I. የማርቆስ ወንጌል መዋቅር
የማርቆስ መጽሐፍ ጴጥሮስ ስለ ክርስቶስ መሢሕነት በሰጠው ምስክርነት ላይ ያማከለ ይመስላል (ማር. 8፡29)። የቀረቡት ተአምራት ሁሉ፥ ሰዎች ክርስቶስ መሢሑ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንዲገነዘቡ የታሰቡ ናቸው። ከጴጥሮስ ምስክርነት በኋላ፥ የማርቆስ ወንጌል በመጭው የክርስቶስ ስቅለት ላይ ያተኩራል። ከመጽሐፉ ግማሽ ያህሉ ስለ ክርስቶስ የመጨረሻ ሳምንትና የመስቀል ላይ ሞት ይዘግባል።
ሌላው የመጽሐፉ መዋቅር መልክዐ ምድራዊ አቅጣጫ የተከለ ይመስላል። የመጽሐፉ የመጨረሻ አጋማሽ ክርስቶስ በሰሜን ፍልስጥኤም፥ ማለትም በገሊላና አካባቢዋ ባካሄደው አገልግሎት ላይ ሲያተኩር (ማር. 1-8፡30)። ሁለተኛው አጋማሽ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም ባካሄደው አገልግሎትና በሞቱ ላይ ያተኩራል (ማር 8፡31-16፡20)።
II. የማርቆስ ወንጌል አስተዋጽኦ
የማርቆስ ወንጌልን አስተዋጽኦ በብዙ መንገዶች መመልከት ይቻላል። የሚከተለው አንድ መንገድ ነው።
1. የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ለይፋዊ አገልግሎት መዘጋጀት (ማር. 1፡1-5)
2. ኢየሱስ በገሊላና በሰሜን የእግዚአብሔር ልጅነቱን ማሳየቱ (ማር. 1፡16-8፡26)
ሀ. ኢየሱስ አገልግሎቱን በገሊላ መጀመሩ (ማር. 1፡16-3፡6)
ለ ኢየሱስ በገሊላ ያካሄደው የኋለኛው አገልግሎት (ማር. 3፡7-6፡29)
ሐ ኢየሱስ አገልግሎቱን ከገሊላ ውጭ ማስፋፋቱ (ማር. 6፡30-8፡26)
3. የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ክርስቶስ መሢሑ፥ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ተገነዘቡ (ማር. 8፡27-30)
4. ኢየሱስ ለመሞት ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ (ማር. 8፡31-10፡52)
5. የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ማገልገሉ (ማር. 11፡1-13፡37)
6. ኢየሱስ በስቅላት መሞትና መነሣቱ (ማር. 14-16)
(ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክ፡፡)

እግዝሐብሔር ይባርካቹ
አሜን፡፡ አንተም ተባረክ፡፡
Thanks.. be blessed
Amen.
የማርቆስ ዕድሜ
እንዴት ሆኖ ሞተ
ሰላም፣ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ቅዱስ ማርቆስ (ዮሐንስ ማርቆስ) የዕረፍቱን ወይም የሰማዕትነቱን ዝርዝር ሁኔታ በቀጥታ በወንጌል ወይም በሐዋርያት ሥራ መጻሕፍት ውስጥ በግልጽ አያስቀምጠውም። ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር ቃል እርሱ ለጌታ ሥራ የነበረውን ታማኝነትና ዋጋ በግልጽ ይመሰክራል፤ ሐዋርያው ጳውሎስ በዕድሜው መጨረሻ ላይ ለጢሞቴዎስ ሲጽፍ “ሉቃስ ብቻ ከእኔ ጋር አለ። ማርቆስ ለአገልግሎት ብዙ ይጠቅመኛልና ይዘኸው ከአንተ ጋር አምጣው” በማለት የአገልግሎቱን ፍሬያማነትና ያደረገውን የበጎ አስተዋጽኦ ገልጿል (2 ጢሞ 4:11)። መጀመሪያ ላይ በጳውሎስና በርናባስ መካከል በአገልግሎት ጉዞ ምክንያት የተወሰነ መለያየት ቢኖርም (የሐዋ 15:39)፣ ማርቆስ በጌታ ፊት ራሱን አርሞ ታማኝ አገልጋይ ሆኖ ማለፉን መጽሐፍ ቅዱስ ያሳየናል።
ስለ ማርቆስ ሞት እና ሰማዕትነት ግን ከቀደምት የቤተ ክርስቲያን ታሪካዊ መዛግብት እና ከወግ እንደምንረዳው፣ ማርቆስ ወንጌልን ይዞ ወደ ግብፅ (አሌክሳንድርያ ከተማ) በመሄድ ታላቅ አብያተ ክርስቲያናትን መሠረተ። እዚያም በክርስቶስ ስም ሕያዉን ቃል በማሰራጨቱ ምክንያት በአህዛብና በጣዖት አምላኪዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው።
በታሪክ እንደሰፈረው፣ በ68 ዓ.ም አካባቢ ጠላቶች ተነስተው ማርቆስን ያዙት። በወቅቱም በአንገቱ ላይ ገመድ አስረው በአሌክሳንድርያ ጎዳናዎች ላይ እየጎተቱ በማሰቃየት ሕይወቱን እንዲያልፍ አደረጉት። በዚህም መከራ ውስጥ እያለ ጌታን እየጠራ ነፍሱን ለእየሱስ ክርስቶስ አሳልፎ ሰጠ፤ በዚህ መልኩም የክርስቶስን ወንጌል በሰማዕትነት አተመ።
የጌታ ኢየሱስ ጸጋ ይብዛልዎ!