ነቀፋ የሌለበት / ያለ ነውር መሆን ማለት ምን ማለት ነው?

ስለ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች መንፈሳዊ ብቃት ሲነገር፡ "እንግዲህ ኤጲስ ቆጶሱ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ ነቀፋ የሌለበት…" በማለት ይጀምራል (1ኛ ጢሞቴዎስ 3:2)። ነቀፋ የሌለበት ማለት ፍፁም ወይም ፈፅሞ ኃጢአት ያላደረገ ማለት ሳይሆን፣ በግልፅ የሚታማበት አኗኗር የሌለው ማለት ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ ፃድቃን ሰዎች ነቀፋ የሌለባቸው ተብለው ተጠርተዋል። ለምሳሌ ካህኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ በጌታ ትዕዛዝና ህግ ሁሉ ያለ ነቀፋ ይሄዱ እንደነበር ተመስክሮላቸዋል (ሉቃስ 1:6)። ይህ የህይወታቸውን ፅድቅ ያሳያል።

ይህ ባህሪ አንድ አማኝ ወይም መሪ በህብረተሰቡና በቤተ ክርስቲያን ዘንድ ያለውን መልካም ስምና ምስክርነት ያመለክታል። ጠላቶች እንኳ ክስ ሊያቀርቡበት የማይችሉት ንፁህና ግልፅ የሆነ አኗኗር ነው (ዳንኤል 6:4)።

ነቀፋ የሌለበት ሰው ስህተት ቢሰራ እንኳ ወዲያውኑ ንስሀ የሚገባና ካጠፋው ሰው ጋር ታርቆ ነገሩን የሚያስተካክል ነው። ህይወቱ ለሌሎች መሰናከል ወይም ማሰናከያ አይሆንም (ፊልጵስዩስ 2:15)።

ቃሉ ለእኛም ክርስቲያናዊ ምስክርነታችንን በንፅህና እንድንጠብቅና በውጭ ባሉት ዘንድ መልካም ስም እንዲኖረን መጠንቀቅ እንዳለብን ያስገነዝበናል። የክርስቶስ ስም በእኛ ምክንያት ሊሰደብ አይገባውም።

የእግዚአብሔር ፀጋ ንፁህና ነውር የሌለበትን ሕይወት እንድንኖር ያስችለናል። ሁልጊዜ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት መልካም ህሊና ሊኖረን ይገባል (የሐዋርያት ሥራ 24:16)።

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading