡10 ውስጥ እንደተጠቀሰው ቅድመ ስያሜን ያመለክታል። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደ 2ኛ ዜና 25፡16፥ ኢሳይያስ 19፡17፤ ሉቃስ 22፡22፥ የሐዋርያት ሥራ 17፡26 በመሳሰሉ ስፍራዎችም ይኸው “ውሳኔ” የሚለው ፅንሰ-አሳብ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል። በዚህ ሁሉ ቃላት ሊተላለፍ የተፈለገው መልእክት፥ የእግዚአብሔር ምርጫ ተግባርን የሚቀድምና በራሱ ሉዓላዊ ፈቃድ የሚወሰን መሆኑን ነው።  ምርጫ፥ ቅድመ ስያሜና ቅድመ ውሳኔ እንደ እግዚአብሔር መለኮታዊ ዓላማ የሚከናወኑ ሲሆኑ (ኤፌ. 1፡9፤ 3፡11)፡መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከእግዚአብሔር ቅድመ ግንዛቤ ጋር የተያያዙ ናቸው (ሐዋ. 2፡23፤ ሮሜ 8፡29፤ 11፡2፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡2)። “ጥሪ” የሚለው ቃልም ሮሜ 8፡30 እና ሌሎችም በርካታ ምንባቦች ውስጥ ተጠቅሷል (1ኛ ቆሮ. 1፡9፤ 1፡18፥ 20-21፥ 22፥ 24፤ 15፡9፤ ገላ. 5፡13፤ ኤፌ. 4፡1፥ 4፤ ቆላ. 3፡15፤ 1ኛ ጢሞ. 6፡12፤ ዕብ. 5፡4፤ 9፡15፤ 1ኛ ጴጥ. 2፡21፤ 3፡9፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡1)። “ጥሪ” ስዎችን ወደ እግዚአብሔር መሳብ መሆኑን ጌታችን ዮሐ፡12፡32 ውስጥ አመልክቷል (ከዮሐንስ 6፡44 ጋር ያነጻጽሩት)። እነዚህ ሁሉ ምንባቦች የሚያስገነዝቡን ሉዓላዊው አምላክ ዓላማውን በማሳካት ላይ መሆኑን ነው። የተወሰኑ ግለሰቦች በዚሁ ዓላማው መሠረት ለድነት የተመረጡ ሲሆን፥ የተወሰኑ ሕዝቦችም መለኮታዊውን ልዩ ዓላማ ለማሳካት እንዲሁ ተመርጠዋል። በተለይ እስራኤላውያን የተለየ መለኮታዊ ዓላማ ለማገልገል ተመርጠዋል።  ለ. የመለኮታዊ ምርጫ እውነትነት  ምንም እንኳ የምርጫ እስተምህሮ ከስብእዊ ግንዛቤ ሰላይ ሲሆን፥ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ መሆኑ ግን አያጠያይቅም። እግዚአብሔር በመለኮታዊ ምርጫው የተወሰኑ ግለሰቦችን ለድነት በመምረጥ፥ የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስን ባሕርይ ይመስሉ ዘንድ ወስኗል (ሮሜ 16፡13፤ ኤፌ. 1፡4-5፤ 2ኛ ተሰ. 2፡13፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡2)። ምርጫ ከእግዚአብሔር መሆኑና የዘላለማዊ ዕቅዱ እካል መሆኑ ግልጥ ነው።  መለኮታዊ ምርጫ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዓላማ አካል እንጂ፥ ሰው ከተፈጠረ በኋላ የተወሰነ አይደለም። ይህም “ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን” በሚለው ኤፌሶን 1፡4 እና ሌሎች ብዙ ምንባቦች ውስጥ ተገልጧል። 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡9 እንደሚለው ደግሞ፥ መመረጣችን “እንደራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው። ይህም ጳጋ ከዘላለም በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን።” የእግዚአብሔር ዕቅድ ዘላለማዊ በመሆኑ፥ ምርጫም በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዕቅድ ውስጥ ሆኖ ዘላለማዊ ነው።  ሰምርጫ አስተምህሮ ውስጥ ከሚገኙ ውስብስብ ችግሮች እንዱ ምርጫ ከቅድመ ግንዛቤ ጋር ግንኙነት ያለው መሆኑ ነው። የምርጫን ፅንሰ-አሳብ አለሳልሶ የሚያቀርሰው አንድ የአተረጓጎም ስልት፥ እግዚአብሔር በክርስቶስ የሚያምኑትን ቀደም ብሎ ያውቅ ስለነበር፥ በዚሁ እውቀት ላይ ተመሥርቶ ለድነት መርጧቸዋል በሚለው አሳብ ዙሪያ ትንታኔውን ያቀርባል። ይሁንና፥ ይህ አሳብ እግዚአብሔርን ራሱ ሉዓላዊ ላልሆነበት ዕቅድ ተገዥ አድርጎ የሚያቀርበው ስለሚመስል ችግሮች አሉበት። ምንም እንኳ ምርጫና ቅድመ ግንዛቤ ተያያዥነት ቢኖራቸው፥ ቅድመ ግንዛቤ በራሱ ወሳኝ አይሆንም።  ምንም እንኳ የሥነ-መለኮት ምሁራን ከነዚህ ችግሮች ጋር ታግለው ከአርኪ ድምዳሜዎች ላይ ለመድረስ ባይችሉ፥ መፍትሔ ሊሆን የሚችለው አንድ ነገር የእግዚእብሔርን ሁሉን አዋቂነት ማለት፥ ለዓለማት የሚያሻቸውን ዕቅድ ሁሉ እንደሚያውቅ ከመገንዘብ መጀመሩ ነው። ስፍር ካሌሳቸው ዕቅዶች ውስጥ እግዚአብሔር አንዱን መረጠ። አንድን ዕቅድ በመምረጥና የዕቅዱን ዝርዝር በማወቅ፥ እግዚአብሔር የሚድኑትንና የሚመረጡትን እስቀድሞ ሊያውቅ፥ ከድነታቸው ጋር የሚዛመዱ እውነታዎችንም ሊገነዘብ ይችላል።  ይህን የእግዚአብሔር ቃል ለመተርጎም የሚሞክር ሰው የሚገጥመው ችግር የሰው ልጅ ነጻነት ጉዳይ ነው። ከልምድም ሆኝ ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደሚታየው፥ ሰው ምርጫዎች አሉት። ይሁን እንጂ፥ ሁሉም ነገር አስቀድሞ የተወሰነበት ከሆነ፥ ሰው በራሱ ጤናማና ነጻ የሆነ ሥነ-ምግባራዊ ምርጫ ለማድረግ እንዴት ይቻላል? ይህ ከሆነስ ሰብአዊ ተጠያቂነት እንዴት ትዕከል ይሆናል? በዚህ አስቸጋሪ አስተምህሮ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚ የሚያጋጥሙት ችግሮች እነዚህ ናቸው።  የሥነ-መለኮት ምሁራን መለኮታዊ ምርጫ ከሰብአዊ ምርጫዎችና ሥነ-ምግባራዊ ተጠያቂነት ጋር በተዛመደ መልኩ ያለበትን ችግር እስከዛሬ ሙሉ በሙሉ ለማቃለል አልቻሉም። ይሁንና፥ ችግሩ እልባት የሚያገኘው፥ እግዚአብሔር የመረጠውን ዕቅድ በዘፈቀደ ሳይሆን፥ ሙሉ ለሙሉ በመምረጥ ይመስላል። ሰዕቅዱ ማን እንደሚድንና ማን እንደማይድን ዕቅዱን ከመምረጡ በፊት አውቋል። እግዚአብሔር ከሁሉም የተሻለውን ዕቅድ እንደመረጠ በእምነት መቀበል እለብን። ከዚህ የተሻለ ዕቅድ ቢኖር ኖሮ እግዚአብሔር ያን ይመርጥ ነበር። ዕቅዱ በአብዛኛው እግዚአብሔር ራሱ የሚሠራቸውን ነገሮች አካቷል። እነዚህም እንደ ፍጥረትና የተፈጥሮ ሕግ መደንገግን የመሳሰሉ ናቸው። ዕቅዱ እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ ራሱ የሚፈጽማቸውን ነገሮች፥ ማለትም በነቢያት አማካይነት ራሱን በመግለጥ ሰዎች ምንም እንኳ ስለምርጫቸው ተጠያቂ ቢሆኑ፥ መልካም ምርጫ እንዲኖራቸው ጫና ማድረግን የሚያካትት ነበር።  በሌላ አባባል፥ ዕቅዱ ሰው ስምርጫው በኃላፊነት የሚጠየቅበትን የተወሰነ ነጻነት አካቷል ማለት ነው፡እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ዕቅዱ ሰው ምን እንደሚያደርግ ማወቁ፥ እያንዳንዱ ሰው የማይፈልገውን እንዲያደርግ የሚያስገድደውና ለድርጊቱም የሚቀጣው መሆኑን አያመለክትም።  የእግዚአብሔር ዕቅድ ሁሉ በተካተተበት የክርስቶስ መስቀል ወቅት፥ ጲላጦስ በነጻነቱ ተጠቅሞ ክርስቶስን ለመስቀል መርጧል፤ ለዚህም ምርጫው ተጠያቂ ሆኗል። የአስቆሮቱ ይሁዳም ክርስቶስን አሳልፎ ለመስጠት ነጻ ውሳኔ አድርጓል። ነጻ ውሳኔውም በኃላፊነት እንዲጠየቅ አድርጎታል። ይሁንና፥ የይሁዳም ሆነ የጲላጦስ ምርጫዎች የእግዚአብሔር ፕሮግራም አካላት በመሆናቸው፥ ሰዎቹ ሳይፈጽሟቸው ሰፊት ይታወቁ ነበር።  ስለሆነም፥ ከሰብአዊ ግንዛቤ ረገድ ችግሮች ቢኖሩም፥ ከሁሉም የሚሻለው መፍትሔ ቢገባንም ሳይገባን መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን እውነት መቀሰሉ ነው።  ምርጫና ከዚሁ ጋር የሚመሳሰሉ ቃላት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጥ ቀርበዋል ብሎ ለመደምደም ይቻላል። ይህም አንዳንዶች ድነት እንደተመረጡና ሌሎች ግን ሳይመረጡ መታለፋቸውን የሚያመለከት ነው። ምርጫ ዘላለማዊ የእግዚእብሔር ተግባር ነው። ምርጫ ከእግዚአብሔር ሁሉን አዋቂነት ጋር ይያያዛል። ይህንን አስተምህሮ፥ ሙሉ ስሙሉ መረዳት ባይቻልም እንኳ፥ ስመለኮታዊው መገለጥ መገዛቱ ተገቢ ነው።  ሐ. የምርጫ አስተምህሮ መረጃ  ምንም እንኳን አንዳንድ የሥነ-መለኮት ምሁራን መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ክደው የምርጫን አስተምህሮ ሰማግለል ችግሩን ለመፍታት ቢጥሩ፥ መለኮታዊ ምርጫን በመቃወም የሚሰነዘሩ የመሟገቻ ነጥቦች ባብዛኛው አሳቡን ባለመረዳት ላይ የተመሠረቱ ናቸው። ብዙ ጊዜ ምርጫ እግዚአብሔር ያለ ምንም በቂ ምክንያት እንደሚሠራው ተደርጎ ይነገራል። ይህ አባባል

መለኮታዊ ምርጫ Read More »

የድነት ዋስትና

This entry is part 33 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምኑ ብዙ ሰዎች የድነት ዋስትና ያላቸው ስለመሆኑ እርግጠኞች ናቸው። ብዙ ጊዜ የሚነሣው ጥያቄ ግን፥ “አንድ ጊዜ የዳነ ሰው ድነቱን ሊያጣ ይችላልኝ?” የሚል ነው። ድነትን የማጣቱ ፍርኃት የአንድን አማኝ የአእምሮ ሠላም በከፍተኛ ደረጃ ስለሚጎዳና ለወደፊት ተስፋውም ወሳኝ ጉዳይ ስለሆ፥ ጥያቄው የድነት አስተምህሮ እጅግ ጠቃሚ ክፍል ነው።  አንድ ጊዜ የዳነ ሰው ድነቱን ሊያጣ ይችላል የሚለው አሳብ የተመሠረተው፥ የድነት ዋስትናን አጠያያቂ በሚያስመስሉ የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች ላይ ነው። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ፥ ሁለት ተቃራኒ የአተረጓጎም ዘዴዎች ተከስተዋል። እነዚህም የዘላለማዊ የድነት ዋስትና አስተሳሰብን የሚደግፉ የካልቪን ትምህርት ተከታዮችና፥ ይህን ፅንሰ-አሳብ የሚቃወሙ የአርሜኒዮስ ትምህርት ተከታዮች የሚያስተምሯቸው አስተምህሮዎች ናቸው።  ሀ. የአርሚኒያውያን የድነት ዋስትና አመለካከት  የአርሜኒያውያንን አመለካከት የሚከተሉ ሰዎች በቅድመ ሁኔታዎች ላይ የተመሠረተ የዋስትና አስተምህሮን ያረጋግጣሉ ብለው ያመኑባቸውን ሰማኒያ አምስት ያህል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ዘርዝረዋል። ከነዚህም መካከል ይበልጥ ጠቃሚዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡- ማቴዎስ 5፡13፤ 6፡23፤ 7፡16-19፤ 13፡1-8፤ 18፡23-35፤ 24፡4-5፥ 11-13፥ 23-26፤ 25፡1-13፤ ሉቃስ 8፡11-15፤ 11፡24-28፤ 12፡42-46፤ ዮሐ. 6፡66-11፤ 8፡31-32፥5 1፤ 13፡8፤ 15፡1-6፤ ሐዋ. 5፡32፤ 11፡21-23፤ 13፡43፤ 14፡21-22፤ ሮሜ 6፡11-23፤ 8፡12-17፤ 11፡20-22፤ 14፡15-23፤ 1ኛ ቆሮ. 9፡23-27፤ 10፡1-21፤ 11 ፡29-32፤ 15፡1-2፤ 2ኛ ቆሮ. 1፡24፤ 11፡2-4፤ 12፡21-13፡5፤ ገላ. 2፡12-16፤ 3፡4-4፡1፤ 5፡1-4፤ 6፡7-9፤ ቈላ. 1፡21-23፤ 2፡4-8፥ 18-19፤ 1ኛ ተሰ. 3፡5፤ 1ኛ ጢሞ. 1፡3-7፥ 18-20፤ 2፡11-15፤ 4፡1-16፤ 5፡5-15፤ 6፡9-12፥ 17-21፤ 2ኛ ጢሞ. 2፡11-18+ 22-26፤ 3፡13-15፤ ዕብ. 2፡1-3፤ 3፡6-19፤ 4፡1-16፤ 5፡8-9፤ 6፡4-20፤ 10፡19-39፤ 11፡13-16፤ 12፡1-17፥25-29፤ 13፡7-17፤ ያዕቆ. 1፡12-26፤ 2፡14-26፤ 4፡4-10፤ 5፡19-20፤ 1ኛ ጴጥ. 5፡9፥ 13፤ 2ኛ ጴጥ. 1፡5-11፤ 2፡1-22፤ 3፡16-17፤ 1ኛ ዮሐ. 1፡5-3፡11፤ 5፡4-16፤ 2ኛ ዮሐ. 6-9፤ ይሁዳ 5-12፥ 20-21፤ ራእይ 2፡7፥ 10-11  17-26፤ 3፡4-5፥ 8-22፤ 12፡11፤ 17፡14፤ 21፡7-8፤ 22፡18-19።  እነዚህን ምንባቦች ማጥናቱ አያሌ ጠቃሚ ጥያቄዎችን ያስነሣል።  1. ይህን ጉዳይ አስመልክቶ መጽሐፍ ቅዱስን ዮሚተረጉምን ሰው የሚገጥመው ጠቃሚ ጥያቄ ምናልባት እውነተኛው አማኝ ማነው? ቀሚለው ይሆናል። ብዙ ሰዎች የዘላለማዊ ዋስትና አስተምህሮን የሚቃወሙት አንድ ሰው ድነትን ሳያገኝ የአእምሮ እምነት ሊኖረው ይችላል በማለት ነው።  የዘላለማዊ ዋስትናን እሳብ የሚደግፉት ደግሞ አንድ ሰው በሕይወቱ ውጫዊ ለውጥ ሊታይ እንደሚችል ይስማማሉ። ሰውዬው የቤተ ክርስቲያን አባል በመሆን ወይም በመጠመቅ ክርስቶስን የመቀበል ውጫዊ እንቅስቃሴ ሊያሳይ፥ ከዚህም አልፎ በአኗኗሩ ላይ የተወሰነ ለውጥ ያሳይ ይሆናል፤ ዳሩ ግን በክርስቶስ እውነተኛ ድነት ላይኖረው ይችላል።  የዳነውን ካልዳነው ለመለየት የሚያስችል ደንብ መዘርዘር ባይቻልም፥ በእግዚአብሔር አእምሮ ምንም ዓይነት አጠያያቂ ነገር እንደማይኖር ግልጥ ነው። አማኙ ከሁሉም በፊት ክርስቶስን እንደ አዳኙ የተቀበለ ለመሆኑ እርግጠኛ መሆን አለበት። በዚህ ረገድ ክርስቶስን መቀበል ስለ ድነት መንገድ የተወሰነ እውቀት ሊያካትት የሚችል የፈቃደኝነት ተግባር እንደሆነና፥ በተወሰነ ደረጃም በስሜት ሊገለጥ እንደሚችል መረዳቱ ጠቃሚ ነው። መሠረታዊው ጥያቄ ግን፥ “እውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኜ አድርጌ ተቀብያለሁን?” የሚለው ነው። ይህ ጥያቄ ታማኝ መልስ ካላገኘ፥ ለዘላለማዊ የድነት ዋስትናም ሆነ፥ ለድነት ማረጋገጫ ምንም ዓይነት መሠረት ሊኖር አይችልም። የዘላለማዊ ዋስትናን ፅንሰ- እሳብ የሚቃወሙ ሰዎች ለይስሙላ የሆነ እምነት ለማዳን አይችልም ይላሉ። የዘላለማዊ ዋስትና ደጋፊዎችም ይህን እሳብ ይደግፋሉ። እዚህ ላይ በአግባቡ የሚሰነዘረው ጥያቄ፥ በትክክል የዳነና የዘላለም ሕይወት ያገኘ ሰው ድነቱን ያጣል ወይ? የሚለው ነው።  2. ዘላለማዊ ዋስትናን የሚቃወሙ ወገኖች የሚጠቅሷቸው ምንባቦች፥ ስለ ሰብአዊ ተግባራት ወይም ስለ ድነት መረጃ የሚናገሩ ናቸው። እውነተኛ ድነት ያገኘ ሰው በክርስቶስ ያገኘውን አዲስ ሕይወት በባሕርዩና በሥራ መግለጥ አለበት። ይሁንና፥ አንድን ሰው በሥራው መፍረድ ሊያታልል ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ክርስቲያኖች ያልሆኑ ሰዎች በአንጻራዊነት ከክርስትና ሕይወት ሥነ-ምግባር ጋር የሚነጻጸር ተግባር ሊያከናውኑ ይችላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ እውነተኛ ክርስቲያኖች የሆኑ አንዳንድ ሰዎች በሥጋዊነትና በኃጢአት ተጠምደው ድነትን ካላገኙ ሰዎች በማይለዩበት ሁኔታ ኃጢአት አዘቅት ውስጥ ይሰጥሙ ይሆናል። ሉቃስ 11፡24-26 ውስጥ የተጠቀሰው ዓይነት ሰዶ የግብረ ገባዊነት ተሐድሶ እውነተኛ ድነት እንዳልሆነና፥ ወደ ቀድሞው ሕይወት መመለስም ድነትን ማጣት እንዳልሆነ ሁሉም ይስማማሉ።  ክርስቲያናዊ የእምነት ምስክርነት በፍሬው መረጋገጥ እንዳለበት አያሌ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች ያስገነዝባሉ። ከእግዚአብሔር የሆነ ድነት ሰተራ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን በፍሬው ምንነቱን ያስመሰክራል (ዮሐ. 8፡31፤ 15፡6፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡1-2፤ ዕብ. 3፡6-14፤ ያዕ. 2፡14-26፤ 2ኛ ጴጥ. 1፡10፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡10)። ይህም ሆኖ፥ ሁሉም ክርስቲያኖች፥ ሁልጊዜ የድነትን ፍሬዎች አያሳዩ ይሆናል። በመሆኑም፥ ድነት በሥራ መረጋገጥ እንዳለበት የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የአማኙን ዋስትና አስተምህሮ የሚቃረኑ እይደሉም። ዋናው ጥያቄ እግዚአብሔር ሰውዬውን እንደዳነ ይቆጥረዋል ወይ? የሚለው ነው።  3. የአማኙን ዋስትና እልባነት ለማሳየት የተጠቀሱ ብዙ ምንባቦች፥ በክርስቶስ ዮማመኑ ጉዳይ ተራ ወይም የይምሰል እንዳይሆን ያስጠነቅቃሉ። አይሁዳውያን መሥዋዕቶችን የማቅረቡ ዘመን ስላለፈ ወደ ክርስቶስ እንዲመለሱ፥ ካልሆነ ግን እንደሚጠፉ አዲስ ኪዳን ውስጥ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል (ዕብ. 10፡26)። እንደዚሁም፥ ያልዳኑ አይሁዶችና አሕዛብ አብርሆትን ከሚሰጣቸውና ከሚለውጠው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ “እንዳይወድቁ” ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል (ዕብ. 6፡4-9)። መንፈሳዊ ያልሆኑ አይሁዶች በሚመጣው መንግሥት ተቀባይነት እንደማይኖራቸው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል (ማቴ. 25፡1-13)። ከእስራኤላውያን ቡድን አንጻር የአሕዛብ ቡድንም፥ ባለማመን ምክንያት በአሁኑ ዘመን ያሳቸውን የበረከት ስፍራ እንዳያጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል (ሮሜ 11፡21)።  4. እንዳንድ ምንባቦች የሚያነሡት ክድነት ጥያቄ ይልቅ የሽልማትን ጉዳይ ነው። በክርስቶስ አምኖ የዳነ ሰው ሽልማቱን ያጣ ይሆናል (1ኛ ቆሮ. 3፡15፤ ቈሳ. 1፡21-23)። ለክርስቶስ የሰጠው አገልግሎትም ዋጋ አይኖረውም (1ኛ ቆሮ. 9፡27)።  5. እውነተኛ ክርስቲያን በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ኅብረት ያጣ ይሆናል (2ኛ ዮሐ. 1፡6)። እንዲሁም ከድነቱ የተነሣ በዚህ ሕይወቱ ሊያገኛቸው የሚገባውን የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ማፍራትን (ገላ. 5፡22-23) እና ለክርስቶስ ውጤታማ አገልግሎት አበርክቶ እንደመርካት ያሉ መልካም ነገሮችን ይነፈጋል።  6. እውነተኛ ታማኝ ለኮብላይነቱ፥ ልጅ በአባቱ እንደሚቀባ ሁሉ፥ ይቀጣ ይሆናል (ዮሐ. 15፡2፤ 1ኛ ቆሮ. 11፡29-32፤ 1ኛ ዮሐ. 5፡16)። ቅጣቱም እስከ ሥጋዊ ሞት ሊደርስ ይችላል። ይሁንና፥ ይህ ቅጣት የድነት ማጣት ምልክት ሳይሆን፥ አማኙ የሰማይ አባቱ የሚቀጣው የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን የሚያመለክት ነው።  7. መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው፥ አንድ አማኝ ክጸጋ ይወድቅ ይሆናል (ገላ. 5 ፡1-4)። ይህ በአግባቡ ከተተረጎመ አማኝ ድነቱን የሚያጣ መሆኑን ሳይሆን፥ በአኗኗሩ ከጸጋ መመዘኛ እንደሚወርድና ወደ ሕግ ባርነት ሰመመለስ በክርስቶስ ያገኘውን እውነተኛ ነጻነት የሚያጣ መሆኑን ነው። ስለሆነም፥ አማኝ የሚወድቀው ከድነት ተግባር ሳይሆን፥ ከአኗኗር መመዘኛ ነው።  8. ብዙ ችግር የሚመጣው፥ ያለአገባባቸው የሚጠቀሱ ምንባቦች በተለይም ከሌላ ሥፍራዘመን ጋር የሚዛመዱ ምንባቦችን ከመጥቀስ የተነሣ ነው። በአዲስ ኪዳን ትምህርት ላይ ተመሥርቶ እውነተኛ ዳግም ልደት ያገኘ የብሉይ ኪዳን ቅዱስ፥ የአሁኑን ዘመን ያህል ዋስትና እንዳሰው ለመገመት ቢቻልም፥ ብሉይ ኪዳን ስለ ዘላለማዊ ዋስትና ግልጥ አመለካከት አያስጨብጥም። ቢሆንም፥ ካለፈው ወይም ከሚመጣው ሥፍረ-ዘመን ጋር የሚዛመዱና እንደ ሕዝቅኤል 33፡7-8 ያሉ ምንባቦች በአገባባቸው መሠረት ሊተረጎሙ ይገባል። እስራኤላውያን ሕግን ሰመታዘዝ ስለሚያገኙት በረከትና፥ ባለመታዘዝ ስለሚደርስባቸው መርገም የሚናገረውን ዘዳግም 28ን የመሰሉ ዋና ዋና ምንባቦችም ጥንቃቄ ሊደረግላቸው ይገባል። ሌሎቹ ምንባቦች የሚያመለክቱት በመጨረሻው ዘመን የሚነሡትን ሐሰተኛና ዳግም ልደት ያላገኙ አሰተማሪዎችን ነው (1ኛ ጢሞ. 4፡1-2፤ 2ኛ ጴጥ. 2፡1-22፤ ይሁዳ 17-19)። እንዲህ ያሉ ሰዎች የስም ክርስቲያኖች ሲሆኑም፥ ዳግም የተወለዱ አይደሉም።  9. የዋስትናን አለመኖር ለማገናዝብ ሲባል በስሕተት የተተረጎሙና ማቴዎስ 24፡13 ውስጥ ብስከ መጨረሻው የሚጸና እርሱ ግን ይድናል” የሚለውን የመሰሉ ብዙ ጥቅሶች ቀርበኞል። ይህ የሚያመለክተው፥ ከበደል ወይም ከኃጢአት መዳንን ሳይሆን፥ ከጠላቶችና ከስደት ነጻ መሆንን ነው። ከላይ የተመለከተው ጥቅስ የሚያመለክተው፥ ከታላቁ መከራ ተርፈው በኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት የሚድኑትን አማኞች ነው። ብዙ እውነተኛ ክርስቲያኖች ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት በፊት በሰማዕታትነት እንደሚሞቱና እርሱ እስኪመለስ ድረስ በሕይወት እንደማይቆዩ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ያስተምራል (ራእይ 7፡14)። ጥቅሶች ለዋስትናም ሆን ዋስትና አልባነትን ለመግለጥ እንዴት በተሳሳተ መንገድ ሊያገለግሉ

የድነት ዋስትና Read More »